የታረዱት ነፍሳት ጩኸት፣ በሊቢያ ለተሰውት ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ሞኑመንት ላይ May 10, 2015 የተደረገውን መታሰቢያ ከአዘጋጁት ማህበራት ህብረት የወጣ መግለጫ

በሰብሰባው የነበሩት እነ መምህር ተስፋዬ መቆያ “ይህ አዝማሚያ ከኢህአዴግ መንግሥት ጋራ ያጋጨናል” የሚል ሀሳብ አቀረቡ። “የፈጣሪ ትልቁ ጉዳይ በአምሳሉ የፈጠረው ሰው ነው። ሲወድቅም፤ አምላክ የሰውነትን ባህርይ በመዋሀድ እንደሰው በመውደቅ ከወደቀበት ያነሳው ክቡር ነው። ታዲያ በፈጣሪ እጅግ የተከበረ ሰው በኢህአዴግ አልተዋረደም? ነው የምትሉት?” የሚል ጥያቄ ከኮሚቴው ቀረበላቸው። እነ መምህር ተስፋዬ “አዎ ኢትዮጵያውያን የተዋረዱበት ዘመን ነው” ብለው መለሱ። “ታዲያ አይነገር አይገለጽ እንዴት ትላላችሁ?” የሚል ጥያቄ ኮሚቴው አቀረበላቸው። “በኢትዮጵያ የጀመርነው እቅድ ስላለን በዚህ መንግሥት ሰው ተዋረደ ብለን ብንናገር ከመንግሥት ጋራ እንጋጫለን” የሚል ሀሳብ እነ መምህር ተስፋዬ አቀረቡ። “ሳትደብቁ እውነቱን በመናገራችሁ እናመስጋናችኋል። ነገር ግን ለናንተ ወቅታዊ እቅድ ስትሉ፤ የጠቅላላውን ህዝብ ጉዳት አታፍኑ። የተደራረበ ኋላፊነት ያለባትን የቤተ ክርስቲያናችንን ልሳን ለመዝጋትም አትሞክሩ። በኢትዮጵያ የዘረጋችሁትን እቅድ ከገለጻችሁልንና ተገቢነቱንም ከተረዳን ልንረዳችሁም ፈቃደኞች ነን። ነገር ግን መንግሥት ሰው ገድሎ አትግደል ስንል ፖለቲካ ገባችሁ አትበሉን፤ ሰው በግፍ ሲበደል፤ ሲታሰር፤ ሲገደልና፤ ሲሰደድ፤ አትበድሉ፤ አትሰሩ፤ አትግደሉ፤ አታሳዱ ብሎ መናገር፤ ነገረ_መለኮት ነው። ከዚህ ሌላ የካህናት ተልእኮ የለም። አለመናገር ዝም ብሎ ማለፍ ግን ነገረ_ሰይጣን፤ የሰይጣን ሠራዊት ተልእኮ ነው። የሀሰት መምህራን በዝተው፤ ውሸት በህዝብ ላይ ሲሰፍን፤ ሰው በግፍ ሲደበደብ፤ ሲታሰር፤ ሲገደልና ሲሰደድ ዝም ካላላችሁ ፖለቲከኞች ሆናችሁ” እያለ ያስተማራችሁ ካለ፤ የሰው ጠላት የሆነውን የሰይጣንን ፖለቲካ የሚያራምድ ሰው ነው። መለኮት በሰማያዊ መንግሥቱ ለሰው ልዩ ክብርና ልዕልና የሰጠበትን ፍቅር (ነገረ መለኮት)፤ ሰውን ከሚያሳድድ፤ ከሚያዋርድና ከሚገድል ነገረ_ሰይጣን ለይታችሁ እወቁ” ሲል ኮሚቴው እነ ተስፋይ መቆያን መከራቸው። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

The Ethiopian Orthodox Union church

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s