የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላት “የተቃዋሚዎች ሬድዮ ታዳምጣላቹ በሚል እየታሰሩ ነው

11899854_458103757685979_3718763112024142931_n

በገዢው ስራዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሰፊ የዓመቱ ግምገማ “የተቃዋሚዎች ሬድዮ መስማት” እንደዋነኛ መገምገሚያ ነጥብ ሆኖ መነሳቱን ተገለፀ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በሁሉም የስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ የዓመቱ ግምገማ ወታደሩ ያለማቋረጥ እየፈረሰ በመጥፋት ላይ ያለው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ በሚገኙ ድርጅቶች የሚሰራጨውን ሬድዮ መስማት ዋናው ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ለምን ታዳምጣላችሁ፤ እነማን ናቸው የሚያዳምጡት መታወቅ አለባቸው በማለት እየተካሄደ ባለው ስብሰባ የሰራዊቱ አዛዦች ራሳቸው የስብሰባው መሪዎችና ገምጋሚዎች ሆነው በመቅረብ ለበርካታ የሰራዊቱ አባላት እያባረሩና እያሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።
በተለይ በሰሜን እዝ እየተካሄደ ባለው የዓመቱ ግምገማ ላይ የሰራዊቱ አባላት ሓቀኛና ገምቢ ግምገማ ነው ብለው ስላላመኑበት ማንኛውም ሃሳብ ከመስጠት እንደተቆጠቡና የስርዓቱ ተጠቃሚዎች የሆኑት የበላይ መኮነኖች “እዚህ የተሰበሰብነው ሰራዊቱ አንዣቦበት ካለው የመበታተን አደጋ ለማዳን ስለሆነ የተቃዋሚዎች ሬድዮ ለምን ትሰማላችሁ ብለው ላቀረቡት ሃሳብ በተሰብሳቢዎቹ ማንኛውም ሚድያ መከታተል የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብት ነው” ብለው የተቃወሙትን የናንተ አመለካከት ከተቃዋሚዎች ጎራ ነው በማለት እንድፋሰርዋቸው መረጃው ጨምሮ አስርድቷል።

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/9822#sthash.H9i74N23.dpuf

አንድ አገር ሰላሟና ብልፅግናዋ ዘላቂና አስተማማኝ የሚሆነው የሕግ የበላይነት በተግባር ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡

አንድ አገር ሰላሟና ብልፅግናዋ ዘላቂና አስተማማኝ የሚሆነው የሕግ የበላይነት በተግባር ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ዜጎች በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውን ሲያምኑ፣ ሕግም ለሁሉም ዜጎች እኩል ጥበቃ ሲያደርግ፣ ፍትሕ ለሁሉም ተደራሽ ሲሆንና የፍትሕ ሥርዓቱ በነፃነት ሲንቀሳቀስ የሕግ የበላይነት መኖሩ ይረጋገጣል፡፡ ‹‹አንድን ንፁኅ ዜጋ ከማሰር ይልቅ አንድ ሺሕ ዜጎችን መፍታት የተሻለ ነው›› የማለው የሕግ ጽንሰ ሐሳብ በአንድ አገር ውስጥ ተግባራዊ ሲደረግ፣ ዜጎች በነፃነት በአገራቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ውስጥ በንቃት ይሳተፋሉ፡፡ ነገር ግን በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ሰበብ እየተፈለገላቸው በሚከሰሱና በሚታሰሩ ዜጎች ምክንያት አገራችን ውስጥ በፍትሕ ላይ መተማመን ጠፍቷል፡፡ ኢሕአዴግ ይኼ ካላሳሰበው ሌላ ምን ያሳስበዋል? ሰዎች ያለጥፋታቸው ታስረው የቀረበባቸው ክስ የማያወላዳ በመሆኑ በነፃ ሲሰናበቱ አሁን መታየት ጀምሯል፡፡ የአንዳንዶችም ክስ ሲቋረጥም ተስተውሏል፡፡ ከመነሻው እንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ተግባር ለምን ይፈጠራል? የፍትሕ ሥርዓቱስ ለምን ይሳጣል? ለሕግ የበላይነት ለምን ቅድሚያ አይሰጥም? ብዙ ማለት ይቻላል፡፡

ዜጎች በገዛ አገራቸው ሰብዓዊ መብታቸው ሲጣስ ዝም ይባላል፡፡ በአመለካከታቸው ምክንያት መደብደብ፣ መታሰር፣ መንገላታት፣ ከሥራ መባረር፣ የቤተሰብ መበተን፣ ወዘተ ሲደርስባቸውና ጩኸቱ ሲበረክት በተደጋጋሚ ተሰምቷል፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላቶቻቸው እንደተገደሉባቸው በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡ በታዳጊ ዴሞክራሲ ውስጥ የሚያጋጥም ነው እየተባለ ዜጎች በገዛ አገራቸው ሲሰቃዩ እስከ መቼ ይቀጥላል? የመልካም አስተዳደር እጦት ምሬት ከዳር እስከ ዳር ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ሥራ መሥራት ያቃታቸው ሹማምንት የተመደቡበት ኃላፊነታቸውን መወጣት ሳይችሉ በመቅረታቸውና ለአገር ደንታ የሌላቸው ሹማምንት የግል ጥቅማቸውን እያሳደዱ ሕዝብ ሲያስለቅሱ ዝምታው ምንድነው? ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ እነዚህን ችግሮች መፍታት ያቃተው ለምንድነው? ችግሮቹስ ለምን ይድበሰበሳሉ? በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡

የዴሞክራቲክ ተቋማት አለመጠናከርና በፍርኃት ቆፈን መያዝ፣ የሲቪል ማኅበረሰቡ ደብዛው መጥፋት፣ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓቱ ደብዝዞ የአውራ ፓርቲ ሥርዓት መንገሥ፣ የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች ሕግ የማውጣትና አስፈጻሚውን የመቆጣጠር አቅም አለመጠንከር፣ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያሉ መገናኛ ብዙኃን የገዥው ፓርቲ ብቻ አገልጋዮች መሆን፣ የግሉ ሚዲያ መፍረክረክ፣ ወዘተ ግልጽነትና ተጠያቂነትን እያጠፋ ነው፡፡ በየቦታው ትንንሽ አምባገነኖች እየተፈለፈሉ ነው፡፡ ለአገር አደጋ ነው፡፡

ሙሰኞች የአገር ሀብት እየዘረፉ ሲከብሩ ዞር ብሎ የሚያያቸው የለም፡፡ ጭራሽ በድርጅት አባልነት ከለላ፣ በሹማምንት ትውውቅና ኔትወርክ ዕውቅና የተሰጠው ሙስና ግለሰቦችን በቀናት ውስጥ ሚሊየነር ሲያደርግ ዝም ይባላል፡፡ የፀረ ሙስና ትግሉ የለም እንዳይባል ያህል እዚህም እዚያም በአለፍ ገደም አንዳንድ የሚጠየቁ ግለሰቦች ቢኖሩም፣ ሙስና የሥርዓቱ መግለጫ እስኪመስል ከተራ ዜጋ እስከ ውጭ ኢንቨስተር ድረስ የምሬት ምክንያት እየሆነ ነው፡፡ በሕገወጥ የመሬት ወረራ፣ በሕንፃ ግንባታና ዕድሳት ፈቃድ፣ በወጪና ገቢ ንግድ የጉምሩክ ኬላዎች፣ በአገር ውስጥ ገቢ፣ በአነስተኛና በትልልቅ ግዢዎችና ጨረታ፣ በንግድ ፈቃድ ምዝገባና በብቃት ማረጋገጫ፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጀት ምዝበራ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርፊያ፣ በኤሌክትሪክ፣ በውኃና በስልክ መሠረተ ልማት ዝርጋታዎች፣ በመንገድ ግንባታዎችና በመሳሰሉት አገሪቱንም ሕዝቡንም ራቁታቸውን የሚያስቀሩ የሙስና ተግባራት እየተፈጸሙ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ሆይ የት ይሆን ያለኸው? አባላትህና ደጋፊዎችህ ምን እያደረጉ ነው? የምዝበራው ተሳታፊ ወይስ የዳር ተመልካች?

አገሪቱ ከነበረችበት የድህነት አረንቋ ውስጥ ለማውጣት የሚደረገውን ጥረት ሕዝቡ መስዋዕትነት እየከፈለበት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሕዝብ አሁንም በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እየተመታ ነው፡፡ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች በየቀኑ ዋጋቸው እየጨመረ ኑሮን መቋቋም ተስኖታል፡፡ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ ከአቅም በላይ እየሆነበት ነው፡፡ የቤት ኪራይ ክፍያ ከሚቋቋመው በላይ ነው፡፡ በትራንስፖርት እጦት በፀሐይና በዝናብ ይንገላታል፡፡ ፈረቃ በይፋ ያልታወጀላቸው ኤሌክትሪክና ውኃ ለቀናት እየጠፉበት ይሰቃያል፡፡ ይህንን ሁሉ ጫና ተቋቁሞ አገሩን የሚገነባ ሕዝብ እንዴት ነው ድጋፍ ማግኘት ያለበት? በስሙ በድጎማ የሚመጡትን ዘይትና ስንዴ በጥቅም የተሳሰሩ ሌቦችና ደላሎች አየር በአየር ይሸጡበታል፡፡ የግብይት ሥርዓቱ እጅግ በጣም ኋላቀርና ተቆጣጣሪ የሌለው ከመሆኑ የተነሳ ሕዝቡን በቁሙ እየገደለው ነው፡፡ ኢሕአዴግ እስከ ጆሮ ዳባ ልበስ

ዜጎች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችም ሆነ በተለያዩ መንገዶች የሚያቀርቡዋቸው አቤቱታዎችና ብሶቶች አይደመጡም፡፡ ቅሬታዎች በአግባቡ አይስተናገዱም፡፡ ችግሮች ሲፈጠሩ ጥድፊያው ለማድበስበስ እንጂ መፍትሔ ለመፈለግ አይደለም፡፡ ኢሕአዴግ ስኬቱን እያወደሱ የሚያሞካሹትን ጆሮውን ሰጥቶ የሚያዳምጠውን ያህል ለምን ተቃውሞዎችን፣ ምክሮችንና ቅሬታዎችን ለማዳመጥ አይተጋም? በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ከነአጋሮቹ ያገኘው መቶ በመቶ የፓርላማ መቀመጫዎችን እንጂ፣ መቶ በመቶ የሕዝቡን ይሁንታ አይደለም፡፡ ካገኘው የሕዝብ ድጋፍ ጋር ባይወዳደርም የማይናቅ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ይቃወሙታል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ኢሕአዴግ በውስጡ ከሕግ በላይ የሆኑ ግለሰቦችን በመያዙ፣ አድርባዮችና ሌቦችን በማቀፉ፣ ፀረ ዴሞክራሲና አምባገነን በህሪያት ይንፀባረቁበታል በሚል ነው፡፡ ይኼም በተደጋጋሚ ተተችቶበታል፡፡ አገራቸውንና ሕዝባቸውን በቅንነት የሚያገለግሉ እየተገፉና ዕድገት እየተከለከሉ ወረበሎች አገር እየበደሉ ነው፡፡

ማሪንጌ ቻቻ ፤ የወያኔ (የሃይልዬ) ጨዋታ – ሰሎሞን ታምሩ ዓየለ (ከካሊፎርኒያ)

የሃይልዬ የድርቅ ፖለቲካ !!!
ጉድ ሳይሰሙ መስከረም አይጠባም !!!

ሰሎሞን ታምሩ ዓየለ (ከካሊፎርኒያ)

ለጽሁፌ መነሻ የሆነኝ በቅርቡ የኢትዮጵያው ጠ / ሚኒስቴር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ” የዳያስጶራ “ ሳምንት በሚል በአዲስ አበባና አካባቢዋ ስለተከበረውና ከተሳታፊዎቹ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ በአገራችን እየተንሰራፋ ስላለው ድርቅ ገጽታውን እንዲያብራሩ ተጠይቀው እንደነበር ይታወሳል። የሰጡትን ምላሽ በኢሳት ሬዲዮ ካዳመጥኩኝ በኋላ ሰውዬው ምን ነካቸው ? ምንስ ቢተማመኑ ነው የኢትዮጵያውን ድርቅ ከካሊፎርኒያና ከአገረ አውስትራሊያ ጋር ለማዛመድ ያነሳሳቸው የሚል ሃሳብ በጭንቅላቴ እየተመላለሰ ስላስቸገረኝ ፤ እስቲ እኔም የድርሻዬን የማውቀውንና የተረዳሁበትን መንገድ አንድ ልበል በሚል ምላሽ ለመስጠት ነው። ከሁሉ ደግሞ የደነቀኝ “ ዳያስጶራው “ ንግግራቸውን በጭብጨባ ማጀቡ፤ ኢትዮጵያ ሌላ ተፈጥሮን መቆጣጠር የሚችል መሪ አገኘች ወይ የሚል ጥያቄ በህሊናዬ ማጫሩ አልቀረምና የድርቁን ችግር በራሷ ጥረት ብቻ ልትቀረፍ የተዘጋጀች አገርም መሰለኝ። ለማንኛውም ትችቴ በዕውቀትና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ እንዲሆንልኝና ሰውዬው ” የሳቱትንና “ በእኔ አማርኛ ደግሞ “ የቀዘቀዙበትን “ ጉዳይ በተጨበጠ ማስረጃ አያይዤ ነካ ነካ ላድርገው። ሌሎቻችሁም ሃሳባችሁን እንድንሰማ ያብቃን እላለሁኝ። ጽሁፌንም ለአንባቢያን ምቹና ተስማሚ ወዲያውም ግንዛቤ ጨማሪ እንዲሆን በማሰብ በሁለት ክፍል ከፍዬዋለሁኝ።ትልቅ ትንተና ውስጥ ግን አልገባም። በቀላሉ ከዚህም ከዚያም ያገኘሁትን አስረጂዎችና ዘገባዎች በማዛመድ ለማቅረብ እሞክራለሁኝ ። የመጀመሪያውን ክፍል እነሆ !!!california drought

ትናንት ሃይሌ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሊስትሮ ሆነው ሊያገለግሉ የቆረጡለትን የፖለቲካ ፓርቲያቸውን ዛሬ ደግሞ መንፈሳቸውንና ኩራታቸውን ከፍ አድርገው ከፊታቸው የተደቀነውን የድርቅና አስከፊ ውጤቱን ለማሸነፈ የመንፈስ ዝግጅት ያደረጉበት እስኪ መስል ድረስ ድርቁን አጣጥለው ችግሩ የኛ ብቻ አይደለም በካሊፎርኒያም በአገረ አውስትራሊያም ተከስቷል አሉን። ትልቅ ማሰባቸው ባልከፋ ነበር። መልዕክታቸው ግን ዕውን የሚወዱትና የሚንገበገቡለት መንግስታቸውእንዲህ ጉልበትና አቅም ፈጥሮ እናንተ አታስቡ ለችግሩ እኔ አለሁ የሚል ከሆነ እሰየው ብለን እንለፈው። ታለባለዚያ ግን እንደው እንደ “ መልስ በኪሴ “ጫን ብሎ ለመጣው ጥያቄ በቂና አሳማኝ መልስ ጠፍቶ ለማምለጫና ለብልጣብልጥነት የተሰነዘረ ከሆነ ግን “ የሃይሌ ቶክ ሾው “ ነው ብዬ ልደምድመው።

ድርቅ የተፈጥሮ ክስተት በመሆኑ በማናቸውም የዓለማችን ምድር ላይ በሚገኘ አህጉሮችና አገሮች ላይ ይከሰታል ፤ ዋነኛ ምልክቶቹ በየትኛውም የአየር ንብረትና ሃብት ፤ ወቅቶችና ከባህር ወለል በላይ ከፍታዎች ላይ ሊታይ ይችላል። በቀጠሮም አይመጣም። ሲጀማምረውም በቅጡ ላናስተውለው እንችላለን። እያዘገመ ቀስ በቀስ ግን መጠኑን እያሰፋና እየጨመረ የሚሄድም ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በአንድ ምሽት መጣሁኝ አይልም ወይም ደግሞ የሞቀ ዘይት ውስጥ ሲገባ ወዲያውኑ እንደሚፈነዳው በቆሎና ፈንዲሻ ማሽላም አይደለም ። የተወሰነ የወሰንና ድንበር ክልል የለውም። አንድ ወጥ የሆነ ትርጉምም ወይም ፍቺም ያለው አይመስለኝም። የሚያስከትለውም አስከፊ፤ ጎምዛዛ ፤ ጥፋትና ጉዳት ወዲያውኑም ሊገለጽ አይችልም ይሆናል። የማይናቀው ግን በሰውና በእንስሳት ህይወት፤ በሌሎች ብዝሃ ህይወት፤ በተፈጥሮ ሃብታችን፤ በንብረታችንና በምጣኔ ሃብታችን ላይ ግን አሌ የማይባል ጉዳት፤ ጥፋትና ብክነት እስከወዲያኛው እንዳናንሰራራ አድርጎ የማለፍና የማስከተል ብቃት ግን አለው። ዛሬ በዓለማችን የድርቁን ሁኔታ የሚያባብሱና የሚያፋጥኑ ተግባሮች እንደ አሸን ፈልተዋል። በየትኛውም የዓለማችን ክፍል በሚገኙ ህዝቦች በየዕለት የመግባቢያ ቋንቋቸው ውስጥ ስለ ድርቅ አይወራም ማለት ዘበት እየሆነ መጥቷል። በትንሹ ቤተሰብ ውስጥ እንኳን ኑሮው ቢደላም ባይደላም ፤ ድርቅ ሳይወራ የሚታደርበት ቋንቋ ያለም አይመስልም።

በተባበሩት የአሜሪካ መንግስታት ስለሆነችውና ሃይሌ በቅድሚያ ድርቁን አጣጥለው አዲስ ክስተት እንዳልሆነ በድርቅ ስለተመታችው ካሊፎርኒያ ግዛት ትንሽ ከማለቴ በፊት ግን ጠቅላይ ሚኒስቴራችን እንዲህ ብለው ቢሆን ኖሮ ምንኛ ሃሳባቸውን በደገፍኩላቸው። ከሚወዱትና ሁሌ ሳያነቡ ወደ መኝታቸው የማያመሩት ሃይሌ ከመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ድርቅ የተነገረበትን ወንጌልም ሆነ መጽሃፍ ስም ፤ ምዕራፍና ቁጥር ጠቅሰው ድርቅ ከሰው ልጅ ታሪክ ጋር ቁርኝት እንዳለው ወይም ደግሞ ይሄ ታልሆነላቸው በአህጉራችን አፍሪካ በተለይም የሣህል አገሮች ተብለው በሚጠቀሱቱ ሴኔጋል ፤ ሞሪታኒያ፤ ማሊ፤ ቡርኪና ፋሶ ፤ ኒጀር፤ ናይጄሪያና ሱዳን ሌሎችንም እንዲሁም የኛኑ አገር ጭምር ውስጥ የሚኖሩ በመቶዎቹ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች በየጊዜው በድርቅ ምክንያት እንደሚሰቃዩ ፤ በረሃብና በችጋር አለንጋ እየተገረፉ እንደሚኖሩ፤ ያ ታልሆነ ደግሞ ጎረቤቶቻችንን ሶማሊያን፤ ኬኒያን፤ ሁለቱንም ሱዳኖችን፤ ታንዛኒያንና ዑጋንዳን ጠቅሰው ቢሆን ኖሮ ማለፊያ ነበር ብልስ ስህተት የሰራሁኝ አይመስለኝም ።

ካሊፎርኒያ እኔንና አንድ ወንድ ልጄን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ፤ ኢትዮ አሜሪካዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ልክ እንደተወላጁና ነዋሪው ህዝብ የሚኖሩበት ግዛት ነው። በተለይም በሎስ አንጀለስና አካባቢው ፤ በሳንሆዜና አካባቢው ፤ በሳንፍራንሲስኮና በኦክላንድ እንዲሁም በሳንዲያጎ ከተሞች በድምሩ ቁጥሩ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ የኢትዮጵያውያን ደም ያላቸው ሰዎች እንደሚኖሩ ይገመታል። ነገር ግን የካሊፎርኒያ ህዝብ ብዛቱ ወደ 40 ሚሊዮን ይጠጋል። በተለያዩ የቅጽል ስም የምትጠራው ካሊፎርኒያ በዋናነት “ ወርቃማዋ ስቴት “ በመባል ትታወቃለች።

የካሊፎርኒያ ኢኮኖሚ ትልቅ ከሚባሉትና ከአሜሪካም አገር ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ የሚገኝ ነው። በጠቅላላው ኢኮኖሚዋ በቅርቡ በተባበሩት አሜሪካ የኢኮኖሚ ትንተና ቢሮ አማካይነት የተለቀቀው ዘገባ እንደሚጠቁመው ከሆነ ጠቅላላ የግዛቱ ምርትና አገልግሎት ዋጋው 2.342 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል። እንደውም ቀደም ሲል ካሊፎርኒያ እንደ አገር ብትቆጠር ከዓለማችን በምጣኔ ሃብት ብዛቷ የ፲ ኛ (አስረኛ) ደረጃ ይኖራታል ተብሎ የሚነገረውን በማሻሻል ዛሬ ከብራዚል ቀጥላ በ፰ ኛ (በስምንተኛ) ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ታዲያ ሃይሌ እንደው ዕድሜያቸው በፈጣሪ ዕገዛ በዝቶ ከነአመራራቸው እንኳን የ፻ ዓመት ዕድሜ ቢቸራቸው በምን ተአምር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከዚህ ያደርሱት ይሆን?

