የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አርበኞች ማህበር “የአገራችን መሬት ሲቆረስ ፣ ህዝባችን ሲጐዳ እጆቻችንን አጣምረን አንቀመጥም” አለ | መግለጫውን ይዘነዋል

clash
የአገራችን መሬት ሲቆረስ ፣ ህዝባችን ሲጐዳ እጆቻችንን አጣምረን አንቀመጥም !

ከቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት አርበኞች ማህበር የቀረበ ወቅታዊ ጥሪ

እኛ የቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት ዓባላት ለአለፉት 25 ዓመታት በውድ የሃገራችን ሕዝብ ላይ ወያኔ/ህውሃት መራሹ ቡድን የፈፀመውና እየፈፀመ ያለውን ግፍ ፣ በደልና ሰቆቃ እንዲቆም የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ትግል መሆን እንዳለበት እናምናለን ። ይሁን እንጅ የሕዝባችንን ሰቆቃና መከራ፣ ስደትና ዕልቂት ከምንም ባለመቁጠር ይባስ ብለው የሃገሪቷን ልዑላዊነት ለታሪካዊ ጠላቶቻችን አሳልፈው ለመስጠት ሽር ጉድ በማለት ላይ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ የረጅም ታሪክ ውስጥ የሃገሪቷን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፎ ለመስጠት የተደራደረ መንግስት ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ፣ ሃገሩንና ድንበሩን እንዲጠብቅ አደራ የተሰጠውም ወታደርና የፖሊስ ሠራዊት የዚህ እኩይ ተግባር ተባባሪ የሆነበት ዘመን አልታየም።

Read Full Story in PDF

ያሁኑ የኢትዮጵያ ሁነታ፤ ይመስላል የተምታታ – ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

መግቢያ፤

ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

በአሁኑ ሰዓት የወያኔ አገዛዝ በአንድ በኩል በሕዝባዊ እምቢታ፥ በሌላ በኩል በትጥቅ ትግል ተቃውሞ በሰፊው እንደተነሣበት ይሰማል። ስሜትንና አስተያየትን ለሕዝብ ማቅረቢያውን መንገድ የዘመኑ ቴክኖሎጂ ለሁሉም ክፍት ስላደረው፥ ሕዝባዊ እምቢታውንም ሆነ የትጥቅ ትግሉን የሚደግፉና የሚቃወሙ እንዳሉ እያነበብንና እየሰማን ነው። ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው ማናቸውንም ዓይነት ተቃውሞና እምቢታ ቢቃወሙ አይገርምም።ሊታሰብበት የሚገባው ዋናው ጥያቄ የወያኔን አገዛዝ የሚጠሉ አገር-ወዳድ ኢትዮጵያን የትጥቅ ትግሉንና የሕዝቡን ዓመፅ የሚፈሩት በሚገባ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነው። ዋስትና ያለው ታማኝ መልስ የለም። ግን ሁኔታው ግልጽ እንዲሆን ጥያቄው መተቸት አለበት። በእኔ በኩል የሚታየኝን ከመተቸቴ በፊት ሁለት ነገሮችን በሚገባ እንድንረዳ እፈልጋለሁ።

አንደኛ፥ ትግሉን ከሚፈሩት ውስጥ አገር-ወዳድና አገር-ወዳድ መስለው የሚጮሁ ተቃዋሚዎች አሉ። አገር-ወዳድ መሰሎቹን ወያኔዎች በአገር-ወዳዱ ውስጥ የሰገሰጓቸው መሆኑን ሰምቻለሁ። አማራ መስለው ለአማራው እንደሚቆረቆሩትና በክልል እንዲወሰን እንደሚፈልጉት ዓይነት ማለት ነው። ውይይቴ ከአገር-ወዳዶቹ ጋር ነው።

ሁለተኛ፥ አገር-ወዳዱ የወያኔን አገዛዝ በሚገባው ልክ እንዲረዳው ያስፈልጋል። ስለወያኔ አገዛዝ ብዙ ጊዜ የምሰማው (እኔም ሳልለው አልቀርም)፥ “ወያኔ ጨቋኝ ነው”፥” “ወያኔ ፋሺስት ነው”፥” “ወያኔ ሰብአዊ መብት የሚጥስ መንግሥት ነው” የሚሉ አገላለጾች ናቸው። እነዚህ አገላለጾች የሚገልጹት የወያኔን ዘዴ እንጂ የወያኔን ማንነት አይደለም። ወያኔዎች ይጨቁናሉ፤ እንደፋሺስቶች ዘር እየለዩ ሰው ይፈጃሉ። ይኼ ዘዴያቸው ነው። በዓላማ ግን አይመሳሰሉም። የወያኔዎች ዓላማ ዝርፊያ ነው–ድርጅታቸው የዘራፊ ድርጅት ነው።

ስጋቶች፤

ከወያኔ ቀጥሎ የሚመጣውን የሚፈሩ ለሀገርና ለሕዝብ አሳቢዎች “ከዘራፊ (ከማፊያ) የሚብስ ይመጣል ወይ?” ብለው ማሰብ አለባቸው። ወያኔዎች ኢትዮጵያ ለኛ ካልሆነች እናወድማታለን ብለው ምለው ተነሥተዋል። ዓላማቸውን እንዲቀይሩና ዲሞክራሲን አብረን እናስፍን ቢባሉ፥ ብዙ ዓመታት ቢወተወቱ፥ አሻፈረን ብለዋል። እንዲህ ከሆነ፥ የሀገር-ወዳዱ አማራጭ ምንድን ነው? “ከሚያወድሟት ይውሰዷት” ይበል ወይስ የሚመጣውን ደግፎ ውጤቱን ለሁሉ የሚጠቅም ለማድረግ ዘዴ ይፈልግለት?

አገር-ወዳዱን የሚያሰጋው አንዱ የኦሮሞዎች ጥያቄ ነው። ለዚህም ዋናው ምክንያት የሆነው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በማፊያ ቀምበር ተጠምዶ ሳለ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ኦሮሞች ብቻ የተጠቁ አስመስለው ሲናገሩ መሰማታቸው ነው። አገር-ወዳዱ የሚለው “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሲጠቃ ሁላችንም በአንድ ድምፅ እንቃወም፤ የሚጠቃው ኢትዮጵያዊ እንጂ፥ ኦሮሞ፥ ቅማንት፥ አማራ፥ ጉሙዝ፥ . . .፥ እስላም፥ ክርስቲያን አይደለም” ነው።  አማራውንና ኦርቶዶክሱን የበለጠ የሚያጠቁት ለሀገሪቱ አንድነት ማገር ሆነው ስለገኟቸው ነው።

ኢትዮጵያን በአስተዳደር ጊዜ በጎሳ፥ በሃይማኖት መከፋፈል የወያኔ ተንኮል ነው። በአስተዳደርና በፖለቲካ ጊዜ፥ ሀገር የጋራ ነው ሃይማኖትና ጎሳ ግን የግል ናቸው። ለጎሳና ለሃይማኖት ማሰብ  ክፋት የለበትም።ለጎሳቸውና ለሃይማኖታቸው የሚያስቡ ሰዎች ካሉ፥ መከልከል የለባቸውም፤ መብታቸው ነው። መብቱም ባህል ማዳበር ነው፤ ግን መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ሊገባ እንደማይገባው ለጎሳቸውና ለሃይማኖታቸው የሚያስቡም የሃይማኖቻቸውንና የጎሳቸውን ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳይ ሊያደርጉት አይገባም። አገር የጋራ ነው ሃይማኖትና ጎሳ ግን የግል ናቸው።

የከተማዎች መስፋፋት፤

ከተማዎች ሲስፋፉ ከከተማ ውጪ የነበሩ መሬቶችን ወደከተማ ክልል ማስገባት የማይቀር ነው። በዚህ አጋጣሚ መሬቱ ወደከተማ የተከለለለት ሰው ሎተሪ እንደወጣለት ነው የሚቈጠረው። ግማሹን ሸጦ የሚሊዮን ብር ጌታ ይሆናል። በግማሹ ላይ የሚኖርበትንና የሚያከራየውን ቤት ይሠራበታል። ከተራ ገበሬነት ወጥቶ ዘበኛና አሽከር ቀጣሪ ጌታ ይሆናል። ግን ማፊያዎቹ ወዲያው ከተፍ ይላሉ። ገበሬው የወጣለትን ሎተሪ (መሬቱን) ቀምተው ባለቤቱን አልባሌ ቦታ አሽቀንጥረው ይጥሉታል። ተቃውሞው ዛሬ ተጀመረ እንጂ ዘረፋው የተጀመረው ቀደም ብሎ ነው። ማፊያዎቹ ከተማ ውስጥ የሚያበለጽግ ቦታ ሲያዩ ባለቤቱን ወደሩቅ ቦታ ጥለው እነሱ ፎቅ ሠርተውበታል።

በደሉ የደረሰው በኢትዮጵያውያን ላይ ነው፤ የአሁኑን በደል የተቃወሙት ግን ኦሮሞዎች ናቸው። የተፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን እንጂ ኦሮሞዎች ስለሆኑ አይደለም። ገብሬዎቹ ኦሮሞዎች መሆናቸው አጋጣሚ ነው። ጉራጌዎች፥ ዶርዜዎች፥ አማሮች ቢሆኑም ይዘረፉ ነበር። መቃወም ያለብን ማንም ቢዘረፍ ዝርፊያውን  እንጂ ማን ተዘረፈ ብለን መሆን የለበትም። የምናደርገው ግን በወያኔ አስተሳሰብ ለጎሳችን እያሰብን ሆኗል። አማሮች ሲፈናቀሉ የኦሮሞ ድርጅቶች ተቃውሞ ያላሰሙት ስለዚህ ነው። እንዲያውም የአፈናቃሊውና የአራጁ  አካል ሆነው ነበር። ተቃውሞ በተነሣ ቍጥር አገር-ወዳዱን የሚያሳስበው ይኸ ሁኔታ ነው። ማፊያዎች ማንንም ኢትዮጵያዊ ሲዘርፉ፥ ሲገድሉ፥ ሌላው ኢትዮጵያዊ ዝም ካለ የአንድ ሀገር ሕዝብ መሆናችን ይቀራል። ለጎሳ ማድላት ካማረን ጎሳችን ኢትዮጵያ ናት።

የትጥቅ ትግል፤  

በሰሜን በኩል የተነሣው የትጥቅ ትግል የሚያሰጋቸው አገር-ወዳድ ኢትዮጵያውያን አሉ። “እባብ ያየ ልጥ ቢያይ በራየ” (እባብ የነከሰው ልጥ ቢያይ ደነበረ) የሚለውን አባባል “እባብ ያየ እባብ ቢያይ በራየ” እንደ ማለት አይተውታል። አይፈረድባቸውም፤ በኛ ሀገር እንኳን፥ መጀመሪያ ደርግን፥ አሁን ደግሞ ወያኔንና ሻዕቢያን አይተዋል። እነዚህ በትጥቅ ትግል አሸንፈው ሥልጣን የያዙ ድርጅቶች የዲሞክራሲ ስም ሲጠራ ዛር እንደያዛቸው አፋቸው ዐረፋ ይደፍቃል፤ እንደ ተከበበ አውሬ ይወራጫሉ፤ ሰው ይፈጃሉ። “በትጥቅ ትግል የሚመጣ ሁሉ ከነዚህ እንደማይለይ ለምን ከታሪክ አንማርም?” ይላሉ።

ግን አማራጭ ሲጠፋ ከብዙ አንድ አይጠፋም ብሎ ዕድልን መሞከር የግድ ነው። የዛሬው ተቃውሞ ለዕድል ብቻ የሚጣል አይደለም። የታጣቂዎቹ ዓላማ እንደ ወያኔ ራሳቸውን ወይም አንድን ጎሳ ለማበልጸግ አይደለም (የቱን ጎሳ?)። ወያኔዎች ትግል ሲጀምሩ እነማን እንደሆኑ ልጆቹን አናውቃቸውም ነገር። ዓላማቸው ትግራይን ለይቶ ለመጥቀም መሆኑን ግን ሳይደብቁ ነግረውናል። ዛሬ የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱትን ግን እናውቃቸዋለን። የወያኔ ብጤዎች አይደሉም።

ሁለተኛም አገር-ወዳዶች የትጥቅ ትግሉ አካሄድ ካሰጋቸው መድኃኒቱ ተደባልቀው በጦሩና በአመራሩ መሳተፍ ነው። ለመሳተፍ ፈልገው  እምቢ እንደተባሉ አልሰማንም። የምንሰማው ቁጭ ብለው ተቺዎችን ነው። “የምትሰጉትን ውጤት ለማስወገድ ለምን አብራችኋቸው አትታገሉም?” ሲሏቸው፥ “በዚያ በኩል የሚካሄ ትግል ወያኔን ሊጥል አይችልም” ይላሉ። የትጥቅ ትግሉ ውጤት ከሌለው ሊያሰጋቸው አይገባም ማለት ነዋ!! ወያኔዎችም ችላ ይሏቸው ነበር። የምንሰማው ግን ወያኔዎች በየቀኑ የሚያወርዱባቸውን የጥላቻና የፍርሃት ፕሮፓጋንዳ ነው።

