ከፖለቲካው በስተጀርባ ያሉት እውነታዎች – ክፍል ፪ – ከተማ ዋቅጅራ

በክፍል አንድ ላይ ትንሽ ወደ ኋላ መለስ ብዬ ያለውን እውነት በጥቂቱ ለማሳየት ሞክሬአለው። ከባለፈው የቀጠለውን እውነታዎች እንሆ።

ወደ ነጥቦቼ ከመግባቴ በፊት ጥቂት ማመሳሰልን ላመሳስል። ማነጻጸር የፈለኩት የባለፈውን ስርዓት እንዲመለስ ከመናፈቅ አልያም የቀድሞ ስርዓት አራማጅም ሆኜ አይደለም። ነገር ግን ወያኔዎች እና ደቀ መዛሙትቶቹ የሚሰሩትን ስህተት በነገርካቸው ቁጥር አንተ የደርግ ስርዓት ናፋቂ ይሉሃል። ኢትዮጵያኖች አንድ ነን የጠላትነትን ወሬ በመዝራት አታለያዩን ስንላቸው እናንተ የደርግ ትራፊ እናንተ የአጼ ስርዓት ናፋቂ በማለት ለማሸማቀቅ ይሞክራሉ። ምክንያቱም አንድነት ስለሚያስፈራቸው እና የመጨረሻ የልብ ትርታቸውን ስለሚያጮህባቸው ነው። እንዲሁም አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት ድብቅ ሴራቸውን የሚያፈርስባቸውም ስለሆነ  ነው። የቀድሞ ስርዓቶችን በማጣጣል እና ለኢትዮጵያ የማይጠቅሙ በማድረግ ስለሚናገር እና እራሳቸውን በመልካም ምሳሌነት ዲሞክራሲ አምጪዎች እንደሆኑ በማስነገራቸው  ሌላው ቀርቶ  የኢትዮጵያ ታሪክ ከዘመነ ወያኔ እንዲጀምር የሚያስቡ ያላዋቂ ደፋሮች ስለሆኑ ወደኋላ ብዙ ተጉዤ ማንሳት ባያስፈልገኝም ጣልኩት ያለውን ስርዓት እና ለህዝብ እና ህዝቦች(የማይገባኝ ቋንቋ ነው) ነጻነት አመጣው ሁሉን እኩል አደረኩኝ አንባገነኖችን ጣልኩኝ ዲሞክራሲ አመጣሁኝ……ሌላም ሌላም በማለት የሚደሰኩረውን እውነቱን ለማጥራት  ጥቂት እናመሳስል።

mengistu hailemariam

ደርግ፡- አንባገነን ነው? አዎ ነበረ። ደርግ ሰላማዊ ዜጋን ይገድል ነበረ? አዎ ይገድል ነበረ። የደርግ ስርዓት መለወጥ ነበረበት? አዎ መለወጥ ነበረበት። ነገር ግን ዲሞክራሲአዊ መንግስት ነኝ ብሎ በዲሞክራሲ ሰበብ ተሸፍኖ አንባገነን አልሆነም። ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆችን በዚሁ ስርዓት አጥተናል። አብዮቱን ሲቃወሙ የነበሩትን እከሌ እከሌ የሚባሉት ማዕረግ ካላቸው ከነማእረጋቸው በመጥራት አብዮታዊ እርምጃ ተሰውዶባቸዋል ብለው ፊለፊት ይናገር ነበረ።

ወያኔ፡- አንባገነን ነው? አዎ  ነው። ወያኔ ሰላማዊ ዜጋን ይገድላል አዎ ይገድላል። የወያኔ ስርዓት መለወጥ አለበት? አዎ  መለወጥ አለበት። የወያኔ ስርዓት ከደርግ በከፋ መልኩ አደገኛ እና አጥፊ ለኢትዮጵያ የማይጠቅም ስርዓት ነው። ወያኔ ዲሞክራሲ አራማጅ ነኝ እያለ በዲሞክራሲ ሰበብ አንባ ገነንነቱን መሸፈን ይሞክራል። አልገድልም እያለ ይገድላል ከመግደሉም የሚከፋው ወንጀል ደግሞ  ከገደለ በኋላ ከተጎጂ ህዝብ ጋር አብሮ ገዳዩን መፈለጉ ስርዓቱ ምን ያህል አጥፊ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

