ለጋዜጠኞች ጥያቄ ዕድል የነፈገው ‹‹ታሪካዊው›› የዛሬ የምርጫ ቦርድ ጋዜጣዊ መግለጫ (ኤልያስ ገብሩ ጎዳና )

በዛሬው ዕለት ጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ በሂልተን ሆቴል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲንና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)ን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር፡፡ በመግለጫውም የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እና የቦርዱ ጸሐፊና የጽ/ቤቱ ዋና ኃላፊ አቶ ነጋ ዱሬሳ ተገኝተው የመግለጫውን ዓላማ እና ስምንት ገጽ የሆነውን መግለጫ አንብበዋል፡፡Elias Gibru

‹‹የአንድነት የቦርድ ዕውቅና ያለው መተዳዳሪያ ደንብ የ2004 ዓ.ም ስለመሆኑ፣ ቦርዱ የፓርቲውን እንቅስቃሴ ከዚሁ የቦርድ ዕውቅና ካለው ደንብ አንጻር ሲመረምር እንደቆየና አሁንም ከዚሁ አኳያ የመረመረ ስለመሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል›› የሚለው መግለጫ፣ አሁን ተመርጠናል በሚሉት በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ ቡድን በኩል የተፈጸሙ ዋና ዋና ጥሰቶች በሚል ሰባት ነጥቦችን ዘርዝሯል፡፡

በእነ ትፍስቱ አወሉን ቡድን በተመለከተ ደግሞ አምስት ነጥቦችን በመዘርዘር ሕግ ማክበራቸውን ይጠቅሳል፡፡

መግለጫው አንድነትን በተመለከተ በመጨረሻ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የእነ አቶ በላይ ፈቃዱ ቡድን ያካሄዱት የአመራር ምርጫ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና ከምርጫ ሕጉ ድንጋጌዎች ውጪ በመሆኑ ዕውቅና እንደማይሰጠው፤ በሌላ በኩል በእነ ትዕግሥቱ አወል ቡድን በቀን ጥር 16 ቀን 2007 ዓ›ም የተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በቡርዱ ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡ በመሆኑም ቦርዱ የእነ አቶ ትዕግሥቱ ዓወሉ ሁድን ፓርቲውን በመምራት ወደምርጫው እንዲገቡ በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ወስኗል››

መኢአድን አስመልክቶ መግለጫው አሁን ተመርጠናል በሚሉት በእነ አቶ ማሙሸት አማረ ሁድን የተፈጸሙ የህግ ጥሰቶች በሚል አራት ነጥቦች ዘርዝሯል፡፡ በሌላ በኩል በእነ አቶ አበባው መሐሪ ቡድን በኩል ያለውን እንቅስቃሴ የፓርቲውን ደንብ ያከበረ መሆኑን ጠቅሶ ‹‹የእሳቸው የምርጫ ሂደትም ሆነ የተመረጡበት የጠቅላላ ጉባኤ ውጤት ሪፖርት በቦርዱ ዕውቅና ተሰጥቶታል›› ይላል፡፡

መግለጫው በማጠቃለያው፣ አንድነትን እነአቶ ትዕግሥቱ አወሉ እና መኢአድን ደግሞ እነአቶ አበባው መሐሪ ፓርቲውን በመምራት ወደምርጫው እንዲገቡ በአንድ ድምጽ መወሰኑን ይገልጻል፡፡

መግለጫውን ያነበቡት አቶ ነጋ ዱሬሳ ወደመጨረሻ ላይ በፊታቸው ላይ ፍርሃት አዘል ስሜት በግልጽ ይነብባቸው ነበር፡፡ ከመግለጫው ከኋላ በቦታው የተገኘን ከ10 በላይ ጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ብንነሳም ፕሮፌሰር መርጋ ‹‹ጥያቄ አትጠይቁን›› በማለት የቪ.ኦ.ኤ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ጋዜጠኛ መለስካቸው አምሐ አንድ ጥያቄ በትግል ካቀረበላቸው በኋላ አጭር መልስ ሰጥተው ወዲያው ተነስተው ከአዳራሹ ወጥተዋል፡፡

መግለጫው እስር በእርስ የሚጋጩ ሀሳቦችን መያዙን የዚህ ዜና ዘጋቢ ለመረዳት ችሏል፡፡ ይህንንና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ብናስብም እነፕሮፌሰር መርጋ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት ጥያቄ ለማቅረብ ዕድል ማግኘት ሳንችል ቀርቷል፡፡
በስፍራው የነበሩ የግል ጋዜጠኞች ‹‹ዘንድሮ ምን አይነት ምርጫ ልናይ ነው?›› በማለት በሀዘኔታ ሲናገሩ ተስተውሏል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s