አሜሪካ፡ የሰብአዊያን የመጨረሻ ታላቅ ተስፋ ከኢ -ሰብያዉያን ኪሳራ ማዳን ፣

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ 

Hope2

ከናዚ ጀርመን ሰው ልጅ እልቂት የተረፉት እና የኖቤል ተሸላሚ የነበሩት ኤሊ ዊሰል በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኢፍትሐዊነትን ለመከላከል የማንችልበት እና አቅመቢስ የምንሆንበት ጊዜ ሊኖር ይችላል፣ ሆኖም ግን ኢፍትሐዊነትን የምንቃወምበት ጊዜ በምንም ዓይነት ሁኔታ እና በምንም ዓይነት መንገድ በፍጹም ማጣት የለብንም፡፡“

እኔ ደግሞ እንዲህ የሚል አባባል እጨምርበታለሁ፣ ”በቢሮ ተወሽቀው የሚገኙትን የፖለቲካ አስመሳይ እብዶችን እና ምንም ዓይነት ሀሳብ ማመንጨት የማይችሉ እርባና ቢስ የሀሳብ ድሁር ፖለቲከኞችን የምንቃወምበት ጊዜ በምንም ዓይነት መልከኩ እና በምንም ዓይነት መንገድ በፍጹም ማጣት የለብንም፡፡“

የሬፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶናልድ ትሩምፕ ባለፈው ሳምንት “በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪክ የሚገኙ የሙስሊሙን ማህበረሰብ የመረጃ ቁጥጥርን ፍጹም በሆነ መልኩ አካትቶ የሚይዝ የመረጃ ቋት ስርዓት በመንደፍ ተግባራዊ አደርጋለሁ“  ብሎ ነበር፡፡

ዶናልድ ትሩምፕ ይህንን ብቻም አይደለም የተናገረው፡፡ እንዲህ በማለትም ሀሳቡን የበለጠ አጠናክሮታል፣ “የመረጃ ቋቱ ከሚነግረን በላይ አልፎ በመሄድ የተለያዩ የቁጥጥር ስርዓቶች መኖር አለባቸው፡፡ በአሜሪካ የሚገኙትን ሙስሊሞች ለመከታተል እና ለመቆጣጠር እንዲቻል በርካታ ስርዓቶች ሊኖሩን ይገባል፡፡“

ትሩምፕ ከዚህም በተጨማሪ “የሚቻል ከሆነም በተወሰኑ መስጊዶች ላይ ከፍተኛ የሆነ ምርመራ ማካሄድ እና ሊዘጉ የሚችሉትን መስጊዶችንም በጥንቃቄ ማሰብ“ ተገቢ እንደሆነ አድርጎ ማሰብ ይፈልጋል፡፡

አደገኛ የሆነ የሞራል ኪሳራ?

ሌላው የሬፐብሊካን ዕጩ ፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ ቤን ካንሰር በዩኤስ አሜሪካ ሕገ መንግስት መሰረት አሜሪካውያን ሙስሊሞችን ቀጥተኛ በሆነ መልኩ አዕምሯቸው እና ልቦቻቸው የሚያስቧቸውን ሳይቀር ልቅም አድርጎ ማንበብ እንደሚችል አስረግጦ ተናግሯል (የዲስኩር ቱሪናፋ አሰምቷል ልበለው)፡፡

ካርሰን የአሜሪካንን ሀገር የመሰረቱ አባቶቻችን የሙስሊም ፕሬዚዳንት በመኖሩ ጉዳይ ላይ እምነት የላቸውም፣ ወይም ደግሞ የሙስሊም ፕሬዚዳንት ስልጣን መያዝ እንዲችል የሚያድርግ ሁኔታን አያጸድቁም ብሏል፡፡ እንዲህ በማለትም የሀሳቡን ዳህራ ለህዝብ ይፋ አድርጓል፣ “ከእስላም ጋር ተያያዥነት ያላቸውን እምነቶች ከሚያራምድ ማናቸውም ሰው ጋር ከፍተኛ የሆነ ችግር አለኝ፡፡“

(ወንድም ቤን የአሜሪካ መስራች አባቶች ጥቁር ፕሬዚዳንት ማመናቸውን በሚመለከት ምን እያሰበ እንዳለ ግልጽ ቢያደርግልን የሚገርመኝ ይሆናል!)

ካርሰን በአሜሪካ የሚገኙ ሙስሊሞች ሻሪያን እና ከእርሱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሁሉንም ሕጎች በማስወገድ ለአሜሪካ እሴቶች እና ሕገ መንግስት ተገዥ እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡

አንደው ለነገሩ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሕገ መንግስት ውስጥ “በአንድ ቢሮ ውስጥ ስልጣን ለመያዝ ወይም ደግሞ በህዝብ ዘንድ ታማኝነትን ለማግኘት በምንም ዓይነት መልኩ ኃይማኖት በመስፈርትነት የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም“ (አንቀጽ VI) የሚል ቋንቋ የለምን?

“በአሜሪካ-ርሰራውያን ምድር” ዘንድ የሕገ መንግስቱ አንቀጽ እንደማይሰራ እገምታለሁ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ካርሰር እንዲህ ብሏል፣ “በርካታ ጽንፈኝነት በሚካሄድባቸው በማናቸውም ቦታዎች እና ተቋማት ላይ ማለትም በመስጊድ፣ በቤተክርስቲያን፣ በትምህርት ቤት በመገበያያ ማዕከሎች ላይ ክትትል ማድረግ ይኖርብናል፡፡“ በማንኛውንም ነገር እና ሰው ላይ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር ማድረግ ተገቢ ነው!

ድንቄም ቁጥጥር! ጉድ እኮ ነው!

ቁጥጥሩ እንዲህ በሰውም በዕቃውም ላይ ተጠናክሮ ሲቀጥል በጠብመንጃ ሽያጭ ላይ ግን ምንም ዓይነት ቁጥጥር የለም! እንዲያውም በአሸባሪ ስም ዝርዝር ውስጥ ላሉትም ቢሆን እንኳ የጦር መሳሪያ መሸጡ ላይ ቁጥጥሩ ሊደረግ አይገባም ምክንቱም አስፈላጊ ባልሆነ መልኩ በሰዎች ላይ የጦር መሳሪያ ግዥ ክልከላ መጣልን የማይደግፈው የሁለተኛው ሕገ መንግስት ማሻሻያ ዋና ደጋፊ ነኝ፡፡ የተሻለ የሕግ የበላይነት ሊኖር ይገባል፡፡

ድርብ የሞራል ኪሳራ?

በዚህ አላቆመም፡፡ የሶርያውያንን ስደተኞች ከውሾች እኩል አድርጎ ቆጠራቸው፡፡

ካርሰር እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ለምሳሌ ታውቃላችሁ፣ በጎረቤቶቻችሁ አካባቢ አንድ የሚሮጥ የአበደ ውሻ የሚኖር ከሆነ ስለዚያ ውሻ ጥሩ ነገር ለማድረግ አታስቡም፣ እንዲያውም ልጆቻችሁን ሁሉ ከመንገዱ አካባቢ በእጅጉ እንዲርቁ ታደርጋላችሁ፡፡ ይህ ማለት በማንኛውም እሳቤ ማንኛውንም ውሻ የተባለን ፍጡር ሁሉ ትጠላላችሁ ማለት ነውን?“

ካርሰር የተመሳስሎውን ድምጸት የበለጠ ጎላ አድርጎ ለማሳየት በማሰብ ያበዱ ውሾችን ሰብአዊ ፍጡር ከሆነው ሰው ጋር በማነጻጸር የሶርያን ስደተኞች እና ጽንፈኛ አክራሪ ሙስሊሞችን በአንድ በኩል በማስቀመጥ ያበዱ እና ያላበዱ ውሾችን በሌላኛው ጎን ጫፍ በማስቀመጥ የሰውን ልጅ ስብዕና ወደ እንስሳነት ያውም ወደ አበደ ውሻነት ዝቅ በማድረግ ለማነጻጸር ሞክሯል፡፡ (የማይነጻጸሩ ነገሮችን ማነጻጸር?)

ካርሰን እንዲህ ብሏል፣ “በተመሳሳይ መልኩ እኛም በእርግጠኝነት የትኞቹ ሰዎች ያበዱ ውሾች እንደሆኑ ለይቶ ማውጣት የሚያስችል ስርዓት በመንደፍ በስራ ላይ ማዋል አለብን፡፡ እነማን ናቸው በአስመሳይነት ሾልከው የሚገቡ እና በአስመሳይነት ደህና መስለው ቆይተው እኛን ሊያጠፉን የሚችሉ? ያንን ነገር እንዴት መከላከል እንደምንችል እስከምናውቅ ድረስ ልጆቻችንን ያበደ ውሻ ባለበት ሁኔታ አውጥተን በጎረቤቶቻችን አካባቢ እንዲንቀሳቀሱ የመፍቀድ ያህል ሞኝነት የበዛበት ድርጊት ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ችግር ያለባቸውን ወይም ባበደ ውሻ ተመሳስሎነት የቀረቡትን ጽንፈኛ አክራሪዎች ለይተን የምናወጣበት ተገቢ የሆነ ስርዓት እስካላዘጋጀን ድረስ ዝም ብለን የምንቀበላቸው ከሆነ አሁንም የለየልን ሞኞች ነን፡፡“

የካርሰን  አባባል እንግዳ በሆነ እና ባልተለመደ መልኩ “ያበዱ ውሾች እና እንግሊዞች” በሚል ርዕስ የተዘጋጁትን የኖኢል ኮዋርድን እንዲህ የሚሉትን ባለሁለት መስመር ሙዚቃ አስታወሰኝ፡ “ነጮች ሰዎች የሳር ጎጆዎቻቸውን በሚለቁበት ጊዜ ነዋሪዎቹ (በቅኝ አገዛዝ ስር ስላሉት ነው የሚጠቅሰው) ቅሬታዎቻቸውን ያሰሙ ነበር /ምክንያቱም ግልጽ በሆነ መልኩ በእርግጠኝነት አዕምሮ በሽተኞች ናቸው!“

በእርግጠኝነት ወንድም ቤን የአዕምሮ በሽተኛ ነውን?

የሶርያ ስደተኞች ውሾች አይደሉም፡፡ እነሱም በአምላክ አምሳል፣ በአላህ አምሳል የተፈጠሩ እንደ እኛ ሁሉ ሰዎች ናቸው፡፡

የወንድም ቤን ካርሰር ቃላት በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ እንዳይመለስ ሆኖ ተቀብሮ የሚገኘውን የአፍሪካ የቅኝ ግዛት አስከፊ ትውስታ እንደገና ህይወት ዘርቶ የማምጣት ያህል ሆነው ይሰማሉ፡፡

በቅኝ ተገዧዋ አፍሪካ ጊዜ በህዝብ መጠቀሚያ ቦታዎች ላይ ሁሉ “ለአውሮፓውያን ብቻ” እና “ለአፍሪካውያን እና ለውሾች ያልተፈቀደ” የሚሉ ማስታወቂያዎችን እና ምልክቶችን በየቦታው ተሰቅለው ማየት የተለመደ ነበር፡፡

በ20ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹ ግማሽ ዓመታት በቆዳቸው ቀለም ምክንያት አፍሪካ አሜሪካውያን አይፈለጉም ነበር፡፡ እንደዚሁም ደግሞ አይሁዶችም በኃይማኖታቸው ምክንያት አይፈለጉም ነበር፡፡

ያ ጠቅላላ አግላይ መልዕክት እንዲህ በሚሉ ምልክቶቹ ላይ እየተደረገ አፍሪካ አሜሪካውያን እንዲያውቁት ይደረግ ነበር፣ “ለባሮች አይፈቀድም፡፡ ለአይሁዶች አይፈቀድም፡፡ ለውሾች አይፈቀድም፡፡”

አፍሪካ አሜሪካውያን ሰዎች እንጅ ውሾች አይደሉም፡፡ አይሁዶች ሰዎች እንጅ ውሾች አይደሉም፡፡ ሶርያውያን ሰዎች እንጅ ውሾች አይደሉም፡፡

ውጤታማ እና ስኬታማ በሆኑ አፍሪካ አሜሪካውያን ዜጎች ላይ እንደዚህ ያሉ ልብን የሚያቆስሉ ቃላትን መስማት በቀላሉ አዕምሮዬን ይበጠብጡታል፣ የማድረግ ኃይሌን እንዲነጥፍም ያደርጉታል፡፡

ሆኖም ግን ፍርሀትን እና ጥላቻን እየገመዱ ያሉት ትሩምፕ እና ካርሰን ብቻ አይደሉም፡፡

የሬፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚዳንቶች ቴድ ክሩዝ እና ጀብ ቡሽ ከዚህም በተጨማሪ ለክርስትና እምነት ተከታይ ሶርያውያን ብቻ የአሜሪካ ጥገኝነቱ እንዲፈቀድ በማለት ቡድኑን ተቀላቅለዋል፡፡

ክሩዝ በእርግጠኝነት እንዲህ በማለት አውጇል፣ “የሽብር ድርጊትን በመፈጸሙ ረገድ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትርጉም ያለው አደጋ የለም፡፡“

የሬፐብሊካውያን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚዳንት ተወዳዳሪዎች ማርኮ ሩቢዮ፣ ራን ፓውል እና ሌሎችም እንደዚሁ በዋናነት ተመሳሳይ መልዕክትን በማስተላለፉ አስተሳሰብ ላይ የተዘፈቁ ናቸው፡፡ በአሜሪካ ለሶርያውያን ስደተኞች የሚሆን ቦታ የለም፡፡

የሬፐብሊካውያን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ ክሪስ ክሪስቲ “በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ በስደተኝነት ሊፈቀድላቸው የማይገቡት እድሜአቸው ከአምስት ዓመታ በታች የሆኑት ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ብቻ አይደሉም፣ ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ያለው አስተዳዳር እንድንቀበላቸው የሚጠይቁንን ሰዎች ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመመርመር የሚያስችል የብቃት አቅም ይኖረዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የአሜሪካውያንን ደህንነት እና ጸጥታ ማስጠበቅ መቻል አለብን” ብላለች፡፡

ኦባማ ጭካኔ የተሞላበትን የክርስቲንን የፖለቲካ ስብዕና እንዲህ በማለት አቅልሎ ለማቅረብ ሞክሯል፣ “በመጀመሪያ ደረጃ በእነርሱ የምርጫ ቅስቀሳ ክርክር ላይ ፕሬሱ ጠንካራ ሆኖብናል በማለት ሲጨነቁ ነበር፣ አሁን ደግሞ ስለሶስት ዓመት እድሜ ህጻናት መጨነቅ ይዘዋል፡፡ እኔ ይኸ ጉዳይ ብዙም ትርጉም የሚሰጠኝ ነገር አይደለም፡፡“

ሶስት እጥፍ፣ አራት እጥፍ የሞራል ስብዕና ዝቅጠት?

“በሰው ልጅ ልቦች ውስጥ ምን ዓይነት ሰይጣን ተጣብቶ እንዳለ ማን ያውቃል?”

“ጨለማው ያውቀዋል::”

በአሁኑ ጊዜ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ፍርሀት እና ጥላቻን የሚያሰራጩት ብሄራዊ እና አስመሳይ ፖለቲከኞች አይደሉም፡፡

በእስልምና እምነት እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ጥላቻን የሚያራግቡ ጥቂት መንግስታዊ ፖለቲከኞች አሉ፡፡

የሬፐብሊካን የኦክላሆማ ግዛት ሴናተር የሆነው እስልምናን በማስመልከት እንዲህ ብሏል፣ “እስልምና ከሀገራችን ውስጥ መወገድ ያለበት ካንሰር ነው፡፡“ ሴናተሩ በአጠቃላይ የእስልምናን ዋና ተግባር በማስመልከት ሀሳቡን በማጠናከር እንዲህ ብሏል፣ “የምዕራባውያንን ስልጣኔ ከውስጥ ማውደም“

ይኸ አነጋገር በሰሜን ናይጀሪያ የሚንቀሳቀሰው እና ቦኮ ሀራም እየተባለ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን ወይም ደግሞ አይኤስአይኤል/አይኤስአይኤስ (ISIL/ISIS) የሚባለው ጽንፈኛ ቡድን ክርስትና መውደም አለበት እንደሚለው እና የኃይማኖት ጦረኞች ደግሞ እስልምና መውደም አለበት ከሚሉት ጋር አንድ ዓይነት አይደለምን?

ሆኖም ግን በእርግጥ የሬፐብሊካን ፖለቲከኞች እና አስመሳይ ፖለቲከኞች ብቻ አይደሉም እስልምናን እና ሙስሊምን ጥላሸት በመቀባት ላይ የሚገኙት፡፡

ፌዘኞች እና ዲሞክራትስ (በእርግጠኝነት እራሴን ደገምኩን?) በተጨማሪ የሞራል ኪሳራውን ዕኩይ ምግባር ተቀላቅለዋል፡፡

ታዋቂው አስቂኝ ተዋንያኑ/ኮሜዲያኑ (?) እና አሮጌ ባህልን በመገዳደር የሚታወቀው ቢል ማኸር አሜሪካውያንን በማስመልከት እንዲህ ብሎ ነበር፣ “አሜሪካውያን ለበርካታ ሙስሊሞች ሶርያውያን ስደተኞችን ጨምሮ ለአሜሪካውያን እሴቶች እንግዳ ለሆኑ ነገሮች ዕውቅና ለመስጠት አይፈልጉም፡፡“ እንዲህ የሚል ሀሳብ ጨምሯል፣ “ይኸ ሀሳብ ከሞላ ጎደል ሁላችንም የምንጋራቸው እሴቶች ሁሉም ኃይማኖቶች አንድ ዓይነት ናቸው የሚለው ሞኝነት ነው፣ እናም ይህንን ጉዳይ ሞኝነት ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡“

ደህና! በቢል ማኸር ቀልዶች ላይ ተዝናንቻለሁ፣ ሆኖም ግን እርሱ በሞኝነት ሀሳብ ውስጥ የተሞላ ነው፡፡

ሆኖም ግን ጥቂት ዴሞክራቶች አይቀልዱም፡፡ የሞራል ኪሳራን እያስፋፉ ይገኛሉ፡፡

የቀድሞው የዴሞክራቶች ዕጩ ፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ የነበሩት ጄኔራል ዌስሌይ ክላርክ የአሜሪካንን እሴቶች የማይካፈሉትን ለጽንፈኛ ሙስሊሞች ማሰልጠኛ ካምፖች ናቸው የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ክላርክ እንዲህ ብለዋል፣ “እነዚህ (የሙስሊም) ህዝቦች ጽንፈኛ ከሆኑ እና ዩናይትድ ስቴትን የማይደግፉ ከሆኑ  እንደ መርህ ሲታይ ለዩናይትድ ስቴት ታማኝ አይደሉም፡፡ ግጭቱ በሚኖርበት ጊዜ ጤናማ ከሆነው ማህበረሰብ የመነጠል የእነርሱም መብት እና የእኛም መብት እና ግዴታ ነው፡፡“

“የማግለያ ማዕከሎች” ጽንፈኛ ለሆኑ ሙስሊሞች የተጠናከሩ የእስር ቤት ቴክኒኮች ናቸውን?

እርጉዝ ለእርግዝና በመጠኑም ቢሆን የመቀራረቡን ያህል በተመሳሳይ መልኩ መለያየትም ለማግለያ ካምፖች የቀረበ ነው፡፡ የማግለያ ማዕከሎች ወዲያውኑ የማግለያ ካምፖች እስር ቤቶች ይሆናሉ፡፡

በአሜሪካ ጽንፈኞችን እና ታማኝ ያልሆኑ ሙስሊሞችን ከጀግናዎች እና ታማኝ ከሆኑት መካከል እንዴት አድርገን ነው መለየት የምንችለው?

የተቀደሱ የአሜሪካ እሴቶችን ለመጠበቅ ሲባል ግዙፍ የምርመራ ተቋም ማቋቋም እና መመስረት አለብን?

እያንዳንዱ አሜሪካዊ ሙስሊም ለእውነተኛ ለተቀደሱት የአሜሪካ እሴቶች ታማኝ መሆኑን ለማወቅ ወይም ታማኝ ያለመሆኑን ለመገንዘብ ሲባል ግዙፍ ከሆነው የምርመራ ተቋም እያስቀረብን ምርመራውን በማከናወን ታማኝ ያልሆኑትን ወደ ማግለያ ካምፖች ማጋዝ ይኖርብናልን?

በእርግጠኝነት የማግለያ ካምፖችን መጠቀም የጀመርነው የጃፓን ንጉሳዊ አገዛዝ የፒርል ወደብን እ.ኤ.አ በ1942 ማጥቃት በጀመረበት ወቅት ነው፡፡

እነዚህን ካምፖች “እውነተኞቹን” አሜሪካውያን ከጃፓን ዝርያ ካላቸው አሜሪካውያን በመለየት ለመጠበቅ ሲባል እንደገና “አመላካች ካምፖች” (በተለመደው አጠራር ሳይሆን ደግ በሆነ እና በመልካም ስያሜ የማቆያ ካምፖች) በማለት እንጠራዋለን፡፡

ፕሬዚዳንት ሩዝቬልት በዌስት ኮስት የሚኖሩ አሜሪካ ጃፓናውያን ላይ የብዙሀን እልቂት እንዲፈጸምባቸው ትዕዛዝ ሰጡ፣ ምክንያቱም እነዚህ ዜጎች በሙሉ ታማኝነት የሌላቸው እና ከዚህም ባሸገር ለጃፓን ንጉስ በሚስጥር ጽኑ ድጋፍ የሚሰጡ ናቸው የሚል እምነት ስለነበራቸው ነበር፡፡

ከ110,000 በላይ የሚሆኑ በዌስት ኮስት የሚኖሩ አሜሪካ ጃፓናውያን ዜጎች ከሚኖሩበት አካባቢ በኃይል እንዲፈናቀሉ እና በካምፕ እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡ አንዳቸውም ላይ ቢሆን ምንም ዓይነት የወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው አልነበረም! አንድም!

እ.ኤ.አ በ1944 የዩኤስ አሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሳፋሪ በሆነው የኮሬማትሱ እና የዩናይትድ ስቴትስ የብዙሀን ድምጽ የአሜሪካ ጃፓናውያን ዝርያ ባላቸው ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንዲህ በማለት ሕጋዊ አድርጎታል፡

የህዝቦቹን ቁጥር እና ያላቸውን ኃይል በእርግጠኝነት እና በፍጥነት ማረጋገጥ እስካልተቻለ እና እነዚያ ህዝቦች ታማኝነት የሌላቸው መሆናቸው እስካልታወቀ ድረስ ያንን በወታደራዊ ባለስልጣናት እና በኮንግረሱ የተሰጠውን ዳኝነት መሰረተቢስ ነው በማለት ውደቅ ልናደርገው አንችልም፡፡ ጦርነቱን የሚያካሂዱት የመንግስት ክፍሎች በጣም ወሳኝ በሆነ ሰዓትእነዚህንሰዎች ግልጽ በሆነ መልኩ ለመለየት እና ለማግለል የማይቻልበት ሁኔታ ስለሚፈጠር እና ሀገራዊ አደጋን ለመከላከልእናደህንነትን ለመጠበቅ ሲባል እንደዚያ ዓይነቱ ፈጣን እና በቂ የሆነ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ከግንዛቤበማስገባትእርምጃው ተገቢ አይደለም የሚል እምነት ሊኖረን አይችልም፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ኃይል በተቀላቀለበት የሀሳብ ድምጸት የጃፓን ዝርያ ባላቸው አሜሪካውያን ላይ የተወሰደውን እርምጃ ጀስቲስ ዳኛ ኦዎን ጀ. ሮበርት እንዲህ በማለት ተቃውመውታል፣ አውግዘውታልም፡

እነዚህን የጃፓን ዝርያ ያላቸውን ዜጎች በወታደራዊው ፕሮግራም መሰረት ለማጋዝ እና በእስር ቤት እንዲታሰሩ በማድረግ ነጻነትን ለመቀዳጀት ብዙ ነገር ተብሏል፡፡  ሆኖም ግን የሕግ የበላይነትን ባገናዘበ መልኩ ይህንን ስርዓት ዘላቂነት እንዲኖረው እና ነጻነትን መቀዳጀት እዲቻል ከማድረግ ይልቅ ሕጉን እራሱን እንዲታወቅ ማድረግ የበለጠ ድምጸት ይኖረዋል፡፡ ሆኖም ግን ወታደራዊ ትዕዛዝ ሕገ መንግስታዊ ባይሆንም ከወታደራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የዘለለ አይሆንም፡፡ በዚያም ጊዜ ቢሆን እንኳ ተተኪው ወታደራዊ አዛዥ ሙሉ በሙሉ ሊጥሰው ይችላል፡፡ ሆኖም ግን አንድ ጊዜ የሚቀርብ የፍርድ ሀሳብ እንደዚህ ያለውን ትዕዛዝ ከሕገ መንግስቱ ጋር በማያያዝ በሚያገናዝብበት ጊዜ ወይም ደግሞ ሕገ መንግስቱ እራሱ በዚህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ የሚጥለውን ገደብ በመመልከት ፍርድ ቤቱ ምንጊዜም ቢሆን በወንጀል ማጣራት ተግባራት ላይ የጠራ እና በአመክንዮ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ስለሚያስተላልፍ የአሜሪካ ዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ሕጉ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ከዚህ አንጻር ለአስቸኳይ ሁኔታ በሚል ወታደራዊ መሳሪያ ተጭኖአንድን ነገር ለማድረግ ሲባል ለወታደራዊባለስልጣን የሚቀርብ የመርህ ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ጄኔራል ክላርክ ይንን የተጫነውን የጦር መሳሪያ ወደ አሜሪካ ሙስሊሞች እንዲያነጣጥር እና እልቂት እንዲፈጠር ይፈልጋልን?

