የእነብርሃኑ፣ ፍቅረማርምና እየሩሳሌም የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ (ከኤልያስ ገብሩ ጎዳና )

ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል

‹‹ተጨማሪ ምርመራ ይቀረኛል›› መርማሪ ፖሊስ ‹‹መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ››ተጠርጣሪዎች

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚገኙት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ ፍቅረማሪያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ፍርድ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡Fikeramaryam , Berhanu and Eyerus

ሶስቱም ወጣት ተጠርጣሪዎች ችሎት ከመግባታቸው በፊት ሳቅ እና ፈገግ እያሉ በፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ የነበሩትን ቤተሰቦቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ሰላም ሲሉ ተስተውሏል፡፡ ብርሃኑና ፍቅረማሪያም የአንገት ልብስ (ስካርፍ) ያደረጉ ሲሆን እየሩሳሌም ጥቁር እስከርፍ አድርጋ ነበር፡፡

በመጀመሪያ ወደ ችሎት ተጠርተው የገቡት ፍቅረማርያም እና እየሩሳሌም ሲሆኑ ከጠበቃ ዳዊት ነጋሽ በስተቀር ማንም መግባት አልቻለም ነበር፡፡ [እኔና ጥቂት ሰዎች ግን ከችሎቱ በር ትንሽ ርቀት ላይ ቆመን የፍርድ ቤት ሂደቱን ለማየት ጥረት አድርገገን በመጠኑ ተሳክቶልናል] ጠበቃ ዳዊት ከችሎት በኋላ እንደነገሩን ከሆነ፣ መርማሪ ፖሊስ ምርመራ አለመጨረሳቸውን፣ ተጠርጣሪዎች ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር ግንኙነት እንደነበራቸውና ይሄንንም በማጣራት ላይ እንደሚገኙ፣ የቴክኒክ መረጃዎች (የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት፣ የስልክና የፌስ ቡክ) እንደሚቀራቸው፣ ለሽብር ተግባር ብር ሲቀበሉ እና ሲልኩ የነበረውን የባንክ ቤት መረጃ እየተከታተሉ መሆናቸውና ቢለቀቁ መረጃዎችን ሊያጠፉ ስለሚችሉ የተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ጠበቃ ዳዊትም መርማሪ ፖሊስ ይቀሩናል ሲል ለፍርድ ቤቱ ያቀረባቸው መረጃዎች ከተጠርጣሪዎቹ ቁጥጥር ውጪ ሆነው በቃላሉ የሚገኙ ስለሆነ ተጠርጣሪዎቹ በዋስትና እንዲለቀቁ ፍርድ ቤትን ጠይቆ ነበር፡፡ ጠበቃው ምክንያቱን ሲያብራራም፣ የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት፣ የስልክና የፌስ ቡክ መረጃዎችን ፖሊስ እስከአሁን ሊያገናቸው ይችል እንደነበረ፣ ከባንክ የሚገኝ መረጃም በአጭር ቀናት ውስጥ የሚገኝ መሆኑን፣ ግብረ አበሮች አሉ ከተባለም ግብረአበሮች የሚያዙት ተጠርጣሪዎችን በመያዝ አለመሆኑና ተጠርጣሪዎቹ ቢለቀቁም የተለየ ነገር እንደማይመጣ ተናግሯል፡፡

መርማሪ ፖሊስም ‹‹የጦር መሳሪያ ተይዟል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በህቡዕ ነው የሚንቀሳቀሱት፡፡ ከእስር ቢለቀቁ ወደኤርትራ ሰው ወደመመልመል ስራቸው ይመለሳሉ›› የሚል ተቃውሞ በማሰማት የጦር መሳሪያ የታጠቀ የሰው ምስል ለችሎት ማሳየቱንና መሳሪያ የያዘው ግለሰብ ማን እንደሆነ በግልጽ እንደማይታይ ለዚህ ዜና ዘጋቢ ገልጾለታል፡፡

ፍቅረማርያም እና እየሩሳሌምም ቃላቸውን፣ የፌስ ቡክና ሌሎች መረጃዎችን በምርመራ ወቅት ለፖሊስ መስጠታቸውን፣ መሳሪያ ከተባለው ነገር ጋር የሚያገናኛቸው ነገር አለመኖሩንና ይሄም በግልጽ እንደሚታወቅ በመግለጽ ‹‹መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ›› የሚል ሀሳባቸውን ለችሎቱ አቅርበዋል፡፡

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ከተጠየቀባቸው በኋላ ብርሃኑ ተክለያሬድ ከጠበቃ ዳዊት ጋር ወደ ችሎት ገባ፡፡ መርማሪ ፖሊሱ፣ ብርሃኑ ላይም ‹‹የጦር መሳሪያ ተገኝቷል›› የሚለውን ቃል ሳይደግም በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ያረቀበውን ሀሳብ ለችሎቱ ማስረዳቱን ጠበቃ ዳዊት ይናገራሉ፡፡ ጠበቃውም በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ያቀበረቡትን የተቃውሞ ሀሳብ ለብርሃኑም አቅርበዋል፡፡ ብርሃኑም በበኩሉ ‹‹ቃላችንን ለፖሊስና ለፍርድ ቤቱ ሰጥተናል፡፡ የቀረ ነገር የለም፡፡ የእስር ሁኔታችን ከህግ አግባብ ውጪ ነው፡፡ ‹‹ጨለማ ክፍል›› በሚባለው እስር ቤት መብራት 24 ሰዓት ይበራል፡፡፡ እኔ የዓይን ችግር አለብኝ፡፡ በቀን ለ15 ደቂቃ ብቻ ነው ከታሰርኩበት ክፍል ወደ ደጅ የምወጣው፡፡ ቤተሰብና የህግ ጠበቃ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ከጠበቃ ጋር ሳልማከር ነው ቃሌን ለፖሊስ የሰጠሁት፡፡ የመብት ጥሰት አለ፡፡ ቤተሰቦቻችንን፣ ጠበቃና ጠያቂዎቻችንን መግኘት ይፈቀድልን፡፡ ሌሎች ከእኔ ጋር የታሰሩ እስረኞች ግን ቤተሰቦቻቸው ሲመጡ ለጥየቃ ይወጣሉ፡፡ በዚህ ላይ ትዕዛዝ ይሰጥበት፡፡ …መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ›› ብሏል፡፡
[የዚህ ዜና ዘጋቢም ብርሃኑ ድምጹን ከፍ አድርጎ አቤቱታውን ለችሎቱ ሲያቀርብ በከፊል ለማየትና ለመስማት ችሏል]

የችሎቱ ሴት ዳኛም የተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ መብት መጠበቅ እንዳለበት ጠቁመው፣ ‹‹ተጠርጣሪዎቹ ከቤተሰብ፣ ከጠበቃ፣ ከሃይማኖት አባቶቻቸውና ለወዳጆቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚል ትዕዛዝ በቃል ሰጥተው በብርሃኑም ላይ የ28 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሠጥተዋል፡፡

በቀልድ የታጀበው ምስክሮችን የመስማት ውሎ -የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ (ዞን9)

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየው የማስረጃ መስማት ውሎ ዛሬ ምስክሮችን በማስማት ተጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት አቃቤ ህግ ጉዳዬን ያስረዱልኛል ያላቸውን 17 ምስክሮች ያስመዘገበ ሲሆን 15ቱ በፍርድ ቤቱ ተገኝተው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ አቃቤ ህግ ችሎቱ በዝግ ችሎት አንዲሆን የጠየቀ ሲሆን ምስክሮቼ እና የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት ለመጠበቅ ችሎቱ በዝግ ሊሆን ይገባል የሚለውን አቤቱታውን ጠበቆች በከፍተኛ ደረጃ ተቃውመውታል፡፡Zone 9 bloggers

ምስክሮቹ የጭብጥ ምስክሮች ሳይሆኑ ፍተሻን የታዘቡ የደረጃ ምስክሮች በመሆናቸው እና ስማቸውም በግልጽ ተከሳሾች ጋር ስለደረሰ ምንም አይነት የደህንነተ ስጋት የለባቸውም ከሚለው የጠበቆች ክርክር በኋላ ፍርድ ቤቱ በጉዳዬ ላይ ተወያይቶ ለመወሰን ረፍት ወስዷል፡፡ በዚህም መሰረት የአቃቤህግን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ችሎቱ በግልጽ ሆኖ መስክሮች ምስክርነታቸውን እነዲያሰሙ ታዟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አቃቤ ህግ ያቀረባቸው ምስክሮች አነማን ላይ አንደሚመሰክሩ እና ምን አንደሚመሰክሩ በተጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱም በጠበቆቹ ስለተነሱት ነጥቦች የአቃቤ ህግን ምላሽ ጠይቋል፡፡ አቃቤ ህግም በዛሬው ዕለት የቀረቡት ምስክሮች በ2ኛ፣ በ3ኛ፣ በ5ኛ፣ በ6ኛ፣ በ7ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ( በስድስቱ የዞን9 ጦማርያን ላይ እና በጋዜጠኛ አስማማው ላይ ) ላይ እንደሚመሰክሩ ገልጾ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቡድን በብርበራ ያገኛቸው ማስረጃዎች ከተከሳሾች የተገኙ ስለመሆናቸው ያስረዱልኛል ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በምላሹም መሰረት የአቃቤ ህግ ምስክሮች ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡ ምስክርነታቸው ሲሰጡ በነበረበት ወቅት የተከሳሾችን ስም አለማወቅ አንዲሁም የተከሳሾችን መልክ አለመለየት የመሳሰሉት ጉዳዬች የተስተዋሉ ሲሆን ምስክርነታቸውን የሰጡት ሰዎች ስም ዝርዝር እና የምስክርነታቸው ጭብጥ በአጭሩ አንደሚከተለው ነው ፡፡

1. ሙሉጌታ መዝገቡ ለማ – ናዝሬት ነዋሪ ነኝ መአከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄጄ ፓሊስ ታዛቢ ምስክር አንድሆን ጠይቆኝ በዚያ መሰረት ምስክር ሆኜ ተገኝቻለሁ፡፡ ከአቤል ከኮምፒውተሩ ላይ ጽሁፍ ሲወጣ እና ሲፈርም አይቼ እኔም ፈርሜያለሁ ፡፡ የጽሁፉን ይዘት አላነበብኩም አንዳንድ ቦታ አፍሪካ ሪቪው ኬንያ የሚል ቃል አይቻለሁ የሚል ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡

2. በለጡ አበበ ዮሴፍ ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 32 ሲሆን ከፍተኛው ፍርድ ቤት የካ ምድብ ሰራተኛ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ በማን ላይ ለመመስከር እንደመጡ ሲጠየቁ በስም እንደማያስታውሱት ገልጸው በአካል ግን ለይተው አሳይተዋል፡፡ መስካሪዋ በ6ኛ ተከሳሽ ዘላለም ክብረት ላይ የሚመሰክሩ ሲሆን በተለየ ስም ሲጠሩት ተስተውለዋል “የሽብርተኝነት ጉዳይ የሚያመለክት ይመስለኛል፡፡ ወደ 70 ገጽ አማርኛና 10 ገጽ እንግሊዝኛ ጽሁፍ ተገኝቷል፡፡ ያየሁትን አይቼ ፈርሜያለሁ፡፡” ካሉ በኋላ ተከሳሹስ ፈርሟል ተብለው ሲጠየቁ መጀመሪያ አላስታውስም ቢሉም እንደገና ሲጠየቁ ግን አዎ ፈርሟል ብለዋል፡፡

3. እታፈራሁ ጌታቸው ወልዴ የሚባሉ ሲሆን እድሜያቸው 36 ነው፡፡ በመንግስት ት/ቤት በአስተዳደር ሰራተኛነት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ማን ላይ እንደሚመሰክሩ ሲጠየቁ ፍቃዱ እና…..(ስሙ ጠፍቶባቸው ቆይተው) እ…አጥናፉ ብለዋል፡፡ በአካል ደግሞ በፍቃዱን አሳዩ ሲባሉ አጥናፍን አሳይተዋል፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ማእከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄደው ጽሁፎች ሲታተሙ ማየታቸውንና በፍቃዱ በፍቃደኛነት ሲፈርም ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ስለጽሁፎቹ ሲጠየቁ “የአማርኛ ጽሑፎች ናቸው፡፡ 60 ገጽ የሚሆን ‹ወያኔ ይውደም› ምናምን የሚል ጽሑፍ አይቻለሁ፡፡ እንግሊዝኛም አለው 10 ገጽ ይሆናል፡፡ በምስል ከውጭ ሰው ጋር ሆነው የሚነጋገሩትም አይቻለሁ፡፡ ይዘቱ ግን ግር ይለኛል፡፡” ብለዋል፡፡ አጥናፍን አስመልክቶ ደግሞ ‹‹የእሱንም በዚያው መልኩ ነው ያየነው፡፡ ዕለቱም ግንቦት 16/2006 ነው፡፡ ኮምፒውተሩ ላይ የነበሩትን ጽሁፎች እዚያ ለነበሩት ሲያሳይ ነበር፡፡ ጽሑፎችን አይቻቸዋለሁ….‹የጨለማው ቀን….የጨለማው ንጉስ› የሚል አይቻለሁ፡፡ ‹ኢትዮጵያ አንድ ናት› የሚልም አይቻለሁ፡፡ ወደ 30 ገጽ ይሆናል፡፡ ሁሉም ፕሪንት ተደርጎ ሁላችንም ፈርመንበታል፡፡››ብለዋል

ሶስቱ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ጠበቆች በሂደቱ ላይ አስተያየት አለን በማለት፣ ዶክመንቶቹ ፕብሊክ ዶክመንት ናቸው በአደባባይ የተጻፉ ጽሁፎቻቸው እና በማንኛውም ቦታ የሚገኙ ስለሆኑ ዶክመንቶቹን ክደን አልተከራከርንም የእኛ ክርክር ዶክመንቶቹ ለወንጀል ስራ የሚበቁ አይደሉም ነውና በዚህ ጭብጥ ዙሪያ ምስክር መስማቱ ያብቃልን የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡አቃቤ ህግ በበኩሉ ሁሉም ምስክሮች አንዲሰሙልኝ እፈልጋለሁ በማለቱ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ያስረዱልኛል ካለ ይቀጥል በማለቱ ምስክሮቹ ቀጥለዋል፡፡ ጠበቆች መስቀለኛ ጥያቄ ሳይጠይቁ ተከታዬቹ ምስክሮች መሰማታቸው ቀጥሏል፡፡

4. አራተኛው ምስክር አፈወርቅ ካሳ ይባላሉ፡፡ የግል ሰራተኛ ሲሆኑ እድሜያቸው 46 ነው፡፡‹‹ቀኑ ሚያዝያ 18/2006 ነው፡፡ የተከሳሹ አስማማው ቤት ጠዋት 3፡00 አካባቢ ሲፈተሸ ታዛቢ ነበርኩ፡፡ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ ፓስፖርት…ብዙ ወረቀቶች ላይ ‹‹አዎ የእኔ ናቸው›› እያለ ሲፈርም አይቻለሁ፡፡ እኔም ፈርሜያለሁ፡፡ ቤተሰቦቹም ቤት ውስጥ ነበሩ፡፡ አብዛኛው ያየሁት የግል መጽሄቶችን ነው፡፡ ማህተምም አይቻለሁ፡፡ ደሞ ቢሮው ሄደን ላፕቶፕ፣ ፍላሽ፣ ሲዲ፣ መጽሔቶች አይቻለሁ፡፡ ፖሊስ የሚፈልገውን እየለየ ፈርመናል፡፡ ወደቢሮው የሄድነው በመኪና ነበር፡፡ ከዛ ደግሞ አድራሻችንን ይዘው ስለነበር ሰኔ 4….አይ 14/2006 ነው መሰለኝ ከማዕከላዊ ተጠርተን ላፕቶፕ ላይ የነበረውን ስዕሎችና የእንግሊዝኛ ንግግሮች ሲወጡ አይቻለሁ፡፡ የእኔ ነው ብሎ ሲፈርም እኛ ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡›› ብለው ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

