የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የሚያስቅ እና የሚያሰቅቅ ጉብኝት – በኢትዮጵያ! (ዳዊት ከበደ ወየሳ አትላንታ- ጆርጂያ)

ይህ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ጉብኝት፤ ድንገት ትላንት የመጣ ሳይሆን – ቀደም ሲል ሲገነባ በቆየው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ነው። የትላንት ታሪካችንን ማየት የተሳናቸው የዘመኑ ገዥዎች ይህንን ላያውቁ ይችላሉ። ነገር ግን ታሪክ ሊፋቅ የማይቻል ሃቅ በመሆኑ፤ ደግመን ደጋግመን በእውነት በትር አናት አናታቸውን መቀወር ያስፈልጋል።   በ PDF ማንበብ ከፈለጉ እዚህ ላይ ይጫኑ።

ይህ ፎቶ የተላከው ከታዋቂው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት፤ ለአጼ ምኒልክ ነው። ከላይ ያለው ጽሁፍ ቃል በቃል - To His Majesty King Menelik II of Abyssinia. Niguse Negest of Ethiopia. From Theodore Rooevelt. ይላል።

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በኦፊሴል ዲፕሎማቲክ ግንኙነት ከጀመሩ 112 አመታት ተቆጠሩ። በታህሳስ 1903 ከአጼ ምኒልክ ጋር የተነጋገሩት ከአሜሪካው ፕሬዘዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት የተላኩት፤ ሮበርት ስኪነር ነበሩ። ከአጼ ምኒልክ ጋር የተደረገው ስብሰባ ዘጠኝ ቀናትን የፈጀ ነበር። የሁለቱም አገር ህዝቦች በነጻነት እንዲዘዋወሩ፣ የንግድ ግንኙነት፣ እና አሜሪካ አባይን ለመገደብ እውቀቱ ያላቸውን ሰዎች እንድታበረክት ነበር። በኋላ ላይ ሃኪም ወርቅነህ እሸቴ (ዶ/ር ቻርልስ ማርቲን) በ1927 ወደ አሜሪካ መጥተው ሃርለምን ሲጎበኙ፤ የራስ ተፈሪን መልእክት አስተላለፉ። ወደአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመሄድም፤ በአጼ ምኒልክ ዘመን ስምምነት ላይ የተደረሰበትን የአባይን ግድብ ጉዳይ ተነጋገሩ። በእርግጥም አሜሪካውያን ጥናቱን ለማድረግ ብቻ ሳይሆን፤ ግድቡንም ለመስራት ስምምነት ላይ ተደረሶ ነበር። እነዚህን ነገሮች በደምሳሳው የምንጠቃቅሰው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ግንኙነት ወይም የአባይ ግድብ ሃሳብ ጭምር ትላንት የተጀመረ አለመሆኑን ለመግለጽ ነው። አንድ አንቀጽ እንጨምርና ወደ ዋናው ጉዳይ እንሄዳለን።

እንዲህ እንዲህ እያልን… ጥቁሮች ዩኒቨርስቲ መግባት በማይችሉበት ወቅት እነመላኩ በያን ኦሃዮ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ያደረጉትን የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ዋረን ሃርዲንግን ጭምር ማንሳት አስፈላጊ ነው። በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ልባቸው ኢትዮጵያን ሲያስብ ኖሯል። በኢትዮጵያ እና ጣልያን ጦርነት ወቅት አለም ሁሉ ፊቱን ሲያዞርብን፤ የጣልያንን ወረራ ካልተቀበሉት አምስት አገሮች ውስጥ አሜሪካ አንዷ ነበረች። በኢትዮጵያ ውስጥ ግዙፉን አየር መንገድ እና የቀድሞውን አውራ ጎዳና መስሪያ ቤት የመሰረቱት አሜሪካኖች ናቸው። በ1963 ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለስላሴ አሜሪካንን ሲጎበኙ፤ ፕሬዘዳንት ጆን.ኤፍ.ኬኔዲ ተቀብለው አስተናግደዋቸዋል። ኋይት ሃውስ በክብር የገቡትም የመጀመሪያው ጥቁር መሪ፤ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሆነዋል። አሜሪካኖች ከመልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታችን በተጨማሪ ተዋጊ መርከቦችን ጨምሮ፤ የሰጡን የጦር መሳሪያ እና የጦር ልምድ የትየለሌ ነው። ይህን ሁሉ ወደ ጎን ብንተው እንኳን፤ በ19ሰማንያዎቹ የድርቅ ዘመናት ከሌላው ህዝብ በላይ “We are the world” ብለው የታደጉንን ከቶ አንረሳውም። አለም በአውሮፕላን መቀራረብ ከጀመረች በኋላ የቀድሞዎቹ የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ጂሚ ካርተር፣ ቢል ክሊንተን እና ጆርጅ ቡሽ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። አሁን ደግሞ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ጎበኙ። ከዚያስ? የሆነውን አብረን እንከታተል።

የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የሚያስቅ እና የሚያሰቅቅ ጉብኝት – በኢትዮጵያ!

ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ- ጆርጂያ)

ምን ያህል ሰው ልብ እንዳለው ማወቅ ያስቸግራል። የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን የእራት ምሽት ንግግር ልብ ይበሉ። በአማርኛ ቋንቋ “እንደምን ዋላቹህ?” ብለው ነው ንግግራቸውን የጀመሩት። “የኢትዮጵያ ታሪክ የ200 አመት ታሪክ ነው” ሲሉን ለነበሩ ሰዎች ነው – ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ መሆኗን እና ጥንታዊነቷን የመሰከሩት።

የአጼ ምኒልክን ወራሪነት ለሚሰብኩት ሰዎች ነው፤ “ኢትዮጵያ – ከጥቁር አሜሪካውያን በፊት ለነጻነቷ የተዋጋች አገር ናት” ብለው ያሞገሷት። ሌላው ቀርቶ የንጉሥ ሰለሞን እና የንግሥተ ሳባን ግንኙነት፤ “ተረት ተረት ነው” ሲሉን የነበሩ ሰዎች በብሄራዊ ሙዚየም፤ የንግሥተ ሳባን ስዕል እያዩ እና እያሳዩ ስናይ፤ የታሪክን አሸናፊነት ተገ2ነዘብነ።

ሌላው ቀርቶ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የሉሲን አጽም በመገረም ሲመለከቱ፤ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ “የዚህ አጽም ብሄር ምን ይሆን?” ብለው… ሆዱን ቁርጠት ይዞት ፊቱን ቅጭም ያደረገ ህጻን ልጅ መስለው ነበር።

በአጠቃላይ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በዝርዝር ያቀረቧቸው የኢትዮጵያዊነት መገለጫዎች፤ በሰዎቹ የፖለቲካ መዝገበ ቃላት ውስጥ “የነፍጠኞች ታሪክ” ተብሎ የተመዘገበ ነው። ኢህአዴግ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ሰሞን፤ “በብሄራዊ ሙዚየሙ ውስጥ የሚገኙት የአጼ ምኒልክ እና የሌሎች ነገስታት አልባሳት መቃጠል አለባቸው” ሲሉ የነበሩትን ወገኖች በሙዚየሙ ጉብኝት ወቅትአላየናቸውም። ቢያንስ ተወካያቸው ግን በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያን ታሪክ የተማረ ይመስለናል። እናም “በፕሬዘዳንት ኦባማ ጉብኝት ወቅትት፤ ጎልቶ እና አሸንፎ ለወጣው የኢትዮጵያውያን ታሪክ ዘላለማዊ ክብር ይሁን!” አልነ።

3በነገርዎ ላይ… የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በእራቱ ግብዣ የመጨረሻ ንግግራቸው ላይ፤ ለሁለቱ አገሮች ግንኙነት፣ ቀስተ-ደመና ለተወለደባት ለኢትዮጵያ እንዲሁም “ለጤናችን” ብለው ፅዋቸውን ለማንሳት ሲዘጋጁ፤ (የአስተናጋጁን ነውር አይታችኋል?) አተናጋጁ በግራ እጁ መለኪያውን ሰጥቶ ሂድት ይላል። የሱ ገርሞን ሳያበቃ… የኛው ሰውዬ ደግሞ በምላሹ፤ ከጽዋው ባይጎነጩም (ምናልባት በሃይማኖት ምክንያት ይሆናል)፤ “እኛም እጃችንን ዘርግተን እንቀበላችኋለን” ብለዋል። በቅሌት ላይ ቅሌት ሲደራረብብን፤ ከአንድ ቀን በፊት ቦሌ ላይ የነበራቸውን ሁኔታ አስታወሰን። ቦሌ ላይ እጅ ዘርግቶ መቀበል ብቻ ሳይሆን፤ ተንበርክከው መቀበል ቢኖርባቸው የሚያደርጉት ነው የሚመስለው። ለዚህ አባባል ምስክር እንዲሆነን፤ በፊልም ደንብ Flash back ሂደት ወደ ኋላ በማጠንጠን፤ ለፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ቦሌ ላይ የተደረገላቸው አቀባበል፤ “ኧረ የፕሮቶኮል ሹም ያለህ!” የሚያሰኝ ነውና – እስኪ ትንሽ እንጨዋወት።

ጁላይ 26 ቀን፣ 2015 የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ አዲስ አበባ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸው የብዙዎች ግምት ነበር። ሆኖም ምስቅልቅሉ በወጣ እና ፕሮቶኮሉን ባልጠበቀ፤ አሳፋሪ ግርግር የአቀባበሉ ስነ ስርአት ተበላሸ። እዚያ የተገኙት ጥቂት የኢህአዴግ ሹመኞችን ብንጠላቸውም እንኳን፤ እንደሰው መጠን አሳዝነውናል። ከሃዘናችን በላይ ግን ሰዎቹ ኢትዮጵያን ወክለው ሲቆሙ፤ ክብራችንን ዝቅ በሚያደርግ ደረጃ እንዲያዋርዱን መፍቀድ የለብንም። ለፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የተደረገውን አቀባበል የተመለከተ ማንም ሰው፤ በአገሪቱ የፕሮቶኮል ሹም ወይም የእንግዳ አቀባበል ስነ ስርት እንደሌለ ሊስማማ ይችላል።

እናም ቦሌ ላይ… “ኤርፎርስ አንድ” አውሮፕላን ካረፈ በኋላ፤ የመውረጃውን መሰላል የተሸከመው መኪና ግራ እንደተጋባ ያስታውቅ ነበር። መኪናው መሰላሉን ተሸክሞ ወደ ፓይለቱ መውረጃ ገሰገሰ። ሆኖም ቁመቱ አልደርስ ብሎት እየታገለ ሳለ፤ በአውሮፕላኑ ያልታሰበ ክፍል፤ ባራክ ኦባማ ከውስጥ በሩን ከፍተው ብቅ አሉ። መሰላሉ ግን በስፍራው የለም። ሰውየው ባራክ ኦባማ መሆናቸው በጀ እንጂ፤ ሌላ ቀልቃላ ፕሬዘዳንት ቢሆን ከአውሮፕላኑ ላይ ሊፈጠፈጥ እንደሚችል አትጠራጠሩ። እናም እንደአለም ዋንጫ ሂደቱን በቴሌቭዥን እያየን፤ “ኧረ ቆይ ክቡርነትዎ” እያልን ሰጋን። ሆኖም አትሙች ያላት ነፍስ ተመልሳ ወደ ውስጥ ገባች። ባራክ ኦባማ ከፍተው ሊፈጠፈጡበት የነበረው በር ተመልሶ ተዘጋ። ያ – የመውረጃ መሰላል የተሸከመውና በፓይለቱ መውጫ በኩል ለማስጠጋት ይጥር የነበረ ሹፌር… በፍጥነት አነዳድ ተከፍታ ወደተዘጋችው በር ሄደ። (ትዕይንት አንድ አበቃ)

ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ከአውሮፕላን ሲወርዱ ቀይ ምንጣፍ ተዘጋጅቶ አልጠበቃቸውም። ትንሽ ቆይተው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ቀይ የቃልቻ የሚመስል ጃንጥላ ተይዞላቸው ወደ አውሮፕላኑ መጡ። ከሳቸው በፊት ቆመው የሚጠብቁትን ጥቂት ሚንስትሮቻቸውን ቀና ብለው እንኳን ሳያዩ ወደ አውሮፕላኑ ስር ተጣድፈው ደረሱ። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ከአውሮፕላኑ ወርደው ሳይጨርሱ፤ ህጻናቱ አበባ ለመስጠት አሰፈሰፉ። አንድ ሳይሆን ሁለት አበባ ይዘዋል። ሁለተኛው አበባ ለማን እንደሆነ አምላክ ይወቀው። (ትዕይንቱ ቀጥሏል)

አቀባበል ሊያደርጉ ከሄዱት ሚንስትሮች መካከል፤ ፌስ ቡክ ላይ ፎቶ በመለጠፍ የሚታወቁት የውጭው ጉዳይ ሚንስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ባራኪ ስልካቸውን ይዘው፤ ለፌስ ቡካቸው የሚሆን ፎቶ ለማንሳት ቢሞክሩም የአሜሪካው ሴኩሪቲ ኮስተር ብሎ ሲያያቸው፤ የሚገቡበት ጠፋቸው። ሌሎቹ ሚንስትሮች እንደምንም ተጋፍተው ወደ ባራክ ኦባማ ሲሄዱ ዶ/ር ቴድሮስ ከኋላ ተሸፍነው ቀሩ። ነገሩ ቅጥ አምባሩ ጠፋ። ፕሮቶኮል ትሁን ምን ያላወቅናት ሴትዮ፤ ከህጻናቱ ጋር አብራ ትጋፋለች። ተጋፍታ ሄዳ ፕሬዘዳንት ኦባማን ትጨብጣለች። የህወሃቱ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ጎንበስ ብሎ የሚሆነውን ሲመለከት፤ ሌሎቹም እሱን ተከትለው ሲያጎነብሱ – በሁኔታው ሃፍረት የተሰማቸው በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ግርማ ብሩ፤ የብርሃነ ገብረክርስቶስን ጀርባ ደልቀው፤ ስነ ስርአት እንዲይዙ ለማድረግ ይሞክራሉ። ትርኢቱ እያሳቀ ያሳቅቃል።

4ይሄ ሁሉ ሲሆን… ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ደግሞ፤ ስለህጻናቱም ስለሚንስትሮቻቸውም ግድ ሳይሰጣቸው፤ ከሁሉም በላይ ተንሰፍስፈው ወደ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ አመሩ። (እኛ በቲቪ እያየን “ኧረ አትንሰፍሰፉ” እንላለን) ጠ/ሚንስትሩ – ፕሬዘዳንቱን ጨብጠው ምን እንዳሏቸው ባናውቅም፤ አቶ ኃይለማርያም በደስታ የሚይዙት እና የሚጨብጡት ጠፍቷቸው ፍንድቅድቅ አሉ። እግር ኳስ ጨዋታ ሲጀመር፤ የቡድኑ ካፒቴን ግዜ ወስዶ – ሌሎቹን ተጫዋቾች የሚያስተዋውቀውን ያህል እንኳ አልተጨነቁም – አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ። ሚንስትሮቹን በስርአት ሳያስተዋውቁ፤ ወደ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ መኪና አብረው ሄዱ። ልክ ወደዛ እየሄዱ ሳለ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ቴዎድሮስ አድሃኖም፤ ለፌስቡክ የሚሆናቸውን ፎቶ ለማንሳት ስልካቸውን ይዘው ፎቶ ለማንሳት በድጋሚ ታዘብናቸው። ሆኖም በዚያች ቅጽበት ፕሬዘዳንት ኦባማ ወደመኪናቸው ገብተው፤ በፍጥነት ቦሌ አየር ማረፊያን ለቀው ሄዱ። እናም ለታላቁ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት የተደረገው አቀባበል እዚህ ላይ አበቃ። ለጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያምም፤ ለቃልቻ የሚያዘው ቀይ ባለ አዝራር ጃንጥላ ተይዞላቸው አየር መንገዱን ለቀው ወጡ።

እንደ እብድ ቡድን የተዘባረቀ ሱፍ የለበሱትን ሚንስትሮች ትተን አበባ እንዲሰጡ የተደረጉትን ልጆች እንቃኝ። ልጆቹ አበባውን ከሰጡ በኋላ ፕሬዘዳንቱን መኪናቸው ድረስ ተከትለው፤ የማናውቀውን ነገር ያወሯቸዋል። እነዚህ ልጆች እንደባህላችን ጸጉራቸውን ሽሩባ ተሰርተው… ደግሞም የአገር ባህል ለብሰው አልቀረቡም። ጭራሹን ከአራቱ አንዷ… ጸጉሯን ጨበርኛ ተሰርታ፣ ካኪ ኮት እና ጥቁር ሱሪ አድርጋ… ከታች ሸራ ጫማ ሸብ አድርጋ እንድትቀበል ነው የተደረገው። እንደዚህ አይነት አለባበስ ኢትዮጵያውያንን ሊወክል አይችልም። እንጨምር ከተባለ ሌላም ማለት ይቻላል።

በንጋታው ቡና ሲፈላ የነበረውን ሁኔታ እንመልከት። ቡና የሚያፈሉት ሴቶች ‘ለምን አሮጊቶች ሆኑ ብሎ መከራከር ወይም ለምን የትግሬ ሹሩባ ተሰሩ?’ ማለት አግባብ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ቡና ሲፈላ፤ በሙቀጫ የተወቀጠ የሚመስል – ጋቢ አይሉት ነጠላ አድርጎ ቡና ማስተናገድ ምን የሚሉት ባህል ነው? ባህል ለማሳየት ከሆነ ያስፈለገው እጣኑ በገል፣ ስኒው በረከቦት፣ ቄጤማው ተጎዝጉዞ፣ ፈንዲሻው ተበትኖ፣ ቁጢጥ ከሚሉም በርጩማ ላይ ቁጭ ብለው – አቦል ቶና በረካ ቢጠጡ ደስ ይል ነበር።

5በዚያ ላይ ለዳንኪራ የተጠሩት ልጆች እንደድሮ የቀበሌ ኪነት፤ አራምባ እና ቆቦ ሲረግጡ አይተን… “የአገር ፍቅር ቴያትር ቤት ተወዛዋዦች ባይኖሩ፣ የማዘጋጃ እና የብሄራዊ ልጆች ወዴት ሄዱ?” ብለን አዝነናል። በዚያ ላይ ልጆቹ እስክስታቸውን ሲጨርሱ፤ አበባየሆሽ ለማለት እንደመጡ ህጻናት እየተገፈታተሩ ሲወጡ አይተን… “ምን እየተካሄደ ነው?” ማለታችን አልቀረም።

አቀባበሉን ከኬንያው ጋር ማነጻጸር አይቻልም። ኬንያዎቹ ሽር ጉድ ሳያበዙ ዘና ብለው ነው አቀባበል እና አሸኛኘት ያደረጉት። በሬድዮ እና በቴሌቭዥን ብዙ በጣም ብዙ ሲባል ነበር። 6 በየመንገዱ ሳይቀር የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ፎቶ ተለጥፏል። ከፎቶውም ስር በትላልቁ፤ “Thank you for vesting Ethiopia!” ተብሎ ተጽፏል። የዚህ ቀጥታ ትርጉም “ኢትዮጵያን እንዳሻዎ ስለሚያደርጓት እናመሰግናለን” የሚል ነው። ይሄን እንዲጽፍ ሃላፊነት የተሰጠው ሰው visiting ለማለት ፈልጎ vesting ማለቱ እውነት ነው። “Thank you for visiting Ethiopia” ለማለት ነበር የተፈለገው። እንግዲህ ዲግሪ በገንዘብ በሚገዛበት አገር ይህ ነገር መፈጸሙ ሊገርመን አይገባም፤ ሆን ተብሎ ቢደረግም አይደንቀንም።

ወደ እንግዳው አቀባበል እንመለስ። በአገራችን ከአጼ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ ትላልቅ እንግዶች ሲመጡ፤ ለክብራቸው 21 ግዜ መድፍ ይተኮሳል። እ.አ.አ በ1903 በአሜሪካው ፕሬዘዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የተላከው የመጀመሪያው ዲፕሎማት ሮበርት ስኪነር፤ አዲስ አበባ ገብቶ ከአጼ ምኒልክ ጋር ከተገናኘ በኋላ፤ ለክብራቸው 21 ግዜ መድፍ እንደተተኮሰ እና የንጉሠ ነገሥቱ የሙዚቃ ባንድ አጅቧቸው ወደ ራስ ወልደጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት ለማረፍ መሄዳቸውን ጽፏል። ከመቶ አመት በፊት አጼ ምኒልክ ለአሜሪካ ልዑካን ቡድን ያደረጉትን ያህል አቀባበል ማድረግ ሊያቅተን አይገባም ነበር። ይህችን አጋጣሚ በመጠቀም በወቅቱ የምኒልክን ፎቶ አንስቶ ነበር እዚህ ላይ ፎቶዋን አናካፍለናቹህ ወደ ጉዳያችን እንለፍ።7

በኢትዮጵያ ታሪክ ለሰማይ እና ለምድር የከበዱ ሰዎች ሲመጡ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በዘመኑም ሆነ አሁን ጭምር በአለም ህዝብ ዘንድ ከፍ ብለው የሚታዩት የእንግሊዟ ንግሥት ኤልሳቤጥ ከአዲስ አበባ አልፈው ጢስ አባይን ጭምር ጎብኝተዋል። ከማርሻል ቲቶ ጀምሮ የብዙ አገር መሪዎች በክብር ተስተናግደዋል። የኩባውን ፕሬዘዳንት ፊደል ካስትሮን ጨምሮ በርካታ ፕሬዘዳንቶች ኢትዮጵያን ሲጎበኙ በጥሩንባ ጭምር፤ ህዝቡ በነቂስ እንዲወጣ ተደርጎ ነው አቀባበል ያደረገላቸው። ይሄን ማንሳታችን እንኳን፤ አንዳንድ ግዜ እራሳችንን እስከሚገርመን ድረስ፤ ከዚህ ዘመን በፊት አንድም ታዋቂ የአለም መሪ ኢትዮጵያ መጥቶ እንደማያውቅ ተደርጎ ስለተነገረን – በቁጭት አይነት ያነሳነው ጉዳይ ነው።

የደቡብ አፍሪቃው ኔልሰን ማንዴላ ለአፍሪካ አንድነት ስብሰባ አዲስ አበባ ሲገቡ፤ በሽግግር መንግስቱ ወቅት ፕሬዘዳንት የነበሩት መለስ ዜናዊ ጃኬት አድርገው ያደረጉት አቀባበል ገርሞን ሳያበቃ፤ የአሁኖቹ ደግሞ ሙሉ ሱፍ ልብስ አድርገው ይበልጥ አሳቀቁን። የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሬሳ ቦሌ ሲገባ የተደረገለትን ያህል አቀባበል፤ ለፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ማድረግ ተስኗቸው፤ እንደገመሬ ያለስርአት ሲግበሰበሱ አይተን ተገረምነ። እንደው… ‘ወደፊት ገና ብዙ የምንሸማቀቅበት ጉዳይ ይኖራል’ ብለን በማሰብ፤ ‘የባሰ አታምጣ’ ብለን በመጸለይ፤ ሃፍረታችንን ዋጥ አድርገን ትዕይንቱን ያለቁጥር መቁጠር ቀጠልን።

የሚገርመው ግን… ይሄን ሃፍረት የተመለከተ አምላክ አሳፍሮ አላሳፈረንም። ለአቀባበል በሚመስል መልኩ… በአዲስ አበባ ላይ ትልቅ ቀስተ ደመና ታየ። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ታላቅ አቀባበል ያደረገላቸውን ቀስተ ደመና ለማስታወስ ይመስላል። የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን፤ “Here is the land where the first harmony in the rainbow was born…” በማለት በእራት ግብዣ ንግግራቸው ላይ ታዳሚውን አስጨብጭበዋል።

