አገር የምትኖረው በ3 ነገር ነው በወታደር በገበሬ እና በመምህር!!! – ከአዲስ ብርሃኑ

Ethiopiaethiopiaአገር ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳው ወያኔ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንድትኖር በመሰሪ ሃሳቡ ሌት ተቀን የማይቆፍረው ግድጓድ የለም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ነገር ግን እንደ አሳቡ ሊሆንለት አልቻሉም  ዘር  ከዘር ሊያጋጭ ብዙ ጣረ አልተሳካለትም፤ ሐይማኖት ከሃይማኖት ሞከረ ይሄም አልሰራ አለው ሃሳቡ ሁሉ መና  ሲቀርበት  እራሱ ከሳሽ  እራሱ ፈራጅ  በሆነበት ፍርድ ቤት  የብዙሃን ነጽሃን  ሰው መሰቃያ  ወደ ሆነው ወህይኒ እየወረወረ ባልሰራበት ወንጀል ባላደረጉት  ድርጊት ንጽሐኑን ማሰቃየት ከጀመረ ድፍን 24 አመት አለፈ።

መምህር…..

አንድ አገር ከሚያስፈልጋት ዋናው መሰረታዊ ነገር መምህር ነው። መምህር ከሌለ የተማረን ህብረተሰብ ማግኝት አይቻልም።  መምህር በጠመኔው ለአገር የሚሆን ፍሬ ለህዝብ የሚጠቅም ዘር በሰው አእምሮ  ውስጥ የሚዘራ እና ብዙ ጥበቦች ባለ ብዙ እውቀት  ባለቤት አገርን በጥበብ የሚመራ ላገሩ በእውቀት የሚያገለግል ለአገር የሚጠቅመውን ካመነበት የሚሰራ ካላመነበት ደግሞ እንቢ የሚል  ማንኛውንም ነገር ሰለ ህዝብ ብሎ ስለ አገር  ብሎ ማድረግ የሚቻል ዜጋን የሚቀርጹት መምህራናን ናቸው።  ዛሬ  ወያኔ እያደረገ ያለው እኔ የምላቹሁን አድረጉ እኔ የምላቹሁን አስተምሩ እኔ የምላቹሁን  መመርያ ተቀበሉ  ብሎ አገርን የሚያጠፋ ሆኖ ሰላገኙት የወያኔ ደጋፊ ባለመሆናቸው ብቻ  አገርን የሚያቀኑን መምህራን ትውልድን የሚቀርጹ  መምህራን በካድሬ በመተካት የተማረ እንዳይበቅልባት ያወቀ  እንዳይወጣባት ትምህርት ቤቶችና ዪንቨርስቲዎች ያቃጣሪወች መናህርያ  አድርጓታል። እንግዲህ ወገኔ የመምህራን መነካት የኢትዮጵያ አንዱ መሰረቱ እየተናጋ ነውና  ልትነቃ እና  የወያኔ አገር አጥፊነቱን አውቀን በቃህ ልንለው ይገባል።

ገበሬ……

አገር የምትኖረው ገበሬው አምርቶ በሚያበቅለው ምርት ነው ገበሬው ጠንክሮ በማረስ አገርን በመመገቡ ሂደት የአገርን መሰረት ነው። ዛሬ  ገበሬው ከመሬቱ በማፈናቀል ለውጪ ባለሃብት  ለኢንቬስተር በመስጠት እንዲሁም በግድ  ማደበርያ  እንዲወስድ እያደረጉት  ባለ  እዳ በማድረግ እዳውን መክፈል ሳይችል ሲቀር መሬቱን ጥሎ እንዲሄድ በማድረግ ተሳዳጅ አድርገውታል። ገበሬ የለም ማለት አገር የለችም ማለት ነው ።ገበሬው በማሰቃየት እረፍት በመንሳት  እስመርረውት ያሉት ወያኔወች ሃሳባቸውም ራያቸውም ሰለ  ኢትዮጵያ  እና ሰለ ሕዝቧ ስላልሆነ ስለሚያደርጉት ነገር  መጸጸት እንኳን አያሳዩም ስለዚህ ገበሬው ሲነካ የአገር መሰረት  መነካት ነውና ወገኔ እንግዲህ ንቃ።

ወታደር…..

አገር የምትጠበቀው በወታደር ነው አንድ አገር ጠንካራ የወታደር ከሌላት  ጠላት በቀላሉ ይዳፈራታል። ስለዚህ ጠንካር የወታደር ተቋም  ለአገር አጥርም መሰረት ነው። ዛሬ ግን ወያኔ እየሰራ ያለው የወታደር ተቋም  በወታደራዊ ስልጠና  እንዲሁም ትምርት በብቃት  የሚበልጣቸው እያሉ  ትግሬ በመሆኑ ብቻ  አዛዥ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ይደረጋል  ይሄ አካሄድ ለወያኔወች የአገር ማፍረስ አላማቸው ስለሆነ  ምንም አይሰማቸው  ለትግሬወች ግን  ጊዚያዊ ሹመት ሲሰጣቸው ሁሉንም ቦታ ያለ እውቀታቸው ቦታውን እንዲይዙት ሲደረግ ለምን ብላቹ መጠየቅ  ሲገባቹሁ የተሰጣችሁን ስልጣን ተቀብላቹ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ላይ  በደልና ጫና የምትፈጥሩ እንግዲህ እዳው በእጃቹ ነው። የወያኔ ባለስልጣን ባንተ ስም የአገርን ንብረት እየዘረፉ  እያሸሹ ይገኛሉ አንተ ግን  ከህብረተሰቡ ጋር የትም አትሄድም  ያኔ  በሰፈሩት መስፈርያ  እንዳይሆንባቹሁ የትግሬ ተወላጆች  በወታደር  ላይ የምታደርጉትን በደል ታቆሙ ዘንድ ያስፈልጋል። እንተም ከጥቂት የአገር አጥፊ እና ዘረፊ ጋር ባለመወገን አንድነታቹሁን የምታሳዩበት ጊዜ በጣም አጭር ነውና ይታሰብበት። ካለበለዚያ ግን  ወደ የኢትዮጵያ  የመከላከያ ሰራዊት ደምና ጉልበት እንዲሁም በኢትዮጵያ ሕዝብና  ሃብት እንደፈለጋቹ እየሆናቹ የምትኖሩበት ጊዜ ማብቂያው ይመጣል።

ወታደሩም እራሱንና  አገሩን ሕዝቡን የመጠበቅ ነጻ የማውጣት ሃላፊነት እንዳለበት ወያኔ የሚያውቅበት ጊዜ  ቅርብ ነው።  ወያኔወች የመከላከያ  ሰራዊት የሃገር መሰረት ስለሆነ ይህንም ለማፍረስ  እና ለመበተን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።  እውነት ነው መምህሩም ወደቀድሞ ቦታቸው  ተመልሰው ባላቸው እውቀት ጠመኔን ይዘው ያለምንም ተጽእኖ ዜጋን የሚያፈሩበት ጊዜ ቅርብ ነው። እውነት ነው ገበሬው ሞፈሩን አንስቶ  እርሻውን አስፍቶ  በትራክተር አርሶ  ሕዝቡን የሚመግብበት ቅርብ ነው ። እውነት ነው ወታደሩ ወያኔን የተባለ ወንበዴን አጥፍቶ ለሕዝቡና ለአገሩ ዘብ የሚቆምበት ጊዜ ቅርብ ነው ።

ሞት ለወያኔ!!!

አዲስ ብርሃኑ

Email- berhanu.addis@yah

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47026#sthash.hsLbn3B7.dpuf

ማስተዋል። (ሥርጉተ ሥላሴ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 30.09.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

አትቀመሽ – ኃይለኛ ነሽ። …..

አትጠጪ – መራራ ነሽ። …….

አትዋጭም – ጎምዛዛ ነሽ፤

አፈ ታሪክ እልም – አይደለሽ። …..

ቁልጭ ብለሽ  – ትታያለሽ፤

እውነት ደፋር ካላገኘሽ፣

ቃና የለሽ ትሆኛለሽ። ሽሽሽ-ሽሽሽ-ሽሽሽ-ሽሽሽ-ሽሽሽ ……

ሰላም ነው – እንዴት አላችሁልኝ – ክብረቶቼ? ደህና ናችሁ ወይ?

