የባህር ዳር ህዝብ አደባባይ ወጣ፤ የባሕር ዳር ሕዝብም ተቃውሞውን እየተቀላቀለ ነው::

የባህዳር ነዋሪ በነቂስ በመውጣት በክልሉ ም/ቤት ፊት ለፊትና በአዲሱ ም/ቤት(ቀበሌ 10) መስቀል አደባባይ የቤተክርስያን የታቦት ማደሪያ ፣ ንብረትነቱም የቤተ-ክርስቲያን ነው ልትነጠቅ ወይም መንግስት እንደሚለው ለባለሀብት ሊሰጥ አይገባም በማለት ቁጣቸውን በማሰማት ላይ ናቸው፡፡ የባጃጅ ሾፌሮችም በየቦታው ትላክስና ጩኸት እያሰሙ ነው፡፡ የመስቀል አደባባይን መፍረስ በመቃወም በባህርዳር ከተማ የነበረው ሰልፍ ጥያቄውን አሰምቷል::

ነገረ ኢትዮጵያ እንደገለጸው ዘገባ

“• አምስት ሰዎች ሲቆስሉ ሁለት ሞተዋል
ዛሬ ጠዋት ባህርዳር ከተማ ላይ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ፖሊስ በኃይል ለመበተን ጥረት እያደረ ቢሆንም ህዝቡ በብዛት ተቃውሞውን እየተቀላቀለ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሌሎች አምስት ያህል ወጣቶች እንደቆሰሉ ተገልጾአል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከቀበሌ 10 አባይ ማዶ ያለው መንገድ ተቃውሞውን በተቀላቀለው ህዝብ የተዘጋ ሲሆን ወደ ጎንደር የሚወስደው መንገድም መዘጋቱ ታውቋል፡፡ የቀበሌ 8፣ 10ና 11 ነዋሪዎች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞውን እየተቀላቀሉ ነው ተብሏል፡፡ የአፈ ጉባኤ ጽ/ቤት አካባቢም በርካታ ህዝብ የተገኘ ቢሆንም ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት የሉም እንደተባሉ ገልጸውልናል፡፡” ነገረ ኢትዮጵያ

የሰልፉን ፎቶዎች ይመልከቱት:1937456_312016248996709_1054682142798199146_n

9783_596573470488802_1311708396556689267_n

የደብረ ዘይት የአየር ሃይል ባልደረባ ፓይለት አዲሱ አገኘሁ የግፍ አገዛዙን በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቀለ

Meron Ayele

የደብረ ዘይት የአየር ሃይል ባልደረባ ፓይለት አዲሱ አገኘሁ የግፍ አገዛዙን በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቀለ።Arbegna_Andinet_Bg_full

ሕዳር 30/2007 ዓ.ም ወደ አርበኞች ግንባር የትግል ጎራ የተቀላቀለው ፓይለት አዲሱ አገኘሁ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፓዊ ወረዳ ውስጥ ተወልዶ ያደገ መሆኑ ሲታወቅ በደብረ ዘይት አየር ሃይል ውስጥ ለስድስት/6/ ዓመት ያህል በአውሮፕላን አብራርነት ሙያ ላይ ተመድቦ ሲሰራ መቆየቱ ታውቋል።

ፓይለት አዲሱ አገኘሁ የመጀመሪያውን በረራ ያደረገው S.F 260 በሚባለው አውሮፕላን መሆኑ ሲታወቅ፦ በአየር ሃይል የቆይታ ጊዜያቶቹም የተለያዩ ስልጠናዎችን የተከታተለ መሆኑን ፓይለት አዲሱ አገኘሁ ገልፆ ከተከታተላቸው ኮርሶች መካከል በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ለ3 ዓመት ያህል ስልጠና የወሰደ ሲሆን፦ በግራውንድ ቶሪ ስልጠና በተመሳሳይ ለ3 ዓመት ያህል ሲከታተል ቆይቶ ከአሰልጣኞቹ ጋር ባለመግባባቱ ምክንያት ስልጠናውን ለማቋረጥ እንደተገደደ ፓይለት አዲሱ አገኘሁ አክሎ ገልጿል።

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የተቀላቀለው ፓይለት አዲሱ አገኘሁ ጨምሮ እንደገለፀው፦በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ተቋም ውስጥ በተማሪዎች የምግብ በጀት ላይ የተቋሙ አስተዳዳሪዎች እየፈፀሙት ያለው የሙስና ወንጀልና እንዲሁም በአየር ሃይል አባላት ላይ እየተሰራ ያለው የዘር መድሎ ልዩነት የተነሳ አገዛዙን ለመክዳትና የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች…

View original post 160 more words

ፓይለት አዲሱ አገኘሁ የግፍ አገዛዙን በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቀለ

Sebhat Amare

የደብረ ዘይት የአየር ሃይል ባልደረባ ፓይለት አዲሱ አገኘሁ የግፍ አገዛዙን በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቀለ።181277_330466667083194_498206512_n

ሕዳር 30/2007 ዓ.ም ወደ አርበኞች ግንባር የትግል ጎራ የተቀላቀለው ፓይለት አዲሱ አገኘሁ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፓዊ ወረዳ ውስጥ ተወልዶ ያደገ መሆኑ ሲታወቅ በደብረ ዘይት አየር ሃይል ውስጥ ለስድስት/6/ ዓመት ያህል በአውሮፕላን አብራርነት ሙያ ላይ ተመድቦ ሲሰራ መቆየቱ ታውቋል።

ፓይለት አዲሱ አገኘሁ የመጀመሪያውን በረራ ያደረገው S.F 260 በሚባለው አውሮፕላን መሆኑ ሲታወቅ፦ በአየር ሃይል የቆይታ ጊዜያቶቹም የተለያዩ ስልጠናዎችን የተከታተለ መሆኑን ፓይለት አዲሱ አገኘሁ ገልፆ ከተከታተላቸው ኮርሶች መካከል በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ለ3 ዓመት ያህል ስልጠና የወሰደ ሲሆን፦ በግራውንድ ቶሪ ስልጠና በተመሳሳይ ለ3 ዓመት ያህል ሲከታተል ቆይቶ ከአሰልጣኞቹ ጋር ባለመግባባቱ ምክንያት ስልጠናውን ለማቋረጥ እንደተገደደ ፓይለት አዲሱ አገኘሁ አክሎ ገልጿል።