ከጭብጨባው ወጥተን ወደ ከተማው ከሄድን ደግሞ ብዙ ሹክሹክታ አለ። የቱን ይዘን የቱን እንደምንተው ግራ ይገባናል። “የብአዴን ሰዎች ለምን የሉም?” የሚሉ ሰዎች አሉ። በረከት ስምኦን ኦባማን እንደማይቀበል ሲያውቅ ወዲያው ነው የታመመው አሉ፡) “ግን እነአዲሱ ለገሰ? ተፈራ ዋልዋ? ከኦህዴድ የተጠራ ማንም የለም እንዴ? አባ ዱላ፣ ኩማ ደመቅሳ የታል? ከህወሃት ሰዎች እነሳሞራ አልተጠሩም? የመለስ ሚስት የት ገባች? እነብሃት ነጋ? ስዩም መስፍን?” ይሄ ሁሉ ጥያቄ የውስጥ ለውስጥ ሹክሹክታ ነው። ከነዚህም ሰዎች አልፎ፤ በትክክለኛው ፕሮቶኮል መሰረት፤ “ፕሬዘዳንትን የሚቀበለው ፕሬዘዳንት ነው” ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ። ሃሳባቸውን ለአንድ ደቂቃ እንጋራና፤ “እውነት ግን… ለመሆኑ የኢትዮጵያው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የት ናቸው?” ማለታችን አይቀረም። (እንደ’እውነቱ ከሆነ… ብዙ ኢትዮጵያውያን ፕሬዘዳንቱን ቀርቶ፤ የፕሬዘዳንቱን ሙሉ ስም አያውቁም።)

በህገ መንግስቱ አንቀጽ 71 የፕሬዘዳንቱ ሚና ውሱን ቢሆንም፤ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ቢያንስ እንግዳ ለመቀበል የሚያንስ ትከሻ እንደሌላቸው ይታወቃል። እናም አንዳንዶች ‘ፕሬዘዳንቱ ቢያንስ ቦሌ ሄደው ባራክ ኦባማን ሊቀበሉ ይችላሉ’ ብለው አስበው ሊሆን ይችላል… ቦሌ ላይ ሲያጧቸው ደግሞ ‘ብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል ያደርጉላቸዋል’… ብለውም አስበዋል። ሁለቱም ግን አልሆነም። ህገ መንግስቱ እንደማይከበር ብናውቅም፤’ ፕሬዘዳንቱን በእድሜ እንኳን አክብረው ለዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ትንሽ ሚና ይሰጧቸው ይሆናል’ ብለን ብናስብም… ሰውየው የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩ። ከዚያው ጋር ግን አንድ ቀልድ ሰማነ። ነገሩ እንዲህ ነው።

ፕሬዘዳንት ኦባማ አዲስ አበባ ከመግባታቸው በፊት የብሄራዊ ቤተ መንግስት በር ተንኳኳ። ፕሬዘዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋቢያቸውን እንዳደረጉ፤ ‘ምን መጣ?’ ብለው በሩን ሲከፍቱ፤ ከአሜሪካ ኢምባሲ ከተላኩ ሰዎች ጋር ይፋጠጣሉ።

“ምን ልታዘዝ?” ፕሬዘዳንቱ ናቸው።

“ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ሲመጡ፤ ስለአቀባበላቸው ለመነጋገር ነበር።” አሜሪካኖች ይመልሳሉ።

“ታዲያ እኔ ምን አውቃለሁ? ሰዎቹን አናግሯቸው እንጂ።” ይላሉ ፕሬዘዳንት ተሾመ።

“እርስዎ በዚህ ጉዳይ መነጋገር አይችሉም?” አሜሪካኖቹ ገርሟቸው ጠየቁ።

“እኔ ቤት ጠብቅ ተብዬ ነው። አሁን ሰዎቹ የሉም።” ብለው በሩን ዘጉባቸው – አሉ።

የ’ነዚህ ሰዎች ነገር… አንዳንዱ ድርጊታቸው ቢያስቅም፤ ኢትዮጵያን ወክለው የሚያደርጉት ተግባር ግን እያሳቀቀን ነው።

የሆነው ሁሉ ሆኖ ግን በአንድ ነገር እንጽናናለን። ልብ በሉ። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ኢህአዴግ ለ17 አመታት አደረኩት ስላለው የጀብድ ትግል አላወሩም። ነገር ግን 130 አመታት ወደ ኋላ ተመልሰው፤ አጼ ምኒልክ አድዋ ላይ ያደረጉትን ድል አወደሱ። አጼ ምኒልክን የሚጠሉ ሰዎች አንገታቸውን ሊደፉ ይችሉ ይሆናል። ፕሬዘዳንቱ ግን… ደግመው ደጋግመው የኢትዮጵያውያንን ተጋድሎ ሲተርኩ፤ የምኒልክ ዘመን ሰዎችን ገድል ነው – የነገሩን። ሌላው ቀርቶ በአፍሪቃ ህብረት ንግግራቸው ላይ… በአፍሪቃ የሚገኙ አምስት ዲሞክራቲክ አገሮች ብለው፤ እነናይጄርያን፣ ጋና፣ ታንዛንያ የመሳሰሉትን አገሮች በምሳሌነት ሲጠቅሱ ኢትዮጵያ በዝርዝሩ ውስጥ የለችበትም። ይሄ ለነአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዱብ’ዳ መሆን አለበት።

እንዲህም ሆኖ ግን… ኢህአዴግ መራሽ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች አሁንም “ለፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።” ሲሉ ‘የት? መቼ?’ ማለታችን አይቀረም። የቦሌው ሲገርመን… በንጋታው በብሄራዊ ቤተ መንግስት ሲደርሱ፤ በጃንሆይ ግዜ አሎን ሲነጠፍ የምናውቀውን ምንጣፍ ውጪ አውጥተው ዘረጉት። 8 ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፈውን ኢሳት እና ሌሎች ድረ ገጾች ለማፈን በቀን ብዙ ሚልዮን ዶላር የሚያባክን አምባገነን መንግስት በDust mite የነተበ ምንጣፍ ለባራክ ኦባማ ክብር ዘረጋላቸው። በጣም የሚያስቀውና የሚያሳቅቀው ደግሞ “Welcome” የምትል፤ ከWal Mart በ$3.99 ገዝተን ውጪ የምናቀምጣት አይነት፤ መናኛ እግር መጥረጊያ ተደረገላቸው። ከዚያም ለ20 ሰከንድ ያህል የቆየው የማርሽ ሙዚቃ አስደመመን። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማም… እንደ”አሳ በለው በለው” ዳንስ አራት መአዘን ሆኖ በተነጠፈ ምንጣፍ ላይ፤ ሲሽከረከሩ፤ ‘ነገሩ የህጻን ጨዋታ ነው እንዴ?’ አልነ። በዚያ ላይ ከዳይኖሰር አፍ የወደቁ ፓስታ የሚመስሉ ቀጫጭን ሰዎች ተሰልፈው ስናይ፤ የድሮ ት/ቤታችንን ባንድ አመሰገንን። ካልሲያቸውን ሱሪያቸው ላይ ገድግደው፤ ወይም ገምባሌያቸውን በሱሪያቸው ላይ ለብሰው ቆመው ስናይ፤ “የቤተ መንግስቱ የክብር ዘቦች እነዚህ ናቸው?” ብለን ተገረምን።

ሌላ ትዝብት እንጨምር። ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ከአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተሻለ እንግሊዘኛ ቢችሉም፤ አሜሪካም ሆነ የተባበሩት መንግስታት ፊት በአገራቸው ቋንቋ ነበር የሚያወሩት። ይቺን ጫፍ ይዘን ወደ ጋዜጣዊ መግለጫው እናምራ። “ፕሬዘዳንት ኦባማ – ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ።” ከዚያ በኋላ… አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንግሊዘኛውን እያነበቡ ሳለ፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ደግሞ ትርጉሙን ባማርኛ ያስነብበን ጀመር። የሚገርመው ታድያ አቶ ኃይለማርያም በእንግሊዘኛ የሚሉት እና ባማርኛ ተተርጉሞ የሚጻፈው አረፍተ ነገር ፈጽሞ የሚገናኝ አልነበረም። ይሄ ገርሞን ቀና ስንል ደግሞ፤ ኦባማ ማናገሪያ ላይ ኮከቧን ለጥፈዋታል። “ይሁን” ብለን ስናልፈው ደግሞ የማይታለፍ ነገር ገጠመን። ከሁለቱ ሰዎች ጀርባ አይናችንን የሚስብ ነገር አየነ። የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ባንዲራ በስቴፕለር ሽቦ አንድ ላይ ተሰፍተዋል። የኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ ሲንከረፈፍ አልታይ እያለ የሚያስቸግረውን፤ አምባሻ መሰል ሰማያዊ ኮከብ ለማሳየት ሲሉ፤ እንደሰፈር ልጆች… የኢትዮጵያን ባንዲራ በግድ ወደ ጎን ወጥረው ከአሜሪካ ባንዲራ ጋር ሰፍተውት ብንመለከት፤ መግለጫውን በደንብ ሳናጣጥመው አለቀ። በኋላ ላይ እንደሰማነው ግን፤ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ አንዳንድ ቁም ነገሮችን ተናግረዋል – አሉ። በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ አለመኖሩን በዘወርዋራ፤ በኤርትራ በኩል ዘልቀው የሚዋጉት አርበኞችም አሸባሪዎች አለመሆናቸውን በቀጥታ ማሳወቃቸውን ሰማነ።

9ከዚያ በኋላ፤ “ፕሬዘዳንት ኦባማ ቡና ጠጡ። እስክስታ መቱ።” ይሄ ሁሉ እልል ሊያስብል ይችል ይሆናል።

እንግዲህ ሁሉም ነገር አበቃ። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ጽዋቸውን ሲያነሱ፤ ‘የኛ ሰውዬ’ ደግሞ እጃቸውን ዘረጉ። ከዚህ በኋላ ያለውን ታሪክ ለመጻፍ፤ የታሪክ መዝገቡ ክፍት ሆኖ እየጠበቀን ነው። እዚህ መዝገብ ላይ፤ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኘው ሃይል በአዲስ ምዕራፍ… የራሱን ታሪክ ጽፎ ማለፍ አለበት።

ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ያመኑበትን ጉብኝት አድርገዋል። ያላመኑበት ነገር ደግሞ አለ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ሰብአዊ መብት እንደማይከበር ገብቷቸዋል። የፕሬስ ነጻነት እንዲከበር አበክረው ገልጸዋል። ይህ አቋማቸው አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በመነባረቁ ነበር፤ ከሳቸው ጉብኝት በፊት የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች በከፊል እንዲፈቱ የተደረገው። በአፍሪቃ አንድነት አዳራሽ ውስጥ፤ “ምርጫ ማድረግ ማለት፤ ዲሞክራሲያዊ አያሰኝም።” ሲሉ በአዳራሹ ከላይ የተቀመጡት ሰዎች በጭብጨባ እና በሆታ ሃሳቡን ተቀበሉት። በነገራቹህ ላይ እነዚህ ሰዎች ብዙዎቹ፤ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ናቸው። ደሞዝ የሚከፍላቸውን መንግስት ቢወክሉም፤ የኢህአዴግ መንገድ ትክክል ስላልሆነ ነው – “ምርጫ ማድረግ ማለት፤ ዲሞክራሲያዊ አያሰኝም።” ሲባል፤ ሆ ብለው በደስታ የጮሁትም እነሱ ነበሩ። (አሸባሪ ተብሎ ከመከሰስ ያድናቹህ)

ፕሬዘዳንት ኦባማ በሌሎች አገሮች ጉብኝት ሲያደርጉ፤ ለመሪዎቹ የሚሰጡትን አክብሮት እርግፍ አድርገው በመተው፤ አምስት ካሏቸው ዲሞክራቲክ አገሮች ውጪ የኢትዮጵያን መሪዎች ጨምሮ ሙልጭ አድርገው ነው የነገሯቸው። መሪዎች በስልጣን ላይ የመቆየታቸውን በሽታ አስመልክቶ ትዝብታቸውን ከገለጹ በኋላ… ከአፍሪቃ ኔልሰን ማንዴላን፤ ከአሜሪካ አብርሃም ሊንከንን እንደጥሩ ምሳሌ አድርገው አቅርበዋል። ስልጣን ላይ የሚቆዩትን የአፍሪካ መሪዎች አምርረው ወቅሰዋል። የፕሬስ ነጻነትን ቀጫጫነት፣ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ኢትዮጵያ ውስጥ በበቂ መጠን እንዳልጎለበተ አምነዋል። የኤርትራን ድንበር አቋርጠው ለነጻነት የሚታገሉ አርበኞች አሸባሪዎች አለመሆናቸውን በቃላቸው መስክረዋል። ይህንን የበለጠ ማጉላት ያስፈልጋል።

ፕሬዘዳንት ኦባማ ከአፍሪቃ መልስ ኋይት ሃውስ ከገቡ በኋላ፤ “Shame on you” ከማለት ይልቅ (ብዙም ደስ የማይል ቃል ነው)፤ መልካም ጅምራቸውን አድንቆ፣ እውነቱን በመመስከራቸው አመስግኖ፤ ንግግራቸውን የሚያጠናክር ተጨባጭ መረጃ ማቀበል ያስፈልጋል። ያለበቂ ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎች እና የፖለቲካ እስረኞች ሊፈቱ፤ ንብረታቸውም ሊመለስላቸው እንደሚገባ፤ ደግመን ደጋግመን ለአሜሪካ መንግስት መግለጽ አስፈላጊ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ሚዲያ – የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ጉብኝትን አመልክተው ብዙ ብለዋል። ብዙ የተባለው በሙሉ ግን፤ ለፖለቲካ ፍጆታ ያህል ጥቅም ላይ የዋለ ነው። የዚያኑ ያህል የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ቆይታ፤ በአሜሪካ ትላልቅ ሚዲያ ምንም አልተባለለትም – ማለት ይቻላል። ይህ ምን እንደሚያሳይ ግልጽ ነው። ከዚህ በመነሳት ወደ ቀጣዩ የታሪክ ምዕራፍ ራሳችንን ማሸጋገር ይኖርብናል።

በመጨረሻም ስንበት። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በተደረገላቸው የእራት ግብዣ ላይ፤ የኢትዮጵያዊነት መአዛ ያለውን የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን አንቀፀ-ቃል ትንሽ አቃምሰው ነበር። ፕሬዘዳንቱ ሙሉውን አላሉትም። ሙሉው አንቀፀ-ቃል ከዚህ የሚከተለው ነው።

“Here is the land where the first harmony in the rainbow was born. We walk on the bed rock of our planet’s first continent. Here is the root of the Genesis of Life; the human family was first planted here by the evolutionary hand of Time….We walk on the footprints of the evolutionary ancestors of Man.” ፕሬዘዳንቱ ይህን ብለው ሲያበቁ፤ እኛም ጽዋችንን በቀኝ እጃችን አንስተን፤ “እነሆ በረከት” እንኳን ደህና ወጡ – ብለናቸዋል – ፕሬዘዳንታችንን።

የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን የኢትዮጵያ ቆይታ በወፍ በረር ቃኝተናል። ጉብኝታቸውም ተጠንቆ ተሸኝተዋል። እኛንም ሸኙን። እነሆ ለስንብት “አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ” ብለን ጽዋችንን አንስተናል። በያላችሁበት አሜን በሉ።

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ (ከቴዎድሮስ ሓይሌ)

ከቴዎድሮስ ሓይሌ

“…… ይህ ጦርነት ወደን ሳይሆን ተገደን የገባንበት በመሆኑ ገደልን እያልን የምንፎክርበት አይደለም ፤ በዚያም በኩል ያሉት የኛው ወንድሞች ናቸውና ፤ ምርጫችን ይህ መሆኑ ቢያሳዝንም መብታችንን ለማስከበር ያለው አማራጭ ይህ በመሆኑ ነው ……..’’

ይህን ከላይ የሰፈረውን መልካምና ትሁት አባባል ሰሞኑን የተናገሩት የግንቦት ሰባናትና የአርበኞች ግንባር ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ወሳኙ ትግል በርሃ ከመውረዳቸው አስቀድሞ ነበር። ‘’ የዘመድ ቄስ እየፈታ ያለቅሳል’’ አበው እንዲሉ እኝህ የኢኮኖሚክስ ሊቅና የነጻነት ትግል መሪ ሳንወድ ተገደን ገባንበት ባሉት ትግል ፈቅደውም ሆነ ተገደው የወያኔ ወታድር ሆነው ለሚሰውት ኢትዮጽያውያን ያላችውን ሃዘንና ቁጭት የገለጹበት ቋንቋ በብዙዎች ዘንድ ክብርና አድናቆትን አትርፎላቸዋል።

Dr Berhanu Nega with Patriotic Ginbot 7 Freedom Fighters

ጀግና ይልሃል እንዲህ ነው በትዕቢት ሳይሆን በትህትና ፤ በፉከራ ሳይሆን በትንተና ፤ በጥላቻ ሳይሆን በወገናዊነት ፤ ሳንጃ ወድሮ ጥይቱን ታጥቆ ለሚፋለመው ወገን ያለውን ፍቅርና ሃዘኔታ የሚገልጽ በጎና አስተዋይ መሪ በመሆን ዶ/ር ብርሃኑ ያሳይው አቀራረብ በታሪክ የሚጠቀስ ነው። ከዚህም በላይ እኝህ ታላቅ ምሁር ህዝባችንን ያስደመሙት ፤ በዚህ ከራሴ በላይ ላሳር በሚባልበት ፤ ራስ ወዳድነት መለያችን በሆነበት ፤ ስግብግብነትና ምንቸገረኝነት በተንሰራፋበት ዘመን ፤ ሃብታም ሲሆኑ እንደ ድሃ ፤ በነጻነት ቢኖሩም እንደ ተጨቋኝ ፤ በምቾት ቢኖሩም እንደ ጎስቛላ ፤ ፌሽታ ደስታ ሁካታና ዳንኪራ ባለበት መኖር እየቻሉ ፤ ረሃብና ጥም ፤ ሞትና ዋይታ እባብና ጊንጥ ወዳለበት ወደከፋው በርሃ ያስውረዳቸው ፤ ሕሊና የሚባለው የሰውነት እዳ ፤ ነጻነት የሚባል ቅዱስ መንፈስ ፤ ሃገር የምትባል መልካም ርስት ፤ ሕዝብ የሚባል ታላቅ ቤተሰብ ፤ የወደቀበትን የግፍ አገዛዝ ለማስወገድ ለውሳኙ ትግል ጠቅለው ወደ ትግሉ ግንባር በማቅናታችው ከፍተኛ እክብሮት ከመቸራቸውም በላይ ለትግሉ መነቃቃትን ፈጥረዋል።

ዶ/ር ብርሃኑ የሃገር ፍቅርና ህዝባዊነት ግድ ያለው ዜጋ በመሆኑ ያኔ ባፍላነት እድሜው የተማሪውን እንቅስቃሴ ተከትሎ ወደ በርሃ በመውረድ የከፈለው የዜግነት ግዴታ ይበቃል ሳይል ባለፉት 40 አመታት ውስጥ ያልተቋረጠ ተሳትፎና ትግል ያካሄደ ከራሱ በላይ ለሌሎች የሚያስብ መልካም ዜጋ በመሆኑ ይህው ዛሬም የምቾት ኑሮውን ትቶ ስለ ሃገርና ወገን ሲል ለመስዋእትነት ተሰልፋል ። ይህ ሰው የፖለቲካ ትግሉን እንደገና ከመቀላቀሉ በፊት ያኔ ገና ወያኔ ስልጣን እንደያዘች ከመሪዎቿ ጋር በነበረው ትውውቅ የፖለቲካና የኢኮኖሚክስ ምክር በመለገስ ለስርአቱ መሻሻል እንዲያደርጉ በማገዝ ያደረገው ጥረት ምንም ውጤት ሊያስገኝ ካለመቻሉም በላይ የዚህን ሃገር ወዳድ ምሁር እንቅስቃሴ በቅጡ ባለመረዳት በግዜው እኔን ጨምሮ በተቃውሞው ጎራና በነጻ ሚድያው የተሰለፍነው ፤ በአድርባይ ምሁርነትና ፤ በጥገኛ ከበርቴነት ቁም ስቅሉን በትችትና ከዛም በዘለለ መደዴ ቃላት እንወቅሰው የነበረውን ሁሉ በመቋቋም በትግዕስትና በስክነት ቆይቶ ያ በታሪካችን የሚዘከረውን የዲሞክራሲና የነጻነት ማዕበል ካንቀሳቀሱት የቅንጅትና የሕብረት ጎምቱ ፖለቲከኞች አንዱና መሪ ተዋናይ በመሆን በተለይ ለሕዝብ በቀጥታ ይተላለፍ በነበረው የቴሌቭዥን ስርጭት የወያኔን ሹማምንት ድንቁርና በማስረጃና በትንተና እያጋለጠ ዶ/ር ብርሃኑ ያሳየው ምሁራዊና ሕዝባዊነት ታሪክ ይማይዘነጋው ሃቅ ነው።

ዶ/ር ብርሃኑ በሰላማዊ መንገድ በምርጫ ስርዐት ሕዝብ የስልጣን ባለቤት ይሆናል ከሚል እምነት በመንሳት በዲሞክራሲያዊ ሂደት ለውጥ ሊያመጣ ከጓዶቹ ጋር ያደረገው ትግል ፤ በቀማኛውና በሕገ አራዊቱ የዳቢሎስ የግብር ልጅ የሆኑት ወያኔዎች ሠብአዊነት የራቃችው የሠላምን መንገድ የዘነጉ ፤ በድንቁርና ተውጠው እሳቤያቸውን ሁሉ ባነገቱት ጠመንጃ ባደረጉ ወንበዴዎች የዶ/ብርሃኑ የሰላም ጉዞ ጨንግፎ ፤ ለሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ትግል የተደርገው ጥረት የማታ ማታ ውጤቱ ለብዙዎች ሞት ለሺዎች እስርና ስደት ከማትረፉም በላይ ለማያቋርጥ ጥቃትና በደል የሚዳርግ ማህብራዊ መገለልንና በማስፈን የማያላውስ የጭቆና አገዛዙን በማስፈኑ ፤ ትዕቢት ያደነደናቸውን ሃገር ሻጮችና ጠባብ ዘራፊ ዘረኞች ለማስወገድ ግድ ያላውን የምርጫዎች ሁሉ መጨረሻ ፤ ከመፍትሄዎች ሁሉ መዳረሻ የሆነውን የብረት ትግል ሊያስተባብር ሊታገልና ሊያታግል እነሆ የሞቀ ቪላውን የምቾት ኑሮውን ትቶ ድንጋይ ትራሱ ዳዋ ልብሱ ኮቾሮ ጉርሱ አድርጎ በጡረታ እድሜው ለሃገርና ለወገን ሲል ወስኖ በርሃ ወርዷል።

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ በርሃ መውረድ በዕርግጥ ሕሊና ላለው ለዚህ ትውልድ ሃፍረት ነው ፤ በችግር እሳት የሚገረፈው በሃገር አልባነት የሚሠደደው ፤ ሰርቶ የመኖር ነግዶ ማትረፍ ያልቻለው ፤ ባለግዜዎች ላቆሙት የዘር ጣዖት ካልሰገደ እንድባይተዋር ለሚታይው ፤ የባርነት መርግ የግፍ አገዛዝ የተጫነው ዘረኞች በጎጥ ተጠራርተው በሚከብሩብት ፤ ደናቁርት የስልጣንና የጥቅም ምንጮችን በተቆጣጠሩበት መኖር አይደለም ተስፋ ማድረግ እንኳ በማይቻልበት ሃገር እየኖረ ያለው ይህ ትውልድ ፤ ለመብት ለነጻነቱ ዋጋ መክፈል እያለበት ፀጥ ያለው ፤ እየሞተ የሚፈራውን እየተራበ የሚስቀውን ፤ እየዘፈነ የሚሰደደውን ፤ ከዚህ አስከፊ ሰው በላ አገዛዝ ለመላቀቅ ወኔ ያጠረውን ፤ ይህ የኔ ትውልድ ፤ ለመታደግ ብርሃኑ የወሰድው እርምጃ የሚያኮራ ቢሆንም ፤ እኛ የዚህ ትውልድ አባላት የዚህን ምሁርና ባለጸጋ ፤ ምንም ሳያጣ የእኛን ችግር ችግሩ አድርጎ ከጨካኞች መዳፍ ሊያላቅቀን በተምሳሌትነት ሁሉን ትቶ በርሃ የወረደውን መሪ ፈለግ በመከተል ን ለመብታችን ለመፋለም እንነሳ ዘንድ ለራሳችን ቃል መግባት ይኖርብናል።

ይህ ትውልድ ከዶ/ር ብርሃኑ ከቶስ ምን ይማራል? ይህ ሰው ታላቅ ምሁርና ባለጸጋ ሲሆን ለሃገርና ፤ ለዚህ ትውልድ ሲል ሃብት ፤ንብረቱን ፤ማዕረግ ፤ ክብሩን፤ የደመቀ የአሜሪካ ቅንጡ ኑሮውን ፤ ልጆችና ሚስቱን ፤ ብቻ ሁሉን ትቶ በርሃ ወረደ ። ይህ ትውልድ በሃገሩ ለመኖር መብት ነጻነትና የስራ እድል አጥቶ በሊብያ እንደክብት እንዲታረድ ፤ በደቡብ አፍሪካ እንደቆሻሻ እንዲቃጠል ፤ በሳውዲና በየመን እንደውሻ ተቆጥሮ እንዲገላታ ሃገር አሳጥቶ ያሰደደው አዋርዶ ያዋረድው የሸጠና የለወጠው ፤ በሃገሩም ተምሮ ድንጋይ አንጣፊ አንገት በመድፋቱ ፈሪ ተደርጎ ከሃገሩ ሃብት የበይ ተመልካች በመሆን የቀንና የሌት ህልሙ ነገ ምን በልቼ እውል ይሆን በሚል ተለውጦ ኑሮ ዳግት ሆኖብህ በዘር ሚዛን ከስራው እድል እየተገፋህ እነታሪኬ ባጭሩ በዘርና በፖለቲካ ታማኝነት ሁሉን ማድረግ ሲችሉ፤ በብርሃን ፍጥነት እነ እንቶኔ ኢንቨስተር ሆነው ቤትህን በላይህ እያፈረሱ ከከተማ ሲያባርሩህ ከቀበሌ እስከ ቤተመንግስት የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሹማምንት በታማኝነት እየተሾሙብህ ሰርቶ የመኖር ነግዶ የማትረፍ መብትህ በነዚህ ወራሪ የወያኔ አፓርታይድ ጉጅሌዎች ጫማ ተደፍጥጦ እስከመቼ ትኖራለህ!

