ማስተዋል። (ሥርጉተ ሥላሴ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 30.09.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

አትቀመሽ – ኃይለኛ ነሽ። …..

አትጠጪ – መራራ ነሽ። …….

አትዋጭም – ጎምዛዛ ነሽ፤

አፈ ታሪክ እልም – አይደለሽ። …..

ቁልጭ ብለሽ  – ትታያለሽ፤

እውነት ደፋር ካላገኘሽ፣

ቃና የለሽ ትሆኛለሽ። ሽሽሽ-ሽሽሽ-ሽሽሽ-ሽሽሽ-ሽሽሽ ……

ሰላም ነው – እንዴት አላችሁልኝ – ክብረቶቼ? ደህና ናችሁ ወይ?

ሰንበትን ተንተርሶ የትንቢቴን ፍጻሜ – እያያችሁ፤ ልዑቅ በሉኝ ሲል ሌላም፤ በሰው ልጆች በመኖር ሂደት ውስጥ ስለሚፈጠሩ ገጠመኞችም ሟርትን በመመኘት፤ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ – አስነብቦናል። መርመጥመጥ። የሆነ ሆኖ ባላገኛቸው ህልሞቹ – የቁራኛ እስረኛ ዕሳቢዎቹ ዙሪያ ትንሽዬ ነገር ማለት – እሻለሁ።

Neamen zeleke zehabeshaየተከበሩ አቶ ነአምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት 7 የዓለም አቀፍ አመራር፤ የውጪ ግንኙነት ኃላፊና የንቅናቄው የምክር ቤት አባል፤ የዘመቻ እንቅስቃሴያቸውን አስመልክቶ ብዬም ነበር ዓይነት ነው። እንዲህም ይለናል እኛንም አክሎ … ይወርፈናል፤ „ተመላሹ  ታጋይ የኢሳት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የአርበኞች ግንቦት ሰባት የውጪ ጉዳይ ሃላፊ፤ ጓዜን ጠቅልዬ ለትግል ገባሁ ብለውን በሰበር ዜና ሰምተን ነበር። ሰው፤ ምነው ለድል ሳያበቁን ተመለሱ ብሎ ህዝቡ መጠየቁ አይቀርምና፤ አስቀድመው በየሜዲያው ላይ፤ ወከባ መፍጠር ተገቢ መስሎ ታይቷቸዋል። “ጉሮ ወሸባዬ ባልዘፈንሽ፤ ዘንድሮ ባላፈርሽ” ይላል የአገሬ ሰው። ምናልባት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች፤ በራሳቸው ፈቃድ፤ ይሸወዱ እንደሆን ነው እንጂ፤ የሚዲያ ወከባው፤ በነቃው ሕ/ሰብ ዘንድ ውኃ አልቋጠረም ። ዛሬ ሰው ፤ እንደ ድሮው ዝም ብሎ “ይሁን እስቲ” እያለ ማለፉን ትቶታል ። መጠየቅ ጀምሯል ። እኔም እንዲሁ አንዳንድ ጥያቄዎችን ላነሳ ነው ። በአሜሪካ ድምፅ ከተላለፈውም ሆነ ፤በኢሳት ተደረገ፤ ከተባሉት ቃለ-መጠይቆች፤ ባዶ የሆኑትን ስሜት የማይሰጡ፤ አባባሎች ትቼ፤ የተወሰኑ ነጥቦችን ቀጥዬ አነሳለሁ።“