ለበርካታ ዓመታት በተለያያዩ ብዙ አጋጣሚዎች እምነት የማይጣልባቸውን የጃፓን ዝርያ ያላቸውን አሜሪካውያን የቡድን አባላት በካሊፎርኒያ በጣም ሩቅ ከሆነ በረሀማ አካባቢ ላይ የተዘጋጀውን “የማንዛናር እስር ሰፈራ” ማዕከልን ጎብኝቻለሁ፡፡

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የጀፓን አሜሪካዊነት ዜግነት ያላቸው እና ሌሎች የውጭ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለው የሚታሰሩበት የነበረው ያ ቦታ በአሁኑ ጊዜ ታሪካዊ ቦታ ሆኖ ይገኛል፡፡

ሁልጊዜ ወደ ማንዛናር በምሄድበት ጊዜ ፋሲሊቲዎች ካሉበት በስተምዕራብ በኩል በመቆም በዘር ልዩነት፣ የአንድን ሰው ንብረት ከሕግ አግባብ ውጭ ለእራስ ማድረግ፣ አንድ ሰው የአናሳ ብሄረሰብ ቡድን አባል በመሆኑ እና በአንድ ሰው ግላዊ አስተሳሰብ ያለምንም ማስረጃ እምነት የሌለው እና ታማኝነት ያልሆነ በሚል ምክንያት የሚደርስበትን ውርደት እና ሊመጣ የሚችለውን ነገር በምዕናብ አሰላስላለሁ፡፡

እንዴት ኃይልን በመጠቀም እየገፈተሩ፣ እያዳፉ ወደ መኪናዎች፣ አውቶብሶች፣ የጭነት መኪኖች እና ባቡሮች እያስገቡ በማጨቅ ምንም ነገር በማይታይበት አውላላ የበረሀ ካምፕ ውስጥ ያስገቧቸው እንደነበር በምናብ ስቃኘው በጣም አድርጌ እገረማለሁ፡፡

እያንዳንዱ ግለሰብ እና ቤተሰብ ወደ ማንዛናር እና ወደሌሎች ካምፖች ከዋሽንግተን፣ ከአሪጎን፣ ከካሊፎርኒያ እና ከአሪዞና ፋሲሊቲዎች በወታደራዊ ጥበቃ ከተላከ በኋላ የመለያ ቁጥር ይሰጠዋል፡፡ (የመለያ ቁጥሮች በንቅሳት ይደረጋሉ አላልኩም፡፡ እንደዚያ ዓይነቱ ድርጊት የሚፈጸመው በአውስችዝ-ቢርከናው፣ በቡቸንዋልድ፣ በዳቻው፣ በትሬብሊንካ እና በሌሎች ቦታዎች ነበር፡፡)

ለእኔ በማንዛናር ቦታ አካባቢ መዘዋወር ሁልጊዜ የጭንቀት ክስተት ነው፡፡

ሆኖም ግን የማንዛናርን የመኪና ማቆሚያ ቦታ በለቀቅሁ ጊዜ ጭንቅላቴን በማወዛወዝ ተጻራሪ በሆነ መልኩ የተጻፉትን እና እንዲህ የሚሉትን ቃላት በምልክቱ ላይ ተጽፈው ስመልከት እስቃለሁ፡  “ማንዛናር የጦር ማግለያ ሰፈር ማዕከል“

በምንም ዓይነት መንገድ ምንም ዓይነት ወንጀል ያልሰሩ አሜሪካውያን ዜጎችን “ማግለያ ማዕከል?”

ወደ “ማግለያ ማዕከሉ” የሚላክ ማናቸውም ሰው ቢሆን የወንጀል ድርጊት ፈጽመሀል ተብሎ ክስ ተመስርቶበት አያውቅም፡፡

ሁሉም ወደዚያ ቦታ በኃይል ተይዘው የሚጋዙት ሁሉ ምንም ዓይነት ወንጀል ያልሰሩ ንጹሀን ዜጎች ናቸው፡፡

ጆርጅ ኦርዌል “የፖለቲካ ቋንቋ…ነጩን ውሸት የጠራ እውነት አስመስሎ የሚያቀርብ እና ስሙ በገዳይነት ያደፈውን የተከበረ አድርጎ የሚያቀርብ፣ ምንም ዓይነት መሰረት የሌለውን ጠንካራ መሰረት ያለው አስመስሎ የሚያቀርብ ሊጨበጥ ሊዳሰስ የማይችል ባዶ ነፋስን መጨበጥ አድርጎ የሚያቀርብ ነው፡፡“

በኦዌንስ ሸለቆ መካከል በጦር መሳሪያ የታጀበ ማማ ማቆም በእስረኞች ማጎሪያ ካምፕ “የማግለያ ማዕከል” የማይዘገን ጉም ማለት ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ “ለጽንፈኛ ሙስሊሞች” ዘመናዊ ማንዛናር ለማዘጋጀት እያሰቡ ነውን?

ምናልባትም እንደ “አቡ ዛር የሰላም ጊዜ ማግለያ ማዕከል” ሁሉ ማናዛርን እንደገና ለመክፈት አስበው ነውን?

በእርግጠኝነት “39ኛውን ዓመታዊ የማናዛናርን የቅዱስ ኃይማኖት ጉዞ” የተሳተፉት 1,500 ሰዎች በዚህ ጉዳይ ላይ አይስማሙም፡፡

ሚስጥራዊ ቃላትን በመጠቀም የፍርሀት አራጋቢዎች እና ሁሉንም ሙስሊሞች ጥላሸት የሚቀቡ የፖለቲከኞች የስም ዝርዝር ከጊዜ ወደ ጊዜ እጨመረ በመምጣት ላይ ይገኛል፡፡

የእስልምና ጥላቻን በመዝራት እና ፍርሀት በማራገብ ለሶርያውያን ስደተኞች መስብክ የዕለት ከዕለት ፋሽን እየሆነ መጥቷል፡፡

በርካታ የሆኑ በአሜሪካ እና በመላው ዓለም የሚኖሩ ሙስሊሞች የጽንፈኛ እስልምና እምነት ተከታዮች ድብቅ የሚስጥር ባልደረቦች ናቸው በማለት የሀሰት መረጃን እየሰበሰቡ የሚያሳዩ ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡

እነዚህ ሰዎች የሙስሊም “የሻሪያን ሕግ” ተፈጻሚ በማድረግ ሁሉንም የምዕራቡን ዓለም ስልጣኔ ዶግ አመድ በማድረግ “ከእስልምና እምነት ተከታዩ ዓለም” ለማጥፋት ይፈልጋሉ ይላሉ፡፡ በካሊፌቶች አገዛዝ፣ የነብዩ መሀመድ ተተኪ አድርጎ እራሱን በሚሰይም እና በእስልምና ዓለም አቀፍ ሕግ በመመራት መኖርን ይመርጣሉ ይላሉ፡፡

ይኸ ዓይነት ስለሙስሊሞች የሚነገረው የድድብና ንግግር ብዙ አሜሪካውያን ጥቁሮች ከነጮች የበለጠ ዘረኞች፣ ሂስፓኒኮች ወይም ደግሞ አብዛኞቹ ነጭ አሜሪካውያን በተለይም ደግሞ ወጣቶች ድብቅ ዘረኞች ናቸው ከሚለው ጽንፈኛ አመለካከት ጋር ብዙም የተለዬ አይደለም፡፡

አስደንጋጩ ነገር እንደዚህ ዓይነቶቹ የድድብና አስተሳሰቦች ለምን እንደሚባሉ በእርግጠኝነት የክርክር ተግዳሮት የማይቀርብባቸው የመሆኑ ጉዳይ እና በሸፍጥ የተሞሉ ሀሰት መሆናቸውን ማጋለጥ ያለመቻሉ እንዲሁም የፍርሀት ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ የእስምልና ጥላቻ፣ የውጭ ኃይሎችን መፍራት፣ ሀሜት ማሰራጨት እና የመሳሰሉት ሁኔታ ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ በአሜሪካ ሕዝብ ጨዋነት፣ ፍትሀዊ አመላካከት እና ተፈጥሯዊ መልካምነት ላይ ፍጹም የሆነ አዎንታዊ እምነት አለኝ፡፡

በስሜታዊነት በተሞሉ አምባገነኖች የሚራገቡትን እና ፍቅር እና ሰላም የተሞላባቸውን ታላላቆቹን የአሜሪካንን እሴቶች ለማውደም እየተሸረበ ያለበትን ሁኔታ ፊት ለፊት የምንቃወምበት ጊዜው አሁን ነው፡፡

የምችል ብሆን ኖሮ ስለቤን ካርሰን መጥፎ መግለጫዎች እና አረመኒያዊ ኢሰብአዊ ድርጊቱ በአሁኑ ጊዜ ሌላ ቀን ለመኖር እየተጋሉ ላሉት ለእያንዳንዳቸው የሶርያ ስደተኞች እኔ በግሌ ይቅርታ ብጠይቃቸው እወድ ነበር፡፡

ለእያንዳንዳቸው ሶርያውያን አሜሪካኖች እንደዚህ አይደሉም በማለት ልነግራቸው እፈልጋለሁ፡ አሜሪካኖች በጥላቻ የተሞሉ አይደሉም፣ አሜሪካኖች ጎጂዎች አይደሉም፣ አሜሪካኖች በቀልተኞች አይደሉም፣ አሜካኖች አዋራጆች አይደሉም፣ አሜሪካኖች ክብርን የሚነኩ አይደሉም፣ አሜሪካኖች መጥፎዎች አይደሉም፣ አሜሪካኖች ጨካኞች አይደሉም፡፡

አሜሪካኖች በመሬት ላይ የወደቀን፣ ዕድሉ የጠመመውን፣ በባህር ውስጥ የሰመጠውን፣ በተስቢስነት አዘቅት ውስጥ የሚማቅቀውን፣ የተራበውን፣ ተስፋየለሹን፣ ተከላካይ የለሹን እና ኃይል የለሹን ወንድ፣ ሴት፣ ልጅ የሚመቱ ባለመሆናቸው ላይ እምነት እንዳለኝ ልነግራቸው እወዳለሁ፡፡

አሜሪካኖች እንደዚያ አይደሉም፡፡ ለእኔ የአሜሪካውያን ባህሪያት በነጻነት፣ በክብር፣ በለጋሽነት፣ በወንድማማችነት መንፈስ፣ በእኩልነት፣ በእርዳታ ሰጭነት፣ በጓዳዊነት፣ በመግባባት፣ በእርግጠኝነት፣ በስልጡንነት፣ በጋራነት እና በአብሮነት መንፈስ ላይ የሚሽከረከሩ እና በጽናት የሚተገብሩ ህዝቦች ናቸው፡፡

በአሜሪካ የነጻነት ሀውልት በመዳብ እና በብረት ቅልቅል ጠንካራ መሰረት ላይ ተጽፈው የሚገኙትን እና የአሜሪካውያንን መንፈስ በትክክል የሚገልጹትን እንዲህ የሚሉትን ሀረጎች እና ቃላት እንዲህ አቀርባለሁ፡

መድከምህን፣ መቸገርህን ንገረኝ፣

አካልህ ሁሉ ነጻ አየር እንዲተነፍሱ፣

በስቃይ ላይ ሆነው የሚወራጩትን፣

እነዚህን መጠለያ የለሾች እና የተበሳጩትን ወደእኔ ላካቸው፣

ለእነዚህ ሁሉ ወገኖች ከወርቃማው በር ላይ ቆሜ ፋኑሴን አበራላቸዋለሁ፡፡

እነዚህ ቃላት እ.ኤ.አ በ1883 በአሜሪካዊው አይሁድ ገጣሚ በኢማ ላዛሩስ በኒዮርክ ከተማ በግዙፉ ሀውልት ተጽፈው ከተቀመጡት የተወሰዱ ናቸው፡፡

ማህተመ ጋንዲ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “በሰው ልጆች ሰብአዊነት ላይ እምነት ማጣት የለብህም፡፡ ሰብአዊነት ውቅያኖስ ነው፣ የውቅያኖሱ ጥቂት የውኃ ጠብታዎች ቆሻሻ ቢሆኑ ውቅያኖሱ በሙሉ ቆሻሻ ሊሆን አይችልም፡፡“ እኔም እንደዚሁ በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ እምነት ማጣት የለብንም እላለሁ፡፡

አልበርት አነስታይንም እንዲህ በማለት ተቀላቅለዋል፡ “ምንጊዜም ሰብአዊነትህን ብቻ አስብ፣ ሌላውን ነገር ሁሉ እርግፍ አድርገህ ተወው፡፡“

“ኢፍትሀዊነትን ለመከላከል አቅመቢስ የምንሆንበት ጊዜ ሊኖር ይችላል፣ ሆኖም ግን ኢፍትሀዊነትን ለመቃወም ምንም ዓይነት ጊዜ ልናጣ አይገባም፡፡”

በሙስሊም ወገኖቻችን ዘንድ እየተፈጸመ ያለውን ኢፍትሀዊነት ለማስቆም አቅሙ የለኝም፣ ሆኖም ግን ያንን ኢፍትሀዊነት ለመቃወም አቅመቢስ ልሆን ፈጽሞ አልችልም!

እቃወማለሁ!

እቃወማለሁ፣ ሆኖም ግን በተወሰኑ ቡድኖች እና በተለዬ እምነት ላይ ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ ለሚጠቀሙ፣ ባላቸው የስራ ኃላፊነት እና ሀብት አላግባብ በመጠቀም ስም ለሚያጠለሹ፣ ስብዕናን ለሚያጠፉ፣ ለሚወነጅሉ፣ ጥላቻን ለሚያሰራጩ፣ ወጥነት አሰራርን ለሚያጠፉ እና የጠቅላይነት ስሜትን ለሚያራምዱ በጥቂት ሰይጣናዊ ምግባርን በተላበሱ ፍጡሮች የሚፈጸመውን ኋላቀር እና አረመኒያዊ ተግባራት ለመግለጽ  የምችልበት ቃላት ያጥሩኛል፡፡

ዓለም ሁሉንም አፍሪካ አሜሪካውያንን እንደ ቤን ካርሰር እና ሁሉንም ነጭ ህዝቦች እንደ ዶናልድ ትሩምፕ አድርገው የሚቆጥሩ ከሆነ በፍርሀት ድንጋጤ የምርድ ይሆናል፡፡

ማንም በአመክንዮ የሚያምን እና በእራሱ የሚተማመን አሜሪካዊ ሁሉንም አሜሪካውያንን ለበርካታ ዓመታት በሰው ልጆች ላይ እልቂት በመፈጸም እና አሸባሪነተን በማራመድ ተሳታፊ ሆኖ ከቆየው ድርጀት ከበኩ ክሉክስ ክላን የጥላቻ ድርጊቶች ጋር በመሆን ዓለም ሁሉንም አሜሪካውያንን መፈረጅ ይችላልን?

ወደ አስርት ዓመታት ገዳማ ያህል ሳምንታዊ ትችት ጸሀፊ ሆኘ በቀጠልኩባቸው ጊዚያት ሁሉ  ከጊዜ ወደ ጊዜ አሜሪካንን በከፍተኛ ደረጃ ሀሳባዊ በማድረግ፣ ስለአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም፣ ስለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ፣ ስለካፒታሊዝም፣ ስለጀብደኝነት፣ ስለወታደራዊነት፣ ስለኮርፖራል፣ ስለኒዮሊበራሊዝም፣ ስለምሁራዊነት፣ ስለአድርባይነት፣ ስለአካባቢያዊነት፣ ስለኋላቀርነት፣ ስለጽኑ የአርበኝነት መንፈስ፣ ስለግዛት እና ስለሌሎች ነገሮች አታነሳም በሚል ተከስሻለሁ፡፡

በአሜሪካን ሕገ መንግስት ታምናለህ ትማፀናለህ ይላሉ ።አሜሪካኞች በጣም ልዩ ናቸው  ትላለህ ይላል ክሱ።

በእኔ የስራ ዓለም የአሜሪካንን ሕገ መንግስት ለመደገፍ እና ለመጠበቅ ለበርካታ ጊዚያት ይፋ የሆኑ ቃል ኪዳኖችን ፈጽሚያለሁ፡፡ ቁጥራቸውን ረስቻለሁ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለም፡፡ ግልጽ በሆነ መልኩ በዩ ኤስ አሜሪካ ሕገ መንግስት ቃለ መሀላ ፈጽሚያለሁ፡፡

በርግጥም አሜሪካኞች በጣም ልዩ ናቸው።

ሁለቱን ም ክሶች አቀበላለሁ፡፡

ለእኔ የአሜሪካ ልዩ መሆን ማለት በተጨባጭ ምን ማለት ነው?

ጥቂቶች እዲህ ይላሉ፣ “የአሜሪካ ልዩ የመሆን ሁኔታ“ በወግ አጥባቂዎች የሚራመድ ሚስጥር ነው ይላሉ፡፡

ሀሳቡ ከአሜሪካ ታሪክ ጀርባ ባርነትን ጨምሮ፣ የአሜሪካ ቋሚ ዜጎችን ለመለያየት ጂም ከሮው ሳውዝን እና የአሜሪካንን መስራች አባቶች እና ሕገ መንገስቱን ቅዱስ አድርጎ ለማቅረብ የተሰነዘረ ነው ይላሉ፡፡

ለእኔ ስለዴሞክራሲ እና ስለግል ነጻነት ልዩ በሆኑ ሀሳቦች ላይ በማህበረሰቡ የተመሰረቱ መርሆዎች ናቸው፡፡

ከዚያም በማለፍ አንድ እርምጃ ወደፊት እራመዳለሁ፡፡

አሜሪካ ለሰብአዊነት የመጨረሻ ተስፋ ናት፣ እናም በርካታ ችግሮችን ሊያስከትሉ ከሚችሉ እና በስሜት ከሚነዱ እምባገነን እና አስመሳይ ፖለቲከኞች የሞራል ኪሳራ መጠበቅ አለባት ብየ አስባለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 1/1862 የነጻነት ስምምነት አዋጁ ከመፈረሙ አንድ ወር ቀድም ብሎ ፕሬዚዳንት አብርሃም ሊንከን ለኮንግረሱ መልዕክት ልከው ነበር፡፡ ስለአሜሪካ አንድነት ስለመጠበቅ ንግግር ያደርጉ ነበር፡፡ እንዲህም ብለው ነበር፣ “እንዴት እንደምትጠበቅ ዓለምም እኛም እናውቃለን፡፡“ በመቀጠልም እንዲህ ብለው ነበር፣ “ለባሮች ነጻነት በመስጠት ለነጻ ነጻነትን አረጋገጥን ማለት ነው- ለሰጠናቸው ክብር እና ምንንስ ማስጠበቅ እንዳለብን ግልጽ በማድረግ ማለት ነው፡፡ በቅድስና እንጠብቃለን ወይም ደግሞ በመሬት ላይ ያለችውን የመጨረሻዋን ነገር እናጣለን፡፡“

በምድር ላይ ያለችውን የመጨረሻዋን የተሻለች ተስፋ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛው አስርት ዓመታት ውስጥ ክብር ባለው ሁኔታ ልንጠብቃት እንችላለን? ስለሆነም አሜሪካ የሙስሊሙን እምነት ለሚከተለው አሜሪካዊ ምንድን ናት?

በምድር ላይ ያለች የተሻለች የመጨረሻዋ ተስፋ?

ለሰብአዊነት?

ምናልባትም የሙስሊም እምነትን ለሚከተሉ አሜሪካውያን መልሱ በታላቁ አፍሪካ አሜሪካዊ ገጣሚ በላንግስተን ሁግ “አሜሪካ እንደገና ለአሜሪካ ትሁን” በሚል ርዕስ  እንዲህ የሚሉ የግጥም ስንኞችን ቋጥረዋል፡

የጥንቷ አሜሪካ እንደገና ትምጣ፣

ጋራ ሸንተረሩን ሜዳውን አቋርጣ፣

ውቅያኖሱን ሰብራ ወንዙን አቆራርጣ፣

የጭቅና ምንጩን ድሪቶ ገልብጣ፣

ፍትህን ቀምራ እኩልነት መርጣ፣

የጥንቷ አሜሪካ አዲስ ሆና ትምጣ፡፡

 

ውቢቷ አሜሪካ ህልሞቿን ታሳካ፣

መብት ሳትደፈጥጥ ፍትህን ሳትነካ፣

ሰላም ሳይደፈርስ ቦምብ ሳይንካካ፣

ምድር ሳትናወጥ ሰማይ ሳይንኳኳ፣

አዝመራ እያሸተ አበባ እየፈካ፣

ዕድገትን ታስመዝግ ውቢቱ አሜራካ፡፡

 

ልዕለ ኃያሏ ቁንጮ የሀገራት፣

ለሰላም ለፍትህ የምትቆም በጽናት፣

ላለም ስልጣኔ ታላቅ ድርሻ ያላት፣

ዜጎቿ ባንድነት ዘብ የሚቆሙባት፣

መልካሟ አሜሪካ የሰው ልጆች እናት፡፡

 

ነጻ ህዝብ ይኑራት ነጻ ቤትም ታግኝ፣

ሰላም ዝናብ ይስጣት የሌለው ውርጅብኝ፡፡

 

አሜሪካ ለኔ መች እንዲህ ነበረች፣

በሾህ ባሜከላ ባጥር የታጠረች፣

አሸባሪነትን ቀፍቅፋ የያዘች፣

ቅጥረኛ ጽንፈኛን በውን ያረገዘች፣

ላምባገነን ቆማ ፍትህን የጣሰች፣

በመንታ ምላሷ ቅጥፈት ያነገሰች፣

አስመሳይነትን ፈጥራ የጸነሰች፣

እረ መላ በሉ እባካችሁ ሰዎች፣

የጥንቷ አሜሪካ ወዴት ትገኛለች?

 

ሀገሬ አሜሪካ የህልመኞች ትሁን፣

ሌት ቀን ለሚያስቧት ለማምጣት ዕድገትን፣

ፍቅር ያለበሳት ታላቅ ሀገር ትሁን፡፡

 

ነገስታት በሀሰት ሸፍጥ የማይሰሩባት፣

ሙሰኛ አምባገነን የማይጨፍሩባት፣

የሰው ልጆች መብት የማይጣሱባት፣

የጽንፈኛ ወሬ የማያሸብራት፣

የአሸባሪ ድርጊት የማይታይባት፣

የውሸት አርበኝነት ቦታ የሌለባት፣

ግን መልካም ዕድሎች የተንሰራፉባት፣

እውነት ድንኳን ተክሎ የተቀመጠባት፣

ህይወት ነጻ ሆኖ የሚቦረቅባት፣

የጥንቷ አሜሪካ ከቶ ከወዴት ናት?