ሌላው ስጋት እርዳታው ከኢሳይያስ አፈ ወርቂና ከሻዕቢያ መምጠቱ ነው። “ኢሳይያስና ድርጅቱ ለኢትዮጵያ በጎ አያስቡም፤ ቢያስቡ ኖሮ የኤርትራን መገንጠል ለኢትዮጵያ ችግር መፍትሔ አያደርጉም ነበር” የሚል ነው። ይኸንን ልንክድ አንችልም፤ እውነት ነው። እርዳታቸውን ለማግኘት ስንልም ታሪክ አንከልስም። ኤርትራ ወስጥ አንድነቱን መቃወም የተጀመረው ከፌዴሬሽኑ መፈጠርም መፍረስም በፊት ነው። ሻዕቢያ ጦር ያነሣው ፌዴሬሽኑ በመፍረሱ ምክንያት አይደለም፤ እሱ ሰበብ (casus belli) ነበረ።

ፌዴሬሽኑ ማንንም ኤርትራዊ ያላስደሰተ፥ ትርጕሙ ለሁሉም እንቆቅልሽ የሆነ  ዱብ እዳ ነበር። አንድነቶች የተቀበሉት ውሕደቱን ሲያደናቅፍ ባለማየታቸው ነው። የኤርትራ ፓርላማ ፌዴሬሽኑ እንዲነሣ ሐሳብ ሲቀርብለት፥ የአንድነት አባላት ያሉት፥ “ለመሆኑ ምንድነው እሱ፥ አንድ ሆነን የለም እንዴ? ፌዴሬሽን የሚባለው ለአንድንታችን ገደብ ለመፍጠር የታቀደ ኖሯል ወይ? ኧረ ወዲያ ጣሉት” ነው።

ኢሳይያስ የሚሠራው ሥራና የሚያካሂደው ፖለቲካ ያቺን የነጠቃትን ግዛት ለመጥቀም ብሎ ነው። ከወያኔ በቀር ለያዘው አገር ጥቅም የማይሠራ ገዢ የለም። “ወያኔዎችን የሚቃወሙ ድርጅቶችን የሚደግፈው ለኢትዮጵያ ጥቅም ነው” የሚል ያለ አይመስለኝም። የአንድ ሀገር ገዢዎች ለሌላ ሀገር ጥቅም አይሠሩም። ግን ምክንያቱ ምን እንደሆነ ባናውቅም (ልንጠረጥር እንችላለን) ኢሳይያስ  የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ተቃዋሚዎችን ይደግፋል። የሚፈልገውን ቢያገኝ/ሲያገኝ ድንገት ድጋፉን ሊነፍጋቸው ይችላል። በዚህ ጊዜ የወያኔ ማፊያ ተቃዋሚዎች ግዴታ ድጋፉን  እስካገኙ ድረስ  የሚያደናቅፉ ጥያቄዎችን ሳይሰሙ ቶሎ ቶሎ በድጋፉ መጠቀም ነው። “ጀምበር ሳለ ሩጥ . . .” ዋናው ነገር በሰላማዊ ትግል የዘመቱት የትጥቅ ትግሉን ብቻ ተስፋ በማድረግ የራሳቸውን ትግል እንዳያረግቡ ነው።

መደምደሚያ፤

ትግሉን የሚደግፉና የሚቃወሙ ድምፃቸው በየቀኑ ስለሚሰማ፥ ሁኔታው የተምታታ ይመስላል፤ ግን አይደለም። ምክንያቱ የተለያየ ይሁን እንጂ ዓላማው አንድ ነው። ከአገር-ወዳድ ነን ከሚሉ ሳይቀር መጠን የሌለው ስድብ ሲወርድባቸው ጆቷቸውን ዘግተው ለነፃነት መታገላቸው የሚያስደንቅ ነው።  አሸንፈው፣ ሥልጣን ሲይዙ ማየት እንፈልጋለን። ይዘው እነሱም እንደሌሎቹ የሚያስቸግሩን ከሆነም፥ ዕድላችን ነውና እንደፈረደብ አዲሱን (ሌላውን ዓይነት) ችግር ለማስወገድ እንታገላለን። ወያኔዎች አንገፍግፈውናል።

በዛሬዋ የወያኔው ኢትዮጵያ ውስጥ አማራን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን ሰው መሆንን እንጅ በጎሳ ማሰብን አይጠይቅም !!

welkayt

ከዛሬ 25 ዓመታት በፊት በነበረችው ኢትዮጵያ ሐገርነቷ የዜጎቿ የራሳቸው ሐብት ስለነበረች ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ግዛት ተዘዋውረው የሚኖሩባት ፤ሐብትና ንብረት ያፈሩባት፤ ደስታንና መከራን የተጋሩባት፤ ተጋብተውና ተዋልደው ተተኪ ትውልድ የፈጠሩባት፤ ባሕልና ቋንንቋ የተለዋወጡባት፤ በእምነት የተሳሰሩባት በአጠቃላ የሰው ዘር ምንጭ የሆኑት ውህዳን ነገዶችና ጎሳወች ኢትዮጵያዊ ሆነው ለረጅም ዘመናት የኖረባት ታላቅና ታሪካዊት ሐገር ነበረች። በዚህ አይነት የህዝባችንና የሐገራችን የታሪክ ትውስታ ሲዘከር መዘንጋት የማይገባው የአማራው ውህዳዊ ኢትዮጵያዊነት አስተወፅኦ ነው።

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

ለሰብዓዊ መብት ውይይት መቋረጥ ምክንያት የሆነው የመብት ጥያቄ

በዚሁ ሰፊ አዳራሽ ባለው ጠባብ በር ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጋር ተጋፍቶ የወጣው ለምሳ ነበር፡፡ ርቦታልም፡፡ ደጃፍ ላይ ቆሞ ግን አጠገቡ ከሚታየው የምግብ ገበታ ይልቅ ዩኒቨርሲቲው በር ላይ የሆነ ነገር ቀልቡን የሳበው ይመስላል፡፡ እጃቸው ላይ ደብተርና ስክርቢቶ የያዙ በርከት ያሉ ተማሪዎችና ሌሎችም ተለቅ ተለቅ ያሉ ሻንጣዎች ያነገቡ (አስተማሪዎች ሳይሆኑ አይቀሩም) ሰብሰብ ሰብሰብ ብለው ይታያሉ፡፡ በሩ ተዘግቷል፡፡ የፀጥታ ኃይሎችም በብዛት ይታያሉ፡፡

ከበሩ ገባ ብሎም እዚህም እዚያም በቡድን በቡድን ሆነው የተሰባሰቡ ተማሪዎች ይታያሉ፡፡ የከነከናቸው ነገር ያለመሆኑ ያሳብቅባቸዋል፡፡ ከአዳራሹ የወጡ ሰዎች በእነዚህ ሰዎች ቀልብ የተሳቡ ያህል፣ እነሱም ለታዳሚዎች የማይታየው ከውጭ የሆነ የሚረብሽ ነገር ቀልባቸውን ገዝቶታል፡፡

ምሳውን በመያዝ መቀመጫውን የያዘው አምሐም በሁኔታው ግር ተሰኝቷል፡፡ የምሳ ኩፖኑን እያስረከበ ምግቡን የሚያነሳው ታዳሚ ምን እንደተፈጠረ እምብዛም ግድ ያለው አይመስልም፡፡ ከውጭ ግን መጠነኛ ጩኸት መሳይ ነገር ይሰማል፡፡

‹‹ሰምታችኋል? መውጣት አትችሉም እየተባልን ነው፡፡ በር ተዘግቷል፤›› አምሐ ስልኩን ከዘጋ በኋላ ፍርኃትና ድንጋጤ ፊቱ ላይ ተቀላቅለውበት ያወራ ነበር፡፡ ከታዳሚዎች መካከል ሌላ ወጣት ተማሪ ክፉኛ ደንግጣ ‹‹ምን ተፈጠረ?›› በማለት ጠየቀች፡፡ ‹‹ውጭ ግርግር አለ፡፡ በፌደራሎችና በተማሪዎች መካከል ግጭት ተፈጥሯል፤›› አለ፡፡

ይኼ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሰባት ዓመታት በፊት በተቋቋመው የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል በተዘጋጀው ውይይት የተከሰተ አጋጣሚ ነው፡፡ በታዋቂው የሕገ መንግሥቱ አርቃቂ በአቶ ክፍሌ ወዳጆ የሰላምና የሰብዓዊ መብቶች ማስታወሻ ማዕከል ውስጥ የከተመው የሰብዓዊ መብቶች ተቋም፣ ከሌሎች የዩኒቨርሲቲው ማዕከላት ጋር በመተባበር ጭምር በሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ምርምር የሚያካሂድ ሲሆን፣ የሁለተኛና የዶክትሬት ዲግሪ እየሰጠ የሚገኝ ነው፡፡

ተቋሙ ታኅሣሥ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ከኖርዌይ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና በሰብዓዊ መብት ላይ ባተኮረው ውይይት ግብዣ የተደረገላቸው እንግዶችና ቁጥራቸው በርከት ያሉት የዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተውበት ነበር፡፡ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ውይይት የተደረገበት ይህ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ማስተር ፕላኑን መነሻ በማድረግ የተነሳው ግጭት የመወያያ አጀንዳ የነበረበት ጊዜ ነበር፡፡

በመንግሥት ላይ የሚካሄድ ማናቸውንም ተቃውሞዎች ቀድሞ በመምራት የሚታወቀው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ደግሞ፣ የኦሮሞ ተወላጆች በማስተር ፕላኑና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተቃውሞውን እንዲቀላቀል ተደጋጋሚ ጥሪዎች ቢደረጉለትም ሙከራ እንኳ ያደረገው ነገሮች መርገብ ከጀመሩ በኋላ ነው፡፡ በዋዜማው ታኅሣሥ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. የተቃውሞ መልዕክት የያዙ ወረቀቶች ከተበተኑ በኋላ፣ በዚሁ በርካታ ፕሮፌሰሮችና የውጭ ዲፕሎማቶች የተገኙበት የሰብዓዊ መብት ውይይት የተደረገበት ቀንና ተማሪዎቹ መጠነኛ እንቅስቃሴ አድርገው ከፌዴራል ፖሊስ ጋር  የተጋጩበት ዕለት ሊገጣጠም ችሏል፡፡ ቦታውም ተጋጥሟል፡፡

ውይይት

‹‹የሰብዓዊ መብት አተገባበር በኢትዮጵያ›› በሚለው ርዕስ ላይ የተደረገው ውይይት ከሰብዓዊ መብቶች ጽንሰ ሐሳብ ፍልስፍና ተነስቶ፣ ሴቶችና የፍትሕ አስተዳዳር አተገባበር ድረስ የአንድ ሙሉ ቀን ፕሮግራም ሆኖ፣ ስድስት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እንዲደረግበት ታቅዶ የተያዘ ነበር፡፡ በማዕከሉ ኃላፊ ዶ/ር ይታየው ዓለማየሁ፣ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ምትክ ዶ/ር ዮሴፍ መኮንን፣ እንዲሁም በኖርዌይ አምባሳደር ሚስተር እንድሪያስ ጋርደር የመክፈቻ ንግግሮች የተጀመረ ሲሆን፣ እንደታሰበው እስከ መጨረሻ ሰዓት የዘለቀ ውይይት አልነበረም፡፡

‹‹አገር በቀል የፍትሕ ሥርዓት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር እንቅፋት ይሆን ወይ?›› በዶ/ር አበራ ደገፋ፣ ‹‹የሰብዓዊ መብቶች የፍልስፍና መሠረት›› በዶ/ር በቀለ ጉተማ፣ ‹‹በመካከለኛው ምሥራቅ በዝቅተኛ የሥራ በቤት ሠራተኝነት የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርስ የሥነ ልቦና ችግር›› በዶ/ር ብርቄ አንበሴ፣ ‹‹ጫት ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በተገናኘ›› በዶ/ር የራስ ወርቅ አድማሴ የተዘጋጁ ጥናታዊ ጽሑፎች በአቶ ዘካርያስ ቀንአ የመድረክ መሪነት ቀርበው መጠነኛ ውይይት ተደርጎባቸው ነበር፡፡ የተቀሩት ግን የወኃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል፡፡

ጫት ላይ የቀረበው ጥናት ከአብቃዮች ሰብዓዊ መብት ጀምሮ በቃሚዎች ላይ የሚያሳድረው የጤና እክል ላይ በቀረበው ሐሳብ ላይ ተንተርሶ ቀጣይና ሰፋ ያለ ጥናት እንዲደረግበት፣ እንዲሁም የጋምቤላና የትግራይ ክልሎች የክልከላ ፖሊሲ ሞክረው ለምን እንዳልተሳካላቸው ሲዳስስ፣ መንግሥት በአሁኑ ወቅት ከዘርፉ የሚያገኘውን ገቢ በመጪው ትውልድ ላይ ሊያሳድረው ከሚችለው ጉዳት አንፃር እንዲመዘንና በአገር አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ ፖሊሲ ቢወጣበት የሚሉ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡

እንዲሁም በቅርቡ በሕግ የተከለከለውና እስካሁንም መፍትሔ ያልተደረገለት ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ገቢ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች ወደ መካከለኛ ምሥራቅ መጉረፋቸው፣ ከዚያም አብዛኞቹ እዚያው ከሚገጥማቸው የባህል ግጭት፣ መደብደብና የሥራ መደራረብ በአዕምሮአቸው ላይ እያሳደረባቸው ያለው የጤና ችግር በዝርዝር የቀረበ ነበር፡፡ ‹‹ከስደትና የአዕምሮ ጤና›› የሚለው ይኼው ጥናታዊ ጽሑፍ በዘጠና የስደት ተመላሽ ወጣት ሴቶች ላይ በተሠራው ዳሰሳ፣ ብዙዎች የአዕምሮ ችግር እንዳለባቸው በጥናት አቅራቢዋ ዶ/ር ብርቄ አንበሴ ተረጋግጧል፡፡ የብዙዎቹን ቀልብ የሳበው ይኼው ጥናት ከሰብዓዊ መብት ጥሰት አንፃር የቀረበ ነው፡፡ ሴቶቹ በተሳሳተ መረጃ እንደሚጓዙ፣ አብዛኞቹ በሚደርስባቸው አካላዊና ወሲባዊ ጥቃት ለአካላዊና ለሥነ ልቦናዊ ችግሮች እንደሚጋለጡ ያስረዳል፡፡

