በሕዝብ ጫና የሕወሓት መንግስት የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ወደ ቦታው ሊመልስ ነው

abune_petros
የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ከስፍራው በልማት ስር አንስቶ ታሪክን ሊያጠፋ ነበር ተብሎ ሲተች የነበረው የሕወሓት አስተዳደር ሕዝቡ በአደባባይ ይህን ታሪክ ሐውልት እንዲመልስ ባደረገው ጫና መሰረት ወደ ቦታው ሊመልስ መሆኑ ተሰማ:: መንግስታዊው ራድዮ ፋና “የአደባባይ ዲዛይን ስራ እየተገባደደ በመሆኑ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት በቅርቡ ወደ ቀድሞ ስፍራው እንደሚመለስ ተገለፀ” በሚል ዜናውን ቢያስነብብም ሕዝቡ አሁንም ሐውልቱ እስኪመለስ ድረስ ተቃውሞውን እንደሚቀጥል ታውቋል::

በተለያዩ ሶሻል ሚድያዎችም ሐውልቱ ቦታው እስኪመለስ እንጮሓለን የሚሉ መል ዕክቶች እየተሰራጩ ነው::

መንግስታዊው ራድዮ ፋና ስለሐውልቱ ወደ ቦታው ሊመለስ መሆኑን እንደሚከተለው ዘግቦታል:: እንደወረደ እነሆ:-

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት የሚያርፍበት አደባባይ ዲዛይን ዝግጅት የመጨረሻ ምእራፍ ላይ የደረሰ በመሆኑ ግንባታ ተካሂዶ ሀውልቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀድሞ ስፍራው እንደሚመለስ የፌደራል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ ገለፁ።

አቶ ዮናስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ሀውልቱ የሚያርፍበት አደባባይ ገፅታ እና ይዘት ምን መምሰል አለበት ለሚለው የመጨረሻ መልስ ለመስጠት የቀላል ባቡሩ ስራ የሚጀምርበት ጊዜ ሲጠበቅ ቆይቷል።

ይህም ያስፈለገው ባቡሩ በሚንቀሳቀስበት ወቅት የሚፈጠረውን ንዝረት አጥንቶ የአደባባዩን ዲዛይን ማጠናቀቅ ስላስፈለገ ነው ብለዋል።

አደባባዩ ሊኖር የሚችለውን ንዝረት በተግባር ተፈትሾ መገንባቱ ወደፊት ሀውልቱ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳይደርስበት ያደርጋልም ነው ያሉት።

ታሪካዊው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሲነሳ
ባለፈው እሁድ ቀደም ሲል ሀውልቱ የነበረበትን ስፍራ የሚያካልለው የሰሜን-ደቡብ የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር መስመር አገልግሎት በመጀመሩ የንዝረት መጠኑን በተመለከተ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን አቶ ዮናስ አስረድተዋል።

መረጃ የመሰብሰቡ ስራ እንዳበቃም የአደባባይ ዲዛይኑ ተጠናቆ ወደ ግንባታ ይገባል፤ ከዚያም ሀውልቱ በቀድሞ ስፍራው ይተከላል ብለዋል።

ለአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ግንባታ ሲባል 2005 ዓመተ ምህረት ሚያዚያ ወር ላይ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ከቆመበት ተነቅሎ በብሔራዊ ሙዚየም በክብር እንደሚገኝ ይታወቃል

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46910#sthash.YmuNsYro.dpuf

ትግሉ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ወይንስ ለምንይልክ ቤተ መንግሥት (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ

ፈጣሪ ዕድሜ ከጥንካሬ ጋር ያደላቸው በሀገር ጉዳይ የማይታክቱት ፕ/ር መስፍን ወልደ ማሪያም ሰሞኑን በምድረ አሜሪካ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር ያደረጉትን ውይይት ዘመነ ቴክኖሎጂ ምስጋን ይግባውና በያለንበት ሆነነን ተከታትለናል፡፡ ከውይይቱ ታዳሚዎቸች ከቀረቡ በርካታ ጥያቄዎች አንዱ በያ ትውልድ ላይ ጨከኑበት የሚል ነበር፡፡ ፕ/ር መስፍን ሲመልሱም አልጨከንኩበትም እውነቱን ነው የተናገርኩት አንዳንዶቹ እንደውም ተማሪዎቼ ነበሩና አነጋሬአቸዋለሁ፣ ፍላጎታቸው ለሀገርና ለሕዝብ ሳይሆን ሥልጣን ነበር ብለዋል፡፡

በዚሁ ሰሞን እጄ የገባው ባለ 96 ገጽ ሰነድ ውስጥ ፕ/ር የተናገሩትን የሚያረጋገጥ ከጉዳዩ ባለቤቶች አንዱ በሆነው የተነገረ አገኘሁ፡፡ ሰነዱ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ“ በሀገርና ሕዝብ ደህንነት ጥበቃ ምኒስቴር የማዕከላዊ ምርመራ ድርጅት የወንጀል መዝገብ ቤት” የሚል ማኅተምና “ጥብቅ ምሥጢር” የሚል ማሳሰቢያ ያረፈበት ሲሆን ከኢህአፓ መሪዎች አንዱ የነበረው ብርሀነ መስቀል ረዳ በእስር ቤት የሰጠውን የምርመራ ቃል የያዘ ነው፡፡ ከአጀማመራቸው አንስቶ እስከ መንዝና መርሀ ቤት ቆይታው ይዘረዝራል፡፡

ምንም ዘመናዊ የግንኙነት ዘዴ ባልነበረበት ዘመን አፍሪካ አውሮፓና አሜሪካ ሆነው በደብዳቤ ግንኙነት ሰነድ ማዘጋጀት ድርጅት መመስረት አመራር መምረጥ መቻላቸው ብሎም ከተለያዩ ሀገራትና ድረጅቶች ጋር ግግንኙነት በመፍጠር ወታደራዊ ሥልጠና መውሰዳቸውና በኤርትራ እስከ አሲምባ መዝለቃቸው አዲስ አበባም ላይ በህቡዕ ያደረጉት አንቅስቃሴ በእውነቱ የሚያስደንቅ ነው፡፡ ግና ምን ዋጋ አለው ያንን ችሎታ፤ ያንን እውቀት፤ ያንን ድፍረትና ቁርጠኝነት የሥልጣን ጥም በላው፡፡ እንታገልለታለን ብለው የተነሱለትን ዓላማ የሥልጣን ፍላጎት በለጠውና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ቀርቶ ርስ በርሳቸውም መስማማት አንዳይችሉ አደረጋቸው፡፡ሁሉንም ሊደፈጥጥ የተዘጋጀው ደርግ አፍንጫቸው ስር እያለ የሥልጣን ጉጉት የሀሳብ ልዩነቶቻቸውን በውይይት ከማስታረቅ ይልቅ አጥፊና ጠፊ ሆነው አንዲሰለፉ አበቃቸውና፤ የአንድ ድርጅት አባላት ርስ በርሳቸው አንዲሁም አንዱ ድርጅት ከሌላው ያለምንም በቂ ምክንያት እየተጠፋፉ ለአጥፊያቸው ራሳቸውን አመቻቹ፡፡ ሊድን ያልቻለ በሽታም አስፋፉ፡፡

ብርሀነ መስቀል ከማዕከላዊ ኮሚቴ ከተባረረ በኋላ ክሊክ ብሎ ከሚጠራቸው የትግል አጋሮቹ ግድያ ሽሽት ድርጅቱ ካስቀመጠው ሰባ ደረጃ አካባቢ ለቆ እንደተሰወረና የእርማት ንቅናቄ የሚል ስራ እንደጀመረ ብዙም ሳይቆይ ደግሞ የደርግን አሰሳ በመሸሽ ከሌሎቹ አጋሮቹ ጋር ከአዲስ አበባ ወጥተው መንዝና መርሀቤት ጫካ ለመግባት እንደበቁ ይናገራል፡፡ በትግል አጋሮቻቸው የተገደሉ የአመራር አባላትን ስምም ይዘረዝራል፡፡ ግን ለምን መጠፋፋት መገዳደል! ይገኝ አይገኝ ላልታወቀ ገና ላም አለኝ በሰማይ ለሆነ ስልጣን በአንድ አላማ ስር ተሰልፈው በአንድ ድርጀት ታቅፈው ለትግል የተማማሉ የአንድ ሀገር ልጆች እስከመገዳደል መድረሳቸው ያሳዝናል፤ ይበልጥ የሚያሳዝነው ደግሞ የዛ ድርጊት መሪ ተዋናዮች ሲያዝኑም ሲያፍሩም ሲጸጸቱም አለመሰማቱ ነው፡፡

እንደ ብርሀነ መስቀል ገለጻ ከሆነ ኢህፓ ከውስጥ አመራሩ ርስ በርስ ይቆራቆሳል፣ ይህን መልክ ሳያሲዝ ከላይ ከደርግ ከጎን ደግሞ በተለይ ከመኢሶን ጋር ይታገላል፡፡ በወቅቱ የችግሮች ሁሉ ቁንጮ የነበረው የመኢሶንና የኢህአፓ ቅራኔያቸው አንቶ ፈንቶ ልዩነታቸው መሰረት የለሽ ጠባቸው የግለሰቦች የሥልጣን ጥም(ድርጅታዊ ያልሆነ) አንደነበረ በተለያየ ሁኔታ ተገልጹዋል፡፡ ይህንኑ የሚያሳይ ትንሽ ግን የትልቅ ነገር ምልክት ከብርሀነ መስቀልም ቃል ውስጥ እናገኛለን፡፡

“ሚያዚያ 13/68 የታወጀው የብሔራዊ ዴሞክራሲዊ አብዮት ፕሮግራምና በተቀዳሚ ም/ል ሊቀመንበሩ ለተራማጆች ሁሉ የተደረገውን አስቸኳይ የግንባር መቋቋም ጥሪ… በሳምንት ውስጥ ማ/ኮ ተሰብስቦ የግንባሩን ጥሪ አንቀበል የምንል ወገን የብዙሀኑን አባላት ደምጽ አግኝተን ክሊኩ በግልጽ ተሸነፈ”፣ ይልና ተሸናፊው ወገን የተለያየ ሰበብ እየፈጠረ አዘግይቶ ባወጣው መግለጫ “በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለግንባሩ ብቁ ተብለው ሲዘረዘሩ ያኔ ፕሮግራሙን በይፋ አውጆ የነበረው መኢሶን ሳይጠቀስ ቀረ” ካለ በኋላ “ለግንባር ጥሪው ምላሽ የሚለው የፓርቲው መግለጫ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተለይ የሰፊው ሕዝብ ድምጽ ጋዜጣ “ኢህአፓን ለግንባር ማን ጠራትና ተኳኩላ ቀረበች” ወዘተ የሚል የኩርፊያ ጽሁፍ አወጣ” ይላል፡፡ እስቲ ይታያችሁ ጋባዡ ተቀምጦ ተጋባዦቸ ሲጣሉ፡፡ ይህ ታዲያ የጤና ነው፡፡ በሽታው ተዛምቶ በቅርብ ግዜም እገሌ የሚባል ድርጅት ከተገኘ አንገኝም አገሌ የሚባል ሰው ከተጋበዘ አንካፈልም ሲባል ሰምተናል፡፡ መድሀኒት ያልተገኘለት መጥፎ በሽታ፡፡

የሀሳብ ልዩነትን በውይይት ማስታረቅ ሳይሆን በጉልበት መደፍለቅ፣ የተለየ ሀሳብ የሚያራምዱትን በማዳመጥ ሳይሆን በመርገጥ/በማስወገድ እኔ ብቻ ትክክል ማለትና አሻቅቦ ቤተ መንግሥትን እያዩ አባሉንና ተከታዩን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እየጋቱ ለመስዋዕትት መዳረግ፤ተደጋጋፎ ሊታገሉ የሚገባን ድርጅት ስም እየሰጡ ወንጀል እየፈበረኩ ከቻሉ ለማጥፋት ካልሆነም ሽባ ለማድረግ እቅልፍ የሚነሳ በሽታ መቼ አንደጀመረ ባላውቅም ጎልቶ የታየውና ነጥሮ የወጣው በአብዮቱ ዘመን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይሄው በሽታ መድሀኒት የሚፈልግለት ጠፍቶ፣ ሊያረጅም ሊዘምንም አልችል ብሎ እስካሁን የፖለቲካችንና የፖለቲከኞቻችን መታወቄያ እንደሆነ ይገኛል፡፡ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም ሆኖብን አንደሁም አንጃ ዛሬም ከኢትየጰጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ መነሳት አለበት ከምንለው ሀይል ጋር ከሚደርገው ትግል ይልቅ የጎንዮሽ ርስ በርስ የሚደረገው ትግል የከፋ ሆኖ ነው ወያኔ ከሀያ አራት አመታት አገዛዙ በኋላ መቶ በመቶ በምርጫ አሸነፍኩ ብሎ ሊቀልድብን የበቃው፡፡