ካሊፎርኒያ ለግብርና ስራ አመቺና ተስማሚ ነች። አፈሯ ለም ነው ፤ ብዝሃነት ያላቸውን ተክሎች ፤ አዝርዐቶች፤ ፍራፍሬዎች፤ አትክልቶችና ሌሎች ጠቀሜታ ያላቸውን ዕጽዋቶች ለማብቀል የሚያስችል ተስማሚና ረዠም ቆይታ ያለው ወቅት አላት። የዘመኑ የግብርና ቴክኖሎጂዎች መጠቀሚያና ማፍሪያም ግዛት ነች። ሸለቆዎቿን በዘመኑ የመስኖ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ጭምር የውሃ ሃብቷን እያጠጣች ምርቶቿን ታመርታለች። የወተትና ተዋጽዎቿም በዓይነትም በጥራትም የታወቁና የተመረጡ ናቸው ። በግብርና ምርትና ውጤቶቿ በዓለምም ሆነ በአሜሪካ ደረጃ ቀዳሚውን ስፍራ ይዛ የምትገኘው ካሊፎርኒያ የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚዋ ግምቱ ወደ 46 ቢሊዮን ዶላር በላይ ደረጃ ደርሷል። የካሊፎርኒያ ግብርና ምርትና ወጤቶችም በተቀረው ዓለምም ላይ ተጽዕኖ ማሳረፋቸው አልቀረም። ወደ ውጭ የሚላኩት የግብርና ምርቶችም እንደ 2013 መረጃ መሰረት ከ21 ቢሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል ።የግብርና ኢኮ ኖሚው ለብቻው ድርሻው በመቶኛ ትንሽ ቢመስልም ቅሉ፤ መሬት ላይ ያለው ዕውነታው ግን የተለየ ነው። ግብርና በግዛቷ ኢኮኖሚ ትልቅና ዘርፈ ብዙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰራተኛ ህዝቧ የኑሮው መሰረቱና ምንጩ ይኸው የግብርናውና ተያያዥነትና ተደጋጋፊነት ያላቸው የስራ ዘርፎች ነው።

ካሊፎርኒያ ታዋቂ ፍራፍሬዎቿን ፤ አትክልቶቿን፤ የምግብ ሰብል ምርቶቿን ለማምረት ከፍተኛ የሆነ የውሃ ሃብቷን እንደምትጠቀም ጥናቶች ያመለክታሉ። 80 % የሆነውን የውሃ ሃብቷን ለግብርናው ልማት ታውላለች። በመስኖ የሚጠጣው መሬት መጠን ልክም ወደ 10, 000,000 ኤከር ( 5,000,000 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ) ይደርሳል ። መንግስትም በተለያዩ ተቋሞቹ አማካይነት ይህንን ውሃ ሃብት በማሰራጨትና በማደል ተግባር ላይ ተሰማርቷል ። የውሃ ሃብቷ ምንጭም ወቅቱን ጠብቆ የሚጥለው ዝናብና በሲየራ ተራራማ ሰንሰለቶችና በሰሜን አቅጣጫ ገዝፎ የሚታየው የሻሽታ ተራራዎች ላይ የሚጥለው ጥቅጥቅ የበረዶ ክምርና የደቡቡ ክፍል ደግሞ ከኮሎራዶ ወንዝ ነው። ይህ የውሃ ሃብት ምንጭ ነውታላላቅ ወንዞ ቿን ፤ ጅረቶቿን፤ ምንጮቿን፤ የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎቿን ረግረግማ ስፍራዎቿን በውሃ የሚያረሰው ።ዝናብ አብዛኛውን ጊዜ በግዛቱ የሚጥለው በክረምቱና በጸደይ ወቅቶች ( ከጥቅምት እስከ ግንቦት ) ነው። ሞቃታማው የበጋው ወቅት ግን በአብዛኛው የግዛቱ ስፍራዎች ላይ ዝናብ አልባና ደረቅ ነው። ይህ ደረቅ ወቅት ከተራዘመና በቂ የበረዶ ክምር በተራሮቿ ጫፍ ላይ ከሌለ ካሊፎርኒያን ድርቅ ይመታታል።

በርግጥ ካሊፎርኒያን ድርቅ መቷታል ?

አዎን ! ካሊፎርኒያን ካለፉት አራት ዓመት ጀምሮ ድርቅ እየመታት ይገኛል። አንዳንዶቹ እንደሚናገሩት በግዛቷ ታሪክ አስከፊ ነው ይሉታል። የግዛቱ ዋና ዋና ከተማ ነዋሪዎች ፤ በትናንሽ ከተሞች የሚኖሩ የተለያዩ ማህበረሰብ አባላቶችና ነዋሪዎች ፤ የተለያዩ በቀጥታ ከውሃ ሃብት ጋር የሚሰሩ የመንግስት ተቋሞች፤ የሁለቱም ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰዎችና ምክር ቤቶች፤ መገናኛ ብዙሃኖች፤ የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎችና ወዳጆች ፤ በዋናነት ሰብል አብቃይ ገበሬዎችና በእንስሳት ርባታ ላይ የተሰማሩ ቢዝነስ ሰዎች፤ የዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች፤ የውሃ ላይ ስፖርት አፍቃሪዎችና በሳርማ አረንጓዴው ላይ ጎልፍ ስፖርት አዘውታሪዎች ወዘተረፈ ሁሉም በውሃና በውሃ ሃብታቸው መብት፤ አጠቃቀምና አይያዝ እንዲሁም በመንግስት ሚና ላይ ይከራከራሉ ፤ ይጨቃጨቃሉ ፤ ይወያያሉ ፤ ህግ ያጸድቃሉ። ትልቅ መነጋገሪያ አጀንዳ ነው። የድርቁ ፖለቲካ ድብቅ የለውም ፤ መሸዋወድ ቦታ የለውም ፤ እኔን ብቻ ስማኝ የሚል መልዕክትም ስፍራ የለውም ። ልኩ ሲበቃ ወደ ህግ ተቀይሮ መተግበር ብቻ ነው። ወለም ዘለም የለም። ህግና ስነ ስርዓት የተከበረበትና ተጠያቂነት ያለበት ነው። በጠመንጃ ነካሾች አይደለም ካሊፎርኒያ የምትገዛውና የምትተዳደረው።

የኛው ጠቅላይ ሚኒስቴር የእርሳቸውን አገር ድርቅ ደረጃውን ሳይረዱና ግንዛቤ ሳይጨብጡ በካሊፎርኒያና በአውስትራሊያም ተከስቷል ብለው ለማጣጣልና ትኩረት እንዳይሻው ለማድረግ ሞ ክረዋል። በዕለተ ሃሙስ በኦገስት 18 2015 ላይ በሳክራሜንቶ ቢ ጋዚጣ ላይ ግን የሚከተለው ዘገባ በታዋቂ የዩኒቨርስቲ ካሊፎርኒያ ተመራማሪዎች ድርቁ በግዛቱ ያስከተውን ውጤት እንዲህ ገልጸውታል። በ2015 የካሊፎርኒያው ድርቅ የግዛቱን መንግስት በጠቅላላው ወደ 2.74 ቢሊዮን ዶላር ወጭ እንዳስወጣውና የግብርናው ሴክተርም ለብቻው 1.84 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ የሚገመት ወጭ ላይ እንደጣለው ተገምቷል። በተጨማሪም ግምቱ 542,000 ኤከር ( 220,000 ሄክታር ) መሬት ስፋት ገበሬዎች በውሃ ዕጥረት ሳቢያ መሬታቸውን ጦም እንያሳደሩ እንደተገደዱና ወደ 10, 000 ( አስር ሺ) የሚጠጋ ጊዜያዊ ሰራተኛ ስራ አልባ እንደሆነባቸው ገልጸዋል። ርግጥ ነው የምግብ ምርቶችም የሸቀጥ ዋጋቸው ቀጥሏል ነገር ግን አብዛኛው ሰው ስራውን ይሰራል ኑሮውን እንደ ቀድሞው ይኖራል። ተርቦ ምግብ ፍለጋ ቀዬውን የለቀቀ ወይም የተሰደደ ሰው የለም። ካሊፎርኒያም የአሰቸኳይ የረሃብ ጊዜ አዋጅም አላወጀችም። የትኛውንም መንግስት የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋላት ልመና አልገባችም። እንደውም ይህ ሁሉ ሆኖ እንኳን ግብርናው ኢንዱስትሪ በተመራማሪዎች ያላሰለሰ ምርምርና የቴክኒክ ድጋፍ በተለይም በብቅለት ወቅታቸው አነስተኛ ውሃን መጠቀም የሚችሉ ተክሎች ዝርያዎችንና ዓይነቴዎችንና የመስኖ አጠቃቀማቸውን ውሃ ቆጣቢ በማድረግ ክፍለ ኢኮኖሚው አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በመጣር ላይ ናቸው።በአጠቃላይ መግለጫቸው ምሁራኖቹ ሲናገሩ የግዛቱ ግብርና ኢኮኖሚ ካላፉት ዓመቶች ሲነጻጸር የተሻለ፤ በማበብና በማደግ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

እንግዲህ ይህ ነው ድርቅ መታት ተብላ የተነገረላት ካሊፎርኒያ ዕውነታው። ዕውን የጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማሪያም መንግስት ” የድርቅ ፖለቲካ “ ማብራሪያ ካሊፎርኒያን እንደ ምሳሌ ማቅረቡ በዕውቀትና በመረጃ ላይ ተመስርቶ ወይስ እንደው ተባራሪ ዜና ሰምቶ ነው ለአገራችን ድርቅ ተመጣጣኝ ያልሆነ ማወዳደሪያና ማነጻጸሪያ ያቀረበው ?

ለዛሬው ላብቃና በሚቀጥለው እስክንገናኝ ቸር እንሰንብት !!!!!!

ከመድፍ ድምጽ አይሎ የተሰማ የጽናት ቃል (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

ከመድፍ ድምጽ ያየለ፣ ጽናትን፣ እምነትንና ጥንካሬን የሚያሳይ ታላቅ ድምጽ በመዲናችን ተሰማ። ማንም ቀስቃሽ ከሚያደርገው ጥሪ በላይ የክተት አዋጅ የመሰለ የእምነት ቃል ፈጽሞ ሊሆን ይችላል ተብሎ ከማይጠበቅበት አቅጣጫ ተሰማ! አዎ ለፍልሚያው ቆርጫለሁ እናንተን ከመንበረ ሥልጣኑ ለማንሳት በኔ አቅም ያለውን ሁሉ ለማድረግ ጉዞ ጀምሬአለሁ። በአካል ከስፍራው አልደረስኩም እንጂ በመንፈስ ሸፍቻለሁ ይህንን አምናለሁ ግን ግን ፈጽሞ ጥፋተኛ አይደለሁም! አሁንም ባለሁበት ሁኔታና ካለሁበት ለመታገል ከቶውንም ወደሗላ አልልም!

Ethiopian youth commitment to freedom

በእርግጥም ከነጎድጓድ ያየለ ከመድፍ ድምጽ አስርሺህ ጊዜ የበለጠ ሃያል ድምጽ በ‘አንበርካኪዎቹ’ ማማ ላይ በ‘አስጎንባሾቹ’ መድረክ ላይ ተሰማ። ኢትዮጵያ ያልታደለ ሕዝብ የሚኖርባት ግን የታደለች ሀገር ናት። አፈርና ውሀዋ የሰራው ዜጋዋ ከአየሩ ጋር አብሮ ከሚተነፍሰው የነፃነት መንፈስ ጋር ተዳምሮ ከዘመን ዘመን በኩራት እንዲረማመድ ሆኖ የተሰራ ነው። ለዚህም ነበር የጥቁር አፍሪካ ፈርጥ ለነፃነት ፈላጊዎች የመንፈስ ምርኩዝ ተብሎ የሚጠራው። ግና የእናት ሆድ ዥጉርጉር እንዲሉ ባርነትን የተከተቡ፣ ጥላቻ የተጠናወታቸው በአእምሮ ድህነት የሚሰቃዩ ከዚችው ኢትዮጵያ የተፈጠሩ የሰው አረሞች ቁልቁል ደፍቀው እምነትና ነፃነቱን ክፉኛ ፈትነውታል። አወቅን ባይ የትምክህት ባሮች እንቅፋት እየሆኑት በጠላት ወጥመድ ውስጥም እየጣሉት ከችግር ወደመከራ ከበረዶ ወደ እሳት የሚገላበጥበትን ገሃነማዊ ህይወት እንዲመራ አድርገውታል። የትግራይ ጎጠኞች ተስፋውን ያሟጠጠ እንዳሻን የምናደርገው ፈሪ ሕዝብ ፈጥረናል በሚሉበት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ አለንልሽ የሚሏት ለክብሯ ለነፃነቷ ሊሞቱላት የቆርጡ ጀግኖች ወደ ትግል ሜዳ ሲተሙ፣ በያሉበት ስንደቅዓላማዋን ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ ለተመለከተ ግን እውነትም የታደለች አገር! እንዲል ያስገድደዋል።

ይህ ያበቃለት የመሰለው የራሱ ወገኖች ደካማና ፈሪ አድርገው የሚስሉት ሕዝብ ጀግንነትና ቆራጥነት በደሙ ውስጥ መመላለሱን የሚያረጋግጥና ያለነፃነት ከመኖር ማናቸውንም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ግን ዕለት በዕለት እያስመሰከረ ነው። በየአደባባዩ፣ በየጉድባውና ሰርጣ ሰርጡ ጣዕረሞት ከመሰሉት የሀገርና የሕዝብ ጠላቶች ጋር ለመፋለም መቁረጣቸውን የሰማ ሁሉ ተስፋ በውስጡ እያበበች ነው። በርገር በሊታዎቹ ቂጣ ለመብላት የተዘጋጀ ስነልቦና እንዳላቸው አስመስክረዋል። ስሜታቸው ብቻ ሳይሆን አጥንታቸው የሟሟ የሚመስል በወያኔ እስር ውስጥ ተጠፍረው ያሉ ከአሳሪዎቻቸው ገዝፈውና ታላቅ ሆነው ደካሞቹን ቁልቁል ሲመለከቱ ማየትም ያለውን እምቅ ሃይል አመላካች ነው። የርዕዮት ብዕር ወረቀት ማድማቱን ማየት ስሜት የሚያሞቅ ነው። እነ አብርሃ ደስታ ቁም ነገር ሊከትቡ ወደ ትልቁ እስር ቤት መመለሳቸው እነ ሃብታሙ ‘እመነኝ!’ ሲሉ እንደገና ልንሰማ መሆኑን ማሰብ ደስ ያሰኛል።

በሌላ ወገን ወያኔ የተማመነበት ሰራዊት ኢትዮጵያዊነቱ በልጦበት እየከዳ ነው። መሳርያውንም ወደ አገር አፍራሽ ጎጠኞች እንደሚያዞር ምልክቶቹ ሁሉ እየታዩ ነው። ስማቸውን ያልሰማን ማንነታቸውን ያላወቅን ለጊዜው ማወቅም የማይገባን በርካታ ጀግኖች በዚህ የትግል መስመር ገብተው ለፍልሚያ ስለመዘጋጀታቸው ከቶወንም ጥርጣሬ የለንም። የሰላም በር ሲዘጋ የፍልሚያ መስኮቶች ይበረገዳሉና በየአቅጣጫው መነሳሳትን ማየታችንም ለዚሁ ነው። ከተሞች ሁሉ የትግል አምባ ወደመሆንና ጎጠኞችንና የሀገር ጠላቶችን በህግም በትጥቅም ቢሆን ለመፋለም ዝግጁነታቸውን እያረጋገጡ ነው። ፍርሃት ያራዳቸው የወያኔ ጉልተኞች ብር በሻንጣ ይዞ መሮጥ መጀመራቸውም የዚሁ አይነተኛ የውድቀት ምልክት ነው።

ወደ ጀመርኩት ርዕስ ልመለስና የነብርሃኑ ተክለያሬድን ዜና እንደሰማሁ ኢካድፍ የለጠፈውን ምስል ተመለከትኩ ሰውነት የሚወር ስሜት ተሰማኝ በወጣቶች ያለኝ ጽኑ እምነት ታደሰ። ኢየሩሳሌምን በስስት ዐይን ተመለከትኩ፣ የጀግና ክብር የሚገባት የጣይቱ ልጅ በሰላሙም ጎዳና ሁሉን ችላ በፅናት የሄደችበት ጀግናዬ ናት። ሽንታም እያሉ ለሚሳደቡት እንደኛ ለመሆን የጫካውን መንገድ ሞክሩ ለሚሉና ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ሆነው ኢትዮጵያን ወግተው በፈረንጅና በተጃጃሉ ኢትዮጵያውያን ትከሻ ስልጣን ላይ የወጡትን እብሪተኞች ለመፋለም ጉዞውን የጀመሩትን ጀግኖች አንኳን እኔ ጠላትም እንዲያደንቃቸውና እንዲያከብራቸው ግድ ይለዋል። መድረኩን አገኙ ቃላቸውን ሰጡ። ቃላቸው ግን ድፍን የኢትዮጵያ ወጣቶችን የሚያስሸፍት እንዲሆን ቅንጣት ታክል አልጠራጠርም።

ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ኢየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ ዳሴ ካሳሁን ክብር ለናንተ ይሁን። ካሰባችሁበት ያልደረሳችሁ መስሏችህ ከሆነ አትሳሳቱ ማናችንም ከምናሰበው በላይ ግዳጃችሁን ተወጥታችሗል። መድረስ ብቻ አይደለም አልፋችሁ ሄዳችሗል። ከጠላት ምሽግ ገብቶ የጨበጣ ውጊያ ከመግጠም በላይ የእምነት ቃላችሁ ስራውን ሰርቷል። በዚህ በርካቶች አንገት በደፉበት ሰዐት፣ በርካቶች በሌሎች ትከሻ መሸጋገርን በሚሹበት ጊዜ እናንተ ድልድይም መስዋዕትም ሆናችሁ ለታሪክ የሚተርፍ ገድል ፈጽማችሗል። አዎ ጥፋተኛ ሳትሆኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግኖቹ ናችሁና ደስ ይበላችሁ። ፈለጋችሁን የሚከተሉ በረሃ የሚዘልቁም ሆነ ባሉበት ሆነው በተጠንቀቅ የሚጠብቁ በርካቶችን በማነሳሳታችሁ ክብር ለእናንተ ይሁን።

ኢትዮጵያ በነፃነትና በክብር ለዘለዐለም ትኑር!

