ነጻነት

… ነጻነታችን ምሉዕ የሚሆነው ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችን ለማስከበር ዘር ሳንለይ በጋራ ስንታገል ብቻ ነው!!! ብዕርና ወረቀት የሚፈራ ባለጊዜ ዕድሜው አጭር ነውና!!!!!

መብትና ነፃነት በልመና አይገኝም

የኢትዬጵያ ህዝብ ከአምባገነኑ ኢህአዴግ አገዛዝ የሚላቀቀው አምፆ ሲነሳ ብቻ ነው፡፡ መብትና ነፃነት በልመና ወይም በልምምጥ ያለዝያም በገዥዎች መልካም ፈቃድ የተገኘበት ታሪክ አይታወቅም። ነፃነት ዋጋ አላት ዋጋዋን ለመክፈል መዘጋጀት ይገባል። አባገነኖች የፈለገውን ያህል መሳሪያ ቢታጠቁና ሃይለኛ መሥለው ቢታዩም ሕዝብ ተባብሮ ሲነሳባቸው ኢምንት ናቸው ምንም የመቋቋሚያ ሃይል የላቸውም። የተባበረ ሕዝብ ሁልጊዜም አሽናፊ ነው።

Ethiopia: Human rights campaigner says African Union should move headquarters out of Ethiopia

የአፍሪካ ህብረት መቀመጫነቱ ከኢትዮጵያ መነሳት እንደመፍትሄ
ጋዜጠኛና ሰብዓዊ መብት ተከራካሪ የሆነው አንጎላዊው ራፋኤል ማርክስ በኢትዮጵያ ያለው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ገና የሚቀረው በመሆኑ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫነቱ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በሰብዓዊ መብት ጥበቃ የተሻለ ወደ ምትባል ሀገር መቀየር ይገባል ባይ ነው፡፡
ህብረቱ 53 የአፍሪካ ሀገራትን የሚወክል ቢሆንም በሰብዓዊ መብቶች ረገድ ምንም አልሰራም ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ይህ የአንጎላ ዜግነት ያለው ጋዜጠኛና ሰብዓዊ መብት ተከራካሪ በሚሊየኖች በሚቆጠሩ ዶላሮች መጭበርበር ላይ የምርምር ጋዜጠኝነት ስራ በመስራቱ ሞዛምቢክ ውስጥ እ.አ.አ በ2000 ስለተገደለው ሞዛምቢካዊ ጋዜጠኛ ያስታውሳል፡፡ ስታር ትሪብዩን እንደዘገበው

ምንጭ

ፖሊስ እና ደህነንቶች የዛሬውን ሰልፍ መበተናቸው የስርዓቱን ፍርሃት ደረጃ እንደሚያሳይ ኢ/ር ይልቃል ገለጹ


police 2
police 3
police 1
ኢንጅነር ይልቃል በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም እንደሚያደርገው ለምን እስከመጨረሻው አንበተንም አላላችሁም? ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹የአንድ ወር መርሃ ግብር አውጥተናል፡፡ ምርጫው ነጻና ፍትሓዊ እስኪሆን ድረስ የነጻነት ትግሉ የሚቀጥል ነው፡፡ በአራት ኪሎ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችን ጠርተን ልናነጋግር በሞከርንበት ወቅት ብዙ እስርና ደብደባ ተፈጽሟል፡፡ ከዚህ የስርዓቱ ፍርሃት አንጻር ገና በመጀመሪያው ስራችን ወደኃይል እንዲገባ አልፈለግንም፡፡ ለሚቀጥሉት ስራዎቻችን ስንል ነው፡፡ ለሚቀጥለው ያንን በሚመጥን ደረጃ መዘጋጀት አለብን፡፡›› ብለዋል፡፡ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት አክለውም ‹‹እኛ ዛሬ የአራት ኪሎን አካባቢ ሰዎች ነው የጠራነው፡፡ በዚህ ደረጃ ፈርተው ይህን ስብሰባ ያግዳሉ ብሎ ለመገመት ይከብዳል፡፡ ድሮውንም የሌላቸው የህዝብ ድጋፍ ጭራሹን እንደተሟጠ ነው የሚያሳየው፡፡ ትንሹም ነገር ለስልጣናቸው አስጊ ነው ብለው ማሰባቸው የፍርሃት ደረጃቸው ጫፍ እንደደረሰ ያሳያል፡፡›› ብለዋል፡፡

