የወታደሮቻችን ነገር – ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት

የመቅደላው ጀግና ዐፄ ቴዎድሮስ በመጨረሻዋ ሰዓት ለጄኔራል ናፒየሪ በጻፉት ደብዳቤ አበክረው የጠየቁት ነገር ከሁለት ቀናት በፊት በተደረገው ውጊያ የወደቀውን የወዳጃቸውንና የጦር መሪያቸውን የፊታውራሪ ገብርዬን አስከሬን ለመቅበር እንዲፈቀድላቸው ነበር፡፡ ‹‹ፊታውራ ገብርዬን የኔን ወዳጅ ሳላነሣው ያደርኩ ከሞትኩኝ ሁሉንም አብረው ይቅበሩኝ ብየ ነበር፡፡ ቁሜ ከዋልኩ ግን ልቅበረው ይፍቀዱልኝ›› ይላል ደብዳቤው፡፡ ለሀገሩና ለወገኑ በክብር የተሠዋ አስከሬኑም የክብር ዕረፍት ይሻዋልና፡፡

last letter
አሜሪካኖችና አውሮፓውያን የተሰጣቸውን ግዳጅ ለመወጣት የዘመቱ ወታደሮቻቸው ሲሠው በክብር አስከሬናቸውን ወደ ሀገር በማምጣት በብሔራዊ ሥነ ሥርዓት የመቅበር ያልጠፋ ልማድ እንዳላቸው በየጊዜው ሚዲያው ያሳየናል፡፡ እነዚህ ወታደሮች ሀገራዊ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የዘመቱ በመሆኑ መሥዋዕትነታቸውም ሀገራዊ ሆኖ መታሰብ አለበት፡፡
በኢትዮጵያ የቅርብ ዘመን ታሪክ የተሠዉ ወታደሮችን በክብር የመዘከር፣ በክብር የመቀበልና በክብር የመቅበር ሥነ ሥርዓት አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ በኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት የተሠዉ ስንት ወታደሮች ናቸው? የተሠዉትስ ወታደሮች መርዶ እንዴት ተነገረ? የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውስ እንዴት ተከናወነ? ሚዲያውስ ለዚያ ምን ዓይነት ሽፋን ሰጠው? የሁል ጊዜ ጥያቄዬ ነው፡፡ እኔ ሳልሰማና ሳላውቅ ተከናውኖ ካልሆነ በቀር፡፡ ለምንስ አስከሬናቸው በወታደራዊ ሥነ ሥርዓት ታጅቦ፣ ሰንደቅ ዓላማ ለብሶ፣ ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ፣ ሕዝቡ ወደ አደባባይ በነቂስ ወጥቶ አላከበርናቸውም? እያልኩ እጠይቃለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር በአፍሪካ ልዩ ልዩ ሥፍራዎች ዘምቷል፡፡ ሲዘምትም በክብር እንደተሸኘ በሚዲያዎቻችን አይተናል፡፡ እነዚህ ዘማቾች ሁሉም በሰላም ነው የተመለሱት? የተሠዋ ካለ ለምን ይፋዊ በሆነ ሀገራዊ ሥነ ሥርዓት አስከሬኑን ተቀብለን አልቀበርነውም? ፖለቲካው ተፈርቶ ከሆነ ለግዳጅ የተሠማራ ወታደር ወይ በድል መመለስ፣ ወይ መማረክ፣ ወይ መቁሰል አለያም መሠዋት እንደሚያጋጥመው እንኳን እኛ ታሪካችን በጦርነት የተሞላው ቀርቶ ሌሎችም ያውቁታል፡፡
የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሶማልያ ሲዘምቱ ፓርላማው ወስኖ ነው የዘመቱት፡፡ የሄዱት በእር በርስ ጦርነት ሲታመስ ወደኖረውና እጅግ አስቸጋሪ ወደሆነው የጦርነት ሥፍራ ነው፡፡ ከሶማልያ መንግሥት ወታደሮችና ከአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር ጋር በጋራ በመሆን በሶማልያ ከአልሸባብና ከሌሎችም ኃይሎች ጋር በመዋጋት ያገኙትን ድል ሚዲያዎቻችን ይዘግባሉ፡፡ መቼም የሄዱት ለጦርነት ነውና፣ በጦርነት ውስጥ መግደል፣ ድል ማድረግና መማረክ እንዳለ ሁሉ መሞት፣ መቁሰልና መማረክም አለ፡፡
ታድያ የሀገሬ ወታደሮች አልተሠዉም፣ አልቆሰሉም፣ አልተማረኩም? የሄዱት ሁሉ ሰላም ናቸው? ከሆኑ መልካም፡፡ ግን ቦታውም የነ አልሸባብ ቦታ፣ ሁኔታውም ጦርነት፣ ሰዎቹም ወታደሮች ናቸውና ቢያንስ መሞትና መቁሰል አይቀርም፡፡ የአሜሪካና የአውሮፓ ሚዲያዎች በአፍጋኒስታን፣ በኢራቅና በሶርያ ጦርነት የተሠዉትንና የቆሰሉትን ማንነት እንደሚናገሩት፣ በክብርም ሲቀበሩ እንደሚያሳዩት፣ የኛዎቹ የተሠዉት በክብር ሲቀበሩ፣ የቆሰሉት በክብር ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ለምን እንደ ሕዝብ አናያቸውም? ለመሆኑስ በክብር የተሠዉ የኢትዮጵያ ወታደሮች መቃብር የት ነው?
ወደኋላም ተመልሰን ከአድዋ ጦርነት በኋላ የሆነውን ስናስታውስ በእንዳ ኢየሱስ ያለው የአባቶቻችንን መቃብርና ከዚያ እልፍ ብሎ የሚገኘውን የጣልያኖች መቃብር መመልከቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በእንዳ ኢየሱስ የሚገኘው የአድዋ ዘማቾች አባቶቻችን መቃብር ለመሥዋዕትነታቸው የማይመጥን ነው፡፡ አልፎ አልፎም ፈርሶ እናየዋለን፡፡ የጣልያኖቹ መቃብር ግን በክብር ታጥሯል፡፡ ጠባቂም ተመድቦለታል፡፡ መቃብሩንም ለማየት የጣልያን ኢምባሲ ፈቃድ ይጠይቃል፡፡

grave of americane soldiers
በአሥራ ሰባቱ የደርግ ዓመታት የዘመቱት ወታደሮች ኢትዮጵያ የመለመለቻቸው፣ ያሠለጠነቻቸውና ያዘመተቻቸው ነበሩ፡፡ ምንም ጦርነቱ የእርስ በርስ ጦርነት ቢሆንም፡፡ የተሠዉት አብዛኞቹ ወታደሮች ለቤተሰብ መርዶ አልተነገረም፡፡ በተለይ ኤርትራ በረሃ የቀሩት መጨረሻቸው ምን እንደሆነ አልታወቀም፡፡ ጦሩ ሲበተን ወደ ቤተሰባቸው መምጣት የቻሉት ቁርጣቸው ታወቀ፤ ከዚያ ውጭ ያሉት ግን አሁንም ለቤተሰብና ለሀገር ጥያቄ እንደሆኑ ናቸው፡፡
የአንድ ወታደር ክብር የሀገራዊ ዓላማና የሀገራዊ ግዳጅ ክብር ማሳያ ነው፡፡ አሜሪካ ውስጥ በአውሮፕላን በተጓዝኩ ቁጥር ለአሜሪካ ወታደሮች የሚሰጠውን ክብር አደንቃለሁ፡፡ አውሮፕላኑ ምድር ደርሶ ተሣፋሪዎቹ እንደተቀመጥን ለወታደሮቹ ቅድሚያ ተሰጥቶ እያጨበጨብን ወደ በሩ እንሸኛቸዋለን፡፡ ወደ አውሮፕላን ውስጥ ስንገባም አስተናጋጆቹ ‹ዩኒፎርም የለበሱ ጀግኖቻችን አሉና እናክብራቸው›› ብለው ያውጃሉ፡፡ ሁላችንም እንጨበጭባለን፡፡ እኔ የሀገሬ ወታደር በአውሮፕላን እንኳን ባይሆን በታክሲና በአውቶቡስ፣ በመዝናኛ ቦታዎችና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዲህ ሲከብር ማየት እናፍቃለሁ፡፡
ወታደሮቻችንን ጉሮ ወሸባየ ብለን እንደሸኘናቸው ሁሉ የጀግና አቀባበል እንድናደርግላቸው፣ ሲሠዉ በክብር አደባባይ ወጥተንና የሞቱለትን ሰንደቅ ዓላማ አልብሰን እንድንሸኛቸው፣ የቆሰሉትን በክብር እንድንቀበላቸው፣ ያስገኙት ድል ብቻ ሳይሆን የገጠማቸው ፈተናና የከፈሉት መሥዋዕትነትም እንዲነገርላቸው እመኛለሁ፡፡ የክብር አቀባበልን ላሸነፈ ሯጭና እግር ኳስ ተጨዋች፤ የክብር አቀባበርንም ለአርቲስት ብቻ ማን ሰጠ?

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47767#sthash.O3NKiXbZ.dpuf

Andargachew Tsege ‘fears he will die in Ethiopia’

A British man locked up for more than a year in Ethiopia fears he could die in prison.

Andargachew “Andy” Tsege, a father-of-three, has been detained in the country since he was removed from an airport in Yemen in June 2014.UK “stands shoulder to shoulder” with Ethiopia

Legal charity Reprieve said the 60-year-old asked the British Government to ensure that he is buried in England and told his children to “be brave” during a recent visit by the UK ambassador.

Mr Tsege, a prominent critic of Ethiopia’s ruling party, was sentenced to death in his absence in 2009 for allegedly plotting a coup – charges he and others deny.

The trial has been described as “lacking in basic elements of due process”.

He fled Ethiopia in the 1970s, seeking asylum in the UK in 1979.

Maya Foa, head of the death penalty team at Reprieve, said: “It is tragic that he now feels the only way he will return home to Britain is in a coffin.

“The Foreign Office must urgently push for his release, so he can return to his partner and children in London before it’s too late.”

Last week, Foreign Secretary Philip Hammond discussed the case with the Ethiopian Foreign minister.

Mr Hammond said: “I raised the case of Andargachew Tsege with the Ethiopian Foreign Minister during our meeting on October 21, and made it clear that the way he has been treated is unacceptable.

“I welcome the improvement in access to him, following the British Government’s intervention, but it must be more regular and it must include access to a lawyer.

“I am still not satisfied that Mr Tsege has been given an ability to challenge his detention through a legal process, and this is something we are continuing to pursue.

“The Foreign Office will continue to provide consular support to Mr Tsege and his family.”

Source: BT.com

ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሀብ ማቆም ይችላልን?

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Famine 2ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በአውዳሚ ረሀብ መካከል ተሰንጋ መያዟ ታላቅ ዓለም አቀፍ ሚስጥር ሆኖ ይገኛል፡፡

.. 1984-85 ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተ ታላቅ ረሀብ!

ባለፈው ሳምንት ግሎባል ፖስት/Global Post የተባለው የዜና ወኪል በርዕሰ አንቀጹ የመጀመሪያ ርዕስ በማድረግ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርቧል፡

“ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በአስከፊነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ድርቅ ተጋፍጣ ትገኛለች፡፡ መንግስት በአሁኑ ጊዜ የተከሰተውን ረሀብ ማስቆም ይችላልን?”

ግሎባል ፖስት መንግስት ረሀቡን ማስቆም ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ ያቀረበለት እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ ለሚጠራው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ነው፡፡

እ.ኤ.አ ወደ 1984-85 መለስ በማለት የነበረውን የወያኔ ታሪክ ስንመለከት ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ አሸባሪ ቡድን ነበር፡፡

በአሁኑም ጊዜ ህወሀት በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት/Global Terrorism Database ስም ዝርዝር ውስጥ ስሙ ሰፍሮ አሸባሪ ቡድን ተብሎ ተፈርጆ ይገኛል፡፡

ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ሊቀርብ የሚችለው ዋና ጥያቄ፡ ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሀብ ማስቆም ይችላልን? የሚለው ነው፡፡ (“ዘ” የምትለዋ ፊደል ዘራፊ የሚለውን ቃል ትገልጻለች፡፡ የዘራፊ መንግስት ማለት ደግሞ ለዘራፊዎች በዘራፊዎች የተቋቋመ የዘራፊ ወሮበላ መንግስት ማለት ነው፡፡)

ከዚህ በላይ ለቀረበው ጥያቄ መልስ ሊሆን የሚችለው፡ ዘ-ህወሀት የልመና አኮፋዳውን በመያዝ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ላይ የምግብ ልመናን፣ ተመጽዋች መሆንን ሊያቆም ይችላልን? የሚል ይሆናል፡፡

ላለፉት 24 ዓመታት ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ሲከሰት የቆየውን የረሀብ ችግር ለመቋቋም ሲል በእያንዳንዱ ዓመት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የምግብ እርዳታ የልመና ጥያቄ ሲያቀርብ እና ምጽዋዕት መጽውቱኝ እያለ ሲማጸን ቆይቷል፡፡

በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዓለም አቀፍ የምግብ እርዳታ ልመና፣ የተመጽዋችነት ሱሰኞች እና በአሜሪካ ከተማ ማዕከል በሚገኘው ጠባብ መንገድ እየተዘዋወረ የዜጎችን አዕምሮ በሚያደነዝዘው አደንዛዥ የሀሺሽ ዕጽ አዘዋዋሪዎች መካከል ያለው ልዩነት በጣም ትንሽ ነው፡፡

ሁለቱም አንድ ዓይነት ባህሪ አላቸው፡፡

ያላቸው ብቸኛው ልዩነት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የልመና ሱሰኞች በደንብ ያልተሰፋ ሱፍ ልብስ ለብሰው መዞራቸው ብቻ ነው።

አንድን ሰው ልመናን እንደ ሙያ ባህል በመያዝ እንደ ህይወት መርሆው አድርጎ እየተጠቀመበት የሚሄድ ከሆነ እንዴት አድርጎ ነው ውርደትን በማስወገድ የእራሱን ክብር ሊይዝ የሚችለው?

አንድ ሰው በምን ዓይነት መስፈርት እና መለኪያ ነው ከልመና ወጥቶ ባለፋብሪካ ሊሆን የሚችለው?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አጠቃላይ ሁኔታ በሸክስፒር ስለኪንግ ጆን የተቋጠሩትን እና እንዲህ የሚሉትን ለአሁኑ ሁኔታ ተስማሚ የሆኑ የግጥም ስንኞች አስታወሰኝ፡

ለማኝ በሆንኩ ጊዜ በርትቼ እዞራለሁ፣
ጸሐይ ቁር ውርጅብኝ ማለትን ትቻለሁ፣
በመዞር፣ በመንጎድ ምጽዋት አግኝቻለሁ፡፡

ምንም ሀጢያት የለም ሀብታም መሆን እንጅ፣
ምጽዋትን ማግበስበስ ከዘመድ ወዳጅ፣
ክብር እና ሞገስን በመጣል ከደጅ፣
ልመናን ማጦፍ ነው ከነጭ ከፈረንጅ፣

እናም ብልሀቱ የማግኘት ዘዴው፣
ሌት ከቀን ልመናን ባህል ማድረግ ነው፣
ክብር እና ህሊናን ገደል መጣል ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ልመናን ክብር እና ሞገስ አድርገውታል፡፡

ለእነርሱ ከሚገኘው እርዳታ በሙስና እያግበሰበሱ ለግል ጥቅማቸው በማዋል ርካሽ ሀብታምነትን መጎናጸፍ እንጅ በልመና ጊዜ ምንም ዓይነት የሞራል ስብዕና ኪሳራ ጉዳይ የሚባል ነገር አይነካቸውም፡፡

ባለፉት ስምንት ዓመታት የታየው መረጃ በትክክል እንደሚያረጋግጠው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የለማኝ አገዛዝ መሆኑን በውል ያመላክታል፡፡

እ.ኤ.አ የካቲት 2014 እንዲህ የሚል ዘገባ ቀርቦ ነበር፣ “ኢትዮጵያ 2.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ረሀብተኛ ዜጎቿን ለመመገብ የለጋሽ ድርጅቶችን እርዳታ አጥብቃ ትሻለች፡፡“ እ.ኤ.አ በ2014 መጀመሪያ አካባቢ የዩኤስ አሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ ለዚያ ረሀብ ግዙፍ የሆነ 218 ሚሊዮን ዶላር ችሮታ ሰጥቶ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2013 ኢትዮጵያ ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ለመመገብ ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ለሰብአዊ እርዳታ ተቀብላለች፡፡ የዩኤስ አሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ 236 ሚሊዮን ዶላር ችሮታ ሰጥቶ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 2012 “የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ዓመት በነሐሴ እና በታህሳስ መካከል 3.7 ሚሊዮን  እና በጥር ወር ደግሞ 3.2 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎቹ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ይፋ አድርጓል፡፡“  የዩኤስ አሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ 307 ሚሊዮን ዶላር ችሮታ ሰጥቶ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 ለኢትዮጵያ የተሰጠው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ 500 ሚሊዮን ደርሷል፡፡ የዩኤስ አሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ 313 ሚሊዮን ዶላር ችሮታ ሰጥቶ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ነሐሴ 2010 የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት/Food and Agricultural Organization (FAO) እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣ “ወደ 5.2 ሚሊዮን አካባቢ የሚገመት የኢትዮጵያ ህዝብ እስከ አሁን ድረስ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ጥገኛ ሆኖ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ ድርጅቶች በረዥም ጊዜ ዕቅድ በሀገሪቱ ውስጥ አስከፊ የሆነ ረሀብ ሊከሰት እንደሚችል ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡“

ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እ.ኤ.አ በ2010 ባወጣው ዘገባ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከዓለም አቀፉ እርዳታ ሰጭ ድርጅት የተገኘውን እርዳታ ለማዳበሪያ፣ ለዘር እና ለስራ አገልግሎት እንዲውል በመመደብ የአከባቢ ባለስልጣኖች፣ ሚሊሻዎች እና ሰላዮች ያሉበት ሰፊ መሰረትን በመዘርጋት ማን ምን ማግኘት እንዳለበት፣ መቸ እና እንዴትስ ማግኘት እንዳለበት ይጫወቱ የነበረውን ተደጋጋሚ እና ገዳይ የሆነ ጨዋታ ግልጽ በሆነ መልኩ መዝግቦት ይገኛል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ 588 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነውን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተገኘውን እርዳታ ከተራበው የህዝብ ጉሮሮ በመንጠቅ ለግሉ በማድረግ እንክት አድርጎ በልቶታል፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ዋና ተቆጣጣሪ የሆነው ቢሮ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት/United States Agency for International Development (USAID) የተባለው ድርጅት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተብሎ ከአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ የተገኘውን በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠረውን ዶላር ለምን ለምን ተግባር ሊያውለው እንደሚገባ ሊገልጽ የሚችል ትክክለኛ መንገድ እንደሌለ እንዲህ በማለት በግልጽ አስቀምጧል፡

ዩኤስኤይድ/ኢትዮጵያ (USAID/Ethiopia) ለገበያ መር ኢኮኖሚ እድገት ስኬታማነት የእራሱን ሚና እየተጫወተ እና ገበሬዎች፣ አርብቶ አደሮች እና ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ተጠቃሚዎች ሁሉ ከተፈጥሮ አደጋ ሊቋቋሙባቸው የሚችሉባቸውን መንገዶች ያመላከተ ነው ቢባልም ድርጅቱ ተጫውቶታል ተብሎ የተነገረለትን ሁኔታ እና ያበረከተውን ድርሻ በእርግጠኝነት መለካት አልተቻለም፡፡ ይህም የሆነበት ዋናው ምክያት የድርጅቱ የአፈጻጸም አስተዳደር እና ዘገባ የማቅረብ ስርዓቱ ደካማ ከመሆኑ አንጻር ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2009 የተባበሩት መንግስታት እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፣ “ወደ 4.8 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን ህዝብ የአስቸኳይ ጊዜ ለምግብ እና ለተመሳሳይ ጉዳዮች የሚውል እ.ኤ.አ በ2010 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት 270 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ያስፈልጋል“ ብሎ ነበር፡፡ ከዚህ አኳያ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ 346 ሚሊዮን ዶላር ችሮታ ሰጥቶ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ነሐሴ 2009 ዘኢንዲፔንደንት/The Independent የተባለው የእንግሊዝ ብሄራዊ መጽሔት እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣ “በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደኃ ኢትዮጵያውያን የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት እና ምናልባትም ለአስርት ዓመታት ሊዘልቅ የሚችል አስከፊ የሆነ የረሀብ አደጋ በዚህ የበጋ ወቅት ተጋርጦባቸዋል፡፡ እናም በዚህ ዓመት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉት ተረጅዎች ቁጥር ተከታታይነት ባለው መልኩ እየጨመረ በመምጣት በጥር ወር ከነበረበት ከ5.3 ሚሊዮን ከፍ በማለት በግንቦት ወር 6.2 ሚሊዮን ሊደርስ ችሏል፡፡“

እ.ኤ.አ በ2008 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ተረጅ ህዝብ ስም ከአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ የተገኘውን 479 ሚሊዮን ዶላር የሰብአዊ እርዳታ ገንዘብ በመቀበል ወደ ኪሱ አጭቆታል፡፡

ባለፈው ሳምንት የኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ቀደም ሲል በነሐሴወርየአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚያስፈልገው የተረጂ ህዝብ ቁጥር 4.55 ሚሊዮን የሚገመት የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር አሁን (ሁለት ወር ሳያልፍ) ወደ 8.2 ሚሊዮን አካባቢ ደርሷል“ ብሎ ነበር፡፡

ኢትዮጵያ እንደገና የተራቡ ህጻናትን ስዕሎች በማውጣት የሰብአዊ እርዳታ መለመኛ አድርጋ በመገኘቷ ዘገባውን ያስደነቀበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኢትዮጵያን የረሀብ መቅሰፍት የሆነው የባለጥቁር የምጻት ፈረሱ (ረሀብ) የማስተዋወቂያ መሬት እንድትሆን አድርጓታል፡፡

በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በረሀብ የተጠቁ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር ከ4.5 ሚሊዮን በሁለት እጥፍ በማሳደግ ወደ 8.5 ሚሊዮን አድርሶታል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንዲህ ዓይነት ድድብና የተሞላበትን የቁጥር ጨዋታ ነው በመጫወት ላይ የሚገኘው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሁሉንም ነገር በማካተት በአንድ ጊዜ እውነታውን አይናገርም፡፡ ረሃቡን ቀላል ለማስመሰል ትንሽ በትንሽ እና ቀስ በቀስ ነው የሚገልጸው፡፡

የአሁኑን የረሀብ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት በዚህ ዓመት መጨረሻ (እ.ኤ.አ) የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በረሀብ የተጠቃውን ህዝብ ቁጥር ወደ 12 ሚሊዮን በማድረስ ሊያውጅ ይችላል የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ የሚችል ሊሆን አይችልምን?

እ.ኤ.አ በ2016 የክረምት ወቅት አቶ “ኤል ኒኖ” በሀገሪቱ ላይ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ጥላውን ካጠላ በኋላ ወደ 25 ሚሊዮን ገደማ የሚደርስ የኢትዮጵያ ሕዝብ የረሀብ ሰለባ ከባለጥቁሩ ፈረስ መዳፍ ስር ሆነው በመሰቃየት የሚገኙ ሊሆኑ አይችሉምን?

2015-16 የምጽአት ቀን! 

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቅን ልቦና አስመሳይነት፣

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሳቸውን እያንዳንዱን ሰው የሚበልጡ እና የሚያደናግሩ አታላዮች አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ እነርሱ ማንንም ሳይሆን እራሳቸውን ብቻ ነው በማሞኘት ላይ የሚገኙት፡፡

እውነታው ፍርጥ ፍርጥርጥ ብሎ ሲታይ ግን ባለፉት 24 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በእያንዳንዷ ዓመት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ሲለምን እና በመቶ ሚሊዮኖች ዶላር የሚቆጠርን ገንዘብ ከዩኤስ አሜሪካ እና ከሌሎች ምዕራባዊ ለጋሽ ድርጅቶች እያጋበሰ ወደ ኪሱ ሲጨምር ነው የቆዬው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ይህንን የልመና ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለው እና እያዳበረው ስለመጣ ቃሉን በትክክለኛው መንገድ ለመግለጽ “የለማኝ መንግስት” በማለት ሰይሜዋሁ፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2014 በዋናነት ዓለም አቀፍ ቀፍ እርዳታዎችን (እርዳታ + ብድር) እና ለሕገወጥ ድርጅቶቻቸው ሕጋዊ ሽፋን በመስጠት በብድር እና በእርዳታ በሕዝብ ስም የሚመጣውን የእርዳታ ገንዘብ በተለያዩ ዓይነት የሙስና መገለጫዎች እና ተሞክሮዎች አማካይነት ለእራሳቸው ጥቅም እና ትርፍ ማጋበሻ የሚያደርጉትን አገዛዞች እና መንግስታትን ለማጥናት  እንዲያስችል በመቀመር “የለማኝ መንግስት” በማለት የቃሉን ጽንሰ ሀሳብ ለማስተዋወቅ ሞክሪያለሁ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለማኝ መንግስት የናይጀሪያ ብሔራዊ ደራሲ እና ቃል አቀባይ የሆኑት አለቃ ኦባፌሚ አዎሎዎ አፍሪካውያንን ለማስጠንቀቅ እንደሞከሩት ሁሉ አንድ ዓይነት የለማኘ መንግስት ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ1967 ተካሂዶ በነበረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት 4ኛ ጉባኤ ላይ አለቃ አዎሎዎ ጥንቃቄ በተሞላበት እና ነብይነትን ባካተተ መልኩ እንዲህ በማለት ትንበያ በመስጠት አስጠንቅቀው ነበር፡

በአሁኑ ጊዜ አፍሪካ እርስ በእርሳቸው የሚወዳደሩ የአፍሪካ ሀገሮች የለማኞች አህጉር ናት፡፡ ከቀድሞዎቹ ቅኝ ገዥዎች አለቆቻችን መዳፍ ስር ወድቀን የተሻለ ነገር ለማግኘት አንዳችን በአንዳችን በመመቃቀን ላይ እንገኛለን፡፡ ይህንንም በማድረግ ሆን ብለን የእጅ አዙር ቅኝ ገዥዎች በተለያዩ የአህጉሪቱ ግዛቶች በመግባት የምጣኔ ሀብት ዕድሎቻችንን እንዲወስኑ እና እንዲቆጣጠሩ በማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላይ እንገኛለን…

…ስለሆነም ያለንን ስልጣን በመጠቀም እና የትኛው ሉዓላዊነት ተጽዕኖ እንደሚፈጥር ከግንዛቤ በማስገባት እንደዚሁም ሁሉ ምን ዓይነት ዘዴዎችን እና ሸፍጦችን እንደምንተገብር እና የትኛውን ዓይነት ዓለም አቀፍ  ዴፕሎማሲ በመጠቀም ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የበለጠ ምጽዋዕት ለመቀበል ይህንን ድርጊታችንን ልንቀጥልበት እንድምንችል እና በእርግጥም በትክክለኛው መስመር ላይ እንዳለን በመቁጠር በድርጊቱ ልንቀጥልበት እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ከጊዜ ወደጊዜ ችግር በመፍጠር ላይ የሚገኘው ዋናው ሰይጣን ሌላ ከማንም ጋር ሳይሆን ከእኛ ጋር ተጣብቆ ይገኛል፡፡  ለማኝ እንዲወገድ ካልተደረገ እና ሊመለስ በማይችል መንገድ እጁን ከልመና ወደ ልማት አቅጣጫ እስካላዞረ ድረስ የእርሱን የልመና ባህል በማጠናከር ለዘላለሙ ለማኝ እንደሆነ ይኖራል፡፡ ይህ ዓይነት አገዛዝ ብዙ በለመነቁጥር ተነሳሽነት የጎደለው፣ ድፍረት የሌለው እና በእራስየመተማመን ባህልን በማስወገድ ልመናን ባህል እያደረገ የሚጓዝ ይሆናል፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

የአለቃ አዎሎዎ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ ከግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ በኋላ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የልጆች የረሀብ ማስታወቂያ ፖስተሮች ለአፍሪካ ለማኞች አንጸባራቂ ምሳሌ ሆነው ቀርበዋል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ 9 ሚሊዮን የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን የረሀብ ሰለባዎች መመግብ ይችላልን?

የሚችል ከሆነስ በምን ዓይነት ሁኔታ እና እንዴት?

ከዓለም ሕዝብ ምግብ በመለመን?

ልመና፣ ልመና፣ ልመና፣ ልመና…

በታሪክ በየትኛውም ሀገር ቢሆን በምጽዋዕት እና በልመና ረሀብን ማስወገድ የተቻለበት ክስተት የለም፡፡

ታዲያ እውነታው ይህ ከሆነ የማይሞከረውን እና ከቶም ሊፈጸም የማይችለውን ነገር ኢትዮጵያ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ  ተችላለች?

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ከፍተኛ የሆነውን የውጭ እርዳታ ስትቀበል የቆየች እና አሁንም በመቀበል ላይ የምትገኝ ሀገር ናት፡፡

የውጭ እርዳታ ከፍተኛ በሆነ መልኩ ለልመና የሚያመች አማላይ ቃል ነው፡፡ ይህ ቃል በሀገሮቻቸው ሕዝቦች ስም ለሚለምኑ ለማኝ ለሆኑ አገዛዞች የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

እንደ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ/Global Humanitarian Assistance ከሆነ እ.ኤ.አ በ2012 ኢትዮጵያ 484 ሚሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ እርዳታ በመቀበል ከዓለም በእርዳታ ተቀባይነት በ7ኛ ደረጃ ላይ እንድትገኝ አድርጓታል፡፡

እ.ኤ.አ በ2013 በመጀመሪያ የተገመተው እርዳታ 550 ሚሊዮን ዳላር ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ከሚቀበሉ 10 የመጀመሪያዎቹ ሀገራት ስም ዝርዝር ውስጥ ስሟ ሰፍሮ እንደሚገኝ ድርጅቱ ዘገባውን አቅርቧል፡፡ እ.ኤ.አ በ2008 በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ በከፍተኛ ደረጀ በማደግ 987 ሚሊዮን ዶላር በመድረስ ከዓለም ሁለተኛዋ ታላቅ እርዳታ ተቀባይ ሀገር በመሆን ተመዝግባለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ኢትዮጵያ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ ዘመናት አስር ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካ ከሁሉም ሀገሮች መካከል በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የምትገኘ ሲሆን ከዓለም ሀገራት ደግሞ ሰብአዊ እርዳታን ከሚቀበሉ ሀገሮች 10 የመጀመሪያ ሀገሮች መካከል አንዷ ሆናለች፡፡

እንደ የልማት እርዳታ ቡድን በኢትዮጵያ የተባለው እና በኢትዮጵያ የሚገኘው የለጋሽ ድርጅቶች ስብስብ ዘገባ ከሆነ እ.ኤ.አ በ2008 ለኢትዮጵያ ለልማት ተብሎ የተሰጠው እርዳታ 3.819 ቢሊዮን ዶላር፣ እ.ኤ.አ በ2010 ደግሞ 3.525 ቢሊዮን ዶላር እና እንደዚሁም በ2011 3.563 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 እንግሊዝ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ከፍተኛውን ደረጃ የልማት እርዳታ ተቀባይ ሀገር አድርጋ መርጣታለች፡፡

ዩኤስ አሜሪካ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ የምትሰጠውን የልማት እርዳታ እ.ኤ.አ በ2005 ከነበረበት 1.8 ቢሊዮን አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ እ.ኤ.አ በ2008 ወደ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ከፍ እንዲል አድርጋለች፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሶስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ የሚያገኘውን የእርዳታ ምጽዋዕት ግማሽ በግማሽ ያህል ከፍ እንዲል ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡

የዩኤስ አሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ በተለይም ማህበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት)/Relief Society of Tigray (REST) እየተባለ ከሚጠራው ድርጅት ጋር የምግብ እርዳታን በጋራ በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡

ባለፈው ዓመት ዩኤስኤአይዲ/USAID እንዲህ የሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር፣ “ማረት/REST በዩኤስኤአይዲ/USAID ድጋፍ ከድርጅቱ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የምግብ ለስራ ፕሮግራምን/Productive Safety Net Program (PSNP)ን ከሚተገብሩ አራት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የካቶሊክ እርዳታ አገልግሎት/Catholic Relief Servicesን፣ ምግብ ለተራቡ/Food for Hungry እና የህጻናት አድን ድርጅት/Save the Childrenንን ያካትታል፡፡“

በአሁኑ ጊዜ ከዩኤስ አሜሪካ እርዳታ የአንበሳውን ድርሻ (ይቅርታ የጅቡን ድርሻ) የሚወስደው ማን ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ?

ማረት/REST ምንድን ነው?