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የተቀላቀለው ፓይለት አዲሱ አገኘሁ ጨምሮ እንደገለፀው፦በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ተቋም ውስጥ በተማሪዎች የምግብ በጀት ላይ የተቋሙ አስተዳዳሪዎች እየፈፀሙት ያለው የሙስና ወንጀልና እንዲሁም በአየር ሃይል አባላት ላይ እየተሰራ ያለው የዘር መድሎ ልዩነት የተነሳ አገዛዙን ለመክዳትና የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች…

View original post 160 more words

የደብረ ዘይት የአየር ሃይል ባልደረባ ፓይለት አዲሱ አገኘሁ የግፍ አገዛዙን በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቀለ

ሕዳር 30/2007 ዓ.ም ወደ አርበኞች ግንባር የትግል ጎራ የተቀላቀለው ፓይለት አዲሱ አገኘሁ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፓዊ ወረዳ ውስጥ ተወልዶ ያደገ መሆኑ ሲታወቅ በደብረ ዘይት አየር ሃይል ውስጥ ለስድስት/6/ ዓመት ያህል በአውሮፕላን አብራርነት ሙያ ላይ ተመድቦ ሲሰራ መቆየቱ ታውቋል።Arbegna_Andinet_Bg_full

ፓይለት አዲሱ አገኘሁ የመጀመሪያውን በረራ ያደረገው S.F 260 በሚባለው አውሮፕላን መሆኑ ሲታወቅ፦ በአየር ሃይል የቆይታ ጊዜያቶቹም የተለያዩ ስልጠናዎችን የተከታተለ መሆኑን ፓይለት አዲሱ አገኘሁ ገልፆ ከተከታተላቸው ኮርሶች መካከል በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ለ3 ዓመት ያህል ስልጠና የወሰደ ሲሆን፦ በግራውንድ ቶሪ ስልጠና በተመሳሳይ ለ3 ዓመት ያህል ሲከታተል ቆይቶ ከአሰልጣኞቹ ጋር ባለመግባባቱ ምክንያት ስልጠናውን ለማቋረጥ እንደተገደደ ፓይለት አዲሱ አገኘሁ አክሎ ገልጿል።

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የተቀላቀለው ፓይለት አዲሱ አገኘሁ ጨምሮ እንደገለፀው፦በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ተቋም ውስጥ በተማሪዎች የምግብ በጀት ላይ የተቋሙ አስተዳዳሪዎች እየፈፀሙት ያለው የሙስና ወንጀልና እንዲሁም በአየር ሃይል አባላት ላይ እየተሰራ ያለው የዘር መድሎ ልዩነት የተነሳ አገዛዙን ለመክዳትና የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ለመቀላቀል እንደቻለ ፓይለት አዲሱ አገኘሁ ጨምሮ ገልጿል ።

የደብረ ዘይት የአየር ሃይል አባላት በግፍ አገዛዙ በመማረር ከፊሉ ሃገር ጥለው እየኮበለሉ መሆናቸው ሲታወቅ፦ ከፊሉ ደግሞ ፀረ-ወያኔ የነፃነት ትግሉን በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፓይለት አዲሱ አገኘሁን ጨምሮ አምስት/5/ የአየር ሃይል ባልደረቦች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን መቀላቀላቸው የሚታወስ ነው።

በተያያዘ ዜና፦ ብዛት ያላቸው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቀሉ።

ሕዳር 30/2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ከተቀላቀሉት የጎንደር ዩኒቨርስቲ የB.A ተመራቂ ከሆኑት ተማሪዎች መካከል ተማሪ ቻላቸው ተክሉ ወ/ማሪያም ፣ ተማሪ ተስፋሁን ፈንታ እና እንዲሁም የጎንደር የቴክኒክ ማሰልጠኛ የ2ኛ ዓመት ተማሪዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቅለዋል።

እኒሁ በቡድን ሆነው ግንባሩን የተቀላቀሉት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በሰጡት የጋራ አስተያየት የመንግስት ሥራን ለመያዝ መስፈርቱ የፓለቲካ አመለካከት ወይም ወያኔያዊ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ የፓለቲካ ምዘና በመሆኑ በአሁኑ ጊዜ አፍቃሪ ወያኔ ያለሆነ የሐገሪቱ የተማረ ዜጋ እንኳንስ የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ ራሱን፣ ቤተሰቡንና ሃገሩን ሊያገለግል ቀርቶ በሥራ አጥነት እየባዘነ በሰላም ለመኖር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል በማለት በአገዛዙ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ተማሪዎቹ በቁጭት አስተያየታቸውን በጋራ ሰንዝረዋል።

አክራሪ … አሸባሪ … የሰለቸን መንግስታዊ መዝሙር … የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አክራሪነት/አሸባሪነት የህዝቦች ስጋት ነው፡፡ – ምንሊክ ሳልሳዊ

ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት/አሸባሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው:: ጥላችሁን እንዳታምኑ እየተባለ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር አክራሪነት ነው፡፡

«መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተ-አምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባል አይችልም፤»…የአክራሪ ክርስትና ወይንም እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም::አክራሪ ተብሎ የሚፈረጀው የሚራመዱ የፖለቲካ ጡዘቶች በሰዎች ላይ ሌላ እምነትን በመጫን በግዳጅ እና በሃይል ሊያስገድዱ ሲሞክሩ ይህ ማለት አህበሽን እና ተሃድሶን በጥንታውያኑ እስልምና እና ተዋህዶ ላይ በኢትዮጵያ እንደተሞከረው ማለት ነው::

አክራሪነት አሉታዊ ትርጉም ሲኖረው የራስን እምነትና አመለካከት በሌሎች ላይለመጫን መሞከር ነው፡፡ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር ራሱ አክራሪነት ነው፡፡ አክራሪነት የፖሊቲካ ገጽታ ያለው ነው፡፡ ኾኖም ግን ሃይማኖትን ማጥበቅ አክራሪነት አይደለም፡፡ሃይማኖት ፍጹም እውነታን በፍጹም እምነት ስለሚቀበል ከሌሎች ግላዊ አስተሳሰቦች የተለየ ነው፡፡ የሃይማኖት መገለጫዎችን መጠቀም የዚያን ሃይማኖት ጥልቀት የሚያሳይ እንጂ እንደ ችግርም የሚወሰድ ወይም አክራሪነት ሊኾን አይችልም፡፡ «መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተአምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባልአይችልም፤» ይላሉ የዘርፉ ምሁራን፡፡

