ለጋዜጠኞች ጥያቄ ዕድል የነፈገው ‹‹ታሪካዊው›› የዛሬ የምርጫ ቦርድ ጋዜጣዊ መግለጫ (ኤልያስ ገብሩ ጎዳና )

በዛሬው ዕለት ጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ በሂልተን ሆቴል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲንና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)ን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር፡፡ በመግለጫውም የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እና የቦርዱ ጸሐፊና የጽ/ቤቱ ዋና ኃላፊ አቶ ነጋ ዱሬሳ ተገኝተው የመግለጫውን ዓላማ እና ስምንት ገጽ የሆነውን መግለጫ አንብበዋል፡፡Elias Gibru

‹‹የአንድነት የቦርድ ዕውቅና ያለው መተዳዳሪያ ደንብ የ2004 ዓ.ም ስለመሆኑ፣ ቦርዱ የፓርቲውን እንቅስቃሴ ከዚሁ የቦርድ ዕውቅና ካለው ደንብ አንጻር ሲመረምር እንደቆየና አሁንም ከዚሁ አኳያ የመረመረ ስለመሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል›› የሚለው መግለጫ፣ አሁን ተመርጠናል በሚሉት በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ ቡድን በኩል የተፈጸሙ ዋና ዋና ጥሰቶች በሚል ሰባት ነጥቦችን ዘርዝሯል፡፡

በእነ ትፍስቱ አወሉን ቡድን በተመለከተ ደግሞ አምስት ነጥቦችን በመዘርዘር ሕግ ማክበራቸውን ይጠቅሳል፡፡

መግለጫው አንድነትን በተመለከተ በመጨረሻ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የእነ አቶ በላይ ፈቃዱ ቡድን ያካሄዱት የአመራር ምርጫ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና ከምርጫ ሕጉ ድንጋጌዎች ውጪ በመሆኑ ዕውቅና እንደማይሰጠው፤ በሌላ በኩል በእነ ትዕግሥቱ አወል ቡድን በቀን ጥር 16 ቀን 2007 ዓ›ም የተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በቡርዱ ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡ በመሆኑም ቦርዱ የእነ አቶ ትዕግሥቱ ዓወሉ ሁድን ፓርቲውን በመምራት ወደምርጫው እንዲገቡ በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ወስኗል››

መኢአድን አስመልክቶ መግለጫው አሁን ተመርጠናል በሚሉት በእነ አቶ ማሙሸት አማረ ሁድን የተፈጸሙ የህግ ጥሰቶች በሚል አራት ነጥቦች ዘርዝሯል፡፡ በሌላ በኩል በእነ አቶ አበባው መሐሪ ቡድን በኩል ያለውን እንቅስቃሴ የፓርቲውን ደንብ ያከበረ መሆኑን ጠቅሶ ‹‹የእሳቸው የምርጫ ሂደትም ሆነ የተመረጡበት የጠቅላላ ጉባኤ ውጤት ሪፖርት በቦርዱ ዕውቅና ተሰጥቶታል›› ይላል፡፡

መግለጫው በማጠቃለያው፣ አንድነትን እነአቶ ትዕግሥቱ አወሉ እና መኢአድን ደግሞ እነአቶ አበባው መሐሪ ፓርቲውን በመምራት ወደምርጫው እንዲገቡ በአንድ ድምጽ መወሰኑን ይገልጻል፡፡

መግለጫውን ያነበቡት አቶ ነጋ ዱሬሳ ወደመጨረሻ ላይ በፊታቸው ላይ ፍርሃት አዘል ስሜት በግልጽ ይነብባቸው ነበር፡፡ ከመግለጫው ከኋላ በቦታው የተገኘን ከ10 በላይ ጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ብንነሳም ፕሮፌሰር መርጋ ‹‹ጥያቄ አትጠይቁን›› በማለት የቪ.ኦ.ኤ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ጋዜጠኛ መለስካቸው አምሐ አንድ ጥያቄ በትግል ካቀረበላቸው በኋላ አጭር መልስ ሰጥተው ወዲያው ተነስተው ከአዳራሹ ወጥተዋል፡፡

መግለጫው እስር በእርስ የሚጋጩ ሀሳቦችን መያዙን የዚህ ዜና ዘጋቢ ለመረዳት ችሏል፡፡ ይህንንና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ብናስብም እነፕሮፌሰር መርጋ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት ጥያቄ ለማቅረብ ዕድል ማግኘት ሳንችል ቀርቷል፡፡
በስፍራው የነበሩ የግል ጋዜጠኞች ‹‹ዘንድሮ ምን አይነት ምርጫ ልናይ ነው?›› በማለት በሀዘኔታ ሲናገሩ ተስተውሏል፡፡