ሰሞኑን አሜሪካ ለንባብ የበቃው የሌ/ኮ ፍሰሀ ደስታ መጽሀፍ ሲተዋወቅ ጸኃፈው የኢህአፓ ቆራጥነት የመኢሶን ርዕዮተዓላመዊ ብቃት የደርግ ሀገር ወዳድነት ቢቀናጅ ተአምር ሊሰራ ይቻል እንደነበረ በቁጭት መግለጻቸውን ሰምተናል፡፡ኮረኔሉ ከዚህም አልፈው እስካሁን ማንም ያልደፈረውን ደፍረው አውቀው በድፍረት ሳያውቁ በስህተት ለፈጸሙት የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ በሁሉም ዘንድ ያለው የሥልጣን ጥም በምን ልጓም ተገቶ እንደምንስ ሰክኖ ለዚህ መብቃት ይቻላል፡፡ ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ እንዲሉ ይቅርታው ቀርቶ ባለፈ ስራ መጸጸትና ለአለቀው ወጣት ማዘንም አይታይም፡፡ ካለፈ መማር ቢኖር የቤተ መንግሥቱ ወንበር ለሁሉም ሊሆን አንደማይችል ነገር ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ሥርዓት መፍጠር ሁሉንም ንጎሶች እንደሚደርጋቸው አምነው እውቀት ልምዳቸውን ተሰጥኦ ተሞክሮአቸውን በማቀናጀት ትግሉ አንዴት፤ የት፤ በምን ሁኔታና በማን መካሄድ እንደሚችልና አንደሚገባው ሊመክሩ ሊያቅዱና ስትራቴጂ ነድፈው አንደ አቅም ችሎታው ተደጋግፈው በመታገል የግዞቱን ዘመን ባሳጠሩት ነበር፡፡ ግና አልታደልንምና ዛሬም ብዙዎቹ ራሳቸው ለሥልጣን ስለሚበቁበት ብቻ እያሰቡ የሚያውቁትን ያደጉበትንና አላረጅ ያለውን የጎንዮሽ ትግል የሙጢኝ አንዳሉ ናቸው፡፡ላያገኙት ሥልጣን ትግሉንና ታጋዩን በትንሹም ቢሆን ይጎዳሉ፤ለገዢው እድሜ መርዘም ይሰራሉ፡፡

በአብዮቱ ወቅት ከነበሩት ፓርቲዎች የአንዱ የወዝ ሊግ መሪ የነበሩት አቶ ተስፋየ መኮንን ይድረስ ለባለታሪኩ በተሰኘው መጽሐፋቸው “በሕዝባችን ፊት ተሰባስበን ችግሮቻችንን ለመፈታት ችሎታው ያልነበረን የኢትዮጵያ ልጆች የኮ/ል መንግሥቱ የግድያ ጉሮኖ ውስጥ ለመጨረሻ ግዜ ተገናኘን፡፡

ሁላችንም በተዘዋዋሪ መንገድና ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ሲበዛ ለድርጅት ሲያንስ ለግል የሥልጣን ሽኩቻ ስንባላ ለዚያው ተመሳሳይ ዓላማ የቆሙት ኮ/ል መንግሥቱ በአሸናፊነት ሊበሉን በአንድ ቦታ አሰባሰቡን ፡፡ ክቡር በሆኑ የሕዝብ ጥያቄዎች ላይ ካደረስነው በደል አንጻር ከዚህ የበለጠ ምን የታሪክ ፍርድ ይኖራል፡፡” በማለት ነበር የወቅቱ አብይ ችግር የሥልጣን ጥም አንደነበረ ያሳዩት፡፡ ይሄው ድርጊት ነው እስከዛሬ የቀጠለው፣ ዛሬም ያለውና ወደፊትም የማይቆም የሚመስለው፡፡ ተባብሮ መስራት ቀርቶ ተከባብሮ መኖር የተሳናቸው ፓርቲዎች አባላት በወያኔ እስር ቤት በአንድ ላይ ይታሰራሉ፡፡ በመሪዎች የሥልጣን ጥም ምክንያት ትግሉ አንድ ርምጃ መራመድ ተስኖት አባላትና ደጋፊዎች ግን ሞት እስር ስደት ስቃይ እየደረሰባቸው ነው፡፡ይህንንም የዜጎች መስዋዕትነት ለእነርሱ ፍላጎት ማሳኪያ ሊጠቀሙበት የሚዳዳቸው ፖለቲከኞች እናያለን፡፡

በኢትጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ይዘጋጅ በነበረው ርዕይ 2020 መድረክ ላይ ዶ/ር ታደሰ ብሩ ኬርሴሞ ሰላም ዴሞክራሲና ልማት የልሂቃን ሚና ዛሬና ነገ በኢትዮጵያ በሚል ርእስ ባቀረቡት ጽሁፍ «የኢትዮጵያ ልሂቃን በጣም መበታተናቸው ሳያንስ እርስ በርሳቸው በእጅጉ የሚጻረሩ አንዱ ሌላኛውን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከመረረ ጥላቻ ጋር የተነሱ መሆናቸው አገራችን ዛሬ ለምትገኝበት አሳዛኝ ሁኔታ የዳረገን ይመስለኛል፡፡ የመጠፋፋቱ ትግል በደርግ ግዜ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም አሁንም መልኩን እየቀያየረ ቀጥሏል ፡፡ ኢትዮጵያዉያን ልሂቃን በአገራዊ ጉዳዮች የጋራ መግባባት ላይ ካልደረሱ በስተቀር ይህ የጥላቻና የመጠፋፋት ፖለቲካ በቀላሉ የሚቆም አይመስለኝም፡፡ ብለው ነበር ፡፡ ዶ/ር ታደሰ እንዲህ ብለው ብቻ አላበቁም፣የልሂቃኑ ለድርድር መዘጋጀት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ሲገልጹ « እዚህ ላይ አጽንኦት ልሰጥበት የምፈልገው ጉዳይ ግን ጥሩ ሕገ መንግሥት፣ ጥሩ የምርጫ ሕግ እና ግልጽና ፍትሀዊ ምርጫ ወዘተ..ቢኖሩም እንኳን ልሂቃኑ ለድርድር የተዘጋጁ ካልሆኑ ዲሞክራሲ መኖር የማይችል መሆኑ ነው» ነበር ያሉት፡፡ ጽሁፉ ከቀረበ 10 አመታት ያለፉት ቢሆንም የተለወጠ ነገር የለም፤ እንደውም መሻል ቀርቶ ብሶበታል፡፡ዛሬስ ወደፊትስ…፤

ለውጥ ያለመታየቱ ምክንያትም ፕ/ር መስፍን በአሜሪካው የውይይት መድረክ ላይ የተናገሩትና በተለያዩ ጽሆፎቻቸው የገለጹት በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለው የሥልጣን ጥም ነው፡፡ ከዚህ እንዴት መገላገል ይቻል ይሆን! ፕ/ር መስፍን ሥልጣን ባህልና አገዛዝ፣ፖለቲካና ምርጫ በሚለው መጽሀፋቸው አንዲህ ይላሉ ፡፡

“እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወደ ፖለቲካ ሲገባ ከልጅነት እስከ እውቀት በውስጡ የተመረገውን የጌትነትና የሎሌነት ባህል ፍቆ ፈቅፍቆ ማርገፍ አለበት፡፡በግድ የአሰተሳሰብ የጽዳት ዘመቻ ያስፈልገናል፡፡ ዓላማን የማጥራት ዘመቻ ያስፈልግናል፡፡በግድ የነጻነትና የእኩልነት አራማጆች በቁርጠኝነት መነሳትና ማሳየት ያስፈልገናል፡፡ ብዙዎቹ የተቀናቃኝ መሪዎች ላይ የሚታየው የድሮው መኳንንትና መሳፍንት ለመምሰል የመሞከር ጠባይና ከዚህም ጋር ተያይዞ ሎሌዎችን በገንዘብ ሆነ በወደፊት ተስፋ እየገዙ የአገዛዝን ባህል ለማራማድ የሚደረገው ሙከራ የፖለቲካውን ሥርዓት አያራምድም ፡፡ ጥረቱ ሁሉ በሥልጣን ላይ ያሉትን ሰዎች ለመለወጥ እንጂ ሥርዓትን ለመለወጥ አይመስልም” (ገጽ 32)

ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን በአንድ ወቅት ከጦቢያ መጽሄት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በገለጸው ስጋት ልሰናበት“ኔልሰን ማንዴላ እንደ ስምጥ ሸለቆ ቁልቁል የጠለቀውን ‹የልዩነት›› መቀመቅ በዴሞክራሲ ድልድይ ገደሉን አስተካሎ የመቻቻልን ጥበብ ለወገኑ ሲታደግ የኛ ተቀዋሚዎች ፖለቲከኞች ግን በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል አዳስ ሰምጥ ሸለቆዎች አንዳይቆፍሩ እሰጋለሁ፡፡”

Zone9 Bloggers Are Not Alone: More Ethiopian Netizens Face Terrorism Charges

by Tedla D. Tekle | GlobalVoices

Alongside the now-famous case of the Zone9 bloggers, there are so many detained Ethiopian bloggers, online activists and politicians, whose names are not yet on the map.

Zelalem, Yonatan, Bahiru and Abraham

Last year on July 8, 2014, Ethiopia detained a number of local opposition leaders, bloggers, online activists and concerned citizens. Some were released after four months of interrogation. However, ten were charged on October 31, 2014 under Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation with having links to diaspora-based Ethiopian opposition groups such as Ginbot 7, applying to attend an online security training, and engaging in online activism. Three of the 10 defendants are not members of any political party but ordinary citizens who were arrested for applying to attend a course. These are Zelalem Workagenegu, Yonatan Wolde and  Bahiru Degu.

The controversial Anti-Terrorism Proclamation was adopted in July 2009. Ethiopian officials tend to defend the law by arguing that its controversial provisions were copied from the existing laws of countries such as the United Kingdom. Article 6 of the Proclamation, which has been used to curtail freedom of expression, provides that:

[w]hosoever publishes or causes the publication of a statement that is likely to be understood by some or all of the members of the public to whom it is published as a direct or indirect encouragement or other inducement to them to the commission or preparation or instigation of an act of terrorism [is subject to between 10 and 20 years in prison].

Zelalem, the first defendant, is a human rights activist who blogs at DeBirhan. Yonatan and Bahiru, who are best described as concerned citizens, had applied along with Zelalem for a social media and Internet security training that was brought to their knowledge by a US-based Ethiopian journalist. After an email from the Ethiopian journalist in the US was found in their possession, these young men were also arrested and later charged with applying for “a terror training” when in fact the training was about Internet safety and security.

Ethiopian court last month acquitted Abraham Solomon, detained for having connections with the first defendant Zelalem, along with four other opposition politicians namely Abraha Desta, an official of the opposition Arena Tigray Party and social media activist, Yeshiwas Assefa, council member of the Blue (Semayawi) Party, Daniel Shibeshi, official of the now defunct Unity for Democracy and Justice (UDJ) party and Habtamu Ayalew, former Public Relations Head of the defunct UDJ. However, until today they have not been released because the Prosecutor has reportedly appealed the decision.

An article by the Electronic Frontier Foundation shows the increasing attempts of silencing online activists and netizens in Ethiopia. The organisation called Ethiopia to:

Immediately free all journalists in prison, including the remaining Zone 9 bloggers, and relieve them of all charges for the “crime” of reporting the news.
End the prosecution of individuals for pursuing security training and using encryption technologies, and free Zelalem Workagegnehu, Yonatan Wolde, Abraham Solomon, and Bahiru Degu.

Cease and desist from using invasive surveillance technologies like FinFisher and Hacking Team’s Remote Control System to spy” on Ethiopian journalists, Diaspora, and opposition groups.

While Zone9 remains among Ethiopia’s best-known case of its kind, stories like that of Zelalem demonstrate that the issues these bloggers face extend far beyond a few individuals. The next court appearance of Zelalem, Yonatan and Bahiru is between November 7-9, 2015.

