‹የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል›› እስክንድር ነጋ – በላይ ማናዬ

 

Eskinder Nega(ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በነገው ዕለት ለዘላለም ወርቃገኘሁ መከላከያ ምስክር ሆኖ ልደታ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህን በማስመልከት ህዳር 19/2007 ዓ.ም ለ10 ደቂቃዎች ያህል እስክንድርን ቃሊቲ ስናገኘው የተናገረውን በሚመለከት ከተጻፈው ለማስታወስ….)

በላይ ማናዬ

‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!››

ይህን ያለው ትንታጉ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ነው፡፡ እስክንድር ነጋን ካወኩት ወዲህ እንደዛሬ በኃይለ ቃል ሲናገር ሰምቼው አላውቅም፤ ወይም ትዝ አይለኝም፡፡ ህዳር 19/2007 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሆኖም ሁኔታው ሁሉ እንደማንኛውም ቀን አልነበረም፡፡ በር ላይ ስደርስ በርከት ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት ሰሞኑን እያካሄዱት ያለውን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በማስመልከት እስክንድር ነጋን፣ አንዱዓለም አራጌን እና ሌሎችንም ሊጠይቁ በቦታው ተገኝተው ነበር፡፡

በጠዋት ቂሊንጦ የሚገኙ ወዳጆቼን ጠይቄ አብረውኝ ከነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጋር ነበር ወደ ቃሊቲ ያመራሁት፡፡ ቃሊቲ የተገኘው ሰው ሁሉ መጠየቅ የሚፈልገውን ሰው እና ሙሉ አድራሻውን እያስመዘገበ ሳለ በመሐል እኔም እስክንድርን መጠየቅ እንደምፈልግ ነግሬ ተመዘገብኩ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ግን ስማችሁ ከዚህ ቀደም ያልተመዘገባችሁ አሁን መግባት አትችሉም መባሉን መዝጋቢ ፖሊሱ አረዳን፡፡ እኔ እና ትንሽ ሰዎች መግባት ስንችል አብዛኛው ሰው ግን መግባት እንደማይችል ተነገረን፡፡

በዚህ ሁኔታ እስክንድር ጋር ደርሰን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ አንድ የአንድነት ፓርቲ አባል ሰሞኑን ፓርቲያቸው እስረኞችን በተመለከተ በማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ እየተሰራ ያለውን ስራ ለእስክንድር ያብራራለት ጀመር፡፡ እስክንድር በተለመደ ጥሞናው ሲያዳምጠው ቆይቶ፣ በግሉ የተሰማውን እና መሆን ቢችል ያለውን ነጥብ ተናገረ፡፡ በመሐል ወጣቱ የአንድነት አባል ወደ እስክንድር ጠጋ ብሎ ሌሎች ተጨማሪ ጉዳዮችን ሲነግረው ድንገት አንድ የፖሊስ አዛዥ ጨዋታቸውን እንዲያቆሙና እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እንዲገባ፣ ወጣቱ የአንድነት አባል ደግሞ ወደ ውጪ እንዲወጣ በትዕዛዝ ማጣደፍ ያዘ፡፡

ይህኔ እስክንድር ለስለስ ባለ አነጋገር ምንም እንዳላጠፋን በመግለጽ ፖሊሱ መረጋጋት እንዳለበት አስረዳ፡፡ የፖሊስ አዛዡ ግን ጭራሽ ብሶበት ወጣቱ በቶሎ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ‹ፖለቲካ ማውራት አቁሙ› የሚል ሆነ፡፡ ይህን ተከትሎ እስክንድር ድንገት በኃይለ ቃል ተናገረ፡፡ ‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል! የማወራው ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለህጋዊ ትግል ነው!›› አለ እስክንድር በስሜት ውስጥ ሆኖ፡፡

በግሌ እስክንድር እንዲረጋጋ፣ ሁኔታው ግን ያልተገባ እንደሆነ ገለጽኩ፡፡ ፖሊሱ ግን ሊረጋጋ አልቻለም፡፡ እስክንድርን ይዞት ሄደ፡፡ ‹‹በርቱ! እንቅስቃሴያችሁ ህጋዊና ሰላማዊ ይሁን እንጂ ትግላችሁን ቀጥሉ!›› ሲል እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እየገባ ተናገረ፡፡ የፖሊስ አዛዡም ከእስክንድር ጋር የነበረንን ቆይታ ሰዓቱ ሳይደርስ ገታው፡፡ የእስክንድር ያገባኛል ባይነት አስደመመኝ፡፡ እስር ቤት ሆኖም፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም እስክንድር ስለ ሀገሩ እንደሚያገባው በስሜት ተናገረ፡፡ መብቱን መቼም ቢሆን አሳልፎ እንደማይሰጥ አስረገጠ፡፡

ስለ ያገባኛል ባይነት ሳስብ በጠዋት ቂሊንጦ ያገኘኋቸውን የዞን 9 ጦማሪዎች አስታወስኩ፡፡ ‹ስለሚያገባን እንጦምራለን!› ይላሉ ወጣቶቹ ጦማሪያን፡፡ ከአብርሃ ደስታ ጋር አብረው ያገኘኋቸው እነ በፍቃዱ ኃይሉ እና አጥናፍ ብርሃኔ ብዙ ጉዳዮችን እያነሱ አወጉኝ፡፡ ‹‹ህወሓት አንድ ወይም ሁለት ነባር የህወሓት ባለስልጣናትን በሽብር ከከሰሰ ስርዓቱ እንዳበቃለት እቆጥራለሁ፡፡ ምክንያቱም ሽብር ማታለያ መሆኑ ይቀራል›› አለኝ በፍቃዱ ኃይሉ፡፡ አብርሃ ደስታ ቀበል አድርጎ ‹‹እናት አልጋነሽ በሽብር ስትከሰስ በጣም ብዙ ሰው ተቃውሞ ነበር›› አለ፡፡ አጥናፍ በበኩሉ ‹‹ቄስና ሸህ ሽብርተኛ እየተባለ አይደለም እንዴ›› በማለት ጠየቀ፡፡

አብርሃ ደስታ አንድ ነገር በኃይል እንደሚቆጨው ተናገረ፡፡ ምን እንደሆነ ጠየቅሁት፡፡ ‹‹ብዙ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ሳላደርግ መታሰሬ ይቆጨኛል!›› አለ፡፡ በፍቃዱ በበኩሉ፣ ‹‹እኔም የገባኝ ነገር ያለውን የሰላማዊና ህጋዊ የመስሪያ ልክ አለመስራታችን ነው፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እንዲህ ለሚያስሩን ስንት ህጋዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን እንኳ ሳናደርግ በትንሽ ነገር በርግገው እዚህ ሲያስገቡን ይቆጨኛል›› በማለት ሀሳቡን ቀጠለ፡፡ ‹‹በእርግጥ አንድ ሰው አሁን መጠንቀቅ ያለበት የሚሰራው ስራ ህጋዊ መሆን አለመሆኑን እንጂ፣ ይህን ካደረኩማ ያስሩኛል የሚለውን መሆን የለበትም፡፡ እነሱ ከፈለጉ ያስሩሃል፤ ስለዚህ መብትህን ተጠቅመህ መታሰሩ ይሻላል እንዲሁ ምንም ሳይሰሩ ከመግባት›› ሲል አብርሃ ሀሳቡን አካፈለ፡፡

ቂሊንጦ ከእነ በፍቃዱ ጋር ስንጨዋወት ስለእስክንድር ነጋ ትሁትነት፣ አስተዋይነት፣ ሰላማዊነት እያነሱ ሰላምታ እንዳደርስላቸው ጠየቁኝ፡፡ እኔም እስክንድር ነጋን ሳውቀው በትሁትነቱ፣ በአስተዋይነቱና በሰላማዊነቱ ነው፡፡ ዛሬ በነበረው ሁኔታ ግን ክፉኛ ተበሳጭቶ ነበር የተመለከትኩት፡፡ ያ ፈገግታው ከፊቱ ብን ብሎ ጠፍቶ ‹‹ያገባኛል!›› ሲልበት የነበረውን ስሜት ግር አለኝ፡፡ ካልነኩት የማይነካ ሰው ሲነኩት ትንታግ ነው፡፡ እስክንድር እዛ ስሜት ውስጥ የገባው ተገድዶ ነበር፡፡ ሊጠይቁት የመጡትን ሰዎች አብዛኞቹን አላስገባም ማለታቸው ሳያንስ ከገቡትም መካከል የምታወራውን እኔ ልምረጥልህ በሚል ግብዝነት አባርረዋል፡፡ እስክንድር ይህን አይቶ ዝም ማለት አልቻለም፡፡ ስለሆነም እንዲህ አለ፤ ‹‹…እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል! የማወራው ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለህጋዊ ትግል ነው! ስለሀገሬ ያገባኛል!››

