አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌቶች ላይ የሚሰራው በደል እየተሸፈነ ማለፍ ይቁም!!! (ከተማ ዋቅጅራ)

9973910113-large

 

በአትሌቶች ላይ የሚሰራው በደል እውነቱ ይወጣ ዘንድ ይገባል።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ ያለው ችግር ቢዘረዘር ዘርፈ ብዙ ችግር እንዳለበት ይታወቃል። በቦታው ላይ የተቀመጡት ሰዎች እራሳቸው ችግር እስከሚመስሉ ድረስ በምስኪኑ አትሌቶች ላይ ከፍተኛ በደል ፈጻሚ እና ችግር አምጪ ናቸው። በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቢሮ ሰዎች  ያልተሰደበ፣ ያልተገፋ፣ ያልተንቋሸሸ፣ ያልተንገላታ፣ አትሌት የለም። አትሌቶቹ በዚህ ቢሮ ሰዎች ከሚደርስባቸው ያለአግባብ በደልና ግፍ ያላለቀሰ አትሌት አለ ብዬ ለመናገር ይከብደኛል። በዚህ ቢሮ  ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች አትሌቶችን ለማገልገል ሳይሆን በደል ለመፈጸም የተቀመጡ ይመስለኛል። አትሌቶቹ በፌዴሬሽኑ ላይ በየግዜው ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም ሰሚ ባለማግኘታቸው በደል ፈጻሚዎችም በስልጣን ላይ ስልጣን ሲሰጣቸው ሲመለከቱ አንገቱን ደፍቶ እየተሰደበ እና እየተናቀ የተሻለ ቀን ይመጣል እያሉ በደላቸውን በሆዳቸው ይዘው ተቀምጠዋል። የተወሰኑት አትሌቶች ዜግነት ቀይረው ሌላ አገር ወክለው መሮጥ የተጀመረውም ፌዴሬሽኑ በሚያደርስባቸው በደል ነው።

Ethiopian-Athletes-Association

ኃይሌ ገብረ ስላሴ የፌዴሬሽኑ ሰዎች የተሰጠው ዘለፋ <<አንተ አርጅተኸል ከእንግዲ ወዲያ ምንም አታመጣም>> ብለው ሲተቹት የማራቶንን ሪከር ሰብሮ  አሳፍሯቸዋል።

ቀነኒሳ በቀለ ታዋቂ ከመሆኑ በፊት ወደ ትራክ ትሬኒግ ለመስራት ሲመጣ እግሩ ወፍራም ስለነበረ የተሰጠው ዘለፋ<< ይሄንን እግር ይዘህ ልትሮጥ ነው የመጣኸው? አንተ እሯጭ አትሆንም ይልቅስ ሂድና አገርህ ገብተህ እርሻህን እረስ>> የሚል ነበረ።

ብርሃኔ አደሬ በአንድ ወቅት በፊት ከነበራት ብቃቷ ትቀንሳለች የተሰጣት ትችት ግን ልብ የሚያደማ ነው። <<ከአሁን በኋላ አንቺ መሮጥ አትችይም ሂጂና ኩበትሽን ጠፍጥፊ>> የሚል ነበረ። ብርሃኔ በጣም እልኽኛ ስለነበረች ብቃቷን መልሳ እስከ አለም ሻንፒዮና ድረስ ለመሳተፍ በቅታለች።

ፀጋዬ ከበደ የመጀመሪያውን የውጪ ጥሪ መቶለት ከፌዴሬሽኑ ወረቀት ሊያጽፍ ሲሄድ <<አንተ አጭር አሁን አንተ ማራቶን እሯጭ ነኝ ብለህ ነው የመጣኸው>> እያሉ ይቀልዱበት ነበረ  ፀጋዬ ግን እኔ ምንም የለኝም እባካችሁ እድሌን አታስመልጡብኝ እያለ ሲለምናቸው እነሱ ግን ይሳለቁበት ነበረ።

