ይድረስ ለአንተ ለፈዘዝከዉ – ለታወርከዉ!!!

ይድረስ ለአንተ ለፈዘዝከዉ – ለታወርከዉ!!!

ኖርኩኝ እንዳትለኝ!!!

በአባትህ አዉድማ ተወልደህ ተምቧችተህና ደኸህ ባደግክባት ሀገር እንደ ባዳ ከታየህ . . . በመሬትህ ጭሰኛ እየሆንክ የአያቶችህን ርስት ባንዳ ሲጫረትበት ሆዱ አናቱ ላይ የነገሰ ሀገሩን የከዳ ሲራኮትበት እያየህ እንዳላየህ እያለፍክ . . .
ሀገርህን በሚበታትን ከታሪክ በተቃረነ ጠባብ አስተሳሰብ ጥቂት ዘረኛ ግለሰቦች በቀደዱለህ ቦይ እየፈሰስክ . . .
ኑሮ አናትህ ላይ ንሮ እየሆነብህ እሮሮ . . . ታክስ በምትከፍልበት ቴሌቪዥን እለት ተለት ሙልጭ ተደርገክ ስትዋሽ . . .
የምትከፍለዉ ታክስ ተሰብስቦ በሚከፈለዉ ቅጥር ቅልብ ወታደር ወገንህ ‘በዉሃ ቀጠነ’ ሲደበደብ . . .
መስጊድ ገዳማቱ በሌቦች ተመልቶ ሀይማኖትህ እየተዘረፈ . . . ቤተክርስቲያናት በየቦታዉ ሲቃጠሉ . . . ለምን ያሉ ዘብጥያ ሲወርዱ . . .
በምናገባኝ እያለፍክ እዉነት ኖርኩኝ እንዳትል!!!
ታሪክም የለህ የሚወራ ቆይ ለልጅህስ ምን ልታወርስ? . . . ፍርሃትህን!? ግብዝነትህን!? አድር ባይነትህን!? ወይስ ለሆድህ ማደርክን!?
. . . ስለእዉነት ምን ትለዉ ለወለድከዉ? ሀገርህ ባዶ ሆና ምነ ቢለህ ምን ልትለዉ? . . .
እዉነት ኖርኩ እንዳትል ማፈሪያ ነህ ዉዳቂ ያባትህ አጥንት እማይቆረቁርህ የወገንህ እማባ ደሙ ግድ እማይልህ . . .
እዉነት ኖርኩ እንዳትል ስትወለድ ነዉ የመከንክ . . . ስትፈጠር ነዉ የከሰምክ . . . ቅርንጫፍ ያለ ግንዱና ስሩ ህልዉና እንደሌለዉ የቆምክባትንና የተፈጠርክባትን ምድር የሀገርክን ህማም ችላ ብለህ ግብር-ይዉጣህን ኑሮ ካልከዉ – – – ለመኖር ለመኖር ድንጋይ ቋጥኙም ይኖራል እድሜ ሳይገድበዉ!!!
ወዮ ላንተ ቀን ሲወጣ . . .ሀገር ቀና ሲሆን ባንዳ ሲሆን ባዳ!!!
ይሻልሃል ቶሎ ብትነቃ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s