የአክራሪነትና የአጥባቂነት ፅንሰ ሐሶቦች በጥሩ ኹኔታ ተለይተው ተገልጸዋል፡፡ አንዳንድ ሰነዶች ወያኔም ለይስሙላ የገለበጣቸው ሰነዶቹ አክራሪነትንና አጥባቂነትን በአግባቡ ለይተውና ተንትነው ያስቀምጣሉ፡፡ በዚሁ መሠረት አጥባቂነትን፣ ‹‹የግል ሃይማኖትን ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት ሳይንጠባጠብ ሁሉንም ትእዛዛት መፈጸም ነው፤» በማለት ሲፈታው አክራሪነትን ደግሞ፣ «ከራስ እምነት ወጥቶ ሌላውን መተንኮስና የሌሎችን ሃይማኖት መኖር አለማመንና አለመፍቀድወይም ሌሎቹን አስገድዶ የራስ እምነት ተከታዮች ለማድረግ መጣር ነው፤» ይላል፡፡ በተግባር ላይ አለመዋሉ እና በጣልቃ ገብነት መተርጎሙ ጉዳት አመጣ እንጂ::

ከዚህ ብያኔ ስንነሣ ክርስቲያንም ሆነ ሙስሊም ከርሱ ውጭ የኾኑትን የሌሎቹን መኖር የማይቀበልና ከግለሰቦቹ ፈቃድ ውጭ አስገዳጅ እስከኾነ ድረስ እርሱን አክራሪ ማለት ይቻላል፡፡መብትን መጠየቅ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መሸሽ አክራሪነት አይደለም:: በዚህ መልኩ አክራሪው ይህንኑ ድርጊት ሊፈጽም የተነሣውን ቡድን ብቻ እንጂ «አክራሪው ቡድን» የወጣበትን/የተገኘበትን ቤተ እምነት ሊወክል አይችልም፡፡ ስለዚህ በአለማቀፍ ደረጃ የአክራሪ ክርስትና እና እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም፤ ለሌላው ቤተ እምነትም እንዲሁ፡፡ ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው:: #ምንሊክሳልሳዊ

የማዕከላዊ ጭካኔ ያረፈባቸውን እማዋይሽ አለሙን እንወቃቸው

By: Dawit Solomon

ወይዘሮ እማዋይሽ አለሙ ደልደል ያለ ሰውነት፣አጠር ያለ ቁመና ያላቸው የፊት ገጽታቸው በብዙ ፈተና ውስጥ ለማለፋቸው እማኝነት የሚሰጥላቸው ፣ከአንደበታቸው የሚወጡ የተመጠኑና የተመረጡ ቃላት ከሚገኙበት የቃሊቲ ወህኒ ቤት በላይ ጮሆ የሚያስተጋባ ጠንካራ መንፈስ እንዳላቸው የሚመሰክርላቸው የሶስት ልጆች እናትና የልጅ ልጅ ማየት የቻሉ እንግሊዞች ቢያገኟቸው ጠንካራዋ እመቤት (The Iron Lady) የሚሉላቸው አይነት ናቸው፡፡

ኢህአዴግ የጸረ ሽብር አዋጁ ማሟሻ በማድረግ እነ ጄነራል ማሞን አጥረግርጎ ሲያስር እማዋይሽም ሚያዚያ 16 / 2001 በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ የሽብር ግብረ ሀይሉ በአዋጁ በሚጠረጥራቸው ሰዎች ላይ መረጃ የመሰብሰብ ልቅ የሆነ ስልጣን የተቀዳጀ ቢሆንም ተጠርጣሪዎቹን ወንጀለኛ ለማድረግ የተጠቀሙት ድብደባንና ማሰቃየትን ነበር፡፡

እማዋይሽ የዚሁ ግፍ ሰለባ በመሆናቸው የሰው ጆሮ ሰምቶ ሊሸከመው የማይችለው አይነት ስቃይ አስተናግደዋል፡፡ወደ መርማሪዎቻቸው ቢሮ አይናቸውን በጨርቅ ተሸፍነው ይገቡ የነበሩት እማዋይሽ ልጆቻቸው በሚሆኑ መርማሪዎች ልባሳቸው ወልቆ እርቃናቸውን ተደብድበዋል፣ ጡቶቻቸው በኤሌክትሪክ ሽቦ ተጠብሷል፣እጆቻቸው ታስሮ ከደረጃ ላይ በጡጫ ተገፍትረው እንዲወድቁ ተደርገዋል፡፡ ይህን ሁሉ ስቃይ ያስተናገዱት ‹‹ከሌሎቹ ታሳሪዎች ጋር መንግስት ለመገልበጥ ከግንቦት 7 ትዕዛዝ ተቀብለን ሞክረናል››ብለሽ ፈርሚ ተብለው ነው፡፡

ስቃዩ ሰው ሊሸከመው የሚችለው አልነበረምና እማዋይሽ አጅ ሰጥተው መርማሪዎቹ የሚሏቸውን አደረጉ፡፡ ፍርድ ቤቱም በዚህ መንገድ የቀረበለትን እንደ ማስረጃ ቆጥሮ እማዋይሽ ላይ የዕድሜ ልክ እስራት ወሰነባቸው፤ እማዋይሽ ያለፉትን ስድስት አመታት በወህኒ ቤት ያሳለፉ ሲሆን በምርመራ ወቅት ጡታቸው ላይ የደረሰው በኤልክትሪክ የተደረገ ማሰቃየት ህመም ፈጥሮባቸው በስቃይ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የተሻለ ምርመራ እንዳያገኙ ከመደረጉም በላይ የታዘዙላቸው መድሀኒቶች ዋጋቸው ከወህኒ ቤቱ አቅም በላይ ነው መባሉ ይነገራል፡፡