ወያኔዎችን ወደ ኋላ ሄደህ ታሪካቸውን ብታጣራ ካንተ ያልተሻሉ ለመማርና ለመስልጠን የማይመቹ የአቦጊዳ ሽፍቶች ፤ የባንዳ ልጆችና ቁሳዊና መንፈሳዊ ድሆች ከገላቸው እድፍ ከጎፈሬያቸው ተባይ ውጭ እንኳን አንተን እያስራቡ እነሱ ጮማ ሊቆርጡ ደረቅ ጋቤጣ እንኳ ብርቃቸው የነበረች ቁጭራወች ዛሬ ሃገርህን ወረው ከእናትህ መዐድ በእኩልነት እንዳትቋደስ እጅህን እያሳጠሩ ኑሮህን የመከራ ያደረጕትን የቀን ጅቦች ልትፋለም በምትችለውና ባለህ አቅም ሁሉ እንድትንቀሳቀስ ታሪክ ሃይማኖት ሰው የመሆን ሞራል ግድ ይሉሃል። ወጣቱ ሆይ ዶ/ር ብርሃኑን የመሰል ሊቅና በሳል መሪ እግዚያብሄር አድሎህ ይህን የፋሽስት የሌባና የዘረኛ መንጋ በግዜ ለማስወገድ ካልተነሳህ ተስፋ የሌለህ በመሆኑ በሞራል በወኔና በቆራጥነት ክብርህን ልታስመልስ በቀለም ይሁን በፍራፍሬ አብዮት ፤ በሰላም ይሁን በአመጽ ፤ በጓንዴ ይሁን በጎራዴ ፤ በኤርትራ ይሁን በኡጋዴ ፤ በድግምት ይሁን በቃልቻ ፤ ብቻ በምትችለውና በማንኛውም መንገድ የትግሬ ነጻ አውጭ (ሕወሃት) በሚባለው ወሮበላ የሌባና የባዕዳን ቅጥረኛ ስብስብ ላይ ክንድህን ታነሳ ዘንድ ግዜውና ሁኔታው ግድ ይሉሃል።

ይህ ደግሞ

ይቻላል! ተችሏልም! መቻልም አለበት!!!

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉዞ… (ክንፉ አሰፋ)

ክንፉ አሰፋ

“…ከዚህ በኋላ ህዝብ ሰብስቦ ማውራት ላቆም ነው። ጊዜው ተቀይሯል። ትግል ለደካማ መንፈስ አይሆንም። ትግል መውደቅን ይጠይቃል። ሲወድቁ ግን ለመነሳት መሞከርን ይጠይቃል። ስንወድቅ ልታዩን ትችላላችሁ ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ … ” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ይህንን የተናገሩት የአስመራ ጉዟቸው ከመሰማቱ ጥቂት ቀናት በፊት ነበር። ንግግሩ ለብዙዎች ግርታ መፍጠሩ አልቀረም። ከቀናት በኋላ የኤርትራን ምድር ሲረግጡ “ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ…” ማለታቸው ግልጽ ሆነ።Professor Berhanu Nega in Eritrea

ከምርጫ 97 በፊት ዶ/ር ብርሃኑ በፖለቲካ ስብእናቸው የሚታወቁት ለሰላማዊ ትግል ባላቸው የከረረ አቋም ነበር። በእስር ቤት ሆነው በጻፉት “የነጻነት ጎሕ ሲቀድ፤ …” መጽሐፋቸው ሰላማዊ ትግል ያለውን የሞራል፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነት ምሳሌ እያስቀመጡ ዘርዝረዋል።

ለዚህም ነበር ከሰላማዊ ትግል ወጥተው “ሁለገብ ትግል” ለማካሄድ ማቀዳቸውን ሲገልጹ ለብዙዎች ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የሆነው። የጦርነትን አስከፊ ገጽታ ሲነግሩን የነበሩ እኝህ ምሁር በአንድ ግዜ ወደ ተቃራኒው የትግል ስልት ሲዞሩ ያቀርቡት የነበረው ምክንያት በወቅቱ ብዙዎችን ሊያሳምን አልቻለም። ምክንያቱም አመጽ ወይንም ጦርነት ከባድ ነገር ነው። ገንዘብ እና ግዜን ይበላል። ከሁሉም በላይ የህይወት መስዋእነትን ይጠይቃል። የሰላማዊ ትግሉ ስልቶች ገና በደንብ አልተፈተሹም የሚሉም ጥቂቶች አልነበሩም።

ከአምስት ግዜ ምርጫ በኋላም ህወሃት ሕዝብ ላይ መቀለዱን አላቆመም። በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትንም ጭራሽ ወደ ጫካ እንዲገቡ፣ አልያም እንዲሰደዱ አማራጭ መስጠት ያዙ። የትጥቁን መንገድ “ጨርቅ ያርግላችሁ” ሲሉም አሾፉ።

የ “ምርጫ 2007″ ውጤት በተሰማ ማዕግስት ከዴንቨር-ኰሎራዶ አንድ የቀድሞ ህወሃት ታጋይ ስልኬ ላይ ደውሎ እንዲህ አለኝ። “ግዜው የኛ ነው። ገና መቶ አመት እንገዛችኋለን። ታዲያ ስንገዘችሁ ዝም ብለን አይደለም። እየረገጥን እንገዛችኋለን…” ሰውየው እኔ እንድናገር እንኳን እድል አልሰጠኝም። ስለምርጫው ውጤት በድረ-ገጾች ላይ የሰጠሁት አስተያየት እንዳበሳጨው ገባኝ። በትግርኛ እና በአማርኛ እያቀላቀለ ተሳደበ። ዘር እና ሃይማኖትን ጭምር እየጠራ ተሳደበ። በትእቢት የተወጠረው ይህ ሰው ሙሉ ስሙን እና አድራሻውን ሳይቀር ይናገር ነበር። “ከፈለግክ ቅዳኝ። ማንንም አንፈራም!” ይል ነበር። እርግጥም ድምጹ በቴሌፎኔ መቅጃ ሳጥን ውስጥ ቀርቷል። ይህንን አጸያፊ ስድብ መልቀቁ ወገን ከወገን ማጋደል ይሆናል በሚል እሳቤም ለግዜው ይዤዋለሁ።

ማንነትን የሚፈታተን፣ ክብርን የሚነካ ንግግር ነው። ስድቡን ሁሉ በትእግስት ከሰማሁ በኋላ አንድ ቃል ብቻ ተናግሬ ስልኩን ዘጋሁት። “ትዕቢት ውድቀትን ትቀድማለች።”

የያዝኩትን ትንሽ መረጃ በመንተራስ ስለሰውየው ማንነት አንዳንድ ነገር ማወቅ ቻልኩ። ሰባት አመት የህወሃት ትግል ውስጥ የነበረ ሰው ነው። ይህ ግለሰብ ዴንቨር ኮሎራዶ ከአመታት በፊት ሲገባ ባዶ እጁን ነበር። አሁን ግን ሚሊየነር ሆኗል። የህወሃትን የተዘረፈ ገንዘብ በዶላር ለማጽዳት ወደ ዴንቨር የሚላኩ ሰዎች ቀጥር ቀላል አይደለም። እየረገጥን ገዝተን፣ እየረገጥን እንዘርፋለን፣ ይህንንም አሜን ብላችሁ ተቀበሉ ነው የሚሉን። ከባዶ ተነስተው መጠን የሌለው ስልጣን እና ገንዘብ ሲያካብቱ፤ በያዙት ነገር ይታወራሉ። ድንቁርና ሲታከልበት ደግሞ ስልጣናቸው ዘለአለማዊ፣ ሃብታቸውም የማያልቅ ይመስላቸዋል።

እንደዚህ አይነቶች ወንድነትን እና የሃገርን ክብር የሚፈታተኑ ነገሮች ተቆጥረው አያልቁም። ተሳፋሪዎችን ይዞ እየበረረ ያለ የአየር መንገድ አውሮፕላን በአንድ ካድሬ ትዕዛዝ እንዲመለስ የሚደረግባት ሃገር ሆናለች ኢትዮጵያ። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘሁት አንድ መረጃ የሚያሳየን ይህንኑ ነው። ከአዲስ አበባ ናይሮቢ-ኬንያ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ከጀመረ በኋላ እንዲመለስ መደረጉ እና በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ኪሳራ ደርሶበታል። ይህ የሆነው ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ አውሮፕላኑ ውስጥ ስለነበር ብቻ ነው። እነዚህ ሰዎች ሃገሪጥዋን የግል ንብረታቸው አድርገዋታል።

በፈለጉ ግዜ፣ የፈለጉትን ያስራሉ። በፈለጉ ግዜ የፈለጉትን ይለቅቃሉ። በእስር ላይ ከሉ 19 ጋዜጠኞች ይልቅ ለአንድ ባእድ መሪ ክብር የሚሰጡ፣ በአልሻባብ ከሚገደልው ሰራዊት ይልቅ ለአሜሪካ ብሄራው ጥቅም የሚጨነቁ የውስጥ ባዕዳን ናቸው ስልጣኑን በሃይል ያየዙት።

20 አመታት በአንድ ርእዮተ-ዓለም፣ በአንድ አገዛዝ፣ በአንድ ሰው አስተሳሰብ መዝለቅ እጅግ እጅግ ይከብዳል። በተለይ ደግሞ በምእራቡ አለም ውስጥ ለሚኖር ሰው ፍጹም የማይታሰብ ነገር ነው። በ97ቱ ግድያ እጅግ ተቆጥቶ የነበረው ሰር ቦብ ጌልዶፍ “መቼ ነው የምታድጉት? እስቲ እደጉ!” ብሏቸው ነበር። አሁንም አላደጉም። አሁንም ሰው እየገደሉ ነው። ለማደግ የምኒሊክ ቤተ-መንግስት ሃያ አመታት መቆየት አያስፈልግም። ለእድገት ለውጥ ያስፈልጋል። የስርዓት ለውጥ፣ የሰው ለውጥ፣ የአስተዳደር ለውጥ፣ የአቅጣጫ ለውጥ፣ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል።

በርካቶች በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት እጅግ ጣሩ። ጥረታቸው ግን እንደ ደካማነት ተቆጠረባቸው። በያዙት የጦር መሳርያ ብቻ የሚተማመኑ ጉልበተኞች ቀለዱባቸው። የህዝብን ድምጽ እየሰረቁ መቀመጣቸው ሳያንስ መራጩን ሕዝብ እያሳደዱ መበቀል ያዙ። ኢትዮጵያ በሰላማዊ ትግል ለውጥ ማምጣት ምርጫ ለአምስተኛ ግዜ ተሞከረ። አምስቱም ተጭበረበረ። ከአሁን በኋላ በምርጫ ለውጥ እናመጣለን ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ደረጃ ላይ እንደሆነ የምርጫ 2007ቱ ትዕይንትን ብቻ ማጤኑ ይበቃል። በታሪክ 100% አሸነፍኩ ብሎ የተናገረ አንባገነን መንግስት በኛው ምድር ተፈጠረ። ይህ ሕዝብ ላይ ማፌዝ ነው። ትዕቢት፣ ድፍረት እና ንቀት የተሞላበት ፌዝ። “ምንም አታመጣም!” አይነት ንቀት!

በፖለቲካ አግባብ ጦርነት የዲፕሎማሲ ጣርያ፣ የሰላማዊ ትግል መጨረሻው አማራጭ ነው።

ከዚህ የአገዛዝ ንቀት በኋላ ህዝብ ለአመጽ ቢነሳ ተጠያቂው ያለህዝብ ይሁንታ ስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ብቻ ነው። ህዝቡን ወደ ስደት እና ወደማይፈልገው አመጽ እየመሩት ያሉት እነዚያው የስልጣን እና የንዋይ ጥመኞች ናቸው። ይህ ንቀት ከትጥቅ ትግል ጋር ችግር አለብኝ የምንል ወገኖችን እንኳን የሚፈታተን ነገር ነው።

ዶ/ር ብርሃኑ ሲተቹበት የነበረው ሌላው ጉዳይ ደግሞ ትግሉን ከርቀት መምራት ያለመቻሉ ነገር ነበር። በሻእቢያ ላይ ያለው ጥርጣሬ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ይህ ጉዞ በዶ/ር ብርሃኑ ላይ ይነሳ የነበረውን የሞራል እና የሃላፊነት ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል። ለሰራዊቱ የመተማመን፣ ለህዝቡም የመነሳሳት ስሜት ይፈጥራል።

ከ21 ዓመት በላይ ያለ ለውጥ መቀመት በጣም ያሰለቻል። 21 አመት እየረገጡ እና እየዘረፉ መቀመጥ ይበዛል። ኢትዮጵያ ለውጥ ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ህዝብ ፍትሃዊ ስርዓት ያስፈልገዋል። በሰላማዊው መንገድ ለለውጥ የተሰለፉ ሃይሎች እየታፈኑ፤ እየተሰቃዩ፣ እየተገደሉም ነው። እየተገደሉ የሚገድሉ ሲነሱ “ባንደግፋቸውም አንቃወማቸው” ያለው ማን ነበር?

ለነጻነት ሲባል ራሳቸውን ለመሰዋዕትነት የሚያቀርቡ ወገኖች የሚያምጹት ያለ ምክንያት አይደለም። በሁሉም ውስጥ ቁስል አለ!

ሀገራችን ከመሸጧ በፊት መድረስ የዜጎች ግዴታ ነው! – ጉዳያችን

no water

ኢትዮጵያ በኢህአዴግ ዘመን ከውጭ በተበደረችው ብድር ሳብያ በዓለም ላይ አደጋ ከተጋረጠባቸው 14 ሃገራት ዝርዝር ውስጥ መግባቷን የዓለም ባንክ አስታወቀ።

ኢትዮጵያ የገባችበት ብድር ከፍተኛ ቢሆንም የመሰረታዊ ፍላጎቶችን በዋና ከተማ ደረጃም ማዳረስ አልቻለችም በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር የት ገባ?

አንዲት ሀገር ከጠቅላላ ምርቷ 30 ከመቶው ከለጋሽ ተቋማትና ሃገራት የሚገኝ ብድር ላይ ከተመሰረተ ከፍተኛ የዕዳ ቀውስ ውስጥ እየገባች መሆኗን ያማለክታል ያለው የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የብድር መጠኗ ከጠቅላላ ምርቷ አሁን 45 በመቶ ሲሆን በጥቂት ጊዜያት ውስጥ 65 በመቶ ይደርሳል በማለት የአደጋውን አሳሳቢነት ያመላክታል።

የብድር ጉዳይ አዲሱ የዓለማችን ሃገራትን የማንበርከክያ መሳርያ እየሆነ ነው።በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት የሀገራት ብድር በሁለት ጎራ በተከፈሉ ኃይሎች መካከል በነበረ ፍትግያ ሳብያ የማምለጫውም ሆነ ፋታ ለማግኘት የመደራደር አቅም ነበረ።አሁን ባለንበት ዓለም ግን የእዚህ አይነቱ ዕድል አይታይም።ለእዚህም አይነተኛ ምሳሌ የምትሆነው ግሪክ ነች።የግሪክ የብድር ቀውስ የምጣኔ ሀብቷን ከማድቀቁም በላይ የሀገሪቱን የውስጥ ፀጥታ ያናጋ እና በቅርቡ በሕዝብ በተመረጠውን መንግስቷ እና በሕዝቡ መካከል መተማመንን ያጠፋ አሁንም ይሄው የብድር ቀውስ መሆኑ ይታወቃል።
ኢትዮጵያ በኢህአዴግ/ወያኔ የ24 ዓመታት የስልጣን ዘመን ሀገሪቱ በታሪክ አይታ የማታውቀው ዕዳ ውስጥ ተዘፍቃለች።ብድሩ ለልማ ሥራ ውሎ ቢሆን ጥሩ ነበር።ሆኖም ግን የዓለም የገንዘብ ድርጅቶችም ሆኑ የእራሱ የመንግስት ኦዲተር ሪፖርት የሚያሳየን አንድ ነገር ነው።ይሄውም አብዛግኛው በአሁኑ ትውልድ እና በመጪው ትውልድ ስም የሚፈፀመው ብድር በጥቂት ባለስልጣናት እና ሙሰኛ አጋሮቻቸው ወደውጭ ሃገራት መወሰዱ የአደባባይ ሚስጥር መሆኑ ነው።”ግሎባል ፋይናንስ ኢንተግሪቲ” ባለፈው ዓመት ባወጣው ዘገባ ኢትዮጵያ በአስር ዓመታት ውስጥ ብቻ በሕገ ወጥ መንገድ 16.5 ቢልዮን ዶላር በተለያየ መንገድ መውጣቱን በምሬት ገልጧል።ሀገር በእድገት መንገድ ላይ ነው የሚባለው አብዛኛውን የልማት ሀብት በሀገር ውስጥ አፍርቶ ቀሪውን በብድር ወስዶ የልማት ፕሮጀክት ሲሰራ ነው እንጂ እስከ 65 በመቶ የሚሆን የሀገሪቱን ሀብት በብድር ላይ ጥሎ በብድር የተገኘውንም ገንዘብ ለጥቂት ቅምጥል ባለስልጣኖች እና አጋሮቻቸውም ኪስ ማድለብያ እያደርጉ ሀገሪቱን ወደ ባሰ ድህነት መክተት ከወንጀል ተጠያቂነት አያድንም።ባለፉት 5 ዓመታት የትራንስፎርሜሽን እቅዱን እየሰራን ነው ያለው ስርዓቱ ሚያዝያ 2/2006 ዓም የ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ባቀረበው የአምስት ዓመት ትራንስፎርሜሽን ክንውን ላይ ከተባለው ግብ ኢትዮጵያ መድረስ አለመቻሏን አምኗል። የምክር ቤቱ ብቸኛ ተቃዋሚ አቶ ግርማ ”ቀድሞውንም ዕቅዱ በአግባቡ ያልታሰበበት ለመሆኑ አሁን ላለበት ውጤት መብቃቱ በራሱ ምስክር ነው” ብለዋል።
ይህ ሁሉ ሆኖ ነው እንግዲህ ሀገራችን በብድር ላይ ብድር እየተወሰደ ዛሬ ከ14ቱ በብድር ብዛታቸው አደጋ ላይ ከወደቁ የዓለም ሃገራት ተርታ አሰለፋት።በነገራችን ላይ ”ደፋሮቹ” የስርዓቱ አውራዎች አሁንም ለሌላ 5 ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ እያቀድን ነው ብለው መሰብሰባቸው ይታወቃል።ምናልባትም ነሐሴ መጨረሻ ላይ ለሕዝቡ ማባበያ ያቀርቡት ይሆናል።እውነታው ግን በአሁኑ ትውልድ እና በመጪው ትውልድ ስም ብድር ተበደሩ፣ግልፅነት እና ተጠያቂነት የሌላቸው የልማት ፕሮግራምቀረፅን አሉ፣መሰረታዊ መርሆዎችን ያልተከተሉ ፕሮጀክቶች አስተዋወቁ በፕሮጀክቶቹ ስም ገንዘብ ወደ ውጭ ሸሸ።በመጨረሻ ብድር የመመልስ አቅም የሌላት ብቻ ሳይሆን አሁን ላለው አስመጪ ነጋዴ የውጭ ምንዛሪ ማቅረብ የማይችል ብሔራዊ ባንክ አስታቅፈው ቁጭ አሉ።
ፅሁፌን ከመደምደሜ በፊት ለእዚህ ፅሁፍ መንደርደርያ የሆነውን የ”ዘጋርድያን” ዘገባ መሰረት አድርጎ የ”አዲስ አድማስ” ጋዜጣ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 11/2007 ዓም ለንባብ ያቀረበው ዘገባ ከእዚህ በታች ይመልከቱት ዘንድ እጠይቃለሁ።

የውጭ ብድር እዳ ኢትዮጵያን ያሰጋታል ተባለ

አዲስ አድማስ
Saturday, 18 July 2015 10:55

• ስጋት ከተጋረጠባቸው 14 ሀገራት ውስጥ ተካታለች
• ሴኔጋል፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ሞዛምቢክ በዕዳ ተዘፍቀዋል

የውጪ ብድር እዳ ኢኮኖሚያቸውን ሊፈታተን ይችላል የሚል ስጋት ከተጋረጠባቸው 14 የአለም አገራት ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ዘ ጋርዲያን የአለም ባንክን ሪፖርት ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የብድር እዳ እንዳለባት የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ ከአጠቃላይ አገራዊ ምርቷ 45 በመቶ የሚሆነው ከብድር የተገኘ ገንዘብ እንደሆነ ጠቁሞ፤ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ይህ አኃዝ ወደ 65 በመቶ ሊያሻቅብ እንደሚችል ጠቁሟል፡፡ ከለጋሽ ተቋማትና ሃገራት የሚገኝ ብድር ለአጠቃላይ አገራዊ ምርት ያለው አስተዋጽኦ ከ30 በመቶ በላይ ከሆነ ሀገራት ወደ ከፍተኛ የእዳ ቀውስ እያመሩ መሆኑን እንደሚያመለክት የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ኢትዮጵያም በዚህ የአደጋ ቀጠና በከፍተኛ ደረጃ ከገቡ 14 የአለም ሀገሮች መካከል ተጠቅሣለች። ከፍተኛ የውጭ እዳ ውስጥ ተዘፍቀዋል የተባሉት 14 ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ቡታን፣ ኬፕ ቨርዲ፣ ዶሚኒካ፣ ጋና፣ ላኦስ፣ ሞሪታኒያ፣ ሞንጐሊያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሣሞኣ፣ ሣኦቶሜ ፕሪንቼቤ፣ ሴኔጋል፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል 24 የአለም ሀገሮች የውጭ እዳቸው በሚያሰጋ ደረጃ እየጨመረና ወደ አደጋው ቀጠናም እየተንደረደሩ ነው በሚል ተጠቅሰዋል፡፡