Advertisements

የአንድነት ለፍትሕና ዴሞክራሲ ቢሮ በፖሊሶች ና በደህንነት በመከበቡ አመራሮችና አባላቱ ወደ ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጭ መውጣት አልቻሉም

የአንድነትና የመኢአድ ቢሮ በፖሊስ ተከቧል

UDJ office
የአንድነት ለፍትሕና ዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ቢሮ በፖሊሶች ና በደህንነት መከበቡን አቶ አስራት አብርሃ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ቢሮው በደህንነትና በፖሊስ በመከበቡ አባላት መውጣትና መግባት እንደማይችሉ የገለጹት አቶ አስራት ‹‹ውጭ ያለነው ወደ ውስጥ እንዳንገባ ተከልክለናል፡፡ ውስጥ ያሉትም መውጣት አይችሉም፡፡›› ብለዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችና አባላት እንዳይወጡና እንዳይገቡ የከለከሉት ደህንነትና ፖሊሶች የከበባውን ምክንያት እንደማይናገሩ አቶ አስራት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቢሮው በፖሊስና በደህንነቶች በመከበቡ አመራሮችና አባላቱ ወደ ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጭ መውጣት እንደማይችሉ ተግልጾአል፡፡

– See more at:http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38595#sthash.rFHH300f.dpuf

ትግሬ ሆይ ለራስህ ስትል ጣፍጥ – ከሄኖክ የሺጥላ

ethiowaga.gif

ቆራጡ የትግራይ ሕዝብ ፣ የወያኔ መጠቀሚያ/መጥቀሚያ ከሆነ ሁለት ድፍን አስርት ዓመት አለፉ ። ይህም ያልፋል ፣ የማያልፍና የማይለወጥ የሰማይ የምድሩ ጌታ አንድ አምላክ እግዚያብሄር / አላህ ብቻ ነው የሚለውን እስክያዘነጉዋቸው ድረስ ፣ እናቴን ያገባ ሁሉም አባቴ ነው በሚል ፈሊጥ ፣ አልያም እኔ እንኩዋ ስልጣን ላይ ባልሆን ፣ አጎቴ ግን ስለሆነ በሚመስል መልኩ ይሄን ጨቁዋኝ መንግስት በከፍተኛ ሁናቴ በሁለት እግሩ እንዲቆም ዛሬም ድጋፍ እንደሆኑ ለኛ ሚስጥር አይደለም ። ቆራጡ የትግራይ ሕዝብ ፣ በወገኖቻቸው ላይ ጭካኔ የተሞላበት የግፍና የበደል መዓት በአምባገነኑ ስርዓት ሲፈጸም ዛሬም ልጆቹን ለዚህ ጨቋኝ ስርዓት ዘብ ማድረጉ የአደባባይ ጉድ ነው ። ቆራጡ የትግራይ ሕዝብ በወንድሞቹ …ላይ ቆርጦ ፣ ከጎጠኛ ስርዓትጋ አብሮ ( አንዳንዴም የተገደደ በማስመሰል ) ፣ አንዳንዴም አቅም እንዳጣና ተገዶ እንደሚያደርገው በማስመሰል ይሄን ሁሉ ጊዜ የበደሉ አጋር ሆኖ ጥይት ሲያቀብል ፣ ሲያስር ፣ ሲገል አይተናል ። ይህንን እንድል ያደረገኝ ብዙ ከመጠን ያለፉ የዘረኝነትና የቂመኝነት ስራቸው ብቻ ሳይሆን ፣ በጀርባ የልባቸውን እየሰሩ በፊት ለፊት የትግራይ ሕዝብ ተገዶ ነው እንጂ ይሄንን ስርዓት አይፈልግም የሚሉ ከራሳቸው ብቻ ሳይሆን ከውጭ ጭምር ያሉ አለቅላቂ ፖለቲከኞችንም ስላየሁ ነው ።
ሶስት ወይም አምስት ሚሊዮን ሕዝብ ብዛት ያለው የትግራይ ሕዝብ፣ ከመተማ እስከ ሁመራ ከጋንቤላ እስከ ባሌ ፣ ከአዲስ አበባ እስከ መቀሌ ፣ የንግዱንም ሆነ የሌሎች ማህበራዊ እሴቶች ባላባት የሆነው በስርዓቱ ተገዶ ነው ማለት ፣ ከስላቅም በላይ ነው !
የብሔር ብሄረሰብ እኩልነት አስከበርኩ ለሚል ስርዓት ፣ አንድ የትግራይ ሰው ራሱን የነገሮች ሁሉ አዛዥ ነዛዥ ሆኖ ሲያገኘው ለምን ብሎ የማይጠይቀው ስርዓቱ አስገድዶ ሃብታም አድርጎት ነው እንደማለት ነው ። ይሄ ለኔ ወደል ቀልድ ነው ! ቀልዱን እዚጋ አቁሙ ! ያለበለዚያ በናንተም የሚቀለድበት ቀን ሩቅ አይሆንም ። ማንም ሰው መገፋትን ለዘላለለሙ አይቀበልምና !
እርግጥ ነው ፣ በምንም አይነት ስሌት ሁሉም የትግራይ ሕዝብ የወያኔ ደጋፊ ሊሆን አይችልም ። ይሄ እንዴት ይሆናል ። ግን በድጋፍ ከተሰለፉት አንጻር እየተቃወሙ ያሉት ቁጥራቸው እጅግ ፣ በጣም እጅግ እናሳ መሆናቸውን ማናችንም አንክድም ። እየጠፋ ካለው የሰው ሕይወት ፣ እየደረሰ ካለው የንብረት እና የታሪክ ዘረፋ ፣ እና ሌሎችም ፣ የትግራይ ሕዝብ ዝምታ የሚያስተዛዝብ ብቻ ሳይሆን ፣ ያ የለውጥ ቀን ሲመጣ ደም የሚያቃባ እንዳይሆን ከአሁኑ ወደ ራሳችሁ ተመልሳችሁ ፣ እንደ ዜጋ ማሰብ ትጀምሩ ዘንድ እንመክራለን ። ለውጥ መምጣቱ አይቀርም ፣ ግን ለውጥ ሲባል በስም ብቻ ሳይሆን በግብርም ይሆን ዘንድ ምኞታችን ነው ። እድሜልካችንን በደል ስንመላለስ መኖር ያለብን አይመስለኝም ። ይሄ እንዳይሆን ደሞ የትግራይ ሕዝብ የለውጡ አካል ለመሆን ቆርጦ መነሳት ብቸኛ አማራጩ ነው ። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ማለት ታዲያ ይሄ ነው !

