“ሞት የዘመኑ ዕለት እንጅ የመነኑ ዕለት አይደለም” – በልጅግ ዓሊ

መነገር ያለበት ቁጥር 8

“ከመሸ ተነሳሁ ከተፈታ በሬ፣
እደርስ አይመስለኝም ከእንግዲህ ሃገሬ።“
አገኘሁ እንግዳ

ጀርመን ፍራንክፈርት በሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ውስጥ በሊቢያ ለተሰው ዜጎቻችን ጸሎተ-ፍትሃትና ከዛም ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ተገኝቼ ነበር። በደቡብ አፍሪካም ይሁን በሊቢያ በደረሰው ችግር ሁላችንም ሃዘን ገብቶናል። በዚህ ግፍ እንባ ያነባንም አለን። ከልባችንም ያዘንን ብዙ ነን። ቄሱ ትምህርት ሲሰጡ እነዚህ ለሃይማኖታቸው ሲሉ በወጣትነት የሞትን ጽዋ የተቀበሉ ሰማዕታት ትልቅ በረከት አግኝተውበታል ነው ያሉት። አዎ ለእምነት መሞት ትልቅ በረከት ነው። ጥንትም ለአመኑበት መሞት ታሪክ መስራት ነው፤ ሕይወትን በሌላ ፈርጅ መቀጠል ነው፤ ዳግም ትንሳዔ፣ ዳግም ልደት ነው። አሁንም ቢሆን የተቀየረ ነገር የለም።

ቤተክርስትያን ውስጥ ሆኜ ጸሎተ-ፍትሃቱን በመከታተል ላይ እያለሁ ለማነው የምናለቀሰው? ለምንስ ነው የምንላቀሰው? የሚለው ጥያቄ አዕምሮዬን አጣበበው። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ችግሩ ባለ ብዙ ፈርጅ ነውና እያንዳንዳችን የችግሩን ምንጭ ማሰባችን አይቀርም። የስደቱ ምንጭ ሃገራችን ውስጥ ያለው ቅጥ ያጣ የዘረኝነት ሥርዓት መሆኑ ግልጽ ነው። ምንም እንኳን የምናለቅስው አሁን በወገኖቻቸን ላይ በደረሰው ችግር ቢሆንም የችግሩ መንስዔ ግን ሃገራችን ውስጥ ያለው አገዛዝ መሆኑን ልንዘነጋው አይገባም። ለዚህ አስከፊ ሥርዓት መቀጠል የእኛም አስተዋፅዖ ትንሽ አይደለም። እንዲውም ከፍተኛው ቦታ ሊይዝ ይችላል።

ሁኔታውን ልብ ብለን ስናጤነው ለዚህ ሁሉ መንስዔ የሆነውን ወያኔ እንዳይወድቅ በተለያየ ምክንያት አቅፈን ደግፈን የያዝነው እኛው ነን ማለት ይቻላል ። የሕዝብ ሰቆቃና ስቃይ ያራዘምነው እኛው፤ የስደት አዙሪት ያባዛነው እኛው ነን። ውል የለሾች፣ ማተባችንን የበጠስነው እኛው መሆናችንን ሳስበው ከተለቀሰ መለቀስ ያለበትማ ለእኛ ነው እንጂ ለተሰውት መሆን የለበትም የሚል ድምዳሜ ላይ ደረስኩ። እነርሱማ ለእምነታቸው ውድ ሕይወታቸውን ከፍለዋል።

እውነትም መለቀስ ያለበት ለእኛ ነው። የግፍን ዓይነት ለምንመርጠው፣ ሰው በወገንተኝነት እየለየን ለአንዱ ለምናለቅስ፣ ለሌላው ጆሮ ዳባ ለምንለው፤ ለባለጊዜ ጉልበተኛ ለምንሰግደው፤ በዘር፣ በሃይማኖት ለምንከፋፈለው፤ ራሳችን ያቋቋምነውን (ቤተክርስትያን፣ ማህበር፣ የፖለቲካ ድርጅት፣ የሲቪክ ድርጅት . . . ወዘተ) ራሳችን ለምናፈርሰው፤ አቋማችንን በየወቅቱ ለምንለዋውጠው፤ የሃዘናችን ዳርቻ ከፌስ ቡክ ዋይታ ለማይዘለው፤ የሃይማኖታችን ብጽእና ሻማ ከማብራት አልፎ ወደ ላይ ለማያርገው፤ የምንኩስና ቆባችንን በፖለቲካ እራፊ ለምንጥፈው፣ ሽምግልናችን የእንጨት ሽበት ለሆነብን፤ መክረን ለማንመልሰው፣ ዘክረን ለማንቀልሰው፣ ላለው እምናሸረግድ፣ ለሌለው ፊት እምንነሳ፤ ሞልቶ ለተረፈው የምንሰጥ፤ ድሃውን ለምናሽጓጥጠው፤ የደሃን መጠለያ ጎጆ እያፈረስን መሬት ለምንመራው፤ ማልቀስማ ለእኛ ነው፣ አለን እያልን ለጠፋነው፣ በቁማችን ለሞትነው፤ በእኩይ ምግባራችን ገልሙተን ባህሪያችን ለሸተተው፣ ቀባሪ ዕድር አጥተን እንጂ ከሞትንማ’ ለቆየነው፣ ማልቀስ ለኛ ነው።

የለም! የለም! ዛሬ ለእኛ ነው መለቀስ ያለበት። ሃዘናችን ከቫይበር ስዕል ፣ ከፌስ ቡክ RIP ያለፈ ቁም ነገር ለማይፈይደው፤ ምን አልባትም ለአንድ ቀን “እኔም እነርሱን ነኝ“ ከሚል መፈክር በላይ ለማንሄድ፤ ነገን ለኛ ለምናልም ጉድጓዳችን የተማሰ አዛውንቶች፤ በድሃው አናት ላይ ግራውንድ ፕላስ . . . ቤት ለመስራት ለምንስገበገብው። በሰጥቶ መቀበል ቀመር በደራው የወያኔ ገበያ በዜጎች ሕይወት በዜጎች መብት ለምንነግድ፤ ለምናተርፍ ለእኛ ነው መለቀስ ያለበት።

ጎበዝ! ይለቀስ እንጂ ለእኛ በዘር፣ በድርጅት ተከፋፍለን መነጋገር ላቆምነው፤ የድርጅት መሪ ሆነን በሥልጣን ጥም ጠኔ ለምናጣጥረው፤ ከሕዝብ የተዋጣ ገንዘብ ለምንመዘብረው፤ ትላንት ተቃዋሚ ዛሬ የወያኔ ጋሻ ጃግሬ፤ ትላንት ዓለም አቀፋዊ ዛሬ ጎጠኛ ለሆነው፤ ትላንት ኮምኒስት ነን ብለን ካፒታሊዝምን ያብጠለጠልን ፣ ዛሬ ካፒታሊዝምን ወደን ሶሻሊዝምን የምንረግም፣ ትላንት የተቃዋሚ ሊጋባ ዛሬ የወያኔ አልባሽ አጉራሽ ለሆነው። መለቀስ ያለበትማ ለእኛው፤ ለገበያ ኢኮኖሚ ልማታዊ ባለሃብቶች፣ ፔንዱለሞች፤ አንዴ እዚህ አንዴ እዚያ ለምንዋትት፣ የሁለት ዜጋ ሰዎች፣ በሁለት ካራ በላዎች፣ ማተብ የለሽ ክርስትያኖች፣ ሶላት ለማንሰግድ ሼኮች። ደረት ይመታልን ለእኛ።

ለእኛ ይለቀስ እንጂ! ትላንት አማራዎች ከየቦታው ሲፈናቀሉ አይተን እንዳላየን ለሆነው፤ ስንት የፖለቲካ እስረኞች ቤተሰቦች ሲበተኑ ሰምተን ላለመስማት ለጣርነው፤ በ97 ምርጫ የተገደሉትን ወጣቶች ለረሳነው፤ ወያኔና ሻብዕያ ወጣቱን በጅምላ ለማይረባ ጦርነት ሲማግዱ ለደገፍነው፤ ከክልላችን ይውጡ እያልን ያዙን ልቀቁን ለምንለው፤ ማልቀስ ለኛ ነው በቁማችን ለሞትነው። እንጂማ በሃይማኖቱ ጠንቶ! በዜግነቱ ኮርቶ! ታሪክ ሰርቶ፣ ስም ተክቶ፣ ለሞተው ጀግና ወገንማ ምን ብለን እናለቅሳለን። ለዚህ መሰሉ የሃገር ክብር መግለጫ፣ ለዜግነት ኩራት ለተከፈለ መስዋዕትነት ለማውራትም ይሁን ለማልቀስ ከቶ ስንቶቻችን የሞራል ብቃት ይኖረን ይሆን?

“ሞት የዘመኑ ዕለት እንጅ የመነኑ ዕለት አይደለም“።

ከውጭ ለቃቅመንና ተበድረን በሄድነው ገንዘብ ሃገርቤት ሄደን አሽሼ ገዳሜ ለምንለው፤ በአስረሽ ምችው ዋልጌነት መጥፎ ባሕልን ለምናስፋፋው፤ በማስመሰል ስብእና የድሆችን ቀልብ እያማለልን ስደትን ለምናስፋፋው፤ ጸረ ዘረኝነት ትግልን ለምናጥላላው፤ በየመሸታ ቤቱ በጨበጥነው የድራፍት ብርጭቆ ስፍር የሀገር ልማትን ለምንለካ፣ አዳዲስ የተገነቡትን ሕንጻዎች እንጅ በህንጻው ስር የወደቁትን አዳዲስ ድሃዎች ለማናስተውል፤ የተሰራውን ቀለበት መንገድ ስናደንቅ ጫማ የሌለውን ምስኪን ረግጠን ላለፍነው፤ በተቀዳደዱ እራፊ ጨርቆች ውስጥ ሾልኮ የሚታየውን አቧራ ጸሐይና ቁር የጠገበን ያገር ልጅ ገላ ያላሳሰበን፤ የውስኪውን ጣዕም እንጅ ጥሪኝ ውሃ የሌለውን ወገን ያላስተዋልን፤ የክትፎውን ጣዕም፣ የጥሬውን ስጋ ጮማነት እንጅ . . . እኛ ጠግበን ከጣልነው የእጅ ማበሻ ሶፍት ውስጥ ፈልቅቆ ከትራፊያችን አጥንት ጋር የሚታገለውን ታዳጊ ወጣት የረሳን፤ በሚቀያየር የቀለም መብራት ደንሰን ሻማ መግዥያ የሌለውን ያልተመለከትን፤ አንድ የዕለት ጉርሻ ለመግዛት ገንዘብ ያጣውን ለረሳነው፤ የሃገርን እድገት በሃብታሞች የብር ጥራዝ ለለወጥነው፣ የሆቴሎቹን ማማር፣ የኮረዳዎችን ውበት፣ የሪዞርቶችን ምቾት በየመንገዱ ለምንቆጥረው። ለቅሶ የሚገባው ለእኛ ነው ልማታዊ ቱሪስቶች ለሆነው።

አሁንማ ተራው የእኛ ይሁን እንጂ! ለእኛ ይለቀስ እንጂ፣ የቁም ተዝካራችንን እናውጣ እንጂ፣ የምራዕብውያንን የራስ ጥቅም አሳዳጅነት እያወቅን በየኤምባሲው፣ በስቴት ዲፓርትመንት፣ ነጻነታቸንን ይቸሩናል ብለን 23 ዓመታት ሙሉ ለሰገድነው፤ በሃገራቸን ሕዝብ እምነታችንን ላጣነው፤ ሳንታገል ሳንሰዋ ድል እንደ ኬክ በሳህን ከምዕራብውያን እንዲታደለን ለምንቋምጠው፣ በጣት የሚቆጠሩ ደጋፊዎች አስከትለን በአንድ መሪ አምላኪነት በድርጅት ስም መግለጫ እያወጣን በብዙሃን ትግል ለምንነግደው፤ ሃገርንና ሕዝብን ለስልጣን ጥም በጥቅም ለቀየርነው። መለቀስስ ያለበት ለኛ ነው። በቁም መሞት ከዚህ በላይ ምን አለና!?

ኧረ ሙሾ ደርድሩልን ለእኛ! ከሕዝብ የተዋጣን ገንዘብ ለምንበላው፤ ለጥቅም ስንል ስንት አባላት የተሰውበትን ትግልና ድርጅት እያመከንን ላለነው፤ የውሸትን ፕሮፖጋንዳ እየደሰኮርን ለደጋፊዎቻችን መደለያ ለምናደርገው፤ በድርጅትና በትግል ስም ገንዘብ ለምነን ለግል ጥቅም ለምናውለው፤ ማልቀስ ለኛ ነው ጥሩ እድር አጥተን ላልተቀበርነው ።

ወገን አልቅሱ ለእኛ የስምንተኛው ሺህ የጥፋት ምልክቶች ለሆነው፣ እንደ ቄስ መስፍን (የሙኒኩ) ከህዝብ የተዋጣ 150 ሽህ ዩሮ በላይ የደብሩን ገንዘብ አጥፍቶ “ቀድሼ እከፍላለሁ“ እንዳለዉ በእግዚአብሔርም በዜጋም ለምንቀልድ፣ እንደ(ፕሮቴስታንቱ) ፓስተር ተከስተ የእንስትን ራቁት ፎቶ በስልክ እየበተን ለምንዝናና፣ እንደ አባ ግርማ (የለንደኑ) በሕዝብ ገንዘብ የተገዛን ቤተ-እግዚአብሔር ለግል ጥቅምና ለሹመት ስንል ለዓመታት ለዘጋን፣ ማልቀስ ለኛ ነው እንጅ የስምንተኛው ሺህ ምልክቶች ለሆን፣ ቀብራችን ለተማሰ ግብዓተ መሬታችንን ለምንጠብቅ።

እናልቅስ ከተባለ ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ እናልቅስ! ካልሆነ ግን ለራሳችን እናልቅስ!

ሰሞኑን አዲስ አበባ ለተደበደቡት እናልቅስ፤ የወያኔ ቅልብ ለወንድሞቻቸው ሐዘን የወጡትን ሲደበድቡ እኛም እንቢ እንበል፤ በደቡብ አፍርካ የተደረገውን ግፍ እንዳወገዝን የሃገራችንን አፓርታይድ የክልል አገዛዝንን እናፍርስ፤ ዛሬም ለእነ እስክንድር ቤተሰቦች እናልቅስ ፣ ለነተመስገንም ቤተሰቦች እናልቅስ ፣ ከአንዳርጋቸው ጽጌ ልጆች ጋር አብረን እንነሳ . . . ወዘተ ፣ ለሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንታገል። ለፍትህ እንቁም፣ ለዜጎች መብት እንጋደል፣ ለዲሞክራሲ እንትጋ፣ ለአንድነት በአንድነት እንቁም። በሉ ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ አብረን እናልቅስ።

መታገላችን ካልቀረ፣ ማልቀሳችን ካልቀረ የግፍ ሁሉ ግፍ፣ የስደት ሁሉ ስደት ምክንያት የሆነውን ወያኔን ለማስወገድ፣ ዘረኝነትን፣ ኢ-ፍትሃዊ የሆነውን የሃብት ክምችት፣ ጎጠኝነትን፣ የስርዓት ንቅዘትን፣ ፅንፈኝነትን፣ ብሄራዊ ውርደትን፣ የሉዓላዊነት መደፈርን፣ የአንድነታችን መሸርሸርን ከምንጩ ለማንጠፍ እንታገል። የስርዓቱን ሰለባዎችን ለመታደግ፣ የወገንን ውርደት እንዲያከትም፣ እንነሳ። ሳንከፋፈል ስር የሰደደውን ቀንደኛ የሃገር የሕዝብ ጠላት ወያኔን ለማስወገድ አብረን እንታገል፣ አብረን ተግተን ከልብ እናልቅስ፤ ያኔ ስደትም ይቆማል ሰቆቃችንም ያከትማል፣ እኛም ማልቀሳችንን እናቆማለን ።

ስለ ሰማዕታቱ የሚያስቡ ሁሉ በሰላም ይክረሙ።

beljig.ali@gmail.com

ፍራንክፈርት

29.04.2015

FREE ኔልሰን ማንዴላ! (ታሪኩ አባዳማ)

ታሪኩ አባዳማ ሚያዝያ 2007

“During my lifetime I have dedicated myself to this struggle of the African people. I have fought against white domination, and I have fought against black domination. I have cherished the ideal of a democratic and free society in which all persons live together in harmony and with equal opportunities. It is an ideal which I hope to live for and to achieve. But if needs be, it is an ideal for which I am prepared to die.” ኔልሰን ማንዴላFree Nelson Mandela

የሰው ልጆች ከማናቸውም አይነት የዘር መድልዎ ነፃ የሚሆኑበት ፍትሀዊ ስርዓት እንዲሰፍን ለማረጋገጥ እስከ ሞት ድረስ መስዋዕት ለመሆን ዝግጁ መሆኑን በገቢር አረጋግጧል። ዘረኝነት ይቁም ሲል እሱ ለዚህ አላማ በመቆሙ ሀያ ሰባት መራራ የእስር ዘመናት አሳልፏል። ዘር ላይ የተመረኮዘ አስተዳደር ፣ ዘር ላይ የቆመ ፖለቲካ ፣ ዘር ላይ የታነፀ ማናቸውም ክፍፍል ሊወገዝ ፣ ሊወገድ እንደሚገባው እየተማፀነ ወደ ዘላለም ቤቱ ተሸኝቷል – ይሁንና ሩብ ያህል ዕድሜ ዘመኑን በሰቆቃ እስር እና መንገላታት ያገባደደው ኔልሰን ማንዴላ ለመላው የሰው ዘር ጥሎ የሄደውን አስተምህሮ ዋጋ የሚያሳጡ ድርጊሮች በዚያችው በተወለደበት እና በተቀበረባት ምድር እየተፈፀመ ይገኛል።

