ኦባማ የሚመጣው ለማን ነው? ጌታቸው ሺፈራው

አሜሪካ ከኃይለስላሴ መንግስት ጋር የጠበቀ ግንኙነት የነበራት ቢሆንም ከአሁኑ አንጻር ሲታይ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች አዲስ አበባ ድረስ መጥተው እንዲጠበቅላቸው የሚፈልጉት እንቅልፍ የሚነሳ ስጋት ነበራቸው ለማለት ግን ይከብዳል፡፡ ያም ሆኖ ግን በወቅቱ ለጥቁር ምቹ ባልነበረችው አሜሪካ ለጥቁር ህዝብ ነፃ መውጣት ስትባዝን የነበረችው ኢትዮጵያ መሪን ከዛሬዎቹ ገዥዎች በተሻለ በክብር አሜሪካን እንዲጎበኙ ጋብዛቸዋለች፡፡ ደርግ ወደ ስልጣን ሲመጣ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ኢትዮጵያን የሚጎበኙበት ምክንያት አልነበረም፡፡ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ኢትዮጵያን መጎብኘት የነበረባቸው ባለፉት 24 አመታት ነው፡፡ ራሳቸው በተቋሞቻቸው አግዘው ወደ ስልጣን ያመጡትን ህወሓት/ኢህአዴግ ስራ ያለችውን ኢትዮጵያ ቢጎበኙ ብዙም አይገርምም ነበር፡፡ ሆኖም እነ መለስን ‹‹አዲሶቹ›› እያሉ ሲያንቆለጻጽሱ የነበሩት እነ ክሊንተን እንኳ በህወሓት/ኢህአዴግ ስር ያለችውን ኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሆነው መጎብኘት ያልፈለጉት የራሳቸውን ክብር ዝቅ ስለሚያደርግባቸው ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግም እነሱ ባመኑት መልኩ እንኳ አላገኙትም፡፡ የሰብአዊ መብት፣ ዴሞክራሲና መሰል ቅድመ ሁኔታዎች ጭራሹን ሲሸረሸሩ ከኦባማ አንጻር ሲታይ በጡንቻ የሚያምነው ቡሽ እንኳ በርካታ የአፍሪካ መሪዎች የሚሰባሰቡበት አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ከመምከር የሚፈልጓቸውን መሪዎች ሀገራቸው ድረስ እየሄዱ ማውራትን መርጠዋል፡፡ ሶማሊያ ውስጥ እንዲዘፈቅ የወከሉትን የህወሓት/ኢህአዴግን መሪዎች አሜሪካ ድረስ ጠርተው ከማነጋገር ባለፈ አዲስ አበባ ውስጥ እጃቸውን ሊጨብጧቸው አልፈለጉም፡፡ ይህም የሆነው የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅም ቢሆን አስጠርተው እንጅ የአምባገነኖቹ ቤተ መንግስት ድረስ መምጣት የሚጠይቋቸውን ተቋማት ለገነቡት፣ ሚዲያና ህዝባቸውን ለሚያዳምጡት አሜሪካኖች ክብር የሚቀንስ በመሆኑ ነው፡፡ ግን ደግሞ የግድ ለሀገራቸው ጥቅም አስፈላጊ ሲሆን አሜሪካኖች ሀፍረታቸውን ዋጥ አድርገው ከአምባገነን ጋር ይቆማሉ፡፡
ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑ ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በዋነኛነት ሶስት አይነት አስተያየቶች እየተሰጡ ነው፡፡ አንደኛው የማህረሰብ ክፍል ኦባማ መጣ አልመጣ የሚመጣ ለውጥ የለም የሚል ነው፡፡ በቅርቡ ተደርጎ የነበረው የ‹‹3ኛው ፋይናንስ ለልማት ኮንፈረንስ›› ትራፊክ ያጨናነቀበት ሳይቀር ‹‹እሱ መጣ አልመጣ ምን ለውጥ ይመጣል!›› እያለ ትርፉ የትራፊክ መጨናነቅ ብቻ መሆኑን ታክሲ ውስጥም የሚሰጠውን አስተያየት ሳይቀር ታዝበናል፡፡ ሌላኛው ደግሞ ኦባማ መምጣቱ ለኢህአዴግ እውቅና መስጠት መሆኑን በመግለጽ መምጣቱን የሚቃወም ነው፡፡ ሶስተኛው ደግሞ የኦባማ መምጣት ሀገሪቱ በእድገት ጎዳና መሆኗን የሚያሳይ ብስራት ነው የሚል ነው፡፡ የእኔ ከሶስቱም ይለያል፡፡ ኦባማ ለኢህአዴግ ሲል አልመጣም፣ ኦባማ ኢትዮጵያ በማደጓ ምክንያት አልመጣም፡፡ ኦባማ የሚመጣው በስርዓቱ አፈና ምክንያት ኢትዮጵያ ወደ አደጋ እያመራች በመሆኑ፣ በዚህም የአሜሪካ ጥቅም አደጋ ውስጥ ስለሚገባ ነው፡፡ ኦባማ በመምጣቱ ከተጠቀምንባቸው አወንታዊ፣ ካልተጠቀምንባቸው አሉታዊ ወይንም በዛው የሚረግጡ ጉዳዮች/ጥቅሞች ይኖራሉ፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ነች፡፡ ቻይና ከምዕራባውያን እየነጠቀቻት ያለች ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በህዝብ ቁጥር ሁለተኛ ሀገር ነች፡፡ ኢትዮጵያ የሶማሊያ፣ የሱዳን፣ የደቡብ ሱዳን፣ የኤርትራ፣ በደህንነት በኩል የደካማዋ ኬንያ ጎረቤት ናት፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ባራክ ኦባማ አይነት ጥቁር መሪ ሊኮራባት የምትገባ ታሪካዊም ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ለአሜሪካ በርካታ ምሁራንና የዳያስፖራ ቁጥር ያላት ሀገር ናት፡፡ ምናልባት በመካከለኛው ምስራቅ እስራኤልና ሳውዲ እንዳሉት ሁሉ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ከዛም አለፍ ሲል በአፍሪካ ለአሜሪካ ታሪካዊ የረዥም ጊዜ ወዳጅ ልትሆን የምትችል ሀገርም ናት፡፡ ታዲያ ባለፉት 24 አመታት የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ለምን ወደ ኢትዮጵያ አልመጡም? ያልፈለጉት ስርዓቱን ነው ሀገሪቷን? ለእኔ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎቹን የሚከስባቸው ኒዮሌብራል፣ አሸባሪ፣ የቀለም አብዮተኛ አይነት እነ አሜሪካን ከበስተጀርባ ያስቀመጡ ፍረጃዎች፣ እንዲሁም የአሜሪካ መንግስትና ተቋማት በስርዓቱ ላይ የሚያነሱት የሰብአዊ መብት ክስ በኢህአዴግና በአሜሪካ መካከል ያለውን ቅራኔ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ከኢትዮጵያ ርቀው የቆዩት በኢህአዴግ ምክንያት ለመሆኑ ዋነኛው ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን ስርዓቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ ይለወጣል ብለው ጠብቀውታል፡፡ ሀገሪቱ አደጋ ውስጥ ከመግባቷ በፊትም አስተማማኝና አማራጭ ኃይል ይመጣል ብለው ተስፋ አድርገው ነበር፡፡

አሁን ግን ስርዓቱም መሻሻል አልቻለም፡፡ ከኢትዮጵያ ህዝብ በላይ የራሳቸውን ጥቅም የሚጎዳ አዝማሚያ እየታየ ነው፡፡ ኢህአዴግ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ሲል፣ ከ24 አመት በኋላ የትጥቅ ትግል እንደገና በአዲስ መልክ እንዲያውም ዋና መስሪያ ቤቱን አሜሪካ ባደረገ ድርጅት ሲጀመር ለአሜሪካኖች ትልቅ የማንቂያ ደወል ነው፡፡ በዚህ ሰዓት በኢህአዴግ አምባገነንነት ምክንያት ኢትዮጵያን ማጣት አይፈልጉም፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ እንደ ሶማሊያም እንደ ሱዳንም፣ እንደ ኬንያም ብቻ የምትታይ ሀገር አይደለችም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ችግር ከተፈጠረ አፍሪካ የብጥብጥ ቀጠና እንደሚሆን፣ መካከለኛውን ምስራቅ ከአፍሪካዎቹ ነውጠኞች ጋር የሚያገናኝ የሽብር ቦይ እንደሚከፈት ያውቁታል፡፡
በአሁኑ ወቅት የመን እየተበጣበጠች ነው፡፡ ከየመን ጋር በሰፊ ባህር የምትገናኘውና የበርካታ ሀገራት ሰራዊት ቢላክም ያልተረጋጋችው ሶማሊያ ጋር ትገናኛለች፡፡ ከመካከለኛው ምስራቅም ጭምር የሚመነጨውን የሶማሊያን ችግር በዋነኝነት ትቋቋማለች የምትባለው ኢትዮጵያ ነች፡፡ የመንና ሶማሊያ በፈራረሱበት ኢትዮጵያ ውስጥ ችግር ቢደርስ ይህ ችግር ሙሉ አፍሪካን ያዳርሳል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሶማሊያን ያለውን ችግር የሚመክት ሀገር ስለሌለ ብቻ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ የሶማሊያን ስደተኞች የምትቀበል ሀገር ነች፡፡ በሌላ ጎኗ ደግሞ ደቡብ ሱዳን አለች፡፡ ደቡብ ሱዳን በአንድ በኩል ‹ሎርድ ሪዚስታንስ አርሚ› የሚፈነጭበት ሰሜን ዩጋንዳ፣ በሌላ በኩል ከምትበጣበጠው ኮንጎ በአንድ በኩል ደግሞ ከዳርፉር ጋር ደቡብ ሱዳን ሌላኛዋ የሁከት አገር ማዕከላዊ አፍሪካም ጎረቤት ነች፡፡ ደካማዋ ቻድ የማዕከላዊ አፍሪካም የሱዳንም አጎራባች ስትሆን ይህን መስመር ቦኮሃራም የሚንጣት ናይጀሪያና የሰሜን አፍሪካው የአልቃይዳ ክንፍ መነሃሪያ ለሆኑት ሊቢያና ኒጀር ጋር ትገናኛለች፡ የመንና ሶማሊያ እንዲሁም ደቡብ ሱዳን መካከል ኢትዮጵያ የምትባል ታኮ ከሌለች አልሸባብ እስከ ሊቢያ፣ ቦኮሃራምና የሰሜን አፍሪካ አልቃይዳ እስከ ኪስማዩ ከዛም አልፎ እስከ የመን የሚፈነጩበት መስመር ወለል ብሎ ይከፈታል፡፡ ኢትዮጵያ በአፈናው ምክንያት ችግር ውስጥ ከወደቀች፣ አሸባሪዎች ከየመን ሊቢያ የሚንሸራሸሩበት፣ አፍሪካን ዋና መረማመጃቸው የሚያደርጉበት ክፉ ምልክት እየታየ ነው፡፡ ወቅቱ ደግሞ ኦባማ በየአካባቢው በአሸባሪዎች ጥቅሟ የሚነካባት፣ የዓለም ፖሊስ የሆነችው አሜሪካ ፕሬዝደንት የሆነበት ነው፡፡
ወቅቱ የጣለበት ኃላፊነትና አጣብቂኝ እንዳለ ሆኖ ኦባማ ከሌሎች ፕሬዝደንቶች የሚለየው የቆዩቱ የሚኮፈሱበትን ጉዳይ ሰብሮ ግንኙነት በመጀመር ነው፡፡ ለዚህም ‹‹እኔ ከመወለዴ በፊት የነበረ ጦርነትን ውስጥ ገብቼ መነታረክ አልፈልግም›› ብሎ ግንኙነት የጀመረባት፣ ከ55 አመት በኋላ ኤምባሲ የከፈተባት ኩባ ትልቅ ምሳሌ ነች፡፡ በዚህ ወቅት ግን የኩባን መሪዎች መክሮና ዘክሮ ኩባን ከማራቅ ይልቅ ወደ አሜሪካ እንድትቀርብ የራሱን ጥረት አድርጓል፡፡ ‹‹ብዙ ጊዜ ራሳችንን ከማሳመን ባለፈ ጉዳይ ውስጥ ስናስገባ የሚብሰን መዘዙ ነው›› ነበር ያለው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ሌላ መዘዝ በሚያመጣ ጉዳይ ለስርዓቱ መፍትሄ ከመስጠት ከሰሙ እኔ እግረ መንገዴን ሄጀ ላነጋግራቸው የሚል አቋም እንዲይዝ ተገድዷል፡፡ ግብፅ ውስጥ እንዲያውም ሌሎቹ ‹‹አክራሪ›› የሚሏቸው ባዘጋጁት መድረክ መጥቶ ታሪካዊ ንግግር ሲያደርግ ማስጠንቀቂያም የግንኙነት አረንጓዴ መስመርም እያሳየ ነበር፡፡ ውየስት ባንክን ሲጎበኝ ለአሜሪካ በጎሪጥ ለማትታየው እስራኤልም ለሙስሊሙ ዓለምም መልዕክትም፣ ማስጠንቀቂያም አስተላልፏል፡፡ ከኢራን ጋር ቁጭ ብሎ ተደራድሯል፡፡ እነዚህ አብዛኛዎቹ ሌሎች ያልደፈሯቸው ከገባቸው ግንኙነታቸውን የሚያድሱበት፣ ካልገባቸው ማስጠንቀቂያ የሰጠባቸው ናቸው፡፡ ኢህአዴግም የሚሰጠው የመጨረሻ እድል ወይንም ማስጠንቀቂያ ነው፡፡
ኦባማ ካለፉት የአሜሪካ ፕሬዝደንቶችም፣ በዓለም በወቅቱ ካሉት ፕሬዝደንቶችም በላይ በርካታ ሀገራትን የጎበኘ ፕሬዝደንት እንደሆነ ይነገራል፡፡ የአሜሪካ መከላከያ ሰራዊት ያለባቸው ኢራቅና አፍጋኒስታን ከሁለት ጊዜ በላይ ተመላልሷል፡፡ ወደ እነዚህ አገራት ሲሄድ በሌላ ስብሰባ ምክንያት ሳይሆን በቀጥታ ነው፡፡ በእርግጠኝነት ኢትዮጵያ ሶማሊያ ውስጥ አሜሪካን ወክላ ባትገኝና የአሜሪካ ሰራዊት ሶማሊያ ውስጥ ቢሆን ኖሮ ኦባማ ከአንዴም ሁለቴ ወደ ሞቃዲሾ ማቅናቱ የማይቀር ነበር፡፡ አሁን ባለው አዎንታዊ ሁኔታ ግን ሶማሊያ ብቻ ሳትሆን ኢትዮጵያም በህወሓት/ኢህአዴግ አፋኝነት ምክንያት የባሰ ችግር ውስጥ እየገባች በመሆኑ የኦባማ አስተዳደር ገንዘብ ደጉሟቸው ሪፖርት የሚያወጡት ተቋማት በየጊዜው እያወጡት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለመውደቅ ስጋት ላይ ያለች ሀገር ነች፡፡
በመሆኑም ይች አፍሪካ የቀጠና ዞን እንዳይሆን ታኮ የሆነችው ሀገርን ሳትፈርስ ደርሰው፣ አሜሪካ ውስጥ ጠርተው፣ መልዕክተኛ ልከው ያስመከሯቸውን የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች ኢትዮጵያ ድረስ መጥተው ቢገባቸው መምከር ነበረባቸው፡፡ ይህን ሲያደርጉም በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ መምጣትን አልፈለጉም፡፡ የሚያዙት አምባገነን ስርዓት ጋር ለመጨባበጥ ምክንያት አስፈልጓቸዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ! ያውም ኬንያ ውስጥ ለሌላ ስብሰባ ከመጡ በኋላ እግረ መንገዳቸውን፡፡ ኦባማ በቀጥታ ኢትዮጵያን ቢጎበኝ እንኳ የሚገርም አይደለም፡፡ ኦባማ ጆርዳን፣ ትሪንዳድና ቴቬጎ፣ ጃማይካ፣ ኮስታሪካ፣ ታንዛኒያን እና ሴኔጋልን የመሳሰሉ ትንንሽና ለሀገሪቱ ጥቅም ከኢትዮጵያ አንጻር ይህን ያህል ጥቅም አላቸው የማይባሉ ሀገራትን ጎብኝቷል፡፡ ከእነዚህ መካከል ከአሜሪካ ጎን የምትገኘውን ጃማይካን ጨምሮ አብዛኛዎቹን ሀገራት ሲጎበኝ ስልጣን ላይ ያለ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ነው፡፡ ባለፉት አመታት ኢህአዴግ ጋር እጅ መጨባበጥ አሳፋሪ ሆኖ ሌሎች ባለመምጣታቸው፣ አሁን ግን የማይታለፍ ሁኔታ ላይ በመደረሱ ኦባማ ኢትዮጵያን የጎበኘ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ሆነ፡፡ ‹‹በእድገቱ ምክንያት ነው›› የሚባለው ግን ውሃ የማይቋጥር ምክንያት ነው፡፡ አብዛኛዎቹን ትንንሽና የኢትዮጵያን ያህል በርካታ መሪዎችን በአንድ ጊዜ የማይገኙባቸው፣ የኢትዮጵያን ያህል ጥቅማቸውን የማያስጠብቁ ሀገራትን የጎበኘው በመጀመሪያው የስልጣን ዘመኑ ሆኖ ኢትዮጵያን ከሁለተኛ ዙር ስልጣኑ በኋላ (ያውም ሊያልቅ ሲል በጥድፊያ) ለመጨረሻ ጊዜ መጎብኘቱ አሜሪካኖች ይችን ማጣት የማይፈልጓትን ሀገር ለመጎብኘት የከለከሏቸው በርካታ ምክንያቶች እንደነበሩ በጉልህ የሚያሳይ ነው፡፡

ኦባማ ለኢኮኖሚ፣ ለፖለቲካዊና ለደህንነት ጉዳይ ሲባል ኢህአዴግ የሚገዛትን ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ኢህአዴግን የምታግዘውን፣ ከምዕራባውያን እንዲያፈነግጥ አይዞህ የምትለውን ቻይናንም ጎብኝቷል፡፡ በአምባገነንነት ከሆነ ሳውዲ የሚባል ጋዜጠኛና ሌሎች ጥያቄ የሚያነሱትን በጅራፍ የሚገርፍ፣ አሰቃቂ ግድያ የሚፈፅም ሀገርንም በተደጋጋሚና በቀጥታ ጎብኝቷል፡፡
በርማ ወይንማ ማይናማር በዓለም የሰብአዊ መብት በመጣስ ከሚታወቁት አስር አገራት መካከል አንዷ ናት፡፡ በወታደራዊ አገዛዝ ስር የሆነችው በርማ ኢህአዴግ ውስጥ ካለችው ኢትዮጵያ ቢበዛ እንጅ የማያንስ በደል የሚፈፀምባት ሀገር ናት፡፡ በርማ ድረስ ሄዶ ከገዥዎቹ ጋር መጨባበጥም ኢትዮጵያ ውስጥ መጥቶ ከኢህአዴግ መሪዎች ጋር የመጨበጥን ያህል ለአሜሪካውያን የሚያሳፍር፣ የሚያስተች ነው፡፡ የበርማ መንግስት ከዜጎች መሬት በመንጠቅ ለውጭ ባለሀብቶች ይሰጣል፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የመከላከያ ሹሞችና ሌሎችም ባለጊዜዎች ነዋሪዎችን ከቤትና ቀያቸው በማፈናቀል የራሳቸውን ንብረት የሚያካብቱባት ሀገር መሆኗንም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሪፖርቶች ያመላክታሉ፡፡ ስርዓቱን የሚተቹ በገፍ የሚታሰሩበት አገርም ነው፡፡ ዘመናዊ ባርነትም በስፋት የሚታይበት ሀገር ነው፡፡ ህፃናትን ለቁፋሮ ብቻ ሳይሆን ለመከላከያም ይለምላል፡፡ ከ70 ሺህ በላይ የሰራዊቱ አባላት ከ15 አመት ጀምሮ እስከ 18 አመት እድሜ ያላቸው ናቸው፡፡ በየእስር ቤቱ እስረኞች በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገረፉበት ሀገርም ነው በርማ፡፡ የዘር ማፅዳት በተለይም ሙስሊሞች በአደባባይ የሚታረዱበት ሀገር ነው በርማ፡፡ መከላከያው እንደ ፈቀደ ሰው የሚገድልበት ሀገር ነው በርማ፡፡ ይህን ሀገር ግን ኦባማ ለሁለት ጊዜ ያህል ጎብኝቷል፡፡
ምንም እንኳ የበርማ ወታደራዊ አገዛዝ በሙስናም በምንም ብሎ የውጭ ባለሀብቶችን እየጠራ ሰፋፊ መሬትን በመስጠት፣ ግድቦችን በመስራት ልማት እያፋጠንኩ ነው ቢልም ኦባማ ግን ሁለት ጊዜም መሪዎቹን ያገኘው ለመምከርና ለመውቀስ ነው፡፡ ሳን ሱ ኪ የተባለችውን የተቃዋሚ መሪ ጨምሮ በርካቶችን በማሰቃየት ሀገሪቱን ወደ ብጥብጥ ሊያመራት ነው ብለው ስለፈሩ እዛው ቦታው ድረስ ሄደው ምክር ለግሰዋል፡፡ ይህ የሆነው ከእጃችን ትወጣለች ወዳሏት ኢትዮጵያ ከመውጣቱ ከሶስት አመት በፊት ነው፡፡
የአሜሪካ መንግስት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣበት ዋነኛ ምክንያት የደህንነት እንደሆነ ገልጾአል፡፡ ከዚህም ባሻገር ኢህአዴግ ያለ መረጃ ያሰራቸውን ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያንና ተማሪዎች በአጋጣሚ መፍታቱ ኦባማ የኢኮኖሚ እድገቱ አማልሎት ሳይሆን ኢህአዴግ እየሄደበት ያለው መንገድ የተሳሳተ በመሆኑ የፖለቲካ ማሻሻያዎች እንዲያደርግ ለመገሰፅ እንደሚመጣ ምስክር ሆኗል፡፡ ኦባማ የሚያዘውንና ይፈርሳል ብሎ የሚፈራውን ሀገር ብቻ ሳይሆን አሜሪካም ለውጦችን እንድታደርግ ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ አውሮፓ ውስጥና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ሚስጥራዊ እስር ቤቶችን እንዲዘጉ አድርጓል፡፡ የቀደሙት መሪዎች የማይደፍሩት የጓንታናሞ ጉዳይ የተደፈረው በኦባማ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ በምትባለው አሜሪካ ለብሄራዊ ጥቅሟ ስትል በሌሎች ላይ የምታደርገውን እንድትቀንስ እየሰሩ ያለው ኦባማ ታዛዥ መንግስታት ለስልጣን ሲሉ በህዝባቸው ላይ የሚፈፅሙትን እንዲቀንሱ እየወተወተ ነው፡፡ የሀገራቱ የፖለቲካ ቡድኖችና ሌሎችም የለውጥ አካላት የበኩላቸውን ሲያደርጉ ለአሜሪካ ምቹ ይሆናል፡፡ በእርግጠኝነት ለኢትዮጵያውያን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ የኦባማ መምጣት ሲሰማ ጥቂቶችን የፈታው ኢህአዴግ ሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ አሁን ካለው የተሻለ እንቅስቃሴ ቢኖር ይበልጡን ተገዶ ሌሎች ማሻሻያዎችን የማያደርግበት ምክንያት የለም፡፡
ያም ሆነ ይህ ኦባማ ላክ ሲባል ጦር የሚልከውን ኢህአዴግን ብሎ ቢመጣ ኖሮ ከ9 አመት በፊትም በመጣ ነበር፡፡ ጋና፣ ሴኔጋል፣ ኤልሳቫዶር፣ ጃማይካ ከመሄዱ በፊት ደግሞ ደጋግሞ ኢትዮጵያ በጎበኘ ነበር፡፡ የቀድሞዎቹ ፕሬዝደንቶችም በመጡ ነበር፡፡ እንዲያውም በዚህ በፈራረሰ ቀጠና መሪዎችን ሰብሰብ ብለው ወደ ሚያገኙባት ኢትዮጵያ ሌሎች ፕሬዝደንቶችም ያልመጡት ኢህአዴግ መልዕክት ተልኮበት፣ አሊያምና ቶሎ ተብሎ ከመምከር የበለጠ ክብር የማይሰጠው ሆኖ ስላገኙት ነው፡፡ በዚህም ከኢህአዴግ ጋር መቆም ስላፈሩ ብቻ ከሚፈልጓት ኢትዮጵያ ርቀዋል፡፡ አሁን ደግሞ የሚያልፈው ኢህአዴግ የማያልፍ ዕዳ እንደሚያመጣ፣ መራቁም መፍትሄ እንደማይሆን ተገንዝበዋል፡፡ ለመምከርና ለማስጠንቀቅም ወስነዋል፡፡
የአካባቢው ሁኔታ፣ የኢህአዴግ የቀልድ ምርጫ በመልዕክተኛም የሚያልቅ አልሆነም፡፡ ጭራሹን ኢትዮጵያ አደጋ ላይ መሆኗን የሚያመላክት እንጂ! በመሆኑም ሚዲያዎቻቸው፣ ተቋሞቻቸው እየተቿቸውም ቢሆን ኢትዮጵያ አደጋ ውስጥ ወድቃ ጥቅማቸው እንዳይነካ ስርዓቱን መክረው መሄድ አለባቸው፡፡ ለአሜሪካ ሲባል ኢትዮጵያን ከውድቀት መታደግ አለባቸው፡፡ ስርዓቱ ከሰማ! ተቃዋሚዎችም ይህን አጋጣሚ ከተጠቀሙበት! ተቃዋሚዎች ካልተጠቀሙበት ደግሞ ስርዓቱ ተመክሮ ሰማም አልሰማም የኦባማ መምጣት እውቅና ይሆንለታል፡፡ ጥቅሙም ጉዳቱም ማን በምን መልኩ ይጠቀምበታል በሚለው ይወስነዋል፡፡