እውነተኛ ፍላጎታችን ኢትዮጵያን መታደግ ከሆነ ለኢትዮጵያ ስንል ሁሉን እናድርግ

ናትናኤል በርሔ

Ethiopia ስለ ታላቅዋ የአፍሪቃ እንቆቅልሽ፤ ስለ ሥልጣን አያያዝና ሥልጣን ላይ መውጣት፣ ሥልጣንም ላይ መሰንበትና ከእሱም አልወርድም ማለት ምን እንደሆነ እንድናስብ እንድናውቀው ተጨባጩ ሁኔታ እንደሚያሳየው ለአንድ አምባገነን ለዚያም አስተሳሰብ ልቡን ለሸጠ ሰው ይህ ሆድ አደር ትልቅ ቦታ አለው። ያለመታደል  ሆኖ ሗላቀር የሆኑ አገሮች በተለይ በአፍሪካ በመሪነትና በወሳኝነት ቦታዎች ላይ የሚቀመጡበት አብዛኞች በልምድና በስነምግባር የተራቆቱ ስለሚበዙባቸው በራሳቸው ስለማይተማመኑ ገንዘብ ማጋበስና በስልጣን ለመቆየት ሲሉ ውሸትና ማታለል ይበዛሉ። ዛሬን እንጂ ነገንና ለነገው ትውልድ ደንታ ስለሌላቸው ከወገንና ከሀገራቸው ሕዝብ ይልቅ ከውጭ መንግስት ፍላጎት ጋር ግንባር ቀደም ትብብር ያደርጋሉ  ከመላው አለማት በአምባገነት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው አገራት መሀከል ግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው  የወያኔ አገዛዝ አንዱ ነው።  ላለፉት 24 ዓመታት እየተጨቆነች እና እየተረገጠች ላለችው አገሬ ኢትዮጵያ እኛ ኢትዮጵያውያን ወያኔ ከሥልጣን ላይ ከወጣ ጊዜ አንስቶ በእያንዳንዷ ዓመት የተባበረ እንቅስቃሴ የምናደርግበትን መተማመንና መከባበርን በወያኔ ጋሻ ጃግሬዎች እርዳታ የብሔር ፖለቲካ ከፋፍለህ ግዛ እነሆ ዛሬ ወያኔ ባዘጋጀልን ወጥመድ ወድቀን በመንፈራገጥ ላይ እንገኛለን።

ኢትዮጵያ ብዙ ውስብስብ ችግሮች ያለባት አገር ናት። በተለያዪ ጊዜዎች እነዚህ ለራሳቸው የግል የቡድን ፍላጎት መጠቀሚያ ለማድረግ የፈለጉ ወይም እነዚህን ችግሮች ዲምክራሲያዊ ባልሆነ መንገዶች በህዝብ ስም እንፈታለን ብለው የተነሱ አምባገነን ሀይሎች የሀገራችንን ችግሮች የበለጠ አወሳስበው በመጨረሻ እራሳቸውም አይወድቁ አወዳደቅ ሲወድቁ አይተናል ይሄውም በቅርብ ጊዜ በሰሜን አፍሪካ ሆነው ማንሳት በቂ ነው። ሕወሃት ስልጣን ከጨበጠ ከጅምሩ በኢትዮጵያ የዘረጋዉ ፖለቲካ በዘር ላይ የተመሰረተ ከፋፋይ ፖለቲካ ነዉ። ኢትዮጵያ የብዙ ብሄረሰብ አገር ናት። በታሪኳ የተሰሩ ብዙ ስህተቶችና በደሎች አሉ። በአንጻሩም ደግሞ ኢትዮጵያዉያን ከተለያዩ ቋንቋዎችና ክልሎች በሰላም በፍቅር ኖረዋል፣ ተዋደዋል፣ ተደባልቀዋል። በጋራ የዉጭ ወራሪ ኅይላትን መክተዋል። ወያኔ/ኢሕአዴግ ከደደቢት በረሃ ተነስቶ አዲስ አበባ ገብቶ በመንገሥ በአባቶቻችን መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየውን ድንበራችን በማፍረስ፣ ከቤቶቻችን በማፈናቀል፣ መሬታችንን ለባዕድ በመስጠት ያደረሰብን በደል ጣሊያን ከአውሮፓ በመምጣት ከተቃጣብን ወረራ ካደረሰብን ጉዳት በልጦ ይገኛል። በሽፋን ስሙ ኢሕአዴግ ተብዮው ወያኔ/ሕወሐት ዕድሜውን ለማራዘም ይመቸው ዘንድ በውስጣችን ቅራኔን በማስፋት በዘር እያደራጀ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ሕዝብን በእሥራት፥ በግድያ፥ በበሽታ፣ በረሐብ እየፈጀና እያስፈጀ ፋሽስታዊ ሥርዓቱን ከጫነብን  ላለፉት ሁለት አስር አመታት በላይ አልፎናል። የተቃዋሚው ጎራም ባልረቡ ልዩነቶች እርስ በርስ ባለመግባባትና ተለጣፊውም በዝቶ ትግላችን ግብና ዓላማውን ከመሳቱም አልፎ ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ አስፈራርቶና አሽብሮ ለመግዛት በሚያደርገው ትግል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ድጋፍ እያበረከትን ነው። ከወያኔ ጋር መደራደር በሀገራችን የዴሞክራሲን ሥርዓት መመሥረት አያስችልም። ወያኔ በታሪኩ ሁኔታዎች ወጠር ሲያደርጉት ለማዘናጋት እንደራደር ቢልም በመጨረሻ ቅራኔዎችን የሚፈታው በኃይል ብቻ ነው። ከወያኔ መደራደር የሕዝቡን ትግል እጅ ለማሰጠት ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ለሚደረገው የዴሞክራሲያዊ ትግል መሳካት ዋነኛው መሠረት የኃይል ሚዛንን ወደ ሕዝብ ወገን እንዲያጋድል የሚያደርግ ሕዝባዊ ጉልበት በጥንቃቄና በቁርጠኝነት ሲገነባ ብቻ ነው። ከዚያ ባነሰ አቅም መደራደር ሽንፈትን ለማረጋገጥ ነው።

በጎንደር በኩል ያለ የኢትዮጵያ ሰፊ ለም መሬት ከህዝብ ደብቆ ለሱዳን መንግስት በገጸ በረከትነት በማቅረብ የውሃውን ጥልቀት ሞክሮ ዛሬ ደግሞ በምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል ኢትዮጵያውያንን ከሀገራቸው መሬት በሃይል እያፈናቀለ የቤልጀየምን የቆዳ ስፋት ያክል መሬት እየቆረሰ ለተለያዩ ሀገሮች ሀገራችንን እየሸነሸነ በመሸጥ ላይ ያለ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሌት ተቀን የሚሰራ ቡድን ነው።  ይህ የኢትዮጵያ የሆነን ነገር ሁሉ ብዙ መስዋዐትነት የከፈሉት አርበኞች አባቶቻችን የሚሸጥና የሚለውጥ አፋኝ ወሮበላ መንግስት ኢትዮጵያዊነትን ሸርሽሮ በጎሳ የተከፋፈለ ደካማ ህዝብና ደካማ ሀገር ለማድረግ ይዞ የተነሳውን ዓላማ ሲሰራበት ቆይቶዋል። ይህ አፋኝ የኢትዮጵያ ጠላት የህዝቡን የሰውነት መብቱን ገፎ ከመኖር በታች ከሞት በላይ አድርጎት በረሃብ ከሚታመሰው ህዝብ ጉሮሮ እየነጠቀ ከመሬት ሽያጭ የሚያገኘውን ገንዘብ በተለያዩ የውጭ ባንኮች የሚያሸሸውንና የሚያጉረው አልበቃ ብሎት ዛሬ ደግሞ የአምስት አመት  ሁለተኛው  እቅድና ትራንስፎርሜሽን በሙሉ የሚነደፈውና የሚጠነጠነው ከሀገሪቱ ጥቅም አኳያ እንጅ ከእውነትና ከሀሰት ከሰብአዊነትና ከዴሞክራሲ ጋር በተዛመደ መልክ ስላልሆነ የምታወሩት ሌላ የምታደርጉት ሌላ ብለን ብናሳጣቸው ብንወቅሳቸው ለኛ ጠብ የሚል ነገር አይኖርም ።

ይህ እንዲሆን ከተፈለገ  ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ራዕይ አንግበው ሕዝቡን የሥልጣን ባለቤት
ለማድረግ ፤ በኢትዮጵያዊነት ላይ በማንኛውም ዓይነት መልኩ በማንም ግፊት ሳይደራደሩ በጽናት የሚከፈለውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚያታግሉ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች ከፍተኛ አክብሮትና ድጋፍን ከመስጠት ወደ ኋላ
ማለት የለብንም። የተያያዝነው ትግል የዴሞክራሲ ብቻ ሳይሆን ሀገር አድንም መሆኑን ጠንቅቀን ማወቅ አለብን።  እንዴት ከዚህ ልንደርስ ቻልን ብለን እያንዳንዳችን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ራሳችንን ብንጠይቅና ጊዜ ሳንፈጅ መተማመንና መከባበርን እንዳ ሀገሬ ወጌሻ ለቃቅምን ከቦታው እንዲገባ መጠገን መጀመር ይኖርብናል። ይህ ጥረት ደግሞ እያንዳዳችን ትከሻ ላይ ወድቋል።

ይኄው የአሜሪካ መንግስት ነው በአንድ በኩል ሰብዓዊ መብትና ዲሞክራሲ እያለ ሲለፍፍ በሌላ ወገን ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ስቃይ መከራና የሰብዓዊ መብት ረገጣ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ በመሆን እንደ ሰሜን ኮርያው አይነት በዓለም በዕኩይነቱ አቻ የሌለው አምባገነን መሪ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲደግፈው የሚታየው ለጥቅም እንጂ ሰብዓዊ መብት፣ ዲሞክራሲ ወይም የሰው ልጅ ጣዕርና ዕልቂት ምኑም ያልሆነው የአሜሪካ መንግስትና የዚሁ ፖሊሲ አራማጅ መሪዎቹ  የሶርያው ፣ የአፍጋኒስታኑ ፣ የሩዋንዳ የእርስ በርስ ፍጅት ዳር ሆነው ሲያዩ ዓለም ታዝቧል።

ኢትዮጵያ፡ እንደሀገር፡ እንድትቀጥልና፡ የኢትዮጵያ፡ ህዝብም፡ ከተጫነበት፡ የመከራ ቀንበር፡ እንዲገላገል፡ ከልብ፡ የምንናፍቅ፡ ከሆነ ምኞት፡ የሚጭበጠው፡ በሥራ ነውና፡ ያለምንም፡ ማቅማማት፡ እያንዳንዳችን፡ የዜግነት ድርሻችንን፡ የምናበረክትበት፡ ቀን ቢኖር፡ ዛሬ ሥአቱም፡ አሁን፡ ነው፡ በካሀዲው፡ ጎራ ከተሰለፉትና፡ በመሀል፡ ከሰፈሩት፡ ጥቂት፡ ሰዎች፡ ውጭ ሁሉም፡ ኢትዮጵያዊ፡ ማለት፡ ይቻላል፡ የወያኔን፡ ሀገር፡ አጥፊነት

ከነዚህ ወጥመዶችና የተንኮል ተግባራቱ መካከል አንዱ ሰላዮቹን ለተቃዋሚዎች እጃቸውን እንደሰጡ በማስመሰል የሚታወቁ መረጃዎችን በመድገም ወይም አሳሳች መረጃ በመስጠት ባለስልጣን ነበርኩ፤ ብዙ ነገር አውቃለሁ በማለት አልፎ ተርፎም የኢትዮጵያውያን ትግል ለማዳከም  አንድነትን ወገን ለመከፋፈልና የሕዝቡን ትግል ለማኮላሸት የሚጠቀሙበት ስልት ነዉ። እኛም ሁለት አማራጭ ነዉ ያለን ከዚህ በፊት ከሰራናቸዉ ስህተቶች ተምረን ልዩነቶቻችን አቻችለን የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በኛ ላይ የሚዘረጉትን ወጥመዶች ሰባብረን፣ ይህ ችቦ የበለጠ እንዲቀጣጠል ማድረግ አንደኛዉ አምራጫችን ነዉ። ሁለተኛዉና ሌላዉ አማራጭ የሕወሃት መንግስትን እድሜ የሚያራዝም፣ የተለኮሰዉን ችቦ የሚያዳፍን፣ አገራችን ኢትዮጵያውም ከድጥ ወደ ማጡ እንድትሄድ የሚያደርግ የርስ በርስ የመከፋፈልና አብሮ ያለመሥራት አጉል ኀላ ቀር ልማዳን መቀጠል ነዉ።

አንድ ግን ለማሳረጊያ ማንሳት የምንፈልገው ነገር ቢኖር፣ እኛ ተከባብረንና ተፋቅረን አብረን በሰላም ለመኖር ከአወቅንበት እንደሚባለው እንደ አውሮፓውያኖች ገና ብዙ አመታት መጠበቅ ሳይሆን ነገ ማድረግ የምንችለው ነገር ነው። ያገኘነው ልምምድ የቀመስናቸው መከራዎች በቂ ትምህርቶች ናቸው። ነጻነትና ነጻ አስተሳሰብ ማለት ደግሞ ማንኛውንም ዓይነት “ባርነትን” አልፈልግም ማለት ነው።

ቸር እንሰንብት።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያ አገራችንን ይጠብቅልን፡፡

ናትናኤል በርሔ

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46848#sthash.AWa3eESu.dpuf

የኣንድነት ችቦ እየተንቦገቦገ ነው – ከአቶ ቸሩ ላቀው

unityከወያኔ የዘር ኣገዛዝ በፊት የኢትዮጵያ መለዮ ለባሾች ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጡ ስለነበሩ ከሥልጠና ቦታቸው ጀምሮ በየደረሱበት የውጊያ ዐውደ ግንባርና የጦር ሠፈር ኑሮኣቸው እንደ ወንድማማች፣ እህትማማችና ጓደኛሞች የሚተያዩ  ነበሩ እንጂ የዘር ቆጠራ ውስጥ ኣይገቡም ነበር። ኣብሮ መብላትና መጠጣት፣ ኣብሮ መዝናናትና ለሞትም ሆነ ለድል ኣብሮ መሰለፍን ዓላማቸው ኣድርገው የሚንቀሳቀሱ ነበሩ። የትግል ኣጋራቸውን ሕይወት ከተቃራኒው ጦር ኣረር ለማዳን እንጂ ጓደኛቸውን መግደልና ማስገደል እንኳን ሊደረግ ታስቦም ኣያውቅም ነበር።

ወያኔ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ችግር ሳይኖር ራሱ በራሱ ላይ ችግር በመፍጠሩ ሁለት ኣጣብቂኝ ውስጥ ገባ። ሌሎችን ማመን ስለኣልቻለ ማንኛውንም እንቅስቃሴ በትግራይ ተወላጆች ብቻ ለማንቀሳቀስም ዓላማው ነበር። መለዮ ለባሾቹንም በትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዳያዋቅር በቂ ሊሆኑለት ኣልቻሉም። ስንቱ ቦታ ይሰለፋሉ። በሆኑለት ደስ ባለው ነበር። ስለሆነም ሌሎችን በሁለተኛ ዜጋነት ቀጥሮ  ማሠራቱ ኣይቀሬ ሆነበት። የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ግን በመሪነት እንዲያገለግሉ ኣደረገ።