ዘረኝነት የጭፍን ጥላቻ ምንጭ ነው ፤ እናም ከምንጩ መድረቅ አለበት። ማንዴላ ህያው ክብር የሚገባው ተግባር ትቶልን አልፏል የሚሉ ካሉ እሱ ሲዋጋው የቆየውን የዘር አድሏዊነት ዳር ማድረስ ግዴታ አለባቸው። በተለይም ስልጣን ላይ ያለው የደቡብ አፍሪካ መንግስት ልዩ ተልዕኮ አለበት።

ዘረኝነትን በመዋጋቱ የከፈለውን መስዋዕትነት ሲያስቡት ለህሊና ይከብዳል – በጦር መሳሪያ እና ስለላ መረብ መላ አገሪቱን ቀፍድዶ ይዞ የነበረው ዘረኛ ስርዓት በደቡብ አፍሪካ ያሻውን ማድረግ ይችል ነበር – ዘርና ቆዳ ብሎም የፀጉር አይነት በሁሉም ማህበራዊ ህይወት ውስጥ መመዘኛ መለኪያ ሆኖ ቆይቷል። አንደኛ ሁለተኛ ሶስተኛ ደረጃ ዜጋ እየተባለ በእርከን አጥር ተሸንሽኖ ይኖር ከነበረበት ምድራዊ ሲኦል ወገኑን ሊታደግ ሲል ነበር ማንዴላ የቁም ፍዳ መቀበሉ…

ከዘር መድልዎ ሰንሰለት ነፃ የወጣው ዜጋ ገሚሱ አስተምህሮውን ጠልቆ የተገነዘበ አይመስልም – እንደገና ዘር ላይ የተመረኮዘ ጥቃት በዚያች ምድር ላይ ተፈፅሟል። ማንዴላን እንደገና ወደ እስር ቤት ለማስገባት ሰይፍ ታጥቀው የተነሱ ጥቁሮች በደቡብ አፍሪቃ ተነስተዋል።

ማንዴላ ተመልሶ ወህኒ ሊገባ ነው – ትናንት በቁሙ ዘረኛ ነጮች እንዳንገላቱት ሁሉ ዛሬ መንፈሱን ሰላም በመንሳት በዘረኝነት ካራ ሌሎችን የሚያጠፉ ጥቁሮች ተነስተዋል። የሰውን ዘር እንደ ማገዶ እያነደዱ ትናንት በነሱ ደም የከረፋውን መንደር ክቡር በሆነው የሰው ገላ በክለውታል። ብካይ ትውልድ በደቡብ አፍሪቃ ምድር እያበበ ነው።

በሰማይ መስኮት ብቅ ብሎ ይህን ቢያይ ማንዴላ ከቶ ምን ይሰማው ይሆን?

ማንዴላን እንታደገው! FREE ኔልሰን ማንዴላ!

በዘመነ ደርግ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ነፃ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል አግኝተው ይሰለጥኑ የነበሩ ደቡብ አፍሪቃውያን ፣ የዚምባብዌ እና ናሚቢያ ዜጎች ብዙ ነበሩ። ያኔ ሶስቱም አገሮች ገና ነፃ አልወጡም – ማንዴላም ከሀያ ዓመታት በላይ እስር ላይ ነበር። በግሌ በወቅቱ የቅርብ ወዳጅነት መስርተን ከነበሩት ተማሪዎች መካከል ሚሼል የተባለ ደቡብ አፍሪካዊ ወጣት ይገኝበታል – እንደ አገራችን ዘመን አቆጣጠር 1974 አንደኛ አመት ተማሪ ሳለን ነበር ለመተዋወቅ ፣ ለመቀራረብ እና ብዙ ቁምነገሮችን መጋራት የበቃነው። ወዳጅነታችን እስከ መጨረሻው የዩንቨርሲቲ ህይወታችን ዘልቋል – ሚሼል በወቅቱ ከትምህረቱ ሌላ የምስራቅ አፍሪካ ክልል የ ANC ወጣቶች ሊግ መሪ ነበር። በምጣኔ ሀብት ዘርፍ ተመርቆ አገሩ ነፃ ስትወጣ መመለሱን አውቃለሁ። እንደ ዛሬው ኢሜይል እና ስካይፕ አይነት ቀላል የመገናኛ ዘዴ ባለመኖሩ ይኸው እስከ ወዲያኛው ተራርቀን ቀረን።

ከሚሼል ጋር በነበረኝ ጓደኝነት ሰበብ አዲስ አበባ ነዋሪ ከነበሩ ብዙ የደቡብ አፍሪቃ ስደተኞችና የትግሉ መሪዎች ጋር በማህበራዊ እና ባህላዊ ብሎም ፖለቲካዊ ተሳትፎ ተቀራርበናል። ቀበና ይገኝ በነበረው የተንጣለለ ቪላ ፅ/ቤታቸው በተካሄዱ ውይይቶች በግል ለመሳተፍ ዕድል አግኝቻለሁ። ቪላው በነፃ የተሰጠ እንደነበር እና የድርጅቱ ተጠሪ መኖሪያ እንደነበረም አውቃለሁ።

በዘመኑ FREE NELSON MANDELA የሚሉ ስቲከሮች ደረታችን ፣ ቦርሳችን ፣ በመማሪያ እና መኖሪያ ህንፃዎቻችን ላይ ለጥፈን ለደቡብ አፍሪቃ ጥቁር ህዝብ የትግል አጋርነታችንን ገልፀናል ፤ ስደት በመጡባት አገር ሲጋቡ ሰርጋቸው ላይ ተግኝተን አድምቀናል ፣ አንዳች የቅስቀሳ ስብሰባ ሲጠራ ተሳታፊ ሆነን ትግላቸውን አግዘናል… ብዙ ብዙ ነገር አድርገናል። ኢትዮጵያ የተሰደዱባት አገር ብቻ ሳትሆን ዕውቀት የገበዩባት ፣ የተዳሩባት የተኳሉባት ጭምር ነበረች። ተሰደው መጡ በክብር ተስተናግደው ፣ ተምረው ፣ እንደ ሙሽራ ተመርቀው እስከ ነፃነት ዘልቀዋል – ብርቱ ታጋዮች ነበሩ ኢትዮጵያም የክፉ ቀን ተጠሪ ነበረች። ይህ ሁሉ የተደረገው በኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት እና ለውጭ ዜጎች ለእንግዶቹ ከሚሰጠው ክብር የመነጨ ጥልቅ ስሜት ነው። አትዮጵያ ያንን ያደረገችው ግን ተርፏት አልነበረም። ይህን የምዘረዝረው ውለታ ለመቁጠር ባይሆንም አለምክንያት አይደለም …

እነ ሚሼል አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሲማሩ ልዩ እንክብካቤ ይደረግላቸው እንደነበር መጥቀስ አስፈላጊ ይመስለኛል። እኛ በዩንቨርሲቲ ሳለን አንድ መኝታ ክፍል ለአራት መጋራት አለብን እነ ሚሼል ግን እያንዳንዳቸው በግል አንዳንድ መኝታ ቤት ነበራቸው። ከህንፃ እንኳ ህንፃ ተመርጦ መኝታ ቤታቸው በአፄ ሀይለስላሴ ዘመን ለህግ ተማሪዎች ‘ክብር’ በተለይ ነጠል ብሎ እንዲታነፅ ባደረጉት Law House በተሰኘው ፎቅ አልባ ንፁ ቤት ውስጥ ነበር።

ይህ ብቻ አይደለም ፣ ስደተኞቹ ተማሪዎች እኛ የምንመገበውን በጅምላ የሚዘጋጅ ምግብ እንዳይበሉ በሚል በወጥ ቤት በልዩ ዝግጅት የሚቀርብ ማዕድ ነበራቸው። አገሩ ላይ ክብሩ ተዋርዶ ለስደት የተዳረገውን ደቡብ አፍሪካዊ እንደ እንግዳ ሳይሆን እንደ ቤቱ አክብረን ተንከባክበን አስተናግደናል። ብዙዎቻችን ታላቁ ሰው ኔልሰን ማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና ያደረገው እና የታጠቀው ኢትዮጵያ መሆኑን ከማወቅ ሌላ እንደ ህዝብ እና እንደ አገር ለሌሎች ለተንገላቱ ፣ ለተረገጡ እና ለተዋረዱ አፍሪቃውያን በተለይ ለደቡብ አፍሪካውያን ሲደረግ የነበረው ክብካቤ እና ድጋፍ ብዙ አናውቅም።

ተሰደው የመጡትን ማስተናገድ ብቻ ሳይሆን አገሪቱ ወደ ነፃነት ጎዳና እንድትገሰግስ መንግስት ከሚሰጠው ሌላ እንደ አፍሪካዊ እና እንደ ነፃነት ወዳድ ህዝብ እኛም ልባዊ የትግል አጋርነታችንን ስንሰጥ ነበር። ለምን እንደተሰደዱ በውል ለመረዳት ፣ ለመገንዘብ ተግተን ሰርተናል። አፓርታይድ ምን ማለት እንደሆነ እናም በዚያች ምድር ፍትህ ምን ያህል ተረግጣ እንደቆየች መረዳት ችለናል።

ልባዊ ድጋፋችን የመነጨው ችግራቸውን ጠንቅቆ ከመገንዘብ የተነሳ ነበር። ለመሆኑ የዛሬዎቹ ካራ ሰባቂ ደቡብ አፍሪካውያን ኢትዮጵያውያን ለምን እንደተሰደዱ ያውቃሉ? ኢትዮጵያ ዘረኝነትን ምርኩዝ ያደረገ ጉልበተኛ የፖለቲካ ሀይል መዳፍ ስር መውደቋንስ ይረዳሉ – እዚህ እዚያ ክልል መኖር አትችልም ተብሎ በዘር ግንዱ የተነሳ የኑሮ ዋስትና ማጣቱንስ ፣ መዋከቡን ፣ መጋዙን ፣ መገደሉን ይገነዘባሉ? ትናንት ችግራቸውን ለማወቅ እና ለመጋራት የፈቀደ ህዝብ ዛሬ ራሱ በዘር መድልዎ የተነሳ ችግር ላይ መሆኑን ይረዳሉ? የዘር አድልዎ ምን ያህል ግፍ የተመላበት መሆኑንስ ለነሱ ይነግሯል? ለምንስ በዘር ተጠራርተው ሌላውን ዘር ለማጥቃት ተነሳሱ?

እነሱ በዘር እና ቆዳ አድልዎ የተነሳ ተሰደው መጡ – አከበርናቸው ፣ አንድም ነገር አልጎደለባቸውም እኛ በዘር እና ጎጥ ቆጠራ ምሬት ገብቶን ፣ ቀን ጎድሎብን ተሰደን ብንሄድ እንደ ቁሻሻ ዕቃ ቆጠሩን – ስብዕናችንን ገፈው ራቁታችንን አቆሙን። ወደ መጣችሁበት ሂዱ አሉን – የት እንሂድ?!

ዘረኝነት የህይወት ዋስትናቸውን ገፍፎ ከቄየ ምድራቸው ያባረራቸው ኢትዮጵያውያን በተሰደዱበት ደቡብ አፍሪካ የቆያቸው ያው ዘረኝነት ሆነ – ክልልህ አይደለም ውጣ እየተባሉ በገዛ አገራቸው ምድር የተንገላቱ ወገኖቻችን ለሌላ የዘር መድልዎ ሰለባ ሆኑ።

ማንዴላ እንደገና ወህኒ ገባ!

የማንዴላ ሌገሲ ቀጭጮ የመለስ ሌገሲ መቋሚያ ይዞ ጠበቃቸው። መለስ ዜናዊን ደቡብ አፍሪካ አገኙት – ዘረኝነትን እንደገና ተጋፈጡት – ዘረኝነት በማናቸውም ቅርፅ ቢመጣ ለሰው ዘር መርዝ እንጂ መድሀኒት አለመሆኑን የወቅቱ በዘር እና ሀይማኖት ጥላቻ የተነሳ የሚፈፀመው አረመኔአዊ ጥቃት ይበልጥ እያረጋገጠ ነው። ዘር ቆጠራ ሰብአዊ ህሊና በሌላቸው ሰዎች እንደሚራመድ እንደገና ተረጋገጠ። ዘረኞች ለሰው ዘር ክብር እንደሌላቸው ደግመን ደጋግመን እንድንማር ተገደድን።

As I walked out the door toward the gate that would lead to my freedom, I knew if I didn’t leave my bitterness and hatred behind, I’d still be in prison

ድምፃችንን ከፍ አድርገን ዛሬም እንላለን FREE NELSON MANDELA !!!

ሰው በአሹቅ ብቻ አይኖርም ! (አሌክስ አብርሃም)

‹‹ጥጋብ ፍንቅል አድርጓችሁ ነው የተሰደዳችሁት እንጅ …አገራችሁ ማሩ ወተቱ …›› ማለት ‹‹ጠግባችሁ ሂዳችሁ ነው የታረዳችሁት እንኳን የእጃችሁን አገኛችሁ ›› ከማለት አይተናነስም !!አሁን ከትላንት ወዲያ ታዋቂው የማስታወቂያ ባለሙያ አርቲስት ሰዊት ፍቅሬ ጨርቆስ ሃዘን ቤቱ ንግግር እንዲያደርግ ተፈቅዶለት በሚያስገመግም ድምፁ እንዲህ አለ ‹‹ ከሰው አገር ወርቅና ብር እናታችን እቅፍ ውስጥ አሹቅ እየበላን ሙቆን ብንኖር ይሻላል›› ቆይ እውነቱን እናውራ እንጅ ! የታለ ጥጋቡ … የታለ ስራው … የታለ አሹቁ….እንዴዴ ….ምናይነት በሰው ህይዎት ላይ መቀለድ ነው ይሄ ! ሰው እኮ እንስሳ አይደለም …በልቶ ጠጥቶ ሆዱ ከሞላ መተኛት ብቻውን በቂ ነው ሊባል አይገባም !

እከሌ መቶ ሽ ብር ከፍሎ ተሰደደ ለምን እዚሁ አይሰራባትም የሚል የዋህ ሒሳብ የሚያሰሉ ሰዎች ገጥመውኛል ….እጁ ላይ አፈር ከድቤ በልቶ ያጠራቀማትን ገንዘብ እየበላ አጨብጭቦ ከሚቀር ….ስደት ላይ ኢንቨስት ሊያደርግ ወሰነ በቃ ….ለምን አገሩ ላይ ስራ አይሰራባትም ….አገራችን ላይ ስራ እድል በሆነበት በዚህ ጊዜ መቶ ሽ ብር ምን እንደሚሰራ ሁላችንም እናውቃለን ….ቤት ልከራይ ቢባር የስድስት ወር ኪራይ የአመት ኪራይ በአንዴ በሚጠየቅባት አገር ….መቶ ሽ ብር እና ከዛ ያነሰ ብርን እንደትልቅ ካፒታል የሚቆጥር ሰው …ምናልባት ነፍሱ ድሮ ላይ የቆመ ሰው ይሆናል !

እናቴ ያሳደገችኝ እኮ እሷ ስር ተወሽቄ አሹቅ እንድበላ አይደለም ! የተሻለ ኑሮ እሻለሁ …ለእናቴ ላሳልፍላት እፈልጋለሁ … ቤት እፈልጋለሁ የተሻለ ትምህርት እፈልጋለሁ ማግባት መውለድ ለቤተሰቤ አለኝታ መሆን እፈልጋለሁ ! ልጆቸ ጥሩ ትምህርት ቤት እንዲማሩ ጥሩ እውቀት እንዲኖራቸው እፈልጋለሁ ….አሹቅ እየበላሁ ነገ ይሄንኑም አሹቅ ያጡ ልጆችን መፍጠር አልሻም ! አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ህዝብ የሚሰደደው ደላላ ስለደለለው ወይም አገሩን ስለጠላና …አገሩ ላይ ((ሚሊየነር መሆን ስለደበረው)) አይደለም ! ከእለት ጉርስ ያለፈ ነገር ማግኘት ዘበት ስለሆነበት ለፍቶ ጠብ የሚል ነገር ስላጣ ነው !! ዛሬን ብቻ አይደለም ማሰብ …ዛሬ ለፍቶ ጉልበቱን ገብሮ ይኑር ነገስ እድሜው ሲገፋ ነገስ ልጆች ሲወልድ ….ነገስ ነው ጥያቄው ! እህት ወንድሞቹ ለእግራቸው ጫማ ሲያጡ እየተመለከተ አሹቁን እየቃመ ቁጭ የሚል ልብ ያለው ሰው የለም !

ተው እንጅ ባለቢላዎቹ ሲገርሙን የብሶት አንገታችንን በቃል ስለታችሁ አትረዱን ! በመጀመሪያ ድግሪ ሁለት ሽ ብር እንኳን በማትከፍል አገር … ጠግባችሁ ተሰደዳችሁ ይባላል እንዴ ….ስደት በባህሪው እኮ ተፈጥሯዊ ህግ አለው ….ካልተሸለ ቦታ ወደተሸለ ቦታ መሄድ ማለት ነው ! አገራችን የተሻለች ብትሆንማ እንኳን እኛ ልንሄድ ሌሎችም ወደኛ በተሰደዱ ነበር ! ጠላታችን ድህነት ነው ብለን አውጀናል እኮ … አቅም ያለው ድህነትን ይፋለመው አቅም ያጣ ደግሞ ከጥላት ቀጠና ማፈግፈጉ የጦርነት ህግም ነው ! ጦርነት እውነት ነው ጨካኝ ጠላት ነው ….በመፎክር ብቻ አይመለስም ! ስጋህን ብቻ ሳይሆን ነፍስህንም አጋድሞ ያርድሃል !
ድህነት ያባረረውን ህዝብ ስደተኛን ተቀባዮቹ ግፍ ዋሉበት ይሄ ነው እውነቱ !