ደርግ፡- ሹመት ወይንም እልቅና የሚሰጣቸው በችሎታቸው ተመዝነው ነው። የደርግ መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ ሰራዊት ተብሎ የሚታመን ነበረ። ምክንያቱም በብሔር ተኮር ሳይሆን በችሎታው፣ በብቃቱ፣ በትምህርቱ ተኮር ተደርጎ የተመሰረተ ስለነበረ። ደርግ በአገር ጉዳይ አስተሳሰቡ በሁሉም ክልሎች ውስጥ የሚኖሩትን ህብረተሰብ በእኩልነት በማየት አገራዊ ፍቅር እንዲኖራቸው አድርጎ የሚያስተዳድር ነበረ።

TPLF 1

ወያኔ፡- ሹመት ወይንም እልቅና የሚያሰጣቸው በዘራቸው ተመዝነው ነው። የወያኔ መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ ሰራዊት ነው ተብሎ አይታመንም። ምክንያቱም መከላከያ ሰራዊቱ የሚመራው በችሎታቸው ተመዝነው ሳይሆን የዘር ሃረጋቸው ተመዞ ስለሆነ። ወያኔ አገር አስተሳሰብን ያጠፋ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የሚኖሩትን ዜጋውን በጠላትነት እንዲተያዩ  መረቡን የዘረጋ፣ በህብረተሰቡ ልቦና ውስጥ የአገር ፍቅርን በማጥፋት ወደ ዘር ተኮር በማዞር ጥላቻን በኢትዮጵያ ምድር ለማምጣት ቀን ከለሊት የሚሰራ ነው።

ደርግ፡- ከአንባ ገነን ስርዓት ውጪ ለኢትዮጵያ ጠንካራ የሚባል አቋም ያላው ስርዓት ነበረ። ለዚህም የኢትዮጵያን ንብረት በመዝረፍ ህዝቡን አላስራበም ፣  ከአበዳሪ አገሮች ብድርን ተበድሮ ኢትዮጵያን  እዳ ውስጥ አልከተተም፣ ኢትዮጵያንን በውጪ አገር አላስደፈረም አላስናቀም፣ አገር አልሸጠም፣ በኢትዮጵያ ክብር ጉዳይ ከማንም ጋር አልተደራደረም አይደራደርምም ለዚህም ኢትዮጵያን እንድትከበር አድርጓል። ኢትዮጵያ ማለት ሁሉም ህብረተሰቡ በኩራት የሚኖሩባት፣ በክብር የሚዘምሩላት፣ መሆኗን ያሳወቀ የአገር ፍቅርን ዘፋኞች በሚያወጡት ካሴታቸው ላይ እንኳን አንድ ስለ ኢትዮጵያ ክብር የሚያወድስ ስራን እንዲሰሩ ያደረገ አገር ወዳድ ነበረ።

ወያኔ፡- ከአንባገነን አስተዳደር ጋር ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን የሚጠላ ስርዓት ነው። በአለማችን ላይ የሚጠላትን አገር የመሩዋት የነገሰባት ብቸኛዋ አገር ኢትዮጵያ ሆናለች። ከአበዳሪ አገራት ከፍተኛ የሆነ ብድር በመበደር ብድርራቸውን መክፈል ከማይችሉ አገራት ተርታ  ኢትዮጵያ አንዷ እንድትሆን አድርገዋታል።ወያኔ  የኢትዮጵያን ንብረት በመዝረፍ ወደ ግል ካዝናቸው ከተዋል። ጥቂት ሚሊዮነሮችን በመፍጠር ሚሊዮኖችን  እንዲራቡ እና እንዲደኸዩ  አድርገዋል። ኢትዮጵያን በታሪኳ በውጪ ዜጋ የተዋረደች እና የተናቀች አድርገዋታል። ኢትዮጵያን በኩራት የምትታይ ሳይሆን ሁሉም እየተነሳ የሚያንቋሽሻት የሚሰድባት የሚያዋርዳት ተሳዳቢዎች መሪዎች እና ተከታዮችን አፍርተዋል። ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለት ለአገርህ ጥልቅ ስሜትህንና ፍቅርህን መግለጽ በወያኔዎች ፖሊሲ ጠላት ሆኖ የሚያሳስር ከአገር የሚያሰደድ መከራ የሚደርስበት ዲሞክራሲ አፍራሽ እና የልማት ጠር የሚያስብል  አድርገውታል።