5. አምስተኛ ምስክር አጌና አንከና ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 48 ሲሆን ነዋሪነታቸው አ.አ ነው፡፡ የሚመሰክሩት ደግሞ በ3ኛ ተከሳሽ ናትናኤል ላይ ነው፡፡ የምስክርነት ቃላቸው፣ ‹‹ሰኔ 17/2006 ለግል ጉዳይ ማዕከላዊ ነበርኩ፡፡ ከቀኑ 8፡00 ታዛቢ ሁነኝ ብሎ ፖሊስ ጠይቆኝ ታዝቤያለሁ፡፡ ላፕቶፑ ላይ አማርኛ ጽሑፎች አይቻለሁ፡፡ ጽሑፎቹ የተከሳሹ ስለመሆናቸው አምኖ ሲፈርምባቸው ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡ ይዘቱን ግን አላነበብኩትም፤ አልተረዳሁትም፡፡ የገጹን ብዛትም አላስታውስም፡፡›› የሚል የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

6. ስድስተኛ ምስክር ገብረጨርቆስ ገብረመስቀል ይባላሉ፡፡ የ50 ዓመት የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ ምስክሩ በአስማማው ላይ ለመመስከር እንደመጡ ቢናገሩም በአካል ግን ለይተው አላወቁትም፡፡ እንዲያውም አስማማውን አሳዩ ሲባሉ አቤልን አሳይተዋል፡፡

ከፍርድ ቤቱ ውሎ በኋላ አስተያየታቸው የሰጡት የተከሳሾች ጠበቆች አቃቤ ሀግ ያቀረባቸው ምስክሮች ወረቀት ሲፈረም አየን ከማለት ውጪ ምንም አይነት ለሂደቱ ቁም ነገር ያለው ምስክርነት የሚሰጡ አይደሉም ፡፡ ተከሳሾች ተገኘባቸው የተባለው ጽሁፍ የአደባባይ ዶክመንት ከመሆኑም በላይ አልተገኘብንም ብለን ክደን አልተከራከርንም በይዘቱ ላይ ክርክር ስላልተደረገ መስቀለኛ ጥያቄ ለማቅረብም ብዙ አልጨነቅንም ብለዋል፡፡አቃቤ ሀግ የወንጀሉን የመጀመሪያ ደረጃ ጭብጥ የሚያሳዬ ምስክሮችን ያቅርብ አይቅርብ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ የማስረጃ ማሰማት ሂደቱ ነገ ይቀጥላል፡፡

በተቃራኒው ምሳቸውን ችሎት ውስጥ የተመገቡት ሁሉም እስረኞች በጠንካራ መንፈስ ሆነው ሲጨዋወቱ እና ሲነጋገሩ ተስተውለዋል፡፡ የችሎቱ ተሳታፌዎች በምስክሮች መደናበር እየሳቁ ነበረ ሲሆን የዞን9 ወዳጆች አጋሮች ቤተሰብና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል፡፡

የዞን 9 ማስታወሻ

የዛሬውን አስቂኝ የፍርድ ቤት ውሎ ባልተካደ ነገር ላይ ወርቃማውን የተከሳሾች ሰአትም ሆነ የፍርድ ቤቱን የስራ ሰአት ማባከኑ የሚገርም ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ችሎቱ በግልጽ አንዲካሄድ መፍቀዱን በበጉ መልኩ ተመልክተነዋል፡፡ አቃቤ ህግ ለምስክሮቹ ደህንነት ሳይሆን የራሱን መዋረድ ለመቀነስ ሲል ችሎቱን በዝግ ለማድረግ መሞከሩ ተከትሎ የመጣውም የምስክሮች መወዛገብ ግልጽ የሚያደርገው ነው ፡፡ የዞን9 ጦማርያን አና ጋዜጠኞች ላይ የቀረበባቸው ማስረጃ በተለያየ ቦታ የጻፏቸው የራሳቸው እና የሎሎች የአደባባይ ምሁራን ጽሁፎች በመሆናቸው ጽሁፉ የእኛ መሆኑ ምስክር አያሻውም ፡፡ በተደጋጋሚ እንዳልነው ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው የታሰሩት ወጣቶች ክስ የጸፉት ጽሁፍ ይዘት ላይ ነው፡፡ የታሰሩ ወዳጆቻችንን ለመፍታት አሁንም አልረፈደም ፡፡

በዚህ አጋጣሚ ፍርድ ቤት ተገኝተው አጋርነታቸውን ለሚያሳዬ የዞን9 ወዳጆች ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ህገ-መንግስታዊ መብት ይከበር ፡፡

ዞን9

በ4ኛው ቀን ዘመቻ “ወሳኙ ማዕበል” እና አበይት ክንውኖቹ . . .

yemen1

* ትናንት ቅዳሜ መጋቢት 19 ግብጽ ሻርማ ሸክ ተሰብስበው የነበሩት 22 የአረብ ሊግ ሀገራት መራሄ መንግስታት በ26 ኛው መደበኛ ስብሰባ የየመንን ጉዳይ በሰፊው ተነጋግረውበታል

* መራሔ መንግስታቱ የሁቲ አማጽያን በኃይል ከያዘው ስልጣን ለማስወገድና ህጋዊውን የአብድልረቡ መንግስት ወደ ቦታው ለመመለስ ተስማምተዋል!

* የሳውዲው ንጉስ ሰልማን “ዘመቻው ግቡን እስኪመታ አያቆምም!” ሲሉ የግብጽ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ በበኩላቸው የጽንፈኝነትን መንሰራፋት በማውሳት በአረብ ሀገራትን አደጋና ከኢራን ትንኮሳ ለመታደግ ጥምር የጦር የአረብ ሀገራት ሰራዊት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ በአጽንኦት ተናግረዋል

yemen al sisi* ጉባኤው በአረብ ጥምር የህብረት ጦሩን ጉዳይ ከመከረ በኋላ በስብሰባው መዝጊያ የአብ ሊግ ዋና ጸሃፊ ነቢል አል አረቢ ባሰሙት የአቋም መግለጫ ከዚህ ቀደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያቀረቡት ረቂቅ ህግ ተጠንቶ በአጠቃላይ ጉዳይ በአንድ ወር ውስጥ ተገናኝተው በመምከር ታሪካዊ ያሉትን የህብረት ጦሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመመስረት እቅድ መያዙን አስታውቀዋል

* የኩዌትን አሚር ጨምሮ የተለያዩ አረብ ሀገራት ኢራን የአካባቢውን ሀገር ሰላም ለመንሳት በተዘዋዋሪ የምታሳየውን ተደጋጋሚ ፍላጎት ተቃውመውታል

* ፖለቲካ ነውና ያልተጠበቀው ይሆናል፣ የፍልስጥኤም መሪ ፕሬዚዳንት መሀሙድ አባስ በአረብ ሊግ ስብሰባ የተገኙ ሲሆን ከኢራን ድጋፍ ያገኛል የሚባለው የፍልስጥኤሙ ሽምቅ ተዋጊ ሃማስ የአረብ ሀገራቱን አቋም የሚደግፍ አስገራሚ የድጋፍ መግለጫ አውጥቷል

* የየመንን ህጋዊ መሪ አብድልረቡ መንሱር አልሃዲን መንግስት ወደ ስልጣን ለመመለስ በሳውዲ የሚመራውን ዘመቻ እንደሚደግፈው ፍልስጥኤምን ነጻ ለማውጣት ጠመንጃ ያነሳው ሽምቅ ተዋጊው ሃማስ ዘመቻውን ደግፎ መግለጫ ማውጣቱ ብዙዎችን አስገርሟል

* ስድስቱ ኦማንን ሳይጨምር የባህረ ሰላጤ ሀገራትን ሳውዲ፣ ኢምሬት፣ ቃጣር፣ ኩዌትና ባህሬንን ጨምሮ ዮርድያኖስ፣ ግብጽ፣ ሱዳን፣ ሞሮኮ በዘመቻው ተሳታፊ ሲሆኑ ቱርክ፣ ሞሮኮ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ቤልጅየም ድጋፍ መስጠታቸው ይጠቀሳል በአንጻሩ ሶርያ፣ ኢራን፣ ራሽያና ቻይና ዘመቻውን አጥብቀው ተቃውመውታል

* ኢራን የሁቲ ሸማቂዎችን በማስታጠቅና በመደገፍ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተች የየመን ፕሬዚዳንት አብድልረቡ መንሱርና የአረብ ሀገር መራሔ መንግስታት ቢጠቁሙም ኢራን የሚቀርብባት ውንጀላ ሁሉ “መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነው!” ስትል አስተባብላለች

የትዕንግርተኛው የመን “ድብደባውን አቁሙ!” ተማጽኖ . . .

* የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ ከ30 ዓመት በላይ የመንን ሲያስተዳድሩ አቀማጥለው የደገፏቸው ፣ የአረብ አብዮት መጥቶ ሀገር የመን ስትታመስና ፕሬዚዳንት አብደላ ሳላህ በአጥፍቶ ጠፊ ሲጎዱ አፈፍ አድርገው ህይወታቸውን የታደጉትንና ወደ ኋላም የመን በተቃውሞ ስትናጥና ስልጣናቸው አልረጋ ሲል መውጫ መንገድ ያበጁላቸው በቅርብ ሳውዲዎች፣ በርቀት የባህረ ሰላጤ ሀብታም አረብ ሀገራትና ምዕራባውያን ናቸውyemen2

* ዛሬ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከቁርጥ ቀን ደጋፊያቸው ከሳውዲ፣ ከአረብ ሀገራትና ከምዕራባውያን በተቃራኒ ጎራ መሰለፋቸው ይጠቀሳል፣ የቀድሞ ታዛዥ አጋራቸውና ስልጣናቸውን ሳይወዱ በግድ ያስረከቧቸውን የፕሬዚዳንት አብድልረቡ መንበረ ስልጣን እንዳይረጋ እንደ ኢራን በድብቅም ባይሆን በግላጭ ሁቲዎችን በመደገፍ የቀድሞው መሪና ልጃቸው አህመድ የመንን ለዚህ ውጥንቅጥ እንዳደረሷት ይጠቀሳል

* የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ በ26 ኛው የአረብ ሊግ የመሪዎች ስብሰባ ለተቀመጡት መራሔ መንግስታት ሳውዲ መራሹ ዘመቻ ያቆም ዘንድ “ችግሩ የተፈጠረው በፕሬ አብድልረቡ የአስተዳደር አቅም ማነስ ነው፣ ድብደባውን አቁሙ፣ መፍትሔው በድርድር እንጅ በጦርነት አይደለም!” የሚል አንድምታ ያለው ትንግርተኛ ተማጽኖ በአንድ ታዋቂ የአረብኛ ቴሌቪዥን በኩል መልዕክት አስተላልፈዋል

* የቀድሞው ፕሬዚዳንት የቆየውን የሳውዲና የሀገራቸውን መልካምና ጠንካራ ግንኙነት፣ ከ1.7 ሚሊዮን በላይ የመናውያን በሳውዲ በተለያዩ ስራዎች ተሰማርተው የመገኘታቸውን መልካም ጉርብትና በማውሳት ሳውዲ መራሹ ጦር በየመን ላይ የከፈተውን ዘመቻ ልጆቻችንና ሀገራችን እያወደመ ነው ሲሉ ድብደባው በአስቸኳይ ያቆም ዘንድ ልዩ መልዕክትን ለሳውዲ መንግስት አስተላልፈዋል

* የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ በዚሁ ንግግራቸው የመንን በድርድር የማረጋጋቱ ስራ ቅድሚያ ይሰጠው ሲሉ የየመን ወቅታዊ ችግር በድርድር ከተፈታ በቀጣይ ምርጫ ቢደረግ እርሳቸውም ሆኑ የቤተሰብ አባሎቻቸው ወደ ስልጣን መንበር የመውጣት ፍላጎት እንደሌላቸው በንግግራቸው አስታውቀዋል

* የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ ልጆች መካከል የጦር መኮንኑ አህመድ በሶስተኛው ቀን የአየር ላይ ድብደባ እንደቆሰሉ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ጠቁመዋል። የተረጋገጠ መረጃ ነው ማለት ግን አይቻልም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቀድሞው የየመን አስተዳደር በከፍተኛ የጦር ኃላፊነት ያገለግሉ ከነበሩት ውስጥ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ልጅ አህመድ በሳውዲ የተመራው ጦር የዘመቻ ጥቃት ከመደረጉ አስቀድሞ የሁቲ አማጽያንን ከስልጣን ለማስዎገድ እድሉ እንዲመቻችለት ጥያቄ አቅርቦ ተቀባይነት አለማግኘቱን አል አረቢያ ዘግቦታል

የሁቲዎቻ ዛቻና የዘመቻው መምሪያ መግለጫ

* የሁቲ ከፍተኛ ባለስልጣን አብል ሙንኢም አል ቁረሽ የሳውዲን ጣልቃ ገብነት በዚህ ከቀጠለ ሳውዲ ልትቆጣ ጠር የማትችለው ጥቃት እንሰነዝራለን ሲሉ ለኢራን አል ፋሪስ ዜና ወኪል በሰጡት መግለጫ ዝተዋል

* በሁቲዎች ዛቻና በዘመቻው ዙሪያ ትናንት መግለጫ የሰጡት በሳውዲ የተመራው የህብረት ጦር ቃል አቀባይ  ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ ስለ አራተኛው ቀን የአየር  ድብደባ መግለጫ ሰጥተዋል

* ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በተለያዩ ከተሞች በዘመቻው መምሪያ በተጠኑ የሁቲ አማጽያን ወታደራዊ ኢላማዎች አልፎ ወደ ሳውዲ የመን ድንበር የጀዛንና ነጅራን ዘልቀው ጥቃት ሊሰነዝሩ የነበሩ የሁቲ ቡድን አባላት እግር በእግር  እያታሰሰ የመደምሰሱ ስኬታማ ስራ መስራቱን የዘመቻው ቃል አቀባይ አስረድተዋልyemen3

* ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በዚሁ መግለጫቸው በሳውዲ የተመራው የህብረት ጦር በሁቲ አማጽያን እጅ የነበረውን የብላስቲክ ሚሳየል ክምችት ballistic missile stockpile በአብዛኛው ማውደሙን አስታውቀዋል

* ከየመን ሰንአ የህብረቱ የአየር ኃይል ጦር የደቡብ ከተማዋ በዳሊያ ባደረገው ወታደራዊ ይዞታዎች ኢላማ ያደረገ ድብደባ የሁቲ አማጽያን ጸረ አውሮፕላን በመተኮስ መልስ መስጠታቸውም ተጠቁሟል

* ወደ ሶስት መቶ የሚጠጉ የሳውዲ ፣ የምዕራባውያን ሀገር ዲፕሎማቶች እና የተባበሩት መንግስታት ሰራተኞችን በተለያየ ዘመቻ ሰንአ የመንን ለቀው መውጣታቸው ታውቋል

እስኪ ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 20 ቀን 2007 ዓም

መለሰ ዜናዊ ናፈቁኝ – የለቅሶ አየር ሰዓት አማረኝ

meles funeral3

ሰላም ወገኖቼ!! ተጠፋፋን። ግን አንለያይም። ድሮ የዘፈን ምርጫ ክፍለ ጊዜ ነበር። እሁድ እሁድ ወታደሮች ከደጀን፣ እናትና አባት፣ ቤተሰብ ከቤት ሆነው ይኮሞክሙት ነበር። አሁን ግን ለምን ተከለከለ? ባድመ፣ ሽራሮ፣ ዛላምበሳ፣ ገመሃሎ፣ ላከ ኤርትራም አሉ፤ ዘላበድኩ መሰለኝ … ብቻ የዘፈን ምርጫ ክፍለ ጊዜው ትዝ ብሎኝ ነው። ቀጭኑ ዘ-ቄራ ነኝ!!