እስቲ አሁን ዝቅ ብሎ መስራትን ከጨርቆስ ልጆች የበለጠ ማን ያውቃታል …. ዝቅ ተብሎም ጠብ የሚል ነገር ጠፋ ሄዱ ! እና ስራ ንቀው እንል ዘንድ ተገቢ ነው እንዴ …. ለምን ወሬ እናሳምራለን …. አስር ጊዜ ‹‹ደላላ እያታለላቸው ›› ይላል ሚዲያው …ከኑሯችን የበለጠ ደላላ የለም ! እንደውም ለስደት የሚገፋፉ አንደኛ ደላሎች የማስታወቂያ ባለሙያዎች ናቸው !
አሹቅ ብሉ ዳቦ ብሉ ….የተፈጠርኩት አሹቅ እየበላሁ ጮማ የሚቆርጡ ሰዎችን ምራቄን እየዋጥኩ እንድመለከት አይደለም ! ለዚህ ደግሞ ሰው ነኝና መጀመሪያ አገሬ ላይ አቅሜ የፈቀደውን ሁሉ ለመስራት እሞክራለሁ …. አገሬ የልፋቴን ካልከፈለችኝ በተለይ ደግሞ ከእኔ በታች የሚደክሙትን እያነሳች አናቴ ላይ ካስቀመጠች … ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ከሌለ …ከሰውነቴ ይልቅ ባለኝ ገንዘብና ደረጃ የምመዘን ከሆነ ….እንደሰው የምቆጠርበት ተንቄም ቢሆን የተሸለ የገንዘብ አቅም የተሸለ ነገር የማገኝበት ቦታ ሁሉ ምርጫየ የማይሆንበት ምክንያት የለም !

‹‹እናትህ እቅፍ ውስጥ ሁነህ አሹቅም በልተህ ቢሆን መኖር ይሻላል ››ይሉት ቀልድ …አሹቅ እየበላህ የእኔን ማስታወቂያ እየተመለከትክ በአምሮት ኑር ከማለት ውጭ ምን ትርጉም ይኖረዋል ! እንዴ ራሳቸው የማስታወቂያ ባለሙያዎቹ አይደሉ እንዴ …‹‹ለበዓል ለእናትሽ ብር ላኪ በዚህ ባንክ መንዝሪ›› እያሉ የተሰደደው ሁሉ ሃብታም የተሰደደው ሁሉ ላኪ መንዛሪ መሆኑን እንቁልልጭ እያሉ ለስደት የሚገፉን …የምን ዞሮ ‹‹አሹቅ ቂጣ›› እያሉ በሰው ቁስል እንጨት መስደድ ነው ! እስቲ ሃቁን እናውራ በቴሌቪዥን ከሚሰራጩ ማስታወቂያዎች አንድ እንኳን ‹‹የአሹቅ በሊታዎች›› ማስታወቂያ አይታችሁ ታውቃላችሁ ?…. አሹቅ እየበላሁ ነው ኢንሹራንስ የምገባው? ….አሹቅ እየበላሁ ነው የተንፈላሰሰ ቪላ በሶስት ጊዜ ክፍያ የምገዛው ?…አሹቅ እየበላሁ ነው ….መኪና የማማርጠው? ….አሹቅ እየበላሁ ነው ዱባይ ያለ ምግብ ቤት የምዝናናው? …. አሹቅ እየበላሁ ነው ባለምናምን ኮከብ ሆቴል የምዝናናው ?… አሹቅ እየበላሁ ነው ለቴሌቶን ሚሊየን ብር የማዋጣው?

‹‹ፍሪጅ ከሌለዎት ምኑን ኖርኩት ይላሉ ›› የምባለው ፍሪጁን አሹቅ እንዳስቀምጥበት ነው ??…..ለምን ስራችን እና ስብከታችን ዬቅል ይሆናል ….በእርግጥ ስደት አስቀያሚ ነው ….ግን አገር ላይ በድህነት እንደመገፋት የባሰ አሰቃቂ ነገር የለም ! ሚሊየኖች በቤት ኪራይ ችግር በተንገሸገሹበት ሰዓት … እልፎች በስራ አጥነት ችግር ድግሪያቸውን እንደዣንጥላ እራሳቸው ላይ አድርገው በየማስታወቂያ ሰሌዳው ስር በሚንከራተቱባት ሰዓት ‹‹ጠግባችሁ ተሰደዳችሁ ›› ማለት …ሌላ እርድ ነው !

እንደው እነዚህ ወገኖቻችን በግላጭ በአደባባይ በግፍ ሲገደሉ አየን እንጅ በየጓዳው ስንቱ ነው የተራዘመ የችግር ሞት የሚሞተው ?! አሁንም ደላላ መርገም ስደተኛውን ተቀፅላ ስም እየለጠፉ ማሸማቀቅ መፍትሔ አይሆንም ….ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ….ለህዝቡ እንደልፋቱ የሚከፈልበት ስርዓት …. ሙስናን የሚፀየፍ አስተዳደር …. እናም ጠንካራ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና አፈፃፀም ያስፈልገናል ! ‹‹አህያውን ፈርተን ዳውላውን ››አይነት ከንቱ ልፈፋ የትም አያደርስም ! ህይዎት ብዙ መሻት ብዙ የማይገደብ ፍላጎት አላት …..ሰው በአሹቅ ብቻ አይኖርም !!

በአፍሪካና በአረብ አገሮች በስደት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸሙ ስላሉት ፋሽስታዊ ድርጊቶችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

ENTCሀገር በቀሉ የወያኔ አፓርታይድ ሰርአት በሃገር ውስጥ በህዝባችን ላይ የፈጠረውን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ስነልቡናዊ ቀውስ በመሸሽ በአፍሪካና በአረብ አገሮች በስደት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን፤ የዜጎቹን መብት የሚያስጠብቅ ኢትዮጵያዊ መንግስት ባለመኖሩ እጅግ አሳዛኝና ዘግናኝ ለሆኑ ስቃይና ግድያዎች ተጋልጠዋል።

ባሳለፍንው የአንድ ሳምንት ጊዜ ብቻ፤ የመን ውስጥ በተፈጠረው ጦርነት፤ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወገኞቻችን የድረሱልን ጥሪ ቢያቀርቡም ስርአቱ ዜጎችን ለመታደግ ምንም ዐይነት ፍላጎት እንደሌለው በድጋሚ አሳይቷል። ወገኖቻችን መውጫ አጥተው በየእለቱ ህይወታቸውን ለማትረፍ በሚጮሁበት በዚህ የስቃይ ወቅት፤  የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ እጅግ አሳፋሪ በሆነ መንገድ በፌስ ቡክ ላይ የስልክ ቁጥር በማስቀመጥና የሳውዲ መንግስት የሚያካሂደውን የአየር ድብደባ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ በመግለጽ በህዝብ ደምና እንባ ላይ በማላገጥ፤ ዛሬም እንደወትሮው ከባእዳን ጋር ያላቸውን አጋርነት አረጋግጠዋል።

በደቡብ አፍሪካ በተለያዩ ስደተኞች ላይ በጅምላ እየተደረገ ያለውን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ የተለያዩ አገሮች፤ የደቡብ አፍሪከን ኤምባሲ እስከመዝጋት ሲያስጠነቅቁ፤ የወያኔ ስርአት ግን ኢትዮጲያዊያኖች ከነህይወታቸው ሲቃጠሉና ሲገደሉ እያየ፤ አንድ ኢትዮጲያዊ ብቻ መገደሉን ከመናገር በስተቀር ምንም አይነት እርምጃ አልወሰደም፡፡

በሊብያ፤ አይሲስ የተባለው አሸባሪ ቡድን ኢትዮጵያውያንን፤ ክርስቲየናች በመሆናቸው ምክንያት ብቻ በጠራራ ፀሃይ ባሰቃቂ ሁኔታ አንገታቸውን በመቅላትና በጥይት በመደብደብ ገሏቸዋል። አሸባሪ ቡድኑም ክርስትያን በሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ ይህን ፋሽስታዊ ድርጊት መፈጸሙን በይፋ ማረጋጡን የተለያዩ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃኖች ቢዘግቡትም፤ የወያኔው ፋሽስታዊ ስርአት ግን በግብፅ ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ ስደተኞቹ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እንዳልሰጠ በመግለጽ የተለመደውን ከፍተኛ ክህደት ፈድሟል፡፡

የኢትዮጲያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ከላይ የተዘረዘሩትን ፋሽስታዊ ድርጊቶችና ሀገር በቀሉን የወያኔ አፓርታይድሰርአት በጅምላ እያወገዘ በዚህ አጋጣሚ ለሟችና ተጎጂ ቤተሰብ፤ ዘመድና ወዳጆች በሙሉ የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን።

ከላይ ባጭሩ የተዘረዘሩት በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እይተፈጸሙ ላሉት ፋሽስታዊ ድርጊቶች፤ ቀደም ሲል ለተፈጸሙት ተደጋጋሚ ብሄራዊ ቅሌቶችና ላለፉት 24 አመታት የኢትዮጵያ ህዝብ እያሳለፈ ላለው የመከራ ዘመን ዋናው ምንጭ ሀገር በቀሉ የወያኔ አፓርታይድ ስርአት ነው። ይህን መሰሪ ስርአት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ብቸኛ መፍትሄው፤  የኢትዮጲያ ዲሞክራሲ ሃይሎችን በማስተባበር የነጻነት ትግሉን  በአንድ ማእከል እንዲመራ ሊያደርግ የሚችል፤ ለኢትዮጲያ ህዝብና ለአለም አቀፍ ህብረተሰቡ አማራጭ የሚሆን ሁሉን አቀፍ ያማራጭ ሃይል ወይም የስደት መንግስት ማቋቋም ሲቻል ነው በለን እናምናለን።

የሽግግር ምክር ቤቱ ከመግለጫና ይፋዊ ጥሪ ከማድረግ ባሻገር ከላይ የተቀመጠውን ጭብጥ ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ ቆይቷል። ባሳለፈንው ወር የካቲት 2007፤ ሽግግር ምክር ቤቱ ከሸንጎ ጋር ስምምነት በማድረግ ለዚህ አማራጭ ሀይል መመስረት የመሰረት ድንጋይ መጣሉ አንድ ምሳሌ ነው። በተመሳሳይም ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት በማድረግ ላይ ሲሆን እነኚህን የሁለትዮሽ ውይይቶች ወደወል ውይይቶች ባስቸኳይ እንዲሸጋገር ለማድረግና ያማራጭ ሃይል እንዲቋቋም ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። የሂደቱን ውጤትና፤ ከእያንዳንዱ ድርጅት ጋር የምናደረገውን ሰምምነት ለህዝባችን ይፋ እንደምናደርግ እየገለጽን፤ በዚህ አጋጣሚ ዛሬም እንደወትሮው ነጻነት ናፋቂ ለሆነው ኢትዮጵያዊ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ሲቪክ ማህበራት፤ ለእምነት ተቋሟት፤ ለመገናኛ ብዙሃን (የፓልቶከ ክፍሎች)፤ ታወቂ ምሁራንና አክቲቪስቶች ይህን ወቅታዊ አጀንዳ የግል ጉዳይ በማድረግ አስተዋጽኦና ግፊት ታደርጉ ዘንድ ሃገራዊ ጥሪያችንን ባክብሮት እናስተላልፋለን።

ትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!             የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC                                                                                                           Zehabesha Amharic

የዜጎችን ስቃይ ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል – ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

semayawi14ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

መንግስት በሰማያዊ ፖርቲ ላይ የከፈተውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በአስቸኳይ ያቁም!!!

ሰማያዊ ፓርቲ በየመን፣ ደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እየተከታተለ መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡ በእነዚህ ሀገራት ችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል በማውገዝና መንግስትም መፍትሄ እንዲሰጥ መግለጫ ከማውጣት ባለፈ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል እንዲያስቆም አዲስ አበባ ለሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ደብዳቤ በመጻፍ ፓርቲያችን የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በተመሳሳይ መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ እርምጃ ለመቃወም የጠራውን ሰልፍም በመደገፍ ሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያው ተቃዋሚ ፓርቲ ነው፡፡

ይሁንና የዜጎችን ስቃይ ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል የፈለገው ሕወሀት ኢህአዴግ ሰማያዊ ፓርቲ በወገኖቻችን ላይ ለሚደርሰው በደል መፍትሄ እንዲሰጥ መወትወቱ፣ የፖለቲካ ልዩነታችን ወደ ጎን አድርገን በሰልፉ ላይ መገኘታችን እንዳላስደሰተው ከሰልፉ ቀን ጀምሮ በፓርቲያችን ላይ የተከፈተው ዘመቻ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ መንግስት ሊቢያ ውስጥ በወገኖቻችን ላይ ለተፈፀመው ጭካኔ ምንም አይነት ትኩረት ባለመስጠቱ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማታቸው ያላሰበውን ሰልፍ ጠርቷል፡፡ በጠራው ሰልፍ ላይም መንግስት ለወገኖቻችን ያሳየው ንቀት ያበሳጫቸው ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡ በተቃውሞው ወቅት ከፍተኛ ድብደባ የፈፀመው ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢህአዴግ አባላትን ጭምር ማሰሩ ይታወቃል፡፡ ይህ በሆነበት ወቅት ኢህአዴግ ለተነሳበት ቅሬታና ተቃውሞ ጣቱን ሰማያዊ ፓርቲ ላይ በመቀሰር ከፍተኛ ውንጀላና ዛቻ እያደረገ ይገኛል፡፡

ከሰልፉ ማብቃት ጀምሮም ጉዳዩን ገና ፖሊስ ሳይመረምረው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን ሰማያዊ ፓርቲ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት እየጣረ ነው የሚል ውንጀላ አሰምቷል፡፡ ከዚህ ዕለት ጀምሮ የስርዓቱ አፍ በሆኑት ሚዲያዎች ሁሉ ቀን ከሌሊት ሰማያዊ ፓርቲ ሁከትና ብጥብጥ ሊያስነሳ ነው እያለ እያላዘነ ይገኛል፡፡ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም ተብለው በተጠሩ ሰልፎችም ሁሉ ከአራጁ ቡድን ይልቅ ሰማያዊ ፓርቲ ለመቃወም እየተጠቀመባቸው ይገኛል፡፡

በሰልፉ ዕለት አባላቶቻችን ገና ሰልፉ ሳይጀመርና መስቀል አደባባይ ሳይደርሱ፣ ሁከትና ብጥብጥ ልታስነሱ ነው ተብለው የታሰሩ ሲሆን ሕወሀት ኢህአዲግ እንደሚለው በሰልፉ ላይ ያልነበሩት አባላቶቻችንም እንዲሁም ሰልፉ ካበቃ በኋላ እየታደኑ ተይዘው ታስረዋል፡፡ ይህን ያደረገው የራሱን አባላት ከቀበሌ ደብዳቤ እያስመጣ በፈታበት ወቅት ሲሆን በቦታው ያልነበሩትን አባላቶቻችንን በማሰር የፈጠራ ክስ በመክሰስ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም በፌደራል ፖሊስ አማካኝነት ተደጋጋሚ የስም ማጥፋት ዘመቻ በፓርቲያችን ላይ እያደረሰ ይገኛል፡፡

ትናንት ሚያዝያ 18/ 2007 ዓም ምሽት 2 ሰዓት ዜና ላይ የፌደራል ፖሊስ 7 የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና ከ20 በላይ አባላትን ማሰሩን በማስመልከት ፈፅሞ ከእውነት የራቀ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በእስር ላይ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ቁጥር 6 ብቻ ሲሆን እነዚህ በእስር ላይ የሚገኙ የፓርቲው አባላት እንደማንኛውም ዜጋ ሀዘናቸውን ለመግለፅ ወደ መስቀል አደባባይ በማቅናት በነበሩበት ወቅት ሰልፉ የሚካሄድበት ቦታ እንኳን ሳይደርሱ በደህንነቶች አባላት ታፍነው የታሰሩ ናቸው፡፡ ሰልፉ ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት የታሰሩ የሰማያዊ አባላትን በሰልፉ ላይ ለተፈጠሩት ማንኛውም ድርጊቶች ተጠያቂ ማድረግም በእጅጉ መሰረተቢስ ነው፡፡

ይህ በህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት አማካኝነት እየቀረበ ያለው ክስ እና የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ህወሓት/ኢህአዴግ ለዜጎች ህይወት የማይጨነቅ እና በዜጎች ሞት የራሱን የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ እና ጠንካራ ተቃዋሚ የሆነውን ሰማያዊ ፓርቲን ለማጥቃት እየተጠቀመበት መሆኑን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው፡፡ በፍርድ ቤት ውሳኔ ያልተሰጠበትን ጉዳይ ተጠርጣሪ ከማለት ይልቅ ወንጀለኞች ናቸው በማለት በህገወጥ ስራ ላይ ተሰማርቶም ይገኛል፡፡