‹‹ማዕከላዊ ነው እንዴ ያለነው?›› (ክፍል ፩) – በናትናኤል ፈለቀ

እራሳቸውን ድንገት ስተው ‹‹ኮማ›› ውስጥ የገቡ ወላጅ አባቱን ለማስታመም እና በቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈውን አሳዳጊ ሴት አያቱን እርም ሊያወጣ ከ15 ዓመት በላይ ወደተለያት ሀገሩ እየተመለሰ ነው፡፡ ለጉዞው ቀና ብሎ ያሰበው መንገድ ከሚኖርበት ሴንት ፖውል፣ ሚኒሶታ ወደካናዳዋ ቶሮንቶ አቅንቶ ከዛ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት እና በማግስቱ አውቶቢስ ተሳፍሮ አባቱን ወደሚያገኝበት የሱማሌ ክልል ከተማ ጎዴ ማምራትን ነበር፡፡
ወደ ሀገሩ ተመልሶ አባቱን ለማግኘት እጅግ ቸኩሏል፤ ተጨንቋል፡፡ ጭንቀቱን የሚያሳብቀው ገና ከተወለደች ሁለት ሳምንት ያልሞላትን ሁለተኛ ልጁን እና የሦስት ዓመት ወንድ ልጁን አራስ ባለቤቱ ላይ ጥሎ ጉዞውን መጀመሩ ነው፡፡ ነገሮች ሁሉ እንዳቀደው ከሄዱለት በአንድ ወር ግዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ቆይታውን አጠናቆ ዜጋዋ አድርጋ ወደተቀበለችው አሜሪካን ይመለሳል፡፡
በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ግንቦት 29 ቀን፣ 2006 ዓ.ም ዕለተ ዓርብ የ31 ዓመቱ ፈረሃን ኢብራሂም አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ የጢያራ ማረፊያ ደረሰ፡፡ አብረውት አዲስ አበባ እንዲደርሱ የሸከፋቸው ሻንጣዎች ግን አልደረሱም፡፡ ጉዳዩን ያስረዳቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ጓዙ የሚመጣው በሚቀጥለው በረራ እንደሚሆን፤ ይህ ማለት ደግሞ አዲስ አበባ የሚደርሰው ከሁለት ቀን በኋላ እንደሚሆን አስረዱት፡፡ የዕቅዱ መዛነፍ የመጀመርያ ምዕራፍ ይህ ሆነ፡፡ ነገርየው ብዙም የሚያስጨንቅ ሆኖ አላገኘውም፡፡ በሥራው ምክንያት የብዙ ግዜ የአየር ጉዞ ልምድ ስላለው እንደዚህ ዓይነት አጋጣሚዎች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ያውቃል፡፡ አባቱን የሚያገኝበት ግዜ መራዘሙ ቢያሳስበውም አዲስ አበባ ውስጥ ሁለት ቀን እንዲቆይ መገደዱ ከተማዋን ዞር ዞር ብሎ ለማየት የሚፈጥርለትን ዕድል በማሰብ ለመፅናናት ሞከረ፡፡
***
ፋይሰል ሜድኮ ባዮ ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ የሁለተኛ ዓመት የፋርማሲ ተማሪ ነው፡፡ የትምህርት ወጪውን የሚሸፍንለት በፎቶ ብቻ የሚያውቀው የአጎቱ ልጅ ከአሜሪካን ሀገር ሲመጣ ተቀብሎ አዲስ አበባ ያለውን መስተንግዶ ጨርሶ ወደጎዴ ለመላክ ያለውን ኃላፊነት እሱ ወስዷል፡፡ የአጎቱ ልጅ ሲያገኘው እንዲኮራበትም በቅርቡ በላከለት ገንዘብ ያሰፋውን ጥቁር ሱፍ ግጥም አድርጎ ለብሶ፣ አበባ ይዞ ቦሌ ዓለም አቀፍ ጢያራ ማረፊያ መንገደኞችን ለመቀበል ከተደረደሩት ሰዎች መኻከል ተገኝቷል፡፡
እሁድ ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 12፡30 ገደማ ፋይሰል ፈጽሞ ሊገባው ባልቻለ ሁኔታ እራሱን የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የተጠርጣሪዎች ማረፊያ ክፍል ቁጥር 9 ውስጥ አግኝቶታል፡፡ ከሱ አስቀድሞ ክፍሉ ውስጥ ነበሩትን ሰዎች ምን እየተፈጠረ እንደሆነ እንዲያስረዱት በሚችላት ትንሽ አማርኛ ተፍጨረጨረ፡፡ ሊገባው የቻለው ነገር ያለበት ቦታ በተለምዶ ማዕከላዊ እየተባለ እንደሚጠራ እና ያሉበት ክፍል የሚገኝበት ሕንፃ በቅዝቃዜው ምክንያት ‹‹ሳይቤርያ›› የሚል ስያሜ እንደተሰጠው
ብቻ ነው፡፡
***
ፈረሃን ለመጀመርያ ጊዜ በዕጁ ያጠለቀውን ካቴና ፈትተው አንድ ደብዛዛ ብርሃን ያለበት ክፍል በር ከፍተው ገፈተሩት፡፡ ከሻንጣው ውስጥ ወደማረፊያ ቤቱ ይዞት እንዲገባ የተፈቀደለትን አንድ ቅያሪ ቱታ እና የጥርስ ብሩሽ እና ሳሙና በቢጫ ፌስታል እንዳንጠለጠለ በሩ አጠገብ ቆሞ የገባበትን ክፍል ይቃኝ ጀመር፡፡ በር ድረስ አጅበው ይዘውት የመጡት ሰማያዊ ቀለም ያለው ሬንጀር የለበሱ ሰዎች በሩን ሲዘጉት የወጣው ድምጽ የክፍሉን ቅኝት አቋርጦ በድንጋጤ ከበሩ አካባቢ እንዲርቅ አስገደደው፡፡
ደቂቃዎች አለፉ፤ ፌስታሉን በዕጁ እንዳንጠለጠለ ቆሟል፡፡ ቀድመው ክፍሉ ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ቆጠራቸው፣ 13 ነበሩ፡፡ ‹‹ቁጭ በል›› ብለው ቢጋብዙትም አልገባውም፡፡ በቋንቋ እንዳልተግባቡ ሲረዱ ከመካከላቸው ተኝቶ የነበረ አንድ ልጅ ቀሰቀሱና ‹እንግዳ ተቀበል› አሉት፡፡ ከንቅልፉ የተቀሰቀሰው ልጅ ከፍራሹ ተነስቶ ወደቆመው ሰውዬ አመራና እጁን ለሰላምታ ዘረጋ፡፡ ኡመድ ብሎ እራሱን አስተዋወቀ;; የቆመው ሰውዬ ለሰላምታ የተዘረጋለትን እጅ በቸልታ እየጨበጠ ‹‹ፈረሃን እባላለሁ›› አለ፡፡ ኡመድ ሌላኛውን እጁን ፌስታሉን ለመቀበል እየሰደደ እንግዳውን እንግሊዘኛ መናገር ይችል እንደሆነ ጠየቀ፡፡ ፈረሃን ጭንቅላቱን ላይ ታች ወዝውዞ መለሰለት፡፡ ሊግባባው ሚችል ሰው ማግኘቱ ቢያስደስተውም አሁንም ፈፅሞ ደኅንነት እየተሰማው አይደለም፡፡ ለማየት የሚረዳውን መነጽር ከዓይኑ ላይ አወረደና በእጁ ያዘ፡፡ አንድ ጊዜ እንደገና ክፍሉን ቃኘ፡፡ በኮንክሪት የተሰራ ጣራ እና ግርግዳ፣ ለአየር መውጫና መግቢያ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ብርሃን የሚገባበት በፍርግርግ ብረት የተገደበ ከበሩ በስተግራ በኩል ጣራውን ታክኮ ያለ ትንሽ ክፍተት፣ ክፍሉ ውስጥ ባሉ ሰዎች ቁጥር ልክ የሚመስል ጥግ ይዘው የተደረደሩ የውኃ ማሸጊያ ላስቲኮች፣… ከላስቲኮቹ መኻከል አንዳንዶቹ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ሽንት ስለመሰለው በመጠየፍ መራቅ ፈለገ፡፡ ኡመድ ተኝቶ ወደነበረበት ፍራሽ ተመለሰና ‹‹ፈረሃን፣ ወደዚህ ና›› ሲል ጋበዘው፡፡ ከላስቲኮቹ መራቅ የፈለገው ፈረሃን በትክክለኛው ሰዓት የመጣለትን ግብዣ ተቀብሎ ጫማውን አወለቀና በፍራሾች ላይ ተረማምዶ ከኡመድ አጠገብ ተቀመጠ፡፡
ክፍሉ ውስጥ ያሉት ሌሎች ሰዎች የኡመድ እና የፈረሃንን ዓይን አፈራርቀው እያዩ ለኡመድ በጥያቄ አጣደፉት፡፡ ኡመድ ወደፈረሃን ዞሮ ‹‹ሱማሌ ትመስላለህ?›› አለው፡፡ ፈረሃን በመስማማት በመስማማት ጭንቅላቱን ነቀነቀ፡፡ ኡመድ አብረውት ከታሰሩ ሶማሌዎች ካስተማሩት የሚያስታውሳትን ሱማልኛ ተናገረ ‹‹ማፊዓንታሃይ?›› ፈረሃን ክፍሉ ውስጥ ከገባ በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ፈገግ ብሎ መልስ ሰጠ – ‹‹ፊዓን›› ሲል፡፡ የሚችለውን ሱማልኛ የጨረሰው ኡመድ በእንግሊዘኛ መናገር ቀጠለ፡፡ ‹‹ከየት ነው የመጣኸው?›› ፈረሃን ጥያቄውን ለመመለስ ጥቂት ሰከንዶች ከወሰደ በኋላ የሚኖረው አሜሪካን ሀገር እደሆነ፣ ለጥቂት ግዜ እረፍት ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ አስረዳ፡፡ ኡመድ ጥያቄውን ቀጥሎ ለምን እንደታሰረ ያውቅ እደሆነ ጠየቀው፡፡ ፈረሃን ግራ መጋባቱን በሚያሳብቅ ሁኔታ ዓይኑን ግራና ቀኝ ካንከባለለ በኋላ ትከሻውን ሰብቆ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገለፀ፡፡ አብረዋቸው ያሉት ሰዎች ጥያቄዎቻቸውን እያዥጎደጎዱ እንዲያስተረጉምላቸው ቢፈልጉም ከዚህ በላይ ፈረሃንን ማስጨነቅ ያልመረጠው ኡመድ ‹‹አሁን ተረጋግተህ እረፍት አድርግና ጠዋት እናወራለን፡፡ ለሁላችንም የሚበቃ ፍራሽ ስለሌለ ከኔ ጋር ፍራሽ እንጋራለን፡፡ ሽንት መሽናት ከፈለክ ከነዛ ላስቲኮች አንዱን ተጠቀም፡፡›› አለውና አንሶላ አነጠፈለት፡፡ ፈረሃን ‹‹አመሰግናለሁ›› አለና እንደማመንታት ብሎ ማውራት ቀጠለ፡፡ ‹‹ታውቃለህ? መጀመሪያ እዚህ ሲያስገቡኝ የምትደበድቡኝ መስሎኝ ነበር፡፡ እኔ የምኖርበት ሀገር እስር ቤት ውስጥ አዲስ ሰው ሲገባ የቆዩት እስረኞች በድብደባ ነው አቀባበል የሚያደርጉለት፡፡›› ኡመድ ጮክ ብሎ ሳቀ፡፡ ሌሎቹ እስረኞች ምን እንዳሳቀው ለማወቅ ጓግተው ጠየቁት፡፡ ፈረሃን የነገረውን ተረጎመላቸው፡፡ ሁሉም እየተሳሳቁ ፍራሾቻቸውን ማንጠፍ ጀመሩ፡፡ ኡመድ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሌሎች እስር ቤቶች ውስጥም ተመሳሳይ ነገር ሊከሰት እንደሚችል ለፈረሃን አስረዳው፡፡
ፈረሃን ለመተኛት ትንሽ ሲገላበጥ ቆየና የረሳው አንድ ነገር ድንገት ትዝ አለውና ኡመድን ‹‹ፀሎት ማድረግ እችላለሁ?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ኡመድ፤ በክፍሉ ውስጥ የነበሩት የእስልምና ዕምነት ተከታዮች የመግሪብ ፀሎት እንዳደረጉ፣ ትንሽ ከቆየ አብሯቸው የኢሻ ፀሎት ማድረግ እንደሚችል አልያ ግን ብቻውን ቢፀልይ ችግር እንደሌለው እና ቦታ ሊያመቻችለት እንደሚችል ነገረው፡፡ ፈረሃን ቆይቶ በጋራ ፀሎት ማድረጉን መረጠ፡፡
***
ከእንቅልፉ ነቅቶ አይኑን ሲገልጥ ግር ተሰኘ፡፡ ዙሪያውን ሲያይ የማያውቀው ቦታ እራሱን ስላገኘው ተደናገጠ፡፡ ዓይኖቹን አሻቸው፤ የተለወጠ ነገር ግን አልነበረም፡፡ ቀስ ብሎ ለማስታወስ ሞከረ፡፡ ደስ የማይል ስሜት ውስጡን ሲወረው ተሰማው፡፡ ከ17 ሰዓታት በፊት የተፈጠረውን ነገር አስታወሰ፡፡ በህልሙ ቢሆን ምርጫው ነበር፡፡
***
የዘገዩት ሻንጣዎችን ለማምጣት እሁድ ረፋድ ላይ ካረፈበት ሆቴል ታክሲ ተኮናትሮ ወደቦሌ አቀና፡፡ የአየር መንገዱ ሰራተኞች ለተፈጠረው ስህተት እና መጉላላት ይቅርታ ጠይቀው ሻንጣዎቹን አስረክበው ሸኙት፡፡ ወዳረፈበት ሆቴል እየተመለሰ ለፋይሰል የስልክ ጥሪ አደረገና የዘገዩት ሻንጣዎች በእጁ መግባታቸውን ከነገረው በኋላ ወደጎዴ የሚወስደውን የአውቶቢስ ትኬት ለመቁረጥ ሰኞ ጠዋት ለመገናኘት ተቀጣጠሩ፡፡ ፋይሰል ያረፈበት ሆቴል ድረስ መጥቶ አብረው ሄደው ትኬቱን እንደሚገዙ ነበር የተሰማሙት፡፡
የሚያደርገው ስላልነበረው ዕረፍት ለማድረግ አስቦ ጋደም አለ፡፡እንቅልፉ መኻል ላይ ያረፈበት ሆቴል ክፍል በር ሲንኳኳ ሰማ፡፡ የሚጠብቀው እንግዳ አልነበረም፤ ከፋይሰል በስተቀር ያረፈበትን ቦታ የሚያውቅ የቅርብ ሰው የለውም፡፡ ከፋይሰል ጋር ደግሞ ከሰኞ በፊት ሌላ ቀጠሮ አልነበራቸውም፡፡ በሰመመን ሆኖ የሆቴሉ ሰራተኞች ለፅዳት ወይንም ሌላ አገልግሎት መግባት ፈልገው ሊሆን እንደሚችል ገመተ፡፡ ከእንቅልፉ ጨርሶ መንቃት ስላልፈለገ የበሩን ጥሪ ትቶ ወደእንቅልፉ ለመመለስ ሞከረ፡፡ ከቆይታ በኋላ ግን በሩ እንደገና ተንኳኳ፡፡ ይኼው መንኳኳት እንደቀደመው ሊተወው የሚችለው አልነበረም፡፡ በከፍተኛ ድምጽ እና ቶሎ ቶሎ ነበር በሩ የሚደበደበው፡፡ በንዴት ሱሪውን እንኳን ሳያጠልቅ ከአልጋው ወረደና ወደበሩ ሄዶ ከፈተው፡፡ በሩ ላይ ቆመው መከፈቱን ይጠባበቁ የነበሩት ብዛት ያላቸው መሣርያ የታጠቁ ዥንጉርጉር ሰማያዊ መለዮ የለበሱ ሰዎች እና አንድ ሲቪል የለበሰ ሰው ፈረሃንን ገፍትረው ወደክፍሉ ገቡ፡፡ የሚያየውን ማመን ከብዶት ነበር፡፡ የታጠቁት ሰዎች የክፍሉን ጥግ ጥግ ይዘው ቆሙ፡፡ ሲቪል የለበሰው ሰውዬ የፈረሃንን ክንድ ይዞ እንዲቀመጥ ጎተተው፡፡ ሰውየው ቤቱን ዞር ዞር ብሎ ካየ በኋላ ፊት ለፊቱ ተቀመጠ፡፡ ሰውየው በተሰባበረ እንግሊዘኛ ፖሊሶች መሆናቸውን እና ያረፈበትን ክፍል ሊፈትሹ እንደሚፈልጉ ገልፆ ሻንጣዎቹን የት እንዳደረጋቸው ጠየቀው፡፡ ፈረሃን በአገጩ ወደሻንጣዎቹ ጠቆመ፡፡ ሰውየው በተጠንቀቅ ወደቆሙት ወታደሮች ዞሮ በዓይኑ ምልክት ሰጣቸው፡፡ ሁለቱ መሣሪያቸውን ወደጀርባቸው አዙረው አዘሉና ሻንጣዎቹን መበርበር ጀመሩ፡፡ ላፕቶፕ ኮምፒውተሩን፣ ለዘመዶቹ ይዟቸው የመጣው አራት ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልክ ቀፎዎች እና ሻንጣው ውስጥ ያገኟቸውን ወረቀቶች በሙሉ ለብቻ ለብቻ ዘረገፏቸው፡፡ ሲቪል የለበሰው ሰውዬ ወረቀቶቹን አለፍ አለፍ እያለ ገረበባቸው እና ወደፈረሃን ዞሮ ‹‹ፓስፖርትህ የት ነው ያለው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ፓስፖርቱን ከሱሪ ኪሱ አውጥቶ ሊሰጠው ከተቀመጠበት ፈረሃን ብድግ ሲል ሰውየው ከፍ ባለ ድምጽ ተቆጥቶ እንዲቀመጥ አዘዘው፡፡ ‹‹ፓስፖርቴ ያለው ሱሪ ኪሴ ውስጥ ነው፡፡›› አለ በድንጋጤ ተውጦ ሱሪው ወዳለበት ቁምሳጥን እየጠቆመ፡፡ ሰውየው እራሱ ሳጥኑን ከፍቶ ሱሪውን ፈተሸ፡፡ ጥቂት የኢትዮጵያ ብሮች፣ ብዛት ያለው የአሜሪካን ዶላር እና የአሜሪካን ዜጋ መሆኑን የሚያረጋግጥ ፓስፖርቱን ካወጣና ሌላ ምንም እንዳልቀረ ካረጋገጠ በኋላ ሱሪውን ለፈረሃን ወረወረለት፡፡ ፈረሃን በተቀመጠበት ሆኖ ታግሎ ሱሪውን አጠለቀ፡፡
ከሻንጣዎቹ የወጡትን ንብረቶቹን ለብቻ አድርገው ሻንጣዎቹን ዘግተው ይዘዋቸው ወጡ፡፡ ሲቪል የለበሰው ሰውዬ እንዲነሳ አዝዞ ወደበሩ በአገጩ ጠቆመው፡፡ ዝም ብሎ ከዚህ በላይ መሄድ ያልፈለገው ፈረሃን ምን እየተካሄደ እንደሆነ ጠየቀ፡፡ ሲቪል ከለበሰው ሰውዬ ‹‹ፖሊሶች ነን›› ከሚል ምላሽ ውጪ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማግኘት አልቻለም፡፡ ገፍትረውት ከገቡት ክፍል እየገፉ ይዘውት ወጡ፡፡
