ወዴት እየሄድን ነው?!

እንደ ሀገር እየተጓዝንበት ያለው ጎዳና ትክክል ነው ወይ? ጉዞዋችንስ? እውነት የያዝነው መንገድ ካሰብንበት ያደርሰናል? ወዴት እየሄድን ነው? ሠርክ በውስጤ የሚመላለሱ፣ አእምሮዬም መልስ ፍለጋ የሚደክምላቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ እንድጠይቅ የሚያደርገኝ ደግሞ አንድም በየመስኩ እየተጓዝንበት ያለው ጎዳና እና የጉዞው ስልት በበቂ የተጠና ስለማይመስለኝ፣ አንድም ከማስተዋል ይልቅ በጥድፊያና በ“በል በል” ስሜት የተቃኘ ስለሚመስለኝ ነው፡፡ አስተያየቴ ግብታዊ ቢመስልም ዝግ ብላችሁ ስታስተውሉት እንደምንስማማ ተስፋ በማድረግ ጥያቄዬን ይዤ ልቀጥል፡፡ ወዴት እየሄድን ነው?!ጥያቄውን የሚመልሱ የሚመስሉ (የሚመስሉ ነው ያልኩት) ንግግሮችን ከተለያዩ
እቅዶችና አቅጣጫዎች ላይ አንብበን ወይንም ሲነበብ ሰምተን፣ እንዲሁም ከመንግስት ሹማምንት አንደበት ሲነገር አድምጠን ይሆናል፡፡ እርግጥ ነው ለማመን መስማት አንዱ ምክንያት ቢሆንም የምንሰማው ከምናየው ጋር ካልሰመረ ግን ለማመን ይገደናል፡፡ (ደግሞም ከምንሰማው ይልቅ የምናየው ውሃ ይቋጥራልና የምናየውን እናምናለን፡፡) እናም ገለጻዎቹን በአንድም ሆነ በብዙ ምክንያቶች ለማመን እቸገራለሁ፡፡ ለዚህም አንድ ሁለት ምክንያቶችን ላንሳ፡፡ አንደኛ የአስተያየቶቹ ባለቤት “ጉዞውን የሚመራው” መንግስት በመሆኑ “ባስያዘን” ጎዳና ላይ በቂ ጥናቶችን ከማድረግ ይልቅ ለአላስፈላጊ ፕሮፓጋንዳዎች ትኩረት በመስጠት ላይ የሚጠመድ ስለሚመስለኝ ነው፡፡ ይህንንም በየጊዜው ትክክለኛ አቅጣጫዎች ናቸው ብሎ ካወጃቸው፣ አውጆም ከተገበራቸው ሆኖም (እሱ በገሀድ ባያምንም) ብዙም ሳይቆይ ከሰረዛቸው (ሲተቻቸው ባንሰማም) አቅጣጫዎቹና ተግባራቱ በተደጋጋሚ ታዝበናል፡፡ ሁለተኛ በየመስኩ የተቀመጡት ሕጎችና መመሪያዎች ለአንድ ግብ የቆሙ እንዲሆኑ ስለሚጠበቅ እርስ በርስ ሊመጋገቡና ሊናበቡ የሚገባ ቢሆንም ከዚያ ይልቅ እርስ በርስ የሚጋጩ መሆናቸው ነው፡፡ ይህ አለመናበብና እርስ በርስ መጋጨት በአንድ ከተማ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ክፍለ ከተሞች ውስጥ ወይንም በአንድ ክፍለ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ የተለያዩ ሕጎች/መመሪያዎች ተፈጻሚ ሲሆኑ እስከማየት ይደርሳል፡፡ አንዱ ጋ የሚፈቀደው ሌላው ጋ ክልክል ሊሆን ይችላል፡፡ አንዱ ጋ የሚያስቀጣው ድርጊት ሌላው ጋ ሊያስመሰግን ይችላል፡፡ ሌላም ብዙ! እናም ጥያቄዬ መልስ ይሻልና እጠይቃለሁ፡፡ እውነት ወዴት እየሄድን ነው? እውነት እላችኋለሁ ነገራችን ሁሉ የተጠና እና የምር የታሰበበት አይመስልም ቀሪውን ከአዲስ አድማስ_Issue-774 ያንብቡ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s