መምህር ግርማን ዘመነኞች ለምን ወንጀለኛ ብለዉ ወደ እስር ቤት ከተቷቸዉ?

Memhir girma
ሸንቁጥ አየለ
ልክ እንደ መምህር ግርማ ሁሉ ባህታዊ ገብረመስቀልን የዛሬ 20 አመት ህዝቡ ከኋላቸዉ እንደተከተላቸዉ ያስተዋለችዉ ወያኔ ባህታዊ ገብረመስቀልን በሀሰት ወንጅላ እስር ቤት ወርዉራ በርካታ ዉንጀላ አድርጋባቸዉ ነበር:: ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች መሃከል በእዉቀት መሰረት ላይ የቆመ ጽኑ እና ሀሰት የሌለበት እምነት የሚያራምድ እንደሆነ ሲያዉቁ አሸባሪ ብለዉ ድርጅቱን ለማፍረስ እየሰሩ ነበር:: አሁንም አጀንዳዉ የተንጠለጠለ ይመስላል::

እንግዲህ በርካታ ንጹሃንን ሀሰተኛ እና ወንጀለኛ ናቸዉ ለማለት በርካታ የሀሰት ፊልሞችን መስራት የለመደችዉ ወያኔ በመምህር ግርማ ላይ የተቀነባበረ የሀሰት ፊልማና ድራማ አዘጋጅታ ለህዝብ ታቀርባለች:: በህዝብ ለማስጠላት: ከህዝብ ለመነጠል::

ህዝቡ የሚያድነዉና የሚፈዉሰዉ እንዳይኖር ለማድረግ እንዲሁም ህዝቡ ተስፋ የሚያደርገዉ እንዳይኖር ለማድረግ ሁሉንም ደባዎችና ተንኮሎች
በመምሀር ግርማ ላይ ትሰራለች::ሀሰተኛ የሆኑ: የመፈወስ ጸጋ የሌላቸዉ: ጉበኞች: በክርስቶስ የማያምኑ: በቅናት የሚቃጠሉ : በርኩስ መንፈስ ሀይል የሚመሩ: ጉሰኞች የሆኑ ሰዎች ግን በእምነት ስም የሚነግዱ ሰዎችንም መልምላ በምስክርነት ታቀርባለች:: በቃ ይሄዉ ነዉ:: እዉነትን እፍን አድርጎ በገመድ መስቀል:: ከዚያም መምህር ግርማን ወንጀለኛ ናቸዉ እያሉ በሚዲያቸዉ ያናፋሉ::

እዉነተኞችን የሚፈራ : የሚያሳድድ: የሚወነጅል እና ከምድረ ገጽ እዉነትን የሚሰብኩ ወገኖች እንዲጠፋ የሚሰራ የማን ሀይል እንደሆነ የተገለጸ ነዉ:: እርኩሱ መንፈስ ነዉ:: ቢሆንም የኢየሱስ ክርስቶስን የጥበበ ስራ ማንም አያሸንፈዉም::

መምህር ግርማ ሁል ጊዜ ትምህርት ሲጀምሩ መዝሙር 68 ማለትም
1 እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።
2 ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ኅጥኣን ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።
3 ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥ በደስታም ደስ ይበላቸው።
4 ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ በፊቱም ይደነግጣሉ።
የሚለዉን ሙሉዉን የመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንብበዉ : አስከትለዉም የዮሐንስ ወንጌልን ቁጥር አንድን ሙሉዉን ማለትም 1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
2 ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።
4 በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።
5 ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።

የሚለዉን የወንጌል ቃል ሙሉዉንም ዕራፍ አስተምረዉ እንዲሁም ልዩ ልዩ የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ስራዎች ካስተማሩ ብኋላ የማዳን ስራቸዉን ይጀምራሉ:: በተጨማሪም እግዚአብሄር ለቅዱሳን እና ለመላዕክት እንዲሁም ለጻድቃን የሰጣቸዉን በርካታ ጸጋዎች እያጣቀሱ ካስተማሩ ብኋላ የሰዉን ልጅ እያጠቁ ያሉ ልዩ ልዩ አጋንንትና እርኩስ መንፈሶችን ከክቡሩ የሰዉ ልጅ ላይ ያባርራሉ::
በመላዉ አለም እዬሄዱ የአዳምን ልጆችም ጥቁር ነጭ ሳይሉ ይፈዉሳሉ:: ከአለም እስከ አለም ያለ እርኩስ መንፈስ ያለበት ሀይል እኝህ ሰዉ በሚሄዱበት ሁል ይርዳል:: ይርበተበታል:: በኢየሱስ ክርስቶስ ሀይልና ጥበብ ሁሉ ይከናወንላቸዋልና መምህር ግርማ ሲመጡ እርኩሳን መናፍስት ሁሉ ከክቡሩ የአዳም ልጅ ላይ ይወገዳል:: ልክ እንደ ቀደሙ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊ አባቶች እንደ እነ አቡነ ዜናማርቆስ ያለ የማስተማርና የመፈወስ ጸጋ የተሰጣቸዉን መምህር ግርማን ግን ሰይጣን ማጥቃትና ማስጠቃት ከጀመረ ቆዬ:: የሰይጣን ሰራዊቱ ብዙ ነዉ:: ድምጹን ከፍ አድርጎ የሚጮህዉም በዛ:: በስማ በለዉ እኝህን ክርስቲያን አብረዉ የሚሳደቡ አንዳንድ የዋሃን በደራሽ ዉሃ ተወሳጅ የዋህ ሰዎችም ሞልተዋል::