ይህ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በዋነኝነት ያነጣጠረው
1- ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ ለማስወጣት እና ምርጫ 2007ን ያለምንም ተቀናቃኝ እና ስጋት ለማለፍ
2- ያለይሉኝታ እና ያለ ሀፍረት የፓርቲ እና የመንግስት ስልጣንን አቀላቅሎ የያዘው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጁ 662/2002ን በሚቃረን መልኩ ያሉትን የመገናኛ ብዙሀንን በሙሉ ተቀናቃኞቹን እና ተፎካካሪዎቹን ለማጥቂያነት እየተጠቀመባቸው መሆኑን ለማድበስበስ
3- ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት ህወሓት/ኢህአዴግ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም የሰማያዊ አመራሮችን እና አባላትን በማሰር ትግሉን ለማዳከም የተወጠነ ሴራ መሆኑን፡፡
4- በተለይም በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ሚዲያዎች በሊቢያ እና በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ህይወት አደጋ ውስጥ እንዳለ እየተገለፀ በሚገኝበት ወቅት እና የኢትዮጵያ ህዝብም በአንድ ድምፅ መንግስት የዜጎችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ እና በአይ ኤስ አይ ኤስ ላይ የአፀፋ እርምጃ እንዲወስድ እየወተወተ ባለበት ወቅት የህዝብን መሰረታዊ ጥያቄ ለማስረሳት እና ለማዘናጋት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያውን ላይ የጭካኔ ድርጊት የፈፀመውን አይ ኤስ አይ ኤስን ወደጎን በመተው ሰማያዊ ፓርቲን የጥቃቱ ዋና አላማ አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

ስለዚህ ሰማያዊ ፓርቲ መንግስት እና የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ከዚህ አኩይ ተግባራቸው የማይታቀቡ ከሆነ ፣የሰማያዊን ስም በሀሰት በማጠልሸት ስራ ላይ የተሰማሩ የመንግስት ተቋማትን እና ግለሰቦችን በህግ ፊት ለማቆም ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን እየገለፀ ሌሎች ተከታታይነት ያላቸውን እርምጃዎችም ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን እያስታወቀ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰማያዊ ፓርቲ ለሚያደርጋቸው ህዝባዊ ጥሪዎች በንቃት ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ሚያዝያ 19/2007 ዓም
አዲስ አበባ

አልሸባብ አይሲስን ሊቀላቀል ነው ተጨማሪ የሽብር ስጋት በኢትዮጵያ

በሶማሊያ የሽብር ተግባራትን በመፈጸም የሚታወቀው አልሸባብ ደመኛና አረመኔውን አይሲስን ሊቀላለቀል መሆኑ ተሰማ፡፡አገራችንን በተጨማሪ የሽብር ስጋት ውስጥ እነደሚጥላት ተገምቷል፡፡

የሶማሊያን ስፊ ግዛት የሚቆጣጠረው አልሸባብ የማእከላዊ ስልጣኑን ካጣ ወዲህ በደረሰበት ወታደራዊ ኪሳራ የአለም አቀፍ አሸባሪው አልቃይዳ ክንፍ በመሆን እያካሄደ ባለው የደፈጣ ውጊያ ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ርቋት በንጹሃን ደም የታጠበች መንግስት አልባ ጦር ሜዳ ከሆነች ከሁለት ዓስርት አመታት በላይ አስቆጥራለች።

ሟቹ አቶ መለስ የቆሰቆሱት የሶማሊያ ችግር እስካሁን አልበረደም፤ የኢትዮጵያን ጦር ጨምሮ ከተለያዩ አፍሪካ ሃገራት የተውጣጡ ወታደሮች የሶማሊያን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር እያደረጉ ያለው ጥረት መና ቀርቶ የእሳቱ ወላፈን ድንበር ተሻግሮ ለዜጎቻቸው ጦስ እስከ መሆን ርቆ የሄደበት አጋጣሚ የሰላም አስከባሪ ሃገራቱን ዜጎች በሰላም ወጥቶ የመግባት ደኅንነት ስጋት ውስጥ ጥሎታል።

ሶማሊያ ውስጥ ወታደሮቻቸውን ካሰለፉ ሃገራት መሃከል በዩጋንዳ እና ኬንያ ዜጎች ላይ ይህ እስላማዊ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን “አልሸባብ” ድንበር ተሻግሮ በንጹሃን ላይ የፈፀመው ዘግናኝ ድርጊት ሳይጠቀስ የማይታለፍ ነው።

አልቃይዳን በይፋ ከተቀላቀለ ወዲህ ከአለም ህዝብ የተገለለው አልሸባብ አለም አቀፋዊ ትኩረትን ለመሳብ በአሜሪካ ላይ ጥቃት ለመፈጸም እቅድ እንዳለው በተደጋጋሚ በሚያወጣቸው የዛቻ መግለጫዎቹ ቡደኑ ሃያል ነን ለሚሉ ሃገራት ሳይቀር ራስ ምታት ሆኗባቸዋል።

በኢህአዴግ ድጋፍ ወፌ ቆመ እያለ የሚገኘውን ሞቃዲሾ ላይ የተገደበ በአምሳሉ የፈጠረውን ስርዓት ባለስልጣናት አልሸባብ ሲሻው በሽብር ጥቃት በመግደል አሊያም እርስ በርሳቸው እንዲናቆሩ ጀሌዎቹን አሾልኮ በማስገባት ከሚፈጽመው ደባ ባሻገር ጊዜ እየጠበቀ ከርቀት በሚያስወነጭፋቸው የከባድ ጦር መሳሪያ አረር የቤተመንግስቱን ሰላም መቅኖ በማሳጣት ሶማሊያ ውስጥ አለ የሚባለውን መንግስት ህግና ስርዓት ትርጉም አልባ አድርጎታል።

የሶማሊያ አለመረጋጋት አገርሽቶ ለጎረቤት ሃገራት ጦስ እየሆነ በመጣበት በአሁኑ ጊዜ አልሸባብ የሽብር ስትራቴጂውን በመቀየር በቅርቡ ኬንያ ላይ በአንድ ዩኒቨርስቲ ማዕከል በክርስትና እምነት ተከታይ ተማሪዎች ላይ የፈፀመውን አረመኔያዊ ድርጊት በሌሎች ላይ አጠናክሮ ለመቀጠል አለምአቀፍ አሸባሪ ቡድን ከሆነው አይሲስ ጋር በመዋሃድ እንደ ሊቢያ ቢጤዎቹ የሰው ልጅን አንገት በካራ ለማረድ የነደፈው እቀድ በአልሸባብ የአመራር አባላት መካከል ንትርክን ፈጥሮ መሰንበቱ ይነገራል። አልሸባብ ከቡድኑ ጋር ለመዋህድ ያቀረበው ጥያቄ ወታደራዊ የሎጀስቲክ አሊያም የሰው ሃይል ድጋፍ ከዚህ ከአረመኔ አይሲስ ለማግኘት እያደረገ ያለው ጥረት የአልሸባብን ወታደራዊ አቅም እየተመናመነ መምጣት በግልጽ የሚያሳይ ጣረሞት ነው በማት አንዳንዶች ይገልጹታል፡፡ በአንጻሩ ሌሎች አልሸባብ አለምአቀፋዊ አቅሙን እያጎለበት የመጣውን አረመኔ አይሲስ ተዋጊዎች ሶማሌያ በማስገባት ኢትዮጵያን በማተራመስ ለመበቀል የታቀደ ስትራቴጂ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ።

በሃይማኖት ሽፋን ምዕራብ አፍሪካ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ቦኮ ሃራም በአካባቢው ሃገራት መንግስታት ወታደሮች በቅንጅት የከፈቱበትን ጦርነት መቋቋም ሲሳነው የቦኮ ሃራም መሪ “ሼካው” ኢራቅ እና ሶሪያ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የዚህ ራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራው አይሲስ አሸባሪ ቡድን አካል መሆኑን መግለጹ ይታወሳል። አልሸባብ ሰሞኑን እያሰማ ያለው ጩኸት ቡድኑን ለሁለት መክፈሉን ቢሰማም ይህ አጋጣሚ በአባላቱ መሃከል የተፈጠረው ልዩነት ሰፍቶ ለአልሸባብ ከሶማሊያ ምደር መጥፊያው ምክንያት ካልሆነ የ አይሲስ ዱካ ሶማሊያ ውስጥ ከታየ ኢራቅ፣ ሶሪያንና ሊቢያን እያተራመስ የሚገኘው ሰይጣናዊ ሃይል ለሃገራችን ሰላምና መረጋጋት በእንቀርት ላይ ጆሮ ደግፍ ከመሆን ሊያግደው የሚችል ምድራዊ ኃይል እንደሌለ በበርካቶች ዘንድ የሚታመን ሐቅ እየሆነ መጥቷል።

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች!

(Ethiopian Hagere Jed Bewadi ለጎልጉል የላኩት)

ክርክር 6፡ ኢህአዴግ እና 1997 ስብርባሪዎች!!!! ግርማ ሠይፉ ማሩ

በዛሬው ሰድስተኛ ዙር የምርጫ ተብዬ ክርክር ጉዳዩ በመሰረተ ልማት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ኢህአዴግ ጎምቱ ያላቸውን ሹሞቹን ለክርክር ይዞ የቀረበበት ቢሆንም ለእኔ ግን ትኩረቴን የሳበው የተከራከሩበት ርዕስ ሳይሆን ተከራካሪዎቹ ሰዎች እና ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ማለት የፈለኩት የመሰረተ ልማት በሚል ርዕስ ክርክር ስመለከት የተገነዘብኩት ጉዳይ ቢኖር ኢህአዴግ ክርክር እያደረገ ያለው የዛሬ አስር ዓመት ለሚዲያ ክርክር ድመቅት ይሰጥ ከነበረው ከቅንጅት ስብርባሪ ጋር አንደሆነ ተረዳሁኝ፡፡ ህብረትም ቢሆን አሁን በመድረክ በኩል በድሮ ግርማ ሞገሱ አይታይም፡፡ እውነቱን ለመናገር አሁን በክርክሩ ላይ የሚገኙት ሰዎች ኢህአዴግ በልኩ የሰራቸው፤ በእግራቸው ገመድ የተበጀላቸው ጭምር ናቸው፡፡ ምንም ቢሉ ማንም ምንም የማይሰማቸው፡፡

ኢዴፓ በ1997 ከተቀናቃኙ መኢህአድ ጋር ያለውን የውስጥ ግብ ግብ ቅንጅት የሚባል ፓርቲ እውን እንዳይሆን በማድረግ፣ አንድ አንዶቹን በግል ታሪካዊ የፖለቲካ ዋጋ አስከፍሎ አሁን ባለበት ደረጃ ይገኛል፡፡ ይህ የኢዴፓ አመራር ውሳኔ ኢትዮጵያ ሀገራችንም በመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ ዋጋ እየከፈለች እንድትገኝ አድርጓል፡፡ በሁለት ሺ ሰባት ምርጫ ኢዴፓ እንደ ፓርቲ መንግሰት እንደማይሆን ቢታወቅም ወደፊት ፓርቲስ ይሆናል ወይ? የሚል ጥያቄ ሁሉ ማንሳት የግድ የሚል ነው፡፡ ይህ በፍፁም ሟርት አይያደለም በምድር የሚታይ ሀቅ ነው፡፡ ለማነኛውም ኢዴፓ የዛሬ አሰር ዓመት በ1997 ክርክር የቅንጅት ፈርጥ ሆኖ ክርክሩን ያደመቀ ቢሆንም ዛሬ ይህን ሊያደርግ አልተቻለውም፡፡ ኢህአዴጎች በጥርስና ጥፍራቸው ቅንጅትን ሲያፈርሱ ያተረፉት ሽራፊ ኢዴፓ አሰር ዓመት አፈር ልሶ መነሳት ሳይችል ቀርቷል፡፡ አሁንም በምድር ላይ እየዳከረ ይገኛል፡፡

ኢዴፓ ማህተም አላደርግም በማለት ያፈረሰውን ቅንጅት ቢያንስ በፍረስራሽ በቅጡ እንዳይሰራ ያደረገው ደግሞ አቶ አየለ ጫሚሶ ነው፡፡ መቼም ይህን ሰም የማያውቅ ያለ አይመስለኝም፡፡ “ቅንጅት” በአቶ አየለ ጫሚሶ ተወክሎ ቅንጅት ቢመረጥ እንዲህ ያደርጋል ይህን ይፈጥራል ሲሉን እኛ የምናወቀው የ1997 ቅንጅት የሌለ መሆኑን፤ የፈለግነው ቅንጅት እንዳይኖር የተሰራው “ቅንጅት” እንኳን ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅም አጀንዳ አይደለም እንደ ድርጅትም ቁመናውን አስተካክሎ የሚሄድ እነዳልሆን እናውቃለን፡፡ እውነቱን ለመናገር እነርሱም በሚዲያ ቀርበው አይተናቸዋል፡፡ ለማነኛውም ይሉሹን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ የሚባለው የዚህ ዓይነቱ ድርጊት ነው፡፡ የቅንጅት ምልክት የነበረው ሁለት ጣት አሁንም “ቅንጅት” ለሚባው ድርጅት ቢሰጥም በተግባር ግን በስራ ላይ እንደሌለ ይታወቃል፡፡ ትዝ ይላችሁ እንደሆን “ጣት እንቆርጣለን” እስክንባል ድርስ ይህች አስማተኛ ምልክት የዛሬ አስር ዓመት የሰራቸው ስራ በእውነት ግሩም ድንቅ ነበር፡፡ የእኛን ቅንጅት ነብስ ይማር ብለናል፡፡

መድረክ አሁን ባለው ቁመና የ1997 ህብረት ሰዎች በተወሰነ ደረጃ ቢይዝም ህብረትን የሚያክል አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ ከምርጫ በኋላ ቅንጅት የሚባል እንዳይኖር የአሁኖቹ መድረኮች ያላቸው ጥላቻ ቀላል አይደለም፡፡ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አሁንም ቢሆን ከቅንጅት መንፈስ ጋር ግብ ግብ ላይ እንዳለ ማወቅ የፈለገ የ1997 ጫወታ አንስቶ መሞከር ነው፡፡ በሌሎቹም የህብረት አባል ድርጅቶች እሰከ ፓርላማ የደረሰ ደባ በቅንጅት ላይ እንደሚሰራበት የሚታወቅ ነው፡፡ የዚህ ደባ ባለቤቶች አሁንም የመድረክ አባሎችና አመራሮች ናቸው፡፡ መድረክ አንድነትን ከሚጠላበት አንዱ ምክንያት በአንድነት ውስጥ የሚታየው የቅንጅት መንፈስ ጭምር ነው፡፡ የአሁኖቹ አመራሮች ከአንድነት ጋር ሲነነጋገሩ የሚሰማቸው ሰሜት በ1997 ህብረት ሆነው ከቅንጅት ጋር የሚያደርጉት ውይይት/ክርክር ነው፡፡ በክርክሩ ውስጥ ሁሌም ጠልፉ መጣል አለ!! የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ልዬ ችሎታ፡፡
አሁን ደግሞብ በብረት ሰንሰለት ተይዞ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ነው፡፡ ሰማያዊ የት ድረስ ይጓዛል? አላውቅም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲም ቢሆን የቅንጅት አብዛኛውን አመራርና አባል ይዞ የተመሰረተው አንድነት ፓርቲ ስባሪ ነው፡፡ ስለዚህ የቅንጅት አካል እንደነበር ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ በሁለት ሺ ሁለት ምርጫ አንድነትን ምርጫው ላይ ውጤታማ እንዳይሆን ከኢህአዴግ ባልተናነሰ ገትረው የያዙት ልጆች ሳይዘገዩ በአምስተኛ ዓመቱ የምርጫ ፈተና ከኢህአዴግ ጋር እንዴት እንደሆነ እየቀመሱት ነው፡፡ በሆነ ባልሆነው ሰማያዊ የሚለው መንግሰትም ከሰማያዊ አልላቀቅ ብሎ ምን ሊያደርግ እንደሚችል እየተጠበቀ ነው፡፡ የኢህአዴግ ትልቅ ግብ በዚህ ምርጫ መንግሰት መመስረት የሚመስለው ካለ ተሳስቷል፡፡ ሰማያዊን ለማዋረድ ነው የሚሰራው፡፡ በኢቲቪ በሰማያዊ ላይ የተያዘው ዘመቻ የአንድ አንድ የህግ ባለሞያዎች ተብዬ አስተያየት ጥፍራችን ውስጥ እንድንደበቅ የሚያደርግ ነው፡፡ እረ በህግ መባል ያለባቸው ናቸው፡፡

ሌሎች ተሳታፊ ፓርቲዎችን ትተን ከላይ የዘረዘርናቸው ፓርቲዎችን ስንመለከት ኢህአዴግ የዛሬ አስር ዓመት ሰንገው ይዘውት ከነበሩ አሁን ግን ምንም ማድረግ ከማይችሉ ደካማ ስብርባሪ ፓርቲዎች ጋር ተራ ገብቶ እየተጫወተ ነው፡፡ ሁሌም እንደምለው ኢህአዴግ ብጤዎቹን በትክክል መርጦዋል፡፡ ከዚህ ከፍ ያለ ጫወታ አይችልም፡፡ ከዚህ ከፍ ካለ ኢህአዴግ ቀልድ አያውቅም ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲል ታንክም ባንክም ለመጠቀም ወደኋላ የሚል አይደለም፡፡ አሁን ለጊዜው በቁጥጥር ስር ያሉ ሚዲያዎች እና ሆዳሞች ይበቁታል፡፡ ታንክ አያስፈልግም ማለቴ ነው፡፡ ሚዲያና ሆዳሙን ለመጥቀም ያህል ባንክ ይጠቀም ይሆናል፡፡
ቸር ይግጠመን!!!!!