ይኸ የትግሬዎችን በበላይነት የማየቱ ተንኮል ሌሎችን እንዳያስነሳበት እያንዳንዱን ብሔር በጥርጣሬ እንዲተያዩ  የዘር ልዩነት መርዝ ጋታቸው። ስለሆነም ሁሉም እንደ ጭዳ በግ ወደ እርድ መነዳት ሆነ። ኣትግደለኝ፣ ኣታግለኝ፣ ኣታንገላታኝ፣ መብቴን ጠብቅልኝ፣ ወዘተ የሚል የመብትና የዜግነት ጥያቄዎች በራቸው ተዘጋ። የጋራ ጠላታቸውን ለመፋለም መዘጋጀት ሳይሆን እርስ በርስ እንዲፋጠጡ ሆነ። ሲዘምቱ ግን ወርቃማዎቹ ከኋላ ሆነው ወደፊት እያሉ ይነዱኣቸዋል፣ ወደ እሳቱ ይማግዱኣቸዋል። እንደ እንስሳ የተጠመዱ ፈንጂዎች ላይ እንዲሔዱ ኣደረጉኣቸው። የፈንጂ መሞከሪያ ኣደረጉኣቸው። የጠላት ጦር ሳይገድላቸው ራሱ ወያኔ ገዳያቸው ሆነ። እኔ ልቅደም፣ እኔ ልቅደም ይባባሉ ነበር እንጂ ኣንዱ ሌሎችን ወደ እሳት ወላፈን የሚገፈትርበት ጊዜ ኣልነበረም። ያንን ጊዜ ወያኔ እንደ ኋላቀር ቆጠረው።

በወርቃማው ዘር ላይ ተንተርሶ  በመሣሪያ ኃይል ሀገሪቱን የሚያሽከረክረው የወያኔ መንግሥት በሰሜን ጎንደር፣ በሰሜን ወሎና በሰሜን ኣፋር እያደረገ እንዳለው ጨርቆቹ ቢያልቁለት መሬቱ ስለሚለቀቅለት ወርቃማዎቹን ያሰፍርበታልና ጦርነትን ይፈልጋል፣ በሰበቡ ጨርቆቹ እንዲያልቁለት ይፈልጋል። “የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች፣ እነርሱም ያልቃሉ እርሷም ትሞታለች።” እንደተባለው ወያኔ መራሹ መለዮ ለባሽ እስከ ዛሬ ባየው የዘር ፖለቲካና የነርሱ መገለል ቆም ብለው እንዲያስቡ እያደረጋቸው ጀርባቸውን እየሰጡ ናቸው። ወያኔዎቹ በለኮሱት እሳት ራሳቸው ይቃጠሉበት እንጂ እኛ በምን ተዕዳችን እያሉ ናቸው። ወያኔ የማይሆንና ሊሆንም የማይችል መርዝ ላለፉት 24 ዓመታት ቢረጩም ለጊዜው ትንሽ ተሳክቶለት ቢፈነጩም ዘለቄታ ኣላገኘም። ኣሁን ወደ ዜሮ እየወረደ ነው።

ወያኔ ላለፉት ኣርባ ዓመታት የኢትዮጵያውያንን ኣንድነትና ኣብሮነት ለማፍረስ እየጣረና እያስገደደም እስከ ዛሬ ቢለፋም ሊሳከለት ኣልቻለም። እንዲያውም ራሱን እየለበለበው ከመሆንም ኣልፎ በሰሜኑ ኢትዮጵያችን በኩል የሚያቃጥለው የኣንድነት መሠረት ተጥሎ  ወደርሱ እየገሠገሠ ነው። ይህ ወያኔን እንደ ጎርፍ ውሃ ጠራርጎ  የሚወስደው በጠንካራ መሠረት ላይ የተጣለው የኣንድነት ኃይል በቅርቡ እንደታየው የተቃዋሚው  ሕዝባዊ ኃይል ከየብሔረሰቡ የተውጣጣ ሆኖ ተገኝቷል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ኣብሮነት ሊያለመልም ነው። ዱብ ዕዳ ሆኖበት ሊዋጥለት ያልተቻለውን ኣንድነትን የማፍረስ ዘመቻ የሚያፈርሱ ኃይሎች መፈጠራቸው የወያኔን መንደር እያፈራረሰው ነው። ይህ የሚያሳየን ወያኔ ለማፍረስ ደፋ ቀና ሲል የቆየውን የኣርባ ዓመት ትግል ድባቅ መታበት።

ወያኔ ከሰውም፣ ከእንስሳቱና ከደኖቹም ጋር የተጣላ ስለሆነ ተግባሩ መቀበሪያ ቦታም ሊያሳጣው ነው። ግዑዟንም መሬታችንን ደኖቿን ኣቃጥሎ ያራቆጣትና ያጎሳቆላት ስለሆነ ሲሞቱም ለመቃብራቸው ኣትመቻቸውም። ትተፋቸዋለች። ሬሳቸውን ኣውሬዎችና ኣሞራዎችም ኣይበሉም። እነርሱንም መከለያ ወይም መጠለያ ኣሳጥተዋቸዋልና ይጠየፉኣቸዋል።

ቸሩ ነኝ

ቸር ይግጠመን

abatemsas@gmail.com.

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46866#sthash.WmUfau7L.dpuf

የተናገሩት ከሚጠፋ… (በኤፍሬም ማዴቦ – ከአርበኞች መንደር)

በኤፍሬም ማዴቦ

ባለፈዉ መጣጥፌ “ቃል የእምነት ዕዳ ነዉ” ብዬ ጀምሬ “ቃላችን አይለወጥ” ብዬ ነበር የተለየኋችሁ። አለምክንያት አልነበረም እንዲህ ያልኳችሁ፤ በአንድ በኩለ ቃል መከበርም መከፈልም ያለበት ዕዳ ስለሆነ በሌላ በኩል ደግሞ ቀትር ላይ የገባዉን ቃል ሳይመሽ እንደ ጴጥሮስ ሦስቴ የሚክድ ብዙ ቃላ አባይ ሰላለ ነዉ። አገሬን ከወያኔ አጸዳለሁ ብሎ ቃል የሚገባ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዕዳ አለበት። ዕዳዉ ደግሞ ገንዘብ ወይም ንብረት አይደለም። ቃሉን መጠበቅ ወይም ቃሉን ማክበር ነዉ።Ephrem Madebo with Patriotic Ginbot 7 fighters

ደግሞም አንድ ሰዉ የተናገርዉን ቃል ሰብሮ የእምነት ባለዕዳ ከሚሆን ዕድሜ ልኩን የገንዘብ ባለዕዳ ቢሆን ይሻለዋል። የገንዘብ ዕዳ ቆይቶም ቢሆን ይከፈላል ወይም አበዳሪዉ ሊምረን ይችላል፤ የዕምነት ዕዳ ግን የማይሽር ጠባሳዉ እየቆረቆረን አብሮን ይኖራል እንጂ አይጠፋም። ማንም ሰዉ ለአገሬ ህይወቴን እሰጣለሁ ብሎ ቃል ሲገባ መሃላዉ ከህዝብና ከአገር ጋር ብቻ አይደለም፤ እንዳዉም የሰዉ ልጅ ቃል የሚገባዉ መጀመሪያ ከራሱ ጋር ነዉ። ለራሱ የገባዉን ቃል የማያከብርና ቃሌ ቃል ነዉ ብሎ የገዛ ራሱን የእምነት ዕዳ ያልከፈለ ሰዉ ለህዝብና ለአገር ቃል መግባት አይችልም። ዛሬ ወያኔን እናጥፋ ብሎ ካራ ጨብጦ አብሮኝ የቆመ ሰዉ ነገ ከወያኔ ጋር ሆኖ ካራዉን እኔዉ ላይ አዙሮ ባየዉ እሱ ቀድሞዉንም ካራ የጨበጠዉ ወያኔን ለማጥፋት ሳይሆን ስጋ ሊቆርጥብት ነዉና ብዙ አይገርመኝም። እንዲህ አይነቱን ለቁም ነገር ሲፈልጉት አልሰማ ብሎ ሆዱ ሲሞላለት ግን ሳይጠሩት አቤት የሚል ስጋ ወዳድ ሆዳም ደግሞ ኢትዮጵያ በየዘመኑ አፍርታለችና ብዙ ሊገርመን አይገባም። ከሰሞኑ ከምድረ ኤርትራ የነፈሰዉ ነፋስ ያስተማረን አንድ ትልቅ ቁም ነገር ቢኖር እንዲህ አይነቱን ሞላ ጎደለ የሚባል የካራና የስጋ ጨዋታ ነዉ። አዎ! የካራ ጨወታ – ወዲህ ማዶ ስጋ ሊቆርጡበት ወዲያ ማዶም ስጋ ሊቆርጡበት።

“የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” . . . ገዢዎቻችን በተለይ የዛሬዎቹ ቃል አባዮች እንደቆሻሻ ዕቃ መሬት ላይ ጣሉት እንጂ ቃል የዕምነት ዕዳ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ዘመን አይሽሬ የአገራችን አባባል ነዉ። አባቶቻችን የተናገሩትን ወይም ቃል ገብተዉ የተማማሉትን ነገር ከሚያጥፉ የወለዱትን ማጣት ይቀላቸዋል። እኛ ልጆቻቸዉ ግን ከዬት የመጣን ጉዶች አንደሆንን አላዉቅም ቃል አባይነታችን እኛን፤ ልጆቻቸንና አገራችንን ሲያጠፋ በአይናችን እያየን ቅር እንኳን አይለንም። “እመጣለሁ ብሎ ሰዉ እንዴት ይዋሻል፤ ማበል እንኳን አንቺን ምድር ያበላሻል” መሬት ላይ ጠብ የማይል ትክክለኛ አባባል ነዉ። አገራችን ኢትዮጵያ ትናንት እንሞትልሻለን ብለዉ ዛሬ በሚገድሏት ቃል አባይ ልጆቿ እየተበላሸች ነዉ። እነዚህ ቃልአባዮች የኢትዮጵያን የምድር ላይና የምድር ዉስጥ ኋብቷን አንጂ የገረጣዉን ፊቷን ማየት አይፈልጉም- አዎ ወያኔ የሚያየዉ ኃብትሽን፤ የሳዑዲዉ ሰዉ ወርቅሽን፤ ባዕድ ከበርቴዉ ለምለም መሬትሽን . . . ወይኔ ኢትዮጵያ ማን ይሆን የሚያየዉ የጠቆረዉ ፊትሽን፤ ማን ይሆን የሚያብሰዉ እምባሽን፤ እኮ ማን ይሆን የሚያቆመዉ መከራሺን . . . ማን ይሆን?. . . ማን ይሆን?

የዛሬዋ ኢትዮጵያ አንድ ትዉልድ ዉሸት ብቻ እየሰማ ያደገባት የዉሸት መዲና ሆናለች። ጳጳሱ፤ ቄሱና ፓስተሩ “እኔ መንገድ፤ አዉነትና ህይወትና ነኝ” ያለዉን የሰማዩን አምላካቸዉን ረስተዉ ለምድር ዉሸታሞች አደሩ። ሂዱና ዋሹ ሲባሉ ሄደዉ ዋሹ፤ እዉነትን በዉሸት አስተባብሉ ሲባሉ አስተባበሉ፤ በሀሰት መስክሩ ሲባሉ አፋቸዉን ሞልተዉ በሀሰት መሰከሩ። “ታላቁ መሪ” እየዋሸን ኖሮ እየዋሸን ሞተ። መታወቂያዉ ዉሸት ነዉና ሞቶም አልሞተም ተብሎ ተዋሸለት። ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር ምን ለምዳ ትመጣለች እንዲሉ ሌላ ሁሉ ቢቀር ዉሸትን ይፀየፋል ተብሎ የተነገረለት የዛሬዉ ጠ/ሚኒስቴር ጭራሽ “ታላቁን መሪ” እንደዋቢ እየጠቀሰ ስራዉ ሁሉ ዉሸት፤ ዉሸት፤ ዉሸት ብቻ ሆኖ ቀረ። የኢትዮጵያ ሬድዮ ሲከፈት ዉሸት ይናገራል፤ ሲዘጋ ደግሞ ነገ ስለሚዋሸዉ ዉሸት ያስባል። ጋዜጦች በስህተት አንኳን እዉነት አይጻፍባቸዉም። የኢቲቪ ዜና አንባቢ ተመስገን በየነ ግማሽ ሰዐት የዋሸዉን ዉሸት ለማካካስ ዜናዉን አንብቦ ሲጨርስ ለ15 ደቂቃ ጎንበስ ብሎ ይሰግዳል።