የሶርያ ስደተኞችን ለመርዳት ንቁ ተሳትፎ አደርጋለሁ፡፡

እንዲያውም ከዚህም በላይ እ.ኤ.አ የ1981 የፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬጋን የዩ ኤስ አሜሪካ የኢሚግሬሽን እና ስደተኞች ፖሊሲ መግለጫ “ተግባራዊ ማዕቀፍ” ከ5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሶርያውያን ዜጎች ለተፈናቀሉበት ሰብአዊ ቀውስ ምላሽ ይሆን ዘንድ ተግባራዊ እንዲደረግ ሀሳብ አቀርባለሁ፡፡

ይህንን ሁሉ የማደርገው በርዕዮት ዓለም፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በፖለቲካ ትክክለኛነት ወይም ደግሞ በሌላ በምንም ዓይነት ጉዳይ ምክንያት አይደለም፡፡

ሆኖም ግን ይህንን የማደርገው ዘላለምዊ በሆነ መልኩ አንድ ጊዜ ለተነሱ ጥያቄዎች አስፈላጊ የሆነውን ምላሽ ለመስጠት በማሰብ ነው፡፡

ተርቤ በነበረበት ጊዜ ምንም የሚበላ ነገር አልሰጠኸኝም፣ ተጠምቼ በነበረበት ጊዜ ምንም የሚጠጣ ነገር አልሰጠኸኝም፡፡ እንግዳ ሆኘ በመጣሁ ግዜ አላስተናገድከኝም፡፡ ታርዠ በነበረበት ጊዜ አላለበስከኝም፡፡ ታምሜ እና ታስሬ በነበረበት ጊዜ አልጠየቅኸኝም፡፡ በእውነት እንዲህ እልሀለሁ፡ ከእነዚህ ነገሮች አንዳቸውንም ለወንድሞችህ እና ለእህቶችህ ባደረግህ ጊዜ ለእኔ እንዳደረግህ እቆጥረዋለሁ፡፡ 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!         

ህዳር 14 ቀን 2008 .

 

ረሃብ ለምን ደፈረን? ዴሞ ቅጽ 41 ቁ 2 ጥቅምት 2008 ዓ.ም

የአገራችንን ስምና ዝና በማጉደፍ የታወቁት ረሃብና ጠኔ ዘንድሮም ጓዛቸውን ጠቅለው ይዘው አገራችንን እየጎበኙ ነው። ባሁኑ ወቅት 8.2 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ ሲሆን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይህ ቁጥር ወደ አስራ አምስት ሚሊዮን ያድጋል የሚል አስተያየት ጉዳዩን ከሚያውቁ ባለሙያዎች እየተነገረ ነው። በበርካታ አካባቢዎች የቀንድ እና የጋማ ከብቶች በብዛት አልቀዋል በተራበው ሕዝብ ላይም ተመሳሳይ እልቂት ሊደርስ ይችላል የሚለው ስጋት ከፍተኛ ነው። በተለያዩ አገሮች በተለይም በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ድርቅ፤ የዝናም እጥረት፤ የምርት መቀነስ ወዘተ… በየጊዜው የሚከሰት ሲሆን ዜጎች በረሃብና በጠኔ ተሰቃዩ ሲባሉና በዓለም አቀፍ ደረጃ ምጽዋት ሲለምኑ ግን አይታይም። ለምን የሚለው ጥያቄ ሁሉም ላይ የሚያቃጭል ነው። በየጊዜው በአገራችን እየተከሰተ ያለው ድርቅና የዝናም እጥረት ለምን ዜጎቻችንን ለረሃብና ለእልቂት ያጋልጣል? አገራችን በኢኮኖሚ በድርብ አሃዝ አድጋለች መንጥቃለች፤ በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትን አሳይታለች ተብሎ ነጋ፣ ጠባ እየተለፈፈ ለምንድነው አሁንም ምጽዋት ለማኝ የሆነችው? መፍትሔውስ ምንድነው የሚሉት እና ሌሎች መሰል ጥያቄዎች በአዕምሮአችን የሚብላሉና መልስ ማግኘት የሚሹ ናቸው።
ያለመታደል ሆኖ የሀገራቸን አርሶአደር በገዛ አገሩ ላይ እንደ ዜጋ ክብሩ ተጠብቆም ሆነ መብቱ ተከብሮለት አያውቅም። በሚያመርተው የእርሻ ምርት ወገኑን በቀለብ ቀጥ አድረጎ የያዘ ከመሆኑ ሌላ የሀገሩን ሉዓላዊነትና ከብር ለማስጠበቅና ሀገሩን ከውጪ ወራሪዎች ለመከላከል አኩሪ የዜግነት ተግባራትን የፈፀመ ዛሬም እየፈፀመ ያለ የኅበረተሰብ ክፍል ነው። ይህ የአገሪቱ ዋልታና መሠረት የሆነው አኩሪ ዜጋ በተለያዩ ጊዜያት ሥልጣን በያዙ ገዥዎች እንደ ዝቅተኛ ዜጋ እየተቆጠረ፤ መብቱ እየተረገጠና ፍዳውን እየቆጠረ ኖሯል። “የባሰን አታምጣ” እያለ የተለመደ ስቃዩን ችሎ የቆየው ያሳለፈው ስቃይ አልበቃ ብሎት “ዳቦ ከሌለ ድንጋይ ብላ” ከሚሉ ደፋርና ወሮ በላ ካድሬዎች ዘመን ደርሷል። በአፄው ዘመነ መንግሥት በአርሶ አደር ላይ ይፈፀም የነበረውን ግፍ፤ መከራና ስቃይ በውል ያጤኑ፤ አርሶአደሩ ተቸገሮ፤ ተርቦና ተጠምቶ ያስተማራችው ወጣት ተማሪዎችና ምሁራን ” መሬት ላራሹ ለላብ አፍሳሹ” “ዳቦ ለተራበው” የሚለውን መፈክር የትግል አርማቸው አድርገው አገዛዙን ሲቃወሙ የነበሩት የአርሶአደሩ ችግር የጠቅላላ የሀገሪቱ ችግር መሆኑን በውል በማጤን ነበር። በሚያዚያ ወር 1964ዓ.ም ለብዙኃኑ የቆመውን ታጋይ ድርጅት -ኢሕአፓን- የወለደው ይኸው የአርሶ አደሩና ባጠቃላይም የጭቁኑ ሕዝብ ፍዳና መከራ ነበር።
በወቅቱ የነበሩት ተማሪዎች እና የየካቲት 1966ቱ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ አራማጆች መሬት ላራሹ ለላብ አፍሳሹ ብለው ሕዝባዊ መፈክር ያስተጋቡለት፤ በግንባር ቀደምትነት የታገሉለትና ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉበት የመሬት ጥያቄ እስከዘሬ አልተመለሰም። አርሶአደሩ ዛሬም የመሬቱ ባለቤት አልሆነም። የመሬት ጥያቄ በአገራችን በአግባቡ መልስ እስካለገኘ ድረስና መሠረታዊ የሆኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የፍትህ ጥያቄዎች በአግባቡ እስካልተፈቱ/እስካልተመለሱ ድረስ አገራችን ከመከራ፣ ከችግርና ከረሀብ ተላቃ በኢኮኖሚ፣ በልማትና በሥልጣኔ ጎዳና መራመድ የምትችል አይሆንም።
ኢትዮጵያ አገራችን የእለት ጉርስና መጠላያ የሌለው ሕዝብ የሚተራማስባት የምድር ሲኦል ሆናለች። ሁሉም የኢኮኖሚ የማኅበራዊ የአገልግሎት ዘርፎች ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። በምግብ እህል ራሰን መቻልና መሠረታዊ የሆኑ የፍጆታ እቃዎችን በአገር ውሰጥ ማምረት የሚያስችሉ ሁኔታዎች አልተፈጠሩም። ከጊዜ ወደጊዜ ተለዋዋጭ የሆነው የዋጋ ንረት የሠራተኛውን የነፍስ ወከፍ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ስለጎዳው ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነው ሥራ አጥ የጥቂቱ አምራች ጥገኛ በመሆኑ የተነሳ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ተመጽዋች/ረሀብተኛ ለመሆን ተገደዋል። ወያኔ ከጥቂት ከበርቴዎችና ከባእዳን ባላቱጃሮች ጋር የጥቅም ተካፋይ በመሆን መሬትና የአገሪቱ የተፈጥሮ ሀብት በጥቂቶች እጅ እንዲገባ በማድረጉ የተነሳ በሀብታምና በደሀው መካከል ያለው ልዩነት በሚያስደነግጥ ደረጃ እጀግ ሰፍቶ ይገኛል።
የደርግ የእዝ ኢኮኖሚ የወደቀ ቢመሰልም መልኩና ስልቱን ለውጦ ዛሬም እንደትናቱ የአገሪቱ ዋና ዋና የኢኮኖሚ አውታሮች በወያኔ ቡድን በሞኖፖል (በወያኔ የእዝ ኢኮኖሚ) ተይዞ ይገኛል። ለአገሪቱ ኢኮኖሚ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ የማምረቻና የማከፋፈያ ድርጅቶች ወያኔ በፈጠራቸውና በሚቆጣጠራችው የግል ድርጀቶች ቁጥጥር ሥር ገብተዋል። የጥምር አሃዝ እድገት አሳየ እየተባለ በወዳጆቹ ይዘፈንለት እንጅ ወያኔ በየወቅቱ የሚቀይሳቸውና በሥራ ላይ የሚያውላቸው የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች እድገትን የሚያስገኙ ሳይሆን ኢኮኖሚውን የባሰ ችግር ውሰጥ የሚከቱ ሆነው ተገኝተዋል። የነጣና የዕለት ጉርስ የሌለው ሕዝብ ቁጥር ወደ 46 ሚሊዮን ይደርሳል። ከባድ በሆነ የድህነት አረንቁዋ ውስጥ ካሉት ኢትዮጵያዊያን መካከል ወደ ሰላሳ ስምንት ሚሊዮን የሚጠጉት በገጠሩ አካባቢ የሚኖሩ ሲሆን ቀሪዎቹ የከተማ ነዋሪዎች ናቸው። የወያኔ ባለሥልጣናት ድርቅ እንጅ ረሃብ የለም በማለት በተደጋጋሚ የሀሰት ጥሩምባቸውን ቢያጮሁም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በገባው ድርቅና ተያይዞ በተከሰተው ረሃብ ምክንያት በተለያዩ ቦታዎች የቀንድና የጋማ ከብቶች መሞታቸው ሲታወቅ በቅርቡ ረሃቡ የህጻናትን ህይወት እየቀሰፈ መሆኑ ተዘግቧል። እስካሁን ድረስ እስከ 8.2 ሚሊዮን የሚደርስ ሕዝብ በረሃቡ እየተጠቃ ነው የሚል ግምት የተሰጠ ሲሆን በተባበሩት መንግሥታት አዋቂዎች ዘገባ መሠረት ከሚቀጥለው ጥር ወር ጀምሮ የረሃብተኞች ቁጥር ወደ 15 ሚሊዮን ይጠጋል ተብሎ ተገምቷል። የሕዝብ ቁጥር በፍጥነት እያደገ በሄደበት ሁኔታ የምግብ አቅርቦቱ ተመጣጣኝ ካልሆነ ከድርቁ በተጨማሪ ሕዝብን ለረሃብና ለጠኔ የሚዳርግ መሆኑ ግልጽ ነው። ከመቶ ሰባ አምስት(75%) የሚሆነው የገጠሩ ነዋሪ ሕዝብ ዛሬም በንፁህ የመጠጥ ውሃ እጦት ይሰቃያል። የጤና ጉዳይ ከተነሳም አምራቹ ኃይል ለወባ፣ ለሳንባ ነቀርሳና ለሌሎች ተላላፊ በሽታዎች የተጋለጠ በመሆኑ በምርት ላይ የሚያደርሰው ችግር ቀላል አልሆነም።
በአገራችን ለሚታየው መጠነ ሰፊ ድኽነትና እየተመላላሰ ለሚጎብኘን ረሀብ በዋነኛነት ተጠያቂው የመልካም አስተዳደር እጦት ነው። የኋላቀርነታችንና የድኽነታችን ምንጭ የአስተዳደር ድከመት፤ የአመራር ጉድለትና የፍትህ መዛባት መፈራረቃቸው ለመሆኑ የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ዘመናትን አስቆጥሯል። እነሆ ዛሬም ቢሆን ታታሪና ጠንካራ ሠራተኛ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የድካሙን ፍሬ መጠቀምና መቋደስ ያልቻለው ከጎኑ የሚቆም፣ የሚረዳው፣ አይዞህ የሚለውና የሚያስተባበረው መሪ ባለማግኘቱ ነው።
ወያኔ ከፍጥረቱ ጀምሮ በየጊዜው በሚፈፅማቸው ፀረ-ሕዝብና ጸረ-አገር ተግባራት የሕዝብ አመኔታን ያላገኘና ከሕዝብ የተነጠለ መሆኑ ግልጽ ነው። በሕዝብ ላይ ያለው የበቀል ስሜትና ጥርጣሬ ከፍተኛ በመሆኑ ሕዝብ በፖለቲካው ብቻ ሳይሆን በልማት አጀንዳዎች ላይ በነፃነት እንዳይመክርና እንዳይሳተፍ አድርጓል።
አገዛዙ በየጊዜው የሚያወጣችው የኢኮኖሚ መመሪያዎችና ፖሊሲዎች እንዲሁም እነዚህኑ ተግባራዊ ለማድረግ የሚወስዳቸው እርምጃዎች የሚያረጋግጡት ይህንኑ እውነታ እንጂ፣ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ያላቸውን ንዋይ በኢንዱስቲሪና ልማት ዘርፍ እንዲያውሉ የሚያበረታታ አይደለም። የወያኔ አገዛዝ ከታሪክና ከስህተት ለመማርና ተምሮም ለመስተካከል ባህርዩና ተፈጥሮው የማይፈቅድሉት በመሆኑ በየጊዜው ለሚከሰቱ እንደ ድርቅና ረሃብ ለመሳሰሉት ችግሮች ዘላቂ የሆነ መፈትኄ ከመስጠት ይልቅ ተፈጥሮንና ለጋሽ አገሮችን ሲኮንና ሲያወግዝ ይደመጣል።
በዓለማችንም ሆነ በሀገራቸን የድርቅ ክስተት የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው የተፈጥሮ ባሕርይ ነው። ድርቅ ጥንትም ሲከሰት የነበር ዛሬም ሆነ ወደፊትም ሊከሰት የሚችል የአየር ለውጥ ነው። ለድርቅ መንስኤ ናቸው ተብለው ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ውስጥ፡- የሕዝብ ቁጥር መጨመር፤ ለእርሻ ተግባር የሚውለው መሬት ለምነት መቀነስ፤ ከኋላ ቀር የአስተራረስ ዘዴ የተነሳ ከእርሻው ክፈለ-ኤኮኖሚ የሚገኘው የምርት ውጤት ሕዝቡን መመገብ አለመቻል- የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ፤ በአንድ ሀገር ውስጥ ለሚከሰት ረሀብ ግን ምክንያቱ በሥልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የሚከተለው የተሳሳተ የኢኮኖሚና የልማት ፖሊሲ መሆኑ ጥርጥር የለውም።
ወያኔ መሬትን በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያደረገው በዘር ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ፖሊሲውን ለማራመድና ሕዝቡን በመያዣነት ለማፈንና ለመቆጣጠር ነው። በዚህ ጨቋኝ ፖሊሲ የተነሳ ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ለረሐብና ለበሽታ ተጋልጠዋል። መሬት በአገዛዙ ቁጥጥር ሥር በመዋሉ ታታሪውና አምራቹ አርሶ አደር በትጋት ወደልማቱ እንዳያተኩር ትልቅ ጋሬጣ ደቅኖበታል። ዛሬ በወያኔ ብልሹ ፖሊሲ ምክንያት የብር ዋጋ እጅግ በመቀነሱ ለዘመናዊ እርሻም ሆነ ለፋብሪካ የሚሆኑ መሳሪያዎችንና ጥሬ እቃዎችን ከውጪ ለማስመጣት ለሚጥሩ ሀገር በቀል ባለሃብቶች የውጭ ምንዛሪን ማግኘት የሰማይን ያህል ርቆባቸዋል። የሀገር ውስጥ ባለሀበት ከባንክ ተበድሮ የልማት ሥራ እንዳያካሂድ ወለዱ ንሮበታል። በአንጻሩ የወያኔ ባለሥልጣናት የአገሪቱ አንጡራ ሀብት የሆነውን ለም የእርሻ መሬት ሕዝቡን እያፈናቀሉና እያባረሩ ለውጪ ባላሀብቶች በርካሽ በመቸብቸብ ከፍተኛ ገንዘብ በመዝረፍ ላይ ይገኛሉ።
በአገር ውስጥ ባንኮች በአነስተኛ ወለድና ከቀረጥ ነጻ የሆነ ኢንዱስትሪን ማስፋፋት በሚል ፌዝ የቻይና፣ የቱሪክ፣ የሕንድ፣ የፓኪስታንና የአረብ፣ … ወዘተ ቱጃሮች በቀላሉ አገሪቱን እንዲቀራመቱ በሩን ከፍቶላቸዋል። ወያኔ በዚህ ብቻ ሳይገታ አገራችን ካላት አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሃያ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ (1,127,200) እስክዌር ኪሎ ሜትር የቆዳ ሥፋት መሬት ውስጥ ሥድሳ-አራት (64,000) ሺህ እስኩዌር ኪሎሜትር (6%) የሚሆነውን መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ ሰጥቷል። ይህ ለባዕድ የተሰጠው መሬት ቢያንስ ከሁለት መቶ (200) ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ የግዛት ቁጥጥር ስር የቆይ ለመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመሰከረ ነው።
በርካታ የዓለም አቀፍ የምርምር ተቋማትና ጥናቶች እንዳረጋገጡት ከሆነ አገራችን በከርሰ ምድሯ በሚገኝ ሀብትም ሆነ ከምድር በላይ ባላት የተፈጥሮ ሀብት የበለፅገችና በቂ ክምችት ያላት አገር ናት። ያለመታደል ሆኖ ግን በዓለም ላይ ስሟ የሚጠራው በድኽነትና በረሀብ ነው።
በመሠረቱ ድርቅ ብቻውን ለረሀብ አይዳርግም። ድርቅ ረሀብን የሚወልደው የኅብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መሠረት ደካማ ሲሆን ብቻ ነው። ጠንካራ የኢኮኖሚ መሠረት ያላቸው፣ በማኅበራዊ ተቋምና አገልግሎት በሚገባ የተደራጁ አገሮች ድርቅን ሳይሆን የድርቅን ተጽእኖ መቋቋም ችለዋል። በድኽነት ላይ የተመሠረተ ኑሮና ከእጅ ወደ አፍ የማምረት ዘይቤ በአንድ ወቅት የሚደርስ የሰብል መበላሸትን ወይም መቀነስን ሊቋቋም የማይችል መሆኑ ግልጽ ነው። አንድ የድርቅ ወቅት ሕዝቡን በስደት ለመፈናቀልና ለእልቂት ይዳርገዋል። በአንጻሩ ጠንካራ የኢኮኖሚ መሠረት ያለው፤ ከእጅ ወደአፍ ከሆነ አምራችነት የተላቀቀ፤ ከዓመት ልብስና ከእለት ጉርስ በብዙ እጅ የበለጠ ምርት የሚያመርት ሕዝብና ለክፉ ቀን የሚሆነውን ጥሪት ያዳበረ ኅብረተስብ በአንድ ወይም በሁለት ዓመታት በሚከሰት ድርቅ ለረሃብና ለሞት አይዳረግም። በመሆኑም የረሀብ መሠረታዊ ምክንያት ድርቅ ሳይሆን ድኽነትና ኋላቀርነት ነው። የድኽነትና የኋላቀርነት ዋና መንስኤ ደግሞ የዴሞክራሲና የመብት አለመረጋገጥ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር፣ የፍትህ እጦት ነው ።
ዛሬ በአገራችን በያመቱ በረሃብ አለንጋ የሚጠበሰውና የሚሰቃየው ወገናችን የመሥራት ችግር ኖሮት ወይም ችግርን የመቋቋም ችሎታ አንሶት አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ እጅግ ታታሪና የፈጠራ ችሎታም ያለው ሕዝብ ነው። የሀገሪቱ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ አስቸጋሪ በሆነበት ተራራማና ገደለማ ቦታዎች እንኳን ሳይቀር ወገቡን በገመድ ጠፍሮ ከገደል ላይ ተንጠልጥሎ፤ ቆፍሮ ለማምረት የሚጥርና የሚለፋ በራሱ የሚተማመን ኩሩ ሕዝብ ነው። ለም አፈሩ በጎርፍ ተጠርጎበት ማምረት ሲያቅተው ከዳገት የወረደውን ደለል አጠራቅሞ አፈሩን በማልማት ለማምረት የሚችል ትጉ ሕዝብ ነው። ሰብሉ በዱር አራዊትና በአእዋፍ አንዳይበላበት ማማ ሰርቶ ሲከላከል የሚውል፤ ዝናብና ቁር ሳያግደው ሲንከራተት በወባና በተስቦ በሽታ እየተሰቃየ ግን በደካማ ጉልበቱ እንኳ አርሶ ለመብላት የሚጥር ታታሪ ሕዝብ ነው።
ሕዝባችን ለረሃብ የተዳረገው የሀገሪቱ የተፈጥሮ ሃብት ደሀ ሆኖም አይደለም፡፡ ለእርሻ አመቺ ከሆነው አሥራ ስደሰት (16) ሚሊዮን ሔከታር መሬት ውስጥ ሥራ ላይ የዋለው በጣም ጥቂቱ ነው። ታታሪና አምራች ሕዝብ እያለን፤ ሥራ ላይ ያልዋለ የሀብት ምንጭ ሞልቶ ለምን ተራብን? ብሎ መጠየቅ አግባብነት ያለው ጥያቄ ነው። መልሱም ግልፅና አጭር ነው። የአገራችን አርሶ አደር የሚያግዘው ሳይሆን የሚጫነው፤ የሚሰጠው ሳይሆን የሚነጥቀው ስለበዛበት ነው። አማራቹ ኃይል የተረጋጋ ህይወት ኖሮት ኑሮን ለማሻሻልና ቤተሰቡን በሚገባ መግቦ ለማሳዳር ለአንዴም ፋታ ያገኘበት ወቅት አለ ለማለት ያስቸግራል። በገዥዎቹ የሚወጡት የኢኮኖሚ/የእርሻ ፖሊሲዎች በሙሉ ራስ መቻልን፤ በራስ መተማመንና ምርታማነትን የሚያበረታቱ አልነበሩም አሁንም አይደሉም።
የሚቀየሱት የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ሁሉ የሕዝቡን የአደጋ መከለከያ ስልቶች የሚያዳክሙ ምርትንና ምርታማነትን የሚያግቱ ከመሆናቸውም አልፎ ሕዝብ በመንግሥት ላይ፤ መንግሥት በሕዝብ ላይ እምነት እንዳይኖረው ስለተደረገ፤ ሕዝቡ ለድኽነትና ለችግር ተጋልጧል። በድርቅ ተፅእኖ በቀላሉ የማይደፈረው አካባቢ ዛሬ በአነሰተኛ የሰብል መጥፋት የተነሳ ሕዝቡ ለከፋ ረሀብ ተዳርጓል። ለክፉ ቀን ብሎ እህል በጉድጓድ ያስቀምጥ የነበረውና፤ ለዘር ይሆነኛል ብሎ ያስቀመጠውን እህል መብላት እንደ “እርም” ይቆጥር የነበረው አርሶ አደር በአገዛዙ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የተነሳ ዛሬ ጥሪት እንኳ እንዳይኖረው ተደርጓል።
አረሶ አደር ሆኖ የኔ ነው የሚለው የግል ማሳ፤ ገበሬ ሆኖ ለማረስ የሚያስችለው ጥማድ በሬ የለውም። አርሶ አደሩ ዛሬ የአገዛዙ ጭሰኛ ሆኗል። እነዚህና ከሌሎች የተሳሳቱ የአገዛዙ የፖሊቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፖሊሲዎች ጋር ተዳምረው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ኢኮኖሚ መቅኖ ከማሳጣታቸውም በላይ ሕዝቡን ለስደት፣ ለረሀብና ለበሽታ ዳርገውታል።
ወያኔ በሕዝባችን ላይ ግፍና ደባ እየፈጸመ ያለው በነፃ ኢኮኖሚ መርህ ስም ነው። በነፃ የገበያ ኢኮኖሚ ስም የሀገሪቱ ሀብት ጎሳዊ ለሆነ አድሎአዊ ጥቅም ውሏል። ወያኔ ሀብትን ወደግል ይዞታ ማዛወር በሚል
ሰበብ ከውርስ ባልተለየ ሁኔታ የሕዝብን ሀብትና ንብረት በምርጥ አባላቱና በዙሪያው በኮለኮላቸው ተለጣፊ ድርጅቶች አባሎችና ቤተሰቦቻቸው ስም በእጁ አሰገብቶአል።
በልማቱ መስክ ለራሱና ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ ሚና ሊጫወት የሚችለው የተማረና በሥራ ልምድ ተመክሮን ያካበተው የሰው ኃይል ከሥራው እየተባረረና እየተሰደደ በመስኩ እውቀትና ልምድ በሌላቸው የአገዛዙ ካድሬዎች እንዲተኩ ተደርገዋል።
ወያኔ በሚከተለው የጎሳ ፖለቲካ (የአፓርታይድ ፖሊሲ) የተነሳ የሀገሪቱ ዜጎች በሙያቸው፤ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው በሀገራችን የተለያዩ ክፍሎች እንዳይዘዋወሩና በፈቀዱት የሥራ መስክና አካባቢ እንዳይሰሩ ማነቆ በመሆኑ ለሥራ አጥነትና ለረሀብ ተዳርገዋል። አገዛዙ ከተወሰነ ክልል ውጭ ባሉ የሀገሪቱ ክፍሎች የልማት ሥራዎች እንዳይሰሩም ሆነ መዋዕለ ነዋይ እንዳይፈስ የማይሽርበው ሴራ የለም። በሌላ በኩል ደግሞ ለመዋዕለ ንዋይ አቅርቦት እየተባለ የተለያዩ ጥቅሞችን በስውር ዘዴ በማግኘት የወያኔ ባለሥልጣናት በብድር ስም በገፍ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡት ገንዘብ አገሪቱን ከፍተኛ እዳ ውስጥ ዘፍቋታል።
የከተማንም ሆነ የገጠር መሬትን በባላቤትነት በሞኖፖል በመያዝ ሕዝቡ የአገዛዙ ጭሰኛ እንዲሆን ከማደረጉም በላይ በሊዝ ፖሊሲ ስም የሀገሪቱ አንጡራ ሀብት የሆነውን መሬት ለባዕዳን አሳልፎ በመሸጡ ኢትዮጵያዊው ዜጋ በአገሩ የበይ ተመልካች እንዲሆን ተገዷል። ይህ አጥፊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሆን ተብሎ ሀገሪቷንና ሕዝቡዋን በመግደል ወያኔን በሥልጣን ላይ ለማቆየት እና የቡድንና የጎሳ ፍላጎትን ለማሟላት በረዥሙ ታቅዶ የተዘጋጀ ሲሆን በዚህ ፖሊሲም ተጠቃሚዎቹ ወያኔና ባዕዳን ኃይላት መሆናቸው በገሃድ የሚታይ ነው።
የወያኔ አገዛዝ ለባእዳን ጥቅም ያደረ ከመሆኑም በላይ በየጊዜው ከባእዳኑ ጋር ከሕዝብ ጀርባ በሚያደርጋቸው ውሎችና ስምምነቶች የተነሳ በሕዝብ ላይ የሚደርሰው ችግርና መከራ ተባብሶ ይገኛል። የአገራችን የተፈጥሮ ሀብት የሆኑት ብርቅዬ የዱር እንስሳት፣ የተፈጥሮ ደኖችና የውሃ ሀብቶቻችን ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጠዋል። በዚህም የተነሳ ለዘለቄታው በአገራችን የአየር ንብረት ላይ ሊከተል የሚችለውን አሉታዊ ሰጋት በመስኩ የተሰማሩ ባለሙያ የሆኑ ምሁራን የሚያወጡዋቸው ጥናቶች ያመለክታሉ።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በዓለም ከመጨረሻዎቹ ተርታ ድኻ ተብለው ከተመደቡት አገሮች መካከል አንዱዋ ናት። ሰማንያ ከመቶ (80%) የሚሆነው ሕዝብ የሚተዳደረው በእርሻው ኢኮኖሚ ዘርፍ ሲሆን መሬት በመንግሥት ስም በወያኔ አገዛዝ ቁጥጥር ስር ስለሆነና አርሶ አደሩ መሬቱን የኔ ነው ብሎ እንደ ልጁ ተንከባክቦ እየጠበቀ ምርታማንቱን ለማሳዳግ ባለመቻሉ የእርሻው ክፍለ ኢኮኖሚ የአምራቹን አረሶ አደርም ሆነ የከተማውን ነዋሪ የምግብ ፍጆታ የሚያሟላ ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም ዋና ችግር አርሶ አደሩ በሚያርሰው መሬት ላይ የይዞታ መብት ብቻ ሳይሆን የባለቤትነት መብት ማለትም መሬቱን የመሸጥ፣ የመለወጥ፣ የማውረስ፣ በዋስትና የማስያዝ፣ …ወዘተ መብቱን ማወቅና በሕግ ማረጋገጥ ባለመቻሉና የአገዛዙ/የወያኔ ጭሰኛ በመሆኑ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል።
ከዚህ አዙሪት መውጣት የሚቻለውና የአገሪቷን የልማት እርምጃ አፋጥኖ ሕዝቡን ከድኽነትና ከረሃብ ማላቀቅ የሚቻለው በቅድሚያ በሀገሪቱ የሕዝብን መብት የጠበቀና ሕዝብን ያሳተፈ ዴሞክራሲያዊ የፖሊቲካ ሥርዓት እውን ሲሆንና የሀገርንና የሕዝብን ብሔራዊ ጥቅም ያስቀደመ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተነድፎ ተግባራዊ ሲሆን ነው ብሎ ኢሕአፓ ያምናል። የሕዝብ መሠረታዊ ነፃነትና መብት መከበርና የኢኮኖሚ እድገት ተነጣጥለው የሚታዩ አይደሉም፤- ሁለቱ ተደጋጋፊዎች እንጅ ተፃፃራሪዎች አይሆኑም። በነፃ የመንቀሳቀስ፤ የማሰብና ሃሳብን ወደ ተግባር የመቀየር ነፃ መብት ከሌለ የራስ አነሳሽነትንና አፋልቂነትን መሠረት ያደረገ የልማት እንቅስቃሴ ከቶ የሚቻል አይሆንም። ወያኔ በዘር ላይ የተመሠረተ የክልል አገዛዝን አዋቅሮ ባለበት ሁኔታ በጋራ ወይም በኅብረት ላይ የተመሠረተ ብሔራዊ/አገራዊ እድገትና ብልፅግና ከቶ ሊመጣ የማይችል መሆኑን ኢሕአፓ ደጋግሞ ገልጿል።
ስለሆነም ድርቅን እንቆጣጠራለን የሚል ቅዠት ባይኖረንም በድርቅ ሳቢያ እየገባ በየጊዜው ወገኖቻችንን የሚጨርሰውን ረሃብ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት የወያኔን አፋኝ ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ በተባበረ ክንድ እናስወግድ እንላለን።
ረሃብ ከአገራችን ይጠፋል !
ሕዝብ በተባበረ ትግል መብቱን ያስከብራል !