እንግዲህ ለማነጻጸር እንደሞከርኩት በትንሹም ቢሆን ያለውን እውነታዎች ለማስቀመጥ ሞክሬአለው። ስለታገለበት አላማ እንመልከት። ተግባርና ቃል

ወያኔ በተግባር የሚያሳየው ስራ  እና በአፉ የሚናገረው ቃል አይገናኝም እንደውም አይተዋወቁም ብለው ያስኬደኛል። ለህዝብ እና ለውጪ መንግስታት የሚናገረው እኩልነት አመጣው፣ ዲሞክራሲ አመጣው፣ ሰላም አመጣው፣ እድገት አመጣው፣ ልማት አመጣው፣ ….አመጣው……አመጣው…….. ይለናል። ለኢትዮጵያኑ ወያኔ ያመጣለት ነገር ቢኖር መዓት፣ መርገም፣ ሞት፣ ውርደት፣ ስደት ነው። እስቲ አመጣው ወደሚለው ወደዘረዘርኩት እውነታዎች እንግባ…..

tplf

ነጻነት፡ ነጻነት ማለት ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ በሚፈልጉት ሙያ ወይንም በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ የሚወዷትን አገራቸውን በነጻነት የማገልገል ፍላጎት አላቸው። ወያኔ እያደረገ ያለው ግን ይሄንን አይደለም። መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ወይንም  ወደፈለጉት ሙያ ወይንም  በተማሩበት ዘርፍ ለማገልገል ስሄዱ ቅድመ ሁኔታዎች ይቀመጡላችኋል። የመጀመርያያዎቹ ባለ ሙሉ መብት የሆኑት የትግራይ ተወላጅ ሆነው የወያኔ አላማን የመደገፉ ከሆኑ በየትኛውም የስራ ዘርፍ ላይ 100% ይሰጣቸውና ያለ ምንም ተቀናቃኝ ማመልካቻቸው ተቀባይነት ያገኛል። ተቀባይነት ማገኝት ብቻ ሳይሆን ስልጣንም ይጨመርላቸዋል። ምክንያቱም እነርሱ አንደኛ ዜጋ ናቸውና። ሌላው ደግሞ በተመሳሳይ መስክ ለሚያመለከቱት ማመልከቻ ሁለተኛ ቦታ የሚሰጣቸው ደግሞ ከየትኛውም ብሔር ይወለዱ ብቻ የካድሬ ወረቀት ይኑራቸው እነዚህ 10% ወይም ከዛ ያነሰ ይሰጣቸዋል። ይህ ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት ወሳኝ የሚባሉ ተቋም  ውስጥም ሆነ ወሳኝ ባልሆኑት ተቋም ውስጥ 100 ሰራተኛ ቢቀጠሩ  ከመቶው ተቀጣሪ ባለሙሉ መብት ሆነው 90%ቱን የሚይዙት ትግሬ ሆነው  የወያኔን አላማ የሚደግፉ ሲሆን ቀሪው  ደግሞ  ለአላማቸው  ደጋፊ የሚሰጠው ቦታ 10% ነው። እንግዲህ ወያኔ  ያመጣውሁት  እኩልነት ብሎ የሚሰብከው  ይሄንን ነው። ለምሳሌ መከላከያ ሚንስቴር፣ የደህንነት ሚኒስቴር፣ የኢሚግሬሽን፣ ጉምሩክ፣ አየር መንገድ፣ ሁለተኛውን ቴሌ ማለትም የተለያዩ የውጪ ሚድያን የሚቆጣጠርበት መስመር የተለያዩ ድረ ገጾችን ፌስ ቡክ ዩቱብ ያሆ ጎግል የመሳሰሉትን የሚያፍንበትን የኔቶርክ ሲስተም የሚቆጣጠሩበት ተቋም ነው።በዚህ ተቋም ውስጥ ማንም ያልተደባለቀበት በውጪም በአገር ቤት ያሉትን ዜጋችንን የሚሰልሉበት እና የውጪ ሚዲያዎችን ለማፈን የሚጠቀሙበት በከፍተኛ በጀት የሚንቀሳቀስ ሲሆን 100% ከትግራይ የተወለዱ እና 100% የወያኔ አላማ  የሚያስፈጽሙ ናቸው። ታዲያ ይሄ ነው እውነታው። በኢትዮጵያ ላይ በሁሉም  አቅጣጫ ወያኔወች የበላይ ሆነው የሚቀመጡበትን ስትራቴጂ ቀይሰው እና ተፈጻሚ እያደረጉት ያለውን ጉዳይ እኩልነት አመጣን እያሉ አይን ያወጣ ውሽታቸውን በመዋሸት በለመደው አንደበታቸው እኩልነት አለ ብለው የሚነግሩን።