„ምናልባት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች፤ በራሳቸው ፈቃድ፤ ይሸወዱ እንደሆን ነው እንጂ፤“ ይሄ ነው መነሻዬ። ስለምን እንሸወዳለን? የራሳችን ጌቶች እራሳችን መሆናችን ብቻ ሳይሆን፤ መነሻችንም፤ መድረሻችንም በበቀልና በጥላቻ ያልበከተ፤ ለመርህ የሚገዛ ህሊና ስላለን ጊዚያዊ ወጀብ ወይንም አውሎ ከዓላማችን ንቅንቅ – አያደርገንም። ወይንም በፋሻ ተጠቅልለን የግል ኢጓ ገመናችን እንደ ቄጤማ -አንነሰንስም። ቋሚ ፍላጎት አለን። ጽላታችን ከፋሽቱ ህወሓት የምትላቀቅበት ማናቸውም መንገድ ውስጣችን ነው። ለበጎ ነገሮች – ለአዎንታዊ ጠረን ብቻ መፈጠራችነን አስምረን – እናውቃለን። „አቤቱ ንፁህ ልብን ፍጠርልኝ፤ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ  አድስ።“ (መዝ ምዕራፍ ፶ ቁ. ፲ ) የህይወት ዘመናችን ሰማያዊ መርህ ይህ ነው፤

የማከብራችሁ  – ናፍቆቶቼ የእናት ኢትዮጵያ ልጆች። „ባዶ“ የተባለውን የጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ስላቅን – እንዲህ ከመሰረት ብነሳ የተሻለ ነው። በጥልቀት ሳይሆን በጫፍ እጅግ በስሱ ንድፈ ሃሳብ ትንተና ነገር ….

ድርጅት ማለት ምን ማለት ነው? ድርጅት ማለት – ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ወይንም ስብስቦች፤ በፍላጎታቸው ወይንም በዓላማቸው ወይንም በእምነታቸው ዙሪያ የሚሰባሰቡበት የሰዎች ማህበር – የወልዮሽ ማእከል ሲሆን፤ ጊዜያዊ ወይንም ቋሚ ሊሆንም ይችላል። ድርጅት አጭርና ረጅም ራዕዮችን ለማሳካት የሚያስችል ተቋም፤ አሰባሳቢ ማእድ ነው። ሰብሳቢም ነው።

በተለይ የፖለቲካ ድርጅት ከሆነ ሰፊ ህዝባዊ ኃላፊነትን ወስዶ – ይደራጃል። ስለሆነም የፖለቲካ ድርጅቶች መሰረታዊ ሰነዶቻቸውን መሰረት ያደረገ መርኃ ግብር አላቸው። አካሎቻቸው የሚፈጠሩትም በአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ነው። በየደረጃው የሚካሄዱት ጉባኤዎች ምክር ቤታቸውን ይመርጣሉ። ምክር ቤቱ ደግሞሥራ አስፈጻሚውን ይመርጣል።

ተግባራቸው — ጉባኤው እስኪሰበሰብ ድረስ ምክር ቤቱ የጉባኤውን ኃላፊነት ወስዶ – ይሰራል።፤ ምክር ቤቱ እስኪ ሰበሰብ ድረስ ደግሞ የድርጅቱን ዕለታዊ ተግባሩን የሚከወነው ሥራ አስፈጻሚው ይሆናል።

የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቲው የበቃ ውክልና ስላለው፤ የድርጅቱ አካላትን ሆኑ አባላትን እንደ የኃላፊነታቸው – ይደለድላል፤ ያሰማራል፤ ተግባራቸውን – ይገመግማል፤ ተጨማሪ ኃላፊነቶችን – ይሰጣል። በፈለገው የግዳጅ መስመር – ይልካል። የፓርቲ አባላትም በየደረጃው ያሉ አካላትን በመብታቸው ተጠቅመው በፈቃዳቸው እንደ መረጡ ሁሉ፤ ለመረጡት አካላት የስምሪት ድርሻን በውዴታ ተቀብሎ ኃላፊነትን የመወጣት ግዴታ – ይኖርባቸዋል። መብትና ግዴታ ተግባር ላይ በዚህ መልክ ኪዳን – ያስራሉ።