***
የረፈሃንን ስልክ ጥሪ ተቀብሎ ለሰኞ ቀጠሮ ከሰጠው በኋላ ፋይሰል ወትሮ እሁድ ከሰዓት እንደሚያደርገው ከጓዶቹ ጋር ኳስ እየተጫወተ ለማሳለፍ ከሚኖርበት ቦሌ ሚካኤል የጋራ መኖርያ ቤቶች አቅራቢያ ወደሚገኘው የእግርኳስ ሜዳ አመራ፡፡ ቀድመውት ከደረሱት ጓደኞቹ ጋር ኳስ እየተጫወቱ ወደማጠናቀቁ ሲቃረቡ ያልተለመደ ሁኔታ አካባቢው ላይ አስተዋለ፡፡ ሁሉም ጓደኞቹ ቆመው ኳሷ ብቻዋን ሜዳው ላይ ተንከባለለች፡፡ አስር የሚደርሱ ፌደራል ፖሊሶች ኳስ መጫወቻ ሜዳውን ከበው እያጠበቡ እየተጠጓቸው ነበር፡፡ የፖሊሶቹ ጣቶች ያነገቡት መሣርያ ቃታ አካባቢ ተሰድሯል፡፡ ፋይሰል አብረውት ኳስ ከሚጫወቱት ጓደኞቹ መካከል አንደኛውን እንደሚፈልጉ ገምቶ ነበር፡፡ የመጡት ፖሊሶች ‹ፌደራሎች› መሆናቸው የመጡበት ጉዳይ ቀላል እናዳልሆነ ጠቁሞታል፡፡ ይህ እያሰላሰለ ለጥቂት ሰከንዶች ከገባበት ሐሳብ ስሙ ሲጠራ ሰምቶ ባነነ፡፡ የከበቧቸውን ፖሊሶች ከኋላ ሆኖ የሚመራው ሲቪል የለበሰ ሰውዬ ነበር ሥሙን የጠራው፡፡ በፍጥነት ነገሩ ሁሉ ተደበላለቀበት፡፡ ስሙ ድጋሚ ሲጠራ መደናገሩ ስላለቀቀው ቆሞ ከማፍጠጥ ውጭ ምንም ማድረግ አልቻለም፡፡ የጓደኞቹ ዓይኖች በሙሉ እሱ ላይ አነጣጠሩ፡፡ ለሦስተኛ ግዜ ስሙ ሲጠራ የሚማርበት ክፍል ውስጥ ጥያቄ ለመመለስ እንደሚያደርገው የግራ እጁን ወደላይ አነሳ፡፡
***
ሊነጋጋ ሲል ያደሩበት ክፍል በር ተከፍቶ በሽንት የተሞሉትን ላስቲኮች እያንጠለጠሉ እየተጣደፉ ሲወጡ ምን እንደተፈጠረ እንዲያስረዳው ፈረሃን ኡመድን ጠየቀ፡፡ በቀን ውስጥ ሽንቱን መሽናት እና ውሃ ለመቅዳት ከሚያገኛቸው ሁለት አጋጣሚዎች አነደኛው መሆኑን፤ ይህ አጋጣሚ ግፋ ቢል ለ20 ደቂቃዎች ብቻ ስለሚቆይ ፈጠን ብሎ ተነስቶ ጉዳዩን እንዲጨርስ ከማሳሰቢያ ጋር ኡመድ መለሰለት፡፡ ፈረሃን ያገኘው መልስ ባይዋጥለትም ማሳሰቢያውን ተቀብሎ ወደመጸዳጃ ቤቱ አመራ የሽንት ሰዓቱ አብቅቶ በሩ ተመል እንደተዘጋ ጉዳዩን እንዲያብራራለት በድጋሚ ኡመድን ጠየቀው፡፡ ኡመድ የተለየ መል አልነበረውም፡፡
ኡመድ እና ጓደኞቹ የፈረሃንን ቁርስ ተቀበሉለት እና አብሯቸው በላ፡፡ ሁሉንም በሥም ተዋወቃቸው፡፡ በዕድሜ፣ በተክለ ሰውነት፣ በፊታቸው ቀለም ይለያያሉ፡፡ ሁሉም እዛው የተዋወቁ እንደሆነ ገብቶታል፡፡ ነገር ግን ከእንቅልፉ ሲባንን ነጭ አንሶላ የመሰለ ልብስ ተከናንበው ቆመው በቃላቸው ሲያነበንቡ የነበሩት ሽማግሌ ሰውዬ ከትግራይ የመጡት ቄስ ጎይቶም፣ ከኡመድ ቀጥሎ ግርግዳውን ታክኮ ያለው ፍራሽ ላይ ለሁለት የተኙት ወጣቶች የጅማና የሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ምህንድና ተማሪዎቹ ሌንጂሳ እና ቢልሱማ፣ ከራሱ በስተቀኝ በኩል ተኝቶ ያደረው ወጣት የ16 ዓመቱ የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ታጋይ አብዱ፣ ከሱ በተቃራኒው ከቄሱ አጠገብ የተኛው ጎስቋላ ጎልማሳ የቤጊው ገበሬው በሊስ (አስፋው)፣ ከነሌንጂሳ በተቃራኒ ያለውን ፍራሽ የሚጋሩት የጅማው ኢማም ሼህ ጀማል እና ጣሂር፣… ባጠቃላይ ከኤልያስ በስተቀር ሲገባ ከቆጠራቸው 13 ሰዎች ውስጥ 12ቱ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በምርመራ ላይ ያሉ መሆናቸው ገና አልገባውም፡፡
ቁርሳቸውን ጨርሰው ሁላቸውም ፍራሾቻቸው ላይ ቁጭ ቁጭ ብለው በዝምታ ተዋጡ፡፡ ማታ ሲቀላቀላቸው በጨዋታ ደምቆ የነበረው ክፍል ለምን በዝምታ እንደተዋጠ አልገባውም፡፡ ምናልባት ወደኋላ እየሞቃቸው ሲሄድ ዝምታው እንደሚጠፋ ገመተ፡፡ በአብዛኞቹ ጭንቅላት ውስጥ ገብቶ ዝምታውን ያሰፈነው ሰኞ ጠዋት መሆኑ ነበር፡፡ እሁድ ቀን ከምርመራ ሚያርፉባት ናት፡፡ ሰኞ ጠዋት ደግሞ ምርመራው የቆመው ምን ጋር እንደነበር እያስታወሱ እንዴት እንደሚቀጥል እና ከግርፋት እና ከእንግልት የሚድኑበት መልስ ምን እንደሆነ የሚያሰላስሉባት ናት፡፡
ፈረሃን ዝምታን ለመስበር ለኡመድ ጥያቄ አነሳ፡፡ ‹‹አሁን ምንድነው የሚሆነው? ምንድን ነው የምሆነው?›› ኡመድ ረጋ ብሎ ለፈረሃን መመለስ ጀመረ ‹‹ዛሬ ምናልባት ፍርድ ቤት ይወስዱህ ይሆናል፡፡ ለምን እዚህ እንዳመጡህ ለፍርድ ቤት ሲያስረዱ ትሰማለህ …›› ፈረሃን ኡመድን አቋረጠውና ‹‹ፍርድ ቤት በእንግሊዘኛ ነው የሚሰራው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ኡመድ ፈገግ ብሎ ‹‹ፍርድ ቤት በእንግሊዘኛ አይሠራም፡፡ ሱማልኛ አስተርጓሚ መጠየቅ ግን ትችላለህ፡፡›› አለው፡፡ ማስረዳቱን ቀጥሎም ‹‹በደረቅ ወንጀል ከሆነ የጠረጠሩህ እስከ 14 ቀን የሚደርስ ቀጠሮ አለበለዚያ በሽብር የሚጠረጥሩህ ከሆነ ደግሞ …›› ፈረሃን በድጋሚ ኡመድን ቋረጠውና ‹‹ይህ ሊሆን አይችልም!›› አለ፡፡ ኡመድ ፈገግ ብሎ ‹‹በጣም ጥሩ›› ብሎ መለሰ፡፡ በልቡ ግን ፈረሃን ፍርድ ቤት ከሄደ የ28 ቀን ቀጠሮ ይዞ እንደሚመጣ ጠንካራ ግምት ነበረው፡፡
ትንሽ እንደተጨዋወቱ ያሉበት ክፍል በር ተከፈተና ኡመድ ተጠራ፡፡ እየተቻኮለ እየወጣ ወደፈረሃን ዞሮ ‹‹ምርመራ መሄዴ ነው፡፡›› አለው፡፡ ብዙም ሳይቆይ ፈረሃንም ተጠርቶ ወጣ፡፡ ለምሣ ሰዓት ጥቂት ግዜ ሲቀረው ፈረሃን ተመልሶ መጣ፡፡ ፊቱ ላይ የመቆጣት ስሜት ይነበብበት ነበር፡፡ ምርመራውን ጨርሶ ከፈረሃን በፊት ወደክፍሉ ተመልሶ የነበረው ኡመድ ‹‹ፈረሃን፤ እንኳን በደህና ተመለስክ፡፡ ፍርድ ቤት ወሰዱህ እንዴ?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ተስፋ በቆረጠ የተሰላቸ ድምጽ ‹‹28 ቀን ቀጠሩኝ፡፡›› ብሎ ፍራሹ ላይ በደረቱ ተደፋ፡፡
***
የክፍሉ መቀርቀሪያ በኃይል ተወርውሮ ሲከፈት ያወጣው ድምጽ ሁሉንም ከእንቅልፍ ቀሰቀሳቸው፡፡ በርግጥ ከመካከላቸው ገና ወደበሩ እየቀረበ የነበረውን የእግር ኮቴ እና ሲንቀጫቀጭ የነበረውን የካቴና ድምጽ ሰምተው ከእንቅልፋቸው አስቀድመው የነቁ ነበሩ፡፡ በሩ ተከፍቶ ‹‹ሌንጂሳ አለማየሁ›› የሚል ድምጽ ተጣራ፡፡ ሁሉም ዓይናቸውን ወደሌንጅሳ ወረወሩ፡፡ ‹‹አቤት›› ብሎ ብርድ ልብሱን ከላዩ ላይ እየገፈፈ ተነሳ፡፡ ከመውጣቱ በፊት የመተኛ ሱሪው ላይ ሌላ ሱሪ ደረበ፡፡
ፈረሃን ክፍሉ ውስጥ የቀሩት ሰዎች ሌንጂሳን ያዩ የነበረበት ሁኔታ የሆነ ክፉ ነገር እንዳለ ነግሮታል፡፡ ከእንቅልፍ አስቀስቅሶ የሚያስወስድ አሳሳቢ ነገር ምን ይሆን ሲል አሰበ፡፡ ስንት ሰዓት እንደሆነ ጠየቀ፡፡ ኡመድ በግምት ሶስት ሰዓት አካባቢ እንደሚሆን ሲናገር ፈረሃን ቀና ብሎ የክፍሉን አራት ማዕዘን ግርግዳዎች ቃኘ፡፡ የፈለገውን አላገኘም፡፡ ‹‹እዚህ ምንም ሰው ሰዓት የለውም?›› ሲል ጠየቀ፡፡ ኤልያስ የፈረሃን ጥያቄ ያለአስተርጓሚ ስለገባው ተሰባበረ እንግሊዘኛ ወደማረፊያ ቤት ሰዓት ይዞ መግባት የተከለከለ መሆኑን አስረዳ፡፡ ፈረሃን የበለጠ ግራ በመጋባት ‹‹ታድያ የፀሎት ሰዓት ሲደርስ በምንድን ነው የምናውቀው?›› ኤልያስ ጥያቄውን መረዳት ስላቃተው የኡመድን ዓይን ያይ ጀመር፡፡ የኤልያስ ችግር የተረዳው ኡመድ የፈረሃንን ጥያቄ ተርጉሞ ነገረው፡፡ ‹‹አሃ…›› ኤልያስ መልሱን በእንግሊዘኛ ሲያደረጅ ቆየና ተሰላችቶ ኡመድን በቃ አንተ ንገረው በሚል አኳኻን አይቶት ዝም አለ፡፡ ጠዋት እና ማታ የሚቆጥሯቸው ፖሊሶች ሲመጡ ስንት ሰዓት እንደሆነ እንደሚጠይቋቸው እና ከዛ የቀረውን ግዜ በግምት እንደሚያሟሉት ኡመድ አብራራ፡፡ ፈረሃን ያለበት ቦታ ሲዖልነት ቀስ በቀስ እየገባው ነው፡፡ ቀጥሎ በጠየቃቸው ጥያቄዎች የተረዳው ነገር ደግሞ ለደህንነቱ አብዝቶ እንዲጨነቅ አስገደደው፡፡ ሌንጂሳ እና ጓደኛው ቢልሱማ ከሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ በቁጥጥር ስር የዋሉት መንግሥት ሊተገብረው ያቀደውን የአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞኖች የተቀናጀ ማስተር ፕላንን በመቃወም የተካሄዱ ሰልፎች ላይ ተሳትፋቹኻል እና ተቃውሞውን አስተባብራቹኻል በሚል ምክንያት ሲሆን በተለይ ሌንጂሳ ጅማ ዩኒቨርስቲ ደጃፍ ላይ በደህንነቶች ከተያዘ በኋላ አዲስ አበባ እስኪመጣ ድረስ የነበረውን 3ቀን እህል የሚባል እንዳልቀመሰ፣ አሁን ያሉበት ቦታ ካመጡት ጀምሮ ደግሞ በየቀኑ ማታ ማታ ተጠርቶ ሌሊቱን ክፉኛ እየተደበደበ በምርመራ እንደሚያጋምስ ነበር የተነገረው፡፡ ምርመራ ተወስዶ መደብደብ ማንም ሰው ላይ ሊከሰት እንደሚችል፣ ክፍሉ ውስጥ ከነበሩት ሰዎች መካከል ጨዋታ ከሚወደው ባለ ደንዳና ሰውነቱ የቡና ነጋዴ ኤልያስ በስተቀር ሁሉም ክፉኛ ድብደባ የደረሰባቸው መሆኑን ኡመድ አንድ በአንድ እየጠቆመ ነገረው፡፡
እንቅልፍ አጥቶ ሲገላበጥ ብዙ ሰዓት አለፈው፡፡
የክፍሉ በር ተከፈተና ሌንጂሳ በፖሊስ ተደግፎ ወደክፍሉ ገባ፡፡ እራሱን ችሎ መራመድ ስላቃተው ቢልሱማ ተነስቶ ድጋፍ ሆኖት ወደፍራሹ አደረሰው፡፡ ሁሉም ድጋሚ ከእንቅልፋቸው ተነስተው በትካዜ ተዋጡ፤ የተከሰተው ለሁሉም ገብቷቸዋል፡፡ ፈረሃን አንድ ነገር ድንገት ጭንቅለቱ ውስጥ አቃጨለ፡፡ አንድ ጓደኛው ከወራት በፊት በአግራሞት አውርቶለት የነበረ ‹‹Human Rights Watch›› የተባለ የመብት ተሟጋች ቡድን ‹‹They Want Confession›› በሚል ርእስ ያወጣው ዘገባ ትዝ አለውና ወደኡመድ ዞሮ ‹‹ማዕከላዊ ነው እንዴ ያለነው?›› ሲል ጠየቀ፡፡
***
ፋይሰል ፍርድ ቤት የተከሰተው ነገር ጭራሽ ግርታውን አብሶበታል፡፡ ከሱ እና ከአጎቱ ልጅ በተጨማሪ አይቷቸው የማያውቃቸው ሶስት ወንድ እና አንድ ወጣት ሴት ሱማሌዎች አብረዋቸው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ሶስቱ ወንድ ሱማሌዎች የሚያመሳስላቸው ነገር እንዳለ ፋይሰል አስተውሏል፡፡ የአነጋገር ዘይቤያቸው ልክ እንዳጎቱ ልጅ ውጭ ሀገር ቆይተው እንደመጡ ያስታውቃል፡፡ 18 ዓመት እንኳን የሞላት የማትመስለው አብራቸው ፍርድ ቤት የቀረበችው ሴት ደግሞ ከአነጋገሯ የኢትዮጵያ ሱማሌ እንዳልሆነች ገብቶታል፡፡
ከፍርድ ቤት እንደተመለሰ ክፍሉ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ጥያቄ ያጣድፉት ያዙ፡፡ ፍርድ ቤት የተከሰተውን ለማስረዳት ሞከረ፡፡ ስድስት ሆነው እንደሄዱ፣ ችሎት ውስጥ ለሁለት ከፍለው ሦስት ሦስት አድርገው ይዘዋቸው እንደገቡ፣ እሱን በዕድሜ ሸምገል ካለው ሰውዬ እና ከወጣቷ ጋር ችሎት ፊት እንዳቀረቡት ነገራቸው፡፡ በጥሞና ሲያዳምጡት የነበሩት ሰዎች በምን ወንጀል እደተጠረጠረ ለማወቅ ነበር፡፡ ፋይሰል በረጅሙ ትንፋሽ ወስዶ ‹‹አል ሸባብ ከተባለ ቡድን ተልዕኮ ተቀብለው አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የሽብር ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ይዣቸኋለው፡፡›› የሚል ክስ ይዟቸው የሄደው ፖሊስ አንብቦ የ28 ቀን ቀጠሮ እደጠየቀና መነፅራቸውን ዝቅ አድርገው ጥያቄውን የሰሙት አዛውንት ሴት ዳኛ የ28 ቀን ቀጠሮውን መፍቀዳቸውን አስረዳቸው፡፡ ከጠበቁት ብዙም የራቀ ነገር አልነገራቸውም፡፡ ምንም የመደንገጥም ሆነ የመሸሽ ዓይነት ስሜት ስላላየባቸው እረፍት ቢሰማውም ሽብርን የሚያክል ትልቅ ክስ ቀረበብኝ ሲላቸው አለመገረማቸው ግር አሰኝቶት ነበር፡፡ ኋላ ላይ ሲረዳ ግን ማዕከላዊ የገባ ሰው ከሱማሌ ከሆነ አልሸባብ ወይንም ኦብነግ ተብሎ፣ ኦሮሞ ከሆነ ኦነግ፣ ከትግራይ ከሆነ ትሕዴን፣ ሙስሊም ከሆነ አልቃይዳ፣ አማራ ከሆነ አርበኞች ግንባር፣ ጋዜጠኛ ወይንም የፖለቲካ ድርጅት አባል ከሆነ ግንቦት 7 ተብሎ መከሰሱ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
***
ምሣ በልተው እንደጨረሱ በሩ ተከፈተና የፋይሰል ስም ተጠራ፡፡ ‹‹አለሁ›› ሲል ለጥሪው መልስ፡፡ ‹‹ዕቃህን ይዘህ ውጣ›› የሚል ትዕዛዝ ተከተለ፡፡ የተባለው ስላልገባው እንዲደገምለት ‹‹እእ…›› አለ፡፡ በሩ ላይ የቆመው ፖሊስ ቁጣ በተቀላቀለበት ድምጽ ‹‹ዕቃህ ይዘህ ውጣ!›› ሲል ደገመለት፡፡ ከኳስ ጨዋታው መልስ ታጥቦ ሊቀይር ይዞት የነበረውን ልብስ በስስ ፌስታል ይዞ ወጣ፡፡
በር ላይ ቆሞ የነበረው ፖሊስ ካቴና አለመያዙን ሲያስተውል ተስፋ ቢጤ ተሰምቶት ነበር፡፡ ግን የተሰማው የተስፋ ስሜት በፍጥነት ወደተስፋ መቁረጥ ተለወጠ፡፡ ከሰው ጋር አብሮ ይታርሰር ከነበረበት ማረፊያ ቁጥር 9 የወጣው ብቻውን ወደሚታሰርበት ጨለማ ክፍል ቁጥር 8 ለመዘዋወር ነበር፡፡
***
በተለምዶ ሳይቤሪያ ተብሎ የሚጠራው የማዕከላዊ ሕንጻ ቁጥር 84 በረጅም ኮሪደር ለሁለት የተከፈለ ሲሆን የእስረኛ ማቆያ ክፍሎቹ ከኮሪደሩ ግራና ቀኝ የተደረደሩ ናቸው፡፡ ኮሪደሩ ሲጀመር በግራና በቀኝ 2ቁጥር እና 10 ቁጥር ማረፊያ ክፍሎች ፊት ለፊት ተፋጠዋል፡፡ በግራ በኩል ከ2ቁጥር አንስቶ እስከ 6ቁጥር የሚዘልቅ ሲሆን በስተቀኝ በኩል ደግሞ ከ10 ቁጥር ጀምሮ ቁልቁል እየቆጠረ እስከ 7ቁጥር ይሄዳል፡፡ ከ7 ቁጥር ማረፊያ ክፍል ቀጥሎ ደግሞ ዘጠኙ ክፍሎች ውስጥ የሚታሰሩት ሰዎች በየተራ ክፍሎቹ እየተከፈቱ በቀን ሁለት ግዜ (ጠዋት እና ማታ) ቢበዛ ለ20 ደቂቃዎች የሚጠቀሙበት ባለ6 የሽንት ቤት ክፍል እና አንድ መታጠቢያ ክፍል ያለው መጸዳጃ ቤት ይገኛል፡፡
ሳይቤርያ ውስጥ የሚገኙት ክፍሎች በስፋት ካልሆነ በቀር አንድ ዓይነት ናቸው፡፡ ከሁሉም ክፍሎች የሚለየው 8ቁጥር ነው፡፡ ከውጪ በሩ ተዘግቶ ለሚያየው ሰው 8 ቁጥርም ቢሆን ከሌሎቹ የሚለይበት ነገር የለም፡፡ በሩ ተከፍቶ ወደውስጥ ሲገባ ግን በግራና በቀኝ በኩል ሁለት ሁለት የራሳቸው በር ያላቸው ሌላ ከፍሎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ክፍሎች ጠንከር ያለ ምርመራ እየተደረገባቸው ላሉ መንፈሰ ጠንካራ ሰዋች የተዘጋጀ ነው፡፡ እነዚህ ክፍሎች ውሰጥ የሚታሰር ሰው በቦታ ጥበት፣ በጨለማ እና ብቸኝነት ይፈተናል፡፡
ይህ ታሪክ ለአንባቢ ምቾት ሲባል ከተደረገለት ዘይቤያዊ ማስተካከያ በስተቀር እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡
(ይቀጥላል)