ጥናቱ በተሰማሩበት የሥራ ቦታ ከአሠሪዎችና ከአገሮቹ መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ብቻ የተቃኘ ነበር፡፡ ከመጀመሪያው ጥናት አቅራቢዋ የሰውን ልጅ የመሥራትና ሠርቶ የመኖር መብት ላይ ጥያቄ ባለማቅረባቸው፣ ጥናቱ አካላዊ ጉዳት ላይ ከሚገደብ ቢሰፋ የሚል አስተያየት ግን ቀርቧል፡፡ ጥናቱ መንግሥት ሊወስደው የሚገባ ዕርምጃና ከአስቸኳይ የዜጎች መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ አንፃር ቀርቦ ቢሆን፣ ሙሉ ይሆን ነበር ተብሎም በመድረኩ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

‹‹አገር በቀል የፍትሕ ሥርዓቶች ለሰብዓዊ መብቶች መከበር እንቅፋት ይሆናሉ ወይ?›› በሚል በዶ/ር አበራ የቀረበው ጥናት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችን ከባህላዊ ሥርዓት አተገባበር አንፃር የሚዳሰስ ነው፡፡ የቦረናን ማኅበረሰብ በምሳሌነት በመወሰድ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የሚታወቀው አገር በቀል የአስተዳደርና የዳኝነት ሥርዓት የሆነው የገዳ ሥርዓት ቢከበር ‹‹ሕገ መንግሥቱ ውስጥ የተካተተ የሰብዓዊ መብት መርሆች የበለጠ ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳል እንጂ የሚፃረር አይደለም፤›› የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ አጥኚው እንደሚሉት፣ ገዳ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉት ባህላዊ የዕርቅ፣ የዳኝነትና የግጭት አፈታት ዘዴዎች ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና አግኝተው እኩል ተግባራዊ ቢደረጉ፣ በሰብዓዊ መብታቸው ላይ የሚፈጸሙ ጥሰቶች ይቀንሳሉ፡፡

በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን አገር በቀል የዳኝነት ሥርዓትን በመደፍጠጥ የተማከለና አንድ ወጥነት ያለው የፍትሕ ሥርዓት ለመፍጠር መሞከሩ፣ በደርግም ያው ሁኔታ እንደቀጠለ፣ በኢሕአዴግ ዘመን ግን በመርህ ደረጃ በሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 34 እና በአንቀጽ 38 ዕውቅና የተሰጣቸው ቢሆንም፣ በተግባር ግን ወደ ንጉሡ የመመለስ አዝማሚያ እንዳለ በማስረዳት ሥጋታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የቦረና የዳኝነት ሥርዓትን ጨምሮ ለአገር በቀል አስተዳደራዊ ሥርዓቶች ዕውቅና አለመስጠት፣ ከሰብዓዊ መብት ጋር የሚፃረር አካሄድ መሆኑን ተከራክረዋል፡፡

‹‹በአሁኑ ወቅት ‹‹Legal Pluralism›› (የሕግ ብዝኃነት) አልተከበረም ማለት እንችላለን ወይ?›› የሚል ጥያቄ ቀርቧል፡፡ አማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆናቸውን በመጥቀስም አስተያየት ቀርቦ ነበር፡፡ ሌላም ‹‹በባህላዊ የዳኝነት ሥርዓትና በማዕከላዊ የፍትሕ ዳኝነት መካከል ግጭት አይፈጥርም ወይ?›› ‹‹የመጨረሻውስ የትኛው ይሁን ይላሉ?›› የሚሉ አስተያየት አዘል ጥያቄዎችም ቀርበው ነበር፡፡ ለቀረቡላቸው አስተያየቶችና ጥያቄዎች በስሜት መልስ የሰጡት ዶ/ር አበራ ደገፋ፣ ‹‹Why do you impose a law because you think it is good, but the Borena people think it is bad›› [የቦረና ሕዝብ የማይፈልገውን መንግሥት ብቻ ስለፈለገው የራሱ ያልሆነ ሕግ ከላይ ለምን ይጫንበታል?›› በሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ አካሄዱ ከፌዴራል መንግሥት ሥርዓት የሚፃረር መሆኑንም ጭምር ተንትነውታል፡፡

‹‹የጋን መብራት››

የኢሕአዴግ መንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ከሽግግሩ ጊዜ ጀምሮ፣ የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ለመከላከል የተለያዩ የቃልኪዳን ሰነዶች ተቀብሏል፡፡ በ1987 ዓ.ም. በፀደቀውና ሥራ ላይ ባለው ሕገ መንግሥትም አሉ የተባሉትን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዩኒቨርሳል ዶክላሬሽን ኦፍ ሂውማን ራይትስ ሁለንተናዊ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ ቃል ኪዳን (UIDHR) ጨምሮ፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሰነዶች ተቀብሎ ያፀደቀና የፈረመ መንግሥት ነው፡፡ በተግባር ግን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች እንደሚሉት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፈረማቸውን የሰብዓዊ መብት ቃል ኪዳኖች ለመተግበር የሚያደርገው እንቅስቃሴ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በተለይ በኑሮ ዝቅተኛ የሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ሰብዓዊ መብት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማትና ግለሰቦች ሲጣስ፣ ፍትሕ ሲያጣና አቤት የሚልበት አካል ሲጠፋ ይስተዋላል ተብሎ ትችት ይቀርባል፡፡

መንግሥት የአገሪቱን ዜጎች ሰብዓዊ መብቶች ለማስከበር የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አቋቁሞ ለመብቶቹ ጥበቃ እያደረገ እንደሆነ ቢገልጽም፣ በተግባር የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የዜጎች ሳይሆን የመንግሥት ስም እንዳይጠፋ ሲከላከልና ሲጠበቅ የሚውል ነው በሚል እየተወቀሰ ነው፡፡ ለዓመታት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች መርሐ ግብር በማውጣትና በመወያየት ሲዘልቅም ይስተዋላል፡፡ የሰብዓዊ መብቶችን መርሆዎች በማስተማር ላይ መጠነኛ ሥራ ይሠራ እንደሆነ እንጂ፣ ዋናው ሥራው የሆነው ተፈጥሮዓዊ የሆነ የዜጎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሲያጋልጥ፣ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ላይ ሪፖርት ሲያወጣና ለዜጎች ሲከራከር አይስተዋልም ተብሎም ይወቀሳል፡፡

በዕለቱ አንድ የውይይቱ ተሳታፊ ወጣት፣ ‹‹ስለሰብዓዊ መብት ስናወራ ይገርመኛል፡፡ ሰው እየተገደለ ‹አልተገደለም› የሚል የሰብዓዊ መብት ተቋም ባለበት፣ ሰው እየጠፋ ‹አልጠፋም› የሚል የመንግሥት ሚዲያ ባለበት ማን ከማን ጋር ነው የምንወያየው? ሚዲያው የማን ነው?›› የሚል ጥያቄ አንስቶ ነበር፡፡ ወጣቱ ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ከዚያም ወደ ገጠር በተወረደ ቁጥር ሰዎች በየቀኑ የሚጨቆኑበት ሁኔታ እንዳለ፣ የዜጎች ሰብዓዊ መብት ጭራሽኑ እንደሌለ ተናግሯል፡፡ ‹‹እስቲ ወርዳችሁ ተመልከቱ፣ እስቱ ወደ ሕዝቡ ሂዳችሁ ጠይቁ፣ ይነግሯችኋል፤›› ሲል የሰብሰባው ተሳታፊዎች አዳራሹን በጭብጨባ አድምቀውት ነበር፡፡

ወጣቱ አስተያየት ሰጪ ጉዳዩን ከወቅታዊው በኦሮሚያ ክልል ከተነሳው ግጭትና ከመንግሥት ምላሽ ጋርም ለማገናኘት ሞክሮ ነበር፡፡ ለምሳ የወጡ ተጋባዥ እንግዶች ተመልሰው ውይይቱን መቀጠል አልቻሉም፡፡ አምሐ ጌታቸው እንዳለው፣ በአዳራሹ ውስጥ በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ ከግቢው ውጪ ግን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥያቄ ሲነሳ ነበር፡፡ በዋናው ስድስት ኪሎ ግቢ በተነሳው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት የተፈጠረ ሲሆን፣ ፌዴራል ፖሊስ የተቃውሞ ሙከራውን በኃይል አቁሞታል፡፡ ለተወሰኑ ሰዓታት ከግቢው መውጣት አትችሉም ተብሎ የስብሰባው ታዳሚዎችም ቆይተው ነው የተለቀቁት፡፡ በሰብዓዊ መብት ላይ የተጠራው ውይይት የቀትር በኋላ መርሐ ግብር ከአዳራሹ ውጪ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ በተነሳው ተቃውሞ ሳቢያ ተቋርጦ ቀርቷል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያዊያን ህዝባዊ መንግስት መመስረት እና የሐገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰበ፡፡

ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፋ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ውስጥ ትገኛለች፡፡ ( ሰማያዊ ፓርቲ ) #Ethiopia #Blueparty @semayewiparty

ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያዊያን ህዝባዊ መንግስት መመስረት እና የሐገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰበ፡፡
ፓርቲው ‹‹ሕዝባዊ መንግስት መመስረትና የሐገር ሉዓላዊነት መጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት ነው›› በሚል ዛሬ ታህሳስ 20/2008 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፣ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፋ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ውስጥ ትገኛለች፡፡ መግለጫውን የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ም/ሊቀመንበሩ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እና የውጭ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አበበ አካሉ ናቸው፡፡

ሰማያዊ በመግለጫው፣ ‹‹በሀገራችን የደረሰው ግፍና በደል የማስቆምና ህዝባዊ መንግስት የማቋቋም፣ የሀገርን ብሄራዊ ክብር የማስጠበቅ ኃላፊነት የጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ድርሻ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው›› ብሏል፡፡ በመሆኑም ‹‹…ሁሉም ዜጎች አርዓያቸው የሆኑትን የቁርጥ ቀን ልጆች የመስዋዕትነት ጥሪ በመቀበል ቆርጠው እንዲነሱና የድርሻቸውን እንዲወጡ…›› ፓርቲው ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ፋና ወጊና የነቁ ዜጎች የእሳት ራት እየሆኑ ነው ያለው ሰማያዊ፣ ‹‹አርዓያዎቻችንን እያስበላን ዝም ማለታችን አገዛዙ እድሜውን ለማራዘም›› ተጠቅሞበታል ሲል ገልጾዋል፡፡ መንግስት ተጠያቂነት በጎደለው ሁኔታ የፓርቲ አባላትንና አመራሮችን፣ ጋዜጠኞችንና ንቁ ዜጎችን በጅምላ እያሰረ መሆኑን ፓርቲው በመግለጫው አስታውሷል፡፡

በሌላ በኩል የሐገር ድንበርንና ሉዓላዊነትን የሚጠብቁ ዜጎችን መንግስት ‹‹ሽፍቶች›› ሲል መጥራቱ ታሪካዊ የክህደት ምስክርነት በገዛ ዜጋ ላይ መስጠት ነው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው አውግዟል፡፡ — በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር==

(ሙሉ መግለጫው ከታች ተያይዞ ቀርቧል)

“…የተገፋንበት ማጥ፣ እንኳን ተለያይተን አንድ ሆነንም ከተወጣነው ታላቅ ነገር ነው”

በአሊ ጓንጉል | ከ“ህልውና” የተወሰደ፣ 1992፣ ዶ/ር ሰለሞን ይርጋ፣

ይህ ጦማር በኢዲቲንግ ስህተት ተቆርጠው የቀሩ አንቀጾች በስተመጨረሻ ተጨምረውበታል፣ አንባቢያንን ይቅርታ እንጠይቃለን።

የትግራይ ጉጅሌ በህዝብ ላይ ያደረሰው ግፍ እና በደል፣ በአንድ አናሳ በሆነ የትግራይ ጎሳ/ነገድ አባላት በሆኑ ጥቂት ሰዎች አማካይነት እየሆነ ያለው ዝርፊያ ቅጥ ማጣት፣ የፍትህ መጥፋት፣ የሌሎቹ የሁሉም ጎሳዎች/ነገዶች ድምር (አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣ ከንባታ ወዘተ…) አባላት የሆኑ ኢትዮጵያዊያን የገቡበት የድህነት እና የተስፋ መቁረጥ ደረጃ፤ እያንዳንዱ ዘራፊ ባለስልጣን፣ ደህንነቱን የሚመዝነው ባጠራቀመው ገንዘብ/ሃብት እና በስሩ ባሰለፈው አንጃ ብዛት እና (አንጀኞቹ እንደየሚወከሉት ነገድ/ጎሳ/ዘር እና/ወይም የቤተሰብ ዘር ሃረጋቸው እና ስልጣን ደረጃ ልክ ወዘተ…) መሆኑ፤ የአገራችንን ህልውና ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ጥሏል። ጉጅሌው ለዝርፊያ እና ለአገዛዝ እንዲያመቸው የተከለው የጎሳ/ነገድ ፖለቲካ ዛሬ፣ ዘግይቶም ቢሆን፣ ጎጂነቱን ሁሉም ጎሳ እየተረዳው ይመስላል። ግን ከመረዳት በላይ አንድ እርምጃ ተራምዶ መሄድን የሚጠይቅ ጊዜ ላይ ደርሰናል–አበረታች የሆኑ ጅምሮች ቢኖሩም።

