ጀግናዋ አያልነሽ ስሜነህ

ኢሳት ቴሌቪዥን

ይህ ፎቶ የጀግናዋ አያልነሽ ስሜነህ የቅርብ ጊዜ ምስል ነው

Ayalnesh

ክብር ለጎንደርና ጎጃም ህዝብ ይሰጥ

በብዙ ሰው ልብ ውስጥ ተስላ ያለችው አያልነሽ ስሜነህን ያቅርብልን !!!

በልጂነት እድሜዋ ደርግም፣ ኢህኣዴግም ለአካባቢዋ ህዝብ የማይጠቅሙ መሆናቸውን የተረዳችና የኢህኣፓ አባል ና መሪ ሆና ለለብዙ አመታት ሁለቱንም በሀይል የተዋጋችው አያልነሽ ስሜነህ በህይወት እያለች እንዴት አናያትም???

እንዴትስ ታሪኳን አንሰማውም ፤ ስንትና ስንት ጦር ስትመራ የነበረች ሴት??? አያልነሽ የምትረሳ ሴት ናት ???

— በደርግ ላይና ኢህአዴግም በገባ ወቅት ትሰራው በነበረ ጀብዱ በጎጃምና ጎንደር ህዝብ ዘንድ ስሟ የገነነ ና የተከበረች፤

— እረኞች በሜዳ፣ በዱር በገደሉ ሌላውም በሰርግ ፣በየቦታው ፣ ልጆች በጨዋታ የዘፈኑላት

— ብዙሃኑ ህዝብ በስራዋ እንጂ በአካል የማያቃት ፤ መንፈስ ትመስለው የነበረችው ሴት ኢሳት በእንግድነት ከሚያቀርባቸው እልፍ አእላፍ ሰወች ውስጥ አንዷ የመሆን ተራ ይደርሳት ዘንድ እንማጸናለን፡፡

ባሁኑ ወቅት የ50 ዓመት ሴትና የስዊዘርላንድ ነዋሪ የሆነችው ከ 11 ዓመቷ ጀምራ እስከ 27 እድሜዋ ድረስ ዱር ቤቴ ያለችው አያልነሽ ስሜነህ በፎቶ አየናት፡፡ ሀሌ ሉያ ደሞ እስኪ ስታወራ እንያት፡፡

ከተዘፈኑላት ዘፈኞች ጥቂቶቹ ከየቦታው የተለቃቀሙ

አያል ነሺ በደጋ እያጉረመረመች
ከብቶቼን በሜዳ በትና ከረመች
………………………..
አያል ነሽ አንበሳ
…… ዞረሽ ነይ በደጋ
አሰፋልሻለሁ ሳምሰለስል ነጋ
…………………………..
የአያል ነሽን ግዛት አህያ በላው
አልቢን ስጡኝና እኔ ላባረው
…………………….
አያል ነሽ ጀግናዋ
ስለወደድኩሽ
ክላሽ ልግዛልሽ
………………..
አያልነሽ ጓሮሽ ተበላልሽ
ክላሺ ስጭኝና እኔ ላባርልሺ

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8191#sthash.0jTXPJhw.dpuf

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s