ባልተገኘበት እና ባልተካሄደ ጦርነት ተሸንፈሃል ተብሎ የተወሰነበት የአማራ ነገድ እና ኢትዮጵያዊነት

 

ከአበበ ተድላ

እንደምናውቀው ትህነግ (ወያኔ) ትግራይ የተባለውን ክፍለሃገር ከተቆጣጠረ በኃላ፤በተለይ አማራውን መስዋእትነት አስከፍሎ፤ ወደሌላ የኢትዮጵያ ክፍለሃገሮች ተሻግራ፤ ደርግን ከ 25 አመት በፊት ገደማ ማሸነፏ ይታወሳል። እውነቱ፤ ደርግ ማለት ትግሬን ጨምሮ የተለያዩ የኢትዮጵያ ነገዶች የተሳተፉበት ሰው በላ አምባገነን ወታደሮች መንግስት ነበረ። ነገር ግን፤በምን ስሌት እንደሆነ ባይታወቅም፤ ደርግን ሲላቸው የአማራ መንግስት በማለት አማራን አሸንፍን ሲሉ ይሰማል፤ እንዲያ ሲላቸው ደግሞ አንድ ትውልድን ያጠፋ የኢትዮጵያ ጠላትን ደርግን ስላሸነፉ ብቻ፤ ኢትዮጵያዊነትን አሸነፍን ይላሉ። እስከምናውቀው፤ ደርግ የአማራን ትውልድ፤ አድሃሪ እና ሌላ ሌላ ስም እየሰጠ ከጨረሱት መካከል ነው፤ምንም እንኳን የትህነግን ያህል አማራን ባያጠፋም። ጎንደር እኮ እንዲህ ነው ያለው ለደርግ ባለስልጣን፦

መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድም፤

ያሁኑን ማርልኝ ሁለተኛ አልወልድም። 

ታዲያ እንዴት ነው ደርግ የአማራ መንግስት ነበር የሚባለው?

በከተማዎችም ደርግ ከማንም በላይ አማራውን ነው የጨረሰው። መሪው መንግስቱም ቢሆን በአባቱ ኦሮሞ ነው። ይሄ ሁሉ እውነት ሆኖ ሳለ፤ ደርግ አማራን እንደሚወክል አድርገው፤ ደርግን ከአማራ ጋር ሆነው ካሸነፉ በኃላ፤ አማራን እንዳሸነፉት አድርገው፤ ስንት የስድብ ቃላት እና ጥቃት አማራው ላይ ሲወርድ አይተናል። ችግሩ፤ አማራው ሳይደራጅ ስለሆነ ከትህነግ ጋር ሆኖ ደርግን ለመጣል ደሙን ያፈሰሰው፤ ውጤቱ መገደል እና ምንም እንዳላደረገ መሰደብ ነው የሆነው። ይሄ የአማራው ሳይደራጅ ህይወቱን መስጠቱ ጥፋት መሆኑን ነው የሚያሳየው እንጂ፤ እነታምራት ላይኔ ደርግን ለመጣል ስንት የአማራን ልጅ ደም እንዳስፈሰሱ ይታወቃል።

amhara

ይሄ ብቻ አይደለም። አንዳንዴም የደርግን መሸነፍ የኢትዮጵያዊነት መሸነፍ አድርገው ይቆጥራሉ ትህነጎች እና አጋሮቻቸው። ልብ በሉ ደርግ አንድ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሰባሰበ አምባገነን መንግስት ቢሆንም፤ ሌሎች ደርግን የሚቃወሙ ነገር ግን በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑ በርካታ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ነበሩ አሁንም አሉ። ትህነግ (ወያኔ) በምእራባዊያን እርዳታ በጦርነት ያሸነፈችው፤ስልጣን ላይ የነበረውን ደርግን ብቻ ሆኖ ሳለ፤ልክ ኢትዮጵያዊነትን እንዳሸነፉ አድርገው ነው የሚደሰኩሩት። ለዚህም ፕሮፓጋንዳ ተባባሪዎቻቸው ደሞ እነ ኦነግና ሌሎች ነፃ አውጪ ግንባር ነን ተብዬዎች ናቸው። የረሱት፤ከኢትዮጵያዊነት ሃሳብ አራማጆች መካከል ተሳስቶ ኢትዮጵያን ወደጥፋት የገፋውን የወታደሮች ስብስብ ደርግን አሸነፉ ማለት፤ ኢትዮጵያዊነትን አሸነፉ ማለት፤ እንዳልሆነ አለመገንዘባቸው ነው።

ይሄንን ከላይ ደርግን ስላሸነፉ ብቻ አማራን እና ኢትዮጵያዊነትን እንዳሸነፉ ያስባሉ ያልኩበት ምክንያት መረዳት ከፈለጋቹ፤ ይሄ አሁን ህገመንግስት ተብዬውን ህገ አራዊት ሲያፀድቁ የተገኙት ነፃ አውጪ ግንባር ተብዬዎች ብቻ እና አማራን ሳይጨምር በሺ የሚቆጠር አባላት ያላቸው ትንንሽ ሌሎች ብሄሮች ተወካዮችን ጨምሮ ሲሆን፤ በዚህ ኢትዮጵያ ላይ “ህገ መንግስት” በሚል ሽፋን የተላለፈው “የሞት ውሳኔ” ስብሰባ ላይ አንድም አማራ እና አንድም በኢትዮጵያዊነት አምናለው የሚል ድርጅት እንዳላሳተፉ ልብ ማለት ነው። አንድ ለእናቱ ፕ/ር አስራት ወልደየስ በዛ የኢትዮጵያ የጥፋት ስብሰባ ላይ ተጋብዘው ነበር። እሳቸው ይሄ ሸፍጥ ገብቷቸው መቃወማቸውን እናውቃለን። ነገር ግን ብዙ አጋር ባለማግኘታቸው ህይወታቸውን አሳጣቸው ነፍስ ይማር ብለናል። ይህ የሚያሳየው ምንም እንኳን ትህነጎች ደርግን ቢሆንም ያሸነፉት፤ አማራ ስላልተደራጀና ስላልተናገረ ብቻ አሸንፈንዋል ቀብረንዋል እንዳይነሳ አድርገን አከርካሪውን ሰብረንዋል በማለት በሃገሪቱ በተደረጉ በማንኛውም ውሳኔዎች ላይ እንዳይገኝ አደረጉት። አማራን ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑትን ድርጅቶችን ጭምር ኢትዮጵያዊነትን አሸንፈናል ስላሉ እንዳይገኙ አደረጉ የነሱ አሽከር በወቅቱ ኢህዴን የሚባለውን ካልጠራቹ በስተቀር። ግን መቼ ነው አማራውን ጦርነት ገጥመው ያሸነፉት? አማራው ኢትዮጵያዊነት በሚለው ስሜት የበለጠ ስለሚያምን (ምናልባት የመንግስት ቓንቓ አማርኛ መሆኑ ጠቅሞታል ካላላቹ በስተቀር አማራ ከኢትዮጵያዊነት ከሌሎች የተለየ ምንም የተጠቀመው ነገር ባይኖርም) አማራነቱን የተለየ ቦታ ሳይሰጥ በአማራነቱ ስላልተደራጀ እና ራሱን ለማዳን ሳይደራጅ በመቅረቱ ሳይዋጉት አሸነፍነው ብለው ትህነጎች ደመደሙ። ይሄ አማራውን አንገቱን ለማስደፋት ሆን ተብሎ የሚደረግ የስነ አእምሮ ጦርነት እንደሆነ እንዳትዘነጉ። ደርግ፤ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ የተውጣጣ ትግሬንም ጭምር የሚያካትት ሆኖ ሳለ፤ እንዲሁም ደርግ ራሱ ዋና አማራን ያጠፋ ሆኖ ሳለ (የትህነግን ያህል የከፋ ባይሆንም)፤ ደርግን ስላሸነፉ ብቻ አማራን አሸነፍነው ማለት፤ ምንም ሚዛን የማይደፋ ሃሳብ ነው። ነገር ግን እንዲህ የሚሉት እውነቱ ጠፍቷቸው ሳይሆን፤ አማራ አሁንም በአማራነት ስላልተደራጀ፤ ሳይነቃ ሆን ተብሎ አማራን አንገቱን ለማስደፋት የሚደረግ ተንኮል ነው።

ደርግን ማሸነፍ በራሱ ብቻ ኢትዮጵያዊነትን ማሸነፍ እንዳልሆነ ትህነጎች መረዳት የሚችሉት በተከታታይ በኢትዮጵያዊነት በሚያምኑ ወገኖች አሁንም ድረስ በሚነሳባቸው አመፆች ነው። ለዚህም ይመስለኛል 1997 ኢትዮጵያዊነት ሞቷል ከዚህ በኃላ ህዝቡ እኛ ባሰመርንለት አፓርታይድ ክልል ብቻ ነው የሚያስበው ብለው የልብ ልብ ተሰምቷቸው ምርጫ ገብተው ኩም ሲደረጉ፤ አሻፈረኝ ብለው ስልጣን አንለቅም ብለው የስንት ደሃ ንፁህ ደም አፍስሰው እስካሁን ስልጣን ላይ ቆዩ። አሁንም ድረስ በኢትዮጵያዊነት የሚያስቡትን እነ እስክንድር ነጋ፤ እነ አንዱአለም አራጌ ወዘተ ላይ ከሌሎቹ የብሄርተኛ ድርጅቶች ተቃዋሚዎች በላይ የከፋ ቅጣት እንዳስተላለፉባቸው አይተናል፤ አማራነታቸው የበለጠ ቅጣታቸውንም መጨመሩ እንዳለ ሆኖ።

የሚያሳዝነው ግን፤ አሁንም ኢትዮጵያዊ ነን ብለው የተደራጁት፤ የአማራን በደል፤ ያውም አማራን ነው የምትወክሉ እየተባሉ እየተብጠለጠሉ ጭምር፤ ገሸሽ ማድረጋቸው ነው። ግን አማራው ራሱን ነው እንጂ ማዳን ያለበት ሌሎች ተደራጅተው እንዲያድኑት ሊጠብቅ አይገባም። እያደረገውም ነው መደራጀቱ ተጀምርዋል፤ይቀጥላል። የበፊቱ ይቅርና አሁን ስላለው እስቲ ላውራ። እስቲ የትኛው በአንድነት ስም የተደራጀ የፖለቲካ ድርጅት ወይንም ሚዲያዎቻቸው ናቸው አማራን ከትግሬ ጋር አብሮ ኦሮሞን እና ሌላውን ኢትዮጵያዊ እየበደለ ነው ብለው ቢቢሲ እና አውሮፓ ህብረት ዜና እና መግለጫ ሲያወጡ፤ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተዉ አማራ ተበዳይ ሆኖ ሳለ፤ የዘር ማጥፋት እየደረሰበት ሳለ ፤መልሳቹ በዳይ አትበሉት ያለው። ቢቢሲም፤ አውሮፓ ህብረትም ትህነግን ማውገዛቸው እሰየው የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን አማራን ያለሃጢያቱ መወንጀላቸው የሚያሳዝንም ፤የሚያስጠይቅም ነው። ሲጀመር በብሄር ፖለቲካ አናምንም የምትሉ ለትህነግ ጥፋት ትግሬ ሁሉ መጠየቅ የለበትም ትላላቹ ብዬ ነበረ እኔም አምናለው ለትህነግ ጥፋት ሁሉም ትግሬ መጠየቅ የለበትም፤ ምንም እንኳን ከጥቂት ትግሬዎች በስተቀር፤ ትህነግን እና ትግሬ አንድ አድርጋቹ አትዩ ሲሉ ባይሰሙም። ይሄ አልበቃ ብሎ ምንም አማራ ስልጣን ላይ ሳይኖር (አሻንጉሊቶቹ ብአዴን ዋና ዋና መሪዎች እንኳን አማራ እንዳልሆኑ እናውቃለን)፤ አማራ ተበዳይ ሆኖ መድረሻ አጥቶ እየተንከራተተ አብሮ ከትግሬ ጋር ሲወነጀል ዝም ያሉ በተይ የአንድነት ሃይል ነን የሚሉ ብዙ አስተዛዝቦናል። እነ ኢሳትም ያቺን አማራን ያለሃጢያቱ ከትህነግ (ትግሬ) ጋር የምትወነጅለውን አረፍተ ነገር ያላነበቡ ይመስል ሌላውን የትህነግን መወገዝ ብቻ አስተጋብተው ዝም ማለታቸውም ውስጣችንን አሳዝንዋል።

የሚያሳዝነው አማራው ባልተገኘበት ውጊያ ተሸንፈሃል ተብሎ፤ በሌለበት የተከለለውን የአፓርታይድ አከላለል፤ በብሄር የተደራጁትም ሆኑ በኢትዮጵያዊነት የተደራጁት ፤ካልተቀበልክ ከአማራ ጋር አንደራደርም ይሉታል፤ አልፎ ተርፎም የድሮ ስርአት ናፋቂ ይሉታል፤ አማራው ከድሮ ስርአት የተጠቀመ ይመስል። እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን ሞት አለ? አማራው ሳትሞት ሞተሃል መባሉ አልበቃ ብሎ እና ሁሉም የአፓርታይዱን ድንበር ለማስመር ድርሻውን ወስዶ የተረፈውን የአማራ ተብሎ የተሰጠው አልበቃ ብሎ፤ ኧረ አለው አልሞትኩም ቢልም፤ የለም ሞተሃል ብለናል ሞተሃል፤ እና በቃ የተሰጠህን የመቃብር ቦታ ብቻ ተቀበል፤ ከመባል በላይ ምን ሞት አለ! ደስ የሚለው አማራው እየነቃ ነው። እንዲህ ሸፍጥ ያቀዱለት ካሁን በኃላ በፈለጉት አይነዱትም። በአማራ ደም የምትሰራ ኢትዮጵያም ይሁን እነሱ የሚያስቡት ትንንሽ ሃገሮች አይኖሩም። ወይ አብረን በሰላም እንኖራለን ወይ ስንጠፋፋ እንኖራለን!