ሰንበትን ተንተርሶ የትንቢቴን ፍጻሜ – እያያችሁ፤ ልዑቅ በሉኝ ሲል ሌላም፤ በሰው ልጆች በመኖር ሂደት ውስጥ ስለሚፈጠሩ ገጠመኞችም ሟርትን በመመኘት፤ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ – አስነብቦናል። መርመጥመጥ። የሆነ ሆኖ ባላገኛቸው ህልሞቹ – የቁራኛ እስረኛ ዕሳቢዎቹ ዙሪያ ትንሽዬ ነገር ማለት – እሻለሁ።

Neamen zeleke zehabeshaየተከበሩ አቶ ነአምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት 7 የዓለም አቀፍ አመራር፤ የውጪ ግንኙነት ኃላፊና የንቅናቄው የምክር ቤት አባል፤ የዘመቻ እንቅስቃሴያቸውን አስመልክቶ ብዬም ነበር ዓይነት ነው። እንዲህም ይለናል እኛንም አክሎ … ይወርፈናል፤ „ተመላሹ  ታጋይ የኢሳት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የአርበኞች ግንቦት ሰባት የውጪ ጉዳይ ሃላፊ፤ ጓዜን ጠቅልዬ ለትግል ገባሁ ብለውን በሰበር ዜና ሰምተን ነበር። ሰው፤ ምነው ለድል ሳያበቁን ተመለሱ ብሎ ህዝቡ መጠየቁ አይቀርምና፤ አስቀድመው በየሜዲያው ላይ፤ ወከባ መፍጠር ተገቢ መስሎ ታይቷቸዋል። “ጉሮ ወሸባዬ ባልዘፈንሽ፤ ዘንድሮ ባላፈርሽ” ይላል የአገሬ ሰው። ምናልባት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች፤ በራሳቸው ፈቃድ፤ ይሸወዱ እንደሆን ነው እንጂ፤ የሚዲያ ወከባው፤ በነቃው ሕ/ሰብ ዘንድ ውኃ አልቋጠረም ። ዛሬ ሰው ፤ እንደ ድሮው ዝም ብሎ “ይሁን እስቲ” እያለ ማለፉን ትቶታል ። መጠየቅ ጀምሯል ። እኔም እንዲሁ አንዳንድ ጥያቄዎችን ላነሳ ነው ። በአሜሪካ ድምፅ ከተላለፈውም ሆነ ፤በኢሳት ተደረገ፤ ከተባሉት ቃለ-መጠይቆች፤ ባዶ የሆኑትን ስሜት የማይሰጡ፤ አባባሎች ትቼ፤ የተወሰኑ ነጥቦችን ቀጥዬ አነሳለሁ።“

„ምናልባት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች፤ በራሳቸው ፈቃድ፤ ይሸወዱ እንደሆን ነው እንጂ፤“ ይሄ ነው መነሻዬ። ስለምን እንሸወዳለን? የራሳችን ጌቶች እራሳችን መሆናችን ብቻ ሳይሆን፤ መነሻችንም፤ መድረሻችንም በበቀልና በጥላቻ ያልበከተ፤ ለመርህ የሚገዛ ህሊና ስላለን ጊዚያዊ ወጀብ ወይንም አውሎ ከዓላማችን ንቅንቅ – አያደርገንም። ወይንም በፋሻ ተጠቅልለን የግል ኢጓ ገመናችን እንደ ቄጤማ -አንነሰንስም። ቋሚ ፍላጎት አለን። ጽላታችን ከፋሽቱ ህወሓት የምትላቀቅበት ማናቸውም መንገድ ውስጣችን ነው። ለበጎ ነገሮች – ለአዎንታዊ ጠረን ብቻ መፈጠራችነን አስምረን – እናውቃለን። „አቤቱ ንፁህ ልብን ፍጠርልኝ፤ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ  አድስ።“ (መዝ ምዕራፍ ፶ ቁ. ፲ ) የህይወት ዘመናችን ሰማያዊ መርህ ይህ ነው፤

የማከብራችሁ  – ናፍቆቶቼ የእናት ኢትዮጵያ ልጆች። „ባዶ“ የተባለውን የጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ስላቅን – እንዲህ ከመሰረት ብነሳ የተሻለ ነው። በጥልቀት ሳይሆን በጫፍ እጅግ በስሱ ንድፈ ሃሳብ ትንተና ነገር ….

ድርጅት ማለት ምን ማለት ነው? ድርጅት ማለት – ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ወይንም ስብስቦች፤ በፍላጎታቸው ወይንም በዓላማቸው ወይንም በእምነታቸው ዙሪያ የሚሰባሰቡበት የሰዎች ማህበር – የወልዮሽ ማእከል ሲሆን፤ ጊዜያዊ ወይንም ቋሚ ሊሆንም ይችላል። ድርጅት አጭርና ረጅም ራዕዮችን ለማሳካት የሚያስችል ተቋም፤ አሰባሳቢ ማእድ ነው። ሰብሳቢም ነው።

በተለይ የፖለቲካ ድርጅት ከሆነ ሰፊ ህዝባዊ ኃላፊነትን ወስዶ – ይደራጃል። ስለሆነም የፖለቲካ ድርጅቶች መሰረታዊ ሰነዶቻቸውን መሰረት ያደረገ መርኃ ግብር አላቸው። አካሎቻቸው የሚፈጠሩትም በአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ነው። በየደረጃው የሚካሄዱት ጉባኤዎች ምክር ቤታቸውን ይመርጣሉ። ምክር ቤቱ ደግሞሥራ አስፈጻሚውን ይመርጣል።

ተግባራቸው — ጉባኤው እስኪሰበሰብ ድረስ ምክር ቤቱ የጉባኤውን ኃላፊነት ወስዶ – ይሰራል።፤ ምክር ቤቱ እስኪ ሰበሰብ ድረስ ደግሞ የድርጅቱን ዕለታዊ ተግባሩን የሚከወነው ሥራ አስፈጻሚው ይሆናል።

የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቲው የበቃ ውክልና ስላለው፤ የድርጅቱ አካላትን ሆኑ አባላትን እንደ የኃላፊነታቸው – ይደለድላል፤ ያሰማራል፤ ተግባራቸውን – ይገመግማል፤ ተጨማሪ ኃላፊነቶችን – ይሰጣል። በፈለገው የግዳጅ መስመር – ይልካል። የፓርቲ አባላትም በየደረጃው ያሉ አካላትን በመብታቸው ተጠቅመው በፈቃዳቸው እንደ መረጡ ሁሉ፤ ለመረጡት አካላት የስምሪት ድርሻን በውዴታ ተቀብሎ ኃላፊነትን የመወጣት ግዴታ – ይኖርባቸዋል። መብትና ግዴታ ተግባር ላይ በዚህ መልክ ኪዳን – ያስራሉ።

እና ለእኔ የአቶ ወንድም የትንተና አግባብ – የፓርቲ የአደረጃጀት መሰረታዊ መርህን ካለማገናዘብ የመጣ ነው። በተጨማሪም ዘመኑ 21 ኛው ምዕተ ዓመት ላይ ነን። የሰለጠኑ ሂደቶች እንዲስተናገድባቸው ግድ ይላል። ሰው አልባ አውሮፕላን የግዳጅ ስምሪትን እያዬን እኮ ነው። ሥልጣኔው በራሱ ከዴሞክራሴያዊ ፍላጎት አፈጻጸም ጋርም በመስተጋብር የተቃኜ ነው። ይህም ብቻ አይደለም፤ ስለ አርበኞች ግንቦት 7 መሪዎች የተግባር ስምሪት ቀዳሚ መረጃ ለማግኘት አቅሙ – አይፈቅድም። በፓርቲው ውስጥ እሱ እራሱ ጋዜጠኛው የለም። በይሆናል እና በነሲብ ደግሞ የፓርቲ መርህ እንዲህ ለቡና ተርቲም – አይደፈርም። ስለዚህም እንደ ማንኛውም ዜጋ እኩል ሁሉ የሚሰማውን ብቻ መስማት ግድ ይላል። በሌላ በኩል የነፃነት ትግል የሠርግ ርችት የሚተኮስበት – አይደለም። እንደ ቄጤማ የአካላቱ ስምሪትም አይነሰነስም። መራር ትግል – ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ዲስፕሊንን – ይጠይቃል።

ከሁሉ በላይ እንደ ቀደመው ጊዜ የፍንጪ ቧንቧው አይገኝም – ተከርችሟል። እስከ አሁን የተከፈለው መስዋእትነት – ይበቃል። የኢትዮዽያ ህዝብ አርበኞችና የግንቦት ውህደቱ ይህን ሁሉ እምስ ፍላጎቶችን – አምክኗል። ለዚህም ነው ነጋ ጠባ ሥጋ እንደ ተቀማ ሥጋ በይ እንሰሳ ጉምጅቱ በብራና እና በብዕር ላይ ሲደፋ የምናዬው፤ የእንብርክክ – የሚያስኬደውም፤ ለዚህም ነው በመደዴና በድንብስ ታቱ – የሚባላው። የባላደራው ራዕይ እንደ ቀደመው ጊዜ – እንደ ረጋ ኩሬ ባለህበት እርገጥ ዛሬ የለም። እያንዳንዷ ማዕልት በቅኔ ጥልፍ የተቃኘች ስለሆነች፤ ከፍጥነቱ ጋር ለመጓዝ ነሲብ የሙጥኝ ማለት ግድ – የሆነውም ለዚህ ይመስላል። ሰረገላው ባለቤት አለው። ገና ምን ታይቶ። የአፍሪካ ቀንድ የፍቅር ናሙና ቀንዲል – ትሆናለች። ምእራቡ ዓለም ይሁን የኤርትራ መንግስት ፋሽስቱን ህወሃትን ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን፤ የነገውን የተረጋጋ ሥርዓት ለመዘርጋት በሰፊ ትእግስት የጠበቁትን፣ የተመኙትን አግኝተዋል –  ብየ አስባለሁ – እኔው። ህልሙ ያልተሳካለትም አቅሙን – ይጠይቅ። የአቅሙ ምጣኔ – ኮከብ ቆጣሪ ሳይጠይቅ  – ደረጃውን ይነግረዋል። ምን ያህል ተጉዞ  – ምን እንዳተረፈ?