አንዳንድ በአስጊ ደረጃ እዳ ውስጥ ተዘፍቀዋል የተባሉ ሀገራት፣ የተበደሩትን ገንዘብ ለተገቢው አላማ መጠቀም አለመቻላቸው ለቀውስ እንደዳረጋቸው በሪፖርቱ የተጠቆመ ሲሆን በዚህ ረገድ ጋና ምሣሌነት ተጠቅሳለች፡፡ ሌሎችም አዋጭ የሆነ የብድር አመላለስ ስርአት ባለመከተላቸው የችግሩ ሠለባ እየሆኑ እንደመጡ የጠቆመው ሪፖርቱ፤ እነዚህ ሀገራት ከዚህ እዳ የሚወጡበትን መንገድ ካላጤኑ ከፍተኛ ቀውስ ሊገጥማቸው ይችላል ብሏል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የግል ኩባንያዎችና መንግስታት አለም ባንክን ከመሳሰሉ አበዳሪ ተቋማት ከ2009 እ.ኤ.አ ጀምሮ በየአመቱ የሚበደሩት ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው ተብሏል፡፡ በ2013 እ.ኤ.አ የአለም ሀገራት አጠቃላይ የብድር መጠን 11.3 ትሪሊዮን ዶላር ሲሆን በ2014 13.8 እንዲሁም በዘንድሮው አመት 14.7 ትሪሊዮን ዶላር መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ሐምሌ 11/2007 ዓም (ጁላይ 18/2015)

Source:: gudayachn

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8788#sthash.KXRWFT8G.dpuf

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎች አመራሮች የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮችን በአካል ተቀላቀሉ

በ1997ቱ ሀገር አቀፍ ምርጫ ወቅት ቅንጅትን ወክለው ተወዳድረው በከፍተኛ ድምጽ አሸንፈው የአዲስ አበባ ከንቲባ እንዲሆኑ ተመርጠው የነበሩት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወያኔ የድምጽ ኮሮጆዎችን ገልብጦና ምርጫውን አጭበርብሮ ስልጣኑን በጉልበቱ ይዞ ለመቀጠል በመወሰኑ ምክንያት ከበርካታ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ጋር ለሁለት ዓመት ያህል በእስር ቤት እንዲቆዩ ተደርገዋል።Dr. Berhanu Nega Ginbot 7 Chairman

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከእስር ተፈተው ቀደም ሲል ይኖሩበት ወደነበረው አሜሪካን ሀገር ከተጓዙ በኋላ አፍታም ሳይቆዩ ነበር የሁለገብ ትግልን አስፈላጊነት መናገር የጀመሩት። ዶ/ር ብርሃኑ ወዲያውም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ከሌሎች ሃሳባቸውን ከሚጋሩ ስመጥር ፖለቲከኞች እና የለውጥ አራማጅ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄን መሰረቱ፣ በወቅቱ ዶ/ር ብርሃኑ የእርሳቸውን እና በግንቦት 7 ዙሪያ የተሰባሰቡ ጓዶቻቸውን ቁርጠኛነት ሲያስገነዝቡ “ዘረኛውን የወያኔ አምባገነን አገዛዝ ከህዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድ የማንፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም” ነበር ያሉት።

ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ግንቦት 7 ጠንካራ የተዋጊ ሃይል ማቋቋም የቻለ ሲሆን ለጥቆም ቀደም ሲል ጀምሮ ወያኔን ማስወገድ የሚቻለው በሃይል ብቻ ነው በማለት መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ከነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ጋር በመዋሃድ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄን መፍጠር ተቻለ።

ዛሬ በወያኔ እጅ ወድቆ የሚገኘው በሳሉና ቆራጡ ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስካሁን ግንቦት 7 በተጓዘባቸው የስኬት ጎዳናዎች ሁሉ አሻራው እንዳለበት በቅርብ አብረውት ሲታገሉ የነበሩ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይመሰክራሉ።

በወጣት አርበኞች የተገነባውና እራሱን ለውጊያ ብቃት ሲያደራጅ የሰነበተው አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ ክንዱን ማሳረፍ በጀመረ ማግስት ነው እንግዲህ የንቅናቄው መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም አመራሮች በአካል የትግሉን ጎራ ለመቀላቀል ወደ ሜዳ የወረዱት።

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋንና የሌሎች አመራሮችን የትግሉን ጎራ በአካል መቀላቀል አስመልክቶ ንቅናቄው ባሰራጨው አጭር መልዕክት እንደገለጸው፣

“የተቀደሰ አላማን ያነገብን እርኩስ አላማን በሚያራምዱት ላይ ድልን እንቀናጃለን፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም የንቅናቄው አመራሮች የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ነጻነት፣ የፍትህ እና የዴሞክራሲ ጎዳና እንደሚመሩት ጥርጥር የለንም” ብሏል።

አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም የንቅናቄው አመራሮች በአካል ከአርበኞቹ ጎን መገኘት ከፍተኛ ሞራል እና መነቃቃትን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ ጥቃት የመሰንዘሩ እድምታዎች

The Patriotic Ginbot 7 attacks factors

እድምታው በወያኔ ጎራ

– ለወትሮው ጭቃ በመትፋት የሚታወቀው የወያኔ ሹማምንት እና ካድሬዎች አንደበት የመኮማተር አዝማሚያ ታይቶበታል። በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ኢትዮጵያውያን አፈናው እና ጫናው በዛብን ሲሉ “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ” በማለት የሚታወቁት ወያኔዎች የጦርነትን አስከፊነት መስበክ ጀምረዋል።

– ኢትዮጵያን እንደ ሃገር፣ የኢትዮጵያን ታሪክ እንደታሪክ እውቅና ለመስጠት እጅግ የሚጠየፉት ወያኔዎች “እምዬ ኢትዮጵያ” ማለት አብዝተዋል።

– ኤርትራን ከእናት ሃገርዋ ኢትዮጵያ ለመገንጠል፣ ኢትዮጵያን ባህር በር አልባ ለማድረግ ከሻብያ ጋር ተቀናጅተው ኢትዮጵያን ሲወጉ የኖሩት ወያኔዎች ኤርትራ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ናት በፍጹም ከኤርትራ ጋር አትነካኩ ሲሉ እየተደመጡ ነው። የወያኔዎቹ ቁንጮ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ከኤርትራ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ሲጠየቅ “ግንኙነታችን እንደ መርፌና ክር ነው” ማለቱን ራዕዩን የወረሱት ወያኔዎች የአርበኞች ግንቦት 7 ምት አስረስቷቸዋል። ሌላኛው የወያኔዎች ቁንጮ ስበሃት ነጋ “ኤርትራ ጥቃት ቢሰነዘርባት ወያኔ ከኤርትራ ጎን ተሰልፎ ይዋጋል” ማለቱን የአርበኞች ግንቦት 7 ጠንካራ ጡጫ አስረስቷቸዋል።

– ቀደም ሲል ከኤርትራ ባለስልጣኖች ጋር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር እንደሚፈልግ ያሳወቀው አሻንጉሊቱ ሃይለማርያም ደሳለኝ አርበኞች ግንቦት 7 ጥቃት በሰነዘረ ማግስት “ኤርትራ አሸግራናለች የኢትዮጵያን ህዝብ አስፈቅደን ጦርነት እንገጥማለን” ብሏል።

– በተለያየ ጊዜ አርበኞች ስለሚፈጽሟቸው ጥቃቶች እውቅና ላለመስጠት ሲል ትንፍሽ የማይለው ወያኔ፣ “አንድ ጊዜ በአካባቢው በመሬት ይገባኛል የተነሳ የነበረ ግጭት ነው” ሲል በሌላ ጊዜ ደግሞ “የሻብያ ተላላኪዎችን ደመሰስኩ” በማለት በተዘዋዋሪም ቢሆን ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር በመፋለም ላይ እንደሚገኙ አምኗል።

የተቃዋሚ ጭንብል በለበሱት ጎራ የአርበኞች ግንቦት 7 ጥቃት የመሰንዘር እድምታ

– ላለፉት በርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች ውጤት ማስመዝገብ ሲጀምሩ ውዥምብር በመንዛት፣ የሃሰት ከፋፋይ ዜናዎችን በማሰራጨትና የትግሉን ግለት ለማቀዝቀዝ ሙከራ በማድረግ የሚታወቁ ግለሰቦች የአርበኞች ግቦት 7ን ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘር ተከትሎ ባልተቀናጀ መልኩ አደባባይ እየወጡና እራሳቸውን እያጋለጡ ይገኛሉ።

– ኤልያስ ክፍሌ (የኢትዮጵያን ሪቪው ድረገጽ አዘጋጅ) አንዱ ነው። ኤልያስ ክፍሌ ወያኔን እየተፋለሙ ባሉ አርበኞች ላይ በርካታ የሃሰት ዘገባዎችን በማሰራጨት የሚታወቅ ቢሆንም ሰሞኑን አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ የሚናገራቸው ነገሮች “ይህ ሰው አበደ?” የሚያስብሉ ናቸው። ከብዙ እጅ እግር ከሌላቸው ጸረ አርበኞች ግንቦት 7ና ጸረ ኢሳት ቴሌቪዥን ንግግሮቹ ለመጥቀስ ያህል “የኤርትራ መንግስት ከኳታር እና ከሳውዲ አረቢያ በእርዳታ ከሚያገኘው ብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ውስጥ ግማሹን ለአርበኞች ግንቦት 7 እና ለኢሳት ይሰጣል” በማለት ተላብሶ የኖረውን የተቃዋሚ ጭምብል ገፎ ወጥቷል።

– ሌላኛው የአርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ ጥቃት መሰንዘር ሽብር የለቀቀበትና የተቃዋሚ ጭምብል አጥልቆ የኖረው የቀድሞ ተወዛዋዥና የአሁኑ ጋዜጠኛ አበበ በለው ይባላል። በሰሜን የአርበኞች እንቅስቃሴ እያየለ ሲመጣ ነው አበበ በለው መተራመስ የጀመረው። የኢሳት ጋዜጠኞች ወደ ኤርትራ ተጉዘው የአርበኞቹን እንቅስቃሴ በስፋት እየዘገቡ በነበረበት ወቅት ሁኔታው ያላስደሰተው አበበ በለው ከረጂም አመታት በፊት በምግባረ ብልሹነት ከአርበኞች ግንባር የተወገዱ ግለሰቦችን በማፈላለግ የቻለውን ያህል በትግል ሜዳ እየተዋደቁ በሚገኙ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች ላይ ጭቃ ሲለጥፍ ሰንብቷል። አበበ በለው ይባስ ተስፋ በቆረጠ ሁኔታ እራሱን ባደባባይ ማጋለጥ የጀመረው ግን አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ ጥቃት መክፈቱን ይፋ ባደረገ ሰሞን ነው። አበበ በለው እንዲህ አለ “ወያኔ እና ሻብያ በፍጹም አልተጣሉም… ለማረጋገጫም ወያኔ በየዓመቱ ለኤርትራ መንግስት 250 ሚሊዮን ዶላር በስጦታ መልክ ያበረክታል” አበበ በለው ይህንን ከተናገረ በኋላ በቃለ-ምልልሱ ወቅት የተቀዳው ድምጽ ድረገጾች ላይ ሲለጠፍ “ወያኔ በየዓመቱ ለኤርትራ መንግስት 250 ሚሊዮን ዶላር በስጦታ መልክ ያበረክታል” የምትለው ሃረግ ተቆርጣ እንድትወጣ ተደርጋለች።

የአርበኞች ግንቦት 7 ማጥቃት በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጎራ የፈጠረው እድምታ

– በተለያዩ የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ብዙ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሰብስበው ለአርበኞች ግንቦት 7 ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ አበርክተዋል።

– በሃገር ቤትም ሆነ በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን አርበኞቹን በርቱልን ከጎናችሁ ነን እያሉ ነው።

– አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ ጥቃት መሰንዘር በጀመረባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአርበኛውን ጎራ በስፋት በመቀላቀል ላይ እንደሚገኙ አርበኞቹ እየገለጹ ነው።

– የማህበራዊ ድረገጾችን የሚጠቀሙ ለውጥ አራማጅ ኢትዮጵያውያን እጅግ ፈጣን በሆነ ሁኔታ ዜናዎችንና መልዕክቶችን በማሰራጨት በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥረዋል፣ የመረጃ ክፍተት እንዳይኖርም የላቀ አስተዋጸኦ በማበርከት ላይ ናቸው።

አርበኞች ግንቦት 7 በወልቃይትና አርማጭሆ መሬቶች ላይ እየተደረገ የሚገኘው ጦርነት በህዝቡና በህወሓት መካከል ሆኗል አለ

arebegnoch
የአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ እንደዘገበው:

* ‪‎የተጀመረው‬ የነፃነት ትግል በኢትዮጵያ መሬት ላይ በህዝቡ መካከል ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
* የህወሓት‬ አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሲፈፅመው የቆየው እስር፣ አፈና፣ ግድያ፣ ማንገላታት፣ ማሸበርና ማፈናቀል በነፍጥ የሚደረገው ትግል ከተጀመረ ወዲህ በእጅጉ ከፍቷል፡፡

ሁለገብ የትግል ስልት የሚከተለው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ በጠብመንጃ ስልጣን ጨብጦ በመንግስትነት ስም የኢትዮጵያን ህዝብ አፍኖ እየገዛ እና አንጡራ ሀብቱን ከገደብ በላይ እየመዘበረ የሚገኘውን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የተባለ ዘረኛ ቡድን ከመመካትም አልፎ በሚያመልከው ጠብመንጃ ደምስሶ በምትኩ ህዝባዊ መንግስት እንዲመሰረት ለማድረግ በበረሃ የጀመረው የትጥቅ ትግል በኢትዮጵያ መሬት ላይ በህዝቡ መካከል አንድ እግሩን በአስተማማኝ ሁኔታ ተክሏል፡፡
መላ ኢትዮጵያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በሸፈነ መልኩ በቅርቡ ለሚደረገው የህወሓትን ጎጠኛ ቡድን በኃይል ጠራርጎ ከአገራችን ምድር የማስወገድ ጦርነት የነፃነት ትሉ ብቸኛ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ በሙሉ እንዲሳተፍ እና በበላይነት እንዲመራው የሚያስችሉ ህወሃትን ህልውና በማሳጣት ግብአተ መሬቱን የሚያፋጥኑ ሰፊና ጥልቅ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

ሰኔ 25 2007 ዓ.ም በወልቃይት የተጀመረው ህወሓትን የማድማትና ከስሩ የመገዝገዙ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ወደ አርማጭሆ ተስፋፍቶ ህዝባዊነትን በተላበሰ ሁኔታ የማውደም ስልቱን እየቀያየረ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 ሉኣላዊ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን የሚታገልለት የኢትዮጵያ ህዝብም የትግሉ ባለቤትና መሪ ሊሆን የሚችልበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥራል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በወልቃይትና አርማጭሆ መሬቶች ላይ እየተደረገ የሚገኘው ጦርነት በህዝቡና በህወሓት መካከል ሆኗል፡፡ በአካባቢው ህወሓት ሲያደርሰው በቆየው ግፍና በደል ተማረው ከፋኝ ብለው ነፍጥ በማንሳት ጫካ ገብተው የሸፈቱት ገበሬዎች በአርበኞች ግንቦት 7 ጥላ ስር በአንድነት እየተሰባሰቡና በአንድ ዓላማ ተሳስረው የነፃነት ፍልሚያውን አጋግለውት ይገኛሉ፡፡ ህወሃት መራሹ የመከላከያ ሰራዊት በያቅጣጫው በሚደርስበት የደፈጣ እና ድንገተኛ ጥቃት መድረሻው ጠፍቶበት እየታመሰ ይገኛል፡፡ በሰራዊቱ መካከል እርስበርስ አለመተማመን እያየለ ከመምጣቱ በተጨማሪ ሽሽትና መክዳት የዕለት ከዕለት ተግባሩ ሆኗል፡፡

በመላው ኢትዮጵያ ብልጭ ድርግም ሲል የቆየው የፀረ ህወሓት ትግል ንቅናቄ ችቦ ተለኩሶ መንቀልቀል በመጀመሩ ህዝቡ በየአካባቢው ያለማንም አነሳሽ በራሱ ውስጥ ለውስጥ እየተደራጀ ለአይቀሬውና የመጨረሻው ፍልሚያ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 በህወሓት ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ ወዲህ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ወጣቶች የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ላይ ናቸው፡፡ ከአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የእንቀላቀል ጥያቄ የሚያቀርቡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በጅጉ በመጨመሩ አርበኞች ግንቦት 7 አዳዲስ ታጋዮችን የመቀበሉ ተግባር ከአቅሙ በላይ እየሆነበት መጥቷል፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 በኢትዮጵያ መሬት ላይ በህዝቡ መካከል እያደረገ ከሚገኘው ጦርነት ጎን ለጎን ከመተማ እስከ ጎጃም እንዲሁም አርባ ምንጭ ድረስ የድርጅቱን ህዝባዊ ዓላማና የትግል ጥሪ የያዙ በራሪ ወረቀቶችን አሰራጭቷል፡፡

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለ24 ዓመታት ሲፈፅመው የቆየውን መጠነ ሰፊ ሽብር አሁንም በተለይም ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ በከፋ ሁኔታ አጠናክሮ ቀጥሎበት ይገኛል፡፡

ህወሓት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ታማኝ የሚላቸውን ደህንነቶቹንና የታጠቁ ቡድኖቹን አሰማርቶ ህዝቡን በተለይም ደግሞ ወጣቶችን እያፈነ ወደ ስውር ማጎሪያው በመውሰድና ሰቆቃ በመፈፀም ተግባር ከመጠመዱ አልፎ ሌላ ጭምብል በማጥለቅ ህዝብ ጨፍጭፎ የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት ስውር ሴራ መጠንሰሱን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ አጋልጧል፡፡

ከህወሓት የደህንነት ቢሮ ታማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያረጋግጠው ህወሓት በጎንደርና አካባቢው በጦር አውሮፕላን ህዝብ በመጨፍጨፍ በአርበኞች ግንቦት 7 እና በኤርትራ መንግስት የማላከክ ስውር ዕቅድ ነድፎ አሳቻ ሰዓት እስኪያገኝ እየተጠባበቀ አድብቶ ይገኛል፡፡

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45158#sthash.JJWrCWNl.dpuf

ኢትዮጵያ ከ184 አገራት 171ኛዋ ደሃ አገር!

women-carrying-e1437195426496-620x310“ኢኮኖሚ በመንገድና ፎቅ ሥራ አይለካም”

ዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የአምስት ዓመታት አኻዝ ያካተተ የዓለማችንን ሃብታምና ደሃ አገራት ዝርዝር ሰሞኑን አውጥቷል፡፡ የዓለም የፋይናንስ መጽሔት ላይ የታተመው ይኸው ዘገባ እንደሚያሳየው በሃብታምና ደሃ አገራት መካከል ያለው ልዩነት በእጅጉ እየጨመረ እንደመጣ ነው፡፡ በዚህ የአምስት ዓመት አኻዛዊ ዘገባ መሠረት ከ184 አገራት መካከል ኢትዮጵያ 171ኛ ተራ ላይ የምትገኝ ስትሆን ይህም በድህነት ከሚጠቀሱት ቀዳሚ አገራት ቁጥር ውስጥ አስገብቷታል፡፡ ዘገባውን የተመለከቱ የኢኮኖሚ ባለሙያ የአንድ አገር ኢኮኖሚ በከተሞች ውስጥ በሚሰራ ፎቅ ብዛት እና የመንገድ ሥራ አይለካም ይላሉ፡፡ ሌላ የኢኮኖሚ ባለሙያ ደግሞ “ኢኮኖሚ ከቁጥር ሌላ ሥነ ልቦናዊ ጉዳይም ነው፡፡ የኑሮ ጉዳይም ነው፡፡ የጉሮሮ ጉዳይም ነው፡፡ በቁጥር ብቻ አይለካም፡፡ … የሕንፃ መሐንዲስ ቢሳሳት ሕንፃ ይደረመሳል፡፡ የሰው ኑሮ መሐንዲስ ሲሳሳት ግን ሕይወት ይጠፋል፣ ሕዝብ ያልቃል፣ ትውልድ ይረግፋል፣ አገር ይበጠበጣል፡፡ በዓይናችን እያየነው ነው” ይላሉ፡፡

ይፋ በሆነው ጥናት እንደተገለጸው ደረጃው የወጣው በተለይ ሁለት የኢኮኖሚ መለኪያዎችን በማቆራኘት ነው፡፡ እነዚህም የአገር ውስጥ ምርት (GDP) በካፒታል የሚባለውንና የመግዛት ኃይል ንጽጽር (purchasing-power-parity (PPP) በማጣመር ነው፡፡ በቀላል አገላለጽ PPP ማለት ኅብረተሰቡ የሚጠቀምባቸውን የተወሰኑ የተለመዱ ሸቀጦችን (ለምሳሌ ዳቦ፣ እርሳስ፣ የብርቱካን ጭማቂ፣ ወዘተ) ሰብስቦ በአንድ ቅርጫት ውስጥ በማድረግ ዋጋቸውን መተመን ነው፡፡ እነዚህ በአንድ ቅርጫት ውስጥ የተካተቱት ሸቀጦች አጠቃላይ ዋጋ ኢትዮጵያ ውስጥ 50 ዶላር ቢሆን ኬኒያ ደግሞ 100 ዶላር ቢሆን በኢትዮጵያና በኬኒያ መካከል ያለው የመግዛት ኃይል ንጽጽር 1፡2 (አንድ ለሁለት) ነው ማለት ነው፡፡ ይህንን ቀመር ከአጠቃላይ የዓለም አገራት ጋር በማነጻጸር የአንድን አገር ሕዝብ የመግዛት አቅም ከመላው ዓለም አገራት ጋር ማነጻጸር ይቻላል፡፡ ጥናቱ ያደረገውም ይህንኑ ነው፡፡

በኢኮኖሚክስ ጥናት መሠረት የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒን) መለኪያዎች በርካታ ናቸው፡፡ አንዱ ምርቱን ለማምረት በወጣው የመለካት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከዋጋ ንረት ጋር በማገናዘብ የመለካት ስልት ነው፡፡ ይህ ጥናት የተጠቀመበት መለኪያ ደግሞ ጂዲፒን በካፒታል መለካት ሲሆን ይህም የአንድ አገር ገቢ በነዋሪው ሕዝብ ተካፍሎ የሚመጣው ነው፡፡ የጥናቱ አቅራቢዎች ይህንን የጂዲፒ ውጤት ከመግዛት ኃይል ንጽጽር ጋር በማካፈል ነው መረጃውን ይፋ ያደረጉት፡፡ ይህ ዓይነቱ የመግዛት ኃይል ንጽጽርን ግምት ውስጥ ያስገባ የጂዲፒ አለካክ በኅብረተሰቡ ውስጥ የሚታየውን የኑሮ ውድነት በስሌቱ ውስጥ የሚያካትት በመሆኑ ከሁሉም የጂዲፒ መለኪያዎች የተሻለ ነው የሚል አስተያየት ይሰጥበታል፡፡
በድህነት ከሰፈሩት አገራት ተራ የምትመደበው ኢትዮጵያ (171ኛ $1,258.60) በበርካታ የአፍሪካ አገራት ተቀድማለች፡፡ ሴራሊዮን 170ኛ ($1,559.95)፣ ማሊ 168ኛ ($1,136.77)፣ ጊኒ ቢሳው 166ኛ ($1,268.46)፣ ኮሞሮስ 164ኛ ($1,296.77)፣ ሩዋንዳ 162ኛ ($1,591.71)፣ ዑጋንዳ 160ኛ ($1,459.62)፣ ታንዛኒያ 159ኛ ($1,670.21)፣ ዛምቢያ 158ኛ ($1,841.64)፣ ኬኒያ 156ኛ ($1,884.57)፣ ቻድ 155ኛ ($2,061.63)፣ ሱዳን 144ኛ ($2,550.10)፣ ናይጄሪያ 141ኛ ($2,883.44)፣ ጂቡቲ 139ኛ ($2,778.25)፣ ጋና 137ኛ ($3,501.53)፡፡በእነዚህ የኢኮኖሚ ስሌቶች መሠረት የተደረገው የአምስት ዓመታት ጥናት (እኤአ 2009-2013) እንዳመለከተው በዝርዝሩ ከተካተቱት አገራት ኢትዮጵያ 171ኛ ተራ ላይ ነው የምትገኘው፡፡ ኳታር በአንደኛነት ስትገኝ ሉግዘምበርግ ሁለተኛ፣ ኖርዌይ ሦስተኛ፣ ብሩናይ አራተኛ፣ ሲንጋፖር አምስተኛ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ስድስተኛ፣ አሜሪካ ሰባተኛ፣ ሆንግ ኮንግ ስምንተኛ፣ ስዊትዘርላንድ ዘጠነኛ፣ ኔዘርላንድስ አስረኛ ተራ ላይ ሰፍረዋል፡፡ በዘገባው ላይ እንደተጠቀሰው የእነዚህ አገራት በካፒታል ላይ የተሰላው የ2013 ዓም ጂዲፒ ከመግዛት ኃይል ንጽጽር ጋር ተካፍሎ የተገኘው ውጤት በአሜሪካ ዶላር የሚከተለው ነው፡፡ ኳታር $105,091.42፣ ሉግዘምበርግ $79,593.91፣ ኖርዌይ $56,663.47፣ ብሩናይ $55,111.20፣ ሲንጋፖር $61,567.28፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ $49,883.58፣ አሜሪካ $51,248.21፣ ሆንግ ኮንግ $53,432.23፣ ስዊትዘርላንድ $46,474.95፣ ኔዘርላንድስ $42,493.49፡፡ ይህ ማለት አንድ አገር የምታመርተውን አምርታ፣ የኑሮው ውድነት ተሰልቶ እና በዚያች አገር ውስጥ ያሉት ሸቀጦች የሚያወጡት ዋጋ ከሌሎች የዓለም አገራት ጋር ተነጻጽሮ አንድ ሰው ሊኖረው የሚችለው የገንዘብ መጠን ተብሎ በግርድፉ ሊወሰድ ይችላል፡፡ (ማሳሰቢያ፡ እዚህ ላይ ለማሳያነት የ2013 ዓም ብቻ በማውጣታችን የቁጥርና የደረጃ ልዩነት ይታያል፡፡ ይህም የሆነው የአንዳንዶቹ አገራት ዘገባ የተወሰደበት ዓመት ከሌሎቹ ጋር ተመሳሳይ ባለመሆኑ ነው፡፡ ሙሉውን ዘገባ እዚህ ላይመመልከት ይቻላል)