ማረት/REST እ.ኤ.አ በ1984-85 በወቅቱ በረሀብ ሰለባ ለወደቀው ለትግራይ ሕዝብ ተብሎ ከዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ቀርቦ የነበረውን እርዳታ ከታለመለት ውጭ በመቀልበስ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ለድርጅቱ ወታደራዊ እና ለመሪዎቹ ያከፋፈለ በእርዳታ ሰጭነት ስም የተቋቋመ አጭበርባሪ ድርጅት ነው፡፡

“ለመስረቅ ፈቃድ ያለው ድርጅት” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ በ2010 አቅርቤው በነበረው እና በሁፊንግተን ፖስት/Huffington Post ድረ ገጽ በተለቀቀው ትችቴ ላይ የማረት/RESTን አጭበርባሪነት እና መሰሪነት ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡

ማረት/REST ከሶስት አስርት ዓመታት በፊት ለረሀብ ተብሎ ለሕዝብ እንዲቀርብ ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የተላከውን እርዳታ እያጭበረበረ ከታለመለት ዓላማ ውጭ ለእራሱ የግል ጥቅም ሲያውል የነበረበት የሽፍጥ አካሄድ ድርጅቱ ቅንነት የሌለለው ሰይጣናዊ ድርጅት መሆኑን በግልጽ የሚያመላክት ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ1984-85 መጀመሪያ አካባቢ ማረት/REST ያደረገው የምግብ እርዳታ የማጭበርበር ሸፍጥ ሶስት ደረጃ ሂደቶችን የያዘ ነበር፡፡

በደረጃ ሂደት አንድ ላይ አንድ የህወሀት/ማረት ባለስልጣኖች ቡድን ሕጋዊ የእህል ነጋዴ መስሎ በማጭበርበር በመቅረብ በርካታ የሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የምግብ እርዳታ አከፋፋይ መስሎ በመቅረብ ለረሀብ ሰለባ ለሆኑት ተጠቂዎች በአፋጣኝ እና በአስቸኳይ እህል በማቅረብ መሸጥ እና ማከፋፈል እንደሚችል የአጭበርባሪነት አንደበቱን ተጠቅሞ ተግባራዊ እንዲሆን አድርጎ ነበር፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን ህወሀት ከተለያዩ ምንጮች ማለትም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጨምሮ ለእርሱ ተዋጊዎች አገልግሎት የሚውሉ በድብቅ በርካታ የሆነ የምግብል እህል በማግኘት በመጋዝኑ ውስጥ እንዲታጨቅ አደረገ፡፡ ይኸ በድብቅ እና በሚስጥር በመጋዝን ውስጥ የታጨቀው የምግብ እህል ክምችት በእርግጥ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ለሽያጭ የቀረበ ነበር፡፡ የህወሀት/ማረት እህል አዳዮች የሽያጭ ስራውን በማከናወን ካጠናቀቁ በኋላ የእህል ሽያጭ ክፍያቸውን ከመንግስታዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በመቀበል ወደሚደበቁበት ቦታቸው ተመለሱ፡፡

በደረጃ ሂደት ሁለት ላይ ሌላ የህወሀት/ማረት ቡድን በትግራይ ውስጥ የምግብ እርዳታ እህሉን የማከፋፈል ኃላፊነቱን ተረከበ፡፡ መንግስታዊ ባልሆኑ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ዘንድ ታማኝነትን ለማትረፍ ሲሉ የህወሀት/ማረት ባለስልጣኖች በድብቅ ባለው የክምችት መጋዝናቸው እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች የፍተሻ ስራዎችን በመስራት የማስመሰል ዕኩይ ምግባራቸውን ማድረግ ቀጠሉ፡፡ ሆኖም ግን በመጋዝኑ ውስጥ ታላቅ የማጭበርበር ድርጊትን ፈጽመዋል፡፡ ያንን ሸፍጥ የተሞላበትን ማጭበርበር እንደተመለከተው አንድ የህወሀት አባል የዓይን ምስክርነት “እዚያ ሄዳችሁ ብትመለከቱ ግማሽ ያህሉ የመጋዝኑ ቦታ አሸዋ በተሞሉ ጆንያዎች የተሞላ ነበር“ በማለት ሸፍጡን ይፋ አድርጓል፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ተወካዮች የእህል ክምችት ያለባቸውን ቦታዎች በመገኘት በዓይን በማየት ፍተሻ እና ምርመራ በማድረግ አስተያየታቸው እንዲጸድቅ በማድረግ እንደገና ተጨማሪ የእህል ግዥ ለመፈጸም ወደ ሱዳን ይመለሱ ነበር፡፡

በደረጃ ሂደት ሶስት ላይ አንድ ዓይነት ወይም ሌላ የህወሀት/ማረት ባለስልጣን ቡድን ወደ መንግስታዊ ያልሆኑ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በመሄድ በሌሎች የተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ሊሰራጭ የሚችል እህል ሽያጭ ክንውን እንዲፈጸም እና እንዲታደል ሀሳብ ያቀርባል፡፡ በዚህ መልኩ የተገኘው አዲስ እህል ወይም ደግሞ ንጹህ የሆነ እህል ለረሀብ ሰለባዎቹ አይታደልም ነበር፡፡ ከዚያ ይልቅ በትግራይ በተለያዩ አካባቢዎች ድብቅ የእህል መጋዝን ውስጥ የነበረው እየተጫነ መንግስታዊ ላልሆኑት እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የለገሷቸው አዲስ እና ንጹህ የሆነው እህል ለረሀብ ሰለባው ሕዝብ እየተሰራጨ የሚደርስ በማስመሰል የለየለት የማጭበርበር የሸፍጥ እኩይ ምግባራቸውን ፈጸሙ፡፡ የእርዳታ ሰጭ ሰራተኞች ነጻ በሆነ መልኩ አዲሱ እህል ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመወሰድ የሚሰራጭ እና የሚታደል መሆኑን የሚያረጋግጡበት ዘዴ ስለሌላቸው በጣም ፈጣን እና ጥልቀት የሌለው ዓይነት ፍተሻ በማድረግ ክፍያዎችን ይፈጽሙ ነበር፡፡

በዚያ ዓይነት ሁኔታ ህወሀት/ማረት ቀደም ሲል አንድ ጊዜ የተገኘውን እህል ብዙ እና ለበርካታ ጊዚያት በመደጋገም እየሸጡ በርካታ ሚሊዮን ዶላር ሽያጭ ለማግኘት ቻሉ፡፡ ህወሀት/ማረት እ.ኤ.አ በ1985 መንግስታዊ ካልሆኑ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ጋር ያላቸውን ሸፍጥ የተሞላበት የማጭበርበር የንግድ እንቅስቃሴ ተግባራዊ ለማድረግ እና በእርዳታ ሰጭ ሀገሮች የተላከውን የመርከብ እህል እየሸጡ ለእራሳቸው ጥቅም አዋሉት፡፡

እ.ኤ.አ በ2009 የዩኤስ አሜሪካ የመንግስት መምሪያ ለምግብ እና ለጸረ ድህነት እንቅስቃሴዎች እርዳታ እንዲውል ተልኮ የነበረውን 850 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ በወቅቱ በነበረው የፓርቲው ጠቅላይ ሚኒስትር ትዕዛዝ የፖለቲካ ወገንተኝነትን በያዘ መልኩ የታደለ ለመሆኑ ምርመራ እንዲደረግበት ቃል ገብቶ ነበር፡፡

ሆኖም ግን እስከ አሁን ድረስ ምንም ዓይነት የምርመራ ዘገባ አልቀረበም፡፡ (የአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ ዶላር ለፖለቲካ ወገንተኝነት ወይም ደግሞ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አላማጭ ተምቾች በውድ ሆቴሎች እየተዘዋወሩ ኮኛክ ሲገለብጡበት፣ የተለያዩ ውድ ምግቦችን ሲያማርጡበት እና ሌሎችን ሕገወጥ ድርጊቶች በመፈጸም በብክነት ላይ ውሏል በማለት ዩኤስኤአይዲን ለበርካታ ጊዚያት አስጨንቄ በመያዝ ጥያቄ እያቀረብኩለት ነበር፡፡)

በአሁኑ ጊዜ የዩኤስ አሜሪካ መንግስት ቀደም ሲል እንደዚያ ያለ የማጭበርበር ስራ ሲሰራ የነበረውን ማረት የተባለውን ያንኑ ሸፍጠኛ ድርጅት በኢትዮጵያ የረሀብ ሰለባ ለሆኑ ወገኖች የእርዳታ እህል ማከፋፈል እንዲችል በድጋሜ መርጦታል፡፡

እንግዲህ እስኪ አስቡት የዩኤስ መንግስት የረዥም ጊዜ ግንኙነት (ሽሪካ) (የዩኤስኤአይዲን አባባል በመዋስ ከማረት ጋር ባለው የትብብር ግንኙነት) የማፍያው ኮሚሽን ወይም ደግሞ በአሜሪካ በከተሞች አካባቢ ለሚገኙት ድሆች የእርዳታ እና የማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማከፋፈል የተዘጋጀ የማቃጠያ እቶን/ፈርናስ ነው የሚሆነው፡፡

የአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ በእንደዚህ ያለው የመንግስታቸው ወራዳ የቅሌት ተግባራት ቢያውቁ ከባድ ትያቄ ያቀርቡ ነበር።

ሆኖም ግን በአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ ሊታወቅ በማይችል መልኩ በድብቅ በኢትዮጵያ በስልጣን እንደመዥገር ተጣብቆ ከሚገኘው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጋር ሽርክና በመፍጠር በአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ ላይ ተመሳሳይ ሸፍጥን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና የምዕራብ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች የጋራ ጥምረት የተፈበረኩ አዳዲስ የማታለያ ጨዋታዎችን በመፈልፈል ለዓይናችን እይታ እንዲቀርቡ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ላለው ረሀብ መነሻው አንድ “ኤል ኒኖ” እየተባለ በሚጠራ ሰው የተከሰተ ነው በማለት የባጥ የቆጡን በመቀባጠር ላይ ይገኛሉ፡፡

የብሉምበርግ የዜና ወኪል ቃል አቀባይን ጠቅሶ እንደገለጸው ባለፈው ሳምንት አንድ አብርኃም ተከስተ እየተባለ የሚጠራ እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ልምድ የሌለው ሚኒስትር ደኤታ “በኢትዮጵያ ለተከሰተው ረሀብ መንስዔ ኤል ኒኖ ሲሆን አሁንም ቢሆን የኢኮኖሚ ዕድገታችን ለቀጣዮቹ 12 ወራት እስከ ሀምሌ 7 ድረስ 10 በመቶ እድገት በማሰመዝገብ አሁንም ቢሆን ግቡ የሚደረስበት ነው“ በማለት በድፍረት የገለጸ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

ምን ዓይነት ቅጥፈት ነው እባካችሁ***!

የብሉምበርግ ዘጋቢ በአሁኑ ጊዜ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ “የ10 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ይመዘገባል” የሚለው በምንም ታምር ሊሳካ የማይችል ሸፍጥ እና በአሁኑ ጊዜ ኤል ኒኖ የተባለው የአየር ለውጥ በረሀቡ ላይ ያለው ተጽዕኖም በጣም ትንሽ እንደሆነ በመግለጽ ውሸት የሚያመርተውን ተከስተ የተባለ ሚኒስትር ዴኤታ በጥያቄ አላፋጠጠዉም፡፡

ጠንካራ ትችትን የማይወዱት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች፣ መሰረታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ ጥቂት የውጭ ሀገር ዘጋቢዎች እና ሌሎች በኢትዮጵያ ያለው ኢኮኖሚ በሁለት አሀዝ ዕድገት በማስመዝገብ በዘላቂነት ይቀጥላል በማለት ያለምንም ሀፍረት ታላቅ ውሸት በማራመድ ላይ ይገኛሉ፡፡

ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚለውን ቅጥፈት ከዓመታት በፊት ፍጹም በሆነ እና ሙሉ በሙሉ ዉሸት መሆኑን ደጋግሜ አሳይቻለሁ።  ሆኖም ግን የውጭ ዘጋቢዎች ያለምንም ማሰብ በዘፈቀደ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጋዜጣዊ ፍትህን ለመስጠት በሚል የለዬለትን ውሸት ደግመው እና ደጋግመው መዋሸታቸውን ቀጥለዋል፡፡

ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት በሚለው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሸፍጥ ሙሉ በሙሉ ሸፍጥ መሆኑን ከዚህ ቀደም ባለኝ አስተማማኝ መረጃ ላይ በመመስረት ሀሰት እና ቅጥፈት መሆኑን ከማንም የውጭ ዘጋቢ ጋር ለመሞገት እችላለሁ፡፡

“የዓለም ባንክ እና የኢትዮጵያ ዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችቴ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስለ ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት እያቀረበ ያለውን ተራ ቅጥፈት በሬ ወለደ ከሚለው የባሰ ነው።

ግሎባል ፖስት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “እነርሱ [ኢትዮጵያውያን] ከፍተኛ የሆነ የማህበራዊ ፕሮግራምን በሚተገብር እና በ20 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ድህነትን በግማሽ እቀንሳለሁ በሚል መንግስት እየታገዙ በአሁኑ ጊዜ በፈጣን ዕድገት ላይ ከሚራመደው ኢኮኖሚ ጋር አብረው ይኖራሉ፡፡“

በኬንያ የሚገኘው እና ደይሊ ኔሽን እየተባለ የሚጠራው ታዋቂ ዕለታዊ ጋዜጣ በቅርቡ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣ “ወደ ሁለት አሀዝ ገደማ የተቃረበው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት እና ግዙፍ የሆነ የመሰረተ ልማት የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ሀገሪቱን ከአፍሪካ ቀዳሚ የኢኮኖሚ ስኬታማ እና የውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾችን የመሳብ ኃይል ያላት ሀገር እንድትሆን እድርጓታል“ ብሏል፡፡ ይህ አባባል ተራ የሆነ ውሸት፣ ውሸት አሁንም እንደገና ውሸት ነው!!!

ምን ዓይነት ተራ ቅጥፈት ነው***!

እውነታው ፍርጥ ፍርጥርጥ ብሎ ሲታይ ግን በዓለም ባንክ የቢዝነስ ስራ የ2015 ዘገባ መሰረት በዓለም ላይ ከሚገኙ ከ189 ኢኮኖሚዎች መካከል ኢትዮጵያ በ132ኛ ደረጃ ላይ ሆና ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 ኢትዮጵያ ትንሽ  “ትሻል” ነበር ከ2015፡፡

ቢዝነስን መጀመር ከሚለው ክፍፍል ጋር ሲታይ እ.ኤ.አ በ2015 ኢትዮጵያ ከ189 ሀገሮች መካከል በ168 ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

እ.ኤ.አ አቆጣጠር በ2014 ኢትዮጵያ ከ189 ሀገሮች ኢኮኖሚ መካከል በተመሳሳይ ክፍፍል በ165ኛ ደረጃ ላይ ትገኝ ነበር (እ.ኤ.አ በ2015 ከነበረው በመጠኑ ብልጫ በማሳዬት)፡፡

እነዚህ እውነታዎች ቢሆኑም ቅሉ እነዚህ የአዋቂ ማይም የውጭ ደንቆሮ ጋዜጠኞች በስንፍና እና አዕምሯቸውን በመሸፈን በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና በዓለም አቀፍ የድህነት ወትዋች አቃጣሪዎች የሚቀርብላቸውን የውሸት እና የሸፍጥ መረጃ መሰረት በማድረግ ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት እና ኢንቨስትምነት እድገት ውሸትን እንደ በቀቀን በመድገም እና በመደጋገም ላይ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ የውጭ ጋዜጠኞች ተራ አጭብርባሪዎች ናቸው፣ ሌላው ቀርቶ በዓለም ላይ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ነው የምትባለው ሀገር ለምን ህዝቦቿን መመገብ አልቻለችም እና 10 በመቶ የሚሆነው ህዝቧ ለምን የረሀብ ሰለባ ሆነ የሚል ጥያቄ እንኳ አያቀርቡም፡፡

ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት ስለኢትዮጵያ ዘገባ የሚያቀርቡት የውጭ ጋዜጠኞች “ብጫ ጋዜጠኞች” ወይም ተራ ወሬ ለቃሚዎች ናቸው ።

በአሁኑ ጊዜ ለማመን የሚያስቸግረው እና ትልቁ እውነታ ግን በማንኛውም በሚቻለው ነገር ሁሉ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ተንሰራፍቶ ለሚገኝው አስከፊ ረሀብ ዋናው መሰረቱ ኤል ኒኖ የተባለው የአየር ሁኔታ ነው የሚሉት ጉዳይ ነው፡፡

ጋዜጠኞች እየተባሉ የሚጠሩት ባለፉት 15 ዓመታት ቢያንስ ሶስት ኤል ኒኖዎች የነበሩ መሆናቸውን ያለማወቃቸው እውነታ አውቀው ማይም መሆንን የመረጡ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ ሆኖም ግን እስከ አሁን ድረስ ረሀብ በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ እየታየ ባለው ሁኔታ ረሀብን ለማስወገድ እና የረሀብ ሰለባ የሆኑትን 9 ሚሊዮን የሚሆኑ ወገኖቻችንን በምን ዓይነት ሁኔታ ለማስተናገድ እንደተዘጋጁ ያለማወቃቸው ጉዳይ ነው፡፡

በእርግጥ እ.ኤ.አ በ1997-98 ተከስቶ የነበረው ኤል ኒኖ እ.ኤ.አ ከ1950 ጀምሮ ተከስቶ ከነበረው ሁሉ በጣም ትልቅ በመሆን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ እየታዬ እንዳለው አውዳሚ ረሀብ በአስከፊ ሁኔታ የተከሰተ አልነበረም፡፡

እንደተባበሩት መንግስታት ዘገባ ከሆነ በኢትዮጵያ ያሉ የረሀብ ሰለባዎች በአሁኑ ጊዜ በእርስ በእርስ ጦርነትእየተበጣጠቀችካለችው ሶርያ በከፋ መልኩ በሚቀጥለው ዓመት ወደ 15 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በረሀብ በመጠቃት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ዘገባው እንዲህ በማለት ተጨማሪ አስተያየቱን ግልጽ አድርጓል፣ “በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጠንካራ የእርዳታ ምላሽ እስካልተሰጠ ድረስ ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዋስትና እጦት እና የምግብ ቀውስ ሊፈጠር የሚችልበት አጋጣሚ ሊከሰት ይችላል፡፡“

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና ምዕራባውያን ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝቦች በረሀብ ሲያልቁ ደስታ እና ፈንጠዝያ እያደረጉ ነው በማለት የዓለምን ሕዝብ በማታለል ለማሳመን በመውተርተር ላይ ይገኛሉ፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የመንግስት ኮሙኒክሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆነው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቀልደኛ ሬድዋን ሁሴን የተባለው በሀገሪቱ ውስጥ አስከፊ የሆነ የምግብ ቀውስ እንዳለ ዕውቅና የሰጠ ሲሆን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እርዳታ ማድረግ እንደማያስፈልግ እና በመንግስት አቅም ሁሉም ነገር መሸፈን እንደሚችል ዓይኑን በጨው ታጥቦ በድፍረት ውሸት ተናግሮ ነበር (ሀሳቤን በተሻለ ሁኔታ ይገልጽልኝ እንደሆን መናገር ሳይሆን መቀደድ ልበለው ይሆን?)

