ይህን መከራና ውርደት የሚያስቆም ለውጥ ለማምጣት ሁለት ነባራዊ ሁኔታዎች መቀየር አለባቸው ። አንደኛው እስከዛሬ የተለመደውና የሚመቸንን መፍትሄ ቢስ የተቃውሞ ሂደትን መቀየር ሲሆን ፣ሁለተኛው እየተባባሰ የመጣውን የኢትዮጵያውያንን ስቃይና መከራ በፍጥነት ማስቆም ነው። ይህም ተልዕኮ የሚሳካው ፣የችግራችን ምንጭ የሆነውን ፣ ሕዝብን እና አገርን ለባርነት ገበያ አቅራቢውን ደላላ ኢህአዴግ በኃይል ስናስወግድ ብቻ ነው። ይህን በዋናነት ውጤታማ ለማድረግ የሚቻለውም የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆነው ኢትዮጵያዊ ኃይል ሲነሳ ብቻ ነው። ይህም የሚሳካው ኢትዮጵያውያን ለራሳቻው ነፍስና ሕይወት ዋጋና ክብር ሲሰጡ ነው።