 

በሞት ጥላ መካከል ብሄድ እንኳን ክፉን አልፈራም !!! የሀብታሙ አያሌው መልዕክት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት

Millions of voices for freedom - UDJ's photo.November 21,2015
የልቤን ምጥ ልፃፈው ብዬ ደጋግሜ ብዕሬን ይዤ ወረቀቱ ላይ ብፅፍም እንደተራበው ወገኔ ሆድ ብዕሬ ባዶ ሆኖ ቀለም አልነጥበው አለ፡፡ በቅሊንጦ ማጎሪያ ቤት ሰማይ ስር ነፍሴ ሀዘን አቆርዝዛ በማይገፉ ቀንና ሌሊቶች ውስጥ ባዘነች፡፡ ለወትሮው ወገኔ እንደከፋው ስሰማ እንደወፍ በርሬ ችግሩን ልጋራው ከመሃሉ እደርስ ነበር፡፡ ዛሬ ግን የህዝቤ ስቃይ ወደ ሰማይ ጉኖ በጠኔ ሲንበረከክ እንደ ጅብራ ተገትረው በማያንቀሳቅሱኝ ወታደሮች ተከብቤ በጭንቀት እየባዘንኩ ከመጠውለግ በቀር አደርገው ነገር አጣሁ ፡፡ ወይ ሀገሬ!!! ወይ ወገኔ!!!

….. እመነኝ እንዳልኩህ አሁንም እመነኝ … አሁንም እመነኝ !!! እመነኝ ደርግ ወድቋል ኢህአዴግ ይወድቃል፡፡ ዛሬ በአሳሪዎቼ ጡጫ ተደቁሼ፤ ድምፄ በኢትዮዮጵያ ሰማይ ስር ባይሰማም የታገልኩለት እውነት ወደ አደባባይ ወጥቶ ህዝቤ የነፃነት ሻማ እሚጎናፀፍበት ቀን እንደሚመጣ ግን ጥርጥር የለኝም፡፡ 

የልጄ ናፍቆት የሚስቴ ስቃይና እንግልት የእህቶቼ መባከን እና መሳቀቅ አቅሜን ሲፈታተኑት በማዕከላዊ የስቃይ ማማ ስር ጉዳት ያተረፉት ሁለቱ ኩላሊቶቼ የቀን ከሌት ስቃዬን ሲያረዝሙት የነከስኩት ጥርሴ ጉልበቴ አበርትቶ የነፍሴን መዛል ብሸሽግም… ዛሬ ግን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖ የታገልኩለት ህዝብ በረሃብ ጠኔ እየተመታ በሞት ጥላ መንበርከኩን ስሰማ ነፍሴ በውስጤ አለቀች እናም የልቤን ሀዘን እፅፍ ዘንድ ሞከርኩ… ሞከርኩ ግን አቃተኝ….
ጃርት እንደ በላው ዱባ በየቦታው የተፈረካከሰው ፓለቲካችን ዛሬም እርስ በእርስ እየተሸነቋቆጠ ይቀጥላል ወይስ ወገኑን ለመታደግ እንኳ አንድ ይሆናል? ነፍሴ በየእለቱ የምትሟግተኝ ጥያቄ ነው ፡፡ ሳንተባበር ጉልበት አንድ ሳንሆን ኃይል ከወዴት እናገኝ ይሆን ? የአምባገነኖች ጡጫ እየደቆሰን ረሃብ በየዘመኑ የሚቆላንስ እስከመቼ ነው? በእውነቱ በሀሳብ ብዙ ባከንኩ አገኝለት ዘንድ ግን መልስ አጣሁ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር እና የኢትዮጵያ ህዝብ መልስ አጥተው አያውቁም እና ተስፋዬ ፈፅሞ አይመክንም፡፡
እናም ያገባናል ለሚሉ ሁሉ እላለሁ የኢትዮጵያ ገፅታ የሚገነባው በየሰርጡ በጠኔ የሚሞቱ የወገኖችን እሬሳ በመደበቅ እንዳልሆነ ካሳለፍናቸው ክፉ ጊዜያት ተምረን ባለን አቅም ተረባርበን ወገኖቻችንን ለመታደግ እንበርታ እላለሁ…!!! በአዲስ አበባ፤ በባህር ዳር፤በአርባ ምንጭ፤ በጎንደር፤ በደሴ፤ በአዳማ፤ በአዋሳ፤ በወላይታ ህዝብ በሚንቀለቀል የለውጥ ፍላጎት ድምፁን ባሰማባቸው ሰላማዊ ሰልፎች… ‹‹ኢህአዴግ ከታሪክ ይማር፤›› ‹‹አምባገነኖች ባሉበት ሀገር የጀግና ሞቱ እስር ቤት ነው ፤›› ‹‹ታጋይ ይታሰራል ትግሉ ይቀጥላል፤ ›› ‹‹ እጃችን ባዶ ነው እነዚህ አምባገነኖች ነገ አሸባሪ ይሉናል›› ፤ ‹‹እመነኝ ደርግ ይወድቃል ኢህአዴግም ይወድቃል›› ማለታችንን ….. በእርግጥም ልክ ነበርን፡፡ ዛሬ አሸባሪ ተብለን ከትግል አጋሮቼ ከዳንኤል ሺበሺ ፤አብርሃ ደስታ ፤ የሺዋስ አሰፋ ፤አንዷለም አራጌ፤ ተመስገን ደሳለኝ ፤እስክንድር ነጋ ፤ ወዘተ…. ስፍር ቁጥር ከሌላቸው ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ጋር የነፃነት ቀንን እየናፈቅን በእስር ቤት አለን ፡፡ የፍርድ ቤት ድራማውም ተጠናክሮ ቀጥሏል ፍርድ ቤቶችን ከጀርባ ቆመው የሚዘውሩ በቀጭን ትዕዛዝ ማረሚያ ቤቶችን የሚያሽቆጠቁጡ፤ በፍትህ ስም የሚቀልዱ ፓርቲዬን ያፈረሱ፤ የህዝቤን ተስፋ ለማምከን ቀን ከሌት የሚደክሙ የካዛንቺሱ መንግስቶች እጃቸው የሚያጥርበትን ቀን አብዝተን እንናፍቃለን ፡፡
በእውነት እላለሁ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ ክፉን አልፈራም !!!

“የየጁ ደብተራ…” በኤርሚያስ ለገሰ

ermias copy
ከቅርብ አመታት ወዲህ በአከባበር እየተለወጠ የመጣውን የህውሀት እና ልጆቹን ልደት አጨንቁሮ ለተመለከተ ብዙ ነገሮችን መናገር ይችላል። በልሙጡ ለሚያይ ሰው የብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴግ የልደት በአላት ” መወድሰ ህወሀት” እየሆኑ መሔዳቸውን በቀላሉ መታዘብ ይችላል። ህውሀቶች የየካቲት 11 እና እሱን ተከትሎ የነበሩት ሳምንታት አልበቃቸው ብሎ ህዳር 11 ( የኦህዴድ እና የሐይለማርያምን ልደት ቀን ረሳሁት) በቤቢ ሻወርነት እየተጠቀሙበት ነው። ርግጥ ነው ህውሀቶች ወገባቸውን ይዘው ” እኛ በልጆቻችን ውስጥ አድረን ቡራኬያችንን ብንወስድ እናንተን ለምን አሳከካችሁ?” እንደሚሉን ይገባኛል። ባያሳክከን ጥሩ ነበር። ፈር የሳተው ቡራኬ በኢትዬጲያ ህዝብ ላይ እያሳረፈ ያለው ጫና በአይናችን ላይ እየሔደ አላሳከከንም ማለት እንደ ብአዴን አባላት ቧልት ስለሚሆንብን ነው። እናም ቢያንስ የብአዴን አባላትን የውስጥ ጩኸት እኛ ብንጮኸው ምስጋናቸው ዘግይቶም ይደርሰን ይሆናል።

1• ” ከማን አንሼ!”
ብአዴን በዘንድሮው ልደቱ የማንነት ቀውስ በፈጠረው ምክንያት ያልሆነውን ሆኖ መታየት ፈልጓል። ያልሆኑትን ሆኖ የመታየት ጉጉት የመነጨው በተለያየ ምክንያት ሊሆን ይችላል። የመጀመሪያው ምክንያት ባለፈው የካቲት ህውሀት የተመሰረተበት በአል ከደደቢት (መቀሌ) እስከ ሞያሌ፣ ከጐሬ እስከ ደወሌ፣ ከሞቃዲሾ እስከ ሎስ አንጀለስ በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ነበር። በልደት በአሉ በኢትዬጲያ ምድር ታይተው የማይታወቁ አንፀባራቂ ገድሎች ተደምጠዋል። የህውሀትን ታላቅነት የሚያስተጋቡ ውዳሴዎች ተሰምተዋል። ለህዝብ የሚቀርብ እዚህ ግባ የሚባል ሀሳብ ማመንጨት የተሳነው ህውሀት አልፋ እና ኦሜጋውን ያለፋት መንግስታት ሲረግምና ሲያወግዝ ተስተውሏል። የኢሳት ባልደረባ የሆነ ጋዜጠኛ ወዳጄ ሁኔታውን ለመግለጵ የተጠቀመበት ቃል በህሊና ግርግዳዬ ላይ ተለጥፋ ቀርታለች። ጋዜጠኛው ” የየጁ ደብተራ ፣ ቅኔው ቢጐድልበት ቀራርቶ ሞላበት” ነበር ያለው።የህውሀት ልደትን ለመዘከር ወደ ደደቢት የተጓዘው እንግዳም ከብዙዎች ግምት በላይ ነበር። ታዳሚዎች የራሳቸውን አለም ፈጥረው በፈንጥዝያ ባሕር ውስጥ ሲዋኙ ነበር። የሀገሪቱን መንበረ ስልጣን ለብቻቸው የተቆጣጠሩት ህውሀቶች ” ሀገሬን አልረሳም!” በሚለው ተወዳጅ ዘፈን ሲጨፍሩ የተመለከቱ ደግሞ እስከ ዛሬም ከመገረም እንዳልወጡ አጫውተውኛል። በተለይም የጫካ ዘመኑን ” እንበር ተጋዳላይ!” በሚለው ቀስቃሽ ዘፈናቸው ያሳጠሩት ዘፋኞች ተቀምጠው ” ሀገሬን አልረሳም!” በሚል ኢትዬጲያዊ ዜማ መፈንጠዙ ከመጋረጃው በስተጀርባ ያለውን ለማወቅ አያዳግትም። እነ አቦይ ስብሀት ከዘመናት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሸራተን ያገኙትን የዘፈኑ ባለቤት ” ስማ አንተ! …” ( ያልጨረስኩት ቃሉን ብጠራ በጣም አስቀያሚ፣ ኢትዬጲያ ብሆን ደግሞ ሶስት ወር ስለሚያሳስር ነው) …ለማንኛውም ሽማግሌው ስብሀት ” ስማ አንተ…”በማለት ያንቋሸሹትን ሰው እንዲዘፍን ሲያዙት የንቀት ደረጃቸውን የሚያሳይ ነው።
እንደዚህ አይነት መጠኑ ለግምት የሚያስቸግር ድግስ እና ሽብረቃ ያለበት የልደት አከባበር ያስቀናል። ያልሆኑትን ሆኖ በልጦ ለመታየት ፍላጐት ማሳደሩም አይቀርም። ያውም በ11% !!…ስለዚህ ብአዴን ይህን ማድረግ ነበረበት። የአማራ ህዝብ በግዴታ ገንዘብ ማዋጣት አለበት። መዋጮው የክልሉ ተወላጆች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም መገደድ ነበረባቸው። ባጃጆች የበአሉ ማድመቂያ መሆን ነበረባቸው። የመንግስት ሰራተኛው የስራ ዋስትናውን በመያዣነት አስይዞ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ነበረበት። ጡሩንባ እና ርችት የባህርዳርን ሰማይ ማድመቅ ነበረበት!
2• የህሊና እዳ!
ብአዴን ከግማሽ ቢሊዬን ብር የሚጠጋጋ ብር አውጥቶ ልደቱን በሚያከብር ሰአት ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ አለምን ያስደነገጠ ሆኗል። ከ15 ሚሊዬን የሚሆኑ ዜጐቻችን የሚላስ የሚቀመስ ባጡበት ሰአት ይህን ያህል ገንዘብ አውጥቶ ልደት ማክበር ከታሪክ ለመማር ዝግጁ ካለመሆን የመጣ ነው። ንጉሱ ይህን አድርገዋል። ደርግም አድርጓል። ህውሀትም በብአዴን በኩል እያደረገው ነው። እዚህ ላይ እርግጠኛ መሆን የሚቻለው ችግሩ የተከሰተው ህውሀት እውነተኛ ልደቱን በሚያከብርበት የካቲት ወር ቢሆን ኖሮ አስረሽ ምችው ዙሩ አይከርም ነበር። ከንጉሱ እና ደርግ ጥፋቶች እርምት ወስደናል በማለት ውጫዊው ዳንኪራ ጋብ ይል ነበር።
የብአዴኑ ሊቀመንበር ደመቀ መኮንን ቤተሰቦች ቄያቸውን ነቅለው የተሰደዱበት የ67 ረሀብ በመቶ ሺዎች ህይወት ቀጥፏል። ድብቁ የወሎ ረሀብ በነበረበት ሰአት ንጉሰ ነገስቱ እጅግ ውድ የሆኑ እቃዎችን ስጦታ ያጋብሱ ነበር። የአዲሳአባ የመንገድ መብራቶች ልዩ ድምቀት እንዲሰጡ ተደርገው ነበር። በ77ቱ ረሀብ ደግሞ የኢሰፓ ምስረታ እና የአብዬቱ 10ኛው አመት በአል ከውጭ ሀገር በልዩ ትእዛዝ በመጣ ውስኪ እንዲደምቅ ተደርጓል። ዜጐች በተራቸው በተከሰተው ረሀብ እንደ ቅጠል ይረግፉ ነበር።
ዛሬ ደግሞ ቤተሰቦቹ በወሎ ረሀብ የተጠቁበት ጓድ! ደመቀ የትላንት ጠባሳውን ወደ ጐን ትቶ የሼሼ ገዳሜው የበላይ ጠባቂ ሆኗል። እያወቀ ከሚፈጵመው አስነዋሪ ድርጊት የመፀፀት እና የመታረም አዝማማሚያ አይታይበትም። ይባስ ብሎ ” ድርቁን ለህዝብ ንቅናቄ እንጠቀምበታለን” የሚል ክብረነክ ንግግር በአደባባይ ያሰማል። ሸክሙ የከበደው ህዝብ እንደሱ ዘመዶች ቄዬውን እየለቀቀ መሄዱን እየተመለከተ ችጋር የለም ይለናል። ፈረንጆቹ ለአለም ቀርፀው የሚያሳዩት የውርደት ሞት እየተመለከተ ” ሞት የለም!” ብሎ በጡንቻው እያሰበ መሆኑን ይነግረናል። …ኧረ ለመሆኑ ወዴት እየሔድን ይሆን?… የአድርባዬች እና ደናቁርት ስብስብ እስከ መቼ ፊታችን ይደነቀራል?… ወደ እንጦሮጦስ እየወረደች ያለችው ሀገራችንን የምንታደገው መቼ ይሆን?
ለማንኛውም የዛሬውን አጭር ማስታወሻ በአንድ አርፍተነገር መቋጨት ፈለኩ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብአዴንን ሳስብ ፊትለፊቴ የመከደቀንብኝ አባባል ነው። አባባሉ የህውሀት ታጋይ የነበረው ገብሩ አስራት ነው። ገብሩ ” ዲሞክራሲ እና ሉአላዊነት በኢትዬጲያ” በሚለው መጵሀፏ ገጵ 135 ላይ ብአዴንን በተመለከተ የሚከተለውን ይለናል፣
” ኢህዴን/ ብአዴን ደርግን ለመጣል ካደረገው ወታደራዊ አስተዋጵኦ ይልቅ የፓለቲካ አስተዋጵኦው ይልቃል።”

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48397#sthash.T8T3w626.dpuf

የአማራ ህዝብና የህወሀቱ ብዓዴን – አቻምየለህ ታምሩ

ሰሞኑን ባህር ዳር ላይ የህወህት ስኬት የሆነው የአማራ እልቂት በራሱ በአማራው እየተዘከረ ይገኛል። የአማራ ህዝብም «በግ ካራጁ ኋላ እንደሚጎተት» እየተጎተተ ሞቱን እያነገሰ ገዳዮቹን አበጃችሁ እያለ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። ይህንን እንድል ያስደፈረኝ «35ኛውን የብዓዴን ዝክረ በዓል» ለማክበር የተሰበሰበው አማራ ሁሉ በበደኖ፣ በአርባጉጉ፣ በነቀምት፣ጊዳብ ሺራቦ፣ በአሰቦት፣በባሌ፣ አርሴ ፣ በቦረና፣ በጅማ፣ በኢሉባቦር፣በወተር፣ በቤንሻንጉል፣ በጉራ ፈርዳ፣ በወልቃይት፣ ወዘተ የተካሄደውን የአማሮች ጭፍጨፋና የብዓዴንን ግብረ መልስ የማያውቅ የኔዘመን ትውልድ ስለሌለ ነው።

ይህንን አስመልክቶ ከሶስት ሳምንት በፊት « ብዓዴን የህወሀት ነውረኛ ቡድን እንጂ የአማራ ህዝብ አካል አይደለም» በሚል ርዕስ የጻፍሁትን ጽሁፍ እዚሁ ፌስቡክ ገጼ ላይ አትሜ ነበር። የጽሁፌ አላማም «ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ» እንዲሉ የመጀመሪያውን የኢህዴን ሊቀመንበር አግኝቼ ስለድርጅቱ አፈጣጠርና አላማ ዛሬ በጸጸት አለንጋ እየተገረፈ ያጫወተኝን እውነት ለዘመን ተጋሪዎቼ ለማካፈል ነበር። የሆነው ሆኖ የአማራው እልቂት በራሱ በአማራው ገንዘብ አገር አቀፍ ድግስ ተዘጋጅቶ ባህር ዳር ላይ እየተከበረ ይገኛል። ይህ ክስተት እጀ መድሀኒቱ ሀኪም ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ስለአማራው የተናገሩት ሙሉ በሙሉ በዚህ ዘመን ትውልድም ገቢር እንደሆነ ማሳያ ነው።

