ሕወሃት እና የባቡር ፖለቲካ – ምላሽ ለሕወሃቱ ጦማሪ – ግርማ ካሳ

10422499_342861759252503_474584120838076462_n“Ethiopia steams ahead with vision for a modern NATIONAL rail network “ ሲሉ ዶ/ር ቴድሮስ ጦምረዋል። እኝህ ሰው ምን ያህል በሶሻል ሜዲያ የሚሰጣቸው አስተያየት እንደሚከታተሉ አላወቅም። ለምን ትንሽ ጊዜ ወስደው ምላሽ ሲሰጡ አላይምና። እርሳቸው አነበቡትም አላነበቡትም፣ ባቡርን በተመለለተ በጫሩት ውይይት ላይ አስተያየት መስጠት እፈልጋለሁ።

በተለያዩ የአገራችን ክፍሎ የባቢር መስመሮችን ለመዘርጋት። ይህ እቅድ በጣም የሚአስይደንቅና የሚያስደስት እቅድ ነው። ሆኖም ማንም የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ተመሳሳይ የሚስብ እቅድ በኮምፒተር ዲዛይን ሰርቶ ሊያቀርብ ይችላል። እቅድ ማወጣቱ ላይ አይደለም ትልቁ ቁም ነገር። ነገር ግን እቅዱን መፈጸሙ ላይ ነው።
የዶር ቴድሮስ ሕወሃት ( ሕወሃት የምለው የሚገዛ ሕወሃት በመሆኑ ነው። ሌሎቹ በቁማቸው የሞቱ ናቸዉና) በ2002 ዓ.ም የአምስት አመት እቅድ በሚል፣ በስድስት ኮሪደሮች የባቡር ግንባታ እንደሚያደረግ ተናግሮ ነበር። ይሄን መቼም ዶር ቴዶርስ አይክዱም። በአጠቃላይ በአምስት አመት ዉስጥ ወደ 2300 ኪሎሜትር ለመገንባት ነበር የታቀደው። ኮሮደሮቹም የሚከተሉት ናቸው፡ የአዲስ አበባ መልስተኛ ባቡር፤ የአዲስ አበባ ጅቡቲ ፣ የአዋሽ ወሊዲያ፣ የመቀሌ – ታጁራ፣ የሰበታ- ጂማ-በደሌ፣ የሞጆ-አርባ ምንጭ ወይጦ ኮሮደሮች።

ከነዚህ ዉስጥ ስራ የተጀመረው በሁለቱ ብቻ ነው። የአዲስ አበባ መለስተኛ ባቡር ወደ 34 ኪሎሜትር ብቻ የምትሆን ናት። ሃዲዱ ተዘርግቶ በአንድ መስመር ሙከራ ተደርጓል። ሆኖም በችኮሎ ለምርጫው ሲባል ፣ እቅድና የሕዝቡን ፍላጎት ባካተተ መልኩ ስላልተሰራ፣ ከተማዋን ለሁለት ከፍሏታል። ለሴፍቲ ጥንቃቄ ስላልተደረገም በሃዲዱ መኪናዎች እየሄዱበት ከወዲሁ ጥቅም ላይ ሳይወል እየተበላሸ ነው። ባቡር ለመጀመሪአይ ጊዜ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገባ ይመስል (ከመቶ አመት እብፎት አጼ ሚኒሊክ ያስገነቡትን ረስተው) እስክንደነቁር ድረስ ሲለፈፍበት ከቆየው፣ ዶር ቴዶርስን ጨምሮ ፣ የአገዛዙ ባለስልጣናት በሙሉ ታጭቀው ሙከራ ከተደረገበት ቀን ዉጭ፣ ባቡሩ ቆሟል። መቼ ሥራ ላይ እንደሚዉል የሚታወቅ ነገር የለም። የሃዲድ መስመሩ ኤሌትሪክ ሲለቀቅም ብዙዎች ለአደጋ ይጋለጣሉ ተብሎ ይፈራል።

የአዲስ አበባ ጅቡቲ መስመር ምን ያህል እንደተሰራ የሚያወቅ የለም። እዚህ ላይ አንዘንጋ አዲስ መስመር አይደለም የሚሰራው።፡የነበረዉን እንደገና ማደስ ነው። ያለፈው ሰኔ ወር ሪፖርተር ገና እንዳልተጀመረ ነበር የዘገበው። ቢበዛ አሁን ከአዲስ አበባ ሜኤሶ ግማሹ ቢጠናቀቅ ነው። ( ወደ 200 ኪሎሜተር)። ስለዚህ በአጠቃላይ ከ2300 ኪሎሜትር ወደ 300 ብቻ ነው የተሰራው ማለት ነው። በሌሎቹ አራት ኮሪደሮች ግንባታ ገና አልተጀመረም። ከመቀሌ – ታጁራ ላለው መስመር የካቲት 11 በመቀሌ ድንጋይ አኑረዋል።ከጥቂት ቀናት በፊት።