እኚህን በዚህ ስርዓት የግፍ ጡጫ ያረፈባቸውን እናት በቃሊቲ ወህኒ ቤት አግኝቼ መጎብኘት በመቻሌ በቅርቡ በተለቀቀው የማዕከላዊ የግፍ ሚስጥር ሪፖርት የተጠቀሰው የጭካኔ ድርጊት እውነት ለመሆኑ እንድመሰክር አድርጎኛል፡፡ ሙሉውን ሪፖርት ለማድመጥ ሊንኩን ይጠቀሙ

ክብር የግፍ በትር እያረፈባቸው ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ይሁን

የነጻነት ታጋዮች መልዕክት ከቃሊቲ እና ቂሊንጦ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

‹‹በሰላማዊ ሰልፈኛ ላይ ዱላ መሰንዘር ሽንፈት ነው›› እስክንድር ነጋ

ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች በትብብሩ ውስጥ የታቀፉ ፓርቲዎች በጠሩት የአዳር ሰልፍ ላይ የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰደውን አሳፋሪ እርምጃ ሰምቻለሁ፡፡ እርምጃው ሁለት ነገሮችን በጉልህ ያሳዬ ነበር፡፡ አንደኛ የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ሽንፍትን ያሳየ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ሰላማዊ ትግሉ እየተጠናከረ መምጣቱን ያመላከተ ነው፡፡

አንተ ባዶ እጅህን መብትህን ለመጠየቅ ስትንቀሳቀስ፣ መሳሪያ ወደታጠቀ አካል በሰላም ስትገሰግስ ባለመሳሪያው ዱላውን ከሰነዘረብህ አሸናፊው አንተ ሰላማዊው ታጋይ ነህ፡፡ በትብብሩ ሰልፍ ላይ የሆነው ይኸው ነው፡፡ አሁን ሰላማዊ ትግሉ ፍጹም ሰላማዊነቱን እንደጠበቀ መጠናከር ነው ያለበት፡፡ ሰላማዊ ትግል ላይ ልብ ማለት ያለብን ነገር አለ፤ እሱም ሰላማዊ ሆኖ መዝለቅ የሚለው ጉዳይ ነው፡፡

ሰላማዊ ታጋይ ይሰደባል፣ ይደበደባል፣ ይሞታልም፡፡ ግን ደግሞ ሰላማዊ ታጋይ አይሳደብም፣ አይደባደብም፣ አይገድልም፡፡ ይህ ከሆነ ሰላማዊ ትግል ያሸንፋል፡፡ አምባገነኖች ሰላማዊ ታጋዮችን በተለያየ መንገድ ከሰላማዊነታቸው እንዲወጡ ሊገፋፏቸው ይሞክራሉ፤ ስሜት ውስጥ በመክተትም የኃይል በትራቸውን ለማሳረፍ ይቋምጣሉ፡፡ ይህ ሴራ ሰላማዊ ታጋዮችን ሊያዘናጋቸው አይገባም፡፡

በቀደም በተደረገው ሰልፍ ላይ ድብደባው በሰላማዊ ሰዎች ላይ መፈጸሙ ለተደብዳቢዎቹ ሳይሆን ሽንፈቱ ለደብዳቢዎቹ ነው፡፡ በደረሰው ድብደባ ባፍርም፣ ባዝንም በውጤቱ ግን ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ሰላማዊ ሰልፈኞች ሰላማዊነታቸውን አሳይተዋልና! በሰልፉ ወቅት ድብዳባ እና እስር የደረሰባቸውን የመብት ጠያቂዎች ሁሉ በርቱ ልላቸው እፈልጋለሁ፡፡ ባደረጉት ሰላማዊ እንቅስቃሴ በጣም ኮርቻለሁ፡፡ ሰላማዊና ህጋዊ ትግላችሁን ቀጥሉ ማለትም እፈልጋለሁ!

‹‹አሸናፊው ህዝብ ነው›› አንዱዓለም አራጌ

ግለሰቦች የለውጥ ሐዋርያ ሊሆኑ ይችላሉ፤ በዚያው ልክ የሚሳሳቱትም ግለሰቦች ናቸው፡፡ የግለሰቦች አስተሳሰብ ህዝባዊ ከሆነ ግን በአሸናፊው ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡ ምክንያቱም አሸናፊው ህዝብ ነው፤ አሸናፊው ሀገር ነው፡፡ የሁላችንም አሸናፊነት የሚገለጸው ሀገር ከፍ ከፍ ስትል ነው፡፡ ስለዚህ ስራችን ሁሉ ሀገርን ከፍ ለማድረግ መሆን አለበት፡፡

በትብብሩ ፓርቲዎች በተጠራው ሰልፍ ላይ የሆነውን ሰምቻለሁ፡፡ በሆነው ነገር አዝኛለሁም፤ ኮርቻለሁም፡፡ ያዘንኩት በደረሰው ድብደባ እና እስር ነው፡፡ የኮራሁት ደግሞ መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ ሊጠይቁ በድፍረት አደባባይ በወጡት ታጋዮች ነው፡፡ በእነዚህ ታጋዮች የእውነት ኮርቻለሁ፡፡

በቀጣይ ፓርቲዎች በአጋርነት መስራት አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ በተለይ በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ፓርቲዎች ከእጩ አቀራረብ ጀምሮ ተቀራርበው መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይ ሰማያዊ እና አንድነት ተቀራርበው ቢሰሩ የበለጠ ውጤታማ የሚሆኑ ይመስለኛል፡፡ በተረፈ ግን በትብብሩ ሰልፍ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ ጥንካሬን እንዲሰጣቸው እመኛለሁ፡፡ ትግላቸውንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ እላለሁ፡፡

‹‹ቃላችሁን ጠብቃችኋልና ክብር ይገባችኋል፣ ኮርቸባችኋለሁም!›› የሺዋስ አሰፋ

ሰማያዊ ፓርቲ መርህ አለው፡፡ ያመነበትን ነገር ህጋዊና ሰላማዊነቱን ጠብቆ እንደሚፈጽም አውቃለሁ፡፡ ትብብሩ በጠራው ሰልፍ ላይም የሰማያዊ ወጣቶችና ሌሎችም ቃላቸውን ጠብቀው ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ በእውነት በጣም ኮርቸባቸዋለሁ፡፡ እንደሁሌውም ቃላቸውን ጠብቀው ለህዝቡ መብት መቆማቸውን አይቼ ደስ ብሎኛል፡፡ እኔ በእስር ላይ ብሆንም ሌሎች የትግል ጓዶቼ ባደረጉት ነገር በጣም ነው ደስ የተሰኘሁት፡፡