“የለቅሶ ማስተላለፊያ የአየር ሰዓት/ክፍለ ጊዜ ቢጀመር ጥሩ ነው። ምርጫውን ያደምቀዋል” የሚል አስተያየት ሟርተኞች ያቀርባሉ። ግን ምን አለበት የከፋቸው ቢያለቅሱ። በየጓዳው እያለቀሱ ነው። አደባባይ ወጥተው ቢያለቅሱ ምን ነውር አለው? ለመለስ ደረት እየተመታ ሲለቀስ የአየር ሰዓት ተፈቅዶ የለ? ለሞተ ሰው ከተፈቀደ በህይወት ላለው፣ ግብር ለማያጓድለው ለምን ይከለካል? ወይስ ነዋሪው በሟች ተበልጧል?

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲባል የመለስ ለቅሶ በጊነስ ቡክ አለመመዝገቡ አያስገርምም። አማራ ደረት ሲደቃ፣ ደቡብ በዜማ ሲናባ፣ ትግሬ በለቅሶ ሲያዜም፣ ኦሮሞ እንባውን “ያ አባ ኮ” እያለ ሲያንዘቀዥቅ፣ ማን ቀረ? ሃይሌ ገ/ስላሴ ሲቃ ይዞት የእንባ “ቫት” ሲገብር … ድፍን አገር ሃዘን ሰብሮት፣ መሪው በድንገት እንደ ቡሽ ተስፈንጥረው ሲሄዱበት፣ ራዕያቸው ሲተንበት፣ ህልማቸው እንደ ጉም በድንገት ሲበተነበት፣ ጉሮሮው በድንገት ሲዘጋበት፣ ኑሮ ወደ ጎዳና ተዳዳሪነት ሲለወጥ፣ “የመጪው ጊዜ ብሩህነት” ሲደበዝዝ፣ እንዴት አያነባ? ጎበዝ ለመለሰ ዜናዊ ማን ያላነባ አለ?

መለስ አማረረን ብለው የተሰደዱ፣ በስደት ካምፕ የመለስን ፎቶ ሰቅለው ለቅሶ ተቀምጠዋል። ጠጅ ቤት፣ ጫት ቤት፣ … ምርጫ ሲመጣ ቀጭኑን ያመዋል። ምርጫ የግል ነው። የምርጫ ሰሞን ወሬ ለቃሚዎች ሲሳይ ይሆንላቸዋል። እገሌ ይህን አለ እያሉ በጀት ያስጨምራሉ። ወሬ ለመልቀም ይከንፋሉ። በየጫት ቤቱ ይራወጣሉ። ተናግሮ ማናገርና መልቀም። ጓደኞቻቸውን ማስበላት። አሳልፎ መስጠት። በህወሃት የባህር መዝገብ ማስመዝገብ።

OLYMPUS DIGITAL CAMERAአቶ መለስ አፈር አይክበዳቸውና (ለነገሩ አፈር ውስጥ አልገቡም) 99.6 በመቶ ምርጫን በማሸነፍ “ታሪክ መሰራቱን” ሲያበስሩ 96 በመቶ እንዲያሸንፉ ያደረጓቸው ወዳጆቻቸው ፊት ሰክረው ነበር። አራዳው መለስ በደስታ ቢሰክሩም መስታወት ቤት ውስጥ ሆነው መናገርን ግን አይረሱትም። ደስታ እየደቃቸው መስታዋት ቤት ውስጥ ሆነው “ኮራሁባችሁ” ሲሉ ከሲኤምሲ በ200 አውቶቡሶች ተጭነው መስቀል አደባባይ የደረሱ የኮብል ድንጋይ አንጣፊዎች አጨበጨቡ። በፉጨት አስተጋቡ። መለስ ደስታቸውን ሳያጣጥሙ ሾለኩ … ከመስታወት ቤት ወደ ግራውንድ ሲቀነስ ወረዱ። እዛ ወከባ የለም። ጭብጨባና ፉጨት የለም። ራዕይ፣ ቅዠት፣ “ሌጋሲ”፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ ህዳሴ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ኒዎሊበራል፣ ምናምን የለም። የዘላለም እረፍት … ቀጭኑ እንባ ባይረጭም ሃዘን ገባው።

የዜናዊ ልጅ ምነው ሞትን ሞተው በነበር? ቀጭኑ ጠየቀ። ሞት ያለ ሳይመስላቸው እንዲሁ በትዕቢት ማማ ላይ እንዳሉ ኮበለሉ። ቢያንስ ህዝብ የመምረጥና የመሻር ወሳኝ ሃይል እንዳለው አይተውና አሳይተው ቢነጉዱ ኖሮ እስከዛሬ ባነባን ነበር – ለነገሩ አይተዋል ማሳየት አቃታቸው እንጂ። ቀጭኑ መለስን የሚወቅሰው በዚህ ነው። ነጻ ትውልድ እንዲፈጠር አድርገው ቢያልፉስ ምን ነበር? የሚገርመው አሁንም ትምህርት የሚወስድ የለም። አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ኦቦ ሃይለማርያም ማለቴ ነው። ከ96 ወደ 100 በመቶ ለማሳደግና ሲሞቱ ደቡብ ሱዳን፣ ፑንትላንድ፣ ሩዋንዳና ኡጋንዳ የዘለቀ ሃዘን እንዲታወጅላቸው የሚተጉ ይመስላሉ። ሃይሌ ዕዳቸው ብዙ ነው፤ ለነገሩ የአገር መሪዎች ባለብዙ ዕዳ ናቸው፤ የሃይሌ ግን የበዛ ይመስለኛል፤ የራዕዩ፣ የሕዳሴው፣ የውዳሴው፣ የሌጋሲው፣ … ኧረ ስንቱ?! ራዕያቸውን፣ ሌጋሲያቸውን፣ … ተግባራዊ እናደርጋለን፤ እያሉ ስለ መለስ እንደሚናገሩት አንድ ቀን “ሞታቸውንም ተግባራዊ እናደርገዋለን” ብለው ንግግር ቢያደርጉስ? ለነገሩ ምን ይተገበራል? ለመሆኑ ስንቶቻችን ነን ህያዋን የሆንን? ወደ ጉዳዬ ልመለስ …meles in box1

“እኒህ ፖለቲከኞች ነፍስ የላቸውም እንዴ” ስትል ማይሟ እናቴ ሁሌም ትጠይቃለች። ደግ ስራ ሰርቶና ተወድዶ መሞት ለምን እንደማይወዱ አይገባትም። ለመለስ ለቅሶ አልሄደችም። ለዚህ ነው መሰል የቀበሌው ሊቀመንበር አሁን ድረስ ይገላምጣታል። በነገራችን ላይ ያንዱ ቀበሌ ሊቀመንበር ባልደረባዬ ነበር። የመለስን ለቅሶ ቀበሌ ድንኳን አስተክሎ ሲያከናውን ወደ ጓሮ እየጠራሁ ጫት አጎርሰው ነበር። ድንገት ስናወራ “ለመለስ ለቅሶ ከልብህ አላዘንክም፣ መልፈስፈስ አሳይተሃል፣ ቁርጠኝነት አይታይብህም፤ …” ተብሎ መገምገሙንና 40 ሳይደግስ መሰናበቱን ነግሮኛል። አይ ግም-ገማ!!

አሁን ማን ይሙት እነዚያ ጎንደር ላይ አበል ከፍለው ደሃውን ሲያላቅሱትና በግምገማ ደረት ሲያስመቷቸው የነበሩት ሴቶች መለስን ያውቋቸዋል? ጋምቤላ አኙዋክ ምድር ለመለስ የሚያነባ ሰው ይገኛል? ፊልም የሚሰራ ደፋር ጠፋ እንጂ ከዚህ በላይ ምን ፊልም አለ? ኤርትራ ቤተ መንግስት ውስጥ አንድ ክፍል በድብቅ ሃዘን ተካሂዶ ነበር ብሎ የፈተለ ሰው አጋጥሞኛል። የኤርትራ ባንዲራ ዝቅ ስለማለቱ ግን መረጃ የለውም። የስምዖን ልጅ ሲሽቀነጠር እናያዋለን።

ባገራችን ምርጫ ያለ ፈቃድ ማልቀስና ደረት መምታት ነው። ባገራችን ምርጫ የራስ ሳይሆን የሌሎችን ምርጫ ማጽደቅ ነው። ባገራችን ምርጫ የራስን መብት ለሌሎች በህጋዊ ሰነድ ስም ማስረከብ ነው። ምርጫ!! በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ምርጫ ብሎ ነገር የለም። አለመስማማት ተፈጥሯዊ ነው። አለመቀበልና አለመስማማት ግላዊ ነው። ልዩነት ያለ፣ የነበረ፣ የሚኖር እውነት ነው። ምርጫ በነዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ይገኛል። ከዚህ ውጪ ያለ የጫና ምርጫ የሰውን ልጅ አሻንጉሊት አድርጎ የማሳነስ ያህል ነው። የሰው ልጅ ክቡር ነው። ምርጫውን ያውቃል። ግን የእኛን አገር አይመለከትም።

ምርጫ በመጣ ቁጥር አየሩ ሁሉ ይከረፋል። ምርጫ በመጣ ቁጥር የህወሃትና ኢህአዴግ እብደት ይገንናል። እነሱ ሰማይና ምድሩን አፍነው የፈጣሪ ያህል የሆኑ ይመስላቸዋል። ቅጠሉና ዛፉ እንኳ አይታመንም። ወይ አንደኛውኑ ምርጫውን ቢዘጉት አይሻልም? ቀጭኑ ይህንን ሃሳብ ያቀርባል። ምርጫ የሚኖረው ምርጫና የመምርጥ መብት ሲከበር ነው። አስመራጩ ባንዳ፣ አስፈጻሚው ባንዳ፣ የበላዩ ባንዳ፣ የበታቹ ተላላኪ፣ መቃወም፣ መተንፈስ፣ ማስተማር፣ መናገር፣ መዝለፍ፣ ማጋለጥ፣ ነጻ ሚዲያ፣ ነጻ የመጫወቻ ሜዳ ሳይኖር ምርጫ? ይቀፍፋል። መቼ እንደምንሰለጥን አይታወቅም። ሁሉም ጋር ችግር አለ። የዜናዊ ልጅ ግን ናፍቀውኛል። መልካም ነገር አስተምረውን አለፉ፣ ተፈተለኩ፣ ተነቀሉ፣ ተደለቱ፣ አሁንም ለሳቸው ማልቀስ የሚፈልጉ አሉ። የማልቀሻ የአየር ሰዓት ይፈቀድ ብለው የሚጠይቁ አሉ። ለመለስ የለቅሶ ምርጫ ክፍለ ጊዜ ይመደብልን። ከየብሔሩ እያፈራረቅን መስማት የምንፈልግ ቧልተኞችም አለን። ቀጭኑ የምርጫ እድል ቢሰጠው “ያ አባ ኮ” በሚል የኦሮሞ አርሶ አደሮች ያነቡበትን ለቅሶ ቀዳሚ ክሊፕ አድርጎ ይመርጠዋል። ከዚያም “ሰለሜ ሰለሜ” የሚለውን በለቅሶኛ ያስከትላል። ቸር እንሰንብት!! ቀጭኑ ዘ-ቄራ!!

http://www.goolgule.com/

የምርጫ ክርክር ሶስት- ግብርና እና ገጠር ልማት (ከግርማ ሰይፉ ማሩ)

“በ24 ዓመት አሁንም በአዝማሚያ ላይ ነኝ የሚለው ኢህአዴግ ……”
“የ1997 የምርጫ ክርክር ይደገም ……”
ግርማ ሠይፉ ማሩ
girmaseifu32@yahoo.com; girmaseifu.blogspot.com
ተከራካሪዎች፤
አቶ ተፈራ ደርቤ እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ
አቶ ግርማይ አደራ እና ዐዐዐዐዐ
አቶ ትዕግሰቱ አወሉ እና አቶ ዮሃንስ አሰፋ
አቶ ግዑሽ ገብረሰላሴ እና ትዕግሰቱ ዱባለ
አቶ ጥላሁን እንዳሻው እና ሙላቱ ገመቹ

(ግርማ ሰይፉ)

በመጋቢት 18 እና 19 2007 ለግንቦት ምርጫ የተደረገው “የምረጡኝ ክርክር” የተጀመረው በአቶ ተፈራ ደርበው በተመራው የኢህአዴግ ቡድን በግንባሩ ውስጥ በከባድ ሚዛኑ ህወሃት ተወካዮ ዶክተር አብርሃም ተከሰተ በመታገዝ ነበር የተገኘው፡፡ ተከራካሪዎቹ በኢህአዴግ በተተኪ መስመር የሚገኙ ቢሆኑም እንደ ወትሮ ሁሉ ኢህአዴግ የሚያቀርበው አዲስ ሀሳብ ለሚቀጥለው የስልጣን ዘመን ሊያቀርብ አልቻለም፡፡ እነዚህ የኢህአዴግን ሹሞች ልብ አውልቅ የሆነውን በእውሸት የተሞላውን የቁጥር ጫወታ ይዘው ብቅ ያሉ ሲሆን በዚህ ደረጃ ሊሞግታቸው የሚችል፤ አንድም ተቃዋሚ ነኝ የሚል ለማየት አልቻልንም፡፡ ኢህአዴጎች ከታቃዋሚዎች በላቀ ደረጃ ጎላ ያደረጋቸው የለበሱት ሱፍና የተጫሙት ጫማ ማብቅረቅ ሲሆን ተቃዋሚዎች አሁንም ከጀርባቸው ያስቀመጧቸው አማካሪ ተብዬዎች ምንም ያለመፈየድ ሳይሆን እንቅልፍ ሲያንጎላጃቸው ማየት ኢህአዴግ በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ምን ዓይነት ሰዎችን ወደፊት እያመጣ እና ወደፊትም እንደሚያመጣ አመላካች ነው፡፡ ከተቃዋሚ ጀርባ ለተቀመጡትም ሆነ በፊት መስመር ላሉት ደካማ ተቃዋሚዎች ተጠያቂው ኢህአዴግ እና የዘረጋው ስርዓት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡
ኢህአደግ ለቀጣይ አምስት ዓምት በስልጣን እንደሚቆይ ቢያውቅም ይህን በትህትና ለገጠሩ ህብረተሰብ ያስተላለፉት ዶክተር አብርሃም ተከሰተ እና ቆጣ ቆጣ ሲሉ የነበሩት አቶ ተፈራ ደርቤ ናቸው፡፡ ለዚህም እንደማስረጃ ያቀረቡልን
· 60 ሺ በላይ የገጠር ልማት ሰራተኞች እና የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች(በተቃዋሚዎች በትክክል ካድሬዎች ተብለው የተፈረጁት)፤
· ድህነትን በ1988 ከነበረበት 48 ከመቶ ወደ 24 ከመቶ ዝቅ ማድረጋቸው፤ (በመቶኛ ቀነሰ ቢባልም በቁጥር ግን በ1988 ከነበረው ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡)
· መስኖ እና ሰፈራ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ማስፋፋቱ፤
· 2.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በግል ባለሀብት እየለማ መሆኑ (ይህ መረጃ በቅርቡ እየተነገረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን በዚህ መስክ የሚያደርጉት ተሳትፎ በግልፅ የሚታይ አይደለም)
· የመሰረተ ትምህርት እና ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት መስፋፋቱ፤ ወዘተ ሲሆን