ዲሞክራሲ፡- ኢትዮጵያ  ውስጥ ዲሞክራሲ የማይፈልገው የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ነውን?  ዲሞክራሲን የማይፈልገው የአማራ ህዝብ ብቻ ነውን? ዲሞክራሲን የማይፈልገው  የኡጋዴው ወይስ የጋንቤላው ወይስ የደቡቡ ነው። ዲሞክራሲ የተከበረለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሆነ እስር ቤቶች  ዲሞክራሲያዊቷን አገር ልታፈርሱ ነው እየተባሉ የአማራን፣ የኦሮሞ፣ የደቡብ፣ የጋንቤው፣ የሱማሌው፣ ህዝብ  ምክንያት እየተፈለገላቸው የሚገደሉት እና የሚታሰሩት ምን በደል ሰርተው ይሆን? እስር ቤቶችን በነዚህ ኢትዮጵያን የሞላው ለምን ይመስላቹህ ይሆን? ከሚሊዮኖች ታሳሪዎች ውስጥ  በመቶ የማይቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች አይታሰሩም። ከሚሊዮንስ ኢትዮጵያን  የሚገደሉት የትግራይ ተወላጆች  በመቶዎች  አይቆጠሩም።  ከሚሊዮንስ  ተፈናቃዮች  በመቶ የሚቆጠር የትግራይ ሰው አታገኙም። ገዳይ ወያኔ አፈናቃይ ወያኔ ሆኖ ሳለ አማራውን በሚገድልበትና  በሚያስርበት ጊዜ የኦሮሞ  ጠላት እና የትግሬ  ጠላት የነበሩ በማለት  ድጋፍን ከሌላ  አካል በማግኝት  ጥፋቱን ሌሎች እንዲጋሩ ያደርጋል።  ኦሮሞን በሚገድልበት ጊዜ የአማራ ጠላት እና የትግሬ ጠላት እያለ ጥፋቶችን ሌሎች እንዲጋሩ እያደረገ። ወይ አማራ የለ፣ ወይ ኦሮሞ የለ፣ ወይ ጋንቤላ የለ፣ ወይ ኡጋዴን የለ፣  ወይ ደቡብ የለ፣ ሁሉም በየተራ የመከራ ገፈት ቀማሽ ነው። በዲሞክራሲ ሰበብ ሲገድሉ እና እስር ቤቶችን በታሳሪ ሲያጨናንቁት ወያኔን የሚደግፍት  የትግራይ ልጆች እና ወያኔወች ግን አይታሰሩም አይገደሉም ጭራሹኑ ዲሞክራሲ ወያኔ  አመጣልን ብለው አፋቸውን ሞልተው ሲናገሩ 90 ሚሊዮን ህዝብን እየዋሹ  መሆናቸውን  እንኳን ህፍረት አይሰማቸውም።