“ሀገር የተቀማ ትውልድ” የተሰኘው የዳንኤል ተፈራ መጽሐፍ እየተነበበ ነው

10982923_1628074940797036_6567925336806387860_nሰሞኑን በዳንኤል ተፈራ ተፅፎ ለገበያ የቀረበው ‹‹ሀገር የተቀማ ትውልድ›› የተሰኘው ወጥ የሆነ የፖለቲካ መፅሐፍ እየተነበበ መሆኑን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡

እንደምንጮቻችን ገለፃ ወጣቱ ደራሲ፣ አርታኢና ፖለቲከኛ ዳንኤል ተፈራ በአጠቃላይ ለአንባቢ ያደረሳቸው መፅሐፎች ሦስት ሲሆኑ ስድስት ለሚሆኑ የፖለቲካ መፅሐፎችም የአርትኦት ስራ ሰርቷል፡፡ ሰሞኑን ገበያ ላይ ውሎ እየተነበበ ካለው ‹‹ሀገር የተቀማ ትውልድ›› ከሚለው መፅሐፉ በፊት እጅግ ተነባቢ የሆኑ ሁለት መፅሐፎችን ለአንባቢያን እንዳደረሰም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የደራሲው ቀዳሚ ስራ በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት እና በኋላም የተቃውሞ ጎራው መሪ የነበሩትን ዕውቅ ሰው ዶ/ር ነጋሶ ጎዳዳ ሶለንን የህይወት ታሪክ የሚዳስስ ‹‹ዳንዲ- የነጋሶ መንገድ›› የተሰኘው ነው፡፡ ይሄ መፅሐፍ በ2003 ዓ.ም ለህትመት የበቃ ሲሆን በአንድ ሳምንት ብቻ ሃያ ሺ ኮፒ በመሸጥ ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው፡፡ ከዚያ በኋላም ለአራት ጊዜ እንደታተመ ደራሲው አረጋግጧል፡፡ ደራሲው እንደሚገልጠው መጽሐፉ 384 ገፆችና አምስት ንዑስ ክፍሎች ያሉት ሲሆን የዶክተሩን ከልጅነት እስከ ዕውቀት እንዲሁም የፖለቲካ ታሪካቸውን ያካተተ ነው፡፡ መፅሐፉን ለማዘጋጀት አመት ከሶስት ወር እንደፈጀ ደራሲው ይናገራል፡፡

Daniel Tefera

ቀጣዩ የዳንኤል ስራ ከ1997 ዓ.ም በኋላ በፓርላማ አባልነታቸው በከፍተኛ ተከራካሪ በነበሩት የተከበሩ አቶ ተመስገን ዘውዴ የፖለቲካ ህይወትና እንዲሁም በፓርላማው ውስጥ ሕወሃት/ኢህአዴግ ሲፈፅም የነበረውን ሸፍጥ ያጋለጡበት ‹‹ከፓርላማው በስተጀርባ›› የተሰኘው መፅሀፉ መሆኑን ለዘጋቢያችን ተናግሯል፡፡

ሰሞኑን ገበያ ላይ የዋለው ‹‹ሀገር የተቀማ ትውልድ›› ደግሞ የፀሃፊው ወጥ የፖለቲካ ስራ ሲሆን 224 ገፅ ያለው ነው፡፡ መፅሐፉ በ27 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን በዋናነት በዘመነ ኢህአዴግ ወጣቱ ትውልድ እንዴት የሀገር ፍቅር እንዲያጣ እንደተገረገና ሀገር አልባ ለማድረግ የተከናወኑ የፖለቲካ ሸፍጦችን የሚተርክ መፅሐፍ ነው፡፡ ደራሲው እንደገለፀው፡- ‹‹ስርዓቱን በአሽከርነት ካላገለገልክ እጣ ፈንታህ ሃገር መቀማት ነው፡፡ ‹‹ሃገር ማለት ሰው ነው!›› ይሉሃል እንጂ ሃገር ኢህአዴግ ሆኗል፡፡ ኢህአዴግ ካልሆንክ ስራ አይኖርህም፣ ኮንዶሚንየም አይደርስህም፣ መነገድ አይፈቀድልህም፣ ደመወዝ አይጨመርልህም፣ ጡረታ አይከበርልህም፣ የትምህርት እድል አይሰጥህም፣ በነፃነት መወዳደርና ጨረታ ማሸነፍ አያስችልህም፡፡ ይህ ማለት ሃገር ተቀምተሃል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ለመፃፍና ትውልዱ ሀገር እንዲቀማ የሰሩ፣ የቀሙ፣ ያስቀሙ፣ ያቀማሙና የተቀሙትን ታሪክ በማንሳት ሀገር ይረከባል የሚባለው ትውልድ እንዲነቃቃና የሀገር ባለቤት እንዲሆን በማሰብ የተፃፈ ነው በማለት ሀሳቡን ገልጧል፡፡

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46085#sthash.pSy2L0s9.dpuf

የድህረ-መለሱ ኢሕአዴግ አሰላለፍና የ“አዲሱ” ሥራ አስፈጻሚ የቢሆን ዕድል

tplf-eprdf-e1440205736459-620x310የአራት ድርጅቶች ስብሰብ የሆነው ኢሕአዴግ፤ በሕወሓታዊ የድርጅት መንፈስ እየተመራ የስልጣን ቆይታ ዘመኑን ከአመታት ልኬት ወደ አስርታት ያሻገረ በመሆኑ፣ ከእንግዲህ የአገዛዝ ዘመኑን በክፍለ ዘመን ክፋይ አገላለጽ መጥራቱ ተራዛሚ የስልጣን ቆይታውን ይበልጥ የሚገልፀው ይሆናል፡፡ እናም ሩብ ክፍለ ዘመን ያህል በስልጣን ላይ ያለው ኢሕአዴግ በሰሜን ኢትዮጵያ የፖለቲካ ተዋረድ አገሪቱን “እየመራ” እዚህ ደርሷል፡፡ ግንባሩ ከፊት ለፊቱ አንደ “ትልቅ” ድርጅታዊ ጉባኤ ይጠብቀዋል፡፡

ነሐሴ 20/2007 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ የድርጅቱ አስረኛ ጉባኤ መካሄድ ይጀምራል፡፡ የመቀሌው ጉባኤ ከመካሄዱ ከቀናት በፊት፣ አራቱም ድርጅቶች በየክልል ርዕስ ከተማቸዉ የየራሳቸውን ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ የድርጅታችዉን ሊቀ-መንበርና ም/ሊቀመንበር የሚመርጡ ይሆናል፡፡ ዛሬ ላይ እየታየ ካለው የግንባሩ ከፍተኛ አመራሮች እንቅስቃሴ አኳያ፣ አራቱም አባል ድርጅቶች የሊቀመንበር ለውጥ የሚያደርጉ አይመስልም፡፡ ይህ የሚሆን ከሆነ፣ ህወሓት አባይ ወልዱንና ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ ብአዴን ደመቀ መኮንንና ገዱ እንዳርጋቸውን፣ ኦህዴድ ሙክታር ከድርንና አስቴር ማሞን እንደ ቅደም ተከተላቸው በሊቀመንበርነትና ምክትል ሊቀመንበርነት እንዲቀጥሉ ይደረግ ይሆናል፡፡ ደኢህዴን በበኩሉ የድርጅቱ እና የኢሕአዴግ የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑትን ኃይለማርያም ደሳለኝን በሊቀመንበር ማስቀጠሉ አይቀሬ ነው፡፡

ይሁንና በሥራ አፈጻጸም ድክመት ከደቡብ ክልል ርዕስ መስተዳደርነታቸው በመነሳት የትምህርት ሚኒስትር በመሆን እንደ ተሾሙ የሚነገርላቸዉ (ትምህርት ሚኒስቴር ግን የ“ዲሞሽን” ማራገፊያ ሆነ ማለት ነዉ!?) አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ የወቅቱ የደኢህዴን ምክትል ሊቀ መንበር ቢሆኑም አሁን ካላቸው አፈጻጸም አኳያ የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር እንደሆኑ እንዲቀጥሉ የሚደረግበት ሁኔታ የሚኖር አይመስልም፡፡ ሰውየው በምክትል ሊቀ መንበርነት የማይቀጥሉ ከሆነ ቦታው ላይ አዲሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደሴ ዳልኬ መተካታቸው አይቀሬ ነው፡፡

የሆነዉ ሆኖ፤ በቀኝ ሲጠብቁት በግራ፣ መኃል ላይ ሲፈልጉት ከዳር የሚገኘው ኢሕአዴግ፤ በመቀሌው አጠቃላይ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ከሚወስናቸው ተጠባቂ ውሳኔዎች ውስጥ ድርጅቱን እስከ ቀጣዩ ጉባኤ ድረስ በሊቀ-መንበርነት እና ምክትል ሊቀመንበርነት የሚመሩትን አመራሮች መምረጥ እንዲሁም ለረጅም አመታት ያገለገሉ አንጋፋ አመራሮችን ማሰናበት ወ.ዘ.ተ. የመሳሰሉት ዉሳኔዎች ይገኙበታል፡፡ የዚህን ጉባኤ ውሳኔ ተከትሎ በአዲሱ ዓመት መግቢያ ወር ላይ “አዲስ” የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ እንደሚዋቀርም ይጠበቃል፡፡ የቀጣይ ጊዜያት የግንባሩ ሊቀ-መንበር እና ምክትል ሊቀ-መንበር ማን ይሆናል? በ“አዲሱ” የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ እነ ማን ይቆያሉ? እነ ማንስ ይሰናበታሉ? የሚሉ ጉዳዮችን በቢሆን እድል ከማስቀመጣችን በፊት በድህረ-መለስ አጠቃላይ የስልጣን ገፅታ የአራቱ አባል ድርጅቶች አሰላለፍ ምን ይመስላል የሚለውን ጉዳይ አንድ በአንድ ማየቱ የሚጠቅም ይሆናል፡-

አስኳሉ-ሕወሓት

የፖለቲካ መሪነትን በበረሃ ትግል ተፈትኖ ከማለፍ ጋር ብቻ በማያያዝ የሚተረጉሙ የፖለቲካ ትምክህተኞች ስብሰብ የሆነው ይሄው ድርጅት በግንባሩ ውስጥ ያለውን የበላይነት ለመግለፅ “የኢሕአዴግ አስኳል” የሚለው ሀረግ የድርጅቱን ጉልበታምነት ይበልጥ የሚገልፀው ይሆናል፡፡ የግንባሩን አባል ፓርቲዎች በራሱ የፖለቲካ አጀንዳ ልክ ቀርፆ በመስራትም ሆነ “አጋር ፓርቲዎች”ን ለ’ንጉስ አንጋሽ’ነት ፖለቲካ አመቻችቶ በመፍጠሩ ረገድ ረጅም ርቀት የተጓዘው ይሄው ድርጅት፤ ከድህረ መለስ በኋላ ያለው የስልጣን ከራሞቱ በመተካካት ችግር (succession crisis) የተጠቃ አስመስሎታል፡፡ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ የሰውየውን ቦታ አሳልፎ ላለመስጠት በህወሃት በኩል ለህዝብ ይፋ ያልወጡ ድርጅታዊ መተጋገሎች ተከስተው እንደነበር እሙን ነው፡፡ ለዚህ ማሳያ ሆኖ የሚቀርበው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ህልፈት በኋላ የአቶ ኃይለማርያምን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ለማፅደቅ የወሰደው ጊዜ፣ በነዚህ ጊዜያት አቶ ኃይለማርያም ይጠሩባቸው የነበሩ የሹመት መጠሪያዎች (አንዴ ውጪ ጉዳይና ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ሌላ ጊዜ ደግሞ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚል መሆኑ) እንዲሁም ከሰውየው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት በኋላ ለሠላሳ አንድ ቀናት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተመንግስቱን ባለመልቀቅ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከብስራተ ገብርኤል አራት ኪሎ ድረስ በተመላላሽ እንዲቆዩ የተደረገበት አጋጣሚ እና ህገ መንግስታዊ አግባብ በሌለው መልኩ ሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር (በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ … የምትለዋ ሀረግ የፖለቲካ ሀሁ ስለገባን ለጊዜው እናቆያት) የተሾመበት መንገድ ላስተዋለ ሰው ሕወሓት እንደ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሁሉንም ስልጣን መጠቅለል የሚችል ሁነኛ የፖለቲካ መሪ በማጣቱ የተነሳ አሳልፎ የሰጠው ወንበር ስለመሆኑ ድምዳሜ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡

በርግጥ ህወሓት ሁነኛ የፖለቲካ መሪዎቹን ያጣው (ጥብቅ ብሔርተኝነታቸውን ተከትሎ ይታይባቸው የነበሩ አምባገነናዊ ባህሪያቶችን ሳንዘነጋ) የኢትዮ-ኤርትራ ግጭትን ተከትሎ በድርጅቱ ውስጥ በታየው መከፋፈል የተነሳ ነው፡፡ በወቅቱ “አንጃ” በሚል ፍረጃ መጀመሪያ ከማዕከላዊ ኮሚቴ ቀጥሎም ከድርጅቱ አባልነት ከታገዱት ሲቪል ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ ተወልደ ወ/ማርያም፣ ስየ አብርሃ፣ ገብሩ አስራት፣ አረጋሽ አዳነ፣ ዓለምሰገደ ገ/አምላክ፣ አውዓሎም ወልዱን የመሳሰሉ ጉምቱ የፖለቲካ አመራሮች የሚገኙበት ሲሆን፣ ከዚህ ጊዜ በኋላ እነዚህን የፖለቲካ መሪዎች የሚስተካከሉ የአደባባይ ፖለቲከኞችን ወደ ፊት ማውጣት ያልቻለው ድርጅት ከመለስ ሞት በኋላ የመተካካት ችግሩ ይፋ ሆኖ ወጥቷል፡፡ በ1993ቱ የህወሓት ክፍፍል ወቅት አባይ ፀሐየ እና ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከ“አንጃ”ው ጋር ተፈርጀው የነበረ ቢሆንም በድርጅቱ “ተሐድሶ” ሂሳቸውን በመዋጥ ለመመለስ በቅተዋል (ምናልባትም ህወሓት እነዚህን ሁለት የጊዜያችን አራጊ ፈጣሪ የፖለቲካ መሪዎች በ“ተሐድሶ” መልክ ባይቀበላቸው ኑሮ ዛሬ ላይ ድርጅቱ በእነ ቴድሮስ አድሐኖም እንዴት ሊደገፍና የበላይነቱን ሊያስረግጥ እንደሚችል ማሰብ ይከብዳል)

እጅግ አስገራሚዉ ነገር! አባይ ጸሀየ የዛሬ አርባ አመት (1968ዓ.ም) የህወሓት የህዝብ አደረጃጀት በመሆን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበሩ፡፡ ይሄዉ ከአርባ አመት በኋላም የድርጅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ አባል ናቸዉ፡፡ ይህ አልበቃ ብሎ ገና ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የህወሓት ፖሊት ቢሮና የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ አባል በመሆን የጀርባ አሽከርካሪነታቸዉን አጠንክረዉ ይቀጥላሉ፡፡ የድህረ-መለሱ የስልጣን ሽግሽግ በህወሓት ዉስጥ የአባይ ጸሃየን ያህል የጠቀመዉ ሰዉ የለም፡፡ ድርጅቱም የመተካካት ድርቅ እንዳጋጠመዉ የሰዉየዉ ተራዛሚ የስልጣን ቆይታ ጮኾ ይመሰክራል፡፡ ድንቄም መተካካት!!