የተበላው እቁብ (ምርጫ2007) እና እኔ ባይተዋሩ…

አቤንኤዘር ጀምበሩ (አዲስ አበባ)

ጥር 11/07 ዓም ቦታው አፍንጮ በር፣ ከዩሀንስ፣ ከጊዬርጊስ እና ቀጨኔ መድሃኒያለም ታቦቶች ለከተራ ወደ ጃንሜዳ ሲተሙ የሚጋጠሙበት ቦታ። እልልታው ፣ጭፈራው፣ መዝሙሩ ፣ የሐገር ባህል ልብስ፣ ዱላ ፣ሸንኮራ ፣ጠጠር መጣያ ከሌለው ህዝብ ጋር አብረው ሽኝቱን አድምቀውታል ። ከሁሉ ከሁሉ ድምጽ ግን ከጀርባዬ የቆሙ እናት ጮሆ ውስጥ ድረስ ዘልቆ ተሰማኝ ። መቼ ነው ምልጃ እና አግዚኦታ የሚያልቀው? “አምላኬ ወጣቶችን ጠብቅ፣ ምርጫውን በሰላም አጠናቀው ፣ደም መፍሰስን አንተ በቃ በል ፣ ልጆቻችንን ጠብቅ፣ ተለመነን … ” ፣ ሁሉ አንቅስቃሴ ፣ ሁሉ አዲስ ነገር ፣ ሁሉ አዲስ ሐሳብ የስጋት ምንጭ እንደምን ይሆናል? ስጋትን ወደ መልካም አጋጣሚነት መቀየር አይቻልም?ethiopian election 2015