በዚህ መነሻ አርሶ አደሩ ሀብት እያከባተ በመሆኑ ወደ ማንፋክቸሪንግ ዘርፍ እንሚገባ አሰረድተውናል፡፡ አህአዴጎች በዛሬው ክርክር የቀደሞ ሰርዓት መክስስ ዘዴያቸውን የገቱ ቢሆንም ተቃዋሚዎችን ማጣጣል በተለይ መድረክ ላይ ለመዝመት ተዘጋጅተው እንደመጡ አቀራረባቸው ያሳብቅ ነበር፡፡ አቶ ተፈራ ደርቤ በተደጋጋሚ ተቃዋሚዎች ከላይ የተዘረዘሩትን የኢህአዴግ ሰኬት በመቃወም መሬት ይሸጥ ይለወጥ በማለት አርሶ አደሩን በማፈናቀል ለጥቂት ባለሀብቶ የቆሙ መሆናቸውን ያረጋገጡበት ክርክር ነበር፡፡ አቶ ተፈራ ደርበው ከመድረክ ጋር ተከራከሩ ተብለው መመሪያ እንደተሰጣቸው በሚያሳብቅ ሁኔታ መድረክን መሬት ይሽጥ? ነው የምትሉት ወይስ ሌላ አማራጭ አላችሁ? እያሉ በተደጋጋሚ አንስተውታል፡፡ አቶ ጥላሁን እንሻውም እንዳሻቸው መልሰውላቸዋል፡፡

ከኢህአዴጉ ተወካይ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ያነሱት ሀሳብ ግን ወደ 1997 ክርክር መልሶኛል፡፡ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ አቶ አዲሱ “ግብርና ሴክተር የእድገት ፍንጭ” እያሳየ ነው ሲሉ ለሰጡት አሰተያየት “ከ14 ዓመት በኋላ ፍንጭ እየታየ ነው አትበሉን” በሚል የሰጣቸውን ምላሽ አሰታውሶኛል፤ በ2007 ክርክር ዶክተር አብርሃም ተከስተ የግብርና ፖሊሲው “የስራ አጥ ቁጥርን የመቀነስ አዝማሚያ” እያሳየ ነው ብለውን ከ24 ዓመት በኋላ አዝማሚያ ላይ እንደሆኑ ነግረውናል፡፡ በእኔ እምነት የግብርና ዘርፉ ይህን ሁሉ ጉልበት ይዞ መቀመጥ አይጠበቅበትም፡፡ በግብርና ዘርፍ ያለው ትርፍ ጉልበት ሊቀበል የሚችል ግብርና ያልሆነ ዘርፍ መፍጠር ያልቻለው ኢህአዴግ ሊከሰስበት የሚገባው ዋና ነጥብ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ 24 ዓመት ያልበቃው ኢህአዴግ ምን ሲሰራ ነበር ተብሎ አይጠየቅም፡፡ ብዙዎቹ ሚኒሰትሮች ከሁለተኛ ደረጃ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም ድህረ ምረቃ ትምህርት ሲከታተሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡ አንድ አንዶች ለሶሰተኛ ዲግሪ የሚሆን ጊዜ ነበራቸው፡፡ አበበ ገላው እየገዙ ነው የሚለውን ወደጎን እንተወው ከተባለ ማለት ነው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ያሉትም ማሰታወስ ያሰፈልጋል “እነዚህ ሰዎች ሀገር እየመሩ/እያሰተዳደሩ ሶሰተኛ ዲግሪ መያዛቸው ወይ ሰራቸውን እየሰሩ አይለም፣ ካልሆነም ትምህርቱ ቀሎዋል ማለት ነው” አሰተያየት ሰምቻለሁ፡፡ ቃል በቃል ባይሆንም፡፡

ለማነኛውም ኢህአዴግ መነሻ ሀሳቡንም፣ ማብራሪያውንም ማጠቃለያውን “በሚመጥነው” ደረጃ አቅርቦ ክርክሩን አጠናቆዋል፡፡ ከዚህ የጠነከረ ክርክር ቢያቀርብ ማን ከቁብ ሊቆጥርለት ነው፡፡ በእኔ ግምት ዶክተር አብርሃም ተከስተ በዚህ ክርክር ላይ ባልመጣው ሳይል የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ጠንከር ያለ ቁጥርና ቁጥር ነክ ጥያቄዎች በተለይ ደግሞ የመዋቅራዊ ሽግግር ጥያቄዎች እና ማክሮ ኤኮኖሚክ ነክ የሆኑ ለምሳሌ በውጭ ምንዛሪ ግኝት፣ በግብርና ሴክተር የመሪነት ሚና ላይ ዝርዝር ሀሳቦች ለመመለስ በክርክሩ ላይ የተገኘ ይመስል ነበር፡፡ ዶክተር አብርሃም ተከስተ የክርክር ጊዜውን ለመግደል ዘና ብሎ ሲመልስ ላስተዋለ በእግር ኳስ ጫወታ እየመራ ያለ ቡድን ጎል ጠባቂ ጊዜ ሲያባክን የሚያሳየውን ባህሪ የሚያሰታውስ ነው፡፡

ለማነኛውም አቶ ተፈራ ደርቤ ያቀረቡት የመሬት ጉዳይ በህገ መንግሰት ውስጥ መግባቱ እና አሁን የሚከተሉት የመሬት ፖሊሲ መሰረቱ ኤኮኖሚያዊ ነው ብለው ቢዋሹም፣ ኢህአዴግ መሰረቴ ነው የሚለውን አርሶ አደር ለመቆጣጠር እንዲችል የተቀመጠ ፖለቲካዊ መሰረትነቱ መቼም ክዶት የማያወቅው ታውቆ ያደረ ጉዳይ መሆኑን የሚያስታውሳቸው አላገኙም፡፡ የዶክተር አብርሃም ተከሰተ ትህትና የተሞላበት የምረጡን ጥያቄም አማላይ ነበር፡፡

ኢህአዴግ በአቶ ግርማይ አደራ በሚባሉ ሰው የተወከለ ሲሆን በረዳትነት የተገኘውን ለማወቅ እድል አላገኘንም፡፡ አቶ ግርማይ ጊዜው አይበቃም ቢሉም ሲጀምሩ ቀስ ብለው ተዝናንተው ሲጨርሱም ሁለት ደቂቃ አሰቀርተው ሲያጣቃልሉም ለጊዜ አጠቃቀም ምንም ግድ ሳይሰጣቸው ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር ከእኝ ግለሰብ ልይዝላቸው የቻልኩት ነጥብ መሬት ለኢትዮጵያን የዜግነት፣ የሀገር ባለቤትነት፣ የነፃነት መገለጫ ነው የሚሉት እና የማዳበሪያ ዕዳ ለመክፈል አዲስ አባባ ለልመና የሚመጡ አርሶ አደሮች መኖራቸውን ያስታወሱን መሆኑን ነው፡፡ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ በፅሁፍ የያዘውን በቅጡ የማያነብ፣ በቂ አይደለም ብሎ ካለው ጊዜ ውስጥ በመግቢያና በመውጫ ሠዓት ማባከን ምን ግምት እንደሚያሰጥ ተከራካሪው ያሰቡበት አይመስለም፡፡ ለማነኛውም ኢህአዴግ አቻውን አግኝቶዋል ማለት ይቻላል፡፡ በቃ ኢህአዴግ የሚመጥነው እንደ አቶ ግርማይ አደራ ያሉ ፖለቲከኞች ናቸው፡፡ ምርጫቸው ነው እና ማክበር አለብን፡፡ አቶ ግርማይ አርማው ጋሻና ጦር የሆነ እድር ቢኖራቸው ችግር የለኝም ነገር ግን እርሳቸውም ሆነ የእርሳቸው ፓርቲ በሚሰጡት አመራር በማጠቃለያ እንደነገሩን በምግብ እህል ራሷን የቻለች ኢትዮጵጰያ ሊዚያውም ተርፎዋት ኤክስፖርት የምታደርግ ሀገር አይሰሩልንም፡፡ ለኢትዮጵያዊ የቀረበለት ከዝንጀሮ ቆንጆ መረጣ ነው፡፡

“ድንኩ አንድነት” እንደ ተለመደው በትዕግስቱ አወሉ የተወከለ ሲሆን በረዳትነት የተመደበለት ደግሞ አቶ ዮሐንስ አሰፋ ነው፡፡ አቶ ትዕግሰቱ በቴሌቪዥን በክርክር የሰንብት ክርክሩን አድርጎ ሄዶዋል፡፡ እኛም ተገላገልን፡፡ ባለፈው ድንኩ አንድነት የአንድነት ፓርቲ ውስጥ አባል ያልሆነ ሰው ለክርክር ቀረበ ብለን ትንሽ ተንጫጭተን ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ በረዳትነት የመጣው አቶ ዮሃንስ አሰፋው ለጫጫታ መነሻ የሚሆን አወዛጋቢ ግለሰብ ነው፡፡ ዮሐንስ በወረዳ 24 ውስጥ፣ ገዢውን ፓርቲ ወክሎ ወረዳውን ሲያምሰ የነበረ ነው፡፡ የሴራው ማጠንጠኛም አስራት አብርሃም ነበር፡፡ ፓርቲው አምኖበት በከፍተኛ ሃላፊነት ላይ ያስቀመጠውን ሰው የወያኔ ተላላኪ ነው እያለ ውንጀላ ሲያደርግ፣ በአስራት አብርሃም ደረጃ አሰተዋጽኦ የሚያደርግ ከየትም ቢመጣ ችግር እንደሌለብን አሰርደቼው ነበር፡፡ ለነገሩ ፓርቲውን ለመፍረስ ከሚያሴሩት ጋር በግልፅ እንደሚሰራ እያወቅን በዝምታ ያለፍነው የውስጥ አርበኛ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በአሰራት አብርሃም ቦታ ወረዳ 24 ዕጩ ሆኖ የቀረበ ሲሆን ለትዕግሱቱ አወሉ ቡድን በቂ አማካሪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ከዚህ የተሻለ ከትዕግሱቱ ጎን ማግኘት አጉል ነው የሚሆነው፡፡ ትዕግስቱም የልኩን አማካሪ ኢህአዴግም የሚመጥነውን ተቃዋሚ አግኝተዋል፡፡

ትዕግሰቱ የአንድነትን የፖሊሲ አማራጭም ሆነ ዝርዝር የኢህአዴግን የአፈፃፀም ክፍተት በተሟላ ይዞ ሊቀርብ እንደማይችል ማንም ያውቃል፡፡ በድፍረት ግን “የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ በአሰቸጋሪ ሁኔታም ቢሆን አንድነትን ምረጡ” የሚል ቃል እንዴት ሊወጣው እንደቻለ አልገባኝም፡፡ ከሁሉም ያስገረመኝ ደግሞ “ኢህአዴግ የመሬት ፖሊሲ የምቀይረው በመቃብሬ ላይ ነው” ይላል በሚል የሰጠው አስተያየት ነው፡፡ ኢህአዴግ ለስልጣኑ ዋልታና ማገር ያደረገውን የመሬት ፖሊሲ በመቃብሬ አለ የሚለው ትዕግሰቱ አወሉ እልህ ምላጭ ያስውጣል በሚል መፈክር ከራሱ ሌላ አንድ ሌላ ድምፅ ለማግኘት ያልቻለበትን አንድነት ፓርቲን ከምርጫ ቦርድ እና ከገዢው ፓርቲ ጋር እርሱ በሚያውቀው መስመር ተመሳጥሮ ድንክ ያደረገ ግለሰብ፣ ታንክና ባንክ ለማዘዝ የሚያሰችል ስልጣን የሚያስገኝን የመሬት ፖሊሲ በመቃብሬ ላይ ቢባል ምን እንደሚያስገርም አልገባኝም፡፡ ትዕግሰቱ አወሉ ታንክና ባንክ የሚያዝ መንግስት ቢሆን ብዬ ሳሰበው ዘገነነኝ፡፡

አቶ ትዕግሰቱ አወለ በክርክሮች ሁሉ ቀና ብሎ የቴሌቪዥን ካሜራ ለማየት ማፈሩ ተገቢ ሆኖ ባገኘውም የሚያፍር ከሆነ ለምን ቴሌቪዥን ላይ እንደሚመጣ ነው የማይገባኝ፡፡ አንድነት አማራጭ እንዳለው ሰንድ ማሳየት ይቻላል ያለው ትዕግሰቱ የአንድነትን ፕሮግራመ በቅጡ ማንበብና መዘጋጀት ሳይችል (የምርጫ ማኒፌስቶ እርሱ ሊያገኘው አይችልም፣ ቢሮ ዕቃ በጉልበት ሲዘርፍ በአባላት ጭንቅላት የሚገኝ እውቀት ግን በእርሱ እጅ አልገባም) የዛሬ አምስት ዓመት የተዘጋጀውን ሰትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ለዚያውም በመግቢያ ላይ የተፃፈውን ሰለ ዜጎች ሰደት የሚያወራውን ክፍል ለግብርና ክርክር ይዞ ሲቀርብ፣ “የድንኩ አንድነት” ተወካይ መሪ አቶ ትዕግሰቱ ለመዘጋጀት ፈተና የሆነበት ምን ያህል የውስጥ ሰላም አጥቶ እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው፡፡ አንድነት በየትም ቦታ ዜጎች ወደ ከተማ መምጣት ችግር ነው ብሎ አያውቅም፡፡ ይልቁንም ችግር ከሆነ እንደ ችግር የሚያየው ዜጎች ከመሬት ጋር ተጣብቀው በገጠር እንዲኖሩ መደረጋቸወ ነው፡፡

ሌላው ያስገረመኝ የጥርሶቹ ማለቅ ሲሆን (መለስ መላጣ ማለት ይቻላል፣ መንካት ግን አይቻልም ባለው መሰረት)፣ እንዴት ነው አሁን ያለው የገንዘብ ፍሰት ለዚህ የሚሆን እንጥፍጣፊ የለውም ወይ? የሚል ጥያቄ ጭሮብኛል፡፡ ከዚህ በፊት ጥርሳቸውን ያስተከሉ መሪዎች በፓርቲው ገንዘብ ነው እያለ እርሱ ሲያወራ ስለነበር ነው፡፡ ለማነኛውም “ሞያ በልብ ነው አንድነትን ምረጡ” ያለው ትዕግሰቱ በግሌ የወረዳ 8 ነዋሪ ከራሱ በስተቀር አንድም ድምፅ እንዳያገኝ በማድረግ እንዲያዋርደው በማክበር ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ በሰፈሩ ያሉት እድሮችና የትዕግሱ የማሪያም ፅዋ ማህበርም ይህን እንዲያስተባብሩ እና ትዕግሰቱ ከራሱ በስተቀር አንድም ድምፅ እንዳያገኝ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን የኢህአዴግ ኮካዎች ማህበራዊ ማግለል ወንጀል ነው ይሉታል፡፡ በትዕግስቱ ላይ ማህበራዊ ማግለል ወንጀል የሚሆንበት ህግ ካለ ለመማር ዝግጁ ነኝ፡፡ መቼም ትዕግሰቱን በመወከል ታዛቢ ይኖራል ብዬም አላምንም፡፡ በተጨማሪ የአንድነት ደጋፊዎችም ትዕግሰቱ ከራሱ ሌላ አንድም ሌላ ድምፅ እንዳያገኝ ጠንክረው መስራት ይኖርባቸኋል፡፡ ይህን ሳናደርግ ብንቀር ሌሎች ትዕግሰቱዎች ለዚህች ሀገር እየጋበዝን መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ አንድነት ዋንጫ የሚያነሳው ትዕግሰቱና የትዕግሰቱ ቡድን ድምፅ ሲያገኝ ሳይሆን እነርሱ ተገቢውን ውርደት ሲከናነቡ ነው፡፡