“ኮከቡ ያልሰመረለት ትሪሊየን ጂዲፒ” በሚል ርዕስ (June 14, 2015) በታተመው ሪፖርተር ላይ ጽሁፍ ያቀረቡት የኢኮኖሚ ባለሙያ ጌታቸው አሰፋ በኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚ ሁኔታና መጪውን እንደሚከተለው ይገልጹታል፡፡

“ገንዘቡ ዋጋ ያጣው ገቢ አሁንም ቢሆን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ቢሆንም፣ የገቢ ዕድገት ከምርታማነት ዕድገት በላይ ስለሆነ ነው፡፡ ምርታማነት የቀነሰው የመንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ ዕድገት፣ የሥልጠና ዕድል፣ ሙያዊ ክህሎትን መገንባት፣ ወዘተ የሚቻለው አለቃን በማምለክ እንጂ ችሎታን አዳብሮ ውድድር ውስጥ በመግባት ስላልሆነ ነው፡፡ … ሥራ ፈጠራ በብሎኬት ምርት፣ መስኮትና በር መግጠም፣ አልባሳት፣ ቦርሳና ቀበቶን የመሳሰሉ የግል መጠቀሚያዎችን ማምረት ጀምሮ አሁን ወደ ጀበና ቡና፣ ቦርዴ (ሻሜታ) ጠመቃ፣ የዓረብ ሱቅ፣ በቆርቆሮ ግድግዳ ደሳሳ ጎጆ የሆቴል ኪዮስክ ወርዷል፡፡ ከዚህ በታች ወዴት እንደሚወርድ አይታወቅም፡፡ …

“ምርታማ ሆኖ ገንዘብ ማግኘት ካልተቻለ አጭበርብሮም፣ ቀምቶም፣ ሰርቆም፣ የሰው አካልንም ቢሆን ደልሎ ገንዘብ ለማግኘት ይሞከራል፡፡ ውድድር ሳይሆን ሽሚያ ይፈጠራል፡፡ በኢትዮጵያ እያደገ የመጣው ይህ አጉል የመስገብገብ፣ የመሻማት፣ የመሻሻጥ ባህሪይ ነው፡፡ ሁላችንም በባህሪይ፣ በአስተሳሰብና መስሎ በመታየት ደላላ እየሆን ነው፡፡ በመንግሥት ድጋፍ በሦስት ሺሕ ብር የፈጠራ ሥራ ጀምሮ በዓመቱ ሦስት ሚሊዮን ብር ካፒታል ማስመዝገብ፣ መቶ ሺሕ ብር ለደላላ ከፍሎ ወደ ሞት ለመሄድ መደራደር፣ ለጥቂት ደቂቃዎች መዝናኛ በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ማውጣት፣ ቅጥ ላጣ የውጭ አገር ጉዞ የቅንጦት ወጪ ማድረግ፣ ምልክት የጥሬ ገንዘብ ከጓሮ የሚሸመጠጥ ቅጠል መምሰል ነው፡፡ …

“አምና በመቶ ሺሕ ብር መነሻ ካፒታል የከተማ ሥራ ጀምሬ ዘንድሮ ሦስት ሚሊዮን ብር ካፒታል አለኝ፣ በግማሽ ሔክታር መሬት የግብርና ሥራ አሥር ሚሊዮን ብር ካፒታል አለኝ፣ የሬድዮና የቴሌቪዥን ፕሮፓጋንዳ የወጣቱን ሥነ ልቦና ሰለበ፡፡ የሥራ ባህል ጠፋ፡፡ ገንዘብ ተሠርቶ የሚገኝ ሳይሆን ከሜዳ የሚታፈስ ወይም ጓሮ ከበቀለ ዛፍ የሚሸመጠጥ መሰለ፡፡ መቶ ሺሕ በትኖ ሚሊዮን ለማፈስ የተሰናዳ ትውልድ ተፈጠረ፡፡ ከሠርቶ በሌው አውርቶ በሌውና ዘሎ በሌው በዛ፡፡ የዩኒቨርሲቲ ትምህርትን አቋርጦ ጊታር ማንሳት ተለመደ፡፡ …

“የጋራ በሆነ መሬት ላይ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ መሥራት የሚቻለው በጋራ ብቻ ነው፡፡ የጋራ የሆነም የግል አይደለም፡፡ የግል ያልሆነም ገበያ አይወጣም፡፡ ገበያ ያልወጣም የገበያ ዋጋ የለውም፡፡ የገበያ ዋጋ የሌለውም በገበያ ዋጋ በገንዘብ አይተመንም፡፡ ስለዚህም በሪፖርት ከምናየውና ከሚነገረን የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) መጠን ገሚሱ የገበያ ዋጋ የሌለው ምናባዊ ስሌት ነው፡፡ የኑሮ መሐንዲሱ ኢኮኖሚያዊ ኑሮን ወደ ምናባዊ ሥሌት ከወሰደው የሕዝብ ገቢ መጠንና ኑሮም በገበያ ተለክቶ እውነቱ የሚታወቅ ሳይሆን ምናባዊ ይሆናል፡፡ አመለካከቱና አስተሳሰቡም የኑሮው ነፀብራቅ ነውና ኑሮውን ተከትሎ ምናባዊ ይሆናል፡፡ ሲያገኝም ሲያወጣም በምናባዊ ሥሌት ነው፡፡ ሳይበላ የበላ መስሎ፣ ሳይጠጣ የጠጣ መስሎ፣ ሳይደላው የደላው መስሎ፣ ያላመነውን ያመነ መስሎ፣ ያልተቀበለውን የተቀበለ መስሎ፣ የናቀውን ያከበረ መስሎ፣ የጠላውን የወደደ መስሎ በመታየት በምናባዊ ዓለም ውስጥ ይኖራል፡፡…poor

“ሕዝቡ ከምናባዊ ዓለም ወጥቶ ገሃዱን ዓለም እንዲቀላቀል የኑሮ መሐንዲሱ ኢኮኖሚስት አለ ብሎ በወረቀት ላይ የሚጽፈውን የምርት መጠን ለሽያጭ ወደ ገበያ አውጥቶ፣ በበያ ዋጋ አስተምኖ እውነተኛውን በገበያ ዋጋ የተለካ የምርት መጠን ያሳየን፡፡ ያለበለዚያም የገንዘብ አቅርቦቱ ለገበያ በቀረበው ምርት መጠን ልክ ሆኖ በዋጋ ግሽበት ስቃይ እንዳን፡፡ እኔ እንኳ በሩቁ ከማውቀው ወደ ገበያ ከማይቀርቡና ማገበያያ ገንዘብ ከማያስፈልጋቸው ምርቶች ውስጥ ከጠቅላላ ጂዲፒው አንድ ሦስተኛው የሚሆነው፣ ገበሬው ከራሱ እንደገዛ ተቆጥሮ በምናባዊ ሥሌት በገንዘብ የሚለካው የግብርና ምርት ይገኝበታል፡፡ በወረቀት ላይ የሚመለከቱ የአገር ውስጥ ምርት መጠን ቁጥርና ለፕሮፓጋንዳ የሚያገለግሉ ጥንስስ ፕሮጀክቶች ስም ጋጋታ ሳይሆን፣ የአጠቃላዩ ሕዝብ ምርታማነት ብቻ የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ወሳኝ ነው፡፡…

“አንጀት ላይ ጠብ የሚለው ሺዎች ለሚሊዮኖች አስበውና ተደራጅተው ሲሠሩ ሳይሆን፣ የአጠቃላዩ ሕዝብ ሚሊዮኖች ለራሳቸው አስበው በገበያ ውስጥ ተወዳድረው እንዲሠሩ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች ሲመቻችላቸው ነው፡፡ ‹‹ጧት ጧት ዳቦአችንን ጠረጴዛችን ላይ የምናገኘው በዳቦ ጋጋሪው የፅድቅ ሥራ ሳይሆን፣ ለራሱ ገንዘብ ለማግኘት ሲል በሚሠራው ሥራ ነው›› አዳም ስሚዝ፡- ነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ሥርዓት ጠንሳሽ፡፡ ‹‹ልማት ማለት አንድ ሰው ሊሆንና ሊያደርግ የሚፈልገውን ሕጋዊ ነገሮች የመሆንና የማድረግ ነፃነትና አቅም ሲያገኝ ነው›› አማርተያ ሴን፡- በ1998 በልማት ኢኮኖሚክስ የኖቤል ተሸላሚ፡፡”

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በፋይናንስ መጽሔት ላይ ያወጣውን ይህንን መረጃ የተመለከቱ በኢትዮጵያ የግል ትምህርት ተቋም የኢኮኖሚክስ ባለሙያ የሆኑ ለጎልጉል እንዳሉት የዴሞክራሲን መንገድ የተከተለችው ጋና ከሌሎቹ የሰሃራ በታች አገራት በከፍተኛ ፍጥነት የማደጓ ምክንያት ከዚህ ጋር ተያይዞ እንደሚጠቀስ ጠቁመዋል፡፡ የዕድገቷ መጠንም ዘገባው በተጠናቀረበት ባለፉት አምስት ውስጥ ያልተዛባ ነገር ግን ሥርዓት ያለው ዕድገት እያሳየች መሆኗን ጨምረው ተናግረዋል፡፡ አክለውም ሲናገሩ “አንድ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ ያልሆነ ሰው ይህንን ዘገባ በመመልከትና የኢትዮጵያን ደረጃ ከሌሎቹ የአፍሪካ አገራት ጋር በማነጻጸር ብቻ ለምን ኢትዮጵያውያን ለተሻለ ኑሮ ወደሌሎች አገራት እንደሚኮበልሉ መናገር ይችላል፤ የአገራችን ሕዝብ ያለው አቅም እጅግ የወደቀ በመሆኑ በአቅም ከምትበልጠን ጂቡቲ መሰደድ እንደ አማራጭ ሊወሰድ ይችላል” ብለዋል፡፡ በመጨረሻም “እንደ ባለሙያ ለመንግሥት አካላት የኢኮኖሚውን ጉዳይ ስናስረዳ የሚሰማን የለም፤ ከዚያ ይልቅ እንደ ካድሬ ፕሮፓጋንዳ እንድንናገር፣ ኢኮኖሚው በድርብ አኃዝ እንዳደገ እንድንደሰኩር፣ ወዘተ ነው የሚፈለግብን፡፡ ሃቁ ግን ይኸው በገሃድ የሚታይ ነው፤ የአንድ አገር ዕድገት በበርካታ የኢኮኖሚ መመዘኛዎች በሳይንሳዊ መንገድ የሚለካ ነው እንጂ በዘጋቢ ፊልም በታጀበ የመንገድ ሥራና የፎቅ ብዛት ጨርሶውኑ ሊሆን አይችልም፤ ምናልባትም ካልተሳሳትኩ በዓለም ላይ ኢኮኖሚዋን በመንገድ ሥራና በፎቅ ብዛት የምትለካ አገር ኢህአዴግየሚያስተዳድራት ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አትቀርም” ብለዋል፡፡ethio poor

የኢኮኖሚ ባለሙያው ጌታቸው አሰፋ ሪፖርተር ላይ ያወጡትን ጽሁፍ ሲያጠናቅቁ እንዲህ ይላሉ፤ “የአገር ውስጥ ምርት በግሳንግስ ምርቶች ማበጡ የምርታማነት ማደግ አይደለም፡፡ ያበጠ ነገርም ይፈርጣል፡፡ ኢኮኖሚ ሲፈርጥ ደግሞ ማኅበራዊ ቀውስ ያመጣል፡፡ ‹ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል› ተረት እንዳይተረትብን፡፡ የብሔራዊ ገቢ ሒሳብ ባለሙያው በተቀመጠለት የማዕከላዊ ዕቅድ የጊዜ ገደብ አገሪቱን በእጁም በእግሩም ገፍቶ መካከለኛ ገቢ ደረጃ ለማድረስ አስቦ፣ በነፃና በጋራ የሚሠራውን የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሥራ በምናባዊ ሒሳብ የአገር ውስጥ ምርት ሥሌት ውስጥ አካቶ ሊሆንም ይችላል ምርቱን ያሳበጠው፡፡ ኢኮኖሚ ከቁጥር ሌላ ሥነ ልቦናዊ ጉዳይም ነው፡፡ የኑሮ ጉዳይም ነው፡፡ የጉሮሮ ጉዳይም ነው፡፡ በቁጥር ብቻ አይለካም፡፡ እንደ ዶሚኖ ጨዋታ ቁጥር በመገጣጠም ብቻም የሚገነባ አይደለም፡፡ የሕንፃ መሐንዲስ ቢሳሳት ሕንፃ ይደረመሳል፡፡ የሰው ኑሮ መሐንዲስ ሲሳሳት ግን ሕይወት ይጠፋል፣ ሕዝብ ያልቃል፣ ትውልድ ይረግፋል፣ አገር ይበጠበጣል፡፡ በዓይናችን እያየነው ነው፡፡”

ይህንን ዓለምአቀፍ የደረጃ ዘገባ በመመርኮዝ እኤአ እስከ 2020 ድረስ ይህ የደረጃ ስሌት እምብዛም ለውጥ ሳያሳይ እንደሚቀጥል በርካታ ትንበያዎች አሉ፡፡ በሌሎች ደግሞ ምናልባትም በዝቅተኛው ተራ ላይ የሚገኙት አገራት እጅግ እየደኸዩ በሃብታምና በደሃ መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ ለከፍተኛ የማኅበራዊ ቀውስ እየተጋለጡ ይሄዳሉ የሚል ሙያዊ ስሌትም ይሰጣል፡፡ (ፎቶ: ከኢንተርኔት የተገኙ በጎልጉል የተገጣጠሙ)

ምንጭ፦ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8778#sthash.OEDmrWLL.dpuf

የታቀደው የኦባማና የአሜሪካ ቁንጮ ባለሥልጣናት ጉብኝት ዓላማና የኢትዮጵያ ሕዝብ አቤቱታ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እንደሚመስለኝ የኦባማና የሌሎቹ ቁንጮ ባለሥልጣናት ጉብኝት እርግጥ ሆኗል፡፡ ይሄንን የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጉብኝት በተመለከተ ከአሜሪካን የኅትመት የብዙኃን መገናኛዎች እስከ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን ማኅበረሰብ ድረስ ያሰሙት ተቃውሞ የተደረገው ርብርብ ሊሠራ አልቻለም፡፡ የኦባማ አሥተዳደር በወንዲ ሸርማን የጀመረውን ቅሌት ቀጥሎበት “የሸርውድ ንግግር ይገርማቹሀል እንዴ!” የሚል በሚመስል ስላቅ ይግረማቹህ ብሎ “ለዴሞክራሲ (ለመስፍነ ሕዝብ) ታማኝ ያልሆኑ መንግሥታትን በፕሬዘዳንት (በርእሰ ሥልጣናት) ደረጃ አንጎበኝም!” የሚለውን የቆየ አቋም በመቀልበስ ሀገራችን ከመቸውም ጊዜ በላይ በፈላጭ ቆራጭ አንባገነን አገዛዝ ሥር በሆነችበት ወቅት ጉብኝቱ ሊደረግ ነው፡፡ ይሄ ለአሜሪካዊያን ታላቅ ሐፍረትና ውርደትም ነው፡፡ ይሄንን የምለው ወያኔን ለዚህ ያበቃው እነሱ መሆናቸውን ዘንግቸ አይደለም በፍጹም፡፡ ነገር ግን በግልጽ እያወገዙ በድብቅ ደግሞ እየደገፉ የሚያደርጉትን ያደርጋሉ እንጅ በይፋ በአደባባይ እንዲህ መሰሉን ስሕተት ከማድረግ የተቆጠቡ ነበሩና አሁን ይሄንን መመሪያ ወይም አቋም ለውጠው እንዲህ ማድረጋቸው ስለገረመኝ ነው፡፡

እኔ በዚህች አሜሪካ በምትባል ሀገር ምን እየተደረገ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ወይ ሁለት ሦስት መንግሥት አለባት ወይ ደግሞ ማስመሰልን በሚገባ የተካኑ ናቸው፡፡ በአንድ በኩል ወያኔን በመደገፍ እያቆሰሉን እያደሙን እየገደሉን በሌላ በኩል ደግሞ ሙሾ እያወረዱ አብረውን ያለቅሳሉ፡፡ መንግሥታቸው ይገለናል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤታቸው የኅትመት የብዙኃን መገናኛዎቻቸውና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶቻቸው ደግሞ ሙሾ እያወረዱ ያላቅሱናል፡፡ መንግሥታቸው በሌሎች ሀገራት ላይ እንዲህ ዓይነት አቋም እርምጃዎችን እየወሰደ ሊያስጠብቀው የሚጥረው ኢፍትሐዊ ጥቅም የአሜሪካ ሕዝብ ጥቅም ከሆነና በእኛ ላይ ደባ የሚፈጽመው በዚህ ምክንያት ከሆነ እነኝህ አላቃሾቻችን ለምን ከመንግሥታቸው ጋር እንዳልቆሙ ወይም ደግሞ በዲሞክራሲያዊ (በመስፍነ ሕዝባዊ) የአሥተዳደር ሥርዓት ትልቅ አቅም ጉልበት አላቸውና በመንግሥታቸው ለምን እንዳልተፈሩ እንዳልተደመጡ እንዳልተከበሩ ግራ ይገባኛል፡፡ እንግዲህ ወይ ሲያላቅሱን እያስመሰሉ ነው ወይ በሀገሪቱ አለ ከሚባለው የአሥተዳደር ሥርዓት በተቃረነ መልኩ ተንቀዋል ወይ ደግሞ ዲሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) በዚያች ሀገር የለም፡፡ በዚህም ምክንያት በመንግሥታቸው ተደማጭ ተፈሪና ተከባሪ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡

ከዚህ አንጻር ይሄ ጉብኝት ብዙ ግልጽ የሚያደርጋቸው ነገሮች አሉ፡፡ የኦባማ አሥተዳደር በወያኔ ዘመን የነበሩት ሌሎቹ የአሜሪካ አሥተዳደሮች ይዘውት የነበረውን እሳቸውም እራሳቸውም ሳይቀር ይዘውት የነበረውን አቋምና መርሕ ጭራሽ የወያኔ አገዛዝ አንባገነንነቱ ፈላጭ ቆራጭነቱ ከመቸውም ጊዜ በላይ ብሶ ባለበት ሰዓት ያንን ነባር አቋምና መርሕ በመቀልበስ በሥልጣን ላይ ባለ ፕሬዘዳንት (ርእሰ ሥልጣናት) ደረጃ ጉብኝቱ ሲደረግ ምንም ዓይነት መልእክትና እንድምታ የሌለው ከመሰለን ሲበዛ የዋሀን ነን፡፡ መልእክቱና እንድምታውም አንደኛ እስከዛሬ የነበረውን የተሳካ የተዋጣላት የወያኔ አሜሪካ ግንኙነትና ስኬት በአንድነት በጋራ ለማክበር (ሰሌብሬት ለማድረግ) ሲሆን ሌላው የአሜሪካ መንግሥት አሥተዳደር የማስመሰያ ካርዳቸው ስላለቀባቸው ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን የሚመለከታቸው እንደ ሞቡቱዋ ዛየር እንደ ሶሞዛዋ ኒካራጉዋና እንደሌሎቹ አሜሪካኖች ሸፍጥና ግፍ እንደፈጸሙባቸው ሀገራት መሆኑን ለሚያይ ለሚሰማ ለማረጋገጥና ለወያኔ የለየለት ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለበት ቡራኬ ሰጥቶ አገዛዙን ማጀገን ነው፡፡ የተቀረውን ወደኋላ በዝርዝር እያየዋለን፡፡ እነኝህ ሁለቱ ነገሮች ለእኛ ምን ያህል መቅሰፍት እንደሆኑ ለመረዳት የወንዲ ሸርማንን ንግግር ማስታወሱና የሞቡቱዋን ዛየርና የሶሞዛዋን ኒካራጉዋ የየሀገራቱን ዘመን መለስ ብሎ ማየት በቂ ነው፡፡ ለነገሩ አሜሪካኖች ካለፈው ተሞክሯቸው በመማር አቶ መለስን መክረው አቶ መለስ ሲገሉና ሲጨፈጭፉ እንደ ሞቡቱና እንደ ሶሞሳ በግልጽ በዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ዕይታ ስር ስላላደረጉ እንጅ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዕይታ ውጪ በሆኑ ሁኔታዎች ማንም ድርሽ እንዳይል በማድረግ የጨፈጨፉት የገደሉት ከሞቡቱና ከሶሞዛ ቢበልጥ እንጅ የሚያንስ አይደለም፡፡

አሜሪካንን ሳስብ ምን ይሰማኛል መሰላቹህ፡- ሀገሬንና ሕዝቧን በተመለከተ የአሜሪካ መንግሥትና የአሜሪካ ሕዝብ ያላቸው አቋምና መርሕ አንድ መሆኑን ማረጋገጥ አልቻልኩም እንጅ አንድ መሆኑን ባረጋግጥ ልወስድ የምችለውን የበቀል እርምጃ ባላውቅም ከአልቃይዳና ከአይሲስ በከፋ መልኩ ለአሜሪካና ለሕዝቧ ጠላቷ እኔ መሆኔን በግልጽ ላሳውቃቸው እወዳለሁ፡፡ ይሄንን ማረጋገጥ ግን እንዲህ የዋዛ ሊሆንልኝ አልቻለም፡፡ እስከማውቀውና እስከሚገባኝ ድረስ ሀገሬና ሕዝቧ የራሳችንን ጥቅምና ሉዓላዊነት መጠበቅ ስላለብን ካልሆነ በስተቀር በእብሪት ተነሣሥተን የአሜሪካንንም ሆነ የሌላ ሀገርንና ሕዝብን ጥቅም የጎዳንበት ያጠቃንበት ዘመንና አጋጣሚ ኖሮ አያውቅም፡፡ ያለው ሀቅ ይሄ በሆነበት ሁኔታ የአሜሪካ መንግሥታት የሌሎችም ምዕራባዊያን ሲጀመር ጀምሮ ሀገሬንና ሕዝቧን መፈናፈኛ መተንፈሻ አሳጥተው በጭራቅ ጥርሳቸው ነክሰው ሰቅሰው የያዙበት ምክንያት ፈጽሞ ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም፡፡