የቤታችን በር በአማካኝ ሶስት ጊዜ ትንኳኳለች፣ ሰሞኑን አህዟን በእጥፍ አሳድጋ ስድስት ጊዜ መንኳኳት ጀምራለች። ምክንያት ብትሉ ያካባቢያችን ምርጫ አስፈፃሚዎች “ካርድ ወሰዳችሁ፣ ውሰዱ ፣ማን አልወሰደም ፣ መቼ ተወሰደ …” እያሉ ይመጣሉ። ለመምረጥ ካለኝ ጉጉት ሳይሆን መልካም ዜጋነቴን ለማስመስከር ወደ ምርጫ ጣቢያ ሄድኩ ። አሁንም እንደ ጥንቱ ቁራጭ ካርድ ፣ መዝገብ ፣ እስክሪፕቶ የሃገራችን የምርጫ ቴክኖሎጂ? ምርጫው ሲመጣ ደግሞ ባምስት አመት የሚራገፉ ቀዳዳዎች የበዙበት የሸራ ኮሮጆ። በቢሊዬን ህዝብ ያላት ሕንድን ጨምሮ ብዙ የአፍሪካን ሐገራት የምርጫ ቴክኖሎጂን ምርጫን ለማቀላጠፍ ሲጠቀሙ ፣ እኛ ሐገር ስማችንን እንኳን በኮምፒውተር መመዝገብ እንደምን ተሳናቸው?ስራ አጥተው የተቀመጡ ባለ ዲግሪ ወጣቶች ድንጋይ ፍለጡ እየተባለ ፣የትምህርት ደረጃቸው በአብዛኛው ከሁለተኛ ደረጃ ያልዘለሉ የሰፈር ፊትአውራሪዎች ለምን ዋና ተዋንያን ሆኑ? ካርድ ለመውሰድ በሄድኩበት ወቅት በአካባቢያችን የማውቃቸው እናቶች ፣ ፕሮፌሽናል ያልሆኑ የመንግስት ሰራተኞች፣ የቀበሌ ሰራተኞች ተሰብስበዋል (በእርግጥ አንዳንዶቹን አይቼያቸው ስለማላውቅ ማን እንደሆኑ አላውቅም) ። ከመሃላቸው አንዷ ቡና ታፈላለች። በወቅቱ ቦታው ስደርስ የሞቀ ሰላምታ ሰጥተው በፍጥነት አስተናገዱኝ፣ ስወጣ ገለፃ እንደተሰጠብኝ እገምታለሁ ።

የሰሞኗ የአዲሳቤዎች ቀልድ ታዲያ ቀልቤን ስባዋለች። የኢትዮጵያ ፣ የራሺያና የአሜሪካ ልኡካን ስለ ምርጫ ውጤት ልምድ ሲለዋወጡ፣ የራሽያው ልኡክ “እኛ ሐገር ምርጫ በተደረገ በአንድ ቀን ውስጥ ውጤቱ ይታወቃል” አለ። አሜሪካዊው ለጠቅ አድርጎ “ይህማ ዘግይቷል የኛ ከ3–6 ሰአት ውስጥ ” አለ። የኛው ቀበል አድርጎ “የኛ ከሁላችሁም የተሻለ ነው፣ ውጤቱ ከምርጫው በፊት ነው የሚታወቀው ” ብሎ አረፈው (lol)። እናም አሁን ላይ ምርጫው በሰላም ይለቅ ሲባል በቅንፍ ገዥው ፓርቲ ያለግርግር ያሸንፍ እንደማለት ይመስለኛል። እንደሚያሸንፉ የተማመኑት ገዥዎቻችን የቀጣይ አምስት አመት እቅድ መንደፍ ይዘዋል። የተበላ አቁብ ማለት ይህ አይደል ታዲያ?

እናም እላለሁ መንግስት በአንፃራዊ የተሻሉትን ተቃዋሚዎች ተከፋፈሉ እያለ ጊዜ እየገዛባቸው እንደሆነ ይሰማኛል። ችግራቸውም ጊዜው ሲደርስ ይፈታል።ግን በፊት ያልነበረ ክፍፍል ከየት መጣ?፣ የእጩ ማቅረቢያ ጊዜ ለምን ተራዘመ? ከኋላው የፓለቲካ ቁማር መኖሩ አያጠራጥርም። ምርጫው ጥቂት ወራቶች ቀርተውት እንኳን እኛ አዲሳቤዎች በሙሉ አፋችን የተቃዋሚ ፓርቲ ስም አንጠራም (በእርግጥ እነሱም የት እንዳሉ አይታወቅም) ፣ ብንጠራም ግራ ቀኛችንን አይተን ነው። ክርክር የለም፣ የሐሳብ ልውውጥ የለም፣ አማራጭ የለም፣ አዋጪ መንገዶች ዝርዝር የለም። ያለው ስጋት እና የምርጫ ቦርድ ሪፓርቶች። እውን ይሄ የማን ሌጋሲ ይሆን?