እና ለእኔ የአቶ ወንድም የትንተና አግባብ – የፓርቲ የአደረጃጀት መሰረታዊ መርህን ካለማገናዘብ የመጣ ነው። በተጨማሪም ዘመኑ 21 ኛው ምዕተ ዓመት ላይ ነን። የሰለጠኑ ሂደቶች እንዲስተናገድባቸው ግድ ይላል። ሰው አልባ አውሮፕላን የግዳጅ ስምሪትን እያዬን እኮ ነው። ሥልጣኔው በራሱ ከዴሞክራሴያዊ ፍላጎት አፈጻጸም ጋርም በመስተጋብር የተቃኜ ነው። ይህም ብቻ አይደለም፤ ስለ አርበኞች ግንቦት 7 መሪዎች የተግባር ስምሪት ቀዳሚ መረጃ ለማግኘት አቅሙ – አይፈቅድም። በፓርቲው ውስጥ እሱ እራሱ ጋዜጠኛው የለም። በይሆናል እና በነሲብ ደግሞ የፓርቲ መርህ እንዲህ ለቡና ተርቲም – አይደፈርም። ስለዚህም እንደ ማንኛውም ዜጋ እኩል ሁሉ የሚሰማውን ብቻ መስማት ግድ ይላል። በሌላ በኩል የነፃነት ትግል የሠርግ ርችት የሚተኮስበት – አይደለም። እንደ ቄጤማ የአካላቱ ስምሪትም አይነሰነስም። መራር ትግል – ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ዲስፕሊንን – ይጠይቃል።

ከሁሉ በላይ እንደ ቀደመው ጊዜ የፍንጪ ቧንቧው አይገኝም – ተከርችሟል። እስከ አሁን የተከፈለው መስዋእትነት – ይበቃል። የኢትዮዽያ ህዝብ አርበኞችና የግንቦት ውህደቱ ይህን ሁሉ እምስ ፍላጎቶችን – አምክኗል። ለዚህም ነው ነጋ ጠባ ሥጋ እንደ ተቀማ ሥጋ በይ እንሰሳ ጉምጅቱ በብራና እና በብዕር ላይ ሲደፋ የምናዬው፤ የእንብርክክ – የሚያስኬደውም፤ ለዚህም ነው በመደዴና በድንብስ ታቱ – የሚባላው። የባላደራው ራዕይ እንደ ቀደመው ጊዜ – እንደ ረጋ ኩሬ ባለህበት እርገጥ ዛሬ የለም። እያንዳንዷ ማዕልት በቅኔ ጥልፍ የተቃኘች ስለሆነች፤ ከፍጥነቱ ጋር ለመጓዝ ነሲብ የሙጥኝ ማለት ግድ – የሆነውም ለዚህ ይመስላል። ሰረገላው ባለቤት አለው። ገና ምን ታይቶ። የአፍሪካ ቀንድ የፍቅር ናሙና ቀንዲል – ትሆናለች። ምእራቡ ዓለም ይሁን የኤርትራ መንግስት ፋሽስቱን ህወሃትን ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን፤ የነገውን የተረጋጋ ሥርዓት ለመዘርጋት በሰፊ ትእግስት የጠበቁትን፣ የተመኙትን አግኝተዋል –  ብየ አስባለሁ – እኔው። ህልሙ ያልተሳካለትም አቅሙን – ይጠይቅ። የአቅሙ ምጣኔ – ኮከብ ቆጣሪ ሳይጠይቅ  – ደረጃውን ይነግረዋል። ምን ያህል ተጉዞ  – ምን እንዳተረፈ?