አቶ ኦባማ ሊጎበኙን ሲመጡ ሕዝብ ፊት ንግግር የሚያደርጉ ከሆነ ልጠይቃቸውና እንዲመልሱልኝ የምፈልገው ጥያቄ ቢኖር ይሄና ይሄ ብቻ ነው፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ይሄ ዕድል ሊኖር የሚችልበጽ ፋታና ቅጽበት አለመኖሩ ነው እንጅ ችግሩ፡፡ ይህች ሀገር በሀገሬና በሕዝቧ ላይ በምትፈጽመው ግፍ ምክንያት እንዲህ እንዳስብ የተገደድኩት እኔ ብቻ የምሆን አይመስለኝም፡፡ እኔ ብቻ ልሆን የምችልበትም ምንም ምክንያት የለም፡፡ ነገር ግን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ጭምር በጸረ አሜሪካ ስሜት ለመጠቃት ተገዷል፡፡ ምንም አያመጡም ብላቹህ ንቃቹህን እንጅ በፈጸማቹህብን በደል ሁሉ ከባድ ጥላቻ ሊያድርብን እንደሚችል እናንተም የምታጡት አይመስለኝም፡፡ ይሄ ንቀት ግን ድንቁርናና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው፡፡ ለምን ቢባል ትናንት እናንተ አልነበራቹህም እኛ ግን ነበርን ዛሬ እኛ የለንም እናንተ ግን አላቹህ ነገ ዙሩ ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም ለቻይና ተመልሶ እንደመጣው ሁሉ ማለት ነው፡፡ ያኔ እናንተ አትኖሩም እኛ ደግሞ እንኖራለን በዚያ ጊዜ የዘራቹህትን እንድታጭዱ የምትገደዱ መሆኑን ማሰብ አልቻላቹህም፡፡ ከየትኛውም ሀገር ጋር የምታደርጉት ግንኙነት እንዲህ ዓይነት ጊዜ ጠብቆ ዋጋ ሊያስከፍላቹህ በሚችል መልኩ ባይቃኝ መልካም ነው፡፡ ይህ የምትከፍሉትን ዋጋና ጠላት ያበዛ እንደሆን እንጅ ምንም የሚፈይድላቹህ ነገር የሚኖር አይመስለኝም፡፡ በሳልና አርቆ አሳቢ ከሆናቹህ ዛሬ ያላቹህበትን ቦታና ሁኔታ ብቻ አትዩ፡፡ ነገ ምን ይዞ እንደሚመጣ ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልምና ለነገ ግምት ቢኖራቹህ መልካም ነው፡፡ እንዲህ ብታስቡ ብቻ ነው በሳል አርቆ አሳቢ ለሀገራቹህና ለሕዝባቹህም ጠቃሚ ልትሆኑ የምትችሉት፡፡

ከተቃውሞ ጎራ ያሉ ወገኖችና ሥሉጣን (አክቲቪስቶች) ሳይቀር ኦባማ ሀገራችንን መጎብኘታቸው በጥሩ ጎኑ እንዳዩት የገለጹ አሉ፡፡ ምክንያታቸውንም ሲያቀርቡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምን ዓይነት አስከፊ የሰብአዊ መብት እረገጣና ችጋር ውስጥ እንደሆነ በዓይናቸው የመመልከት ዕድል ስለሚኖራቸው የሚደግፉት አገዛዝ ምን ያህል በደል እያደረሰ እንደሆነ ለመረዳት ስለሚረዳቸው መጎብኘታቸው ጥሩ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ እኔ ይሄንን አባባል አልተቀበልኩትም በሦስት ምክንያቶች አንደኛው ኦባማ ጉብኝታቸው ቤተመንግሥት ላይ ብቻ የተወሰነ በሆነበት ሁኔታና በድንገት በአጋጣሚ በአንዱ መንደር ወይም ሰፈር ተገኝተው የድሀውን ሕዝብ ኑሮ ምን ይበላል? ምን ይጠጣል? ኑሮው ምን ይመስላል? የሰብአዊና ፖለቲካዊ መብቱ አንዴት ተይዟል? ብለው እስካልጎበኙት ጊዜ ድረስ ያለንን ችግርና ሰቆቃ ያውቃሉ ያያሉ ይረዳሉ ብሎ መጠበቅ ስለማይቻል፡፡ ሁለተኛው ሕዝባችን በምን ዓይነት ኢሰብአዊ ግፍና አገዛዝ ስር እንደሆነ ምን ምን ዓይነት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና እረገጣዎች እንደተፈጸመበት እዚህ መምጣት ሳያስፈልጋቸው እዛው ሳሉ ከእያንዳንዳችን በላይ ልቅም አድርገው የሚያውቁት ጉዳይ በመሆኑ ሌላው ቀርቶ ወያኔ ማለት በገዛ ሕዝቡ ላይ ፈንጅ እያጠመደ እንደሚያፈነዳና መንግሥታዊ ሽብርን ሥራዬ ብሎ የያዘ አገዛዝ እንደሆነ ሁሉ ጠንቅቀው ያውቃሉና፡፡ ሦስተኛው የጉብኝቱ ዓላማ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰቆቃና ችግር ለማየት ለመጎብኘት ባለመሆኑ የኦባማን ጉብኝት መደገፋቸው በፍጹም ትክክል አይደለም፡፡

የዚህ የኦባማና የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጉብኝት ዓላማ ዘርፈ ብዙ ነው እሱም፡- ወያኔን ለሥልጣን ከማብቃት አንሥቶ በ24 ዓመታት የሥልጣን ዘመኑ ተናበው ተማክረው ለሠሩት ሥራዎቻቸው ስኬታማነት የተሳካ ግንኙነትና ወዳጅነት ማረጋገጫ ለመስጠት፣ ወደፊትስ ይህ የሰመረ ወዳጅነትና ግንኙነት በተጠናከ መልኩ እንዴት ልናስቀጥለው እንችላለን? የሚለውን ለመምከር፣ የዚህ ስኬታማ ግንኙነታችን ጥምረታችን ወዳጅነታችን ፈተና ጠላት ችግሮች ምን ምንና እነማን ናቸው? እንዴትስ ልንቀርፋቸው ልናስወግዳቸው እንችላለን? በማለት ከቅርብ ጊዜና ከረጅም ጊዜ አኳያ አቅድ ለመንደፍና ለመንቀሳቀስ የሚደረግ ጉብኝት ነው፡፡ ይህ ደግሞ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ይድረስልን እንጅ ለዚህች ሀገርና ሕዝቧ ከነበረው የከፋ ምን ምን ዓይነት ችግር ይዞ እንደሚመጣ ለመገመት ከከዚህ ቀደሙ የወያኔ አሜሪካ ግንኙነትና ጉድኝት ምን ያህል እንደተጎዳን መለስ ብሎ ማየቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ የአሜሪካና የወያኔ ጉድኝትና ጥምረት የጥቅም ትስስር ጥብቀት እንዲህ እንደምናስበው በግልጽ እንደሚታየው ብቻ እንዳይመስላቹህ! ልገልጸው ከምችልው በላይ በጣም ጥብቅና ስር የሰደደ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ኃይል ካልታከለበት በስተቀር ወያኔ የፈለገውን ያህል የዘር ማጥፋትም በሰብእና ላይ የተፈጸመም ሆነ የጦር ወንጀሎችን በግልጽ ቢፈጽም ወይም ደግሞ በእኛ በኩል የፈለገውን ያህል ጥረት ብናደርግ ሊደፈርስ ሊለወጥ የሚችል አይመስለኝም፡፡ ይች ሀገር ከጭካኔያቸውና ከፈላጭ ቆራጭነታቸው የተነሣ የሰው ደም ይጠጣሉ ተብሎ ይነገርባቸው ከነበሩና የገዛ ሕዝባቸውን ከፈጁ ከዛየሩ ቦቡቱና ከኒካራጉዋው ሶሞዛ ከሌሎች አንባገነኖችም ጋር በጥብቅ ወዳጅነት የሠራች ሀገር መሆኗን አትርሱ፡፡

ከዚህ ባሻገር አቶ ኦባማ ሀገሬን እንዲረግጧት የማልፈልግበት ምክንያት በግሌ ኦባማና አሥተዳደራቸው ለግብረሰዶማዊያን በሰጡት አሳፋሪ ድጋፍና ባረጋገጡት ነውረኛ መብት ነው፡፡ ይሄንን ነውረኛ ተግባራቸውንም ከራሳቸው አልፈው በመላው ዓለም ሊፈጽሙት ይጥራሉ እየተንቀሳቀሱም ነው፡፡ ይህ ነውረኛ ተግባር የሰው ልጆችን ደኅንነትና ህልውና እጠብቃለሁ አስጠብቃለሁም ከሚል ኃላፊነት ከሚሰማው መንግሥት ፈጽሞ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ እንዴት እንደሆነ በአጭሩ ዕንይ፡- ይህ አሥተዳደር በዚህ ጸያፍና ነውረኛ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው ተግባሩ ያደረገውና እያደረገ ያለው ነገር ጤናማና ተፈጥሯዊ የወሲብ ፍላጎትና አፈጻጸም የሌላቸውን አደገኛ ውርጋጦች ስዶች እርኩሶች ነውረኞች ክፉ የአእምሮ ሕመም ባለባቸው ግለሰቦች ተደፍረው የወሲብ ባሪያዎቻቸው የሆኑትን ሕፃናትና አዋቂ ወንዶችን በመደፈራቸው ከደረሰባቸው አካላዊና ሥነ ልቡናዊ ጉዳቶች የጤና መታወክ ሊያገግሙ የሚችሉበትን ሁኔታ መፍጠር አጥቂዎቻቸውንም አድነው ሕግ ፊት በማቅረብ ፍትሕ እንዲያገኙ ማድረግ ሲገባቸው ከአንድ ኃላፊነት ይሰማኛል ከሚል መንግሥት ፈጽሞ በማይጠበቅ መልኩ ከተጠቂዎቹ ይልቅ ለአጥቂዎቹ በመቆም ግፈኞችን አደገኛ ወንጀለኞችን በመደገፍ የያዙትን የሚያደርሱትንም ጥቃት ሕጋዊነትን አግኝተው ካለምንም ሥጋት አጠናክረው እንዲቀጥሉና ሰለባዎቻቸውን እንዲያበራክቱ አድርጎ እያደር በመጨረሻም የሰው ልጆች ትውልድ ተቋርጦ ዝርያቸው ከዚህች ምድር እንዲጠፋ ለማድረግ የሚችል ትውልድ እንዲቀጥል የሚያደርገውን ተፈጥሯዊና ጤናማ የወሲብ ጉድኝት የሚጻረረውን ድርጊት ሕጋዊነትን የሰጠበት ውሳኔ ነው፡፡

ይህ የኦባማ አሥተዳደር እነኛን ጤናማና ተፈጥሯዊ የወሲብ ፍላጎት የሌላቸውን ባለጌዎች ወሲባዊ ጥቃት እየፈጸሙ ሰለባዎችንና መጠቀሚያዎቻቸውን የሚያበራክቱ የግፈኞችና የእርኩሶች ተሟጋች ጠበቃና አለኝታ በመሆኑና ይሄንን የሚያህል ግዙፍ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ግፍ የፈጸመ የሰብአዊ መብትን ምንነት የማያውቅ የማይገባው፤ የአውሬዎች ሰለባ የሆኑ ሕፃናትና አዋቂ ወንዶች ከተጠቁ በኋላ በሚፈጠርባቸው አካላዊና ሥነልቡናዊ የጤና ቀውስ መሰቃየታቸው ሰብአዊ መብታቸው በጣሱ መገፈፉ መረገጡ መጠቃቱ ፍትሕ መነፈጉ እንደሆነ ለመረዳት ጨርሶ ባለመፈለግ ጭራሽ ሳያፍርም “ሰብአዊ መብት” የሚለውን ቃል ኢሰብአዊና ኢሞራላዊ (ኢቅስማዊ) ድርጊት ለሚፈጽሙት ጤናማና ተፈጥሯዊ የወሲብ ፍላጎት ለሌላቸው ውርጋጦች ጥቅም ማስጠበቂያ ለማድረግ የሚጥር ግፈኛና ነውረኛ የደነቆረ አሥተዳደር ቅድስቷን ሀገሬን እረግጦ ይሄንን የደነቆረና ግፈኛ አስተሳሰቡን ሀገሬ ላይ ጥሎ እንዲሔድ ስለማልፈልግ ነው ሀገሬን እንዲጎበኙ የማልፈልገው፡፡

ሃይማኖትና በሳል ጽዱ ባሕል ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማይውቅ የምናምንቴ መንጋ በሃይማኖታችን በባሕላችን መሠረት እያልኩ የዚህን ጸያፍና ነውረኛ ድርጊታቸውን ከንቱነት ብላሽነትና ወራዳነት ለመውቀስ ለመከላከል ለማሳየት መሞከር ከንቱ ድካም ስለሆነ ነው ይሄንን የኦባማ አሥተዳደር ጥብቅና የቆመለትን እርኩስና ጸያፍ ግብር ከሃይማኖታችንና ከባሕላችን አንጻር እንዲህ እንዲህ ስለሆነ ብየ ልገልጽ ላስረዳ ያልፈለኩት፡፡ እዚህ ላይ አቶ ኦባማንም ሆነ አሥተዳደራቸውን የምጠይቀው ነገር አለ፡- በራሳቸውና በልጆቻቸው ላይ እንዲፈጸም የማይፈልጉትን ነገር በማን ላይ እንዲፈጸም ነው ሕጋዊ እንዲሆን የፈቀዱት? በራሳቹህ ላይ እንዲፈጸም አልፈለጋቹህም ማለት ለድርጊቱ ተፈላጊ አለመሆንና ጸያፍ ተወጋዥነት በቂ መረጃ አይደለም ወይ? ለምንድን ነው ይሄ ድርጊት በራሳቹህና በልጆቻቹህ ላይ እንዲፈጸም የማትፈልጉት? ድርጊቱ ከሰብአዊ አስተሳሰብ ጋር የማይጣጣም ሥነልቦናዊና አካላዊ ጤናን ስለሚያቃውስና አስጸያፊ ስለሆነ አይደለም ወይ?

እንግዲህ ይሄንን የምለው አቶ ኦባማና ይሄንን ጸያፍ ድርጊት ሕጋዊ እንዲሆን ያበቁት ባለሥልጣናት ግብረሰዶማዊያን አይደሉም ከሚል አስተሳሰብ በመነሣት ነው፡፡ “አይ! በእኛና በልጆቻችን ላይ እንዲፈጸም የማንፈልገውን ድርጊት አይደለም ሕጋዊ እንዲሆን ያደረግነው እኛ ራሳችንም ግብረ ሰዶማዊያን ነን” የምትሉ ከሆነም እናንተ ወንዴው ናቹህ ወይስ ሴቴው? ለሚለው ጥያቄየ ምላሻቹህን ባውቅ እንዴት ጥሩ ነበር፡፡ ለማንኛው ሴቴ ግብረሰዶማዊያን (ቀላጭ) ከሆናቹህ ይህ ጸያፍ ድርጊት በሥነልቡናና አካላዊ ጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ከማንም በላይ እናንተው ታውቁታላቹህና እባካቹህ ኃላፊነት ይሰማቹህና ሕዝባቹህን ወደዚህ ስቃይ ባትጨምሩት ምን አለበት? ለማለት እወዳለሁ፡፡ ወንዴው ግብረሰዶማዊ ከሆናቹህ ደግሞ የመንግሥትን ሥልጣን አላግባብ በመጠቀም ይሄንን ጸያፍ ድርጊት ሕጋዊነት እንዲያገኝ ያደረጋቹህት ለራሳቹህ ጸያፍና ነውረኛ ጥቅም ስትሉ በመሆኑ ለእናንተ ለጥቂቶቹ ስትሉ የብዙኃኑን ሕዝብ ብሎም የሰው ልጆችን ደኅንነትና ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ በማሳለፋቹህ ፍጹም ኃላፊነት የማይሰማቹህ ጉዶች በመሆናቹህ ልታፍሩ ይገባል፡፡ ለማንኛውም አቶ ኦባማ ይሄንን ጸያፍ ድርጊት ሕጋዊነት እንዲያገኝ ያደረጉት እርስዎ በመሆንዎ ለጥቁር ሕዝቦች ታላቅ ሐፍረትና ውርደት አሸክመውናልና በዚህም በኩል ባለ ዕዳ ነዎት፡፡ በዚህ እርስዎ በሰብአዊነት ላይ በፈጸሙት ግዙፍ ስሕተት የተነሣ እኔም ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቁርነቴ እንዳፍር አድርገውኛል፡፡

እኔ ግን እርስዎ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመመረጥ ተወዳድረው ምርጫ በተደረገበት ቀን ውጤቱን ሳላውቅ መተኛት ተስኖኝ እንቅልፍ በዐይኔ ሳይዞር የዓለም ዓቀፍ የቴሌቪዥን (የምርዓየ ኩነት) ጣቢያዎች ላይ እንዳፈጠጠጥኩ ነበር የነጋው፡፡ ከዚያም ማሸነፍዎ ሲታወቅ ደስታው እንቅልፌን አጥፍቶት ሁለት ቀናት ያለእንቅልፍ ማሳለፌን መቸም የምረሳው አይደለም፡፡ በተለይ እኛ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካን ሀገር ያለው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ ማለቴ ነው እርስዎን ለማስመረጥ ያላገረጉት ጥረት አልነበረም፡፡ ካላቸው ገቢና አቅም አንጻር ከማንኛውም አሜሪካ ውስጥ ካለ ማኅበረሰብ በላቀ መልኩ ጉልበታቸውን አድክመዋል ገንዘባቸውን ከስክሰዋል እንቅል አጥተው ዋትተዋል፡፡ ኢትዮጵያዊው ማኅበረሰብ እንደዛ ዓይነቱን ጥረት ለማንም አድርጎት አያውቅም ነበር፡፡ ወደፊትም ለማንም የሚያደርገው አይመስለኝም፡፡ እርስዎ ከመመረጥዎ በፊት በኢትዮጵያዊው ተወካይዎ አማካኝነት የወያኔ አገዛዝ በሀገራችንና በሕዝባችን ላይ የፈጠረብንን ችግር መፍትሔ እንደሚሰጡልን ቃል ገብተውልን እንደነበርና በዚህም ምክንያት በእርስዎ ትልቅ ተስፋ ጥለን እንደነበር የሚረሱት አይመስለኝም፡፡ ነቢይ አይደለንምና ቃልዎን በማጠፍ እንዲህ ዓይነት ሰው ሆነው አሥተዳደርዎ ከወያኔ ጋር በማበር በህልውናችንንና በደኅንነታችን ላይ የሚያሴር የሚዶልት መሆኑን ባለማወቅ ጠላታችንን አስመርጠን ቁጭ አልን፡፡

አቶ ኦባማ አሜሪካ ውስጥ ያለው ማኅበረሰባችን ሁለት ሚሊዬን እንኳ የማይሞላ ሊሆን ይችላል፡፡ እርስዎን እንዲመርጥ ሌላውን አሜሪካዊ ማኅበረሰብ ለማሳመን የተጫወተው ሚና ግን የላቀ ከመሆኑ የተነሣ ኢትዮጵያዊያን በእርስዎ ላይ ትልቅ ተስፋ በመጣል እንደዛ ባይረባረቡ ኖሮ አይመረጡም ነበር ተብሎ ቢነገር አለቅጥ የተጋነነ አባባል አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጵያዊያኑና ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ከሌላው አሜሪካዊ ማኅበረሰብ ጋር ባላቸው ግንኙነት ሁሉ የተቀረውን አሜሪካዊ ማኅበረሰብ ለመማሳመን ያላቸውን አቅም ሁሉ አሟጠው ተጠቅመው ነበር፡፡ እርስዎን ለአሸናፊነት ያበቃዎት ጨዋታ ይህ ነው የነበረው፡፡ አንድ የሌላ አሜሪካዊ ማኅበረሰብ አባልን ማሳመንና ይህ በጋለ ስሜትና መነሣሣት እንዲያምን የተደረገ አሜሪካዊ እሱም ደጎሞ በዚያ ስሜት ሌሎቹን እንዲምኑ ማድረጉ ነው ድምር ውጤቱ እርስዎን በአሸናፊነት እንዲወጡ ያስቻለዎት፡፡ ምን ዋጋ አለው “ባጎረስኩ ተነከስኩ” ሆነና ነገሩ እጃችን አመድ አፋሽ ሆኖ ቀረ እንጅ፡፡

እኔ ለነገሩ አቶ ኦባማ እንዳሉት ቢመጡና ቢጎበኙ አንድ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ሀገራችንን የጎበኘ መስሎም አይሰማኝ! እንዳንዴ ሳስበው አቶ ኃይለማርያምና ኦባማ አንድ ይሆኑብኛል፡፡ ኃይል (power) የለሽነታቸው ነው እንዲመሳሰሉብኝ የሚያደርጋቸው፡፡ መጠቀሚያዎች ናቸው፡፡ ምክንያታቸውን እነሱ ያውቃሉ አሜሪካኖች ለኦባማ ያላቸውን ንቀት ሲያንጸባርቁ እሳቸው የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት የተባሉት ትልቁ ባለሥልጣን ባልሰሙት ባላወቁት ሁኔታ የእስራኤልን ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁን ጠርተው እንዲጎበኙ በሕግ መወሰኛ ምክርቤቱም ተገኝተው ንግግር እንዲያደርጉ አደረጉ፡፡ አየ አቶ ኦባማi አያሳዝኑም? ደሞ ሥልጣን እንዳለው ሰው “አሜሪካ ዓለምን ትመራለች! ትገዛለች!” ይባልልኛላi አየ አቶ ኦባማi ለመሆኑ ይሄ ማለት ምን ማለት ነው አቶ ኦባማ? መቸም እስከምናውቀው ጊዜ ድረስ የዓለም ሀገራት መሪ ወይም ገዥ ሀገር ለመምረጥ ተሰብስበው ምርጫ አኪያሒደው አሜሪካንን መሪ ወይም ገዥ አድርገው እንዳልሾሙ እንዳልመረጡ ግልጽ ነው፡፡ ያለው እውነታ እንዲህ ከሆነ ታዲያ እንዴት ባለ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ነው ዓለምን ለመምራት ለመግዛት የተነሣቹህት አቶ ኦባማ? እናንተ አሜሪካኖች አንባገነንነት ማለት ምን ማለት ነው የሚመስላቹህ? እኔ ልንገራቹህ እንዴ? አንባገነን ማለት እራሱን ሾሞ በኃይል የሚገዛ ማለት ነው እሽ? ወይስ ከዚህ በኋላ ለማስመሰል የምትለፍፉትን መስፍነ ሕዝብ (ዲሞክራሲ) ትታቹህ የጨዋታውን ሕግ በመቀየር ቅኝ አገዛዝን ልትመልሱና የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅኝ ገዥ ሆናቹህ ዓለምን ለመግዛት አስባቹሀል? ከስልሳ ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን ቅኝ የመግዛት ፍላጎትና ዓላማ እንደነበራቹህ እናውቃለን፡፡ ይህች ፍላጎት አድጋ ነው ዓለምን ለመግዛት እንድታስቡ ያደረገቻቹህ?