ኢድአን አቶ ግዑሽ ገ/ሥለሴ እና ትዕግስቱ ዱባለ በተባሉ አባላቱ ተወክሎ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ አቶ ግዑሽ ገ/ሰላሴ በ2002 ምርጫ ወቅት መድረክ ሞቅ ያለ የምርጫ ስራ ላይ እያለ “ኢድአን ከምርጫ ወጥቶዋል” በሚል መድረክን ያመሱ ግለሰብ ናቸው፡፡ በምርጫ ወቅት የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎችን የሚያዳክምበት መሳሪያ ናቸው፡፡ ከምርጫ በኋላ እዚህ ግባ በሚባል ፖለቲካ ውስጥ ጉልዕ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አይታዩም፡፡ አቶ ግዑሽ ካቀረቡት ክርክር ነጥብ አድርጌ የያዝኩላቸው “ … እሰከ መገንጠል መብት የሰጠ መንግሰት፣ ለአርሶ አደሩ መሬትን እሰከ መሸጥ ለምን መስጠት ፈራ” የሚለው ነው፡፡ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብት እሰከ መገንጠል ስለተሰጠ የተገነጠለ የለም በሚል የሚከራከረው ኢህአዴግ አርሶ አደሩ እሰከ መሸጥ የሚደርስ መብት ቢያገኝ በመሬቱ ተጠቃሚ ከሆነ አይሸጠውም የሚል መርዕ እንዴት ሊገባው አልቻለም የሚል ነው፡፡ ተዋዋሚዎች ትንሽ ከሚሏት የክርክር ደቂቃ ሁለት ደቂቃ ያገኘው የአቶ ግዑሽ ረዳት አቶ ትዕግሰቱ ዱባለ ያገኛትን ሁለት ደቂቃ በቅጡ የሚረባ ነገር ሳይናገር ላብ በላብ ሆኖ ወጥቶዋል፡፡ ከእንቅልፉ ድባብ ተቀስቅሶ በመናገሩ የተቸገረ ነው የሚመስለው፡፡ ኢህአዴግ የመጨሻውን ማጠቃለያ መስጠቱን ዘንግቶ ለኢህአዴግ ጥያቄም አቅርቧል፡፡ ለማነኛውም በማጭድ ምልክት ዘመናዊ የግብርና መሳሪያ በድጎማ ማቅረብ አማራጭ አድርጎ ያቀረበልን ኢድአን ከቁም ነገር የሚቆጠር አማራጭ ነው ብለን ልንወሰደው እንቸገራለን፡፡ እንኳን ሌሎች እንዲመርጧቸው ልንደግፋቸው አይደለም የራሳቸው “ከተመረጥን” የሚለው ድምፅ ለመመረጥ እንዳልተዘጋጁ የሚያሳጣ ነው፡፡

መድረክ ተወክሎ የገባው በአቶ ጥላሁን እንዳሻው እና በአቶ ሙላቱ ገመቹ በሚባሉ አባላት ሲሆን፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን በዋነኝነት ሊከራከረው የገባው ከላይ እንደገለፅኩት ከመድረክ ጋር ብቻ እንደሆነ ያስታውቅ ነበር፡፡ መድረክ በመጀመሪያ ሰድስት ደቂቃ አንዱን ደቂቃ ጊዜው ትንሽ ነው በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ጊዜ ያባከነ ሲሆን፤ በተጨማሪ መልስ በሌላቸው ህገመንግሰታዊ ድንጋጌዎችና ትርጉም ጊዜውን እንዳባከኑት ይሰማኛል፡፡ በእኔ ግምት በመሃል የተቆረጠ በሚመስል ሁኔታ አምሰት ደቂቃ የሚሞላ ሀሳብ አልሰማንም፡፡ ኢቲቪ ኢህአዴግን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ የቆረጠው ሃሳብ እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ መድረክ በቀጣዩ በነበረውን ዘጠኝ ደቂቃም ቢሆን ኢህአዴግ ላቀረበለት ጥያቄ መልስ በመስጠት፣ ለምሳሌ በሚል የአቶ ጥላሁን እንዳሻው ትውልድ አቅራቢያ ቦታዎች ላይ የሚገኙ የመሬት መፈናቀልና የመሰረተ ልማት እጥረትን በመዘርዘር ለክርክሩ የሚመጥን ነበር ለማለት የሚያስቸገር ሃሳብ ሲያቀርቡ ነበር፡፡ በ2002 አቶ ጥላሁን እንዳሻው በተመሳሳይ ርዕስ ተከራካሪ የነበሩ ሲሆን ይህን ልምድ ይዘው በተሻለ የመቅረብ እድሉ ቢኖራቸውም ሊጠቀሙበት አልቻሉም፡፡ ከመድረክ ክርክር ነጥብ የሚወሰድ ከሆነ በልማት ሰራተኛ ስም የተሰገሰጉት ካድሬዎች ጉዳይ ሲሆን ኢህአዴጎች ይህን ከሰራተኞቹ ጋር ለማጋጨት ሊጠቀሙበት የሞከሩ ቢሆንም በልማት ሰራተኛ ሰም በገጠር የሚንከራተቱት ሰራተኞች ይህን ተጨማሪ ያለፍላጎታቸው የሚሰጣቸው ሰራ እንደማይወዱት ለሚያውቅ የኢህአዴግ መንገድ የሚሳካ አይመስለኝም፡፡ በክርክሩ የመጨረሻ ተከራካሪ መሆን ያለውን ከፍተኛ የማጥቃት እድል በማያሰፈልግ ሁኔታ ከረዳታቸው ጋር የተካፈሉት አቶ ጥላሁን ረዳታቸውም ምንም አዲስ ነገር ሳይነግሩን ክርክሩም እንዲያበቃ አደርገውታል፡፡

በእኔ እምነት ኢህአዴግ አሁንም ቢሆን መንግሰት ሆኖ ያከናወናቸውን ስራዎች ይህን ማድረግ የማይችሉትን ተቃዋሚዎች መክሰሻ አድርጎ ለማቅረብ ሲሞክር ከመስማት የበለጠ አሳፋሪ ነገር የለም፡፡ ይህ ማለት ግን ተቃዋሚዎች በያዘው ስልጣን ሊያከናውን ያልቻለውን፣ በተለይ ደግሞ ባለፈው አምስት ዓመት በግብርና ዘርፍ አሳካዋለሁ ብሎ ያላሳካቸውን ነጥቦች አንሰተው ደካማ መሆኑን ማሳየት አይችሉም ማለት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አሁን የሚሞግተን የግብርና ፖሊሲና ስትራቴጂ፤

· ባለፉት 24 ዓመታት ይህችን ሀገር በምግብ እራሷን እንድትችል ባለማድረጉ የሚከሰሰበት ዋነኛ ነጥብ ነው፡፡ በሃያ አራት ዓመት አሁንም አዝማሚየ በሚባል ሁኔታ መሆናችን ተቀባይነት የለውም፤

· በኢትዮጵያ ሀገራችን በገጠር የሚኖረው ህዝብ ባለፉት 24 ዓመታት ከነበረበት 85 ከመቶ ወደ 83 በመቶ ብቻ ነው ዝቅ ሊል የቻለው፡፡ ይህ ደግሞ በአፍሪካ ደረጃ ከተሜነት 50 ከመቶ በላይ በደረሰበት ወቅት እጅግ አሳፋሪ ሲሆን፤ ይህን እንደ ነጥብ አንሰቶ የሚሞግት ያለመኖሩ ከዚያ ይልቅ የገጠሩ ህዝብ ወደ ከተማ እየፈለሰ ነው የሚል ቅሬታ የሚያሰሙ ተቃዋሚዎች መኖራቸው የሚያሳዝን ነው፤

· የከተሜነት ያለመስፋፋት፣ ዜጎች በገጠር ከመሬት ጋር ተጣብቀው እንዲኖሩ እያደረገ ያለው ደግሞ፤ ኢህአዴግ በውሸት ኤኮኖሚያዊ ምክንያት የሚለው ነገር ግን ፖለቲካው ምክንያት የሆነው መሬትን ህገመንግሰት ውስጥ መደንቀሩ ነው፤ ይህን ፖለቲካዊ የሆነ ጉዳይ ኤኮኖሚያዊ ነው ብለው ምንአልባት ከፓርቲው አቋም ውጭ የግብርና ሚኒሰትሩ ሃሳብ ሲሰነዝሩ የሚሞግታቸው አላገኙም፤

· ኢህአዴግ መሬት መሸጥ መለወጥ የሚለውን ሃሳብ ሲያነሳ መሬት የሚገዙ ጥቂት የሚላቸው ዜጎች መሬቱን የሚገዙት ምርት ለማምረትና ለማትረፍ በዚህም ሀገራችንን በምግብ እህል ራሰን ከመቻል አልፎ ኤክሰፖርት ለማድረግ መሆኑ ቀርቶ ለቀብራቸው መሬት የሚገዙ ያሰመስለዋል፡፡ መሬቱን ሸጦ የሚፈናቀል አርሶ አደር ደግሞ በሌሎች አገልግሎት ዘርፍ የማይገባ፣ ከመሬት ጋር ብቻ ተጣብቆ እንዲኖር የተፈረደበት ያሰመስልብናል፡፡
ባጠቃላይ በእኔ እምነት የ1997 የግብር እና የገጠር ልማት ስትራቴጂ ክርክር በድጋሚ ይቅረብልን ብዬ ማጠቃለል መርጫለሁ!!!

ቸር ይግጠመን!!!!!!!

Zehabesha.com

ትግላችን ሁለት ቀስት ያለዉ መሆን አለበት! የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ

10985866_1635084086704699_8526347471541260905_n

እንደምትመለከቱት አማራ ከቤንሻንጉል ሲፈናቀል የሚያሳይ ነዉ፡፡ ተፈናቀልን አግባብ አይደለም እያልን ስንጮህ እነ ሌንጮና ገብረ መድን ትግል ፌስ ቡክ አይደለም እንደኛ በረሃ ገብቶ ነዉ ሲሉ እነ ሌንጮ ደግሞ ነፍጠኛውን ቀብረነዋል ይህ ጅማሮ ነዉ ገና እንጠራርጋቸዋለን ይሉናል፡፡ የኞቹ ዘመዶች ደግሞ ለማበጣበጥ ነዉ ወንድሞቻችን ናቸዉ ይሉናል፡፡ እኛ ወንድሞቻችን አይደሉም መች አልን በወንድሞቻችን ተፈናቀልን ነዉ ያልነዉ በወንድም መፈናቀል ደግሞ ያሳምማል፡፡ ለነዚህ የአማራ መፈናቀል ጮቤ ለሚያስረግጣቸዉ የምላቸዉ ቢኖረኝ የሌሎችን ሳልወክል የኔና የኔን መሰል የትግል ስልት የሚከተለዉ በጣም ብዙ ነዉ፡፡

ይህም ልክ እንደናንተ ሁለት ቀስት ነዉ ያለን ለዛዉም ፌስ ቡክ ላይ ሳይሆን በራችሁ የሚደርስ ቀስት!!! መቸም የትግል ስልቱን ይነግረናል ብላችሁ ተስፋ እንደማታደርጉ እርግጠኛ ነኝ! ነገር ግን ትንሽ ፍንጭ ልስጣችሁ፡፡ ምን መሰላችሁ አሁን ስትለፈልፉ የሚሰማ ቃል አለ እሱም አማራን ነፍጠኛን ትምክተኛዉን ቀብረነዋል የቀረዉንም አንገቱን አስደፍተናል፡፡ ትላላችሁ! ታዲያ ለማን ነዉ በየጊዜዉ ስሙን እያነሳችሁ የምትዘልፉት? ነዉ ከቀበራችሁበት አውጥታችሁ ልታሰሙት ነዉ? ለምን በሌለ ነገር ላይ ትጮሃላችሁ? እኔ ግን በጊዜ ከድርጊታችሁ ታቅባችሁ ለአገር አንድነት በሚበጅ መስመር ብትጎዙ ጥሩ ነዉ!!! በዚህ መንገድ ከቀጠላችሁ አድፍጦ ካለዉ ሁለት ቀስት አታመልጡም! እስከአሁን ብዙ ደማውቃቸዉ ሰዎች በተቃዉሞ ጎራ ብቻ ይታገሉ ነበር፡፡

ሌሎቹ ግን በዘረኝነት ባህሪያቸዉ ምክኒያት በሁለት ቀስት እየመቱን ነበር አንደኛው በላቸዉ የተቃዉሞ ጎራ የሚመጣ ሲሆን ሁለተኛዉ በመንግስት ስር ባለዉ መዋቅራቸዉ የሚመጣ ነዉ፡፡ እኛ ግን ከቤተሰቦቻችን በወረስነዉ ከዘረኝነት የፀዳ አመለካከት የተነሳ ቀስታችን አንድ ሲሆን እሱንም ወደብዙ አቅጣጫ ለማዞር ስንሞክር እየተጎዳንበት የመጣ ነዉ፡፡ አሁን ግን መስመር ቀይረናል ይህም እኛ የመንግስትን መዋቅር መጠቀም ጀምረናል፡፡ ለዚህም በሳልና ነገሮችን መለወጥ የሚችሉ ሰዎችን አስገብተናል፡፡ ስለዚህ መቆናጠጥ የምንችለዉ እንደዚህ ቀደሙ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አይደለም፡፡ በሁለት ነዉ! ይህ መዋቅር የለለበት አደረጃጀት የለም፡፡ ስለዚህ እንደዉም እናንተ እያወራችሁ እኛ የምንሰራበት ይሆናል ሁሉም አማራና የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈልግ መቀላቀል ነዉ፡፡ ስለዚህ ይህን ሁለት ቀስት መያዝ ለአማራ አማራጭ የሌለው ወቅቱን ያገናዘበ መፍትሔ ነዉ!!!

satenaw

የመረጃ ግብአት … በ5 ኛው ቀን ዘመቻ … የዘመቻ ” ወሳኙ ማዕበል ” አበይት ክንውኖች ዳሰሳ !ነቢዩ ሲራክ

* በሳውዲ የሚመራው የአረብ ሀገራት ህብረት ጦር የአየር ድብደባው ተጠናክሮ ቀጥሏል

* የየመን ባህርና አየር በሳውዲ አየር ሃይል ቁጥጥር ስር መዋላቸው ሲጠቆም ኢራንን ጨምሮ ለሁቲ አማጽያን ስንቅና ትጥቅ ማቀበያ በሮች መዘጋጋታቸውን የህብረቱ ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ አስታውቀዋል

* ከዘመቻው መምሪያ ጋር በተደረገ ቅንጅት የመን የገባው የፖኪስታን ጃምቦ ጀት 482 ፖኪስታናውያንን ከመንን አውጥቷል

* በጦርነቱ መካከል ያሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል ። በጥብቅ በታጠረው የሳውዲ ድንበር ወዲህና ወዲያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጦረነቱ እሳት መካከል በአጣብቂኝ ውስጥ ስለ መሆናቸው በግል የሚደርሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ

* በሳውዲ የመን ድንበር በባህር ጠረፎች ከፍተኛ የእግረኛና የባህር ኃይል ሰራዊትና የሜካናይዝድ ጦር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተመልክቷል

* በሳውዲ ድንበር ፣ በጀዛን እና በኤደን የባህር ወሽመጥ በባብ አልመንደብ አካባቢ የባህር ኃይልና የምድር ጦር ዝግጅቱን አስመልክቶ የተጠየቁት ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ ” በጦርነት ውስጥ እያለህ ይህ መሰሉ ዝግጅት የተለመደ ነው! ” ብለው መልሰዋል

* የምድር ጦር በሚመለከት በአንድ ታዋቂ የአሜሪካ ቴሌቪዠን የተጠየቁት በአሜሪካ የሳውዲ አምባሳደር አድል አል ጃብሪ በሳውዲ በኩል የምድር ጦር ለማዝመት እስካሁን ውሳኔ አለመደረሱን ጠቁመዋል

* የየመን ፕሬ አብድልረብ መንሱር በሳውዲ ስደት ላይ ሆነው በኢምሬት የየመን አንባሳደር አድርገዋቸው የነበሩትን አህመድ አሊ አብደላ ሳላህን ከስልጣን አባረሩ ። አህመድ አሊ በአባታቸው የአገዛዝ ዘመን ከፍተኛ የጦር መኮነን ነበሩ ። በኢምሬት አምባሳደር የተሰጣቸው በፕሬ አብድልረቡ ሲሆን ከነበሩበት ቁልፍ የጦር መሪነት ተጽዕኖ ፈጣሪ ቦታ ለማሸሸት ታስቦ ነበር ። አህመድ የፕሬ አብድልረቡ ወዳጅና የአሁን ሁነኛ ባላንጣቸው የሆኑት የቀድሞው ፕሬ የአሊ አብደላ ሳላህ የብኸር ልጅ ናቸው ፣ ከቅርብ ወራት ጀምሮ አህመድ ከአባታቸው ጋር ሆነው ፕሬ አብድልረቡን ለማውረድ የሁቲ አማጽያንን በመደገፍ መሪውን አሽቀንጥረው የመንን ለዛሬ መከራ እንደዳረጓት ይወነጀላሉ

* ባሳለፍነው ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2007 በግብጽ ሻርማ ሸክ የተደረገው የአረብ ሊግ ስብሰባና ውጤቱ የአረብ መገናኛ ብዙሀን በሰፊው እየተዘገበበት ይገኛል

* እዚህም እዚያም የቃላት ጦርነቱ ተጋግሟል …
===========================

* የሁቲ አማጽያን የሳውዲ መራሹን የጦር አውሮፕላን ጣልን ይላሉ ፣ የሳውዲ መራሹን ጦር ቃል አቀባይ በአንጻሩ የሁቲ አማጽያን ከዚያ የሚያደርሰውን አቅም በመጀመሪያ ቀን የአየር ድብደባ ብቻ አክሽፈነዋል በማለት በተዋጊ ጀቶቻቸው ላይ ጥቃት አለመድረሱን በመግለጫቸው በአጽንኦት ተናግረዋል

* በየመን የሁቲ አማጽያንን በሳውዲ መራሽነት የተጀመረው የአየር ድብደባ እንዲያቆም ከሚፈልጉት ሀገራት መካከል ቀዳሚ የሆነችው የራሻው ፕሬ ፑቲን ለአረብ ሊግ ስብሰባ በላኩት ደብዳቤ አረብ ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ የወደፊት ሰላምን ለማምጣት ከጦርነት ውጭ ያለውን የሰላማዊ መንገድ አማራጭ ይጠቀሙ ዘንድ መክረዋል

* የሳውዲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዑድ አል ፈይሰል ግን የፑቲንን መልዕክቱን ተቃውመዋል ። በኢራን የሚደገፈውን በሶርያ የአሳድን መንግስት የገዛ ዜጎቹን እየፈጀ በራሽያ ስንቅና ትጥቅ ይደገፋል ሲሉ የራሻን ተቃርኖ መንገድ ላይ የሰላ ሂስ ያቀረቡት ልዑሉ የራሻው ፕሬ ፑቲን ከአረብ ሀገራት ጋር የቆየ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል ንግግራቸውን አርመው አቋማቸውን ይፈትሹ ዘንድ አሳስበዋል።

* ከኢራን እርዳታ በማግኘት የሚታሙት የሽምቅ ተዋጊው የሀማስ መሪዎች ሳውዲን ጭምሮ የ10 አረብ ሀገራትን ዘመቻ ሲደግፉ የኢራንና የሶርያ መንግስት ደጋፊ የሊባኖሱ የሂዝቦላህ መሪ ሸህ ሀሰን ነስርአላህ የሳውዲ መራሹን ዘመቻ በማውገዝ በተለይ በሳውዲ መንግስትን መወረፋቸው የሳውዲን መንግስት አስቆጥቷል

* በሊባኖስ የሳውዲ አምባሳደር አሊ አዎድ አሲሪ ጭብጥ የሌለው ሀሰት ነው ያሉት የሂዝቦላሁ ሀሰን ነስርአላህ ንግግር ሂዝቦላህ የሚወክለውን የኢራን አቋም የተንጸባረቀበት አሳሳች መልዕክት እንደሆነ ለአረብ ኒውስ አስረድተዋል

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ

ኢትዮጵያ የፈረመችው ስምምነት ያስነሳቸው ጥያቄዎች Questions raised over Ethiopia’s agreement with Egypt and Sudan about Nile

 በ  

‹‹ባሳየነው በጎ የፖለቲካ ፍላጎት ዛሬ እዚህ ላይ ደርሰናል፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የመርህ መገለጫዎችን (Declaration of Principles) በሱዳን ከተማ ካርቱም ላይ ለመፈራረም ችለናል፡፡

የቀረን ነገር ቢኖር በየአገሮቻችን ሕገ መንግሥታዊ የሕግ አወጣጥ ሥርዓት አልፎ ወደ አፈጻጸም እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ምክንያቱም የስምምነታችን ፋይዳ ያለው በቃላቱ ላይ አይደለም፡፡ ፋይዳው ያለው ስምምነታችንን በቀናነትና በታማኝነት ወደ ተግባር ስንቀይር ነው፡፡›› ከላይ የተገለጸውን ንግግር ያደረጉት ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ናቸው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት በኢትዮጵያ ሕግ አውጪ አካል ለሆነው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ጉባዔ ነው፡፡ 

ፕሬዚዳንት አልሲሲ በኢትዮጵያ ፓርላማ ያደረጉት ንግግር ማጠንጠኛ ከላይ የተቀጠው ሐሳብ ብቻ አይደለም፡፡ በሁለቱ አገሮች ሕዝቦች ቤተሰባዊ ግንኙነትና የጋራ ህልም ለሁለቱ አገሮች ሕዝቦችና መጪ ትውልድ ሲባል አዲስ ታሪክ አሁን መጀመር እንዳለበት ጠቅሰዋል፡፡ 

‹‹ከመጣንበት አስቸጋሪ ሁኔታም እንድንማር እጠይቃችኋለሁ፡፡ የቀድሞ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ለመቅረፍ የምናደርገው ስምምነት ዛሬያችንን ወይም የወደፊት ምኞታችንን እንዲያጨናግፍብን መፍቀድ የለብንም፡፡ አዎ መተማመንን መገንባት አለብን፡፡ የጥርጣሬ ክፍተቶች እንዳይሰፉና ሸለቆ ሆነው ጨርሶውኑ እንዳይለያየን መጠንቀቅ አለብን፤›› ብለዋል፡፡ 

ፕሬዚዳንት አልሲሲ የግብፅን አብዮት አረጋግተው በሕዝባዊ ምርጫ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ፣ በአጀንዳቸው ካመጧቸው የግብፅ የውጭ ፖለቲካ አንኳር ጉዳዮች መካከል ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ 

ፕሬዚዳንት አልሲሲ ወደ ሥልጣን ከመጡ በአጭር ጊዜ ውስጥም በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ከተማ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር በተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጐን ለጐን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር በህዳሴው ግድብና በዓባይ ወንዝ ውኃ አጠቃቀም ዙሪያ ተወያይተው የመግባቢያ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ 

ፕሬዚዳንት አልሲሲ የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ በዋናነት እየተጉበት ያለው ጉዳይ፣ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የግብፅን የውኃ ፍላጎት እንደማትጎዳ በተለያዩ ባለሥልጣናቷ የምታስነግረውን በሰነድ እንዲሰፍር ማድረግ ነው፡፡ 

በሰኔ ወር 2006 ዓ.ም. በማላቦ ከተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት በኋላም የግብፅ ፕሬዚዳንትና የካቢኔ አባሎቻቸው ይህንኑ የግብፅን ታሪካዊ የውኃ መጠን ለማስከበር የሰነድ ዝግጅት ውስጥ እንደገቡ፣ ይህንኑ ሰነድም ኢትዮጵያና ሱዳን እንዲመለከቱትና እንዲመክሩበት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ 

የዚህ የመርህ መግለጫ ሰነድ በግብፅ በኩል ተዘጋጅቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የተላከው ፕሬዚዳንት አልሲሲና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በማላቦ በሰኔ ወር ከተገናኙ በኋላ በነሐሴ ወር መሆኑን፣ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

የመጀመሪያው ረቂቅ በተለየ ፎርማት ማለትም በአዋጅ መልክ የተቀረፀ በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ በኩል ቅርፁንና ይዘቱን በማሻሻል የመርህ መገለጫ እንዲሆን መደረጉን ቃል አቀባዩ ያስረዳሉ፡፡ 

ሰነዱ ይህንን ቅርፅ ከያዘ በኋላ በየካቲት እና በመጋቢት 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያና በግብፅ እንዲሁም ሱዳንን ጨምሮ ጥልቅ ውይይት ተደርጎ፣ ‹‹የመርህ መግለጫ ወይም ዴክላሬሽን ኦፍ ፕረንሲፕልስ›› ሆኖ ስምምነት መደረሱን ያስረዳሉ፡፡ 

የመርህ መግለጫው ውስጣዊ ይዘት

የመርህ መግለጫው አሥር አንቀጾችን የያዘ ባለ አምስት ገጽ ሰነድ ነው፡፡ የሰነዱ መግቢያ እንደሚያስረዳው ሦስቱ አገሮች ማለትም ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ሦስቱም አገሮች እየጨመረ ያለውን የውኃ ፍላጎታቸውንና ለዚህም የዓባይ ወንዝ ፋይዳን ከግምት በማስገባት የደረሱበት መግባቢያ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ 

የሰነዱ የመጀመሪያ አንቀጽ ስለ ትብብር መርህ የሚያትት ሲሆን፣ ሦስቱ አገሮች በጋራ መግባባት፣ የጋራ ተጠቃሚነትን በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ባረጋገጠ መንገድ መተባበር፣ የላይኛው ተፋሰስና የታችኛው ተፋሰስ አገሮችን የውኃ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት መተባበርን ስለመፍጠር ያትታል፡፡ 

የመርህ መግለጫው አንቀጽ ሁለት ቀጣይነት ስላለው ልማትና አካባቢያዊ ትስስር ይመለከታል፡፡ በውስጡም ‹‹የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሠረታዊ ዓላማና ጥቅም የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት፣ ለኢኮኖሚ ልማት አስተዋፅኦ ለማድረግ፣ ድንበር ዘለል ትብብርንና አስተማማኝ በሆነ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል የአካባቢው አገሮችን ማስተሳሰር›› መሆኑን አስቀምጧል፡፡ 

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኞችና ከህዳሴ ግድብ ፖለቲካ ጋር በተገናኘ በጥልቀት የሚያውቁ በስምምነቱ ከተጠቀሱት ዝርዝር ነጥቦች መካከል ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ባፀደቀው ዓለም አቀፍ የውኃ ሕግና ሌሎች ዓለም አቀፋዊ ልማዳዊ ሕጎች፣ እንዲሁም ከግብፅና ከሱዳን በስተቀር ሌሎቹ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች የተፈራረሙበትና ሦስት አገሮች በፓርላማቸው ባፀደቁት የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ውስጥ የተገለጹ ናቸው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ሰሞኑን የተፈራረሙት የመርህ መግለጫ ሰነድ ባይኖርም በሰነዱ የተገለጹት አብዛኞቹ ነጥቦች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው አሠራሮች በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ የምትገዛባቸው መሆኑን ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ፡፡ 

ይሁን እንጂ የመርህ መግለጫው አንቀጽ ሁለት በቀጥታ የህዳሴውን ግድብ የሚመለከት ለሦስቱም አገሮች ወሳኝ ነጥብ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግና አስተዳደር ኮሌጅ በማስተማር ላይ የሚገኙትና በዓባይ ወንዝ ፖለቲካ ተመራማሪ የሆኑትና እንዲሁም በዚሁ ዙሪያ “International Water Cources Law in the Nile Basin River: Three States at a Crossroads” የሚል መጽሐፍ እ.ኤ.አ. በ2013 ያሳተሙት ዶ/ር ታደሰ ካሳ፣ ኢትዮጵያ ሰሞኑን በፈረመችው ስምምነት 74 ቢሊዮን ሜትሪክ ኪዩብ የተንጣለለ ውኃዋን የምግብ እህል ዋስትናዋን ለማረጋገጥ እንዳትጠቀምበት ሊያደርጋት ይችላል ሲሉ ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ 

ይህንን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ሕዝቦቿ ከ74 ቢሊዮን ሜትሪክ ኪዩብ ውኃ ላይ የመጠጥ ፍላጎታቸውን ለማርካት እንዳይችሉ፣ በህዳሴው ግድብ አካባቢ የሚቋቋሙ ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች የውኃ ፍላጎታቸውን ከዚህ የውኃ ምንጭ እንዳያሟሉ በራሷ ፈቃድ በገባችው ስምምነት እያገደች ነው ሲሉ ይከራከራሉ፡፡

ግብፆች የታላቁ ህዳሴ ግድብ የደረሰበት ደረጃ የሚቀለበስ አለመሆኑን በመረዳት ላለፉት ጊዜያት በታታሪነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩት፣ ከግድቡ መጠናቀቅ በኋላ የግድቡ ውጤት የሚያመጣውን ተፅዕኖ ከወዲሁ ለማስተካከል እንደሆነ ዶ/ር ታደሰ ይናገራሉ፡፡ 

ይህ ጥረታቸውም ሰሞኑን ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በተፈራረሙት ‹‹የመርህ መግለጫ›› ሰነድ አንቀጽ ሁለት ላይ መቀመጡን ያስረዳሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የህዳሴው ግድብ የሚያጠራቅመው ውኃ ወደፊት ምን ዓይነት ጥቅም ሊሰጥ ይችላል የሚለውን በአግባቡ ማስረዳት፣ እንዲሁም ውኃውን ለማንኛውም ጥቅም የማዋል ሉዓላዊ መብቷ መሆኑን አስረግጦ ማስገንዘብ ሲገባ ግድቡ የሚያጠራቅመው ውኃ የሚውለው ለኃይል ማመንጫ ብቻ ነው በማለት መስማማት የተደረገው ዘመቻ ውጤት መሆኑንም ያስገነዝባሉ፡፡ 

በውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበርና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት የቀድሞ ዳይሬክተር፣ በአሁኑ ወቅት የምሥራቅ ዓባይ ተፋሰስ የቴክኒክ ቢሮ ዋና ዳይሬክተርና ኢትዮጵያን በመወከል በህዳሴው ግድብ ተደራዳሪ የሆኑት አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ ግን ከላይ በተቀመጠው ሐሳብ አይስማሙም፡፡ 