ባህር ዳር ላይ እየሆነ ያለውን የአማራው ክራሞት ግን አንድ ነገር ደጋግሞ አስታወሰኝና ልከትበው ወደድሁ። የባህር ዳሩ የአማራው ሽርጉድ ታላቁ አርበኛና ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ በፋሽስት ጥሊያን ወረራ የኢትዮጵያ መንግስት በፈረሰ ጊዜ ከራስ እምሩ ኃይለ ስላሴ ጋር ሆነው ስለነጻነታቸው በሚጋደሉበት በዚያ ወቅት፥ ቆመውም፥ ተቀምጠውም፥ ተኝተውም፥ የሚያቃጥላቸው ያገር ፍቅር እየቀቀላቸው፤ እንፋሎታቸው እየገነፈለ፤ አይናቸው እንባ እየሞላ ስላስቸገራቸው በናታቸው ስም «የኢትዮጵያ ስቅሶ» ብለው ሀዘናቸውን ለወንድሞቻቸው ለማካፋል ሲሉ በንባቸው የጻፉትን ግጥም ያስታውሰኛል።

የአማራው ህዝብ ከአራጁ ከወያኔ ኋላ እየተጎተተ ራሱ እንዲጠፋ የሞት አዋጅ የታወጀበትን፤ እንዲታረድ ካራው የተሳለበንት ቀን ለማክበር እንዲህ ሲያጀረጅር ከማየት በላይ ውርደትና ክሽፈት የለም።

የአርበኛ የሀዲስ ግጥም ምንም እንኳ በዚያ ዘመን የተቋጠረ ቢሆንም ዛሬም ባህር ዳር ላይ የህወሀቱን ብዓዴን ልደት ለማክበር ለተሰበሰበው ሆዳም አማራ ሁሉ ገላጭና ከመጠነኛ ማሻሻያ ጋር እነሆ፤

የኢትዮጵያ ልቅሶ
ልጆቼን በማመን ባለመጠራጠር፣
የሚደፍረኝ የለም፣ ብዬ እመካ ነበር፤
ግን አሁን ተደፈርሁ ላልቅስ ፣ እርሜን ላውጣ፣
ጀግኖች ያለቁብኝ ፣ ስለሆንሁ አይቶ አጣ፤
አድምጡኝ ልጆቼ ፣ ላስጠንቅቃችሁ፣
ሳምናችሁ ብትከዱኝ ፣ ስመካበችሁ ፣
ዘላለም ውርደት ነው ፣ ደመወዛችሁ።
አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወዬ ።

ጀግና አልተተካም ወይ ፣ በቴዎድሮስ ስፍራ፣
ጎበዝ አልቆመም ወይ ፣ በዮሃንስ ስፍራ፣
ሰው የለበትም ወይ ፣ በምኒሊክ ስፍራ፣
ጠላቴ ሲወርረኝ ፣ ከቀኝ ከግራ፣
የሚሰማኝ ያጣሁ ፣ ብጣራ ብጣራ፤
ወይ እኔ ኢትዮጵያ የጀግኖች እናት፣
ሁሉም አለቁና ፣ ትተው ባዶ ቤት፣
ደርሶብኝ የማያውቅ ፣ አገኘኝ ጥቃት።
አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ፣ ከዳችሁኝ ወዬ ።

ገንዘብ እዬዘራ ሲመጣ ጠላት፣
ከማታለል ጋራ ፣ ከውሸት ስብከት፣
ባጠመደው ወጥመድ ፣ እንድትገቡለት፣
ተንኮሉን ሳታውቁ ፣ መስሎዋችሁ እውነት፣
በግ ካራጁ ሁዋላ ፣ እንደሚጎተት፣
ትጎተታላችሁ፣ እናንተም ለሞት።
አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወዬ።

ገንዘብ ተበድሮ አሁን ሲሰጣችሁ፣
ሁልጊዜም እንደዚያው ፣ የሚያደርግ መስሎዋችሁ፣
እንዳትታለሉ ፣ ሁዋላ ወየላችሁ፤
አሁን ገንዘብ ሰጥቶ ፣ እንዳትታገሉት ካረገ በሁዋላ፣
እንኩዋንስ የራሱ ፣ ገንዘቡን ሲበላ ፣
የናንትም ይሄዳል ይሰጣል ለሌላ።
አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወየ ።

አሁን ቢሰጣችሁ ገንዘብ ተበድሮ ፣
በጁ ስትገቡለት ፣ እንዲህ ጥሮ ግሮ ፣
ከያዘ በሁዋላ ክንዱን አጠንክሮ ፣
ያጠፋውን ገንዘብ ፣ አንድ ባንድ ቆጥሮ፣
ይቀበላችሁዋል ፣ ወለዱን ጨምሮ ።
አየ ዋየ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ፣ ከዳችሁኝ ወይ።

አይ ሞኞች ልጆቼ ፣ ተላላዎች ሆይ ፣
ድርጅት ያቆመ በህዝባችሁ ላይ፣
እናንተን ለማክበር ፣ መሰላችሁ ወይ?
አሁን ስነግራችሁ ፣ ቢመስላችሁ ዋዛ፣
በሁዋላ መከራው ስቃዩ ሲበዛ ፣
ሞትን ብትፈልጉት ፣ በወርቅ አይገዛ፤
አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወየ ።

ፀፀቱ ይውጣልኝ እስቲ ልንገራችሁ፣
ምናልባት ብትሰሙኝ ፣ ትንሽ ቢቆጫችሁ፣
ጠመንጃው ጥይቱ ፣ እያለ በጃችሁ ፣
ዱሩ ሸንተረሩ ሳለ በጃችሁ ፣
አሁን ጊዜው ሳያልፍ ፣ካልተጋደላችሁ፤
ይህን ሁሉ በጁ ፣ ካረገ በሁዋላ ፣ አጥቂው ጠላታችሁ፣
ቢጭኑት አጋስስ ፣ ቢያርዱት ሰንጋ ናችሁ ።
አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወየ ።

ከዚህ ወድያ በቃኝ ፣ መክሬያችሁዋለሁ ፣
ለኔም ለናንተም ሞት ፣ እርሜን እውጥቻለሁ፤
መክሬያችሁዋለሁ ፣ ጠላትን በህብረት እንድትቃወሙ፣
አሁን ይህን ጊዜ ፣ በጣም ሳትደክሙ፣
የናትነት ምክሬን ፣ ቃሌን ብትፈፅሙ፣
እግዜር ይባርካችሁ ፣ አብቡ ለምልሙ፣
ግን ይህን ጨኸቴን ፣ ልቅሶየን ባትሰሙ፣
በመልእልተ መስቀል ፣ የፈሰሰው ደሙ ፣
ርጉም ያድርጋችሁ ፣ እስከ ዘላለሙ ።
አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወዬ።

ፖለቲካ በደም አይጋባም – አርበኞች ግንቦት7 (ኢዲቶርያል)

Patriotic Ginbot 7 logoህዝባዊ ተቀባይነቱን ያጣው ወያኔ በሽፍትነት ዘመኑ ትግራይ ውስጥ ሲያደርግ እንደረነበረው ሁሉ፣ መንግስታዊ ስልጣኑን ከያዘም በሁዋላ መሰልጠን አቅቶትና እንደመንግስት ማሰብ ተስኖት፣ አገዛዜን ይቃወማሉ ብሎ የሚጠረጥራቸውን ዜጎች የቅርብ ቤተሰቦችና የሩቅ ዘመዶች ሳይቀር ማሰቃየት መጀመሩን ከአራቱም የአገራችን ማዕዘናት በየቀኑ የሚደርሱን ሪፖርቶች ያመለክታሉ።

በቅርቡ በአርባ ምንጭ ከተማ ለአገራቸው ነጻነት በገዛ ፈቃዳቸው ተነሳስተው ታሪካዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በሞከሩ ወጣቶች ላይ የስርዓቱ ታማኝ ጥቂት የደህንነት ሃይሎች የወሰዱት እርምጃ ዘግናኝና ልብ የሚያቆስል ነው። ይህም አልበቃ ብሎ የተፈላጊ ወጣቶች መኖሪያ ቤቶች በታጠቁ የደህንነት ሃይሎች ተወረው ፍተሻ ተካሂዶባቸዋል:: እናቶች ህጻናት ልጆቻቸው ፊት “የተደበቁ ልጆቻችሁን አምጡ ” ተብለው መሳሪያ ተደቅኖባቸው፣ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል።

በአገዛዙ ዘረኛና የተጨማለቀ ፖሊሲ ተማረው ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ እርምጃ መውሰድ የጀመሩ የቴፒ ወጣቶችን ለማደን የተደረገው ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ የፈደራል ፖሊስና መከላኪያ ሠራዊት በወላጆች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል። ወጣት ሴቶች እና እናቶች ርህራሄ በጎደላቸው የስርዓቱ ታማኝ ወታደሮች ተደብድበዋል፣ ተደፍረዋል፣ ታስረዋል። በሰሜን ጎንደርም እንዲሁ መብታችን ይከበር ብለው በተነሱ ወጣት ቤተሰቦች ላይ የገዢው ሃይል ታማኞች ፣ ግድያና አስገድዶ መድፈር ፈጽመዋል። እህትማማች ሴቶች መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ ተገድለዋል። በወታደሮች የተደፈሩ ሴቶች ቅስማቸው ተሰብሮ ወደ አደባባይ ለመውጣት እንኳ የማይችሉበት ደረጃ ደርሰዋል።

በመርአዊ ከተማ መኳንንት ጸጋዬ የተባሉ በሰላማዊ ትግል ስርዓቱን የሚቃወሙ ግለሰብ፣ በልጆቻቸውና በባለቤታቸው ፊት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ የልጆችን ስነልቦና በሚነካ መልኩም ሰዋዊ ክብራቸው እንዲዋረድ ተደርጓል።

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ድንበር የለውም፤ የወያኔን የበቀል ዱላ ያልቀመሰ፣ ማንነቱና ክብሩ ያልተዋረደ ህዝብ ማግኘት አይቻልም። በገዳዩ ስርዓት እየደረሰ ያለው ግፍ አንድ ጊዜ በሰሜን፣ ሌላ ጊዜ በደቡብ፣ ሌላ ጊዜ በምስራቅ እያለ ቀጥሎአል። የዚህ ፍጹማዊ የአፈና አገዛዝ ህልውና እንዲቀጥል እስከተፈቀደለት ድረስ ጭቆናው፣ መዋረዱ፣ መታሰሩና መሞቱ አይቆምም። የአገዛዙ ባህሪ እነዚህን ሰይጣናዊ ድርጊቶች ለመፈጸም እንጅ መልካም ነገር ለመፈጸም አያስችለውም።

ለነጻነት የሚደረገው ትግል በመሬት ላይ አድማሱን እያሰፋ በመጣ ቁጥር የጥቃቱ አይነትና መጠንም እየጨመረ እንደሚመጣ ስናስብ፣ ይህን ጥቃት የምናስቆምበት ወይም የምንቀንስበትን መንገድም መሻት ተገቢ ነው። ወያኔ በነጻነት ታጋይ ቤተሰቦች ላይ ጥቃቱን ሲፈጽም ከሚጠቅሳቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ “ልጅህ ወይም ወንድምህ መንግሥታችንን ለመናድ ሌት ተቀን እየሰራ አንተ በሠላም ልትኖር አትችልም” የሚል ነው። ይህ ሁዋላ ቀር አስተሳሰብ ወያኔን ከሚመሩ ሰዎች የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ፖለቲካ ወይም የነጻነት ጉዳይ በደም የሚወረስ ሳይሆን ከግለሰቦች ማንነት ጋር ተያያዞ የሚመጣ መሆኑን፣ ቀድም ብለው በሁለት ጎራ ለይተው ሲፋለሙ የነበሩ ወጣቶችን ታሪክ ማስታወስ በቂ ነው። ከአንድ ማህጸን የወጡ የአንድ እናት ልጆች የተለያዬ የፖለቲካ አመለካከት እንደሚይዙ ታሪካችን ብቻ ሳይሆን፣ የወያኔ ታሪክ ራሱ ምስክር ነው።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ በጅምላ በቤተሰብ ላይ የሚደርሰው ጥቃት፣ ከሁዋላ ቀርነትና ከግንዛቤ ማነስ የመጣ ነው ተብሎ የሚመጣ ብቻ ሳይሆን፣ ድርጊቱን ከሚፈጽሙት ሰዎች ስነልቦና ቀውስና የሁዋላ ታሪክ ጋር የሚያያዝ ነው። በንጹህ ዜጎች ላይ ጭካኔና ግፍ የሚፈጽሙ ሰዎች፣ የሰው ማንነት የሌላቸው፣ ከአስተዳደጋቸው ጀምሮ የተበላሹና ማህበረሰቡ “አይመጥኑም” ብሎ የተፋቸው ናቸው። አሁን በስልጣን ላይ ያሉና በህዝባችን ላይ የጭካኔ ዱላቸውን የሚያሳርፉ ገዢዎች የሁዋላ ታሪክ ቢጠና ከዚህ የተለየ እውነታ አይኖረውም።

ሌላው የወያኔ ስልት ደግሞ በአገር ውስጥ ያሉትን ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጭ የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ታጋዮችን ቤተሰቦችና ዘመዶች እየተከታተሉ ” እባካችሁ ዘመዶቻችሁ ከፖለቲካው እንዲርቁ አድርጉ፣ እንዲህ ካደረጋችሁ የምትፈልጉትን ነገር እናድርግላችሁዋለን፣ ለእነሱም የፈለጉትን ነገር እናደርግላችሁዋለን” በማለት ለመደለል መሞከራቸው ነው።

ለወያኔ ነጻነት ማለት ገንዘብ ነው፤ ቤት ነው፤ ሆድ ነው፤ ነጻነት የህሊናና የማንነት ጉዳይ መሆኑን ገና አላወቀም። ሁሉም ሰዎች ነጻነታቸውን በገንዘብ፣ በቤት፣ በሆድ ወይም በብልጭልጭ ምድራዊ ነገር ይሸጣሉ ብሎ ያስባል፤ በርግጥ በእነዚህ አላፊና ጠፊ ነገሮች ተታለው ነጻነታቸውን የሸጡ ቢኖሩም፣ ሁሉም ሰው ግን እንደዛ አይደለም። የወያኔን የግፍ አገዛዝ ተቃውመው ለነጻነት የሚታገሉ ሃይሎች ሁሉ፣ ቁሳዊ ፍላጎታቸውን ትተው፣ ህሊናዊና ማንነታዊ ፍላጎትን ለራሳቸውም ለህዝባቸውም ለማምጣት የሚታገሉ ናቸው። በወያኔና በእነዚህ ታጋዮች መካከል ያለው ልዩነትም ይህ ነው፤ ወያኔ ለአላፊ ጠፊው ምድራዊ ህይወት ሲጨነቅ፣ እነዚህ ተጋዮች፣ ዘላለማዊ ለሆነው ለነጻነትና ለማንነት ክብር ይጨነቃሉ። ስለዚህ ወያኔ ለህሊናቸውና ለማንነታቸው የሚታገሉ ሃይሎችን በቁሳዊ ፍላጎት ለመደለል የሚያደርገው ጥረት መቼውንም ፍሬ አያፈራምና ቤተሰቦችን እየጠራ ባያንገላታቸው ይመረጣል።

የአገዛዝ ዕድሜን ለማራዘም ሲባል በነጻነት ታጋይ ቤተሰቦች ላይ እየተወሰደ ያለው ጥቃት ከዚህ ቀደም በነበሩ ሁለት መንግሥታት ዘመን እንኳ ታይቶ የማይታወቅ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልግም:: መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት በተለየበት ሰሞን የአገዛዙ ጋዜጠኞች አደዋ የሚገኘውን የወላጆቹን መኖርያ ቤት በቴለቪዥን ለህዝብ ዕይታ አቅርበው ፣ መለስ ዜናዊ ከጫካ እየሾለከ መጥቶ ያርፍ እንደነበር በገዛ ወንድሙ አፍ እንዲነገር አድርገዋል::

በአጭሩ ፓለቲካ በደም አይተላለፍም፤ ደምን ቆጥሮ በፖለቲካ ታጋይ ቤተሰቦች ላይ የሚደርስ ጥቃትም፣ ቂምና በቀልን ከመውለድ ውጭ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም። ህዝባዊ የነጻነትን ትግልን፣ የታጋዮችን ቤተሰቦች በማሰቃየት ወይም በመደለል ማስቆም አይቻልም። አፈናና ሰቆቃ ባለበት ቦታ ሁሉ ፣ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር፣ አመጽ የማይቀር ማህበራዊ ክስተት ነው :: በተለይ “የህዝብ ብሶት ወለደኝ” በማለት መሣሪያ አንስቶ 17 አመት ታገልኩ ለሚለው ወያኔ ይህ ግልጽ እውነታ ምርምር የሚጠይቅ ውስብስብ ፍልስፋና ሊሆንበት ባልቻለ ነበር :: ዳሩ ከተጣመመ አፈጣጠሩ፣ ከመሪዎቹ ምንነትና ማንነት እንዲሁም ስልጣን ከተያዘም በሁዋላ በዘረፋ የተሰበሰበው ሃብት የፈጠረው የኑሮ ምቾትና የተከማቸው የጦር መሳሪያ ያቀዳጀው እብሪት አይነ ልቦናውን ጋርዶታልና ለወያኔ ይህ ሃቅ ሊገባው አይችልም።

አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔ የአፈና ክንዶች ሺ ጊዜ ቢፈረጥሙም ፤ በተቃዋሚዎችና የነጻነት ታጋዮች ቤተሰብ ላይ የሚወሰደው እርምጃ የህይወት መስዋትነት እያስከፈለ ቢመጣም እንኳ ለነጻነት የሚያደረገው ትግል ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል እንጂ ለአፍታም ቢሆን አይዘናጋም። የታጋይ ቤተሰቦችና ዘመዶችም፣ አሁን በወያኔ የሚደርስባችሁ ግፍና በደል፣ ለመላው አገራችን ነጻነት ሲባል የሚከፈል ዋጋ በመሆኑ ልትኮሩ እንጅ ልለትሸማቀቁ አይገባም ። በህዝብ ፊት የነጠሉዋችሁና ከማህበራዊ ህይወታችሁ እንድትገለሉ ያደረጉዋችሁ ቢመስላችሁ፣ እውነታው ተቃራኒው ነው፤ ከህዝብ የተገለሉት እነሱ ናቸው፤ የሚዋረዱትና የሚያፍሩት እነሱ ናቸው።

በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ሥር የሚማቅቅ እያንዳንዱ ዜጋ አርበኞች ግንቦት 7 የለኮሰውን የነጻነት ትግል ችቦ አንግቦ በወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ የታፈረች የተከበረችና የዜጎቿን መብት በእኩልነት የምታስከብር አገር ለመገንባት በሚደረገው ትግል እንዲቀላቀል አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪውን ያቀርባል:: የወያኔ የጥቃት እጆች የሚያጥሩትና ዜጎች በአገራቸው ተከብረው የሚኖሩት ወያኔ ሲወገድ ብቻ ነው!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

ችጋር በሰው ዘር ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነው

ያሬድ ኃይለማርያም

ከብራስልስ

 

