አጥፍቶ ጠፊዎች! – ከኪዳኔ አማነ

በአሁኑ ወቅት አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ጥንቃቄ በሚያስፈልገው ጊዜ ትገኛለች፡፡ ሃላፊነት እሚሰማው ተቃዋሚ ፓርቲ እና ለህግ ተገዢ የሆነ ጥበበኛ ገዚ ፓርቲ ትሻለች፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ በብሄር ፍትጫ የተወጠረች እና ልትበጠስ ትንሽ የቀራት ስስ ክር ሆናለች፡፡ አገሪትዋ በአንድ በኩል ኢህኣዴግ እሚባል ላፀደቀው ህግ ደንታ የሌለው ጠበንጃ አምላኪ ጉጅሌ ስትታመስ በሌላ በኩል ደግሞ ኢህኣዴግን በማንኛውም መንገድ ከስልጣን ለማውረድ ብቻ እንጂ ስለነገይትዋ ኢትዮጵያ ግምት ውስጥ አስገብተው የማይንቀሳቀሱ አንዳንድ ተቃዋሚዎች በመኖራቸው የወደፊት ተስፋዋ እየጨለመ ነው፡፡ እነደኔ እነደኔ እነዚህ ሁለቱም አካላት ለአገር የማይጠቅሙ አጥፍቶ ጠፊዎች ናቸው፡፡ ሁለቱም አጥፍቶ ጠፊዎች አጀንዳቸው ስልጣን እንጂ ኢትዮጵያና ህዝብዋ አይደለም የሚያስቀድሙት፡፡ፋሺስት ደርግ ስለዴሞክራሲ ሁሌ ይናገር እነደነበረና በዴሞክራሲ ስም ምሎ ሲገዘት እንደነበረ ሁሉ የአሁኑ ገዢው ሃይልም ከዴሞክራሲ ሆድና ጀርባ ሆኖ ስለ ዴሞክራሲ ይዘምራል ፅንፈኛ ተቃዋሚዎቹ ደግሞ ከጠላቶቻችን ጋር አብሮው ስለ አገር እንደሚጨነቁ ይለፍፋሉ፡፡ ይሄ አጥፍቶ ጠፊነት አይደለምን? እንዲሁም ኢህኣዴግ ከስልጣን ላለመውረድ የቻለዉን ሁሉ በውንብድና ይጨፈልቃል ሃላፊነት የማይሰማቸው ጫፍ የረገጡ አክራሪ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስርዓቱና አገሪትዋ አናግተው ስልጣን ላይ ቁጢጥ ለማለት ሌት ተቀን ይፍጨረጨራሉ፡፡ አንዳንዶቹ እብድ ተቃዋሚዎችማ (ባህር ማዶ የሚገኙ)ህዝብና ድርጅት መለየት አቅቷቸው ሁሉም ህዝብ በትግራይ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ እንዲያካሂድ የሚሰብኩ አሉ(አንድ ብሄር ከምድረገፅ አስወግደው የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ብን ብለው በአንዴ ይጠፉ ይመስል )፡፡
እነዚህ ከጠላቶቻችን (ከነሸዓብያ) በማበር አገራችን ለመውጋት ሁላ እየተንቀሳቀሱ እንደሆኑ በዛ አውዳሚ ሚድያቸው ይነግሩናል፡፡ ይሄ (ከጠላት ጋር ማበር) የፀጥታና የአገር ጉዳይ ስለሆነ (ገዢው ፓርቲ ብቻ የሚመለከት ብቻ ስላልሆነ) የሰለጠነ አቀዋም ልንይዝ ይገባል፡፡ በብሄራዊ ጥቅም እና ደኅንነት አንድና ተመሳሳይ ሃሳብ ማንፀበረቅ አለብን፡፡ የሚከተሉትን የትግል ስልት አዋጭ ነው ብለው ካመኑ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆኖው በኢትዮጵያ መሬት ላይ መፋለም ነበር እንጂ የጠላትየ ጠላት ወዳጄ ነው የሚለው ያረጀ ያፈጀ አውዳሚ ስልት መከተል ለኔ ለአገርና ለህዝብ መቆርቆርን አያሳይም፡፡
እኛ ተቃዋሚዎች ህልማችን ኢህኣዴግን ከስልጣን ለማውረድ ብቻ ሳይሆን ገዚው ፓርቲ ከወረደ በኋላ በአገራችን የተሻለ ሰላም፡ ፍትህ፡ ዲሞክራሲ እና መረጋጋት እንደሚኖርና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችዋ በርግጠኝነት እንደምንፈታላት በተጨባጭ ማረጋገጥ ብሎም ይህንን ከባድ አገራዊ ተልእኮ የሚሸከም ድርጅታዊ መዋቅር መፍጠር ግድ ይለናል፡፡ እስካሁን እንዳየነው የኢህአዴግ አካሄድ በማንኛውም መንገድ እንድታስወግደው እጅግ የሚገፋፋ ነው ሆኖም ግን ከሁሉም በላይ አገር ይቀድማልና አንዳንዴ ለምጣዱ ስንል አይጥዋ እንድትፈነጭ መፍቀድ ሁኔታውን ያስገድደናል፡፡
እስኪ መጀመርያ ድርጅት መመስረት ብቻ ሳይሆን የተመሰረተው ድርጅት በሁሉም ብሄረሰብ ተደማጭ መሆኑንና የሁሉም ህዝብ ፍላጎት ያማከለ ፖሊሲና ስትራተጂ መከተላችን እና ስልጣን ብንይዝ ኢህአዴግ ከስልጣን ወርዶ ኢትዮጵያ እንደማትፈርስ ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስኮች የተሻለ ስራ እንደምንሰራ በሳይንሳዊ መንገድ እናረጋግጥ፡፡
እርግጥ ነው የኢህአዴግ መንግስት መቼም ቢሆን ላፀደቀው ህግ ተገዢ እና ታማኝ አይሆንም ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚመኩበት፡ ውስጠ ዴሞክራሲ ያለው እውነተኛ ህብረ-ብሄር ድርጅት ይኑረንና ምልአተ ህዝቡን ከኋላችን አሰልፈን ማንም ብሄር በሌላው ብሄር ሳይነሳና አንድም ንብረት ሳይወድም በሰላማዊ መንገድ አምባገነኑ መንግስታችን በህዝባዊና ድርጅታዊ ጥንካሬያችን አስጨንቀን ወዶ ሳይሆን ተገዶ ለህግ ተገዢ እንዲሆን ማድረግና የሰከነ ፖለቲካዊ የእርምተ እርምጃዎች በመውስድም ኢህአዴግን ማንበርከክ እንችላለን፡፡ ይህንን ስልጡን ሰላማዊ ስልት ኢህአዴግ ከጦር በላይ እንደሚፈራውና አገራችን ከገባችበት አጣቢቂኝ የሚያወጣ ይመስለኛል፡፡10995826_1561343667457725_6766180167450618065_n

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s