‹‹እኔም ሆንኩ ሌሎች የመንግሥት ኃላፊዎች ግድቡ የሚያጠራቅመው ውኃ ለመስኖ አይውልም የምንለው፡፡ መብታችንን አሳልፈን ለመስጠት ሳይሆን በትክክልም ለግብርና አመቺ የሆነ መሬት ባለመኖሩ ነው፤›› ይላሉ፡፡ 

አቶ ፈቅአህመድ ይህንን ይበሉ እንጂ፣ በቤንሻንጉል ክልል ለእርሻ ምቹ የሆኑ አካባቢዎች መኖራቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ለአብነት ያህል በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን ብቻ 345 ሺሕ ሔክታር ማለትም አዲስ አበባን ስድስት ጊዜ የሚበልጥ መሬት መኖሩን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህ ለግብርና ምቹ የሆነ መሬት ከህዳሴ ግድብ ውኃ መጠቀም ሳያስፈልገው ከሌሎች የውኃ ምንጮች መጠቀም ቢቻል እንኳ፣ ሉዓላዊ መብትን አሳልፎ በመስጠት የወደፊት ትውልድን የመጠቀም መብት መገደብ አይገባም የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡ አሉ፡፡ 

ዶ/ር ታደሰ በበኩላቸው የመንግሥት ኃላፊዎች እንደሚሉት አካባቢው ለእርሻ ምቹ ባይሆን እንኳን፣ ግብፅ ብዙ ማይሎችን አቋርጣ በፓምፕ ለግብርና ልማት እንደምታውል ሁሉ ኢትዮጵያም ይህንኑ ማድረግ ትችላለች ይላሉ፡፡ 

ከዚህ ቀደም ከባለሥልጣን ተሰምቶ የማይታወቀውን አሁን መናገር የቻሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ናቸው፡፡ ስምምነቱ ከተፈረመና ፕሬዚዳንት አልሲሲ የአዲስ አበባ ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ለፋና ብሮድካስቲንግ በሰጡት አስተያየት፣ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ግድቡን ለግብርና ልማት እንዳታውል የሚከለክላት አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

እንደሳቸው አባባል ከሆነ ኢትዮጵያ ውኃውን መሳቢያ ቱቦዎችን በመጠቀም መለስተኛ የእርሻ ልማቶችን ማከናወን፣ እንዲሁም ለቱሪዝምና ለዓሣ ዕርባታ ማከናወን እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ 

በድርድሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩት አቶ ፈቅአህመድ በበኩላቸው፣ በግብፅ በኩል ቀርቦ የነበረው ረቂቅ ሰነድ የህዳሴው ግድብ የሚይዘው ውኃ ለግብርና ልማት አይውልም ይል እንደነበር አስታውሰው፣ ይህ ግን በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት እንደሌለው ተገልጾ የኢኮኖሚ ልማት በሚል እንዲተካ መደረጉን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

‹‹በመሆኑም ኃይል ከማመንጨት ውጪ ለመረጥነው ዓላማ ለመጠቀም አንቀጹ የሚገድብ ነገር የለውም፤›› ብለዋል፡፡ የመርህ መግለጫ ሰነዱ በአንቀጽ ሁለት ካስቀመጠው አወዛጋቢ ሐሳብ ውጪ ያሉት ሌሎች ነጥቦች ይህንኑ ማዕከላዊ ሐሳብ ለመደገፍ የገቡ እንጂ፣ በአብዛኛው የኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ ፍላጎት የሚጋፉ አይደሉም በማለት ዶ/ር ታደሰ ይከራከራሉ፡፡ 

ለዚህ የሚሰጡት ምክንያትም ሌሎቹ አንቀጾች በመርህ መግለጫው ላይ ባይሰፍሩም፣ በሌሎች ዓለም አቀፍ ሕጎች፣ በዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA) ውስጥ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ልማዳዊ ሕጎች (International Customary Laws) ኢትዮጵያ የምትገደድባቸው ናቸው ይላሉ፡፡ 

ይሁን እንጂ የመርህ መግለጫ ሰነዱ አንቀጽ አምስት ላይ የተቀመጠው ሐሳብ ኢትዮጵያን በእጅጉ የሚጠቅም ድንቅ አንቀጽ ነው ብለዋል፡፡ ይህ አንቀጽ በአሁኑ ወቅት ሦስቱ አገሮች የውጭ አማካሪ በመቅጠር ኩባንያው በጥናቱ የሚደርስበት ግኝት ተመልሶ ለሦስቱ አገሮች የቴክኒክ ኮሚቴ እንዲቀርብና እነሱ ከተቀበሉት ብቻ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሚገልጽ ነው፡፡ 

በመጀመሪያ በግብፅ በኩል በዚህ አንቀጽ ላይ ሰፍሮ የነበረው ዓረፍተ ነገር የሚቀጠረው ኩባንያ የሚያደርገውን ጥናት ተንተርሶ የሚሰጠው ምክረ ሐሳብ በቀጥታ ተቀባይነት እንደሚኖረው የሚገልጽ እንደነበርና እንዲስተካከል መደረጉን አቶ ፈቅአህመድ ያስረዳሉ፡፡

በመሆኑም በዚህ ረገድ ሊቀርብ የሚችልን የግድቡ የውኃ የመያዝ አቅምና ከፍታ የመሳሰሉትን የግብፅ ጥያቄዎችን በሦስቱ አገሮች የቴክኒክ ኮሚቴ መመለስ እንደሚቻል አቶ ፈቅአህመድ ገልጸዋል፡፡ 

የመርህ መግለጫ ሰነዱ ሕጋዊነት

አገሮች በመረጧቸው ጉዳዮች ላይ የሚያደርጓቸው ስምምነቶች የተለያዩ የሕግ ደረጃዎችን እንደሚይዙ ይታወቃል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1996 የወጣው የቪየና ኮንቬንሽን አገሮች እርስ በርሳቸው የሚያደርጓቸውን ስምምነቶች የሚገዛ ነው፡፡ በዚህ የቪዬና ኮንቬንሽን መሠረት የተለያዩ ሕጋዊ ተቀባይነት የሚኖራቸው ስምምነቶች መካከል ‹‹ትሪቲ፣ ፕሮቶኮል፣ አክት፣ ፓክት እንዲሁም ኮቬናንት›› ጥቂቶቹ መሆናቸውን ዶ/ር ታደሰ ያስረዳሉ፡፡ 

የመርህ መግለጫ ሰነዱ የሚሰጠው ትርጓሜ የፖሊሲ መልዕክት ለማስተላለፍ ቢመስልም፣ ሦስቱ አገሮች ይህንን ሰነድ ለማዘጋጀት ያለፉባቸው ድርድሮችና ይዘቶቻቸው የሦስቱ አገሮች ፍላጎት ከታከለበት አስገዳጅ ሕግ መሆን እንደሚችል ይከራከራሉ፡፡ 

አቶ ፈቅአህመድ በበኩላቸው፣ በመጀመሪያ በግብፅ በኩል የቀረበው ረቂቅ ሰነድ በሦስቱም አገሮች ሕግ አውጪ አካል እንዲፀድቅ ሐሳብ የሚያቀርብ ቢሆንም ይህ አንቀጽ እንዲሰረዝ መደረጉን ይገልጻሉ፡፡ 

ይሁን እንጂ በግብፅ በኩል አሁንም ፍላጎት መኖሩን አቶ ፈቅአህመድ ይናገራሉ፡፡ አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የፖለቲካ ተንታኝ በበኩላቸው፣ ስምምነት የተደረሰበት ሰነድ የፖለቲካ እንጂ ሕጋዊ ግዴታን የሚጥል አይደለም ሲሉ አስተያየታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

ሰነዱ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው በሦስቱ አገሮች ሕግ አውጪ አካል ሰነዱ እንዲፀድቅ የሚል አንቀጽ በስምምነቱ ባለመኖሩ፣ እንዲሁም በሰነዱ ላይ ከተገለጹት አንቀጾች መካከል አንቀጽ ዘጠኝ ‹‹ሦስቱ አገሮች የሚተባበሩት በእኩል የሉዓላዊነት መርህ ነው›› የሚል በመሆኑ አስገዳጅ ሊሆን አይችልም ብለዋል፡፡ 

በግብፅ በኩል ይህ የመርህ መገለጫ ሰነድ ሕጋዊ ግዴታን የሚጥል እንዲሆን ፅኑ ፍላጎት መኖሩን ፕሬዚዳንት አልሲሲ ለኢትዮጵያ ፓርላማ ካደረጉት ንግግር፣ ወይም ሰነዱ ፀድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ያላቸውን ፍላጎት ለፓርላማው አባላት በመግለጻቸው ፍላጎታቸውን በግልጽ መገንዘብ ይቻላል፡፡ 

ፕሬዚዳንት አልሲሲ በዓረብኛ ያደረጉትን ንግግር ብቁ ባልሆነ ትርጉም ያዳመጠው ፓርላማው በደመቀ ጭብጨባ ተቀብሎ ቢሸኛቸውም፣ ሰነዱን እንዲያፀድቅ ይቀርብለት ይሆን? ቢሆንስ ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ የሚጠራቀመውን ውኃ ለፈለገችው ዓላማ የማዋል ሉዓላዊ መብቷን ያስከብራል? የሚለው ያልተመለሰ ጥያቄ ነው፡፡ (ሚኪያስ ሰብስቤ ለዚህ ዘገባ አስተዋጽኦ አድርጓል)

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቅስቀሳ መልዕክታችን ላይ የቅድሚያ ምርመራ እየተደረገ ነው ሲሉ ከሰሱ

oposition parties

-ኢዴፓ ድርጊቱ ካልቆመ ራሴን ከምርጫ አገላለሁ አለ

በመጪው ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚደረገው ጠቅላላ ምርጫ ተሳታፊ የሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በምርጫ ቅስቀሳ መልዕክታቸው ላይ የቅድሚያ ምርመራ (ሳንሱር) እየተደረገ ነው ሲሉ ከሰሱ፡፡

ኢዴፓ ቅድመ ምርመራው ከተደገመ ራሴን ከምርጫ አገላለሁ ብሏል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እስከ ግንቦት 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚዘልቀው የምርጫ ቅስቀሳና ዘመቻ የጊዜ ሰሌዳ የተለያዩ መልዕክቶቻቸውን በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚዲያ ተቋማት ሕገ መንግሥታዊ ከለላውን በመጣስ የቅድመ ምርመራ በማድረግ መልዕክቶቻችንን አናስተላልፍም አሉን በማለት ፓርቲዎቹ ቅሬታ እያቀረቡ ነው፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 29(3) (ሀ) ላይ የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ባወጣው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ ቅስቀሳዎቹ እንዳይተላለፉ በመደረጉ፣ በምርጫ ተሳትፎው ላይ ትልቅ ተግዳሮት እንደፈጠረበት ገልጿል፡፡

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትና በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) እንዳይተላለፍ የተከለከለው የቅስቀሳ ፕሮግራም ይዘት ሕግን የተፃረረ አለመሆኑንም አስምሮበታል፡፡ የሚዲያ ተቋማቱ ድርጊት ግን ሕግን የሚፃረርና በሕገ መንግሥቱ የተከለከለውን የቅድሚያ ምርመራ ያለመደረግ መብት የሚጥስ ሆኖ እንዳገኘው ፓርቲው አስገንዝቧል፡፡

‹‹በዘንድሮው ምርጫ የመወዳደሪያ ሜዳው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጠበበ መምጣቱን የሚያሳይ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል፤›› ሲል ያሰፈረው የኢዴፓ መግለጫ፣ መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ለፋናና ለኢብኮ የላከው የቅስቀሳ መልዕክት እንዲስተካከል የቀረበው ጥያቄ አሳማኝ ምክንያት እንዳላካተተ አመልክቷል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አክሲዮን ማኅበር እንዲሁም ኢብኮ ለኢዴፓ በጻፉት ደብዳቤ፣ ‹‹በአገሪቱ አሉ የሚባሉ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ሁሉ የኢሕአዴግ ሥልጣን መጠቀሚያና መጠበቂያ ብቻ እንዲሆኑ በማድረጉ፣ ተቋማቱ በገለልተኝነት እንዳይሠሩና ዓላማቸውን ለማሳካት የሚያስችል ነፃነት ብቻ ሳይሆን አቅምም እንዳይኖራቸው አድርጓል፤›› በማለት ኢዴፓ መልዕክት ለማስተላለፍ መሞከሩ ሕገ መንግሥቱን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅን፣ የምርጫ ሕጉን፣ የመገናኛ ብዙኃን ሕጉን፣ እንዲሁም የተቋማቸውን ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ሌሎች ሕጎችን የሚጥስ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ በተለይ በኢብኮ የምርጫ ዴስክ ሰብሳቢ በአቶ ሰለሞን ተስፋዬ መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ተፈርሞ የወጣው የኢብኮ ደብዳቤ፣ ‹‹ይህ መልዕክት በሕገ መንግሥቱ የተቋቋሙ የዴሞክራሲ ተቋማትን ሁሉ ህልውና የሚክድና ተግባራቸውን የሚያንቋሽሽ፣ ሕዝቡ በተቋማቱ ላይ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርግ መልዕክት በመሆኑና ሕገ መንግሥቱን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ሥነ ምግባር ሕጉን አንቀጽ 29(1) እንዲሁም የድርጅታችንን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ የሚፃረር ሆኖ አግኝተነዋል፤›› በማለት ገልጿል፡፡ የአዋጁ አንቀጽ 29(1) ማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ፣ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅንጅት፣ ግንባር፣ ጥምረት፣ ንቅናቄ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲ መሪ፣ ኃላፊ፣ ዕጩ፣ አባል፣ ወኪልና ተጠሪ የምርጫ ዘመቻውን ሰላም የሚያናጋ ወይም ግጭት የሚቆሰቁስ ወይም ስም የሚያጠፋ ወይም አመፅ የሚጋብዝ ወይም ሥጋት የሚፈጥር ንግግር ካደረገ የሥነ ምግባር ጥሰት እንደፈጸመ እንደሚቆጠር ይደነግጋል፡፡

ኢዴፓ በመግለጫው፣ ‹‹ለዴሞክራሲ ተቋማት ያለንን ተቆርቋሪነት ኢሕአዴግ በነፃነት እንዳይሠሩ እያደረጋቸው መሆኑን መግለጽና ተቋማቱ ለተቋቋሙለት ዓላማ ግብ መምታት ኢሕአዴግ እንቅፋት መሆኑን መግለጽን፣ እንዴት የተቋማቱን ስም ማጥፋት እንደሆነ ሊገባን አልቻለም፤›› ብሏል፡፡

ኢዴፓ ይህ የመብት ጥሰት የማይቆም ከሆነ ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮ ከምርጫ ተሳትፎው ራሱን ሊያገል እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ የኢዴፓ የጥናትና ምርምር ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ፣ ‹‹ሐሳቦቻችንን በነፃነት ካልገለጽን ተሳትፎአችን የይስሙላ ስለሚሆን ድርጊቶቹ የሚቀጥሉ ከሆነ በምርጫው መሳተፋችን ከማጀብ ስለማይለይ ራሳችንን ከምርጫው ልናገል እንችላለን፤›› በማለት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አቶ ዋሲሁን ፋናና ኢብኮ አላስተናግድም ያሉት ጽሑፍ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መስተናገዱ ከክልከላው ጀርባ የግለሰቦች ፍላጎት ይኖር ይሆን እንዴ ብለው እንዲጠራጠሩ እንዳደረጋቸውም አመልክተዋል፡፡ ጉዳያቸውን ለፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አቅርበው በችግሩ ላይ ስምምነት መፈጠሩን ግን እንደ ጥሩ ምልክት ወስደውታል፡፡