ምንጭ

My heartfelt gratitude to all participants of the #ሰዉበመሆኔ

My heartfelt gratitude to all participants of the #ሰዉበመሆኔ campaign! In my view we were very successful in advocating for ALL Ethiopians! You my friend deserve a million thanks, as you helped awakening for the minds of many by advocating for all Ethiopians for what they have to go through in a daily basis!
This campaign also showed that there are a lot of us who realized what the neocolonialist are doing to put our country yet in to the ditches of tribal/ethnic politics/war where there will be no end to conflicts.
We showed our solidarity by standing up for all and by standing up against Amnesty International unethical distortion of report by only applying it to one group of people, their little trick (ethnic card) won’t work anymore and the data and report that Amnesty International released speaks and shows the daily reality of all ETHIOPIANS!
Cooking reports and data to use it as it please them whenever they want to instigate ethnic ambiguity under their plan of destabilization should stop and that only can be done by people like you who outsmarts the Westerners tribal war game!
Say No To Ethnic Politics! Say No To TPLF’s authoritarian ethnic apartheid regime! Thank you all for you participation! I attached this photo so you can change your profile picture to this diverse beautiful people of ETHIOPIA!

በጅማ ከተማ የሆቴል ባለቤት የሆኑት እናትና ልጅ በወያኔ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተረሽነው በገዛ ቤታቸው ተገኙ!!

በጅማ ከተማ የሆቴል ባለቤት የሆኑት እናትና ልጅ በወያኔ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተረሽነው በገዛ ቤታቸው ተገኙ!!

በጅማ ከተማ የሆቴል ባለቤት የሆኑት እናትና ልጅ በወያኔ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተረሽነው በገዛ ቤታቸው ተገኙ!!

ወያኔ ሰላማዊ ህዝብን ገለው ጨረሱ!!

ወያኔ የመለስን እራዕይ የኢትዬጵያን ህዝብ መግደ በሰፊው ሁኔታ እያፈፅሙ ይገኛሉ!!

በቅስቀሳ ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች እየታሰሩ ነው

ነገረ ኢትዮጵያ በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ለእሁዱ የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የታሰቱትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄዱት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታሰሩ፡፡ በቅስቀሳ ወቅት የነበሩት የሰማያዊ አባላትና አመራሮች መያዛቸውን ተከትሎ የእሁዱን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ለስበስባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ያሳወቁበትን ህጋዊ ደብዳቤ በመያዝ የአባላቱና አመራሩ እስራት ህገ ወጥ መሆኑን ለማስረዳትና አባላቱን ለመጠየቅ ወደ አራዳ መምሪያ ፖሊስ ጣቢያ ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ የፋይንስ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወሮታው ዋሴ እና የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡

1920593_613309012128094_4439816027396922242_n

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር 10173740_613277408797921_4625849180036064757_nእሁድ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ለሚያደርገው የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ታሰሩ፡፡ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነው አቶ ዮሴፍ ተሻገር እንዲሁም የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል የሆነው ሲሳይ በዳኔ መገናኛ አካባቢ ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ታስረዋል፡፡ በተመሳሳይ የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ ሳምሶን ግዛቸው እንዲሁም የአዲስ አበባ ዞን ምክትል ሰብሳቢና ህዝብ ግንኙነት አቶ ማቲያስ መኩሪያ በአራዳ ክፍለ ከተማ ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት በፖሊስ ተይዘው አራዳ ፖሊስ መምሪያ ታስረዋል፡፡