ጃዋር ሙሃመድ ከሰሞኑ በኢሳት “… የኦሮሞ ህዝብ በህይወቴ እንደዚህ ተቆጥቶ አይቸው አላውቅም። … ይህን [የኦሮሞ] ቁጣ [የትግራይ ጉጅሌ መንግስት] አሸንፎ ይወጣል ማለት ዘበት ይመስለኛል …” ማለቱን ሰማሁ። እኔ ደግሞ፣ ጉጅሌው ይኸንንም አመጽ አፍኖ ለማስቀረት የማይችልበት ምክንያት አይታየኝም (ዶ/ር መሳይ፣ ይልማ በቀለ ሌሎቹም በቅርቡ በለቀቁት ጽሁፉ ውስጥ አስቀምጠውታል)። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊያኑ የኦሮሞ ጎሳ/ነገድ ተወላጆች ሰልፍ ወጥተው ብቻቸውን ተቃውሞ ሲያሰሙ፣ በትግራይ ጉጅሌ መንግስት ሲገደሉ አሁን የመጀመሪያው አይደለም። ይኸን ያሁኑን አመጽ እና ያስከተለውን ግድያ እንደ አዲስ ነገር አድርጎ ማውራት፣ አምቦ፣ ወለጋ፣ ወዘተ ላይ ከዚህ ቀደም በግፍ የተገደሉ ዜጎቻችንን መስዋዕትነት ዋጋ ማሳጣት ይመስለኛል። የኦሮሞ ጎሳ ብቻ ሳይሆን፣ በአዲስ አበባ፣ ሲዳማ፣ ከንባታ ወዘተ… ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን አገዛዙን ተቃውመው ሰልፍ ወጥተዋል፣ ተገድለዋል፣ ታስረዋል። ሰልፍ የወጡ በወሎ፣ ሸዋ፣ ጎንደር እና ጎጃም ወዘተ የተለያዩ ጎሳ/ነገድ ኢትዮጵያዊያን ተረሽነዋል።

የትግራይ ጉጅሌ እነዚህን ሁሉ የተለያዩ ቁጣዎች፣ በሚዘገንን የግድያ እና እስራት አጸፋ አሸንፎ ወጥቷል (በመሰረቱ እኔ “አሸነፈ” አልልም። በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እና በደል ስብስብ ውጤት፣ ጉጅሌውን እንደ ማዕበል ጠራርቶ እንደሚያስወጣው መገመት አያዳግትም። አስፈሪው ጉዳይ፣ ጊዜው እየረዘመ በሄደ ቁጥር፣ ማዕበሉ ሁሉንም ጠራርጎ እንዳይወስድ ነው)። ለጊዜውም ቢሆን ግን አፍኖ ማስቀረት የማይችልበት ምክንያት አይታየኝም (ይህን ጽሁፍ የጀመርኩት ካንድ ሶስት ቀን በፊት ነው፤ በስራ ውጥረት ምክንያት አልተመለስኩበትም ነበር፣ አሁን ይኸው እየሆነ ያለውን እያየን ነው)። አስፈሪው ነገር የጉጅሌው ግድያ፣ እስራት እና የሃገር ሃብት ዘረፋ እየከፋ እና፣ የዜጎች ችግር እና አበሳ እየባሰ በሄደ ቁጥር፣ ሊከተል የሚችለው ምስቅልቅል ነው።

ይህን ሁሉ ግፍ እና ወንጀል ለመፈጸም ጉጅሌው ወትሮም ራሱ ብቻውን ሆኖ አይደለም፣ የየጎሳ/ነገዱ የ“ፖለቲካ ነጋዴዎች ”ን እጅ ተጠቅሞም ነው። የ“ፖለቲካ ነጋዴዎች” ስል እንደ ኦህዴድ ያሉትን ብቻ ማለቴ አይደለም። እንደ ኦህዴድ እና ኢህዴን አይነቶቹ፣ የለየላቸው ናቸው። አብዛኞቹም የየጎሳው የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ማህበረሰብ ተወካዮች ነን ባዮች “የፖለቲካ ነጋዴዎች”፣ ጉጅሌው መዝዞ የሰጣቸውን ብሄር /ብሄረሰብ የሚሉ ካርታ እየመዘዙ ሲጫወቱ ኖረው፣ እነሆ ጃዋር አሁን እንዳልከው፣ “[ጉጅሌው] … ያቺን አገር በታትኗት እርስ በርስ አጫርሶን…” ሊሄድ ነው።

“እርስ በርስ አጫርሶን ሊሄድ…” እንደሆነ ባደባባይ መናገር፣ ከሩብ ምዕተ አመት በኋላም ቢሆን፣ እሰየው ነው። በጊዜ በጣም ጠቃሚው ጊዜ “አሁን” ነው። ጃዋር ከተናገረው ውስጥ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቆም ብሎ በጥልቀት ሊያስብበት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር “ይህ መንግስት ካሁን በኋላ 5 ወይም 10 አመት ከቆየ– እርሳው። ያቺን አገር በታትኗት ህዝቡን አጫርሶ ነው የሚሄደው … ሌላ የሚያስማማ ነገር እንኳን ቢጠፋ፣ ራስን ከመጥፋት ለማዳን መስማማት ያስፈልጋል” ያለው ነው።

“… እንርሳው”። “ጫወታ ፈረሰ፤ ዳቦ ተቆረሰ” ብለን እንርሳው? እንወክለዋለሁ የምንለው ኦሮሞስ እጣ ፈንታው ምን ይሁን? እርስ በርስ ተጨራርሶ ሲያልቅ እንየው እና … እንርሳው? ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ የለም? ጃዋር፣ እስኪ ራስህን፣ አሁንም ሆነ ከ5 አመት በኋላ አገርቤት እንዳለህ አስበው እና እርስ በርስ እንደሚተላለቀው ህዝብ አንዱ አድርገህ አስበው።

እኔ ጃዋርን ብሆን አማራጩን አያለሁ። “… እወክለዋለሁ/እቆረቆርለታለሁ” የምለውን ህዝብ ከጥፋት ለማዳን፣ እስካሁን የሄድኩበት መንገድ ካልሰራ እና በተዘዋዋሪ መንገድም ቢሆን ለህወሃት የጎሳ/ነገድ መንግስት መሳሪያ ሆኖ መጠቀሚያ ከሆነ … “ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነው፣ አንድ ህዝብ ነን” ብዬ አውጃለሁ፣ በጋራ ለመስራት ብሄራዊ አጀንዳ ይዘው ከሚንቀሳቀሱት ጋር ለመነጋገር በሩን እከፍታለሁ፣ ከመዘግየቱ በፊት። አለበለዚያም፣ ፕሮፌሰር እዝቅኤል ጋቢሳ በቅርቡ በOMN እንደተናገሩት “… ዲያስፖራው ተከታይ ነው መሆን ያለበት፣ …በዚያ አገር ያለውን የወደፊት የፖለቲካ ስርዓት፣ ሼፕ ሊያደርጉት የሚችሉት…ወደፊት ሊኖሩበት የሚችሉት ወጣቶች ናቸው… እነሱ ናቸው ዋና ተጋፋጮች፤ ዲያስፖራው የነሱን አመራር እየተከተለ፣ … ቀድሞ ‘እንዲህ መሆን አለበት…’ ከማለት…የድጋፍ ሰጪነትን ሮል (ድርሻ) ነው መስጠት ያለበት… በውስጡ ያለው ዳይናሚክስ አለ… ያንን ቀደም ብለን ማየት መቻል አለብን።… ወዴት እየሄደ ነው? ለውጥ የራሱ አካሄድ አለው፣ ለለውጡ ዲስትራክቲቭ እንዳይሆን (ከጃዋር “…በሜጫ ነው የምንለው…”፣ “Ethiopia out of Oromia… ” አይነቶቹ አፍራሽ ንግግሮች ማለታቸው ይመስለኛል) ፣… ወደፊት ነው ማየት ያለብን፣ ባለፉት ሞዴሎች ብቻ እንዳንያዝ ማለቴ ነው…”፣ እንዳሉት የህዝቡን ሞት እና መከራ ከማራዘም ይልቅ፣ አገር ቤት መሬት ላይ ያለው ህዝብ ትግሉን በራሱ መንገድ እንዲያስኬድ መተው ነው። ፕሮፌሰሩ “… የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ከሌላው ህዝብ ጥያቄ የተለየ አይደለም..የዲሞክራሲ፣ የልማት እና የሰላም ጥያቄዎች የሰው ልጅ የሆኑ ጥያቄዎች እንደሆኑ በማረጋገጥ ትክክለኛ የሆነ ጥያቄ እንደሆነ መናገር ያስፈልጋል፣… የኦሮሞ መሪዎች ራሳቸው ጥያቄያቸው የሰው ልጅ መብት ጥያቄ እንደሆነ፣ እነዚህ ጥያቄዎች ደግሞ የሰው ልጅ ሁሉ ጥያቄ እንደሆኑ በማረጋገጥ…” መናገር እንዳለባቸው ነው ያሳሰቡት። እውነታቸውን ነው። For every failure, there’s an alternative course of action. You just have to find it. When you come to a roadblock, take a detour. Mary Kay Ash.

“Detour” … ለውጥ መንገድ ማየት ያስፈልጋል። ዛሬም ያንኑ የነገድ/ጎሳ ፖለቲካ ከማራመድ፣ እናም ከ5 ዓመት በኋላ የሚሆነውን ነገር እያዩ ከመርሳት የተሻለ አማራጭ አለ፣ የሚያስማማን ነገርም ሞልቷል። ትንሽ ሰብዓዊ እና ቅን መሆንን ብቻ ነው የሚጠይቀው። ትንሽ አሁን ካሉበት ቦታ ወርዶ፣ “ተሳስቼ ነበር” ማለት ብቻ ይበቃል። መንግስት ካሁን በኋላ 5 ወይም 10 አመት እንዳይቆይ እና ከርስ በርስ መጨራረስ ለመዳን፣ “ራስን ከመጥፋት ለማዳን”፣ የጎሳ/ነገድ ፖለቲካ እና/ወይም ሲቪክ ድርጅቶች ተወካዮች እና ተጠሪዎች፣ ከ“መርሳት” የተሻለ ትልቅ ሚና መጫወት ይችላሉ። እንደሚከተለው፦

1) ጎሳ/ነገድን መሰረት ያደረገ ስም ያለውን የማናቸውንም የፖለቲካ ድርጅት ቢቻል ኢትዮጵያዊ ስም መስጠት፤ የሲቪክ እና ሜዲያ ድርጅቶች እንደፈለጉ ስም ማውጣት ቢችሉም እንኳን፣ ኢትዮጵያዊ አቋም ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ እና ይህንንም ታዋቂ የሆኑት የየድርጅቱ ተጠሪ ግለ-ሰቦች ተሰባስበው አንድ መግለጫ እንዲያወጡ ማድረግ እና በአለም አቀፍ የሜዲያ ድርጅቶች፣ በተለይም አብዛኛውን የኢትዮጵያ ህዝብ ሊደርሡ በሚችሉ ሜድያዎች (ኢሳት፣ ቪኦኤ፣ ጀርመን ድምጽ ሬድዮ፣ አዲስ ድምጽ፣ ኦ.ኤም.ኤን ወዘተ…) በመግለጫ ደረጃ እንዲሰራጭ ማድረግ። እና የየድርጅቱ ተወካዮች እያንዳንዳቸው በመግለጫው ውስጥ ካሁን በኋላ አጀንዳቸው ኢትዮጵያን ከትግራይ ጉጅሌ ነጻ ማውጣት እና ማውጣት ብቻ የሆነ ብሄራዊ አጀንዳ እንደሆነ፣ እስካሁን የተሄደበት መንገድ፣ እንደማያስኬድ መግለጫዎች እንዲሰጡ ማድረግ (ምሉዕነት ባይኖረውም ተጀምሯል። የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር መሪ አቶ ሌንጮ ለታን እና ሌንጮ ባቲ በሩን ገርበብ አድርገውታል። በርግደው መክፈት ያለባቸው ይመስለኛል)፤

2) በትጥቅ ደረጃ ከጉጅሌው ጋር እየተዋደቁ ያሉ ድርጅቶች መሪዎች፣ በመነጋገር አንድ ማእከላዊ አመራር እንዲኖራቸው ማድረግ፤ እና ምንም አይነት የጎሳ/ነገድ ቅጥያ የሌላቸውን፣ ብሄራዊ አጀንዳ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉ፣ ነገር ግን ሁሉም ድርጅቶች፣ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ እና ሂደት፣ የሚያምኑበትን ግለሰብ/ቡድን አመራሩን እንዲይዝ/ዙ ማድረግ።