US urges Ethiopia to ensure fair trial to bloggers and journalists

(U.S. Department of State) The United States is concerned by the Ethiopian Federal High Court’s January 28, 2015, decision to proceed with the trial of six bloggers and three independent journalists on charges under the Anti-Terrorism Proclamation. The decision undermines a free and open media environment—critical elements for credible and democratic elections, which Ethiopia will hold in May 2015.US on Ethiopian bloggers

We urge the Ethiopian government to ensure that the trial is fair, transparent, and in compliance with Ethiopia’s constitutional guarantees and international human rights obligations. We also urge the Ethiopian government to ensure that the trial is free of political influence and continues to be open to public observation.

The use of the Anti-Terrorism Proclamation in previous cases against journalists, activists, and opposition political figures raises serious questions about the implementation of the law and about the sanctity of Ethiopians’ constitutionally guaranteed rights to freedom of the press and freedom of expression.

Freedom of expression and freedom of the press are fundamental elements of a democratic society. We call on the government of Ethiopia to support freedom of expression and freedom of the press to demonstrate its commitment to democracy as it approaches its May 2015 national elections.

ሰበር ዜና – ምርጫ ቦርድ አንድነትና መኢአድን ለእነ ትግስቱ አወሉና ለእነ አበባው መሃሪ ሰጠ

• ‹‹እውቅናውን የሰጠነው ለቦርዱ ለሚታዘዘው ነው›› ፕ/ር መርጋ በቃና

(ነገረ-ኢትዮጵያ) ምርጫ ቦርድ አንድነትን ለእነ ትግስቱ አወሉ፣ እንዲሁም መኢአድን ለእነ አበባው መሃሪ መስጠቱን ዛሬ ጥር 21/2007 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳወቀ፡፡ ምርጫ ቦርድ በመግለጫው ‹‹የእነ በላይ በፍቃዱ ቡድን›› በጠቅላላ ጉባኤ እንዳልተመረጠ፣ አምስት አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ አባላት እንዳልመረጠ፣ የተመረጡበትም 51 ሲደመር አንድ መርህ አለመሆኑን፣ ጠቅላላ ጉባኤ ሲያደርግ ሪፖርት አለማድረጉንና ለአባላቱና ለፓርቲው ክብር የሌለው በመሆኑ ፓርቲውን ማስቀጠል እንደማይችል ገልጾአል፡፡

በሌላ በኩል የትግስቱ አወሉ ቡድን መርህ ይከበር እያለ እየታገለ በመሆኑ፣ የኢ/ር ግዛቸው ካቤኔ አባላት ተገፍተው የወጡ በመሆናቸው፣ ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ለቦርዱ ሪፖርት እንዳደረጉ፣ ‹‹የእነ በላይ ቡድን›› ፈቃደኛ ባለመሆኑ እንጂ እነሱ ችግራቸውን በውይይት ለመፍታት ፈቃደኛ በመሆናቸው እንዲሁም ለአባላቶቻቸውና ለፓርቲው ክብር ስላላቸው እውቅናውን ለእነሱ ሰጥቻለው ብሏል፡፡ ምርጫ ቦርድ በመግለጫው ‹‹ምርጫ የሚገባ ፓርቲ በማስፈለጉ፣ ‹‹የእነ በላይ ቡድን ፓርቲውን የሚያስቀጥለው ባለመሆኑና ፓርቲውን እንደ ፓርቲ እንዲቆይ ስለሚፈለግ ዛሬ ጥር 21 ቦርዱ ባደረው አስቸኳይ ስብሰባ እነ ትግስቱ አወሉ ወደ ምርጫ እንዲገቡ ወስኗል›› ብሏል፡፡