ሬድዋን እንዲህ ይላል “ኢትዮጵያ የውጭ የምግብ እርዳታ አትፈልግም፡፡“ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ መንግስት ከሬድዋን መግለጫ ጋር በተጻረረ መልኩ 8.2 ሚሊዮን የሚሆነውን የረሀብ ሰለባ የሆነ ሕዝብ ለመመገብ የውጭ እርዳታ ያስፈልጋል ይላል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደናቁርት ታሪካቸውን እንኳ ቀጥተኛ በሆነ መልኩ ሊያቀርቡት አይችሉም፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሬድዋን እንዲህ ብሎ ነበር፣ “እራሳችንን መመገብ እንችላለን፣ እናም በዝናብ እጥረት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ጨምሮ የረሀቡ ችግር በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ምንም ዓይነት ጉዳት ሊያስከትልስለማይችልእራሳችንን መመገብ እንችላለን“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ስለሆነም 8.2 ሚሊዮን የሚሆኑት ህዝቦች በአሁኑ ጊዜ በምግብ መትረፍረፍ ምክንያት በደስታ እና በፈንጠዝያ ላይ ነው ያሉትን?

ይኸ ሬድዋን የሚባል ሰው ክህደት እየፈጸመ ነው ወይስ ደግሞ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ህይወት ላይ እርባናየለሽ ቀልድ እያደረገ ነው?

ምናልባትም ከጆንያ ሙሉ ድንጋይ የደነዘ እና ትንሽም ቢሆን የእውቀት ጭላንጭል የሌለው ውሸታም እና አስመሳይ ፍጡር ነው?

እንደ ሬድዋን አባባል ከሆነ የረሀብ ሰለባ የሆኑት ኢትዮጵያውያን በረሀብ መጠቃታቸውን አያውቁትም ማለተ ነው፡፡

ስለሆነም እውነተኛው ጥያቄ መሆን ያለበት፡ ሬድዋን እና (ምናልባትምምናልባትም ሬድዋን  የወያኔ ወሮበላ የዘራፊቡድንሊቅ ተብሎ ሊታይ ይቻላል) 8.2 ሚሊዮን የሚሆኑትን የረሀብ ሰለባ የሆኑትን ኢትዮጵያውያን ከረሀብለመታደግይችላሉን?

እ.ኤ.አ መስከረም 2010 አሁን በህይወት የሌለው የሬድዋን አለቃ መለስ ዜናዊ (የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አዕምሮ) እራሱን ከፍ ከፍ እያደረገ ምጸትን በተላበሰ መልኩ እንዲህ በማለት አውጆ ነበር፣ “የተትረፈረፈ ምርት ለማምረት የሚያስችለንን ዘዴ ቀይሰናል፣ እናም እ.ኤ.አ በ2015 ምንም ዓይነት የውጭ እርዳታ ሳያስፈልገን እራሳችንን መመገብ እንችላለን፡፡“

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእነርሱ የድድብና አገላለጽ ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ኢንቨስትመንትን መሳብ፣ እና ሌላም ሌላም በማለት ሁሉንም ህዝብ ማታለል እንደሚችሉ አድርገው እራሳቸውን አሳምነዋል፡፡

ማንም ቢሆን መረጃዎችን በመጠቀም እውነታውን ነቅሶ በማውጣት ውሸት መሆኑን ያረጋግጥብናል ብለው አያስቡም፡፡

(ፍትሀዊ ለመሆን ስንት ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ተንታኞች፣ ወዘተ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እምነተ ቢስ ከሀዲ እና በቅጥፈት የተሞላ መሆኑን አረጋግጠዋል?)

ደህና እውነቱ መነገር አለበት፡፡ ለሴቷ ዳክዬ ጥሩ የሆነው ነገር ሁሉ ለወንዱ ዳክየም ጥሩ ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስቦች ውሸታሞች ሆነው እንደተፈጠሩ ሁሉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የምሁርነት አንደበታቸው ሽባ ሆኗል፡፡

የበለጠ አስከከፊው ሁኔታ ገና ወደፊት ይመጣል፣

እ.ኤ.አ በ2011 የዩኤስ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እ.ኤ.አ በ2050 አሁን ካለበት ከሶስት ጊዜ በላይ እጥፍ በማደግ 278 ሚሊዮን እንደሚሆን ትንበያ ሰጥቷል፡፡

እ.ኤ.አ በ2025 ማለትም ከዛሬ 10 ዓመታት በኋላ የዩኤስ አሜሪካ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 131 ሚሊዮን እንደሚሆን ትንበያ ሰጥቷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ 99 ሚሊዮን ሕዝቦቿን መመገብ አትችልም፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 87 ሚሊዮን የነበረውን ሕዝብ መመገብ አልቻለችም ነበር፡፡

እንደዚሁም ሁሉ እ.ኤ.አ በ2006 78 ሚሊዮን የነበረውን ሕዝብ መመገብ አልቻለችም ነበር፡፡

አንግዲህ ያሉት ተጨባጭ መረጃዎች ሁሉ ይህንን የመሰለ እውነታ የሚያመላክቱ ከሆነ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2025 131 ሚሊዮን የሚሆነውን ሕዝብ ለመመገብ ከፍተኛ የሆነ ችግር ሊሆንባት አይችልምን?

ኢትዮጵያ በተዛነፈው እና በተሳሳተው የማልተስ የእልቂት መንገድ፣ (በሽታ፣ ረሀብ፣ ጦርነት፣ ወዘተ ተመጣጣኝ የምግብ አቅርቦት ደረጃ ላይ እስከሚደረስ ድረስ የሕዝቡን ቁጥር ወደፊት ሊቀንሱት ይችላሉ ወደሚለው አስተሳሰብ) በፍጥነት በመጓዝ ላይ ናት፡፡

በኢትዮጵያ ረሀብ በኤል ኒኖ፣ በኤል ኒና ወይም ደግሞ በኤል ቻፖ አልተፈጠረም፡፡

እንደዚሁም ደግሞ ረሀብ በድርቅ አልተፈጠረም፡፡

ረሀብ በኢትዮጵያ የተፈጠረው በብልሹ አስተዳደራዊ ስርዓት ምክንያት ነው!

ረሀብ በኢትዮጵያ የተፈጠረው በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኤል ፓትሮንስ ማለትም የረሀብ ቋሚደንበኞችአማካይነት ነው፡፡

የዓለም ባንክ ዋና ኢኮኖሚስት የሆኑት ወልፍ ጋንግ ፌንግለር ይህንን በማስመልከት እ.ኤ.አ በ2011 አንዲህ ብለው ነበር፡

በአፍሪካ ቀንድ ያለው ረሀብ ዋና ምክንያት በተፈጥሮ እና በአካባቢያዊ ምክንያቶች ከመሆን ይልቅ በዘፈቀደ በሚጨመረው የምግብ ዋጋ እና በህብረተሰቡ መካከል በሚደረገው ግጭት ምክንያት ነው፡፡ ቀውሱ ሰው ሰራሽ ነው፡፡ ድርቆች በተደጋጋሚ ይከሰታሉ፣ ሆኖም ግን ያንን ረሀብ እንዲከሰት የሚያደርገው መጥፎ የፖሊሲ አነዳደፍ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ በኢትዮጵያ ለረሀብ ችግር ድርቅ ወይም ደግሞ ሌላ አካባቢያዊ ሁኔታ ሳይሆን ዋናው መንስኤ መጥፎ እና ደካማ አስተዳደር ነው፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ “ኤል ፓትሮንስ” (የዝርፍያ አባቶች) በኢትዮጵያ ረሀብን ሊያጠፉ አይችሉም፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ ወደ ስልጣን የመጡት እ.ኤ.አ በ1984-85 በጥቁር የምፃት (ረሃብ) ፈረስ እየጋለቡ ነው፡፡

ረሀብ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለኤል ፓትሮንስ የእናት ጡት ማለት ነው፡፡

ረሀብ በኢትዮጵያ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትርንስ ትልቅ የቢዝነስ ስራ ነው፡፡

ረሀብ እ.ኤ.አ በ1984-85 ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ ታላቅ የቢዝነስ ስራ ሆኖላቸው ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2015 ረሀብ በኢትዮጵያ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ ትርፋማ የሆነ የቢዝነስ ስራ ሆኗል፡፡

እ.ኤ.አ በ2016 ትልቅ ረሀብ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ ትልቅ የወተት ላም ማለት ነው፡፡

ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፓትሮንስ በየዲፕሎማሲ ጽ/ቤቶች እና በየኤምባሲዎች በመሄድ እንደበግ በመጮህ መነጋጋቸውን ያፋጫሉ፣ የልመና አኩፋዳቸውን ይዘረጋሉ፡፡ ለተራቡት ወገኖች የሚሆን እባካችሁ ምጽዋዕት ለግሱን በማለት ይለምናሉ!

እ.ኤ.አ በ2016 የረሀብ ቢዝነስ መልካም የሚሆነው ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ ብቻ ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ በረሀብ በዓላቸው ጊዜ እንዲህ በማለት የመዝናናት ቸበርቻቻ ድርጊቶችን ይፈጽማሉ፡

ምንድን እፈልጋለን? ረሀብ! ረሀብን የምንፈልገው መቼ ነው? አሁኑኑ!

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ረሀብን ከኢትዮጵያ እንዲያጠፋ መጠየቅ ማለት ከማፊያ ቡድን በከፍተኛ የወለድ ምጣኔ ብድር መበደርን፣ ማጭበርበርን፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ማካሄድን እና የፖለቲካ ሙስናን ማስወገድ እንዲችል ከመጠየቅ ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡

“በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ያለውን ረሀብ ማስቆም ይችላልን?” ለሚለው ጥያቄ እንዲህ የሚል ሌላ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል፡፡

“በአሁኑ ጊዜ የማፊያ ቡድን ወንጀል መስራትን ማቆም ይችላልን?“

“የወንጀል አረም መራራ ፍሬን ትሰጣለች፡፡ ወንጀል አዎንታዊ ውጤት የለውም“ ያለው ማን ነበር?

ደህና!!! እንደዚሁም ሁሉ የረሀብ አረም መራራ ፍሬን ትሰጣለች፡፡ ሆኖም ግን ረሀብ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ የተንፈላሰሰ የምቾት የኑሮ ዘይቤን ያመቻቻል!

ይቀጥላል 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ጥቅምት 16 ቀን 2008 .

ነውረኛ ውሸታም ኣገዛዝ ፡ ወገን በረሃብ አና በድህነት አያለቀ ተኣምር አንፈጥራለን ማለት በሕዝብ ላይ ማሾፍ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በስድስት ወራት ትምህርት ዶክተሬት ያገኘው ኣርከበ አቁባይ በኢኮኖሚ ፖሊሲው ዙሪያ ባለፉት ኣመታት ሲያጭበረብር ቆይቶ ኣልተሳካለትም። የቁጥር ቁልሎችን ከመፍጠር ውጪ ምንም የተገበረው ነገር የለም፤ በላኪዎች የሚገኘውን የውጪ ምንዛሬ በዜሮ ያንደፋደፈ ሀገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ገንዘብ በሙስና ያዘረፈ ግለሰብ ዛሬ ላይ ሆኖ ለሚቀጥሉት ኣምስት ኣመታት ተኣምር አንሰራለን በማለት የተለመደ ሃሰቱን አየደሰኮረ ይገኛል፤ተአምር ጠብቁ የሚል ሙድ መያዝ ጀምሯል:: የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ኣውታሮች ዲያስፖራው ለቤተሰቡ በሚልከው ዶላር አና የኣለም ነዳጅ ዋጋ በመውረዱ ተደግፎ መኖሩ አየታወቀ በየትኛው መስመር ተኣምር ሊሰራ አንደታሰበ ግራ ያጋባል፤ግራ ከማጋባትም ኣልፉ ግልጽ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ኣገዛዙ ኣጣብቂኝ ውስጥ መሆኑን በገሃድ ያሳያል፥፥በብድር ገንዘብ ተኣምር ሊሰራ ከታሰበ አንዴት ኣበዳሪዎችስ ያበድራሉ፥ወያኔ የተበደረው ገንዘብ ከኣቅም በላይ ከመሆኑ ኣንጻር ካሁን በኋላ ልበደር ማለት ኣሳሳቢ ነው ሲሉ የኣለም ኣበዳሪ ድርጅቶች ሲያማርሩ ተስተውሏል::በባዶ ካዝና ምን አይነት ተአምር እንደሚሰራ አቶ አርከባ ካሳዩን በባዶ ካዝና ተአምር ይሰራ ኢኮኖሚስት ተብለው በአለም አስደናቂ ጉዳዮች መዝገብ ላይ ይሰፍራሉ::

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ሕንጻ ሶስተኛ ፎቅ ላይ ተዘፍዝፈው መላ ሃገሪቱ በምቾት የተንቆጠቆጠች የመሰላቸው አቶ አርከበ እንደ ዘራፊ ባልንጀሮቻቸው እርሳቸውም በአዲስ ስልት በድህነት እና በረሃብ በተጎዳው ሕዝብ ላይ እየተዘበባቱ ይገኛሉ::ሃምሳ ከመቶ የሚሆነው ገበሬ ምርጥ ነጋዴ ወቶታል የሚለው የሕወሓቱ አህያ አሻንጉሊት ሃይለማርያም ደሳለኝ ገበሬው የማዳበሪያ ኬሚካሎች በፈጠሩት የመሬት ድርቀት የተፈጥሮ ችግሮች በጋረጡበት አደጋ እንዲሁም በአገዛዙ ፖሊሲ ከባድ ችግር ውስጥ መሆኑን ሊናገሩ አልደፈሩም::ያው ተቃዋሚው ስለ ሕዝብ ከመጮህ ይልቅ እርስ በእርሱ በወያኔ አጀንዳ እየተባላ ባለበት በዚህ ወቅት አውሬዎቹ ወያኔዎች በሃገር እና ሕዝብ ሕልውና ላይ እየቀለዱ ይገኛሉ::

ይህ አሳፋሪ እና ጨካኝ አገዛዝ በፖለቲካ ጫና ሕዝቡን እያሰቃየ በብዝበዛ የሃገሪቱን ካዝና አራቁቶ በጉልበት እና በድርድር ፍትህን እየነገደ ተአምር ልሰራ ነው በሚል እጅግ አደገኛ የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን እያራገበ ነው::በመልካም አስተዳደር እጦት ሕዝብ እያለቀሰ ቃልና ተግባር አልገናኝ ብለው ሕዝብን እየተማርረ ራሳቸውን ከሕግ በላይ ያደረጉ ሹማምንት ኢሰብዓዊ ተግባር እየፈጸሙ መብትን መጠየቅም ሆነ ቅሬታ ማቅረብ አሸባሪ እያሰኘ ሃላፊነት በጎደለው ግብረገብነት ባሌለው የሹማምንት እብሪተኝነት የነጻነት መብት እየተደፈጠጠ ዜጎች እየተሸማቀቁ ሐሳብን በነፃነት መግለጽም ሆነ መብትን መጠየቅ ወንጀለኛ አሸባሪ በሚሰኝበት አገር ምን አይነት ተአምር ከሹማምንት ይጠበቃል::ይህችን አይነት ማጭበርበር ለማንም አትበጅም ሃገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ አደጋ ውስጥ ባለችበት በዚህ ሰአት ስልጣን ለሕዝብ ከማስረከብ ውጪ ምንም ተአምር ሊሰራ አይችልም::ባለፉት አመታት የነበሩ የኢኮኖሚ እድገቶች ከቁጥር ቁልል ውጪ ምንም አልፈየዱም::አሁንም ቢሆን በረሃብ የተጎዱ ዜጎቹን መመገብ ያልቻለ ሃሰተኛ አገዛዝ እንዴት አድርጎ ተአምር ሊሰራ ይችላል::የማይመስል ነገር ነው::የወያኔን ተአምር ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ በአንድነት ታግሎ ይህንን ሃሰተኛ አገዛዝ ማስወገድ የለውጥ ሃይሎች ድርሻ መሆን ይገባዋል::በባዶ ካዝና ተአምር እፈጥራለሁ ብሎ መነሳት ራስን ከማጭበርበር ውጪ ምንም ውጤት የለውም::ነውረኛ ውሸታም ኣገዛዝ ፡ ወገን በረሃብ አና በድህነት አያለቀ ተኣምር አንፈጥራለን ማለት በሕዝብ ላይ ማሾፍ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ነውረኛ ውሸታም ኣገዛዝ ፡ ወገን በረሃብ አና በድህነት አያለቀ ተኣምር አንፈጥራለን ማለት በሕዝብ ላይ ማሾፍ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በስድስት ወራት ትምህርት ዶክተሬት ያገኘው ኣርከበ አቁባይ በኢኮኖሚ ፖሊሲው ዙሪያ ባለፉት ኣመታት ሲያጭበረብር ቆይቶ ኣልተሳካለትም። የቁጥር ቁልሎችን ከመፍጠር ውጪ ምንም የተገበረው ነገር የለም፤ በላኪዎች የሚገኘውን የውጪ ምንዛሬ በዜሮ ያንደፋደፈ ሀገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ገንዘብ በሙስና ያዘረፈ ግለሰብ ዛሬ ላይ ሆኖ ለሚቀጥሉት ኣምስት ኣመታት ተኣምር አንሰራለን በማለት የተለመደ ሃሰቱን አየደሰኮረ ይገኛል፤ተአምር ጠብቁ የሚል ሙድ መያዝ ጀምሯል:: የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ኣውታሮች ዲያስፖራው ለቤተሰቡ በሚልከው ዶላር አና የኣለም ነዳጅ ዋጋ በመውረዱ ተደግፎ መኖሩ አየታወቀ በየትኛው መስመር ተኣምር ሊሰራ አንደታሰበ ግራ ያጋባል፤ግራ ከማጋባትም ኣልፉ ግልጽ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ኣገዛዙ ኣጣብቂኝ ውስጥ መሆኑን በገሃድ ያሳያል፥፥በብድር ገንዘብ ተኣምር ሊሰራ ከታሰበ አንዴት ኣበዳሪዎችስ ያበድራሉ፥ወያኔ የተበደረው ገንዘብ ከኣቅም በላይ ከመሆኑ ኣንጻር ካሁን በኋላ ልበደር ማለት ኣሳሳቢ ነው ሲሉ የኣለም ኣበዳሪ ድርጅቶች ሲያማርሩ ተስተውሏል::በባዶ ካዝና ምን አይነት ተአምር እንደሚሰራ አቶ አርከባ ካሳዩን በባዶ ካዝና ተአምር ይሰራ ኢኮኖሚስት ተብለው በአለም አስደናቂ ጉዳዮች መዝገብ ላይ ይሰፍራሉ::

