ደላሎች ለሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ እንዳያከራዩ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

‹‹ለአሸባሪ ፓርቲ ቢሮ ብታከራዩ ተጠያቂነቱን ትወስዳላችሁ›› የቂ/ክ/ከ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ

የቤት ደላሎች ለሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ እንዳያከራዩ ከቀበሌ ባለስልጣናት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ተደራጅተው በመስራት ላይ የሚገኙት ደላሎች የቂ/ክ/ከ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ከበደ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ አሸባሪ ፓርቲ ነው፡፡ ለአሸባሪ ፓርቲ ቢሮ ብታከራዩ ተጠያቂነቱን ራሳችሁ ትወስዳላችሁ›› ብለው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ እንደሰጧቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ለማከራየት ተስማምተው የነበሩ አንድ ግለሰብ በቀበሌ ካድሬዎች ትዕዛዝ ቤቱን እንዳያከራዩ ተደርገዋል፡፡ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ደላሎች ግለሰቧን ‹‹መጀመሪያ ቀበሌ ሄደሽ ለሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ልታከራይ መሆኑን አሳውቂ›› ብለው በመከሯቸው መሰረት ቀበሌ ሄደው ‹‹ለሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ላከራይ ነበር፡፡ ምን ችግር ይኖረዋል?›› ብለው ሲጠይቁ የቀበሌ ካድሬዎች ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ህገ ወጥና አሸባሪ ፓርቲ ነው፡፡ ለእሱ ቢሮ ማከራየት በህግ ያስጠይቅሻል›› ብለው ስላስፈራሯቸው ለማራየት ሳይደፍሩ ቀርተዋል፡፡

የየካ ክፍለ ከተማና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ በጋራ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ እንዳይከራይ ደላሎቹና አከራዮችን እያስጠነቀቁ ሲሆን ሰማያዊ ፓርቲ ካሳንቺስ የሚገኘው ጽ/ቤቱን እንዲለቅ በቤቱ ባለቤቶች ላይ ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ አከራዮቹ በቀበሌ ባለስልጣናትና በደህንነቶች በደረሰባቸው ጫና ምክንያት ፓርቲው ቤታቸውን እንዲለቅላቸው፣ ካልለቀቀም አሁን ከሚከፍለው 3 እጥፍ ገንዘብ እንዲከፍላቸው ጠይቀዋል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s