አርበኞች ግንቦት 7 ተገብቶ የተፈለገው መረጃ ተዝቆ የሚወጣበት – አይደለም። አመሰራረቱ፥ የአትኩሮት መሰረቶቹ መርኽ  ከወትሮው እኛ ከምናውቀው ሆነ ከተለመደው የተለየ ነው። ስለሚጠጥርም ነው ወደ ትችቱ የሚዘነበለው። ፍልስፍናው እረቂቅ፤ በእውቀትና በብቃት የተገነባ ነው። ልምዱም ተመክሮውም በአዲስ የአስተሳሰብ ዲዛይን እንደ ራሳችን ሆኖ፣ ለነባር ድክመቶች በር ዘግቶ ከአዲሶችም ለመማር ፈቅዶ ነው  – የተፈጠረው። ማስተዋል። ለአዲሱ ሥልጡን ዘመን በተወሳሰበ ችግር ለማለፍ ብልህና ጥንቁቅነትን – ያስቀደመ። ማስተዋል። በእጁና በመንፈሱ ያለውን ስለሚያውቅም ነው ለተረት ተረቶች መልስ ሰጥቶ ደረጃውን ዝቅ የማያደርገው። ማስተዋል። ለዚህም ነው ለንቅናቄው አክብሮትን መንፈሳችን አብዝቶ የሚለግሰው። ጥቂቶች ደግሞ አዳዲስ ጠቃሚ ግኝቶችን እንደ መፍትሄ አመንጪ ሳይሆን፤ እንደ አንጡራ ጠላት በማዬት፤ አቅም ማጠሩ የብጭት እስረኛ ሲያደርጋቸው የሚታዩትም በዚህ ምክንያት ነው።

የተከበራችሁ የጹሁፌ ታዳሚዎች – ታስታውሱ እንደሆን ኤርትራ የገባው የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ መሪ አካል፤ በአርበኞች ካንፕ ተገኝቶ ባደረገው ንግግር የአቶ ነአምን ዘለቀ ቃል ጭብጥ እንዲህ ይል ነበር „ውጪ የሚገኘው ወገናችሁ ድጋፉ እንደማይለያችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።“ ይህ ማለት አቶ ነአምን ዘለቀ ይህን ሀገራዊ ኃላፊነት መውሰድ የሚችሉ ስለመሆኑ ይገልፃል። ለዚህ ቃል ጠንቋይም መጸሐፍ ገላጭም – አያስፈልግም። በኪዳኑ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ክቡርነታቸው እንዳሉበት፤ በኤርትራ ቋሚ ቆይታ እንደለላቸው – ይገልጣል። አንድን ሃሳብ ለዛውም የፖለቲካ ንግግር እንደ ወረደ – አይተረጎምም። ፈልፈል አድርጎ እያገላበጡ በቅንነት መመርመር – ያስፈልጋል። ይሄን ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ አላዳመጠውም። ወይንም ንግግራቸውን ለመረዳት አልቻለም ማለት ነው።

ለማንኛውም ይህ ገለጻ በቀጥታ ውጭ ባለው ተግባር ላይ እንደሚያተኩሩ፤ እድምታው ካለ አስተርጓሚ – ያብራራል። እንዲያውም ከሀገረ አሜሪካ ነቅለው እንዲወጡ አስደረግናቸው የተባለው ዜና ነው  „በሬ ወለደ“ የሚያሰኘው። ከዚህም በተጨማሪ ሌላም አመክንዮ ልከል፤ ፓርቲያቸው የመደባቸው ቦታና ድርሻቸው „የውጪ ግንኙነት ኃላፊ“ ይሄ ነው።

ይህ ዓለምአቀፋዊ ኃላፊነት ኤርትራ መሬት ላይ ተሁኖም  – አይሰራም። አቶ ነአምን ዘለቀ ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት የግድ ነው ወደ አሜሪካ መመለስ፤ ነገም ቢሆን ወቅቱ እንደሚጠይቀው ኃላፊነት ፓርቲው አካሎቹን ሊያንቀሳቅስ – ይችላል። በፈለገው ቦታና ጊዜ፤ በሚገጥመው አወንታዊ ሆነ አሉታዊ ተጨባጭ ሁኔታ የፈለገውን እርምጃ – ይወስዳል። ኮከብ ቆጣሪ – አያሻውም።