(የሊቢያው ጉዳይ) ‹‹አሁንም የመሄድ ሐሳባችንን አልቀየርንም›› በግፍ የተገደሉት የሠፈር ጓደኞች

በየማነ ናግሽ

አሸባሪው አይኤስ ምንም ከለላ በሌላቸው ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ላይ በሊቢያ ሜዲትራንያን ባህር ዳርቻ ላይ የፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊቱን የሚያሳይ ቪዲዮ ከተለቀቀ በኋላ፣ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተቀባብለውታል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ይኼ አስደንጋጭ ዜና ያጥለቀለቀው ማኅበራዊ ሚዲያውን ነበር፡፡
yemane Nagish
ሰላሳ ወጣት ኢትዮጵያውያን የዚህ አስከፊ ግፍ ሰለባ በመሆናቸው በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል፡፡ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ሥፍራ የሚሰጠው የዳግማይ ትንሳዔ በዓል ዕለት በአሸባሪው በአይኤስ የተለቀቀው ቪዲዮ፣ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈጸሙት አሰቃቂ የሽብር ድርጊቶች እጅግ የከፋው ነው እየተባለ ነው፡፡ ይኼ አረመኔያዊ ድርጊት ቀደም ብሎ በሌላ መጥፎ ዜና ከወደ ደቡብ አፍሪካ የታጀበ ነበር፡፡ የደቡብ አፍሪካ በዘር ጥላቻ የተለከፉ ግለሰቦች፣ ‹‹የውጭ አገር ስደተኞች ከአገራችን ይውጡልን፤›› በማለት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ አፍሪካውያን ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ምላሾች ተለሳልሰዋል በማለት ብዙዎችን ሲያበሳጭና ሲያናድድ አንድ ሳምንት አልሞላውም ነበር፡፡

ጥቃቱም በዚሁ አላበቃም፡፡ የመንግሥት ለመንግሥት ግንኙነት በልጦባቸዋል እየተባሉ ሲተቹ የቆዩት የመንግሥት ባለሥልጣናት ምላሽም በዚህ አላበቃም፡፡ በሊቢያ የኢትዮጵያውያን ምሥል እየታየ የተለቀቀው ቪዲዮ እውነትነት ጥርጣሬ ገብቶዋቸው ይሁን ወይም በሌላ ምክንያቱ ባይታወቅም፣ ብዙዎቹ በሊቢያ የተፈጸመውን ድርጊት ፈጥነው ማውገዝ አልቻሉም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንዱ የአይኤስ ሰለባ እህት የወንድሟን አገዳደል ቀድማ መለየት በመቻሏ፣ በተለይ በተለምዶ ጨርቆስ (ቂርቆስ) በመባል በሚታወቀው አካባቢ ሐዘንና ቁጣ ቀሰቀሰ፡፡

በፀጉሩ ምክንያት ቤተሰቡ በቀላሉ መለየት የቻሉት ኢያሱ ይኩኖአምላክ ነው፡፡ ጓደኛው አብሮ መጓዙን የሚያውቁ የወጣት ባልቻ በለጠ ቤተሰቦችም መጠርጠር ጀመሩ፡፡ እሱም የሰለባው አካል መሆኑ ታወቀ፡፡ ድንኳኑ በጋራ ተጣለ፡፡ የቂርቆስ አካባቢም ድባብ በሐዘን ተዋጠ፡፡ ይህ የሆነው ሰኞ ጠዋት ሲሆን፣ መንግሥት የሰጠው መግለጫ አልነበረም፡፡ በተለይ ‹‹የሟቾቹን ማንነት እናጣራለን፤›› የሚል መግለጫ መባሉ ብዙዎችን አስቆጣ፡፡ በሐዘን ቤት የተገኙት ለቀስተኞች በመንግሥት መግለጫ ማዘናቸውን ገልጸው ነበር፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያው ደግሞ ማውገዙን ቀጠለ፡፡ በኢሕአዴግ ደጋፊነታቸው የሚታወቁ ፌስቡከሮች ሳይቀሩ መንግሥትን አወገዙ፡፡ አንዱ፣ ‹‹መንግሥታችን ለመሆኑ የሰብዓዊ ፍጡር ስብስብ ነው ወይ?›› አለ የኢሕአዴግ የምርጫ ቅስቀሳ ሰኞ ማታ ሲተላለፍ አይቶ፡፡ በእርግጥ ወደ ኋላ መንግሥት ስህተቱን ያረመ ይመስላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሐዘን መግለጫ አሰሙ፡፡ በነጋታውም የአገሪቱ ፓርላማ የሦስት ቀናት ሐዘን አወጀ፡፡ የአገሪቱ ባንዲራም ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተደረገ፡፡ የመንግሥትን አቋም የለወጠው የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት ተሰማ፡፡

የሟች ኢያሱ እናት ወ/ሮ አኸዛ ካሳዬ፣ ልጃቸው ወደ ሊቢያ መጓዙን የሰሙት ዘግይተው ነበር፡፡ የበለጠ ቤተሰቦችም ቢሆኑ አላወቁም ነበር፡፡ ጉዳዩ በሁለቱ አብሮ አደጐችና ጓደኞች በሚስጥር የተደረገ ነበር፡፡ አሁን የሰሙትን መቀበል አቅቷቸዋል፡፡ የሰለባዎቹ ቤተሰቦች በሥርዓቱ አልነበረም የተረዱት፡፡ በፌስቡክና በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ነበር ያወቁት፡፡

ሐዘኑ በዚህ አላበቃም፡፡ በትግራይ ክልል የእንትጮ ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆነው የ25 ዓመቱ ወጣት ዳንኤል ሐዱሽ ፎቶም ተለይቶ ተለቀቀ፡፡ ዳንኤል ባለፈው ዓመት ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በዲግሪ የተመረቀ ነው፡፡ በ1982 ዓ.ም. በአስመራ ከተማ የተወለደው ዳንኤል፣ የሁለት ዓመት ሕፃን ሆኖ ወደ አገሩ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ከቤተሰብ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ተወልደ ተክሉ ከተባለው (አሁን ያለበት ሁኔታ አልታወቀም) ጓደኛው ጋር ነበር ወደ ሊቢያ የተጓዘው፡፡ በዚሁ አረመኔያዊ ድርጅት አራተኛ ልጃቸውን ያጡ እናት ወ/ሮ ዛፏ ገብረ ኢየሱስ እንደ ሌሎቹ እሳቸውም የልጃቸውን ወደ ሊቢያ መሄድ አያውቁም፡፡ ሑመራ የስኳር ፋብሪካ ውስጥ እንደሚሠራ ነግሯቸው ነበር የሄደው፡፡ ‹‹በአካባቢው ኔትወርክ አይሠራምና አልደወለም ብለሽ እንዳታስቢ፤›› ብሏቸው ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም. መሄዱን ይናገራሉ፡፡ ሪፖርተር ያናገራት አንዲት ዘመዱ እንደምትለው፣ ‹‹ሥራ አላገኘሁም፡፡ ሰው በዘመድ ነው ሥራ የሚገባው፡፡ እኔ ዘመድ የለኝም፤›› ብሎ ነበር፡፡ ሑመራና መቐለ ተመላልሶ ሥራ በማጣቱ ምክንያት ስደትን አማራጭ አድርጐ መወሰኑን ትናገራለች፡፡

አሁንም መርዶ

በዚሁ አላበቃም፡፡ ባለፈው ሳምንት እሑድ ጀምሮ በሐዘን በቁጣና በተቃውሞ በተጨናነቀው ቂርቆስ፣ አሁንም ሌላ መርዶ ተሰማ፡፡ ከሦስት ወራት በፊት የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀደም ብለው ወደ ሊቢያ ያመሩት ሦስት ወጣቶች ከሰለባዎች መካከል መሆናቸው ታወቀ፡፡ ኤልያስ ተጫነ፣ ብሩክ ካሳና በቀለ ታጠቁ ይባላሉ፡፡ ሁሉም ኑሮ የከበዳቸውና ምንም የሥራ አማራጭ ያጡ እንደነበሩ የሠፈር ጓደኞቻቸው ይናገራሉ፡፡

ከእነዚህ መካከል የበቀለ ታጠቁ የአጐት ልጅ የሆነውን ታምራት ታረቀኝን ሪፖርተር አናግሮት ነበር፡፡ በቀለ ከወልቂጤ ነው የመጣው፡፡ ቤተሰቡ አሁንም ድረስ እዚያው ነው ያሉት፡፡ ሲሄድ አልነገረውም፡፡ መተማ ዮሐንስ እንደደረሰ ግን ደውሎ 11,000 ብር እንዲልክለት ይነግረዋል፡፡ ዱብ ዕዳ ሆኖበት አገር ቤት ልጆች በሰንበት ትምህርት ቤት ተሰብስበው ቲሸርት ያሳትሙ ነበር፡፡ ኃላፊውም በቀለ ራሱ ነበር፡፡ በቀጣይ ዓመት ተመሳሳይ ነገር ለመሥራት ያተረፉትን 3,600 ብርና የቀረውን ጨምሮ ይልክለታል፡፡ ቀጥሎም ከሁለት ቀናት በኋላ ሱዳን ካርቱም ላይ ሆኖ 34,000 ብር እንዲልክለት በደላሎቹ ያስነግራል፡፡ ካልሆነም ወንድሙ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ይነግሩታል፡፡ ሊያገናኙት ግን አልቻሉም፡፡ ወልቂጤ ድረስ በመሄድ ለወላጆቹ ነግሮ ከዚያም ከዚህም ተበድሮ አሰባስቦ አሁንም ሕይወቱን ለማትረፍ ይልክለታል፡፡ እንደምንም ደውሎ አንድ ጊዜ ድምፁን ሰምቷል፡፡ ከዚያ በኋላ አላገኘውም፡፡ አሸባሪው አይኤስ ይህንን ዘግናኝ ድርጊት የፈጸመ ዕለት እሑድ ታምራት አገር ቤት ነበር፡፡ ቀደም ብሎ ያያትን ልጅ ለማጨት ከጓደኛው ጋር ነበር የሄደው፡፡ እንደ አገሩ ባህል ሽማግሌዎች የላከ ሲሆን፣ ከመካከላቸው የሟቹ የወጣት በቀለ አባት አቶ ታጠቁ ይገኙበታል፡፡

እሑድ ከሰዓት በኋላ ‹‹ሰጠናችሁ›› ተብሎ እዚያው የደስ ደስ ፍንጥር አድርገው ነበር ያደሩት፡፡ ሰኞ እዚህ እንደመጣ ይህንን መጥፎ ዜና ታክሲ ውስጥ ይሰማል፡፡ ይደነግጣልም፡፡ ‹‹ቀልቤ ልክ አይደለም፤›› ይላል፡፡ በቀለ መሄዱን ከእሱ ውጪ እምብዛም ሰው አያውቅም ነበር፡፡ ለጓደኞቹ በቀለ እንደሄደ ነግሯቸው በፌስቡክ እንዲያዩ ይጠይቃቸዋል፡፡ ‹‹እኔ ማየት አልቻልኩም፡፡ ድፍረቱም የለኝም፤›› ይላል፡፡ ከዚያ ሐሙስ ጠዋት ሌላ አጐቱ ዘንድ በመሄድ እሱም ከሌሎቹ ጋር እንደሞተ ይናገራል፡፡ በኃላፊነት ከአገር ቤት አስመጥቶ በዕዳ የላከው ልጅ ሐዘን በርትቶበት እንባ እየተናነቀው፣ ከዚያ ውጪ መናገር አልቻለም፡፡ የሦስቱ ወጣቶች ሐዘን የተከናወነው በአንድ ድንኳን ሲሆን፣ የሌሎችም ታሪክ አሳዛኝና ተመሳሳይ ነው፡፡ አንዳች ዕርዳታና ድጋፍ ካልተደረገላቸው በቀላሉ የሚፅናኑ አይመስልም፡፡

በአካባቢው ከተቀመጡት ወጣቶች መካከል መናገር የሚፈልገው ነገር እንዳለ እያሳበቀበት ነው፡፡ ‹‹እባካችሁ ሕገወጥ ስደተኞች አትበሉ፡፡ ልጆቹ ሕገወጥ አይደሉም፡፡ እንጀራ ፈላጊ ናቸው፡፡ ሱዳን ኤምባሲ ከፌዴራል ፖሊስ ጽሕፈት ቤት መቶ ሜትር አይርቅም፡፡ በሕጋዊ መንገድ ነው የሚወጡት፡፡ በሰላምና በስካይ ባስ ነው ተሳፍረው በሱዳን የወጡት፤›› ይላል የሰለባዎቹ ጓደኛ ወጣት ያሬድ አሰፋ፡፡ ‹‹እዚህ አካባቢ ያለው ሰው በሙሉ መሥራት ይፈልጋል፡፡ መንጃ ፈቃድ ማውጣት ይፈልጋል፡፡ አልቻለም፡፡ ክፍያው ቀላል አይደለም፡፡ ለመንግሥት ንገሩልን፡፡ ይቀንስልን፤›› በማለት በተስፋ መቁረጥ መንፈስ ተናግሯል፡፡

የሠፈሩ ልጆች ብሎኬት አምርቱ ተብለው ለሥራ ተሰማርተው እንደነበር ያስረዳል፡፡ የሚሠሩበት የኮንዶሚንየም ሳይት ቃሊቲ አካባቢ በመሆኑ የባሰ ዕዳ አመጣችሁ ተብለው የመንግሥት ትራንስፖርት ተከልክለው በራሳቸው እንዲጓዙ መደረጋቸው፣ በዚህም ተስፋ ቆርጠው ሥራውን እንዳቆሙ ይናገራል፡፡

‹‹እኛም ለመሄድ ነው የምናስበው››

ሮቤል ደፋሩ የኤልያስና የብሩክ ጓደኛ ነው፡፡ ከዋሊያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ስለሺ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አብሮአቸው ተምሯል፡፡ በ2002 ዓ.ም. በኮብልስቶን ሠልጥነዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን ቁጭ ብለናል፤›› ይላል፡፡ ‹‹እኛም ለመሄድ ነው የምናስበው፡፡ ልንከተላቸው ነበር፤›› በማለቱ ‹‹አሁንስ ምን ታስባላችሁ?›› የሚል ጥያቄ ቀረበለት፡፡ ሮቤል ብቻ ሳይሆን አጠገቡ የነበሩት ሌሎችም የሠፈሩ ልጆች አንድ ላይ፣ ‹‹አሁንም እንሄዳለን፡፡ ምንም ተስፋ የሚሰጥ ነገር የለም፡፡ ዕድላችንን እንሞክራለን፤›› አሉ፡፡

በአሸባሪዎች ሊቢያ ውስጥ የተጨፈጨፉ ጓደኞቻቸውን እየተመለከቱ አሁንም ለመሄድ ያስባሉ፡፡ እዚህ አገር ባለው ነገር ተስፋ መቁረጣቸውን ይናገራሉ፡፡ ሄደው ጣሊያንና ጀርመን ገብተው ያለፈላቸው እንዳሉም ያስረዳሉ፡፡

አሸናፊ ቦጋለ የተባለው ወጣት ከመካከላቸው በጣም ተስፋ የቆረጠ ይመስላል፡፡ ‹‹እኛ ምርጫ በመጣ ቁጥር ነው መንግሥት የሚፈልገን፤› በማለት እሱም በኮብልስቶንም፣ በኤሌክትሪክም ሠልጥኖ ምንም መሥራት አለመቻሉን ይናገራል፡፡ ‹‹አንዳንድ ጊዜ የምናገኛትን ብር አጠራቅመን እንሄዳለን፡፡ ሕጋዊ መንገድ ተዘጋ፡፡ እዚህ ያለው ወጣት በሙሉ በዚሁ መንገድ ለመሄድ የተዘጋጀ ነው፤›› ይላል፡፡

ሪፖርተር በአካባቢው ተዟዙሮ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ጥያቄያቸው ተመሳሳይ ነው፡፡ ምንም የሥራ አማራጭ እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ወሮአቸዋል፡፡ አንድ ስሙን መጥቀስ ያልፈለገ ወጣት፣ ‹‹ሌላስ ይቅር እባካችሁ መንግሥት ሊቢያ በአደጋ ላይ ያሉትን ሕይወት ለመታደግ ምን እየሠራ እንደሆነ ጠይቁልን፤›› ይላል፡፡ ‹‹አገር ውስጥ ስላለው ችግር ብናገር ምንም አዲስ ነገር ስለሌለው ባልናገር ይሻላል፤›› በማለት ተንሰቀሰቀ፡፡

ዓምደ ዲኖ የተባለው ሌላው ጓደኛው ግን ጣልቃ ገብቶ፣ ‹‹ስብሰባ ጠርተው ሃምሳ ሃምሳ ብር ሰጥተው ወጣቱ እየሠራ ነው የሚል ፕሮፓጋንዳ ከሚሠሩብን ምን አለ ሥራ ቢፈጥሩልን?›› በማለት ይጠይቃል፡፡

ዳዊት ላቀው የተባለው ሌላው ወጣት ግን ችግሩ ከመንግሥትም አቅም በላይ እንደደረሰ ይናገራል፡፡ ‹‹ምንም ዓይነት የሥራ ዕድል የለም፡፡ የሚወራውና መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ነገር ለየቅል ነው፡፡ ያልፍልናል ብለው ነበር የሄዱት፡፡ አሁን ግን ከቤተሰብም አልፈው አገር አሳዝነዋል፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ ሰው ተሳክቶለታል፡፡ ያንን ስኬት አይተው ነው የተሳሳቱት፤›› ይላል፡፡ እሱም ከመንግሥት የሚጠብቀው አንዳች ነገር የለም፡፡