እንግዲህ መጠየቅ ያለብን ለምን ከ2300 ኪሎሜትር 300 ብቻ ሊገነባ ቻለ ? ምንድን ነው ችግሩ ? የሚሉትን ጥያቄዎች ነው። በዋናነት የአመራር ብቃት ማነስ ነው። ሕወሃት የተማሩ ኢንጂነሮችን ሃላፊነት ላይ ማስቀመጥ ሲገባው፣ ወታደር ወርቅነህ ገበየዉን የትራንስፖርት ሚኒስተር አደረጎ ሾመ። ስራዉን ስላልቻለ ይሁን በሌላ ምክንያት ሰዉዬው እንዲለቅ ተደረገ። በምትኩ አቶ መኩሪያ የሚባሉ ሰው ተሾሙ። እርሳቸው ደግሞ በቅርቡ ሙስና ትልቅ ችግር እንደሆነ የገለጸበት ሁኔታ አለ። ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆን ወጭ በሙስና እንደሚዘረፍ አቶ መኩሪያ እንደተናገሩ ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

አንድ ትልቅ ፕሮጀክት ሲሰራ በዋናነት ወጭው መታሰብ አለበት። እንኳን በሌሎች አሥራ አንድ ኮሪደሮች የባቡር መስመሮችን ለመገንባት፣ በዚህ አመት መጠናቀቅ የነበረባቸው ፕሮጀክቶችም የትም አልደረሱም። (እንዳልኩት ከአዲስ አበባ መለስተኛ ባቡር ግንባት ዉጭ) ።

የአዲስ አበባ መለስተኛ ባቡር ወጭ 400 ሚሊዮን ዶላር ነው። ከአዲስ አበባ ጅቡቲ ወደ 2.3 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከመቀሌ-ወሊድያ (የመቀሌ-ታጁራ ኮሪዶር ግማሹ) 1.5 ቢሊዮን ዶላር ነው። ይሄ ወደ 3.9 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ የሚገኘው በብድር ቻይና ነው። ከአዋሽ – ወልዲያ ላለው መስመር አንድ የስዊስ ባንክ ወደ 1.7 ቢሊዮን ዶላር ያበድራል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ። ብድሩ ግን ምን ደረጃ እንደደረሰ የሚታወቅ ነገር የለም። ለሰበታ-በደሌ እና ሞጆ – ወይጦ ኮሪደሮች እንዲሁም ከወልዲያ -ታጁራ፣ እንኳን ግንባታ ሊጀመር፣ ምንም ብድር እንደሚሰጥም ገና አይታወቅም። የታወቀ ነው ሕወሃት ሁሌ ቅድሚያ ለማን እንደሚሰጥ።

አንደኛ አንድ ትልቅ የኢንጂነሪን ፕሮጀክት እናደርጋለን ከመባሉ በፊት ግንባታዉም በምን ወጭ እንደሚሸፈን መታወቅ አለበት። ሁለተኛ ለግንባታው የሚዉለው ወጭ እንዳይመዘበር ገለልተኛ የሆነ ኦዲተር ያስፈልጋል። ሶስተኛ ለግንባታ የሚዉሉት እቃዎች ጥራት እንዳላቸው ለማረጋገጥ ገለልተኛ የሆነ ኢንጂነርሪን ኢንስፔክተሮች ያስፈልጋሉ። በአጭሩ ግልጽነትና ተጠያቂነት መኖር አለበት። አራተኛ እንደዚህ አይነት ትልቅ ፕሮጀክት ትልቅ ሕዝባዊ ሞቢላይዜሽን ያስፈልጋል። በቻይና ተማምኖ፣ ተተኪ ትዉልድ ያየሌለ ይመስለ ዝም ብሎ መበደር ትልቅ ስህተት ነው። በአገር ቤት ሆነ ቤትውም ከአገር ዉጭ የሚኖረዉም ሕዝብ መረባረብ አለበት። ህዝቡ መታቀፍ አለበት።