የተስፈኞች የሰሞኑ ጫጫታና እንደምታው (ዶ/ር አሸናፊ ጐሳዬ)

ዶ/ር አሸናፊ ጐሳዬ

የአገራችንን ፖለቲካ በቅርብ የምትከታተሉ ሰሞኑን ለነጻነት የሚደረገውን ጉዞ ለማዳከም የተከፈተውን ዘመቻ እና የዘንድሮውን አገር አቀፍ የምርጫ ውጤት ተከትሎ ብዙ አዳዲስ የሚመስሉ ነገር ግን የጠበቅናቸው ክስተቶች እንዳስተዋላችሁ እገምታለሁ። ከእነዚህ ውስጥ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፦

1. ወያኔ/ኢሕአዴግ 100% አሸንፌአለሁ በማለት ከእንግዲህ በምርጫ የሚመጣ የፖለቲካ ለውጥም ሆነ ለይስሙላ የነበረው የመድብለ ፓርቲ ስርአት እንዳበቃለት አሁንም በድጋሚ ማረጋገጡ፤

2. በሰላማዊ ትግል ወያኔ/ኢሕአዴግን አሸንፈን የስርአት ለውጥ እናመጣለን ብለው በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች የምርጫውን ኢፍትሀዊነት በየመግለጫቸው ከማውገዝ ያለፈ የተሰረቀባቸውን የህዝብ ድምፅ ለማስመለስም ሆነ እጩዎችቸውንና አባሎቻቸውን በጠራራ ፀሀይ የገደሉ በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ህዝብ ቀስቅሰው አደባባይ ውጥተው ድምጻቸውን እንኳን ማሰማት ሳይችሉ መቅረታቸው፤

3. ወያኔ/ኢሕአዴግን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ማስወገድ እንደማይቻል ካወቅን ቆይተናል የሚሉ ኃይሎች ደግሞ ወያኔን በሚገባው ቋንቋ ለማነጋገርና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ዝግጅታችንን ጨርሰን የነጻነት ጉዞ ፊሽካ ነፍተን ጀምረናልና ነጻነት ናፋቂዎች ሁሉ ተቀላቀሉን ሲሉ ማውጃቸው እና

4. አላማው ከላይ በቁጥር ሁለትና ሶስት ከተጠቀሱት ኃይሎች የተለየ ወገን ደግሞ በቅርቡ የትጥቅ ትግሉን አስመልክቶ የከፈተው የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት የሳበና ህዝብን እያነጋገረ መሆኑ ናቸው። በዚህ አጭር ጽሁፍ እነዚህን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በጥልቀት ለመዳሰስ ስለማይቻልና ምናልባትም ብዙዎች በተራ ቁጥር አራት የጠቀስኩትን ኃይል ማንነትና ድብቅ አላማ እንዲሁም በቅርቡ የትጥቅ ትግሉን አስመልክቶ የከፈተውን የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በተመለከተ ጥያቄዎች ሊኖራቸው ስለሚችል የታዘብኩትን ባካፍልና በዚህ ጉዳይ ላይ በግልጽ መወያየት ብንጀምር ለነጻነት የሚደረገውን ትግል ያግዛል ብዬ ስላመንኩ ነው።

ባለፉት አምስት ዓመታት የአገራችን የፖለቲካ ኃይሎች ለምን በሚግባቡባቸው ጉዳዮች ተባብረው በመስራት ውጤታማ ለመሆን አልቻሉም ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ብዙ ጊዜዬን አጥፍቻለሁ። ችግሩ የርዕዮተ-ዓለም ልዩነት፣ በዘር በቋንቋ መከፋፈላችን፣ ታሪካችን ጥሎብን ያለፈው ጠባሳ ወይስ የወያኔ ጥንካሬ ይሆን ለሚለው ጥያቄዬ መልስ ለማግኘት ብዙ ሞክሬአለሁ።

የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ሳልሆን እዚህ ሲያትል ውስጥ ከሚገኙ አክቲቪስቶች ጋር ሆነን በፈጠርነው ሕዝባዊ ፎረም አማካይነት በብዙ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ተካፍያልሁ መርቻለሁ፣ ከአብዛኛዎቹ የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች፣ የሲቪክ ማህበራት ሀላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ለመወያየትም እድሉን አግኝቻለሁ። የተቻለኝን ያህል ስለ አገሬ ፖለቲካ እከታተላለሁ አነባለሁ። በዚህ ጽሁፌ የማቀርበው ትዝብት ከዚህ ሁሉ የመነጨ ነው።

ትዝብት አንድ

ከላይ በተራ ቁጥር አራት የጠቀስኩት ኃይል በአንድ ድርጅት ጥላ ስር የተሰባሰበ ሳይሆን በሁሉም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ያለ ነው። ሆኖም ይህ ኃይል ድብቅ ዓላማ አለው። ብዙ ጊዜ የዚህ ዓላማ አራማጆች የተቀላቀሉት ድርጅት የቆሙለትን አላማ የማያሳካ መስሎ በታያቸው ቁጥር እና አመራሩን እነሱ ካልተቆጣጠሩት የሚወስዱት እርምጃ ሁሌም አፍራሽና አደገኛ ነው። አንድም ድረጅቱን አዳክመው ያፈርሱታል አልያም መሰሎቻቸውን ይዘው በመውጣት አላማቸውን ለማሳካት ይሞክራሉ። ቅንጅትን ጨምሮ ብዙ ተስፋ የተጣለባቸው ድርጅቶች ለውድቀታቸው ምክንያቶች ከወ ያኔ ይልቅ እነዚህ ኃይሎች መሆናቸው ቢታወቅም ይህን በይፋ ስላልተነጋገርንበትና መፍትሄ በጊዜ ስላልሰጠነው ደግመን ደጋግመን እዛው ወጥመድ ውስጥ ስንወድቅ እንገኛለን። መቼ ይሆን “ዓላማችሁ ገብቶናል በቃችሁ” የምንላቸው?

ትዝብት ሁለት

የዚህ ዓላማ አራማጆች ከማንም በላይ የወያኔ ጠላት ናቸው። ብዙ ጊዜ የነዚህን አፍራሽ ኃይሎች ድርጊት ያስተዋሉ ወገኖች፣ ወያኔ ወደ ተቃዋሚ ድርጅቶች አስርጎ ያስገባቸው ናቸው ብለው iske meterater yigersalu ይጠራጠራሉ። ጥርጣሬአቸው እውነት ቢመስልም ሀቁ ግን ሌላ ነው። እንዲያውም ወያኔንና የትግራይን ህዝብ መለየት እስከሚያቅታቸው ድረስ የወያኔን አምባገነንነት፣ ዘረኝነትና አድሎአዊ አገዛዝ ለማጋለጥ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ወያኔን ለመቃወም በተጠሩ ዝግጅቶች ሁሉ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ሲሆኑ ገንዘባቸውንና ጊዜአቸውን ለመሰዋትም ወደኋላ አይሉም።

ትዝብት ሶስት

እነዚህ ኃይሎች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነትና ሉአላዊነት መቆማቸው ምንም ጥርጥር የለውም። ችግሩ ሌሎችም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ከነሱ ባላነሰ እንደሚወዱ መረዳት አለመቻላቸውና በተለይ የብሄር ጥያቄ የሚያነሱና በዚያ መሰረት የተደራጁ ወገኖች ጋር ተቀራርቦ መስራት እንዳይቻል ዋነኛ እንቅፋት ሆነው መቆየታቸው ነው። በነሱ እምነት በአገራችን የመደብ እንጂ የብሄር ጭቆና መቼም ኖሮ አያውቅም። የኢትዮጵያን አንድነት ለማምጣት በተደረጉ ጦርነቶች ወገኖቻችን አልቀዋል፣ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ በባርነት እንዲያገለግሉ ሆነዋል፣ ንብረታቸው ወድሟል ወይም ተወርሷል፣ ስለሆነም ወደድንም ጠላንም እንደምንኮራባቸው ታሪኮች ሁሉ ይህም ያገራችን ታሪክ ነውና ተመዝግቦ ለትውልድ ይተላለፍ የሚሉትን ወገኖች በኢትዮጵያ ጠላትነት ለመፈረጅ ለአፍታም አያቅማሙም።

ትዝብት አራት

የዚህ ዓላማ አራማጆች የትግል ስልት ምርጫ የላቸውም። ወያኔ የሚወድቀው በምርጫ፣ በህዝብ አመጽ ወይም በትጥቅ ትግል ቢሆን ግድ የላቸውም። ወያኔን የሚጥለው ኃይል ከኬንያ፣ ከሱዳን፣ ከሱማሌ ወይም ከኤርትራ ቢነሳ ጉዳያቸው አይደለም። ዋንው ቁም ነገር ወያኔ ወድቆ ያ በሚስጥር የያዙት ዓላማቸው መሳካቱ ብቻ ነው። ታዲያ ሰሞኑን ከኤርትራ ተነስተን ተከዜን አቋርጠን አገራችንና ህዝባችንን ከወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ነጻ የማውጣት ጉዞአችንን ጀምረናል በሚሉት ኃይሎችና በህዝብ ተሳትፎ የቆመውንና አማራጭ የመረጃ ምንጭ የሆነው ሚዲያ ላይ ኃይለኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ የከፈቱት ለምንድነው? ከተወሰነው የአገራችን ክፍል ወጣቶች መጥተው እነዚህን የነጻነት ታጋዮች እንድይቀላቀሉ የሚማጸኑትስ ለምን ይሆን?

ትዝብት አምስት

እኔን ጨምሮ ብዙዎች ተመልሰን ወደ ጦርነት መግባታችንና ወንድማማቾች ሊገዳደሉ መሆኑን ስናስብ እናዝናለን። ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ስለማንችል ስጋታችንም በዛው ልክ ከፍተኛ ነው። ነገር ግን የሰላሙ ሁሉ በር ተዘግቶ ወደዚህ አማራጭ ተገደን እየገባን እንደሆነም እንረዳለን፣ ህይወታቸውን ለአገራችን ነጻነት ለመስጠት የቆረጡትን

ጀግኖቻችንን እናከብራለን መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማቸውም እንመኛለን። በተቃራኒው እኔ እንደምገምተው አፍራሽ ኃይሎቹ ይኸ ሁሉ ጫጫታ የሚያበዙትና አቧራ የሚያስነሱት ይህ የነጻነት ኃይል ከተሳካለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የቆሙለትን አላማ ገድሎ እንደሚቀብረው ስለሚያውቁ ነው። የነጻነቱ ኃይል በኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ አንዳርጋቸው ጽጌ ራዕይ የታነጸ፣ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ወጣቶች የተሰባሰቡበት እና ሰብአዊ መብቶች የሚከበሩባት፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ በእኩልነት ላይ የተመሰረተች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መመስረት እንደሚፈልግም ጠንቅቀው ይረዳሉ።

ውድ አንባቢ

እኔ እስከሚገባኝ ድረስ እነዚህ ኃይሎች ሁለት ገጽታ አላቸው። የመጀመሪያዎቹ ብዙ ተከታይ ያላቸው ሲሆኑ ዋና ዓላማቸው ያለውን የአንድ ብሄር የበላይነትን አስወግዶ በሌላ መተካት ነው። ይህን አላማቸውን ይፋ አውጥተው በዚያ ዙሪያ ተደራጅተው መታገል እንደማያዋጣቸው በሚገባ ስለሚረዱ የተለያዩ ጭንብሎችን አጥልቀው አፍራሽ ተልኮአቸውን ሲፈጽሙ ይስተዋላሉ። ሁለተኞቹ ደግሞ ዓለም የምትሽከረከረው በእነሱ ዙሪያ ብቻ የሚመስላቸው ግለሰቦች ሲሆኑ እነሱ ያልመሩት ድርጅት ወይም ትግል ውጤታማ ሲሆን ማየት ሞታቸው ስለሆነ ያንን ለማጨናገፍ የማይገቡበት የለም።

እነዚህ ኃይሎች ናቸው እንግዲህ ግንባር ፈጥረው የነጻነት ጉዞውን ለማደናቀፍ ሌት ከቀን የሚሰሩት። ለዚህም ነው እንግዲህ በቅርቡ በነጻነት ታጋዮች እቅስቃሴ ላይ ተልካሻ ምክንያቶቻቸውን በመደርደርና የአዞ እንባቸውን በመርጨት ነጻነት ናፋቂው ህዝብ በጥርጣሬ እንዲመለከተው ለማድረግ የሚሞክሩትና በሁላችንም ጥረት በየጊዜው እየጠነከረ የመጣውን የመረጃ ምንጫችንን ጥላሸት በመቀባት ለማጥፋት ከወያኔ ባልተናነሰ ጦርነት የከፈቱበት።

በግልጽ ተነጋግረን እነዚህ አፍራሽ ኃይሎች ያጠለቋቸውን ጭንብሎች እስወልቀን ካላጋለጥናቸው አንድም አፍራሽ ተልእኮአቸውን እንዲቀጥሉ ፈቅደን የወያኔን ዘላለማዊነት እናረጋግጣለን አለያም ለአገር ከፋፋዮችና ገንጣዮች መንገዱን ከፍተን ቁራሽ ቁራሻችንን ይዘን እንበታተናለን።

ከደርግ የባሰ ግፍ በጎንደር

– የሚሊዮኖች ድምጽ

ወያኔ/ኢሕአዴግ “ብሶት ነው የወለደኝ” በሚል ደርግን በሚዋጋበት ጊዜ፣ መንገድ አሳልፎ ወደ መሃል አገር እንዲገባ ያደረገው የጎንደር ሕዝብ ነበር። በመላኩ ተፈራና በደርግ መከራን ያየና በመከራ የተማረረ ህዝብ፣ የተሻለ ሊመጣ ይችላል በሚል ነበር ወያኔን አሳልፎ ያስገባው።
ሆኖም ጎንደሬው ከደርግ የባሰ ግፍና መከራ እየደረሰበት ነው። ደርግ ያላደረገው በደል ህዝቡ እየተፈጸመበት ነው። ገበሬው ከምርታማ የጎንደር መሬት በኃይል እየተፈናቀለ ፣ ለአገዛዙ ቅርበት ላላቸው ኢንቨርስትሮች መሬቱ እየሰጠበት ነው። እሰ ሰሊጥ የመሳሰሉት የሚያበቅለው ለምለሙ መሬት በኢንቨርስተሮች ሕግ ወጥና ጸረ-ሕዝብ በሆነ መንገድ እየተወረረ ነው። ይሄን አይነት ዜጎችን ማፈናቀል ደርግ እንኳን ያልፈጸመው ግፍ ነው።
በምእራብ ወያኔ ገበሬዎችን ቀምቶ የጎንደርን መሬት ለሱዳን አሳልፎ እየሰጠ ነው። ይሄንን በደርግ ጊዜ ያልታየ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥም መቆም ሳይሆን አገርን መሸጥ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
Gonder
ሕዝቡ ለመብቱ፣ ለክብሩ፣ ለነጻነቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ ሲያነሳ ደግሞ እየተደገደል፣ እየታሰረ፣ ክፍተኛ እንግክትና መከራ እየደረሰበት ነው። በኢትዮጵያ በሰለጠነ መልኩ በሰላም ለዉጥ እንዲመጣ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጋዮች ብዙዎቹ ሲሰደዱ፣ ብዙዎቹ ወህኒ ወርደዋል። በአንድነት ፓርቲ ሥር በጎንደር ክፍል ሃግር ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ጀግና ወገኖቻችን መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
1. ኣንጋው ተገኝ (ሰሜን ጎንደር)
2. አባይ ዘዉዱ (አብርሃ ጅራ ጎንደር)
3. እንግዳው ዋኘው (አብርሃ ጅራ ጎንደር)
4. በላይነህ ሲሳይ (መተማ ጎንደር
5. አለባቸው ማሞ (መተማ ጎንደር)
6. አለበል ዘለቃ ሃይማኖት አየና ( ውሮታው፣ ደቡብ ጎንደር)
7. ጸጋዬ ገበይየሁ (አርማጭሆ)
8. መምህርት ግዛው ( ሰሜን ጎንደር)
9. አውቀ ብርሃኑ (ጎንደር)
10. ማሩ አሻግሬ ( የአርማጭሆ ተወላጅ፣ የዞኑ የአንድነት አመራር – ቀይ የለበሰው))
11. አለላቸው አታለለኝ ( የሰሜን ጎንደር አንድነት ሰብሳቢ)
12. አስቴር ስዩም ( በጎንደር የምእራብ አርማጮሆ የአንድነት አመራር)

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45044#sthash.Cbh6tiAY.dpuf

የኢትዮጵያ ርዕዮት ተናገረች

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

አይበገሬዋ ጀግናዋ ርዕዮት!

በንጹሀን ዜጎች ላይ ስቃይን በመፈጸም ከሚታወቀውና ከአዲስ አበባ ከተማ እምብርት በስተደቡብ ምስራቅ ተንጣሎ ከሚገኘው እና በተለምዶ ቃሊቲ እየተባለ ከሚጠራው የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት (የኢትዮጵያ “ሮቤን ደሴት” ማለትም ነልሶን ማንደላ የታሰሩበት) ባልተጠበቀ ጊዜ የተለቀቀችው ጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ ከማጎሪያው እስር ቤት በወጣች በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ቃለ መጠይቅ ሰጠች፡፡

reyot
ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ የሆነች ኢትዮጵያን እስከማይ ድረስ ትግሌን በተጠናከረ መልኩ እቀጥላለሁ በማለት የዓላማ ጽናቷን በድጋሜ አረጋግጣለች፡፡

ርዕዮት በአምባገነኑ ገዥ አካል የ14 ዓመታት እስር ተበይኖባት ይህ እስር እንደገና ወደ 5 ዓመታት ከተቀየረ በኋላ 4 ዓመታት ከ17 ቀናት (1480 ቀናትን) በእስር ቤት አሳልፋለች፡፡

አሁን በህይወት በሌለው በመለስ ዜናዊ እና በእርሱ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) የጸረ ሽብር ሕግ እየተባለ በሚጠራው ሰላማዊ ዜጎችን የማጥቂያ መሳሪያ የፈጠራ እና የሸፍጥ ክስ ተመስርቶባት ነበር ወደ ዘብጥያ የተወረወረችው፡፡

ታላቁ መሪ ኔልሰን ማንዴላ ለዘረኛው የጥቂት ነጮች ፈለጭ ቆራጭ አምባገነን ስርዓት ጭቆና አራማጆች እንዲህ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር፣ “በማዘግየት በኩል ውጤታማ ልትሆኑ ትችላላችሁ፣ ሆኖም ግን ደቡብ አፍሪካ ወደ ዴሞክራሲ የምታደርገውን ሽግግር በምንም ዓይነት መልኩ በፍጹም ልታስቀሩት አትችሉም፡፡“

የርዕዮት ዋናው መልዕክት ማጠንጠኛውም ይኸው በታላቁ መሪ በኔልሰን ማንዴላ የተነገረው የአፓርተይድ ዓይነት ወሮበላ የዘራፊ አምባገነን ቡድን ስብስብ ለሆነው ለወያኔ ትክክለኛ የሆነ ገላጭ ድርጊት ነው፡፡ “ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡” ነው ያለችው፡፡

ትግሉ ይቀጥላል!