ኢትዮጵያዊነትም  ይኖራል ይለመልማል ነገር ግን ይቺ በአማራ ደም ሁሌ እንደአዲስ የምትሰራውን ኢትዮጵያን  ለመስራት የሚደረገው ጥረት የትም አያደርስም። አማራንም ጨምሮ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የምትሆን አገር እንዲኖረን እንስራ እንጂ ያለ አማራ ወይንም ያለ ኦሮሞ ወይንም ያለ ትግሬ ወይንም ያለ ሌላ ነገድ ኢትዮጵያ በ2 እግሮቿ አትቆምም።

በነገድ ፖለቲካ የሚያምኑትም (ምሳሌ ትህነግ፤ኦነግ/ኦህዴድ፤ኦብነግ ወዘተ)አማራውን ጠላቴ ብለው ሃገር አሳጥተው ለማጥፋት የሚያደርጉትን ከቀጠሉ፤ እንዲሁም በአንድነት ስም ያሉትም አማራውን አብሮ ከሌላው ጋር ተባብረው ለማጥፋት እና አንገቱን ለማስጎንበስ የሚያደርጉትን ጥረት ካላቆሙ አማራው ራሱን ለማዳን ይገደዳል። ይሄ ደሞ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት የሚያመራ እንደሆነ እናምናለን ፤ግን አማራው ብቻውን ከሚያልቅ አብሮ ቢያልቅ ይሻለዋል። አማራው ደሞ ህይወትና ሞት ትርጉም ካጣለት ቆይትዋልና ሌላው ከሰላም ይልቅ በእርስ በእርስ ጦርነት ካመነ ምን እስካፍንጫቸው ቢታጠቁ ማን እንደሚጎዳ እናያለን።

ባልተሳተፍንበት ጦርነት አማራን አሸንፈንዋል አትበሉት ትህነግ እና ወዳጆቹ። አውሎንፋሱ እስኪያልፍ ብሎ አንገቱን እንደሰንበሌጥ ደፋ እንጂ ፤ነፋሱን አሳልፎ እንደገና አንገቱን ቀና ያደርጋል። አማራ አለ አልሞተም፤ አልተቀበረም ፤አከርካሪውም አልተመታም፤ አልተሸነፈም። ትህነግ ሆይ ያሸነፍሽው ደርግን ብቻ ነው ያውም የአማራ ደም ፈሶ ጭምር።

ኢትዮጵያዊነትም አልሞተም ምንም እንኳን በኢትዮጵያዊነት ስም ያሉ ቢያጭበረብሩበትም በአማራ ደም ኢትዮጵያን ሊያቆሙ ቢሞክሩም፤ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እኩል የምታደርግ ኢትዮጵያዊነት አሁንም አልሞተችም አለች።

ፉከራ አይደለም ለውጥ እያየን ነው፤እውነት ነው አማራው ይነሳል፤ አልተሸነፈም፤አልሞተም፤ እንዳላቹት አልተቀበረም!!! ሁሉንም እኩል የምታደርግ ኢትዮጵያም አለች አልሞተችም!!!

የአማራ ልጅ ተደራጅቶ ራሱንም የአባት የእናቶቹን ሃገርም ያድናል!!!

ጥር 2008

ርዕዮት ሆይ! ወኔ ቢሶቹን “እንካ መቀኔቴን – ቀበቶህና ስጠኝ” ብለሽ ገስጭልን! 

alemu

አዜብ ጌታቸው

አቅም በፈቀደ መጠን በየጊዜው በሃገራችን ወቅታዊ ሁነቶችና ክስተቶች ዙሪያ የተሰማኝን ለመግለጽ ስሞክር ቆይቻለሁ።ታዲያ በእያንዳንዱ ጽሁፍ ላይ በርካታ አስተያየቶች ይደርሱኛል።አብዛኞቹ አበረታች፤ ጥቂቶቹም አርበትባች። አርበትባች ስል ማስፈራራት መሞከራቸውን ለመግለጽ ያህል እንጂ ተርበተበትኩ ማለቴ እንዳልሆነ ይጠፋችኋል አልልም። “እንኳን ለሙቅ ለገንፎ አልደነግጥ አሉ…”። መዳፋቸው ውስጥ ሆና ያርበተበታቻቸውን የርዕዮት ዓለሙን ገድልና ጀግንነት እያየሁ ! እየሰማሁ! እኔ ከ4 ኪሎ ቤተ መንግስት (ቤተ መጥምጥ) በስንት ሺህ ማይልስ ርቀት ላይ ሆኜ እንዴት ልርበተበት? ያውም በኤሜል? እ ተ ተ ተ ተ…. !

አደራ! ራሴን ከርዕዮት ጋር ማመሳሰሌ መስሏችሁ ወዴት ጠጋ ጠጋ..? እንዳትሉኝ። በፍጹም! ደግሞስ እንዴት ልንመሳሰል እንችላለን? እኔ በሪሞት የምቧጥጥ እሷ ገዳዮቹን በአካል የምትጋፈጥ፡፡

የዛሬው ጽሁፌ በምን ላይ እንደሚያጠነጥን ፍንጭ ያገኛችሁ ይመስለኛል። አዎ! የዛሬው ትኩረቴ በዚኽቺው ጀግና እንስት ገድል ላይ ነው ።

በርግጥ ርዕዮት እጇ በወያኔ አፋኞች ከተያዘበት ግዜ ጀምሮ ያሳለፈቺውን ስቃይና ታሳይ የነበረውን ጽናት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ላለፉት 4 -5 አመታት ስከታተል በመቆይቴ ለሷ ያለኝ ክብርና አድናቆት የቆየ ነው።ይሁንና በውስጤ የገዘፈውን አድናቆትና ክብር አውጥቼ ለመግለጽ የተነሳሳሁት ግን ሰሞኑን በኢሳት ከሲሳይ አጌና (በርባሪው ጋዜጠኛ) ጋር ያደረገቺውን በሁለት ክፍል የቀረበ ቃለ መጠይቅ ካደመጥኩ በኋላ ነው።

ከሁሉ አስቀድሜ ግን የአተራረክ ብቃቷ እጅግ እጅግ በጣም እንዳስደነቀኝ ሳልገልጽ አላልፍም። ድሮስ መምህርነትና ጋዜጠኝነትን መሰል ሙያ አጣምራ ይዛ… እንደምትሉ እገምታለሁ። ጋዜጠኛ ሲሳይ እስከዛሬ ካነጋገራቸው እንግዶች ሁሉ ስራውን ያቀለለችለት እንግዳ ርዕዮት ነች ብል፤ አጋነንሽ ወይም የጾታ አድሎ ነው እንደማልባል ተስፋ አደርጋለሁ። ወደ ዓብይ ጉዳዪ ልመለስ።

በተለምዶ የጀግና ባህሪ፤ ብዙ የማይፈክር ወይም ብዙ የማይናገር፤ አዘኔታን ወይም ምህረትን ከማንም የማይጠብቅ፤ የተበደልኩ ሮሮ የማያበዛ ነው ይባላል፡፡ አባባሉ እውነት አለው ።ከርዕዮት ቃለ መጠይቅም የተረዳሁት ይህንኑ ነው።

አስተውላችሁ ከሆነ ርዕዮት ባደርገቺው ከሁለት ሰአታት በላይ በዘለቀው ቃለ-መጠይቅ ውስጥ ከአራት አመታት በላይ የቆየችበትን ስቃይ፤ የተፈጸመባትን ግፍና በደል… ቁብ ሳትሰጥ የፍትህ ስርዓቱን ዝቅጠት በሚያሳይ መልኩ ብቻ ነበር የምትተርከው። ጀግና ሮሮ አያበዛም። ጀግና እንባውን በወኔው እንጂ የሚያብስው ፤ በደሉን በገድሉ እንጂ የሚረሳው፤ ማንም በአዘኔታ ከንፈሩን እንዲመጥለት አይሻም።

ጀግና ነጻነቱን ከጠላቱ እጅ ፍልቅቆ እንጂ የሚወስዳት በምህረት አይቀበላትም። ርዕዮትም ነጻነቷን በምህረት ሳይሆን አፍንጫቸውን ሰንጋ ከእጃቸው ፈልቅቃ ወሰደች። ለ24 አመታት የቆየውን የወያኔ እስር ቤት “የሰጥቶ መቀበል” (ይቅርታ ተቀብሎ ምህረት መስጠት) ስልት በጽናት አመከነች።

ጀግና በራሱ እንዲደርስ የማይሻውን በሰው ላይ አይፈጽምም፡፡ ርዕዮትም በንጹሃን ሰዎች ላይ መስክረሽ ነጻ እንልቀቅሽ ስትባል፤ “የለም በንጹሃን ላይ መስክሬ ነጻ ከምወጣ እኔኑ ክሰሱኝ” ብላ ጸናች።

በዋናነት ጀግና ፍርሃት አያውቅም። አዎ! አፋኞቹ የፈጠራ ክሱን ለማዘጋጀት ግንቦት 7 እንበለሽ? ኦነግ እንበልሽ? በሚል ላቀረቡላት የፌዝ ጥያቄ ርዕዮት የሰጠቺው መልስ፤ “የፈለጋችሁትን በሉኝ ብቻ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  አትበሉኝ!” የሚል አፈር ያስገባቸውን መልስ ነበር።

ውድ አንባቢያን እስኪ ንባቡን ለደቂቃ ቆም አድርጉና ይህን አስቡ፡..

ገለው እንኳ ጭካኔያቸው አላረካ ሲላቸው ሬሳውን  በሰደፍ የሚደበድቡ አረመኔዎች እጅ ገብታ በእንዲህ አይነት ድፍረት ምላሽ የሰጠችን ነፍስ በህሊናችሁ አስቡና ራሳችሁን በሷ ጫማ ከታችሁ ተመልከቱ! ታደርጉታላችሁ? አዎ! ርዕዮትን ልዩ ጀግና የሚያደርጋት ይኽው ነው። ልዩ የጭካኔ አቅም ያላቸውን ጠላቶቿን መጋፈጧ። ብሎም ማንበርከኳ!

እዚህ ላይ አንድ ሌላ ነገር ታወሰኝ፦

በ1997 ምርጫ ማግስት ማለትም በግንቦት 7 ምስረታ ዋዜማ፤ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አንድ አወያይ ጽሁፍ አቅርበው ነበር፡፡ ጽሁፉ ያለፈውን የሰላማዊ ትግል ሂደትና ውጤት የገመገመና መጪው የትግል አቅጣጫ ምን መሆን እንዳለበት ያመላከተ እንደነበር አስታውሳለሁ። የአቶ አንዳርጋቸው ጽሁፍ ወያኔ ሰላማዊ  የሚባል ነገር የማይገባው መሆኑን አሳይተው፤ በቀጣይ አመጽንም የሚያካትት ሁለገብ የትግል ስልትን መከተል እንደሚገባ አስረግጠው ያስገነዘቡበት ነበር።

በዚያ ወቅት ታዲያ “ሰላማዊ ትግሉ መቼ ተነካና ?” የሚሉ ወገኖች የአቶ አንዳርጋቸውን ሃሳብ በጽኑ ተቃወሙ። መች ተነካና ያሉትን የሰላማዊ ትግል አይነት እየዘረዘሩ አቀረቡ፤ ጋንዲንም ማርቲን ሉተር ኪንግንም ከመቃብር ቤት ለምስክርነት ጠሩ። ዳግም ወደ ጦርነት አንገባም ፤ በሰላማዊ ትግል ቆርበናል ያሉ ሁሉ አቧራውን አጨሱት።

አቶ አንዳርጋቸው “ሰላማዊ ትግሉ መቼ ተነካና ?” በሚል የተነሳባቸውን ተቃውሞ አስመልክቶ በዛው ሰሞን ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሰጡት ምላሽ ታዲያ መቼም የምረሳው አይደለም፡፤

አቶ አንዳርጋቸው የሰጡት መልስ፦  የጋንዲንና የማርቲን ሉተር ኪንግን የትግል ተመክሮ እየጠቀሱ ሰላማዊው ትግል መቼ ተነካና የሚሉ ወገኖች አንድ የሳቱት ነገር አለ። የጋንዲም ሆነ የማርቲን ጠላቶች የሰለጠኑ ጠላቶች ነበሩ፡፤ ጋንዲ የረሃብ አድማ ሲያደርግ እንዳይሞትባቸው የሚጨነቁ፤ ከውሃ ጋር ፈሳሽ ምግብ(ግሉኮስ) ደብቀው እየሰጡ ህይወቱን ለማትረፍ ይሞክሩ የነበሩ ናቸው። የኛ ጠላት ወያኔ ግን የሰለጠነ ጠላት አይደለም። ሁሉንም ጥያቄ በጠመንጃ አፈሙዝ ለመመለስ የቆረጠ፤ ባህሪውም ፍጥረቱም ሰላማዊ መንገድ እንዲከተል የማይፈቅድለት ጠላት ነው። ስለዚህ የኛም ቀጣዩ የትግል ስልት መነደፍ ያለበት ከወያኔ ድርጅታዊ ባህሪና ተፈጥሮ በመነሳት እንጂ ከነጋንዲ ተመክሮና ታሪክ አይደለም፡፡ የሚል መልስ ነበር የሰጡት (ቃል በቃል ሳይሆን ፍሬ ሃሳቡን  በራሴው መንገድ ነው የገለጽኩት) ከአስራ ሃንድ አመት በፊት “ሰላማዊ ትግሉ መች ተነካና ?” በሚል የሰላማዊ ትግል ስልትን ጥራዝ እየገለጡ አቶ አንዳርጋቸውን ሲሞግቱ የነበሩ ወገኖች ዛሬ ላይ ቆመው ሲያስቡት የአቶ አንዳርጋቸው አርቆ አስተዋይነት ሊታያቸው ግድ ይላል።

አሁንም ወደ ተነሳሁበት ልመለስ፦ የአቶ አንዳርጋቸውን ምላሽ እዚህ ላይ መጠቀስ ያስፈለገኝ ፤ የዛሬዋ ተዘካሪ ጀግና የርዕዮት አለሙ ገድል ከወርቅ ጸዳል ፈክቶ እንዲታይ ግድ የሚለው፤ ካልሰለጠኑ ጠላቶች ጋር ታግላ በማሸነፏ መሆኑን ለማሳየት ነው። ጨካኝ ጠላትን ለመታገል ብርቱ ጽናት ያስፈልጋል።ለማሸነፍ ደግሞ ጀግንነት።