አሁን ያለው የሕወሃት መንግስት ፍጹም በሙስና የተጨማለቀ ነው። የተማሩ ኢትዮጵያዉያንን የሚገፋ ነው። እንኳን ሕዝቡን ሊያሰባስብ ህዝቡን እያሸበረ ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ በሕዝቡ እየተጠላ የመጣ ቡድን ነው። ሕወሃቶች ፣ የቻይናዎችን ጫማ እየላሱ የተወሰኑ ነገሮች እያሳዩ፣ በልማት ስም በሕዝብ ስም ከሚገኘው ገንዘን እየሰረቁ ፣ የሚታዩ ጥቂት ግንባታዎችን በሜዲያዎቻቸው ለፖለቲካ ፍጆታ እያሳዩ ያወራሉ እንጂ ኢትዮጵያን በባቡር አያገናኙም። ከምጣዱ ያስታወቅል እኮ ነው የሚባለው። ለ ኤምባሲዎቻቸው የሚከፍሉት እንኳ እስለሌላቸው ለቪዛ የሚጠይቁት እጥፍ አድርገዉታል። ታክሲዎችን በግድ ቦንድ ካልገዛችሁ ብለው ቦሎ አይሰጥጅ እያሏቸው ነው።
ሌላ ምሳሌ ልንገራችሁ። የአባይ ግድብ የት ደረሰ ? ግዱቡ በዚህ አመት ማለቅ ነበረበት። ግን አላለቀም። በዚህ አመት የ ኤሌትሪክ አቅም ወደ 10000 ሜጋ ዋት እናደርሳለን ሲሉ ነበር። ገና 2300 ሜጋ ዋት ናት። ለምን ? የገንዘብ ችግር።

ትዝ ይላቹሃል እንደ አምላክ የሚያመልኩት ሟቹ መለስ ዜናዊ በአስር አመት ዉስጥ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በቀን ሶስቴ ይመገባል ያለው። ከጥቂት አመታት በፊርት ቁምስ አሁን ደግሞ ቁምራ የሚባሉ ቃሎች ተፈጥረዋል። ቁምራ ማለት ቁርስ፣ ምሳ ራት አንድ ጊዜ ማለት ነው። የሕወሃት በቀን ሶስት የመመገበ ተስፋ ቁምራን ነው ያተረፈልን።

ሽንፈታዊ አስተሳሰብ ለማራገብ አይደለም።፡ይህ ስርዓት ቢቀየር ወይንም መሰረታዊ የሆኑ ለዉጦች ቢያደረግ፣ ለብሄራዊ እርቅ ቢዘጋጅ፣ ኢትዮጵያዊያንን በዘር መከፋፈሉ ቆሞ ሁሉንም በአንድ ማሰብሰብ ቢቻል፣ እመኑኝ ከቻይናዎች ሳንበደር የታቀደ ግንባታዎች እኛው ራሳችንን መሸፈን እንችላለን። ለምሳሌ ለአዲስ አበባ መለስተኛ ባቡር ግንባታ ወጭው 400 ሚሊዮን ዶላር ነው። ከዚህ 360 ሚሎዮኒ ከቻይና በበድር የተገኘ ነው። በዉጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ወደ 2 ሚሊዮን ይጠጋሉ። በቀን አንድ ፣ አንድ አንድ ዶላር ቢያዋጡ፣ በስድስት ወር ወጭው ሊሸፈን ይችላል። ይሄን ትልቅ የኢትዮጵያ ሃብት መጠቀም ያልተቻለው ሕወሃት በሚያራምደው ግራዚያናዊ የአፓርታይድ ፖሊሲ ነው።

መልካም አስተዳደር፣ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ሕዝብን የሚንቅ፣ የሚከፋፍልና የተጠላ ሳይሆን ሕዝብ የሚያከበር፣ አንድ የሚያደረግና የሚወደድ መንግስት ከመጣ እንኳን የባቡር መስመሮች ሌላም ፣ ሌላም መገንባት እንቻላለን።
በመጨረሻ ለሕወሃቶች ብዙም እንዳይመጻደቅ አንድ ነገር ልበል። ፎቶዎችና ግንባታዎችን የሚያሳዩ ፎቶዎች አትለጥፉልን። ግንብታ የለም አላልንም። ግን ግንባታው እየተሰራ ያለው በቻይናዎች ፣ ከቻይናዎች በተገኘ ብድር ነው። ከቻይና በቻያና ማለት ነው። ስለዚህ አገርችንን የቻይና “ቅኝ ግዛት” በማድረጋችሁ ብዙ አትመጻደቁ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ወሮ በነበረ ጊዜም ብዙ የልማት ግንባታዎችን እንደተፈጸሙም አትርሱ።

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/4923#sthash.IEADwcsm.dpuf

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s