ማንዴላ ከዚህ በተጨማሪም እንዲህ ብለው ነበር፣ “እስር ቤት እራሱ ትዕግስትን እና ጽናትን የሚያላብስ ተዝቆ የማያልቅ ትምህርት የሚሰጥ ተቋም ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የአንድን ሰው የአድራጊነት እና የመፈጸም ችሎታ የሚመዝን ፈተና ነው፡፡“

ርዕዮት እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015 ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመውጣት በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ መስፈን ያላትን ለድርድር የማይቀርበውን ቁርጠኛ የሆነውን የዓላማ ጽናቷን በተግባር አረጋግጣለች፡፡ ይህንን ያደረግችው ግን እንዲሁ ከምንም ሳይሆን ከፍተኛ የሆነ ዋጋ ከፍላ ነው፡፡

ለአራት ዓመታት እና ለ17 ቀናት ርዕዮት በመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በየዕለቱ ውርደት፣ ለብቻ ተነጥሎ መታሰር፣ ዝቅተኛ አድርጎ የመመልከት እና ከሰብአዊነት የወረደ አስቀያሚ ድርጊት ይፈጸምባት ነበር፡፡

ሆኖም ግን ጀግናዋ ርዕዮት ሁሉንም ነገር በጽናት ተቋቁማዋለች፡፡

ለአራት ዓመታት እና ለ17 ቀናት ርዕዮት በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት የበቀል እና የሰይጣናዊ ጥላቻ መፈጸሚያ ከርስ ውስጥ ምርኮኛ ሆና ቆይታለች፡፡

በማጎሪያው እስር ቤት ውስጥ እጅግ በጣም አስቀያሚ የሆነውን የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ እና ከህግ አግባብ ውጭ በሆነው አያያዝ የሚፈጸምባትን ስቃይ እየገለጸች ድምጿን ከፍ አድርጋ ስታሰማ ቆይታለች፡፡

ታጋሽ ሆናም በጽናት ቆይታለች፡፡

ለአራት ዓመታት እና ለ17 ቀናት ርዕዮት በመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ ጭንቅላቷ እየደማ ሆኖም ግን ለአንዲት ቅንጣት ሰከንድ እንኳ ለአምባገነኖች ሳታጎበድድ በጽናት ግዳጇን የተወጣች ጀግኒት ናት፡፡

ርዕዮት እንደ አረብ ብረት እየጠነከረች የመጣች ጀግኒት ናት!!!

ርዕዮት በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ለዓመታት ስቃይ እና ግፍ ስትቀበል ቆይታለች፡፡ ሆኖም ግን ምንም ዓይነት ፍርሀት ሳይጎበኛት በጽናት ቆይታለች፡፡

ጀግኒቱ ምንም ዓይነት ፍርኃት የለባትም ምክንያቱም ርዕዮት የዕጣ ፈንታዋ እመቤት ባለቤት እና የነብሷ መርከብ ካፒቴን ሌላ ማንም ወሮበላ ዘራፊ ሳይሆን እራሷ ናትና፡፡

ታዋቂው ገጣሚ ዊሊያም ኢርነስት ሄንለይ ከበርካታ ዓመታት በፊት “የማይበገሩ ጀግኖች” በሚል ርዕስ እንዲህ የሚሉ የግጥም ስንኞችን የቋጠሩት ለካስ ለእነ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አብርሃ ደስታ፣ ለዞን 9 ጦማሪያን እና እንደ እነርሱ ላሉት ለሌሎች ጀግና የፖለቲካ እስረኞች ኖሯል፡

ጋርዶኝ ከነበረው ድቅድቁ ጨለማ፣
ጥልቀትን ከያዘው ከጉድጓዱ ወማ፣
ጥቁር ከለበሰው የመሬት ውስጥ ካስማ፣
አሻግሮ ከያዘው የምድር ላይ ማማ፡፡

ገብቸ በመሀል ሳንድዊች ተደርጌ፣
ባልፈጸምኩት ጥፋት ተጥዬ ከግርጌ፣
ሀበሳ ግፍ አየሁ ከጨቋኝ በርግጌ፡፡

እናም ፈጣሪዬን አምላኬን ላመስግን፣
ለመንፈሴ ጽናት ለሰጠኝ ብርታቱን፣
ከወገኔ ፍቅር እንዳይ በረከቱን፣
ግፍን ለማስወገድ ለመስበር መርገምቱን፡፡

በግፈኞች መዳፍ ስደቆስ ታፍኘ፣
ያለፍትህ አካል መጫወቻ ሆኘ፤
የይስሙላ ዳኛ መጨፈሪያ ሆኘ፡፡

አጥቸ ፍርድ ቤት፣
አቤት የምልበት፣
ፍትህ የማይበት፣
ግፍ የሚመታበት፡፡

ፍትህ ካደባባይ ከመንበሩ ጠፍቶ፣
አምባገነን ነግሶ ስርዓቱ ከርፍቶ፣
ህዝብን አተራምሶ ሀገርን አራቁቶ፣
ዜጋን አሰድዶ ወገን አስከፍቶ፣
በህዝቦች ጫንቃ ላይ ገኖ ተንሰራፍቶ፣
ለዘላለም ሊኖር ሁሉንም አጥፍቶ፣
በተንኮል በደባው ምሎ ተገዝቶ፣
አልሞ ተነስቷል ንጉስ ሊሆን ከቶ፡፡

ለማይበገረው ጠንካራው መንፈሴ፣
አምላክን ለመስግን በመርካቷ ነብሴ፡፡

በግፈኞች መዳፍ በወጥመድ ብወድቅም፣
ሰብአዊነት ክብሬ ቢጣስ ቢረገጥም፣
ብሩሁ አእምሮዬ አካሌ ቢቆስልም፣
ስሜንም ቢያጎድፉት ጥላሸት ቢቀቡም፣
ከዓላማዬ ጽናት አንዲት ጋት አልሸሽም፣
ግርፋት ስቃዩ ጡጫው ቢጨምርም፣
እራሴ ቢደማም አልተንበረከኩም፣
ተሰቃየሁ ብዬ አላፈገፍግም፣
ለጨቋኞች ደስታ አላጎበድድም፡፡

ከዚህ በላይ በቀል አድልኦ ጥላቻ፣
ስምን የማጠልሸት የሰይጣን ዘመቻ፣
ይፈጸማል እኮ በዕኩዮች ሽኩቻ፡፡

እናም የዘመናት ስቃይ ይቀጥላል፣
እኔን ግን መንፈሴ ቆራጥ ያደርገኛል፣
የወገኔ ፍቅር ያንገበግበኛል፡፡

ከምንጊዜም በላይ በሩ ቢጣመምም፣
የተንሸዋረረው ፍትህ ቢጓደልም፣
በኔ ላይ ደጋግሞ ቅጣት ቢቆልልም፣
ከዓላማዬ ፍንክች በፍጹም አልልም፡፡

የእራሴ እጣፈንታ ወሳኙ እራሴ ነኝ፣
ማንም አምባገነን የማይጨፍርብኝ፣
በዲያብሎስ መንገድ የማያስገድደኝ፣
የነብሴ መርከቡ ካፕቴኑ እራሴ ነኝ፡፡

አራቱ የዞን 9 ጦማሪያን ባስቸኳይ ይፈቱ፣

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ገዥ አካል 5 ወጣት ጦማሪያንን እና ጋዜጠኞችን የህግ አማካሪዎቻቸው፣ እራሳቸው ግፉ የተፈጸመባቸው እና ወላጆቻቸውም ሳይቀር ምንም ነገር ሳያውቁ ባልተጠበቀ ሁኔታ በድንገት ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያው እስር ቤቱ ለቋቸዋል፡፡ ከሕግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ቤት ሲማቅቁ ቆይተዋል፡፡ ዴሞክራሲ እና ፍትህ በዓለም ላይ ሁሉ በአደባባይ እየሰፈነ እና እየለመለመ ባለበት በአሁኑ ጊዜ በማጎሪያ እስር ቤት አስገብቶ እንደ እባብ የሚቀጠቅጥ፣ በንጹሀን ዜጎች ህይወት ላይ ቁማር የሚጫወት እና እንደፈለገ ወስዶ እንደ ጥጃ የሚያስርና የሚፈታ የዘራፊ ወሮበላ ቡድን ስብስብ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ መታየቱ እጅግ ያሳዝናል፡፡ እነዚህ ንጹሀን ዜጎች በወጡባት እግራቸው ነገም ተመልሰው የማይገበቡት ምን ዋስትና ሊኖር ይችላል! ምንም፡፡

የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ (ጋተኮ) “የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣኖች የዞን 9 ጦማሪያንን ከሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጋር በመስራት እና የማህበራዊ የግንኙነት መስመሮችን በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ አለመረጋጋት እንዲፈጠር በመስራት ላይ ናቸው:: ቡድኑ በኢትዮጵያ ስላለው የፖለቲካ ጭቆና እና ማህበራዊ የፍትህ መጓደል ሲጽፍ የነበረ ሲሆን የእነዚህ ጦማሪያን ድረ ገጾች በሀገሪቱ ውስጥ በየጊዜው ይታፈኑ ነበር፡፡” በማለት ስለተናገረው ስለዞን 9 ጦማሪያን ነው እየጻፍኩ ያለሁት፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 8/2015 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ገዥ አካል ሁሉንም የውንጀላ ክሶች በመጣል ባልታሰበ ሁኔታ ጦማሪያኑን እና ጋዜጠኞችን ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ለቋቸዋል፡፡

እስረኞቹ ለሌሎቹ ከአንድ ዓመት በላይ በግፍ ታስረው በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት ንጹሀን ወገኖቻቸው እና ጓደኞቻቸው እንኳ በሉ ደህና ሁኑ ለማለት ጊዜ አላገኙም ነበር፡፡

ከማጎሪያው እስር ቤት የወጡት ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች የሚከተሉትን ያካትታል፡ ዘላለም ክብረት፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ እና ኤዶም ካሳዬ ናቸው፡፡

ከማጎሪያው እስር ቤት የተፈቱት ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ከእነርሱ ጋር በተመሳሳይ የፈጠራ ክስ ተመስርቶባቸው በማጎሪያው እስር ቤት የሚገኙት ሌሎች አራት ጓደኞቻቸው ለምን እንዳልተፈቱ ያሳሰባቸው መሆኑን እና የእነርሱ መፈታት ምሉዕ ደስታ ያልሰጣቸው መሆኑን ለህዝብ ግልጽ አድርገዋል፡፡ ደህና፣ እንግዲህ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ሚስጥራዊ እንቆቅልሽ እዚህ ላይ ነው፡፡ በተመሳሳይ ውንጀላ ያሰራቸውን ዜጎች እውነት ባይሆንም እንኳ ተመሳሳይ ፍትህ የማይሰጥ በፖለቲካ ቡድኑ የሚጦዝ ድሁር የፍትህ አካል መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ ርዕዮት ዓለሙን የመሰለች ጀግኒት አለቻት፣

ሁሉም ሀገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚፈጠሩ ጀግኒቶች እና ጀግኖች በመታደል ላይ ናቸው፡፡

አሜሪካ በርካታ ጀግኖች እና ጥቂት ጀግኒቶች አሏት፡፡ አብዛኞቹ የአሜሪካ ጀግኒቶች ያልተዘመረላቸው ናቸው፡፡

አሜሪካዊት ጀግኒት ሐሪዬት ቱብማን እ.ኤ.አ በ1950ዎቹ ባሮች ነጻነታቸውን እንዲቀዳጁ በማሰብ “የምድር ስር ባቡር” ማለትም ከባርነት ወደ ነፃነት ለመጥፋት የሚሞክሩትን የባርነት ተገዢዎች ህቡዕ በሆነ መልኩ በማደራጀት እና በማስተባበር የስብሰባ ቦታዎችን፣ የሚስጥር መንገዶችን፣ በመጓጓዣ ቦታዎች እና በሰላማዊ የህዝብ መኖሪያ ቤቶች በመጠቀም ትግሉ በተጠናከረ መልኩ እንዲካሄድ ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ1870ዎቹ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት አካባቢ ሱሳን ቢ.አንቶኒ የአሜሪካ ሴቶች የመምረጥ፣ የንብረት የባለቤትነት መብት እና ከዚህም በላይ በመሄድ የሰራተኞች ማህበር አባል እንዲሆኑ የሚያስችሏቸውን መብቶቻቸውን ለማስከበር አመራር ይሰጡ የነበሩ ጀግኒት ሴት ነበሩ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት “የሲቪል መብቶች ተከራካሪ የመጀመሪያዋ አመቤት” እና እ.ኤ.አ በ1950ዎቹ አጋማሽ የአሜሪካ የሲቪል መብቶች ንቅናቄ እናት እያለ የሚጠራቸው ሮሳ ፓርክስ ቀላል የሆነውን ህዝባዊ እምቢተኝነትን እንደ ትግል ስልት በመጠቀም ለነጻነት፣ ለእኩልነት እና ለፍትህ ሲካሄድ የነበረውን ትግል አቀጣጥለዋል፡፡ ከፊት ለፊት የተቀመጠችበትን የአወቶብስ መቀመጫ እንድትለቅ እና ወደ ኋላ ሄዳ እንድትቀመጥ የሚያዝዘውን የጨቋኞች ትዕዛዝ አሻፈረኝ፣ እምቢ በማለት ለሴቶች መብት መከበር ስትል የመጀመሪያዋ ሆናለች፡፡

ይህች ጀግኒት እንዲህ ብላ ነበር፣ “የለም፣ በፍጹም ከዚህ መቀመጫ አልንቀሳቀስም!“ በማለት ዜጎችን በጾታ ለሚከፋፍለው ሸውራራ የፖሊስ እና የፍትህ ስርዓት በአደባባይ በግልጽ ተናግራለች፡፡

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካ አሜሪካውያን ወዲያውኑ ትግሉን በመቀላቀል ከመብት ታጋዩዋ ጋር አብረው መዘመር ጀመሩ፡፡

“የትም አንንቀሳቀስም!/ልክ በውኃ አጠገብ እንደቆመ ዛፍ/ ህብረት ከእኛ ጎን ነው የተሰለፈው/እኛ ለነጻነታችን እንታገላለን/ ለልጆቻችን ስንል እንታገላለን/ ጠንካራ የሆነ ማህበር እንመሰርታለን/ጥቁሮች እና ነጮች በአንድነት ሆነን/ወጣቶች እና አዛውንቶች በአንድ ላይ በመቆም/ የትም አንንቀሳቀስም፣ የትም፡፡“

የአፍሪካ አሜሪካዊ ሴቶች ለሲቪል መብቶች እንቅስቃሴ ትግል ዋና የጀርባ አጥንት ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ያልተዘመረላቸው ጀግኖቶች ናቸው፡፡

የዘመናዊ ሰብአዊ መብቶች ንቅናቄ እናት የሆኑት ኢሊኖር ሩዝቬልት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ለሰብአዊ መብቶች ስምምነት መሰረት የሆነውን የዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ድንጋጌ በማርቀቁ ሂደት ከፍተኛ ኃላፊነትን ይዘው የነበሩ ብቸኛዋ ሴት ነበሩ፡፡

በእኔ አመለካከት ርዕዮት ዓለሙ የዚህ ዓይነት አብዮተኞች ቡድን አባል ናት ማለት እችላለሁ፡፡ እንደዚህ ያሉት ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለሲቪል እና ሰለብአዊ መብቶች ዓይናቸውን ሳያራግቡ በመንፈሰ ጠንካራነት ታሪክን የሚለውጡ ደፋር፣ በአመክንዮ የሚያምኑ እና ለህዝብ ሲሉ መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ የሆኑ ሴቶች ናቸው፡፡

እውነት ተናጋሪዋ፣

ርዕዮት “የኢትዮጵያ እውነት ተናጋረዊ ሴት” በመባል ትጠራለች፡፡

ዘመናዊው የአፍሪካ ታሪክ በሚጻፍበት ጊዜ እና በአፍሪካ አዳራሽ የዝነኞች ስም ዝርዝር ከአፍሪካ አዳራሽ ተዋራጆች ስም ዝርዝር ተለይቶ ሲጻፍ የርዕዮት ስም “በእሳት ውስጥ ተፈትነው ያለፉ” ከሚለው ከጀግኖቹ የክብር ስም ዝርዝር ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጻፍ ይሆናል፡፡

ርዕዮት ዓለሙ አራት ዓመታት ከ17 ቀናት በቆየው ጊዜ ውስጥ የመለስ ዜናዊን የገኃነም ቅጣት ተጋፍጣለች፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015 ወጣት የሆነችዋ የአረብ ብረቷ ሴት ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመውጣት ለዓለም ህዝብ እንዲህ በማለት አውጃለች፡

ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ የሆነች ኢትዮጵያን እስከማይ ድረስ ትግሌን በተጠናከረ መልኩ እቀጥላለሁ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ እርሷን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ በጉልበቷ እንድትንበረከክ ለማድረግ ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልቧጠጠው አቀበት አልነበረም፡፡

የስነ ልቦና ስብራት ለማድረስ እና ያላትን ጠንካራ ተስፋ ለማዳፈን ለብቻዋ ለይቶ በአንድ ክፍል ውስጥ እንድትታሰር አደረገ፡፡

ለህይወት አስጊ በሆነ በሽታ ተይዛ በነበረበት ጊዜ ህክምና እንዳታገኝ አበርትቶ ሰርቷል፡፡

ሴትነቷን እና ሰብአዊ ፍጡር መሆኗን ክደው ተንቀሳቅሰዋል፡፡

መንፈሷን ለመግደል የሞት ሽረት ትግል አድርገዋል፡፡

የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመባል በሚታወቀው እስር ቤት የጥላቻ እና የበቀል ቦታ ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል፡፡

ሆኖም ግን በምንም ዓይነት መልኩ የርዕዮትን ቅስም መስበር ሳይቻላቸው ቀርቷል፡፡

አዕምሯዋን መቆጣጠር አልቻሉም፡፡

መንፈሷን መስበር አልቻሉም፡፡

ለመኖር ያላትን ምኞት ማጥፋት ሳይቻላቸው ቀርቷል፡፡

በኩራት ደረቷን ነፍታ በመቆም ለዓለም እንዲህ ትላለች፡

ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ የሆነች ኢትዮጵያን እስከማይ ድረስ ትግሌን በተጠናከረ መልኩ እቀጥላለሁ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አሳሪዎቿ ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት እንድትወጣ ከማድረጋቸው ከደቂቃዎች በፊት አሁን እንዳለችው እንደምትሆን ነግራቸዋለች፡፡ ከማጎሪያው እስር ቤት እንድትወጣ አይፈቅዱላትም ምክንያቱም ከአራት ዓመታት በፊት ታደርግ እንደነበረው ሁሉ አሁንም ትግሏን እንደምትቀጥል ያውቃሉና፡፡

ርዕዮት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን እንዲህ በማለት አስጠንቅቃለች፣ “ባላጠፋሁት ጥፋት ምንም ዓይነት ይቅርታ ሳልጠይቅ ከማጎሪያው እስር ቤት ወጣሁ ብዬ ለህዝብ ስናገር መልሳችሁ ወደ ማጎሪያው እስር ቤት ልታመጡኝ ትችላላችሁ፣ እኔ ግን በዓላማዬ ጸንቼ እቆያለሁ፡፡ ስለእኔ ከእስር መፈታት ሀሰት ብትናገሩ እውነቱን ለህዝብ ይፋ አደርጋለሁ እናገራለሁ፡፡“

በተለያዩ በርካታ አጋጣሚዎች የርዕዮት አሳሪዎች ይቅርታ ጠይቃ ነጻ ሆና እንድትወጣ የምትፈርምበትን ፎርም እያዘጋጁ ፈርሚ እያሉ በተደጋጋሚ ለምነዋታል፡፡

እርሷግን ወረቀቱን ወስዳ እንደምትጥለው ነግራቸዋለች፡፡

“ብረቷ ወይዘሮ ” እየተባለች እንደምትጠራው የንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ማጊ ታቼር በህይወት ብትኖር ኖሮ እንዲህ እላት ነበር፣ “ማጊ እባክሽን ወደ ጎን ሁኝ፣ ቦታውን ለርዕዮት ልቀቂ!“

ርዕዮትን እና ሌሎችን ጦማሪያን እና ጋዜጠኞችን የፈቷቸው ለምንድን ነው?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ርዕዮት ለፍትህ ወይም ደግሞ ስለእርሷ የልብ ሀዘን መናገር እንድትችል እኔንም ጨምሮ አይፈቅዱላትም ምክንያቱም ተጻራሪ በሆነ መልኩ እነርሱ የሚያዝኑበት ልብም ሆነ መልካም ነገር የላቸውምና፡፡

ርዕዮት ከእስር ቤት ወጥታ ስትሄድ ጥርሳቸውን እንደሚነክሱ እና የሆድ ቁርጠት እንደሚይዛቸው ጥርጥር የለውም፡፡ ቢቻላቸው ኖሮ እርሷ በክፉ በሽታ ምክንያት ህይወቷ አልፏል በማለት ለዓለም ህዝብ ማሳወቅን ይመርጡ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ዕድል ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጋር አይደለችም፡፡

ይህንን ድርጊት ያደረጉት ለግንባር መሸፈኛ እና በዚህ ወር የሚመጡትን የኦባማን ልብ ለመማረክ ታስቦ የተደረገ ነው፡፡

ይህንን በማድረግ ለኦባማ ጥሩ ነገር እየሰሩ እንዳሉ ለማስመሰል የተደረገ የቅጥፈት ተውኔት ነው፡፡ የኦባማ ጉብኝት ርዕዮትን እና ሌሎችን የታሰሩ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ ከሆነ የሚፈልጉት ነገር አይደለም፡፡