ለረጂም ግዜ ተማምነን ጀርባችንን የሰጠነዉ ሰዉ ለጠላት እጁን ሰጥቶ ጦርነት ሲያዉጅብን አንዳንዴ በትግሉ ዉስጥ ማንን አምነን ጀርባችንን እንደምንሰጠዉ ግራ ሊገባን ይችላል። ከሰሞኑ የሰማነዉ ዜና እንዲህ ግራ የሚያጋባ ዜና ነዉ። ሆኖም ሳንተማመን ትግል ብሎ ነገር የለምና የትግል ጓዶቻችንን ማመን ብርታት እንጂ ደካሞች እንደሚሉት ሞኝነት ወይም የዋህነት አይደለም። በጓዶቻችን ላይ ክህደት ፈጽመን ከምናሰቃያቸዉ እኛ ብንሰቃይ ይሻላል፤ ደግሞም ጓዶቻችንን ማመን አቅቶን በጥርጣሬ ተፋጥጠን ባለንበት ከምንረግጥ አንዳንዴ አዉቀንም ቢሆን ብንታለል ብዙ መንገድ መጓዝ እንችላለን። ትግል በተለይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ከሚያስተምረን ትምህርቶች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ሌሎች በኛ ላይ እምነት እንዲኖራቸዉ ከፈለግን እኛ አስቀድመን ልናምናቸዉ አንደሚገባን ነዉ። አለዚያ ሁለታችንም አንተማመንም። አለመተማመን ደግሞ ያጠፋፋናል እንጂ አንድ ቤት ዉስጥ አብሮ አያኖረንም። እንደኔ እንደኔ የወያኔን ስርዐት ደምስሰን ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር የምናደርጋት እያንዳንዳችን ለትግል ጓዶቻችን የገባነዉን ቃል ሰብረን ረጂም ህይወት ከመኖር ቃላችንን አክብረን ዛሬዉኑ መሞትን ስንመርጥ ብቻ ነዉ። ወያኔ አንደ እሳት የሚፈራዉና በፍጹም የማያሸንፈዉ አንዲህ አይነቱን ከብረት የጠነከረ ጽኑ አቋማችንን ብቻ ነዉ። ለዚህ ነዉ እንዲህ አይነት ጽናት የሌላቸዉን ደካማ ግለሰቦች ፈልጎ እያማለለ ጽናታችንን የሚፈታተነዉ። ከሰሞኑ ለህዝብ ከመታገል ህዝብን መታገል መርጦ ከለየላቸዉ የህዝብ ጠላቶች ጋር የተቀላቀለዉ ሞላ አስገዶም ለዚህ ዉሳኔ የበቃዉ ህዝባዊዉ ትግል የሚፈልገዉ የአለማ ጽናት የሌለዉ ደካማ ግለሰብ ስለሆነ ብቻ ነዉ። ዉድ ኢትዮጵያዉያን ክህደት ትናንት ነበር፤ ዛሬ አለ፤ ነገም ይኖራል። ስለዚህ ክህደት ሊያስተምረን እንጂ በፍጹም ሊያስበረግገንና አንገታችንን ሊያሰደፋን አይገባም። ክህደትና ከሀዲዎችን እያሰላሰልን የምንኖር ከሆነ የበለጠ እንዲጎዱን ተጨማሪ ዕድል እንሰጣቸዋለን እንጂ ሌላ ምንም የምንፈይደዉ ፋይዳ የለም።

ሞላ አስገዶም እሱን የመሰሉ ደካማ ጓደኞቹን ከተቀላቀለ በኋላ መቀሌ፤ አዲስ አበባና አዳማ ዉስጥ ክህደቱን አስመልክቶ እርስ በርሳቸዉ የሚጣረሱ ሦስት ጋዜጣዊ መግለጫዎችን ሰጥቷል። እርግጠኛ ነኝ ይህ ቁርስ ላይ የተናገረዉን ምሳ ላይ የማያስታዉስ ግለሰብ በተያዘለት የጉብኝት ሰሌዳ መሠረት ዘጠኙን ክልሎች የሚዞር ከሆነ ዘጠኝ የተለያዩና እርስ በርሳቸዉ የሚጣረሱ ምክንያቶችን መደርደሩ አይቀርም። የወያኔ የመረጃና የደህንነት መ/ቤት ተብዬዉም ቢሆን ምን ያህል የዉሸትና የጉራ ቤት ለመሆኑ መረጃ ብሎ የለቀቃቸዉን ዉሸቶችና ቱልቱላዎች መጥቀሱ ይበቃል። ለምሳሌ የመረጃና ስለላ ድርጅቱ ከአንድ አመት በላይ ከሞላ አስገዶም ጋር በሚስጢር ይሰራ እንደነበር ተናግሯል። ይህ እዉነት ከሆነ የደምህት ታጋዮች በዚህ አንድ አመት ግዜ ዉስጥ በወያኔ ታጣቂዎችና ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ለወሰዷቸዉ እርምጃዎች በተለይ እግር ኳስ ጨዋታ በመከታተል ላይ እንዳሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር እንዳለ ለተደመሰሱት የኢትዮጵያ ወታደሮች ተጠያቂዉ ከሞላ አስገዶም ጋር ይሰራ የነበረዉ የወያኔ የመረጃና የስለላ ድርጅት ነዉ ማለት ነዉ።

ሞላ አስገዶም ትናንት ከኛ ጋር ሆኖ እኛ ሲል ነበር፤ ዛሬ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጠለቶች ጋር ሆኖ እኛ ይላል። ይህ ሰዉ “እኛ” ሲል የሱ እኛ እነማንን እንደሚያጠቃልል አይታወቅም፤ እሱ እራሱም የሚያዉቀዉ አይመስለኝም። ሞላ አስገዶም ወያኔን እንደተቀላቀለ አፉን ሞልቶ ጥምረቱን የፈጠርነዉ “እኛ” ነን ብሎ ሲናገር በተደጋጋሚ ተደምጧል። ጥምረቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና ህዝባዊ ትግሉ የደረሰበት የዕድገት ደረጃ ዉጤት ነዉ እንጂ ሞላ አስገዶም ስለፈለገዉ የሚፈጠር አለዚያ የሚቀር የሞላ አስገዶም የቤት ዉስጥ ዕቃ አይደለም። ደግሞም እንደ ሞላ አስገዶም ፍላጎት ቢሆን ኖሮ የደምህት ጥምረቱ ዉስጥ መግባት ለግዜዉም ቢሆን ሊዘገይ ይችል ነበር። ደምህት ጥምረቱ ዉስጥ ገብቶ አገር አድን የጋራ ንቅናቄዉ የተፈጠረዉ የደምህት ሠራዊትና ከሞላ አስገዶም ዉጭ ሁሉም የደምህት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከሌሎች ኢትዮጳያዉያን ወገኖቻቸዉ ጋር ሆነዉ በጋራ ለመታገል በመወሰናቸዉ ነዉ። የሞላ አስገዶም ፈርጥጦ ወያኔ ጉያ ዉስጥ የመሸጎጡ ዋነኛዉ ምክንያትም የዚህ ዉሳኔ ዉጤት ነዉ እንጂ የወያኔ መረጃና ስለላ ድርጀት ሚስጥራዊ ግንኙነት ዉጤት አይደለም። ሌላዉ እርስ በርሱ የሚጋጭ የወያኔ ዉሸት – በአንድ በኩል ሞላ አስገዶምና የደምህት ሠራዊት ሙሉ ትጥቃቸዉን እንደታጠቁ ጠቅልለዉ ወደ አገራቸዉ ተመለሱ የሚለዉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ቁጥሩ ወደ 700 የሚጠጋ የደምህት ሠራዊት ወደ አገሩ ተመለሰ የሚለዉ የተምታታ ዘገባ ነዉ። እዚህ ላይ የደምህትን ሠራዊት ብዛት መናገሩ አስፈላጊ ባይሆንም ግንዛቤ ማግኘት የፈለገ ሰዉ ግን ተመድ ያወጣቸዉን ሪፖርቶች መመልከቱ የሚበቃ ይመስለኛል። ደግሞም ሞላ አስገዶም አታልሎ መንገድ ካስጀመረዉ ሠራዊት ዉስጥ ገሚሱ ወደ ትግሉ ሜዳ ተመልሷል፤ የተቀረዉ ደግሞ ወደ ትግሉ ሜዳ ካልተመለስኩ እያለ ከሱዳን ባልስልጣኖች ጋር እየተደራደረ ነዉ። በነገራችን ላይ የዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ ሞላ አስገዶም አታልሎ ሀምዳይት ከወሰዳቸዉ በኋላ ትግል ወይም ሞት ብለዉ ተመልሰዉ ከትግል ጓዶቻቸዉ ጋር ከተቀላቀሉ ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን ጋር አብሮ ቡና ጠጥቷል።

ጓዜን ጠቅልዬ ትግሎ ሜዳ ከመግባቴ በፊትም ሆነ ከገባሁ በኋላ የደምህት ስም በተነሳ ቁጥር አብረዉ የሚነሱ ሁለት መላምቶች አሉ። አንደኛዉ መላምት ደምህት የኤርትራ መንግስት ሆን ብሎ የፈጠረዉና ጭራሽ ኤርትራ ዉስጥ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎችን ተክቶ በመንግስታዊ ተቋሞች ጥበቃና ደህንነት ስራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ነዉ የሚል መላምት ሲሆን ሁለተኛዉ መላምት ደግሞ ሞላ አስገዶም በኤርትራ መንግስት ድጋፍ ሁለተኛዉ መለስ ዜናዊ ሆኖ ህወሃትን ተክቶ አትዮጵያን ይመራል የሚለዉ መላምት ነዉ። ደግነቱ የነዚህ መላምቶች የማዕዝን ራስ የሆነዉ ሞላ አስገዶም ኮብልሎ ወያኔን መቀላቀሉና ከተቀላቀለ በኋላ የሰጣቸዉ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ሁለቱንም መላምቶች እንዳልነበሩ አድርጓቸዋል። እኔን አልገባ ያለኝና በጣም የሚገርመኝ ግን በአንድ በኩል የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ትብብር እንዲፈጥሩ አይፈልግም ይባላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ጥምረቱ የተፈጠረዉ በሻዕቢያ ግፊት ነዉ ይባላል። መቼም ገና በልጅነቴ ካልጃጀሁ በቀር ሻዕቢያና የኤርትራ መንግስት መሃል ልዩነት ያለ አይመስለኝም። ሌላዉ የሰሞኑ አስቂኝ ድራማ ደግሞ ሞላ አስገዶም ጥምረቱን የፈጠርነዉ እኛ ነን ሲል የሱን መኮብለል አስመልክቶ የሚሰጠዉ አስተያያት ደግሞ ሞላ አስገዶም ጨርቁን ጠቅልሎ ወያኔን የተቀላቀለዉ ብርሀኑ ነጋ በኤርትራ መንግስት ግፊት የጥምረቱ ሊ/መንበር መሆኑ አልዋጥ ብሎት ነዉ ይባላል።

ሌላዉ አሁን በቅርቡ ወይም ከሞላ አስገዶም መኮብለል በኋላ የተጠነሰሰዉ መላምት ደግሞ ደምህቶች እራሳቸዉ ኤርትራ ዉስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ ድርጅቶች በወያኔ ስርዐት ላይ ወታደራዊ እርምጃ መዉሰድ እንዳይችሉ ሆን ተብለዉ በወያኔ የተፈጠሩ እንቅፋቶች ናቸዉ የሚለዉ መላምት ነዉ። በኔ ግምት ይህኛዉ መላምት ከሁሉም መላምቶች የከፋና እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ጽንፈኛ መላምት ነዉ። እንደዚህ መላምት ፈጣሪዎች አባባል የትግራይ ህዝብ በህወሃት አመራር በደል አይደርስበትም ወይም የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ሆኖ የህወሃትን ግፈኛ ስርዐት አይታገልም ማለት ነዉ። እንዲህ አይነቱ ጭፍንነትና ጠባብነት የሚመነጨዉ ደግሞ ሞላ አስገዶምንና ደምህትን ወይም ህወሃትንና የትግራይን ህዝብ ለያይቶ ማየት ካለመቻል አባዜ ነዉ። በደርግ ስርዐት ዉስጥ ጭቆናዉና በደሉ በዛብኝ ብሎ ጠመንጃ ያነሳዉ ጀግናዉ የትግራይ ህዝብ ህወሃት ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹ ተነጥሎ እንዲታይ ለማድርግ የሚሸርብበትን ሤራና የሚያደርስበትን ግፍና መከራ አፉን ዘግቶ የሚቀበልበት ምንም ምክንያት የለም። ስለዚህ ደምህት የትግራይ ህዝብ ብሶትና ምሬት አምጦ የወለደዉ ፀረ ህወሃት ንቅናቄ ነዉ እንጂ ወያኔ የፈጠረዉ ድርጅት አይደለም፤ሊሆንም አይችልም። ሞላ አስገዶምም ቢሆን የራሱ የተጠረቃቀመ ድክመት ከንቅናቄዉ ሊ/መንበርነቱ እንደሚያስነሳዉ ሲያዉቅ የፈረጠጠ ፈርጣጭ እንጂ እሱና ወያኔ እንደሚሉት የአንድ አመት ቀርቶ የአንድ ወርም ተከታታይ ግንኙነት አልነበራቸዉም።

ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረከ ብቅ ብለዉ የጠፉትንም ሆነ ዛሬም ድረስ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች ባህልና ድርጅታዊ አሰራር ስንመለከት የድርጅቶች ህልዉና መመዘኛና የማንነታቸዉ መለኪያ ቆምንለት የሚሉት አላማ ሳይሆን የመሪዎቻቸዉ በተለይ የዋናዉ መሪ ተክለሰዉነት ነበር። የድርጅት ወይም የፓርቲ ሊ/መንበር ከድርጅቱ ባለይ ነዉ፤ እሱ ይሁን ያለዉ ይሆናል፤አይሁን ያለዉ አይሆንም። ብዙ ግዜ የድርጅት/ፓርቲ ሊ/መንበር ድርጅቱን የማፍረስ አቅም ጭምር አለዉ። ይህንን ደግሞ በቅርብ ግዜ ታሪካችን በተደጋጋሚ አይተናል። አንድን ድርጅት ወይም ፓርቲ አባላት ሲቀላቀሉ የሚመለከቱት የፓርቲዉን ሊ/መንበር እንጂ የፓርቲዉን የፖለቲካና የኤኮኖሚ ፕሮግራም አይደለም። የፓርቲ ሊ/መንበርም ቢሆን የኔ የሚላቸዉን ሰዎች ነበር እየመረጠ የሚያሰባስበዉ። እንደዚህ አይነቱ የፓርቲ አደረጃጀትና አሰራር አሁን እየተቀየረ የመጣ ቢሆንም ለረጂም ግዜ የፖለቲካ ትግላችን ችግር ሆኖ ቆይቷል። ሞላ አስገዶም በቅርቡ የደምህትን ሠራዊት ከነሙሉ ትጥቁ ይዤ ኢትዮጵያ ገባሁ ብሎ በድፍረት የተናገረዉ ንግግር ይሄዉ የድርጅት ሊ/መንበር ያሰኘዉን ሁሉ ማድረግ ይችላል የሚለዉ የቆየ የፖለቲካ ባህላችን በሽታ ተጠናዉቶት ነዉ። “ዝንጀሮዉን ከጫካ ያዉጡታል እንጂ ጫካዉን ከዝንጀሮዉ ዉስጥ አያወጡትም” የሚል ብህል አለ፤ ትክክለኛ ብህል ነዉ። ሞላ አስገዶም ህወሃት/ወያኔ የኢትዮጵን ህዝብ በአጥር እየለያየ በትናናንሽ ጎጆዎች ዉስጥ ማኖሩ አልዋጥ ብሎት ሁሉንም የሚያቅፍ ሰፊ ቤት ሰርተን ኢትዮጵያን የዲሞክራሲ አገር እናደርጋለን ብሎ ለብዙ አመታት የታገለ ሰዉ ነዉ። ችግሩ ሞላ አስገዶም ነዉ ከነዚያ ትናንሽ የወያኔ ጎጆዎች የወጣዉ እንጂ ትናንሽ ጎጆዎቹ ከሞላ አስገዶም ዉስጥ ስላልወጡ እንደ ማግኔት እየሳቡት ወደነበረበት ቦታ መልሰዉታል። ለሁሉም የሞላ አስገዶም ታሪክ ሲጻፍ – መጣና ሄደ ከሚሉ አምስት ሆሄያት የዘለለ ምንም ቁም ነገር የለዉም። እየመጡ መሄድና እየሄዱ መምጣት ደግሞ ትናንሽ ቤት የሚናፍቃቸዉ ትናንሽ ሰዎች እስካሉ ድረስ ይቀጥላል።

ሁለት ሺ ሰባት ሊጠናቀቅ ሦስት ቀን ሲቀረዉ አንድ የብዙ ኢትዮጵያዉያንን ጆሮ የሳበ ዜና ቴሌቪዥኑን፤ ሬድዮኑን፤ ጋዜጣዉንና ድረገጹን ተቆጣጠረዉ። ዜናዉ የወያኔ/ህወሃትን ስርዐት በመሳሪያ ኃይል የሚታገሉ አራት ድርጅቶች አገር አድን የጋራ ንቅናቄ ፈጠሩ የሚል የአዲስ አመት የምስራች ነበር። የኢትዮጵያ ህዝብ ለረጂም ዘመን የናፈቀዉ የምስራች ነበር። ግን ምን ያደርጋል – በጥባጭ እያለ ንጹህ ዉኃ አይጠጣምና ይሀንን የአዲስ አመት የምስራች ሰምተን ሳናጣጥም ነበር የሞላ አስገዶምን ዜና ክህደት የሰማነዉ። አስደንጋጭ ዜና ነበር። በእርግጥም የአራት ድርጅቶች ጥምረት ተፈጠረ የሚል ዜና በተሰማ ማግስት የጥምረቱ ምክትል ሊ/መንበር ሠራዊት እየመራ ሄዶ ወያኔን ተቀላቀለ የሚል ዜና መስማት የሚያስደነግጥና በመጀመሪያዉ ዜና ላይ ቀዝቃዛ ዉኃ የቸለሰ ልብ ሰባሪ ዜና ነዉ። ደግነቱ ሁሉም ነገር ለበጎ ነዉ። የሞላ አስገዶም መክዳት ተራ ዜና ነዉ ማለቴ አይደለም። ግን ሞላ አስገዶምና የወያኔ መረጃ ድርጅት በትብብር ሠራነዉ ያሉት አዲስ ድራማ ተዉኔቱ ሳይጻፍ አየር በአየር የተከወነ ምናቡ ያልተባ ድራማ በመሆኑ ድራማዉ ከያኒዉን ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብና ለአንድነቱና ለነጻነቱ የሚታገሉ ልጆቹን በከፍተኛ ደረጃ የጠቀመ መሆኑን ማሳዉቁ አስፈላጊ ይመስለኛል።

ደምህት በዚህ የወያኔ ድራማ ዉስጥ በእሳት ተፈትኖ ወርቅነቱን አረጋግጧል። ሞላ አስገዶም የደምህትን ሠራዊት ለወያኔ አስረከብኩ ብሎ በተናገረ ማግስት የደምህት መሪዎች የሰጡት አርቆ አስተዋይነት የታየበት አመራርና ያሳዩት ቆራጥነት የፖለቲካ ድርጅቶቻችን የደረሱበትን የዕድገት ደረጃ በግልጽ አሳይቷል። ደምህት እራሱም እንደ አንድ የትግል ድርጅት የተደቀነበትን አደጋና ፈተና በጣጥሶ በመዉጣት በትናንሾችና በደካሞች ሴራ በፍጹም የማይናጋ ጠንካራ ድርጅት መሆኑን በተግባር አሳይቷል። የዛሬዉ ደምህት ዉስጡን ከአድርባዮች ያፀዳ ሁለትና ሦስት እርምጃዎች ወደፊት የተራመደ ጠንካራ ድርጅት ነዉ። እርግጠኛ ነኝ ይህ የደምህት መሪዎች ያሳዩት አስተዋይነት፤ ጽናትና ቆራጥነት እኔ የምፈልገዉ ነገር ካልሆነ ድርጅቱን በአፍጢሙ እደፋዋለሁ ብለዉ ለሚያስቡ ዕብሪተኛ መሪዎች ጥሩ ትምህርት ነዉ። ሌላዉ የሞላ አስገዶም ክህደት በግልጽ ያሳየን ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ የሀዝብ መብትና ነጻነት ይከበር በሚሉ የነጻነት ሀይሎችና ህዝብን ረግጠን እንገዛለን በሚሉ ፀረ ህዘብ ሀይሎች ለሁለት መከፈሉን ነዉ። ወደድንም ጣላን ካሁን በኋላ ያለን አማራጭ ሁለት ብቻ ነዉ፤ ወይ ወያኔ ሆኖ ከህዝብ ጋራ መዋጋት ወይም ከህዘብ ጋር ሆኖ ወያኔንና ስርዐቱን መዋጋት። ሞላ አስገዶም ጎራዉን ለይቷል፤ እኛም ጎራችንን እንለይ። መኃል ቆሞ መመልከት አብቅቷል።

ጠላቴን አግዝፌ መመልከት አልወድም፤ ትንሽ ነዉ ብዬም ጠላቴን በፍጹም አልንቅም። በቅርቡ የወያኔ የመረጃና ደህንነት መ/ቤትና ሞላ አስገዶም ከአንድ አመት በላይ አብረን ሠራን ያሉትን የጀማሪዎች ስራ ስምለከት ግን ወያኔ/ህወሃት “የምትሰሩትን ብቻ ሳይሆን የምታስቡትን ጭምር የሚያይ አይን አለኝ” እያለ የኢትዮጵያን ህዝብ ከማስፈራራት ዉጭ የረቀቀ የመረጃ ስራ መስራት ቀርቶ አረፍተነገሮችን አገጣጥሞ ለጆሮ የሚጥም ንግግር ማድረግ የሚችል አዋቂ የሌለበት የባዶዎች ድርጅት መሆኑን ነዉ የተረዳሁት። ሞላ አስገዶምም በወዶገባነት ሄዶ የተቀላቀለዉ ይህንኑ አዋቂ የሌለበትን እሱን የመሰለ ድርጅት ነዉ። ይህንን ደግሞ እስከዛሬ በሰጣቸዉ ቃለመጠይቆች በግልጽ አይተናል። ህወሃት/ወያኔን እስከዛሬ በሥልጣን ላይ ያቆዩት ሁለት ነገሮች ቢኖሩ አንዱ ጠመንጃ ሁለተኛዉ የኛ የነጻነት ኃይሎች መበታተን ብቻ ነዉ።

ነገ የምንፈልጋት ኢትዮጵያ እንደ መኪና ተገጣጥማ አትጠብቀንም – የዛሬዉ ጥረታችንና ድካማችን ዉጤት ናት። ኢትዮጵያና ህዝቧ ከወያኔ ሲፀዱ የሚነፍሰዉ የነጻነት አየር ሁላችንንም ቢያስደስትም ደስታዉ የሚገለጸዉ በግለሰብ ደረጃ ነዉ። ዛሬ ከጠላት ጋር ተፋልመን የተቀማነዉን ነፃነት ማስመለስና እንደገና እንዳንቀማ ነቅቶ መጠበቅ ግን የሁላችንም የጋራ ሀላፊነት ነዉ። እንግዲህ ወገን ወገባችንን ጠበቅ የምናደርግበት ግዜ አሁን ነዉና ሁላችንም በየተሰለፍንበት መስክ እንበርታ። ጠላታችን ጠንካራ መስሎ የሚታየዉና ያለ የሌለ ጡንቻዉን የሚያሳርፍብን የማይቀረዉን ድል ማሽተት ስንጀምር ነዉ። የድል መአዛችንን የምናሸትበት ግዜ ደግሞ ሩቅ እንዳይመስለን ነገና ከነገ ወዲያ ነዉ። ከወላዋይና እዚህም እዚያም እየዘለለ ከሚያዘናጋን አጉል ጓደኛ አንዱኑ የለየለት ጠላት ይሻላልና የሞላ አስገዶም ክህደት ትግላችንን ሊያጠራዉና መንገዳችንንም ሊያሳጥረዉ ይገባል እንጂ በፍጹም ግራ ሊያጋባን አይገባም። አይዞን. . . ሞኝ ከዘመዱ ከሚያገኝዉ ጥቅም አዋቂ ከጠላቱ የሚያገኘዉ ጥቅም ይበልጣልና ጠላቶቻችን የፈጠሩልንን አጋጣሚዎች ሁሉ በሚገባ እንጠቀምባቸዉ እንጂ ለጠላት አንመቻች። ጠላታችን እየተሳሳተልን ነዉ፤ ጠላት ሲሳሳት ማቋረጥ ነዉር ነዉ። ቸር ይግጠመን!!!

አፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር ebini23@yahoo.com

Neamin Zeleke tells ESAT “The struggle for freedom & democracy reached a critical stage”

ESAT News 

Mr. Neamin Zeleke, Head of Foreign Affairs of Patriotic Ginbot 7 International Leadership and a member of AG7 Council, told ESAT that the formation of United Movement for the Salvation of Ethiopia through Democracy has elevated the struggle for freedom and democracy in Ethiopia to a higher level.Ato Neamin Zeleke Patriotic Ginbot 7 leadership member

Mr. Neamin travelled to Eritrea and remained there for three months before returning at the end of last week. He said Ethiopian opposition forces unequivocally have full confidence in the government of Eritrea and highly appreciative of the support it has been proving for Ethiopian liberation forces. Mr. Neamin also affirmed that the Eritrean government does not make undue interference in the internal affairs of Ethiopian forces based in Eritrea.

Mr. Neamin condemned certain groups and individuals who have made a carrier out of fabricating baseless stories that would shed negative light on Ethiopian opposition based in Eritrea. He said the misinformation and blackmailing that few individuals disseminate about the government of Eritrea, Ethiopian opposition forces, and the leaders of these organizations are groundless and utterly fictitious. He called for Ethiopians from all walks of lives not be hoodwinked by these uncanny individuals with nefarious agenda that is contrary to the primacy of the struggle and its ultimate objective— the liberation of Ethiopia from the Woyane ethnocentric and brutal dictatorship.

Asked about the defection of Mola Asgedom, Chairman of Tigray People’s Democratic Movement, Mr. Neamin stated that the defection of individuals like Mola, who has been hatching a hidden agenda aligned with the ruling TPLF cabal on Friday September 11, 2015, was not surprising as such. “These kinds of defections are common in other struggles, in our own recent political history too, and that it is a blessing in disguise that Mola Asgedom defected early before inflicting heavy damage at a later stage.”

Mr. Neamin left for Eritrea three months ago with a mission to accomplish several tasks. He said, there was a need to assess and discuss the situation with the leadership on the ground. Second, he went to Eritrea to assess and facilitate the relocation of senior leaders, including Berhanu Nega, to Eritrea. In addition, he said that there was a need to reach to an agreement and understanding on a number of vital issues with members of the leadershipon the ground, as well as many other tasks that could not be discussed on the media.