‹‹ምን ማድረግ እንደሚቻል አይታወቅም፡፡ መንግሥትም የሚቻለው ነገር አይመስለኝም፡፡ ስደት ይብቃ ብለህ የምታስቆመው አይደለም፡፡ ይህንን ያህል ሥራ አጥ ወጣት ማብቃት ከባድ ነው፡፡ መንግሥት እንዴት እንደሚቋቋመው አላውቅም፡፡ ከባድ የቤት ሥራ ነው ያለበት፤›› ብሏል፡፡

ሌላ ‹‹ሕገወጥ›› የሚለው አገላለጽ እጅግ ያስከፋው ወጣት፣ ‹‹ደልቶት ወይም ከመንግሥት ጋር ተጣልቶ አይደለም የሄደው፡፡ ይኼ ነገር ቢታረም ደስ ይለኛል፤›› ብሏል፡፡ የአንድ የመንግሥት ባለሥልጣን አነጋገርንም በመተቸት ‹‹እባክህ ምን አለበት አንድ የሚያሳርፍ ቃል ቢጠቀም፤›› ብሏል፡፡

‹‹ያመለጠው››

በአካባቢው ከተገኙት የሟቾች ጓደኞች መካከል ወጣት ልዑል ሰገድ ንጉሥ አንዱ ነው፡፡ ጉዳት ከደረሰባቸው ጓደኞቹ በፊት ከሌሎች ሦስት የሠፈር ልጆች ጋር ነበር ወደ ሊቢያ የተጓዘው፡፡ ታሪኩን ይናገራል፡፡ ከአዲስ አበባ ትኬት ቆርጠው ባህር ዳር ይደርሳሉ፡፡ ከዚያም መተማ ከደላሎች ጋር ተገናኝተው ወደ ገለባት ሄዱ፡፡ ገለባት ላይ የኢትዮጵያና የሱዳን ሲም ካርድ ተሰጣቸው፡፡ ሁለቱም ይሠራሉ፡፡ ከመተማ ወደ ካርቱም 12,000 ብር ተጠይቀዋል፡፡ ብሩ የሚከፈለው ካርቱም ሲገባ ነው፡፡ እዚህ ያለ ቤተሰብ ነው የላከለት፡፡ የሚቀበሉዋቸው ደላሎች ሱዳናውያን ሲሆኑ፣ አልፎ አልፎ ሐበሾችም አሉ፡፡ ጉዞ በመኪና በመሆኑ በሌሊት ነው፡፡ ገዳራት የሚባል ቦታ ላይ 15 ቀናት ያህል ቆይተዋል፡፡ ‹‹ምንም ምግብ አይሰጡንም፡፡ በረሃብ አልቀን ነበር፤›› ይላል፡፡

ከዚያ ካርቱም ላይ ከሚጠብቃቸው ልጅ ጋር ተገናኝተው፣ ከሌሎች በጐንደር አቋርጠው ከመጡ ሦስት ልጆችም ጋር ተቀላቅለው ሰባት ሆኑ፡፡ በልጁ ቤት አራት ቀናት ቆዩ፡፡ ከዚያ ወደ ሊቢያ ተነሱ፡፡ 28,000 ብርም ተጠየቁ፡፡ ‹‹የተጓዝነው በፒካፕ ሲሆን፣ ደህና ብር የከፈሉት ጋቢና ሌሎቻችን ከ30 በላይ የምንሆን ከኋላ ተጫንን፤›› ይላል፡፡

ለሁለት ቀናት ከተጓዙ በኋላ ሊቢያ ድንበር ላይ የሱዳን ፖሊሶች ይይዟቸዋል፡፡ ፖሊሶቹ ከደላሎች ጋር እያወሩ እንዲከፈላቸው ቢጠይቋቸው አልተስማሙም፡፡ ከዚያ ሦስት ጊዜ አስቁመው ጠየቁአቸውና አልተስማሙም፡፡ ቀጥሎ ወደ ፖሊስ ጣቢያ አስገቡዋቸው፡፡ እስር ቤቱ ውስጥ ብዙ ኤርትራውያንንና ኢትዮጵያውያንን ተመልክተዋል፡፡ አድራሻቸው አዲስ አበባ መሆኑን ተናግረው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ አምስት አምስት ጅራፍ ተገርፈው ወጡ፡፡

ከዚያ ለ15 ቀናት ‹‹ጉዳ›› የሚባለው ማረሚያ ቤት ላይ ታሰሩ፡፡ በቀን ሁለት ሁለት ቂጣና የተቀቀለ ምስር ይሰጡዋቸዋል፡፡ ‹‹እዚያ ውስጥ ብዙ ነገር ብዙ ፈተና ይገጥምሃል፤›› በማለት ለመናገር ያዳገተው ነገር እንዳለ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ከዚያ ወደ ካርቱም መለሱዋቸው፡፡ ስደተኞች ካምፕ ውስጥ ገቡና ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ወሰዱዋቸው፡፡ እነሱም መክረውና የይለፍ ወረቀት ሰጥተው ወደ መተማ መለሱዋቸው፡፡

ልዑል ሰገድ እንደሚለው በዚሁ ጉዞ ላይ ምንም ዓይነት ሕጋዊ መታወቂያም ሆነ ፓስፖርት መያዝ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው መንገድ ላይ አደጋ ሲገጥም ሰው ማንነቱ የማይታወቀው፡፡ ሁለቱ ጓደኞቹ ከመተማ ተመልሰው ወደ ሊቢያ የሄዱ ሲሆን፣ እሱና ጓደኛው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ አንዱ ጓደኛው ጣሊያን ሲገባ፣ አንዱ ወደ ጣሊያን ለመሻገር መርከብ የሚጠበቅበት ሥፍራ ላይ መሆኑን ነግሮታል፡፡ አሁን የደረሰውን አደጋ እያሰበ ‹‹ለበጐ ይሆናል›› በማለት ታሪኩን ቋጨ፡፡ ዋይታው ግን ቀጥሏል፡፡

“መንግሥት የሌለው እዚህ ብቻ ነው!”

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግለጫ

ባለፈው እሁድ አይሲስ ባሰራጨው ቪዲዮ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ሲገደሉ ተመልክተናል። ስለ ቪዲዮው ብዙ ማለት ቢቻልም ወገኖቻችን ከአገራቸው ወጥተው ወደ ተሻለ ኑሮ ፍለጋ መንከራተታቸው ለዚህ ዓይነቱ አሰቃቂ ሞት ዳርጓቸዋል። ከአገራቸው የወጡት እየኖሩ ከመሞት ለመትረፍ ቢሆንም በስደት ደግሞ እጅግ መራራውን የሞት ጽዋ ጠጥተዋል። ይህ የወገኖቻችን ዕልቂት በዓለማችን ላይ በሚገኝ በምንም ዓይነት ቋንቋ፣ አገላለጽ፣ አጻጻፍ፣ እንባ፣ ወዘተ ሊገለጽ የማይችል ነው። ረዳት አልባ ሆነው የተመለከትነው ትዕይንታቸውም በውስጣችን ለዘመናት የማይሽር ቁስል ይዞ ይቀመጣል።

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ዘር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ቦታ፣ ወዘተ ሳይለዩ ይህ በአገር ወገን ላይ የደረሰው ሐዘን በጋራ በመሆን እርስ በርስ በመጽናናት፣ በመበረታታት እንዲወጡ፤ ሌሎችንም በተመሳሳይ የስቃይና የመከራ ሁኔታ ላይ የሚገኙትን ወገኖች ለመርዳት የሚችሉበትን መንገድ እንዲቀይሱ አሳስበዋል። አቶ ኦባንግ ሲቀጥሉም፤

“በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የእነዚህን ለሃይማኖታቸው የቆሙ ጀግና ወገኖቻችንን ተመልክቷል፤ የሞት ከበሮ ቢደለቅባቸውም ሳይፈሩና በድፍረት ሰብዓዊነታቸውን በናቁባቸው አረመኔዎች ፊት ለእምነታቸው ቆመዋል፤

“እኔም ሆንኩ በጋራ ንቅናቄያችን ሥር የሚገኙ ቤተሰቦችና ሌሎች እጅግ በርካታ ወገኖች የተሰማንንን ጥልቅ ሃዘን በምንም ዓይነት ቃላት መግለጽ አንችልም፤ ይህንን ፍጹም አረመኔያዊ የሆነ፤ አንዳች ሰብዓዊነት የሌለበት ድርጊት ባሉት ቃላት ሁሉ ተጠቅመን እናወግዛለን፤ ልጃቸውን፣ ወንድማቸውን፣ አጎታቸውን፣ ወገናቸውን፣ ወዘተ ላጡት ቤተሰቦች እንደ እነርሱ እኩል ማዘን ባንችልም የአንዲት ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል እንደ መሆናችን ይህንን መራር ሃዘን የራሳችን አደርገን በመውሰድ አብረናችሁ እናዝናለን፤ እናለቅሳለን፤ እናነባለን። በዚህ ሃዘን ውስጥ ከፈጣሪ የተሰጠንን የአብሮነት እና የመተባበር መንፈስ በማጎልበት ሁላችንም ሃይማኖታችንን፣ የፖለቲካ አመለካከታችንን፣ ጾታችንን፣ ዘራችንን፣ ዕድሜያችንን፣ ወዘተ ሳንመለከት እንደ አንድ ሰብዓዊ ፍጡር ከወገኖቻችን ጋር አብረን እንዘን፤ እናንባ፤ ከመሰል ሰቆቃ የምንላቀቅበትን እና ዳግም የማናለቅስበትን መንገድ በትብብር እንፈልግ” በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በአገር ውስጥ በህወሃት/ኢህአዴግ አማካኝነት ከሚደርስባቸው የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ስደት፣ የመሬት ንጥቂያ፣ ጭቆና፣ የዘር መድልዖ፣ አሰቃቂ ድህነት፣ ወዘተ ወደ ተሻለ ኑሮ ፍለጋ በየአገሩ እንደ ጨው ዘር የተበተነው የአገራችን ሕዝብ ባለፉት ትቂት ሳምንታት ውስጥ በተለያዩ አገራት የተቀናጀ ጥቃት ሲደርስበት ቆይቷል።

በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከመደብደብ አልፈው ተገድለዋል። ሁለት ኢትዮጵያውያን ጎማ ተደርጎባቸው በእሣት ተቃጥለዋል፤ ነድደዋል፤ እነርሱ ጨምሮ በአጠቃላይ ሶስት መሞታቸው ተነግሯል። የደረሱበት ለማወቅ ባለመቻሉ እንደ ሞቱ ሳይቆጠሩ የቀሩ ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በቅርቡ እንደተነገረው የውጭ ፓስፖርት የያዘ ወይም የደቡብ አፍሪካ መታወቂያ ካርድ የሌለው ማንም ሰው አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል በስፋት በመነገሩ በርካታዎች የሚሄዱበት ባይኖራውም አገሩን ለቅቀው ሄደዋል።

ከዚህም ሌላ ባለፈው እሁድ ከ700 እስከ 950 ስደተኞችን ከመጠን በላይ አሳፍራ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሜዲተራኒያን ባህር በመገልበጧ እጅግ ብዙዎቹ በውሃው ሰጥመው ሲሞቱ ጥቂቶች እንደተረፉ ተነግሯል። ከሟቾቹ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ በስፋት ይታመናል።

ባለፈው ወር በየመን የሚገኙ ወገኖቻችን እዚያ በሚካሄደው ጦርነት ምክንያት መሄጃ አጥተው በመከራ ውስጥ መሆናቸውን ሰምተናል። ከዚህ ባለፈ መልኩም የስደተኛ ካምፓቸው በቦምብ ተደብድቧል ቁጥራቸው ስንት እንደሆነ ለመናገር ባይቻልም ወገኖቻችን በስደት ምድር ህይወታቸው አልፏል። ወደ መቶ ሺህ የሚጠጉ ወገኖቻችን በዚያ እንደሚገኙ ሲታመን ከየመን መውጣት የሚፈልጉት እጅግ በርካታ ቢሆኑም ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የሚፈልጉት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው። ይህ መረጃ የጋራ ንቅናቄያችን በዚያ ከሚገኙትና መከራው ከሚደርስባቸው ጋር በየጊዜው በሚያደርገው የቅርብ ግንኙነት እነርሱንም በዓለምአቀፍ ድርጅቶች ረጂነት ከዚያ ለማስወጣት በሚያከናውነው ሥራ ያገኘነውና ከራሳቸው ከኢትዮጵያውያኑ የተነገረን ነው።

በዚህ ሁሉ ቀውስ ውስጥ በሊቢያ የተከሰተው ጭፍጨፋ ከሁሉ የበለጠና በምንም መለኪያ የማይሰፈር ነው። እንደ ኢትዮጵያዊነታችን በየጊዜው ከምንሰማውና ከምናየው እጅግ የከፋ በመሆኑ ሃዘናችንን የመረረ ያደርገዋል። አረመኔዎቹ ነፍሰበላዎች ወገኖቻችንን ሲያርዱ የተናገሩት ነገር ይህንን የሚያደርጉት ለፈሰሰው የሙስሊም ደም ለመበቀልና ኢትዮጵያ የመስቀል አገር ስለሆነች ነው ብለዋል። ለመቀበል ያልፈለጉት ነገር ቢኖር ኢትዮጵያ የሙስሊም፣ የክርስቲያን፣ የአይሁድ (ፈላሻ) ዕምነት ተከታዮች በጣምራነት ተጋብተው፣ ወልደው፣ ተዋልደው፣ የኖሩባት አገር ናት። በዚህም ለዓመታት በዘለቀው አብሮ የመኖር ህይወት ኢትዮጵውያን በአንድ አገር ዜግነት ብቻ ሳይሆን በደምም ተሳስረዋል። ከዘር፣ ከሃይማኖት፣ ከቋንቋ በላይ ኢትዮጵያዊነት በሚባል ጠንካራ ገመድ ተገምደዋል፤ በሰንሰለቱ ላይለያዩ ተቆራኝተዋል።

ለዚህም ነው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ይህንን አሰቃቂ፣ አረመኔና አሸባሪ ተግባር በገሃድ ወጥተው የኮነኑት፤ ያወገዙት። ንጹሃን በመገደላቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በኢትዮጵያዊነት ስም ወጥተው ኮንነውታል። መግለጫው በግልጽ እንዳስቀመጠው የአይሲስ ተግባር “ኢግብረገባዊ፣ ሕገወጥ፣ አረመኔያዊ እና ከዕምነታን ጋር በቀጥታ የሚጋጭ” ነው በማለት ገልጸዋል። “ስለዚህ በሊቢያ የኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ግድያ እጅግ በከረረ መልኩ የምናወግዘው ሲሆን ይህንን በፈጸሙ ላይ ፍትሕ እንዲበየን እንጠይቃለን” በማለት መግለጫው ድርጊቱን አውግዟል።

ስለዚህ ይህ የአይሲስ የጭከና ተግባር ከሃይማኖት ጋር የተገናኘ ሳይሆን የአምላክን ሥራ እየፈጸምን ነው በሚል ሽፋን የፈጣሪን ሕግ እየጣሱ የራስን ምኞች፣ ስግብግብበት፣ የሥልጣን ጥማት፣ ጥላቻ እና የግል ጥቅም ማሳደጃ ጸያፍ ድርጊት ነው።

ለሌሎች እነዚህ በግፍ የተገደሉ ወገኖች ቁጥር ሊሆኑ ይችላሉ፤ ለእኛ ኢትዮጵያውያን ግን ስም፣ ዕድሜ፣ የሕይወት ታሪክ፣ ማንነት፣ ያላቸው የራሳችንና የቅርባችን የሆኑ ወንድሞቻችን ናቸው። አንዳንዶቹ እየታወቁ በመሆናቸው የእናቶቻቸው፣ የአባቶቻቸው፣ የእህቶቻቸው፣ የወንድሞቻቸው፣ ሃዘን ቅስማቸውን ሰብሮታል። እስካሁን ያልታወቁም አሉ፤ አንዳንዶቹም ሳይታወቁ ሊቀሩ ይችላሉ። እነዚህ ወገኖቻችን የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከአገራቸው ተሰደዱ፤ ኑሮ ሲደላቸው መልሰው ቤተሰባቸውን ለመርዳት ዓላማ አድርገው፤ አልመው ከቀዬአቸው ወጡ፤ “የት ደረሱ” እያሉ አብረዋቸው ሲጨነቁ፣ ሲሰቃዩ፣ የነበሩ ቤተሰቦቻቸው ይህንን ዘግናኝ መልዕክት ሲሰሙ በህይወታቸው የተፈጠረው ጉድጓድ እጅግ ጥልቅ ብቻ ሳይሆን መድረሻም የለውም። ስለ ወገኖቻቸው እያሰቡ ፍትህን ይመኛሉ፤ ግን በዚህ ዘመን ላያገኙ ይችላሉ። ሌላ የሚፈርድ ግን አለ፤ በፍርድ የማያጓድል፤ መማለጃን የማይቀበል፤ እንደ ሰው ያልሆነ! መጽሐፉ እንዲህ ይላል “እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋል።” መክብብ12፡14።

ሌላው የወገኖቻችን ጭፍጨፋ ኢህአዴግ በሚመራት ኢትዮጵያ እንደ አንድ ተራ ዜና መቅረቡ ሃዘናችንን ይበልጥ ያስመረረና ያስከፋ ነው። አናሳ በሆኑት የትግራይ ተወላጆች ነን በሚሉ ቁጥጥር ሥር የሚገኘው ህወሃት/ኢህአዴግ የተጨፈጨፉትን ወገኖቻችንን ጉዳይ ዓለም እየተነጋገረበት ባለበት ወቅት “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እናጣራለን” ማለቱ ለብዙዎቻችን ሁለተኛ ሞት፤ ሁለተኛ መታረድ ነበር። እንዲህ ዓይነት በጣም መረን የለቀቀ ስግብግብነትና ራስወዳድነት ሥርዓት በሆነባት ኢትዮጵያ መኖር ስላቃታቸው ነው ወገኖቻችን አገራቸውን ጥለው የተሰደዱት። ጥቂቶች ሲበለጽጉ እነርሱ የበዪ ተመልካች መሆናቸው፣ የሃብት ክፍፍልና የሥራም ሆነ ማንኛውም ዕድል ለጥቂቶች የሥርዓቱ አቀንቃኞች በመፈቀዱና እነርሱ እንደ ሌላ ዜጋ በመታየታቸው፤ “አገር እያለኝ ከሌለኝ ለምን አገር ፍለጋ አልወጣም” በማለት አገርና ኑሮ ፍለጋ ወጥተው በበረሃ የቀሩ ናቸው። ማነው ለዚህ የዳረጋቸው? ከህወሃት/ኢህአዴግ ሌላ ማን ሊሆን ይችላል!?