ኦባማ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ እናስብ፡ “ክቡር ፕሬዚዳንት ወደ መለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመሄድ የእርስዎን መሄድ የሚጠባበቁትን እና በግፍ በእስር ላይ እየማቀቁ የሚገኙትን እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ ተመስገን ደሳለኝን፣ የዞን 9 ጦማሪያንን እና በሺዎች የሚቆጠሩትን ሌሎችን የፖለቲካ እስረኞች ሊጎበኙ ይችላሉን? በደርዘን በሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ይገኛሉ፡፡ እባክዎትን ሄደው ለመጎብኘት ይችላሉን?“

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በልካቸው የተሰፋ የማስመሰያ ልብስን በመልበስ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች በተደጋጋሚ እንደሚሉት የሰው ልጆችን መብት በመጣስ ታላቅ እና አስቀያሚ ሰይጣኖች ናቸው የሚሉትን በመተው ኦባማ ይኸ መንግስት እንደሚባለው አይደለም ብለው እምነት እንዲያድርባቸው ለማድረግ ተዘየደ የሸፍጥ ስራ ነው፡፡ ከልብ እና ከፍቅር ያለመሆኑን አይደለም የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርና የዓለም ህዝብም አሳምሮ እንደሚያውቀው ጥርጥር የለውም፡፡

አይዟችሁ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ምንም መጨነቅ አያስፈልግም፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጠባቂ መላዕክት አሏቸው – ሱሳን ራይስ እና ዌንዲ ሸርማን በኦባማ ጉብኝት ሁሉ እየተከታተሉ የሚከላከሉላችሁ መላዕክት ናቸው፡፡ ወታደራዊ ማነጻጸሪያ ቃል በመጠቀም እናንተን ለመጠበቅ በቁጥር 1 በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሶስት ቢራቢሮ የሚመስሉ ፍጡሮች የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አናት ላይ እያንዣበቡ በመዞር ይጠብቋችኋል ጠንቅቃቺሁ ተመልከቱ ፡፡

ርዕዮት በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፣

ርዕዮት ዓለሙ በመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ለአራት ዓመታት ከ17 ቀናት በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፡፡

ከቤተሰቦቿ፣ ከጓደኞቿ እና ከዘመዶቿ ተለይታ ቆይታለች፡፡

እናት እና አባቷ ብቻ እንዲያዩዋት ተፈቅዶ ነበር፡፡ (የእርሷ አባት ከሆኑት እና በተጨማሪም የሕግ አማካሪ ጠበቃዋ ከሆኑት አባቷ ጋር እንኳ የሕግ ምክር ውይይት እንዲያደርጉ አየፈቀድላትም ነበር፡፡)

ቢሆንም ግን ርዕዮት በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፡፡

እርሷን የሚወዷት እና የሚደግፏት በዓለም ዙሪያ ሁሉ በሺዎች የሚጠቆሩ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለሁልጊዜ በአዕምሯቸው እና በመንፈሳቸው ከእርሷ ጋር ነበሩ፡፡

በፌስቡክ ድረ ገጽ እና በማህበራዊ የመስመር የግንኙነት ዘዴዎች አማካይነት የሚጽፉላት ወጣት እና ቁጡ የሆኑ ወገኖች አሏት፡፡

በምንም ዓይነት መልኩ በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፡፡

ታላቅ ክብርን ለሚያጎናጽፉ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ድርጅቶች ተሸላሚ እንድትሆን ስሟን በጥቆማ የሚሰጡ በርካታ ወገኖች ነበሩ፡፡

በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፡፡

ሌሎችም ለቁጥር የሚያዳግቱ እንደ እኔ ያሉ የእርሷን እና ሁሉንም በወያኔ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች እና ጀግኖች የማይበገሩትን የእስክንድር ነጋን፣ ዉብሸት ታዬን፣ ተመስገን ደሳለኝን፣ አብርሃ ደስታን፣ የዞን 9 ጦማሪያንን እና እንደ እነርሱ ያሉትን ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን ጉዳይ የእራሳቸው የግል ተልዕኮ አድርገው የሚከታተሉ ወገኖች ነበሩ፡፡

ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህሊና ፍርድ አደባባይ በመቆም ስለ ርዕዮት ጥብቅና ቆሜ ስሟገት ታላቅ ክብር ይሰማኛል፡፡

በርዕዮት ጉዳይ ላይ በተለይም ወይም ደግሞ በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች እና በአጠቃላይ በሰው ልጆች ላይ በወያኔው አምባገነን ገዥ አካል ስለሚፈጸመው ወንጀል በርካታ ትችትችን ጽፊያለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2012 “ርዕዮት ዓለሙ፡ የኢትዮጵያ ፕሬስ ነጻነት ወጣቷ ጀግኒት“ በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችቴ ላይ ርዕዮት ለምን እንደታሰረች ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡

ርዕዮት እና ከእርሷ ጋር እንዲከላከል የተያዘው ውብሸት ታዬ እ.ኤ.አ ሰኔ 2011 በቁጥጥር ስር ውለው በስልክ እና በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ አደጋ ለመጣል የሚል የፈጠራ ክስ በወያኔው ስብስብ የሀሰት ውንጀላ ተፈብሮኮ ወደ መለስ የማጎሪያ እስር ቤት እንዲወረወሩ ተደረገ፡፡ ለወራት ያህል ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖር በእስር ቤት ታጉረው ቆዩ፡፡ ሌላው ቀርቶ የግፍ ሰለባዎችን የሕግ ጠበቃዎች እንኳ እንዲጎበኟቸው አይፈቀድም ነበር፡፡

ርዕዮት በቁጥጥር ስር ለመዋሏ ትክክለኛው ምክንያት በዚያው ዓመት ሰኔ 17 በወጣ ፍትህ እየተባለ ይጠራ በነበረው እና በተከታታይ ከህትመት ውጭ ሆኖ በታገደው ሳምንታዊ መጽሔት ላይ ጽፋ ባወጣችው ጽሁፍ ነበር፡፡

በዚያ ባወጣችወ ጽሁፏ ላይ ርዕዮት አሁን በህይወት የሌለውን አምባገነኑን መለስ ዜናዊን ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እየተባለ ሌት ቀን ስለሚደሰኮርለት የቅንጦት ግድብ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ በቁጥር አንድ የሀገሪቱ አምባገነን ላይ ደፍራ ጥያቄ በማቅረቧ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 2011 አሁን በህይወት የሌለው መለስ በግል ትዕዛዝ በመስጠት ውብሸት እና ርዕዮት “የሽብር ድርጊት ለመፈጸም እና ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ተሳትፎ በማድረግ ደባ ለመስራት አሲረዋል” የሚል የፈጠራ የክስ ወንጀል ተፈብርኮ ክስ እንዲመሰረትባቸው አደረገ፡፡

በርዕዮት ላይ የቀረበው “ደባ ለመፈጸም እየተባለ በመለስ ዜናዊ የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ይጠራ የነበረው ማስረጃ በኢሜል የተጻጻፈቸው እና በባለሽቦ ስልክ ስለሰላማዊ ተቃውሞ እና ለውጥ ስለማምጣት በሚል ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር የተነጋገረችው ተቀድቶ የቀረበ ነበር፡፡

ርዕዮት እና ውብሸት ወደ ችሎት ከመቅረባቸው በፊት በነበሩት ሶስት የእስር ወራት ጊዜ ውስጥ የህግ አማካሪ የማግኘት እድሉ አልነበራቸውም፡፡

ሁሉቱም ጋዜጠኞች የህግ አማካሪ እንዳያቀርቡ ተከልክለዋል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የዝንጀሮው ፍርድ ቤት እስር ቤቱ የማሰቃየት ድርጊት እያስፈጸመብን ስለሆነ፣ ከህግ አግባብ ውጭ የሆነ አያያዝ ያለ በመሆኑ እና ህክምና እንዳናገኝ ክልከላ ተደርጎብናልና ምርመራ ይደረግልን በማለት የቀረበውን ውንጀላ አልቀበልም በማለት ውድቅ አደረገ፡፡

ከእስር ቤት እንድትለቀቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ በቀረበላት ጊዜ ርዕዮት ከህግ አማካሪዎቿ ጋር መገናኘት እንዳትችል ከተፈረደባት ጊዜ ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ያህል ተከልክላ የቆየች መሆኑን አረጋግጣለች፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2012 “የኢትዮጵያ ርዕዮት፡ የጥናካሬዬ ዋጋ“ በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት “ክብር በእሳት ፈተና ላይ” በማለት ትክክለኛ ትርጉሙን ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ የ2012 የደፋር ጋዜጠኝነት ሽልማት/Courage in Journalism Award አሸናፊ መሆኗን ተከትሎ በእጅ ጽሁፏ አዘጋጅታ በዓለም አቀፍ የሴቶች ሜዲያ ፋውዴሽን/International Women’s Media Foundation (IWMF) ስነስርዓት ላይ ቀርቦ እንዲነበብላት በድብቅ ከማጎሪያው እስር በት እንዲወጣ ባደረገችው ደብዳቤ ላይ “ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ” ከመሆን የበለጠ ዋጋ የሚያስከፍለኝ ምንም ዓይነት ነገር የለም በማለት ግልጽ አድርጋ ነበር፡፡ ለድፍረቷ ከፍተኛ የሆነ ዋጋ ሊያስከፍላት እንደሚችል እና እውነታውን በጽናት መቀበል እንዳለባት አሳምራ ታውቅ ነበር፡፡

ርዕዮት እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015 ከመለስ የማጎሪያ እስር ቤት በተለቀቀችበት ዕለት የክርክር አመክንዮዋን እንደገና በድጋሜ አረጋግጣለች፡፡

የፈለገውን ያህል ዋጋ ቢያስከፍልም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እና ፍትህ እንዲሰፍኑ በጽናት ለመታገል ቆርጣ የተነሳች መሆኗን አውጃለች፡፡ ትክክለኛ የድፍረት ትርጉሙ ምን እንደሆነ ለእኔ እና ለሁሉም ደጋፊዎቿ አስተምራናለች፡፡

የስዊድን ጋዜጠኞች ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን ፔርሰን እራሳቸው አሁን በህይወት በሌለው በመለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ ሰኔ 2011 አሸባሪነት በሚል የሸፍጥ ክስ ተመስርቶባቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ርዕዮትን በእስርኞች የማማላለሻ አውቶብስ ውስጥ ሆና እጆቿ በካቴና ታስረው ለፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመቅረብ ላይ እንዳለች ያገኟት መሆናቸውን ግልጽ አድርገዋል፡፡

ሽብዬ “ምን እያደረግሽ ነው?” በማለት ጥያቄ አቀረበላት፡፡

ርዕዮት እንዲህ በማለት ምላሽ ሰጠች፣ “እኔ ጋዜጠኛ ነኝ፣ ብቻችንን አይደለንም፣ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ነን እዚህ በአሸባሪነት ወንጀል ተከስሰን ያለነው“ በማለት እስር ቤቶቹን አመላከተችው፡፡

ርዕዮት ለሽብዬ እንዲህ በማለት ነገረችው፣ “በምትፈታበት ጊዜ እኔ ምንም ዓይነት አሸባሪ ያለመሆኔን ለእውነት የምሰራ ጋዜጠኛ መሆኔን ለዓለም ህዝብ ሁሉ ንገርልኝ፡፡“

ሽብዬ ትኩር አድርጎ ተመለከተ እና እንዲህ አለ፣ “እነዚህ ሁሉም ወጣት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ለአንድ ምርጫ ተዳርገዋል፡፡ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው እና የተማሩ ናቸው፣ ቀላል የሆነ ህይወትን መምረጥ ይችሉ ነበር፡፡ ሌሎችን የሙያ ዘርፎች መርጠው መሰማራት ይችሉ ነበር፡፡ ሆኖም ግን እውነትን፣ ሀገራቸውን እና ወገኖቻቸውን በማፍቀራቸው ጋዜጠኞች የመሆን ምርጫቸውን ይዘዋል፡፡“

ርዕዮት በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፣

ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ተመስገን ዳሳለኝ፣ አብርሃ ደስታ፣ የዞን 9 ጦማሪያን እና ሌሎቹ እንደ እነርሱ ተመሳሳይ የሆኑት በኢትዮጵያ የሚገኙት በርካታዎቹ የፖለቲካ እስረኞች ብቻቸውን አይደሉም፡፡ በእያንዳንዷ ዕለት እና ሰከንድ በእዕምሮ እና በመንፈስ ከእነርሱ ጋር ነን፡፡

ርዕዮት ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉ ጓደኞች ነበሯት፣

የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ (ጋተኮ)/CPJ የእርሷ ጉዳይ ከሌሎች በእስር ላይ ከሚገኙት ጋዜጠኞች ጉዳይም ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ በማስረጃ የተደገፈ ዘገባ ስላለው ለበርካታ ዓመታት ከፍተኛ የሆነ ጥረት በማድረግ ሲከታተለው ቆይቷል።

ጋተኮ/CPJ በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሽብር ወንጀል እየተባለ በነጻ ዘገባ ላይ የሚደረገውን የጽሑፍ ምርመራ አውግዟል፡፡

ጋተኮ/CPJ እንዲህ በማለት የኢትዮጵያን መንግስት ለማስተማር እና ወደ ህሊናው እንዲመለስ ሲያስተምር ቆይቷ፣ “የኢትዮጵያ ጨካኝ አምባገነኖች መንግስት አሸባሪ ናቸው ብሎ ከፈረጃቸው ድርጅቶች እና ቡድኖች ጋር ዘጋቢዎች መነጋገር መቻላቸውን አይወድም፡፡ ሆኖም ግን ጋዜጠኞች ማድረግ ያለባቸው እንደ እነዚህ ያሉ ተግባራትን ነው፡፡ ከዚህ ያነሰ ስራን የሚያከናውኑ ከሆነ ዝም ብሎ ተራ ወሬ የሚያስተላልፍ አፈ ቀላጤ የመሆን ትግባራትን መፈጸም ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ባለስልጣኖቹ እንደዚህ ዓይነቶቹን የሞኝ የውንጀላ ክሶች በአስቸኳይ እርግፍ አድርው በመተው ጓደኞቻችንን መልቀቅ አለባቸው፡፡”

ሂዩማን ራይትስ ዎች/HRW በአጠቃላይ ከርዕዮት ጎን ነበር፣

ሂዩማን ራይትስ ዎች/HRW በርዕዮት እና በውብሸት ላይ ተመስርቶ የነበረውን የድድብና ክስ እንዲህ በማለት አውግዟል፡፡ “እንደ ክሱ ፋይል ከሆነ ማስረጃው በዋናነት በድረ ገጽ መስመሮች በመጠቀም በመንግስት ላይ ሸንቋጭ የሆነ ትችቶችን የሚያቀርቡትን እና በስልክ የተደረጉትን ውይይቶች በተለይም በምንም ዓይነት ሁኔታ ከሽብር ወንጀል ጋር ሊገናኙ የማይችሉትን ስለሰላማዊ ተቃውሞ ድርጊቶች የሚደረጉት ውይይቶች ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመጀመሪያ በቀረበው የክስ ፋይል ላይ ተከላካዮች ለተከሰሱበት ወንጀል ሌላው ቀርቶ መሰረታዊ የሆኑ የወንጀል ዝርዝሮችን እንኳ ያላሟ ነው…“ በማለት በይፋ ተቃውሞታል፡፡

አምነስቲ ኢነተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅትም ከርዕዮት ጎን በመሰለፍ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት በእርሷ ላይ እያደረገ ባለው የችሎት ሂደት ላይ ያለውን ቁጣ እንዲህ በማለት ገልጿል፡፡ “ምንም ዓይነት የወንጀል ጥፋት ለማጥፋታቸው ሊያስረዳ የሚችል ማስረጃ የለም፡፡ እነዚህ እስረኞች ህጋዊ በሆነ መልኩ መንግስትን በመተቸታቸው ምክንያት እየተቀጡ ያሉ የህሊና እስረኞች ናቸው ብለን እናምናለን፡፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ መፈታት አለባቸው፡፡“

ፓምባዙካ የዜና ወኪል/Pambazuka News ርዕዮት መፈታት እንድትችል የውትወታ ዘመቻ አደራጅቶ ነበር፡፡ ፓምባዙካ እንዲህ በማለት አውጆ ነበር፣ “የመንግስትን ኢፍትሀዊነት መርህን መሰረት ባደረገ መልኩ ለእውነት እና ለፍትህ በጽናት በመቆሟ ምክንያት ዓለም አቀፍ ዝናን እንድትጎናጸፍ አስችሏታል፡፡“

ደፋር ጋዜጠኞችን እየመረጠ ሽልማት የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የሴቶች ሜዲያ ፋውንዴሽን ሽልማት/International Women’s Media Foundation’s Award የሎስአንጀለስ ታይምስ/Los Angeles Times መጽሔት እ.ኤ.አ በ2012 የአሸናፊነት ሽልማቱን በሰጠበት ወቅት ለርዕዮት እንዲህ በማለት ተሟግቶላት ነበር፣ “ርዕዮት ዓለሙ በቬርሊ ሂልስ በተደረገው ጠቃሚ እራት ግብዣ ላይ ሳትገኝ ቀርታለች፡፡ ሆኖም ግን ጥሩ ይቅርታ ይደረግላታል፡፡ የ31 ዓመቷ ጋዜጠኛ የኢትዮጵያ መናገሻ በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው እና በጣም አስከፊ በሆነው አይጦች በሚተራመሱበት እና ቃሊቲ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት ውስጥ ታስራ ትገኛለች፡፡ ስለድህነት፣ ስለተቃውሞ ፖለቲካ እና ስለጾታ እኩልነት በድፍረት በመጻፏ ምክንያት ከተበየኑባት አምስት ዓመታት ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በሁለተኛው ዓመት እስር ላይ ትገኛለች፡፡“

ርዕዮት ከጎኗ የቆሙ ወንድሞችም አሏት፣

ኤሊያስ ወንድሙ፣ የጸሐይ አሳታሚዎች አሳታሚ፣ በርዕዮት ስም ሽልማቱ ከሚገኝበት ቦታ በመገኘት IWMF ያዘጋጀላትን እና አሸናፊ የሆነችበትን ሽልማት ተቀብሎላታል፡፡

ኤሊያስ በርዕዮት ስም ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ርዕዮትን ለዚህ ሽልማት ስጠቁም በእርሷ ላይ ያለውን ድፍረት ለማሳየት ነበር የፈለግሁት፣ ስለሆነም በሀገራችን ያሉ ልጃገረዶች ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ የለሾች ድምጽ ለመሆን ከመደፋፈር ወደኋላ አይሉም፡፡ የአንድን መንግስት ፖሊሲ በመጻፍ ትችት የሚያደርግን ሰው በአሸባሪነት መክሰስን እንዴት አድርጎ በመሬት ላይ ማነጻጸር ይቻላል?“

ኤሊያስ እንዲህ የሚል ሌላ አማራጭ ሰጥቶ ነበር፣ “ተገቢ በሆነ ስልጠና እጥረት መሰረት ጋዜጠኞቻችን ፍጹም አይደሉም ሊሆኑም አይችሉም፣ ሆኖም ግን ለዚህ መፍትሄ ሊሆን የሚችለው የሚሰሯቸውን ስህተቶች እየተከታተሉ ወንጀለኛ በማድረግ መቅጣት ተገቢ አይደለም፣ ሆኖም ግን ማረም እና ማስተማር ተገቢ ይሆናል፡፡“

የርዕዮት የእጅ ጽሁፍ ደብዳቤ ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ሾልኮ በመውጣት ለIWMF በመድረስ እውነተኛውን የጋዜጠኝነት ድፍረት በተገባር አሳይቷል፡፡ በቁራጭ ወረቀት ላይ በመጠቀም የሚከተሉትን ቃላት አስፍራ ነበር፡

በኢትዮጵያ ወደፊት የተሻለ ነገርን ለማምጣት አንድ ነገር ማበርከት እንዳለብኝ እምነት አለኝ፡፡ በኢትዮጵያ በርካታ ኢፍትሀዊነቶች እና ጭቆናዎቸ ስላሉ በማወጣቸው ጽሁፎቼ አማካይነት ማጋለጥ እና መቃወም አለብኝ፡፡ ምክንያቱም ጋዜጠኝነት እራሴን በፅናት ላሰማራበት የሚገባ ሙያ በመሆኑ ነው፡፡ ለኢህአዴግ ጋዜጠኝነት ማለት ለፕሮፓጋንዳ ስራ ለገዥው ፓርቲ መጠቀሚያ ብቻ አድርጎ እንደሚያየው አውቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን ለእኔ ጋዜጠኞች ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ የለሾች ድምጽ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው የተጨቆኑትን የሚያጋልጡ በርካታ ጽሁፎችን የጻፍኩት፡፡

ነጻነትን ዴሞክራሲን ለመጠየቅ ወደ አደባባይ በመውጣት በመንገዶች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉ ንጹሀን ዜጎችን በጥይት መደብደብ፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን እና ጋዜጠኞችን ወደ እስር ቤት ማጋዝ…እንዲሁም የመናገር፣ የመደራጀት ነጻነትን መከልከል እና ፕሬስን ማፈን፣ በሙስና መዘፈቅ፣ የአንድ ጎሳ ቡድን በሌሎች ላይ የበላይ ሆኖ መቅረብ የመሳሰሉት ነገሮች የመንግስታችን ጥቂት መጥፎ ስህተቶች ናቸው፡፡ እንደዚህ ያሉ ዘገባዎችን ፈልፍዬ በማውጣት በማሳየው ድፍረት ዋጋ ሊያስከፍለኝ እንደሚችል አስቀድሜ አውቃለሁ፡፡ እናም ያንን ዋጋ ለመቀበል ዝግጁ ነበርኩ፡፡

እ.ኤ.አ በ2013 ርዕዮት የዩኔስኮን የጉሌርሞ ካኖንን ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት/UNESCO Guillemo Cano World Press Freedom Prize አሸናፊ ሆና ተሸልማለች፡፡

ሽልማቱን ከሰጠ በኋላ ዩኔስኮ እንዲህ የሚል ጥቆማ ሰጥቶ ነበር፣ “ወ/ት ርዕዮት ነጻ በሆነ ዓለም አቀፍ የሜዲያ ባለሙያዎች የዳኞች ቡድን ላሳየችው ልዩ የሆነ ድፍረት፣ እምቢተኝነት እና ሀሳብን በነጻ ለመግለጽ ባላት የዓላማ ጽናት ለእርሷ ዕውቅና በመስጠት ለሽልማቱ እንድትቀርብ ተደርጓል፡፡“

ርዕዮት ዓለሙ እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015 ከአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ጋር ያደረገችው ቃለመጠይቅ፣

ርዕዮት ዓለሙ በአሜሪካ ደምጽ የአማርኛው አገልግሎት ጋዜጠኛ በሆነው በሰለሞን አባተ ቃለ መጠይቅ ተደርጎላታል፡፡ (ከዚህ በታች ያለው በእንግሊዝኛ ከተረጎምኩት በመውሰድ እንደገና ወደ አማርኛ የተተረጎመ የእራሴ ትርጉም ነው፡፡ የርዕዮትን ቃላት በተቻለ መጠን ትክክለኛ ትርጉማቸውን በማዘጋጀት የቃላት ትርጉማቸውን ብቻ ሳይሆን ተመሳስሎዎችን እና የተለመዱ የቋንቋ አባባሎችንም በማከተት ለማቅረብ ሞክሪያለሁ፡፡)

ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ የነበረው ቃለመጠይቅ እንደገና ወደ አማርኛ ተመልሶ ለአንባቢዎች እንደሚከተለው ቀርቧል፡

ሰለሞን፡ ርዕዮት ዓለሙ፣ እንኳን ደስ ያለሽ (ከእስር ቤት በመፈታትሽ ምክንያት) እናም እንኳን በሰላም ወደ ቤትሽ ለመመለስ አበቃሽ፡፡

ርዕዮት፡ እናንተንም እንኳን በሰላም ለማግኘት አበቃኝ፡፡

ሰለሞን፡ ከእስር ቤት በመለቀቅሽ ምክንያት ደስ የተሰኙ በርካታ ሰዎች አሉ፡፡ ለመሆኑ በስንት ሰዓት ነው ከእስር ቤት የተለቀቅሽው?