ፕ/ር መርጋ በቃና ‹‹የእነ ትግስቱ አወሉ ቡድን ያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የተሟላ ስለመሆኑ በምን ታረጋግጡልናላችሁ?›› በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ሁለቱም ችግር አለባቸው፡፡ እኛ ያየነው በአንጻራዊነት ነው፡፡ የእነ ትግስቱ አወሉ ቡድን ችግር ቢኖርበትም ከዛኛው የተሻለ ነው፡፡ እውቅናውን የሰጠነው ለቦርዱ ለሚታዘዘው ነው፡፡›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ እነ ማሙሸት አማረ በጠቅላላ ጉባኤ ባለመመረጣቸው፣ ለተከታታይ 3 ወራት ወርሃዊ መዋጮ ያላወጣ አባል ከአባልነት የሚሰረዝ በመሆኑና ከፓርቲ አባልነትም ስለተባረሩ እንዲሁም ህገ ወጥ ማህተም በማሳተማቸው እውቅና እንዳልሰጣቸው ገልጾአል፡፡ በሌላ በኩል 2005 ዓ.ም ላይ አበባው መሃሪ የተመረጡበት ጠቅላላ ጉባኤ የተሟላ እንዳልነበር ቢታመንም በተደረገ ምርመራ የተሟላ መሆኑ በመታወቁ፣ በትክክለኛው ማህተም ስለሚጠቀም፣ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጉ በተባለበት ወቅት ጠቅላላ ጉባኤ በማድረጉና ሪፖርቱንም ስላቀረበ ወደ ምርጫው እንዲገባ ወስኛለሁ ብሏል፡፡

አንድነት የተሰጣቸው የእነ ትግስቱ ቡድን፣ እንዲሁም መኢአድ የተሰጣቸው የእነ አበባው መሃሪ ቡድን በአሁኑ ወቅት ሁለቱንም ፓርቲዎች ወክሎ ጽ/ቤት ከሚገኘው የፓርቲ አመራር ጋር አለመግባባት በመፍጠራቸው በውጭ የሚገኙ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 – ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለጦር ሠራዊትና ፓሊስ አባላት ወገናዊ ጥሪ

የሰላም በሮች ሲዘጉ የሁለገብ ትግል ስልት በሮች ይከፈታሉ!  (አርበኞች ግንቦት7)

January 29, 2015

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ አማካይነት እየደረሰበት ያለውን በደል ለሕዝብ ለማሰማት ጥር 17 ቀን 2007 ዓም በአዲስ አበባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ጂንካና ሸዋ ሮቢት የተቃውሞ ሰልፎችን ጠርቶ ነበር። በተለይ በአዲስ አበባው ሰልፍ ላይ የተገኙ ወገኖቻችን ለህወሓት ፍጹም ታማኝ በሆነው የፓሊስ ክፍል ያለርህራሄ መደብደባቸው እና የተቃውሞ ሰልፉም በጉልበት መበተኑ ነፃነትና ፍትህ ናፋቂውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሳዘነ ብቻ ሳይሆነ ያስቆጨ ጉዳይ ነው። በመላው ዓለም በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የተለመደውን ድንጋይ ውርወራ እንኳን ሳይከጅሉ፤ የፓሊሶችን ሰብዓዊ ርህራሄ ለማግኘት “ፓሊስ የኛ ነው” እያሉ እየዘመሩ በፓሊስ ተደበደቡ። ሴቶችና አዛውንት ብቻ ሳይሆን ተላላፊ መንገደኞች እንኳን ከፓሊስ ዱላ አላመለጡም። ከሁሉም በላይ የሚዘገንነው ደግሞ የ 7 ወራት ነብሰ ጡር ሴትም በፓሊስ መመታትዋና ሆዷ መረገጡ ነው። ይህ እኩይ ተግባር የሚፈጥረው ቁጭት በህወሓት ላይ ብቻ አያበቃም። ትዝብቱ ለፓሊስም ተርፏል። ይህ የጭካኔ ተግባር ለፍትህና ለነፃነት በሚደረገው ትግል የሕዝብ አጋር ይሆናል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የፓሊስ ሠራዊትን የሚያዋርድ ነው። ደካማ እናቶችን፣ አረጋዊያንን፣ ባዶ እጃቸውን ተቃውሞ እያሰሙ ያሉትን ወጣቶችንና ነፍሰጡሮችን በጭካኔ መደብደብ ለራሱና ለሥራው ክብር ለሚሰማው ፓሊስ ውርደት ነው፤ የሞት ሞት ነው። የኢትዮጵያ የፓሊስ ሠራዊት አባላት ተግባራቸው ያሳፍራቸዋል፣ ይቆጫቸዋል፤ ቁጭታቸውንም ይህን ትዕዛዝ በሰጡ አለቆቻቸው ላይ በግልም ሆነ በተደራጀ መንገድ በሚወስዱት እርምጃ እናያለን ብሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ ያደርጋል።