ተፈሪ የሚባል አንድ አትሌት ከክፍለ ሃገር መቶ ማራቶን ይወዳደራል ያደረገው ቁምጣ የእግር ኳስ ተጫዋች ቁምጣ ነው። በዚህ ውድድር ላይ ሰባተኛ ይወጣና ውድድሩን ይጨርሳል በኋላ ላይ ቁጥር ሊቀበል ሲሄድ አመናጭቀው አባረሩት በኋላለይም ፌዴሬሽን ሄዶ ሲያናግራቸው <<ሂድ አንተ ዝም ብለህ ከመንገድ መተህ ማራቶን እሯጭ ነኝ ትላለህ ሂድ ውጣ>> ብለው አመነጫጭቀውት ሲናገሩት ተፈሪ ግን አንድ ነገር ብሎአቸው ነበረ የወጣው ትሰማላችሁ አላቸው የሚቀጥለውን ማራቶን ውድድር ሳሸንፍ ምን እንደምትሉኝ አያለው ብሎ ይወጣል። በሌላ የማራቶን ውድድር ላይ በዛው ቁምጣ እሮጦ ሁለተኛ በመውጣት ውድድሩን ይጨርሳል ያላቸው ነገር ቢኖር ዛሬስ ቁጥሩን አትሰጡኝም ዛሬስ ከመንገድ ነው የመጣሁት ትሉኝ ይሆን? ብሎአቸው ብቃቱን አሳይቷል።

ከላይ እንደገለጽኩት እነዚህን ታላላቅ እና ብርቅዬ አትሌቶቻችንን ለምሳሌነት ጠቀስኳቸው እንጂ በፌደሬሽኑ  ሰዎች  በደል ያልደረሰበት እና ያላለቀሰ  አትሌት አለ ብዬ ለመናገር ይከብደኛል።

አንድ አትሌት በክለብ ታቅፎ መስራት ከጀመረ በክለቡ ውስጥ ጥሩ ተፎካካሪ ከሆነ ኢንተርናሽናል ውድድር እንዳይወዳደር የሚከለክለው ህግ እስከሌለ ድረስ የውጪ ውድድሮችን የመጋበዝ እድሉን ካገኘ ፌዴሬሽኑ አትሌቱ በፌዴርሽኑ ስር ታቅፈው ከሚሰሩት ክለብ ውስጥ መሆኑን ጠቅሶ በሚጻፍ ፋንታ ወረቀት በመከልከል የአትሌቶቻችንን እድገት እየቀጩት ይገኛሉ። አትሌቶቹም እራሳቸውን ችለው ለአገርም እንዳይጠቅሙ አድርጎ በማምከን አዳዲስ አትሌቶች እንዳይወጡ እያደረገ ነው። አዲስ አትሌት ከማየት ይልቅ በኛ አገር የተለመደው ሁለት ወይም ሶስት አትሌቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የአትሌቲክስ አገር የነበረችውን አገራችንን ምንጩን  እያደረቁት ይገኛሉ። ለዚህም ደግሞ ትክክለኛው መፍትሄው በአትሌቶቹ ላይ  በደል  በመስራት ያሉትን ወንጀለኞች በህግ ተጠይቀው መጪው ፌዴሬሽኑን የሚረከበው አካል በንጹ አዕምሮ  እና ተጠያቂነት ባለው ስራ እንዲሰራ ማድረግ ሲቻል ሊጠፋ የተቃረበው አትሌታችንን ማዳን ይቻላል።

በዚህ አጋጣሚ አንድ ነገር ጠቆም አድርጌ ልለፍ

በፌዴሬሽኑ ህጋዊ እውቅና ተሰጥቶአቸው አትሌቶችን በመመልመል በማናጀር ስር በማቀፍ የሚያሰሩ ግለሰቦች አሉ። እነዚህ ግለሰቦች ከፌዴሬሽን ሶዎች ጋር ጥብቅ ሚስጢራዊ ስራ  አላቸው ያም ህገ ወጥ አሰራር ነው ። ለዛሬ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥቂት ልበል ወደፊት ግን በሰፊው እመለስበታለው።