ድብደባውና እስሩ የፈሪ ዱላ ነው፡፡ ኢህአዴግ በህዝብ ፊት ኪሳራን ነው ያተረፈው፡፡ ሰላምን እና ህግን ማስጠበቅ የሚቻለው በልምምጥ ሳይሆን ትክክለኛ መስመርን በመከተል ነው፡፡ በዚህ መሰረት የትግል ጓዶቼ ትክክለኛ መስመር ላይ እንደሆኑ ይገባኛል፡፡ በርቱልኝ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ መሰል ሰላማዊነት ነው አምባገነኖችን ማሸነፍ የሚቻለው፡፡

የማለዳ ወግ …አስገራሚው ትዕይንት “በተስፋዋ” የአረብ ምድር በሳውዲ!

saudi-1* የገቡት ይወጣሉ ፣ የወጡት ተመልሰው ይመጣሉ
* የሳውዲ መንግስት “ህገ ወጦችን” የማጽዳቱ ዘመቻ ቀጥሏል
* ስፍር ቁጥር የሌላቸው ዜጎች ከሞት ጋር ተፋጠው እየተሰደዱ ነው
* የሳውዲ መንግስት ማስጠንቀቂያና እርምጃ …

የሳውዲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውንና ህጉ በማይፈቅደው መንገድ የመኖሪያ ፈቃዳቸው ካለው ሙያ ውጭ የሚሰሩ የማናቸውንም ሀገር ዜጎች በመላ ሀገሪቱ ለማጽዳት የተደራጀ ዘመቻ ከተጀመረ ወር ደፍኗል። በየቀኑ በመንግስትና በግል መገናኛ ብዙሃን የሚለቀቁት የማስጠንቀቂያ መረጃዎች ከበድ ከበድ ያሉ ናቸው ።

ዛሬ ማለዳ   ” ህገ ወጦችን ጠራርገን እናስዎጣለን ” ያሉትን የሰራተኛ ሚኒስቴር አድል ፈቂን ይዞ የወጣው አረብ ኒውስ ሚኒስትሩ ሃገራቸው ለህገ ወጥ ሰራተኞች ቦታ እንደሌላት በአጽንኦት መጠቆማቸውን ያስረዳል። የሰራተኛ ሚኒስትሩ በማከልም መንግስት ህገ ወጦችን እግር በእግር እየተከታተለ በመያዝ የማስወጣቱን ስራ እንደሚገፋበት ሲያስታውቁ 150 የሚደርሱ ተጨማሪ የሴት ተቆጣጣሪዎች ስልጠና ተሰጥቷቸው ህገ ወጦችን በማጣራቱ ስራ መሰማራታቸውን አስረድተዋል። ተቆጣጣሪዎች ስራቸው ሲከውኑ በተአማኒነት  ፣ በሃላፊት ፍትሃዊ በሆነ አግባብ ባለው መንገድና ስርአት መሆን እንደሚገባው ሚኒስትር አድል ፈቂ አሳስበዋል። የሰራተኛ ሚኒስቴር አድል ፈቂ በቤት ሰራተኛ አቀጣጣጠር ዙሪያ ያለውን ችግር ለመፍታታ ከ200 የተለያዩ ሃገር ዜጎች ጋር መምከራቸውንና በጠቃሚው ምክክር የተገኙትን መፍትሄ ሃሳቦች በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ አሳስበዋል።

ዘመቻው …

ወር በደፈነው በዚህ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ኢላማዎች ፈርጀ ብዙ በሆነ ምክንያት ሳውዲ ገብተው በህገ ወጥነት የሚኖሩትን ጨምሮ በኮንትራት ቪዛ መጥተው ከአሰሪዎቻቸው የጠፉትን ያጠቃልላል። ዘመቻው ጅዳ ደርሶ በተለያዩ አካባቢዎች በየመኖሪያ ቤቱ አሰሳው ተጠናክሮ መቀጠሉን የሳውዲ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡት ነው ። እስካሁን በቀጠለው በዚህ ዘመቻ በኢትዮጵያን ላይ ሲያዙ ማንገላታትም ሆነ የተለየ ጥቃት መስተዋሉን አልሰማሁም። መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ቢያዙም እየተጣራ ተለቀዋል። ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውና ለአሰሪያቸው የጠፉት ግን እየተያዙ ተወስደዋል። ዘመቻው ግን አሁንም ቀጥሏል … በዘመቻው የተያዙት በርካታ ዜጎችን ስልክ እየደወሉ እንደገለጹልኝ ከሆነ  ” በፍተሻው ስንያዝ የረባ ልብስ እንኳ አልለበስንም ፣ ለአመታት ያፈራነው ንብረታችን አልሰበሰብንም ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ቢያንስ ሻንጣችን ይዘን የምንገባበትን መንገድ ያዘጋጅልን  ” ሲሉ ተደጋጋሚ ምሬታቸውን ገልጸውልኛል !

ወደ ” ተስፋዋ ምድር ” ያላባራው ጉዞ …

ወደ “ተስፋዋ” የአረብ ሃገር ምድር ወደ ሳውዲ የሚደረገው ጉዞ አላቆመምም። የእኛ ደላሎች ከሳውዲ እስከ ሀገር ቤት ትላልቅ ከተሞች፣  ገጠርና የወረዳ ከተሞች በዘለቀ የእዝ ሰንሰለት ተደራጅተው በወገናቸው ስደት ተጠቃሚ ሆነዋልና በማን አለብኝነት ሰውን እያጋዙት ይገኛሉ ። አምና ካቻምናና ዘንድሮ በአሳር በመከራ ሀገር ቤት የገቡት ኢትዮጵያውያን እነሱ ” የተስፋ ምድር ” ወደ ሚሏት ሳውዲ እየጎረፉ ነው። ባሳለፍነው ወር በተደጋጋሚ የየመን የቀይ ባህር ዳርቻ የቅርብ ርቀት ባህር ከበላቸው ወገኖች ባልተናነሰ በየበርሃው በአሸጋጋሪ ደላሎች ታግተው አሳር መከራቸውን የሚያዩትን ወገኖች የከፋ የስቃይ ስደት ህይዎት ያማል ።