አርበኞች ግንቦት 7 ተገብቶ የተፈለገው መረጃ ተዝቆ የሚወጣበት – አይደለም። አመሰራረቱ፥ የአትኩሮት መሰረቶቹ መርኽ  ከወትሮው እኛ ከምናውቀው ሆነ ከተለመደው የተለየ ነው። ስለሚጠጥርም ነው ወደ ትችቱ የሚዘነበለው። ፍልስፍናው እረቂቅ፤ በእውቀትና በብቃት የተገነባ ነው። ልምዱም ተመክሮውም በአዲስ የአስተሳሰብ ዲዛይን እንደ ራሳችን ሆኖ፣ ለነባር ድክመቶች በር ዘግቶ ከአዲሶችም ለመማር ፈቅዶ ነው  – የተፈጠረው። ማስተዋል። ለአዲሱ ሥልጡን ዘመን በተወሳሰበ ችግር ለማለፍ ብልህና ጥንቁቅነትን – ያስቀደመ። ማስተዋል። በእጁና በመንፈሱ ያለውን ስለሚያውቅም ነው ለተረት ተረቶች መልስ ሰጥቶ ደረጃውን ዝቅ የማያደርገው። ማስተዋል። ለዚህም ነው ለንቅናቄው አክብሮትን መንፈሳችን አብዝቶ የሚለግሰው። ጥቂቶች ደግሞ አዳዲስ ጠቃሚ ግኝቶችን እንደ መፍትሄ አመንጪ ሳይሆን፤ እንደ አንጡራ ጠላት በማዬት፤ አቅም ማጠሩ የብጭት እስረኛ ሲያደርጋቸው የሚታዩትም በዚህ ምክንያት ነው።

የተከበራችሁ የጹሁፌ ታዳሚዎች – ታስታውሱ እንደሆን ኤርትራ የገባው የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ መሪ አካል፤ በአርበኞች ካንፕ ተገኝቶ ባደረገው ንግግር የአቶ ነአምን ዘለቀ ቃል ጭብጥ እንዲህ ይል ነበር „ውጪ የሚገኘው ወገናችሁ ድጋፉ እንደማይለያችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።“ ይህ ማለት አቶ ነአምን ዘለቀ ይህን ሀገራዊ ኃላፊነት መውሰድ የሚችሉ ስለመሆኑ ይገልፃል። ለዚህ ቃል ጠንቋይም መጸሐፍ ገላጭም – አያስፈልግም። በኪዳኑ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ክቡርነታቸው እንዳሉበት፤ በኤርትራ ቋሚ ቆይታ እንደለላቸው – ይገልጣል። አንድን ሃሳብ ለዛውም የፖለቲካ ንግግር እንደ ወረደ – አይተረጎምም። ፈልፈል አድርጎ እያገላበጡ በቅንነት መመርመር – ያስፈልጋል። ይሄን ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ አላዳመጠውም። ወይንም ንግግራቸውን ለመረዳት አልቻለም ማለት ነው።

ለማንኛውም ይህ ገለጻ በቀጥታ ውጭ ባለው ተግባር ላይ እንደሚያተኩሩ፤ እድምታው ካለ አስተርጓሚ – ያብራራል። እንዲያውም ከሀገረ አሜሪካ ነቅለው እንዲወጡ አስደረግናቸው የተባለው ዜና ነው  „በሬ ወለደ“ የሚያሰኘው። ከዚህም በተጨማሪ ሌላም አመክንዮ ልከል፤ ፓርቲያቸው የመደባቸው ቦታና ድርሻቸው „የውጪ ግንኙነት ኃላፊ“ ይሄ ነው።

ይህ ዓለምአቀፋዊ ኃላፊነት ኤርትራ መሬት ላይ ተሁኖም  – አይሰራም። አቶ ነአምን ዘለቀ ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት የግድ ነው ወደ አሜሪካ መመለስ፤ ነገም ቢሆን ወቅቱ እንደሚጠይቀው ኃላፊነት ፓርቲው አካሎቹን ሊያንቀሳቅስ – ይችላል። በፈለገው ቦታና ጊዜ፤ በሚገጥመው አወንታዊ ሆነ አሉታዊ ተጨባጭ ሁኔታ የፈለገውን እርምጃ – ይወስዳል። ኮከብ ቆጣሪ – አያሻውም።

ወገኖቼ ጠቃሚው ነገር በልካችን „ልክ“ ሙያችን ለማስከበር መጣር ብልህነት – ይመስለኛል። ጎንደሬም ሲተርት „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላል። ቅን ወገኖቼ – የሀገሬ የኢትዮጵያ ልጆች እውነቱ ያለው ከፖለቲካ ድርጅቱ ከንቅናቄው ከመርኹ እንጂ ከቂምና ከጥላቻ ማሳ አይደለም። ቀረብ ብላችሁ የቆዩትን የምስረታ ንጥር ሂደቶች መልሳችሁ፣ መላልሳችሁ ስታዳምጡት ብልሃቱ  – ያስተምራችኋል። ከሽሽትም – ይታደጋችኋል።  እድሜ ያላስተማረው አልቃሻ ፍላጎት ጸጸትን አዝሎ – ይኖራል። ጊዜን ያላዳመጠ ስብዕና ማለቁን የሚያውቀው ከሹልከቱ በኋላ ነው።

አንዲት የመጨረሻ ብልህ ነገር፣ ልባም ግን የተመሰጠረች ነገር ላንሳ፤ ታስታውሳላችሁ አይደል? በውጭ ሀገር የሀገር ውስጥ ሰላማዊ ትግሎችን ለማገዝ ሆነ ለርዳት ስለሚደራጁት፤ በሀገር ቤት ላሉት ሁለገብ እንቅስቃሴው የውጭ ሀገሩ የሥነ – ልቦና እስረኛ ወይንም ጥገኛ ያደርገዋል። ፍላጎቶቹ በጫና የተወጠረ ነው። የሉዓላዊ ልዕልናው ነፃነቱ በስውር የታፈነ ነው። የኢኮኖሚ አቅም ጥገኝነቱ መብቱን – ይጫነዋል። እንደልቡ አያንቀሳቅሰውም ዋ፥ ሱ ስለሚባል ለብዙ ነገር የተጋለጠ ነው። የጥቅሙን ያህል ጉዳቱም ያን ያህል ነው። እርግጥ እነ ቅንዬ ሊኖሩ ይችላሉ፤ ቅኖች ግን ጥቂት ናቸው። በአርበኞች ግንቦት 7 ግን የጥፋቱ በሽታ ሁሉ አይደገምም። ስለምን? ማርከሻው በመዳፉ ውስጥ ነውና። አርበኞች ግንቦት 7 ሌላ ቅጥልጥል ቻፕተር – አላስፈልገውም። የእራሱ አካል ይህንን የውጭ ሀገሩን ተግባር በኃላፊነት – ይከውናል። መደበኛ ሥራው ነው። ሽክፍ ያለ – ትጥቁ ያማረ – ስንዱ። ማለፊያ። ልባም የተመክሮ – ተቋም።

አንዲት መሸብያ አመክንዮ ልከል – አቶ ነአምን ዘለቀ የአባቱ ታሪክ አስከባሪ ልጅ ፤ የጀግኖች ቁንጮ – ልዕልት ኢትዮዽያ በ100 ዓመት ከማታገኛቸው በኢትዮዽያ የባህር ኃይል ታሪክ ጉልላተ – ጀግና የሆኑት የኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ ልጅ እኮ ነው። ኧረ ቀልድ – ይቁም። ወጣቶች – የእኔ ውዶች የለጠፍኩላችሁን – የውስጣችን ታሪክ ነበብ አድርጉና፥ ትናንትና ዛሬን የጀግናውን የአብራክ – መንፈስ ቃኘት – አድርጉት፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ አለ ከእኛ ጋር የጀግና – ጠረን። ታሪክ የጨዋታ ማሟያ አይደለም፣ ለባለ – ህሊናዎች። http://www.abugidainfo.com/index.php/9920/

ክወና – የማከብራችሁ የጹሁፌ ታዳሚዎች፥ ለኢትዮዽያ ህዝብ መልካም ዜና፣ የተስፋው ማህደር ነውና፤ በተስፋው ላይ የጉሮሮ አጥንት የሆኑ ዕሳቤዎችን መዋጋት የተግባራችን ሁሉ አህዱ ሊሆን  -ይገባል። ዛሬ አንድ በረሃብ የተጎዳ ወገናችን መልካም ሰምቶ ደስ ብሎት ሲተኛ፥ ላይመለስ ሊያሸልብ – በዛው እንደ ተኛ ሊቀር ይችላል። የዛች ቅጽበት ደስታውን እንደ ሰነቀ እንዳያልፍ፥ ይህ እንኳን ረመጥ የሆነባቸውን፤ አንደበቶች ሆኑ ብዕሮችን ልንታገላቸው – ይገባል። ለተስፋ ቀማኛ ርህርህና ወንጀል ነው። ተስፋ ለተስፈኛው ኑሮው፣ ህይወቱ፣ እስትንፋሱ፤ ቀልቡ፤ አደቡ፤ ነገው ነው። ነው። ነው። ይህ ሲያስቀና፤ ይህም ሲቀናበት የተገፋው ህዝብ ከፋሽስቱ ህወሓት የተላቀቀ ቀን ገመድ እራት ሳይሆን – አይቀርም። እንበርታ። ያ …. እንዳለፈው ….. ይህም ያልፋል። ይነጋል – በያነጋል።

የመስከረም 24.09.2015 የራዲዮ ሎራ Tsegaye Radio or www.tsegaye.ethio.info Aktuell Sendung ዝግጅት የመስከረም 5.2015 የአርበኞች ግንቦት 7 የድጋፍ ስብሰባ ሁለተኛ ክፍልና ሌሎችንም ለምትፈቅዱ ቅኖች አርኬብ ላይ ማዳመጥ – ትችላላችሁ። የጥራቱ ግድፈት የእኔ – አይደለም፤ የራዲዮ ዝግጅቱ ነው።

ሀገር የማዳን የደጀንነት ብሄራዊ በሳል የዕንባ ጥሪ  ….  የእመቤት ኢትዮጵያ ልባዊ ጥሪ ….