አዎ! ወያኔ ፈሪ ነው! ፈሪ ደግሞ ፎካሪና ጨካኝ ነው።

የፈሪ ነገር ሲነሳ ባለ ራዕይው መሪ ፈሪ እንደነበሩ አብሮ አደግ ጓዶቻቸው ያጋለጧቸው ነገር ትዝ አለኝ፡፤ ይቅርታ ነፍሳቸውን ይማርና ማለት ነበረብኝ ለካ? (ዳሩ የላይኛው ጌታ እንደሳቸው የይቅርታ ፎርም አስሞልቶ አይደል ምህረት የሚሰጠው። በስራ ሚዛን እንጂ፡ .. እንደስራቸው! ..ማለቱ ይሻላል ) እናም የባለ ራዕይው መሪ ፍርሃት ወደር አልነበረውም አሉ። ፈሪ ፎካሪ አይደል፤ ሲፎክሩም አቻ የላቸውም። ባጠቃላይ ተፈጥሯቸው፦

የሞተ ባገኝ እሱን አያርገኝ!
የቆመ ሳገኝ ፈሴም አይገኝ! አይነት ነበር አሉ አብሮ አደጎቻቸው።

ፈሪ ባይኖር ኖሮ ጀግና አይኖርም ነበር። ፍርሃት የሚባል ነገር ባይኖር ጀግንነትም ትርጉም ባልኖረው ነበር፡፤ ለዚህ ነው
የርዕዮትን ገድል እያወራሁ ድንገት ወደ ባለ ራዕይው ማንነት የገባሁት።ለንፅፅር ።

ፈሪውን እዚህ ላይ ላውርደውና ወደ ጀግናዋ ልመለስ። ጀግና ሲወደስ ደስ ደስ ይላል። ርዕዮት በእሳት የተፈተነች ወርቅ ነች።

ከሃገር ቤት በብዙ ሺህ ማይልስ ርቆ በውጭው አለም እየኖረ የወያኔን መንግስት ለመቃወም በሚጠራ ሰልፍ ላይ ሰፌድ የሚያህል ባርኔጣና ጥቁር መነጽር ደንቅሮ አዩኝ አላዩኝ እያለ በፍርሃት የሚርደውን ዜጋ ስናስብ የርዕዮት ገድል ገዝፎ ሊታየን ግድ ይላል።

ለኩርማን መሬት ብሎ የወገኑን ስቃይ አይቶ እንዳላየ በሚያልፈው ስግብግብ ኢትዮጵያዊ ተብዬ ተግባር የሚያዝነው  ህዝባችን በርዕዮት መሰል ጀግኖች መስዋእትነት ይጽናናል።

በርዕዮት ጀግንነት የተደመሙ! ወገኖች የዘመናችን ጣይቱ ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸውላታል፡፤ ይገባታል! ጣይቱ ባህር ተሻግሮ የመጣን ፋሽሽት አሳፍራ መለሰች። ርዕዮት ደግሞ ወንዝ አፈራሹን ፋሽሽት ብቻዋን! አንበረከከች።

በነገራችን ላይ በታሪክ ጎልቶ የሚጠቀሰው የእቴጌ ጣይቱ ጀግንነት ይሁን እንጂ በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት ውስጥ ሳጋ እየገቡ የተጠቀሱ ሌሎችም በርካታ ጀግና እናቶች ነበሩ። ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት ተብሎ ጦርነት ሲታወጅ፤ ለሰራዊቱ ስንቅ የማዘጋጀቱ ኃላፊነት መሉ ለሙሉ የእናቶች ነበር።

ደረቅ ስንቅ ከማዘጋጀት ባሻገር አብረው ዘምተው ከተዋጊው ኋላ እንጀራ እየጋገሩ ወጥ እየሰሩ ሰራዊቱን ይመግቡ ነበር። ይህ ብቻም አይደለም። እናቶቻችን በውጊያ ወቅት ፈርቶ የሚያፈገፍግ ወታደር ሲመለከቱ መቀነታቸውን እየፈቱ “እንካ መቀኔቴን – ዝናርክን ፍታና ለኔ ስጠኝ” በማለት እየገሰጹ ፊቱን ወደ ጠላት አዙሮ በወኔ እንዲዋጋ ያበረታቱ እንደነበርም ተጽፏል፡፡

ንጉስ ክተት ሰራዊት ብሎ ጦርነት ሲያውጅ እያንዳንዱ ለአቅመ አዳም የደረሰ ሰው በራሱ ስንቅና ትጥቅ ለዘመቻ ይዘጋጃል። አልጋ የያዘ በሽተኛ ካልሆነ በስተቀር ከንጉስ ሰራዊት ተነጥሎ የሚቀር ሰው፤ እንደ ሰው አይቆጠርም።ሚስቱም ባል አታደርገውም።ወንዶች የዋሉበት ያልዋለ ባል ለሚስቱ ማፈሪያ ነው። አባትም ከሆነ ለልጆቹ መሰደቢያ ነው።

ተወዳጁ የባህል ዘፈን አቀንቃኝ ባህሩ ቀኜ፡

ገዳይ ገዳይ ያልሽው ባልሽ ሰው አይገድል፤
አርሶ ያብላሽ እንጂ ሆድሽ እንዳይጎድል፤

ሲል በዜማ የቋጠራቸው ስንኞች ይህኑ የሚያሳዩ ናቸው። ህይወትን ከፍሎ ሃገርን ማቆየት የሰውነት መገለጫ ነበር ።  ዛሬ ደግሞ በተቃራኒው አገርን አሳልፎ ሰጥቶ(ችላ ብሎ) ህይወትን ማቆየት ተለመደ፡፡ የርዕዮት ጀግንነትም በበርሃ ውስጥ እንደ በቀለች ጽጌሬዳ ብርቅ የሚሆነውም ለዚህ ነው።

ውድ አንባቢያን ጽሁፌን ልቋጭ ነው፦ ከዚያ በፊት ግን ይህቺ መልዕክት ለርዕዮት አድርሼ እመለሳለሁ ታገሱኝ።

ውድ እህቴ ርዕዮት ሆይ! ከሁሉ አስቀድሜ ለአራት አመታት የተሸከምሺውን የመከራ ቀንበር ሰባብረሽ፤ እንኳን ከነክብርሽ ለነጻነት በቃሽ እላለሁ።

ውድ እህቴ ርዕዮት! በታሪክ ሲዘከር የሚኖር ጀግንነት ፈጽመሻል፡፡ የአርአያነትሽ ፋይዳም ግዙፍ ነው።

ጽናትሽ አንቺ ያሳለፍሺውን ስቃይ እያሳለፉ ላሉት የህሊና ዕስረኞች የመንፈስ ብርታት ነው።
ቁርጠኝነትሽ  ለህዝብ ነጻነት ለሚታገለው ወገን ጉልበት ነው።
መስዋዕትነትሽ  ለሆዳቸው አድረው ለሚልከሰከሱ ባንዶች የህሊና ቁስል ነው።
እንስትነትሽ በጓዳቸው ከትመው ሃገራቸውን ለረሱ እህቶቻችን ማነቃቂያ ደውል ነው።
ድልሽ የነጻነት ቀን መቅረቡን አመላካች ተስፋ ነው፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአራት አመታት ስቃይ በኋላም እረፍት ስታፈልጊ ብረት አንስተው ዘረኛውን መንግስት ለመጣል የተሰለፉ ወገኖችን መቀላቀልሽ በራሱ፤ በፍርሃትም ሆነ በለዘብተኝነት እጁን አጣጥፎ የተቀመጠውን ወገን “እንካ መቀኔቴን – ዝናርክን ፍታና ለኔ ስጠኝ” ብለሽ የገሰጽሽበት ድንቅ ተግባር ነውና ልትኮሪ ይገባሻል። ወኔ ቢሶቹ ለዝናር ባይታደሉም ቀበቶ አያጡምና “እንካ መቀኔቴን – ቀበቶህና ስጠኝ” ብለሽ ገስጭልን። ፈሪን መገሰጽ በጀግና ያምራል። ፈተናሽን በጽናት እንድትወጪ የደገፉሽ ወላጆችሽና ቤተሰቦችሽ በሙሉ ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል።

ውድ አንባቢያን በጣም ይቅርታ! አቆየኋችሁ፡ የርዕዮት ገድል ብዙ ቦታ ውስጥ ከተተኝና ጽሁፌ ረዘመ። በትዕግስት አንብባችሁ እዚህች ድረስ ከደረሳችሁ፡፤ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው፡፤ እንዲሁ ደግሞ ጊዜ በሚያፈራው ሌላ ጉዳይ የሚሰማኝን ጣጥፌ እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑልኝ።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

azebgeta@gmail.com

መተባበር በተግባር – ይገረም አለሙ

 

unity

በሀገር ውስጥም በውጪም ቁጥራው እጅግ የበዛ ተግባራቸው ግን ብዙም የማይታይ ፓርቲዎች አሉ፡፡ እነዚህ  የሚችሉት ተዋህደው አንድ በመሆን የማይችሉት ተባብረው ትብብርም ይሁን ግንባር በመፍጠር የነጻነት ቀናችንን ለማፋጠን የሚያስችል ትግል ያደርጉ ዘንድ ስንመኝ፣ስንጠይቅ፣ስንማጸን፣ይህን ባለማድረጋቸውም ስንኮንን ወዘተ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ እነርሱ ግን መተባበሩ ቀርቶ መከባበሩ አልሆን ብሎአቸው፣ ተደጋግፎ መቆሙ ቢቀር አንዱ ለአንዱ እንቅፋት ከመሆን መቆጠብ ተስኖአቸው ወያኔ ያሻውን እንዳሻውና ባሰኘው መንገድና ግዜ እየፈጸመ  ከዚህ እንዲደርስ አድርገውታል፡፡

 

ከፖለቲከኞቹ ትግል ይልቅ የተጠራቀመ ብሶት የቀሰቀሰው የህዝብ ቁጣ ወያኔን አንበርክኮት የአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ያለውን ካልፈለጋችሁት ትቸዋለሁ፣ ካልወደዳችሁት አይተገበርም እስከማለት አድርሶታል፡፡ ፖለቲከኞቻችን ግን ከዚህም በቅጡ የተማሩም የተመከሩም አይመስልም፡፡ ለወራት የዘለቀው የህዝብ ተቃውሞ የታቀደ የተቀናጀና በአግባቡ የተመራ ቢሆን ምን ሊሆን ይችል ነበር;

 

ይህ አያሌ ኢትዮጵያውያን የሞቱበት፤ የታሰሩበት፤ ቁም ስቀል ያዩበትና በትንሹም ቢሆን ፍሬ ያሳየ ትግል የተቃውሞ ጎራው ፖለቲከኞችም ከየመሸጉበት ብቅ ብቅ እንዲሉ አስችሏል፡፡ ነገር ግን ሁሌም እንዲህ አይነት ክስተት ሲፈጠር የሚያሰሙትን  መተባበር አስፈላጊ ነው የሚል መግለጫቸውን ካሰሙን በኋላ ሕዝቡ በትግሉ ቀጥሎ እየሞተ እየታሰረ እነርሱ የሚታይ የሚሰማ ጉልህ እንቅስቃሴ አለማድረጋቸው መግለጫ ያወጡት በእምነት ወይንስ አለን ለማለት የሚል ጥርጣሬ የሚያጭር ሆኗል፡፡

 

ይህን ስል ከመግለጫዎቹ ማግስት ሰላማዊ ሰልፍ  ለመጥራት የተባበሩትን፣ ወያኔ ለሱዳን መሬት ለመስጠት የያዘውን ሽር ጉድ በመቃወም ትብብር ያሳዩትን በመዘንጋት ሳይሆን ፖለቲከኞቹ እንታገልለታልን ከሚሉት ዓላማ፤ ሕዝቡ እየከፈለ ካለው መስዋዕትነትና ወያኔ የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም ከሚሰራው አንጻር ከቁጥር የሚገባ ባለመሆኑ ነው፡፡

 

የወቅቱን የህዝብ አንቅስቃሴ ምክንያት አድርገው ለወያኔ አገዛዝ መርዘም ዋናው ምክንያት  የተቀዋሚዎች አለመተባበር መሆኑን የተናገሩት ፖለቲከኞች ይህን ባሉ ማግስት ያለፈው ሁሉ አስቆጭቶአቸው ቃላቸውን ወደ ተግባር የማሸጋገር የምር ስራ መጀመር ነበረባቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ሳይታይባቸው ወራቶች እየነጎዱ ነው፤ መተባበር የሚለው ጩኸትና መግለጫም እንደተለመደው የአንድ ሰሞን እየመሰለ ነው፡፡

የነገሩን የሚያምኑበትን ቢሆን፣ የተሰለፉበትን ትግል ከምር የያዙት ቢሆን፣የወያኔ አድራጎት ከምር አስቆጥቶአቸው ቢሆን፤ የእነርሱ የአመታት ድል አልባ ትግል  ከልብ አስቆጭቶአቸው ቢሆን..ወዘተ  መግለጫ ባወጡ ማግስት ተጠራርተው መተባበር አቅቶን የወያኔን እድሜ የምናራዝመው ስለምን ነው ብለው በሽታቸውን ለማወቅና መድሀኒት ለመፈለግ ተጣጥረው አንድ ነገር ባሳዩን ባሰሙን ነበር፡፡ድምጻቸውን አጥፍተው እየሰሩ ከሆነና  ውጤት ላይ ሲደርሱ ሊነግሩን አስበው ከሆነ ደግሞ እሰየው የሚያሰኝ ነው፡፡

 

የፓርቲዎች ትብብር የተወሰኑ ሰዎች ተገናኝተው ኮሚቴ ወይንም ግብረ ሀይል አቋቁመው በሚያዘጋጁት ሰነድ ላይ ተመስርቶ የሚፈጠር ሳይሆን በሚተባበሩት ወገኖች እምነትና ግልጽ ውይይት የሚመሰረት መሆን አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ የሀያ ዓመት ተሞክሮአችን በበቂ ያሳየን ይመስለኛል፣ አልተማርነብትም እንጂ፡፡ ስለሆነም ቀዳሚው ተግባር የአገዛዝ ዘመናችንን ያራዘመንው እኛው ነን ባለመተባበራችን  ብለው የሚያምኑ፣ከእንግዲህ በዚህ መልኩ የኢትጵያውያን የግዞት ዘመን መርዘም የለበትም ብለው የወሰኑ፤ ያለፈውን መርምረው የአሁኑን አጢነው መጪውንም ተንብየው በጋራ ለአስተማማኝና ዘላቂ  ድል የሚያታግላቸው መርሀ ግብር ለመንደፍ የሚያበቃቸው ውይይት መጀመር ይኖርባቸዋል፡፡

 

ወይይቱ የሚፈለገው ውጤት ላይ እንዲደርስ መሰራት ያለባቸው ቀዳሚ ተግባራት፡፡

 