የሆነው ሆነ በፖለቲካ መሪ መኻንነት አብዝተን ልንተቸው የሚቻለን ህወሓት ከአረጋሽ አዳነ በኋላ አዜብ መስፍንን እንጂ የተሻለች ሴት ፖለቲከኛ ወደ አደባባይ ለማውጣት አልተቻለም፣ እንደ ገብሩ አስራት ያለ ሞግዚት ፖለቲከኛ በትግራይ ክልል አመራሮች ማየት የማይታሰብ ሆኗል፤ እንደ ዓለምሰገደ ገ/አምላክ ያለ የሚዲያ ጠርናፊ በህወሓት ቤት ደግሞ አልተከሰተም … ድርጅቱ እነዚህን የፖለቲካ መሪዎች በማጣቱ በብዙ መልኩ የፖለቲካ ባዶነት ታይቶበታል፡፡ ለዚህ እኮ ነው ድርጅቱ ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በጤና አጠባበቅ ዙሪያ የሰሩትን ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖምን ከጤና ሚኒስትርነት በማንሳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በማድረግ ለማስቀመጥ የተገደደው፤ ሰውየው ለቦታው ምን ያህል ይመጥናሉ? የትምህርት ዝግጅታቸውና ዝርዝር የሥራ ኃላፊነትና ተግባራቸው ይመሳሰላል? ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉ ጥያቄዎች ወደ ጎን ተገፍተው፣ ስለ ስልጣን ሽሚያ ሲባል የድርጅቱ ሰው ስለሆኑ ብቻ እንዲቀመጡ የተደረገበት መንገድ ሕወሓት በምን ያህል መጠን የአመራር ድርቅ እንዳጋጠመው ያሳያል፡፡

ያም ሆኖ ግን፣ ሕወሓት የፖለቲካ አመራር ድርቀቱን የሚሻገርባቸው ሁለት ዋና ዋና ምርኩዞች አሉት፡፡ አንደኛው የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ሰራዊቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ተቋማት ለጊዜውም ቢሆን የድርጅቱ ፖለቲካዊ ጉልበት እንዳይነጠቅ የላቀ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ የድርጅቱ የአስኳልነት ምንጭም ይሄው ነው፡፡

ሁሌም ለደረጃ ሁለት – ብአዴን

በ1993ቱ የህወሓት ክፍፍል ወቅት የብርቱ ደጀንነት ሚና የተጫወቱት የብአዴን አመራሮች ከህወሓት/ኢሕአዴግ የድርጅት “ተሐድሶ” በኋላም ቢሆን የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀንደኛ ደጋፊ በመሆን በማዕከላዊ መንግስቱ ላይ የሁለተኛ ደረጃ የመሪነት ተሳትፏቸው እንዳይነጠቅ የፖለቲካ ታማኝነታቸውን ገቢር ሲደርጉ ቆይተዋል፡፡ የብአዴን አመራሮች ጮክ ብለው ስለከፈሉት መስዋዕትነት የሚያወሩትን ያህል ባይሆንም እንኳ ከወታደራዊ አበርክቶ ይልቅ የፖለቲካ አበርክቷቸው የላቀ እንደነበር ይታመናል፡፡ ይህ ሲባል ግን ደርግን በመፋለም ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ፣ የአካል ጉዳተኛ የሆኑ የኢህዴን/ብአዴግ ታጋዮችን ዋጋ ለማቅለል እንዳልሆነ ልብ ይባል፡፡ ሁሌም ቢሆን ኢህአዴግ ከወቅታዊ የፖለቲካ መሪነት ብቃት ይልቅ የበረሃ ላይ መስዋዕትነትን ታሳቢ ያደረገ የስልጣን ድልደል ያለው በመሆኑ እንጂ፡፡

በድህረ-መለስ የስልጣን እርካብ ላይ የብአዴን አመራሮች በተለይም በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ህልፈት ሰሞን ብዙዎቹ የህወሓት አመራሮች ድምፃቸው በጠፋበት ሁኔታ የበረከት ስምኦንና የአዲሱ ለገሰ ለሚዲያ ቅርብ መሆን፣ ካሳ ተክለብርሃን ከቀብር አስፈፃሚነት እስከ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጪነት የደረሰ ድርብ ሚና ይዘው ብቅ ያሉበትን ሁኔታ ስናስታውስ፣ አጋጣሚውን ተጠቅመው የደረጃ ሁለት የመሪነት ሚናቸውን ለማሳደግ ሙከራ ውስጥ ገብተው እንደነበር አስረጂ ምሳሌ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፡፡ አልሆነም እንጂ፡፡

ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ በተደረገው የአመራር ሽግሽግ የብአዴን አመራሮች የተመኙነትን የደረጃ አንድ መሪነት ሚና ባያሳኩም፤ በመተካካት ሰበብ አጥተውት የነበረውን የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ እንዲሁም በአቶ መለስ የስልጣን ቆይታ ጊዜ “የቦዘኔ ቦታ” በአቶ ኃይለማርያም ጊዜ ደግሞ በግልባጩ “የስልጣን የሻሞ ውጤት” ተደርጎ በሚወሰደው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊስና ጥናትና ምርምር አማካሪነት ቦታ ላይ ከባድ ሚዛን ተጫዎቹን አቶ በረከት ሰምኦንን ማስቀመጥ መቻላቸው፣ አቶ አዲሱ ለገሰ በጡረታ ከተሸኙበት ድርጅታቸው ዳግም በስራ አስፈፃሚነት ሚና እንዲከሰቱ የተደረገበትን አጋጣሚ ስናስተውል … ደረጃ ሁለት የሆኑት የድርጅቱ አመራሮች የሰርክ ቦታቸውን በማስጠበቅ ለቀጣዩ ቦታ የስልጣን ሽሚያ ውስጥ ለመግባት ያቆበቆቡ ይመስላል፡፡ በአንፃራዊ እይታ ብዛት ያላቸው የተማሩ መካከለኛ አመራሮች እንዳሉት የሚነገርለት ይሄው ድርጅት በየትኛውም መጠን ተተኪ አመራሮችን አዘጋጀ ቢባል እንኳ ወደ ደረጃ እንድ የፖለቲካ መሪነት የማደግ እድሉ ጠባብ መሆኑን በአዲስ መስመር እንመልከት፡-

ብአዴን “እየመራሁት ነው” በሚለው ክልል ውስጥ እንደ ድርጅት የህዝባዊ ቅቡልነት ችግር እንዳለበት ከአንባቢ የተሰወረ አይደለም፡፡ ከዚህም ባለፈ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “የብአዴን መካከለኛ አመራሮች ሲፋቁ አርበኞች ግንቦት ሰባት ናቸው” የሚል የአደባባይ ሐሜት ተንሰራፍቷል፡፡ ለዚህ ጉዳይ አስረጂ ምሳሌ ሆኖ የሚቀርበው በ2006 ዓ.ም በጥር ወር ላይ የብአዴን ዋና ፀሐፊና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የሆነው አቶ አለምነው መኮንን በባህር ዳር ከተማ የድርጅቱን መካከለኛ አመራሮች ሰብስቦ “አማራ”ን በተመለከተ ያደረገው የጥላቻ ንግግር (hate speech) ተቀርጾ ለኢሳት መድረሱና የአንድ ሰሞን የማህበራዊ ድረ ገፆች መነጋገሪያ የመሆኑ ጉዳይ አንደኛው አስረጂ ምሳሌ ነው፡፡ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ በ2007 ዓ.ም ህዳር ወር ላይ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች በበረከት ስሞንና አዲሱ ለገሰ ሰብሳቢነት ያደረጉት ዝግ ስብሰባ ላይ የተቀነጨበ የድምፅ ሪከርድ ለኢሳት ጋዜጠኞች የደረሰበትን አጋጣሚ ስናስታዉስ፣ የድርጅቱን መካከለኛ አመራሮች በውስጥ አርበኝነት ለመበየን ድፍረት ይሰጠናል፡፡

ዛሬ ላይ ከህወሓት/ኢሕአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ ብአዴንን በድፍረት “የብአዴን መካከለኛ አመራሮች ሲፋቁ አርበኞች ግንቦት ሰባት ናቸው” ለማለት የሚደፍር የፖለቲካ መሪ ባይኖርም፣ ከቃላት በላይ አንዳንድ ድርጊቶች ጮኸው እየተናገሩ ያለበት ሁኔታ አለ፡፡ እናም የዚህ ድርጅት መካከለኛ አመራሮች የጀርባ መደብ ፈርጅ በፈርጅ ባልተጠናበት ሁኔታ ስለ ድርጅታዊ ኮታ ሲባል ወደ ከፍተኛ አመራርነት በተለይም ወደ ማዕከላዊ መንግስቱ ይሳባሉ ብሎ መጠበቅ አንድም የዋህነት ሁለትም የሕወሓትን ጫፍ የረገጠ ጥርጣሬ ካለመረዳት የሚመነጭ ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያ “እኛ ከፊት መስመር ገለል ብለን ከኋላ መደገፍ ይኖርብናል” በሚለው የበረከት ስምኦን አገላለፅ መሰረት፣ ደረጃ ሁለትነቱን አምኖ የሚቀበል ተተኪ አመራር እየተመለመለ በኋላ ደጀኖች እየተደገፈ ድርጅቱ የሚቀጥል ይመስላል፡፡

በጥንቸሎች የታሰረው ዝሆን – ኦሕዴድ

ኦሕዴድ፣ ከኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ውስጥ በቀዳሚነት የተረጋጋ አመራር የሌለው ድርጅት ነው፡፡ ህወሓት በስልጣን ዘመኑ ሁለት የድርጅት ሊቀመንበሮች ያየ ሲሆን፣ በአንፃሩ ኦሕዴድ ኩማ ደመቅሳ፣ አባዱላ ገመዳ፣ አለማየሁ አቶምሳ (ነፍስ ይማር!) እና ሙክታርና ከድር ተፈራርቀውበታል፡፡ ሃያ ሰባት ሚሊዮን የሚሻገር ህዝብ “የሚመራው” ኦሕዴድ ያልተረጋጋ አመራር እና እርስ በርስ ባለመተማመን የተከፋፈሉ የፖለቲካ መሪዎች ያሉበት ድርጅት ለመሆኑ ከኩማ ደመቅሳ እስከ ሙክታር ከድር ድረስ ያለው የድርጅቱ ታሪክ የአደባባይ ምስክር ነው፡፡ ከግንባሩ አባል ድርጅቶች በተለየ መልኩ የአቶ መለስ ጣልቃ ገብነት ረዝሞ ይታይ የነበረው በዚሁ ድርጅት ላይ ነበር፡፡

የኩማ ደመቅሳ የቀደመ የፖለቲካ ፊትነት ከ1993ቱ የህወሃት ክፍፍል በኋላ መገታት፣ የአባዱላ ገመዳ የኔትወርክ ፖለቲካ እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ ያለፉ መካከለኛ አመራሮችን የማፍራት ሂደት ሰውየውን ወደ ማዕከላዊ መንግስቱ መቀመጫ በመሳብ ሂደቱ መጨናገፉ፣ የአቦ አለማየሁ አቶምሳ ፀረ-ሙስና ትግል መስመር ሳይዝ አወዛጋቢ በሆነ መልኩ በምግብ መመረዝ ምክንያት ለሞት መዳረግ፣ አቶ ሙክታር ከድር የህዝብ ተወካዮች የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት አባል ባልሆኑበት ሁኔታ የክልሉ ፕሬዚዳንት በመሆን መሾማቸውና ሌሎች መሰል ክስተቶችን ከህግ አግባብ አኳያ ላስተዋለ ሰው፣ ድርጅቱ በአባላት ብዛት የገዘፈ ቢሆንም አነስተኛ የህዝብ ውክልና ይዘው ማዕከላዊ መንግስቱን በተቆጣጠሩት የህወሓት ባለስልጣናት ዕዝ ሥር የወደቀ ፓርቲ ለመሆኑ መረዳት አያዳግትም፡፡

ማዕከላዊ ኃይል አልባነትና የኢኮኖሚ በዝባዥነት መገለጫቸዉ የሆነው የኦህዴድ አመራሮች በድህረ-መለስ የስልጣን እርካብ፣ ድርጅታዊ ኮታን ከማስጠበቅ አኳያ የሙክታር ከድር ወደ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ከመሳብ፣ ቆይቶም በአስቴር ማሞ ከመተካቱ ውጭ፣ የድርጅቱን አመራሮች ይህ ነው በሚባል የስልጣን ከፍታ ላይ ለማየት አልቻልንም፡፡ የአምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ በመቀበልና በመሸኘት የተገደበው የማዕከላዊ መንግስቱ የፕሬዝዳንትነት ቦታ እንደሆነ ከድሮውም ቢሆን የኦህዴድ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ጥናትና ምርምር አማካሪ በሚል ተሹመው የነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር በሚል ከተሾሙ በኋላ በምትኩ የኦህዴድ አባል የሆነ አመራር አለመተካቱ፣ ፓርቲው በግንባሩ ውስጥ በምን ያህል መጠን እየተገፋ እንዳለ ያሳያል፡፡

በኦህዴድ የፖለቲካ መስመር ላይ ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ በመሮጣቸው የተነሳ “መተካት” በሚለው ድርጅታዊ ፈሊጥ ከኦህዴድ ስራ አስፈጻሚነት የተነሱት አቶ አባዱላ ገመዳ በድህረ-መለስ የፖለቲካ ሜዳ ላይ በአንፃሩ ጎላ ብለው የታዩ ብቸኛው የድርጅቱ ሰው ናቸዉ ማለት ይቻላል፡፡ በተለይም ከአዲስ አበባ የተቀናጀ የልማት ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ግጭት ለማብረድ ከአምቦና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በተደረገው ውይይት የፊት መስመር ተሰላፊ መሆናቸው፣ በወቅቱ ለአንድ የውጭ አገር ሚዲያ በሰጡት ቃለመጠይቅ ላይ በሟች ወጣቶች ላይ የስርዓቱ ወታደሮች የወሰዱት እርምጃ ተገቢ አለመሆኑን በድፍረት የገለፁበት ሁኔታ፣ “የአዉራ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ባህሪያት” በሚል ርዕስ ዙሪያ የኢሕአዴግን አዲስ የስልጣን አቋም የሚያስተነትን የጥናት ወረቀት የምክር ቤቱ ቋሚ የኮሚቴ አባላት፣ ከሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤት የተወከሉ አመራሮች እና የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች በተገኙበት ማቅረባቸው፣ በ2007 ዓ.ም የካቲት ወር ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ባህር ዳር ላይ በተከበረው የመከላከያ ሰራዊት ቀን ስለ ጦር ሰራዊቱ አጠቃላይ ሁኔታ የሚያተኩር የጥናት ወረቀት ማቅረባቸው፣ በአባይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራውን አዲሱን “የፐብሊክ ዲፕሎማሲ” ቡድን በመምራት ወደ ተለያዩ አገራት ማቅናታቸው፣ የ2007ቱን ሀገር አቀፍ ምርጫን አስመልክቶ በነበረው ቅድመ ዝግጅት ቴክኒካዊና ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንደ ሀሳብ አመንጪነት ማገልገላቸው፣ በኦህዴድ ምስረታ የብር እዮቤልዬ በዓል አከባበር ላይ የኦህዴዱ መለስ በሚመስል ድርጊት መወከላቸውን እና ሌሎች የአደባባይ እንቅስቃሴያቸውን ስናስተውል፣ ያረጀ እባብ ቆዳውን ገፎ እንደሚወጣው ሁሉ ሰውየም የመለስ አለመኖር የፈጠረላቸውን ምቹ እድል ተጠቅመው እያንሰራሩ እንዳለ ለመገመት አይከብድም፡፡

በድህረ-መለስ የስልጣን እርካብ ላይ ኦህዴድ እንደ ድርጅት ካሳየው እንቅስቃሴ በላይ የአባዱላ ገመዳ ፖለቲካዊ ጥን-ጥን የተሻለ ለመሆኑ የሰውየውን የሦስት አመት ቆይታ ማስተዋል በቂ ነው፡፡ የነገሩ ምፀታዊነትም ይኼው ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ሰፊውን የቆዳ ስፋትና ቀዳሚውን የህዝብ ቁጥር የያዘውን የኦሮሚያ ክልልን “የሚመራው” ኦህዴድ፣ ኢሕአዴግ አሉኝ ከሚላቸው ስድስት ሚሊዮን አባት ውስጥ ሁለት ሚሊዮኑን ቢረክዝም፣ የ“አጋር ድርጅቶች”ን ወንበር ሳይጨምር ኢሕአዴግ በፓርላማው ካለው 501 የምክር ቤት መቀመጫ ውስጥ 178 ወንበሮችን ቢያዋጣም (የትግራይ ክልል በፓርላማው ያለው የመቀመጫ ብዛት ሠላሳ ስምንት ከመሆኑ አንፃር፣ ኦህዴድ ከህወሓት አራት እጥፍ ዋጋ ያለው የወንበር መጠን እንዳለው ልብ ይሏል) የዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት እስረኛው ኦህዴድ፣ በጥንቸሎች እንደታሰረ ዝሆን ግዝፈቱ እንጂ እንቅስቃሴው ሊታይ አልቻለም፡፡

ሚዛን አስጠባቂው – የደኢሕዴን

የድል አጥቢያ መሪዎች ስብስብ የሆነው የደኢህዴን፣ በመለስ/ኢህሐዴግ ዘመን እንደ “አቻ”ዎቹ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች (በዋናነት ህወሓት-ብአዴን) ወሳኝ የሆኑ የፖለቲካ መሪነት ሚናውን የሚያሳይባቸው የስልጣን ቦታዎች አምብዛም አልነበሩትም፡፡ የግንባሩ የመተካካት ፖሊሲ ይፋ ከሆነበት የሐዋሳው ድርጅታዊ ጉባኤ በኋላ፣ የ2002ቱን “ምርጫ” ተከትሎ የመጀመሪያው ዙር መተካካት ገቢር በሆነበት ጊዜ፣ ከዚህ ቀደም በማዕከላዊ መንግስቱ የፖለቲካ አደባባይ ላይ በአንፃሩ ይታወቁ ከነበሩት ከእነ ዶ/ር ካሱ ኢላላ፣ የወቅቱ አፈ-ጉባኤ ተሾመ ቶጋና መሰል አመራሮች በተሻለ ቦታ በዋናነት ኃይለማርያም ደሳለኝ ውጭ ጉዳይና ም/ጠቅላይ ሚኒስተር፣ ሽፈራው ተክለማርያም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር፣ ሲራጅ ፈጌሳ የመከላከያ፣ መኩሪያ ኃይሌ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ደሴ ዳልኬ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ሲሆኑ፤ ጥቂት የማይባሉ የድርጅቱ አመራሮች በልዩ ልዩ ሚኒስተር መስሪ ያቤቶች በሚኒስተር ዲኤታነትና በዋና ዳይሬክተርነት በቀድሞዎቹ የሕወሓት-ብአዴን አመራሮች ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን ተክተው በመስራት የአደባባይ ፖለቲከኛነታቸው በስፋት መታየት ጀመረ፡፡

በመጀመሪያው ዙር የመተካካት ሂደት ውስጥ እንደ “ኃይል” (ያው ዋናው ኃይል ያለው ደህንነት መሰሪያ ቤቱና መከላከያ ውስጥ ስለሆነ በሚል ነው ቃሉ ትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ የገባው) ሚዛን ማስጠበቂያነት የደኢህዴን አመራሮች አገልግለዋል ማለት ይቻላል፡፡ የደኢህዴንን ሚዛን አስጠባቂነት በተሻለ የሚገልፀው አጋጣሚ ደግሞ የአቶ መለስን የደህንነት ህልፈት ተከትሎ በግንባሩ አባል ድርጅቶች በተለይም በህወሓትና ብአዴን ውስጥ የጠቅላይ ሚኒስተርነት ቦታውን ለመውሰድ የነበረውን የድርጅት ውስጥ መተጋገል ለማስታረቅ የተሄደበት መንገድ የድርጅቱን ሚዛን አስጠባቂነት ይበልጥ ያስረግጠዋል (ርግጥ ህወሓት በወቅቱ ሁነኛ ጠቅላይ ፖለቲከኛ ቢኖረው የብአዴን አቅም ያን ያህል ባላስቸገረው ነበር፡፡ ዳሩ፣ አቶ መለስ ከ1993ቱ የህወሓት ክፍፍል በኋላ ህወሓትን ለመቀሌ አመራሮች ትተው የብቻ ጠቅላይነታቸውን “ግፋ ብለው” ያሉ በመሆኑ በማዕካለዊ መንግስቱ ላይ የተሻለ አቅም ያለው የህወሓት ሰው አልነበረም፡፡ በጊዜዉ ከስኳር ኮርፖሬሽን ኃላፊነት ተስበው የመጡት አባይ ፀሐየም ቢሆን የዛሬን አያድርገውና ከህወሓት አመራሮች ጋር በድህረ 93ቱ የህወሓት ክፍፍል የዋጡት ሂስ እንደፈለጉት ለመናገር “ስትራፖ” ሆኗቸው ስለ ነበር እድሉ አምልጧቸዋል)

የሆነው ሆኖ ዘመን የፈቀደለት ሚዛን አስጠባቂው ደኢህዴን የመለስን ሞት ተከትሎ ከምስረታ ጊዜው 1984 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ በሃያ አመታት ቆይታው በእውኑም ይሁኑ በድርጅታዊ ህልሙ አልሟቸው ይሁን አስቧቸው የማያውቃቸው የስልጣን ቦታዎች ለአመራሮቹ ክፍት ሆኑለት፡፡ በዋናነት የአቶ መለስ ህልፈት ኃይለማርያምን ወደ አይነኬ-አይጠጌው ወንበር ሲያመጣ፣ ለሬድዋን ሁሴን ደግሞ ያልታሰበ ሲሳይ ጥሎ አልፏል፡፡ ዶ/ር ካሱ ኢላላም ቢሆኑ በአስራ አንደኛው ሠዓት በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊስና ጥናትና ምርምር አማካሪ በመሆን ተሹመዋል፡፡ (መቼም በ“ዲሞሽን” ከደቡብ ክልል ርዕስ መስተዳደርነት ወደ ትምህርት ሚኒስተርነት የመጡትን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን እንደ ሹመት መቁጠር የሚጠበቅብን አይመስለኝም)

ምንም እንኳ የደኢህዴን አመራሮች ሹመት ጉዳይ ከሚዛን አስጠባቂነት ጋር የተያያዘ ቢሆንም የድህረ መለስ የስልጣን እርካብ ላይ ላዩን ላየው በአመዛኙ ለደኢህዴን የተመቸ ይመስላል፡፡ በተለይም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሟቹን ጠቅላይ ሚኒስተር ቦታ ከያዙ በኋላ እንደ ቀላል የማይታዩ የስልጣን ቦታዎች ላይ የደኢህዴን ጓዶቻቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ለአብነት፡- በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ቦታ ላይ አሰፋ አብዮን፣ ደበበ አበራን የኢሕአዴግ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ፣ ውዱ ሀቶን የፀረ-ሙስና ምክትል ኮሚሽነር፣ አማኑኤል አብርሃምን በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ፣ ሰለሞን ተስፋየን በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ አማካሪ፣ ካይዛ ኬ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ምክትል ዳይሬክተር (የገብረዋህድ ቦታ መሆኑን ያስታውሷል)

ከዚህ በላይ የተመለከትናቸው ሹመቶች ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ በማዕከላዊ መንግስቱ ለደኢህዴን አመራሮች የተሰጡ መሆናቸውን ስናስተዉል፣ የደህንነት መስሪያ ቤትና መከላከያ ሰራዊት የተባሉ ቁልፍ የኃይል ማዕከሎች ባይኖሩ ኖሮ፣ ደኢህዴን የደቡቡ ህወሓት፣ ኃይለማርያም ደግሞ የደቡቡ መለስ ለመሆን ባስቻላቸው ነበር:: ነገሩ ያለው ወዲህ ነውና ይሄ ሁሉ የደኢህዴን አመራሮች ያልተጠበቀ ሹመት ከሚዛን አስጠባቂነት የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡ ቢሆንም ግን! የአቶ መለስ ሞት ለደኢህዴን አመራሮች የትንሳኤ ያህል ለማገልገሉ ከሰውየው ህልፈት በኋላ ወደ ፊት መስመር የቀረቡትን የደኢህዴን አመራሮችን ብዛት ማስተዋል በቂ ይመስላል፡፡

ከመቀሌው ጉባኤ ምን ይጠበቃል?