በሉ እንግዲህ አቶ አባማ መልካም ጉብኝት ተመኝቸልዎታለሁ ዲስኩርዎትንም ለማድመጥ ባልጓጓም ምን እንደሚሉ ለመታዘብ ግን ቸኩያለሁ፡፡ ያው መቸም የታወቀ ነው እንደተለመደው ሀገሪቱ ፈጣን የምጣኔ ሀብት እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት አንደኛዋ መሆኗን፣ መሠረተ ልማት መስፋፋቱን፣ ድህነት ከ60 በመቶ ወደ 25 በመቶ መቀነሱን፣ ሩቅ ባልሆነ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ልማታዊ መንግሥታችን ወደ መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ ሊያደርግ እንደሚችል እምነትዎ የጸና መሆኑን እንደሚነግሩን አልጠራጠርም፡፡ ያኔ እኔ አጠገብዎ ብሆን ምን እንደምልዎ ልንገርዎት? አየ አቶ ኦባማi ይሄንን ይሒዱና ለአማትዎ ይንገሯቸው፡፡ ተመዘገበ የሚሉት የምጣኔ ሀብት ዕድገት የሀገሪቱ ሳይሆን የወያኔ የንግድ ድርጅቶችና የአጋር ባለሀብቶች በመሆኑ ዕድገቱ የሀገሪቱ ሳይሆን በኢፍትሐዊ መንገድ የበለጸጉትና ምጣኔ ሀብቱን ተቆጣጥረው እየተንቀሳቀሱ ያሉት የእነዚህ ተቋማትና ድርጅቶች መሆኑን፣ ተሠራ ተገነባ የሚሉት መሠረተ ልማትም ወያኔ ብድሩን በሀገራችን ስም ተበድሮ ሲያመጣው የሚሠሩት መሠረተ ልማቶች ዓለማቀፋዊ የጥራት ደረጃቸውን በጠበቁ መልኩ ሊያሠራ የሚችል የገንዘብ መጠን ተበድረው ያምጡ እንጅ ይህ ገንዘብ ከ80 በመቶው በላይ በእነሱው እየተመዘበረ በመበላቱ የተሠሩት መሠረተ ልማቶች እንኳንና ዓለማቀፋዊ የጥራት ደረጃ የመንደር እንኳን ያልያዙ ተጠናቀው ለአገልግሎት ከመብቃታቸው በፊት መንገዱ የሚፈረካከስ የሚፍረከረክ፣ የነር (የኤሌክትሪክ) ኃይል ማስተላለፊያዎች የሚቃጠሉ፣ የመናግር (በዓረብኛው የስልክ) እና የሌሎች የግንኙነት (የኮሚውኒኬሽን) አገልግሎቶች የሚቆራረጡና ተገቢውን አገልግሎቶች የማይሰጡ ባጠቃላይ ሊነገር ከሚቻለው በላይ ከፍተኛና የተወሳሰበ የጥራት ችግሮች የተሞሉ መሆናቸውንና ሀገርና ሕዝብ ወይ በገንዘቡ ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ተሠርቶበት አልተጠቀምን ወይ ብድሩ ሳይመጣ ቀርቶ ከዕዳ ነጻ አልሆንን የድርብ ድርብርብ ኪሳራ ባለቤት መሆናችንን እነግርዎ ነበር፡፡ እርስዎ ደግሞ ይህ ገንዘብ መመዝበሩን የማያውቁ አይመመስለኝም ካላወቁ ግን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሙያዎችን ቢጠይቁ እነሱ ሊደርሱበት የቻሉትን ያህል የተበዘበረውን ገንዘብ በየጊዜው ሲያወጡት ከነበረው አኃዝ ጭምር ያስረዱዎታልና እነሱን ይጠይቁ፡፡

ከዝርፊያቸው ዐይን ማውጣት የተነሣ ይሄ ተሠራ አቤት ማማሩ! የሚሉን የባቡር የመጓጓዣ አግልግሎትን ሲሠሩ የሸክላ ሀዲድ ዘርግተው ሕዝብ ሊያስፈጁ ነበር፡፡ ነገሩን የሚያውቅ አንዱ በማጋለጡ ነው ያ የሸክላ ሀዲድ ተነሥቶ እንደገና ትክክለኛ ነው የተባለው የብረት ሀዲድ የተዘረጋው፡፡ አሁንም እነሱ አሉ እንጅ መልሶ የተዘረጋው ትክክለኛው መሆኑን አላረጋገጥንም አቅሙም መብቱም የለንም፡፡ በእርግጥ በዚያ ሰሞን የሸክላው እየተነሣ ሲጫን ዓይተናል፡፡ ይሄንን የምናረጋግጠው ባቡሩ አግልግሎት ሲሰጥ ትክክለኛው ካልሆነ በሚደርስብን አደጋ ነው፡፡ ሀገርዎ ሞግዚት የሆነችው አገዛዝ ይሄንን ያህል ነው፡፡ ጅብነታቸው ነገ በተደረሰበት ጊዜ ምን ብለን እንመልሳለን ብለው እንዲያስቡ አላደረጋቸውም፡፡ በእንዲህ ዓይነት ጉደኛ ጅብ ነው ሀገሪቱ እየተበላች ያለችው፡፡ እንጅማ ወያኔ በሀገራችን ስም በበርካታ ቢሊዮኖች (ብልፎች) የሚቆጠር እንደተበደረው የገንዘብ መጠንና እንተገኘው እርዳታ ቢሆንማ ኖሮ ይህች ሀገር የት በደረች ነበር፡፡ እነኝህ የሚያዩዋቸው ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ዜጎች ሠርተው ባፈሩት የተገነቡ ሳይሆኑ በሙሰኛ ባለሥልጣናትና በተሟሳኝ ባለሀብቶች የሙስና ገንዘብ የተገነቡ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ የሀገርና የሕዝብ ኪሳራ እንጅ እድገት ወይም ልማት አይደለም፡፡ የሀገር ካዝና ተራቁቶ ተዘርፎ የተገነባ በመሆኑ፡፡ በዚህ ሀገሪቱ ባልተጠቀመችበት በስሟ የተመዘገበ የብድር ዕዳ ደባ ግን በትውልደ ትውልድ በቸም ተከፍሎ ለማያልቅ የዕዳ ማጥ ውስጥ እንድትዘፈቅ ተደርገናል፡፡ እንዲህ በመደረጉም ለቀጣዩ ትውልድና ለዚህች ሀገር መንግሥታት የማያንቀሳቅስ የማያፈናፍን የእግር ብረት ነው፡፡ ይሔም የተደረገው ሆን ተብሎ መሆኑንም ጭምር እናውቃለን፡፡

“ኢትዮጵያ ውስጥ ድህነት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል” የሚሉትንም ሕዝቡ ቢሰማዎት እንዴ! እንደኛ ሀገር ኢትዮጵያ የምትባል ሌላ ሀገር አለች እንዴ! በማለት ሕዝቡ የተናገሩት ነገር ስለ እሱ መሆኑን ሊያምንዎ እንደማይችል ሊያውቁት ይገባል፡፡ የቀነሰው በድህነት ያለው ሕዝባችን ሳይሆን በመካከለኛ ገቢ ደረጃ ያለው ኅብረተሰብ ነው፡፡ የሚበዛው የመካከለኛ ገቢ ኅብረተሰብ ወደ ድህነቱ ደረጃ በመቀላቀሉ ባለ መካከለኛ ገቢ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እጅግ አሽቆልቁሏል፡፡ ልጆቻቸውን የግል ትምህርት ቤት ማስተማር ይችሉ የነበሩ ባለ መካከለኛ ገቢ ዜጎች በኑሮ ውድነቱ በመመታታቸው ምክንያት ማስተማርና ወጫቸውን መሸፈን አቅቷቸው ልጆቻቸውን አስወጥተው ወደ የመንግሥት ትምህርት ቤት ያስገቡ የኅብረተሰባችን ክፍል በርካቶች ናቸው፡፡

ከዚህም በላይ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ እኛ ኢትዮጵያዊያን ዐይተነው በማናውቀው መልኩ የመንግሥትና የሕዝብ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚበሉትን በማጣት ምክንያት ባዶ ሆዳቸውን ወደ ትምህርት ቤት ስለሚሔዱ በየትምህርት ቤቱ እራሳቸውን ስተው የሚወድቁ ተማሪዎች አስደንጋጭና ክስተት ሊባል በሚችል ሁኔታ በመታየቱ ምክንያት የተነሣ ድርጅቶች አቅማቸው በፈቀደላቸው መጠን በየትምህርት ቤቱ ለበርካታ ተማሪዎች ቁርስና ምሳ የማብላት ግዴታ ውስጥ የተገባበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶችም ከአንዳንድ ሆቴሎች (ቤተ እንግዳዎች) የሚወጡ ትርፍራፊ ምግቦችን ለመመገብ የተገደዱበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ይህንን ሁኔታ በታሪካችን ዓይተንም ሰምተንም አናውቅም፡፡ እነኝህ ሁኔታዎች የሚያሳዩት ድህነት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ስር እየሰደደ እተስፋፋ መምጣቱን እንጅ መቀነሱን አይደለም፡፡

አዎ በእርግጥ የማይካደው ሐቅ ሥርዓቱ ቆሜላቸዋለሁ ደሜን አፍሸላቸዋለሁ አጥንቴን ከስክሸላቸዋለሁ መሥዋዕትነትን ከፍየላቸዋለሁ የሚላቸው የግል ሥራዎችን የመሥራትና የመንግሥት መሥሪያቤቶች የመቀጠር ቅድሚያ ዕድል ያላቸው አናሳ የትግሬ ጎሳ አባላት ዘንድ ድህነቱ ከ60 በመቶ ወደ 25 በመቶ ወርዶ ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ እንዲያውም ከዚህም በታች እንደሆነ እገምታለሁ፡፡ ከእነሱ የተረፈውን ፍርፋሪውን ደግሞ የአገዛዙ የፖለቲካ (የእምነተ አስተዳደር) አባል የሆኑና ለመኖር ሲሉ ለባርነት ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ዜጎች ያገኛሉ፡፡ ከዚህ ውጭ ግን ኢትዮጵያዊያን በገዛ ሀገራችን በነጻነትና በፍትሐዊ አሠራር ሠርተን መለወጥ የምንችልበት ዕድል በፍጹም የሌለ በመሆኑ ለውጣችን በመጥፎ ጎኑ እንጅ በመልካም ጎን ሊሆንልን አልቻለም፡፡ ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ የአንድ አናሳ ጎሳ ንብረት ሆናለች፡፡ ሀገራችን ተቀምተናል በሀገራችን ግዞተኛ ሆነናል፡፡

“አገዛዙ አናሳ ጎሳ ሆኖ እያለ እንዴት 95 ሚሊዮን (አእላፋት) የሚሆነውን የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደዚህ ቀጥቅጠው ረግጠው ሊገዙ ቻሉ ታዲያ?” ብለው እንደማይጠይቁኝ ተስፋ አደርጋለሁ አቶ ኦባማ፡፡ የዚህ ጠባብ አናሳ ጎሳ አገዛዝ ጡንቻ አቅም ጉልበት እናንተ እንደሆናቹህ ጠንቅቃቹህ ታውቁታላቹህና፡፡ ይህ አገዛዝ የእናንተ ሁለንተናዊ ድጋፍ ባይኖረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስንጥር ማንሣት ሳያስፈልገው ሦስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሚወድቅ የሚፈርስ የሚጠፋ የመጨረሻው ደካማ አገዛዝ ነበር፡፡ ይህ አገዛዝ ይሄንን ቀጤማ ጉልበቱን አቅሙን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነው የሀገር ክህደት በመፈጸም በባንዳነትና በቅጥረኝነት ለባዕዳንና ለጠላት ሀገራት በማደርና ከዚህች ሀገር የሚፈልጉትን ግፈኛ ጥቅማቸውን ከሚፈልጉትም በላይ በማቅረብ በመስጠት በመፈጸም የእናንተን አቅም ጉልበት ሁለንተናዊ ድጋፍ መጠቀም የቻለውና ጉልበታቹህን ጉልበቱ ጡንቻቹህን ጡንቻው አቅማቹህን አቅሙ በማድረጉ ሊያቅተንና እስከዛሬም ሊዘልቅ የቻለው፡፡

ሌላው ቀርቶ “የኔ ፓርቲ አባል ካልሆናቹህ በስተቀር” እየተባልን መማር እንኳን ተከልክለናል፡፡ ከመንግሥት ሥራ እንባረራለን በግል ሠርተን ማደር አልቻልንም፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው የዚህ ግፈኛ አገዛዝ ድርጊት ደግሞ በድርቅ በመጠቃታቸው ምክንያት የእርዳታ እህል መጥቶላቸው ያጋጠማቸውን ችግር በእርዳታ እህል ብቻ ለማሳለፍ የተገደዱ ወገኖቻችንን “የኔ አባል ካልሆናቹህ በስተቀር አታገኙም!” ብሎ ከልክሎ ማሰቃየቱና ለሞት መዳረጉ ነው፡፡ እንዲህ በማድረጉ ያለውን የጭካኔና የአረመኔነት ደረጃ ያሳየ ክፉ አገዛዝ እንደሆነ ከዓመታት በፊት ከለጋሽ ሀገራት ድርጅቶች ሪፖርት (ዘገባ) “ባላቸው የፖለቲካ አቋም ምክንያት አገዛዙ የእርዳታ እህል እንደከለከለ” መስክረው አድምጠውታል፡፡ በሀገራችን ያለን ነጻነት ይሄንን ይመስላል፡፡ የዚህን አገዛዝ አረመኔነት እንግለጽ ከተባለ በእርግጠኝነትም ጉዳዩን ያውቁታል ብየ አስባለሁ በግልጽም በስውርም ወደ ሦስት በሚሆኑ ብሔረሰቦች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል እየፈጸመም ይገኛል፡፡ ከዚህ ከዚህ በላይ የወያኔን አረመኔነት ፈላጭ ቆራጭነት ሊያሳይ ሊያስረዳ የሚችል ምን ጉዳይ ሊኖር ይችላል አቶ ኦባማ?

ወያኔን በየ ዓመቱ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫዎቻቹህ እንደምታቀርቡበት የይስሙላ ክስ እንደ ክሳቹህ ሁሉ በተግባርም ተጠያቂ ሳታደርጉት ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረጋቹህ እንዲህ ዓይነት የመጨረሻ የወንጀል ድርጊቶችን ከፈጸመ አገዛዝ ጋር ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረጋቹህ አብራቹህ መሥራታቹህ ለፈጸመው ወንጀል ሁሉ ከሱ ባልተናነሰ ደረጃ እናንተም ተጠያቂዎች መሆናቹህን አታውቁም አቶ ኦባማ? እንዴት ነው ተጠያቂ መሆናቹህን ላታውቁ የምትችሉት? እኛ ይሄንን ልናደርግ የምንችልበት አቅም እንደሌለን አውቃቹህ ንቃቹህን ነው እንጅ ማወቅማ አሳምራቹህ ታውቁታላቹህ፡፡ እንዲያው እናንተ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ሌላው ሁሉ ይቅርና በዚህ ሁሉ ግፍ ኅሊናቹህ ምንም የሚላቹህ ነገር የለም አቶ ኦባማ? አይ! ይሄንን እንኳን መጠየቅ አልነበረብኝም ኅሊና እያላቹህ ይሄንን ልታደርጉ አትችሉም ነበርና፡፡

እናም ፈጣን እድገት ድህነት ቅነሳ ምንትስ የሚሉት ነገር ሁሉ ለኛ ተረት ነው፡፡ ይሄ ሁሉ ነገር የእነሱ ብቻ ነው፡፡ ምናልባትም ለመጎብኘት ካመቸዎትና እሽ ካሏቸው የእነሱን ወገኖች ስኬትና ከድህነት መላቀቅ ሊያስጎበኙዎት ይችሉ ይሆናል፡፡ ያ ግን በምንም ምልኩ ቢሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ ሕይዎት የሚያሳይና የሚወክል አይደለም፡፡ የተቀረነው ኢትዮጵያዊያን እየማቀቅን ነው ብልዎት ይህ ቃል የደረሰብንንና ያለብንን ችግር ክብደት መጠን ለመግለጹ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ አሁንም የማይካደው ሀቅ ግን ይህ አገዛዝ አግባብነት በሌለው በኢፍትሐዊና በሙስና በተተበተበው የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አንጻር ሲታዩ 0.00004 የሚሆኑትን ቢሊየነሮች (ብልፋሞች) ማፍራት መቻሉ ነው፡፡

ለማኝኛውም አቶ ኦባማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያላቹህን የአቋም ለውጥ የምትገልጹበት መንገድ በጣም አስግቶኛል፡፡ በእርግጥ የአቋም ለውጥ ላይሆን ይችላል፡፡ በድብቅ ይሁን እንጅ ስታደርጉት የቆያቹህት አቋምና መርሕ በመሆኑ፡፡ ነገር ግን “ምን ይሉን!” ማለቱን ትታቹህ እንዲህ በአደባባይ የምትገልጹትና የምታደርጉት ነገር ሁሉ ሥጋት ላይ የሚጥል ነው፡፡ ለማንኛውም ልነግርዎት የምፈልገው ነገር ቢኖር የየትኛውም ሀገር ሕዝብ ቢሆን መንግሥታቸው አንባገነን እስከሆነባቸው ጊዜ ድረስና በሰላማዊ የትግል አማራጭ መስፍነ ሕዝባዊ (ዲሞክራሲያዊ) የሆነ ሕዝባዊ መንግሥት መመሥረት የማይችሉበት ሁኔታ እስከተፈጠረ ጊዜ ድረስ ማንኛውንም የትግል አማራጭ ተጠቅመው መስፍነ ሕዝባዊ (ዲሞክራሲያዊ) መንግሥት መመሥረት ዜጎች ከማንም ሊቸራቸው የማይገባ መብትና የዜግነት ግዴታቸውም እንደሆነ ሊያውቁ ይገባል፡፡ የዲሞክራሲ መርሆዎችን ጠንቅቀን እናውቃለን ለመርሖዎቹ ተግባራዊነትም እንታገላለን ለምትሉ ይሄ ግልጽ አለመሆኑ እጅግ የሚገርምና የሚያሳዝንም ነገር ነው፡፡

ሀቁ ይሄ ሆኖ እያለ “አሻንጉሊታቹህን አንባገነኑን የወያኔን አገዛዝ በኃይል ለማስወገድ የሚደረግን እንቅስቃሴ እንቃወማለን እንቅስቃሴውንም የምናየው በሽብርተኝነት ነው” ማለታቹህ “የዲሞክራሲና የነጻነት ቃፊር ነን” የሚለው መፎክራቹህ ባዶ ጩኸት እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል፡፡ “shame on you” እኔም ብያቹሀለሁ፡፡ በውጭ ጉዳይ (state department) መሥሪያ ቤታቹህ የአዞ እንባ እያፈሰሳቹህልን በማጃጃል ውስጥ ውስጡን ግን ወያኔን ከባለ ጥፍርነት ወደ ባለ ጥርስነት ከባለ ጥርስነት ወደ ጭራቅነት እንዲለወጥ አድርጋቹህ ጥቅማችን ነው ለምትሉት ግፈኛ ኢፍትሐዊ ጥቅም ታማኝ ሎሌ አድርጋቹህ የሀገራችንንና የሕዝቧን ዕጣ ፋንታ አጨልማቹህ ሀገሪቱን የአንድ አናሳ ጎሳ ብቻ አድርጋቹህ ስላጃጃላቹህንና ስላስበላቹህን የብዙ የግፍ ሰለባ የንጹሐን ኢትዮጵያዊያን ደምና ዕንባ  በታሪክና በእግዚአብሔር ፊት ይፋረዷቹሀል፡፡ እግዚአብሔር ፈርዶ አንዲት ጣቱን ባነቃነቀ ጊዜ ከጣቱ መነቃነቅ የተነሣ ብቻ አሜሪካ መቀመቅ ትወርዳለች በምን አመታት እንደሚመታቹህ በፍጹም አታውቁም፡፡

የገነባቹህት ተወዳዳሪ የሌለው የጦር ኃይልና ምጣቴ ሀብት የደረሳቹህበት የሥልጣኔ ደረጃ ከቶውንም ሊያድናቹህ አይችልም፡፡ “ ንጉሥ በሠራዊት ብዛት አይድንም ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም፡፡ ፈረስም (ታንክና የጦር አውሮፕላን) ከንቱ ነው አያድንም በኃይሉም ብዛት አያመልጥም፡፡ እነሆ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደሚፈሩት ናቸው በምሕረቱም ወደሚታመኑ፤ ነፍሳቸውን ከሞት ያድን ዘንድ በረሀብም ጊዜ ይመግባቸው ዘንድ” መዝ. 33(34)፤16-19

ይሄንንም ባለፈው ጊዜ ቀምሳቹህታል፡፡ እንዴት ከቁጥጥራቹህ ውጪ በሆነ መንገድ ሊከሰት እንደቻለ ጨርሶ በማታውቁት ሁኔታ ኢኮኖሚያቹህ (ምጣኔ ሀብታቹህ) ተቃውሶ የምትይዙትን የምትጨብጡት አሳጥቷቹህ እንደነበርና ከውድቀት አፋፍ ደርሳቹህ እንደነበር የምትረሱት አይመስለኝም፡፡ እሷ ቅጣት እግዚአብሔር ሊጥላቹህ ሊቀጣቹህ ከፈለገ በቀላሉ እንዴት አድርጎ በአይቀጡ ቅጣት ሊቀጣቹህ እንደሚችል ማሳያ ነበረች ልብ የላቹህምና አታስተውሉምና መረዳት አልቻላቹህም፡፡ የሚያጠቃቹህን ተምዘግዛጊ የጦር መሣሪያ ጦርና የጦር አውሮፕላን አትጠብቁ፡፡ ለማየት ያብቃቹህ የንጹሐን ኢትዮጵያዊያን ደምና እንባ ያስፈርድባቹሀል፡፡ እውነቴን ነው የምላቹህ በዚህች ሀገርና ሕዝብ ላይ እንዲህ እንዳሾፋቹህ እንደቀለዳቹህ እንደተጫወታቹህ አትቀሩም፡፡ ልዑል ይሄንን ካላደረገ በእውነት አዶናይ በዚህ ሰማይ የለማ!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው  amsalugkidan@gmail.com

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8774#sthash.J9x2ohWT.dpuf

በሻቢያ እርዳታ ይደረጋል የሚባለው የትጥቅ ትግል “ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ”

ማሳሰቢያ
ይህች መጣጥፍ በቅርቡ እዚህ ድረገጽ ላይ ወጥታ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ጸሃፊው ያነሷቸው ጭብጦች ሰሞኑን ግንቦት ሰባት ጀምሬያለሁ ካለው የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴና ወያኔም ለዚህ ከሰጠው ምላሽ ጋር ወቅታዊነትና ቀጥተኛ መስተጋብር ያለው ሆኖ ስላገኘነው ለግንዛቤ ማዳበሪያ እንዲረዳ በድጋሚ አቅርበነዋል።

ከታደሰ አርጋው

መግቢያ
የወያኔ አገዛዝን በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ኤርትራ ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ ስለተባሉት “አርበኞች” ሰሞኑን በመካሄድ ላይ ያለው ውይይት በውጭ በሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያውያን የዜና ማሰራጫዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶታል። በተለይም በአቶ አበበ በለው አዘጋጅነትና አቅራቢነት በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ አካባቢ በሚሰራጨው አዲስ ድምጽ ሬዲዮ ላይ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ሳምንታት የቀረበው ውይይት እጅግ ጠቃሚ ሃሳቦች የቀረቡበትና በተለይም ኤርትራ ውስጥ ከዚህ ቀደም አርበኞች ግምባርን ተቀላቅለው ሁኔታውን በአይናቸው ያዩና በሂደቱ የተሳተፉበት እማኞች የቀረቡበት በመሆኑ ሁሉም አገር ወዳድ ወገኖች በጽሞና ሊከታተሉትና የራሳቸውን ግንዛቤ ሊወስዱበት የሚገባ ውይይት ነው። በውይይቱ ላይ የተገኙት እንግዶች አቶ ክንፉ አሰፋ ከኔዘርላንድስ፣ አቶ ሰናይ ገብረመድኅን ከአውስትራሊያ እንዲሁም አቶ ልዑል ቀስቅስና አቶ ካሣዬ ከጀርመን ናቸው።የተለያዩ አድማጮችም ስልክ በመደወል ተሳትፎ አድርገዋል። እኔም በውይይቱ ላይ የተንሸራሸሩትን ሀሳቦች አስመልክቼ የራሴን ግምገማና አስተያየት በዚህች አጭር መጣጣፍ አቅርቤያለሁ።

የውይይቱ ጭብጥ በሻቢያ እርዳታ ወያኔን ለመጣል የሚደረግ እውነተኛ ትግል አለ ወይ? ሻቢያስ እውነተኛ እርዳታ እያሰጠ ነው ወይ?