የማሸነፋችን መልእክቱ – የነፃነት ቀበኛ መረቦችን በተግባር ስንረታ ብቻ ነው። የእምዬዋ የመሃጸን ፍሬ ዘሮች – የጥቁር አንበሳ ጥሪ በረከት ተሳታፊ ለመሆን፤ የእናት ሀገር ብሄራዊ ለዕንባዋ ዋቢነት፤ ቀጠሮ አልባ፤ በቦታው መገኘትን በማስተዋል ይጠይቃል። ለሃዘኗ ቀን ጋባዥና ተጋባዥ – የለም። በህወሓት ለተጠቀጠቀው ዜግነት ሁሉም ደምመላሽ መሆን – ይገባዋል። የተቀደሰ ተሳትፎ የአደራ ኪዳናዊነት ነው። ሊንኮቹን ተከትለው ዝርዝር መረጃ – ያገኛሉ። በተሳትፈወት መጠን የነፃነት ናፍቆትን – ያቅፋሉ። በፍጥነተወት ልክም ህሊናዎት የእርስዎ፤ ስለእርስዎ የተፈጠረ መሆኑን – ይለኩታል። ሁሉም  – በመዳፈዎ። ፍቅር – ተስፋ  – ሐሤት – ማሸነፍ የነጋ ነገ። ቅድስት ነፃነት በብርክት አንባ።

http://ecadforum.com/category/events/

A call to the Salvation of Ethiopia in Chicago, IL, USA

A call to the Salvation of Ethiopia in Atlanta, Georgia, USA

A call to the Salvation of Ethiopia in San Jose, CA, USA

A Call to the Salvation of Ethiopia in Boston, USA

መሸቢያ ሰሞናት – ዘሃበሻ ትእግስታችሁ ዕለታዊ ትምህርት ቤቴ ነው። ኑሩልኝ።

አርበኞቻችን መንገዶቻችን ናቸው።

እልፍ ነን፤ እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47036#sthash.gfXPGYYj.dpuf

የትጥቅ ትግልና ግራ የሚያጋባ አስተያየት – ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

Getachew Haile  - Satenaw

በኢትዮጵያ ትከሻ ላይ የተቆለፈውን ቀምበር ለማላቀቅ ቍልፉ የትጥቅ ትግል መሆኑ በተነሣ ቍጥር ከአንዳንድ ሰዎች የሚሰጠው አስተያየት ግራ የሚያገባ ነው። ገዢዎቹና ደጋፊዎቻቸው ቢቃወሙ ይገባኛል። የሚሰጡት አስተያየት ግን ሕፃንን ሳይቀር የሚያሥቅ ነው። “ጦርነት በቃን” ይላሉ። “አትንኩን” ማለታቸውን የማናውቅ ይመስላቸዋል። ጦርነት ካላስፈለገ፥ ለምን ከንጉሣዊው አስተዳደር ጋር ተዋጉ? ለምን ከደርግ ጋር ተዋጉ? ጨቋኝ ገዢ የት አገር ነው በሌላ መንገድ ሥልጣን ለሕዝብ ሲለቅ የታየው? የምሥራቁ ዓለም ጨቋኞች የወደቁት በሕዝብ ዐመፅ ነው ማለት፥ የምዕራቡን ዓለም ከባድ እጅ ሚና መርሳት ይሆናል።

የኛዎቹ ጦርነት ከመረራቸው፥ ሕዝብን ወደጦርነት የሚመራ በደል አይሥሩበት። ምን ጊዜም ቢሆን የትጥቅ ትግል የመጨረሻው አማራጭ ነው። የትጥቅ ትግል የሚያደርሰው ጉዳት በአንዱ ወገን ላይ ብቻ አይደለም። መሣሪያ የሚያነሣ መሣሪያ ማንሣት የሚያመጣበትን ጉዳት ሳያውቅ አይነሣም። ሰው ሆኖ እንደከብት መገዛት ያልቻለ ሰው በቃኝ ሲል፥ ክብሩን በመጠበቁ ከተቀመጡበት ተነሥቶ “ነወር” የሚባል እንጂ፥ በባርነት ጥላ ሥር ተቀምጦ የሚተች አይደለም። “ጦርነት መርሮናል” የሚለውን ምክር መገዛት ለመረረው አይመክሩም።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ግራ አጋቢ አስተያየት “ጦርነትስ አስፈላጊ ነው፥ ግን . . .” የሚለው ነው። ይህ አስተያየት በቅን አሳብ፥ የተሰጠ ሊሆን ይችላል። ግን አዛኝ መስሎ፥ ቀምበረኛውን ለመደገፍ የተሰጠ አስተያየት አለመሆኑ በምን ይታወቃል? እውነተኛ አሳቢና ሠጊ ሰው አስተያየቱን የሚሰጠው ሲጠየቅ፥ ካልተጠየቀም በግሉ ትጥቅ ያነሡትን ፈልጎ በጨዋ ደምብ መንገር ነው። ሳይጠየቁ ተነሥቶ በይፋ ምክር መስጠት ግን ሰሚው ሕዝብ ትግሉን እንዳይደግፍ መገፋፋት ነው። የትጥቅ ትግል ከታመነበት እንዲፋፋም የማይፈለግበት ምክንያት ምንድን ነው?

ትጥቅ ትግል የራስን ሕይወት ለወገን ነፃነት መሠዋት ማድረግ ነው። ሌላ ዓለማ የሌለው ሰው መሣሪያ ሲያነሣ፥ እንዴት ይኸንን የሚሰነዘርበትንና የሚሰነዘርለትን ምክር ሳያስብበት ራሱን ለመሥዋዕትነት ያቀርባል? የሚካኼደው የትጥቅ ትግል የሚያዋጣ የመሰለው እርዳታውን ያቅርብ፤ የማያዋጣ የመሰለው ለምንድን ነው የሚቃወመው? ተቃውሞው ማንን ለመጥቀም ነው? ለታጋዮቹ አስቦ ከሆነ፥ ከባለቤት ያወቀ ቡዳ ነው። “የኔን ያህል የማሰብ ችሎታ የላችሁም” ማለት ነው። እንዴት ነው ለታጋዮቹ ያልተገለጠ ሥጋት ለምክር ሰጪዎቹ የተገለጠው?

አንዳንዱ ደግሞ፥ “ይኸው እንታገላለን ሲሉ ዓመታት አሳለፉ፥ ግን አንዳች ውጤት አላሳዩም” ይላል፤ ውጤት እንዲያሳዩ የቀጠራቸውና ካልሆነላቸው የሚያሰናብታቸው ሹም ይመስል። አርፎ መቀመጥ ስንት ውጤት አሳየ? ሌሎችን ሙከራዎችም “አንዳች ውጤት አላሳዩም” ብለን እንንቀፋቸዋ!ውይስ ውጤት አሳይተዋል?

“በመካሄድ ላይ ያለው የትጥቅ ትግል ኢትዮጵያን የሚጎዳ ነው” ከተባለ፥ እርግጥ ሊታሰብበት ይገባል። ግን አሳሳቢው ምክንያት ሊቀበሉት በሚገባ መልኩ አልተሰጠንም። ይህ ትግል የሚያመጣው ጉዳት ከተሸከምነው ቀምበር ይበልጥ ሊከብድ እንደሚችል አሳዩን።

የወያኔ ቀምበር መሰበር አለበት የምንል ሁሉ በመሰለንና በተቻለን መንገድ እንታገል። ካልተቻለን፥ ካልመሰለን፥ አርፈን እንቀመጥ፤ ታጋዮችን አለማደናቀፍ፥ እንደ ትግል እንዲቈጠርልን።

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/10537#sthash.PiuBnPia.dpuf

በ1857 ዓ.ም በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን በኢትዮጰያ የመጀመርያው የቁንጅና ውድድር በጎንደር ከተማ ተደርጎ ነበር፡፡

የዛሬ አንድ መቶ ሃምሳ አንድ ዓመት በ1857 ዓ.ም በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን እንዲህ ሆኖ ነበር፡፡
የመስቀል በዓል በዋለ በሁለተኛው ቀን በዓሉን ምክንያት በማድረግ ምናልባት በኢትዮጰያ የመጀመርያው የቁንጅና ውድድር በጎንደር ከተማ ተደርጎ ነበር፡፡ ከልደታ ምሥራቅ ለአበራ ጊዮርጊስ ሰሜን ከሆነችው በቀሃ ወንዝ አጠገብ ከምትገኘው አጤ ሰቀላ ከምትገኘው ኮረብታ ላይ የንጉሠ ነገሥቱ ሸራ ድንኳን ተተከለ፡፡ ከጧቱ ከሶስት ሰዓት ጀምሮ በዓሉ ወደሚከበርበት ሜዳ የከተማውና የገጠሩ ሕዝብ ይጎርፍ ጀመር፡፡

4 ሰዓት ሲሆን ምርጥ መሣርያ የያዙ ወታደሮች እና አጋፋሪዎች ሰለፈኛውን ለማስተናበር ጸጥታውን ለማስከበር በበዓሉ ሜዳ ተሠማሩ፡፡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ፊታውራሪ ገብርዬ በሠራዊቱ ታጅቦ ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበ አጤ ሰቀላ ደረሰና የዙፋኑን አቀማመጥ ተመለከተ፡፡ እንዲሁም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ በፈረሶች በሚሳብ ሠረገላ ተቀምጠው ሊቀ መኳስ ዮሐንስ ቤል ባሠለጠናቸው ወታሮች እየታጀቡ መጥተው በዙፋናቸው ላይ እንደተቀመጡ እምቢልታ እና መለከቱ ተብላላ፡፡ ነጋሪት አጅብር አጅብር ውጋው ውጋው እያለ ይጎሰም ጀመር፡፡