Asked why he did not remain in Eritrea like the other senior leaders, Mr. Neamin told ESAT that “The struggle for democracy and freedom is multi-faceted , waged on many fronts , and based in several geographic locations; senior leaders such as Professor Berhanu Nega, Ato Ephrem Madebo, and others will be based in Eritrea to coordinate the struggle along with other members of the senior leadership on the ground based in Eritrea and inside the country; others, like me, have to travel back and forth to coordinate foreign relations, intelligence , public relations, and others tasks of the organization that has components both on the ground, inside Ethiopia, and around the world.”

It was reported that Professor Berhanu Nega and other senior leaders would be based in Eritrea until freedom is achieved in Ethiopia. Yet, members of the international leadership would be traveling back and forth to Eritrea and elsewhere when necessary, Mr. Neamin added.

Mr. Neamin stressed the need to mobilize, focus and intensify the struggle of all Ethiopians diaspora in their endeavor to bring about democracy, freedom and justice for the people of Ethiopia under the yoke of the TPLF/EPRDF ethnocentric and dictatorial regime.

Currently Ethiopian armed opposition groups are well organized and have built significant clandestine networks throughout Ethiopia to wage a full scale offensive against the TPLF forces, the senior leader told ESAT.
It is to be recalled that an agreement was reached very recently among four independent opposition forces on programs and outcomes of the struggle in Ethiopia, thus forming United Movement for the Salvation of Ethiopia through Democracy. Last week, Prof. Berhanu told ESAT that Ethiopia did not need several armed factions that lack confidence in each other but claiming to have the same objectives. Hence, building a unified political movement and a liberation force under a unified command is an essential condition to salvage the country from disintegration a top priority.

የመቀሌ አማርኛ በአዲስ አበባ

mekele
ከአቻምየለህ ታምሩ

ከዚህ ጽሁፍ ጋር አያይዤ የለጠፍኳቸውን የባቡር ጣቢያ ስሞች ስመለከት አዲስ አበባ ወደ መቀሌ የሄደች መስሎ ተሰማኝ። መቀሌ ብዙ ድርጅቶች ከትግርኛ ይልቅ በአማርኛ ማስታወቂያ መለጠፍ ይቀናቸዋል። መቀሌ ውስጥ አማርኛ የቢዝነስ ማስታወቂያ መጻፊያ ቋንቋ ነው። መቀሌ በአማርኛ የቢዝነስ ማስታወቂያ እንደመጻፏ መጠን ለቃላትና ለሆሄያት ግድፈት ግን ግድ የላትም። መቀሌን ለአመታት ለሚያቃት ሰው የአማርኛ ሆሄያትን በማሳከር ባለሁለት ዲጂት እድገት እያስመዘገበች ያለች ከተማ ልትመስለው ትችላለች።

ምስጉን ተስፋይ የሚባል ጎበዝ የአዲግራት ልጅ አንድ የግጥም መድበል አሳትሟል። የግጥም መድበሉን ያሳተመው በአማርኛ ነው። የምስጉንን ግጥሞች አንብቦ መረዳት የሚችል ቢኖር እንደኔ አይነት በአማርኛ አፉን የፈታ ሳይሆን የትግራዋይ አማርኛ [Tigrian Amharic ] የሚችል ሰው ብቻ ነው። ምስጉን ተስፋይ መጽሀፉን ሲጽፍ አማርኛውን በማረም ያገዘውን ወንድሙን አመስግኗል። ግን ወንድሙም ልክ እንደ ምስጉን የትግራዋይ አማርኛ ተናጋሪ በመሆኑ የተነሳ የግጥም መድበሉ የአማርኛ እርማት የተደረገለት ሳይሆን የአማርኛ መፋለስ ተደርጎለት ለመታተም የበቃ ነው የሚመስለው። ሁለቱም የትግራዋይ አማርኛ ጽሁፍ «ጸሀፊዎች» በመሆናቸው ለምስጉን ያልታየው የአማርኛ እርማት ችግር ለወንድሙ ሊታየው አይችልም።

መቀሌ ከተማ በየንግድ ተቋሙና በየአደባባዩ ከተለጠፉ የንግድ ማስታወቂያዎች መካከል ባልተሳካ አማርኛ ከተጻፉት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፤«ሞቫይል ቆፎ ንሸጣለን»፤ «ካራ ቡላ ናጫወታለን»፤ «ሞቫይል ካርድ አሎ»፤ «ሞቫይል ቆፎ ንጠግናለን» «ተራንስ ፎርሜሽኑ ይሳካል» «ኤመይል ንከፍታለን»፤ «ፍስ ቡክ ናስጠቕማለን»፤ «ባለማጮሶ ንመስግንናለን»፤«ዃረንቡላ አንጫወታለን»፤«የተዘጋ ዋሃ ንሸጣለን» [የታሸገ ውሀ እንሸጣለን ለማለት ነው] ወዘተ።

መቀሌ በአማርኛ ለሚጻፉ ማስታወቂያዎች ብቻ ሳይሆን በእንግሊዝኛ ቋንቋም ለሚጻፉ ማስታወቂያዎች ግድ የላትም። የቢዝነስ ማስታወቂያዎችን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ጽፈው የሚለጥፉት አብዛኛውን ጊዜ የአውሮፓን የእግር ኳስ ጨዋታዎችን የሚያሳዩ የDSTV ቤቶችና ፊልም የሚያከራዩ ሙዚቃ ቤቶች ናቸው። «Prison Break» የተሰኝውን የእንግሊዝኛ ፊልም የሚያከራዩ አራት መደዳውን የተሰደሩ ሙዚቃ ቤቶች ማስታወቂያውን የሚያስቅ እንግሊዝኛና አማርኛ ቀላቅለው ጽፈውት ተመልክቻለሁ። የመጀመሪያው «ድንኳን [በትግርኛ ሱቅ ማለት ነው» ማስታወቂያውን <«prison brike» ዚህ ይገኛሉ> ብሎ ለጥፎታል። ሁለተኛው ቪዲዮ አከራይ ደግሞ <«perison braik» በዝካረ ይገኛሉ> ይላል። ሶስተኛው ቪዲዮ ቤት ሙሉ በሙሉ «የእንግሊዝኛ» ቃላትን ተጠቅሞ «price break four rent» ይላል። አራተኛው ነጋዴ ደግሞ በፋንታው <«prisim brek» ፊልም ናከራያለን> ሲል ለጥፏል።

ሌላ መቀሌ የማውቀው የንግድ ድርጅት በተለምዶ ሀውዜን አደባባይ ከሚባለው የከተማይቱ አነስተኛ አደባባይ በስተቀኝ አቅጣጫ በግምት አንድ መቶ ሜትር ያህል ገባ ብሎ በግራ በኩል «ናቲ ምሿለኪያ ካፌና ሬስቶራንት» ይሰኝ የነበረን ቤት ነው። እኔና ጓደኛዬ «ናቲ ምሿለኪያ ካፌና ሬስቶራንት» በተደጋጋሚ እየተገናኘን የቤቱን «ስፔሻል ምግብ» ተመግበናል። አዲስ አበባ ላይ «ምሿለኪያ» የሚል የባቡር መተላለፊያ ተጽፎ ሳነብ ቀጥታ ወደ ጭንቅላቴ የመጣው መቀሌ ከተማ የማቀው «የናቲ ምሿለኪያ ካፌና ሬስቶራንት» ነበር። ለዚያም ነው የጽሁፌን ርዕስ «የመቀሌ አማርኛ በአዲስ አበባ» ብዬ የሰዬምሁት።

የመቀሌን «ድድ ማስጫዎች» ተዘዋውሮ ለጎበኘ በመቀሌ ከተማ የንግድ ማስታወቂያዎችን ከፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ «ባነር» መለየት ይቸግረዋል። በተለይ ዋናው የህወሀት ጽህፈት ቤት አካባቢ በሚገኙ የንግድ ቤቶች ላይ የሚለጠፉ የንግድ «ማስታወቂያዎችን» ላስተዋለ ንግድ ቤቶቹ እቃና አገልግሎት መሸጣቸውን ትተው ፕሮፓጋንዳ መሸጥ የጀመሩ ነው የሚመስሉት። ሰላሳ ዘጠነኛው የህወሀት ልደት መቀሌ ከተማ ሰማህታት አዳራሽ ሲከበር ህወሀት ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ባለ አንድ ካፌ ደጅ ተቀምጠን እኔና ጓደኛዬ ሻይ ቡና እያልን ባካባቢው የሚካሄደውን እንቅስቃሴ እየታዘብን ነበር። ሻይ ቡና በምንልበት ካፌ በር ላይ «መለስ ጅግና እዩ፤ጀግና አይሞትም» ከሚል መፈክር ስር «Meles is alive» የሚል የእንግሊዝኛ ፍቺ ተሰጥቶት መፈክሩ ተሰቅሎ ነበር። ይህ መፈክር ዋናው ህወሀት ጽህፈት ቤት ውስጥም ተሰቅሎ እንደነበር ለማወቅ ችያለሁ።

በአጠቃላይ መቀሌ የተቀመጠ አንድ ለአቅመ ፖለቲካ የደረሰ ሰው ትናንትና የተለቀቁትን የአዲስ አበባ ባቡር ጣቢያ ስሞች ሆሄያት መጣመምን ሲመለከት አዲስ አይሆንም። ይልቁንም ድርጊቱ አዲስ አባባ ላይ ሊፈጸም የቻለው አንድም የባቡር ጣቢያ ስሞቹ መቀሌ ሄደው የተጻፉ መሆን አለባቸው ብሎ ሊያስብ ይችላል፤ አልያም የመቀሌን ማስታወቂያዎች የሚያትሙ ባነር ጻፎች አዲስ አበባ መጥተው የጣቢያ ስሞችን ለመጻፍ የተደረገውን ውድድር «አሸንፈው» ከመቀሌ ይዘው በመጡት የሆሄ መቅረጫ የአዲስ አበባን የባቡር ጣቢያ ስሞች ወደ ማተሙ ገብተዋል ብሎ ያስባል።

በአዲስ አበባና በመቀሌ በተፈጸሙ የሆሄያት ግድፈቶች መካከል ግን አንድ ልዩነት ይታየኛል። የመቀሌ ማስታወቂያዎች ግድፈት የአማርኛ ሆሄያት ብቻ አይደለም፤ የመቀሌ ማስታወቂያዎች ለእንግሊዝኛ ፊደሎችም ግድ የላቸው። የአዲስ አበባዎቹ ግን የአማርኛ ሆሄያቱ ስህተትም ቢሆኑ የእንግሊዝኛ ስሞች ግን በስህተት የተጻፉትን የተሳከሩ የአማርኛ ሆሄያት ተከትሎ በትክክል የተቀረጹ ናቸው። አዲስ አበባ በተሳከረ አማርኛ ተጽፈው ወደ እንግሊዝኛ ሲለወጡ ግን ወጥነት የሚባል ነገር ገደል ገብቷል። ሲያሻቸው ሙሉውን በupper case letters ሌላ ጊዜ ሲፈልጉ ደግሞ በsentence case ጽፈውታል። ይህንን መፋለስ አጸደ ህጻናት ያሉ ልጆች እንኳ አይፈጽሙትም።

በመጨረሻ ከማስታወቂያ ሆሄያቱ ግድፈት ጀርባ ስላለው እውነት አንድ ሞያዊ ቁምነገር ላክል። አንድ የመሰረተ ልማት አውታር ተሰርቶ ሲጠናቀቅ አገልግሎት መስጠት ከመጀመሩ በፊት የጥራት ፍተሻ [ Quality Control] ይካሄድበታል። ፍተሻው የመሰረተ ልማቱ ፊዚካል ግንባታ ደረጃውንና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ መካሄዱን ብቻ ሳይሆን በየቦታው የሚሰቀሉ የአውታሩ ምልክቶችና የማስታወቂያ ሄሆያትን ትክክለኛነትም ያካትታል። በአንድ ባቡር አውታር ላይ የሚካሄድ የማስታወቂያ ሆሄያትና የምልክቶች ፍተሻ የመጨረሻው ደረጃ ፍተሻ ነው። ይህንን ደረጃ ያላለፈ አውታር የጥራት ደረጃ ፍተሻውን እንዳላለፈ ይቆጠራል። በዚህ መሰረት ትናንትና ስራ ጀመረ የተባለው የአዲስ አበባው ቀላል ባቡር ፕሮጀክት የመጨረሻውን የጥራት ፍተሻ ምዘና አላለፈም ማለት እንችላለን። የመጨረሻውን የጥራት ፍተሻ ምዘና ያላለፈ አውታር ማስተካከያ ተደርጎበት ካልሆነ በስተቀር እንዳለ በቁሙ ስራ እንዲጀምር አይደረግም። ይህ ምክረ ሀሳብ የEconomics of infrastructure ሀ ሁ ነው። ትናንትና ኢትዮጵያ የሳተችው ይህንን ምክረ ሀሳብ ነው። ለነገሩ በኢትዮጵያ የሚሆን ነገር እንዳይሆን ሆኖ መደረጉ አዲስ ነገር አይደለም። በኢትዮጵያ እውቀት ከትምህርት ቤት ሳይሆን ከወያኔ ወንበር ስለሚፈልቅ መቆርቆዝና መዝቀጥ ባህላችን ከሆነ ውሎ አድሯል።

እኔን የገረመኝ ግን ከውጭ ማንም ሰው አይቶ የሚለየውን የሆሄያት ግድፈት እንኳ ተመልክቶ ማስተካከል ያልቻለ የጥራት ማረጋገጥ ምዘና፤ ውስብስብ የሆነውን፣ ጥልቅ ሞያዊ ክህሎት የሚጠይቀውን፣ ባይን የማይታየውንና ከባዱን የባቡሩን መስመር ፊዚካላዊ ጥንካሬ ጉድለት ፈትሾ የባቡር መስመሩ ግንባታ ደረጃውን መጠበቁን አለመጠበቁን እንዴት ብሎ ማረጋገጥ ይችላል? በእውነት ስራ ጀመረ የተባለው የባቡር መስመር ፕሮጀክት የጥራት ፍተሻ ተካሂዶበታልን? እንዴት ተብሎ ስንት መሀንዲሶች ባሉባት አገር ውስጥ የባቡሩ አውታር በአይን የሚታየውን የጥራት መመዘኛ [ማለት መስመር አመላካች ሆሄያት በሚገባ ያልተሟሉለት ሆኖ ሳለ] ፈተና ማለፍ ሳይችል በአይን የማይታዩ የጥራት ፍተሻዎችን እንዳለፈ ተቆጥሮ የመጨረሻውን የጥራት ደረጃ ምዘና ባላሟላ ሀዲድ ላይ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲጀመር ይደረጋል?

