ሰለ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ፤ ለሰማዩ አምላኬ ጸሎት አደርሳለሁ…!

ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች ዘጠኝ ፓርቲዎ በመተባበር ”ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ” በሚል ቀጣዩ ምርጫ ነጻ እንዲሆን ምርጫው ብቻም ሳይሆን በኢትዮጵያ ምድር የሰው ልጆች ነጻ እንዲሆኑ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ከህዝብ ጋር በመሆን ድምጻቸውን ሊያሰሙ የክንውን ቅደም ተከትሉን በቅርቡ ይፋ አድርገዋል። ይደረጋሉ ተብለው ከሚጠበቁት የ10484897_675825339202040_7611881303839978882_nሰላማዊ ተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ትልቁ መርሃ ግብር የሚሆነው ህዳር ሃያ ሰባት እና ሃያ ስምንት ሊደረግ የታሰበው የሃያ አራት ሰዓታት /የአዳር/ የአደባባይ ተቃውሞ ነው።

ከእርሱ በፊትም የፊታችን እሁድ በአዋሬ ቤልኤር ኳስ ሜዳ ላይ ከሚደረገው የአደባባይ ሰብሰባ በፊትም በጥቅሉ ከሁሉም መርሃ ግብሮች በፊት እነ ሰማያዊ ሁላችንም በየእምነታችን ለሰማዩ አምላክ ”አደራ ጎፍታ” ብለን እንድንጸልይ ጠይቀውናል… ታድያ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ለአደባባይ ተቃውሞውም ሆነ ለስብሰባው መድረስ ባልችል እንኳ እንደሚከተለው ለምን አልጸልይም… ብዬ አስብኩ…

አደራህን ጎፍታ
አደራህን ጌታ
ከባለ ሰይፎቹ ፊት
ሰልፍ ልንወጣ ነው ጥበቃህ ይበርታ
ብዙ ስንቅ ብዙ ትጥቅ እጅግ ያደራጁ
በስልጣን ወንበር ላይ ጎልምሰው ያረጁ
ስልጣን ብርጭቆ ውስጥ ስኳር በዝቶባቸው
እጅጉን ጣፍጧቸው
ስልጣን ብርጭቆ ውስጥ ብቅል በስቶባቸው
እጅግ አስክሯቸው
ቢጠጡት ቢጠጡት አልበቃም ያላቸው…
ምን ያደርጉን እንደሁ አናውቀውምና
ለኛም ብርታት ስጠን ለነርሱም ልቦና
አደራህን ጎፍታ
አደራህን ጌታ
ከባለ ሰይፎች ፊት
ሰልፍ ልንወጣ ነው ጥበቃህ ይበርታ….

(ይቺን ነገር፤ የግጥምን አድባር ተለማምነን ካረዘምናት እና ተስፋ ሰጪ ሆና ከተገኘች በሌላም መስኮት ይዘናት እንከሰት ይሆናል…!)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s