3) የፖሊቲካ እና የፕሮፓጋዳ ስራው በምንም አይነት አጠቃላዩን የትግራይን ምስኪን ህዝብ የጉጅሌው ደጋፊ አድርጎ ከማየት መቆጠብ ይኖርበታል። እውነታውም ያው ነው። ጉጅሌው በትግራይ ወጣቶችን ለውትድርና እየጠራ እንደሆነ (ጎልጉል ጋዜጣ) እየተነገረ ነው። አያደርግም አይባልም። “የዘራዊነት መጨረሻው እስከ ቤተሰብ ድረስ መሰባሰብ ነው”። የትግራይ ጉጅሌ መሪዎች ዛሬ፣ በትግራይ ህዝብ ስም ተነስተው፣ ኢትዮጵያን በሞላ በቤተሰብ ደረጃ በሚመስል እየዘረፏት ነው። በሚስት እና ልጅ፣ ወንድም እና እህት፣ አክስት እና አጎት እያለ እየወረደ … ያከማቹት ገንዘብ እና ሃብት ያስደነግጣል። ከነሱ የተረፈው ነው ለሌሎቹ እንደነ ኦህዴድ ላሉ የጎሳ/ነገድ መሪ ለሆኑ የ“ፖለቲካ (ደም) ነጋዴዎች” የሚደርሰው። የጉጅሌው መሪዎች ልጆች እና ዘመድ አዝማዶች ዛሬ መሳሪያ አንስተው ቃታ ሊስቡ ቀርቶ፣ እስክሪብቶ የሚጎረብጣቸው ናቸው። የትግራይ ድሃ ልጆች ደግሞ ስለ “ሙስና ሠፈር” እና ባለቤቶቻቸው ብዙ ያውቃሉ። ስለዚህ አብዛኛው የትግራይ ጎሳ እንደሌላው የተገፋ፣ የተገደለ፣ የደኸየ ነው። ይህን ስል በመጠን (ፕሮፖርሽን) ደረጃ፣ የትግራይ ጎሳ/ነገድ ህዝብ ከሌላው ጎሳ/ነገድ ህዝብ በተለየ አልተጠቀመም ማለትም ራስን ማዘናጋት ይሆናል። የጄነራሎቹን ማንነት ማየት ይበቃል። የአማራ፣ ኦሮሞ፣ ከምባታ ወዘተ ጎሳ ተወላጆች በጄኔራልነት ደረጃ ተሰማርተው አገራቸውን እና ራሳቸውን (ከሞራልም ሆነ ከቁስ አኳያ) መጥቀም ይወድላቸዋል። ዛሬ አብዛኛው የመንግስት ቢሮ (ለምሳሌ ኢሚግሬሽን) በአብዛኛው በትግራይ ተወላጆች የተያዘ ነው። መርካቶ ገበያ አዳራሽ ብትገባ እንደቀድሞው በጠንካራ የስራ ባህላቸው የሚታወቁትን ጉራጌዎች አታገኝም። አብዛኛው የትግራይ ህዝብ ግን አሁንም እየተሰደደና በድህነት ውስጥ ያለ ነው። ሁሉንም የትግራይ ተወላጅ ባንድ ላይ የትግራይ ጉጅሌው አባል እና ጠላት አድርጎ ማየት ትክክል አይደለም፣ ከትግራይ ተወላጆች ውስጥ የሚቃወማቸው የለም ማለትም፣ በጉጅሌው በግፍ የተገደሉትን እነ አረጋዊ እና ሌሎቹንም በርካቶች የተሰዉትን፣ የፖለቲካ ስርዓቱን በመቃወም በየእስር ቤቱ ዋጋ እየከፈሉ ያሉትን እንደነ አብርሃም ደስታን እና በስም ያልታወቁ እና በየህቡዕ እስር ቤቱ እየማቀቁ ያሉትን የትግራይ ተወላጆች መርሳት ፍርደ ገምድልነት ነው።

“… በኢትዮጵያዊያን መሃል ጠላትነት የለም። ጠላትነትን የሚፈጥሩት የፖለቲካ ተጠቃሚዎች ናቸው። እነዚህ በፖለቲካ ድርጅት የተደራጁት የህዝባችንን አንድነት ለማስተማር እና አብሮ ለማሰለፍ ካልቻሉ የኢትዮጵያ ህዝብን የሚጠሉ ናቸው። በኢትዮጵያ ህዝብ ስቃይ ራሳቸውን ለማሳደግ የሚፈልጉ ናቸው። …” ይህ ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው በኦሮሞ ሚድያ ኔትዎርክ የተናገረው ነው። የአማርኛ ቋንቋ ፕሮግራም መኖሩ ራሱ በጣም የሚያበረታታ ነው። በተለይ “… ጠላትነትን የሚፈጥሩት የፖለቲካ ተጠቃሚዎች ናቸው…በህዝብ ስቃይ ራሳቸውን ለማሳደግ የሚፈልጉ ናቸው” ሲል የጠቀሳቸውን፣ ዶ/ር ሰለሞን ይርጋ ደግሞ “የደም ነጋዴዎች” ይላቸዋል። ሁለቱም ምሁራን፣ የዘር ፖለቲካ አራማጆች፣ በሰው ደም ሃብት እያካበቱ ያሉ መሆናቸውን ለመንገር ነው። በዘር ፖለቲካ ተጠልሎ፣ ህዝብን በዘር እያጋጩ ሃብት ማግበስበስን ከትግራይ ጉጅሌ መሪዎች “ኢንቬስተርነት” ሌላ ምን ማስረጃ ያስፈልጋል?

አማራው በጉጅሌው ሲገደል እና ሲጨፈጨፍ፣ ጊሚራው በርቀት እያየ ዝም ያለበት፤ ኦሮሞው ሲታረድ፣ ጋሞው እጁን አጣጥፎ ያየበት፤ ሱማሌው በወንድሙ ገዳይ አዛዥነት የገዛ ወንድሙን ሬሳ እንደ ዲንጋይ “ልቀም” ሲባል፣ ሃረሪው ፊቱን ያዞረበት፣ ቤንሻንጉሌው በጫካ ታርዶ ሲጣል አኝዋኩ ጀርባውን ሲሰጥ (vis versa) … ወዘተ፣ ጉጅሌው ያገሪቱን ሃብት ዘርፎ፣ ያገሪቱን ህዝብ አደህይቶ እንሆ የኢትዮጵያ ህዝብ በመኖር እና ባለመኖር ላይ ይገኛል።

ባለፉት 25 አመታት ውስጥ፣ ይህ አሳዛኝ ነገር እንዲሆን፣ የጉጅሌው መንግስት ባደባባይ አደራጅቶ እና አስታጥቆ ካሰማራቸው የየነገዱ ተወካይ ነን ባዮች እና ታጥቂዎች (ለምሳሌ የኦህዴዱ አባዱላ ገመዳ) ሌላ፣ በየዉጭ ሃገሩ የሚገኙ እና ጎሳችንን እንወክላለን የሚሉት ድርጅቶች ተጠሪዎችም፣ የህዝባችን ድምጽ ነው በሚሉት ሶሻል ሚዲያ ሁሉ፣ ከፍተኛ የአፍራሽነት ሚና ተጫውተዋል።

ዶ/ር ጌታቸው “… ያለፉትን ስህተቶች አርሞ የወደፊቱን ብሩህ ጸጋ ሊያጎናጽፈው የሚችለውን ለማየት እንዲችል አብቁት። የፖለቲካ ድርጅቶች … ቶሎ… ቶሎ በአስቸኳይ በመጠራራት፣ በመገናኘት አንድ ጊዜያዊ የመተባበሪያ ሰነድ በማውጣት …መንቀሳቀስ እና የህዝቡን ትግል ማስተባበር ይጠበቅባቸዋል። ይህን የማያደርጉ የፖሊቲካ ድርጅቶች የህዝቡ ጠላቶች ናቸው” ያለውን ማስተዋል እና ባስቸኳይ አቋም ላይ መድረስ እና ያን አቋም ማሰራጨት ያስፈልጋል።

የእገሌ ጎሳ የእገሌ ጎሳን ዘረፈ/አልዘረፈም፣ ገደለ/አልገደለም፣ ወዘተ … ለሚል ክርክር አሁን የተረፈ የቅንጦት ጊዜ ያለን አይመስለኝም። አንድ የምለው ነገር ቢኖር ቢያንስ በደርግ ጊዜ፣ የመሬት አዋጅ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ፣ በአንዱ ጎሳ ቋንቋ/ባህል ላይ ሌላው ከማሾፍ እና ከመበሻሸቅ (Bully ከማድረግ፣ ይኸንንም መደገፌ አይደለም፣ በውነት አንዱ በሌላው ዘር/ጎሳ ላይ ማሾፍ እና ራስን ከፍ አድርጎ ማየት እና ሌላም በደል አልደረሰም አይባልም። አሁንስ ቢሆን ቀልደኞቻችን ቀልዶቻቸው ባብዛኛው ባንዱ ጎሳ ቋንቋ እና አነጋገር ዘይቤ መሳቅ መሳለቅ አይደል እንዴ?) ባህር ማዶ ከመጣሁ ሁለት አሰርት ሊሞላኝ ነው። ካገሬው (ያሜሪካ) ሰው የገረመኝ ነገር ቢኖር በእንግሊዝኛዬ ስቆ ወይም አሹፎ የሚያውቅ ሰው የለም። ቋንቋ መግባቢያ ነው። አለቀ!) ባለፈ፣ ዘርን መሰረት ያደረገ ግድያ፣ እስራት እና ዝርፊያ አልሆነም። ቢያንስ በደርግ ጊዜ ይህ አልሆነም።

የትግራይ ጉጅሌ ባለስልጣን አባይ ጸሃዬ ይህን አመጽ ልክ እንደተናገሩት “ልክ አስገብተው” ወይም “…እስር ቤት ቢሞላም እንኳን በረት ውስጥ …” እያሰሩ ሊቆጣጠሩት ቢችሉ ችግሩ የማን ነው? (ስልጣን ላይ የሚያቆየው ከሆነ፣ አይደለም ማሰር፣ በአንድ ሰዓት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ህዝብ ማለቅ ቢኖርበት እንኳን፣ ጉጅሌው ከመግደል የሚመለስ አይደለም። ሰዎቹ ጭካኔያቸው ወደር የለውም። በ1960ዎቹ መጨረሻ/70ዎቹ መጀመሪያ ላይ በትግራይ በረሃዎች ውስጥ፣ በጎሳ ፖለቲካ እና በመሳሰሉት አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከአሁኖቹ ጉጅሌዎች የተለየ አቋም ይዘው የነበሩ የትግራይ እና ሌሎች ጎሳ ተወላጆችን፣ “… በቴትራ ሳይክሊን ካፕሱል ውስጥ የሳይናይድ መርዝ ሞልተው፣ መድሃኒት አስመስለው ሰጥተው በርካቶችን የገደሉ ሰዎች መሆናቸውን…” ማንበቤ/መስማቴ ትዝ ይለኛል። ህወሃቶች ሰብአዊነት የላቸውም ማለት ብቻውን ጭካኔያቸውን ማሳነስ ይሆናል።

ይህ “ህልውና” የሚባል መጽሃፍ “የዘራዊነት መጨረሻው እስከ ቤተሰብ መሰባሰብ ነው…” ይላል። ምሳሌ አደርጎ ያቀረበው ሶማሌን ነው። አንድ ሃይማኖት፣ ቋንቋ፣ ባህል ያላቸው ሶማሌዎች፣ እንዲያ አገራቸውን “መንግስት አልባ” አድርገዋት የኖሩት፣ በነገድ እና ጎሳ (የእገሌ ዘር ከእገሌ፣ ማንትስ እገሌን ቢወልድ… በሚል ተሰባስበው እና ተደራጅተው እና ተከፋፍለው) ሲጫረሱ ኖረው፣ መጨረሻ ላይ እስከቤተሰብ ድረስ እንደወረዱ እና አገሪቱን “መንግስት አልባ” እንዳደረጓት ያወሳል። ከሰማንያ በላይ ጎሳ/ነገድ ባለባት እና ቋንቋ በሚነገርባት፣ በርካታ ሃይማኖቶች ባሉባት አገራችን ውስጥ ሊሆን የሚችለውን እያሰቡ ካሁኑ መዘጋጀት እና ጋዜጠኛዋ ርዕዮት እንዳለችው ተባብሮ እና አንድ ላይ ሆኖ “… ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል”–በተቀናጀ እና ሁሉን ጎሳ/ነገድ/ ባካተተ ሁለገብ ትግል።