ዘፋኞች ይዘፍናሉ፡፡ አዝማሪዎች ይዘምራሉ፡፡ ወታደሮች ይጨፍራሉ፡፡ በዚህ ዓይነት ይዞታ ተድላ ደስታ ሆኖ ሲደባለቅ በመካከሉ ለውድድሩ የታጩት ወይዛዝርት ጥልፍ ቀሚሳቸውን እያንሰረተቱ፣ ተቀብተው፣ ተኩለው ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ያልፋሉ፡፡ ቀጥሎም ምርጫው በሚፈጸምበት ጎል እየገቡ ውበታቸው እና ደም ግባታቸው፣ የላሕየ ገጻቸው አወራረድ፣ የፀጉራቸው ሥሬት፣ የቁንዳላቸው እርዝመት፣ ሽንጣቸው ዳሌያቸው እና ተረከዛቸው እየተመረመረ የምርጫው ሥነ ሥርዓት ይጀመራል፡፡

በመካከሉ በሰቀልት ወረዳ ከመቋሚያ ማርያም የመጣችው ትውልዷ ከመቄት አዝማቾች ወገን የሆነ የደጃዝማች ይልማ አሰፋ ልጅ ልጅ፤ ጣይቱ ይልማ አንደኛ ስትሆን፤ እንዲሁም ከጎንደር አዲስ ዓለም የመጣችው የመሐመድ ኩርማን ሚስት የሼህ መሐመድ ጌታ ልጅ ተዋበች በጠጉሯ ማማር፣ በቁንዳላዋ አወራረድ እና መርዘም ሁለተኛነትን አግኝታለች፡፡

ከዚህ በኋላ ዮሐንስ ቤል እና ፊታውራሪ ገብርዬ የምርጫውን ውጤት ለንጉሠ ነገሥቱ ለመንገር ወደ ዙፋኑ ይቀርባሉ፡፡ ወዲያውም ጣይቱ ይልማ አንደኛ፣ ተዋበች መሐመድ ጌታ ሁለተኛ ከገለጹ በኋላ ተመራጮች ከዙፋኑ ፊት በመቅረብ እጅ እየነሡ ሽልማታቸውን ተቀብለው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኖ በሰባት ሰዓት እንደተለመደው ለመሳፍንት፣ ለሊቃውንት፣ ለመኳንንትና ለካህናት የምሳ ግብዣ ተደረገ፡፡ ከውድድሩ በኋላ ጣይቱ ይልማ (ወርመር) ኦርማኤል የተባለውን በጋፋት የመድፍ ሠራተኞች አለቃ በሚስትነት አግብቶ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ወልደዋል፡፡ አሁንም ጋይንት ውስጥ በኦርማኤል ስም የሚጠራ መሬት አለ፡፡

ምንጭ፦ የቋራው አንበሳ አባ ታጠቅ ካሣ ከተሰኘ በገሪማ ታረፈ የተጻፈ መጽሀፍ
በተጨማሪም ጻዉሎስ ኞኞ በፃፉት አጼ ቴዎድሮስ በሚለዉ መጽሃፍ ዉስጥም ይህ ታሪክ ተገልፆል፡፡

ኑሮ በመፈክር (ጌቱ ኃይሉ)

ጌቱ ኃይሉ

አቶ ዠ 57 አመታቸው ነው። መተዳደሪያ አላቸው። እንዴት ያለ ሙያ!! ባሥራ ሰባት አመታቸው የጀመሩት። አርባ አመት ሙሉ ያለማቋረጥ እየሰሩ ያሉት። ሰዉ ከሥራው በመንግሥት ለውጥ፣ በሰበብ ባስባቡ ሲባረር እሳቸው ሥራ አላጡም። ሥራቸው? መፈክር አድምቆ መጻፍ።

መጀመሪያ በሁለት ቃላት ጀመሩ። በነጻ “ኢትዮጵያ ትቅደም!” ብለው አድምቀው ጻፉ። ከዚያ እየተከፈላቸው ደግሞ “ከቆራጡ መሪ ጋር ወደፊት !!” ብለው ቀጠሉ። ሰውየው ብቻቸውን ሲቀሩ። ወደ መጨረሻው ግድም ደግሞ “አብዮታዊት እናት ሃገር ወይም ሞት” ብለው ደጋግመው አድምቀው ጻፉ። “አብዮታዊት እናት ሃገር ወይም ዝምባብዌ!” ብለው አላፌዙም።

አቶ ዠ ፕሮፌሽናል ናቸው። የከፈለ ያጽፋቸዋል። ጊዜው እየረዘመ ሲሄድ መፈክሮቹም መርዘም ጀመሩ። አንድ ገጽ የሚሆን መፈክር ጻፍ ሲባሉ እንኳን “እሺ፣ ሂሳቡ ይሄ ነው።” ብለው ቀጠሉበት።

“ከልማታዊው መንግስታችን ጋር በመተባበር ድህነትን ታሪክ ለማድረግ የየበኩላችንን ድርሻ በቅንነት እንወጣ” ብለህ ጻፍ ሲባሉ አሳምረው ጻፉ። “የቅንድባችንን ጸጉር በማሳደግም አስተዋይነታችንን እናጎልብት !!” ብለው አላፌዙም።

“የሚሰጠንን የአቅም ግንባታ እና የተሃድሶ ስልጠና በማጠናቀቅ ለሃገራችን የህዳሴ ጉዞ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናበረክታለን !!” ብለህ ጻፍ ሲባሉም “እሺ!” እንጂ “በሥልጠናው ወቅት በሚሰጠን የውሎ አበል ግድቡ አቅራቢያ ያለች የገጠር መንደር ሄደን እያጨበጨብን እንጨምሳለን !!” ብለው አላፌዙም።

“ኢትዮጵያ ካሊፎርኒያና አውስትራልያ ተመሳሳይ ናቸው!!” ብለው መፈክር ለመጻፍ በራሳቸው አነሳሽነት ከጀሉ። “ምክንያቱስ?” ሲባሉ “ሦስቱም ሀገሮች ድርቅን ምንም ማድረግ አልቻሉምና !!” ብለው ማፌዝ ግን አልከጀሉም። ያ ፌዝ “copyrighted” ነውና!

“እኔ የምለው? እንዴት ነው ይኸ ነገር? ‘ሙያ በልብ ነው’ የሚባለው ያባቶቻችን ብሂል ገደል ገባ እንዴ? መፈክር ብቻ ሆነ እኮ ነገራችን። አርባ አመት ሙሉ መፈክር። አርባ አመት ሙሉ ፉከራ! አንድ ነገር ሳንሰራ! አይ የኛ ነገር!” ጓደኛቸው አቶ ጠ ጠየቃቸው።