ትምህርታቸዉን አንድ ቀን ሳይሰሙ: አስተምህሮታቸዉን ሳይመረምሩ: የማዳን ስራቸዉን ሳያስተዉሉ በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን እና የመፈወስ ሚስጢር የሚሰሩትን የማዳን ስራ ሳይመረምሩ ዝም ብለዉ ከዲያቢሎስ ሀይል ጋር የሚጨፍሩ አንዳንድ የዋሃንም ያሳዝናሉ:: ሳይገባቸዉ እና በማያዉቁት ፈራጅ ሆነዉ የእርኩስ መንፈስ መጠቀሚያ ሆነዋልና እዉነትም ጸሎት ይገባቸዋል::

የቀደሙ ኢትዮጵያዉያንን ቅዱሳን አባቶችን ታሪክ እና ገድል በሙሉ ተረት ተረት እና ሀሰት ነዉ በማለት ወገቡን ገትሮ ስልጣን እና ጊዜ መከታ አድርጎ በሰዉ ስጋ ተመስሎ የመጣዉ እርኩስ መንፈስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዉስጥ የሚደረጉ የክርስቶስን የማዳን ስራዎች ወንጀል ናቸዉ: አሸባሪነት ናቸዉ: ጽንፈኝነት ናቸዉ እንዲሁም ትምክህት ናቸዉ እያለ በመፈረጅ የክርስቶስን ቤት ለማፍረስ ከተጋ ይሄዉ እሩብ ምዕተ አመት ሆነዉ::የክርስቶስ ቤት ግን አስካሁን የኮሰመነ ቢመስልም አልፈረሰም:: ደግሞም አይፈርስም:: ሀይል እና ዘመን የክርስቶስ ኢየሱስ እንጅ የማንም አይደሉምና::

ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጀለኛ ነዉ : ሀሰተኛ ነዉ ህዝቡን አታሏል ብለዉ እርኩስ መንፈስ ያለባቸዉ እና እግዚአብሄርን የማያዉቁ ሰዎች ስልጣንንና ዘመንን ተገን አድርገዉ እንደሰቀሉት ሁሉ በርካታ ንጽሁን የእግዚአብሄር ሰዎች አሁንም እየተሳደዱ ነዉ::
ጉልበትን እግዚአብሄር የሰጣቸዉ ዘመነኞች ሀሰት በመፈብረክ ነጹሃንን ያስወግዳሉ::

ሀሰት መሰረት ላይ የቆመ ዘመነኛ ባለ ጉልበት እዉነተኛ ክርስቲያኖችን : ሰዉን የሚፈዉሱትን የማንነት መሰረት ያላቸዉን : ኢትዮጵያዉያንን በእምነት አንድ የሚያደርጉትን መንፈሳዊ አባቶችን ፈጽሞ አይወዱም:: መምህር ግርማ ከአረብ እስከ ነጭ : ከነጭ እስከ ጥቁር እንዲሁም መላዉ ኢትዮጵያዊን ሁሉ እምነት ሳይለዩ በኢየሱስ ክርስቶስ ሀይል እየፈወሱ ሳለ በወንጀል ጠረጠርኳቸዉ ሲል ዘመነኛዉ ሀይል አስሯቸዋል::
የሆነ ሆኖ ግን በሀሰት የወንጀል ሰበብ ቢታሰሩም መምህር ግርማ ምንም የሚጎዱት ነገር የለም:: እሳቸዉ ቅዱስ ጳዉሎስ በሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 8 እንዳለዉ እንዲህ የሚል ጽኑ እምነት አላቸዉና:-
35 ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? 36 ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
37 በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
38 ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
39 ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።

እናም በመምህር ግርማ መታሰር ማን ይጎዳል? እየተፈወሰ ያለዉ ህዝብ: በቀን በቀን የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ስራ እያዬ የእምነት መሰረቱን እያጠበቀ ያለዉ ህዝብ ይጎዳል:: ማንስ ይጠቀማል? የሚጠቀመዉማ ያዉ እርኩስ መንፈስ ነዉ:: እንግዲህ ቢያንስ አንድ የማዳን እና የመፈወስ ጸጋ ያለዉን ሰዉ በሀሰት ወንጅሎ አሳስሯል እና ለጊዜዉ ደስታዉ ወደርም አይኖረዉም::

ቢሆንም ይሄ ሁሉ የሆነዉ እግዚአብሄር ቢፈቅድ እንጅ እርኩስ መንፈሥ በክርስቶስ አማኞች ላይ አንድም ስልጣን የለዉምና ሰይጣን ደስ እናዳይለዉ ጠላትም እንዳይኩራራ ቅዱስ ዳዊት እንዳለ እንዲህ እያል እንዘምራለን (መዝሙር 68):-
1 እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።
2 ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ኅጥኣን ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።
3 ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥ በደስታም ደስ ይበላቸው።
4 ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ በፊቱም ይደነግጣሉ።

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47830#sthash.TdWDW3H0.dpuf

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s