ድመትና አይጥ

ቢከፋም ቢደላ ይሻላል ሀገር
ለጠላት አልሰጥም ያገር ዳር ድንበር፡፡
አገር የሚለዉን ቃል ለመረመረዉ፣
በልቡ እያደረ ቆይቶ ላጤነዉ፣
ብዙ ነዉ ሚስጥሩ የትርጓሜዉ፡፡
የአያት የቅድመ አያት አፅም ያረፈበት፣
ስጋቸዉ በስብሶ በአልማዝ የሰራት፣
ይህችን ምስኪን ደግሞ አርሠን ስንዘራት፡፡
እኛን መግባ አጥግባ ታድራለች፣
ደከመኝ ሳትልም እኛን ባሳረፈች፣
ለምን ሀገር ትሸጥ ይህን ባደረገች፡፡
የተሸጠዉ መሬት ሸቶኛል የአያቴ፣
ደግሞም ያደግሁበት ያ— የልጅነቴ፡፡
የምፅዋ ወደብ ርስቴም አስመራ፣
የእኛ የነበረች ከወርቆች ጋራ፡፡
ድንግሉ መሬቴም የሄደዉ ሱዳን፣
ሰፍሮበት የነበር የሃበሻዉ ምስጉን፣
በባእድ ሲበላ እንዴት ላመስግን፡፡
እንኳን የሰዉ አፅም መንፈስ ያለበት፣
ይጣሩ የለም ወይ የዱር አራዊቱ በዚያ የቀሩት፡፡
ኢትዮጵያ ሀገሬ እእዕዋፋቱ፤
ይዘምሩ የለ ሌቱ ከመንጋቱ፡፡
ድሮም የአስመራ ሰዉ የጣሊያን አሽከር፣
ገንጥሎ ወሰደዉ የአያቴን ድንበር፡፡
እያልኩኝ ስተክዝ ሰምቶኝ አንድ ምሁር፣
እንዲህ ሲል መከረኝ ብሎ እያየኝ ትኩር፣
ልጄ የተከዝከዉ ስማኝ ልንገርህ፣
ወሬ አእንዳይሆንብህ በአጭር ልምከርህ፣
እኛ የምናዉቃት ሀገረ ኤርትራ፣
ያን የአሰብ ወደብ ያን ሁሉ ጋራ፣
የተፈጠረ ነዉ ሁሉም ከእኛ ጋራ፡፡
ጣሊያን ምትባል ክፉ ጭቃ እሾህ፣
ጠላታችን ሆና የተሠራች በእልህ
ወንበዴ አደራጅታ ፓስታ እየመገበች፣
የራሷን በሰላም ዉላ እያደረች
አንገታችን ቆርጣ ኤርትራን ወሰደች፣
ከድሮም የእኔ ነሽ ብላ እያቅራራች፣
እስካሁንም ጊዜ ፓስታ ትሰጣለች፣
በዉስጡ ያለንም ሁሉ ትሰርቃለች፣
የሻእቢያን መኳንንት ታሰለጥናለች፡፡
ይህ ብቻም አይደለም ተንኮሉ ብዙ ነዉ፣
የሳጥናኤል እንጅ ሰዉም አያስበዉ፣
ቀጣዩ ስልጠናም ከፋፍለህ ግዛ ነዉ፡፡
ብሔርን ከብሔር በግጭት አናክሳ፣
የሀበሻን መሬት ሸፍና በሬሳ፡፡
ከካርታ ማጥፋት ነዉ የኢትዮጵያን ስም፣
በኒዩክሌር ለመምታት ስለሚያይ አለም፣
ይህን ትሰራለች በወንበዴዉ ስም፡፡
የእነ ዜናዊ አስረስ የባንዳ ልጆች፣
ቀድሞ የነበሩ የጣሊያን አይኖች፡፡
ፋሽስት እየመሩ መረብ ያደረሱት፣
ደግሞ ዉሃ ሲጠማዉ ወንዙን የሚያሳዩት፣
ከፋሽስቱ ጋራ በደም የተጋቡት፣
ጣሊያን ሃገር ሄደዉ ትምህርት የጨረሱት፣
አሁን በሙት መንፈስ ሃገር የሜውኩት፣
እነ መለስ ናቸዉ ይህን የሚያደርጉት፡፡
ይህ የተንኮል ስራ ለእኛ የታሰበዉ፣
የጣሊያን ፖሊቲክስ እጅግ ረቂቅ ነዉ፣
የሀበሻን አንጀት መቁረጡን ስታዉቀዉ፣
የአረቡ አብዮት ወያኔን ሲያቃዠዉ፡፡
አባይ ግድብ ብላ እድሜ ቀጥላለች፣
በጃንሆይ ዝናብ አርሳለሁ ብላለች፣
ኮንትራክተሩንም ሳሊኒ እያለች፣
ደስታ ከረሜላን ለእኛ ሰጥታናለች፣
አፈሬን ቆፍራ ወርቁን ትወስዳለች፣
ህዝቡ እንዲቆጣ ብር አዉጡ ብላለች፣
ቂማችንም አለ እርሷም አላረጀች፣
ማይምነታችን በዉል ተረድታለች፣
በወያኔ እድሜ ላይ እድሜ ቀጥላለች፣
ሮም ተቀምጣ ትምህርት እየሰጠች፣
በእጅ አዙር ወንበዴ ቅኝ ትገዛለች፡፡
ሳሊኒ እሚባለዉ የጣሊያን ኢንጅነር፣
እንዴትስ ያለማል የጠላቱን ሀገር፡፡
ስለዚህ ልጄ ሆይ ተመራመር እና፣
የአይጥና ድመትን ታሪክ ጠይቅና.
ተግባርክን አፍጥነዉ አገር እንዲቃና፡፡
እንዴት ድመት ለአይጥ ምሽግ ትሰራለች?
ጣሊያን ምን አግብቷት አባይን ገደበች?
ደግሞስ ማን አራርቷት አክሱምን መለሰች?
ብለህ እስኪ ራስክን ራስህን ጠይቅ፣
ድመት ከአይጥ ጋራ መቼ ነዉ ሚታረቅ???

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s