በሌሎች የአዲስ አበባ ክፍሎች ቅስቀሳ ላይ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች በፖሊስ ወከባ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ቤልየር ሜዳ ላይ የሚደረገው የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲ የሚያስተብብረው ሲሆን በአንድ ወር የሚደረጉትን ሌሎቹን መርሃ ግብሮች 9ኙ ፓርቲዎች በየተራ እንደሚያሰተብብሩ መስማማታቸው ይታወቃል፡፡

ምንጭ

ኢህአዴግ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አለመሳካቱን አመነ

ዘንድሮ የሚጠናቀቀው የኢህአዴግ የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን የተለጠጠ ዕቅድ በግብርና ዘርፍ መዳከም ምክንያት ሳይሳካ መቅረቱን ኢህአዴግ ለመጀመሪያ ጊዜ  በይፋ አመነ፡፡ ኢህአዴግ «አዲስ ራዕይ» በተሰኘው በርዕዮተ ዓለም ልሳኑ የመስከረም- ጥቅምት 2007 ዓ.ም ዕትም ላይ የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የአራት ዓመታት አፈጻጸም አስመልክቶ ባሰፈረው ሐተታ እንደጠቆመው ለጥጦ የያዘውን ዕቅድ ማሳካት እንዳልቻለ በማስቀመጥ አባላትና ደጋፊዎቹን አጽናንቷል፡፡

ግንባሩ ባለፉት አራት ዓመታት በግብርና ፣በኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት ዘርፎች አመርቂ ውጤት መገኘቱን በደፈናው ካስቀመጠ በሃላ ግንባሩ የተለጠጡ ዕቅዶችን አንግቦ የተነሳና ለማሳካትም ወቅቱ የፈቀደውን ያህል የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ከሞላ ጎደል መሠረታዊውን የዕድገት ምጣኔ እንጂ በተለጠጠ አኳሃን የነደፈውን ግብ ማሳካት ሳይችል መቅረቱን አምኗል፡፡ «በራሳችን ተነሳሽነት ለጥጠን ያስቀመጥነው ግብ ላይ ባለመድረሳችን ዛሬም የምንቆጭና ለነገ በእልህና በላቀ ወኔ መነሳሳት እንዳለብን የምንገነዘብ ቢሆንም በአራቱ ዓመታት በርብርብ የተመዘገበው ውጤት የሚያኮራ ነው» ሲል ይጠቅሳል፡፡

ያለፉት አራት ዓመታት የግብርናው ዘርፍ በአማካይ 7 ነጥብ 15 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት እንዳስመዘገበ የሚጠቅሰው አዲስራዕይ ይህ የዕድገት ምጣኔ በማንኛውም መልኩ ካስቀመጥነው የ14 ነጥብ 9 በመቶ የተለጠጠ ዕድገት ምጣኔ ብቻ ሳይሆን ከመሰረታዊው የ11 በመቶ የእድገት ምጣኔም ትርጉም ባለው ደረጃ ዝቅ ያለ ነው ሲል በይፋ ያምናል፡፡ የግብርና ዘርፉ ከሰባት እስከ ስምንት በመቶ ሲያድግ ኢኮኖሚው ወደ 10 በመቶ ማደጉን፣ የግብርናው ዕድገት ወደ 9 በመቶ ከፍ ሲል ደግሞ ኢኮኖሚው 11 ነጥብ 4 በመቶ ማደጉን  አስታውሶ የግብርና ዘርፉ ባቀድነው መሠረት ከ11 አስከ 15 በመቶ ማደግ ቢችል ኖሮ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገቱ ወደተለጠጠው ግብ በተጠጋ ነበር በማለት ያስቀምጣል፡፡የግብርና ዕድገቱ አጠቃላዩን የዕድገት ምጣኔ ዝቅ ወይንም ከፍ የማድረግ ውጤት ያለው መሆኑ እንደተጠበቀ የሚዋዥቅ ዕድገት የነበረ መሆኑ አጠቃላዩን አገራዊ ፈጣን ዕድገት መጠነኛ መዋዥቅ ያስከተለ ነበር ብሎአል፡፡ በአራቱ ዓመታት የግብርና ልማት ዕድገት የተመዘገበው ውጤት በተከታታይ ፈጣን አይደለም ያለው የአዲስራዕይ ዝቅተኛ ዕድገት የተመዘገበበትን 2004 ዓ.ም በአብነት በመውሰድ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ  ፍጥነታችን ወደታች የወረደ ነበር ሲል ድክመቱን አስቀምጦአል፡፡

