ስንቱ ተነግሮ ያልቃል

ስንቱ ተነግሮ ያልቃል

“…. ዘመናዊ ኢትዮጵያን የፈጠረ ሰው ነው:: ”
– በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን አውቶሞቢል የነዱና ፔርፌክት ድራይቨር የሚለውን የመጀመሪያውን የመንጃ ፈቃድ የተቀበሉ
-የመጀመሪያውን የእህል ወፍጮ መኪና ያስመጡና በወቅቱ ወፍጮው ጋኔን ነው ተብሎ ሰው በመሸሹ ጋኔን ያለመሆንኑን ለማሳየት ቆመው እህል ያስፈጩ
– የመጀመሪያውን ስልክ አስገብተው ጋኔኑ ከዙፋኑ ይውጣ ብለው የዘመኑ ጳጳስ ጭምር ከባድ ተቃውሞ ቢያነሱባቸውም ታግለው ስልክን የመሠረቱ
– የመጀመሪያውን ብስክሌት መንዳት ተምረው ባለቤታቸውንም በማስተማር ሴቶች ከመሸፋፈንና ከማፈር እንዲወጡ የታገሉ
– የመጀመሪያውን ሆቴል ከፍተው ሚስታቸውን ወጥ ቤት አድርገው በገንዘባቸው መኩዋንንት እየጋበዙ ሆቴል መብላትን ያስተማሩ
– የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በ 1881ዓ/ም በአዋጅ አረንጏዴ ቢጫ ቀይ እንዲሆን ያደረጉ
– ለመጀመሪያ ጊዜ ፎቶግራፍ ማንሳትና፣ ፊልም አጥቦ ማተም የተማሩ
– የተለያዩ አበቦችንና ጽጌረዳዎችን ከኤሮፓ እያስመጡ እስካሁን የምንጠቀምባቸውን ልዮ ልዩ አበቦችን ያራቡ
– የኮክ፣ የእንጆሪ፣ የወይን እና የመሳሰሉትን የአትክልት ልዩ ዘሮችን እያስመጡ ያራቡ
– እስከ ዛሬ ለኢትዮዽያ ትልቅ ጥቅም እየሰጠ ያለውን ባህር ዛፍን አስመጥተው የተከሉና ያባዙ
– በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የውጭ አገር ትምህርት ቤት የከፈቱ
– የመጀመሪያውን የሙዚቃ ትምህረት ቤት የከፈቱ – ለመጀመሪያ ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ያስገቡ
– ከጂቡቲ አዲስ አበባ የባቡር ሀዲድ አዘርግተው የመጀመሪያውን የባቡር አገልግሎትን ያስጀመሩ
– የመጀመሪያውን ዘመናዊ የመንገድ ሥራ ያስጀመሩ
– የመጀመሪያውን የፖስታ ድርጅትን የከፈቱ
– ሰው ሲባል እኩል ነውና ማንም ሰው ሰውን ባርያ እንዳይል ብለው የባርያን ነፃነት ያወጁና ሰው እንደከብት እንዳይሸጥ የታገሉ
– ሴት ልጅ በወላጆችዋ ምርጫ ሳይሆን በፈቃድዋ የመረጠችውን ባል እንድታገባ ያወጁና ለሴት ልጆች ነፃነት የታገሉ
– ሠራተኛ በሥራው እንዳይበደል አዋጅ ያስነገሩ
– ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ አስገዳጅ ሕግ ያወጡ
– የተሠራ ጨርቅ ከማስመጣት ይልቅ ድር እያስመጡ ማሠራት እንደሚረክስ አውቀው የመጀመሪያውን ድር ማስመጣትን የጀመሩ
– የመጀመሪያውን የጥይት ፋብሪካን ያቁዋቁዋሙ
– ቧንቧ ውሃ + ሕክምና፣ ሆስፒታል፣ ፋርማሲ + ባንክ፣ ገንዘብ + አረቄ + የሙዚቃ ሸክላ + ማተሚያ + ጋዜጣ + ፖሊስ(ዘበኛ) + የጽሕፈት መኪና + ሲኒማ + ጫማ + ፍልውሃ + ትምባሆ ብቻ…… ስንቱ ተነግሮ ያልቃል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s