አብዮታዊ ግንባር፣ ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ አጠቃላይ ድርጅታዊ ጉባኤውን በመቀሌ ከተማ ያካሂዳል፡፡ በጽሁፉ መግቢያ ላይ እንደተመለከተዉ ግንባሩ በዚህ ድርጅዊ ጉባኤ ላይ ውሳኔ ያሳልፍባቸዋል ተብሎ ከሚጠበቁ ወሳኝ አጀንዳዎች መካከል፣ ድርጅቱን ለቀጣይ አምስት አመታት በሊቀ መንበርነትና ምክትል ሊቀ መንበርነት የሚመሩትን መሪዎች መምረጥ የሚለው አንዱ ነው፡፡

በድህረ መለሱ የስልጣን እርካብ የግንባሩን አባል ድርጅቶች አሰላለፍ ለማየት እንደተሞከረው፣ በእስካሁኑ ሂደት እንደ ኦህዴድ የከሰረ፣ እንደ ደኢህዴድ የተሻለ እድል ያጋጠመው ድርጅት የለም፡፡ ብአዴንም በአቅሙ በድህረ መለስ የስልጣን ሽሚያ የጠበቀውን ያህል ማትረፍ ባይችልም ዋናውን አስጠብቆ የዘለቀ ይመስላል፡፡ ህወሓት የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ቢያጣውም፣ “በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ” ይሉት ሹመትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ በሚል ሰበብ የሀገሪቱን ቁልፍ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችና ሜጋ ፕርጀክቶችን መቆጣጠር ችሏል፡፡ በአናቱም የሀገሪቱ ዋነኛ የፖለቲካ ኃይል ማዕከል የሆኑት የደህንነትና የመከላከያ ሰራዊት ቁልፍ አዛዦች፣ ዋነኛ የኦፕሬሽንና የመስመር ኃይል አመራሮች … በግልፅም ሆነ በህቡዕ ለህወሓት አመራሮች ያደሩ በመሆኑ፣ እነዚህ ተቋማት በህወሓት ሰዎች እስከተያዙ ድረስ ማዕከላዊ መንግስቱን ለመቆጣጠር ከበቂ በላይ ነው፡፡ በመሆኑም በአባይ ወልዱና ደብረጽዮን የሚመራው ህወሓት የኢሕአዴግ ሊቀመንበርነት (በሌላ አጠራር የጠቅላይ ሚኒስትርነት) ቦታውን “ስሙ ነው የባሰን፣ ታንክና ባንኩን ከያዝን ይበቃናል” በሚል የሚዛን አስጠባቂው ደኢህዴንና የኢሕአዴግ ሊቀ መንበር የሆኑት ኃይለማርያም ደሳለኝ ባሉበት እንዲቀጥሉ ሊያደርግ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው፡፡ ርግጥ ይህን ውሳኔ የሚቃወሙ የህወሓት ሰዎች አይጠፉም፡፡ ይሁንና በህወሓት በኩል ብዙ ተስፋ የተጣለባቸው ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልም ሆኑ ቴድሮስ አድሃኖም በሚዲያ ቀርበው ሃሳባቸውን አፍታቶ የመናገር አቅማቸው እንኳንስ ከአቶ መለስ አንፃር ቀርቶ ከአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ሊወዳደሩ የሚችሉ ባለመሆኑ የጠቅላይ ሚኒስተርነቱ ቦታ በህወሓት ሰዎች ብዙም የሚደፈር አይመስልም፡፡ አርከበ እቁባይም ቢሆኑ የህዝብ ተወካዮች ምከር ቤት መቀመጫ በሌላቸው ሁኔታ ለዚህ መሰል ሹመት የሚበቁበት የህግ አግባብ ባለመኖሩ ሰውየውን መርሳት ይቀላል፡፡

በተለምዷዊ የድርጅቱ አሰራር የኢሕአዴግ ምክትል ሊቀ-መንበር ሆኖ በጉባኤው የሚመረጠው አካል፣ የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን የሚሾም ይሆናል (በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ … የሚለውን ሹመት ሳያካትት) ይህን ቦታ ለማግኘት ብአዴንና ኦህዴድ የበለጠ ፉክክር የሚያደርጉ ይመስላል፡፡ አንደኛው ዋናውን ለማስጠበቅ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አዲስ የድርጅት ሪከርድ ለማስመዝገብ፡፡ በዚህ ድርጅታዊ መተጋገል ውስጥ የህወሓትን ባርኮት የሚያገኘው ድርጅት የኢሕአዴግ ምክትል ሊቀ መንበርነቱን ቦታ የሚያገኝ ይሆናል፡፡ ከድህረ መለስ ወዲህ ከኦህዴድ የተሻለ የፖለቲካ ተሳትፎ እያሳየ ያለው ብአዴን እንደመሆኑ መጠን እድሉን አሳልፎ የሚሰጥ አይመስልም፡፡ በአናቱም የወቅቱ የኦህዴድ ሊቀ-መንበር ሙክታር ከድር የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆኖ በመሾሙ ወደ ማዕከላዊ መንግሥቱ የመመለስ እድል የሚኖረዉ አይመስልም፡፡ የሆነዉ ሆኖ፣ ከሁለት አንዱ ድርጅት የኢሕአዴግ ምክትል ሊቀመንበርነቱን (ም/ጠ/ሚኒስትርነቱ) ቢያጡት እንኳ፣ በም/ጠ/ሚንስትር ማዕረግ … የሚለው የድህረ መለሱ ሹመት (የመስተዛዘኛው ዕጣ) እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡

በጉባኤው ማነው ተሰናባች? ማነዉስ ቀጣይ?

ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ የተረሳ የሚመስለው ሁለተኛው ዙር የመተካካት ሂደት በኃይለማርያም ደሳለኝ አስፈፃሚነት እንዲቀጥል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ለድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች እንዳሳሰቡ መረጃዎች እየወጡ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እንደ 2002ቱ ባይሆንም እንኳ የተወሰኑ የግንባሩ አባል ድርጅት ነባር አመራሮች የሚሰናበቱ ይሆናል፡፡ ከዚህ የቢሆን እድል በመነሳት ከአራቱም አባል ድርጅቶች እነ ማን ይሰናበታሉ? እነማንስ ከ“አዲስ” አመራሮች ጋር ይቀጥላሉ የሚለው ቅድመ-ግምት የሚከተለውን ይመስላል፡- (“ይሰናበቱ ይሆናል” በሚል የቢሆን እድል የተጠቀሱ አመራሮች የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ የነበሩትን ብቻ ሳይሆን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሁነዉ ወሳኝ ድርጅታዊ ስራዎችን ሲሰሩ የነበሩ ነባር አመራሮችንም የሚጨምር ይሆናል፡፡ ከግንባሩ የፖለቲካ ባህሪ አኳያ፤ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የድርጅቱ ቀኖና በመሆኑ በዚህ የቢሆን እድል ስር የተካተቱ አመራሮች በቀጣይ ድርጅታቸዉን ወክለዉ የእናት ድርጅታቸዉ ኢህአዴግ ሥራአስፈጻሚ የሚሁኑትን ሰላሳ ስድስት አመራሮችን የሚመለከት መሆኑን ልብ ይሏል)

ሕወሓት፡- እንደ አዜብ መስፍን፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ሮማን ገ/ስላሴ፣ ኪሮስ ቢተው … ያሉ የድርጅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት (ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ውጪ ያሉት በእድሜ መግፋት) ለተተኪ አመራሮች ቦታ ይለቁ ይሆናል፡፡ በአንፃሩ አባይ ወልዱ፣ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ፀሐየ፣ ፀጋየ በርሃ፣ ቴድሮስ አድሃኖም፣ አስመላሽ ወልደ ስላሴ ነባር ስልጣናቸውን በማጠናከር/በማሻሻል፤ አዲስ ይገባሉ ብየ የምገምታቸውን አዲስ አለም ባሌማ፣ አብርሃም ተከስተ እና አርከበ እቁባይን እንደ “አዲስ” አመራር በመተካት የህወሓት ፖሊት ቢሮ እና የኢህአዴግ ሥራአስፈጻሚን ይቀላቀላሉ የሚለው ግምት ሰፊ ነው፡፡ የአርከበ እቁባይን የአደባባይ ፖለቲካ ፊት ፊት ማለት ስናስተዉል ሰዉየዉ በአዲስ መልኩ የኢህአዴግን ስራ አስፈጻሚ መቀላቀላችዉ እንደማይቀር ለማመን እንገደዳለን፡፡

ብአዴን፡- በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የአርበኞች ግንቦት ሰባት እንቅስቃሴ ከመጠናከሩና ከዚሁ ድርጅት ንክኪ ያላቸው የውስጥ አርበኞች ከመከሰታቸው ጋር በተያያዘ ብአዴንን ወክለው ወደ ሥራ አስፈጻሚነት የሚመጡ አመራሮች በጥንቃቄ እንደሚመረጡ አስቀድሞ መገመት ይቻላል፡፡ እንደ በረከት ስሞን (ከጤና ጋር በተያያዘ)፣ አዲሱ ለገሰ፣ ኤሌው ጎበዜ (ቀድሞ የተሰናበቱ ቢሆንም በይፋ ስንብት)፣ ዘነቡ ታደሰ፣ ዮሴፍ ረታ፣ ታደሰ ካሳ … ያሉ የድርጅቱ ነባር የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ለተተኪ አመራሮች ቦታ ይለቁ ይሆናል፡፡ በአንፃሩ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ አለምነው መኮንን፣ ካሳ ተክለብርሃን፣ ተፈራ ደርበው፣ ብናልፈው አንዷለም ነባር ስልጠናቸውን በማጠናከር/በማሻሻል፤ አዲስ ይገባሉ ብዬ የምገምታቸውን ደስታ ተስፋው፣ አባተ ስጦታው እና የሴት አመራሮችን ተሳትፎ ማጠናከር በሚል ፍሬህይወት አያሌውን እንደ “አዲስ” አመራር በመተካት የብአዴን ፖሊት ቢሮ እና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚን ይቀላቀላሉ የሚለው ግምት ሰፊ ይሆናል፡፡ የፖለቲካ ከባድ ሚዛን ተጫዋቹ አቶ በረከት ስሞን ከወቅታዊ የጤና ሁኔታ አኳያ ከኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚነታቸው ገለል ቢሉም የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ሙዳየ ቃላት (Vocabulary) በመሆናቸው ከመጋረጃው ጀርባ ርቀው አይርቁም፡፡ የአቶ አዲሱ ለገሰ ጉዳም ቢሆን የኢህአዴግን የካድሬ ት/ቤት በማጠናከር ረገድ የቀደመ ተሞክሮ ያላቸው በመሆኑ ቀጣይ እጣ ፈንታቸው ከአቶ በረከት የተለየ የማይሆንበት እድል ይኖራል፡፡

ኦሕዴድ፡- “በትልቁ ህዝብ ውስጥ ያለው ትንሹ ድርጅት” በተረጋጋ አመራርና ከጎጠኝነት በተሻገረ (ከአርሲ Vs ወለጋ ኦሮሞ አተካራ በፀዳ) መልኩ ድርጅቱ እንዲታደስ፣ ከፍ ሲል የኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮች ቁርጠኝነት ዝቅ ሲል ደግሞ የሕወሓት ራሮት ያስፈልጋል (መቼም የኦህዴድ አመራሮች ሙሉ ቁርጠኝነት ባሳዩበት ሁኔታ የህወሓት አመራሮች ድርጅቱን ለመጠምዘዝ የሚያስችል ድፍረት የሚያገኙ አይመስለኝም፤ ከሆነም የግንባሩም ሆነ የአገሪቷ ቀጣይ እጣ ፈንታ የሚወሰንበት አጋጣሚ ይፈጠራል) የሆነው ሆኖ ኦህዴድ አሁን ካለበት የፍዘት ጎዳና እንዲወጣ የሚያስችሉ ጠንካራ ስራ አስፈፃሚዎች እንደሚያስፈልጉት ለክርክር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህ እንዲሆን ከተፈለገ እንደ ኩማ ደመቅሳ (ቀድሞ የተሰናበቱ በመሆኑ)፣ ሶፊያን አህመድ (በጤና ሁኔታ)፣ አሊ ሲራጅ (በቅርቡ በሞት የተለዩ) እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ አለቅጥ ተለጥጦ ካለው ሰማንያ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ውስጥ የመስራት አቅም ያላቸውን በማስቀረት ቀሪዎቹን በአዲስ የመተካት ስራ ከተሰራ የድርጅቱ እድል አሁንም የከሰመ አይደለም፡፡ በዚህ አግባብ ሙክታር ከድር፣ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል፣ አስቴር ማሞ፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ ድሪባ ኩማ፣ አብዱልአዚዝ መሀመድ ነባር ስልጣናቸውን በማጠናከር/በማሻሻል፤ አዲስ ይገባሉ ብየ የምገምታቸውን አብይ አህመድ፣ ደሚቱ ሃምቢሳ እና አባዱላ ገመዳን (ብአዴን ውስጥ አዲሱ ለገሰ ከይፋዊ ስንብት በኋላ የድርጅቱን ክፍተት ለመጠገን እንደተመለሰ ያስታውሷል፤ በተመሳሳይ መልኩ ለአባዱላም ይሄው እድል ይሰጥ ይሆናል ከሚል ምልከታ በመነሳት ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰውየው እድሉ የሚሰጣቸው ከሆነ የአቶ ኩማ ደመቅሳን ቦታ በመተካት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ጥናትና ምርምር አማካሪ በመሆን ይሰሩ ይሆናል) እንደ “አዲስ” አመራር በመተካት የኦህዴድን ፖሊት ቢሮ እና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚን ይቀላቀሉ ይሆናል፡፡ መስከረም ላይ በሚሰየመው “አዲስ” የመንግስት ካቢኔ ውስጥ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የኦሮሞ ተዋጽዖ የሳሳ እንዲሆን የሚደረግ ከሆነ ግን ጊዜ ጠብቆ በሚፈነዳዉ ሦስተኛዉ የኢትዮጵያ አብዮት ውስጥ የኦህዴድ መካከለኛ አመራሮችን ከፊት መስመር ፈልጎ ማግኘት አይከብድም፡፡

ደኢህዴን፡- በድህረ-መለሱ የስልጣን ሽግሽግ የበዛ ሲሳይ የዘነበለት ለዚህ ድርጅት እንደሆነ ከላይ ለማሳያነት የጠቀስናቸው ሹመኞች አስረጂ ምሳሌ ይሆናሉ፡፡ የሃያ ሶስት አመት “ብላቴናው” ደኢህዴን፣ እንደ ካሱ ኢላላ ያሉትን አመራሮች አንፃራዊ የስልጣን ቆይታ ጊዜ ያላቸው ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በመተካካት ስም ካላሰናበተ በስተቀር፣ በተለይም በማዕከላዊ መንግስቱ ላይ የተቀመጡ የድርጅቱ አመራሮች “ለጋ ባለስልጣናት” ናቸው፡፡ በመሆኑም በደኢህዴን ቤት “ቁም ስቅል” ከሚያሳየው ግምገማ ጋር በተያያዘ ከሚሰናበቱ የድርጅቱ አመራሮች ውጪ ያን ያህል ነባር አመራር በመተካካት ስም የሚሰናበት አይመስልም፡፡ ከዚህ አኳያ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ደሴ ዳልኬ፣ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ሲራጅ ፈጌሳ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ ሽፈራው ተ/ማርያም፣ አለማየሁ አሰፋ፣ አሰፋ አብዩ፣ ደበበ አበራ ነባር ስልጣናቸውን በማጠናከር/በማሻሻል የደኢህዴንና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚን ይቀላቀሉ ይሆናል፡፡ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሁለተኛው ዙር የስልጣን ዘመናቸው “የጀርባ አሸከርካሪዎችን” ተፅዕኖ ለመቀነስ በተቻለ መጠን የደኢህዴን ሥራ አስፈፃሚ አባላት ጠንካራ እንዲሆኑ ያቅማቸውን ያህል መሞከራቸው አይቀሬ ነው፡፡

ያም ተባለ ይህ ግን፣ የሀገሪቱ ደህንነት መዋቅር የአደረጃጀት ባህሪ አስካልተቀየረና ፍትሃዊ የብሔር ውክልና እስካልያዘ ድረስ፣ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያሉ ነባር የህወሓት ጄነራሎች በጡረታ ለተተኪ አመራሮች ቦታ እስካለቀቁ ድረስ … የደህንነት መስሪያ ቤቱና መከላከያ ሰራዊት የህወሓትን የፖለቲካ አሸከርካሪነት በማስቀጠሉ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ ይዘዉ ይዘልቃሉ፡፡ “እስከ መቼ?” የኢትዮጵያ ህዝብ የቀንድ አዉጣ ኑሮዉን እስከሚያቆም ድረስ!!