ወገኖቼ ጠቃሚው ነገር በልካችን „ልክ“ ሙያችን ለማስከበር መጣር ብልህነት – ይመስለኛል። ጎንደሬም ሲተርት „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላል። ቅን ወገኖቼ – የሀገሬ የኢትዮጵያ ልጆች እውነቱ ያለው ከፖለቲካ ድርጅቱ ከንቅናቄው ከመርኹ እንጂ ከቂምና ከጥላቻ ማሳ አይደለም። ቀረብ ብላችሁ የቆዩትን የምስረታ ንጥር ሂደቶች መልሳችሁ፣ መላልሳችሁ ስታዳምጡት ብልሃቱ  – ያስተምራችኋል። ከሽሽትም – ይታደጋችኋል።  እድሜ ያላስተማረው አልቃሻ ፍላጎት ጸጸትን አዝሎ – ይኖራል። ጊዜን ያላዳመጠ ስብዕና ማለቁን የሚያውቀው ከሹልከቱ በኋላ ነው።

አንዲት የመጨረሻ ብልህ ነገር፣ ልባም ግን የተመሰጠረች ነገር ላንሳ፤ ታስታውሳላችሁ አይደል? በውጭ ሀገር የሀገር ውስጥ ሰላማዊ ትግሎችን ለማገዝ ሆነ ለርዳት ስለሚደራጁት፤ በሀገር ቤት ላሉት ሁለገብ እንቅስቃሴው የውጭ ሀገሩ የሥነ – ልቦና እስረኛ ወይንም ጥገኛ ያደርገዋል። ፍላጎቶቹ በጫና የተወጠረ ነው። የሉዓላዊ ልዕልናው ነፃነቱ በስውር የታፈነ ነው። የኢኮኖሚ አቅም ጥገኝነቱ መብቱን – ይጫነዋል። እንደልቡ አያንቀሳቅሰውም ዋ፥ ሱ ስለሚባል ለብዙ ነገር የተጋለጠ ነው። የጥቅሙን ያህል ጉዳቱም ያን ያህል ነው። እርግጥ እነ ቅንዬ ሊኖሩ ይችላሉ፤ ቅኖች ግን ጥቂት ናቸው። በአርበኞች ግንቦት 7 ግን የጥፋቱ በሽታ ሁሉ አይደገምም። ስለምን? ማርከሻው በመዳፉ ውስጥ ነውና። አርበኞች ግንቦት 7 ሌላ ቅጥልጥል ቻፕተር – አላስፈልገውም። የእራሱ አካል ይህንን የውጭ ሀገሩን ተግባር በኃላፊነት – ይከውናል። መደበኛ ሥራው ነው። ሽክፍ ያለ – ትጥቁ ያማረ – ስንዱ። ማለፊያ። ልባም የተመክሮ – ተቋም።

አንዲት መሸብያ አመክንዮ ልከል – አቶ ነአምን ዘለቀ የአባቱ ታሪክ አስከባሪ ልጅ ፤ የጀግኖች ቁንጮ – ልዕልት ኢትዮዽያ በ100 ዓመት ከማታገኛቸው በኢትዮዽያ የባህር ኃይል ታሪክ ጉልላተ – ጀግና የሆኑት የኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ ልጅ እኮ ነው። ኧረ ቀልድ – ይቁም። ወጣቶች – የእኔ ውዶች የለጠፍኩላችሁን – የውስጣችን ታሪክ ነበብ አድርጉና፥ ትናንትና ዛሬን የጀግናውን የአብራክ – መንፈስ ቃኘት – አድርጉት፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ አለ ከእኛ ጋር የጀግና – ጠረን። ታሪክ የጨዋታ ማሟያ አይደለም፣ ለባለ – ህሊናዎች። http://www.abugidainfo.com/index.php/9920/