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ሕንጻ ሶስተኛ ፎቅ ላይ ተዘፍዝፈው መላ ሃገሪቱ በምቾት የተንቆጠቆጠች የመሰላቸው አቶ አርከበ እንደ ዘራፊ ባልንጀሮቻቸው እርሳቸውም በአዲስ ስልት በድህነት እና በረሃብ በተጎዳው ሕዝብ ላይ እየተዘበባቱ ይገኛሉ::ሃምሳ ከመቶ የሚሆነው ገበሬ ምርጥ ነጋዴ ወቶታል የሚለው የሕወሓቱ አህያ አሻንጉሊት ሃይለማርያም ደሳለኝ ገበሬው የማዳበሪያ ኬሚካሎች በፈጠሩት የመሬት ድርቀት የተፈጥሮ ችግሮች በጋረጡበት አደጋ እንዲሁም በአገዛዙ ፖሊሲ ከባድ ችግር ውስጥ መሆኑን ሊናገሩ አልደፈሩም::ያው ተቃዋሚው ስለ ሕዝብ ከመጮህ ይልቅ እርስ በእርሱ በወያኔ አጀንዳ እየተባላ ባለበት በዚህ ወቅት አውሬዎቹ ወያኔዎች በሃገር እና ሕዝብ ሕልውና ላይ እየቀለዱ ይገኛሉ::

ይህ አሳፋሪ እና ጨካኝ አገዛዝ በፖለቲካ ጫና ሕዝቡን እያሰቃየ በብዝበዛ የሃገሪቱን ካዝና አራቁቶ በጉልበት እና በድርድር ፍትህን እየነገደ ተአምር ልሰራ ነው በሚል እጅግ አደገኛ የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን እያራገበ ነው::በመልካም አስተዳደር እጦት ሕዝብ እያለቀሰ ቃልና ተግባር አልገናኝ ብለው ሕዝብን እየተማርረ ራሳቸውን ከሕግ በላይ ያደረጉ ሹማምንት ኢሰብዓዊ ተግባር እየፈጸሙ መብትን መጠየቅም ሆነ ቅሬታ ማቅረብ አሸባሪ እያሰኘ ሃላፊነት በጎደለው ግብረገብነት ባሌለው የሹማምንት እብሪተኝነት የነጻነት መብት እየተደፈጠጠ ዜጎች እየተሸማቀቁ ሐሳብን በነፃነት መግለጽም ሆነ መብትን መጠየቅ ወንጀለኛ አሸባሪ በሚሰኝበት አገር ምን አይነት ተአምር ከሹማምንት ይጠበቃል::ይህችን አይነት ማጭበርበር ለማንም አትበጅም ሃገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ አደጋ ውስጥ ባለችበት በዚህ ሰአት ስልጣን ለሕዝብ ከማስረከብ ውጪ ምንም ተአምር ሊሰራ አይችልም::ባለፉት አመታት የነበሩ የኢኮኖሚ እድገቶች ከቁጥር ቁልል ውጪ ምንም አልፈየዱም::አሁንም ቢሆን በረሃብ የተጎዱ ዜጎቹን መመገብ ያልቻለ ሃሰተኛ አገዛዝ እንዴት አድርጎ ተአምር ሊሰራ ይችላል::የማይመስል ነገር ነው::የወያኔን ተአምር ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ በአንድነት ታግሎ ይህንን ሃሰተኛ አገዛዝ ማስወገድ የለውጥ ሃይሎች ድርሻ መሆን ይገባዋል::በባዶ ካዝና ተአምር እፈጥራለሁ ብሎ መነሳት ራስን ከማጭበርበር ውጪ ምንም ውጤት የለውም::ነውረኛ ውሸታም ኣገዛዝ ፡ ወገን በረሃብ አና በድህነት አያለቀ ተኣምር አንፈጥራለን ማለት በሕዝብ ላይ ማሾፍ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

“ወህኒ ቤት” ወይም “ወህኒ” የሚለው ቃል ከየት እንደመጣ ያውቃሉ ?

እምነት ታደሰ

ወህኒ የተራራ ስም ነው ። የወህኒ ተራራ በስሜን ጎንደር የሚገኝ ሲሆን በአጼፋሲለደስ ዘመን ለመጀምሪያ ጊዜ ለተገዳዳሪ የነገስታት ወንድ ዘሮች እንደ እስር ቤት አገልግሏል። ይህም እርስ በርስ ጦርነትን ከወደፊቱ ለማስቆም ነበር። ፋሲል ልጁ ዳዊት ሲያምጽ ለመጀመሪያ ጊዜ በእስር ወደዚህ ተራራ ልኮታል። የዚህ ስርዓት ምንጭ ቀደምቱ የደብረ ዳሞ እና ግሸን አምባ ዘይቤ ነበር። አጼ ፋሲል ይህን ተራራ ለእስር ቤት ከተጠቀሙበት ጀመሮ እስከ ዘመነ መሳፍንት (በተለይ 1790) ድረስ አምባው በዚህ መልኩ አገልግሏል። በአሁኑ ዘመን የተለያዩ ሰወች ተራራውን ለመውጣት ሞክረው ከአንድ ሰው በስተቀር አልቻሉም ይባላል፤ በድሮው ዘመን ግን ቤ/ክርስቲያን እና ቤተ መንግስት በተራራው ላይ ተሰርቶ ነበር። ፍርስራሾቹም አሁን ድረስ በምኩራቡ ይገኛሉ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ “ወህኒ ቤት” የሚለው ቃል የወንጀለኛ መቅጫ የዕሥር ቤትን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል። Read more

በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ፡፡

ባለፈው አርብ ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ አባላት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ የሆነውን አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በታጠቀው ኮልት ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 6 ፖሊሶችን መትቶ መሬት ላይ አጋድሟቸዋል፡፡

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ “አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል…” እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡

ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡፡

እጁን ለጠላት አሳልፎ ላለመስጠት እሳት ጨልጦ የአርበኛ ሞት በሞተው ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ የኮልት ጥይት ሰለባ ከሆኑት 6 የፖሊስ አባላት ሦስቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ በጠና ቆስለው በሞትና በህይወት መካከል ሆነው ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙት ፖሊሶች የደረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ከሞት ሊተርፉ እደማይችሉ እየተገለፀ ነው፡፡
ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በህይወት ለመያዝ ሳይሳካላቸው የቀሩት የጎንደር ከተማ ጥቂት የህወሓት ተላላኪ ፖሊሶችና ደህንነቶች እንዲሁም የመስተዳደሩ አገልጋይ ባለስልጣናት አስከሬኑን በቁጥጥር ስር በማዋል “አንሰጥም” ብለው የነበረ ሲሆን በመጨረሻም በአካባቢው ህዝብ ግፊት የጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ አስከሬን ለቤተሰቡ ተሰጥቶ ስርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡

በተመሳሳይም ሳጅን ወለላው ዋናይሁን የተባለው የመተማ ወረዳ ፖሊስ የአመራር አባል እንደዚሁ አንድ በወወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክር ከነተከታዮቹ ተገድሏል፡፡

Source: (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47730#sthash.kfWIv4ZY.dpuf

የኢትዮጵያ ምሑራን በዲሞክራሲ ትግል ውስጥ በስፋት አለመሳተፍ በለውጥ ትግሉ ላይ ያሳደረው ተጽእኖ

October 26, 2015

ጃናሞራ – ከስዊዘርላንድ

ወቅቱን በትክክል አላስታውሰውም ብቻ በግምት በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2010 አጋማሽ ወይም መጨረሻ አካባቢ ይመስለኛል። በጀርመናዊቷ ከተማ በፍራንክፈርት አንድ ሕዝባዊ ሥብሰባ ይዘጋጃል። የሥብሰባው አዘጋጆች የያኔው የግንቦት 7 ንቅናቄ የጀርመን አስተባባሪዎች ነበሩ። የስብሰባውም አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ የጀመረውን የነጻነት ትግል አስመልክቶ ከኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ ለመወያየት ሲሆን በስብሰባው ላይ የተጋበዙት እንግዳ የግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የነጻነት ታጋዩና ጀግናው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ነበሩ።

ስብሰባው እጅግ የተሳካና በስብሰባው ላይ የተካፈሉትን ኢትዮጵያውያን ሥሜት ያረካ ፤ በብዙዎች ጭንቅላት ሲመላለሱ የነበሩ ጥያቄዎችን የመለሰ እንደነበረም ትዝ ይለኛል። በተለይ የተወሰኑ የአገዛዙ ደጋፊዎችና ካድሬዎች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ያነጣጠሩ አሉባልታዎችንና የስም ማጥፋት ተረት ተረታቸውን ባሰሙበት ወቅት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ትዕግስት እና በሳል አስተያየቶች መቼም አይረሱኝም። ከሁሉ በላይ ግን ቀልቤን የሳበውና ለዛሬው ጽሁፌ መነሻ እንዲሆነኝ ያነሳሳኝን አቢይ ጉዳይ ግን እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ። የእለቱን ሥብሰባ ለማገባደድ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አስተያየት መስጠት እንደጀመሩ አንድ በፍራንክፈርት ነዋሪ የሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ካህን ከመቀመጫቸው በመነሳት መስቀላቸውን በቀኝ እጃቸው ይዘው ካማተቡ በኋላ በስብሰባው ላይ የነበርነውን ታዳሚዎች ሁሉ ያስደመመ እና ያስደነቀ ታሪክ እንዲህ በማለት ጀመሩ።

አንድ አባት ለጉብኝት ወደ ሀገረ አሜሪካ ይሄዱና ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም ወዳጆቻቸውን ከጠያየቁ በኋላ ወደ እናት ሐገራቸው ለመመለስ ይዘጋጃሉ።ታድያ ወደ ሐገር ቤት ከመመለሳቸው በፊት በአንዱ ቀን ወደ አንድ የጉብኝት ሥፍራ ይጓዙና ጉብኝታቸውን ይጀምራሉ። ከጥቂት ደቂቃ በኋላም ወደ አንድ በአጸድ የተሞላ የመቃብር ሥፍራ ይደርሳሉ። እኚህ አባት አጸዱን እያቋረጡ በሚሄዱበት ወቅት አይናቸው ወደ አንድ የመቃብር ሥፍራ ያመራል። ሐውልቱን ትኩር ብለው ሲመለከቱት በሐውልቱ ላይ የተጻፈው የሟቹ የህይወት ታሪክ እጅግ ያስገርማቸዋል። ፕሮፌሰር እከሌ በተወለደ በ 8 ዓመቱ አረፈ ይላል ጽሁፉ፤ እኚህ አባት በጣም ይገረሙና እንዴት ነው ነገሩ? እንዴት አንድ ሰው በስምንት አመት እድሜው ፕሮፌሰር ሊሆን ይችላል? እያሉ በውሥጣቸው እያብሰለሰሉ ወደ ሌላኛው መቃብር ሲጠጉ ሐውልቱ ላይ ዶክተር እከሌ በተወለደ በ3 አመቱ አረፈ የሚል ሌላ ጽሁፍ ይመለከታሉ። አይናቸውን ይጠራጠሩና በመሀረባቸው ጠረግ ጠረግ አድርገው እንደገና ቢመለከቱት ጽሁፉ ተመሳሳይ ሆኖ ያገኙታል። በጣም ተገረሙ! ግራ ተጋቡ! እዚህ ሐገር ደግሞ ትምህርቱ እንዴት ነው? ሲሉ ራሳቸውን ይጠይቁና መልሱን ስላላገኙት ሥለ ጉዳዩ ለመጠየቅና ለመረዳት በማሰላሰል ላይ እያሉ ትንሽ እንደተራመዱ አይናቸው ሌላ መቃብር ላይ ያርፋል። ይህኛው ደግሞ ኢንጂነር እከሌ በተወለደ በ5 አመቱ አረፈ ይላል። እጅግ በጣም ግራ የተጋቡት አባት ሥለ ሁኔታው ለመረዳት በአካባቢያቸው ሥለ ጉዳዩ ሊያስረዳቸው የሚችል ሰው እንዳለ በዓይናቸው ይቃኛሉ። በግርምት ከቆሙበት ሥፍራ ከደቂቃዎች በኋላ አንድ በእድሜያቸው ጠና ያሉ አሜሪካዊ አዛውንት ጠጋ ይሉና የምረዳዎት ነገር ይኖር ይሆን? ሲሉ ይጠይቋቸዋል። እኚህ ኢትዮጵያዊ አባትም ደንገጥ ብለው ኧ ኧ አዎ አዎ አንድ ነገር እንዲያስረዱኝ እፈልጋለሁ ይሉና በአመልካች ጣታቸው ወደ መጀመሪያው ሐውልት እየጠቆሙ በሐውልቱ ላይ ያነበቡትን ታሪክ መናገር ይጀምራሉ። እዚህ የመቃብር ሐውልት ላይ ፕሮፌሰር እከሌ በተወለደ በ8 ዓመቱ አረፈ የሚል ጽሁፍ ይነበባል። እንደገና ያኛው ሐውልት ላይ ደግሞ ዶክተር እከሌ በተወለደ በ3 ዓመቱ አረፈ ይላል። ይህኛው ደግሞ ኢንጂነር እከሌ በተወለደ በ5 ዓሙቱ ማረፉን ይገልጻል ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? የዚህ ሐገር ሥርአተ ትምህርትሥ እንዴት ነው? አንድ ሰው በስምንት ዓመት እድሜው ፕሮፌሰር በአምስት እና በሶስት አመት እድሜ ደግሞ ዶክተር እና ኢንጂነር ለመሆን የሚቻለው ብለው ይጠይቃሉ። አሜሪካዊው አዛውንትም ሲመልሱ አዩ አባቴ ይህ ሰው በርግጥ ፕሮፌሰር ነው የተፈጥሮ እድሜውም እዚህ ሐውልቱ ላይ እንደሰፈረው አይደለም። የትምህርት ሥርአቱም ቢሆን ከሌላው ዓለም ብዙም የተለየ ሆኖ አይደለም። ነገር ግን ይህ ይህ ፕሮፌሰር በህይወት ሲኖር ለሐገሩና ለወገኑ የሚጠቅም ተግባር ያከናወነው ስምንት ዓመት ብቻ በመሆኑ በተወለደ በስምንት ዓመቱ አረፈ ተብሎ ሊጻፍ ችሏል። ሌሎቹም ያዩዋቸው ዶክተር እና ኢንጂነር በሕይወት ዘመናቸው ለሕዝባቸውና ለሐገራቸው የሚጠቅም እና የሚበጅ ተግባር የፈጸሙት አምስት እና ሶስት አመታት በመሆኑ የመቃብር ሐውልታቸው ላይ ለትውልዱ ጠቃሚ የሆነ ተግባር የፈጸሙበት አመታት ብቻ ተጻፉ ብለው ያስረዷቸዋል። እኚህ ኢትዮጵያዊ አባትም ባዳመጡት ታሪክ እጅግ ተገርመው እና ተደንቀው ማሰላሰል ይጀምራሉ። ራሳቸውንም እኔስ ለሐገሬ እና ለወገኔ የሚጠቅም ምን ተግባር አከናውኜአለሁ ሲሉ ይጠይቃሉ። በርግጥ እኚህ አባት በሕይወት ዘመናቸው እንደ ሃይማኖት አባትነታቸው የሚጠበቅባቸውን አድርገዋል። ነገር ግን እኚህ አባት በተመስጦ ሲያስቡት እሳቸው በሕይወት ዘመናቸው የፈጸሟቸው ተግባራት ሁሉ አንሰው ይታያቸዋል።

ኢትዮጵያዊው አባትም አሜሪካዊውን አዛውንት አመስግነው የመጨረሻ ጥያቄ አነሱ ። እንዲህ ሲሉ!! በእውነት ከነገሩኝ ታሪክ ብዙ ተማርኩ፤ ወደ ውስጤም ለመመልከት ቻልኩ፤ ራሴንም እኔስ ለወገኔ ምን ሰራሁ ሥል ጠየኩት። ካሉ በኋላ ለመሆኑ እኔሥ ስሞት በመቃብሬ ላይ ምን ተብሎ ሊጻፍ ይችላል ? ሲሉ ጥያቄአቸውን ይሰነዝራሉ። አሜሪካዊው አዛውንትም ጥቂት አሰቡና ለመሆኑ በሕይወት ዘመንዎ ለሐገርዎ እና ለወገኖችዎ የሚጠቅም እና የሚበጅ ምን በጎ ነገር አበርክተዋል ሲሉ ይጠይቃሉ?

