አስገራሚው ደብዳቤ!!!!! የእምዬ ምኒልክ ውለታ ይህ ነው?

አስገራሚው ደብዳቤ!!!!! የእምዬ ምኒልክ ውለታ ይህ ነው?

የፊታችን ታህሳስ 3 የእምዬ ምኒልክን 100ኛ እረፍት በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት እንደሚዘክር የታወቀ ነዉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይም በርካታከሀገር ዉስጥና ከዉጪ ሀገር ምሁራን ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ይገኛሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰማያዊ ፓርቲ ለዝግጅቱ በሚያስፈልጉ ጉዳዩች ላይ ስራ እየሰራ ይገኛል! በስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ መሰረትም ስብሰባ እንደሚያደርግ ለስብሰባና ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ በትናንትናዉ እለት ያስገባ ሲሆን ዘሬ በደብዳቤ የተመለሰዉ መልስ እጅጉን አስቂኝና አጠያያቂ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡

በደብዳቤዉ ላይ ለምታደርጉት ስብሰባ እዉቅና ልነሳጥችሁ አንችልም ምክንያቱም የፖሊስ ጥባቃ መመደብ አንችልም የሚል ነዉ፡፡ የሚገርመዉ ደግሞ የፅፈት ቤቱ ሀላፊ ተብዬዉ አቶ አሰግድ በንቀት ደግሞ ማናችሁና ምኒልክ ምናምን የምትሉት ደግሞ ምኒልክ ማነዉ በሚል በእብሪት የመለሰዉ መልስ ነበር፡፡

እንኳን ድንኳን ጥሎ ለመሰብሰብ ይቅርና ጎዳና ሙሉ ህዝብ በመላበት የሩጫ የሰልፍ መሰል የገዢዉ ፓርቲ መልካም ፈቃድ ያገኙ ፕሮግራሞች ከህዝቡ እኩል ፌደራል ፖሊስ ለጥበቃ እንደሚታዘዝላቸዉ እየታወቀ ፤ በሌላ መልኩም በድፍረት እንወጣለን ብለን በተለያየ ምክንያት በተጠሩ ሰልፎች ላይ ለድብደባ የሚላከው ቁጥር ስፍር የሌለዉ የፀጥታ ሀይል አሁን ምን ቢውጠው ነዉ የጥበቃ የሚሆን የሰዉ ሀይል ልናስተባብር አንችልም ስለዚህ ዝግጅታችሁን እዉቅና አንሰጠዉም መባሉ??? ይህ ከእብሪት በላይ ምን ሊሆን ይችላል!!!?

ያም ሆነ ይህ ዝግጅቱ በታቀደለት ምልኩ እንደሚፈፀም በተለመደ ቁርጠኝነት ላይ ነን! ሲፈልጉ ለጥበቃ የከለከሉትን ሀይል ለድብደባ ይላኩት!!! እኛ የምንዘክራቸዉ ፍርሃት ካልፈጠረባቸዉ ሞተዉም መንፈሳቸዉ ካልተለየን እምቢ ባይ አባቶቻችን ተወልደናል፡፡
ድል ለኢትየጵያ ህዝብ!!!

One thought on “አስገራሚው ደብዳቤ!!!!! የእምዬ ምኒልክ ውለታ ይህ ነው?