እነ ሞት አይፈሬዎች የእኛ ዜጎች አሳምረው የሚያውቁትን የሞት ጉዞ ተከትለው ፣ ሞትን ዳግም ለመፋጠጥ ቆርጠው ፣ ከቀያቸው ነቅለው  የመጡ ይመስላል። እነሱን በአደጋ አስከብቦ እዚህ ስላደረዳቸው ምክንያት አብዛኞችን ስንጠይቃቸው ጣራ የነካው የኑሮ ውድነት ፣  ድህነት ፣ የተሻለ ኑሮ ፍለጋውን አማረው ይነግሩናል። አንዳንዶች ከተጠቀሰው ምክንያት አዳምረው በሀገር ቤት የፖለቲካው ትኩሳት ሙቀት የመለብለቡ ፍርሃቻን እንደ ምክንያት ያቀርቡታል። ያን ሰሞን ሃገር ቤት ለእረፍት የሄዱ የቤተሰብ አባሎቸንና ወዳጆቸን ሀገር ቤት ስላለው የኑሮ ውድነትና ኑሮ ጠይቄያቸው የእድገት ምጥቀቱን ፣ ገንዘብ ላለው ሀገር ቤት የመመቸቱንና አንገቱን ደፍቶ ልስራ ላለ ስራ ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል አጫውተውኛል። ታዲያ ሰው ለምን ይሰደዳል?  ለሚለው ጥያቄየ ግን መልሱ ” እሱ ግራ የሚያጋባ ነው! ” የሚል ነው ። እርግጥ ነው ይህ ምላሽ አጥጋቢ ሆኖ አላገኘሁትም … የሀገር ቤቱ እውነታ እድገት ምጥቀቱ ፣ ገንዘብ ላለው ሀገር ቤት የመመቸቱንና አንገቱን ደፍቶ ልስራ ላለ ስራ ሰርቶ መለወጥ እየተቻለ አስከፊውን ስደት የማያውቁትን ቢያጓጓም ከሞት ጋር ተፋጠው ተሰደውና ወደ ሀገር ቤት በዘመቻ ተመልሰው የገቡት እንዴት የመከራ ሰቀቀኑን የአረብ ሀገር ስደት መረጡት?  ብሎ መጠየቅ ግድ ይላል ፣ ለዚህም ሁነኛ የሆነ መልስ ሰጭ አካል አልተገኘም !  ይህ ምላሽ እስኪያገኝ ግን ወደ “ተስፋዋ የአረብ ምድር ”  የሚደረገው ስደት ተጠናክሮ ቀጥሏል …
ላለፉት ሶስትና አራት ተከታታይ አመታት የሁለት ሃገራት ውል ባልተዋዋሉበት ፣ ቅድመ ዝግጅት ባልተደረገበት ሁኔታ በኮንትራት ስራ ስም ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ አብዛኛው ሴት እህቶቻችን ወደ ሳውዲ ገብተዋል። ምንም እንኳን የተሳካላቸው በተወሰነ መንገድ እራሳቸውን ረድተው ቤተሰቦቻቸውን እየረዱ መሆናቸው ባይካድም መብት ጥበቃ የጎደለባቸው ፣  ያለተሳካላቸው ከአሰሪዎቻቸው ጠፍተው ህገ ወጥ ነዋሪነቱን ተቀላቅለው የሰቀቀን ኑሮን እየገፉ ነው። በአንጻሩ በአሰሪዎቻቸው ተቀፍድደው ተይዘው መላወሻ ያጡት የተጨነቁት ምንም ማድረግ ያልቻሉት ከጨለማው ኑሮ ከእገታው ለመላቀቅ በለየለት ወንጀል ተዘፍቀው ስማችን አክፍተውታል። የቀሩት አሁን ድረስ የገሃነም ኑሮን እየኖሩ ነው። የዚህ ሁሉ ክስተት ምክንያት ህጋዊ ውል በሌለበት ፣ የመብት ጥበቃው ባልተጠናከረበት ሁኔታ የኮንትራት ስራ መጀመሩ መሆኑን ገና ኮንትራት ሊጀመር ነው ሲባል እኔም ሆንኩ ” ያገነባናል ” ያልን ባቀረብናቸው ጭብጥ መረጃዎች እንደ ዜጋ ከነ ነባሬ መፍትሄ ሃሳቡ ጥቁመ ነበር ።  ያ ሰሚ ሳያገኝ ቀርቶ እዚህ ደርሰናል። ይህ በመሆኑ ትልቅ ስህተት ተሰርቷል ባይ ነኝ።

ዛሬም ” ከስህተቱ ተምረናል ” ብለን እያቀነቀንን ፣ ግን ከስህተቱ ያለመማራችን ጠቋሚ መረጃ እየሰማን ነው ። ከአመት በፊት የተዘጋው የኮንትራት ስራ ሊከፈት “ረቂቅ ደንብ ” ወጥቷል ተብሏል። ያን ሰሞን ኤጀንሲዎች በረቂቁ ዙሪያ ሲመክሩ በዜጎች መብት ማስጠበቅ ዙሪያ ያሉት ነገር ባይሰማም ስለሚያስይዙት ገንዘብ አማረው ሲናገሩ ሰምተናል። በውይይቱ የገንዘቡ ከፍ ማለት “ህገ ወጥ ስደቱን ያባብሰዋል” ያሉት ኤጀንሲዎች ስለየትኞቹ ህገ ወጥ ስደተኞች እንደሚያወሩ ግራ እየገባን መመጻደቁን ሰምተነዋል ። ይህን ማለቴ ህገ ወጥነትን ያባብሳል ያሉት አይገባምና ነው ፣ ለመሆኑ ባህር ቆርጠው በየመን እየገቡ ያሉት አብዛኛው ወንድ ወንድሞቻችን የገጠር ልጆች የኮንትራት ስራ ቪዛው ተጠቃሚ አድርጎ መውሰዱና አግባብ ነውን?  ይህ ማስመሰያ ምክንያት ሊታረም ይገባል ።   ያም ሆኖ በኤጀንሲዎችና በደላሎች አማካኝነት በየመን ፣  በሱዳንና በዱባይ የጉብኝት ቪዛዎች ሽፋን እየተሰጣቸው አሁን ድረስ ለሚሰደዱትን መላ አልተገኘለትምና ጉዞው አላቆመም ። የኤጀንሲዎች “ህገ ወጥ ጉዞን ያበረታታል ” ለማለት የሰጡት ምክንያት እኒህኞቹን ለመታደግ ከሆነ ደግሞ እንደ ዜጋ ኤጀንሲዎች አዲሱ ረቂቅ ከገንዘብ ማስያዙ በላይ ቀድሞውንም ባላስጠበቁት መብት ላይ መነጋገር እንጅ በየጣለባቸው ግዴታ ላለማሟላት ጉንጭ አልፋ ምክክር ማድረጋቸው አያስደስትም ።