“ዝም በል አንተ! መተዳደሪያዬን እንዳታሳጣኝ…” መለሱ አቶ ዠ።

እባክዎን ሳያስፈቅዱ ላለመቅዳት መልካም ፈቃድዎ ይሁን።

መስከረም 03/2004 ዓ.ምን ሳስታውሳት… (አንዷለም -ወ- እስክንድር) – ኤልያስ ገብሩ

Andualem and Eskinder  - Sateanw 1

Andualem Aragie - Satenawመስከረም 03 ቀን 2004 ዓ.ም እኔና ጓደኛዬ አናንያ ሶሪ በወቅቱ እንሰራባት ለነበረው አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ፣ በከፍተኛ ትምህርት ጉዳይ ዙሪያ ፊቸር ጽሑፍ በጋራ ለማዘጋጀት አቅደን፤ ለመረጃ ግብዓት መቅረፀ ድምጻችንን ይዘን በቀድሞ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ቢሮ በጥዋት ደረስን፡፡ ለተወሰኑ ጥያቄዎቻችን መረጃ እንዲሰጡን ቀድመን ጥያቄ በማቅረብ ቀጠሮ ይዘን የነበረው ከአቶ አስራት ጣሴ ጋር ነበር፡፡ እሳቸውም ከቀጠሯችን ቀደም ብለው በቢሯቸው ተገኝተዋል፡፡ ከሰላምታ ቀጥለን ወደዋናው ጉዳያችን ዘለቅን፡፡ በዚህ መካከል የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የፓርቲው ፀሐፊ አቶ አንዷለም አራጌና በአሁን ወቅት የዘነጋሁት አንድ ሰው አቶ አስራት ቢሮ ድረስ በሩን በማንኳኳት ገቡ፡፡ከሰዓት ከሁሉም ጋር ሰላምታ ተሰጣጠን፡፡ የእነአንዷለም አመጣጥ አቶ አስራትን ጠርተው አጠር ያለች ኢ-መደበኛ ስብሰባ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ከንግግራቸው ተረድተናል፡፡ ‹‹አስቸኳይ ነው›› ስለተባለ አቶ አስራት እኛን ይቅርታ በመጠየቅ ቀጠሯችንን ከሰዓት በኋላ ማድረግ እንችል እንደሆነ በትህትና ጠየቁን፡፡ እኔ እና አናንያም ሁኔታውን በመረዳት 10፡00 ሰዓት ላይ በድጋሚ ቀጠሮ ይዘን ወጣን፡፡ በወቅቱም አንዷለም አንድ ቀልድ ፈገግ እያለ በመናገር አስቆን እንደነበረም አስታውሳለሁ፡፡
Andualem and Eskinder - Sateanw 1እኔና አናንያም ጊዜውን ለመጠቀም በሚል፣ ሽሮሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ወደሚገኘውና በዶ/ር ተስፋዬ ተሾመ ዋና ዳይሬክተርነት ወደሚመራው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አግባብነትና የጥራት ኤጀንሲ (Higher Education Relevance and Quality Agency) መ/ቤት በመሄድ ከህዝብ ግንኙነት ባለሙያው የምንፈልገውን የሰነድ እና የድምጽ መረጃ አገኘን፡፡ ከቀጠሯችን ቀደም ብለንም አቶ አስራት ቢሮ ደረስን፡፡ የአቶ አስራት ፊት ግን ጥዋት እንዳየነው አልነበረም፡፡ ደስ የማይል ስሜት አረብቦባቸዋል፡፡ ‹‹አንዷለምን እኮ ፖሊሶች አሁን ወሰዱት›› ብለው የሚያውቁትን ያህል ዘርዝረው ነበሩን፡፡ ‹‹ጥዋት ህጻን ልጁ ለመጀመሪያ ጊዜ ት/ቤት ገብቶለት ከሰዓት በኋላ ደስ ብሎት ከት/ቤት ሊያመጣው አቅዶ እንደነበረ ነግሮኝ፣ በጣም ያሳዝናል›› አሉ፡፡ እኛም በአቶ አስራት ቢሮ በጋራ አዘንን፡፡ በዚህ ደስ በማይልና ባልተረጋጋ ስሜት ውስጥ ቃለ-መጠይቁን ማድረግ በድጋሚ ሳንችል ቀረንና ከፓርቲው ቅጥር ግቢ ወጣን፡፡ ከቢሮው ጀምሮ እስከዋናው አስፋልት ድረስ ፊታቸውን ከስክሰው፣ ፈንጥር ፈንጠር ብለው በመቆም አካባቢውን በአይነ ቁራኛ የሚመለከቱ፣ በእኔ አጠራር ‹‹ተከታትሎ አደሮች›› ነበሩ፡፡ በዋናው የአራት ኪሎ መገናኛ መንገድ ዳር በሚገኘው ‹‹ፍሮስቲ ባርና ሬስቶራንት›› መግቢያ በር ጋር ቆሞ ከፓርቲው ቢሮ መውጣታችንን ያወቀው አንድ ጠቆር ያለ ‹‹ተከታትሎ አደር›› አፈጠጠብን፤ እኛም አፍጥጠን አጸፋውን መለስንለት፡፡ እርሱም ወዲያው አንገቱን ለማቀርቀር ጥረት አደረገ፡፡ [ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሰዎች ይገርሙኛል፤ ልባቸው በፍርሃት ውስጥ ሆኖ፣ ሰው እንዲፈራቸው የሚያደርጉት የደካማ ሥነ-ልቦና የትግበራ ሙከራቸው በጣም ያናድደኛል]
የእኔና አናንያ ቢሮ እዚያው ቤል-ኤር አከባቢ ስለነበረ ወዲያው ገባን፡፡ ሁሉም የጋዜጣዋ ባልደረቦች እስሩን ሰምተዋል፡፡ አቤል ዓለማየሁ፣ በዚሁ ቀን፤ ቀትር ላይ የዛሚዋን ሚሚ ስብሐቱ ‹‹እነአንዷለም ይታሰሩ›› የሚል ይዘት ያለው ‹‹የእስር ዋረንት›› ዘመቻዋን ካደመጠ በኋላ ከሰዓታት በፊት ለአንዷለም ስልክ ደውሎለት እንደነበረ በቁጭት ሲናገር አደመጥነው፡፡ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን መታሰርም በዚሁ ቢሮ ውስጥ ተረዳን፡፡ ሀዘን …ዝምታ …ቁጭት …ድጋሚ የሀዘን ስሜት ….ተፈራረቁ፡፡
የጋዜጣዋ ባልደረቦች፣ ኢ-መደበኛ ኤዲቶሪያል ስብሰባ አድርገን፣ በቀጣይ ዕትም ላይ ንጹሕ ወገኖቻችንን ዋጋ እያስከፈለ ስለሚገኘው የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ፊቸር ጽሑፉ እንዲደረግ ተስማማን፣ በቅዳሜ ዕትምም ተደረገ፡፡ ምሽት በሁለት ሰዓት ላይ፣ በቀድሞ የኢቴቪ ዜና እወጃ የአንዷለምንና የእስክንድርን የእስር ሁኔታ በፎቶ ግራፍ ተደግፎ ተመለከትን፡፡ ….
በነሐሴ ወር 2003 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር የወቅቱን የዓረብ ሀገራት አብዮት አስመልክቶ ሙያዊ ትንታኔ እንዲሰጠን እና ከዚህም አኳያ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ በእርሱ አተያይ ምን እንደሚመስልና ተያያዥ ሀገራዊ ጥያቄዎችን በማንሳት ከእኔ ጋር ሰፊ ቃለ ምልልስ አደርግን – በአራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል፡፡
እስክንድርን ቃለ-መጠይቅ እያደረኩለት ባለሁበት ወቅት፣ በዓለም ሀገራት ላይ ስለተደረጉ አብዮቶች አነሳስና ውልደት ታሪካዊ የዓ.ም ፍሰታቸውን ሳያዛንፍ ሲተነትን መስማቴ አስደምሞኝ ነበር፡፡ ቃለ-ምልልሱ አልቆ ቢሮ ገባሁና ወደወረቀት ላይ ልገለብጠው ስል የቃለ ምልልሱ ድምጽ የለም፡፡ በጣም ግራ ተጋባሁ፣ ከባልደረቦቼ ጋር ደጋመን ሞከርነው ግን ምንም የእስክንድር ድምጽ የለም፡፡ ለካ በስህተት ከባልደረባዬ ናፍቆት ዮሴፍ ጋር የማይሰራ መቅረፀ-ድምጽ መቀያየሬን ዘንግቼው ነበር፡፡ በጣም ተናደድኩ – መሰል ነገር በጋዜጠኝነት ሕይወት የሚገጥም ነገር መሆኑን ባውቅም፡፡ ከቢሮ ወጥቼ ተረጋግቼ አሰብኩ፡፡ ያን የመሰለ ቃለ-ምልልስ መቅረት የለበትምና በድፍረት ለእስክንድር እውነቱን ልነግረው ወስኜ ፡፡ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ቃለ-ምልልስ ካደረጉ በኋላ ድንገት መሰል ነገር መፈጠሩ ሲነገራቸው በጣም ይናደዳሉ፤ በድጋሚ ቃላቸውን ለመስጠት ፍቃደኛም ላይሆኑ እንደሚችሉ አውቃለሁ፡፡ እስክንድር ግን በጣም በሚገርም ደወልኩለትሁኔታ ሁኔታውን ተረድቶ በትህትና ‹‹መቼ ይመችሃል›› አለኝ፡፡ በጣም ደስ ብሎኝ በነጋታው ከሰዓት በኋላ እዚያው ቱሪስት ሆቴል ተቀጣጠርን፡፡
ቃለ-ምልልሱን ከመጀመራችን በፊት ወደእኔ ጠጋ አለና ‹‹ከጀርባህ ደህንነቶች አሉ፤ እነሱ መኖራቸውን ሳታስብ ጥያቄህን ጠይቀኝ›› አለኝ፡፡ ዞሬ አየኋቸው፤ ሁለት ናቸው፡፡ ሁለመናቸው እኛ ጋር ነው፤ እየታወቁም ፍጥጥ ብለው ሲያዩና ጆሯቸውን ሲቀርሱ ምንም እፍረት አይነበብባቸውም፡፡
ቃለ-ምልልሱ ሲጀመር ግን ረሳኋቸው፤ የእስክንድር ተመስጧዊ ትንታኔ ብዙ ነገር ያስረሳ ነበር፡፡ በመጨረሻም ደስ የሚል ቃለ-ምልልስ ከእስክንድር ጋር አደረግን፡፡ ‹‹በግሌ፣ ትንታኔህ በጣም ማርኮኛል፤ ከአንተ ጋር አንድ ቀን ተገናኝተን ካንተ ብዙ መማር የምፈልጋቸው ነገሮች አሉኝ›› አልኩት፡፡ ‹‹ኤልያስ እኔ ራሴ ካንተ ብዙ ነገር መማር እፈልጋለሁ፤ ደስ ይለኛል፤ ከአዲስ ዓመት በኋላ እንገናኛለን›› አለኝ በሚያስገርም ትህትና፡፡
መስከረም 02 ቀን 2004 ዓ.ም ለእስክንድር ደወልኩለት፡፡ ለመስከረም 05 ቀን ልንገናኝ ቀጠሮ ያዝን፡፡ ‹‹እንዲያውም አንተ ከፌዴራል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሊ ሱሌይማን ጋር ያደረከውን ሰፊ ቃለ-ምልልስ አንብቤ በአንድ ጉዳይ ላይ ጽሑፍ አዘጋጅቻለሁ፡፡ በባለፈው ዕትም ቃለ-ምልልሴ ስለወጣ ጋዜጣው ላይ በተደጋጋሚ ቦታ እንዳልይዝ ለቀጣይ እትም አደርሳለሁ›› አለኝ፡፡
ለኮሚሽነር አሊ ‹‹አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ከኢትዮጵያ የተመዘበረ 8.4 ቢሊየን ዶላር ገንዘብ ከውጪ ባንክ መገኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ስለዚህ ምን ምላሽ አለዎት? …ብሩ በኢትዮጵያ አቅም በቃላሉ የሚታይ ነው እንዴ?!›› የሚሉ ተከታታይ ጥያቄዎችን አቅርቤላቸው ነበር፡፡ ኮሚሽነሩም ‹‹ግድ የለህም …ይ…ሄ…ን…ን ከጥያቄህ ብታወጣ? ሌላ ዓላማ ስላለው ነው፡፡ ከሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (Money Laundry) ጋር አብሮ ተያይዞ የሚመጣ ነገር አለ፡፡ ለእናንተ ለሚዲያ የማይጠቅም ነገር ነው፡፡›› በማለትና ተጨማሪ ነገር መግለጽ ሳይፈልጉ የተዳፈነና የተድበሰበሰ መልስ ሰጥተውኝ ነበር፡፡ እስክንድር እንደነገረኝ ከሆነም፣ ከዚህ ጥያቄና መልስ በመነሳት፣ ይህ የተመዘበረ ገንዘብን በተመለከተ እና ኮሚሽነር አሊ ይህህን አስመልክቶ ለምን ለመመለስ እንደከበዳቸው የራሱን ምልከታ ለመግለጽ ነበር ጽሑፉን ያዘጋጀው፡፡ ግን ምን ያደርጋል በቀጠሯችን መሰረት ከእስክንድር ጋር ተገናንተን ሳንወያይ እና ጋዜጣዋ ላይ ሙስናን አስመልክቶ እንዲታተም ያዘጋጀውን ጽሑፍ ሳይሰጠኝ ነበር ልክ የዛሬ አራት ዓመት የበኩር ልጁን ከት/ቤት አውጥቶ ወደቤታቸው ሊሄዱ ሲሉ ነበር በግፍ በፖሊሶች የተያዘው! ልክ የዛሬ አራት ዓመት ነበር፣ ውድ ልጁን ከእጁ መንጭቀው በህጻን ልጁ ፊት የብረት ካቴና ያጠለቁለት! የአብራኩ ክፋይ የሆነው ናፍቆት እያለቀሰ ነበር ይዘውት ወደቤቱ ለብርበራ ያመሩት፡፡ አንዷለምም ቢሆን ት/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የገባለትን ልጁን እንደአባት ከትምህርት ቤት በደስታ ሊያወጣው እንደናፈቀ ነበር ወደማዕከላዊ የተላከው፡፡
እንግዲህ እንዲህ ነች ኢትዮጵያ ሀገራችን!!!
…..እናንተ የህሊና እስረኞች፡- አንድ ቀን ከእስር የምትፈቱበትንና ከውድ ቤተሰቦቻችሁ እና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የምትገናኙበትን ቀን እሻለሁ!!!
በእስራችሁ ሳቢያ ከባድ ዋጋን በመክፈል ላይ ለሚገኙት ውድ ቤተሰቦቻችሁም በሙሉ፣ ፈጣሪ ይበልጥ ውስጣዊ ጥንካሬን ይስጣቸው፤ ተስፈኛም ሁኑ እላለሁ!!!