ኢትዮጵያዊው አባትም ጥቂት ሲያሰላሥሉ ቆዩና እኔሥ ለሀገሬም ሆነ ለሕዝቤ ይሄ ነው የሚባል የረባ ነገር የፈጸምኩ አይመስለኝም ሲሉ መለሱ። አሜሪካዊው አዛውንትም እንግዲያው እንደ መልስዎ ከሆነና ለሐገርዎና ለሕዝብዎ የሚበጅ በጎ ነገር ያላደረጉ ከሆነ የርስዎ መቃብር ላይ እንደተወለደ አረፈ ተብሎ ይጻፋል አሏቸው !!!!! ብለው ታሪኩን ደመደሙት።

እጅግ አስደናቂ እና አስተማሪ ታሪክ ፡ የሰው ልጅ ያለውን እውቀት ሁሉ ለሌላው ሲያካፍል ፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በጎ ተግባራትን ለመፈጸም ሲዳክር እና ሲደክም ፤ ዘመን ተሻጋሪ የሆነ አስተሳሰብ እና ተግባራት ሲኖሩት ከዚህች ከምንኖርባት አለም ቢያልፍ እንኳን በሕይወት ዘመኑ የፈጸማቸው መልካም ተግባራት ሕያው ሆነው ሥሙ ከመቃብር በላይ ከትውልድ ትውልድ ሲዘከር እንደሚኖር ታሪክ ያስተምረናል።

እንግዲህ ለመግቢያ ያህል ይህንን በኔ አመለካከት ታላቅና አስተማሪ ሊሆን የሚችል ምሳሌአዊ ቁም ነገር ካቀረብኩ በዚህ ጽሁፍ ለማስተላለፍ ወደ ተነሳሁበት መሰረተ ሃሳብ ልለፍ፡

በአንድ ሃገር ውስጥ የተረጋጋ ሰላም እና እድገት እንዲመጣ በሐገሪቷ የሚኖሩ ምሁራን እውቀታቸውን እና ልምዳቸውን አስተባብረው ሙያዊ አስተዋጽኦቸውን ለሚኖሩበት ሓገርና ማህበረሰብ በማካፈል፤ በማስተማር ፤በማስተባበርና፤ አብሮ በመስራት እንዲሁም የተለያዩ አቅጣጫዎችን በማሳየትና በማመላከት የዜግነት ድርሻቸውን ሲወጡ እንደሆነ ከተለያዩ ሓገራት ልምድ በመነሳት መናገር ይቻላል።

ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያውያን ምሑራን ካለፉት 50 ዓመታት ጀምሮ በሓገራችን በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማስፈን በተደረገው ትግል በተለያዩ ጊዜያት ቀላል የማይባል መስዋእትነት ሲከፍሉ መቆየታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው። ምንም እንኳን በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል ላይ የተካፈሉት ኢትዮጵያውያን ምሑራን ከቁጥራቸው አኳያ ሲታይ ኢምንት ቢሆንም በነጻነት ትግሉ ላይ ትተው ያለፉት አሻራ ግን በቀላሉ የሚዘነጋ አይደለም።

የዚህ ጽሁፍ ዋና ዓላማ በዋናነት ኢትዮጵያዊ ምሑራንን የመተቸት ወይም የመውቀስ ሳይሆን በኔ እይታ ለዘመናት የተደረገው የለውጥ ትግል አመርቂ ውጤት አለማምጣት ዋና ዋና ምክንያቶች ሆነው ያገኘኋቸውን ነጥቦች ለማንሳትና ከተቻለ ጽሁፉን በቅንነት በመመልከት ውይይት ለመጫር እንዲረዳ ነው።

የኢትዮጵያ ምሑራን በዲሞክራሲ ትግል ውስጥ በስፋት አለመሳተፍ በለውጥ ትግሉ ላይ ያሳደረው ተጽእኖ

ሓገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ጎልማሳ እና ዕድሜ ጠገብ ምሑራን ባለቤት ናት።በተለያዩ ጥናቶች ላይ እንደተገለጸው በአሁኑ ወቅት እጅግ በርካታ የተማሩ ዜጎች እና ምሁራን ከሚሰደዱባቸው ሓገራት መካከል የመጀመርያውን ደረጃ ይዛ የምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደሆነች በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ሲገለጽ ሰንብቷል። እነዚህ ቁጥራቸው እጅግ በርካታ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ምሑራን ከትውልድ ሓገራቸው ለመሰደዳቸው ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በሐገራችን ኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ቀውስ መሆኑ አያጠያይቅም።

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ቁጥራቸው እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ምሑራን በየዘመናቱ በነበሩ አምባገነን ገዢዎች ጭቆና እና ዘረኝነት ተማረው የሚወዷትን ሐገራቸውን ጥለው በመሰደድ በተለያዩ የአውሮፓ እና የሰሜን አሜሪካ ከተሞች የተሳካላቸው በሙያቸው፡ ዕድል ፊቷን ያዞረችባቸው ደግሞ በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ተሰልፈው ኑሮአቸውን በመግፋት ላይ ይገኛሉ።እንግዲህ በተለያዩ ምክንያቶች ከሚወዷት የትውልድ ሐገራቸው ከተሰደዱት ምሑራን መካከል የአምባገነኖችን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ በመጣል በምትኩ ፍትህ የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት በሚደረገው ትግል ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ምሑራን ቁጥር እጅግ አነስተኛ መሆኑ በለውጥ ትግሉ ላይ ያሳደረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም።

ይህንን ስል ግን በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ትግል ላይ የግምባር ሥጋ በመሆን በተለያየ የትግል ዘርፍ መስዋእትነት እየከፈሉ ያሉና የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ ያሉ ኢትዮጵያውያን ምሑራን እንዳሉ በፍጹም አይዘነጋም ።ለነዚህ ወገኖቼም ታላቅ ክብር እና ፍቅርም አለኝ።

ለመሆኑ በርካታ ምሑራን ወደ ፖለቲካው ትግል መድረክ የማይመጡበት ምክንያቶች ምንድናቸው?

ምሳሌ ላንሳ ከ6 ዓመት በፊት ይመስለኛል በሳይበር ታሪክ የመጀመርያ የሆነ ፓናል ዲስከሽን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች መወያያ መድረክ (ECADF በወቅቱ እንዳሁኑ በርካታ ሚዲያዎች አልነበሩም ) ይዘጋጃል። በዛ ፓናል ዲስከሽን እንዲሳተፉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ምሑራን ፤ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፤ አክቲቪስቶች እና ጋዜጠኞች ተጋብዘው የነበረ ሲሆን የውይይቱ ርዕስም በርካታ የሆኑ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚታገሉለት ዓላማ እና ማኒፌስቶአቸው ሲታይ በአብዛኛው ተመሳሳይ መሆኑና ሁሉም በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ለመመሥረት የሚታገሉ መሆናቸውን እየገለጹ ነገር ግን የጋራ ጠላታቸውን ለመታገል በህብረት ሲሰሩ አለመታየታቸውን አስመልክቶ እነዚህ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን በጋራ ሊያሰራቸው የሚችል ሚኒመም አጀንዳ ምንድነው የሚል ነበር። በዚህ ውይይት ላይ እንዲሳተፉ ከተጠየቁት በርካታ ምሑራን መካከል ጥቂቶቹ ፈቃደኝነታቸውን በመግለጽ በውይይቱ ላይ በመሳተፍ እውቀታቸውን እና ልምዳቸውን በመጠቀም ለውይይቱ ተሳታፊዎች እና ለታዳሚዎቻቸው ይበጃል ያሉትን አስተያየታቸውን ያካፈሉ ሲሆን በርካቶቹ ግን በውይይቱ ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኞች አልነበሩም። በውይይቱ ላይ ላለመሳተፍ ያቀርቡ የነበረው ምክንያት ግን እጅግ አሳዛኝ እና አስገራሚ ነበር። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ካነሷቸው ምክንያቶች ውስጥ በውይይቱ ቢሳተፉ በገዢው መንግስት ካድሬዎች ጥቃት ሊደርስባቸው እንደሚችል ፤ ወደ ሐገር ቤት ለመሄድ በዝግጅት ላይ በመሆናቸው እንዲህ አይነት ውይይት ላይ መሳተፍ እንደማይችሉ ፤ አንዳንዶቹም ጉዳዩ ፍጹም እንደማይመለከታቸው እና እንደማያሳስባቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ከውይይቱ በኋላ ሊደርስባቸው ስለሚችል ትችት እና ዘለፋ በነሱ አገላለጽ ስድብ ምክንያት በውይይቱ ላለመሳተፍ እንደወሰኑ ነበር የገለጹት። ሌላው እጅግ የሚያሳዝነው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የገዘፈ ስም ያላቸው ምሑራን ጭምር ለውይይት ሲጋበዙ የሌሎችን ተጋባዦች ስም በመጠየቅ እሱ ብሎ ምሑር፤ እሷ ብሎ ምሁር ፤ እሱ ካለ አልመጣም፤ እሷ ካለች አልመጣም በማለት ከአንድ እድሜ ጠገብ ምሁር ፖለቲከኛ የማይጠበቅ አሳፋሪ እና አሳዛኝ መልስ በመስጠት በውይይቱ ሳይሳተፉ መቅረታቸውን አስታውሳለሁ። ይህ አይነቱ ችግር አሁንም ድረስ የቀጠለ እና አፋጣኝ መፍትሄ የሚያስፈልገው አቢይ ችግር እንደሆነ የተለያዩ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ጋዜጠኞች ሲናገሩ ይደመጣል።

ከነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች መካከል በተለይ ትችትን እና ስድብን በመፍራት ወይም በመጥላት ራስን ገለልተኛ በማድረግ ከምንም ነገር ነጻ አድርጎ ለመቀመጥ መሞከር ከአንድ ፊደል ከቆጠረ እና ከፍተኛ እውቀትን ከገበየ ዜጋ የሚጠበቅ አይደለም። ይህ የተያያዝነው የነጻነት ትግል እንዲህ በቀላሉ የማይታይና እጅግ ከባድ የሆነ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑም መዘንጋት የለበትም። ነጻነትም በነጻ እንዲሁ ሳይደክሙ እና ሳይለፉ የማይገኝ ክቡር እና ውድ ከፈጣሪ የተሰጠን ጸጋ መሆኑን ለአፍታ እንኳን ልንዘነጋው አይገባም። በአንድ ወቅት አንድ ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛ ስለተሳዳቢዎች ተጠይቆ የመለሰውን መልስ ልዋስ * ተሳዳቢ ለመሆን ትምህርት ቤት መሄድ አያስፈልግም ተሳዳቢ ለመሆን የሚያስፈልገው ክራይቴሪያ ባለጌ መሆን ብቻ ነው ነበር ያለው * እናም የባለጌዎችን ስድብ እና ትችት ፈርተን እጅግ ክቡር የሆነውን ነጻነታችንን ለመቀዳጀት ከሚደረግ ትግል መራቅ ከሕሊና ተጠያቂነት አያድንም። በዚህ የነጻነት የሞት ሽረት ትግል ውስጥ ምትክ የማይገኝላትን ሕይወታቸውን ለነጻነታቸው እና ለሐገራቸው ሉአላዊነት ለመሰዋት በበረሃ የተሰለፉ ጀግኖች ወንድሞች እና እህቶች አሉና !! ከጊዜያዊ ከበሬታ ይልቅ ዘላቂ እና ቋሚ የሆነው ነጻነታችን ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚ ነውና !!

ሌላው በተለያየ የሙያ ዘርፍ ከፍተኛ እውቀት እና ልምድ ያላቸው ምሑራን በተለያዩ ምክንያቶች በዴሞክራሲያዊ ትግሉ ላይ ባለመሳተፋቸውና ቸልተኝነት በማሳየታቸው የተለያዩ የማህበረሰብ መገናኛ ዘዴዎችን እና የፖለቲካ መድረኩን ሐገራዊ ራዕይ የሌላቸው፤ በስሜት የሚመሩና ካለነሱ ሰው ያለ የማይመስላቸው፤ ለግል ጥቅማቸው የሚዳክሩ የዕውቀት እና የእውነት ድሖች የሆኑ ብልጣብልጦችን በየመድረኩ ላይ እንዲፈነጩበት አድርጓቸዋል። እነዚህ የአስተሳሰብ እና የዕምነት ድሆች ደግሞ በነጻነት ትግሉ ላይ ደንቃራ በመሆን ትግሉን ወደኋላ ለመጎተት ሲፍጨረጨሩ ይስተዋላሉ። እነዚህ ከራሳቸው ጥቅም ውጭ ሌላ ነገር የማይታያቸው ስግብግብ ግለሰቦች ተልኮአቸው ከአንዱ የፖለቲካ ድርጅት ወደ ሌላው በመዝለል ድርጅቶችን ማዳከም ሲሆን በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን የሚሰባሰቡባቸውን ኮሚኒቲዎች እና የእምነት ተቋሞችን ሳይቀር በማዳከም እና በማፈራረስ ኢትዮጵያዊው ተስፋ ቆርጦ ቤቱን ዘግቶ እንዲቀመጥ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም።

በአንዳንድ አካባቢዎች በሐገሩ መኖር ተስኖት ሕይወቱን ለማስተካከል የሚሰደደውን ኢትዮጵያዊ ሥደተኛ የድጋፍ ወረቀት እንጽፋለን በሚል ለፍቶ የሚያገኛትን ሳንቲም መዝረፍን፤ በእምነት ተቋማት ውስጥ ሰርጎ በመግባት ከምእመናን የሚሰበሰበውን ሙዳየ ምጽዋት መስበርን ኑሮአቸው አድርገው ተያይዘውታል። በመሆኑም እንደነዚህ አይነቶቹን ደካሞች በቃችሁ ካላልናቸውና ብቃቱና ችሎታው ያላቸውን ዜጎች መተካት ካልቻልን በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የተሰገሰጉት ሆድ አደሮችና የግልጥቅም ያሳወራቸው ደካሞች ኮሚኒቲዎቻችንን ማዳከምና ማፈራረስ በእምነት ተቋሞቻችንም ውስጥ ገብተው ሙዳየ ምጽዋት መስበራቸውን አያቆሙም።

ሌላው ሳልጠቅሰው የማላልፈው በአንዳንድ ምሑራን ዘንድ የሚንጸባረቀውን የርሥ በርስ መጠላለፍ እና አለመከባበር እንዲሁም የራስን ድክመት ለመሸፈን የሌሎችን ግድፈት ነቅሶ የማውጣት አባዜ ነው። የተያያዝነው የነጻነት ትግል እጅግ አድካሚና ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚጠይቅ መሆኑ እየታወቀ ሁሉም ጠጠሩን በጋራ ጠላቱ ላይ ከመወርወር ይልቅ ትኩረትን ወደ ጎን አዙሮ እርሥ በርስ መናቆር እና እኔን ብቻ ስሙኝ ፖለቲካ የትም ሊያደርሰን እንዳልቻለ ካለፈው ተሞክሮአችን መረዳት ይቻላል። ሁሉም አካባቢውን ቢያጸዳ ከተማችን የጸዳች ትሆናለች የሚል መፈክር ትዝ ይለኛል። አዎ ሁላችንም ትኩረታችንን ወደ ዋናው ጠላታችን በማዞር የድርሻችንን ብንወጣ የምንመኘውን ነጻነት እና ዴሞክራሲያዊ ሥርአት እውን ማድረግ እንችላለን።

አንድ ምሳሌ ላንሳ ከ 5 ዓመት በፊት የተከናወነ ጉዳይ ነው። በወቅቱ በጣም ያስገረመኝ እና ያሳዘነኝ ጉዳይ በመሆኑ ከላይ ለመጥቀስ የሞከርኩትን የመጠላለፍ እና እኔ እበልጥ አተካራ ሊያስረዳልኝ ይችላል በማለት አነሳዋለሁ።

Mr. X በሙያቸው ኢኮኖሚስት የሆኑ ታዋቂ ፖለቲከኛ እና ምሑር ሲሆኑ በነጻነት ትግሉውስጥ ከፊት በመሆን የዜግነት ድርሻቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙ ናቸው። Mr. Y እንዲሁ በሙያቸው ኢኮኖሚስት የሆኑና በተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ አርቲክሎችን በመጻፍ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ናቸው።

ታድያ ከዕለታት በአንዱ ቀን በአንድ የአውሮፓ ከተማ ሥለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ጉዳይ ለመወያየት እና ሐገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ለማስረዳት ሥብሰባ ይዘጋጃል። በዚህ ውይይት ላይ ተገኝተው ንግግር እንዲያደርጉ ከላይ የጠቀስኳቸው ሁለት ምሑራን ይጋበዛሉ። የሥብሰባው አዘጋጆች ውይይቱን Mr. X የኢትዮጵያን ፖለቲካ አስመልክቶ ንግግር እንዲያደርጉ ሲነገራቸው በደሥታ ተቀብለው ለውይይቱ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ። Mr. Y ደግሞ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አስመልክቶ ንግግር እንዲያደርጉ ይነገራቸውና ተስማምተው የስብሰባው ቀን ይጠበቃል። እንዳይደርስ የለም የስብሰባው ቀን በጉጉት እየተጠበቀ ባለበት ወቅት ውይይቱ ሊካሄድ አንድ ቀን ሲቀረው Mr. Y ለስብሰባው አዘጋጆች በውይይቱ ላይ እንደማይገኙ በኢሜል ያሳውቃሉ። የውይይቱ አዘጋጆችም በሁኔታው ተደናግጠው ሥለ ሁኔታው ማብራርያ ይጠይቃሉ Mr. Y ግን ሌላ ቀጠሮ ሥላላቸው መምጣት እንደማይችሉ ይገልጻሉ። የውይይቱ አዘጋጆችም በዛ ሁኔታ ሌላ ሰው ለመጋበዝ በቂ ጊዜ ባለመኖሩ ለ Mr. X የተፈጠረውን ችግር አስረድተው እሳቸው ሁለቱንም አርዕስት እንዲሸፍኑ ይደረግና ውይይቱ በዕለቱ ይከናወናል።