በቃለ መጠይቁ ውስጥ የተነሱት አበይት ጉዳዮች የተለያየ የፖለቲካ አመለካከትና አጀንዳ ያላቸው ቡድኖች/ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም የኦሮሞ፣ የኢትዮጵያ አርበኞች፣ የቤንሻንጉል፣ የጋምቤላ፣ የአፋር፣ የትግራይና ሌሎችም ግምባሮች ለበርካታ ዓመታት በሻቢያ እርዳታ ወያኔን ለማስወገድ ኤርትራ ውስጥ ይገኛሉ ስለሚባሉት ከዚህ በፊት በተለያዩ መድረኮች ላይ ከቀረቡት ነቀፋዎችና ትችቶች ጋር ተመሳሳይነት አላቸው። ሻቢያ ከተፈለፈለበት እ.አ.አ. ከ1970ዎቹ መጀመሪያ አንስቶ አንግቦት የተነሳው መፈክር ኤርትራን ከኢትዮጵያ መገንጠልና የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ማውደምና በምትኳ የተዳከመች፣ እርሱ የሚቆጣጠራትና ተንሰራርታ ለህልውናው የማታሰጋው፣ ደካማ፣ የተከፋፈለችና የደቀቀች ጥሬ ዕቃ አቅራቢና የፋብሪካ ውጤቶች ማራገፊያ የሆነች አገር እንድትሆን ለማድረግ ነው።

በዚህም መሠረት ሻቢያኤርትራን ለመገንጠል ሁለት የቀደሙ የኢትዮጵያ መንግሥታትን ማለትም የኃይለ ስላሴንና የወታደራዊውን መንግሥታት በሚወጋበት ጊዜ እራሱ ፈጥሮ በረጨው “የኤርትራ ታሪክ” በመመርኮዝ ኢትዮጵያ ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ ጉዳት አድርሷል። አሁንም ጦሱና መዘዙን ተሸክመን እየኖርን ነው።

ሻቢያ በኢትዮጵያ ላይ ያደረሰው ጉዳት በጥቅሉ አሁን እንደምንሰማውና በረቀቀ ሁኔታ እየተጋትን እንዳለው የኢሳያስ አፈወርቂ “ የታሪክ መዛባት” ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው የኤርትራ ምሁራንና ታሪክ ጸሃፊዎች ኢትዮጵያዊነት ላይ ዘምተው ሲተናነቁን ኖረዋል። አሁን በኢሳያስ አፈወርቂ ተፈብርኮ በኢሳት በመስተጋባት ላይ እንዳለው “የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች ወንድማማቾች ናቸው፤ የጋራ የሆኑ እሴቶች አሏቸው፣ ወዘተ….” እንደተባለው ሳይሆን ሻቢያ ለረዥም ዓምታት ሲያስተጋባና ሲለፍፍ የነበረው ኢትዮጵያ ኤርትራን በቅኝ ገዥነት ጨቁና ስትገዛ የነበረች ናት በማለት “ቅኝ ግዛት” ለሚለው ሀረግ በመላው ዓለም ከሚሰጠው ትርጉም ጋር በተጣረሰ መንገድ ልብ ወለድ ዝባዝንኬ በመደርደር ዓላማው የሆነውን ኤርትራን ከኢትዮጵያ የመገንጠልና አዲስ ማንነት የመፍጠር እንዲሁም በኢትዮጵያና በኤርትራ ውስጥ የሚኖረውን ህዝብ ለመለያየትና ደም ለማቃባት ተጠቅሞበታል።

የቅርብ ጊዜ ታሪክ

የታሪክ ማህደራትን ብንመለከት ጣሊያን ኤርትራን በቅን ግዛትነት ይገዛ በነበረበት ዘመን ኤርትራዊያን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር ሳይሆን እንደ ከብት ተዋርደው ይገዙ እንደነበር ይታወቃል።አሁንም ቢሆን በሕይወት ያሉ ስቃዩና በደሉ የደረሰባቸው እማኞች ጊዜ ያልሻረውን በደላቸውን ይናገራሉ። በዛ ጨለማ ዘመን ጣሊያኖች ኤርትራውያንን በረባው ባረባው በካልቾ መቀመጫቸውን እየጠለዙ፣ አፍንጫቸውን በቴስታ እያደሙና የስድብ ድንጋይ እያወረዱባቸው ለምሳሌ “አፋንኩሎ” “ቴስታ ዲጋሊኖ” ወዘተ እያሉ አዋርደውና አንቋሸው በባርነት እየቀጠቀጡ ሲገዣቸው አንደነበር ይታወቃል። ብዙዎች ኤርትራውያን ከዚህ አሳራቸውን ከሚያስቆጥራቸው የጣሊያን ባርነት እያመለጡ ወደ ወገናቸው ኢትዮጵያውያን በመግባት ተከብረውና አንቱ ተብለው የተለያዩ የማዕረግና የክብር ስሞች እየተሰጧቸው ለምሳሌ ራስ፣ ፍታውራሪ፣ ጀጃዝማች፣ ቀኝ አዝማች ወዘተ ተበለው ይኖሩ እንደነበርና አሁንም በመኖር ላይ እንዳሉ የአደባባይ ሚስጢር ነው።

በዚህም መሠረት ከኤርትራ ክፍለ ሃገር ባዶ እጃቸውን የወጡ ወገኖቻችን ኢትዮጵያ አስተምራ ለወግ ለማዕረግ ያበቃቻቸው ስፍር ቁጥር የላቸውም። እነዚህ ወገኖቻቸን በጦር አዛዥነት፣ በሚኒስትርነት፣ በአምባሳደርነት፣ ተመድበው ሲያገለግሉ የነበረ ሲሆን እንዲሁም በንግዱ ዘርፍ የትላላቅ ፋብሪካዎች፣ሱቆች፣ ጋራዦች፣የአስመጭና ላኪ ወኪሎች፣ ሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች እንዲሁም የበርካታ የንግድ ተቋማት ባለቤቶች ሆነው ተደስተውና ተከብረው ይኖሩባት የነበረች፣ አሁንም እየኖሩባት ያለች አገር ኢትዮጵያ ናት። ይህንን አገር ያወቀውንና ጸሃይ የሞቀውን እውነታ በመደፍጠጥ ሻቢያ “ኢትዮጵያ ኤርትራን በቅኝ ግዛት ያዘች” በማለት የረጨው መርዝ የለከፋቸው ኤርትራውያን ያጎረሳቸውን የኢትዮጵያን እጅ የነከሱና የእግራቸውን ንቃቃት የደፈነላቸውን ኢትዮጵያ አገራቸውን እውስጧ ተቀምጠው ይገዘግዟትና በማጅራቷ ያርዷት የነበሩ ቀላል ቁጥር ያላቸው እንዳልነበሩ ሳይናገሩ ማለፍ በታሪክ ላይ ማላገጥ ስለሆነ ሊጠቀስ የሚገባውና በታሪክ መዝግብም በዝርዝር ሊሰፍር የሚገባው ነው።

ሻቢያ ለጎረቤት አገሮችና ለዐረቡ ዓለም የተሳሳተ መረጃ በማጠጣት ምንም እንኳ ኢትዮጵያ በኤጼ ኃይለስላሴ መንግስት ከዐረቡ አለም መሪዎች ከግብጹ ፕሬዝዳንት ጀማል አብደልናስር አንስቶ ከሱዳን፣ ሊባኖስ፣ ዮርዳኖስ፣ አልጀሪያ፣ ሞሮኮና ሌሎችም አገሮች ጋር ወዳጅነት ለመመሥረት ከፍተኛ ጥረት አድርጋ የነበረችና በተለይም በሞሮኮና አልጀሪያ መካከል የነበረውን ጦርነት አስቁማ ያስታረቀች አገር ብትሆንም በአጸፋው ያገኘችው ግን በጠላትነት መታየትን ነው። በወታደራዊው መንግሥት ጊዜም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች የፍልስጥኤም ህዝብ ጥያቄን አንግባ በመታገል ከፍተኛ አስተዋጽዖ ብታበረክትም እንዲሁም ከሊቢያ፣አልጀሪያ፣ ምዕራብ ሰሃራ ግብጽ፣ሰሜንና ደቡብ የመን ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት አድርጋ የነበረች ብትሆንም ሻቢያ በተደራጀና ስራዬ ብሎ ሌት ተቀን በሰራው ደባ ኢትዮጵያን ከአብዛኛው የአረብ አገሮች ጋር ጠላትነት ፈጥሮባት ኖሯል። ሻቢያም በዚህ ድርጊቱ ደንበር ጥሶ ኢትዮጵያን ከወረረው የሶማሊያው የሲያድ ባሬ መንግስት ባልተነሰሰ ሁኔታ ኢትዮጵያ ላይ ትልቅ ጉዳት አድርሶባታል።

ከሁሉም በላይ ሻቢያ ወያኔን ከመፍጠሩም ባሻገር በሰው ኃይል በማጠናከር ማለትም መግቢያ መውጫውን በማሳየት፣ በማስታጠቅ በውጭ ከሚገኙ ጸረ- ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር በማገናኘትና በሌሎችም መንገዶች ወያኔን አቅፎና ደግፎ ለስልጣን እንዳበቃው ይታወቃል። ሻቢያ ባይኖር ኖሮ ወያኔ እዛው የበቀለበት ደደቢት ዋሻ ደድቦ ይቀር እንደነበር የማይታበል ሀቅ ነው። ሻቢያና ወያኔ ተዛዝለውና ተደጋግፈው በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱትን ዘመቻ ካጠናቀቁ በኋላ የባድመ ጦርነት እስከተነሳበት ጊዜ ድረስ በጋራ አገሪቱን እየዘረፉ እንደገዙ ይታወቃል። በኢኮኖሚ ጥቅም መጋጨት ምክንያት የባድመ ጦርነት ከተነሳ በኋላ ወያኔና ሻቢያ ግንኙነታቸው የተበላሸ ቢመስልም፣ ሁለቱም ሻቢያም ሆነ ወያኔ አንዱ የሌላውን ህልውና ሊጎዳ የሚችል ድርጊት በተግባርና በተጨባጭ ሁኔታ ሲፈጽም አልታየም። እንደውም በመካከላቸው ቃል ኪዳን ወይም (ፓክት) ያለ በሚያስመስል ሁኔት አንዱ ሌላውን ሲጠብቅና ሲከላከል ነው የሚታየው። ለምሳሌ ያህል በ1997 ዓ.ም. ቅንጅት በምርጫ ባሸነፈበት ወቅት ወያኔ “ሻቢያ ሊወጋን ነው” በሚል ማታለያ አገራዊ አጀንዳ ለመቅረጽና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍ ለማግነት በተንቀሳቀሰበት ወቅት ሻቢያም በበኩሉ ሰራዊቱን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በማስጠጋት ወረራ የሚፈጽም በማስመሰል ለወያኔ ፕሮፓጋንዳ ማረጋገጫ አሳይቷል።በማያሻማና በማያወላዳ ሁኔታ አፍ ሞልቶ ለመናገር የሚቻለው ሻቢያና ወያኔ ተዛዝለውና ተደጋግፈው ኢትዮጵያን እንደተቀራመቷት ሁሉ፤ ሁለቱም በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚችሉት ይህ የኃይል ሚዛን ሲጠበቅ እንደሆነ በደንብ አምነውበት ሥራ ላይ አውለውት እየተሰራበት ይገኛል።

“የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በወያኔና ሻቢያ መካከል አይሰራም በበርካታ ዓለም አቀፍ ግጭቶችና ጦርነቶች ውስጥ ሥራ ላይ የዋለው“የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” የሚለው አካሄድ በወያኔና ሻቢያ መካከል መካካል ግን አይሰራም። ምክንያቱም ወያኔና ሻቢያ እርስ በርስ የተቆላለፈና የተሳሰረ ጥቅም እንጅ ጠላትነት የላቸውም። መሬት ላይ በመታየት ያለው ሀቅ የሚያሳየው ሁለቱ ቡድኖች መግባባታቸውን እንጅ ጠላትነታቸውን አይደለም። ኤርትራ ውስጥ አሉ የሚባሉት የኢትዮጵያ “አርበኞች/ ተዋጊዎች” ተጠናክረው የወያኔን ህልውና ላይ አደጋ ለመጣል የሚያስችል አቅም ያለው እንቅስቃሴ ቢፈጥሩና ለዚህም ሻቢያ ቢረዳቸው፣ አለምንም ማመንታትና መዘናጋት ወያኔ 100% ማለት እችላለሁ ድንበር ተሻግሮ በመግባት ሻቢያን ይደመስሰው ነበር። ሻቢያም በግዛቱ ውስጥ ከ 20 ዓመታት በላይ የኦነግና የአርበኞች ግንባር ተዋጊዎች አሉ እየተባለ ወሬው ቢናፈስም፣ወያኔን የማያስቆጣውን “የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” (ትሕዴን/ደምህት) ነው በሰው ኃይል፣ በስልጠናና በትጥቅ ያጠናከረው። ያም ሆኖ ትሕዴን ወያኔ ላይ አደጋ ለማስከተል የሚበቃ አቅም እንደሌለው ይነገራል። ሻቢያ ሥልጣን ከወያኔ የሚነጥቅና በአሁን ጊዜ ያለውን በኢትዮጵያና በኤርትራ ውስጥ ያለውን የትግሪኛ ተናጋሪዎች የበላይነት የሚያዛባና የሚቀይር እርምጃ ማለትም የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የጋምቤላ ወይም የአማራ ግንባሮችን አላጠናከረም። በወያኔም በኩል ያሉት የሻቢያ ተቃዋሚዎች ከወሬና በየሆቴሉ ድዳቸውን ከማስጣትና ጣራ ሲቆጥሩ ከመዋል ያለፈ ነግር ሲሰሩ አልታዩም፣ ሊሰሩም አይችሉም።

ወያኔ እነዚህን የሻቢያ ተቃዋሚዎች አጠናክሮ በመደገፍ ሻቢያ ላይ ትልቅ ጉዳት ማድረስ ይችል ነበር። ሆኖም ወያኔ የሻቢያን ተቃዋሚዎች ሲጣሉ ከመሸምገልና በየአረቄውና በየሆቴል ቤቱ ከማሽሞንሞንና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ መጠቀሚያ ከማድረግ ያለፈ ነገር አልሰራም፣ ወደፊትም ይሰራል ተብሎ አይጠበቅም። እንደውም እንደ ስብሐት ነጋ ያሉ የወያኔ ቁንጮዎች አሁንም የሚናገሩት በፊትም ለኤርትራ ነጻነት ተዋግተናል፤ ኤርትራ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ችግር ቢፈጠር አሁንም እንዋጋለን ብለው በሁለቱ መካከል ያለውን የግንኙነት መጠን ቁልጭ አድርገው አሳይተውናል። ከዚህ መረዳት የሚቻለው ሻቢያም ሆነ ወያኔ ተዝዛለው ወደ ሥልጣን ኮርቻ እንደወጡ፤ አንዱ ከሌለ ሌላው እንደማይኖር ጠንቅቀው ስለሚያውቁ በግዛታቸው ላይ ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ አቅም ያለው ተቃዋሚ እንዲያቆጠቁጥ አይፈልጉም። ከዚህም በላይ ወያኔና ሻቢያ ባላቸው ያለመጠፋፋት ስምምነት ወይም ህልውናቸውን አስመልክተው በወሰዱት የጋር ግንዛቤ ለወደፊት ሊነሳባቸው የሚችለውን ተቃዋሚዎች/ተዋጊዎች ትግል አስቀድመው ለማኮላሸትና እንዲሁም እነዚሁ ተቃዋሚዎች ለወደፊቱ ሊያገኙ የሚችሉትን ሕዝባዊ ድጋፍ ለማጨናግፍና በሕዝብ ዘንድ ሊኖራቸው የሚችለውን አመኔታ ለማሳጣት ተልካሻና የማይረቡ ነጻ አውጭ ተብየዎችን በግዛቶቻቸው አሉ በማስባል ማወናበዱና ማዘናጋቱ ለሁለቱም ጥቅም እየሰጣቸው ይገኛል።

ግንቦት ሰባትና ሻቢያ

ግንቦት ሰባት የትጥቅ ትግል ጀመርኩ ካለ ሰባት ዓመታት በላይ ቢሆነውም አንድ መንደር ከወያኔ ነጻ ያላወጣ ወይም የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቆ በመግባት አንድ የወያኔ ጆሮ መቆንጠጥ እንኳ ያልቻለ በቅዠት ዓለም የሚዋትት ድርጅት ነው። በጎረቤት አገር ተረድተው ነጻ የወጡ ወይም የሚፋለሙትን አገዛዝ ወጥረው የያዙ በርካታ ግንባሮች ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ የጎረቤታችን የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጭዎች በዩጋንዳና ኬንያ በመረዳታቸው ምክንያት ተሳክቶላቸው አገራቸውን ነጻ አውጥተዋል። ወያኔና ሻቢያም በሱዳን በመደገፋቸው ያቀዱትን አሳክተዋል። ወያኔና ሻቢያ በመጨረሻ አዲስ አበባ ሲገቡ የሱዳን መንግሥት ታርጋ የተለጠፈባቸው ታንኮችና የጭነት መኪኖች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ይታዩ እንደነበር እናስታውሳለን። በትክክል የሚረዳ የጎረቤት አገር እንዲህ ነው እርዳታውን የሚያሳየው። ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም እንደሚባለው ሻቢያ የኢትዮጵያን ተዋጊዎች ለመርዳት ቢፈልግ ኖሮ እስከ አሁን ድረስ አንድ የተጨበጠ የትጥቅ ትግል የሚያካሂድ ጠንካራ ሰራዊት ማቋቋም ያስችል ነበር።እውነተኛ ድጋፍ ከኤርትራ ቢገኝ ኖሮ ወይም እውነተኛ ተዋጊ ቢኖር ኖሮ ቢያንስ የኤርትራን መሬት በደጀንነት በመጠቀም ሰርጎ ገቦችን አሾልኮ በማስገባትና የሽምቅ ጦርነት በወያኔ ላይ ለማድረግ ይቻል ነበር። የዚህ ዓይነት ሁኔታ ለምሳሌ ከ1968 እስከ 1971 ባሉት ዓመታት “የምዕራብ ሶማሌ ነጻ አውጭ ድርጅት” ይባል የነበረው ድርጅት ከሶማሊያ ግዛት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አቋርጦ በመግባት ጥቃት ይፈጽም ነበር። ይህ ሊሳካለት የቻለው የሲያድ ባሬ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ባለው ጠላትነት ምክንያት “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በማለት የኢትዮጵያን ጠላት የነበረውን የምዕራብ ሶማሌ ተዋጊዎችን በመርዳቱ ምክንያት ነው።

ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ባዶ ጭኽት የሚያሰማንና የህልም እንጀራ የሚቀልበን ግንቦት ሰባት እንደ ካሮት ወደታች የሚያድግ ካልሆነ በስተቀር እስከ አሁን ድረስ አንድም ተጨባጭ ነገር ሲሰራ አልታየም። ወደፊትም ሊሰራ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል ተብሎ አይገመትም። በጣም የሚያሳዝነው ግንቦት ሰባት እውነተኛ ትግል የሚያደርግና ኤርትራ ውስጥ ጠለላና ከለላ የሚያገኙ መስሏቸው ኤርትራ በመሄድ ለመታገል ቆራጥነቱን ያሳዩ ሀቀኛ ኢትዮጵያውያን በሻቢያ እየተለቀሙ ሲገደሉ፣ ደብዛቸው ሲጠፋ፣ሰቆቃ ሲፈጸምባቸው፣ ሲታሰሩና ሲዘረፉ ኖረዋል። ግንቦት ሰባት ለዚህ ወንጀል ተቃውሞ ማሰማትና ተቆርቋሪነት ማሳየት ሲገባው ሻቢያን ላለማስቀየም በማለት ትንፍሽ አላለም። በዚህም መሠረት ግንቦት ሰባት የወያኔና ሻቢያ የኃይል ሚዛን አስጠባቂ በመሆን የማዘናጋትና የማልፈስፈስ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ለመገንዘብ አያዳግትም። በተለይም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለወያኔ ተላልፈው የተሰጡበት እጅግ አጠራጣሪ ሁኔታና ተላልፈው ከተሰጡም በኋላ ከግንቦት ሰባት የተላለፉትን ተአማኒነት የጎደላቸው መግለጫዎች በጥንቃቄ ብንመረምር ግንቦት ሰባት ወያኔን በትጥቅ ትግል ለመጣል ፍላጎቱም ሆነ ዓላማው አለመሆኑንን ለማረጋገጥ አያደግትም።

ማጠቃለያ

ሻቢያ የኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች መጠናከርና ሥልጣን መጨበጥ በጣም የሚያሰጋውና እንቅልፍ የሚነሳው ነገር እንደሆነ ከላይ በዝርዝር ተጠቁሟል። በአንጻሩም የአንድነት ኃይሎች የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕዝቦች መለያየትና የኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆን ያንገበግባቸዋል። ስለሆነም የአንድነት ኃይሎች ሥልጣን ቢጨብጡ የሚያደርጉት ነገር በመጀመሪያ እነዚህን የተበላሹ ነገሮች ማስተካከል ነው። ታዲያ ሻቢያ ምኑ ሞኝ ነው የለመደውንና ባህርዩን የሚያውቀውን ወያኔን በሌላ በአመለካከትና በእምነት በሚቃወመው ኃይል የሚተካው? “ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ቀይር” እንደሚባለው ሻቢያ ምኑ ሞኝ ነው ኮትኩቶ ያሳደገውን ወያኔን በሌላ የሚቀይር? የአርበኞች ግንባር፣ ግንቦት ሰባትና የተለያዩ የኦነግ አንጃዎችና ሌሎችም በሻቢያ እርጥባንና ምጽዋት ወያኔን እንጥላለን ብለው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች እስከዛሬ ድረስ በተግባር በተረጋገጠው መሠረት ያስመዘገቡት ምንም ዓይነት ውጤት ስለሌለና የሻቢያ መሳሪያ በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ እያወናበዱ ስለሆነ ሁላችንንም ኢትዮጵያውያን በቃችሁ ልንላቸው ይገባል።

በቀረበላቸው የተሳሳተ መረጃ ተወናብደው ለአገራችን ለኢትዮጵያ የትጥቅ ትግል ለማድረግ ወደ ኤርትራ የወረዱ አገር ወዳድ ግለሰቦች ሻቢያ አሁንም ጽረ ኢትዮጵያ መሆኑን ተረድተውና ትግሉም መደረግ ያለበት አገር ውስጥ መሆኑን አውቀው፣ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ መውሰድ ይኖርባቸዋል። በወያኔ ላይ የሚደረገው ትግል ወደ አገር መመለስ አለበት። ኤርትራ ውስጥ ነጻ አውጭዎች አሉልን የሚለው ማዘናጊያና ማጃጃያ በአስቸኳይ መቆም አለበት። ኤርትራ ውስጥ በሻቢያ ደብዛቸው የጠፋው ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህና ሌሎችም የት እንዳሉ ማሳወቅ የግንቦት ሰባትና የአርበኞች ግንባር ኃላፊነት ነው።

እጅግ የሚያስተዛዝበው ለታሪክ ፍርድ የሚተወው ጉዳይ አስመራ ድረስ ተጉዘው የኢሳያስ አፈወቂን ጫማ ስመው የተነገራቸውን ውሸት ጠጥተው የመጡ ጋዜጠኞች ኤርትራ ውስጥ በእስር ለሚሰቃዩና ለጠፉ ኢትዮጵያውያን ለይስሙላ ከሚያወሩት በስተቀር ምንም ዓይነት ርህራሄ አለማሳየታቸው ነው። ኢሳያስ አፈወቂን እያደነቁና እያቆላመጡ በአንጻሩ የአንድነት ኃይሎች በአገራችን ጉዳይ የሚሰማንን እንዳንተነፍስ ማጥላላታቸውን ማቆም ይገባቸዋል። ማንም ግለሰብም ሆነ ቡድን አሥመራም ሆነ አቆርዳት ወይም ሰዋ ሄዶ የፈለገውን ማድረግ መብቱ ነው። በአንጻሩም ህዝብም ደግሞ የቀረበለትን መረጃ ትክክለኛነት የመመርመር፣ የመጠየቅ፣ የመቃወምና የማውገዝ መብቱ ሊጠበቅለት ይግባል።