የማለዳ ወግ …” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” አንጀሊና * ዘሐራ ጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት ስታደምቅ -ነቢዩ ሲራክ

11030318_10206560045025805_7158802905229137827_n

ለማፍቀር መፈቀር ፣ ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ግድ ይላል ! ይህ ተፈጥሯዊ ህግ ሆኖ በሁላችንም ላይ ባይሰረጽም የታደሉት ሲሆኑትና ሲታደርጉት ከማየት አልፎ የድካማቸው ፍሬ አፍርቶ ሲያዩት ምስክር እማኝ መሆን መታደል ነው ። መልካም መስራት ለራስ ነው እንዲሉ ውስጥን ከሚሰጠው እርካታ ባሻገር የታደሉት የዘሩት አሽቶ መልካም ስራቸው በስኬት ጎዳና ሲታይና በውጤት ስኬቱ ሲደምቁ ማየት ከምንም በላይ ያስደስታል ። በአንጻሩ መልካም ሰርተው እጃቸው ” አመድ አፋሽ ” የሆኑንም አለማችን ከማስተናገድ አልቦዘነችም ። የአማድ አፋሽነቱ ህመም ጥልቆ ቢያመም የሰሩት ለውስጥ እርካታ ነውና ሁሉምም የሚያየው አንድ ፈጣሪ ፍርድ ይሰጣልና ህመሙ ህመም አይባልም ። አድርጎ “አመድ አፋሽ ” መሆን ክሽፈት ነው ከተባለ ምድራዊ ጊዜያዊ ክሽፈትነት ፈቀቅ አይልም ፣ የመልካምነት ሰማያዊ ጸጋቸው ሰፊ ነውና እኒህም የታደሉ ናቸው !

11113558_10206560045465816_5724276787710087968_nየዛሬዋን አጠር ያለች የማለዳ ወጌን እንድሞነጫጭር ምክንያት የሆነኝ ትናንት መጋቢት 20 ቀን 2007 የልጆች ምርጫ Nickelodeon’s 28th Annual Kids’ Choice የተሰኘውን አመታዊ የሽልማት ስነ ስርአት አዋርድ በማሸነፍ ተሸላሚ የሆነችው የኦስካር አሸናፊዋ ድንቅ ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ሽልማት አይደለም። ሰብዕናዋ ፈቅዶ የዘራችው አጎምርቶ ለደስታዋ ድርብ ደስታ መሆኑን በማየቴ እንጅ …ቅዱስ መጽሐፉ ” የዘራቸውን ታጭዳላችሁ! ” እንዳለው ከመከራው ኑሮ አቅፋ ደግፋ ያሳደገቻቸው ልጆቿ በአሳዳጊ እናታቸው አንጀሊና ጆሊ ማሸነፍ እየፈነደቁ ሲያቅፉና ሲስሟት የተሰማኝ የደስታ ስሜት ለመግለጽ ያህል ነበር ብዕሩን መጨበጤ …

የተጨበጨበላት ድንቋ የፊልም ተዋናኝ ፣ ደራሲና በጎ አድራጊዋ አንጀሊና ጆሊ ሽልማቷን ስትቀበል ባሰማችው ንግግር ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” ነበር ያለችው … አዎ ልዪነተ መልካም ነገር ነው ! አንጀሊና እንዳለችው ልዩነት መልካም ነገር ነው ፣ ልዩነት ጌጥ መሆኑን አምኖ በሚያስማማው ነገር ተስማምቶ መኖር ይቻላል ።

አንጀሊና እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በ2005 ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በጉዲፈቻ ወስዳ ያሳደገቻት ዘሐራ ተለውጣለች ። እነሆ አሳዳጊ እናቷ ስትሸለም ከእቅፍ ወርዳ ከጎኗ ተቀምጣ ደስታዋን የምትጋራ የጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት አድምቃታለች ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” እኔም እላለሁ በፍቅር እንድትዋጅ ፍቅርን ስጥ … ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ”

ደስ ሲል: )

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም

satenaw

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s