ፓርቲዎቹ የትግል ስልታቸው ምንም ይሁን ምን አደረጃጀታቸው ሁለት አይነት ነው፡፡ ብሔራዊና ሕብረ ብሔራዊ ወይም ክልላዊና ሀገራዊ ፡፡ ነገር ግን አደረጃጀታቸው ሀገራዊ ሆኖ የዓላማ ልዩነት የሌላቸው ብዙ ድርጅቶች አሉ፡፡ በተመሳሳይ አደረጃጀታቸው ክልላዊ ሆኖ እንወክለዋለን ከሚሉት ብሄረሰብ በስተቀር የዓላማ ልዩነት የሌላቸው በርካታ ድርጅቶችም አሉ፡፡ ከዚህም አልፎ  በአንድ ብሄረስብ ስም የሚጠሩ ድርጅቶች አሉ፡፡እነዚህ የስማቸውም መመሳሰል እያስቸገረ በእገሌ የሚመራው ይሄኛው፤ በእገሌ የሚመራው የኛው እየተባሉ ሲጠሩ እየሰማንም ነው፡፡ እንግዲህ የፓርቲዎች ትብብር ሲታሰብ እነዚህ ሁሉ አንድ መድረክ ላይ እንዲገኙ ይፈለጋል፡፡ ኢትዮጵያ የሁሉችንም ናትና፤ ችግሩ የጋራችን ከቸግሩ መውጫ መንገድም የሁሉም የተባበረ ትግል ነውና፡፡

 

ነገር ግን የጋራ ትብብር ለመፍጠር በሚካሄደው ስብሰባ እነዚህ ሁሉ በአሉበት ደረጃ የሚካፈሉ ከሆነ ውጤታማ ሊሆን ስለማይችል አስቀድሞ እያንዳንዱ በየግሉ ቀጥሎም ተመሳሳይ የሆኑት በመገናኘት ሊሰሩት የሚገባ የቤት ስራ መኖር አለበት፡፡ ሁሉም የቤት ስራውን ሰርቶ ለትልቁ የጋራ ዓላማ ራሱን አዘጋጅቶና ከልብ አምኖ  ወደ ዋናው መድረክ ከመጣ በአጭር ግዜ ውጤታማ ስምምነት ላይ መድረስና የተግባር አንቅስቃሴ መጀመር ይቻላል፡፡በመሆኑም፤

 

አንድ፤ ሁሉም ድርጅቶች በየቤታቸው፤ የአንድ ጎልምሳ እድሜ ያስቆጠሩትም ሆኑ የቅርብ ግዜዎቹ ሁሉም በየቤታቸው ግልጽ ውይይት በማድረግ ከተመሰረትን ጀምሮ ምን ሰራን; ለውጤት ያልበቃነው ለምንድን ነው ;እንደ ድርጅት ጠንክረን መውጣት ያልቻልንበት ምክንያት ምንድን ነው;ከሌሎች ጋር ለመዋሀድም ሆነ በትብብር ለመስራት የሚያግድን ምንድን ነው;ከዚህ በኋላ እንዴት ነው መቀጠል ያለብን;ወዘተ ለሚሉ ጥያቄዎች ግልጽና እውነተኛ መልስ መፈለግ፡፡

 

ሁለትህብረ ብሄራዊ አደረጃጀት ያላቸው፤እነዚህ በአደረጃጀትም በዓላማም ልዩነት የላቸውም፡፡ልዩነት ካለ የየድርጅቶቹ ሊቀመንበሮች የየግል ፍላጎት ብቻ ነው፡፡የብዙዎቹ ድርጅቶች መኖር ለሊቀመንበሮቹ መጠሪያ ከመሆን ያለፈ ይሄ ነው ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ውጤት አለማስመዝገባቸውን አባላቱም የሚከራከሩበት አይደለም፡፡ ስለሆነም በየቤታቸው ግልጽ ነጻና ድፍረት የተላበሰ ውይይት በማድረግ ምን ሰራን; ምን እየሰራን ነው; ወዴትስ እየሄድን ነው; በማለት ራሳቸውን መመርመር ቀጣይ ጉዞአቸወንም መተለም ፡፡ ከዚህ በኋላ ደግሞ በጋራ መድረክ ተገናኝተው  በአደረጃጃትም በዓላማም ተመሳሳይ ሆነን በስም ብቻ ተለያየትን ድርጅት ለመፍጠር ያበቃን ምክንያት ምንድን ነው; እስካሁንስ ወደ አንድነት እንዳንመጣ ያገደን ምንድን ነው ; ከዚህ በኋላስ ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተው መወያየትና የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ፡፡

 

ሶስት፣ በብሄር የተደራጁ፣ በእነዚህ ድርጅቶች መካከል ያለው ልዩነት እንወክለዋለን የሚሉት ብሄረሰብ መለያየት ብቻ ነው፡፡ በየብሄረሰቡ ስም ተደራጅተው እንወክለዋልን ለሚሉት  ህዝብ እስር ሞትና ስደት ምክንያት ሆኑ እንጂ የሚሉትን ነጻነት ማስገኘት ቀርቶ መብቱን ማስከበር አልቻሉም፡፡ ስለሆነም  በየቤታቸው ግልጽ ውይይት በማድረግ ራሳቸውን መጠየቅ፣ በጋራ መድረክ ደግሞ ዓላማና አደረጃጀታችን አንድ ሆኖ መለያየታችን ለምን;በየግል የያዝነውን ዓላማ አቀናጅተን በአንድ ድርጅት ብንሰባሰብ ሊቀመንበሮቻችን ሥልጣን ያጡ ካልሆነ በስተቀር ጉዳት አለውን;  የምንችል ተዋህደን የማንችል ትብብር ፈጥረን እንዳንታገል ምን ያግደናል፣ ብለው መክረው ያለፈውን የሚያካክስ መጪውን ትግል የሚያጎለብት ስምምነት ላይ መድረስ ፡፡

 

አራትበአንድ ብሄረሰብ ስም የተደራጁ፤  በአንድ ብሄረሰብ ስም  ከአንድ በላይ ድርጅቶችን ሲፈጠሩ፡ ብሄረሰቡን አንድ የማያደርጉ ምክንያቶች ኖረው ሳይሆን የግለሰቦች ሥልጣን ፍለጋ ነው፡፡ ስለሆነም ሀገራዊ ጉዳይ ወደሚመከርበትና እቅድ ወደሚወጣበት ጉባኤ ከመሄዳቸው በፊት ዓላማቸው አደረጃጀታቸውና እንወክለዋን የሚሉት ህዝብ አንድ ሆኖ የተለያየ ፓርቲ የፈጠሩበትን ምክንያት፣ ተለያይተው በመደራጀታቸው ያደረሱትን ጉዳት፤ ልዩነታቸውን የሚያስወግዱበትንና አንድ ሊያደርጋቸው የሚችለውን መንገድ፤ከሌሎች የብሄረስብ ድርጅቶች ጋር ምን አይነት ግንኙነት መፍጠር እንዳለባቸው ፤ ከሀገራዊ ፓርቲዎች ጋር ደግሞ አስከምን ድረስ አብረው መጓዝ እንደሚችሉ ወዘተ መምከርና ከአንድ ስምምነት ላይ መድረስ ፡፡

 

እነዚህ ተግባራት አስቀድመው ከተጠናቀቁ በአብዩ መድረክ ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች ቁጥር አነስተኛ አጀንዳውም ውስን ይሆናል፡፡ ይህም ጉባኤው ውጤታማ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡የጉባኤው ዋና ጉዳይም የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት በማረጋገጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት መመመስረት የሚያስችል አንድ ወጥና የተቀናጀ ትግል የማካሄድ  ስምምነት ላይ መድረስ ይሆናል፡፡ ይህ ሀሳብ ሲያዩት ህልም ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን  የወያኔን የአገዛዝ ዘመን በማሳጠር ዴሞክራሲን በኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ቆርጠው ከልባቸው ለሚታገሉ  የማይቻል ነገር አይደለም፡፡ እንደውም ከልብ ከታሰበበትና ቀናነቱ ካለ በአጭር ግዜ  መሆን የሚችል ነው፡፡

 

ሁሉም ድርጅቶች ተዋህደው አንድ ሊሆኑ አይጠበቅም፣ አይታልምም፡፡ አሁን የምንሰማው የድርጅት ብዛትም አያስፈልግም፡፡    ስለሆነም ከላይ ሁሉም በየቤታቸው፣ ብሎም አንድ አይነት አደረጃጀትና ዓላማ ያላቸው በቡድን፣ በሚሰሩት የቤት ስራ መሰረት መጀመሪያ ተመሳሳዮቹ ውህደት ፈጥረው የድርጅቶቹ ቁጥር በጣም ያንሳል፤ ከዛም ተቀራራቢዎቹ በመቀናጀት ጥምረት ይፈጥራሉ፡፡ በመጨረሻ በአንድነት ተባብሮ በልዩነት ተከባብሮ  ለአስተማማኝ ድል የሚያበቃ ትግል ለማካሄድ የሚያስችል ግንባር ይፈጠራል፡፡

 

ይህ ግንባርም ትግሉን በአሸናፊነት ከመወጣት እስከ ሽግግር መንግስት መመስረት የሚያደርሰውን ሁለንተናዊ  ስትራቴጂ ነድፎ  አንድ ወጥ እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡ የግንባሩ መመሪያ በሁሉም ዘንድ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ግንባሩን የመሰረቱት ጥምር ፓርቲዎቸም ሆኑ የቅንጅቶቹ አባል ፓርቲዎች በየደረጃው የግንባሩን እቅድ ተፈጻሚ ከማድረግ ውጪ ተቃራኒ የሆነ ተግባር ላይ መገኘት አይኖርባቸውም፡፡

 

የግንባሩ አባል ያልሆኑ ድርጅቶች፤  የትብብር ምስራታው ሂደት ለማንም የኩርፊያ ምክንያት እንዳይፈጥር ሁሉንም የሚያሳትፍ መሆን አለበት፡፡ የቤት ስራቸውን መስራት ተስኖአቸው፣ ወይንም ተባብሮ የመስራቱ አላማውም ሆነ ፈቃደኝነቱ የሌላቸው ሆነው፤ ወይንም አብዛኛው ወገን የማይቀበለው ምክንያት አቅርበው ወዘተ የትብብሩ አካል ያልሆኑ ድርጅቶች ከተገኙ እኛም በመንገዳችን እናንተም በመንገዳችሁ  ብለው ቢችሉ ለትብብሩ/ግንባሩ ድጋፍ መስጠት ይህ ካልሆነላቸውም ከአደናቃፊ ተግባር መቆጠብ፡፡

 

የየድርጅቶቹ አባልና ደጋፊ፤ የወያኔ አባላት ድርጅታቸው የሚፈጽማቸውን ኢሰብአዊ ድርጊቶች ሳይቀር አይተው እንዳላዩ ሰምተው አንዳልሰሙ ሆነው በመደገፋቸው ጭፍን ደጋፊዎች እያልን የምናወግዝ እኛስ ብለን ራሳችንን እንጠይቅ፡፡ አባል ወይንም ደጋፊ የሆንባቸው ድርጅቶች አንዳች እንቅስቃሴ ሳያሳዩ ፤ በግል የመጠናከርም ሆነ ከሌሎች ጋር ተባብሮ የመስራት ሙከራም ሳያደርጉ  የግለሰቦች መጠሪያ ብቻ ሆነው አመታት ሲያስቆጥሩ ለምን ብለን ሳንጠይቅ መደገፋችን፣  በተግባር እንያችሁ አለማለታችን  ይባስ ብሎም ለምንደግፈው ድርጅት ጥብቅና ቆመን ሌሎችን ማውገዝ ማጥላላታችን ጭፍን ደጋፊ አያሰኝም;

 

እናም ከዚህ እንውጣ፣ ከድርጅቶቹ ጋር ያስተሳሰረንን ሰንሰለት እንመርምር፣ግንኙነታችን የዓላማ ይሁን፤  ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የማየት አለያም ለልጆቻን የማቆየት ዓላማ፡፡ እናም አባልም ሆነ ደጋፊ የሆንባቸው ድርጅቶች ለዚህ ዓላማችን  እውን መሆን በጽናት የሚታገሉ እንዲሆኑ እናግዝ፣ እናበረታታ፤ ሳይሆን ሲቀር እንጠይቅ፣ መልስ ስናጣ ደግሞ እንቃወም፤ድጋፋችንንም አባልነታችንንም እንሰርዝ፡፡ ከእንግዲህ በተግባር ስለሚታይ እንጂ በቃል ስለሚነገር ትግል ድጋፍ አንስጥ፡፡

 

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ አገዛዝ የሚገላገልበት አለያም አገዛዙ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ወይንም ሕዝብ አሁን እንደምናየው ብሶቱ ብሶ በፖለቲከኞቹም ተስፋ ቆርጦ በራሱ መንገድ ትግሉን የሚቀጥልበት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ ይህ የሚወሰነው ደግሞ በተቀዋሚው ተባብሮና ተጠናክሮ መታገል መቻል አለመቻል ነው፡፡ ስለሆነም ነው የድርጅቶች መተባበር ግዜ የማይሰጠው አጣዳፊ ወቅታዊ ጉዳይ የሆነው፡፡ ስለዚህ የየድርጅቶቹ አባላትና ደጋፊዎች ከጭፍን ደጋፊነት በመላቀቅ ሁሉም ድርጅቶች  የየራሳቸውን የቤት ስራ በመስራት  በአስቸኳይ ወደ ውህደት ወደ ጥምረትና ግንባር እንዲያመሩ ግፊት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከእንግዲህ ከፓርቲዎቹ የምንጠብቀው ስለትብብር እንዲያወሩን፣ ወያኔ የሚገዛው በርሱ ጥንካሬ ሳይሆን በእኛ ያለመተባበር ድክመት ነው እያሉ እንዲደሰኩሩልን ሳይሆን መተባበርን በተግባር እንዲያሳዩን መሆን አለበት፡፡ ለዚህም ፈጣሪ  ለሁላችንም ልብ ይስጠን፡፡

ሠርገኛ መጣ … (ዝናዬ ታደሰ)

ከቅርብ ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ነውጥ፤ ዕድሜው በመርዘሙ፣ በርከት ያሉ ከተማዎች ውስጥ በመካሄዱና እና አመጹም በይዘትና በመልክ ከቀደሙት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች የተለየ በመሆኑ ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ጆሮዎቻችንን አቅንተን እንድንከታተለው ተገደናል።

ስለሁኔታው እስካሁን እንደተወራው ከሆነ፣ በተለያዩ የሐገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በአሁኑ ወቅት የሚታየው አለመረጋጋት የአንድ አገር አቀፍ አመጽ አካል አይደለም። ከሁሉም የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መካከል ደግሞ በተለይ “የኦሮሞዎች አመጽ” የተባለው አገር ውስጥ እንዲሁም ውጭ በሚገኙ የዜና አውታሮች (የወያኔዎቹም ጭምር) እና በፖለቲካ ድርጅቶች ልሳኖች ገኖ ይነገርለታል።

ለኦሮሞዎች አመጽ ምክንያት ሆኗል የሚባለው የአዲስ አበባ ክልል እንዲሰፋ የግድ ከኦሮሚያ ክልል ግዛት ተቆርሶ ስለሚወሰድ፣ ያ ደግሞ የአዲስ አበባ ክልል ዙሪያ ነዋሪዎች የሆኑ ኦሮሞዎች ገበሬዎችን ስለሚያፈናቅል ነገሩ ኦሮሞ የሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ማስቆጣቱ ነበር።

እንግዲህ ይህ በመሰረቱ የኦሮሚያ የግዛት ጥያቄ መሆኑና ከተማሪዎቹ በተጨማሪ ሌሎች ኦሮሞዎችም በአመጹ መሳተፋቸው አመጹን የኦሮሞዎች ነው ለመባል ያበቃው ይመስላል። ወያኔዎቹ ተቃውሞው ስላየለባቸው የአዲስ አበባን ክልል ለማስፋት ያወጡትን ዕቅድ እንደሳቡት ተነግሯል። እግረመንገዳቸውንም በርከት ያሉ ሰዎችን እንደገደሉ በተለያዩ የዜና ማዕከሎች ተዘክሯል።