አለም እጅግ በሰለጠነበት በዚህ ክፍለ ዘመን፣ የሰው ልጅ በእውቀትና በቴክኖሎጂም በመጠቀበት ወቅት በሚሊዮኖች የሚገመቱ ሰዎች የሚላስ የሚቀመስ አጥተው፣ ሰማይና ምድሩ ተዳፍኖባቸው ከሞት አፋፍ የሚደርሱበትና ከፊሉም የሚሞቱበት አገርና ስፍራ ቢኖር እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ማሕበራዊ ፍትሕ የተጓደለባቸው፣ ሙሰኝነት መረን በለቀቀ መልኩ በተንሰራፋባቸው፣ ፍጹም የሆነ አንባገነናዊ ሰርዓት በሰፈነባቸው እና የህግ የበላይነት ባልተረጋገጠበት አገሮች ወይም እንደ ሶማሊያ ባሉ መንግስት አልባ ሆነው ለረዥም አመታት በትርምስና እልቂት ውስጥ በቆዩ ጥቂት አገሮች ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከሰተውን ችጋር በተመለከተ እረዘም ላለ ጊዜ ጥናት ያካሄዱትን ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያምን ጨምሮ በርካታ አለም አቀፍ ተመራማሪዎች በጥናቶቻቸው እንዳረጋገጡት የ‘ችጋር’ ምንጩ የተፈጥሮ አየር ንብረት መዛባት ወይም የእዝጌር ቁጣ ሳይሆን ብልሹ የፖለቲካ አስተዳደርና የተሳሳተ የመንግሥት ፖሊሲ ወይም የአፈጻጸም ችግር የሚያስከትለው አደጋ ነው፡፡ ከአንድ መጥፎ ሥርዓት ወደ ባሰ መጥፎ ሥርዓት ስትንከባለል የመጣችው አገራችንም ከ1958 ዓ.ም ወዲህ ባሉት ጊዜያቶች ውስጥ ለበርካታ ጊዜያት ችጋር አንጃቦባታል፡፡ ቁጥራቸው ቀላል ግምት የማይሰጣቸውን ድሃ ልጆቿንም እንደ ጩልፊት አሞራ ነጥቋታል፡፡
ይህ አንባገነንና አፋኝ ሥርዓትን እንደ ጥላ የሚከተለው የችጋር አዙሪት ዛሬም አገሪቱ በልማት ገስግሳለች እየተባለ ሌት ተቀን በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀር በሚዘፈንበት ወቅት የአሥራ አምስት ሚሊዮን ድሃ ልጆቿን ሕይወት ሊቀጥፍ እንደ ጩልፊት አሞራ እያንጃበበ መሆኑን ከአገዛዙ ልሳን ጭምር እየሰማን ነው፡፡ የአገዛዝ ስርዓቱ ለዚህ አደጋ አራሱን ተጠያቂ ላለማድረግ ሁለት ዋና ምክንያቶችን እየደረደረ ነው፡፡ አንድም ችግሩ የተከሰተው በአለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የአየር መዛባት መሆኑን እና በሁለተኛ ደረጃም ችግሩ የተባባሰው አገሪቱ በልማት ጎዳና ላይ ብትሆንም ገና በምግብ እራሱዋን ያልቻለች ደሃ አገር ስለሆነች ነው የሚል ነው፡፡ የመጀመሪያውን ምክንያት ድርቅን ከማስከተል ያለፈ የችጋር አደጋን ሊያመጣ እንደማይችልና ድርቅ ወደ ችጋር የሚለወጠው በምሁራኖቹ ጥናት እንደተረጋገጠው የብልሹ ሥርዓት ውጤት ስለሆነ እሱ ላይ በዙ ማለት አይጠበቅብኝም፡፡ ሁለተኛውን ምክንያት የተመለከትን እንደሆነ በእርግጥም ኢትዮጵያ ድሃ ልጆቿን በችጋር ከሚደርስ የሞት አደጋ ለመታደግ በሚያስቸግር ደረጃ ላይ የምትገኝ ደሃ አገር ነች ወይ የሚል ጥያቄን ያጭራል፡፡
በአገሪቱ የተላያዩ ክፍሎች የችጋር ምልክት መታየት የጀመረው ከአመት በፊት ነው፡፡ በተለይም በአፋርና በሶማሌ ክልል አካባቢ እንስሳቶች መሞት የጀመሩት፣ በምግብና በመጠጥ ውሃ እጦት ሰዎች ከቅያቸው መሰደድ የጀመሩት ከወራቶች በፊት ነው፡፡ ጉዳዩም በተለያዩ የመገናኛ በዙሃን ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ እንደሚታወቀው እነዚህ አካባቢዎች በተለይም በሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ ለረዥም ጊዜ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጭምር ወደ ክልሉ እንዳይገቡና እርዳታ እንዳያደርጉ የአገዛዝ ሥርአቱ የከለከለ በመሆኑ እየደረሰ ያለውን የጉዳት መጠን እንኳን በትክክል ለማወቅ አልተቻለም፡፡ የአገዛዝ ሥርዓቱም ችግሩን በማጤን አፋጣኝ እርምጃዎችን ከመውሰድ ይልቅ የሥልጣን ዘመኑን ለማደስ ባካሄደው የይስሙላ ምርጫና የተገኘውን መቶ ፐርሰንት ድል በማጣጣም ላይ ተጠምዶ ስለነበር በሚሊዮን የሚቆጠሩት ድሆች የሚያሰሙትን የድረሱልን ጥሪ የሚሰማበት ጆሮና የሚያይበት አይን አልነበረውም፡፡ መንግስት ከመደበኛ ስራዎች ባሻገር በብዙ ሚሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ ከሚያፈስባቸው ጉዳዮች ጥቂቶቹን ብንመለከት አገሩቱ በችጋር እየተጠበሱ የሚረግፉ ልጆቿ ለመታደግ የሚስችለውን አቅሟን ሥርዓቱ በምን ላይ እያዋለው እንደሆነ በግልጽ ያመላክታል፡፡
  • በቅርቡ ሥርዓቱ በአለማችን የተለያዩ ከፍሎች ተበትነው ጥቂት ቅሪት ያካበቱ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ድል ያለ ድግስ ደግሶና 40 ፐርሰንት የአውሮፕላን ትኬታቸውን ወጪ ሸፍኖ ሲያበላ፣ ሲያጠጣና አገር ሲያስጎበኝ ቆይቷል፡፡ ለዚህም በሚሊዮኖች የሚገመት የአገሪቷን ሃብት እንዳፈሰሰ በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን አርድቶናል፡፡
  • ባለፉት ሁለትና ሶሰት አመታተ ውስጥ ሥርዓቱ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት ሲል በየኤምባሲው እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ አፍሶ ድል ያለ ድግስ በመደገስ ከአገር ውጭ በተደላደለ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ሲያበላና ሲያጠጣ ከርሟል፡፡ እኔ በምኖርባት አገር የሚገኘው ኤምባሲ እንኳን በተደጋጋሚ ጊዜያት ከ300-400 የሚገመቱ የቤልጂየምና የጎረቤት አገር ነዋሪዎችን እየጋበዘ ከኢትዮጵያ ድረስ አስጭኖ ያስመጣውን ምግብና መጠጥ በከፍተኛ ገንዘብ በተከራያቸው ውድ አዳራሾች ሲያበላና ሲያጠጣ ታዝበናለ፡፡ በችጋር ከሚረግፉት ሚሊዮኖች ጉሮሮ እየነጠቀ በድሎት ከሚኖሩ ጥቂቶች ጋር ቢራና ውስኪ የሚያራጭበት ምክንያት ግልጽ ነው፡፡
  • ከአነስተኛ ሹማምነት አንስቶ እሰከ ከፍተኛ ደረጃ ያሉ የአገዛዙ ባለሥልጣናትና ካድሬዎች ከገቡበት የሙስና አዘቅት ባሻገር ለሥርዓቱ ያላቸውን ታማኝነት ይዘው እንዲቆይ ሲባል ለነሱና ለቤተሰቦቻቸው ምቾት የሚባክነው ገንዘብ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም፡፡ አፈ-ጉዔው አቶ አባዱላ ባለፈው አመት በተወካዮች ምክር ቤት የአፍ ወለምታ ይሁን ከልብ አስበውበት “እኔን ጨምሮ እያንዳንዱ የመንግሥት ባለሥልጣናት ከአንድም ሁለት የሰባት ሚሊዮን ብር እና ከዛ በላይ የሚያወጡ መኪኖችን ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው መገልገያ በመንግሥት ባጀት ማዘዛቸውን ማቆም አለባቸው” ሲሉ የተናገሩትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በርሃብ፣ በውሃ ጥም፣ በሕክምና እጦትና በሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች ችግር በሚለበለቡበት አገር ባለሥልጣናቱ አይን ካወጣ ዝርፊያና ንጥቂያ አልፈው የድሎት በጀት አስበጅተው የአገር ሃብት ሲያባክኑ እየታየ ነው፡፡
  • የገዢው ፓርቲና አጋሮቹ በየጊዜው እየተነሱ የሚያከብሩዋቸው ድርጅታዊ በዓላት በሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ የሚፈስባቸው ናቸው፡፡ በቅርቡ በጅጅጋ የተካሄደውን የወያኔን የድል በዓል አከባበር ማየት በቂ ነው፡፡ የክልሉ ሕዝብ በርሃብና በውሃ ጥም እየተሰቃየና እርዳታ እየተማጸነ ባለበት ወቅት የአገዛዝ ሥርዓቱ በመላ አገሪቱ ያሉትን ካድሬዎች ጅጅጋ ላይ ሰብስቦ ለአንድ ሳምንት ጉሮ-ወሸባዮ ይል ነበር፡፡
  • በየጊዜው እየተሰነጣተቀ የሚገጥመውን የገዢውን ፓርቲ የፖለቲካ ገጽታ ለማሳመርና ያገዛዙን ዘመን ለማራዘም የሚባክነውም ገንዘብ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በባለሥልጣናትና በካድሬዎቻቸው በስብሰባና የውጭ ጉዞዎች የሚባክነውን ከፍተኛ ገንዘብ እንተወውና ሥርዓቱ የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን ፖለቲከኞች፣ ስርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኞችንና የማህበራዊ ድረ-ገጾችን፣ የተቃዋሚና ገለልተኛ ሚዲያዎችን ለማፈንና ለመሰለል የሚያወጣውም ገንዘብ በሚሊዮን ዶላር የሚገመት እንደሆነ በቅርቡ በጣሊያንና በጀርመን ከሚገኙ በኢንተርኔት ጠለፋና ሥለላ ሥራዎች ላይ ከተሰማሩ ደረጅቶች ጋር የነበረው ግንኙነት ጥሩ ማሳያዎች ናቸው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ በሚራብበት አገር ከነሱ ጉሮሮ ነጥቆ በሚሊዮኖች የሚገመት ዶላ ወጪ አድርጎ አንድ ሺ የማይሞሉ ተቃዋሚዎቹንና ተቺዎቹን መሰለያ የሚሆኑ የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን የሚገዛ ድርጅተ ነው፡፡
እነዚህን እና ሌሎች የአገዛዝ ሥርዓቱ በአገርና በሕዝብ ሃብትና ገንዘብ ላይ የሚፈጽማቸውን ብክነቶች እያሰብን ከፍለፊታችን የተጋረጠውን የችጋር አደጋ ስንመለከት ስርዓቱ ከጥይት፣ ከእስር፣ ከስደትና ከልመና የተረፉትን ድሃ የሃገሪቱን ዜጎች ለችጋር አሳልፎ የሰጣቸው መሆኑን ነው የምንመለከተው፡፡ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶችና በተመሳሳይ ሁኔታዎች ከሚባክነው ከፍተኛ ገንዘብና በተለያዩ ጊዜያት ከአገር የሚሸሸውን የገንዘብ መጠን ስንመለከት ኢትዮጵያ ደሃ ሳትሆን የተፈጥሮ ሃብቷንና ገንዘቧን በአግባቡ የሚያስተዳድርላት ሰውና የፖለቲካ ሥርዓት ነው ያጣችው፡፡
ለአገርና ለወገን የሚቆረቆር ጤናማ የፖለቲካ አመራር ባለበት ሃገር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ ዋስትና በማጣት ከሞት ደጃፍ አይደርሱም፡፡ ህሊናቸውን ያልሳቱ፣ በሕዝብ ገንዘብ አእምሮዋቸው ያልናወዘና ስብዕና የሚሰማቸው የፖለቲካ አመራሮች ባሉበት አገር ሹመኞች ከነልጆቻቸው በሚሊዮን ዶላር በሚገዙ መኪኖች እየተንፈላሰሱና በተንጣለሉ ቪላዎች እየተመናሹ የድሃ ልጆች ቁራሽ ዳቦ የሚታደጋቸው አጥተው በየመንገዱ ጠኔ አይጥላቸውም፡፡ ይህ የሚሆነው በተቃወሰ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ አንድ የመንግሥት ሹመኛ ወይም ወታደራዊ ባለስልጣን ወይም የሥርዓቱ ደጋፊ የሆነ ሰው ባጭር አመታት ውስጥ ከመንግሥት ደሞዝተኝነት ተነስቶ ምንጩ ባልታወቀ ሁኔታ ሚሊዮነር ሲሆንና የከፍተኛ ሃብት ባለቤት ሊሆን የሚችለው መረን የለቀቀ ሙስና በተንሰራፋበት ሃገር ብቻ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች መንግስት የሚከፍላቸውን የወር ደሞዝ አንድም ሳንቲም ሳይቀነስለት ለመቶ አመታት እንኳን ሙሉውን በባንክ እንዲቀመጥ ቢደረግ ስሌቱ ባንድ ጀምበር ዛሬ ላይ ያፈሩትነ ሃብት የእሩብ እሩቡ እንኳ እንዲኖራቸው የሚያስችል አይደለም፡፡ ከትቢያ ተነስተው የግዙፍ ህንጻዎችና ኩባንያዎች ባለቤት የሚሆኑት ከሕዝበ ጉሮሮ በነጠቁት ገንዘብ ካልሆነ በቀር ከየት አምጥተው እንደሆነ ሕዝብ የማወቅና የመጠየቅ መብት አለው፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀጽ 25(1) እንዲሁም በአለም አቀፉ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ መብቶች ድንጋጌ በአንቀጽ 11 ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው እያንዳንዱ ሰው እራሱና ቤተሰቡን በተሟላ ጤንነትና ለሰው ልጅ ክብር በሚገባ ሁኔታ የመኖር ዋስትና እንዲረጋገጥለት፣ እንዲሁም በቂ የሆነ ምግብ፣ አልባሳት፣ መጠለያ ቤትና የህክምና ግብአቶችን የማግኘት መብት እንዳለውና መንግስትም እነዚህን መሰረታዊ ነገሮች የማሟላት ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ይህን ግዴታቸውን መወጣት ካልቻሉት ጥቂት የአለማች አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ነች፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የምግብ ዋስትና ማጣትን ተከትሎ ሚሊዮኖችን አደጋ ላይ እስከ መጣል የደረሰውን የችጋር አደጋ የከፋ የሚያደርገው የአገዛዝ ሥርዓቱ አደጋውን ችላ ከማለቱም ባሻገር ለማለባበስ የሚያደርገው አሳፋሪ ጥርት ነው፡፡ የBBC ጋዜጠኛ በNovember 9, 2015 ጥናታዊ ዘገባው (http://www.bbc.com/news/world-africa-34770831 ) ችግሩ በተከሰተባቸው ሥፍራዎች፤ በተለይም ወሎ ውስጥ ቆቦ አካባቢ በመዘዋወር የችጋሩ ተጠቂ የሆኑ ሰዎችን አነጋግሮና በችጋር ልጇን ያጣች አንዲት እናት ጨምሮ ምስክርነታቸውን የሰጡትን ሰዎች የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ልማታዊ ጋዜጠኞች ቃላቸውን እንዲያስተባብሉና በችጋር የሞተ የለም ብለው እንዲናገሩ አስገድደዋቸዋል፡፡ የሚያሳዝነው እንዲህ ያለውን አስነዋሪና ከጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር በራቀ መልኩ የቪኦኤው የመቀሌ ዘጋቢ ከመቀሌ ቆቦ ድረስ ተጉዞ የአገዛዙን ገበና ለመሸፈን ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸሙ ነው፡፡
ይህ እጅግ አሳፋሪና አስነዋሪ ተግባር ከመሆኑማ ባሻገር የተራበን ሰው አልተራብኩም በል፣ በርሃብ ልጇን ያጣችን ድሃ እናት ልጄ በበሽታ ነው የሞተው ብላ እንድትናገር ማስገደድ የሥርዓቱን ብልሹነት በግልጽ ያሳያል፡፡ ለዚች እናት ህመሙ በደርግ ጊዜ የተገደሉባቸውን ልጆቻቸውን አስከሬና ለመውሰድ የጥይቱን ዋጋ እንዲከፍሉ ከተገደዱት እናቶች እኩል ነው፡፡ የእዚች እናት እመም የመንግስት አድራጎት በ1997 ዓ.ም. ምርጫውን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ግጭት የትምህርት ቤት ደጃፎቻቸው ላይ በአጋዚ ጦር ግንባራቸውን እየተመቱ የወደቁትን ሕጻናት ባንክ ሊዘርፉ ሲሉ ነው የተገደሉት የሚል የማላገጫ ምክንያት እንደተሰጣቸው እናቶች ነው፡፡
ሥርዓቱና ይህ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት በችጋር ለሚሰቃየውና ለሚያልቀው ሕዝብ በታሪክ ተወቃሽ ከመሆን ባለፈ በተለይም በኦጋዴንና በተወሰኑ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በችጋር እየተጠቁ መሆኑን እየታወቀ ከአመት በላይ ተገቢውን እንዳታ ባለማድረጉና ለጋሽ ድርጅቶችም ሕዝቡን እንዳይታደጉ እቀባ በመጣሉ የተነሳ ለሚደርሰው ሰብአዊና ሌሎች ጉዳቶች ሁሉ በችጋር የሰውን ዘር ሆነ ብሎ አደጋ ላይ በመጣል በሕግ የሚያስጠይቃቸው መሆኑን ከወዲሁ ልብ ሊሉት ይገባል፡፡
አስተዋሽ አጥተው ለችጋር ለተጋለጡት ወገኖቻችን እጃችንን እንዘርጋ!
ያሬድ ኃይለማርያም