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/10531#sthash.iy2IbPKr.dpuf

የኛ ሃብታሞች ምን ነካቸው? – ከተማ ዋቅጅራ

እኔ የምለው ጥቁር ጣልያን ነው እንዴ የሚገዛን?

Ketemaመቼም በዚህች ምርድ ላይ ሃብታም ሆኖ መኖር የማይፈልግ የለም። በሃብት ቁንጮ ላይ ለመቀመጥ የማይጥር የለም። ታዲያ የሮጠ ሁሉ አንደኛ እንደማይወጣ ሁሉ ቢሊዮነር ሆነው የሚታዩት ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ የአለማችን ቢሊዮነሮች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ላይ ቅድሚያ እንዲጠቀም ወይም መጥቀም የሚፈልጉት የራሳቸውን ዜጋ ነው። የአገራቸው ዜጋ ፍላጎቱ ከተሟላ ወይም ከበቂ በላይ የሚሆን ምርት ካመረቱ ወደ ሌላ አገር መሸጥም ሆነ መርዳት ይጀምራሉ። ይህ በአብዛኛው  አገራት የሚሰራበት አሰራር ነው። አንድ ባለሃብት  የሚያመርተው ምርቱን ቅድሚያ ለአገሩ ማዋል ግዴታ አለበት ለህዝቡም በቂ ምርት ማቅረብ ከተቻለ እና ትርፍ ሆኖ ከተገኘ ወደ ውጪ መላክ አንድ አገሩን እና ህዝቡን ከሚወድ ዜጋ የሚጠበቅ ነው። ታዲያ የኛ ሃብታሞች ምን ነካቸው?

ኢትዮጵያ ውስጥ የኑሮ ውድነትን የፈጠሩት መንግስት ያደራጃቸው የምንግስት ባለስልጣናት አብሮአቸው ከሚሰራው ልማታዊ ባለሃብቶች ለህዝባችን ማሰብ ባለመቻላቸው ከፍተኛ የሆነ እራስ ወዳድነት እና እራስን ለጥቅም አሳልፈው የሰጡ በመሆናቸው ነው።

የኢትዮጵያ ባላሃብቶች ከጥቂቱ በስተቀር ወደ ቢዝነስ ውስጥ ሲገቡ ህዝብን ለመጥቀም የህዝብን ኑሮ ለማሻሻል ሳይሆን በቀላሉ ትርፋማ ሆኖ ሚሊዮነር መሆን የሚችሉበትን መንገድ በቀላሉ ገንዘብ ማግኘት ወደሚችሉበት ያቶኩራሉ።

ባላሃብቶቹ ወደ ቢዝነሱ ከመግባታቸው በፊት እያንዳንዱ ባለሃብት  ከአንድ ባለስልጣን ጋር መጣበቅ ግድ ይላቸዋል ካለበለዛ ግን ማነቆዎቹ ብዙ ስለሚሆኑ አገር ጥሎ መውጣት ካልሆነ በቀር በአገሩ ውስጥ በነጻነት የመስራት መብት አያገኝም። የዱባዬ አገር ህግ አንድ የውጪ ዜግነት ያለው ባለሃብት የቢዝነስ ተቋም በዱባዬ ለመስራት ቢፈልግ ከአንድ ዱባዬ ዘግነት ካለው ሰው ጋር መሆን አለበት ካለበለዛ ግን ምንም አይነት ስራን ማከናወን አይቻልም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ዜጋችን እንደ ውጪ ዜጋ ተቆጥሮ ስልጣን ላይ ካሉት አካል ጋር ተጣብቀህ አብሮ ካልሆነ በስተቀር ልማታዊ ባለሃብት መሆን አይቻልም። ታዲያ ኢትዮጵያ ማለት የነእንትና ቡድን ናት ማለት ነው እንዴ? በአንድ ወቅት የጣልያን ማፍያ ቡድን በጣም ተጠናክረው ጣልያን ውስጥ ያለውን ትላልቅ ቢዝነሶችን በሙሉ በነሱ ስር ካልሆነ በስተቀር መንቀሳቀስ ወደማይቻልበት ደረጃ አድርሰውት ነበረ በኋላ ግን የጣልያን መንግስት ጠንካራ እርምጃ በመውሰድ ነገሮችን ሊያስተካክል አድርጓል። ዛሬም ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለው ይሄ ነው። የኛዎቹ ከጣልያን ማፊያ የሚለዩት በመንግስት ደረጃ የተደራ ዘራፊዎች መሆናቸው ነው።

ህዝብን የሚጎዳ ባለሃብትም ይሁን ህዝብን የሚጨቁን መንግስት በኢትዮጵያ ይኖር ዘንድ አይገባም። ባለሃብቱም መንግስትም ዘላለማዊ  በሚመስልቸው ጥቅም ውስጥ የተቀመጡ ቢመስላቸውም ቅሉ ሃብትም ይጠፋል ስልጣንም ይሻራል ህዝብ ግን ሁል ግዜ ኗሪ ነው። ህዝብን እያስራቡ ሃብታም ለመሆን ከመጣር ህዝብን እየረገጡ ስልጣን ላይ  ለመቆየት ከማሰብ ትቆጠቡ ዘንድ ግድ ይላችኋል። ነገሮች እንዳሉበት ይቀጥላል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ሁኔታዎች ሲቀየሩ የናንተም እጣ ፈንታ አደጋ ውስጥ ነውና ከወዲሁ ስለ አገር ክብር  እና ስለ ህዝብ ፍቅር አርቆ ማሰብ ብልህነት ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝባችንን በማስራብ በቀላሉ መመገብ የሚችላቸውን ምግቦች በማስወደድ የውጪ ዜጋን በመመገብ ስራ ላይ የተሰማራቹ ልማታዊ ባለሃብቶች ለህዝባችን በማንኪያ ህዝባችን ላልሆኑት ደግሞ በጭልፋ በማቀበል ዶላር ቆጠራ ይቁም።

የእንስሳት ስጋን ወደ ውጪ በመላክ የተሰማራችሁ ፣ በጥራ ጥሬ እህሎች ላይ፣ የቅባት እህሎች ላይ፣ ፍራፍሬ ምርቶች ላይ፣ የቅባት እህሎች ላይ የተሰማራችሁ ባለሃብቶች ህዝባችን ላይ በእለት ከእለት በሚመገባቸው ምግቦች ላይ የዋጋ ውድነትን በማምጣት ኑሮውን ያከበዳችሁት  እናተው ስለሆናችሁ በእንደነዚ አይነት ስራ ለይ የተሰማራችሁ ሰዎች መጀመሪያ ህዝባችንን መመገብ ከዛም ለህብረተሰባችን በቂ ምርቶችን ማቅረብ ቀጥሎም የሚያስፈልጉትን ነገሮች ቅድሚያ ለአገርሬ ሰው ማቅረብ ይገባችኋል እንጂ በበቂ ሁኔታ ህዝባችን ሳይዳረሰው ወገባችሁን ታጥቃችሁ  ውጪአዊያኖችን ለመመገብ ስራ ላይ የተሰማራችሁ ባለሃብቶች ከዚህ ድርጊታችሁ ተቆጥባችሁ ቅድሚያ ወገንን ወደመመገቡ ስራ በመግባት የስራ ዘርፋችሁን ትቀይሩ ዘንድ ግድ ይላችኋል።