በወያኔ ዘመን ሁሉ ነገር ፖለቲካ ሆኖ እውቀት፣ጥራትና ልቀት የሚባል ነገር ሁሉ በኢትዮጵያ ምድር አፈር ድሜ በላ። አውሮፓና አሜሪካ ቀርቶ የትም ሶስተኛ አለም ውስጥ የመጨረሻውን የጥራት ምዘና ደረጃ ያላሟላ የባቡር አውታር እንደኛ አገር ሀላፊነት በጎደለው መልኩ ስራ እንዲጀመር አይደረግም። በእውነት የባቡሩ አውታር ላይም የተደረገ ፍተሻ በተሰቀሉ የአውታሩ ምልክቶችና የማስታወቂያ ሄሆያት ልክ ከሆነ፤ ከጣራው በላይ ዳንኪራ የተደለቀለቱ የባቡር ትራንስፖርት በቅርቡ ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ ሰባራ ሀዲድ ብቻ ታቅፈን እንቀራለን። ይህንን እድሜ ያለው ያያል!

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46824#sthash.780ZJIkq.dpuf

‹‹ለማንም አቤት ማለት አልቻልኩም፡፡›› (የነገረ ኢትዮጵያ ባልደረባ ያነጋገራት እስረኛ)

‹‹ለማንም አቤት ማለት አልቻልኩም፡፡››

(የነገረ ኢትዮጵያ ባልደረባ ያነጋገራት እስረኛ)

የ6 አመት ፍርደኛ ነኝ፡፡ ከኤች አይ ቪ በሽታ ጋር እኖራለሁ፡፡ የአንጀት ካንሰርም አለብኝ፡፡ ልጆቼን ያለ አባት ነው ያሳደኳቸው፡፡ በእኔ እስር ምክንያት አሁን እነሱም እየተጎዱ ነው፡፡ አሁን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ አራት አመት ሊሞላኝ ነው፡፡ በህዳር 2007 ዓ.ም በአማክሮ እንድፈታ ማረሚያ ቤቱ ወስኖ ነበር፡፡ ሆኖም ባላወኩት ጉዳይ እንደገና አመክሮዬን ከልክለውኛል፡፡

ቦሌ አየር ማረፊያ ‹‹23›› የሚሉት ስራ አለ፡፡ መንገደኛን ጠብቆ በመኪና አሳፍሮ መንገድ ላይ ይዘርፉና ጥለዋቸው ይሄዳሉ፡፡ አንዲት ልጅ በዚህ ወንጀል ተከሳ ታስራ ነበር፡፡ ከእኔ ጋር ከመገናኘታችን በፊት ከአንድ አመት በላይ ሌላ ቦታ ታስራ ነበር፡፡ ከእኔ ጋር ደግሞ አራት ወር ነው የታሰረችው፡፡ በማላውቀው ወንጀል ይች ልጅ እንድትመሰክርብኝ ተደረገ፡፡

ልጅቱ ወረዳ ዘጠኝ የሚባለው እስር ቤት ውስጥ ታስራ በነበረበት ወቅት በእግዚቪት የተያዘባት ልብስ ብቻ ነው፡፡ ፖሊሶቹም ከዚህ ውጭ ያዝን አላሉም፡፡ እኔም ብጠይቅ ሌላ ነገር ተይዞባታል የሚል አላገኘሁም፡፡ እኔን ግን የሰረኩትን ገንዘብ እስር ቤት ውስጥ ሰጥቻታለሁ ብላ መሰከረችብኝ፡፡ እንግዲህ ገንዘብ ወደ እስር ቤት ሲገባ ተመዝግቦ ነው፡፡ ሳታስመዘግብ አትገባም፡፡ ደግሞ ሰጠኋት የምትለው ገንዘብ እስር ቤት ውስጥ ሊገባ የሚችል አይደለም፡፡ እሷ ለእኔ ሰጠኋት ያለችው ወደ በኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር 40 ሺህ ብር ያህል ነው፡፡ የዱባይ ገንዘብ ነው ሰጠኋት ያለችው፡፡ ስሙን እንኳ በደንብ አታውቀውም፡፡ ሪያድ ነው ያለችው፡፡ ሪያድ የከተማ ስም ነው እንጅ የገንዘብ ስም አይደልም፡፡ የዱባይ ገንዘብ ደግሞ ስሙ ከዚህ ጋር የሚገናኝ አይደለም፡፡ ይህን ያህል ገንዘብ ወደ እስር ቤት ሊገባም አይችልም፡፡ እኔ እጅ ላይ ምንም ገንዘብ ሊገኝ አልቻለም፡፡ ምንም አይነት ማስረጃ አላቀረቡብኝም፡፡ ባለወኩት ምክንያት ሊያጠቁኝ ፈልገው ነው፡፡ ምን እንደሆነ ግን እኔም ሊገባኝ አልቻለም፡፡

ይች ልጅ ይህን ያህል ገንዘብ እስር ቤት ውስጥ ሰጥቻታለሁ ብላ ስለመሰከረችብኝ አመክሮዬን ተከልክያለሁ፡፡ የሚያሳዝነው የሰረኩትን ገንዘብ ለእሷ ሰጠኋት ያለችው ልጅ በእኔ ላይ ከመሰከረች በኋላ ከእስር ተለቃለች፡፡ እኔን ለምን እንዲህ እንደሚያጠቁኝ አላወኩም፡፡ የኤች አይ ቪ በሽተኛ መሆኔን ያውቃሉ፡፡ ሌሎች ችግሮቼንም እንዲሁ፡፡ ይህ በደል እየደረሰብኝ ለማንም አቤት ማለት አልቻልኩም፡፡ የሚሰማ የለም፡፡ ወደ አለቆቻቸው ሄጄ አቤቱታ ማቅረብ አልቻልኩም፡፡

ልጅቱ ገንዘብ ሰርቄ ሰጥቻታለሁ ብላ ለማረሚያ ቤቱ ሰዎች ብትመሰክርብኝም አመክሮዬን ከለከሉኝ እንጅ በፍርድ ቤት ክስ አልተመሰረተብኝም፡፡ እኔም ለፍርድ ቤትም ለሌላም አካል አቤቱታ ማቅረብ የምችልበት አጋጣሚ አላገኘሁም፡፡ ከጠበቃ ጋር እንዳልገናኝ ተደርጌያለሁ፡፡ ለ3 ወር ከ9 ቀን በአጃቢ ነበር ቤተሰብን የማገኘው፡፡ ቤተሰቦቼ እንዳይደነግጡ ብዬ ‹‹እዚህኮ ሁሉንም እንዲህ ነው የሚያደርጉት፡፡ እኔን ብቻ አይደለም›› እላቸው ነበር፡፡ ሽንት ቤት ስሄድም ሳይቀር ይከታተሉኛል፡፡ አደራ ይህን መረጃ ስታወጣ ስሜን እንዳትጠቅስ፡፡ እነሱስ ማንን እንዲህ እንደበደሉ ያውቁታል፡፡ ቤተሰቦቼ እንዳይረበሹብኝ ስለፈለኩ ነው፡፡

መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ ! -ይድነቃቸው ከበደ

Yidnekachew Kebede - Satenaw

“መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ !” መባሉ  ምን አዲስ ነገር አለው ፣ለዛውም የኢትዮጵያ መንግስት በማለት እንዳትሸወዱ ! የህውሓት/ኢህአዲግ ገዥው መንግሰት የምግብ እርዳት እና ድርቅን ለመከላከል ፣ሞቼ ነው በቁሚ የምለምነው ሲል ነበር፡፡

በአገራችን በኢሊኒኖ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ፣ በሰው ሕይወት እና በእንስሳት  ላይ እየደረሰ ያላው አደጋ አሳሳቢነት አስመልክቶ ፤የመንግሰት ኮሚኒኪሽን ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬዲዋን ሁሴን “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት የመንግስታቸውን አቋም ነሐሴ ወር 2007 ዓ.ም መግለፃቸው የሚታወስ ነው፡፡

አቶ ሬዲዋን መግለጫውን በሰጡ ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ   ዳያስፓራ ነን ባዩችን በሚሊኒየም አዳራሽ ሰብስበው “አሁን በክረምቱ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ከላይ እስከታች ድርቅ አጋጥሞናል……፣ወዳጆችን በዚህ ሰዓት ተሯሩጠው መጥተው እርዳታ ይሰጡን ነበር ፣አሁን እስኪ እናያቸዋለን በማለት ዳር ነው የቆሙት……. ፣አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።” በማለት በድፍረት ተናግረዋል፡፡ይህ የድፍረት ንግግራቸው በቀጥታ ስርጭት በኢቲቪ ተላልፏል፡፡

“ጉድ እና ጅራት ….” እንደሚባለው ሆነና አቶ ሬዲዋን ሁሴን ዛሬ ማለትም መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም የመንግስታቸውን አቋም ሲገልፁ ፤በኢሊኒኖ ምክንያት በተፈጠረው የዝናብ እጥረት የተጎዱ ዜጎች ቁጥር ቀድሞ ከተገመተው 2ነጥበ9 ሚሊየን ህዝብ በማሻቀብ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ደርሷል፣ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጠበቀው ድጋፍ በሚፈለገው መልኩ አልተገኘም፣ይህም በመሆኑ ለልማት ከያዘው በጀት እንጠቀማለን “አሉ”፡፡

ይሄ መንግሥት ነኝ ባይ ህውሓት/ኢህአዲግ በዚህ ደረጃ፣ በአገር እና በህዝብ ላይ መቀልዱ የወደፊት የታሪክ ተጠያቂነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤አሁን ላይ የሥርዓቱ ውድቀት እየተፋጠነ ለመምጣቱ ከምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ ቀርቶ መሆኑ ይመጣ ይሆን ? መልሱን አብረን እንጠብቃለን፡፡

አሁንም ግን በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በተለይ በእንስሳት ላይ እየደረሰ ያለው አደጋ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ወገኖቻችን በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ለሞት እየተዳረጉ ነው፡፡የችግሩ አሳሳቢነት ደረጃ ከፍ ማለቱ ገዥው ህውሓት/ኢህአዲግ መንግስት ለመሸሸግ አልቻልም፡፡ በግልፅ ቋንቋ “ከውጭ የሚጠበቀው ድጋፍ ካልተገኘ መንግስት ለልማት የመደበውን ሀብት በማዞር ለዜጎች ምግብና ለእንስሳት የሚሆን መኖ ለማቅረብ እግደዳለው” በማላት በአቶ ሬዲዋን ሁሴን በኩል ገልፆዋል፡፡እንዲህ አይነቱ መንግስታዊ ማስፈራራት ምክንያቱን እና ውጤቱን ለመገመት ቀላል ነው፡፡

ከአንድ ወር በፊት እኔ በግሌ እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት፣ ከመገናኛ ብዙሃን ኢሳት እና የውጪ ሃገር ሚዲያዎች፣ የችግሩን አሳሳቢት በተቻለ አቅም ለመግለፅ ተችሎአል፡፡በተለይ መንግሰት “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት በድፍረት ሲናጋር ፣ይሄ ነገር ተገቢ አይደለም ፣የሚመጣው ነገር አይታወቅም ከአጉል ቀረርቶ እና ባዶ ሽለላ መቅረት አለበት፡፡

ስለዚህም ከችግሩ አሳሳቢነት እና ወደፊት ከሚያስከትለው አደጋ አንጻር፣ ለዓለም አቀፍ ማህብረሰብ እንዲሁም ለለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ መጠየቅ አለበት፡፡በማለት የችግሩ አሳሳቢነት ለገለፁ ለአገር ወዳድ እና ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያን የተሰጠው ምልሽ “አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።” በማለት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአደባባይ ተዘባበቱ፡፡

ይሄን በተናገሩ ሁለት ወር ሳይሞላ የሚረዳን አጣን፣ለዚህ ጉዳይ የያዝነው ገንዘብ እያለቀ ነው፤ከዚህ በኋላ ለልማት የያዝነውን ገንዘብ ነው የምንጠቀመው፤ሲሉ መስማት ያሳፍራል፡፡ነገ ደግሞ ለልማት የያዝነው ገንዘብ ድርቁን ለመከላከል ያወጣነው ስለሆነ፣ አገር የምናስተዳድርበት ገንዘብ የለንም ይሉ ይሆን ? ያኔ ጊዜ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ እርግጥ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/10435#sthash.lVFwfaLt.dpuf