ታድያ እጅግ የሚገርመው እና የሚደንቀው Mr. Y በውይይቱ እንደማይካፈሉ በገለጹበት ወቅት ማለትም ከውይይቱ አንድ ቀን በፊት ለውይይቱ አዘጋጆች ኢሜል በላኩበት ቅጽበት ማለት ነው 15 ገጽ ያለው ጽሁፍ በኢንተርኔት ይበትናሉ። ጽሁፉም የሚያጠነጥነው በውይይቱ ላይ አብረዋቸው እንዲሳተፉ የተጋበዙት Mr. X በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አስመልክተው የጻፉትን ጽሁፍ የሚያጣጥልና ግድፈት ያለበት መሆኑን የሚገልጽ ነበር። Mr. Y ጽሁፉን ማውጣታቸው መብታቸው ቢሆን እንኳን ጽሁፉን ለማውጣት የመረጡት ቀን ሆን ተብሎ የ Mr. Xን ሙያዊ ብቃት ለማሳነስና በውይይቱ ላይ እንቅፋት ለመፍጠር ሆን ብለው ያደረጉት መሆኑን መገመት ይቻላል። በተጨማሪም Mr. Y በውይይቱ ላይ ተካፍለው ለውይይቱ ተሳታፊዎች እና ውይይቱን በተለያየ መንገድ ለሚያደምጡ ዜጎች ከእውቀታቸው ቢያካፍሉ የተሻለ ይሆን ነበር። እዚህ ላይ Mr. Y ሃሳባቸውን ለምን በጽሁፍ አቀረቡ የሚል አመለካከት የለኝም ነገር ግን የሌሎችን ድክመት በማሳየት አዋቂ ለመምሰል ከመጣር የራሥን ጥንካሬ በተግባር በማሳየት ሌሎችን ለማስተማር መሞከር ብልህነትና አዋቂነት መሆኑን ለማሳየት ነው።

በአጠቃላይ ይሉኝታ ፤ ፍርሐት ፤ቸልተኝነት ፤ራሥ ወዳድነት ፤ጊዜያዊ ከበሬታን ፍለጋ ፤መጠላለፍ ፤እኒ እበልጥ እኒ እበልጥ፤ እኒ ከሌለሁ አፈርሰዋለሁ የሚሉት በሽታ ፤በሕዝብ ትግል ራስን ለማሳደግ መጣር ፤ሥግብግብነት ወዘተርፈ የሚባሉ ጥርቅምቃሚ አመሎች የነጻነት ትግሉን ክፉኛ እየጎዱ መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል።

በነገራችን ላይ በዚህ ጽሁፍ ላይ ከሌላው የማሕበረሰብ አባላት የተሻለ ግንዛቤና እውቀት ስላላቸው አስተያየቴን በምሑራን ላይ አተኮርኩ እንጂ ይህ ችግር በሁሉም ኢትዮጵያዊ በአብዛኛው የሚንጸባረቅ መድሀኒት የሚያሻው የፖለቲካ ኢቦላ ነው:: በተጨማሪም ምሑራኖች በተለያዩ ዘርፎች የሚያነሷቸው የግል ሃሳቦችና ውሳኔዎቻቸው ፈጣን የሕዝብ ድጋፍና መነሳሳትን በመፍጠር በሐገሪቱ አጠቃላይ ፖለቲካ ላይ ጉልሕ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችል በመሆኑ የኢትዮጵያ ምሑራንም ሐገራችን ከገባችበት አዘቅት የምትወጣበትን መላ በመዘየድ የመሪ እና የአቅጣጫ አመላካችነት ሚናቸውን በግምባር ቀደምትነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል የሚል የጸና እምነት ስላለኝ ነው።

ዛሬ በስደት የምንኖርባቸው የአውሮፓ እና የሰሜን አሜሪካ ሐገራት ከመሬት ተነስተው አሁን ያሉበት ደረጃ ላይ እንዳልደረሱ ግልጽ ነው። እንደሚታወቀው የቀደመው ትውልድ ምሑራን ሕዝብን በማስተባበር ከፍተኛ መስዋእትነት እና ከባድ ዋጋ ከፍለው ለዛሬው ትውልድ መሰረት እንደጣሉ ሁላችንም የምናውቀው ሀቅ ነው። እንግዲህ እኛም ሐገራችን እንደ ሐገር እንድትቀጥል እና ሌሎች የደረሱበት ደረጃ እንድትደርስ የምንፈልግ ከሆነ ሁላችንም ዛሬ ነገ ሳንል አሁኑኑ የድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል። አለበለዚያ ያቺ የምንመኛት ዘመናዊት ዴሞክራሲያዊት ኤትዮጵያ እንደ መና ከሰማይ አትወርድም። እኛው አምጠን ካልወለድናት።
በመጨረሻም ምንም እንኳን መማር የተፈጥሮን ባህርይ ሙሉ በሙሉ መለወጥ ባይችልም የሰውን ልጅ ባህርይ ለመግራት ያለው አቅም ግን ከፍተኛ መሆኑ አያጠያይቅም። መማር አይነ ልቦናን ይከፍታል፤ ክፉና ደጉን ለመለየት ያግዛል፤ ተፈጥሮን ለመመርመር ይረዳል ። አይነ ልቦና ሲከፈት ደግሞ የችግሮቹ ሁሉ መንስኤዎች ፍንትው ብለው ይታያሉ ። ያኔ መፍትሔውም በእጃችን እንዳለ መረዳት ከባድ አይሆንም።

እንግዲህ ከላይ በጽሁፉ መግቢያ ላይ እንደተቀመጠው ሁላችንም ለሀገራችንና ለወገናችን ሊጠቅም የሚችል በጎ ነገር መስራታችንን ራሳችንን እንጠይቅ። አንድ ሰው በዚህ ምድር ላይ ይሄን ያህል ጊዜ ኖሮ አለፈ የሚባለው በህይወት ዘመኑ ለሐገር እና ለወገን የሚበጅ እና የሚጠቅም መልካም ነገር አበርክቶ የድርሻውን ተወጥቶ ሲያልፍ ብቻ ነው። መልካም የሰራ ሥራው ለዘላለም ሕያው ሆኖ ይኖራልና !! ሥም ከመቃብር በላይ ይኖራል ይባል የለ !!

ጃናሞራ
janamoraeth@gmail.com

“ገብጋባ ውሻ ነክሶ ለጅብ ይሰጣል” (ክፍል ሁለት) ለሀራጥቃ ተሐድሶአዊያን (ከመኳንንት ታዬ)

tehadiso

አንዳንዶች ከተሰበሰበው ሃሳባቸው ሲወጡ እራሳቸውን ከሰፈሩ ያጡታል።ባለባበሳቸው ባካሄዳቸው  በጠቅላላ ኑሩአቸው  የሚኖሩበት ማህረሰብን ያለ መመሳሰልን ነገር  ሲገለፅላቸው  ግራ ይጋባሉ።በዚህን ግዜ ሁሉም ነገር ለእነሱ አዲስ ነው ።ግራ በመጋባት ሄደት ውስጥ ትላንት እንዳልነቡሩና ለምን መንደሩን እንዳልመሰሉ የሚገባቸው ቆይቶ ነው። ወይ መንደሬው  በኑሮው በአብሮነቱ ጥሎአቸው  ከሄደ በኋላ ብሎም እነሱም  ከሰፈሩ መዝገብና ከሰው ልብ ውስጥ  ስማቸው ከጠፋ በኋላ ነው መኖራቸው የሚታሰባቸው። በዚህን ግዜ ቓንቓቸው እንደ ሃገሬው እንደ ሰፈሩ ህዝብ አልሆን ይላቸውና ስህተታቸው ከሰው ሁሉ ትክክል እየመሰላቸው ወጪ ወረጁን ግራ ማጋባት ይጀምራሉ።ለዚህ ያነሳሳኝ መሰረታዊ ሃሳብ  በክፍል አንድ እንዳየነው አሁንም አቅም በፈቀደ  ክፍል ሁለትን እንዲሁ እንድናይ ፈልጌ ነው ።

ለመግቢያ  ያህል ይህን ነጥብ ካነሳን ወደሚቀጥለው  መንደር የፊደል እግር እያየን አብረን እናዝግም።ተሐድሶ ባንድም በሌላም መልኩ ሊሆን ይችላል።በዚህ ረገድ በሐይማኖት ስለመታደስ ተነስቶ ነገር ግን ወትሮም ቢሆን በሐይማኖት ውስጥ  እንዳልነበሩ  የሚያሳየንን ስራዎቻቸውን ሰሞኑን  በተለያዩ ቪድዮች ስናይ  ከርመናል ።እነሱንም በነጥባቸው እንይ።

1.በተለያዩ  ግዜያት  የተለያዩ ሙከራቸውን አድርገው እንዳልተሳካለቸው እና በጌታ ነበሩ  በጌታ  አልነበሩም የሚል ቋንቓ ስለመጠቀማቸው።

2.ለረጅም ግዜ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ቆይተው በጣም ብዙ ነብሳትን (6 ሚሊዮን) ከቤተክርስቲያን አስወጥተው  ለፕሮቴስታንቶቹ እንደገበሩ

3.አሁን እነሱ ያነሱት ተሐድሶ የሚለው  ነጥብ ከዚህ በፊት ደቂቀ እስጢፈኖሳዊያን በሚል መጠሪያ በተነሱ ወንድሞች ተነስቶ እንደነበር እና እነሱም እስከዛሬ ድረስ ለማሪያም  እንደማይሰግዱ እና የመሳሰሉትን ነው ።

እንግዲህ ከላይ ላነሱት ነጥብ በእኔ ብቻ ብዙ የሚገለፅ ባይሆንም፤ ግን አኔ እንደ ቤ/ክርስቲያን ልጅነቴ አጠገባቸው ብሆን ለእነሱ የምመልሰውን  ከአንባቢያን ጋር ለመጋራት ያህል  ይህን ልበል።

ሀራጥቃ ተሐድሶአዊአን (ተዋስያን) በተራ ቁጥር. አንድ  ስላነሳችሁት ጥያቄአችሁ እንደመለስ የምወሰወደው አንድ የመስሃፍ ቅዱስ ቃል ነው ።ይኸውም ።የሐዋርያት ስራ  ም5ቁ34-39 ባለው ላይ ሐዋርያትን  ለማጥፋት አይሁድ በሚመክሩበት ግዜ ገማልያል የሚባል የህግ ሰው  ሲያስረዳ  በተለያየ ግዜያት የተለያዩ ሰዎች ተነስተው ከእግዚአብሔር ስላልነበሩ እንደጠፉ እና እነዚህም(ሐዋርያቱን ማለቱ ነው)  ከእግዚያብሔር ካልሆኑ ይጠፋሉ እንዳለ ያስረዳል። ይህን ስታነቡ በቀላሉ መልሱን የምታገኙት ይመስለኛል ። ወደፊትም ትነሳላችሁ። ከእግዚያብሔር ስላልሆናችሁ አይሳካላችሁም ። ትጠፋላችሁ።ቤተክርስቲያናችን  ግን ለዘላለም ትኖራለች።ጥንትም በቤተክርስቲያኗ ወሰውጥ ስማችሁ ከሰፈሩ አልነበረምና አሁንም ወደፊትም  አትኖሩም።ማስተዋል የላችሁም ።በቤ/ክን ውስጥ በነበራችሁበት ግዜ በፆሙ የላችሁም።በፀሎቱ የላችሁም። በጠቅላላው በእምነት ውስጥ አልነበራችሁም ።ለዚህ ከእግዚያብሔር ያልሆነ ስራ ስትሰሩ አማንያንን  እያሳታችሁ ነው እንጂ ኢ አማንያንን  ወደ እምነት እያመጣችሁ አደለም።ኢትዮጲያ በ4ተኛው ክፍለ ዘመን  ክርስትናን ስትቀበል  በቅጥታ ከሐዋርያት  በተማረችው ትምህርት ትውልዱን ስታስተምር ይኸው እስከ ዛሬ አለች።ታዲያ  ዛሬ እናንተ ከነማን በተማራችሁት ትምህርት ዛሬ ቤተክርስቲያኗን ማደስ ፈለጋችሁ?። ስለዚህ ነው ከእግዚያብሔር አደላችሁም። ስላልሆናችሁም  በየግዚያቱ አፈር ልሳችሁ ብትነሱም  አይሳካላችሁም።ትጠፋላችሁ የምንላችሁ።

2.በሁለተኛ  ላይ ያነሳሁት ነጥብ  የርዕሴም ምክንያት ነው።ምንዛሬውም ብዙ ነው። ግን እንዲህ በቀላሉ እንየው ካልተባለ በስተቀር።ነገሩ እንዲህ ነው ።የስነ ምግባር እኩለነታቸው እራሳቸውን ከተግባር ጋር እንዲያጣምሩ ተፈጥሮ ክህሎቱን ያላደለቻቸው ለሚኖሩበትና ህይወትን ለሚጋሩት ማህበረሰብ የተባይ ያህል ያሳክካሉ።ላሉበት አካባቢ ቀውስ የማይሆኑበትና ሁነቶች በተፈጥሮም ሆነ በስርአት ለሰው ልጆች ምቹ ሆነው እንዳይቀጥሉ በመንገድ ላይ እንዳዋራ  በመበተን ማንም አጣርቶ እንዳያይ  ምክንያት በመሆን የብዙዎችን መንገድ ማሰናከላቸው አውነት ነው። ለዚህም ነው ዛሬም ድረስ ቤ/ክ መረበሿ፤ለዚህም ነው ዛሬም ድረስ የተከተሉት መንገድ ስህተት ያለበት እየመሰላቸው ዘለው ከመናፍቃኑ ጎራ የሚገቡ ቄስ፤ሞለኩሴ፤ዲያቆን መእምን  የመኖራቸው ሚስጥር።እናንተም የምትሉን ይኼና ይኼን መሰል ጉዳየዮች እንዲፈፀሙ ለተግባሩ መሳከት የበኩላችንን አድርገናል ነው።ለምን ብለን አንጠይቃችሁም።አላማችሁ ስለሆነ።በመሆኑም ነው፤ መዕመናን  ከሚኑሩበት ቅድስት ቤተክርስቲአን  አስወጥታቸሁ ለማያቁትና  ወደማያቁት አለም የአውሬው መንፈስ ተካፋይ እንዲሆኑ ስታደርጉ አልፈራችሁም።እስቲ አስቡ እነኚ ወገኖች  ክርስቲያኖች ናቸው ።በእመነታቸው እጅግ ብዙ      ኢ- አማንያን አሉ።እውነት አላማችሁ”ባልበላውም ጭሬ ደፋዋለሁ እንዳለችው ዶሮ” ካልሆነ በስተቀር ስለምን ኦርቶዶክሳዊያን ላይ  መዝመት አስፈለገ።የምዕራብአዊያን ተላለኪዎች ባትሆኑ ኖሮ  ታተኩሩ የነበረው የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ክ ላይ ባልነበር።  ሰዎችን ክርስትናን እንዲያቁ ለማድረግ ቢሆን ትጋታችሁ የምትዘምቱበትና ጦራችሁን የምትሰብቁበት ቦታ  ቤ/ክ ባልሆነች ።ግና የኔ የምትሉት አላማ የላችሁም።ሲጀመርም ተገዝታችሁ ነው።በአዳራሻችሁም የምትሉት አሁንም አሁንም አሜን! እየሱስ ጌታ ነው የመሳሰሉትን ነው። ምክንያቱም  ስማችሁም ክርስቲያን ቢሆን  በቤተክርስቲያን ግን አልነበራችሁም፡፤ስማችሁ ከመንደሩ ሰዎች ጋር የለም ያልኩት ለዛ ነው።ለዚህ  ገና ጌታን(በእናንተ አጠራር) አዲስ እንዳገኛችሁት ስትወበሩ ለሰማ ያሳፍራል።መነሻና መድረሻችሁ ግራ  ያጋባል።ምክንያቱ ማንን መጥቀም ማንን መጉዳት እንኳን  እንደሆነ አይታውቅም።ነገር ግን የኢ/ኦ/ተ/ቤ ለአም እንኳን አስኪደንቅ ድረስ  ፆም፤ፀሎት፤ስግደት፤መመፅወት፤ቅዱሳንን ማክበር ፤በስማቸው ቀዝቀዛ ውሃ ማጠጣት፤ምግባር ፤አንድነት አብሮ መብላት፤ ብቻ ቆጥሬ ነግሬ የማልጨርሰውን አባይት ሁነቶችን በውስጧ ይዛ ትውልድን እየቀረፀች ኢትዮጲያን ዘመን ያሻገረች ንፅህት ሐይማኖት ነች።እንዳለመታደል ሆኖ እንጂ እናተም  ነበራችሁበት ።ነገር ግን ክፍል ስትቀይሩ ማስተዋልም ቀየራችሁና የክህደት ጅራፋችሁን አጮሃችሁባት።አዲሷም አደለም።የመጀመሪያም አደላችሁም።