ርዕዮት፡ ወደ 4 ሰዓት አካባቢ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ሆኖም ግን ሰዓቱን በእርግጠኝነት አላረጋገጥኩም፡፡

ሰለሞን፡ ጧት ነበር የተፈታሽው?

ርዕዮት፡ አዎ፡፡

ሰለሞን፡ የመፈታትሽ ሁኔታ እንዴት ነበር? ከእስር ቤት ሲለቅቁሽ ምንድን ብለው ነገሩሽ? ከእስር ቤት እንደምትለቀቂ ቀደም ሲል የምታውቂው ነገርስ ነበርን?

ርዕዮት፡ የማውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ወደ እኔ በቀጥታ በመምጣት ሂጂ አሉኝ፡፡ ቀልድ ነው የሚል ሀሳብ ነበረኝ፡፡ ለምን እና በምንድን ምክንያት ነው ከእስር ቤት የምለቀቀው በማለት ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡፡ እንዲህ አሉ፣ “ከዚህ ውጭ!“ ምክንያቱም ከሌሎች እስረኞች ጋር ምን እንደሚያደርጉ ስለምገነዘብ ነው ለምን እና በምንድን ምክንያት ነው ከእስር ቤት የምለቀቀው በማለት ጥያቄ አቅርቤ የነበረው፡፡ ስለእኔ ከእስር ቤት የመለቀቅ ሁኔታ ያልተጣራ እና የተድበሰበሰ ዘገባ ለህዝብ እናቀርባለን የሚል ሀሳብ ካላችሁ እኔ እውነቱን እንደምናገር ታውቁታላችሁ፡፡ ስለሆነም እውነቱን ለህዝብ ከተናገርኩ በኋላ መልሳችሁ ወደዚህ እስር ቤት የምታመጡኝ ከሆነ ከእስር ቤት አለመቀቄን እወዳለሁ፡፡

ከዚያ በኋላ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቀረብኩላቸው፣ “ምንድን ነው እየተካሄደ ያለው?“ እንዲህ አሉ፣ “ይኸው ነው፡፡“ እኔ ይቅርታ ወይም ደግሞ ምንም ዓይነት ቅደመ ሁኔታ አልጠይቅም፡፡ ይቅርታ የመጠየቂያ ጊዜዬ ቀደም ሲል አልፏል እና እርሱንም አልቀበልም በማለት ውድቅ አድርጌዋለሁ ምክንያቱም በመጸጸት ቀርቦልኝ በነበረው ቅጽ ላይ “ወደ ቀድሞው ሁኔታ ተመልሻለሁ የሚል ቋንቋ ነበረበት፡፡” ያጠፋሁት ጥፋት ስላልነበር ያንን ጥፋት ያላጠፋሁ መሆኔን አምኘ ያንን ቅጽ አልሞላም በማለት እንዲመለስ አድርጌ ነበር፡፡

መፈታት የነበረብኝ እ.ኤ.አ ጥቅምት 2014 ነበር፡፡ የእኔ በቅድመ ሁኔታ የመፈታት ሁኔታ አልፏል አሉ፡፡ ስለሆነም ከእስር ቤት እንለቅሻለን፡፡ እንግዲህ የሰጡኝ አጭሩ መልስ ይኸ ነበር፡፡ ለእኔ ከእስር ቤት መለቀቅ መሰረቱ ያ ነበር፡፡

ሰለሞን፡ በነገራችን ላይ የጤንነትሽ ሁኔታ እንዴት ነው?

ርዕዮት፡ ሁላችሁም እንደምታውቁት ከጥቂት ዓመታት በፊት በአንደኛው ጡቴ ላይ የቀዶ ህክምና ተደርጎልኛል፡፡ሌላኛው ጡቴ በአሁኑ ጊዜም እብጠት ይታይበታል፡፡ ቀዶ ህክምና ያስፈልገዋል ብለውኛል፡፡ በእስር ቤት ውስጥ ቀዶ ህክምና እንዲደረግልኝ አልፈለግሁም ምክንያቱም ከዚህ ቀደም በአንደኛው ጡቴ ላይ ቀዶ ህክምና ተደርጎልኛል እናም ጥቂት ወሰብሰብ ያሉ ነገሮች ተፈጥረውብኝ ነበር፡፡ ይህንን ነገር አላደረግሁትም፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር የሚፈቅድ ከሆነ አሰራዋለሁ የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡

ሰለሞን፡ የምርመራ ውጤቶች በሁለቱም ጡቶችሽ ላይ ምን ያመላክታሉ?

ርዕዮት፡ ከሁለቱ አንደኛው የተሻለ ነገር ያሳያል፡፡ ሌላኛው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያመመኝ ነው የመጣው፡፡

ሰለሞን፡ ከነገርሽኝ ሌላ በተጨማሪ መደበኛ የሆነ የህክምና ምክር እና የትኩረት ድጋፍ አላገኘሽም ነበርን? ጥብቅ የሆነ የሕክምና ክትትል ታደርጊ ነበርን?

ርዕዮት፡ በፍጹም እንደዚያ አልነበረም፡፡

ሰለሞን፡ በየዕለቱ እና በየሳምንቱ የሕክምና ምክር ይሰጥሽ ነበርን? የሕክምና ምክር ወይም ደግሞ የሕክምና ምርመራ ይደረግልሽ ነበርን?

ርዕዮት፡ የለም፡፡ በፍጹም እንደዚያ አልነበረም፡፡ ቀደም ሲል እንዳልኩት ቀዶ ሕክምና መደረጉን ከተውኩት በኋላ እንደ ሳይነስ ለመሳሰሉት ነገሮች ካልሆነ በስተቀር ለዚህኛው ጉዳይ የሕክምና ትኩረት አላገኘሁም ነበር፡፡ የሕክምና ክብካቤ አላገኘሁም፡፡ ምንም ዋጋ የሌለው ነገር ቢሆንም እንኳ የቀዶ ሕክምና እንዳደርግ ነግረውኝ በፍጹም አላደርገውም ብያለሁ፡፡ ምንም ዓይነት የቀዶ ሕክምና ላለማድረግ ወስኘ ነበር፡፡ ምክሮች ያስፈልጋሉ የሚል አስተሳሰብ አልነበረኝም፡፡ ቀደም ሲል እንደተናገርሁት ከወር በፊት የሕክምና ትኩረት አግኝቼ ነበር፡፡ ስለእኔ ጡቶች ጉዳይ ከእነርሱ ጋር ምንም ዓይነት ንግግር አላደረግሁም፡፡

ሰለሞን፡ በእስር ቤት ስለቆየሽበት ሁኔታ ጥቂት ልትነግሪኝ ትችያለሽን? ይቅርታ አድርጊልኝ ወደዚያ መልሸ ልወስድሽ አልፈልግም ነበር፡፡ ሆኖም ግን ስለዚያ ጉዳይ ማወቅ የሚፈልጉ በርካታ አድማጮች ስላሉ ነው፡፡

ርዕዮት፡ አዎ፡፡ ስለዚያ ጉዳይ እንዴት አድርጌ እንደምነግርህ አላውቅም፡፡ እንደ እስረኛው ሁኔታ ይለያያል፡፡ አጠቃላይ በሆነ ለመናገር ስለእስረኞች ያለው አያያዝ ጥሩ ነው የሚባል አይደለም፡፡ ሆኖም ግን የፖለቲካ እስረኞች በተለዬ ሁኔታ ጥሩ በሆነ ሁኔታ የሚያዙ አይደለም፡፡ የእኔን ጉዳይ ብትወስድ ለአንድ ዓመት ከ8 ወራት ያህል ቤተሰቦችን እንዳላይ ተከልክየ ነበር፡፡ እናት እና አባቴን ብቻ እንዳይ ይፈቀድልኝ ነበር፡፡ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ነው እህቴ መጥታ እንድትጎበኘኝ የተፈቀደው፡፡

ስለሆነም ከቤተሰቦቼ ጉብኝት ጀምሮ መብቶቼ አይጠበቁም ነበር፡፡ ሕጉ የሚለው ነገር ቢኖር የኃይማኖት አባቴን፣ የሕግ አማካሪ ጠበቃዬን እና ሌሎችንም ሰዎች የማግኘት እና እርዳታ እና ምክር የማግኘት መብት እንዳለኝ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ቀደም ሲል እንደተናገርኩት ባለፉት ሁለት እና ሶስት ወራት ብቻ ነበር እህቴ እንኳ መጥታ እንድታየኝ የተፈቀደው፡፡ ለአንድ ዓመት እና ለ8 ወራት ሙሉ እናቴ እና አባቴ ብቻ ናቸው እየመጡ እንዲጎበኙኝ ተፈቅዶላቸው የነበረው፡፡

በእስር ቤት ውስጥ በርካታ ችግሮች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ያህልም የመጽሐፍት ችግር፡፡ መጽሐፍት በተለይም የፖለቲካ መፅሐፍ ለማግኘት እንዲያውም ፖለቲካ የምትል ቃል ያለበት መጽሐፍ በተለይም በአሁኑ ጊዜ ከታዬ እንኳ ከፍተኛ የሆነ ቸግር ነበር፡፡ እንግዲህ መጽሐፍትን ከውጭ ለማግኘት ነው ይኸ ሁሉ ችግር ያለው፡፡ ሌሎችን በርካታ ነገሮችን መግለጽ እችላለሁ፡፡ በአጠቃላይ በእስር ቤት የነበረው ቆይታዬ ጥሩ አልነበረም፡፡ እስር ቤት በፍጹም ጥሩ ነገር ሊሆን አይችልም፡፡ ለእኔ የስቃይ ጊዜ ነበር፡፡

ሰለሞን፡ አባትሽ የአንች የሕግ አማካሪ ጠበቃ ነበሩን?

ርዕዮት፡ አዎ አባቴ የእኔ የሕግ አማካሪ ጠበቃዬ ነበር፡፡ እንደዚሁም ሌላም ጠበቃ ነበረኝ፡፡

ሰለሞን፡ አባትሽን እንደ እራስሽ የሕግ ጠበቃ እንጅ እንደሌላ የሕግ ጠበቃ አልነበረም የምታያቸው?

ርዕዮት፡ አይደለም፡፡ ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ማግኘት አልችልም ነበር፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት ከማንም ጋር ግንኙነት አልነበረኝም፡፡ አባት እና እናቴ ወደ እስር ቤት በመምጣት ይጎበኙኝ ነበር፡፡ ሆኖም ግን አባቴ ለሕግ ምክር አገልግሎት አይመጣም ነበር፡፡ ስለአኔ የህግ ጉዳዮች ምንም ነገር መነጋገር አንችልም ነበር፡፡ ወይም ደግሞ ሌላ የሕግ አማካሪም እንዳገኝ እና ምክር እንድቀበል አይደረግም ነበር፡፡

ሰለሞን፡ በእስር ቤቱ ውስጥ የነበረው ንጽህና ስለምግቡ፣ ውኃው እና ስለሌሎች ተመሳሳይ ነገሮች የነበረው ሁኔታ እንዴት ነበር?

ርዕዮት፡ እኔ በቤተሰቦቼ የሚመጣልኝን ምግብ ነበር የምመገበው፡፡ የእስር ቤቱን ምግብም አይቸዋለሁ፡፡ ጥሩ ብለህ ይመትጠራው ነገር አይደለም፡፡ መጥፎ ነው፡፡ ከፍተኛ ወንጀል ፈጽመዋል ለተባሉ የፖለቲካ አስረኞች የሚቀርበው የተለመደው የኢትዮጵያ እንጀራ እና ወጥ ምግብ በጣም አስቀያሚ ነው፡፡

ሰለሞን፡ የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ስለፖለቲካ እስረኞች ጥያቄ ሲቀርብላቸው የሚሰጡት መልስ “ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኞ የሉም” የሚል ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

ርዕዮት፡ ያ ዓይን ያወጣ ውሸት ነው፡፡ እዚያ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ሌላው ቀርቶ ስለ እራሴ ሁኔታ እንኳ ልነግርህ እችላለሁ፡፡ የእኔ ጉዳይ እራሱ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እንዳሉ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ እኔን ለእስር የሚያበቃ ምን ወንጀል ሰራሁ? ምናልባትም የእኔን የችሎት ክርክር ሂደት ተከታትለኸው ይሆናል፡፡ ሰለሆነም እነርሱ አሸባሪ የሚል ውንጀላ በመለጠፍ የሀሰት ክስ መስርተውብኝ የችሎት ሂደት ሲካሄድ በነበረው እና ሲቀርብ በነበረው ማስረጃ እንዳያችሁትም ምንም ዓይነት ሽብርተኝነትን ለመፈጸሜ ወይም ደግሞ የሽብር ድርጊት ሙከራ ለመፈጸሙ ሊያቀርቡ የሚችሉት ማስረጃ አልነበራቸውም፡፡

ይልቁንም እውነታው እና ትክክለኛው ነገር በስልጣን ላይ ስላለው ገዥ አካል ትችት በመጻፌ ምክንያት ነበር፡፡ ሆኖም ግን ስለአንዳንድ ነገሮች ትችት በመጻፋቸው ወይም ደግሞ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጀት አባል በመሆናቸው፣ ወይም ሰዎች ስለመብታቸው በመጠየቃቸው ብቻ የታሰሩ እያሉ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኞች የሉም የሚል መልስ መስጠታቸው ይቅርታ አድርግልኝ እና የመካድ አካሄድ ነው፡፡ ሆኖም ያንን የመሰለ ምላሽ በመስጠታቸው በጣም ጥቂት የሆኑ ሰዎችን ብቻ ሊያታልሉ ይችላሉ ብዬ ነው የማምነው፡፡

ሰለሞን፡ አብረውሽ የነበሩት ሌሎች እስረኞች ሁኔታስ ምን ይመስል ነበር? አያያዛቸው፣ መንፈሶቻቸው፣ እንዲሁም ሀሰቦቻቸው ምን ይመስል ነበር? በአጠቃላይ እዚያ በነበርሽበት ጊዜ ያለው የእስር ቤት ሁኔታ ምን ይመስል ነበር?

ርዕዮት፡ ወንጀል ለፈጸመ ሰው እና በእስር ቤት ላለ እንዲሁም ምንም ዓይነት ወንጀል ሳይፈጽም በቁጥጥር ስር ውሎ በእስር ቤት ያለ ሰው ሁሉም እስረኞች ቢሆኑም እንኳ ሰብአዊ መብቶቻቸው ሊጠበቁላቸው ይገባል፡፡ መሆን ያለበት ነገር ይህ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ያለው ከምግቡ ሁኔታ ጀምሮ መጥፎ ነገር ነው፡፡ በተለይም በአሁኑ ጊዜ በርካታ እስረኞኝ እየተያዙ እየገቡ እና እስር ቤቱን አጨናንቀውት ባለበት ሁኔታ የሚታየው ነገር ሁሉ አስከፊ ነው፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት እስር ቤት በቆየሁባቸው ጊዚያት ከአጠቃላይ እስረኛ ህዝብ ተነጥለን ከሌሎች አራት እስረኞች ጋር ነበርኩ፡፡ ሆኖም ግን ሌሎች በጣም በተጨናነቀ ሁኔታ ላይ እየተጠበቁ ያሉበት ሁኔተ ነው የሚታየው፡፡ ስለመድኃኒት፣ ስለህክምና ያለው ሁኔታ በቂ ነው የሚባል አይደለም፡፡

የሕክምና ምርመራ የሚባል ነገር የለም፡፡ የህክምና ምርመራ የምታገኘው በከፍተኛ ሁኔታ በምትታመምበት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከዚያ ውጭ ለስቃይ ማስታገሻ መድኃኒቶችን ያዝዛሉ፡፡ በአብዛኛው በእስር ቤቱ ያለው ሁኔታ ይህንን ይመስላል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከፖለቲካ እስረኞች ጋር ሰላምታ ለማቅረብ የሚሞክር ሰው ካለ በርካታ የሆኑ ችግሮችን እንዲጋፈጥ ይደረጋል፡፡ ቦታው የጭንቀት ቦታ ነው፡፡ ከውጭው ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር እንኳ ፍርሀት ንጉስ የሆነበት ግቢ ነው፡፡ በእስር ቤቱ ግቢ ውስጥ የምናየው ነገር እንግዲህ ይህንን ይመስላል፡፡

ሰለሞን፡ በርካታ ችግሮች በምትይበት ጊዜ ምን ዓይነት ችግሮች አሉ? የአካል ስቃይ የማሰቃየት ድርጊቶች ይፈጸማሉን? ድብደባዎች እና ሌሎች ነገሮችም ይፈጸማሉን?

ርዕዮት፡ እኔ እየነገርኩህ ያለሁት ስለሴት እስረኞች ሁኔታ ነው፡፡

ሰለሞን፡ ስለእዚያ ጉዳይ ዘርዘር ባለ ሁኔታ ብትነግሪኝ፡፡ የሴት እስረኞች አጠቃላይ ሁኔታ እና አያያዝ ምን ይመስላል? ከሕግ አግባብ ውጭ የሆነ አያያዝ ፈጸምባቸዋልን?

ርዕዮት፡ አዎ፡፡ይህንን ነው እየነገርኩህ ያለው፡፡ አንድ ሰው የፖለቲካ እስረኛ ጋር ሰላምታ በመለዋወጡ ምክንያት ችግር ሊደርስበት አይገባም ነበር፡፡ ሆኖም ግን ለፖለቲከ እስረኛ ሰላምታ ሲሰጥ ከታዬ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፣ ወይም ደግሞ ስለዚያ እስረኛ ጉዳይ የተለየ ትኩረት በመስጠት ይከታተሉታል፡፡ የተለየ ምርመራ ወይም እንደዚህ ያለ ነገር የሚካሄድበት ሆኖ ይቀመጣል፡፡ አየህ ነገሮች በእስር ቤት እንደዚህ ናቸው፡፡

ሰለሞን፡ የወደፊት ዕቅዶችሽ ምንድን ናቸው? በአጭሩ አጠቃላይ ያለሽ ምልከታ ምንድን ነው? ከዚህ በኋላ ምንድን ለማድረግ ታስቢያለሽ?

ርዕዮት፡ ቀደም ሲል እንደተናገርኩት ይህ ድንገተኛ የመፈታት ነገር ነው፡፡ ስለሆነም የነበረህን ጊዜ አጠናቅቀህ ስትወጣ ወይም በድንገት ስለተፈታህበት ነገር ስታውቅ ነው መናገር የምትችለው፡፡ ስለሆነም በድንገት እስከተፈታህ ድረስ ይህ ጥያቄ ለየት ያለ ሊሆን ይችላል፡፡

ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ የማስበው ነገር ቀደም ሲል ተቋርጦ የነበረውን ህይወቴን እንደገና መምራት መቀጠል ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ምንም ዓይነት ትግል ያካሄድኩ ቢሆንም እንኳ በጽሁፍም ሆነ በማንኛውም በምችለው ነገር ሁሉ ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ የሆነች ኢትዮጵያን እስከማይ ድረስ ትግሌን በተጠናከረ መልኩ እቀጥላለሁ፡፡

(የቃለ መጠይቁ መጨረሻ)፣

ለርዕዮት እና በእስር ቤት ለቀሩት ለሌሎች ወንድሞቿ እና አህቶቿ ያለኝ የእኔ የግሌ አክብሮት፣

ሸክስፒር እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “ጥቂቶች ታላቅ ሆነው ይወለዳሉ፣ ጥቆቶች በሂደት ስኬትን ይጎናጸፋሉ፣ ጥቂቶች ደግሞ በእራሳቸው ላይ በመተማመን ታላቅ ይሆናሉ፡፡“

ለጀግኖች እና ጀግኒቶች በተመሳሳይ መልኩ ማለት ይቻላል ብዬ አስባለሁ፡፡

እንደ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አብርሃ ደስታ፣ የዞን 9 ጦማሪያን እና ሌሎችም እንደ እነርሱ ያሉ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኛ ዜጎች ጀግኖች እና ጀግኒቶች ሆነው አልተፈጠሩም፡፡ ጀግንነትንም አልፈለጉም ነበር፡፡ እድሉ የሚሰጣቸው ከሆነ ጀግንነትን ብቻውን ይተውታል፡፡ ጀግንነት እና ጀግኒነት ሲባል ብቻቸውን መተው ማለት አይደለም፡፡ ዕድል እና እጣ ፈንታ በጀግንነት ላይ ይተማመናሉ፡፡

በርዕዮት ዓለሙ እና በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት የፖለቲካ መሪ በነበረችው በብርቱካን ሚደቅሳ መካከል በርካታ በትይዩ የተሰመሩ ልዩነቶችን አስተውላለሁ፡፡ ብርቱካን ተመሳሳይ የሆኑ ከህግ አግባብ ውጭ የሆኑ የእስር ቤት አያያዞች ማለትም ለብቻ ነጥሎ ማሰር እና ማዋረድ ተፈጽመውባታል፡፡ ብርቱካን በፖለቲካው ዘርፍ የመጀመሪያዋ መንገድ ፈጣሪ ብቻ አልነበረችም ሆኖም ግን ለኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች ሞዴል እና አርአያ ጭምር የነበረች እንጅ፡፡ በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በጽናት በመቆም መንፈሰ ጠንካራነቷን በተግባር በማሳየት ትምህርት ሰጥታለች፡፡

ብርቱካን በአሁኑ ጊዜ እርሷ ተሸክማው የነበረውን ዓይነት ኃላፊነት ርዕዮት ተሸክማ ስታይ በኩራት በመሞላት በኢትዮጵያ የሩጫ ቅብብሎሽ ዱላውን ለሌላ በማስተላለፍ በማበረታታት ትመለከታለች፡፡ በእሳት የተፈተነ ክብር ምሳሌ የነበረች መሆኗን ወደ ኋላ መለስ ብላ ስትመለከት ትንሽ ፈገግ ትላለች፡፡

ርዕዮትን እና ብርቱካንን በማሰር ብቸኛ ኃላፊነቱን መውሰድ የሚገባው እና አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊን ታሪክ የሰይጣን መልዕክተኛ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን የተረገመ እና መቅኖ ያጣ ሰብአዊ ፍጡር ሆኖ ሲታወስ ይኖራል፡፡ ገሀነም በእራሱ እንዳለ ሆኖ መለስ ዜናዊ ሲጨመርበት ግን የገሀነም ገሀነም ይሆናል!