አገራችንን ከሁለት ዓስርተ ዓመታት በላይ በመቆጣጠር እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሚመራው በአናሣዎች መሆኑ ግልጽ ነው። ለስሙ “ኢትዮጵያ” የሚል በድርጅቱ መጠሪያ ላይ በመኖሩ ሁሉን ዓቀፍ ለመሆን ቢጥርም እውነታ ግን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሲነጻጸር አናሣ በሆነው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ቁጥጥር ሥር ያለ ድርጅት ነው። ከኢትዮጵያ የህዝብ ብዛት አንጻር ትግሬዎች 6በመቶ መወከላቸው ለዚህ ጉልህ ማስረጃ ነው። የማዕከላዊው ኮሚቴም በአናሳ ትግሬዎች የሚመራ በመሆኑ የአገሪቱ ቁልፍ ክፍለ ኢኮኖሚዎች የሚቆጣጠሩትና የሚመሩት እንዲሁም ውሳኔ የሚያስተላልፉት እነርሱው ናቸው። ስለሆነም ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው አናሳው የትግሬ ድርጅት መሆኑን ይህም ደግሞ በትግራይ ተወላጆች ስም የሚነግድና እወክለዋለሁ የሚለውን ሕዝብ በስሙ የሚያጭበረብር አሸባሪ ድርጅት እንደሆነ ታሪኩ ይመሰክራል። ድርጅቱ በበረሃ በነበረበት ወቅት በተለይ የአሸባሪነት ተግባራት ተሰማርቶ እንደነበር፤ በረሃብ የሚንገላቱ የትግራይ ተወላጆችን የዕርዳታ እህል እንዳያገኙ በመንፈግ እና ሌሎችን እጅግ ሰቅጣጭ የሆኑ ኢሰብዓዊ ተግባራትን በመፈጸም ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያ ማዋሉን የቀድሞ አባላቱ ብቻ ሳይሆኑ በዓለምአቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ ማስረጃዎች ይመሰክራሉ።

ይህ የህወሓት አሠራር አሁንም አንዲት ሉዓላዊት አገርን በነጻ አውጭ ስም እየገዛ ባለበት ወቅትም ቀጥሏል። እኩይ ተግባሩን ለሚደግፉ ጭፍን ዘረኞችና ሌሎች በገንዘብ ለተገዙ ሆድ አዳሪዎች የአገራችንን ሃብት እንደፈለጉ እንዲመዘብሩ ያለከልካይ ፈቅዶላቸዋል። ይህንን ለማጣፋት ሌላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ “አገሪቱ በድርብ አኻዝ ዕድገት ላይ ትገኛለች” በማለት ቀን ለሌት ራሱ በተቆጣጠረው ሚዲያ ያለማቋረጥ ይለፍፋል። ለሚገዛው ሕዝብ ደንታ የሌለው በመሆኑ በአገራቸው እንደ ዜጋ መቆጠር ያልቻሉና ተመጣጣኝ የሃብት ክፍፍል ዕድል ለማግኘት ያልቻሉ በአገኙት ቀዳዳ ከኢትዮጵያ መሰደድ ቀዳሚ ተግባራቸውና የሕወታቸው ህልም ከሆነ ቆይቷል።

የወገኖቻችን መታረድ እና በጥይት መረሸን በዓለም ዙሪያ እንደተሰማ ህወሃት/ኢህአዴግ “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እናጣራለን” በማለት የተናገረው እስካሁን የብዙዎችን ስሜት የረበሸና እያንዳንዳችን በቁም ያሳረደ ጸያፍ ተግባር በመሆኑ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ያወግዘዋል፤ ይኮንነዋል። ሆኖም ራሱ አሸባሪ የሆነው ህወሃት/ኢህአዴግ የሕዝብ ቁጣ እያየለ ሲመጣ የዜናውን መንፈስ በመቀየር “አሸባሪነትን እዋጋለሁ፤ አወግዛለሁ” በማለት ቢለፍፍም ያቆሰለውንና ያደማውን የህዝብ ልብ ሊጠግን አልቻለም፤ አይችልምም!

ጋዜጠኞችን፣ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን፣ የሃይማኖት መሪዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ ወዘተ ያለ አንዳች ጭብጥ እና ማስረጃ እስርቤት በመወርወር አገሪቱን ወደ ከፍተኛ እስርቤትነት የቀየረው ኢህአዴግ በዚህ ተግባሩ ብቻ ሳይሆን ንጹሃንን በማሰቃየት፣ ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ፣ ከመኖሪያቸው በማፈናቀል፣ በመግደል፣ ወዘተ ተግባራት “ዝነኝነትን” የተረፈው ህወሃት/ኢህአዴግ በጥቅም በሚደልላቸው ጥቂቶች አማካኝነት ገጹን ለማስተካከል ቢሞክርም የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት በኢዴሞክራሲያዊነቱና በመብት ረገጣው ላይ ያወጣበት ዘገባ በራሱ ምስክር ነው።

አቶ ኦባንግ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይ ሰሞኑን የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) አራተኛ ባለሥልጣን በሆኑት ዌንዲ ሸርማን አስተያየት ዙሪ የኢትዮጵያውያን መቆጣታቸውን አስመልክቶ ሲናገሩ

“ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ፣ በሊባኖስ፣ በየመን፣ በኬኒያ፣ በማልታ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በግብጽ፣ በሱዳን፣ በዑጋንዳ፣ ወዘተ ከፍተኛ ስቃይ የሚደርስባቸው እንደው በአጋጣሚ አይደለም፤ ምናልባት በርካታዎች ይህንን የወገኖቻችን ሰቆቃ በተደጋጋሚ ከመስማት የተነሳ ሊሰለቻቸው ይችላል፤ ሆኖም ግን እንደ ዌንዲ ሸርማን ለጆሮ የሚከብድ ጭፍን አስተያየት ቢሰማም ግፉና መከራው ግን ለእኛ አዲስ ነገራችን አይደለም፤

“በዖጋዴን በህወሃት/ኢህአዴግ ነፍጥ አንጋቢዎች የተፈጸመው እጅግ ሰቅጣጭና ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀል፤ በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ስልታዊ ጭፍጨፋና የወገን ምክነት፤ በ424 አኙዋኮች ላይ የተፈጸመው ግድያና ዘር ማጥፋት፤ የ1997ቱ ምርጫ ተከትሎ በአዲስ አበባ ብቻ በ197 ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ግድያ፤ ለቁጥር የሚያታክቱ ኦሮሞ ወገኖቻችን በየጊዜው መገደላቸውና እስርቤቱን ማጣበባቸው፤ በአፋር ሕዝብ ላይ የሚደርሰው የማያቋርጥ ግፍ፤ በእያንዳንዱ የአገራችን ክልል በወገናችን ላይ የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ ስንቱን ቆጥረን ልንዘልቀው እንችላለን። በአይሲስ ከተገደሉት አንዱ ወገናችን ህወሃት/ኢህአዴግ ኦሮሞዎችን ከአዲስ አበባ ዙሪያ በሚያፈናቅልበት ወቅት ተቃውሞውን ያሰማና የተማሪዎች መሪ የነበረ ሲሆን በዚህ ተግባሩ እንደሚታሰር በሚያውቅበት ጊዜ አገር ጥሎ የወጣ ነው። ስለዚህ እውነተኛው የአገር ውስጥ አይሲስ ህወሃት/ኢህአዴግ ካልሆነ በስተቀር ማን ሊሆን ይችላል በማለት ብዙዎች ለጋራ ንቅናቄያችን ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ መልዕክቶች በመላክ ምሬታቸውን እየገለጹ ነው” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ሟቾቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እየመረመርኩ ነው” በማለት በሞቱት ወገኖቻችን ላይ ሲያላግጥ የነበረው ህወሃት/ኢህአዴግ ሁኔታው አላምር ሲለው ሶስት ቀን የሃዘን አዋጅ አወጀ። ድርጊቱ የለበጣ እንደሆነ እና በግዴለሽነት የተደረገ ለመሆኑ አንዱ ማስረጃ ራሱ በተቆጣጠረው 547 ወንበር ባለው ፓርላማ ጉዳዩ ቀርቦ ሲታወጅ የተገኙት 300 አካባቢ የሚሆኑ የፓርላማ አባላት ወይም 56በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው። ሌሎቹ የት ሄዱ? ጉዳዩ አይመለከታቸውም? “በልማት ሥራ ተጠምደው” ነው? ሟቾቹ ወገኖቻቸው ስላልሆኑ ይሆን? ወይስ የሟቾቹ ጉዳይ በክልል የሚታይ ይሆን? ወይስ የ30 ወገኖች ህልፈት የአንድ ሟች ጠ/ሚ/ር ህልፈት ጋር የሚወዳደር አይደለም? ሕዝብ እስኪበቃው ታዝቧል፤ ጉዳዩንም መዝግቧል!!

ይህ ብቻ አይደለም ሃዘኑን እንዲገልጽ የተጠራው ሕዝብ ህወሃት/ኢህአዴግ ኢትዮጵያውያን ከእምነታቸውና ከባህላቸው ውጭ እንዴት ሃዘናቸውን መግለጽ እንዳለባቸውና ማዘን እንዳለባቸው “ንቃት” ለመስጠት የሞከረበት እንደሆነ ለማየት ችለናል። ለመለስ ዜናዊ በየመንገዱ፣ በየቱቦውና በየተገኘበት ቦታ እንዲለቀስ ፈቃድ ሲሰጥ፤ ሲደሰኮር፣ ሲተወን፣ ወዘተ አሁን ለምን ተከለከለ? ለምንስ ለቅሶ በትዕዛዝ ሆነ? ይህ በእውነት እጅግ የዘቀጠ የህወሃት/ኢህአዴግ ጸያፍ ተግባር ነው። ሰልፈኛውም ለዚህ ነው መንግሥት የሌለው እዚህ ብቻ ነው በማለት ምሬቱ የገለጸው፡፡

ከአገራቸው የሚሰደዱትን “ህገወጥ” በማለት ለመጥራት ምንም የማይጨንቀው ህወሃት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎችን ዜጎች አገር ጥለው እንዳይሰደዱ እንዲመክሩ ትዕዛዝ እየሰጠ እንደሆነ ተሰምቷል። ካልሆነ ቀድሞውኑ “ህገወጥ” ይላቸው እንደነበር አሁን ደግሞ ለሞታቸው ተጠያቂው ራሳቸው መሆናቸውን የሃይማኖት መሪዎች እያስጠነቀቁ እንዲነግሩ ተጽዕኖ እያደረገ ነው።

በመሠረቱ የሃይማኖት መሪዎች የዕምነታቸው ቀኖና በሚያስተምረው መሠረት ሃይማኖታቸውን መከተል እንዲችሉ ነጻነት ሊሰጣቸው ይገባል። እውነትን እንዲናገሩ፤ ግብረገብነትን ያለፍርሃት እንዲያስተምሩ፤ ሕዝቡን ሃይማኖታዊ መብቱን እንዲያስተምሩ ነጻ መሆን ይገባቸዋል። ችግሩ ያለው ህወሃት በሚከተለው እኩይና ኢግብረገባዊ ሥርዓት መሆኑን ያለፍርሃት ያመኑበትን በጨዋነት እንዲያስተምሩ፤ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ሊኖር እንደሚገባ፤ ፍትሕ በሚገባ መበየን እንዳለበት፣ ፈጣሪ ሁሉንም በማያዳላ የፍርድ ወንበር ፊት እንደሚያቀርብና ቀኑን ጠብቆ ፍጹም ፍርድን እንደሚሰጥ፣ ሃብት፣ ወርቅና ዝና እንዲሁም የሃሰት እንባ በዚያ የፍርድ ቀን ሊያስጥሉ እንደማይችሉ፤ አገር ማለት ክቡር መሆኗን፤ የአባቶችና ቅድመ አያቶች አጥንትና ደም አገራችንን እንዳስከበሯት ሁሉ አሁን ጥቂቶች የሚፈነጩባት ሳትሆን የሁሉም መሆኗን፤ ብልግና፣ ዋልጌነት፣ በሥልጣን መባለግ፣ ስግብግብበት፣ ዘረኝነት፣ ራስ ወዳድነት፣ ጥላቻ፣ ጭከና፣ ወዘተ እኩይ ተግባራት መሆናቸውን በመግለጽ ሕዝቡን ግብረገባዊነት እንዲስተምሩ ፍጹም ነጻነት ሊሰጣቸው ይገባል እንጂ የህወሃት/ኢህአዴግ የፖለቲካ መጠቀሚያ ሊሆኑ ፈጽሞ አይገባም። እስካሁንም በመሆን ራሳቸውንና ኅሊናቸውን የሸጡ የሃይማኖት መሪዎች ከዚህ እጅግ እርኩስና ጸያፍ ተግባራቸው መታቀብ፤ ካስፈለገም እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው የሰማዓትነት ጽዋ በመጠጣት አርአያ መሆን ካልቻሉም ለእውነት ሲሉ ከያዙት የኃላፊነት ቦታ በራሳቸው ፈቃድ ሊነሱ ይገባቸዋል።

ይህ ብቻ አይደለም የራሱን የሚሰነፍጥ ቁሻሻ ለመሸፈን የሚጥረው ህወሃት/ኢህአዴግ ሰው አስተላላፊዎችን ለዚህ ተግባር ለመወጀልም ይፈልጋል። አቶ ኦባንግ በዚህ ጉዳይ ላይ ሲናገሩ፤

“እርግጥ ነው ሰው አስተላፊዎች ራሳቸውን ለአደጋ ባጋለጡ ወገኖች ላይ የራሳቸውን ጥቅም እንደሚያሳድዱ ይታወቃል፤ ግን ዋናው የችግሩ ሥር ምንድነው? ለምንድነው ይህንን ዓይነት አደጋ እያለ እጅግ በርካታ ዜጎች ከአገራቸው አሁንም የሚሰደዱት? ህወሃት/ኢህአዴግ ችግሩን ወደሌላ ለማላከክ ከመሞከሩ በፊት ራሱን በመስታወት ሊያይ ይገባዋል፤ እንዲያውም ከአንዳንድ ዘገባዎች ለመረዳት እንደቻልነው በዚህ ዜጎችን ለአደጋና ለሞት በሚደርስ ህገወጥ የሰው ማስተላለፍ ንግድ ውስጥ የህወሃት/ኢህአዴግ ጥቅመኞች እንዳሉ ማስረጃዎች አሉ” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ኢህአዴግ የመረጃ አፈና ሊያደርግ ቢሞክርም በተለያዩ የዜና አቀባዮች በግልጽ እንደታየው ሕዝባችን ሐዘኑን በነቂስ በመውጣት ገልጾዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ኦባንግ ሲናገሩ፤

“ልክ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተመለከተው መልካሙ ሳምራዊ ሃይማኖትን፣ ዘርን፣ ጎሣን፣ የፖለቲካ አመለካከትን፣ ወዘተ ሳይመለከት መንገድ ላይ ተዘርሮ ለነበረው ወገን ሰብዓዊነት አነሳስቶት ዕርዳታውን እንደለገሠ ሁሉ የጋራ ንቅናቄያችን የማንንም ጎሣ፣ ዘር፣ ሃይማኖት፣ ወዘተ ሳንመለከት ዕርዳታ መለገስ በሚገባን ቦታ ሁሉ ፈቃደኝነታችንን ማሳየት እንዳለብን ያምናል፤ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በዚህ የታወቅን ብቻ ሳንሆን በተግባርም የምንፈጽም መሆናችንን በተደጋጋሚ እንዳሳየነው ሁሉ አሁንም በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኘው ወገን ሁሉ ከእኛ ለተለዩን ወገኖች ያሳየው የሃዘን ትብብር የሁላችንንም ስሜት የነካ ነው፤ ይህም ደግሞ ማንም የፈለገውን ያህል ኢትዮጵያዊነትን ለማፍረስ ቢሞክር፤ የፈለገውን ቢጥር እንደማይሳካለት ያረጋገጠ ተግባር ነው፤ ኢህአዴግም ከዚህ ሊማር የሚገባው ታላቅ ትምህርት ቢኖር ለ25 ዓመታት አፈረስኩ ብሎ ያሰበው ኢትዮጵያዊነት የተዳከመ ቢመስልም ፈጽሞ እንደማይፈርስ፤ መሠረቱም የጸና፤ አዲሱ ትውልድ እንኳን ሳይቀር በጽናት የሚጠብቀው እንደሆነ ነው። ከዚህ አንጻር የህወሃት/ኢህአዴግ የዘር ፖለቲካ መርዝ እንዳልሰራ ይበልጡንም የከሰረ መሆኑን ያረጋገጠ ሃቅ ነው።