__________________________

[1] እያንዳንዷ [የነገድ “ነጻ አውጪ” ነን ባዮች] የተሰባሰበችው፣ የኔ ዘር ተበደለ፣ ተሰደበ፣ ተበዘበዘ፣ ተናቀ…ዘራችን እንዲህ ሆነ እያሉ…። ዘራችን ተበደለ ሳይል የተሰባሰበ አንድም የዘር ድርጅት የለም። በዚህ ሁሉም አንድ አይነት ናቸው። ከዚህ እንግዲህ ሌላው ዘር በድሎኛል የሚለው ነው። ሁሉም እንዲህ ይላል። ቀጥሎ የኔ ዘር ነው የሚበልጠው ይላሉ። ይህም ሁሉም ጋር ያለ ነው። ጥቂት የተለያዩ የዘር ፓርቲ አፈቀላጤዎችን አነጋግሬ የእነዚህን እውነትነት አረጋግጫለሁ።…አንዱ ስለሱ ዘር ታላቅነት ሲደነፋ፣ አገር የመሰረተ፣ ጥንታዊ ታሪክ የሰራ ዘር ነው ዘሬ ይላል።… ሌላው ደግሞ ይነሳል። እንዴታ፣ ስለዘሩ የቀድሞ ጀግንነት ሌሎቹን እንዴት እንዳራወጣቸው፣ እንደጨፈጨፋቸው፣ የሱ ዘር ሰው እንዴት ሲወለድ ጀምሮ ዲሞክራት ሌሎቹ ግን ከተወለዱ ጀምሮ ጨቋኞች እንደሆኑ ተረቶቹን ይደረድራል። እንደምን ሃብታም የዴሞክራሲ መናኸሪያ የፍትህ አደባባይ የሆነች አገር እንደሚሰራ የተስፋ ማር ወለላውን ምስኪን ህዝብ ላይ ያንጠባጥባል። በተግባር ከድህነት የመውጣት ህልምም የለው። ከቀናው ዲሞክራሲን ለጥይት ያስረክባል። ፍትህን ባደባባይ ያርዳታል። እንደገና የሚገርመው ለዚህም ደጋፊና እርዳታ ሰጪ አይጠፋም። ውጤቱ ግን ያው ጦርነት፣ እልቂት፣ መከራ፣ ረሃብ፣ እናም ድህነት ናቸው። ማን ይጎዳል? ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን። ማን ይጠቀማል? የፖሊቲካ ነጋዴው፣ ህዝቡን ያስጨፈጨፈው የፖለቲካ ነጋዴው።… እኒህ የፖሊቲካ ነጋዴ ያልኳቸውን “የደም ነጋዴ” ማለቱ የበለጠ ይገልጻቸዋል።… ከሩብ ምዕተ አመት በፊት እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ የምናስበው ስለጠቅላላው አገር እድገት እና ስለመላው ህዝብ በነጻነት ሰርቶ መኖር፣ ስለ ዲሞክራሲና ፍትህ መስፈን… ነበር። አሁን ጊዜው በመቶ ዓመታት ስላለፈበት ስለዘርና ዘሮች ሳይናገሩ እነዚያን ጉዳዮች ማንሳቱ የሚረባም አልመሰለኝ። ኢትዮጵያዊ ብቻ በመሆኔ፣ የዘር ፖለቲካ አውራጆች ሲያቀነቅኑ እያዳመጥኩ አለሁ። አዳማጭ ከሆንኩ ተቀባይ እንደማልሆን ግልጽ ነው። በማዳመጤም የአገሬን ህዝብ ስቆቃ እያሰብኩ፣ ታጥቦ ጭቃ በመሆኑ እየተከዝኩ፣ ካስፈለገ የመሳሪያው ሰሪ መሆን የሚገባው ህዝብ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፣ ከሚል መደምደሚያ ጋር ደረስኩ። እናም አውራጆችን የአሳባቸውን ተቃራኒ በማቅረብ እንደምን አንድ ህዝብ እንደሆንን ለመንገር አሰብኩ…”። አንድ ባለ “ትልቅ” ድምጽ አውራጅ፣ በአንድ አጋጣሚ “ለ ‘ሀ’ ህዝብ አንድም እንኳን ጥሩ የሰራ፣ አንድም እንኳ ተበድለዋል ያለ የ ‘ለ’ ዘር ግለሰብ የለም..” በሎ ‘ሲቀድ’ ሰማሁት። እድሉን አላገኘሁም እንጂ “አንተ ውሸታም፣ አንት ሌባ፣ አንት የደም ነጋዴ” ማለት ይገባኝ ነበር። እንደማስረጃም የማቀርበው ‘መሬት ላራሹን’ ነበር። ከጥንስሱ እስከ ፍጻሜው። አሁን ያመጣውን ተረት፣ ‘ዕውነት፣ እርግጥ ነው’ ብሎ ሲተርክ ትናንት የሆነውን የ66ቱን የኢትዮጵያ አብዮት እየካደ መሆኑን እናገር ነበር። የኢትዮጵያ አብዮት የዘር ምልክትም የለው ነበር።…ትከሻ ለትከሻ ተያይዞ የተጓዘ ወንድማማችና እህትማማች፣ ከኢትዮጵያዊነታቸው በስተቀር ምንም ቅጽላቸውን አይተዋወቁም ነበር። ‘የደም ነጋደዴዎች’ በዚያ ጊዜ [የዘር] ማስታወቂያቸውን ቢያቀርቡ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ቀድዶ ይጥልላቸው ነበር…” (የጸሃፊው ማስታወሻ፦ (አቤት የብስለት እና የሰብዓዊ ሞራሊቲ አስተሳሰብ ልዩነት! የህልውና ደራሲ “[የዘር] ማስታወቂያቸውን ቀድዶ ይጥልላቸው ነበር..” ነው ያለው? “… በሜጫ አንገት አንገቱን …” አላለም) በነገራችን ላይ፣ ልጅ ሆኜ፣ በመሬት ላራሹ አዋጅ ጊዜ፣ አንድ ፊውዳል አምጾ ጫካ ገብቶ ሸፍቶ ሲዋጋ፣ የገበሬ ታጣቂዎች፣ አንገቱን ቆርጠው እንደተመለሱ ሲወራ አስታውሳለሁ። ድርጊቱን አሁን ሳስበው አግባብ እንዳልነበረ ይገባኛል። ይህ የሆነው በ1967/68 ይመስለኛል። ጃዋር ያኔ የተፈጠረ እና በመሬት ላራሹ ማግስት አሁን የሚያራምደውን የዘር እና የሃይማኖት ፖለቲካ ያኔ ቢሞክራት ኖሮ፣ ያደገበት አካባቢ አርሶ አደር ህዝብ ራሱ በሜጫ …።

 በጣም የሚያሳዝነው ጃዋር ይህን ሁሉ የሚናገረው አሜሪካ አገር ውስጥ ሆኖ ነው። አንዳንዴ የሰዎች የህይወት አላማ (purpose of life) ልዩነት ይገርማል። አቶ በቀለ ገርባ የNPR ሬድዮ ጋዜጠኛ “… አሁን ተመልሰህ ልትሄድ ነው። አትፈራም..?” አይነት ጥያቄ ጠይቆት ነበር። በቀለ…ምን እንደሚጠብቀው እንደማያውቅ፣ ግን ከመሄድ እንደማይቀር ነበር የተናገረው። አቶ በቀለም የኦሮሞ ጎሳን ወክሎ የተደራጀ ነው፣ የትግሉ ፍሬ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፣ ለሌሎቹ ጎሳ/ነገድ አባል ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ልዕልና ይሆናል ብየ አስባለሁ። በቀለ የሚናገረው እና የሚያደርገው ሁሉ እወክለዋለሁ የሚለው ህዝብ እየደረሰበት ያለውን እስራት፣ ግርፋት፣ ሞትም እንኳን ቢሆን ለመቀበል ቆርጦ ነው ሲሰራ የኖረው እና አሁንም ሊሰራ ነው ተመልሶ የሄደው። እናም ጋዜጠኛው እንደሰጋው ታሰረ። በቀለ አሜሪካ አለመቅረቱ ይጸጽተው ይሆን? አይመስለኝም። በቀለ፣ አንዷለም፣ እስክንድር፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ኤፍሬም ማዴቦ… ወዘተ የመሳሰሉት የህይወት ግባቸው እና  እርካታቸው የሚመነጨው፣ ማደረግ የሚፈልጉትን (ለሌሎች ሰዎች ልዕልና እና ሰላም ሲሉ ጭምር) እያደረጉ መኖር እና ካስፈለገም መስዋዕት መሆን ነው። ማህበረሰብን በመልካም ጉኑ መለወጥ የሚችሉት ደግሞ እንደዚህ አይነት ሰዎች ናቸው።

ጃዋርም ራሱን ለመስዋዕትነት ባያዘጋጅም፣ ሌሎቹን ለመሰዋት ዝግጁ ነው። የጃዋር “በሜጫ…”) አባባል ሲተነተን “… እስላም ያልሆኑትን በሜጫ አርዳለሁ…” ነው። ጃዋር እና የአይሲስ ወይም አልቃይዳ አጥፍቶ ጠፊ፣ ሌሎችን ሰዎች በሃይማኖት ልዩነት ብቻ መግደል ይፈልጋሉና፣ ሁለቱን ያመሳስላቸዋል። ልዩነታቸው ደግሞ፣ አጥፍቶ ጠፊው ጀነት ውስጥ የሚጠብቀውን የቅንጦት እና ድሎት ኑሮ እያሰበ ሲሆን (አቤት ስግብግብነት! ለራሱ የሰማይ ቤት ደስታ ሲል፣ አንተን ምንም ባላውቅኸው፣ ባልገባህ ጉዳይ፣ “ራንደምሊ”፣ በተገኘህበት ይገድልሃል፣ ጀነትየሚያስገባው ከሆነ ደግሞ፣ ከገዛ አገሩ ተርቦ፣ ሰላም እና ደስታ አጥቶ ተሰዶ የመጣ መሆኑ ሁሉ ግድ ሳይለው፣ እጅ እግርህን አስሮ ያርድሃል (አይሲስ እንዳረዳቸው ሰላሳዎቹ ኢትዮጵያዊያን)፤ ጃዋር ደግሞ ደስታን የሚያገኛት እዚሁ ምድር ላይ ነው፤ ያውም አሜሪካ። የ”ህልውና” ደራሲ “የፖለቲካ/የደም ነጋዴ!” ያለውን አይነት ይሆን? ይኼ ሰው የሚመራው ድርጅት አለ ይመስለኛል። በአሜሪካ አገር በ“አትራፊ ያልሆነ ድርጅትነት” የተመዘገበ ድርጅት። ምን ችግር አለ! በየአመቱ የአሜሪካ መንግስት፣ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ናቸው ተብሎ እስከታመነበት ድረስ በ“ሰብዓዊ/ኮሚኒቲ ደቨሎፕመንት” ድርጅትነት ስም ገንዘብ ይሰጣል። አሜሪካም ባይሰጥ፣ የትግራይ ጉጅሌውን አላማ፣ በሃይማኖትም ሆነ በጎሳ ፖለቲካ የመከፋፈሉን ዋና ስራ፣ ጃዋር እየሰራለት ሊሆን ይችላል እና፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ፣ ጉጅሌው ገንዘብ ቢሰጥ አይገርመኝም። Something smells really bad about this guy’s personality!)። በጣም የገረመኝ በ“ሜጫ…” ንግግሩ ጉዳይ የሰጠው ማስተባበያ ነው። “…ሳይኮ አናሊሲስ እንትን ነው ያለው…ሜጫ ምንድነው?… እኛጋ ኦሮሞ ውስጥ ከሰው የማይለዩ እቃዎች አሉ። ለፋርሚንግ የምትጠቀምባቸው፣ … ለአደጋ የምትከላከልባቸው። …ከተነካ ህዝቡ ይነሳብሃል…” “…ሜጫ ማለት እኛ ጋር ቡጢ እንደ ማለት ነው…” ነበር ያለው። ጉጅሌው ኢትዮጵያዊያንን በመከፋፈል እና እርስ በርስ በማባላት ረገድ ተራቅቆበታልና፣ ለኦሮሞ ነገድ ቆሜያለሁ የሚል ሁሉ እና የኦሮሞ ልሂቃን፣ ከዚህ ሰው ጀርባ ያለውን ማንነት ቢከታተሉ መልካም ይመስለኛል። የሚገርመው ነገር፣ ኢሳትም ሆነ ኦኤምኤን፣ የሜጫውን ጉዳይ ባደባባይ ይቅርታ ሳይጠይቅ (እኔ ባላየሁት እና ባልሰማሁት ሜዲያ ጠይቆ የነበረ ከሆነ እኔ ራሴ ይቅርታ እየጠየቅሁ)፣ ዛሬም ጃዋርን በየሜዲያው ጊዜ እየሰጡ ያቀርቡታል።

[2] “… የምጣኔ ሃብት ሊቃውንት …. ብሄርን የሚሰራው ካፒታሊዝም ነው፣ እንዴት ቢሉ ሰዎች ለስራ ብለው ጉልበታቸውን ለመሸጥ ብለው ከየትውልዶቻቸው ቀየዎች ወደ ሌሎች ስፍራዎች እየሄዱ እየሰፈሩ… ከሌሎች ቦታዎች ከመጡት በመገናኘት እየተወዳጁ፣ አብረው እየኖሩ… እየተዋለዱ እንዲያ እንዲያ …ከቀድሞ የሰፋ አድማስጋ ይደርሳሉ። አዲስ ብሄር ይፈጥራሉ… ደርጉ ሊመጣ፣ ጃንሆይ ኃይለ ስላሴ ሊወርዱ ግድም ከላይ የጠቀስኩት ዓይነት ብሄር ጥንሥስ፣ ኢትዮጵያዊ የሚል ብሄር ሽል ተፈጥሮ ነበር።… ‘ኩሩው’ የኢትዮጵያ ልጅ እያንዳንዱን ጎሳ፣ ነገድ ወዘተ …ብሄር (nation) ብሎ ሲል፣ ‘ልክ አይደለህም’ ብሎ ሊሞግት የተነሳ ያለ አይመስለኝም። ‘የእገሌ ብሔር “ሀ” ነው። ምክንያቱም እገሌን ቢወልድ እገሌ፣ እገሌም የእገሌ ልጅ…” … እንዲህ ነው የግለሰብ “ብሔር” ትንተና ሲደረግ የምንሰማ። በርግጥ ግን በደም ዝምድና ላይ የተመሰረተ የህብረተሰብ ስብስብ ዘር፣ ጎሳ፣ ነገድ ይሆን እንደሁ እንጂ ብሔር (nation) አይደለም። … አሁን እስቲ በኢትዮጵያ የትኛው ዘር ወይ ነገድ ነው ከሌላው የሚበልጥ? በመጀመሪያ የተደበላለቅን ነን። ሁላችን ምስኪኖች ነን። ሁላችን የመኖራችን ጉዳይ ከሚያጠያይቅ ደረጃ የደረሰ አሳዛኝ ሰዎች ነን። ያለንበት ጊዜ ችግር (ይህ መጽሃፍ የተጻፈው በ1992 ነው)፣ ያለንበት ሁኔታ፣ የተገፋንበት ማጥ፣ እንኳን ተለያይተን አንድ ሆነንም ከተወጣነው ታላቅ ነገር ነው። (ህልውና፡ ገጽ 92፣ ሰለሞን ይርጋ)።