እነዚህ ደፋር ወጣት ጋዜጠኞች እንደ ሌሎች አብዛኞቻችን ሳይሆን የተወሰነላቸውን የዕድል ዕጣ ፈንታ በሚያገኙበት ጊዜ በአካል ጉዳት ስቃይ ወይም በፍርኃት ተሸብበው ወደኋላ አያፈገፍጉም፡፡

እስክንድር ነጋ በራሱ ድረ ገጽ በመጻፉ ብቻ የ18 ዓመታት እስራት ሲበየንበት በመፍራት አንገቱን አልደፋም፡፡

ርዕዮት ዓለሙ የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት የ14 ዓመታት እስር ሲበይንባት በሎሌነት መልኩ አላጎበደድችም፡፡

ውብሸት ታዬ ነጻነቱን ለመቀዳጀት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን አልለመነም፡፡

ተመስገን ደሳለኝ ለነጻነቱ ሲል ነብሱን አልሸጠም፡፡

አበርሃ ደስታ ደስታ ከሚያምንበት ነገር በመፍራት አላፈገፈገም፡፡

በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከመታሰሩ በፊት እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2014 በራሱ የግንኙነት ድረ ገጽ አብርሃ ደስታ ህወሀት እራሱ ነጻነት ያለው ድርጅት እንዲሆን አጥብቆ ተከራክሯል፡፡ ከህወሀት አባላት ጋር ጠላትነት የማልሆንበት ምክንያት የህወሀትን ካድሬዎች የምሁርነት እጥረት እና ክስረት ስለማውቅ ነው ብሎ ነበር፡፡

ሁሉም የኢትዮጵያ ደፋር ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች ሁሉንም ነገር የላይኛው ከንፈራቸው ሳይንቀጠቀጥ ይቀበላሉ፡፡

በምንም ዓይነት መልኩ ለጭቆና አያጎበድዱም፡፡

መሰረታቸውን በመያዝ በጽናት ይቆማሉ፡፡

በፍርኃት እና በባርነት ተቀፍድደው በዘራፊ ወሮበላ አምባገነኖች መዳፍ ስር ነጻነታቸውን ተነፍገው ከሚኖሩ ይልቅ በእስር ቤት ነጻ ሆነው መኖራቸውን መርጠዋል፡፡

ዌንዲ ሸርማን እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኢትዮጵያ በመጎልበት ላይ ያለ ዴሞክራሲ የምታካሂድ ሀገር ናት፡፡“ በአባባላቸው ትክክል ናቸው ሆኖም ግን ጊዜው ገና ነው፡፡

ርዕዮት እና የእርሷ ትውልድ የሚገባቸውን ቦታ ሲይዙ ኢትዮጵያ ትክክለኛ በመጎልበት ላይ ያለ ዴሞክራሲን እውን ታደርጋለች፡፡ ርዕዮት ላለፉት አራት ዓመታት ከ17 ቀናት በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በእስር ስትማቅቅ ባትቆይ ኖሮ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ምን ያህል አስተዋጽኦ ታደርግ እንደነበር የሚያስገርም አይሆንም፡፡

ለእስክንድር ነጋ፣ ለውብሸት ታዬ፣ ለተመስገን ደሳለኝ፣ ለአብርሃ ደስታ እና ለሌሎችም በእስር ቤት በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያን እና የፖለቲካ እስረኞች ታላቅ ክብር አለኝ፡፡

ለኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ጀግኒት እና ለእኔ ኢትዮጵያዊት ጀግና ለርዕዮት ታላቅ ክብር አለኝ!

አምላክ ረዥም እድሜ እንዲያጎናጽፋት እና ትግሏን እንድትቀጥል እመኛለሁ፡፡

“ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ የሆነች ኢትዮጵያን እስከማይ ድረስ ትግሌን በተጠናከረ መልኩ እቀጥላለሁ፡፡” ርዕዮት ዓለሙ፣ እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ሀምሌ 7 ቀን 2007 ዓ.ም

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45063#sthash.fG2fgxNh.dpuf

አርበኞች ግንቦት 7 የከፈተው ወታደራዊ ጥቃት ከወልቃይት ወደ አርማጭሆ በመስፋፋት እንደቀጠለ ነው

Arbegoch Ginbot 7

~የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት~

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ በህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ላይ የከፈተው ወታደራዊ ጥቃት ከወልቃይት ወደ አርማጭሆ በመስፋፋት በእጅጉ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡

ዘረኛውና ፋሽስቱን የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ቡድን በጠብመንጃ አምበርክኮ ህዝቡን ብቸኛው የስልጣን ባለቤት የማድረጉ የትጥቅ ትግል ከኤርትራ በረሃዎችና ጠረፎች አልፎ በኢትዮጵያ መሬት ላይ በአስተማማኝ ሁኔታ እግሩን በመትከሉ ህወሓት ለእርድ ያሰናዳው ሰራዊት ከአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ብቻ ሳይሆን ከወልቃይትና አርማጭሆ ህዝብ በያቅጣጫው እየተከፈተበት የሚገኘውን ፋታ የሌለውና ጠንከር ያለ የተኩስ ናዳ ፈፅሞ መቋቋም አልቻለም፡፡

ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በአውቶብስ እያጋዘ ሰሜን ኢትዮጵያ ላይ ያከማቸው መከላከያ ሠራዊቱ የአርበኞች ግንቦት 7 ጀግና የነፃነት ፋኖዎች ከህዝብ ጋር ተቀናጅተው ባልጠበቀው ጊዜና ሁኔታ የሚከፍቱበትን የጎሬላ ውጊያ ጥቃት ገና ካሁኑ መመከት ተስኖት ከጦር ሜዳ መሸሽ እና መክዳት በመጀመሩ ህወሓት እንደ ድጋፍ ሰጪም እንደተወርዋሪም የሚጠቀምባቸውን የፌደራል ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል፣ ፀረ-ሽምቅ እና ሚሊሻ ኃይሎችን በተጓዳኝ በገፍ አስፏል፡፡

መከላከያን ጨምሮ በእነዚህ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች መካከል አለመረጋጋት እና በራስ አለመተማመን የወለደው የለየለት መተራመስ በመስፈኑ በህዝቡና በአርበኞች ግንቦት 7 የጎሬላ ተዋጊዎች እየደረሰባቸው ሚገኘውን ጥቃት ተቀናጅተው መመከት አልቻሉም፡፡

በመሆኑም ከትናንት በፊት ሀምሌ 3 2007 ዓ.ም ታች አርማጭሆ ጎደቤ ላይ ልዩ ኃይል እና ፀረ-ሽምቅ ጎራ ለይተው በመሰላለፍ እርስበርሳቸው ውግያ ውስጥ ገብተው በጥይት ተጠዛጥዘዋል፡፡ በእነኚህ ተስፋ የቆረጡ ሁለት የታጠቁ ኃይሎች መካከል በተደረገው ለሰዓታት የዘለቀ ውግያ በትንሹ ስድስት አባላት ሲሞቱ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ አርበኛ ታጋዮች ህወሓት በገፍ ያሰለፈውን የመከላከያ፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል፣ ፀረ-ሽምቅ እና ሚሊሻ ጦር መውጭያ መግቢያና ማረፊያ ነስተው ቁምስቅሉን ከማሳየታቸው ጎን ለጎን የድርጅቱን ህዝባዊ ዓላማ እና ፕሮግራም በበራሪ ወረቀት መልክ ከመተማ እስከ ጎጃም ለሚገኘው ህብረተሰብ በማድረስ ላይ ይገኛሉ፡

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44988#sthash.tAxRdshW.dpuf

የዘረኞች ባንዲራ ቤቱ ሙዚየም ነው! (ታሪኩ አባዳማ)

ታሪኩ አባዳማ – ሐምሌ 2007

በዩኤስ አሜሪካ የግንጠላ ታሪክ ውስጥ ጎልቶ የሚታወቀው የደቡብ ክፍለ ግዛት ባሪያ አሳዳሪ ነጮች እንቅስቃሴ ነፀብራቅ የነበረው ባንዲራ እንዳይወጣ ሆኖ ወረደ። የደቡብ ካሮላይና ግዛት ምክር ቤት በወሰነው መሰረት ለምዕተ ዓመት ሲውለበለብ የነበረው የኮንፌዴሬት ዘረኛ ባንዲራ በቄንጠኛ ስርዓት ከተሰቀለበት ወርዶ ወደ ሙዚየም ተልኳል – የዘረኞቹ ባንዲራ ዘላለማዊ ቦታውን ተጎኗፅፏል። የ19ኛው ክፍለ ዘመን ባሪያ አሳዳሪ ዘረኛ ግፈኞች የሰቀሉት ባንዲራ ዛሬ ቢወርድም በራሳችን አገር በ21ኛው ምዕተ ዓመት በየመንደሩ ተፈብርከው የተሰቀሉ መርዝ የሚነሰንሱ ዘረኛ ባንዲራዎች ደግሞ ተራቸውን እየጠበቁ ነው።Ethiopian racist flag

የደቡብ ካሮላይና ተገንጣዮችን ከኛ አገር ተገንጣዮች የሚለያቸው ነገር ቢኖር የቆዳ ቀለማቸው ብቻ ነው። እርግጥ ነው እኛ አገር ዘረኛ ተገንጣዮች የመንግስት ስልጣን ለመጨበጥ እና ያሻቸውን አስገንጥለው የቀረውንም በዘር ግንድ ከፋፍለው እያንዳንዱ ባንዲራ እንዲነሰንስ ብቻ ሳይሆን አንዱ ሌላውን ዘር ላይ በተመረኮዘ ጥላቻ እና ጥርጣሬ ተፋጦ እንዲቀመጥ ማድረግ ችለዋል – የደቡብ ካሮላይና ዘረኞች ግን የግንጠላ አላማቸውን ማሳካት አልበቁም። በተባበረው አሜሪካ አንድነት ሀይል ክንድ ተደቁሰው የግንጠላ ባንዲራቸውን ግን ታቅፈው ነበር የቆዩት። ዘረኝነት በደም ሲወርድ ሲወራረድ መጥቶ ያንን ጦሰኛ ባንዲራ ከለላ ያደረገ ነጭ ዘረኛ ዘንድሮ እንኳ የዘጠኝ ጥቁሮችን ደም ከደጀሰላም በግፍ አፍሷል – ባንዲራው ሰላምን እና ፍቅርን ሳይሆን ጥላቻ እና ቂም ሲነሰንስ መኖሩን የተረዱ የዛሬው ዘመን አሜሪካውያን ባንዲራውን ከከረፋ ፀያፍ ታሪኩ ጋር ቦታህ ሙዚየም ነው ብለውታል። የፈጀውን ጊዜ ይፈጃታል እንጂ ዘረኞች የሰቀሉት ባንዲራ የትም ይሁን የት ከገፀ-ምድር ተፍቆ አንድ ቀን ወደ ሙዚየም መግባቱ አይቀሬ መሆኑ የተረጋገጠበት አጋጣሚ ነው። ተተኪው ትውልድ ውደ ሁዋላ ዞር ብሎ ሲያይ ማን በትክክለኛው የታሪክ ጎዳና ላይ እንደቆመ እንዲህ ይመሰክራል።

ብሔራዊ ሰንደቅ አላማ አንድ ሉአላዊ አገር የሚታወቅበት የሚገለፅበት መለያ መታወቂያ አምድ ነው። ሁሉም ዜጎች ራሳቸውን ከብሔራዊ ሰንደቅ አላማ ጋር የሚያስተሳስሩበት ታሪካዊ አጋጣሚ አለ። ባንዲራችን የማይደለዝ የማይሰረዝ ነው ስንል ባንዲራውን ተሸክመው ያገራችንን ነፃነት ፣ አንዲት አትዮጵያ ብለው ዳር ድንበር እና ክብር ሲጠብቁ ፣ ሲያስከብሩ ለነበሩ ጀግኖች ያለንን ክብር ማረጋገጣችን ነው።

ከአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ በስተጀርባ የሚታየኝ ባልቻ አባነብሶ መድፉን አነጣጥሮ የጣሊያንን ወራሪ ጦር ሰፈር ሲያነውጥ ነው ፣ ከባንዲራው በስተጀርባ የሚታየኝ እምቢኝ ለአገሬ ብሎ ማይጨው ላይ በመርዝ ጪስ የተጠበሰው ዜጋ ነው – ከባንዲራው በስተጀርባ የሚታየኝ የዚያድ ባሬን ወረራ ለመመከት ሳያሰልስ ቆርጦ የተመመው ከሁሉም የአገሪቱ ክልል የፈለቀው ጀግና ሰራዊት ነው ፣ ከባንዲራው በስተጀርባ የሚታየኝ መሬት ላራሹ ብሎ ፍትሀዊ አስተዳደር እንዲሰፍን የታገለው ትውልድ ነው ፣ ከባንዲራው በስተጀርባ የሚታየኝ የዕውቀት ብልጭታን ለመፈንጠቅ በመላ ገጠር ኢትዮጵያ የዘመተው የእድገት በህብረት ዘማች ነው… እኔ ከባንዲራው በስተጀርባ ደርግም አፄውም አይታዩኝም – አበበ ቢቂላ በሉት የጥቁር አንበሳው ጦር መሪ ኮለኔል በላይ ገብረአብ ወይንም በላይነህ ዴንሳሞ ባንዲራችንን በኩራት ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ የነበረው የአንድነታችን እና የነፃነት ክብራችን መግለጫ ስለሆነ ብቻ ነው። ከብሔራዊ ባንዲራ በስተጀርባ ያለው ህዝብ እና አገር ናቸው። ባንዲራ ለድሀው ሆነ ሀብታሙ ፣ ለገዢው ሆነ ተገዢው ፣ ለገበሬው ሆነ ወዛደሩ ፣ ለተማረው ሆነ ለመይሙ ፣ ጠግቦ ለሚያድረው ሆነ ለተራበው ሳይቀር ለሁሉም እኩል ትርጉም ሊኖረው ይገባል። አለበለዚያ ካንድ ያገሪቱ ጫፍ የተነሳ የጦር አበጋዝ እሱ የመሰለውን ጨርቅ ጠቃቅሞ በብረት ያስገበረውን ሁሉ ይሔ ባንዲራህ ነው ቢል ውሎ አድሮ የሀይል ሚዛን ያጋደለ ጊዜ ውጤቱ አያምርም…

ደቡብ ካሮላይና ትመስክር!!

በኢትዮጵያ ብቻ ዘረኛ የጦር አበጋዞች የበላይነት ተቀዳጅተው ዘረኝነትን በግልፅ የሚያንፀባርቁ ፣ ሲሻቸው አገር መበታተን እንደሚችሉ በህግ የተፈቀደላቸው ሀይሎች ባንዲራ እያወለበለቡ ነው። ህወሀት ባንዲራ አለው – የህወሀት ባንዲራ ከትግራይ እና ከኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ እና ማህበራዊ ግንኙነት አንፃር ለማንኛውም ሰው ግልፅ ሆኖ የሚታይ መግለጫ የለውም። ህወሀት ግን ባንዲራ አስፈልጎት ነበር – ኢትዮጵያን ከባዕድ ጠላት ለመታደግ ሳይሆን ይልቁንም የኤርትራን መገንጠል ለማቀላጠፍ ፣ የሌሎችንም ግንጠላ ለማመቻቸት – ህወሀት በቀሰቀሰው እርስ በርስ ውጊያ የተጠቁት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው – ኢትዮጵያ አንድነቷ ይጠበቅ ያሉ ወገኖች ደም ነው የፈሰሰው።

እናም ኢትዮጵያን ወደብ አልባ አድርጎ ማስቀረት ብቻ ሳይሆን የመኖር ዋስትናዋ እንዲዋዥቅ የሚያረጋግጥ ባንዲራ በየመንደሩ በግዴታ እየተውለበለበ ነው። በየመንደሩ የተሰቀለውን የተጠቃቀመ ጨርቅ ከነ ግሳንግሱ ጥላቻ እና ቂሙ ጋር ሙዚየም ማውረድ የዚህ ትውልድ ሀላፊነት ነው። ጥላቻ እና አለመታማመን ብሎም ዘረኝነት በየመንደሩ ተክሎ ስለ ብሔራዊ ኩራት እና ታሪክ ማውራት አይቻልምና!

እርግጥ ነው ከብሔራዊ ባንዲራ ሌላ ክፍለ አገራት ወይንም የግዛት ክልሎች የራሳቸውን ሰነደቅ አላማ እንደ አስፈላጊነቱ ይቀርፃሉ። በተግባር እንደምናየው በሰለጠነው አለም ሳይቀር ክፍለ አገራት የክልላቸውን ታሪዊ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ እውነት የሚያንፀባርቅ ባንዲራ ያውለበልባሉ። ለምሳሌ ካናዳ እያንዳንዱ ክፍለ አገር ከብሔራዊ ባንዲራ ዝቅ ብሎ የሚሰቀል የራሱ ባንዲራ አለው – በዘር ላይ የተመረኮዘ ሳይሆን ባንድ ታሪካዊ አጋጣሚ በተሰመረ ድንበር ክልል ያለውን ልዩ ልዩ ባህል እነ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ ዜጋ የሚያንፀባርቅ። በአለም ላይ የዘር ባንዲራ በህግ ተገዶ የሚውለበለብባት አገር የወያኔይቱ ኢትዮጵያ ብቻ ናት። የትግራይ ፣ የኦሮሞ ፣ የአማራ ፣ የቤንሻንጉል… ባንዲራ ተብሎ ዘረኝነት ፣ ጥላቻ ፣ ቂም በየመንደሩ እየተነሰነሰ ነው። ትናንት ለኢትዮጵያዊነት ህልውና መረጋገጥ ህይወታቸውን የሰዉ የሁሉም ክልል ዜጎች ክቡር መስዋዕትነታቸውን የሚመሰክረው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ተፍቋል ፣ ኮስምኗል – ተደልዟል!!

‘በባንዲራ አምላክ’ ብሎ ጥቃት የመጣበት ዜጋ ሁሉ አጥቂውን መገዘት ማስቆም ይችል እንደነበር እናውቃለን – ይህም ባንዲራ እንደ በላይ ህግ እና አገራዊ ክብር መግለጫ መሆኑን ያመለክታል። በክብር ተይዞ የቆየውን ባንዲራ ጨርቅ ብቻ መሆኑን ያስገነዘበን ሟቹ ዘረኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ያንን ታሪካዊ ባንዲራ ይበልጥ ለማራከስ ሲል ከለከት ቢስ ቃላት ባሻገር በዘር ላይ የተመረኮዙ አስራ ሁለት የዘር ባንዲራዎች አስታቅፎናል – ከየመንደሩ የመለመላቸው ባንዳዎች ጨርቁን ጠቃቅመው ሰቅለዋል። አውርዶ ወደሙዚየም መላክ የዚህ ትውልድ ሀላፊነት ነው። በህግ የበላይነት ላይ የታነፀች ፣ በታሪኳ የምትኮራ አገር መሰርቶ ማለፍ የዚህ ትውልድ ሀላፊነት ነው።

የዛሬ ሀያ አራት ዓመት የዲሞክረሲ ዝንጣፊ በወያኔ አንቀልባ ታዝሎ የመጣልን መሆኑም ተነገረን – የነፃ ሀሳብ ፣ የነፃ ምርጫ ተስፋ ፣ እኩልነት ፣ የነፃ መደራጀት ፍላጎት ፣ የነፃ ሰለፍ መውጣት… ሁሉም ፖለቲካዊ ጥያቄ በነፃ ይፈታል ሲሉ ነገሩን – መገንጠል እንኳ ነፃነት መሆኑን አረዱን። ውሎ ሳያድር ብሶቱን ለመግለፅ አደባባይ የወጣን ዜጋ ‘… ክልደከመው ባንዲራውን ቀስሮ ሲዞር ይዋል…’ ሲል መለስ ዜናዊ አላገጠ። ዲሞክረሲ የሚባል ነገር ከቶውንም እንደሌለ ጆሮ ላለው ሁሉ ይፋ አደረገ።

ስልጣን በያዙ ሰሞን አያያዙን አላልተው ሲያይ መብት የተጎናፀፈ የመስለው ዜጋ የመሰረት ድንጋዩ ቀስ በቀስ እየተመዘዘ እንደተቦረቦረ ሲመጣ ጫጫታ ብናበዛ ትርፉ… ግመሎቹ ይጓዛሉ አይነት አደንቋሪ የወያኔ ትዝብት ላይ መውደቅ ነው። ዲሞክረሲ ስሙ ሸጋ ነው – ስለሆነም በሚያምር ፣ በሚያማልል ስሙ ለመጠራት ወያኔን ጨምሮ የማይመኝ የፖለቲካ ሀይል በምድር ላይ አለ ማለት አይቻልም።

ልጅ እግር ዲሞክረሲ ፣ ወጣት ዲሞክረሲ ፣ ጎምቱ ዲሞክረሲ ፣ ሰሞኑን አንድ ሀተታ የለጠፈ የወያኔ ሹም ደግሞ አምሰት መቶ ዓይነት ዲሞክረሲ እንዳለ ነግሮናል። በአለም ላይ ያሉ አገሮች አምስት መቶ አይሆኑም እንጂ የትኛው የት አገር የቱ እንደተሰራበት ንገረን ብለን በጠየቅነው። ይኼ ሁሉ ግን ወያኔ መደበቂያ ፍለጋ ሲል የዲሞክረሲን መሰረታዊ እሴቶች ለማድበስበስ የሚጠቀምበት የድንቁርና አካሄድ ነው ከማለት ሌላ ማለት አይቻልም። አምስት መቶ ዓይነት ዲሞክረሲ አለ ማለት አንዱን ተግባር ላይ እያዋልን ነን ለሚል ቅጥፈት ያመቻቻል። ለዲሞክረሲ ያለተፈጥሮው ስም ያወጡለታል – መምሰል እና ሆኖ መገኘት ለየቅል መሆኑን ዘንግተው ያምታታሉ። በመሰረቱ አንድ ነገር ወጣት ነው ሲባል ትርጉሙ ትኩስ ጉልበት ያለው ፣ ሮጦ የማይደክመው ፣ ለማወቅ ለመማር ያለው ፍላጎት የገዘፈ ፣ ሙሉ ሀይሉን ተጠቅሞ በሁሉም መስክ ስኬት ለማስመዝገብ የማይታክት ማለት ነው።

ወጣት ዲሞክረሲ?