በፌዴሬሽኑ በኩል እና  በፌዴሬሽኑ እውቅና በተሰጣቸው እንዚህ ማናጀሮች ተብለው ሚጠሩት እየተሰራ ያለው ስራ አሳፋሪ እና መንግስትም ሆነ ህብረተሰቡ በአትክሮት ሊያየው የሚገባ ጉዳይ ነው። በፌዴሬሽኑ ወይም በማናጀሮች በኩል ወደተለያዩ  አገራት ውድድር ለማድረግ በስራቸው የሚሰለጥኑትን አትሌቶች ይልካሉ። ይሄ የሚደገፍ እና የሚያበረታታ ጥሩ ስራ ነው ወደ ውጪ ወጥቶ  ለመወዳደር ጥሩ አጋጣሚ ነውና። ችግሩ ያለው በአትሌቶች ስም የሚደረገው ወንጀል ነው። ፌዴሬሽኑ ወይም ማናጀሮች ከተለያየ አገራት ለአትሌቶች የውድድር ግብዛ ጥሪ ማስመጣት ይችላሉ በዚህ መሃል ለምሳሌ አምስት አገር በአንድ ወር ውስጥ ቢያስመጡ ለዚህ ውድድር የሚሆኑ እሯጮች አንድ አገር ላይ አራት ሰው ቢልኩ ለአምስቱ አገር ሃያ እሯጮችን መላክ ይችላሉ። ለሁሉም አትሌቶች እኩል የሆነ አገልግሎት በመስጠት የውጪ የመወዳደር እድላቸው የተዘጋ ባይሆን ከበቂ በላይ አትሌቶችን ማፍራት እንደሚቻል ይታወቃል። ነገር ግን በጠበበው የውጪ እድል ላይ በአትሌቶች ስም ፌዴሬሽኑ እና ማናጀሮች የሚሰሩት ቢዝነስ ከአምስት አገር ሊልኳቸው ከታሰቡት ሃያ አትሌቶች መካከል ከግማሽ የሚበልጠው እሯጭ ያልሆኑ ሰዎች ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከፍለው የሚሄዱ አልያም የፌዴሬሽኑ ወይም የማናጄሩ ዘመድ የሆኑት በህገ ወጥ መንገድ  በአትሌቶቹ ስም የሚሰራ ወንጀል ነው። አትሌቶቹ ሲመለሱ እነዛ ግን በዛው የሚቀሩ ናቸው። እውነተኛው እና ደሃው አትሌት ጥሪ አስመጥቶ  አልያም ጥሪ የሚያስመጣለት አጥቶ በፌዴሬሽን ቢሮ በራፍ ላይ እና ማናጀሮቹ ላይ ሲያለቅሱ የሚያጥላላ ስድብ ከመስደብ በተጨማሪ በስፖርቱ ተስፋ እንዲቆርጡ የሚያደርግ ድርጊትን ሲያደርጉ እስከዛሬ ድረስ ዝም መባላቸው ኢትዮጵያውስጥ ህግ እንደሌለ የሚያሳይ ጉዳይ ነው። አትሌቶቹ ላይ የሚደርሰውን በደል ለማወቅ የሚፈልግ ማንኘውም አካል ከጀማሪው አትሌት እስከ ታዋቂዎች አትሌቶችን ጠይቆ እውነቱን መረዳት ይቻላል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ከሞሞቱ በፊት ፌዴሬሽን ያሉት ኮሚቴዎችን በአትሌቶቹ ላይ ለሚሰሩት ስህተት ተጠይቀው አትሌቲክሱን የሚያሳድጉ በቦታው ሊይዙት ይገባል እላለው።

ከተማ ዋቅጂራ

Email- waqjirak@yahoo.com

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/9975#sthash.CTXIG1uc.dpuf

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s