አሊ ጓንጉል
aliguangul@gmail.com

የውስጥ እና የውጪ አጣብቂኝ የዋጠው ወያኔ ለግብጽ ፍላጎት ተንበረከከ::

Image

የውስጥ እና የውጪ አጣብቂኝ የዋጠው ወያኔ ለግብጽ ፍላጎት ተንበረከከ::

የወያኔ/ኢሕአዴግ አገዛዝ ከግብጽ እና ከሱዳን ጋር ባደረገው ስምምነት የአባይን ግድብ ውሃ ላለመሙላት ተስማማ::በዚህም መሰረት አዲስ ይጀመራል የተባለው ጥናት እስከ 15 ወራት የሚፈጅ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ በግድቡ ዙሪያ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ላለማድረግ ተገዝቶ ምሎ ፈርሟል::እንዲሁም ግብጽ ግድቡን በተመለከተ የምታቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት እና አጥጋቢ ምላሽ ካላገኘ ስምምነት ላይ አይደረስም ሲሉ ወያኔዎች ፈርመውል::ግብጽ አሳስቦኛል የምትለው ጉዳይ ካለ የፈለገ ጊዜ ቢፈጅም እንደሚጠና ምንጮች ይጠቁማሉ::በድህነት ላይ ከባድ ኪሳራ ሃገሪቷን ያስታቅፋታል የተባለው ይህ ስምምነት እጅግ አድገኛ እና ብሄራዊ ውርደት ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራል::ግብጾች አሁም ወጥረው የያዙ ሲሆን በወያኔ ላይ የውስጥ እና የውጪ ጉዳይ አጣብቂኙ በርትቶ ቀጥሏል::

Ethiopian Dam Crisis:Ethiopia has agreed to not fill the dam with any water from the Nile River.
ዝርዝሩ እዚህ ላይ ያገኙታል::
http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=108816