እኩልነት፡- ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ እኩልነት መጣ ይሉናል። እኩልነት ማለት በአንድ አገር የሚኖረው ዜጋው በሙሉ ያለ ምንም አድሎ በችሎታው በእውቀቱ በፍላጎቱ አገር ውስጥ በሰላምና  በነጻነት በመኖር የፈለገውን የመስራት የፈለገበት ቦታ የመኖር እንደ ችሎታው ደግሞ የፈለገውን ስልጣን የመያዝ ነው። ታዲያ  ወያኔ ይህንን እያደረገ ነውን? ኽረ በፍጹም እንኳን ሊያደርገው  አስቦትም አያውቅም።  ኽራ ማሰብ አይደለም በእቅድ ውስጥም የለም። ይሄ ነው ከፖለቲካው በስተጀርባ  ያሉት እውነታወች ስልጣኑን በሙሉ የወያኔ ሰዎች ናቸው የተቆጣጠሩት መከላከያ  ውስጥ  በአየር ሃይል ውስጥ ባጠቃላይ ወታደራዊ ተቋም ላይ እውቀቱ  እና ችሎታው ያላቸው ኢትዮጵያኖች በአሰልጣኝነት  ቦታ  ይቀመጡና  በአዛዥ ቦታ  የሚቀመጠው ግን ብቃት ያለው ሳይሆን ለመማር እንኳን ፍቃደኛ ያልሆነ  ምንም ችሎታ የሌለው ስው ይሾምበታል ከዛ መደናቆር ነው ኢትዮጵያኖቹ በሙያቸው ሳይንሳዊን ስልጠና ወይም ትምህርት ሲሰጡ <<ቧይ ማን አባትህ ነው አስተምር ያለህ>> እያሉ ሁሉ ነገር በነሱ ስር እንዳለ እና ፈላጭ ቆራጭ እንደሆኑ ይነግሩታል። የዚህን ግዜ ኢትዮጵያዊው ለውጪ አገር ነው  እንዴ የምንሰራው? ኢትዮጵያ  የኛ አገር አይደለችም  እንዴ?  በአገራችን ጉዳይ ላይ እኛ አይመለከተንም እንዴ? እያሉ ዜጎች እራሳቸውን መጠየቅ ከጀመሩ ቆይተዋል።  ራሳቸውን እንደ ሁለተኛ ዜጋ  እንዲያዩ  እየተደረጉ ያሉት ወታደራዊ  በውስጡ ያለውን እኩል ያለመሆን ጉዳይ ያውቁታል። ታዲያ እኩልነት እኩልነት እያለ በመስበክ ወያኔ አንደኛ ዜጋ ሌላው ኢትዮጵያዊ  ደግሞ ሁለተኛ ዜጋ አድርጎ የመግዛቱ ስርአትን ነውን?።

ሌላው ድግሞ የውጪ ንግዱን የተቆጣጠሩት እነሱ፣ የአገር ንግድ የተቆጣጠሩት እነሱ፣ የኢትዮጵያ  ሃብት እንዳለ  የሚንቀሳቀሰው በነሱ፣ ከፍተኛ ወጪ ተደርጎ የተሰራው  ድርጅት የባለ ብዙ ቅርንጫፍ  ኤፈርት የነሱ፣ በየከተማ የሚገነባው የንግድ ተቁአም የነሱ፣ የትልልቅ ፎቆ ባለቤት እነሱ፣ ብርን እንደ ቅጠል የሚሸመጥጡይ እነሱ፣ ባንኮች የነሱ፣ ፈላጭ እነሱ፣ ቆራጭ እነሱ፣ አሳሪ እነሱ፣ ፈቺ እነሱ፣ ስልጣን ሰጪ እነሱ፣ ስልጣን ከልካይ እነሱ፣ እነሱ እና እነሱ ብቻ ናቸው በኢትዮጵያ ውስት ባለሙሉ ስልጣን እና ባለ ሙሉ መብት ባለቤት። ይህንን ስርዓት አልበኝነትን አይቶ  ለምን እንዲ ይሆናል ብሎ የጠየቀውን  ኢትዮጵያዊ የልማት ጸር፣  የእድገት ጠላት፣ የደርግ እርዝራዥ፣  የድሮ ስርአት ናፋቂ፣   አሸባሪ፣ እየተባለ  ወደ እስር ቤት ይወረወራል።  አይቶ ዝም ያለ  አብሮ  ከስራቸው እየሄደ ትርፍራፊን የሚበላ ክብሩን እና ሞራሉን ህሊናውን እውነትን የሸጠውን ደግሞ የልማት አጋር በማለት ለግዜው ይሾማል እነዚም ተጠቅመውባቸው ታኝከው የሚተፉ ስለሆኑ ነው ለግዜው ያልኩት።  እንግዲህ በአገር ንብረት እና  በሕዝብ ላይ እየቀለዱ  እኩልነት አመጣን ብለው ሊነግሩን የሚፈልጉት።