ምንጭ-ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/9766#sthash.JFSe5FKw.dpuf

ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ -መሳይ መኮነን

11863380_1075538672470183_4920089091793687343_nዛሬ ለኢሳት የደረሰው ጥብቅ መረጃ 11ዓመታትን ወደ ኋላ በትዝታ ወሰደኝ:: ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያጋልጠው ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው:: በወር 13 ሚሊዮን ዶላር(500 ሚሊዮን ብር ገደማ) የወታደሩን ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል:: ይህን ጉዳይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚያውቀው ይመስለኛል:: ለዚህም እኔ የተሳተፍኩበትን የሰላም አስከባሪ ዘመቻ አጋጣሚ በአስረጂነት ማሳየት እችላለሁ:: እኤአ በ2003-2004 በመንግስታቱ ድርጅት የበላይነት: በአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚነት ከተላከው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት ጋር ወደ ቡሩንዲ ሄጄ ነበር:: ወደ 18 የምንሆን አስተርጓሚዎች ከ8 ወር እስከ 1 ዓመት ቆይተናል:: ዝርዝሩን ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ:: ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የተፈጸመውን የህወሀቶችን ለከት ያጣ ስግብግብነትን ላጫውታችሁ::


በዘመቻው በUN ደረጃ ወርሃዊ ደምወዝ ከ1000 ዶላር ያላነሰ: የመስክ ክፍያ በቀን 60 ዶላር: የበዓል ክፍያ በአንድ በዓል 1000 ዶላር: የላብ መተኪያ: …..በጣም ብዙ ዓይነት ክፍያዎች ነበሩት:: አብዛኛው የሰላም አስከባሪ ሰራዊት አባላት በተስፋ ነበር ወደ ቡሩንዲ የተጓዘው:: እዚያ እንደደረስን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆኑ:: ቃል የተገባው: በውል የታሰረው( የሚገርመው የውሉን 3 ኮፒዎች አንሰጥም ብለው እዚያው መከላከያ ግቢ ቀርቷል:: መንግስትን አምነን ነው የተጓዝነው) ክፍያ የለም:: በወር 40 ዶላር ለኪስ እየተሰጠን: ምግብና መጠጥ በአላሙዲን እየቀረበልን: እየበላንና እየጠጣን መኖር ብቻ ሆነ:: ከኢትዮጵያ ሌላ የደቡብ አፍሪካና ሞዛምቢክ የሰላም አስከባሪ ሃይሎችም ለተመሳሳይ ዘመቻ ቡሩንዲ ገብተዋል:: ለእነሱ የሚገባቸው ክፍያና ጥቅማጥቅም ሀገራቸው በባንክ አካውንታቸው የሚገባላቸው ይህንንም የሚያረጋግጥ ደረሰኝ በየወሩ እንደሚደርሳቸው በነበረን ቅርበት ተረዳን:: እኛ ግን ምንም የለም:: ስንጠይቅ ኢትዮጵያ ይጠራቀምላችኋል የሚል መልስ ከማስፈራሪያ ጋር ይሰጠናል:: በእኛና በሌሎቹ ለተመሳሳይ ዘመቻ በመጡ ሀገራት የሰላም አስከባሪው ዘመቻ አባላት መሃል ያለው የኑሮ ሁኔታ የሰማይና የምድርን ያህል የሚራራቅ ነበር:: በህወሀት ስግብግብነት የተነሳ በጣም በሚያሳፍር የኑሮ ገጽታ መቀለጂያ ሆንን:: በሰራዊቱ ውስጥ ቅሬታው ስር ሰደደ:: ተስፋው ጨለመ:: በወር 40 ዶላር እየወረወሩ እዚያ ይጠራቀምላችኋል በምትል ከቃል ያለፈ በደረሰኝ ያልተረጋገጠች ተስፋ ብቻ ይዘን በብስጭት ገፋን:: በመሃል ሲብስብን አስተርጓሚዎች ተነጋግረን ቡጁምቡራ በሚገኝ የUN ጽ/ቤት አቤቱታ ልናቀርብ ሄድን:: የተሰጠን ምላሽ ተስፋችንን ይበልጥ ገደለው:: “ስለ እናንተ የተፈራረምነው ከመንግስታችሁ ጋር በመሆኑ አይመለከተንም:: መንግስታችሁን ጠይቁ::” የሚል ወሽመጥ የሚቆርጥ ምላች ተሰጠን::


በመሃሉ መለስ ዜናዊና ሳሞራ የኑስ ሊጎበኙን ቡጁምቡራ መጡ:: ሳሞራ ሰብስቦን ችግር ካለ ንገሩኝ አለ:: ሰራዊቱ የክፍያው ነገር ሲያንገበግበው ስለከረመ ሳሞራን ሲያገኝው በየተራ እየተነሳ ጠየቀው:: ሳሞራ ጀት ሆነ:: ባለጌ አፍ እንዳለው ያረጋገጥኩት የዚያን ዕለት ነው:: የኢትዮጵያን የችግር መዓት ሲዘረዝር: መዓት ሲያወራ ቆየና ” ሰው እንደ ቤቱ እንጂ እንደ ጎረቤቱ አይኖርም:: የሌሎችን እያያችሁ እንደነሱ እንሁን ማለት አደጋ አለው:: እዚህ ገንዘብ ምንም አያደርግላችሁም:: በብር ኢትዮጵያ እየተጠራቀመላችሁ ነው:: ለሸርሙጣ ፈልጋችሁ ከሆነ ኢትዮጵያ ስትመለሱ ትደርሱበታላችሁ…..” እያለ ወረደብን:: ሰራዊቱ ቅስሙ ተሰበረ:: ብዙ የምንሰራው ስራ አለ:: ትምህርት ቤት እንገነባለን:: ….እያለ ተንዘባዘበ:: የዚያን ዕለት ሌሊት ከአምቦ የመጣ የሰራዊቱ አባል በታጠቀው መሳሪያ ራሱን አጠፋ:: ባርቆበት ነው የሚል ሪፖርት እንድናዘጋጅ በህወሀት የጦር አዛዦች መመሪያ ተሰጥቶን የውሸት ሪፖርት አዘጋጅተን ለUN ተላከ:: ይህ የሆነበትም ራሱን ካጠፋ UN ካሳ አይከፍልም:: እርግጠኛ ነኝ በዚህ የተገኘውን በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ዶላር ህወሀቶች ኪስ ገብቷል:: 


ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ እየተጠራቀመላችሁ ነው እየተባለ ስንሸነገል የከረምንበትን ገንዘብ ሊሰጡን ተዘጋጁ:: ለአንድ የሰላም አስከባሪ ሰራዊቱ አባል በትንሹ ከ250ሺህ ብር በላይ ወይም በወቅቱ ምንዛሪ 10ሺህ ዶላር መከፈል ነበረበት:: በጣም የሚያሳፍር የሚያስደነግጥ ነገር ነበር የጠበቀን:: እንደ ቆይታ ጊዜ ከ15ሺህ እስከ 25ሺህ የኢትዮጵያ ብር ሰጥተው አሰናበቱን:: ከእያንዳንዳችን ከ200ሺህ ብር በላይ ህወሀቶች ተቀራመቱት:: …በሌላ ጊዜ በስፋት እመለስበታለሁ::

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/9755#sthash.L6Mg7Bv3.dpuf

የሰላም ትግሉ በኢትዮጵያ (መዝጊያ) – አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ

እንዴት ትግሉን በትክክል ወደ ፊት ማስኬድ ይቻላል?

በመጀመሪያ ደረጃ ሁላችን መረዳት ያለብን፤ ይህ ትግል በአምባገነኑ ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ብቻ ነው። ይህ መነሻና መድረሻ ተደርጎ መወሰድ አለበት። አሁን ሁላችንንም ወጥሮ የያዘን፤ ትግሉን ለምን በአንድነት፤ የሀገራችን የነፃነት ትግል አናደርገውም? የሚለው ጥያቄ ነው። አንዳችን ከሌላችን የተለየ አመለካከት ስለያዝን ብቻ፤ በመካከላችን ጠላትነት ነግሦ፤ “አንተ ወያኔ ነህ!” የሚል ወፍ ዘራሽ ውንጀላ አስቀድሞ መወርወር ትክክል አይደለም። በመደማመጥ በውይይት ሊፈታ የሚችለውን የሃሳብ ልዩነት፤ እንደ የፖለቲካ ውጊያ አድርጎ መበጣጠሱ ጎድቶናል። የተለያየ ሃሳብ ይዞ፤ በሚስማሙበት አብሮ መስራት ይቻላል። የግድ በሁሉም ነገር ሁላችን መስማማት የለብንም። ይህ መሠረታዊ የዴሞክራሲን ሀ ሁ የተቀበሉ ሁሉ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ታዲያ ለምንድን ነው በመካከላችን መግባባት ያልቻልነው? የዛሬው የማጠቃለያ ጽሑፍ የሚያተኩረው፤ በመካከላችን መግባባትን እንዴት መፍጠር እንችላለን? ምንስ ብናደርግ ትግሉን ወደፊት ማስኬድ እንችላለን? ካለንበት የምስቅልቅል ሀቅ ወጥተን ወደፊት ለመሄድ ከየት እንጀምር? ለሚሉት መልስ በመሥጠት፤ ትክክለኛ አስተባባሪና አስተማማኝ መፍትሔ አቅርቦ፤ ትግሉ በትክክል እንዲመራና ወደ ሕዝባዊ ድሉ ጉዟችን እንዲያቀና መጋበዝ ላይ ነው።

ትግል ወደው የሚገቡበት ክስተት አይደለም። ትግል የሙያ መስክ አይደለም። ትግል ግድ ብሎ የሚመጣ የኅብረተሰብ ክንውን ነው። የአንድ ሀገር ነዋሪዎች፤ በሀገራቸው ያለው ሥርዓት “ትክክለኛ አይደለም!” “ከመስመር ወጥቷል!” ብለው ሲነሱና የሥርዓቱ አራማጅ እንጃላችሁ ሲል፤ ሕዝቡ በእምቢታ ሲነሳ፤ ሕዝባዊ ትግል ነው። ይህ ደግሞ ሁሌ የሚደረግና ለአንዳንዶቹ የሙያ ዘርፍ ሆኖላቸው የሚከርሙበት መኖሪያ አይደለም። በአንድ የታሪክ አጋጣሚ የሚከሰት ነው። አሁን ሀገራችን ላለችበት ሁኔታና ታጋዮች ላለንበት ሀቅ፤ በቂ ምክንያት አለ። ምክንያቱን መርምረን ማግኘት አለብን። ሌሎችን ለዚህ ምክንያት ተጠያቂ ማድረጉ አግባብነት የለውም። ያንን ምክንያት የፈጠርነውና አስተካክለንም ወደፊት መሄድ የምንችለው፤ እኛው ነን። ለየብቻችን መፍትሔ ፈላጊዎች ብቻ ሳንሆን፤ ለየብቻችን ተግባሪዎቹም በመሆን በየበኩላችን ሩጫ ይዘናል። ለምን? ይህ የሀገራችን የሁላችን ጉዳይ አይደለም! ታዲያ ለምን በአንድነት የምንዘምትበትን መንገድ አንፈልግም። በመካከላችን ያለው፤ የትግሉን መንገድ በሚመለከት ያለ ልዩነት አይደለም። በኔ አመለካከት፤ ያሉትን ልዩነቶች በሶስት ከፍዬ አስቀምጭቸዋለሁ።

የመጀመሪያውና ዋናው ማጠንጠኛ፤ የትግሉን መሠረታዊ ምንነት በሚመለከት ያለው ልዩነት ነው። ይህ የትግሉን ሂደት ቅደም ተከተል በሚመለከት የተወሰነ አይደለም። ይህ መሠረታዊ የሆነውን ለምን እንደምንታገል የሚደነግገውን ጉዳይ የሚመለከት ነው። “በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሀቅ ምንድን ነው?” የሚለውን መመለሱ ላይ ነው። ለዚህ የሚሠጠው መልስ ወሳኝ ነው። ከዚህ ተነስቶ ነው የትግሉ እጅና እግር የሚታወቀው። በሀገራችን ምን ዓይነት ሥርዓት አለ? ምን ዓይነት የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ ያቀነቅናል። የዚህ ሥርዓት ጉዳቱ ምንድን ነው? የሥርዓቱስ ባለቤት ማነው? በዚህ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ይላል? የት ነው የምንቆመው? ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ወይንስ ከአምባገነኑ ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ጋር? እዚህ ላይ፤ ትግሉ የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚደረግ ሩጫ አይደለም። ትግሉ የነፃነት ጥያቄ ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎችን ምርጫ አይደለም የያዝነው። ሁለት ሰፈሮች ብቻ ነው ያሉት። አንደኛው የአምባገነኑ ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሲሆን ሌላው የሕዝቡ ሰፈር ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ሆኖ ነው፤ አምባገነኑን ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር እምቢ ያለው። ስለዚህ አንድ ኢትዮጵያዊነት ብለን፣ አንድ ወገናችን ብለን፣ አንድ ሀገራችን ብለን፣ አንድ ትግል ብለን መነሳት አለብን።

ሁለተኛው ደግሞ፤ የሀገርን ጉዳይ ለድርጅቶች ኃላፊነቱን መሥጠቱ ላይ ነው። ትግሉን አሽከርካሪዎች ድርጅቶች ናቸው ብለን፤ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ኃላፊነቱን በነሱ ላይ ጥለናል። ሀገሪቱ እኮ ለተደራጁት ብቻ አይደለችም። ለሁላችንም እኩል ነች። ታዲያ ኃላፊነቱን ሁላችን እኩል መካፈል የለብንም? በርግጥ በድርጅት የተሰባሰቡ ሰዎች ጠርቀም ያለ ጉልበት አላቸው። እናም ቅድሚያ ይሰለፋሉ። ይህ ማለት ግን፤ ኃላፊነቱ የነሱና የነሱ ብቻ ነው ማለት አይደለም። ይልቁንም በሀገራችን ላይ ባለው ሀቅ፤ ቅድሚያ መስለፉን ዘንግተውታል። እናም በየድርጅቶቻቸው መርኀ-ግብር ተቆልፈው፤ ከመጠጋጋት ይልቅ መራራቁን መርጠው፤ ከመፍትሔ ይልቅ የችግሩ አካል ሆነዋል። ስለዚህ፤ ኃላፊነቱ በሌሎች፤ ማለትም በግለሰብ ባለነው ሀገር ወዳዶች ላይ ተጥሏል። ለሀገር መታገልና ለድርጅት መታገል አንድ አይደለም። በርግጥ ትግል ሳይደራጁ አይካሄድም። ያ ድርጅት ደግሞ ትግሉ ምን ዓይነት መስመር እየተከተልን መሆናችንን ይናገራል። ለድርጅት መታገል ማለት፤ ድርጅትን መነሻና መድረሻ አድርጎ፣ የኔ ድርጅት ትክክለኛ ስለሆነ፤ በኔ ድርጅት ብቻ ተመርታችሁ ትግሉን ቀጥሉ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ማስተላለፍ ነው። በርግጥ ይሄ በብዙ የተለያየ የሚመስል ነገር፤ ነገር ግን መሠረቱ አንድ በሆነ መልክ ይከሰታል። መሠረቱ ደግሞ፤ ለግል ማስብና ለሀገር ማሰብ በሚለው መካከል ያለው ልዩነት ነው። የያዝነው ትግል የግል ትግል አይደለም። የሀገር፣ የነፃነት ትግል ነው።

ሶስተኛውና ማጠቃለያው፤ መፍትሔውን በሚመለከት ያለው ልዩነት ነው። አንድ ሀገር፣ አንድ ኢትዮጵያዊነት፣ አንድ ትግል ብለን ከተነሳን፤ የአንድነቱ ትግል ዋናና አማራጭ የሌለው ነው። አንድነትን ከግል የተግባር እርምጃ ማስቀደም አለብን። አዎ! ትግሉ ተጀምሯል። ሰዎች በተለያየ የትግል መስክና ሁኔታ ከገዥው ቡድን ጋር እየተፋለሙ ናቸው። ነገር ግን ትግሉ ትክክለኛ ስኬት እንዲኖረው መቀጠል ያለበት፤ ከዓላማ ጋር ተቆራኝቶ እንዲቀርብ ሲደረግ ነው። ግቡ አንድነትን የሚመሠርት፣ አስተማማኝ የሆነና፤ ሁሉን ለአንድ ዓላማ አሰባስቦ የሚያታግል እንዲሆን፤ አንድነቱ አሁኑኑ፤ ባለንበት ደረጃ ቅድሚያ ሊሠጠው ይገባል። ይህ ማለት፤ አንድ ሳንሆን የተያዘው ትግል አደጋው ከፍተኛ ስለሆነ፤ ታጋዮች በየደረሱበት የትግላቸው ሂደት፤ ከሌሎች ጋር እንዲሆን ማድረግ ነው። ይህ ግድ የሚለው፤ የሚከተለውን አደጋ ተረድተው፤ የያዙትን ትግል ለአንድነቱ እንዲገዛ አድርው፤ ድሉንም ሆነ ጉዳቱን ለአንድነቱ እንዲያስረክቡ ነው። ይህ ማለት፤ በመሰባሰብ ለሚመሠረተው የአንድነት ድርጅት፤ ሙሉ ተገዥ ሆኖ፤ በሙሉ ልብ በኢትዮጵያዊነት መምጣት ነው። በተደጋጋሚ የተገለጹትን የትግሉ ራዕይና መታገያ ዕሴቶች በመቀበል ወይንም አስፈላጊ የሆኑ ማሻሻያዎችን በማድረግ፤ አንድ ድርጅት፣ አንድ ትግል፣ አንዲት ኢትዮጵያ፣ አንድ ኢትዮጵያዊነት ብሎ መነሳት ነው። መታገያ ዕሴቶቻችን የሚከተሉት ናቸው፤

፩ኛ.   በኢትዮጵያዊነታችን አንድ ነን። በሀገራችን፤ በኢትዮጵያዊነታችን  የፖለቲካ ተሳትፏችን እናደርጋለን።

፪ኛ.   ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ ዳር ድንበሯን አስጠብቀን ለኛው ለኢትዮጵያዊያን እናደርጋታለን።

፫ኛ.   በሀገራችን በኢትዮጵያ፤ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን እናደርጋለን።

፬ኛ.   በኢትዮጵያዊነታችን የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችንን እናስከብራለን።

እንግዲህ ከላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ትኩረት ሠጥተናቸው፤ በቁጥር ፩, ፪, ፫ ትና ፬ የሰፈሩትን መታገያ ዕሴቶች አንግበን፤እና አሁን ያለንበትን የያንዳንዳችንን ሁኔታ ራሳችን መርምረን፤ በግለ ሰብ ደረጃ፤ እኔ በኢትዮጵያዊነቴ ምን ማድረግ እችላለሁ? የሚለውን እኔ በኢትዮጵያዊነቴ ምን ማድረግ አለብኝ? ከሚለው ጋር አቆራኝተን፤ መሰባሰብ አለብን። በድጋሜ፤ እያንዳንዱ ድርጅት የያዘው የራሱን ድርጅት ትግል አንጂ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግል አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነት ትግል የሚካሄደው በኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ነው። እናም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድነት የነፃነት ትግል ጥረት እናድርግ። የዚያ አካል እንሁን። ይሄን በሚመለከት ለመተባበር ዝግጁ የሆናችሁ ጥሩኝ፤ ወይንም ወደኔ መልዕከት በመላክ ቅረቡ። የዚህ ትግል ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ፤ አንድ ግለሰብ ወይንም አንድ ድርጅት አይደለም።

የአዲሱ ህውሀት መንግስት መጥፎ አጋጣሚ! (ከኤርሚያስ ለገሠ)

ከኤርሚያስ ለገሠ (ክፍል አንድ )

1 – ደስታ እና ሀዘን

ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ ስትነቃ አቅፎ ሊያነሳት በመቻሉ ደስ ይለኛል። እንኳን ለዚህ አበቃህም ማለት እፈልጋለሁ።Ermias Legesse former Woyane govt. employee

በሌላ በኩል ገዥው ቡድን በምክንያት እያሰረ በምክንያት የሚፈታበት ሁኔታ ለራሱ ስልጣን መቆያ ትክክል ቢሆንም ለኢትዬጲያ የፍትህ ስርአት ምን ያህል ንቀት እንዳለው የሚያሳይ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው። ሰዎች በህውሀት ላይ አደጋ ሲጋርጡ በፓለቲካ ውሳኔ ይታሰራሉ…ህውሀታዊ ምክንያት !። ገዥው ቡድን ላይ የተጋረጠው አደጋ በሌላ ጐን ሲያጋድል ደግሞ በእጁ ይዞ የሚያሰቃያቸውን ይፈታል…ህውሀታዊ የመፍታት ምክንያት!!