መጽሔቱ አያይዞም «በዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አራት ዓመታት ባለሁለት አሀዝ አማካይ ዕድገት ብናረጋግጥም የተለጠጠውን ግብ ያላሳካንበት ሆነ  እድገታችን ወደ 8 ነጥብ 8 በመቶ ዝቅ ያለበትና የመዋዥቅ ገጽታ የተላበሰበት ውጤት የሚያመለክተው የፖለቲካ ጥራታችን በተገቢው ደረጃ ያልተጠበቀባቸው ሒደቶች ውስጥ ማለፋችን ነው ካለ በሁዋላ የልማት ሥራችን በከፍተኛ ፍጥነት የማደግ ውጤት እንዲያስከትል በተሟላ ሕዝባዊ ወገንተኝነት ጠንክረን በላቀ ዲሲፒሊን መንቀሳቀስ ሲገባን በነዚህ መሠረታዊ አቅሞቻችን ላይ መላላት ተፈጥሮ ነበር» በማለት የኢህአዴግን ውስጣዊ ችግር አመልክቷል፡፡

የአምስት አመቱ እቅድ በታቀደበት ወቅት የተለያዩ ምሁራንና በውይይቱ ተሳተፉ የተባሉ ሰዎች እቅዱ ተለጥጧል በሚል መተቸታቸውን  በወቅቱ በስልጣን ላይ የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ተናግረዋል ትችቱን አለመቀበላቸውን የገለጹት አቶ መለስ ከተቻለ 15 በመቶ ካልተቻለም 11 በመቶ እድገት ካገኘን ትልቅ ስኬት ነው በማለት የህዝቡንና የምሁራኑን አስተያየት ሳይቀበሉት ቀርተዋል። ብቸኛው የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ እቅዱ በቂ ዝግጅት ያልተደረገበትና ለፖለቲካ ድጋፍ ማስገኛ ተብሎ በስሜት የተዘጋጀ መሆኑን በጽኑ በመተቸት እቅዱ ባይሳካ ጠ/ሚኒስትሩ በሌሎች አገሮች እንደሚታየው ስልጣን ይለቁ ይሆን ሲሉ ጠይቀዋቸዋል አቶ መለስ 11 በመቶ እድገት ቀርቶ 7 በመቶ እድገት ማግኘት ትልቅ ነገር በመሆኑ፣ ኢህአዴግ ስልጣን እንደማይለቅ ምላሽ መስጠታቸው ይታወቃል።

ለአቶ መለስ ድጋፋቸውን የገለጹት ሌላው የፓርላማ አባል ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እቅዱ መሳካትና አለመሳካቱን የዛሬ አምስት አመት እንገናኝና እንየው ሲሉ አቶ ግርማ ሰይፉን ተችተዋል የተለያዩ ምሁራን ኢትዮጵያ ከአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም እቅዱን ለመተግበር በቂ የሆነ ገንዘብ ላታገኝ ትችል ይሆናል በማለት ስጋታቸውን በወቅቱ ቢገልጹም አቶ መለስ ስጋቱን አጣጥለውታል አቶ ሃይለማርያም የአምስት አመቱ የልማት ግብ በአብዛኛው ተሳክቷል በማለት በቅርቡ ለፓርላማው ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል።

ምንጭ