ማጠቃለያ

የኢትዮጵያ መንግስት በአረብ ሃገሩ ስደት ጉዳይ ላይ ከፕሮፖጋንዳ ያለፈ ጥልቅ ጥናት ባላደረገበት ሁኔታ የሚሰራውን ስራ ቆሞ ሊመረምር ግድ ይለዋል !

ወገኔ ሆይ  ፣ በሃገር ቤት ወደ አረብ ሃገራት ለመሰደድ የቋመጠው ወገንም ከፊት ለፊቱ ያለውን አደጋ ሊያስተውልና ሊመረምረው ይገባል !  በባህር እና በበርሃው በባዕድ ምድር ደመ ከልብ ሆኖ ከማለፍ በወገን መካከል በሃገር የመጣውን ችሎ ማለፉ ይበጃል ባይ ነኝ  !

ባለ ጊዜ ባለጸጋዎች ደላሎች ሆይ  ፣ ላንድ አፍታ ወደ ነፍሳችሁ ተመልሳችሁ በወገኖቻችሁ በተለይል ለአቅመ አዳም በደረሱና ባልደረሱ እህቶችን ላይ ቅቤ እያነጎታችሁ በማማለል እየፈጸማችሁት ያለውን ዘመን የማይሽረው  ግፍና በደል ተረጋግታችሁ አስቡት !  ጊዜው ቢያልፍም ፣ በሰራችሁት በደል ጠያቄ እንኳ ቢታጣ ውሎ አድሮ ከማይተዋችሁ የህሊና ጸጸት ለመዳን ስትሉ ከክፉው ምግባራችሁ ራሳችሁን ለመግታት ሞክሩ  ! ሌላ ምን እላለሁ  !

ቸር ያሰማን   !

ነቢዩ ሲራክ

በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ኢሳትና የግንቦት 7 ፣ በፕሮቴስታንት ደግሞ የኦነግ ሰዎች አሉ ሲሉ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ተናግሩ

ኢሳት ዜና

ታኀሳስ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የፌደራልና የክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች በባህርዳር በተሰባሰቡበት ወቅት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ፣ ይህን የተናገሩት የሃይማኖት ተቋም የፖለቲካ ፍላጎት ማራመጃ መሆኑን ለማስረዳት ነው። ዶ/ር ሽፈራው ከአፋር የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ” መንግስት ለምን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ይገባል? ለምንስ በአገራችን የሌለ ችግር ያመጣብናል?” በሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ዶ/ር ሽፈራው ይህንን ለማስረዳት ይጠቅማል ያሉዋቸውን ምሳሌዎች አቅርበዋል።  በጥቅምቱ የሲኖዶስ ጉባኤ የኢሳት ሬዲዮና ቴሌቪዥን የሲኖዶሱን ውሎ በእየለቱ ሲዘግብ የነበረው በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ በሚገኙ አባላት አማካኝነት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፣ ግንቦት7 እና ኢሳት ሃይማኖትን ለፖለቲካ እምነት ማራመጃ ለመጠቀም እንደሚፈልጉ ዋናው ማሳያ ነው ሲሉ ደምድመዋል

ፕሮቴስታንት ሃይማኖት ለኦነግ አላማ ማስፈጸሚያ እያገለገለ መሆኑን  የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ ኦነግ ከፕሮቴስታንት አልፎ ዋቄ ፈታንም እየተጠቀመ ነው ብለዋል አክራሪነት ስልቱን ቀየረ እንጅ አልተሸነፈም ያሉት ዶ/ር ሽፈራው፣ በሚቀጥሉት ወራት በሃይማኖት ተቋማት ላይ፣ በትምህርት ቤቶች፣ በወጣትና ሴቶች ማህበራት ሰፊ ዘመቻ እንዲጀመር መክረዋል። በተለይ አዲስ አበባ ስራዎች ቢሰሩም ተመልሶ ማጥ የሚገቡበት በመሆኑ፣ የአዲስ አበባ መዋቅራችን አክራሪነትን አሸነፍኩ ብሎ ሊዘናና እንደማይገባው አሳስበዋል።

ማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን በተለይም ፌስቡክና ትዊተር ትልቅ ችግር እየፈጠሩ ነው  ያሉት ሚኒስትሩ፣ እነዚህን የመገናኛ ብዙሃን ለመጠቀም እቅድና ስትራቴጂ ተነድፎ በሙሉ ጊዜና ሃይል የሚሰራ ሰው መድቦ መንቀሳቀስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህን ተግባራዊ ማድረግ የትግሉ ዋናው አካል መሆን ይገባዋል ብለዋል

መጪውን ምርጫ በተመለከተ በሁዋላ ላይ ችግር ሳይፈጠር ከአሁኑ እርምጃዎችን በመውሰድ መንቀሳቀስ እንደሚገባም አክለዋል። በአገሪቱ ያሉ የጸጥታ ሃይሎች በምርጫው ላይ መውሰድ ስለሚገባቸው እርምጃም ውይይት አድርገዋል። የውውይቱ ውጤት እንደደረሰን ለህዝብ የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ማህበረ ቅዱሳን ከቀኖና ጋር በተያያዘ ለመክሰስ የተዘጋጁ የደህንነት መስሪያ ቤት ያደራጃቸው ሰዎች ምክክር እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። ሰዎቹ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ስልጠና እየወሰዱ ሲሆን፣ ከተወሰኑ ጊዜያት በሁዋላ በማህበረ ቅዱሳን ላይ በሃሰት በመመስከር ማህበረ ቅዱሳን የእኛ ነው በሚል ነባሩን ድርጅት ለማሳገድ እና ለገዢው ፓርቲ ተለጣፊ የሆነ ማህበረ ቅዱሳን ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል። በማህበረ ቅዱሳን ስም ማህተም ከማስቀረጽ ጀምሮ የተለያዩ ህገደንቦችን እያረቀቁ መሆኑን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሰጡት አስተያየት