ጥቂት ስለ ሸዋሮቢት እስር ቤት – ናትናኤል ያለምዘውድ

Robit campጥቂት ስለ ሸዋሮቢት እስር ቤት

ናትናኤል ያለምዘውድ

በንጉሱ ዘመን እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሺዋሮቢት ማረሚያ ቤት ከአ.አ በደብረ ብርሃን ጠመዝማዛውን መንገድ ተከትሎ ከተጓዙ በኋላ ከተራሮች ግርጌ የሚገኝ ረባዳ መሬት ላይ የሰፈረ ማረሚያ ቤት ነው፡፡ በዚህ ማረሚያ ቤት ውስጥ አራት ዞኖች ያሉ ሲሆን የመጀመሪያው ዞን የዐማራ ክልልና የደቡብ ክልል ረዥም ጊዜ ፍርደኞችን ጨምሮ ከ3-5 አመት ፍርደኛ የፌደራል ታራሚዎችን የያዘ ነው፡፡ በዞኑ ውስጥ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታራሚዎች ለብቻው በቆርቆሮ በተከለለ ስፍራ ከ150 በላይ ሆነው ቀናትን ያሳልፋሉ፡፡ ሁለተኛው እስከ 2 አመት ከ11 ወር ፍርደኞችን፣ ሶስተኛው ከአንድ አመት እስከ አንድ አመት ከአንድ ወር፣ የመጨረሻው ከሌሎች ዞኖች ለመፈታት 3 ወር የቀራቸውንና የአንድ አመት ፍርደኞች ይይዛል፡፡ ይህኛው ዞን ቤቶቹ ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰሩ ናቸው፡፡
ከሁሉም ዞኖች የመጀመሪያው (ዞን አንድ) በአንፃሩ በህንፃዎቹም ሆነ በግቢው ጥራት የተሻለ በመሆኑ በቅጣት ወደ ሌሎቹ ዞኖች የሚላክ እስረኛ ‹‹ክፍለ ሀገር ገባ!›› ተብሎ ይቀለድበታል፡፡
የእስረኞቹ አኗኗር ሁኔታ በቤትና በዞን የተከፋፈለ ነው፡፡ ከመጨረሻው ዞን አራት ውጭ ሁሉም ዞኖች፣ ከ1400 በላይ ታራሚዎች ይይዛሉ፡፡ እንደየ ቤቶቹ ስፋት ከ160-360 እና ከዛ በላይ ይኖርባቸዋል፡፡ አልጋ ለማግኘት ከ6 ወር እስከ አንድ አመት መጠበቅ የግድ ከመሆኑም በላይ መሬት ላይ ከ2 ፍራሽ ከ5-7 ሰው እንዲተኛ ይገደዳል፡፡ እንደዚህ ተፋፍጎ የሚተኛው ታራሚ ደቦቃ ተብሎ ይጠራል፡፡ ለሽንት የሚነሳ በእነዚህ ደቦቃዎች መካከል መራመድ አለበት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዚህ መካከል በሰላም ተኝቶ ማንጋት ከባድ ነው፡፡ አንዳንድ ቤቶች እስከ 8 ሰዓት ‹‹መሽናት ክልክል ነው›› የሚል ህግ አውጥተው ሮንድ አቁመው ያድራሉ፡፡ አካባቢው በጣም ሞቃት ከመሆኑ ባሻገር የሰው መተፋፈግ ሲጨመርበት ሁኔታውን እንደ አስፈሪ ቅዠት ያመሰቃቅለዋል፡፡
አንድ እንግዳ ሰው ወደ እስር ቤቱ ጎራ ቢልና ለአዲስ ገብ ታራሚዎች የሚሰጠውን መግለጫ ቢያዳምጥ በህግና በግዴታ ብዛት ግራ ሊጋባ ይችላል፡፡ ስፖርት መስራት ክልክል ነው (ሩጫን አይጨምርም)፡፡ የስልክ አገልግሎት ማግኘት አይቻልም፡፡ ማታ መፀዳዳት፣ መፅሃፍ ማስገባት፣ የውጭ ዜና አውታሮችን መከታተል፣ ከ200 ብር በላይ ማስገባት አይቻልም፡፡ ኢቲቪ (ኢቢሲ) በግዴታ ይከፈታል፡፡ ለነገሩ ወዶ የሚከታተለው ባለመኖሩ ማስገደዱ አዋጭ ‹‹ልማታዊ/አብዮታዊ›› ዘዴ ነው፡፡ አደረጃጀት ስብሰባ ግዴታ ነው፡፡ ግዳጅ (ለእርሻና ፅዳት) ግዴታ ነው፡፡
የማረሚያ ቤቱን አጠቃላይ ሁኔታ መረዳት ያስችል ዘንድ ነጣጥለን እንያቸው፡፡
ማደሪያ ቤቶቹን ስንመለከት ህንፃዎቹ 11 ሜትር በ11 ሜትር ስፋት እና ከዚህም ሰፋ ያሉ ሲሆኑ እንደየስፋታቸው በርካታ ሰዎችን ይይዛሉ፡፡ 11 በ11 ሜትር ስፋት ያላቸው ከ160 በላይ ሲይዙ ትልልቆቹ ከ350 በላይ ይይዛሉ፡፡ ትልልቆቹ ሲባል ግዙፍ ቤት አትጠብቁ፣ ሁለቱ ትልልቅ የሚባሉ ቤቶች በአንድ ላይ ሲታዩ እንኳን 700 በላይ ታራሚዎች ይቅርና 400 ያህል ይይዛሉ ተብሎ ለማሰብ ይከብዳል፡፡ ሁሉም ቤቶች በጎን የተጨመረ ለሽንት ቤት ተብለው የተሰሩ ክፍሎች ሲኖራቸው በህመም ምክንያት የግድ የሆነበት የጤና ኮሚቴንና የቤት አስተዳደርን ማስፈቀድ ይጠበቅበታል፡፡ አብዛኛዎቹ ክፍሎች ‹ኤየር ኮምዲሽነር› የላቸውም፤ ወይንም የተገጠመላቸውም አይሰሩም፡፡ ክፍሎች በኬሻ ኮርኒስ የተሸፈኑ ወይንም ከእነ አካቴው የሌላቸው ናቸው፡፡ ወለላቸው ለመወልወልም አይመችም፡፡ ጠረናቸው ይከረፋል፡፡
የውሃ አቅርቦት ችግር አለ፡፡ ቧንቧ በየቤቱ ሳይሆን ለመላው ዞን ሶስት ቧንቧዎች ብቻ አሉ፡፡ ለሚጠጣና ለንጽህና የሚሆን ውሃን በግል በገዙት ከሪካን ተራ ጠብቆ መቅዳት ግዴታ ነው፡፡ እዚህ ቦታ ላይ በወረፋ ምክንያት ተደጋጋሚ ጸብ መከሰቱ የተለመደ ነው፡፡
ምግብ በተመለከተ፣ ቁርስ ዳቦ በሻይ ቢሆንም 80 ፐርሰንት ታራሚው ሻይውን ለልብ ድካም አጋላጭ ነው ስለሚባል አይጠቀመውም፡፡ የዳቦው መጠንም ቢሆን ለኬጂ ተማሪ እንጂ ለአንድ ወጣት ቁርስ ተብሎ የሚቀርብ አይደለም፡፡ ምሳና እራት አንድ እንጀራ በሽሮ ይታደላል፡፡ የእንጀራውም የወጡም ጥራት ዝቅተኛ ከመሆኑ በላይ ለጨጓራ በሽታ የሚያጋልጥ ነው፡፡ የምግብ ለውጥ (ዑደት) ባይኖርም ከስንትና ስንት ቀን በኋላ ጥቅል ጎመን፣ ድንችና ውሃ የቀላቀለ ቅጠላቅጠል (አትክልት) ወጥ ይመጣል፡፡ በዚህ ቀን በስፋት ሽርጉዱን፣ ግፊያውን ላስተዋለ ታራሚው ቀናትን ምግብ ባይኑ ያላየ ይመስለዋል፡፡ ስጋ በዓመት 3 ጊዜ (ምሳ ሰዓት ላይ) በዓመት በዓላት ቀን ይቀርባል፤ ለዘመን መለወጫ፣ ለገና እና ለፋሲካ በዓላት፡፡ የምግብ ችግር አሳሳቢ መሆኑን የሚያጎላው ታራሚው ያን ጣዕም የለሽ ምግብ መሰራረቁና በቅርቡ በ16/02/2008 በተካሄደው የ20 መሪዎች ስብሰባ ላይ የተነሳው ጥያቄ ዋነኛ ትኩረት መሆኑ ሲታይ ነው፡፡
ልብስ ማንኛውም ታራሚ የራሱን ልብስ የሚጠቀም ሲሆን ለመስክ ሰራተኞችና ለተማሪዎች ቱታ ይሰጣል፡፡ አልጋ ለደረሳቸው አንድ ብርድ ልብስ ይሰጣል፤ ብርድ ልብሱ አንድና ከዚያ በላይ ታራሚ ያስተናገደ አሮጌ ሊሆን ይችላል፣ ይሄንም እድለኞች ናቸው የሚደርሳቸው፡፡ ታዲያ ብርድ ልብሷ ጸረ-እንቅልፍ ተባይ አለባት፡፡
ለሽንት ቤትና ሻወር በፈረቃ የሚሰሩ ሁለት ህንጻዎች ሲኖሩ አንደኛው ህንጻ ለብቻው የተገነባና በውስጡ 14 መጸዳጃዎችን ሲይዝ ሁለተኛው ከሻወሩ ጋር የተገናኘና በውስጡ 30 መጸዳጃዎችን ይይዛል፡፡ ከመጀመሪያ ህንጻ 3ቱ፣ ከሁለተኛው 6ቱ አገልግሎት የማይሰጡ ናቸው፡፡ መጸዳጃ ክፍሎች 80 ሴ.ሜ ስፋት በ1ሜ ከፍታ ያላቸው ናቸው፡፡ መተላለፊያ ኮሊደሮች በቆሻሻ ፍሳሽ የተሞሉ ናቸው፡፡ አጠቃላይ የሽንት ቤቱ ሁኔታ ከጽዳቱ ችግር በላይ ከዕይታ የተከለለ አለመሆኑ ሰላም ይነሳል፡፡
ሻወሩ ደግሞ 80 ሳ.ሜ በ80 ሳ.ሜ ስፋትና 140 ሳ.ሜ ከፍታ የሚኖራቸው 20 ክፍሎች የያዘ እና ሁሉም በርና የውሃ አቅርቦት የሌላቸው በመሆናቸው ሻወር ከመባል ይልቅ የጅምላ መታጠቢያ ቢባሉ ይቀላል፡፡ እርቃንን ከሰው ፊት መቆም በጣም ደስ የማይል ስሜት ቢፈጥርም መታጠብ ግዴታ በመሆኑ በጀሪካን ያንጠለጠሏትን ውሃ በጣሳ እየቀዳህ መታጠብ የመጨረሻ መፍትሄ ነው፡፡ ልብስ መታጠቢያ እንዲሆኑ የተዘጋጁ ቦታዎችም ውሃ የሌላቸው ሸካራና የተሰባበሩ በመሆናቸው አንድን ጀሪካ በቁመቱ ከሁለት ከፍሎ ሳፋ መስራት ብቸው መፍትሄ ነው፡፡
እስካሁን የተዘረዘሩት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በስነ-ልቦና ላይ ጫና ማሳደራቸው የሚታበይ ባይሆንም ከአስተዳደራዊ በደሉና ከህገ-ደንቡ አፋኝነት አንጻር ኢምንት ተብለው የሚገለጹ ናቸው፡፡ የአስተዳደራዊ በደሉን ከማየታችን በፊት ግን የህክምናውን ሁኔታ ብናይ መግቢያም ይሆናል፡፡
ህክምና በመደበኛነት በሳምንት 3 ቀናት (ሰኞ፣ ረቡዕ፣ አርብ) ይሰጣል፡፡ አንድ እስረኛ በእነዚህ ቀናት ለመታከም በቀዳሚው ቀን ምሽት መመዝገብ ሲኖርበት ተመዝግቦ ከመቅረቡ በፊት ስክሪን የሚባል ቅድመ ምርመራ በቃል ይሰጠዋል፡፡ ስክሪን ያለፈ ወደ ክሊኒክ ሄዶ ዋና ምርመራ አድርጎ አሞካክስሊን ይዞ ይመለሳል፡፡ አብዛኛው ታካሚ በሽታው ጨጓራ ቢሆንም ‹‹እንጀራ በዳቦ ይቀየርልኝ›› የሚል ጥያቄ ለማንሳት የተፈጠረ ተደርጎ ስለሚታመን በስድብ አሸማቆ ማስመለስ ዋነኛው መድሃኒት ነው፡፡ ቀዶ ጥገና፣ ራጅ፣ አልትራሳውንድ… የሚያስፈልጋቸው ህመሞችን ለመታከም የግድ አዲስ አበባ መሄድ አለበት፤ ይህ ደግሞ እድሉ የሎተሪ ያህል ጠባብ ነው፡፡ በቅርቡ በነሀሴ ወር አንድ የኪንታሮት በሽተኛ የሆነ ወጣት ክፉኛ ታሞ መቀመጥ፣ መጸዳዳት፣ መተኛት ተስኖት እየተሰቃየ ለህክምና ሄዶ ማስታገሻ ኪኒን እንኳ ሳይሰጠው ማባባሻ ግልምጫ ተሰጥቶት ተመልሷል፡፡
ቤቶች ፀረ ተባይ እንዲረጩ፣ ንፅህናውን የጠበቀ ፍራሽ እንዲሰጥ እና መሰል ለንፅህና የሚረዱ ተግባራት እንዲፈፀሙ በማድረግ የመከላከል ፖሊሲውን እውን ለማድረግ የሚታየው ‹‹ቁርጠኝነት›› ከቴሊቪዥን ዘሎ መሬት ላይ ጠብ ብሎ አያውቅም፡፡
አንድ ‹‹ታራሚ›› በሰራው ወንጀል ተፀፅቶ መልካም ዜጋ እንዲሆን ሰብአዊ መብቱ ሊከበርለት ይገባል፡፡ ቤተሰቡን በስልክ ማግኘት ካልቻለ፣ ጠያቂ ሲመጣም ሚስጥሩ ተጠብቆለት ካላወራ፣ ደብዳቤው በትክክል እንዲደርስ ካልተደረገ፣ በእውቀት እንዲታነፅ ካልታገዘ፣…በግቢ ደህንነቶች ክትትል፣ በአደረጃጀት መቀፍደድ፣ የውሸት ግምገማ በማድረግ፣ የኢቲቪን ፕሮፖጋንዳ በመጋት፣ ባዶ ግቢ ውስጥ ባዶ ቀናትን እንዲያሳልፍ በማስገደድ የተሻለ ዜጋ ማፍራት ዘበት ነው፡፡
ቤተ መፅሃፍቱ ባመዛኙ የሴቶች ገመና እና መሰሎቹን አካትቶ፣ አራት የታሪክ መፅሃፍቶችን ብቻ የያዘ ነው፡፡ በእርግጥም ወጣቱ ታሪኩን ሳያውቅ ባዶ ሜዳ ላይ እንዲበቅል የተፈረደበት ይመስላል፡፡ ቤተ መፅሃፍቱ ታዛቢን ፈርተው እንጂ ወጣቱ አንብቦ እንዲለወጥ የተቋቋመ አይመስልም፡፡ መቼም መፅሃፍ ማስገባት ክልክል የሆነበት ግቢ ውስጥ ወጣቱን ለመለወጥ አላማ ይኖራቸዋል ብሎ ለመገመት ይከብዳል፡፡
በግጭት አፈታት ዙሪያ የሚወሰዱ እርምጃዎች እስር ቤት ውስጥ ለሰው የሚሰጠውን ክብር ለመመዘን ይረዱ ይሆናል፡፡ ፀብ ከተፈጠረ የተጣሉ ሰዎች የዱላ መዓት ይወርድባቸውና ጥፋተኛው ይለያል፡፡ ድብደባው የተለያየ ደረጃና አፈፃፀም አለው፡፡ እንዲያኮበኩቡ ያደርጉና በጅዶ፣ በልምጭ፣ በጥፊ፣ በካራቴ፣ እየተራረፉ ይቀጠቅጧቸዋል፡፡ ካስቸገራቸው ሁለት እጁን ወደ ኋላ፣ ሁለት እግሩን ወደፊት አድርገው ይቀጠቅጡታል፡፡ በዱላው ውርጅብኝ መናገርና መቆም ሲያቅተው ድብደባው ይበርድለትና እጁን (አንዳንዴ እግሩም) እንደተሳረ ሹል ድንጋዮች ከተነጠፉበት ጠባብ ጨለማ ክፍል (ቅጣት ቤት) ይገባል፡፡ ይች ቤት አራት ሜትር በአራት ሜትር ስትሆን አንዳንዴ ከ20 በላይ ቅጣተኞች ይገቡበታል፡፡ ብርሃን የሌለባት፣ ትኋን የሚርመሰመስባት፣ ምንም ነገር ማንጠፍ የማይቻልባት፣ ልብስ መቀየር፣ በየጊዜው መታጠብ የሚከለከልባት፣ የእስር ቤቱ እስር ቤት ናት፡፡ ከዚህ እስር ቤት የወጣ ከመቃብር ፈንቅሎ የወጣ ያህል ይሰማዋል፡፡
የሰው ልጅ ክብር ተሟጦ ያለቀ በሚመስለው ግቢ የአእምሮ ህመምተኞች፣ በሰዶም የሚጠረጠሩ ሰዎችም ሲኖሩ የአእምሮ ህመምተኞችን የእንቅልፍ ክኒን (ናርጋቲን) እየወጡ ማስተኛት የተለመደ የየለት ተግባር ነው፡፡ ወጣቱ እስረኛ በግብረ ሰዶም ተጠርጣሪው ጋር መተኛት ስለሚፀየፍ ተጠርጣሪው ብቻውን እንዲተኛ ይፈረድበታል፡፡ ፖሊሶች ግን ድርጊቱን ያወግዙታል፡፡ በእርግጥ ጤነኛው ታሳሪም እስር ቤቱን ከመጥላቱ የተነሳ የሽንት ቤት ቆሻሻ ሰውነቱን ተለቅልቆ እርቃኑን ሆኖ እስረኛውን ማሯሯጥና በበሽተኛ ሂሳብ ወደ አዲስ አበባ ለመዘዋወር ይሞክራል፡፡ ሌሎች እስረኞች ደግሞ አንገት፣ ሆድና ክንዶቻቸውን በምላጭ በመተልተል ደም እያዘሩ በዱላ በማሯሯጥ ወይም ዛፍ ላይ ተሰቅለው (ተንጠልጥለው) የተጓደለብን ፍትህ ካልተመለሰልን አንወርድም በማለት ያንገራግራሉ፡፡ የአስተዳደሮች መልስ ታዲያ ወንድ ከሆንክ ራስክን ፈጥፍጥ ወይንም ጉሮሮህን ቆርጠህ ሙት የሚል ነው፡፡ ለእነሱ የእስረኛው ስነ ልቦና መቃወስ ምናቸውም አይደለም፡፡ በእርግጥ የእየራሳቸው የስነ ልቦና ደረጃ ከታራሚው ቢያንስ እንጂ የሚስተካከል እንኳ አይደለም፡፡ የስነ ልቦና አማካሪዎች ቢኖሩም ጥርሳቸውን ከመፋቅ የዘለለ ተግባር ሲፈፅሙ አይታዩም፡፡ አንድ ሊፈታ የተቃረበን እስረኛ ከድርጊቱ ታቅቦ ጥሩ ዜጋ ይሆን ዘንድ አገልግሎት ለመስጠት ይሞክራሉ፡፡ ወራትን ዓይንህ ለአፈር የተባለ ሰው የሶስት ቀን የምክር አገልግሎት በመስጠት ለመቀየር ወይስ ለማደንቆር! አንዳንዶች ከምክር አገልግሎት ሲመለሱ መለወጥ ይቻላል ካለ ራሱ የማይለወጥ የቁም እስረኛ ሆኖ የሚሰራ ለእኔ ብሎ ነው? እያሉ ያሾፉበታል፡፡ የህግ አማካሪ፣ ቅሬታ ሰሚ፣ በአካል (በስም) ደረጃ ቢኖሩም በራሳቸው ላይ ለቢሯቸው ስያሜ ካወጡት የመፃፊያ ዋጋ የሚበልጥ ተግባር ፈፅመው አያውቁም፡፡ እስር ቤቱ በሚጣሉ ፖሊስ (አባል) በተጋጩ፣ ከቤት አስተዳደር የተነጋገሩ እስረኞች ከጉልበት ቅጣት፣ ከጨለማ ቤት፣ ከዱላ፣ በኋላ ‹‹51›› የሚል ክስ ይመሰረትበታል፡፡
ክሱ የማረሚያ ቤቱን ደንብ መተላለፍ ሲሆን ቅጣቱ የአመክሮ አንድ ሶስተኛ ያስፈርዳል፡፡ አንድ አመት አመክሮ ያለው አራት ወር ይፈረድበታል፡፡ ጥፋቱ ከበድ ካለም ዱላው፣ የጉልበት ቅጣቱ፣ ጨለማ ቤት እስሩም ጨምሮ ክሱ ከበድ ይልበታል፡፡ ሙሉ አመክሮውን እስከማስፈረም ይደርሳል፡፡ በቅጣት ዙሪያ አንድ አይነተኛ ምሳሌ አለ፡፡ ከቤተ መፅሃፍት ተውሶ መፅሀፉ የጠፋበት እስረኛ የጉልበት ቅጣት የመፅሃፉን ዋጋ እስኪከፍል ጨለማ ቤት ከዛ ‹‹51›› ክስ ተመስርቶበት አመክሮውን ይነጠቃል፡፡ ወንጀሉ መፅሃፍት ማጥፋት ነው፡፡ በእርግጥ ይህ ያ የእስረኛ ዳግም መፅሃፍ ስለማያወጣ የአንባቢዎችን ቁጥር ለመቀነስ ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ አመክሮ ማለት የፍርድን አንድ ሶስተኛ ማለት ሲሆን መልካም ስነ ምግባር ያሳየ እስረኛ በፍርዱ መጠን አንድ ሶስተኛው ተቀንሶለት እንዲፈታ የሚደረግበት አሰራር ነው፡፡ ይህን እድል ለማግኘት በተለያዩ የስራ መስኮች መሰማራትና በእስር ቤቱ ቆይታ ልክ ማገልገል ግዴታ ነው፡፡ እስረኛው በቤት አስተዳደር፣ በአስርና ሀያ መሪ የቤት ካውንስሊንግ፣ በረኛ (በር ጠባቂዎች) የቤትና ሽንት ቤት ፅዳተኛ፣ ጎለኛ (ለእስረኛ ወጥና እንጀራ የሚያመጡ)፣ መስክ በመስራት እድሉን ለመጠቀም ይሞክራል፡፡ በክስ እስኪነጠቅ ድረስ! መስክ ማለት ማረሚያ ቤቱ የእርሻ ማሳ ስላለው ይህን ማሳ መንከባከብና ከብቶችን መንከባከብ ይጨምራል፡፡ መስክ ሲባል ችግኝ መደብ፣ እሳር አጫጅ፣ ከብት አላቢ፣ ደረቅና ማንጎ የሚባሉ ክፍሎችን ሲይዝ መቆፈር፣ ማጨድ፣ ማረም፣ መቁረጥ፣ መመንጠር፣ እና መሰል ተግባራት ሲኖሩት ስራው እጅግ አድክሚ ነው፡፡ ከስራው በላይ ግን ለጆሮ የሚሰቀጥጠው የክፍያ መጠኑ ነው፡፡ አንድ መስከኛ በቀን 5 ብር ይከፈለዋል፡፡ የመቶ ብር ስራ ሰርቶ 5 ብር ለንጽጽር የማይመች ክፍያ ነው፡፡
ወፍጮ ቤት፣ ሚንስ ቤት በቀን 8 ብር፣ ጉልኛ ለቀን 2 ብር፣ ዘበኛ (በረኛ) 2 ብር፣ የቤት ጽዳተኛ 2 ብር፣ የሽንት ቤት ጽዳተኛ 5 ብር፣ ከፍተኛው ክፍያ 8፣ ዝቅተኛው 2 ብር ነው፡፡
በአጠቃላይ ሸዋሮቢት እስር ቤት 4400 በላይ እስረኛዎችን ይይዛል፡፡ እስር ቤቱ ይህን ያህል ዜጋ ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ አጭቆ ያሳድራል፡፡ በዚህ ሁኔታ ጥፋተኛን ማረም ይከብዳል፡፡ በእርግጥ ስርዓቱ ለችግሮች መፍትሄ መሻት ባይፈልግም ጦሱ ከህብረተሰቡ ጀርባ የማይወርድ በመሆኑ መንግስትን ትተን በየግላችን ተስፈኛ ወጣት የማፍራቱን ተግባር ከፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትግሉ ጋር ልናስኬደቀው ይገባል እላለሁ፡፡
አምላክ ሀገራችንን ይባርክ!

ወያኔ ለተራቡ ወገኖች እርዳታ ማድረግ የምትችሉት እኔ ስፈቅድና በእኔ በኩል ብቻ ነው አለ

የወያኔ ተላላኪዎች በኩዌትና ባህሬን ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያኖች ባስተላለፉት መግልጫ አዘል ትእዛዝ እንዳሉት ከሆነ “በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረጉ እርዳታዎችና ገንዘብ ማሰባሰቦች እኛ ስንፈቅድና በእኛ አማካኝነት ብቻ ነው” ብለዋል።

የመግለጫው ሶስተኛ አንቀጽ እንዲህ ይነበባል፣

“…በሌላ በኩል ጉዳዩ ከልብ አሳስቧችሁ ነገር ግን ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለው ሁኔታ እንዲሁም ሕጋዊ አካሄድን ሳይከተል “ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል የተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎችን በመጠቀም ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ የምትገኙ ሁሉ ይህንን ህገወጥ ተግባር እንድታቆሙ፣ ሌሎቻችሁም በየዋህነት በእንቅስቃሴው እንዳትሳተፉ እንጠይቃለን”።

“ችግሩ እስካሁን ድረስ ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ አልወጣም፣ በሰዎች ላይም አደጋ አልደረሰም” ሲል ያተተው መግልጫ… በመጨረሻም መንግስት እርዳታ የሚፈልግ ከሆነ እኛ ስንጠይቃችሁ ያን ጊዜ ገንዘቡን ለኛ ትሰጣላችሁ ብሏል።

ይህ በዚህ እንዳለ ታዋቂው የመብት ተሟጋች አርቲስት ታማኝ በየነ እና ሌሎችም የሚሳተፉበት “ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት” በመባል የሚታወቀው የሰብአዊ መብት ማኅበር ሰሞኑን ባወጣው መግለጫማህበሩ ከዚህ ቀደም በሳውዲ አረብያ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ፈጥኖ እንደደረሰ ሁሉ አሁንም አግባብ ካላቸው የአለም ዓቀፍ ረድኤት ድርጅቶች ጋር በመነጋገርና በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር በፍጥነት በርሃብ ለተጎዱ ወገኖች እርዳታ ለማሰባሰብ በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ አስተዳደር ጥንት ጫካ በነበረበት ሰዓት በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ከረሃብተኛው አፍ ነጥቆ መውሰዱን ቢቢሲ እና በወቅቱ የወያኔ አመራር አባል የነበሩት አቶ ገብረመድህን አርአያ ማጋለጣቸው ይታወሳል።

Ethiopia will be in need of food aid

አቶ በረከት ስምዖን “ኢሕአፓ ትልቅ አቅም ይዞ ተነስቶ ያንን ያባከነ ድርጅት ነው” አሉ

Bereket Simon
15 ሚሊዮን ሕዝብ ተርቦ በሚሊዮኖች ብሮች እየፈሰሰ እየተከበረ በሚገኘው የብአዴን (ብዙዎች “በድን” ይሉታል) 35ኛ ዓመት በዓለን አስመልክቶ ሽር ጉዱ እንደቀጠለ ነው:: ፍርፋሪ እየተወረወረላቸው ወይም በተስፋ የሚሰሩት መንግስታዊ ጋዜጠኞች የተለያዩ ባለስልጣናትን ቃለምልልስ እያደረጉ በማቅረብ ላይ ናቸው:: ከነዚህም መካከል በቅርቡ ሞተዋል ተብሎ የተዘገበላቸውና በኋላም አልሞቱም ተብሎ የተወራላቸው አቶ በረከት ስምዖን (ብዙዎች በቁማቸውና በሕዝብ ልብ ውስጥ ከሞቱ ቆዩ ይሏቸዋል) ቃለምልልስ ተደርጎላቸዋል:: በአማራ ክልል ቴሌቭዥን ላይ የቀረቡት አቶ በረከት በአብዛኛው ለማውራት የፈለጉት ስለኢሕ አፓ ነው:: “ኢሕአፓ ትልቅ አቅም ይዞ ተነስቶ ያንን ያባከነ ድርጅት ነው” ያሉት የአቶ በረከትን ቃለምልልስ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ዘ-ሐበሻ እንደወረደ አስተናግዳዋለች::

ጋዜጠኛው አቶ በረከትን ሲያስተዋውቅ እንዲህ ይላቸዋል “በጐንደር ከተማ አስተዳደር አባጃሌ ተብሎ በሚታወቀው ቀበሌ ውስጥ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዚያው በጐንደር ከተማ ተምረዋል፡፡ ከ1967 እስከ 1968 ዓ.ም እድገት በህብረት ዘመቻ አዲርቃይ ከተማ ተመድበው አገልግለዋል፡፡ ከሀምሌ 1968 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ /ኢሕአፓ/ ተቀላቅለዋል፡፡ ኢሕአፓ ሲፈራርስ ከኢሕአፓ ወጥተው ኢሕዴንን ከመሰረቱት ነባር ታጋዮች አንዱ ናቸው፡፡”

ቃለምልልሱን እንደወረደ እነሆ:-

ወደ ኢህአፓ እንዴት ተቀላቀሉ?

የ1960ዎቹ መጀመሪያ የኢትዮጵያ አብዮት ንቅናቄ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ወቅት ነበር:: በወቅቱ የነበሩት ተማሪዎች በጣም ብስለት ያላቸው ሀሣቦች እያነሱ አገሪቱን ይመራ የነበረውን ዘውዳዊ አስተዳደር ይሞግቱ፣ ይታገሉ ነበር:: ትግሉ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው ደግሞ ያኔ በነበሩት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አማካኝነት ነው:: ይህ ግን በእነሱ ብቻ የታጠረ አልነበረም:: ብዙም ሳይቆይ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተዛወረ:: ዘውዳዊውን አገዛዝ በመቃውም የዴሞክራሲ ስርዓት እንዲገነባ፣ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የአርሶ አደሩ የመሬት ባለቤትነት እንዲረጋገጥ፣ ሙሰኝነት እንዲወገድ፣ የብሔሮች እኩልነት እንዲከበር ትግል ይካሄድ ነበር:: በ1960ዎቹ መጀመሪያ በተለይም ከ1963 ዓ.ም ጀምሮ እኛም ወደ ተማሪዎች ነቅናቄ መቀላቀል ጀመርን:: ሁኔታው ከዚያ በፊት የነበሩት ትልልቅ ተማሪዎች የሚያነሷቸውን በጣም ብስለት የተሞላባቸው ሀሣቦች እንድንሰማ፣ ለፖለቲካ እንድንጋለጥ ሠፊ እድል ሰጦን ነበር::

በዚህ መሠረት እኛም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሆነን ትግሉን ተቀላቅለናል:: ቀስ በቀስ የህዝቡ ትግል እየተጠናከረ ሂዶ በ1966 ዓ.ም መላው ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ንጉሳዊውን አስተዳደር መታገል ይጀምራል::ትግሉ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ሲደርስ የተማሪዎች ንቅናቄ ያንን ትግል ወደ ፖለቲካዊ ስልጣን ለማምጣት የሚያስችል ብልሀት ጐድሎት ተገኘ:: ይህን ጉድለት ለመሙላት የፖለቲካ ፓርቲ መመስረት በጣም አስፈላጊ ሆኖ መጣ:: ይህን ተከትሎ ብዙ ድርጅቶች ተመሰረቱ::

ኢህአፓ፣ መኢሶን፣ ህወኃት፣ ኢኮፖ/ኢትዮጵያ ኮሚኒስት ፓርቲ/ የመሳሰሉ በርካታ ድርጅቶች መመስረት ቻሉ:: ከተመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በወቅቱ በመሀል ሀገር ሰፊ ተቀባይነት የነበረው ድርጅት ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ/ ኢሕአፓ/ ነበር:: ስለዚህ እኛም እ ን ደ ማ ን ኛ ው ም የድርጅት ጥማት እ ን ደ ነ በ ረ ው ወጣት ኢሕአፓን ለመቀላቀል ቻልን::

ስለዚህ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ ኢሕአፓን በአባልነት ለመቀላቀል በቃሁ:: ስለኢሕአፓ ምን ይላሉ? ኢሕአፓ ሲጀመር ዴሞክራሲያዊ የትግል ፕሮግራም ይዞ የተነሳ ድርጅት ነው:: በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት በህብረተቡም ፣ በወጣቱ ትውልድም የነበረውን ከፍተኛ ጉጉትና ፍላጐት ተንተርሶ ፕሮግራሙን የቀረፀ ድርጅት ነው:: ስለዚህ በመጀመሪያዎቹ ወቅቶች ላይ ብዙ ሊሻሻሉ የሚችሉ ችግሮች እንዳሉት ሆኖ ኢሕአፓ የሚያታግል ድርጅት ነበር::

በማንኛውም የድርጅት ፕሮግራም ሲጀምር ባለቀለት መልኩ ምንም መሻሻል በማይፈቅድ መልኩ አይደለም የሚዘጋጀው::በሂደት ሊሻሻል የሚችልበት እድል እንደተጠበቀ ሆኖ ለመነሻ ያህል ግን አስፈላጊዎችን የትግል አላማዎች በትክክል የያዘ፣ የትግሉን ስትራቴጅዎች በወሳኝነት የሚያመለክት ሆኖ ከተዘጋጀ ብቁ የትግል መሣሪያ ሆኖ ሊወሰድ የሚችል ነበር:: ኢህአፓም የዚህ አይነት ፕሮግራም ነው የነበረው:: ህውኃትም በወቅቱ የነበረው ፕሮግራም፣ ሌሎች ፓርቲዎችም የነበራቸው ፕሮግራም በሂደት ነው እየተሻሻለና እየጠራ የመጣው::

ስለዚህ ድርጅቱ ለሁላችንንም ሊያታግል የሚችል ፕሮግራም ይዞ የተነሳ ነበር:: በሂደት ፓርቲው ይህን ፕሮግራም ተከትሎ በጽናት መታገልና ይበልጥ እያሻሻለው የሚሄድ እድል ቢኖረውም ይህን ግን ሳይጠቀምበት ቀረ::

1966/1967 ዓ.ም በኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ በጣም ብዙ ድርጊቶች የተፈፀመበት ወቅት ነበር:: ደርግ ወደ ሥልጣን መጣ:: ደርግ ወደ ሥልጣን እንደመጣ የአርሶ አደሩን ትግል ለመግታት መሬት ከፌውዳሎች መንጠቅ የጀመሩ አርሶ አደሮችን አረፋችሁ ተቀመጡ፣ ፊውዳሎችን እንዳትነኳቸው ማለት ጀመረ:: ነገር ግን ደርግ የአርሶ አደሩን ትግልሊያቆመው አልቻለም:: አርሶ አደሩ በጉልበት መሬት መንጠቁን በተለይ በኦሮሚያና በደቡብ በሰፊው ቀጠለ:: በዚህ የተነሳ የመሬት አዋጅ ለማወጅና ትግሉን ለማቀዝቀዝ የተገደደበት ሁኔታ ተፈጠረ:: የመሬት አዋጅ ሲታወጅ ኢሕአፓ ላይ ትልቅ ፈተና መጣ::
Berekey simon