ባጠቃላይ በኢትዮጵያ ንብረት ላይ እና  ስልጣን ላይ 95% በላዩን ወያኔ በሃይል ተቆጣጥሮ ሰለ እኩልነት መናገሩ ያሳፍራል። ሕዝብ በደል ሲበዛበት ግፍ ሲበረታበት  መንግስቱ ሃይለማርያምን የማያውቅ ትውልድ ናና መንግስቱ  ናና እያለ  መዘመሩ  የወያኔ  ስርአት ምን ያህል እንዳንገሸገሸው የሚያሳይ ነው። ቢገባቸው!!። የመንገስቱን ስርአት መምጣት ናፍቆት ሳይሆን በዛ ግዜ የነበረውን ኢትዮጵያዊ   ፍቅርን ናፍቆ ነው። በዛ ግዜ የነበረውን የአገር ስሜት ተመኝቶ ነው። በዛ ግዜ የነበረውን ኢትዮጵያዊ አንድነት አስቦ ነው። ይሄ ቃል ለኢትዮጵያ ህዝብ የማንቂያ አላርም ሲሆን ለወያኔ ደግሞ የማስጠንቀቂያ ነው።

ዘመነ ወያኔ፡- ከአንባገነን አንባገነን ነው። ከአገር ፍቅር የአገር ፍቅር የሌለው ነው። ኢትዮጵያዊ አንድነትን በማጥፋት እየከፋፈለ፣ እያጣላ፣ እየበታተነ፣ ህዝብን ጨቁኖ  እና ረግጦ የሚገዛ ለጥፋት የነገሰ፣ ለዘረፋ የተሰማራ፣ ለመበታተን የተሾመ ስርዓት ነው። ዘርፎን እና አጣልቶን፣ አገር ሽጦ እና እርስ በራስ አጋጭቶ፣ ኢትዮጵያ ላይ አንባገነን ሆኖ ለመቶ አመት ለመግዛት ራእዩ ነው። ሰብስቦን እና አንድ አድርጎን፣ አገር አስከብሮ  እና እርስ በራሳችንን አከባብሮ፣ የኢትዮጵያን ሃብት ሳይዘርፍ ህዝቧንም ሳያስደፍር አንባገነን የሆነው ደርግ ስለተሻለ  ነው ህዝቡ መንጌ ናና ያለው። በኢትዮጵያ ምድር እውነተኛ ዲሞክራሲ እስከሚመጣ ድረስ ሁሉም ሊታገል ይገባይ ያቺ የነጻነት ፀሐይ በኢትዮጵያ ምድር ደምቃ እስከምትወጣ ድረስ የትግል አድማሱ ከግዜ ወደ ግዜ እየተቀጣጠለ የነጻነታችንን ቀን ለማምጣት መታገል ያስፈልጋል።

ድብቅ አላማው፡- ወያኔ ከኢትዮጵያ የሚፈልገው ህዝቦቿን ሳይሆን ሃንቷን ነው። ህዝቦቿ በፍቅር፣ በሰላም እንዲኖሩ ሳይሆን በጥላቻ፣ በጠላትነት እየተያዩ እንዲኖሩ ነው ። ከዚህም አልፎ  አንዱ በአንዱ ላይ በማስነሳት እርስ በራሳችን እንድንገዳደል በማድረግ አላምውን ማሳካት ነው። የወያኔዎች አጀንዳቸው የኢትዮጵያን አንድነቷን  ሳይሆን መፍረሷን፣ መበታተኗን የሚናፍቁ ናቸው። ኢትዮጵያዊ ፍቅርን አጥፍተው ብህዝባችን መካከል ጠላትነትን እና ጥላቻን መትከል ነው እቅዳቸው። ይህንን ካደረጉ በኋላ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የበላይነት ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ ምን አልባትም እርስ በራሳችን ካጣላንና ከበታተነን በኋላ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ካጠፋ በኋላ መቶ አመት እገዛለው የሚለውን ድብቅ አላማውን አሳካ ማለት ነው። ወያኔ ይህ ድብቅ አላማው ይሳካለት ይሆንን? ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ሆይ ግዜው አይናችንን በደንብ ገልጠም ነገሮችን አጥርተን የምንመለከትበት ግዜ ሰዓቱ አሁን ነው። ኢትዮጵያን አፍርሶ የመቶ  አመት የቤት ስራህን እህህህ እያልክ የመከራ ዘመንን ከመግፋትህ በፊት አንድ ሆነን የቀድሞ ፍቅራችንን መልሰን ጣላትን እናሳፍር። ጠላትን ማሳፈር  ኢትዮጵያዊ ጀግንነትም ልማድም ባህላችንም ነውና።

ኢትዮጵያዊ ሙሁራኖች ኽረ ወዴት ናችሁ? በክፍል ሦስት እንገናኝ።

ይቀጥላል….

ከተማ ዋቅጅራ

28.10.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47779#sthash.iLBg1YXQ.dpuf

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s