3.ስለ ደቂደ እስጢፈኖስ ያነሳችሁት ነው።ዋቢ ይሆነናል  የምትሉትን ሁሉ መሞከሩ መልካም ነው።ጥያቄው ያነሳችሁት መፅሃፍ መፅሃፍ ቅዱስ ውጭ አልሆነባችሁም ወይ ነው? ምክንያቱም ወደ ቅድስት ቤ/ክ ስትመጡ ለማሳሳት  የምትጠቀሙበት ቃል አንዱ ቤ/ክ ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጭ ትጠቀማለች ነው።ይገርማል።ማስተዋላችን ውበታችን ነው።ማስተዋልን የማይጋፋ ማንነት እራስንም ሆነ ማሕበረሰብን የሚጠቅም የሞራል ድጋፍ ከውስጡ ይመነጫል።ለወገንም ለሐገርም የማይቆረስ መስዋትነት  ለመክፋል ያለነጋሪ የሚጠበቅበትን  ለመክፈል ዝግጁ ነው።ክህደት የሚያበዛ እኔነት ሐሳቡ እራሱ ብቻ ነው።ሐገር፤ወገን፤ቤተሰብ ፤መጪው ትውልድ ማለት ከቶም አይታሰብም።ለዚህ እናንተ በፈለጋችሁት መንገድ መሮጥ መሮጥ  መድረሻ የለ መነሻ የለ።ይሁን እናንተ(ሓራጥቃ ተሐድሶአዊያኑ) ያነሳችሁት መፅሐፍ እናንሳና በተሳሳተ ግምት የተሳሳተ ቦታ ቆርጣችሁ በመቀጠል ያሳመነችኋቸው ወገኖች ድንገት ከእንቅልፋቸው ቢነቁ።

ነገሩ እንዲህ  ነው ።ሰባኪው(ሓራጥቃ ተሐድሶዊያኑ)ማለቴ ነው።በፕሮፈሰር ጌታቸው ሐይሌ ስለተፃፈው  በህግ አምላክ ደቂቀ እስጢፋኖሳዊያን  አንስቶ በዘመኑ የነበሩ እንኚህ ወገኖች  ከላይ እንዳልኩት ለማሪያም እንደማይሰግዱና አምልኮታቸው አሁን እነሱ ነን እንደሚሉት አይነት እንደነበር በዚህም  በጣም እጅግ  የሚያሳቅቅ  በደል እንደደረሰባቸው   ደጋግሞ ለመጥቀስ ሞክሮአል ።አስቲ ከመፅሐፍና ስለመፅሐፉ ጥቂት  ወስደን ጥቂት እንበል።

አውነት ነው። የመፅሐፉ ስምና የመፀሐፉ ደራሲ።ሌላው ጉዳይ ግን አብረን  ጥቂቱን እንመልከት። ደቂቀ እስጢፋኖኦሳዊያን  ተነስተው የነበሩት ሉተር ከመነሳቱ ሰላሳ አመት  በፊት በአፄ ይስሐቅ ዘመነ መንግስት 1406-1421  ሲሆን የመጀመሪያ በሐይማኖታቸው በጣም ጥብቅ የነበሩና ሁሉን  በቦታው የሚሰጡ እንደነበር ያወሳል።እርግጥ ነው መነሻቸው ላይ ለመቤታችን  እና ለመስቀሉ መስገድ አይገባም የሚል ከፉ ትምህርት ነበረባቸው ።ይሁንና  በፀሎት መፅሐፋቸው ሳይቀር የእመቤታችን ስዕል ይዘው ይዞሩ እንደነበር መፅሐፉ ያስረዳል ።ኋላ ላይ ግን በወቅቱ የነበረው ንጉስ ለእኔ አትስግዱም  እያለ ምክንያት እየፈለገ ሲያሳቃያቸው እነሱም ለአብ፤ ለወልድ፤ ለመንፈስ ቅዱስ፤ ብቻ ስግደት  እንደሚገባ  ይነግሩት ነበር።ይህን ምክንያት  አድርጎ በወቅቱ ያለው ጳጳስ  እንዲገዝታቸው ሲከሳቸው እንደምክንያት  ሲናገር “እኔንም አያከብሩኝም  ለእመቤታችንም አይስግዱም  “የሚል ነበር።ጳጳሱም  ይህ የሚባለው አውነት  ነው ወይ? ብለው ጠየቐቸው፤ እነሱም ለሱ አንሰግድም ያልነው አውነት ነው። ስለ እመቤታችን ያለው ግን ስህትተ አለበት ብለው መለሱ።እንዲያ ካላችሁ ተነሱና  አስቲ አብረን ለእመቤታችን  እንስገድ ብሎ አብረው ሰግደዋል።በዚህም የትግራዩ ንጉስ ያለውን ግዝት ባለማድረጋቸው አሳቸውም አብረው ተግዘዋል።አስቲ ለአብነት  ያህል ከመፅሐፍ  ጥቂት ጥቂቱን ወስደን እንይ።

“አለ መስገድ  እንደ አለማክበር አያዩትም።እመቤታችንን ማክበራቸው አያጠራጥርም።”ምስለ ፍቅሩ ወልዳ”የሚባለውን ቅድስት ማርያም ልጇን(የጌታችንን)ታቅፋ የሚያሳየውን ስዕል በየመፅሐፎቻቸው ውስጥ ስለው ተገኝተዋል። በራሳቸው በአባ እስጢፋኖስ ገድል ወስጥም አለ።(ገፅ 22ተመልከት)በዚያ ላይ እንደ ሌሎች ሁሉ የቅዱስ ኤፍሬምን ውዳሴ ማሪያም  እና የቅዱስ ያሬድን አንቀፀ ብርሃን ይደግሙ ነበር።እነዚህ  ሁለት ድርሰቶች እመቤታችንን የሚያደንቁና የሚያመሰግኑ በየአንቀፁ፡ሰአሊነ ቅድስት”(ቅድስት ሆይ ኀጢያታችንን ይቅር እንዲለን ከልጅሽ ከወዳጅሽ ዘንድ አማልጅን) የሚል ንባብ ያለባቸው ናቸው።ጳጳሱም ለቅድስት ድንግል ማርያም ብትሰግዱ ስሕትተ አይሆንባችሁም ብለዋቸው  አብረው መስገዳቸውን ራሳቸው መስከረዋል”ደቂቀ አስጢፋኖስ ገፅ30 አንቀፅ 4 ይመልከቱ።

ማስረጃ ሁለት።ደቂቀ አስጢፋኖስ ገፀ140 ላይ በፀሎታቸው  ግዜ የፀለዩት ፀሎት”የ አምላክ እናት ሆይ እነሆ ከምህረትሽ ጥላ ስር ተደግፈናል።በጭንቃችን ግዜ ልመናችንን አትናቂ”። አንቀፀ ሁለት  መስመር 10 ይመልከቱ።

ማስረጃ ሶስት፤-  ከደቂቀ አስጢፋኖስ ገፅ152 ንጉስ በተናገራቸው ቃል ተቆጥተው ከነሱ ውስጥ አንዱ እንዲህ አለ።”የትምክህታችን አክሊል የሆነች የማርያም ፍቅርና የዚህን የነፍስ አባት የምዕዳን ቃሉን አስታውሼ ነው እንጂ እንኳን በትርን፤ መራቆትን፤ ረኀብን፤ውሃ ጥምን በመፍራት ላደርገው ቀርቶ ጦር አንጀቴን ቢዘረግፈውእንኳን አላደርገውም። እንግዲህ ለአብነት ያህል ይህን  ጠቀስን እንጂ ብዙ ማለት ይቻላል።

ምን አልባት መፅሐፉን አለቆቻችሁ ሳይፈቅዱላችሁ ያነሳችሁት እንደሆን ወይ አብሮአችሁ ያሉት ቢሰሙም አይሰሙም  ወይ ሰባኪ ተብየውም  እንዲሁ ይጮሐል እንጂ አይሰማም። አያውቀወም። እንጂ ጠቅላላ ይዘቱን ብታገናዘብ ኖሮ እናንተን(ሃራጥቃ ተሓድሳዊያኑን(ተዋስያኑን) አይመለከትም። በጥቅሉ የመጀመሪያ አጥማቂዎቻችሁን እና ሰባኪዎቹን  እና ተሰባኪዎቹን ሳስብ ይህቺ ከዚህ በታች  ታሪክ እንዳስብ አድርጎኛል ።ለሁሉም ለንስሐ ግዜ  ይስጣችሁና ለመመለስ ያብቃችሁ።

በ አንድ ሃገር ሶስት መስማት  የተሳናችው ሰዎች ይኖሩ ነበር።እነኚ ሰዎች ኑሮአቸው አንደኛው የንጉስ ከብቶች ጠባቂ ፤አንደኛዋ  ደግሞ የባለጠጋ ቤት ሰራተኛ  ሆና በተለያየ ጉዳይ የምታገለግል  ስትሆን ሶስተኛው ዳኛ ነበር።ታዲያ ከእለታት በአንዱ ቀን  ከብት ጠባቂው  በድንገት እንቅልፍ ይወሰወደውና ከብቶቹ ይጠፉበታል። በዚህን ግዜ ደንግጦ ተነስቶ ፍለጋ ላይ  እያለ ይህቺኛዋን ሴትየዋ ልጇን ከጎኗ አስቀምጣ የጌታዋን  መሬት እየቆፈረች እያለች  ይህ ጆሮው የማይሰማ ሰውዬ ሴትየዋን እባክሽ የጌታዬ ከብቶች ጠፉብኝ  እና አይተሻቸው እንደሆነ ንገሪኝ ፤ እዛ ውስጥ አንድ እግሩ ሰባራ የሆነ ወይፈን አለኝ። እሱን አሰጥሻለሁ ይላታል። አሷም መስማት የተሳናት ነበረችና  ምን እንዳለ ስላላወቀች እጇን ታወናጭፋለች ። በዚህን ግዜ ወደዛ ሄደዋል ያለችው ይመስለውና  መንገዱን ተከትሎ ሲሄድ ከብቶቹን ያገኛቸዋል።ወደያው ደስ እያለው ወይፈኑን  እየጎተተ ይመጣና በይ እንቺ  ብሎ ቃል በገባው መሰረት  ሊሰጣት ቢል፤ እሷ ደግሞ  አንቺ ነሽ የሰበርሽው ያላት መስሎአት እኔ አደለሁም የሰበርኩት እአለች ። ሁለቱም ሲጯጯሁ መንገደኛ ይደርስና የሁለቱንም ነገር ሰምቶ ሁኔታውን  መዳኘት ስለማይችል  ይዞአቸው  ወደ ሃገሩ ዳኛ ያቀርባቸዋል። እዛ ሲደርሱ ዳኛም መስማት የተሳነው ነው ግን ዳኛ ነው ። ከዛም ነገራችሁን አስረዱ ይልና ለሰውየው እድሉን ይሰጣል።  ሰውየውም  ቃል የገባውን ወይፈን ሊሰጣት ቢል እንቢ እንዳለች ያስረዳና ቁጭ ይላል። ሴትየዋ  በማስረዳት ላይ  እያለች ልጇ ያለቅሳል ። በዚህን ግዜ ከጀርባዋ እያወረደችው  ነገሯን  በማስረዳት ላይ እያለች  ዳኛው በመሃል  ላይ ያስቆማትና  በይ በቃ ዝም በይ፤ ብሎ ወደ ሰውየው ዞሮ” ይህ ልጅ ደሙም ደም ግባቱም አንተን ስለ ሚመስል ከዛሬ ጀምሮ  ሶስት እንቅብ ስንዴ በየወሩ ስፈርላት ብሎ ፈረደ ይባላል።  እናንተም………..ቢሆን ኖሮ።

ይቆየን

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47714#sthash.ayShV14v.dpuf

እውን ፕ/ት ሳዳም ሁሴን እና መሀመድ ጋዳፊ በሰልጣን ላይ ቢኖሩ ለአለማችን ሰላም ይበጁ ነበር?

ከታምሩ ገዳ

በመጪው 2016 አኤ አ የአሜሪካን ፖለቲካ ውስጥ ትለቁን የሰልጣን አርከን የሆነት ፕሬዜዳንትነትን ለመያዝ በሩጫ ላይ ያሉት ቢሊነሩ ቱጃር ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ጥቅምት 25 2015 አኤ አ በአየር ላይ በበቃው “ስቴት ኦፍ ዘ ዩኒኦን” በተባለው የ ሴኤን ኤን ቴለቭዥን ፕሮግራም ላይ “ ዛሬ እየጋየ ከምናየው የመካከለኘው ምስራቅ ችግሮች አኳያ የቀደሞዋቹ አምባገነኖቹ የኢራቁ ፕ/ት ሳዳም ሁሴን እና የሊቢያው ሙሃመድ ጋዳፊ በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ አለማቸን 100% የተሻለ ሰላም ይኖራታል ብዮ አምናለሁ።”ሲሉ አምነታቸውን ገልጸዋል።
Saddam Hussein
በአሜሪካ መራሹ ጦር አኤአ በ 2003 ከሰልጣን ተወግደው በ2006 በሰቅላት የተገደሉት የ ኢራቁ ሳዳም ሁሴን እና ለ አራት አሰር አመታት ሊቢያን የገዙት ሙሃመድ ጋዳፊ (በጥቅምት 2011 ኤአ አ ተገደለዋል) አምባገነኖች እና በእጃቸው ብዙ ነፈሳት አንደጠፉ የሚያምኑት ሪፐብሊካኑ እጩ ፕሬዘዳናታዊ ተፎካካሪ ትራምፕ “ ሰዎች ዛሬ በሊቢም ሆነ በ ኢራቅ አንደ እንሰሳ አንገታቸወን ይቀላሉ ፣ የወረወራሉ። ሊቢያ ቀወስ ውስጥ ገብታለች፡ ኢራቅም ምስቀልቀሏ ወጥቷል ፣ሶሪያም እንዲሁ። በአጠቃላይ መካከለኛው ምስራቅ በእነ ኦባማ እና በእነ ሂለሪ ክሊንተን ፊት እየፈንዳ ነው። ታዲያ ይህ ሁኔታን ሰናነጻጽረው የእነ ጋዳፊ እና የ እነ ሳዳም ዘመን በጣም የተሻለ ነበር ማለት ይቻላል።” ሲሉ ገምታቸውን ሰንዘረዋል።

ኢራቅ የአሸባሪዎች “ሃርቫርድ ዮኒቨርሲቲ” ሆናለች የሚሉት ትራምፕ “የቱን ያህል ሳዳም መጥፎ መሪ ቢሆኑ ዘመነ ሳዳም አሁን ካለንበት ውጥንቅጥ የተሻለ ነበር ።” ብለዋል።በመቀጠልም ትራምፕ አሁን በአለም ላይ ከሚመለከቱት ሁናቴ አኳያ “ዘምናችን የመካከለኛው ዘመን ይመሰላል፣ ቸግራችንንም ለማመን ይከብዳል።” በማለት አለማችን ደህረ ሳዳም እና ድህረ ጋዳፊ ያለውን ችግርን አመላክተዋል።ትራምፕ በምረጡኝ ዘመቻቸው ላይ ቀጣይ ፕ/ት ከሆኑ አሜሪካንን ከሜኪሲኮ የሚያዋሰነው ድንበር ላይ ትልቅ የግንብ አጥር አጥራለሁ በማለት አወዛጋቢ ትችቶችን ተጋፍጠዋል።ሰሞኑንም አንዳንድ “የእክራሪዎች መነሃሪያዎች” ያሏቸው መሰጊዶችን አንደሚዘጉ ፎክረዋል ። ነገር ግን የአሜሪካ ሀገ መንግስት እርምጃቸወን ለማሳካት እንደማይፈቅደላቸው በቅጡ ኣንዳለተገነዘቡት ተናግረዋል። ምቼ ይሄ ብቻ በ ቅርቡ ለመጠይቅ ፈቃድ/እድል ያልሰጡት ጋዜጠኛን በጸጥታ ሰራተኞቻቸው ከ አዳራሽ አስባረወታል ።
dolandl trummp
የኢራቅ ነገር ከተነሳ ዘንዳ የቀደሞው የእንግሊዝ ጠ/ሚ/ር ቶኒ ብለዩር በ 2003 ጦራቸወን ከእሜሪካ ጎን አሰልፍው ኢራቅን መወረራቸው “ሰህተት ነበር” ሲሉ ነገ ሙሉው ቃለምለለሰ በሚቀረበው ሲ አኢን አኤን ፕሮግራም ላይ ቀረበው ይቀርታ የተጠየቁ ሲሆን የኢራቁ ወረራ ዛሬ በመካከለኛው ምስራቅ ለተከሰተው አክራሪ ቡድን (አይ ሲስ) መፈጠር ምንሰኢ ነው።” ብለዋል። ሳዳም ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አከማችተው ነበር የሚል ጥያቄ እና ትችቶች የቀረበባቸው ቶኔ ብልዩር መረጃው ሰህትት እንደ ነበር በማመን ይቅርታ ጠይቀዋል።ቶኒ ብለዪር 45,000 የሚደረሰ ጦር ወደ ኢራቅ በማዘመት ከ 100 በላይ ይ አንግሊዝ ወታደሮቻቸውን አጥተዋል። ሜል የተባለው ጋዜጣ “በመጨረሻ ላይ ቶኒ ብሌር ይቅርታ ጠየቁ ።ይህም ታሪካዊ ክስተት ነው “ብሎታል ።

ምንም ኣንኳን ከ 6ሚሊኦን በላይ ኢራቃዊ ሕይወቱን በከንቱ ቢገብርም፣ያቺ ታሪካዊ አገር እንደዋዛ በትበታተንም የቶኒ ብለዮር ወደ ይቅረታ እና ጸጸት መመጣት ሕዝባቸውን ሳያማክሩ ጦራቸውን የብስ እና ባህር አቋርጦ በሰው ግዛት ላይ ጣልቃ ገብነት/ወረራ ለሚያደረጉ አምባገነኖች /ጀብደኞች ትልቅ ትምህርት ሊሰጥ ይችላል።

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47721#sthash.VdHCAWqJ.dpuf