ኢሕአፓም የመሬት አዋጅ የአርሶ አደሩን ጥያቄ መልሶለታል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰ:: ነገር ግን “አርሶ አደሩ መሬት ቢያገኝም ዴሞክራሲን አላገኘም፣ መሬት ቢያገኝም ስልጣን አላገኘም፣ መሬት ቢያገኝም የብሔር ጥያቄው አልተመለሰትም ነበር:: እነዚህ ምክንያቶች ቢኖሩም ኢሕአፓ አርሶ አደሩ ለትግል የተመቸ አይደለም” ወደሚል መደምደሚያ ላይ ደረሰ:: ስለዚህ ትኩረቱ ሁሉ በከተሞች ወደሚካሄድ ትግል አዘነበለ:: በከተሞች ደግሞ ደርግ የተከማቸ አቅም ይዞ የተቀመጠበት ሁኔታ ነበር:: ወታደሩ፣ የትራንስፖርት አቅሙ፣ የጦር መሣሪያው፣ የእዝ ሠንሰለቱ፣ የኮሙኒኬሽን መሳሪያው በሙሉ የተከማቸው ከተማ ላይ ነው::
ስለዚህ ኢሕአፓ በከተሞች የትጥቅ ትግል ደርግን እጥላለሁ ማለት ሲጀምር ያልተመጣጠነ ግጥሚያ ውስጥ መግባት እንደማይቀርለት የታወቀ ነበር:: የምትገጥመው ተቀናቃኝህ ሀይሉን በሚያከማችበት ቦታ ላይ ሂደህ የምትገጥም ከሆነ ከውድቀት በስተቀር ሌላ እድል የለህም:: የሽምቅ ውጊያ ህግ የሚለው የጠላትን/የተቀናቃኝህን/ ስስ ብልቶች እያየህ ማጥቃት አለብህ ነው:: ኢሕአፓ ግን የጠነከረውን ብልት፣ የጠነከረውን የደርግ አቅም መርጦ መፋለም ጀመረ:: ከዚህ በኋላ ብዙ ነገር ከእጁ እየወጣ እየተበላሸ ሄደ::
ኢሕአፓ በከተማ የትጥቅ ትግል ላይ ሲያተኩር፣ በመፈንቅለ መንግስት ሥልጣን እይዛለሁ ብሎ ሲያስብ በረሀ ላይ ያቋቋመውን ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ወደ መዘንጋት ሄደ:: በዚህ የተነሳ ለሰራዊቱ ብቁ አመራር ለመስጠት የሚያስችላውን እንቅስቃሴ ማካሄድ አቆመ:: ከዚያ በረሀ የነበረው ሀይልም እውነተኛ ተዋጊ ሀይል ሆኖ ሊገነባ አልቻለም:: ከዚህ ይልቅ እንደማቆያ ምናልባትም በከተማ ያለው ትግል ከተሳካ ያንን ደግፎ ኢሕአፓ የማታ ማታ መጠቀሚያ ሊያደርገው የሚችል ሠራዊት ከመሆን በዘለለ እውነተኛ ተዋጊ እንዲሆን ለማድረግ የተደረገ ትግል አልነበረም:: ይህ ሠራዊቱ ውስጥ የነበሩና ለትግል የተዘጋጁ ብዙ ወጣቶችን ሞራል በከፍተኛ ደረጃ የሚጐዳ ሆኖ ነበር::

ወጣቶቹ “የእንዋጋ” ጥያቄ ያቀረቡት ገና ከጠዋቱ ነበር:: በ1968 ዓ.ም ወደ ትግሉ ተቀላቅየ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ “ለምንድን ነው ወደ ጦርነት የማንሄደው? ለምንድን ነው የማታዋጉን” የሚል ጥያቄ እስከመነሳት ደርሶ ነበር:: 25 የማይማሉት የፀለምት ታጋዮች ይህን መሠል ጥያቄ ያቀረቡ ነበር:: ይህን ለመሰለው ታጋይ ግን ብቃት ያለው አመራር
አልተሰጠውም ነበር::

ይህ በሰራዊቱ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች እንዲነሱ በር ከፍቷል:: የከተማውን የትጥቅ ትግል ፋይዳ፣ ብስለት አስመልክቶ መጠየቅ ተጀመረ:: ኢሕአፓ ግን ለጥያቄዎች መልስ ከመስጠት ይልቅ ጥያቄ ያነሱ ታጋዮችን በአንጀኝነትና በፀረ ድርጅትነት እየፈረጀ ማሰር፣ መምታት ጀመረ:: የታጋዮች መታሰርና መመታት እንደገና ሌላ ጥያቄ መቀስቀስ ጀመረ:: ውስጠ ዴሞክራሲው ክፍተት እንዳለበትና ብዙ መሻሻል ያለበት ነገር እንዳለ በፓርቲው አባላት ዘንድ ጥያቄ ሆኖ ተነሳ :: አልፎ ተርፎም ከሌሎች ብሔራዊ የትግል ድርጅቶች ጋር ውጊያ ውስጥ የገባበት ሁኔታ ስለነበር ይህም ትክክል አይደለም “ለምንድን ነው ከትግል ድርጅቶች ጋር የምንዋጋው?” የሚል ጠንከር ያለ ጥያቄ በአባላቱ ዘንድ በስፋት መነሳት ጀመረ::

ስለዚህ ኢሕአፓ ጥሩ ጀምሮ፣ ሊሻሻል የሚችል ብዙ ነገር ነበረው:: ነገር ግን አመራሩ ይህንን በብቃት መምራት ባለመቻሉ ምክንያት ነገሮች ከእጁ እየወጡ ድርጅቱን በስኬትሳ ይ ሆ ን በውድቀት ጐዳና እንዲራመድ አድርጐታል:: ሌላ የፖለቲካ ድርጅት ከመመስረት ይልቅ ኢህአፓን አጠናክሮ መስቀጠል አይቻልም ነበር ወይ? ኢህአፓን አጠናክሮ እንደገና እንዲደራጅ ማድረግ አይቻልም ወይም ይቻላል ያከራክራል:: ለምን አልተሞከረም? ለሚለው ጥያቄ ግን መልሱ ሞክረናል ነው:: ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄው የመጀመሪያ አላማ አድርጐ የያዘው ኢሕአፓን ማቅናት ነበር::

ኢሕአፓ ብዙ መስዋዕት የተከፈለበት ድርጅት ነው:: ይህ ድርጅት ያሰባሰበው ቀላል የማይባል የሠው ሀይል ነው:: በኢትዮጵያ በመሀል ሀገር ከነበረው ወጣት ምርጥ የሚባለውን ሀይል አሰባስቦ ይታገል የነበረው ድርጅት ነው:: ስለዚህ ይህንን ሀይል ከማፋረስ ወይም በሌላ ከመተካት ይልቅ አስተካክሎ ወደ ተሻለ ብቃት ለመምራት የሚቻልበት ሁኔታ ቢኖር ኑሮ ተመራጭ ይሆን ነበር:: በመጀመሪያ የተደረገው ሙከራ ይሄ ነበር:: ይህ ሙከራ እንዲሳካ ለማድረግ ጥረት የተደረገው መሪዎችን በመቀየር ጭምር አይደለም:: ለምሳሌ ኢሕአፓ በ1972 ዓ.ም ሊካሄድ የታሰበው ጉባኤ ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን፣ አመራሩም ተስተካክሎና ታርሞ እንዲቀጥል ማድረግ ይገባናል ብለን ነበር:: አመራሩ እንዲስተካከል ለማድረግ ደግሞ የታጋዮቹ ወኪል የሆነ ኃይል በአመራሩ ውስጥ መግባት አለበት፣ ከታች አመራሩን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ሠዎች ሁሉ ማስገባት አለብን የሚል ንቅናቄ ማካሄድጀምረን ነበር::

ስለዚህ ኢሕአፓን አስተካክሎ መቀጠልየመጀመሪያው ፍላጐት ነበር:: ነገር ግን የኢሕአፓ መሪዎች በነበራቸው ግትርነት ለዴሞክራሲያዊ ሀሣቦችና ጥያቄዎች በነበራቸው ጥላቻና ፍርሀት ምክንያት ሊሳካ አልቻለም:: ኢህአፓ ሀሣቡን ተቀብሎ ከማስተካከል ይልቅ ወደ ማሰር አመራ:: ልዩነቱ በቀላሉ እንዳይታረቅና በቀላሉ እንዳይጠገን የሚያደርግ ግፊት አደረጉ:: ይህ ግፊት በዋነኛነት ለታጋዮች ጥያቄዎች ቀና ምላሽ ባለመስጠት የሚገልጽ ነበር:: አንደኛው ችግር ይሄ ነው:: ሁለተኛው ተጨባጭ ችግር በለሳ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት ጠገዴና አርማጭሆ በሚባሉ ሪጅኖች /ክልሎች/ ላይ የነበረ ነው:: እነዚህን ሪጅኖች/ ክልሎች/ እንደ አንድ አካል ማግኘት ከባድ ነበር::

ስለዚህ መጨረሻ ላይ እያዳንዱ ሪጅን/ክልል/ ለራሱ መቆም የጀመረበት ሁኔታ ተፈጠረ:: አርማጭሆ፣ ጠገዴ፣ ወልቃይት የነበሩት ወደ ሱዳን በቀላሉ ወጡ ወደ ኤርትራ ደርግም በብዛት የገቡበት፣ በለሳ ላይ የነበርነው ደግሞ ለመታገል ሞክረን ሁኔታው አስቸጋሪ ሲሆን ወደ ትግራይ መሄድ የመረጥንበት ሁኔታ ተፈጠረ::

ኢ ሕ አ ፓ ን ለ ማ ቅ ና ት ና አ ስ ተ ካ ክ ሎ ለ ማ ስ ቀ ጠ ል ጥ ረ ት ተ ደ ር ጓ ል : : ነገር ግን በ ኢ ህ አ ፓ አ መ ራ ር እ ም ቢ ታ ና በሁኔታዎች አስገዳጅነት የታሰበው ሊሳካ ባለመቻሉ አዲስ ድርጅት ወደ መመስረት አምርተናል:: ወደ ትግራይ የመሄዱ ሀሣብ እንዴት መጣ?

መጀመሪያ ወደ ትግራይ ከመሄዳችን በፊት 1971 ዓ.ም ህዳርና ታህሳስ አካባቢ ኢሕአፓና ህወኃት ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ ዙር ጦርነት ወልቃይት አካባቢ ይጀምራሉ:: በፊት አካባቢ ጦርነት ሲጀመር በለሳ የነበረው ንቅናቄ አንድ የተጠናከረ ደረጃ ላይ ደርሷል:: በኢሕአፓ ላይም ሙሉ ግምገማ አድርጐ ኢሕአፓ ችግር ያለበት ድርጅት ነው ወደ ሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል:: ኢሕአፓ መስተካከል አለበት የሚል አቋምም ይዟል:: ይህን አቋም ይዞ የነበረው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ኢሕአፓን በመታገል ሂደት እያለ “ ጦርነት ውስጥ ግቡ” ተባልን::

ከብሔራዊ የትግል ድርጅቶች ጋር የሚካሄድ ጦርነት ትክክል አይደለም፤ አንደግፈውም፤ የበለሳው ንቅናቄም ለጦርነቱ አስተዋጽኦ አያደርግም እስከማለት ተደረሰ :: ያም ሆኖ ጦርነቱ ተካሄደና ኢሕአፓ ተሸነፈ:: በዚህ ሁኔታ እያለን ኢሕአፓ ውስጥ የነበረው ቀውስ እየተባባሰ መጣ:: ታጋዩ በብዙ ጉዳዮች ላይ ግራ ተጋባ:: የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣ:: በዚህ ምክንያት ግማሹ ወደ ደርግ መሄድ ጀመረ:: ግማሹ በተናጠል ወደ ቤቱ ተመለሰ:: ግማሹ ወደ ሱዳን ተበተነ::

ይህ ሁኔታ እየጠነከረ ሲሄድ “ምን እናድርግ?” የሚል ጥያቄ አነሳን:: በለሳ ውስጥ ለመቆየት በጣም አስቸጋሪ እየሆነ መጣ:: ደርግ ብዙ ሠራዊት መበተኑን ሲያይ ወታደራዊ ዘመቻዎቹን በተደጋጋሚና በቅርበት መፈፀም ጀመረ:: ሠራዊቱ መዋጋት የማይችልበት ሁኔታ ተፈጠረ፣ አርሶ አደሩ ደግሞ ደርግ የሀልይ ሚዛን ብልጫ እንደወሰደ መመልከት ሲጀምር ኢሕአፓንና ሠራዊቱን ገሸሽ የማድረግ አዝማሚያ እያሳየ መጣ:: ስለዚህ ሁኔታው አስቸጋሪ መሆን ጀመረ::

በዚህ ሁኔታ ንቅናቄው ከዚያ አካባቢ የመቆየት እድሉ ጠባብ ሆነ:: በዚህ ጊዜ “ወደ ትግራይ ብንሄድ ይሻላል” የሚል አቅጣጫ ማውጠንጠን ተጀመረ:: ከመከላከላችን ወደ አርማጭሆ እንሂድ የሚል ሀሣብም ተነስቶ ነበር::

ወደ አርማጭሆ የምንሄደው በደርግ ግዛት አቋርጠን ነው:: የታጠቀ ሠራዊት ይዘን፣ ደርግ የሚቆጣጠረውን ግዛት አቋርጠን ወደ አርማጭሆ መሄድ አደጋው ከፍተኛ ነው:: ሙሉ በሙሉ መጥፋትም ይመጣል:: አርሶ አደሩም የሀይል ሚዛን ብልጫውን ተመልክቶ ወደ ደርግ ያዘነበለበትና እኛን ጠቁሞ መሾሚያ ማድረግ የሚፈልግበት ጊዜ ነበር:: ስለዚህ ያኔ ነጭ መሬት/ነጻ መሬት/ በምንለው በኩል አልፈን መሄድን አንደ መልካም አማራጭ ወስደነው:: ለዚህ ደግሞ የተሻለው አማራጭ ትግራይ መሄድ ነው የሚል ነው:: ከህውሓት ጦርነት ገጥመን የነበረ ቢሆንም አሁን ወደሱ ብንሄድ ኢሕአፓ እንደሚነግረን ላይሆን ይቻላል:: እንደማንኛውም ታጋይ ድርጅት የትግል ፍላጐት ይኖረዋል:: ሲሆን አንድንደራጅ ይተባበረናል:: ካልሆነ ደግሞ ወደ ሱዳን ማለፊያ መንገድ ይሠጠናል:: ገብተን ተደራጅተን ተመለስን በአንዱ የአማራ አካባቢ እንደገና ትግል እንሞክራለን በሚል ሀሣብ ነው ወደ ትግራይ የሄድነው::

ሕወሓት ጋ ምን ጠበቃችሁ?

ትግራይ ስንሄድ ብዙ ነገር ነው ያገኘነው:: ብዙ ነገሮችን ነው የተመለከትነው:: ከሁሉ በፊት እኛ ከቆየንበት ከበለሳ አካባቢ የተለዩ ሁለት ትልልቅ ነገሮችን አግኝተናል:: አንደኛ የትግራይ ህዝብ ሁኔታ ነው:: ሁለተኛ የህውሓት ድርጅትና ሠራዊቱ ሁኔታ ነው:: እነዚህ ሁለቱ ትልልቅ ነገሮች ነበሩ:: በዚያን ወቅት የትግራይ ህዝብ በጣም ከፍተኛ የሆነ የ ት ግ ል መ ነ ሳ ሳ ት እንደነበረው ታዝበናል:: መ ሀ ል ሀገር ያለው ሁኔታ ትግሉ ተቀዛቅዟል:: ደርግ በቀይ ሽብር በወሰደው እርምጃ በጣም ብዙ ወጣቶች ተጨፍጭፈዋል:: የትግል ድርጅቶች ተበታትነዋል:: የህዝቡ የትግል መነሳሳትም ተቀዛቅዟል:: ከዚያ አልፎ ከባድ የሞራል ውድቅት ተከስቷል:: የደርግ መንግስት ባካሄደው ጭፍጨፋ ህዝቡ ከልክ በላይ ስለተቀጣ የተሸማቀቀበትና ግራ የተጋባባት ሁኔታ ነበር::

ትግራይ ላይ ሥንገባ ያየነው ሁኔታ ከዚህ ለየት ይላል:: ህዝቡ በህወሓት እየተመራ የተለያዩ ድሎችን እየተጐናፀፈ ነው:: የተራዘመ የገጠር ትጥቅ ትግል የሚባለው አቅጣጫና ስትራቴጂ በትክክል ተግባራዊ ተደርጐ ውጤት ማምጣት ጀምሯል:: ደርግም በትግራይ ተከታታይ ግዙፍ ዘመቻዎች ያካሄደ ቢሆንም ህወሓትና የትግራይ ህዝብ በጋራ ሆነው ባደረጉት ትግል በብቃት መክተው መልሰውታል:: በትግራይ ነጻ መሬቱ ሠፍቶ ህዝቡ ለሌላ አዲስ ትግል የሚነሳሳበት ሁኔታ ተፈጥሯል:: ስለዚህ በሄድንበት ሁሉ የትግል ወኔን ይበልጥ የሚቀሳቀስ፣ ከታገሉ ይህን የመሰለ ሁኔታ መፍጠር ይቻላል የሚል አስተሳስብ እንድንይዝ የሚያደርግ ተጨባጭ ሁኔታ መመልከት ቻልን::

ህወሓትም ኢሕአፓ ውስጥ እያለን አንስማው ከነበረው የተለየ ነው:: ስንገናኝ በትጥቅ ትግል
አካሄድና በገነቡት ሠራዊት ጥንካሬ በጣም የሚያስቀና ደረጃ ላይ ደርሰው ነበር:: ገና ተፈላጊው የአንድነት ደረጃ ላይ አልደረሱም እንጂ ጠንካራ የሚባል ብቃት ያለው፣ በአግባቡ የተደራጀ፣ በጥሩ ሁኔታ የሚመራ ሠራዊት ገንብተው ነበር:: ተዋግቶ፣ ድል አድርጐ የራሱን ነፃ መሬት ገንብቶ መከላከል የሚችል ሀይል ፈጥረው ነበር:: ይህም ከታገልክ ጥሩ አመራር ማግኘት፣ እንዲህ አይነት የትግል ሠራዊት መገንባት ይቻላል የሚል ትምህርት እንድንወስድ በር የከፈተ ነበር::

በሌላ በኩል ህወሓት ጋ ስንገባ ያገኘነው ሌላው ነገር የአስተሳሰብ ብስለትናግልጽነት ነው:: እኛም ኢሕአፓ ውስጥ ሆነን ስናነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎች በህውሓት ደረጃ ተነሳተው ውይይት ተደርጐባቸው የተሻለ አቅጣጫና ግልጽነት ተይዞባቸዋል:: ስለዚህ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄው ትግራይ ሲገባ ከሞላ ጐደል በጣም የተመቸ ሁኔታ ገጥሞናል:: “መታገል አለብን!”
ብለን መወሰናችን ትክክል እንደነበር የሚያረጋግጥ፣ ወደ መደራጀት እንድናመራ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ
ነበር ::
ረጅም ጊዜ ወስደን በብዙ ነገሮች ላይ ከህወሐት ጋር ለመወያየትና ለመከራከር እንዲሁም በሚያስማሙን መስማማት፣ በሚያለያዩን ነገሮች መለያየት የምንችልባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ማረጋገጥ የጀመርንበት ሁኔታ ተፈጥሯል::

ወደ ትግራይ ከገባችሁበት ጊዜ ኢህዴን እስከ ተመሰረተበት ድረስ ያለው ወቅት ምን ይመስል ነበር?

ያ ስዓት ብዙ ነገሮች የነበሩበት ነው:: መሀል ሀገር ላይ የኃይል ሚዛኑ ተገለባብጧል:: የሀይል ብልጫ ሚዛኑን ደርግ ወስዷል:: በመሀል ሀገር ብቻ አይደለም:: ትግራይ ላይ በተነፃፃሪ የተሻለ ሁኔታ ቢፈጠርም 1969 እስከ 1975 ዓ.ም የቀይ ኮከብ ዘመቻ ድረስ በነበሩት ዓመታት ደርግ የበላይነቱን ያረጋገጠበት ዘመን ነበር::

በዚህ ዘመን መደራጀት አለብን ብለን ስንነሳ መጀመሪያ ያደረግነው ልክ ትግራይ እንደገባን የእርማት እንቅስቃሴ ብለን ራሳችን ንቅናቄው የፈፀማቸው ስህተቶች ካሉ እነዚህን ማረም ጀመርን:: አዲሱ ትግል ከኢሕአፓ ሥህተቶች በፀዳ መንገድ ብቻ ሣይሆን ከራሳችንም ሥህተቶች በፀዳ መንገድ መካሄድ አለበት የሚል አቋም ወሰደን ወደ እርማት እንቅስቃሴ አምርተናል::
የእርማት እንቅስቃሴው ተካሄደ:: የራሳችንን ድክመቶች ሙሉ በሙሉ ወስደን እናስተካክላለን አልን:: አዲሱ መተዳደሪያ ደንባችን ዴሞክራሲያዊ ይሆናል ብለን ያንን በመተዳደሪያ ደንባችን ቀርጽነው:: ይህን ከጨረስን በኋላ የፖለቲካ ፕሮግራማችንን የመንደፍ ሀሣብ ይዘን ተንቀሳቀስን:: የፖለቲካ ፕሮግራማችን በራሳችን ለመንደፍ ጥናቶች ወደ ማድረግ ፣ መከራከርና ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር መስማማት አለበት የሚል አቋም ያዝን::በዚህ ዝግጅት በአብዛኛው ከህወሓት ጋር የሚመሳሰል ግን በተወሰኑ ሁኔታዎች ደግሞ ከህወሓት የተለየና እኛ በምናምንባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የተዋቀረ ፕሮግራም ይዘን ወጣን:: ሦስተኛውና የመጨረሻው የመደራጀት እንቅስቃሴ ነው:: በዚያን ጊዜ በነበርንበት ሁኔታ ይብዛም ይነስም ፕሮግራም ማዘጋጀት፣ የአደረጃጀት መመሪያዎቻችንን ማጠቃለልና ለጉባኤ ዝግጅት የማድረግ ሥራ የምንሰራበት ወቅት ነበር::

የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ኢህዴን/ የተመሰረተበትን ቀን እንዴት ያስታውሱታል?

ለእኔ ትልቅ ቀን ነበር:: ብዙ ጊዜ በትግል በቆየሁባቸው አመታት ውስጥ አንዳንድ ለራሴ የያዝኳቸው ግቦች ተሳክተው ካየሁ በኋላ በትግሉ የሚያጋጥም መስዋእት ቢያጋጥምም ግድ የለኝም የምልባቸው ነገሮች ነበሩ:: ገና ኢሕአፓ እያልን ከኢሕአፓ ወጥተን የራሳችንን ድርጅት አቋቁመን ለትግል የምንነሳሳበትን ሁኔታ አይቼ ብሞት የሚል ሀሣብ ነበረኝ:: ስለዚህ ኢሕዴንን ለመመስረት የነበረው እንቅስቃሴ በጥሩ ሁኔታ ተሳክቶ መጨረሻ ላይ አዲስ ድርጅት በምንፈጥርበት ጊዜ ሁላችንም የተስማን ስሜት በጣም ትልቅ እፎይታ የፈጠረ ነበር:: ድርጅት ምን ያህል አቅም እንደሆነ እናውቃለን::

ኢሕአፓ ትልቅ አቅም ይዞ ተነስቶ ያንን ያባከነ ድርጅት ነው:: እኛ ትንሽ ሆነን ተነስተን ወደ መደራጀት በማምራት ላይ የነበረን ነን:: ህውሓት እንዲህ ትንሽ ሆኖ ጀምሮ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰ፣ ትግራይን ነፃ በማውጣት፣ ለኢትዮጰያ ህዝቦች ትግልም የበኩሉን ማበረከት የሚችልበት ብቃት እየተጐናፀፈ መሄድ የቻለ ድርጅት ነው:: ድርጅት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ምን ያህል ትልቅ የለውጥመሣሪያ እንደሆነ እንረዳ ነበር::

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48360#sthash.rTU7q5Ls.dpuf