“ስለዚህ የእነዚህ ወገኖቻችን ዕልፈት ሁላችንንም በአንድነት ሊያስተሳስረን የሚገባ መሆን አለበት፤ ልዩነቶቻችንን በመከባበር የምንመለከትበትና ኢትዮጵያዊነታችን ከምንም በላይ እንደሆነ የምናሳይበት ሊሆን ያስፈልጋል፤ እንዲህ ባለው ኅብረት ለወገኖቻችን መሰደድና መከራ ማየት ምክንያት የሆነውን ሁሉ የመታገል ኃላፊነት የእያንዳንዳችን ነው፤ በየአረብ አገራትና በየቦታው በስደት እንዲሁም በሌላ ምክንያት ወገኖቻችን እስከመቼ እያለቁ ይኖራሉ? ይህንን የማስቆምና ዳግም በወገኖቻችን ላይ እንዳይደርስ የማድረግ ሃላፊነት ያለው በህወሃት/ኢህአዴግ እጅ ሳይሆን በእያንዳንዳችን ዘንድ ነው፤ መብታችን በማንም የሚሰጠን ወይም እየተቆጠበ የሚሰፈርልን ሳይሆን ስንወለድ አብሮን የተወለደና ከፈጣሪ የተሰጠን የማይገሰስ፣ የማይሻር፣ የማይለወጥ፣ የማይነካ ነው፤ ስለዚህ አስቀድመን በማንም የማይገሰሰውን መብታችንን እንወቅ ከዚያም እናስከብር ቀጥሎም በተግባር እናውለው ለሌሎችም አርአያ እንሁን” በማለት አቶ ኦባንግ ለኢትዮጵያውያን ጥሪ አስተላልፈዋል።

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ እነዚህን ህይወታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ያለፈውንም ሆነ ከዚህ በፊት በህወሃት/ኢህአዴግ እኩይ ተግባር ህይወታቸውን ያጡትን ወገኖቻችን ሁልጊዜ ሲያስታውስ፣ ሲዘክር ይኖራል። ለቤተሰብና ወዳጆቻቸው ሁሉ ከፈጣሪ ዘንድ መጽናናትን ይመኛል። ሁልጊዜ ግን በሃዘንና በቁዘማ ብቻ አንኖርም፤ ይህ የሚያበቃበት ዘመን እንዲመጣ ከምንጊዜውም በበለጠ ይሰራል፤ አንገታችንን ደፍተን ሳይሆን አባቶቻችን ባጎናጸፉን ነጻነት እንደገና እኛም ይህንን ነጻነት ለወጪው ትውልድ የምናስተላልፍበት አዲስ ኢትዮጵያ እንድትመሠረት ተግባሩን በትጋት ማከናወኑን ይቀጥላል። ዓላማውን የሚደግፉ ሁሉ ከጎኑ እንዲቆሙ በድጋሚ ጥሪ ያቀርባል።

የሃይማኖት መሪዎች ህዝባችንን በማጽናናት ብቻ ሳይሆን ሞራሉንም ከፍ በማድረግ የሚጠበቅባችሁን ተግባር እንድትፈጽሙ የጋራ ንቅናቄያችን ጥሪ ያደርጋል። ያላችሁ ኃላፊነት በሰውና በፈጣሪ መካከል ያለ በመሆኑ በሁለቱም ተጠያቂ መሆናችሁን አውቃችሁ እውነትን በትጋት በመስበክ የህዝባችንን መንፈስ ወደ ላቀ ደረጃ የማድረስ አምላካዊ ግዴታ አለባችሁ። የወሰዳችሁት ስምና “ማዕረግ” የሹመት ወይም ራስን ከፍ የማድረጊያ እንዳልሆነ ከእኛ በላይ እንደምታውቁት ሁሉ ለተሰጣችሁ ስም ኑሩ! ኃላፊነታችሁ መስዋዕትነትን የሚጠይቅ መሆኑን የምትከተሉት የተቀደሰ መጽሐፍ ተግባራዊ ምሳሌ እየሰጠ የሚያስተምር መሆኑን እንደምታውቁት ሁሉ ታሪካቸውን እንደምታነቧቸውና እንደምትሰብኳቸው የሃይማኖት አባቶች የሰማዕትነት ህይወት መኖርን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር እንድትፈጽሙ የጋራ ንቅናቄያችን በጥብቅ ያሳስባል። ይህም የግድ ህይወትን መሰዋት ላይሆን ይችላል፤ መስዋዕትነት ከትንሽ የሚጀምርና በየዕለቱ የሚያጋጥም የግል ጥቅምን ከመሰዋት የሚጀምር መሆኑን በውል ትረዱታላችሁ ብለን እናምናለን። የሃይማኖት አባቶች የሚያስተምሩት መንገድ ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ድርጅት መርሃግብር ፍጹም የላቀ እንደመሆኑ የህዝባችንን የመንፈስ ልዕልና ከፍ የሚያደርገውና ከፈጣሪ ለተሰጠው መብቱ በጽናት እንዲቆም የሚያደርገው እንደሆነ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ያምናል።

ስለሆነም ሁላችንም በዚህ ሃዘን ተቆጭተን ብቻ ሳንቀር ይልቁንም በህዝባችን መካከል ሰላም ፈጣሪዎች፣ ዕርቅ መስራቾች፣ ስምምነት አድራጊዎች ሆነን በትጋት መስራት አለብን። ይህ ካልሆነ እና ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማናችንም ለብቻችን ነጻ መሆን አንችልም። መውደቃችንም ሆነ መነሳታችን እርስበርሱ የተገመደና የተሳሰረ ነው።

አሁንም በአደጋ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን አምላክ እንዲታደጋቸው እንመኛለን፤ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚደርስብንን ግፍና መከራ ተመልክቶ ሰላምን እና ዕረፍትን የምናገኝበትን ዘመን ያቅርብልን። ሁላችንንም በትጋት ለመሥራት እንድንችል ጽናቱ ይስጠን።

በድጋሚ ለወገኖቻችን እና ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ከፈጣሪ ዘንድ መጽናናትን እንመኝላቸዋለን።

ኢትዮጵያችን ለሁላችንም ትኑርልን!!

የታሰርኩ ለታ – ኤዶም ካሳዬ አዘጋጅ Soliyana S.Gmichael

 ”   ከጥቂት ሰአታት በኋላ የእግር ኮቴ ስንሰማ ተሽቀዳድመን በቀዳዳ ስናይ ማህሌትን ወደ ሌላ ክፍል ሲያስገቧት አየሁ ፡፡ ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ አለቀስኩ ”

አርብ እለት መስሪያ ቤቴ ጎተራ ስደርስ 1.30 አካባቢ ነው በዚያ ጠዋት ቢሮ መግባት ስላልፈለኩ ለአንድ ሰአት ያህል ትዊተር ላይ ወሬ ስለቃቅም ቆየሁና 2.30 ላይ ቢሮ ገባሁ ፡፡ ጠዋቱ የተለየ ስራ የለውም ነበር የእቅድ ዶክመንቶች ማገላበጥ የስልጠና ዝግጅት እና የመሳሰሉትን ስሰራ ቆየሁ ፡፡ አዲስ ሰራተኛ ስለሆንኩ ብዙውን ጊዜዬን የስራውን ባህሪይ ለማወቅ ነው የማጠፋው ፡፡ ምሳዬን ከበላሁ በኋላ የምሳ እረፍት እስኪያልቅ ከሶሊ ጋር ስካይፕ አወራን፡፡  ከሰአት በኋላ አንዲት የስራ ባልደረባዬ መጥታ ደሞዝ መውጣቱን እና አዲስ ጭማሪ መኖሩን ነገረችኝ ፡፡ አዲስ ደሞዝ ጭማሪ ላይ መጣሽ እድለኛ ነሽ እያሉኝ በደስታ የተሞላ የቢሮ ካባቢ ላይ ስንሳሳቅ ቆየን፡፡  10 ሰአት አካባቢ አንድ ከአመታት በፌት ትምህርት ቤት የማውቀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የደህንነት ሰራተኛ ነኝ እያለ የሚያዋራኝ ወዳጄ ደወለልኝ፡፡ በዚያን ሰሞን በዞን9 አባላት ጓደኞቼ ላይ አንድመሰክር አንደ ጓደኛ አንደመምከር አንደደህንነት በማስጠንቀቅ ሲያባብለኝ ከርሟል፡፡  አንገናኝ ሲለኝ መልሼ እደውልልሃለሁ ብዬው ዘጋሁት ፡፡ ከዚያ አንዲት ሴት ጓደኛዬን ከቢሮ ከመውጣቴ በፌት የት አንደሆነች ጠይቄያት ብሄራዊ አካባቢ መሆኗን ስትነግረኝ ሃሮ ካፌ አንገናኝ ብያት ዘጋሁት ፡፡ ስካይ ላይ ከሶሊ ጋር ስለደሞዝ ጭማሪ እና የመሳሰሉት አውርተን ማታ እቤት ስገባ ትዊተር ላይ እናወራለን ብያት ተሰነባብተን ከቢሮ ለመውጣት ተዘጋሁ፡፡ ከመውጣቴ በፌት የእስክንድር ጽሁፎች ስብስብ ከሆነው ፒዲኤፍ ላይ ቀንጭቤ ትዊተር ላይ ለጥፌ መውጣቴ ትዝ ይለኛል፡ እየወጣሁ እያለ ደህንነቱ ጓደኛዬ ድጋሚ ደውሎ አንገናኝ አለኝ ፣ ብሄራዊ እየሄድኩ አንደሆነ እና ሰው አንደቀጠርኩ እዛ ከመጣ አንደማገኘው ነግሬው ዘጋሁት፣ ሃሮን አላውቀውም ብሎ ጣፋጭ ካፌ ልንገናኝ ተስማማሁ፡፡

ብሄራዊ ስደርስ ጓደኛዬ ስላልደረሰች ጣፋጭ ካፌ  እሱን አንደማገኘው እና ስትደርስ አንድትነግረኝ ነግሬያት ወደጣፋጭ ካፌ ገባሁ ፡፡ ቤቱ በጣም ሙሉ ነው ስደውልለት ትራፌክ ይዞኝ ነው መጣሁ አለኝ፡፡ ከአንድ ከ30 ደቂቃ በኋላ መጣ፡፡ ፌቱ ላብ በላብ ሆኗል፡፡ (በነገራችን ላይ ይህ የትምርህት ቤት ወዳጄ አብሮኝ የበላ አብሮኝ የጠጣ አብረን የሳቅን ብዙ ነገር ያወራን ነው ፣ ለደህንነት እሰራለሁ ከማለቱ ከ2 አመት በፌት ጀምሮ በደምብ ነው የማውቀው) ስለነፍሰጡር ባለቤቱ ደህንነት ጠየኩት ደህና ናት አለኝ፡፡ ፌቱ ግን መረበሽ ይታይበታል፡፡ ያዘዘውንም ማኪያቶ ሳይጠጣ ሂሳብ ከፍሎ ለመሄድ መዘገጃጀት ጀመረ ፣ ለምን እንደፈለገኝና ምን እነዳጣደፈው ስጠይቀው ክላስ አለብኝ መሄድ አለብኝ አለ፡፡ቀና ስል በመስኮቱ ማዶ አንድ ሰሞን ሲያናግረኝ የነበረ አንድ ሌላ የደህንነት አባል አየሁ ያን ጊዜ የሆነ ነገር አንዳለ ጠረጠርኩኝ |፡፡ ወዲያው ስልኬ ጮኽ።  ሶሊ ነበረች ( ያኔ ስለእስሩ ሰምታ ቼክ ልታደርገኝ አንደነበር አላወኩም) ስልኬን ይዜ ስነሳ ተከትሎኝ ስልክ የሚያወራ መስሎ አጠገቤ መጣ፡፡ ደህና ነኝ መልሼ እደውልልሻለሁ ብያት ዘጋሁት ፡፡

ወዲያው ልሂድ ብሎ ወጣ ጣፋጭ በር ላይ ተሰነባበትን ፡፡ ወዲያው አስፓልቱን ስሻገር አንድ መኪና መንገድ ዘጋብኝና ሁለት ተራ ወንበዴዎች የመሰሉ ሰዎች አንድገባ አዘዙኝ፡፡ አልገባም አልኩኝ ፡፡አንደኛው እጄን ጠምዝዞ አስገድዶ ወደመኪናው መራኝ ያኔ መከራከሩ እንደማያወጣ ገባኝ፡፡ ከኋላ አስገብተውኝ ግራና ቀኝ ተቀመጡ፡፡ መኪናዋን ይኸው የትምህርት ቤት ወዳጄ ይዟት እንዳየሁ አስታወስኩ፡። ቆሻሻና ዳሽ ቦርድ የሌላት  መኪና ናት፡። ከነሹፌሩ የቀን ስራ ሲሰሩ ውለው ያላባቸው የሚመስሉ ሶስት ወጣቶች አሉ፡፡ ጋቢና ያለው ወጣት “ኤዲ አንዴት ነሽ ?” አለኝ ጸጥ አልኩኝ፡፡ ፓሊስ ጣቢያ ለጉዳይ አንደፈለጉኝ እና ቶሎ አንደምለቀቅ ተናግሮ ሊያረጋጋኝ ሞከረ፡፡  ሹፌሩ ያለምንም ማቅማማት ጥቁር አንበሳ እና ባንኮዲሮማ ህንጻ ጋር ያሉትን መብራቶች እየጣሰ ጉዞ ወደፒያሳ ሆነ፣ ምን እነዳጣደፈው እንጃ ።። ቤተሰቦቼ ጋር አንድደውል ይፈቀድልኝ ብልም ስልኬን ወስደው ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ ፡፡ ማአከላዊ ስንደርስ 12.50 አካባቢ ሆኗል፡፡ መደበኛ ምዝገባ ተደርጎልኝ ንብረቶቼን አስረከብኩ ፣ እርቃኔን ከሆንኩ በኋላ ቁጭ ብድግ እያልኩ ሰውነቴ ሁሉ ተፈትሿል፡፡ ከታሰሩ ሴቶች ጋር ስቀላቀል እራትና የሌሊት ልብስ ሰጡኝ፡። ከጥቂት ሰአታት በኋላ የእግር ኮቴ ስንሰማ ተሽቀዳድመን በቀዳዳ ስናይ ማህሌትን ወደ ሌላ ክፍል ሲያስገቧት አየሁ ፡፡ ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ አለቀስኩ ፡፡ ቤተሰቦቼ ልጃችን ምን ዋጣት ብለው አንዴት አንደሚነጋላቸው እየተጨነኩ ነጋ፡፡

“I saw Mahlet being taken to another room, I cried for the first time” – Edom Kassaye
That Friday morning I spent an hour on updating myself on Twitter and entered office at 8:30 AM. Since I was a new employee, I spend much of my time in understanding my job’s description. After I ate my lunch, I skyped with Soli.  In the afternoon, a colleague came and informed me that the salary is released and there is also a new incremental change in our salary. My colleagues shared their happiness with me and congratulated me for being a staff at this time. Around 4 PM a friend of mine, who is my school friend years ago and who now said he is working as security agent for the government, called and asked me to meet him. I hang up the call by letting him  know that I will call him back. Before I get off from work, I called to my friend and agreed to meet around National Theater at Haron Cafe. I had a brief skyping with Soli and informed her about the incremental change in our salary and had an appointment with her to talk through twitter when I get home. Lastly, I twitted a quote from Eskinder’s writing, and then, I got off from work. While I was in my way to meet my friend, my friend- the security agent-called me. I informed him about my appointment because he insisted I agreed to meet at Tafac’h Cafe.

When I arrived at the Café, he was not around.  He came after 30 minutes. he was sweating. (Btw this person was a good friend of mine with whom I had good times for the last two years, I had always considered him as a friend)  I asked him about his pregnant wife and he answered that she is doing good. Yet, from his face I learned that he was disturbed.  Before he finished his Macchiato, he wanted to pay the bill and go. When I scanned the surrounding, I saw another security agent, who had been contacting me and suspected that there is something going on. In meantime, Soli called me and when I try to talk with her a bit away from him, he followed me as if he is also speaking through phone.  So, I informed Soli that I will call her back and hang up the phone.( At that time, I did not know that Soli was aware of the crackdown and she called me to check the situation I am in.)

When I crossed the main traffic road, after finished talking to him, a car closed my way and two security agents-who look liked like gang of robbers- asked me to enter into the car. But I denied. One of them wringed my hand and forced me in the direction of the car. They forced me to enter the car in the backseat in the middle of two of them. I remembered that my school friend used to drive this car.

The car was very dirty, so us my detainers. There were three security agents in the car, who sweated as if they spent the whole day as daily laborers. The guy, who sat nearby the driver, asked me “Edi, how are you doing?”. I remained silent. He tried to cool me down by saying that they want to talk to me at the police station and I will be released sooner.I asked them to call to my family but they denied me and confiscated my phone. It was around 6:50 PM when we arrived at Me’akelawi. I went through regular registration, submitted all my belonging materials, and investigated while I was naked. When I joined the women inmates, they gave me night close and a dinner. After few hours, we heard footsteps and when I saw through a hole, I saw mahlet being taken to another room. Then, for the first time since I get detained I cried. I was stressed by thinking of what my family would think of my disappearance and did not able to sleep the whole night.