ሀብታሙ አያሌውና ድርጅቱ ” አንድነት” ህውሀትን በሰላማዊ ትግል ፈተና ውስጥ ለመክተት ስትራቴጂ ነድፈው ሰፊ እንቅስቃሴ ጀመሩ። የለውጥ ንፋስም በስሱ መንፈስ ጀመረ። እነ ሀብታሙ በአደባባይ ” እመኑኝ ኢህአዴግም ይወድቃል! ኢትዬጲያም ነጳ ትወጣለች!” በሚል መሪ መፈክር ገዥዎችን አስጨነቁ። የስርአቱን ባህሪያት በቅርብ የምናውቅ ሰዎች የእነ ሀብታሙ እድሜ አጭር እንደሚሆን አሳወቅን። ርግጥም ” ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም!” በሚል መርህ የሚመራው ገዥ ቡድን እነ ሀብታሙን የውሸት ክስ በማዘጋጀት ወደ ማእከላዊ ወረወረ። ” አንድነት” ፓርቲንም አፈረሰ። ኩሸቱን በመደጋገም የራሱን እውነት ፈጠረ። እነ ሱዛን ራይዝን “በ100%” ጦሽ ብለው እንዲስቁ አደረገ።

በሌላ በኩል ለውጥ በሁሉን አቀፍ ትግል ብቻ መምጣት እንዳለበት የሚያምኑ ኢትዬጲያውያን የለውጥ እንቅስቃሴውን በግላጭ ማቀጣጠል ጀመሩ። ምሁራን ዱር ቤቴ በማለት ወደ በረሀ ተመሙ። አዲስ ህልምና አዲስ አቅጣጫ ይዘው የነጳነት ትግሉን ዙር አከረሩት። እናቶች ከጣታቸው ቀለበት፣ ከአንገታቸው ሀብላቸውን እያወለቁ ትግሉን ወደማገዝ ተሸጋገሩ። የመኪናቸውን ቁልፍ ለአርበኞች አስረከቡ። በየቦታው አዳራሽ ሞልቶ እስኪፈስ ድረስ ” እኔ አርበኞች ግንቦት ሰባት ነኝ!”፣… ” እኔ አንዳርጋቸው፣ ብርሀኑ፣ ኤፍሬም፣ ንአምን… ነኝ!” የሚል ቃልኪዳን ከመግባት ባሻገር እስከ መቶ ሺህ ዶላር መዋጣት ተጀመረ። ይህን የለውጥ ስሜት በስማ ስማ ሳይሆን በአይኔ በብረቱ ተመልክቻለሁ። ቆም ብዬም ለማሰላሰል ሞክሬያለሁ።

እንደ እውነቱ ከሆነ ህውሀት ቆም ብሎ ለትክክለኛው መፍትሔ የማሰቢያው ግዜ ነበር። ይሁን እንጂ አፈጣጠሩ፣ ባህሪውና የበታችነት ስሜቱ ይህን ስለማይፈቅድለት ሌላ መፍትሔ ማሰብ ነበረበት። ከእነዚህም ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ባሉት አንዳርጋቸው ጵጌ ስም መጵሀፍ መጳፍና እንደ ሀብታሙ አያሌው ያሉትን የፓለቲካ እስረኞች መፍታት የሚጠቀሱ ናቸው። በበረከት ፀሀፊነት በአንዳርጋቸው ስም የሚወጣው መጵሀፍ ” የሶስት ምርጫዎች ወግ!” ( ስያሜው የእኔ ነው) ገና ባይወጣም በቅርብ ቀን እንደሚወጣ ይጠበቃል። ምርቃቱም ሸራተን አዲስ አንዳርጋቸው በሌለበት ይሆናል። …እነ ሀብታሙ አያሌውም ተፈተዋል።

( ” የሶስት ምርጫዎች ወግ” በተመለከተ ” የነጳነት ትግሉና ስድስት የህውሀት ማደናገሪያ ነጥቦች” በሚለው ሀሳብ ውስጥ አካትቼ በዳላስ ቴክሳስ በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ አቅርቤ ነበር። ብዙዎች እንዲለጠፍ ስለጠየቁኝ በሌላ ክፍል እንደምመለስበት ተስፋ አደርጋለሁ።)

2 – “መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል”

አዲሱ የህውሀት መንግስት ሁለተኛው መጥፎ አጋጣሚ በኢትዬጲያ ሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ነው። እነዚህ ለሀይማኖታቸው ነጳነት የሚታገሉ ታጋዬች የያዙት አቋም ገዥው ቡድንን ወደ ከፍተኛ ፈተና ጐትቶ ወስዶታል። ይህን ለማለት ያስደፈረኝ ያለምክንያት አይደለም። ከልምድ በመነሳት እንጂ!

የዛሬ ሰባት አመት በዚህ አካባቢ የአዲስ አመት መምጫ በድርቡም የኢትዬጲያ ሚሊኒየም መግቢያ ነበር። በመላው ኢትዬጲያ በተለይም በከተሞች የቅንጅት መሪዎች ካልተፈቱ ” በሚሊኒየም ምንም የለም!” የሚሉ መፈክሮች ተስተጋቡ። ሁኔታዎች አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር (” ታላቁ መሪ” ባለማለቴ እቴጌን ከወዲሁ ይቅርታ እየጠየኩ) መውጫ መንገድ ፈለገ። “የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መጠቀም” የሚል የውስጠ ድርጅት ሰነድ እንዲዘጋጅ አደረገ። ይህ ሰነድ የታሰሩ ተቃዋሚዎችን በይቅርታ የመፍታት ፋይዳውን የሚተነትን ነበር። በዚህ ጵሁፍ ህዝቡ የይቱልን ጥያቄ ያለማቋረጥ እያነሳ ያለው ከአርቆ አስተዋይነት የመነጨ እንደሆነ ዘረዘረ። ህዝቡ ይፈቱልን የሚል ጥያቄ እያነሳ ያለው ” እኔው መርጬ ለዚህ አደረስኳቸው” ከሚል የህሊና ፀፀት እንደሆነ ተገለፀ። በመሆኑም ታሳሪዎችን በይቅርታ መፍታት ህዝቡን ከፀፀት የማውጣት ሁኔታ ስለሚፈጥር መንግስት የሚፈታበት ሁኔታ ማማተር እንዳለበት በሰፊው ተነገረ።
ታሳሪዎች የይቅርታ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የፍርዱ ሂደት እንዲፋጠን ተደረገ። በአስቂኝና ባዶ ማስረጃ ታሳሪዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲወሰን አደረገ። ( በነገራችን ላይ በመስካሪነት የቀረቡት የቀበሌ ካድሬዎች የነበሩት እነ አበባ ሽመልስ ከማል ልምምድ የሚያደርግላቸው በኢህአዴግ ቢሮ ነበር) ። የፍርድ ውሳኔውን አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እስከ እድሜ ይፍታህ አምዘገዘገው። ይህ ውሳኔ ታሳሪዎችና ቤተሰባቸው ተደናግጠው ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት ይገባሉ የሚል ታሳቢን የወሰደ ነበር።

በወቅቱ በታሳሪዎች መስመር ያለውን ተጵእኖ በቀጥታ ከራሳቸው መስማት የምችልበት እድል ባይኖርም በአንዳንድ የቅንጅት አመራሮች እና ቤተሰባቸው ዘንድ ተጵእኖ እንዳሳደረ ሰምቻለሁ። በሌላም በኩል እንደ አንዱአለም አራጌ ያሉ አመራሮች ውሳኔውን ከመቄብ ባለመቁጠር ይቅርታ ለመጠየቅ እንዳስቸገሩ በተባራሪ ሰምተናል።

ዞሮ ዞሮ ህውሀት የገባበት አጣብቂኝ የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መፍትሔ ሊያገኝ ቻለ። ይህን አስመልክቶ አቶ በረከት በጳፈውና የህውሀትን ገድል በሚያሳየው መጵሀፋ ገጵ 233 ላይ እንደሚከተለው አስፍሮ እንመለከታለን፣

“…የፍርድ ሂደቱ ነጳ መሆን በግልፅ መታየቱና መንግስት የቅንጅት መሪዎች የተከሰሱባቸውን ወንጀሎች ከበቂ በላይ በማስረጃ አቅርቦ በማረጋገጡ ህብረተሰቡ የሰዎቹን ጥፋተኝነት በጥያቄ ውስጥ የሚጥልበት አልነበረም። በመሆኑም መንግስት በህዝቡ የቀረበው የይፈቱ ጥያቄ ፣ ማንኛውም ህዝብ በአርቆ አስተዋይነቱ የሚያደርገው… እኔ መርጬ ለእስር አበቃኃቸው ከሚል የህሊና ፀፀት ነጳ ለመውጣት በመፈለግ ያቀረበው ጥያቄ እንደሆነ ተገንዝቧል። ለዚህ አይነቱ የህዝብ ጥያቄ በጐ ምላሽ መስጠት ምንግዜም ቢሆን ግዴታው እንደሆነ የሚገነዘበው መንግስት፣ ጥያቄው የህግ የበላይነት ለድርድር ሳያቀርብ ሊመለስ እንደሚችል አምኗል። እናም በአንድ በኩል የህግ የበላይነትን እያስከበረ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝብን የይፈቱ ጥያቄ ለማስተናገድ የሚችልበትን ሁኔታ ማማተር ነበረበት። በዚህ አኳኃን ነው የኢትዬጲያ ሚሌኒየም ራሱን እንደ መልካም አጋጣሚ የከሰተው” ይለናል።

እንግዲህ ከዚህ ልምድ በመነሳት የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጣቸው። ውሳኔውን መሰረት በማድረግ እስከ ሀያ አመት የሚደርስ እስራት ተፈረደባቸው። ይህ ለመጥራት የሚዘገንን ቁጥር የተበየነበት ምክንያት ታሳሪዎችን ለማስደንገጥ እና ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት እንዲገቡ ታስቦ እንደሆነ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። አንድ ግጥም አቅርበሀል የተባለ ወጣት የተፈረደበትን አመት ለተመለከተ ደግሞ በህውሀት የተጠነሰሰውን ሴራ ለመገንዘብ የእነሱን ያክል ማሰብ ከቻለ በቂው ይሆናል።

ይሁን እንጂ ይህ “የይቅርታ ይደረግልን” ሴራ ቅንጅት ላይ እንደሰራው በሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎቹ ላይ የሚሰራ አይደለም። ሲጀመር የመጀመሪያዉ ፓለቲካዊ፣ የአሁኑ ደግሞ ሀይማኖታዊ ነጳነትን በግንባር ቀደምትነት ያስቀመጠ በመሆኑ በባህሪ የተለያዩ ናቸው። ርግጥ ፓለቲካዊ መብቶች ባልተከበረበት ሀይማኖታዊ መብቶች ይከበራሉ ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ቢሆንም። ከዚህም በተጨማሪ የሀይማኖታዊ ነጳነታዊ ጥያቄዎች ለድርድር የመቅረብ እድላቸው እጅግ ጠባብ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው።

ከላይ የተቀመጠውን ከግምት በመውሰድ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴው አባላት አጥፍተናል እና ይቅርታ ይደረግልን የሚሉ ከሆነ እስከዛሬ ያነሷቸው ሶስት ጥያቄዎች ( ለጊዜው የማውቃቸው) ትክክል አልነበሩም፣ አሊያም ምላሽ አግኝተዋል የሚል እንድምታ ይኖረዋል። ይህም የህውሀትን ድል አድራጊነት ከማረጋገጥ ባሻገር የኢትዬጲያ ሙስሊሞችን የሶስት አመት ትግል ውሀ ይቸልስበታል። ወደ ኃላ የመመለስና በቀላሉ የመክሰም እድል ያጋጥመዋል። የኮሚቴዎቹ አባላት ይህን በመገንዘብ ይመስላል አስደንጋጩ ብይን ሲሠጣቸው ያለምንም መደናገጥ የትግል ጵናታቸውን ለማሳየት የቻሉት። ቤተሰቦቻቸውም ቢሆን የኮሚቴው አባላት እየከፈሉ ያሉት መስዋእትነት ለሀይማኖታቸው ነጳነት መሆኑን በመገንዘብ ከጐናቸው የቆሙት።

ስለዚህ እነዚህ የኮሚቴ አባላት እንደ ቡድን የይቅርታ ጥያቄ ያቀርባሉ ብሎ ማሰብ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደመውጣት ይሆናል። በግለሰብ ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች የይቅርታ ሂደት ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ቢሆንም። ይህ አማራጭ ዝግ ሆነ ማለት ህውሀት መራሹ አዲሱ መንግስት ዝም ብሎ ይቀመጣል ማለት አይደለም። በሁኔታዎች አስገዳጅነት ያለ ይቅርታ ጥያቄ ምህረት የማድረግ ግን ደግሞ በፍርድ ቤት እንዲወሰን ያደረገውን የህዝብ እንቅስቃሴ ገደብ ያለማንሳት ሊኖር ይችላል። ይህም ኮሚቴዎቹን በአይነ ቁራኛ በመከታተል የቁም እስረኛ ወደ ማድረግ መሸጋገር ይሆናል። ይህም ቢሆን ለገዥው ቡድን የሚያመጣለት አንዳችም ፓለቲካዊ ትርፍ አይኖረውም።

ግራም ነፈሰ ቀኝ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የአላማ ጵናት ለአዲሱ የህውሀት መራሹ መንግስት የእግር እሳት እንደሆነ ይቀጥላል። የኢትዬጲያ ሙስሊሞች የነጳነት ትግልም በኢትዬጲያ ታሪክ ውስጥ የሚኖረውን የላቀ ደረጃ እንደጠበቀ ይኖራል!…”መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል” ይሉሀል ይህ ነው!!

ነጻነታችን በእጃችን፣ ህወሃት ካልተገረሰሰ እስሩም ግድያውም ይቀጥላል!

ተስፋዬ ነጋ (ዋሽንግተን፣ ዲሲ)

ዛሬ እነሆ እነ ሀምታሙ አያሌው፣ ዳኤል ሽበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋና፣ አብርሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ የወያኔ ፍርድ ቤት ወስኗል የሚል ዜና ሰማሁ። እንኳንም በውሸት ክስ የታሰሩት ወደየቤተሰቦቻቸው በሰላም ተቀላቀሉ። ከሚወዱት ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ እጅግ ደስ የሚል ስሜት ይፈጥራል። የቤተሰቦቻቸውን ናፍቆታቸውን በአግባቡ እንዲያጣጥሙ ምኞቴ ነው። እውነት መጨረሻ ላይ እውነት ሆና መውጣቷ አይቀርም፣ ይኸው እውነት ነጻ አወጣቻቸው።abraha desta in jail

የሆኖው ሆኖ እነዚህ ወጣቶች ከመጀመሪያውም መታሰር አልነበረባቸውም። በወንጀል ደም ተጨማልቀው የሚዋዥቁ አረመኔዎች አልነበሩም። ለአገራቸውና ለህዝባቸው ከፍተኛ ራዕይ የሰነቁ ንጹህ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፣ አሁንም ንጹሃን ናቸው። ወያኔዎች ሰላማዊ ዜጎችን በማሰር የፖለቲካ ትርፍ እናገኛለን ብለው ቢያስቡም፣ የእነአብርሃ ደስታ መታሰር የህወሃትን ድንቁርና ከማጋለጥ ውጭ በተቃዋሚው ወገን ላይ ያመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ የለም። እንዲያውም ተቃዋሚዎች የትግሉን ዳራ በጥልቅ እንዲመረምሩና የወደፊቱን የትግል አቅጣጫ በጥንቃቄ እንዲቀይሱ አደረጋቸው እንጂ! የታሳሪዎችን ንጹህነት ደግሞ ህወሃቶችም (እዉነትና ውሸት የማያገናዝቡ ሆዳም ካድሬዎችም ጭምር) በሚገባ የሚመሰክሩ ይመስለኛል፣ ያው የሞት ሽረት ነገር ሆኖባቸው ቢያስሯቸውም! የህወሃት ሰዎች ለስልጣናቸው የሚያሰጋቸውን ሁሉ በሃሰት ክስ ከመወንጀል ተቆጥበው አያውቁም፣ እነዚሁ ፖለቲከኛ ወጣቶች በምሳሌነት ሊቀርቡ ይችላሉ፣ የእስሩ ገፈት ቀማሾች ዞን 9ኞችም ሌሎች ሰለባዎች ናቸው። ተመስገን ደሳለኝ፣ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙ፣ ውብሸት ታዬ የፈሪው ህወሃት የሃሰት ፍርድ በትር ተጎጂዎች ናቸው። የህወሃት መንግስት በውሸት የተካነ፣ የፈጠራ ክስ ጸሃፈ-ተውኔት እንደሆነ የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። ህወሃቶች ተቃዋሚ የመሰላቸውን ሁሉ በፈለጉ ጊዜ ሲያስሩ፣ በፈለጉ ጊዜ ሲፈቱ ኖረዋል፣ ጠንከር ያለ ተቃውሞ ሲመጣ ከመግደል ወደኋላ አይመለሱም። ህወሃት በ1996 ዓም ሰላማዊ ሰልፈኞችንና ህጻናትን ሳይቀር በጠራራ ጸሃይ በካሊበር ጥይት በሳስቶ ገሏቸዋል። ወደፊትም የፈጠራ ክስ ማቀናበር፣ ማሰር፣ መፍታት፣ መግደል፣ ስራቸው ሆኖ ይቀጥላል።