 1. በጣም አመሰግናችኋለሁ።
  ዛሬ ለሆድ ማደር በጣም በተስፋፋበትና ማንነት ወደ ጎን ተብሎ የዛሬን ብቻ የማየት ባህል በነገሠበት ወቅት፤ አብሪ ሆናችሁ በመገኘታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ። ወጣቱ በማንኛውም ሀገር፤ ሀገሩን የመጠበቅ፣ ለትክክለኛ ፍትህ የመቆምና የወገኑን ደህንነት ከሁሉ አስቀድሞ የመንከበከብ ተልዕኮ አለው። ይህ በማንኛውም ወቅት፣ በየትኛውም ቦታ ያለና የነበር ነው። እናም በዚያ ፈለግ በመገኘታችሁ፤ የታሪክ፣ የትውልድን የሀገር ኃላፊነታችሁን እየተወጣችሁ ነው።
  ወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት የሚያደርሰውን ሀገር አጥፊ ተልዕኮ በመቋቋም፤ የምታደርጉት እንቅስቃሴ በታሪክ ፊት ያኮራችኋል። ምንጊዜም ቢሆን በጣም ጥቂቶች ናቸው የራሳቸውን ሕልውና ለወገናቸውና ለሀገራቸው በመሰዋት፤ ሀገር የሚገነቡ፤ ታሪክን የሚጠብቁና ቀጣይነትን የሚያረጋግጡ። በሀገራችን ታሪክ ውስጥ፤ ሀገር መሪዎች በተደጋጋሚ ጥፋቶችን አድርሰዋል። ይህ ግን፤ በአንድነታችንና በማንነታችን ላይ ጥያቄ እንድናስቀምጥ አያደርገንም። ይልቁንም ከስህተቶቻቸው ተምረን የተስተካከለና የተቃና የወደፊት እንዲኖረን የማድረጉን ኃላፊነት፤ ትከሻችንን አደላድለን በመቀበል ታሪክ ልንሠራ ይገባናል። እናም በናንተ ጥረት፤ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ሕልውና የተረጋገጠ መሆኑን በማየቴ በደስታ እፎይ ብያለሁ። ኮርቸውባችኋለሁ።
  እናንተም ትሁቶች ሁኑ። የሌሎችን አስተዋፅዖም አድንቁ። የሀገር ጉዳይ ከአንድ ግለሰብ፣ ከአንድ ድርጅት፣ ከአንድ ሃይማኖትና ከአንድ ወገንተኝነት ሁሉ በላይ ነው። የሀገር ጉዳይ ከሁሉም ግለሰቦች፣ ከሁሉም ድርጅቶችና ከሁሉም ሃይማኖቶች የተውጣጣ ነው። እናም የሁሉም አንድነት የሚገኝበትን መንገድ ፈልጉ። ይህም ግድ የሚሆንበት ምክንያት አለው። በሁኑ ሰዓት በሀገራችን ያለው ከወራሪ ባልተለዬ መንገድ የሚገዛ ወገንተኛ አምባገነን ቡድን ነው። እናም ሁሉን የኢትዮጵያ ክፍል በድሏል። ከዚህ ማንነቱም ባልተለዬ መንገድ፤ የፖለቲካ ፍልስፍናውና አስተዳደራዊ መመሪያው ወንተኛና ጨቋኝ ነው። ልንቋቋመው የምንችለውም ሁሉን ባጠቃለለ ታላቅ ኅብረት ነው።
  የሰላም ትግልችሁ ምርጫ የሌለው ግዴታ ነው። ባሁኑ ሰዓት የሰላምን ትግል ምንነት ያላወቁ ዝል! ዝል! ሲሉ ይታያሉ። ሩጫቸው የምቧለሌ ነው። መልሶ ባሉበት መደንከር። ባሁኗ ኢትዮጵያ ያለው ትግል፤ ባሁኗ ኢትዮጵያ ባለው የፖለቲካ እውነታ የተመሠረተ እንጂ፤ ከሰማይ በተዘረፈ የርዕዩተ ዓለም ወይንም ከሌሎች ሀገሮች እንዳለ በተቀዳ የፖለቲካ አመለካከት ላይ ተመርኩዞ አይደለም። በሀገራችን ውስጥ፤ ተማሪዎች በየተቋማቸው፤ የክርስትናና የእስልምና ተከታዮች በየአምልኮት ቦታቸው፤ ነጋዴዎች በንግድ ቦታቸው፤ ወታደሮችና መኮንኖቻቸው በትውልድ ማንነታቸው፤ ጋዜጠኞች በሙያቸው፣ መምህራን በትምህርት ቤታቸው፤ የፖለቲካ ተሳትፏቸውን የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት በሚፈቅደው መሠረት ለማድረግ የተነሱ ሀገር ወዳዶች የሚደርስባቸውን በደል ለማሰማት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት፤ በቦታው ተገኝቶ አብሮ መቆም፤ የሰላማዊ ትግሉ ዓይነተኛ ተልዕኮ ነው። እኒህ ናቸው የሀገሪቱ የትግል መሠረቶች። እኒህን ያልያዘና በቦታው ተገኝቶ እኒህን ያልደገፈ ታጋይ፤ ለምኑ ነው የሚታገለው? በወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ ቡድንና በኢትዮጵያ ሕዝብስ መካከል ያለው ቅራኔ ይኼ አይደለም ወይ? ከዚህስ የተለዬ መታገያ ከየት ሊመጣ ነው?
  እናም የምታደርጉት እንቅስቃሴ፤ ወቅቱን የተከተለ ስለሆነ፤ ታሪክ ከናንተ ጋር ነው።
  ከታላቅ ምስጋና ጋር
  አንዱ ዓለም ተፈራ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s