የጥር 17 ቀን 2007ቱ ሽብር በአንድ ወቅት የተፈጠረ፤ በአንድነት ፓርቲ ላይ ብቻ ያነጣጠረ፣ የተናጠል ክስተት ሳይሆን ህወሓት ደግሞ ደጋግሞ ሲፈጽመው የነበረ ነው። ከዚህ በፊት በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ፈጽሞታል። የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላንን በተቃወሙ የተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎች በተለይም በአምቦ ላይ የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሽብር ነዝቷል። በቅርቡ ደግሞ በሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ተመሳሳይ አረመናዊ ድርጊት ፈጽሟል።

አርበኞች ግንቦት 7: ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የህወሓት ታጣቂዎች በወገኖቻችን ላይ ያደረሱትን ድብደባ፣ ህገወጥ እስር፣ እና የተቃውሞ ሰልፍ ክልከላን አጥብቆ ይቃወማል። አርበኞች ግንቦት 7፣ በወገኖቻችን ላይ የደረሰው ህመም ህመሙ፣ ቁስላቸው ቁስሉ ነው።

ባለፉት ሃያ ሶስት ተከታታይ ዓመታት፣ በአምቦ፣ በጅማና በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞችና ገጠሮች፣ በባህዳር፣በጎንደርና በበርካታ የአማራ ከተሞችና ገጠሮች፣ በጋምቤላ፣ በሶማሊ፣ በአፋር፤ በአጠቃላይ በመላው ኢትዮጵያ በየአስፋልቱ፣ በየሜዳውና በየጥሻው በህወሓትና ተላላኪዎቻቸው የፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 በጽኑ ያምናል። አርበኞች ግንቦት 7 ከሌሎች መሰል ድርጅቶች ጋር በመተባበር የህወሓትን እድሜ በማሳጠር የእናቶቻችን እምባ ሊያብስ ዝግጁ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ኢትዮጵዊያን እንደከብት እየተደበደቡ ወደ ማጎሪያ የሚያጋዙበት እና በጠገቡ ሰላዮችና ፓሊሶች እየታነቁ የሚታረዱበት ጊዜ ማብቃት አለበት ይላል።

የቱን ያህል ቢለመንም ሆነ ቢወገዝ ህወሓት ለነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒን ምርጫ ዝግጁ ሊሆን ቀርቶ በምርጫ የሚወዳደሩት ፓርቲዎች እነማን እንደሆኑና እነማን በእጩ ተወዳደሪነት መቅረብ እንዳለባቸው ሳይቀር የሚወስን ዓይን አውጣ አጭበርባሪ ድርጅት ነው። ይህንን ከዚህ በፊት አይተነዋል፤ አሁንም በአንድነትና በመኢአድ ላይ እየተደገመ ነው። ህወሓት፣ በየአምስቱ ዓመታቱ በሚያደርጋቸው የሴራ ምርጫዎች በሚቀጥሉት አርባና ከዚያም በላይ ለሆኑ ዓመታት በሥልጣን ላይ የሚቆይበትን ስልት ቀይሶ የሚንቀሳቀስ፤ ኢትዮጵያን ለብዙ ዓመታት ለመግዛት ማድረግ የሚችለውን ክፋት ሁሉ ከማድረግ የማይመለስ አገር በቀል ቅኝ ገዥ ነው። ህወሓት የዘረጋው ሥርዓት ህገ-አልባነት፣ ፀረ-ሕዝብነት እና አምባገንነት ለማጋለጥ በሚል ርህራሄን በማያውቁ የሥርዓቱ አገልጋዮች ፊት ባዶ እጅ መጋፈጥ የሚፈጥረው የሞራል የበላይነትና የመንፈስ ጀግንነት ባያጠራጥርም የሚያስከፍለው ዋጋ ከሚገኘው ውጤት ጋር ማመዛዘን ግን እጅግ ተገቢ የሆነ የማይታለፍ ሥራ ነው ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከህወሓት የሴራ ምርጫ ፋይዳ ያለው ውጤት ይገኛል ብሎ አይጠብቅም። ከምርጫው የሚፈልገው ውጤት አንድ ነገር ብቻ ነው፤ እሱም የመንግሥት ለውጥ ነው። ምርጫው በምርጫነቱ ወደ መንግሥት ለውጥ አያደርስም፤ ወደ መንግሥት ለውጥ ወደሚያመራ ሕዝባዊ አብዮት ሊያሸጋግር ግን ይችላል። ይህም ቢሆን የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ በተለይም የሠራዊቱን ዓይነትና አደራጀጀት እግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ መታቀድ ይኖርበታል።