ሕወሃት ሁለት መገለጫዎች አሉት። የመጀመሪያው የጦር ሃይሉን በመተማመን፣ በጉልበት ስልጣን ላይ እንደተቆናጠጠ ዘላለም እገዛለሁ ብሎ ማሰቡ ነው። የመሳሪያ ባለቤት በመሆኑ፣ የተቃወመኝን እያሰርኩ፣ ጠላቴን እየገደልኩ፣ እንዲሁም ከተቃውሞ የማይታቀበውን እያስፈራራሁ ለረጅም ጊዜ እኖራለሁ ብሎ ያምናል። እዉነትም ህወሃት በከፊል ትክክል ነበር፣ በጉልበት እያስፈራራ፣ እያሰረ፣ እየገደለ ለ25 አመታት ያለምንም ችግር ዘልቋል። ከራሱ ከህወሃት የተፈጠሩ የጦር መኮንኖችን ብቻ ስልጣን ላይ አስቀምጦ፣ በሙስና እንዲዘፈቁ በማበረታታትና፣ የሚያማልል ስጦታ በመስጠት፣ እንዲሁም እነዚሁን የጦር መኮንኖች የወንጀል ተባባሪና መሪ በማድረግ የ”አብረን እንዝለቅ” ጨዋታ ተክኖበታል። ሁሉንም የጦር መኮንኖች ከአንድ ብሄር ብቻ በመሾም፣ ለተቃዋሚ እንዳያደሉ “ከካዳችሁን በጦር ወንጀለኝነት ትፈለጋላችሁ፣ የትግራይን ህዝብ ታስጨርሳላችሁ” በሚል ሰንካላ ማስፈራሪያ ከሌላው የኢትዮጵያዊ ጋር እንዳይነናኙና እንዳይተባበሩ አድርገዋቸዋል።

ሁለተኛው የህወሃት መገለጫ ደግሞ ከመንግስት ባለስልጣናት ያውም ከሚኒስትሮች የማይጠበቁ ዘረኝነት፣ ስግብግብነት፣ ውሸትና፣ የሞራል ዝቅጠት ነው። አብዛኞቹ ባለስልጣናት በዘረኝነት ዛር የሰከሩ ወፈፌዎች ናቸው። የራሳቸውን ብሄር “ወርቅ” በማለት የሚያሞካሹ፣ ሌላውን ብሄረሰብ ግን “ትምክህተኛ፣ አክራሪ፣ ብሄርተኛ” የሚል ታፔላ በመለጠፍ በጅምላ የሚሳደቡ [የራሳቸውን ቃል ልጠቀምና] “ወራዳ” ናቸው። በተለይም ለአማራና ለኦሮሞ ብሄረሰቦች ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸውና በካድሬዎቻቸው አማካኝነት እስከዛሬ ድረስ አርሶ አደር ገበሬዎችን በማፈናቀል የተካኑ በክፋት ሃሴት የሚዝናኑ ናቸው።

አቶ መለስና የህወሃት ባለስልጣናት ዋና ዋና መስሪያ ቤቶችን፣ ወታደራዊ ተቋማትን፣ የገንዘብ ተቋማትን፣ የፖለቲካ ተቋማትን፣ የማህበራዊ አገልግሎት ድርጅቶችን በብቸኝነት በመቆጣጠር ለግላቸው ስልጣን ማስረዘሚያና ኪስ ማድለቢያ ማድረጋቸው አሌ የማይባል ሃቅ ነው። ዛሬም የአየር መንገድን፣ የኮንስትራክሽንና የንግድ ድርጅቶችን፣ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን፣ የውጭ ንግድንና የአገር ውስጥ ገቢን፣ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን፣ ብሄራዊ ባንክን መብራት ሃይልንና ቴሌኮም የመሳሰሉትን ዋና ዋና ተቋማትን ምንም ሃፍረት ሳይሰማቸው ከአንድ ብሄር በተውጣጡ ቡድኖች ቁጥጥር ስር በማድረግ፣ ወይም ደግሞ “ታኮ” ከመጋረጃ ጀርባ በማስቀመጥ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል። ከላይ እንደተገለጸው የትግራይ ተወላጅ ሃላፊዎችን በሙስና እንዲዘፈቁ በማድረግ፣ ወይም ሙስና ውስጥ ሲዘፈቁ አይቶ እንዳላዩ ሆኖ በማለፍ፣ በመፍቀድና፣ በማበረታታት የመንግስት ለውጥ ቢታሰብ እንኳን ከተቃዋሚው ጋር ተባባሪ እንዳይሆኑ የማስፈራሪያ ሪሞት ኮንትሮል ገጥመውላቸዋል። ይህ ስግብግብ ባህርያቸው እንቆረቆርለታለን ለሚሉት ለትግራይ ህዝብም እንቆቅልሽ እንደሆነ ነው የሚሰማው። በጦርነቱ ወቅት የትግራይ ህዝብ እነዚህን ግፈኞችን የደገፋቸው ታጋዮቹ እንዲህ አይነት የግለኝነት እና የአምባገነንነት ባህርይ ይኖራቸዋል ብሎ ሳይገነዘብ ነበር። የትግራይ ህዝብ የህወሃት ባለስልጣናት በጊዜው የደገፋቸው ዛሬ ለራሳቸው እልል ያለ ቪላ ቤት እንዲሰሩ፣ ለራሳቸው እጅግ ውብና ውድ መኪና እንዲገዙ፣ ከድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ በመንጠቅና በውጭ አገር በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለግላቸው እንዲያስቀምጡ አልነበረም። ለስልጣናቸው ሲሉ የሃውዜንን ምስኪን ህዝብ በአውሮፕላን ያስጨፈጨፉ እጅግ እኩይ ሰዎች ናቸው። አቶ መለስ ሞት ባይገላግላቸው ኖሮ ከ22 አመት በኋላም ቢሆን ስልጣናቸውን ለመልቀቅ፣ ተተኪም ለማዘጋጀት ፈቃደኛ አልነበሩም።

የህወሃት ባለስልጣናት የራሳቸው ኪስ ስለደለበ ብቻ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የደላው ስለሚመስላቸው የውሸት የእድገት ቁጥር ጨዋታ ያቀርባሉ። እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ከ22 አመታት በኋላም ቢሆን ከችግር፣ ረሃብና፣ እርዛት ኣልተላቀቀም። የህወሃት ባለስልጣናት ግን ገንዘብ ተርፏቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወደ ውጭ አገር እያሸሹ እንደሆነ አለም የሚያውቀው ሃቅ ነው። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይኸው ከ 24 አመት የስልጣን ጊዜ በኋላም ከ24 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን እርዳታ ይፈልጋሉ። የህወሃት ሰዎች ግን ሌላ መልስ አላቸው። ኢትዮጵያ፣ ከካሊፎርኒያ፣ ወይም ከአውስትራሊያ በተለየ መልኩ ድርቅ አልጎዳትም።

እኔ ግን ለእነዚህ ሰዎች ጥያቄ አለኝ። በየትኛው ስሌት ነው የካሊፎርኒያና የአውስትራልያ ድርቅ ከኢትዮጵያ ድርቅ ጋር የሚወዳደረው? በካሊፎርኒያ በድርቅ ሳቢያ የተራበ ሰው የለም። አውስትራሊያም ቢሆን በድርቅ የተነሳ እርዳታ የሚቀበል ሰው የለም። እኛም ጋ በድርቅ ሳቢያ የተራበ ሰው የለም ሊሉን ይሆን? ካሊፎርኒያም ይሁን አውስትራሊያ በድርቅ ምክንያት የቤት እንስሳት አልሞቱም፥ አዝርዕት አልተበላሸም። ቢሆንም በቂ ክምችት አላቸው። የእኛስ? በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ አርብቶ አደር ወይም ገበሬ ነው፥ ያውም ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ምርት የሚያመርት ወይም ከእንስሳት ተዋጽኦ ተጠቃሚ። አዝርዕቱ ከደረቀ፣ ከብቶቹ ከሞቱበት ምን ይሆናል? አቶ ሃይለማሪያም የህወሃት የትሮይ ፈረስ ሆነው እንጂ ይህንን ከመናገራቸው በፊት ሊያስቡበት ይገባ ነበር። ውድድሩን ከማድረጋቸው በፊት የካሊፎርኒያስ ድርቅ ምን ይመስላል? የአውስትራሊያስ? የውሃ አጠቃቀማችንስ እንዴት ነው? የቁም እንስሳት አያያዛችንስ ምን ይመስላል? የሚለውን ሃሳብ እንኳን የማያገናዝቡ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በጭብጨባ በታጀበ መግለጫ አፋቸውን ሞልተው ሶስቱን አገሮች (?) በአንድ ሚዛን ሲለኩ ሰማሁ። የህወሃት የትሮይ ፈረስ ማለት እኚህ ናቸው። ህወሃቶች የሚፈልጉትን ሁሉ በእሳቸው ተመስለው የሚፈልጉትን መልዕክት ያስተላልፋሉ፣ እውነታው ግን ሌላ ነው። አቶ ሬድዋንም ቢሆኑ ያው “አርብቶአደሮቹ በጊዜው ውሃ ስላላጠጧቸው ነው ከብቶቹ ያለቁት” አሉ። አጃኢብ ነው! ከባለቤቱ በላይ ያወቀ ቡዳ ነው ይባል የለ! ጋዜጣዊ መግለጫውን የባዮሎጂ ክፍለጊዜ አስመሰሉት እኮ!

የህወሃት አሽከሮችና ጭፍሮቻቸው በምግብ ራሳችንን ችለናል የሚል ልፈፋ ሲያሰሙ ከርመው ነበር። የታል ታዲያ? እርግጥ ነው የህወሃት ባለስልጣናት ኪስ በ11 ሚሊዮን % አድጓል። የህዝቡ ኑሮ ግን 1% እንኳን ከፍ አላላም። እርግጥ ነው በህወሃት መንደር እና ሎሌዎቻቸው ቤት ምግብ ተትረፍርፏል፣ በሱማሌ፣ በአፋርና፣ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች፣ የገበሬዎች የቤት እንስሳትና የቀንድ ከብቶች ተረፍርፈዋል።

በጣም የሚገርመው የህወሃት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አይነት የፖለቲካ ግንዛቤ የለውም ብለው ማሰባቸው ነው። ያኔ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኋላ አቶ ስዩም መስፍን ባድመ ለኢትዮጵያ ተሰጠች ብለው አስጨፈሩን፣ በኋላ ስንሰማ ግን የጨፈርነው በሞት ለገበርናቸው ወንድሞቻችን ደም ላይ ነበር!

ሌላው ህወሃት ኢትዮጵያ ውስጥ በማህበረሰባችን በነውርነት የሚታወቀው የውሸት ልማድ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው። ትውልድ ከእነዚህ መሃይማን ምን ይማራል? የህወሃት ቁልፍ የበላይ ሃላፊዎች ድርጀቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀመሮ በሸፍጥ፣ በመግደል፣ በማሳደድ፣ በማሰር፣ በማሸማቀቅ እዚህ ለመድረስ በቅተዋል። በህልማቸው እንኳን አስበውት የማያውቁትን ሃብት አካብተዋል፣ አቅማቸው የማይፈቅድላቸውን ስራ ሰርተዋል፣ በማይመጥናቸው ወንበር ተቀምጠዋል፣ ታዛዥ መሆን ሲኖርባቸው በተገላቢጦሽ አዛዥ ሆነዋል። ከሁሉም በላይ ይቅርታ የማያስደርግ ወንጀል ውስጥ ተዘፍቀዋል። 100% የፓርላማና የአካባቢ ምርጫ አሸነፍን ብለዋል። ከህወሃት በላይ ጀግና የለም፣ አገሪቷን ከፈለግን እንደዶሮ ብልት ገነጣጥለን እንሄዳለን ብለዋል፥ አፍርሰን እንሰራለንም ብለዋል… ሌላም ሌላም።

የህወሃት ሰዎች የተከበሩ ተቋማትን አዋርደዋል። በአገራችን ውስጥ ለረጅም ጊዜ የተከበረው ሽምግልና በነፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ አማካኝነት ፈሩን ስቶ ገደል ገብቷል። ፍርድ ቤቶች የህወሃት የፖለቲካ መሳሪያ በመሆን በንጽሃን ላይ የውሸት ክስ በመመስረት ታሪክ ይቅር የማይለውን ፍርድ አስተላልፈዋል። በተለይም ወጣቶቹ የሚሰሩበትን የወጣትነት ጊዜያቸውን በግፍ በወህኒ ቤትና እንዲያሳልፉ በውሸት ክስ ከአሸባሪዎች ጋር በማያያዝ አስረዋቸው፣ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፈተዋቸዋል። ለምሳሌ የዞን 9 ጦማሪያን በአሸባሪነት ክስ ተከሰው በወህኒ ቤት ከአንድ አመት በላይ ሲማቅቁ ቆይተው ፕሬዚደንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ያለምንም የፍርድ ቤት ሂደት ፈተዋቸዋል። እንግዲህ ህወሃቶች ለስልጣናቸው ሊያሰጋቸው የሚችል ሰው ባይሆንም እንኳን ለሆድ የማይደለል ተቃዋሚ ወይም ጋዜጠኛ ባጋጠማቸው ቁጥር በመጀመሪያ ማስፈራራትና ማሰር፣ ካልሆነም መግደል ለአስርተ-አመታት የተካኑበት አሳዛኝ ድራማ ነው። እናም በኢትዮጵያ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በውሸት ፖለቲካዊ ክስ ተፈርዶባቸው የሚማቅቁ ኢትዮጵያውያንን ማዕካላዊ፣ ቂሊንጦ፣ ዝዋይ፣ ሸዋሮቢት፣ እና ስማቸው የማይታወቁት የጨለማ እስርቤቶች ይቁጠሯቸው!

እንግዲህ ምርጫ በመጣ ቁጥር ተቃዋሚዎችን እያደኑ ማሰር ምርጫው ካለፈ በኋላ እንደገና መልሶ መፍታት የተነቃበት የህወሃት ታክቲክ ከሆነ ሰነባብቷል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ጋዜጠኞችን ሰሞኑን የተፈቱበት ሁኔታም ይኸው ነው። ወቅቱ ስለተቀየረ፣ ተፈተዋል። በሌላ ወቅት ደግሞ እነሱን ብቻም ሳይሆኑ ሌሎች ወጣቶች እንዲሁ ዘብጥያ መውረዳቸው አይቀርም። ሀብታሙ አያሌው፣ ዳኤል ሽበሽ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሸዋስ አሰፋ፣ አብሃም ሰለሞን ሲፈቱ ሌሎች ባለሳምንት ደግሞ በቅርቡ ይገባሉ። እነዚህ ፖለቲከኞች አሁን የተፈቱበት ምክንያት የጦዘውን ፖለቲካዊ ተቃውሞ ለማቀዝቀዝ ይሆናል። ሰሞኑን ህወሃት ከባድ ፈተና ገጥሞታል።

በአንድ በኩል ከልዕለ-ሃያላን ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶታል። በሌላ መልኩ ደግሞ ህወሃት ለማድረግ የፈለገው አንድ ነገር ይኖራል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድል ገንኖ መውጣት የመጀመሪያው ሲሆን፣ በኤርትራ በኩል የሚመጣውን ማንኛውንም ሃይል ለመምታት ያኮረፈውን የኢትዮጵያ ህዝብ “5 የፖለቲካ እስረኞችን” በመፍታት መካስ ይፈልጋል። በመሆኑም እነዚህን የተፈቱት የፖለቲካ እስረኞች ለኢትዮጵያ ህዝብ የቀረቡ የእርቅ ገጸበረከቶች መሆናቸው ነው።

በአሁኑ ሰአት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ይህ የህወሃት መንግስት በሰላማዊ መንገድ ስልጣን እንደማይለቅ በጥብቅ ያምናል። በሌላ በኩል በጉልበት ስልጣን ላይ የወጣ እና በሙስና በአንድ ዘር የበላይነት የነገሰ “መንግስት” በምንም መልኩ አሁን ያለውን ጥቅሙንና ክብሩን ለመልቀቅ አይፈልግም። የራሱን ህልውና ሊያጠፋ የሚችል ነገር በምንም መልክ ይሆን ማዳፈን የመጀመሪያ ስራው ነው። በመሆኑም ትናንሽ መደለያዎችን በማቅረብ ህዝቡን ለማታለል መሞከር ከፍተኛ ጅልነት ነው። አቶ ሃይለማሪያም እንዳሉት፣ “የኢትዮጵያ ህዝብን ፈቃድ ጠይቀን ከኤርትራ ጋር ጦርነት እንገጥማለን” የሚል ጨዋታ ከዚህ በኋላ ሰሚ ጆሮ የለውም። ኣንደከዚህ በፊቱ ህዝቡ ሆ ብሎ ሻዕቢያን (አሁን ደግሞ አርበኞች ግንቦት ሰባትን) ለመደምሰስ በነቂስ ይወጣል ብለው ማሰባቸው ምን ያክል ህዝቡን እንደናቁት ያሳያል።

አሁን የጨዋታው ህግ ተቀይሯል። እንደከዚህ በፊቱ ሆ የሚወጣላቸው ተቃዋሚ ወይም ህዝብ አይኖርም። ህወሃሃት የራሷን አባላት ይዛ መዝመት ተችላለች። የአባላቱ ቁጥር ስንት ነበር? 7 ሚሊዮን? አዎ ሰባት ሚሊዮን አባል ለዘመቻ ብቻ ሳይሆን አገር ለመመስረትም በቂ ነው። 85 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብን ግን ይተውት!

አይሆንም! ህዝቡ ጠላቶቹና አሸባሪዎቹ እነማን እንደሆኑ አብጠርጥሮ ስለሚያውቅ ከሁለት አስርተ አመታት በላይ ሲያሸብሩ የኖሩ ወያኔዎች ላይ አፈሙዙን ማዞሩ አይቀርም። አዎ! ህወሃት የአየር ሰአቷን አሟጥጣ ጨርሳለች። የተወሰኑ ሰዎችን በመፍታት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘትና ስልጣናቸውን በጦርነት ለማስረዘም መሞከር በፊት አዋጥቷቸው ይሆናል፣ ለሁለተኛ ጊዜ ግን አያዋጣም። ህዝቡ ነቄ ብሏል፥ ህወሃት እስረኞችን ስለፈታች ተለውጣለች ማለት እንዳይደለ በደንብ ተገንዝቧል። ነገ ደግሞ ሌሎችን ማሰሯ እንደማይቀር ከልምድ የተማረው ህዝብ የህወሃትን ልብና ኩላሊት በደንብ መርምሯል።

ስለዚህ መቀየር ያለበት የህወሃት ሶፍትዌር ነው። አርጅቷል። በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት የዘረኝነት፣ የአምባገነንነት፣ የማን አለብኝ ባይነት፣ አድሏዊና የቂመኝነት አስተሳሰብ ይዞ አገርን የሚያክል ግዙፍ ነገር መምራት አይቻልም። ስለሆነም በአዲስ አሰተሳሰብ መቀየር አለበት። ከአርባ አመት ከፊት በነበረ ሶፍትዌር አሁንም አገር እየመሩ ያሉ ቡድኖች መፍረስ አለባቸው። ያ የሚሆነ ደግሞ የህወሃት ዘረኞችን ከስልጣን በማባረር ነው። ትግል መደረግ ያለበት ከሻቢያ ወይም ከግንቦት ሰባት ጋር አይደለም ፣ ከወያኔ ጋር ነው። ወያኔ ከተለወጠ ዘላቂ ሰላም ያመጣል፣ የሚገደል፣ በውሸት ክስ የሚታሰር አይኖርም። ከሁሉም በላይ ውሸት የሚፈበርክ ተቋም አይኖርም!