የስጋ ተዋጽኦ ወደ ውጪ ከመላኩ በፊት የአንድ ኪሎ ስጋ በኔ ከስምንት አመት በፊት 20 ብር ነበረ አሁን ግን የሙክት በግ ዋጋ ደርሷል። አንድ በግ ከፍተኛው ዋጋ 500 ብር ሲሆን አሁን ግን 5000 ደርሷል። አንድ በሬ በፊት ከፍተኛው 5000 ሲሆን አሁን ግን  40.000  ደርሷል። ይህም የሆነበት ምክንያት የስጋ ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ውጪ በመላክ በህዝባችን ላይ ለፈጠረውን የዋጋ ውድነት እና የኑሮ  ቀውስ ተጠያቂ ያደርጋችኋል።ስጋ ላኪ ድርጅቶች የሚገበያዩት በዶላር ስለሆነ የዋጋ መናርን ቢያመጡም መንግስት ምንም አይጠይቃቸውም ምክንያቱም መንግስት ዶላሩ ይምጣለት እንጂ ህዝባችን ስጋ ቢበላም ባይበላም ቢወደድበትም ባይወደድበትም ግድ የለውም። ከመንግስት አካሎች ጋር በመጣበቅ እራሳችሁን ሚሊዮነር በማድረግ ስራ ላይ የተሰማራችሁ ልማታዊ ባለሃብቶች ህዝባችን ከሚጎዳ ስራ ትታቀቡ ዘንድ ግድ ይላችኋል።

በጥራጥሬም ዘርፍ የተሰማሩ እንደዚሁ ነው። የጥራጥሬን እህሎች በቀላሉ ከገበሬው በመግዛት በሰሩት ትላልቅ መጋዘን ውስጥ በማጠራቀም ለውጪ ሽያጭ ያውሉታል። በፊት አንድ ኪሎ ምስር 2 ብር ገዝቶ ይመገብ የነበረው ህዝባችን ዛሬ 60 ብር ሆኗል።  ከውድነቱ የተነሳ ምስርን እንደ ስጋ ጣል ጣል አድርጎ የሚመገቡ የህብረተሰባችን ክፍሎች በጣም ብዙ ናቸው። በመንግስት ድጋፍ ጥቂት ሚሊዮነሮችን ለመፍጠር አገርን ማስራብ ገዚው መንግስት ለህዝብ ያለውን ጥላቻ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነውና ህዝቤ ሆይ በህዝብ ሃብት እና ንብረት የሚቀልዱትን አንባ ገነኖችን ሁሉ ለፍርድ ለማቅረብ በህብረት በመሆን ለነጻነትህ፣ ለክብርህ፣ ለህልውናህ፣ የምትታገልበት ግዜ ነውና ቆርጦ መነሻው ሰዓቱ አሁን ነው። ካለበለዛ 60 ብር የነበረው ምስር አይናችን እያየ በቅርቡ 100 ከዛም 200 ብር ይገባል። የህዝባችን ሃዘን ለገዚዎቻችን የደስታ ዜማ መሆኑን አትርሱ።

ከየአንዳንዱ ባለ ሃብት በስተጀርባ የባለስልጣናቱ ጥምረት እንዲኖር የተፈለገበት ዋናው አላማ በስልጣን ላይ ያሉት አካላት የኢትዮጵያን ሃብትና ንብረት በነሱ ስር ካልሆነ በስተቀር በየትኛውም የቢዝነስ ስራ ውስጥ መሳተፍም ሆነ መስራት አይችልም የሚል የጥቂቶች የማፍያ ድርጅት መመሪያ ስላለ ነው። በነጻነት ስም አገርን ለመዝረፍ ተደራጅቶ ጫካ መግባት ቢያሳፍርም ቅሉ የኋላ ኋላ የዘረፉትን የሃገር ሃብት ሳይበሏት ዋጋ የሚከፍሉበት እንደሆነ ብናውቅም ከነዚህ ጥቂት የአገር  ንብረት ዘራፊ ጋር ተጣብቀው የህዝብን ኑሮ የሚያውኩ ባላሃብቶች የሚንቀሳቀሱት በህግ መሰረት ሳይሆን አብሮት ከተጣበቀው ባለስልጣን ህግ መሰረት ነው። በኢትዮጵያ በስራ ላይ የተሰማሩትን ባለ ሃብት የመቆጣጠሩ ስራ አብሮ ያለው ባለስልጣን ድርሻ ነው። የኢትዮጵያ ህግ እነሱን አይመለከታቸውም። ባለሃብቱ ከተሰመረላቸው መስመር ፈቀቅ ካሉ ሙስና የሚል ህግ ይመዘዝባቸውና ወደ እስር ይወረወራሉ ከመስመሩ ካልወጡ ግን የኢትዮጵያ ህግ በነሱ ላይ አይሰራም።

አንድ ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው ባለሃብት ያመረታቸውን ምርቶች መኪናዎቹ  ከሚችሉት አቅም በላይ ጭኖባቸው ሲሄድ ኬላ ላይ ይያዛል የኬላ ሰራተኞችም እንደዚህ ጭነህ ማለፍ አትችልም መኪናዎቹ ከሚችሉት አቅም በላይ ተጭኖባቸዋል ስለዚህ አደጋ ሊታደርስ ትችላለህና ህግም ተላልፈሃልና ትቀጣለህ በተጨማሪም ትርፍ የጫንካቸውን አውርደህ ነው ማለፍ የምትችለው ይሉታል። የዚህን  ግዜ ባለሃብቱ በጣም በመናደድ እንዴት ደፈራችሁኝ አታውቁኝም እንዴ እያለ ከህግ በላይ መሆኑን ሊያሳያቸው ህግ እሱጋር እንደማይሰራ ሊነግራቸው ስልክ አውጥቶ ይደውልና ትንሽ ካወራ በኋላ ለኬላ ሰራተኛ አላፊ ስልኩን ይሰጠዋል የኬላ ሰራተኛውም ስልኩን ካናገረ በኋላ ስልኩን ለባለሃብቱ ይመልስለትና ሰላምታ በመስጠት ይቅርታ ጠይቆት ማለፍ እንደሚችል ይነግረዋል። ባለሃብት የደወለው አብሮት ከሚሰራው ባለስልጣን ጋር ነው። ለኬላው ሰራተኛ የተናገረው የማይመለከትህ ጉዳይ ላይ አትግባ ካለበለዛ ትወገዳለህ የሚል ነበረ። ከጥቂትም ሰዓት በኋላ መኪናውን የሚያጅቡ የታጠቁ ሲብል ለባሽ በላንድክሩዘር መኪና መጥተው አጅበውት ዬዱ። እየተሰራ ያለው እንደዚህ ነው ህግ አይሰራም በየመስራቤቱ ትክክለኛ ስራን የሚሰሩ ሰራጠኞችን ከበላይ ቀጭን ትዛዝ በመስጠት በአገሩ ለአገሩ በትክክለኛ መንገድ እንዳይሰራ እያሸማቀቁ ሌባና ቀማኛ የበዛባት አገር እንድትሆን እየሰሩ ያሉት ጥቂቶች ናቸው። ጥቂቶችን ለማኖር አገርም ሆነ ህዝብ ቢጠፋ ግዴ  በሌላቸው ሰዎች ኢትዮጵያ እየመሯት እንዳለ የምናይበት ነው።

የውጭ መንግስታት ሆኑ ባለሃብቶች ከማንኛውም በፊት ቅድሚያ ለህዝባቸው ነው የሚሰጡት። የህዝባቸውን ፍላጎት ለማሟላት የአገራቸው ምርት አናሳ ሆኖ ካገኙት ከውጪ በመግዛት የህዝባቸውን ፍላጎት ሊያሟሉ ይጥራሉ። የኛዎቹ መንግስትና ባለሃብት ደግሞ የውጪ አገር ፍላጎትን ለማሟላት ህዝባችንን ያስርባሉ። ተገላቢጦሽ ማለት ይሄ ነው። እኔ የምለው ጥቁር ጣልያን ነው እንዴ የሚገዛን?።

የኛ ባለሃብቶች መጀመሪያ አእምሮአችሁን ቀይሩት ለወገንና ለአገር ማሰብ የሚችል አድርጉት ለጥቅማችሁ እና ጥቂቶችን በመታዘዝ መኖራችሁን አቁሙ ወደ  ውጪ ከመላካችሁ በፊት ቅድሚያ  ለህዝባችን በበቂ ሁኔታ  የምግብ ፍላጎቶች ተሟልቷል ወይ ብላችሁ ፍላጎቶችን ለሟማሟላት ጣሩ የህዝብን መሰረታዊ የምግብ ፍላጎት ከተሟላ በኋላ ከህዝብ የተረፈው ወደ ውጪ በመላክ ስራ  ውስጥ እንድትሰማሩ የንጹሃን አእምሮ ባለቤት፣ አገር የመውደድ ሃሳብ፣ ህዝብን የማፍቀር ልቦና፤ ሊኖራችሁ ግድ ይላል። የህዝብ መሰረታዊ የምግብ ፍላጎት ሳይሟላ ከህዝብ ጉሮሮ ላይ እየነጠቃችሁ ጥቂቶችን የማኖር ስራ እና የውጪ አገር ዜጋ የመመገቡ ሁኔታ በአፋጣኝ መቆም አለበት። በኢትዮጵያ ውስጥ በምግብ ውጤቶች ላይ ዋጋው እንዲንር በማድረግ  እናንተ እና የናንተ አዛዦች  ተጠቃሾችም ተጠያቂዎችም ናችሁ።

ከተማ ዋቅጅራ

29.09.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47002#sthash.Mb52Yocv.dpuf