ኢትዮጵያ በረሃብ በክፉ ድህነት ሳቢያ፣ በቀላሉ ሊፈነዳ የሚችል አደገኛ አጣብቂኝ ውስጥ የተቀረቀረች አገር ናት።

 Embedded image permalink
የኢትዮጵያ ድህነት፣ በጣም አደገኛ እንደሆነ፣ ለአፍታም ያህል ልንዘነጋው አይገባም ነበር። ግን፣ በተደጋጋሚ እየዘነጋነው፤ በአላስፈላጊ ንትርክና ግጭት ጊዜያችንን እናባክናለን።
ሰዎች፤ ዘንድሮ ያለ እርዳታ አመቱን መዝለቅ የማይችሉ ረሃብተኛና ችግረኛ ኢትዮጵያዊያን፣ ከ18 ሚሊዮን በላይ ናቸው። ድርቅ በማይከሰትበትና ከፍተኛ የእርሻ ምርት በሚሰበሰብበት አመት እንኳ፣ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎች፣ ያለ እርዳታ ከአመት አመት መሻገር አይችሉም። የውጭ የእህል እርዳታ ባይኖርኮ፣ ሕዝብ ያልቅ ነበር። ከዚህ የከፋ አደጋና ውድቀት ምናለ?
በከተሞች፣ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች፣ የሉም። በ1994 ዓ.ም በመካከለኛና ትላልቅ የኢንዱስትሪ ተቋማት የነበሩ ሰራተኞች ቁጥር መቶ ሺ ነበር። ዛሬ ከአስራ ምናምን ዓመታት በኋላ፣ ቁጥሩ 300ሺ ብቻ ነው። ለዚያውም፣ የሰራተኞቹ አማካይ የገቢ እና የኑሮ ደረጃ ሲታይ፤ በ40% የወረደ ነው (በብር ሕትመትና በዋጋ ንረት ሳቢያ)።
በከተማም ሆነ በገጠር፣ ኢትዮጵያ በክፉ ድህነት (በረሃብና በሥራ አጥነት) ሳቢያ፣ በቀላሉ ሊፈነዳ የሚችል አደገኛ አጣብቂኝ ውስጥ የተቀረቀረች አገር ናት።
ወገኛነት ተጠናውቶን፣ ‘የሃብት ልዩነትና የሃብት ክፍፍል’ እያልን እንደሰኩራለን – ሃብት መፍጠር ባቃተው አገር ውስጥ ሆነን። ስለ ‘ካርቦንዳይኦክሳይድ’ እና ስለ ‘አለም ሙቀት’ እንለፍፋለን – ነዳጅ ለመጠቀም አቅም በሌለው ድህነት ውስጥ ሆነን። መሬትንና ገጠርን፣ ግብርናንና ዘልማዳዊ አኗኗርን እያንቆለጳጰስን እናወራለን – የድህነት አጣብቂኝ ጋር የሙጢኝ ብለን ለመቀጠል።
ሰዎች እናስብ እንጂ። በእርሻ ብቻ፣ ከረሃብ የተላቀቀ አገር፣ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የለም። ያለ ኢንዱስትሪና ያለ ከተማ እድገት፣ ወደ ብልፅግና ለመራመድ ይቅርና፣ ከድህነት… ከረሃብና ከስራ አጥነት መውጣት አይቻልም። በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ፣ የፋብሪካ ምርት ድርሻ፣ ከድሃ የአፍሪካ አገራት ጋር ሲነፃፀር እንኳ፣ ግማሽ ያህል አልተራመደም። (ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ – ገፅ 6)።
የመካከለኛና የትላልቅ ፋብሪካዎች ኢንቨስትመንት አልተስፋፋም። የስራ እድሎችን በገፍ ይፈጥራሉ እየተባለ ብዙ የተወራላቸው፣ “የአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት”፣ በተግባር እንቅስቃሴያቸው ሲታይ፣ ከሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፍ የባሰ ቀርፋና ጎታታ ሆኗል። የፋብሪካ ምርት ፈቅ አለማለቱ መንግስትን ቢያስጨንቅ አይገርምም። እድገት ሲቋረጥና ስራ አጥነት ሲስፋፋ፣ ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ የሆኑ አደጋዎች ይፈጠራሉ። የኢንዱስትሪ ጉዳይ፣ “የሞት ሽረት ጉዳይ ነው” ይላል – የእቅዱ ሰነድ።
ከዚህ የኢንዱስትሪ ልምሻ ላይ፣ የኤክስፖርት ድንዛዜ ሲጨመርበት ደግሞ፣ ይበልጥ ያስፈራል። ለዚህም ይመስላል፣ ሁለተኛው የሞት ሽረት ጉዳይ፣ ኤክስፖርት እንደሆነ ሰነዱ በተደጋጋሚ የሚገልፀው።
በእርግጥም፣ በአለማቀፍ ንግድ፣ የውጭ ምንዛሬን ማሳደግ ካልተቻለ፣ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ማፋጠን አይቻልም። እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ፣ በአምስት አመታት፣ ኤክስፖርትን ወደ ሦስት እጥፍ ማሳደግ ያስፈልጋል ተብሎ እቅድ ወጥቶ የነበረውም፤ በዚህ ምክንያት ነው።
ነገር ግን፣ ኤክስፖርት አላደገም። የኤክስፖርት ሽያጭ አምና፣ 10 ቢሊዮን ዶላር እንዲደርስ ቢታቀድም፤ አልተሳካም። 3 ቢሊዮን ዶላር ላይ ደንዝዞ ቆሟል። ለምን? በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የመንግስት ድርሻ እየገነነ፣ በተቃራኒው ኢንቨስትመንት እየቀጨጨ ከመምጣቱም በተጨማሪ፣ ኤክስፖርትን ያደነዘዙ ሌሎች ምክንያቶችም አሉ።
አንደኛ፣ ባለፉት አምስት አመታት፣ መንግስት፣ በአላስፈላጊ የምዝገባ ቢሮክራሲና በአጥፊ የዋጋ ቁጥጥር አማካኝነት የአገሪቱን የቢዝነስ ድባብ ሲያተራምስ ቆይቷል።
ሁለተኛ፣ መረን በለቀቀ የገንዘብ ህትመት ሳቢያ፣ የአገሪቱ ብር መርከሱ እየታወቀ፣ የዶላር ምንዛሬ በዚያው መጠን እንዲስተካከል አለመደረጉ፣ ኤክስፖርትን ጎድቷል። የአለም ገንዘብ ድርጅት እንደሚለው፤ የዶላር ምንዛሬ፣ 27 ብር አካባቢ መሆን ነበረበት። ግን አልሆነም።
እንግዲህ አስቡት። ቡና ወይም ጫማ አምርታችሁ ወደ ውጭ በዶላር ብትሸጡ፤ መንግስት ዶላሩን ይወስድና፣ በራሱ ተመን በብር መንዝሮ ይሰጣቸዋል – ለአንድ ዶላር ወደ 21 ብር ገደማ። ከእያንዳንዱ ዶላር ስድስት ብር ይወስድባችኋል ማለት ነው። ምርት ወደ ውጭ የሚሸጡ ሰዎችንና ድርጅቶችን፣ እንዲህ እየዘረፍናቸው፣… ኤክስፖርት በሦስት እጥፍ እንዲያድግ መመኘት፣ ነውር አይደለም?
ለነገሩ፤ መንግስትም፣ አሁን አሁን ይህንን መካድ እየተወ ይመስላል። ብር በመርከሱ ምክንያት፣ የዶላር ምንዛሬ እንደተዛባ አምኗል። ይህም ብቻ አይደለም። ነገርዬው፣ ኤክስፖርትን እንደሚጎዳ፣ ትናንት አርብ በፓርላማ በፀደቀው፣ ባለ 185 ገፅ እቅድ ውስጥ፣ በግልፅ ተጠቅሷል። መጠቀስ ብቻ አይደለም። ባለፉት አምስት አመታት ካጋጠሙ ሦስት ትልልቅ ፈተናዎች መካከል አንዱ፣ ይሄው የብር መርከስ ጉዳይ እንደሆነ ተገልጿል። በገንዘብ ሕትመት ሳቢያ፣ ብር ሲረክስ፣ በዚያው መጠን የዶላር ምንዛሬ አለመስተካከሉ ኤክስፖርትን እንደሚጎዳ ሰነዱ ያመለክታል (ገፅ 53)። የውጭ ምንዛሬ ተመንን ማስተካከልና ለኤክስፖርት አመቺ እንዲሆን ማድረግ እንደሚያስፈልግ በመግለፅ፣ በዋና ዋና እቅዶች ዝርዝር ውስጥ ገብቷል(ገፅ 78)። ጥሩ ነው። በእርግጥ፣ ዘግይቷል። እንዴት?
በብር መርከስና በዶላር ምንዛሬ አለመስተካከል ሳቢያ፣ ኤክስፖርት እየተዳከመ መሆኑን የሚተነትን ፅሁፍ ከሁለት አመት በፊት በአዲስ አድማስ መውጣቱን ማስታወስ ይቻላል።
“‘የስራ ፍሬውን ስንነጥቀው ይበረታታል’ ብሎ መመኘት ሃጥያት ነው” በሚል ርዕስ የቀረበው የያኔው ትንታኔ እንዲህ ይላል።
“ከመነሻው፣ የብር ኖት አለቅጥ ከማተም በመቆጠብ ብር እንዳይረክስ ማድረግ እንጂ፣ ብር ከረከሰ በኋላ፣ የዶላር ምንዛሪን በቀድሞው ተመን ላይ ቆልፎ ማቆየት አያዋጣም። እንዴት ሊያዋጣ ይችላል? በኤክስፖርት መስክ የተሰማሩ አምራቾችና የቢዝነስ ሰዎችን በግድ እየዘረፍናቸው (ከእያንዳንዷ የዶላር ገቢ ስድስት ብር ነጥቀን እየወሰድንባቸው)፤ በየአመቱ  ተጨማሪ ዶላር የሚያመጡ… የውጭ ምንዛሪ ምንጭ እንደሚሆኑልን… አምነን መቀመጣችን፣ እጅግ አላዋቂነትም እጅግ ሃጥያትም ነው።”
ይሄ፣ ከሁለት ዓመት በፊት የተፃፈና የታተመ ነው። ግን፣ እስካሁን፣ ሁነኛ መፍትሄ ስላልተበጀለት፣ ኤክስፖርት እዚያው በድንዛዜ ተገትሮ ቀርቷል። ከሦስት ዋና ዋና አሳሳቢ የአገር ጉዳዮች መካከል አንዱ ሆኖ የሚጠቀስም ሆናል።
ታዲያ፣ ቅጥ ያጣ የገንዘብ ህትመት… መዘዙ ይህ ብቻ አይደለም። መንግስት አለቅጥ በሚያሳትመው ገንዘብ ሳቢያ፣ ‘ብር መርከሱ’፣ እናም የዋጋ ንረት መከሰቱ፣ ብዙ ነገሮችን አበላሽቷል። ኢኮኖሚውን አተራምሷል። ኢንቨስትመንትን አዳክሟል። እንዴት?
ለእውነትና ለመረጃ ክብር የማይሰጥ፣ ጭፍን ፕሮፖጋንዳ
የዋጋ ንረት ሲፈጠር፣ መንግስት ሁሌም፣ በቢዝነስና በንግድ ሰዎች ላይ ነው የሚሳብበው። ግን፤ ውሸት እንደሆነ ይታወቃል። የዋጋ ንረት፣ ከብር መርከስ ጋር (ከገንዘብ ህትመት ጋር) የተቆራኘ እንደሆነ፣ በግልፅ ይታወቃል። ለዚህም፣ ተጠያቂው መንግስት ነው። ነገሩ ውስብስብ አይደለም። መንግስት፣ ከአገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም ጋር በማይመጣጠን ፍጥነት፣ በገፍ ገንዘብ ካሳተመ፤ ብር ይረክሳል፣ የዋጋ ንረት ይፈጠራል። ቁርኝታቸው በጣም የጠበቀ ከመሆኑ የተነሳ፤… ለምሳሌ በአምስት አመት ውስጥ፣ የገንዘብ ሕትመትና ስርጭትን ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር በማነፃፀር፣ ምን ያህል የዋጋ ንረት እንደሚፈጠር መገመት ይቻላል።
የዋጋ ንረት= (የገንዘብ ስርጭት ፍጥነት) – (የኢኮኖሚ እድገት ፍጥነት)
ያው፣ የገንዘብ ስርጭት፣ ከሞላ ጎደል፣ ዞሮ ዞሮ በገንዘብ ህትመትና ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሚመጣ ‘የባንክ ቼክ’ ላይ የተመሰረተ ነው። እናም፣ ባለፉት አምስት ዓመታት፣በገንዘብ ህትመትና በቼክ አማካኝነት፣ (የገንዘብ ስርጭት ከ54 ቢሊዮን ብር ወደ 167 ቢሊዮን ብር ጨምሯል – የብሔራዊ ባንክ የ2007 የመጨረሻ የሩብ ዓመት ሪፖርት አባሪ – ገፅ 8)። ማለትም… የገንዘብ ስርጭት በየዓመቱ፣ በአማካይ 25% በመቶ ሲስፋፋ ቆይቷል።
የኢኮኖሚ እድገትስ?
ባለፉት አምስት አመታት፣ በአማካይ በ10% እያደገ ነበር።
መረጃዎቹ ግልፅ ናቸው። ኢኮኖሚው አቅም በላይ፣ ምን ያህል የገንዘብ ስርጭት እንደጨመረ መመልከት እንችላለን። 15% ያህል ነው ልዩነቱ። ይሄ ነው፣ ዋነኛው የዋጋ ንረት መንስኤ። የዋጋ ንረት፣ ከወር ወር፣ በተለያዩ ምክንያቶች ሊዛነፍ ይችላል። ሁለት ሦስት አመት፣ ከዚያም እስከ አምስት ዓመት ሰፋ አድርገን ካየን ግን፤ የዋጋ ንረትና የገንዘብ ስርጭት ቁርኝት፣ ፍንትው ብሎ ይታያል።
የዋጋ ንረት = (የገንዘብ ስርጭት ፍጥነት) – (የኢኮኖሚ እድገት ፍጥነት)
የዋጋ ንረት = (25%) – (10%) = 15%
የገንዘብ ስርጭቱ፣ ከአገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም በላይ አለቅጥ መስፋፋቱን በማገናዘብ፤ በየአመቱ በአማካይ 15% የዋጋ ንረት እንደሚከሰት መገመት ይቻላል።
በተጨባጭስ፣ ባለፉት አምስት አመታት፣ ምን ያህል የዋጋ ንረት ተከሰተ?
የሸቀጦችን ዋጋ በየወሩ በማነፃፀር፣ የስታትስቲክስ ባለስልጣን የሚያወጣቸውን መረጃዎች መመልከት እንችላለን።
በየዓመቱ የሸቀጦች ዋጋ፣ በአማካይ በ15% ሲጨምር እንደቆየ፣ የስታትስቲክስ ባለስልጣን መረጃዎች ያረጋግጣሉ። ይሄ፣ በቀጥታ የሸቀጦችን ዋጋ በማነፃፀር ላይ የተመሰረተ መረጃ ነው።
የገንዘብ ህትመትንና ስርጭትን በማገናዘብ ካገኘነው የዋጋ ንረት ግምት ጋር ተመሳሳይ ነው።
በአጭሩ፤ የገንዘብ ሕትመት፣ ከብር መርከስ ጋር፣ እንዲሁም ከዋጋ ንረት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ፣ ከእነዚህ ተጨባጭ መረጃዎች መረዳት ይቻላል። ግን ምን ዋጋ አለው? መረጃንና እውነትን፣ ከምር የማናከብር ከሆነ፣ እስካሁን ያየነው ትንታኔ ሁሉ ከንቱ ይሆናል።
መንግስት፣ ወጪዎቹን ለመሸፈን፣ አለቅጥ በሚያሳትመው ገንዘብ ምክንያት፣ የዋጋ ንረት እንደሚፈጠር ቢታወቅም፤ ሁልጊዜ በቢዝነስ ሰዎችና በነጋዴዎች ላይ ያላክካል። ለምን? ለዛሬ ብቻ፣ ከወቀሳ ለማምለጥ በመመኘት ሊሆን ይችላል። ግን መዘዞች አሉት።
አንደኛ፤ ለመረጃና ለእውነታ ዋጋ የማይሰጥ፣ የአሉባልታና የፕሮፖጋንዳ፣ የጭፍን እምነትና የጭፍን ስሜታዊነት ባህልን ለማጠናከር፣ በወዶ ዘማችነት እየተሰለፈ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርበታል። ዞር ብሎ ግን፣ ‘ተቃዋሚዎች፣ ተጨባጭ መረጃን ለመቀበል የማይፈልጉ፣ የኢኮኖሚ እድገትን የሚክዱ፣ ጭፍን ፕሮፓጋንዳ የሚራግቡ ናቸው’ እያለ  ያወግዛል። ግን፤ ሁለት ወዶ አይሆንም። ያሰኘው ጊዜ…. ‘ተጨባጭ መረጃን በጭፍን ፕሮፓጋንዳ እየሸፋፈነ’፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ፣ ‘ተጨባጭ መረጃ በጭፍን ፕሮፓጋንዳ እንዳይሸፈን እንከላከል’ ብሎ ቢሰብክ፣ ከንቱ ነው።
‘ከገበሬ ጀምሮ እስከ ኢንዱስትሪ ድረስ፣ ኢትዮጵያዊያን፣ በተጨባጭ መረጃ ላይ በተመሰረተ ስልጡን አስተሳሰብ አማካኝነት፣ ውጤታማ ምርታማነትን ማስፋፋትና መበልፀግ ይችላሉ’ ብሎ ይደሰኩራል። ትክክል ነው። ግን፣ ለተጨባጭ መረጃ ክብር የሚሰጥ ባህል፣ በአንዳች ተዓምር አይፈጠርም። በጎን በኩል፣ ለመረጃ ዋጋ የማይሰጥ የጭፍንነት ባህልን ዘወትር እየያጠናከርን፣ እንዴትና ከወዴት ስልጡን አስተሳሰብ ይመጣል? ግን ጉዳቱ ይህ ብቻ አይደለም።
ቢዝነስን እያንቋሸሹ፣ ኢንዱስትሪን ማስፋፋት?
የዋጋ ንረትን በነጋዴዎችና በቢዝነስ ሰዎች ላይ ሲያላክክ፤ የብልፅግና መሰረትንም በእንጭጩ እየሸረሸረ መሆኑን አይገነዘብም። ቢዝነስ ማለት፣ በተፈጥሮው፣ ‘ማጭበርበርና ማታለል’ ማለት እንደሆነ ለማሳመን ዘወትር ይጣጣራል። በሌላ አነጋገር፤ ‘ትርፋማነት’ ማለት ‘አጭበርባሪነት ነው’፣ ‘ባለሃብት’ ማለት ‘አታላይ ነው’ የሚል ስብከት ይግተናል።
እንዲህ፣ ቢዝነስን፣ አትራፊነትን፣ ስኬታማነትን፣ ባለሃብትነትን ሲያንቋሽሽ ይከርምና፤… ትንሽ ቆይቶ ደግሞ፤… “የፈጠራና የምርታማነት ክህሎት፣ የቢዝነስና የትርፋማነት ባህል አልዳበረም። ወጣቶች፣ እየገቡበት አይደለም” በማለት እሮሮ ያሰማል።
አሃ፤ ቢዝነስን የሚያናንቅ ስብከት ለአዲሱ ትውልድ እየጋትን፤ የቢዝነስ ጥበበኞችን በብዛት የሚያፈራ ስልጡን ባህል ለመፍጠር መመኘት… እንዴት አብሮ ይሄዳል?
ግን፣ ነገሩ በስብከት ብቻ የሚቆም አይደለም።
የዋጋ ቁጥጥር እየታወጀበት፣ ፋብሪካ ለመክፈት የሚጓጓ አለ?
የክልል የንግድ ቢሮዎች፣ የፌደራል የንግድ ሚኒስቴር፣ የሸማቾች ኤጀንሲ… ምናምን… ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ፣ የቢዝነስ ሰዎች ላይ የሚዝቱ፣ ከዛቻም አልፈው፣ የዋጋ ቁጥጥርና የዋጋ ተመን የሚያውጁ፣ የመንግስት አካላት ሞልተዋል።
አሁን አስቡት። እናንተ፣ ለኢንቨስትመንት የሚሆን ገንዘብ ቢኖራችሁ፣ ምን ታደርጋላችሁ? የሳሙና ፋብሪካ ለመክፈት ትሞክራላችሁ? ወይስ የሳሙና ነጋዴ ለመሆን ትወስናላችሁ?
መንግስት፣ ካሁን በፊት እንዳደረገው፣ በማንኛውም ጊዜ፣ የሳሙና ዋጋ ላይ ቁጥጥር እንደሚያውጅና የዋጋ ተመን እንደሚያወጣ ታውቃላችሁ። ይህንን እያወቃችሁ፣ የሳሙና ፋብሪካ ለመክፈት ትደፍራላችሁ?
የሳሙና ንግድ ይሻላል። ስራው ቀለል ይላል። በዚያ ላይ፣ መንግስት የዋጋ ቁጥጥር ቢያውጅባችሁ፤ ብዙ ኪሳራ ሳይደርስባችሁ፣ የሳሙና ንግዳችሁን መተውና፣ ወደ ሌላ ንግድ መግባት ትችላላሁ። የሳሙና ፋብሪካ ግን፣ አስቸጋሪ ነው።
ከኪሳራ ማምለጫ አታገኙም። እና፤ ብዙ ሰው፣ ከፋብሪካ ቢዝነስ ይልቅ ወደ ንግድ ቢዝነስ ቢያተኩር ይገርማል?
በአጠቃላይ፣ መንግስት፣ በቅድሚያ ራሱን ለማስተካከል ይጣር። አደገኛው የድህነት አጣብቂኝ (ከአደገኛው የስራ አጥነትና የረሃብ አጣብቂኝ) መውጣት፣… ከዚያም ወደ ብልፅግና መራመድ የሚቻለው፣ በጭፍን የፕሮፓጋንዳ ባህል አይደለም። ቢዝነስንና ትርፋማነትን በሚያንቋሽሽ የውድቀት ጎዳና፣ ወደ ስኬት መጓዝ አይቻልም።

የኢትዮጵያ ድህነት፣ በጣም አደገኛ እንደሆነ፣ ለአፍታም ያህል ልንዘነጋው አይገባም ነበር። ግን፣ በተደጋጋሚ እየዘነጋነው፤ በአላስፈላጊ ንትርክና ግጭት ጊዜያችንን እናባክናለን።የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ያልተነቃነቀው፤ መንግስት በኢኮኖሚ ውስጥ ስለገነነና ቢዝነስን ስላቀጨጨ ነው። ሰዎች፤ ዘንድሮ ያለ እርዳታ አመቱን መዝለቅ የማይችሉ ረሃብተኛና ችግረኛ ኢትዮጵያዊያን፣ ከ18 ሚሊዮን በላይ ናቸው። ድርቅ በማይከሰትበትና ከፍተኛ የእርሻ ምርት በሚሰበሰብበት አመት እንኳ፣ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎች፣ ያለ እርዳታ ከአመት አመት መሻገር አይችሉም። የውጭ የእህል እርዳታ ባይኖርኮ፣ ሕዝብ ያልቅ ነበር። ከዚህ የከፋ አደጋና ውድቀት ምናለ?

በአነስተኛና ጥቃቅን፣ በየአመቱ ከ2 ሚሊዮን በላይ የስራ እድል እየተፈጠረ ነው የሚባለው ወሬ ሃሰት መሆኑን… የአዲስ አድማስ ዘገባ መስከረም 2004 (‘የመንግስት ወከባ – ከፍርሃት የማያላቅቅ የህልም ሩጫ’ በሚል ርዕስ)
ኤክስፖርት መደንዘዙና አሳሳቢ መሆኑ በተደጋጋሚ ተዘግቧል። (“የስራ ፍሬውን ስንነጥቀው ይበረታታል” ብሎ መመኘት ሃጥያት ነው በሚል ርዕስ ታህሳስ 2006 ዓ.ም – አዲስ አድማስ)