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሰጡት አስተያየት ትብብሩ ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ እንደሚገባ በማህበራዊና በሌሎች ሚዲያዎች ተላልፏል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አቶ ግርማ እንደሚከተለው መልስ ሰጥተውበታል፡፡

‹‹እኛ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው›› አቶ ግርማ በቀለ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ

አንድ የሌላ ፓርቲ ደጋፊ ማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ ምርጫው ውስጥ ስለመግባትና አለመግባት ላይ ባነሳው ክርክር የግል አስተያየቴን ሰጥቼ ነበር፡፡ ይህ የግል አስተያየትም ትብብሩም ሆነ አባል ፓርቲዎች በምርጫው ሂደት ላይ ምንም አይነት ጥያቄ ሳያነሱ ወደ ምርጫው እንደሚገቡ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭቷል፡፡

አንድ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ ሲል የምርጫ ፓርቲ ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የምርጫ ፓርቲ ሆኖ እንደ ስልት በምርጫ ላይ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ አይችልም፡፡ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ የሚችለው በምርጫው ሂደት ላይ ነው፡፡ በሌላ በኩል አንድ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ የሚል ፓርቲ ስልጣን ሊይዝ የሚችለው በምርጫ ነውና ምርጫ እገባለሁ ብሎ ሊያውጅ አይችልም፡፡ የምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ ሲያነሳ ደግሞ ከምርጫው ራሱን አገለለ ማለት አይደለም፡፡ እኛ በምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከአሁኑ ራሳችን ከምርጫ ያገለልን የሚመስላቸው አካላት አሉ፡፡ ግን እኛ ራሳችን አላገለልንም፡፡ ከአሁኑ ምርጫ እንሳተፋለን ብሎ ማወጅም አላስፈለገንም፡፡ ከዚህ ይልቅ ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡

ስለሆነም ምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄዎችን አንስተን ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡ ስለሆነም በምርጫው ሂደት ላይ አለን ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በሂደቱ ላይ አለን ማለት ጥያቄዎቹ ሳይመለሱ ምርጫውን እንሳተፋለን ማለት አይደለም፡፡ በምርጫው ሂደት ሲሳተፍ ቆይቶ ሂደቶቹ ፍትሓዊ ባለመሆናቸው፣ የተነሱት ጥያቄዎች ባለመመለሳቸውና በሂደቱ ላይ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው ራሱን ከምርጫው ያገለለ ፓርቲ አውቃለሁ፡፡

ከአሁኑ ምርጫው ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከምርጫው ራሳችን አግልለናል ማለት አይደለም፡፡ እኛም ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው፡፡ ሂደቱ ፍትሓዊ ካልሆነ አጃቢ መሆን አንፈልግም፡፡ ለዛም ነው ሂደቱን ለማስተካከል ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል እየታገልን ያለነው፡፡ በትግላችን መሰረት ሂደቱን እናስተካክለዋለን ብለን እናስባለን፡፡

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሰጡት አስተያየት ትብብሩ ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ እንደሚገባ በማህበራዊና በሌሎች ሚዲያዎች ተላልፏል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አቶ ግርማ እንደሚከተለው መልስ ሰጥተውበታል፡፡

‹‹እኛ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው›› አቶ ግርማ  በቀለ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ

አንድ የሌላ ፓርቲ ደጋፊ ማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ ምርጫው ውስጥ ስለመግባትና አለመግባት ላይ ባነሳው ክርክር የግል አስተያየቴን ሰጥቼ ነበር፡፡ ይህ የግል አስተያየትም ትብብሩም ሆነ አባል ፓርቲዎች በምርጫው ሂደት ላይ ምንም አይነት ጥያቄ ሳያነሱ ወደ ምርጫው እንደሚገቡ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭቷል፡፡ 

አንድ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ ሲል የምርጫ ፓርቲ ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የምርጫ ፓርቲ ሆኖ እንደ ስልት በምርጫ ላይ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ አይችልም፡፡ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ የሚችለው በምርጫው ሂደት ላይ ነው፡፡ በሌላ በኩል አንድ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ የሚል ፓርቲ ስልጣን ሊይዝ የሚችለው በምርጫ ነውና ምርጫ እገባለሁ ብሎ ሊያውጅ አይችልም፡፡ የምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ ሲያነሳ ደግሞ ከምርጫው ራሱን አገለለ ማለት አይደለም፡፡ እኛ በምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከአሁኑ ራሳችን ከምርጫ ያገለልን የሚመስላቸው አካላት አሉ፡፡ ግን እኛ ራሳችን አላገለልንም፡፡ ከአሁኑ ምርጫ እንሳተፋለን ብሎ ማወጅም አላስፈለገንም፡፡ ከዚህ ይልቅ ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡ 

ስለሆነም ምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄዎችን አንስተን ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡ ስለሆነም በምርጫው ሂደት ላይ አለን ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በሂደቱ ላይ አለን ማለት ጥያቄዎቹ ሳይመለሱ ምርጫውን እንሳተፋለን ማለት አይደለም፡፡ በምርጫው ሂደት ሲሳተፍ ቆይቶ ሂደቶቹ ፍትሓዊ ባለመሆናቸው፣ የተነሱት ጥያቄዎች ባለመመለሳቸውና በሂደቱ ላይ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው ራሱን ከምርጫው ያገለለ ፓርቲ አውቃለሁ፡፡ 

ከአሁኑ ምርጫው ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከምርጫው ራሳችን አግልለናል ማለት አይደለም፡፡ እኛም ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው፡፡ ሂደቱ ፍትሓዊ ካልሆነ አጃቢ መሆን አንፈልግም፡፡ ለዛም ነው ሂደቱን ለማስተካከል ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል እየታገልን ያለነው፡፡ በትግላችን መሰረት ሂደቱን እናስተካክለዋለን ብለን እናስባለን፡፡