ወጣት ማለት ከቁመና ማማር ጀምሮ በሚያፈልቃቸው ጥያቄዎች ልክ መልስ ለማግኘት የማይታክት ነው። ታዲያ ዲሞክረሲው ወጣት ነው ካልን ልፍስፍስ ፣ ውሽልሽል ፣ ግራ የተጋባ ፣ ቁርጠኝነት የሚጎድለው ለውድቀቱ ሁሉ ሌሎችን የሚከስ ፣ አስመሳይ እና የመድረክ ተዋናይ እዩኝ ባይ አይነት ብቻ ሲሆን እንዴት ሆኖ ዲሞክራሲያዊ ይሰኛል?… ዲሞክረሲ እና የህግ የበላይነት የማይነጣጠሉ ያንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች መሆናቸውንስ ማን ይዘነገዋል? በዚህስ ተዘናግቶ ራስን ማታለል እሰከመቼ ይቀጥላል?

ዲሞክረሲ ዕለት-ተለት የሚኖሩት ማህበራዊ አደረጃጀት ብቻ ሳይሆን ዳይናሚክ በሆነ የማያቋርጥ እንቅስቃሴ ሂደት ለዜጎች ሰብአዊ ክብር መረጋገጥ እና የተሻለ አኗኗር መስፈን ተስፋ የሚዘራ የዕድገት መደላደል ነው። ካንዱ ዘመን ወደ ሚቀጥለው ሲሸጋገር ዜጋው በህግ ጥላ ስር ሙሉ መብቱ ይበልጥ እየተረጋገጠ መሄዱን ፣ ሰብአዊ ክብር ተፈጥሯዊ ፀጋ እንጂ ጉልበተኛ ሹም እንደ ራስ ምታት መድሀኒት እየመጠነ የሚሰጠው ኪኒን አለመሆኑን የሚያመለክት ማሳያ መስተዋት ነው… ዲሞክረሲ የሚዳብረውም ሆነ የሚጎለብተው ግን መጀመሪያ ህልውና ሲኖረው ብቻ ነው።

ዲሞክረሲ ጭብጥ ነው። ጭብጥ ሆኖ ካልዳሰሱት ፣ ካላዩት ፣ ካልኖሩት እንደ መንፈስ እንደ ትንተና ዘዴ በፖለቲከኞች ምላስ ብቻ የሚንበለበል ቀመር አይደለም።ዲሞክረሲ ህልውና እንዲኖረው ፖለቲካዊ ብስለት ብቻ ሳይሆን ፖለቲካ ቁርጠኝነትም ይጠይቃል – ስለሆነም ዲሞክረሲ በተጨባጭ የህግ የበላይነት ማለት ነው – ማንም ከህግ በላይ አለመሆኑ የተረጋገጠበት ህብረተሰብ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ሊባል ይችላል – ይህ በሌለበት ቦታ ግን ዲሞክረሲ የለም – ከሌለ ደግሞ የለም።

በህግ ጥላ ስር መኖር ለተረጋጋ ማህበራዊ ህይወት መሰረት ነው። የሀሞራቢ ህግ አይን ያጠፋ አይኑ ይጠፋል ሲል – ማንም ይሁን ማን በዚያ ግዛት ክልል ነዋሪ የሆነ ዜጋ ሁሉ የዚህ ህግ ተገዢ ይሆናል ማለት ነው – ከዚህ አንፃር ህግ የሰፈነበት ህብረተሰብ ነበር ማለት ያስደፍራል። አይን አጥፍቶ አይኑ ያልጠፋ ሰው በሀሞራቢ ዘመን ከተገኘ የፍርድ መጓደል ተከስቷል ማለት እንጂ እንዴት አይነት ጨካኝ ህግ ነው? የሚል ትችት ሊቀርብ አይችልም። የሀሞራቢ መንግስት አይን ካላጠፋህ አይንህን አያጠፋም – አሸባሪ ሳትሆን ስም አይለጥፍብህም። መገንጠል መብት ነው ብሎ በደማቅ ብዕር ህግ ያወጣ የፖለቲካ ሀይል ያንን ህግ መልሶ ከረገጠ ለህገወጥነት መንሰራፋት ትልቁ ማሳያ ነው። ራሱ ደንግጎ ያወጣውን ህግ የሚረግጥ ህግ አውጪ እና አስፈፃሚ መንግስት ዞር ብሎ በህግ እየገዛሁ ነው ማለት አይችልምና። ያን አይነቱ መንግስት የወሮበላ መንግሰት ይባላል። ወሮበሎች ከተደራጁ እና በበቂ ከታጠቁ የመንግሰት ስልጣን መቀማት ይችላሉ… የሚከተለው ምን እንደሆነ ግን የወያኔ አስተዳደር በቂ ማሳያ ነው። ሲፈልግ ያስርሀል ፣ ስም ያወጣልሀል… አሸባሪ ቂብጢርሶ ይልሀል – ደግሞ በል ሲለው ነፃ ነህ ብሎ ከወህኒ ይለቀሀል – የቱጋ ነው ህግ የተከበረው? እስከመቼስ ነው ሲሻቸው እንደበግ ጎትተው ሲያስሩ ሲፈቱን የሚቆዩት – እስከመቼስ ነው የዘረኞች ባንዲራ በየመንደሩ ሲነሰነስ የምናየው?

በድንጋይ ዳቦ ዘመን ተፈጥሯዊ የስራ ክፍፍል ከመኖሩ በስተቀር የሰው ልጅ መዋቅራዊ አስተዳደር ለመዘርጋት የቻለበት ደረጃ ላይ አልነበረም። ሰው ይኖር የነበረው ለመብላት – የሚበላውም ለመኖር ነበር።

ለምግብ ዋስትና ሲባል መባላት ያኔ ጥንት ጭምር የነበረ መሆኑን ማንሳቱ ተገቢ የሆነበት ዘመን ላይ ነን። ሰው እየበላ ደግሞ እየተባላ ወዲህም እያሰበ እየተሳሰበ – ደግሞ እየበላ ህልውናውን አቆይቷል። ዛሬ ዛሬ ደግሞ ነገሩ ተሻሽሏል – ቀለቡንም ተቀላቢውንም ለመቆጣጠር ነፃ አውጪ ሰራዊት ማሰለፍ። ተጋድሎ ተሟሙቶ መሬት መቆጣጠር ማስገበር – የገበረ ህዝብ ምርኮ ነው – አስገባሪው እንደፈቀደ ያሳድረዋል። ምርኮኛ ህዝብ የሚያዝበት ንብረት የለውም – ከመሬቱ ቢያፈናቅሉት ፣ ከአገር ቢያሰድዱት… ባንዲራውን እንኳ ቀምተው የነሱን ዘረኛ ባንዲራ ያውም የተወጋበትን ፣ በቁሙ የተዋረደበትን ፣ እና የተበደለበትን እንዲያወለበልብ ቢያስገድዱት ምርጫ የለውም – ልጆቹ ለብሔራዊ ክብሩ እና ነፃነቱ መረጋገጥ በፍልሚያ የወደቁለትን ባንዲራ ቀምተው የነሱን ዘረኛ የቂም እና በቀል ባንዲራ ያስታቅፉታል።

በደቡብ ካሮላይና የተጀመረው የዘረኞችን ባንዲራ ወደ ሙዚየም የመላክ እርምጃ ተከትለን ዘር እና ጎጥ ቆጥረው የተደራጁ የዚህ ዘመን ደናቁርት የተከሉብንን የጥፋት ባንዲራ ፈጥነን እናውርድ – ወደ ተፈጥሯዊ ቤቱ ወደ ሙዚየም እንላከው!!

የኢትዮጵያ ህግ ልዕልና – ከአሜሪካ ፕሬዘዳንት ክብር በላይ ሊሆን ይገባዋል

በስደት ከሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች የሰሞኑን የጋዜጠኞች መፈታት መነሻ በማድረግ ከዚህ የሚከተለውን መግለጫ ሰጥተዋል።የመግለጫውን ሙሉ ቃል በPDF ለማንበብ እዚህ ላይ መጫን ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞችን “አሸባሪዎች” ብሎ በማሰር እና ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ የኢህአዴግ መንግስት ያላቋረጠ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሲፈጽም ቆይቷል። ይህን የሰብአዊ መብት መተላለፍ በመቃወም፤ በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆን ወገናቸን ታድገዋል። ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ብቻ፤ “አሸባሪ” ተብለው በእስር ሲማቅቁ ከነበሩት ጋዜጠኞች እና ጦማርያን መካከል ተስፋለም ወልደየስ፣ ዘላለም ክብረት፣ አስማማው ሀ/ጊዮርጊስ፣ ርዕዮት አለሙ፣ ማህሌት ፋንታሁን እና ኤዶም ካሳዬ ተፈትተዋል።

የእነዚህ ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማርያን መታሰር ከልብ አሳስቧቹህ፣ በማበራዊ ድረ ገጾች፣ በጽሁፍ፣ በቃል እና በሰላማዊ ሰልፍ ጭምር ድምጻቸውን ያሰማችሁላቸው በሙሉ፤ እነሆ የአምላክ ፈቃድ ሆኖ ድምጻቹህ ተሰምቷል። ጋዜጠኞቻችን በከፊል ተፈተዋል። ሆኖም ዛሬም ቢሆን ሰባት ጋዜጠኞች እና ጦማርያን፤ “አሸባሪዎች” ተብለው ክስ ተመስርቶባቸው፤ ከአመት በላይ በእስር ላይ በመማቀቅ ላይ ናቸው። እነዚህ ጋዜጠኞች፡

1- እስክንድር ነጋ
2- ውብሽት ታዬ
3- ተመስገን ደሳለኝ
4- አቤል ዋበላ
5- ናትናኤል ፈለቀ
6- በፍቃዱ ሃይሉ
7- አጥናፍ ብርሃኔ ሲሆኑ፤ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ ጋር ደግሞ – ያሲን፣ የሱፍ ጌታቸውና አቡበኩር አለሙ የተባሉት ጋዜጠኞች “አሸባሪ” ተብለው ታስረዋል። እነርዕዮት አለሙ በተፈቱበት ምሽት ደግሞ ጋዜጠኛ ሃብታሙ ምናለ ከቤቱ ታፍኖ ተወስዶ፤ በእስር ላይ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል እና ሃሳብን በነጻነት መግለጽ በጨለማ ውስጥ እንደሚበራ ጭላንጭል የጧፍ መብራት ነው። ኢህአዴግ – ይህን በሚሊዮኖች መስዋዕትነት የተገኘ የነጻነት ጭላንጭል ካዳፈነው፤ የህዝቡ ቀጣይ አማራጭ አመፅ እና የትጥቅ ትግል መሆኑ በተግባር እየታየ መጥቷል።

ከኢትዮጵያዊነት ባህል ውጪ የሆነውን፤ አሸባሪ ህግ አርቅቆ እና በአዋጅ አሳውቆ – የኢህአዴግ ተቃዋሚን “አሸባሪ” ብሎ የማሰር መጥፎ ባህል ከስሩ ሊነቀል ይገባዋል። ይህ ካልሆነ – በአገሪቱ ውስጥ እየታየ ያለው የጦርነት ጭስ፤ ሰላማዊውን ሰማይ ሙሉ ለሙሉ ሳያጠቁረው በፊት፤ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባሎችን በመፍታት ውጥረትን ማርገብ ብልህነት ነው። ይህ ካልሆነ ግን ያለወንጀላቸው “አሸባሪ” ተብለው በእስር ላይ ለሚገኙት ዜጎችን ሲሉ፤ እሳት ለመጨበጥ የጨከኑ እጆች መኖራቸውን መዘንጋት ከታሪክ አለመማር ይሆናል።

በአጠቃላይ ጋዜጠኞች ሃሳባቸውን በጽሁፍ ስለገለጹ፤ በአሸባሪነት ታስረው ቆይተዋል። ቀሪዎቹም ለአሜሪካ ፕሬዘዳንት ክብር ተብሎ ሳይሆን፤ ስለህግ እና ፍትህ ልዕልና ሲባል – ሊፈቱ ይገባል።

በመጨረሻም – በአሁኑ ወቅት ከእስር ለተፈቱት ጋዜጠኞች እና ቤቴቦቻቸው፤ “እንኳን ደስ አላቹህ” እያልን፤ እስር ቤት የተውናቸውን ዜጎች ነጻ የማውጣቱ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በስደት የሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች

በድንገት ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር የተለቀቁ ጦማርያንና ጋዜጠኞች ጉዳይ እያነጋገረ ነው

– መንግሥት ‹‹ክሴን አቋርጫለሁ›› ከማለት ባለፈ ምክንያቱን ከመናገር ተቆጥቧል

ከአንድ ዓመት በፊት ሚያዝያ 26 እና 27 ቀን 2006 ዓ.ም. በድንገት ተይዘው ከታሰሩ በኋላ፣ በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸውና የሰነድና የሰው ማስረጃ ቀርቦባቸው፣ ለብይን የተቀጠሩበትን ቀን እየተጠባበቁ ከነበሩት አሥር ተከሳሾች መካከል አምስቱ በድንገት ሐምሌ 1 እና 2 ቀን 2007 ዓ.ም. መፈታታቸው እያነገጋገረ ነው፡፡

ለተከሳሾቹም ሆነ ወክለዋቸው ለሚከራከሩላቸው ጠበቆቻቸው ምንም ዓይነት መረጃ ሳይደርሳቸው በድንገት፣ ‹‹ዓቃቤ ሕግ ክሱን አቋርጣል፡፡ በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ከእስር ተለቃችኋል፤›› የተባሉት ተከሳሾች ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪያን ዘለዓለም ክብረትና ማህሌት ፋንታሁን ናቸው፡፡ ክሱ እንደተቋረጠ በማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ከማወቃቸው በስተቀር፣ ከክሱ ሙሉ በሙሉ ነፃ ስለመሆናቸው ወይም በተፈለገ ጊዜ በዚሁ ክስ የሚከሰሱ ስለመሆኑ የሚያውቁት  ነገር እንደሌለ ተገልጿል፡፡

ተከሳሾቹ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(2) ማለትም የኅብረተሰቡን ወይም የኅብረተሰቡን ክፍል ደኅንነት ወይም ጤና ለከፍተኛ አደጋ ማጋለጥ፣ በንዑስ አንቀጽ 4 ማለትም የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም በማቀድ፣ በመዘጋጀት፣ በማሴርና በማነሳሳት ሙከራ፣ እንዲሁም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) ሀ እና ለን በመተላለፍ፣ በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር፣ በመላ ሐሳባቸውና አድራጎታቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን መጠርጠራቸውን ጠቅሶ ዓቃቤ ሕግ ክስ አቅርቧል፡፡ ጉዳይዋ በሌለችበት እየታየ ካለችው ጦማሪ ሶልያና ሽመልስ በስተቀር በሁሉም ተከሳሾች ላይ 18 የሰዎች ምስክሮች፣ የሰነድ፣ የሲዲና ቪሲዲ ማስረጃዎችንም አቅርቦ ጨርሷል፡፡ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ይዟል፡፡ ነገር ግን በፌዴራል ማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን በመከታተል ላይ ካሉት ዘጠኝ ተከሳሾች ውስጥ፣ ከላይ የተጠቀሱት አምስቱ ተከሳሾች ሐምሌ 1 እና 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ከእስር ተፈተዋል፡፡

ተከሳሾቹ ከእስር የተፈቱት የኢፌዴሪ አስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 16(6) መሠረት፣ ፍትሕ ሚኒስቴር በቂ ምክንያት ሲኖረው በሕግ መሠረት ክሱን ማቋረጥ እንደሚችል የሚገልጸውን ድንጋጌ ተጠቅሞ ክሱን በማቋረጡ ነው፡፡

ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ለፍትሕ ሚኒስቴር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በተከሳሾቹ ላይ የመሠረተውን ክስ ያቋረጠ ቢሆንም፣ አዋጁ ‹‹በቂ ምክንያት ሲኖረው በሕግ መሠረት ክሱን ያነሳል›› ለሚለው በየትኛው ሕግ እንደሆነ ዝርዝር ማብራሪያ አለመስጠቱ የሕግ ባለሙያዎችም ግልጽ እንዳልሆነላቸውና ግራ እንዳጋባቸው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ‹‹በቂ ምክንያት ማለት ምን ማለት ነው?›› የሚል ጥያቄ የሚያነሱም አሉ፡፡

የተከሳሾቹ ክስ የተቋረጠው ከፍትሕ ሚኒስቴር መዝገቡን እየመረመረ ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በተጻፈ ደብዳቤ መሆኑን፣ ፍርድ ቤቱም የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ተከሳሾቹን እንዲፈታ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት እንደሆነ በመገለጹ፣ ሪፖርተር ማብራሪያ ለማግኘት ፍትሕ ሚኒስቴር በመሄድ ጠይቋል፡፡ የፍትሕ ሚኒስትሩም ሆኑ ሚኒስትር ዴኤታዎች በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ መሆናቸው በመገለጹ ምላሽ ማግኘት አልተቻለም፡፡ የኮሙዩኒኬሽን ማስተባበሪያ ኃላፊው አቶ ደሳለኝ ተሬሳ የተከሳሾቹ ክስ በአዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 16(6) መሠረት መቋረጡን ከመግለጽ ባለፈ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት አልቻሉም፡፡

መንግሥት በተከሳሾቹ ላይ የጀመረውን ክስ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ማቋረጡን ከመናገር ባለፈ፣ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት መቆጠቡ ተፈቺዎችም ሆኑ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ውዥንብር ውስጥ መግባታቸውን እየተናገሩ ነው፡፡ ተከሳሾቹ በድንገት ክሳቸው ተቋርጦ በመፈታታቸው ደስተኛ ቢሆንም፣ ክሱ ሲቋረጥ ሙሉ በሙሉ ነፃ ስለመሆናቸው ወይም በድጋሚ የሚከሰሱበት ስለመሆኑ አለመገለጹ ግራ የሚያጋባ በመሆኑ፣ የሚመለከተው አካል ግልጽ ማድረግ እንዳለበት አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡ ተፈቺዎቹ ‹‹በነፃ ተፈትተናል ብለው ያለምንም ሰቀቀን መኖር ይችላሉ? ተፈቺዎቹና ጠበቆቻቸው ክሱ ስለተቋረጠበት ምክንያት ማወቅ የለባቸውም? ያለምንም ማብራሪያ ብድግ ብሎ ክሴን አንስቻለሁ ማለት ምን ማለት ነው? ሕጉ በቂ ምክንያት ወይም ጥሩ ምክንያት (Good Cause) ሲል ምን ማለቱ ነው?›› የሚሉ ጥያቄዎች ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የሕግ ባለሙያ አንስተው፣ በቂ ማብራሪያ እንደሚያስፈልገው አሳስበዋል፡፡

ከእስር ከተፈቱት መካከል ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እንዴት እንደተለቀቁና ስለመለቀቃቸው ቅድመ መረጃ እንደነበራቸው ወይም እንደሌላቸው ሪፖርተር ላቀረበለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ፣ እሱና ሌሎቹ ታሳሪዎች እስከተለቀቁበት ሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ 10፡30 ሰዓት ድረስ፣ ምንም የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው የሰነድ ማስረጃዎች ላይ የትችት ማብራሪያ ማቅረብ እንደሚችሉ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የመጀመሪያ የትችት ጽሑፋቸውን ለጠበቆቻቸው ሰጥተው፣ የመጨረሻውን (በጠበቆች ተጽፎ ለፍርድ ቤቱ የሚሰጠውን ትችት) ለማየት ጠበቆቻቸውን እየተጠባበቁ እንደነበሩ ተናግሯል፡፡ በተጠቀሰው ሰዓት በእስር ላይ የሚገኘው አጥናፍ ብርሃኔና እሱ ባሉበት ዞን መዝናኛ አዳራሽ ውስጥ ሆነው፣ በኢቢሲ-3 የሚተላለፍ ፊልም እያዩ እንደነበር የገለጸው ጋዜጠኛ ተስፋለም፣ በጠባቂዎች ዘወትር እንደሚደረገው ከእስር የሚለቀቁ ሰዎች ስም በድምፅ ማጉያ ሲጠራ፣ የአባቱ ስም ትክክል ባይሆንም ‹‹ተስፋለም›› የሚል ስም መስማቱን ገልጿል፡፡