በተመሳሳይ ኢብኮንና ፋናን በቅድሚያ ምርመራ ከከሰሱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ሰማያዊና መድረክም ይገኛሉ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ እስካሁን ፓርቲው ስምንት የተለያዩ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶች እንደተሰረዘበት ገልጸዋል፡፡ ፓርቲያቸው ሕገ መንግሥቱ በግልጽ ባሰፈረው የቅድሚያ ምርመራ ክልከላ ላይ እንደማይደራደር ያስታወቁት አቶ ዮናታን እንደ ኢብኮ፣ አዲስ ቲቪና ኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ ያሉ ተቋማት መልዕክቶቹን እንዲያስተካክሉ መጠየቃቸው ሕገወጥ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ይሁንና በጋዜጦች ላይ ግን የከፋ ችግር እስካሁን እንዳልገጠማቸው ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ መጋቢት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢብኮ እንዲተላለፍ የላከው የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት የጎሳ ፌዴራሊዝም ለግጭት መንስዔ ነው ማለቱ፣ አንዱን ብሔር ከሌላ ብሔር የሚያጋጭ ነው በሚል ውድቅ እንደተደረገበት መግለጹ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹የሕወሓት/ኢሕአዴግ ሥርዓት/መንግሥት›› የሚለውን አጠራር እንዲያስተካክል ጥያቄ እንደቀረበለት ገልጿል፡፡ ከዚህ አስቀድሞ ኢሕአዴግ ‹‹ፖሊስን፣ ሚዲያውን፣ መከላከያ ሠራዊቱንና ደኅንነቱን ሰማያዊና ሌሎች ፓርቲዎችን ለማጥፋት ሲጠቀምባቸው ቆይቷል››፣ ‹‹ምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤትና ሌሎችም ተቋማት ሕግ አክብረው አይሠሩም››፣ የሚሉትን ጨምሮ ሌሎች መልዕክቶች የአገሪቱን ሕጎች የሚፃረሩ በመሆኑ እንደማያስተናግድ ኢብኮ ለሰማያዊ በጻፈው ደብዳቤ ገልጾ ነበር፡፡ በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ይዘቶች የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት ሊያመሩ የሚችሉና የሌላ ፓርቲን ስም የሚያጎድፉ በመሆናቸው፣ ለውጥ ካልተደረገ እንደማያስተናግድ ገልጾ ለሰማያዊ ፓርቲ ደብዳቤ ጽፏል፡፡

መድረክ በበኩሉ የተለያዩ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶቹ ላይ በተመሳሳይ የቅድሚያ ምርመራ እንደተደረገበት ይገልጻል፡፡ በተለይ ምርጫ ቦርድና የፍትሕ አካላት ነፃና ገለልተኛ አይደሉም በማለት ያቀረባቸው መልዕክቶች ውድቅ እንደተደረጉበት፣ የመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንደሻው ገልጸዋል፡፡

ኢብኮ፣ ፋናና አዲስ ኤፍ ኤም እነዚህ ተቋማትና የመንግሥት ሚዲያን ነፃነት አስመልክቶ መድረክ ያቀረበው ትችት እንዲወጣ መጠየቃቸውን ጠቅሰዋል፡፡ መድረክ የፖለቲካ እስረኞች እንዳይኖሩ ያደርጋል በማለት ያቀረበው አማራጭም አሁን የፖለቲካ እስረኛ እንዳለ የሚያመለክት ስለሆነ አናስተናግድም እንደተባሉ አመልክተዋል፡፡ የኦሮሚያ መገናኛ ብዙኃንም ገዥው ፓርቲን ያለመረጃ እየተቻችሁ ነው በሚል መልዕክታቸውን ሳያስተላልፉ እንደቀሩ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሥርዓቱን አትንኩ የሚል አዝማሚያ ነው ያለው፡፡ ሥርዓቱ ላይ የሚነካ ነገር ከሌለ የእኛ ጥቅም ምንድነው?›› ሲሉም አቶ ጥላሁን ጠይቀዋል፡፡

ኢዴፓ፣ ሰማያዊና መድረክን ጨምሮ በቅድሚያ ምርመራ መገናኛ ብዙኃኑን የሚከሱ ፓርቲዎች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቤቱታቸውን ማቅረባቸውንና ቦርዱ ምላሽ እንዳልሰጠም ተችተዋል፡፡ የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በንቲ፣ የኢዴፓን ቅሬታ ገና ያልተመለከቱት ቢሆንም በሰማያዊና በመድረክ ላይ በሕጉ መሠረት ማስተካከያ አድርጉ ማለት ቅድሚያ ምርመራ ተደረገ የሚያስብል እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣንና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲዎቹ ጋር ባደረጉት የጋራ ውይይት አሠራሮቹ ላይ ስምምነት ተደርጓል፡፡ የሁለቱ ፓርቲዎች ጉዳይ ከዚያ ያፈነገጠ ነው፡፡ መልዕክታችን ትክክል ስለሆነ ሕጉን አይፃረርም የሚል አቋም ወስደዋል፡፡ ነገር ግን የመገናኛ ብዙኃኑ ደግሞ ኃላፊነት አለባቸው፤›› ብለዋል፡፡

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፌስቡክ ይፋዊ ገጹ ላይ አንዳንድ ፓርቲዎች የተከለከሉ ይዘቶችን በምርጫ ቅስቀሳ እንደሚጠቀሙ የጠቀሰ ሲሆን፣ ከዚህም መካከል የምርጫ ቦርድን፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን፣ የፍርድ ቤቶችንና የፍትሕ አካላትን ገለልተኝነትና ነፃነት ማጣጣል፣ ብሔረሰብን ከብሔረሰብ የሚያጋጩ፣ አመፅ የሚቀሰቅሱ፣ ስም የሚያጠፉ እንደሚገኙበት ጠቅሷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝም ከመንግሥት ሚዲያ ተቋማት ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ጥቂት ፓርቲዎች ሕገወጥ የቅስቀሳ ይዘት ማምጣታቸውን ያቁሙ ብለዋል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሕግ ባለሙያ ግን በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠውን የቅድመ ምርመራ ክልከላን የሚፃረሩ ሕጎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ የሕጎቹ ሕገ መንግሥታዊነት ላይ ጥያቄ ሳያነሱ ሕገ መንግሥቱን ብቻ በመጥቀስ መከራከር፣ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የራሱ ችግሮች አሉት ብለዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

የአድዋ ዘማቾች – ዳንኤል ክብረት

daniel-kibret

የጉዞው መሥራቾች

ከዛሬ 119 ዓመት በፊት ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን በዓለም ታሪክ ያልተለመደ አዲስ ታሪክ ለመሥራትና ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር የማይደረስበት ከፍታ ላይ ለማስቀመጥ ሲሉ ከመላዋ ሀገሪቱ አንድ ሆነው ወጥተው፣ አንድ ሆነው ወደ አድዋ ዘምተው ነበር፡፡ ያኔ ብዙዎቹ የተጓዙት በእግራቸው ጋራ ሸንተረሩን፣ አረሁን ገደሉን እየተሻገሩ በፍጹም ኢትዮጵያዊ ወኔና ሀገራዊ ፍቅር ነበር፡፡ ያ አንድነትና የሀገር ፍቅር ስሜት ነበር ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችንን ሊደግሙት እንጂ ሊረሱት የማይገባ ታሪክ እንዲሠሩ ያደረጋቸው፡፡ትናንት(እሑድ መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓም) በጨጨሆ የባሕል ምግብ አዳራሽ በተደረገ አንድ መርሐ ግብር ተጋብዤ ተገኝቼ ነበር፡፡ ‹ጉዞ አድዋ› ይባላል መርሐ ግብሩ፡፡

ይህንን የአድዋ መንፈስና ዝና፣ ክብርና ላቅ ያለ ኢትዮጵያዊነት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ፤ አድዋ እንደ አንድ ተራ ሥነ ሥርዓት በምኒልክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን ከማስቀመጥና ‹አስቦ ከመዋል› የዘለለ ትውልዳዊ ፋይዳ እንዲኖረው ለማድረግ፤ አድዋ እንደ ባለሞያ ጠጅ በየጊዜው ከጥንስሱ እየተቆነጠረ በየትውልዱ እንዲጠጣ ለማስቻል፤ እንደ ሰራፕታ ዱቄት በየዘመናቱ ቡኾ ውስጥ እንደ እርሾ እየተጨመረ እንዲበላ ለማብቃት፣ አድዋ ላይ የታየው የላቀ ኢትዮጵያዊነት አንደ ሜሮን ቅብዐት ከትውልድ ትውልድ ሳይቋረጥ እየፈላ የሁሉ ማጥመቂያ እንዲሆን የተነሡ ወጣቶች ያዘጋጁት መርሐ ግብር ነበር፡፡ እንደ አድዋ ዘማቾች ወኔ እንጂ ሌላ ሀብት የሌላቸው ወጣቶች፡፡

እነዚህ ወጣቶች አንድ አስደማሚ ተግባር ጀምረዋል፡፡ በየዓመቱ የአድዋ በዓል ከመከበሩ ቀደም ብለው ከአዲስ አበባ በመነሣት በእግራቸው ወደ አድዋ መዝመት፡፡ አባቶቻቸውና እናቶቻቸው በእግራቸው የተጓዙትን መንገድ እነርሱም በእግራቸው መከተል፡፡ የቀድሞ የአድዋ ዘማቾችን ስሜት  እየተጋሩ፣ ታሪካቸውን እያጠኑ፣ በየደረሱበት ለሚያገኙት ሁሉ የአድዋን የላቀ ኢትዮጵያዊነት እየሰበኩ፣ የትውልድን ቃል ኪዳን ማደስ፡፡

ተጓዦቹ ከመልስ በኋላ

የዘንድሮ ተጓዦች ስድስት ናቸው፡፡ ከስድስቱ አንዷ ሴት ናት፡፡ ጽዮን ትባላለች፡፡ በጉዞው ስሟ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ፡፡ ከአንድ ሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግሯ አቆራርጣ እንደ እቴጌ ጣይቱ አድዋ ላይ ሰንደቋን ተክላለች፡፡ መድረኩ ላይ ወጥታ የእቴጌን ታሪክና የጉዞውን ትዝታ ስትተርክ የሆነ የሚንፎለፎል ትኩስ ወኔ ከውስጧ እየወጣ ይገርፈን ነበር፡፡ እናለቅሳለንም፣ እንገረማለንም፣ እናጨበጭባለንም፡፡ የማትነጥፍ ሀገር፡፡በድንኳን እያደሩ፣ ያገኙትን እየቀመሱ፣ ከአራዊት ጋር እየታገሉ፣ ከተራራና ገደል ጋር እየተገዳደሩ፣ እየወደቁ እየተነሡ፣ እየታመሙ እየተፈወሱ፣ እየደከሙ እየጀገኑ፣ እያዘገሙ እየፈጠኑ ከአንድ ሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግር ማቆራረጥ፡፡ አድዋ ላይ ተጉዘው የታሪክ ማርሽ በዘወሩ ጀግኖች ስም ራሳቸው እየሰየሙ፣ የመንፈስ ወራሽታቸን ማረጋገጥ፡፡

ከጉዞ አስተባባሪዎች አንዱ የሆነው መሐመድ ስለ ጉዞው ዓላማና ሂደት ሲገልጥ እርሱ ራሱ ከዐፄ ምኒሊክ ሠራዊት ጋር የዘመተ ነበር የሚመስለው፡፡ መቼም መሐመድ ስለ ኢትዮጵያ ሲያወራ መስማት በባለሞያ ካህን የተከሸነ ቅዳሴ እንደመስማት ያለ ነው፡፡ ያወጣዋል፣ ይተርከዋል፣ ያውም ከዕንባና ከስሜት ጋራ፡፡

እነዚህ ወጣቶች የዛሬ ዓመት በ2008 ዓም አንድ ታላቅ ታሪክ ሊሠሩ አስበዋል፡፡ የአድዋ አንድ መቶ ሃያኛ ዓመት ሲከበር አንድ መቶ ሃያ ተጓዦችን ይዞ ወደ አድዋ በእግር ለመዝመት፡፡ ወጣቶች ናቸው፡፡ ግን ልባቸው ሸምግሏል፤ ብዙ ሊስቧቸው የሚችሉ  ብልጭልጭ ነገሮች ነበሩ፤ ነገር ግን ሀገራዊውን ታሪክ መርጠዋል፡፡ ከሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግር አቆራርጠው፣ የሀገራችንን ባንዴራ ከፍ አድርገው ፣ በየደረሱበት አድዋ ላይ የተገለጠውን ያንን ሁላችንንም የሚያኮራ ኢትዮጵያዊነት እየተረኩ በእግራቸው ሊጓዙ ተነሥተዋል፡፡

ጽዮን – እንደ እቴጌ ጣይቱ

የጉዞው አስተባባሪ ያሬድ ሹመቴ

እንደ እኔ እንደ እኔ አንድ ትውልድ ታሪኩን ሲያነሣ፣ በማንነቱ ሲኮራ፣ ታሪክም ለመሥራት ሲቆርጥ መደገፍ ይገባል እላለሁ፡፡ ወጣቶች ከሥነ ምግባር ሲወጡ፣ ማንነታቸውንና ታሪካቸው ሲረሱ፣ ለሀገራዊ ነገሮችም የእኔነት ስሜት ሲያጡ እንደምንወቅሰውና እንደምናዝነው ሁሉ፤ በሀገር ፍቅር ስሜት ሲነሡና ታሪካችንን ከፍ አድርገው በአዲሱ ትውልድ አዲስ መንፈስ ውስጥ ሊጽፉት ሲተጉም አብረናቸው መሥራት ይገባናል፡፡ ታሪካችንና ማንነታችን እንደማይዘነጋ ማረጋገጥ የምንችለው ተተኪው ትውልድ የእኔ ነው ብሎ በራሱ መንገድ ሊገልጠው ሲሞክር ካየን ብቻ ነው፡፡

እናግዛቸው፣ አብረናቸውም እንቁም፤ የቻልን የጉዟቸውን ወጭ እንጋራ፣ ያልቻልን በሚደርሱበት ቦታ ሽሮ ሠርተን ውኃ ቀድተን በማስተናገድ የጥንት አያቶቻችን የአድዋ ዘማቾችን የሸኙበትን ታሪክ እንድገመው፡፡ በሚደርሱባቸው ቦታዎች ያሉ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ወጣቶቹ ከተጓዦቹ  ጋር ስለ ታሪካቸው እንዲወያዩ መርሐ ግብር ያዘጋጁ፡፡ የእምነት ተቋማት ደግሞ በሚደርሱባቸው ቦታዎች በመቀበል ለታሪካችንና ማንነታችን ያለንን የከበሬታ ሥፍራ እናሳይ፡፡ በየቦታው የምንገኝ ኢትዮጵያውያንም በየደረሱበት ቦታ እየተቀበልን ባንዴራውን ከፍ አድርገን በማሻገር የታሪክ ተረካቢነታችን እናረጋግጥ፡፡ አንድ መቶ ሃያኛውን የአድዋ በዓል፣ በ2008 ዓም ከአበባ ማኖር በዘለለ በማይረሳ የወጣቶች ታሪካዊ ጉዞ እናክብረው፡፡

ጠቢብ አስቦ ይሠራል

ጎበዝ ደግሞ ከሚሠሩት ጋር ያብራል፡፡