ክወና – የማከብራችሁ የጹሁፌ ታዳሚዎች፥ ለኢትዮዽያ ህዝብ መልካም ዜና፣ የተስፋው ማህደር ነውና፤ በተስፋው ላይ የጉሮሮ አጥንት የሆኑ ዕሳቤዎችን መዋጋት የተግባራችን ሁሉ አህዱ ሊሆን  -ይገባል። ዛሬ አንድ በረሃብ የተጎዳ ወገናችን መልካም ሰምቶ ደስ ብሎት ሲተኛ፥ ላይመለስ ሊያሸልብ – በዛው እንደ ተኛ ሊቀር ይችላል። የዛች ቅጽበት ደስታውን እንደ ሰነቀ እንዳያልፍ፥ ይህ እንኳን ረመጥ የሆነባቸውን፤ አንደበቶች ሆኑ ብዕሮችን ልንታገላቸው – ይገባል። ለተስፋ ቀማኛ ርህርህና ወንጀል ነው። ተስፋ ለተስፈኛው ኑሮው፣ ህይወቱ፣ እስትንፋሱ፤ ቀልቡ፤ አደቡ፤ ነገው ነው። ነው። ነው። ይህ ሲያስቀና፤ ይህም ሲቀናበት የተገፋው ህዝብ ከፋሽስቱ ህወሓት የተላቀቀ ቀን ገመድ እራት ሳይሆን – አይቀርም። እንበርታ። ያ …. እንዳለፈው ….. ይህም ያልፋል። ይነጋል – በያነጋል።

የመስከረም 24.09.2015 የራዲዮ ሎራ Tsegaye Radio or www.tsegaye.ethio.info Aktuell Sendung ዝግጅት የመስከረም 5.2015 የአርበኞች ግንቦት 7 የድጋፍ ስብሰባ ሁለተኛ ክፍልና ሌሎችንም ለምትፈቅዱ ቅኖች አርኬብ ላይ ማዳመጥ – ትችላላችሁ። የጥራቱ ግድፈት የእኔ – አይደለም፤ የራዲዮ ዝግጅቱ ነው።

ሀገር የማዳን የደጀንነት ብሄራዊ በሳል የዕንባ ጥሪ  ….  የእመቤት ኢትዮጵያ ልባዊ ጥሪ ….

የማሸነፋችን መልእክቱ – የነፃነት ቀበኛ መረቦችን በተግባር ስንረታ ብቻ ነው። የእምዬዋ የመሃጸን ፍሬ ዘሮች – የጥቁር አንበሳ ጥሪ በረከት ተሳታፊ ለመሆን፤ የእናት ሀገር ብሄራዊ ለዕንባዋ ዋቢነት፤ ቀጠሮ አልባ፤ በቦታው መገኘትን በማስተዋል ይጠይቃል። ለሃዘኗ ቀን ጋባዥና ተጋባዥ – የለም። በህወሓት ለተጠቀጠቀው ዜግነት ሁሉም ደምመላሽ መሆን – ይገባዋል። የተቀደሰ ተሳትፎ የአደራ ኪዳናዊነት ነው። ሊንኮቹን ተከትለው ዝርዝር መረጃ – ያገኛሉ። በተሳትፈወት መጠን የነፃነት ናፍቆትን – ያቅፋሉ። በፍጥነተወት ልክም ህሊናዎት የእርስዎ፤ ስለእርስዎ የተፈጠረ መሆኑን – ይለኩታል። ሁሉም  – በመዳፈዎ። ፍቅር – ተስፋ  – ሐሤት – ማሸነፍ የነጋ ነገ። ቅድስት ነፃነት በብርክት አንባ።

http://ecadforum.com/category/events/

A call to the Salvation of Ethiopia in Chicago, IL, USA

A call to the Salvation of Ethiopia in Atlanta, Georgia, USA

A call to the Salvation of Ethiopia in San Jose, CA, USA

A Call to the Salvation of Ethiopia in Boston, USA

መሸቢያ ሰሞናት – ዘሃበሻ ትእግስታችሁ ዕለታዊ ትምህርት ቤቴ ነው። ኑሩልኝ።

አርበኞቻችን መንገዶቻችን ናቸው።

እልፍ ነን፤ እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47036#sthash.gfXPGYYj.dpuf

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s