የእሱን ስም የሚጠራው ተሳስቶ እንደሆነ በመገመት ፊልሙን በማየት ላይ እያሉ በተደጋጋሚ በመጠራቱ፣ ወደሚጠራው ሰው ጠጋ ብለው ስም ዝርዝር ሲመለከቱ፣ የዘለዓለምንና የአስማማውን ስም በማየቱ ‹‹የሆነ ነገር አለ›› በማለት፣ ወደ አስተዳደር ሄደው ሲጠይቁ ‹‹ስምህ እየተጠራ አልቀርብ ያልከው አንተ ነህ?›› ተብሎ ሲገባ፣ የሞላው ቅጽ ተረጋግጦ ‹‹ውጣ›› መባሉን ተናግሯል፡፡

‹‹አንድ ዓመት ከሦስት ወራት ታስሬ እንዴት በድንገት ውጣ እባላለሁ? በምን ምክንያት?›› የሚል ጥያቄ ማንሳቱን የገለጸው ጋዜጠኛ ተስፋለም፣ ‹‹ዓቃቤ ሕግ ክሱን አቋርጦ ነው›› መባሉንና የመፈቻ ካርኒ (እንደ ሰርተፊኬት የምታገለግል) ሲሰጠው በካርኒውም ላይ ‹‹ክሱ ተቋርጧል›› ከሚል ውጪ ምንም የተገለጸ ነገር እንደሌለ አስረድቷል፡፡ የማረሚያ ቤቱ የውጭ በር ላይ ሲደርስ ማመን አቅቶት ቆም ብሎ ግራና ቀኝ ሲመለከት ምንም ነገር ማጣቱን የተናገረው ጋዜጠኛ ተስፋለም፣ ማረሚያ ቤት የሚለብሰውን ፒጃማ እንደለበሰ ባጃጅ ውስጥ ገብቶ ልብሱን እንደቀየረና ከባለባጃጁ ስልክ ጠይቆ መፈታቱን መጀመሪያ ያበሰረው ለእህቱ መሆኑን ገልጿል፡፡ እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ እሱም ሆነ ጓደኞቹ ጠበቃቸውን አቶ አመሐ መኰንን አግኝተው ሲያነጋገሩ፣ ጠበቃውም ቢሆኑ እንዴትና በምን ሁኔታ እንደተለቀቁ እንደማያውቁ መናገራቸውን ጋዜጠኛ ተስፋለም ለሪፖርተር አስረድቷል፡፡

ይድረስ ለነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊያን

ከያህያ ይልማ

አሁን ያለው የሕወሐት ሥርዓት ችግሮች ምን እንደሆኑ በውል ተመልክቶ በተቃራኒው ምን ዓይነት የትግል መስመር እንደሚያስፈልግ እኔ ያህያ ይልማ የሚከተሉትን ቁምነገሮች ሳስቀምጥ የሌሎቻችሁም አስተያየት ውሸት የሌለው እና ህሊናዊ ተጠየቅ ባለበት መልኩ እንዲሆን እያስገነዘብኩ በደስታ እጋብዛችኋለሁ::

1. የሕወሐት ሥርዓት ችግሮች

ሀ. የሕወሐት መስራቾች ወደ ትግል ለመግባት ያሰቡት እና የገቡት የንጉሱን ስርዓት ብሎም የአማራውን ገዥ መደብ በተለይም የሰሜን ሸዋን የበላይነት ተዋግቶ በማስወገድ የወልቃይትንና የራያን ለም መሬቶች አስገብቶ ታላቋን ትግራይ መመስረት አልሞ ሆኖ እያለ አምባገነኑን የደርግ ስርዓት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ በማውረድ በምትኩ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አሰፈንኩ እያሉ ያጭበረብራሉ:: እዚህ ላይ የማይካድ ሐቅ አለ:: የሕወሐት ተራ ታጋዮች በቆራጥነት ተዋግተዋል፣ ስርዓጥ አልበኛ ከነበረው ከአምባገነኑ ደርግ አንጻር የሰራዊታቸው ዲስፕሊን የሚደነቅ ነበር፣ የመጨረሻ ደባቸው ምን እንደሚሆን በትክክል ባይታወቅም እንዲሁ በምንረዳው ሐሳባቸውን ከመገንጠል ወደ ኢትዮጵያን መምራት አስተሳሰብ ቀይረውም ነበር:: እነዚህ ሁኔታዎች በትግራይ እና በሌላው የኢትዮጵያ አካባቢ የሚኖሩ ገጠሬዎች እንዲደግፏቸውና አብረዋቸው እንዲሰለፉ ዳርጓቸዋል:: እየፈራረሰ የነበረውን የወቅቱን ሶሻሊስታዊ ርዕዮተ ዓለምን በብልጣብልጥነት የተው መስለው ከምዕራባዊያን ጋር ወዳጅነት መፍጠራቸውም በእጅጉ የጠቀማቸው አካሄድ ነበር::

ለ. የሀገር ድንበርን ከማስከበር እና የህዝቦችን አንድነት ከመጠበቅ አንጻር ሲነጻጻር የወረደ ቢሆንም ሕወሐት የአጼ ዮሐንስን ዘመን አምጥቸላችኋለሁ በሚል ስሜት ትግራዊያንን ተጠቀሙብኝ እያለ በሙስና የማይገባቸውን ሐብት እንዲያጋብሱ እያደረገ ይገኛል::

ሐ. የሕወሐት ስርዓት የለየለት ዘረኛ መሆኑን የራሱ አጋዥና ታዛዥ የሆኑት የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ የደህዴንና ሌሎች አጋር ድርጅቶችም ተረድተውት ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት ጊዜ እየጠበቁ ይገኛሉ:: ለዚህም ማስረጃ ጦሩና ደህንነቱ እንዲሁም ወሳኝ የመንግስት አውታሮች በሕወሐት ብቸኝነትና የበላይነት ተጨንፍረው ይገኛሉ::

መ. ሕወሐቶች በትግል ወቅት ያልነበራቸውን ጭካኔነት በአሁኑ በሰለጠነ ዘመን እንዴት ሊተገብሩት እንደቻሉ በሚያሳዝን ሁኔታ ዜጎችን ሲያስሩ፣ ሲያንገላቱና ሲገድሉ መመልከት የተለመደ ተግባር ሆኗል::

ሰ. የሕወሐት ስርዓት ለብዙሃኑ ኢትዮጵያዊያን ጨለምተኝነትንና ተስፋቢስነትን አስፍኗል:: መማር ትርጉም አጥቷል፣ የመኖር ዋስትና ጠፍቷል፣ ሀላፊነት ያላቸው ሰዎች በውሸት የተሞሉ በመሆኑ ውሸታቸውን እየነዙ በኢትዮጵያዊያን መካከል መተማመን ጠፍቷል፣ ከፋፍሎ የመግዛት ስልትን አጠናክረው ስለቀጠሉበትም ኢትዮጵያዊያን በጎሪጥ እንዲተያዩ ዳርጓል::

ረ. የሕወሐት ስርዓት ሉዓላዊነትን ከማስከበር እና ከማስጠበቅ ይልቅ ስልጣንን የሚያስቀድም በመሆኑ በድንበራችንና በህዝባችን ላይ እየደረሰ ላለው አሳፋሪ ውርደት ተጠያቂ ነው::

ሸ. የመሰረተ ልማት አውታሮች እየተዘረጉ ቢታዩም እንዴት ነው የሚዘረጉት፣ ጥቅሙስ ለህዝቡ እየደረሰ ነው ወይ ተብሎ ሲታይ መልሱ ተቃራኒ ነው:: የመሰረተ ልማት አውታሮቹ የሚገነቡት ኢትዮጵያ በረጅም ጊዜ እንኳ ልትከፍለው የማትችለው ወደ ፵ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የብድር እዳ እንድትሸከም ሆና ሲሆን ከዚሁ እዳ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በፖለቲካ ጉዳይ የሚንቀሳቀሱ ዜጎችን ለማፈኛ ሆኖ ከማገልገል በተረፈ በሕወሐት ባለስልጣናት እየተዘረፈ የሚገኝ መሆኑን የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ::

ቀ. በአጠቃላይ የሕወሐት ስርዓት ለዚህ ዘመን የማይመጥን ፍጹም አምባገነን ዘረኛ ስርዓት ነው:: ህዝቡም ይህን በደንብ ስለሚገነዘብ ሕወሐትን እንደ ዘራፊ ቡድን እንጂ እንደ መንግስት አይመለከተውም::

በመሆኑም የሕወሐት ስርዓት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መወገድ ያለበት የኢትዮጵያዊያን ካንሰር ነው:: ከዚህ በመነሳት የሕወሐት ስርዓት በመሳሪያ የታጀበ ህዝባዊ አመጽን በማቀጣጠል ሊወገድ ይገባዋል::

2. ሕወሐትን ለማስወገድ የሚያስፈልጉ የትግል መስመሮች

ሀ. ሰላማዊ ትግል እያሉ ጊዜን ከማጥፋትና ዜጎች እንዲሰቃዩና እንዲገደሉ ከማድረግ አሁን ባለው ሁኔታ የሕወሐት ስርዓትን ለማስወገድ የሀይል አማራጭ መጠቀም ብቻ መሆኑን ማወቅና ከልብ ማመን ነው::

ለ. ከታሪክ እንደምንረዳው እንኳንስ አምባገነኑ ሕወሐት ይቅርና ዴሞክራስያዊ የሆኑ ስርዓቶችም ይወለዳሉ፣ ያድጋሉ፣ ይሞታሉ:: ከዚህ አንጻር ሕወሐት ተወልዶ ሲያድግ ተመልክተናል:: አሁን ደግሞ የህዝብ እሮሮ በርክቶ ወደመሞቻው ጉዞ ላይ ይገኛል:: ይህንን መረዳትና የኢትዮጵያ ካንሰር የሆነውን ሕወሐት ማስወገጃ ጊዜው አሁን መሆኑን መገንዘብና መነሳት ያስፈልጋል::

ሐ. ተስፋ ሰጭ ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ሀይል ከሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ መደገፍ፣ ቅስቀሳ ማካሄድና መቀላቀል:: አርበኞች ግንቦት ሰባትን መቀላቀልና ማጠናከር የሚጠቅመው ሕወሐትን ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን ሕወሐት ከተወገደ በኋላም ሳይታወቅ የሕወሐት ዓይነት ቡድን ሳይፈጠር ሉዓላዊነት የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ስለሚጠቅም ነው:: የክርስትና እና የእስልምና ሀይማኖቶች እንዳይጨቆኑብን ካሰብን ክርስቲያኖችና እና ሙስሊሞች የሆን በሙሉ አርበኞች ግንቦት ሰባትን መደገፍና መቀላቀል ነው:: የብሔር ጭቆና አለ ብለን የምናምንም አላስፈላጊ የቃላት አተካራን ትቶ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሀይል መሆንና ውሳኔዎችን በጋራ የምናስኬድ መሆን:: ድጋፉ ከተለያየ አቅጣጫ የማይመጣ ከሆነ ግን አርበኛች ግንቦት ሰባት ጎንደሬ ወይም ሰሜን ሸዋ ወይም ጎጃሜ ወይም ወሎየ የበዛበት ወይም አንዱን ሀይማኖት ብቻ ከፍ አድርጎ የሚመለከት ይሆንና በጋራ ወሳኝ ከመሆን የቡድኑን ይሁንታ የምንጠብቅ እንሆናለን:: በዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብና በፍትህ የሚያምነው አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ መዳፍ እንደገባ ሁሉ አሁን በስም ከምናውቃቸው ታጋዮች የድሉን መጨረሻ ለማየት የሚታደሉት ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ:: ይህ ማለት የሁላችንም ተሳትፎ ከሌለ ከድል በኋላ የምናየው አርበኛች ግንቦት ሰባት መልኩን ቢቀይር ችግሩ አሁን ያለመሳትፋችን ውጤት ነው የሚሆነው:: ስለሆነም አሁን የምናደርገው ተሳትፎ ከኢትዮጵያችን ነጻ መውጣት ጋር ተያይዞ ለሚኖረው የህልውናችን፣ የማንነታችንና የአብሮነት ውሳኒያችን አካል መሆኑን ተገንዝበን ከአርበኛች ግንቦት ሰባት ጎን መቆም::

መ. አርበኛች ግንቦት ሰባት እንደ ድርጅት ትግሉን እያፋፋመ ጎን ለጎን ማኒፌስቶ ማዘጋጀት ይጠበቅበታል:: ማንፌስቶው የሚከተሉትን ሶስት ወሳኝ ጉዳዮች ቢያካትታቸው እሻለሁ::

1. ኢትዮጵያ ክብሯ ከፍ ያለች አገር ሆና እንድትቀጥል ህጋዊ ሰውነት ያለው ማንኛውም ተቋም መለሰ ዜናዊና ደቀመዝሙሮቹ እያላገጡ እንዳየነው የኢትዮጵያን ታሪክ የማንቋሸሽ ስራ ነውርና ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ ትኩረት ማድረግ::

2. ሕወሐት ብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች እያለ ትርጉሙ ላገሬው ግልጽ ያልሆነን ማደናገሪያ እንደተጠቀመበት ሳይሆን በቀናነት ከምር ራስን በራስ የማስተዳደር ተግባራዊነት አስፈላጊ ነው:: ለዚህም ፕ/ር መስፍን ከጻፏቸው መጽሀፍት መካከል «ኢትዮጵያና የመንግስት አስተዳደር» [ካነበብኩት ጊዜው ስለረዘመ የመጽሀፉ ትክክለኛ ርዕስ የጠቀስኩት ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም] በሚለው እንደተመራመሩት አካባቢያዊ ስሜቶች የሚንጸባረቁባቸው ማህበረሰቦች የራሳቸው አስተዳዳሪዎች ኖሯቸው ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለማዕከላዊ መንግስት መሆን:: ለምሳሌ የተንቤን፣ የአድዋ፣ የመቀሌ፣ የራያና የጁ፣ የላስታና ዋግ፣ የደላንታና ደቡባዊ ወሎ፣ የከሚሴ፣ የአፋር፣ የኦጋዴን፣ የጎጃም፣ የጎንደር፣ የሸዋ፣ የሐረሪና ድሬዳዋ፣ የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የአርሲ፣ የሀድያ፣ የጉራጌ፣ የስልጤ፣ የባሌ፣ የወለጋ፣ የቤንችማጅ፣ የሐመር፣ የሙርሲና የቱርሲ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ የጋምቤላ ወዘተ. የራሳቸው አስተዳደር ኑሯቸው ተጠሪነታቸው ለማዕከላዊ መንግስት እንዲሆን ማድረግ አንድ ነን በሚል ሽፋን የሚከሰቱ ዘረኛዊ የአስተዳደር በደሎችን በእጅጉ ለመቀነስ ይረዳል:: አካባቢን ለማልማትም ከልብ ተነሳሽነት እንዲኖር ይረዳል::

3. ታሪካዊ በደሎች እንደነበሩ አምኖ ሀገራዊ እርቅ እንዲኖር ቁርጠኝነትን ማሳየት::

ሠ. ሕወሐትን ለመጣል የሚደረገው ትግል ከተከማቸው መሳሪያ አንጻር አልጋ ባልጋ የሚሆን ባይሆንም እንደ ድሮው በቆራጥነት የሚታገል ታጋይ የሌላቸው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል:: ቁርጠኝነት የነበራቸው አርጅተው በሙስና ተዘፍቀው ከመዋጋት ይልቅ ሁሉም አዛዦች ሁነው ያሉበት ወቅት ነው:: እንተማመንበታለን የሚሉት እንደ አግአዚ አይነት ያለው ጦርም ቢሆን እንኳ መሳሪያ ባልያዘ ሰላማዊ ዜጋ ካልሆነ በስተቀር መልስ የሚሰጥ ታጋይ ጋር የመዋጋት ሞራል የለውም:: መልቀምቀም የለመደ ስለሆነ ሞትን የሚጋፈጥ አይደለም:: ረባም አረባ ድሮ የሚሰብኩበት አይዲዮሎጂ ነበራቸው:: አሁን ግን እነሱን ግራ አጋብቶ ሌላውንም ግራ ያጋባው አብዮታዊ ዴሞክራሲ በማንም የተተፋ ስለሆነ የሞራል መቀስቀሻ የላቸውም:: አጭበርባሪና ውሸታም መሆናቸው ስለታወቀ አዲስ ሀሳብ እናምጣ ቢሉም የሚቀበላቸው የለም:: ከሕወሐቶችና ጥቅመኛ አለቆች ውጭ ያለው ተራው ወታደር እጅ ለመስጠት የሚዘጋጅና በነሱ ላይ አዙሮ መተኮስ የሚችል ሀይል ነው ያለው:: ስለሆነም የትግሉ መራራነት በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ነው የሚሆነው::

ረ. ትግልን ለማካሄድ ምክኒያት ማብዛት ወደ ኋላ ያስቀራል:: ለምሳሌ አርበኞች ግንቦት ሰባት ከጅምሩ ህብራዊ እንደሆነ ብንረዳም መሰረቱ አማርኛ ተናጋሪ የሆነው ህዝብ ነው:: ድርጅቱን ኦሮሞዎችና ነጻነትን የሚሹ ሌሎች አካሎች መሰረቱ በአማርኛ ተናጋሪው በመሆኑ መሸሻ ምክኒያት ማድረግ የለባቸውም:: ከላይ እንደጠቀስኩት ካሁኑ መሳተፍ የራስን ሃሳብ ውጤት እንዲኖረው ለማድረግ ይጠቅማል:: ከዚህ በተጨማሪ አማርኛ ተናጋሪው በሕወሐትና ሆድ አደር አጋር ፓርቲዎች ሲገፋና ፍዳውን ሲያይ እንኳ እልህ ተጋብቶ የራሴ ሳይል ለኢትዮጵያ ብሎ ነው ሲጮህና ሲታገል የኖረው:: ታዲያ ስተት ካለ እንተራረም እንጂ ማለት ኢትዮጵያዬ ማለቱ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ነው የምቆመው ማለቱ ድጋፍ ያሰጣል፣ አይዞህ ያስብላል እንጂ በጥርጣሬ ያስተያያልን ? የሕወሐትን ከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካን መቸም ሁላችንም ጠግበነው አንገሽግሾናል:: እና ለምኑ ብለህ ነው ወገኔ የሚልህን የምትርቅ:: ታሪካዊ ስህተቶችንም እንደምንተራረም መስመር እየዘረጋን ነው:: ያለፈው አልፏል፣ የሆነው ሆኗል ለኢትዮጵያ ህዳሴ፣ ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲና ለነጻነት ስንል ዛሬ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጎን ቆመን ለአገራችን ካንሰር የሆነውን ሕወሐትን እናስወግድ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

የሕወሓት አገዛዝ ከኣርበኞች ግንቦት 7 ጋር ጦርነት መግጠሙን አመነ * 30 ወታደሮችን ደመሰስኩ አለ

war
ከደረጀ ሃብተወልድ

ኢሳት ከሳምንት በፊት ያወራውን ወሬ ፋና ትኩስ ወሬ አስመስላና ቆራርጣ አቅርባዋለች።
ዜናው “መቼ ነው ይህ የሆነው?” የሚለውን መጠይቅ በዚህ በዚህ ቀን ብሎ በትክክል አይመልስም። እንዲሁ ወደ መጨረሻው ላይ “ሰሞኑን” ብሎ ነው ያለፈው። “የት?” የሚለውንም እንዲሁ በደፈናው “ከኤርትራ በሚዋሰን ድንበር” ብሎ ነው ያለፈው። በየት አካባቢ በሚዋሰነው ድንበር? ምንም ዝርዝር የለውም። እንኳን ወታደራዊ ዜና፤ አንድ ተራ ዘገባ እነኚህን የዜና አበይት መጠይቆች ሊያሟላ ግድ ነው።
ምነው ፋናዎች! ግልጽነትን ሌላው ቢቀር ከወዳጃችሁ ከሪፖርተር ተማሩ እንጂ!
-ደግሞ ሪፖርተር ምን አለ?
ዘይቱ ድንጋይ ሆነ አለ።
-ከየት የመጣው ዘይት?
ከወዳጅ ቻይና!
-መቼ?
ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም
-ኣሀ ኣሀ…ኣሀ…ለዚህ ነዋ አያቴ እንደዛ ያለችኝ?
ምን አሉሽ?
“አረ አያቴ ሆዴ ጥጥር ብሏል፤ድንጋይ ሆኖብኛል፤ ምን ሆኜ ይሆን?” ስላት ፦” እኔ ምናቅልሻለሁ የቻይና ዘይት በልተሽ ይሆናላ!” አለችኝ።
ህምም…

መንግስት ያመነበት ዜና የሚከተለው ነው

ከኤርትራ ጋር በሚዋሰን ምእራብ ትግራይ ድንበር አካባቢ ሰርጎ ለመግባት የሞከሩ ከ30 የማይልቁ የሻዕቢያ ተላላኪዎች መደምሰሳቸውን የፌደራል ፖሊስ ገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 3፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከኤርትራ ጋር በሚዋሰን ምእራብ ትግራይ ድንበር አካባቢ ሰርጎ ለመግባት የሞከሩ ከ30 የማይልቁ የሻዕቢያ ተላላኪዎች መደምሰሳቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል አሰፋ አብዩ ተናገሩ።

በሻዕቢያ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ትንኮሳ ለመፈጸም ከሞከሩት ጸረ ሰላም ሃይሎች መካከል አብዛኞቹ ሲደመሰሱ ጥቂቶቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

እንደ ኮሚሽነር ጄነራሉ ገለጻ ከተንኳሾቹ አንድም ወደ ኋላ ያፈገፈገ ሳይኖር የትንኮሳ ዕቅዳቸው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የሻዕቢያ ተላላኪዎች አልፎ አልፎ የትንኮሳ ድርጊት የሚያካሂዱ መሆኑን ገልፀው፥ ሰሞኑን የተደረገው ከዚህ ቀደም ከነበረው የተለየ አይደለም ብለዋል።

እነዚህ ሃይሎች ያደረጉት ትንኮሳ አነስተኛ እና በቀላሉ በቁጥጥር ስር ለመዋል የቻለ ነው ያሉት ኮሚሽነር ጄነራሉ፥ ፀረ ሰላም ሃይሎቹ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር ውግያ ለመግጠም የሚያስችል አቅምም ብቃትም የላቸውም ብለዋል።

የኤርትራ መንግስት ኢትዮዽያ እና ሌሎች ሃገሮችን ለማተራመስ የያዘውን አቋም የማይቀይር ከሆነ ኢትዮዽያ ተመጣጣኝ እርምጃ እንደምትወስድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን መናገራቸው ይታወቃል።

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44940#sthash.Itdg8JCl.dpuf