አርበኞች ግንቦት 7 የራሱን ጥናት አድርጎ ለኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ እና ህወሓትን ለመሰለ ጠላት የሚመጥን የትግል ስልት ሁሉንም የትግል ስልቶች እንደሁኔታው ያዳቀለ – ሁለገብ – መሆን ይኖርበታል ብሎ ወስኖ ለተግባራዊነቱ እየተንቀሳቀሰ ነው። ሁለገብ የትግል ስልት ሕዝባዊ ተቃውሞን፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነትንና ሕዝባዊ አመጽን እንደወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ ማፈራረቅና ማደባለቅን ይፈልጋል። ሰላማዊ ትግል በተለይም ሕዝባዊ እምቢተኝነት ሲባል ደግሞ ህወሓት ያወጣቸው አፋኝ ህጎች እያከበሩ የሚደረግ አለመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ይረዳል። ሁለገብ ትግል በተቻለ መጠን የወገን ኃይል ራሱን ፈጽሞ መከላከል በማይችልበት ሁኔታ እንዳይገኝ ለማድረግ ይጥራል። በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት ሁለገብ የትግል ስልት ሰፊ ተቀባይነት የሚያገኝበት ወቅት ደርሷል። ከዚህ በፊት “የሰላም በሮች ሲዘጉ የአመጽ በሮች ይከፈታሉ” ተብሎ በአንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ታጋይ የተነገረው “የሰላም በሮች ሲዘጉ የሁለገብ ትግል ስልት በሮች ይከፈታሉ” በሚል እንዲሻሻልና በዚህ ወለል ብሎ በተከፈተው በር ሁላችንም እንድንገባ አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል። በሁለገብ የትግል ስልት በሰላማዊ መንገድ የሚደረጉ የትግል ዓይነቶች አሉ፤ በሌላም መንገድ የሚደረጉ አሉ። ስለሆነም በሁለገብ ትግል እያንዳንዳችን እንደየዝንባሌዓችንና እንደየችሎታዎቻችን አስተዋጽኦ ልናበረክት የምንችልበት ሰፊ እድል ይከፍትልናል።

ስለሆነም፣ በዚህ አጋጣሚ አርበኞች ግንቦት 7፣ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለጦር ሠራዊትና ፓሊስ አባላት ወገናዊ ጥሪ ያደርጋል።

በህወሓት ዘረኛ አገዛዝ በሚደርስብን ውርደት፣ እንግልት፣ ስደት፣ ሥራ አጥነትና ድህነት የተማረራችሁ እና እኩልነቷ የተረጋገጠ፣ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት የምትመኙ ሁሉ የሁለገብ የትግል ስልትን አዋጪነት እንድታጤኑ የዚሁ ስልት አካል ሆናችሁ እንድትታገሉ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።

የኢትዮጵያ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላት በግል ከሚደርስባችሁ ግፍ በተጨማሪ የገዛ ራሳችሁን ወገኖች መግደላችሁ፣ ማቁሰላችሁ፣ ማድማታችሁና መደብደባችሁ የህሊና እረፍት ሊነሳችሁ ይገባል። ህሊናችሁ እረፍት የሚያገኘው የሥርዓቱ እድሜ ሲያጥር መሆኑን በመገንዘብ ለገዛ ራሳችሁ ክብር፣ ለወገናችሁና ለአገራችሁ ስትሉ ፋሽስቱን ወያኔ ከድታችሁ ከአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል ጋር ተቀላቀሉ።

እነዚህን ጥሪዎች ተግባራዊ ካደረግን ወገኖቻችን መሠረታዊ መብቶቻቸውን በመጠየቃቸው በመወደስ ፋንታ በፓሊስ ዱላ ሲደበደቡ የማናይበት ዘመን ይመጣል። ይህ ካልሆነ ግን “ውሀና መብራት አጣን” ብሎ አቤቱታ ማሰማት እንኳን በጥይት የሚያስገድልበት ቀን ይመጣል። ያ ከመሆኑ በፊት እንወስን፤ ራሳችንና አገራችን ከህወሓት ዘረኛ አገዛዝ ነፃ እናውጣ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

http://ecadforum.com/Amharic/archives/14277/?utm_source=feedburner&utm_medium=twitter&utm_campaign=Feed%3A%20ecadforum%2FHvBQ%20%28ECADF%20Ethiopian%20News%29