ሆኖም፣ እንደሚሰማው ከሆነ የኦሮሚያ የግዛት ጥያቄ ከተመለሰም በሁዋላ አመጹ አለማባራቱ ለተመልካች ትንሽ ያደናግራል። ኦሮሞዎች ያልሆኑ ሁሉ በአመጹ እንዲካፈሉ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በኦሮሞዎች ስም ጥሪዎች ቀርበዋል። ግን የቀጠለው የኦሮሞዎች አመጽ በምን ጉዳይ እንደሆነ በጣም ግልጽ አይደለም ፣ በተጨማሪም እስከ አሁን በሚካሄደው አመጽ ሟቾቹም ሆኑ በአጠቃላይ አማጺዎቹ ሁሉም ኦሮሞዎች እንደሆኑም የቀረበ ማስረጃ እስካሁን የለም።

ሌላው የ “ኦሮሞዎች አመጽ” እንድምታ ደግሞ አባባሉ አመጹን በኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅት የሚመራ ማስመሰሉ ነው። የአንዳንድ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች መታሰር ደግሞ ይሀንኑ ግምት የበለጠ ያጠናክራል። ግን አመጹ የፖለቲካ አመራር የሚሠጠው ከሆነ አመራሩ ስልታዊነት ይጎድለዋል።

የኦሮሞዎች አመጽ ወያኔዎችን አስገድዶ እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ በግልጽ ላልተነገሩ ተጨማሪ የኦሮሞ ጥያቄዎች መልስ ለማሰጠት ከሆነ የቀረው በዙሪያቸው የሚኖረው ሕዝብ ሳይደግፋቸው ኦሮሞዎች ብቻቸውን ዓላማቸውን ማሳካት አይችሉም። ወያኔ ነጥሎ ይመታቸዋል።

ትብብር ለማግኘት ደግሞ ለአመጹ አመራር የሚሰጥ አካል ካለ የግድ ከመነሻው የኦሮሞዎችን አመጽ የረጅም ጊዜ ግብ (እውነትም ይሁን ሃሰት) ማሳወቅ ይኖርበታል። የኦሮሞ ሕዝብ ከዳር እስከዳር እስረኞችን ለማስፈታት መነቃነቁ መልካም ሳለ፣ ለሕዝባዊ አመጽ ይህ የአጭር ጊዜ ግብ ነው የሚሆነው።

በአሁኑ ድብብቆሽ ኦሮሞዎች ያልሆኑ ሰዎች “የኦሮሞዎች ፍላጎት ምንጊዜም እንደ ኤርትራ መገንጠል ነውና እኛን ምን አግብቶን ለኦሮሚያ ነፃነት እንሞታለን? ለኦሮሚያ ነፃነት ኦሮሞዎች ይሙቱ ” ብለው የሚሆነውን ሁሉ ከዳር ሆነው ቢያዩ አያስገርምም።

እንደሚታወቀው የኦሮሞ ነፃነት ትግል ፀረ አማራ እና ፀረ ኢትዮጵያ ነው። ግን የኦሮሞ ድርጅቶች ፀረ አማራ እና ፀረ ኢትዮጵያ ሆነው ወያኔን ለማሸነፍ የግድ ማግኘት የሚያስፈልጋቸውን የኢትዮጵያውያንን ድጋፍ ማግኘት አይችሉም።

ቀድሞ ኢሕአፓ እና ተሐህት ለኤርትራ ነፃነት እንዳገለገሉት፣ (ለምሳሌ) ግንቦት ሰባት እና የኦጋዴኑ ነፃነት ድርጅት ለኦሮሚያ ነፃነት ያገለግሉናል ብለው የኦሮሞ ድርጅቶች ቢያስቡ እንኳን ሁለቱም ድርጅቶች ከኤርትርያ ውጭ ሕይወት የላቸውምና፣ የኢሳያስ አፈወርቂ በዕድሜ መግፋት ብቻውን ለዘለቄታው በኤርትርያ መንግስት ትብብር ላይ ብዙ መተማመን እንደማይችሉ ሊጠቁማቸው ይገባል።

ከዚህ በተጨማሪ ግንቦት ሰባቶች ከኦነግ ጋራ በፍቅር የመተባበር ስሜታቸው ልባዊ እንደሆነ ጊዜ የመሰከረለት ነገር ቢሆንም፣ ለኦሮሚያ ነፃነት ሲሉ ደማቸውን እንዲያፈሱ፣ አጥንታቸውንም እንዲከሰክሱ ኢትዮጵያውያንን አስተባብረው ለእርድ ማቅረብ መቻላቸው እጅግ ያጠራጥራል።

ደግሞም የኤርትራ ነፃነት በላብ አደሩ ዓለም አቀፋዊነት እና በብሔሮች ጭቆና እና በብሔር ነፃነት ሽፍንፍን፣ የኤርትራ ነፃነት የሌሎችም ነፃነት እንደሚሆን ተብሎ ለመሃል አገሩ ሰው በመቅረቡ ምክንያት ነገሩ ብዙዎችን ለማወናበድ በቅቷል። ግንቦት ሰባት ግን እንዲህ ያለ ጥልቅ ርዕዮተዓለማዊ ሽፋን የለውም።

በሌላ በኩል ሕወሀት እና እልፍ አዕላፍ የትግሬ ተጋዳዮች በኤርትራ በረሃዎች ለኤርትራ ነፃነት መስዋዕት ቢሆኑ የ”አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል” ጉዳይ ሁኖባቸው ነበር። የኦጋዴን ሶማሊዎች ለራሳቸው ነፃነት ጦርነት ተዋግተው፣ ለኦሮሚያም ነፃነት ተዋግተው፣ አቅማቸው ፈቅዶ ቢችሉትም እንኳን ከኦሮሞዎች ጋራ ላላቸው ቅርብ ታሪካዊ እና ባሕላዊ ትስስር ሲሉ የሚያደርጉት ነገር አይሆንም። ለትግል አጋርነት የሚያበቃ ታሪክ እና ባህል አይጋሩምና ነው።

ኦነግ እና የኦጋዴኑ ድርጅት አማራን እና ኢትዮጵያን (ምናልባት አሁን ትግሬዎችንም ይጨምር ይሆናል) አንድ ላይ ጨፍልቀው አንድ ትልቅ የጋራ ጠላት ስለጠፈጠፉ ጊዜያዊ የዓላማ አንድነት አላቸው። ኦነግ ጦር ስለሌለው እና የኦጋዴኑ ድርጅት አለው ስለሚባል ደግሞ የኦሮሚያ ነፃነት ቢሳካ በኦጋዴኖቹ ትከሻ ነው የሚሆነው። ዳሩ ግን ነገሩን እንደኦጋዴኖቹ ድርጅት ሆኖ ለተመለከተው፣ ሶማሊዎቹ ለኦሮሚያ ነፃነት መዋጋታቸው የኦጋዴኑን ድርጅት ኃይል ስልሚከፍል፣ እንዲሁም የኦሮሚያ ነፃነት ለኦጋዴን ነፃነት ቅድመ ሁኔታ ባለመሆኑ፣ ኦነግ ቢመኘውም የኦሮሞዎች አፍንጫ ሲመታ የሶማሊዎች ዓይን ማልቀሱ ያጠራጥራል።

ይሄ ሁሉ እንግዲህ ወያኔዎች በኦሮሞ ድርጅቶች ወይም በሌሎች ጦር ቢሰበቅባቸው የወያኔን የበላይነት ለማስረገጥ ሲሉ የኦሮሞንም ሆነ የሌላ ብሔርተኝነትን ከመውጋት ወደሁዋላ እንደማይሉ በመገመት ነው። የኦሮሞ ብሔርተኛ አክራሪዎች እንዲሁም ሌሎች አማራዎችን ሳር ጎጆ ውስጥ አጉረው ቢያጋዩዋቸው ወያኔዎች ለደስታቸው ወሰን አይኖረውም። ሆኖም የዛኑ ያክል የኦሮሞም ሆነ የሌላ ብሔርተኝነት አይሎ ከእጃቸው እንዲወጣም ወያኔዎች አይፈልጉም።

እነዚህንና ለሎችንም ምልክቶች ላጤነ “የኦሮሞዎች አመጽ” የፖለቲካ አመራር የሚሰጠው አካል አለው ለማለት አያስደፍርም። በብዙ መልኩ አመጹ ቅንብር ማጣቱም የአዲስ አበባ አካባቢ ነዋሪ ኦሮሞዎች አመጽ ለመባል ይበቃ እንደሆነ እንጂ ኦሮሞዎች በያሉበት የኦሮሚያ ክልል ግዛት ወደ አዲስ አበባ ክልል መቀላቀሉን ተቃውመው ከዳር እስከዳር ተንቀሳቀሱ ቢባል ማጋነን ይሆናል።

ግን አመጹ የኦሮሞዎች ብቻ ሆነም አልሆነም፣ የዜና አቅራቢዎቹ እንዲሁም ወያኔዎቹ የኦሮሞዎች ጉዳይ ብቻ ሆኖ እንዲታይ ጽኑ ፍላጎት ያላቸው ይመስላል። ወያኔዎቹ “የኢትዮጵያውያን አመጽ” ባይሆንላቸው ለምን እንደሚወዱ ግልጽ ነው። የዜና አቅራቢዎቹ፣ በተለይም ወያኔዎችን አይወዱም የሚባሉት በስህተት እንኳን አንዳንዴ ኦሮሞዎችን ኢትዮጵያውያን ሊያደርጓቸው አለመፈለጋቸው ግን ይደንቃል።

ለማንኛውም የጊዜውን የኢትዮጵያ ሁኔታ የሚያብላሉ ሰዎች ይህ የተቃውሞ ጎርፍ ማዕበል ሆኖ የወያኔዎችን መንግስት እንዲፈነቅለው፣ እንደሚመስላቸው ይህና ያ መደረግ ይኖርባቸዋል እያሉ ሃሳባቸውን ያካፍላሉ። በተደጋጋሚ የህብረት እንዲሁም የድርጅት ጥሪዎች ይደረጋሉ። ሁለቱም የተለመዱ ግብዣዎች ቢሆኑም አሁን አመጹ ሳይታሰብ ቀደመና ከበፊቱ በተለየ “እንዴት ነውጡን መልክ እናሲዘው?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት እየተሞከረ ይመስላል።

መቸም አመጹ እየተካሄደ እያለ “ቅንብርና አመራር እንድንሰጠው ህብረትን ፈጥረን ድርጅትን እስክንመሰርት ተዳፍኖ ይጠብቅ” ማለት አይቻልም። ተቃውሞው ወይ ይብስበታል ወይም ይከስማል፤ ምን እንደሚሆን ከወዲሁ ማወቅ አስቸጋሪ ነው። ግን ይህ አጋጣሚ ለወደፊት የሚጠቅም ትምህርት ይሰጣል። ይኸውም አመጽን መቀስቀስ፣ መምራትና ከግብ ማድረስ እንደሚቻል፤ ግን ያልቀሰቀሱትን፣ ዓላማውን ያላወቁለትን አመጽ ከዳር ማድረስ እንደማይቻል ነው።

ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ግብዣዎች መካከል ህብረት የስነልቦናዊ ክስተት በመሆኑ “እስኪ ህብረት እንፍጠር” ስለተባለ የሚሆን ነገር አይመስልም። ሆኖም በድል ዙሪያ ሰዎች እንደሚሰባሰቡ ደግሞ በግብር የታየ ነው። እና ህብረትን ለመፍጠር ከተፈለገ ትንሽም ቢሆን ድል ያስፈልጋል። ከዚያ በሁዋላ ድል ሌላ ድልን እየወለደ፣ የበለጠ ህብረትንም ይገነባል።

ድል ከተቀነባበረ ትግል ይገኛል። የተቀነባበረ ትግል ለማድረግ ደግሞ መደራጀትን ይጠይቃል። ከምናውቀው በመነሳት ደግሞ ከአብዮታዊ ታሪካችን የተወረሰው ዓይነት መደራጀት፣ ማደራጀት እና ማንቃት በዙ ተነግሮለታል። ሆኖም ለሁሉም ዓይነት ትግል ደግሞ አንድ የድርጅት መልስ ሊኖር አይችልም። አብዮት ለማስኬድ የሚፈጠር ድርጅት ከምንም ይሻል ይሆናል። ግን አንድ ትልቅ ደካማ ጎን አለው። ይኽውም እንዲህ ነው። በደርግ ዘመን በተቃዋሚነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ድርጅቶች (ጀብሃ ሻእቢያ ወያኔ ኢሃአፓ ኢፒዲኤ ኢዲዩ እና የመሳሰሉት) ሁሉም ከኢትዮጵያ ውጭ የሚደግፉዋቸው መንግስቶች ባይኖሩዋቸው ኖሮ ህልውናቸው ወረቀት ላይ ይቀር ነበረ።

እንደዛም ሆኖ በአንድ ወቅት የታጋዮች ሁሉ ጌታ ሻአቢያ በኢትዮጵያ ሰራዊት እስከ መጨረሻ ጣቢያው እስከናቅፋ ድረስ ተገፍቶ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ደረጃ መድረሱ ይታወሳል። በጊዜው ለጦርነት ጫካ ገብተው የነበሩ ድርጅቶች ጥቃት ቢደርስባቸው ወደ ሱዳን ሸሽተው ማምለጥ ይችሉ ነበረ። መሪዎቻቸው እንደፈለጉት በየአገሩ መንቀሳቀስም ይችሉ ነበረ። ሁሉም ድርጅቶች ጠቃሚ እስከነበሩበት ጊዜ ድረስ ያላቋረጠ የስልጠና፣ የገንዘብ፣ የዲፕሎማሲና የመሳሪያ ድጋፍ አግኝተዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ብዙ ጠላቶች ነበሩት። ከሶቪየቶች እና ከጥቂት ደካማ አገሮች በስተቀረ ሌሎች ያገባናል ይሉ የነበሩ በምዕራቡ ኃያላን ዙሪያ የተሰባሰቡ መንግስታት በአንድ መልክ ወይም በሌላ መልክ ተቃዋሚዎችን አግዘዋል። ለድል አብቅተዋቸው የፖለቲካ ስልጣንንም አከፋፍለዋቸዋል። በመሰረቱ ጸረ ኢትዮጵያ ርብርቦሹ ዓለምአቀፋዊ ነበረ ማለት ይቻላል።

በአንጻሩ ወያኔ ጠላት የለውም። የወያኔ ተቃዋሚዎች ወዳጅ መንግስታት የሉዋቸውም። የኤርትርያ እና የተቃዋሚዎች መጣሁ ቀረሁ ከ”የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ”ነት አያልፍም። ስለዚህ በቀድሞው ስሌት አይነት አገር አቀፍ የሆነ አንድ ማዕከል የሚመራው ከከተማ ወደገጠር የትጥቅ ትግል የሚባለው ነገር አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ አይሰራም።

በተጨማሪም በአብዮት ዘመን ሳይንሳዊ ሶሻሊዝም ለኢትዮጵያውያን ባይተዋር ነገር ስለነበር፣ ስለ አዲሱ ርዕዮት ቀድመው ያወቁ “ነቅተዋል” የተባሉ ሰዎች ተሰባስበው ሌሎችን ሳይንሳዊ ሶሻሊዝም አስተምረውና አግባብተው ከጎናቸው ለማሰለፍ የሚያገለግላቸውን ትግሉ የጠየቀውን ከአመራር ወደ ጀሌ ተጋዳይ፣ ከላይ ወደ ታች የተዋቀረ ዓይነት ድርጅት መፍጠር ነበረባቸው።

የወቅቱ ትግል ግን ሌሎች ነቅተው እስኪደራጁ የሚያስጠብቃቸው ሳይሆን ቀድመው “ነቅተዋል” የሚባሉት ሰዎች እራሳቸው የሚታገሉት ዓይነት ትግል ነው። ለሕዝብ የሚያስተዋውቁት አዲስ ርዕዮተ ዓለምም የላቸውም፤ ኢትዮጵያዊነት “ዴሞክራሲያዊ ካልሆነ አትውደዱት” ተብሎ ከተማሪው እንቅስቃሴ ዘመን ጀምሮ አለማቋረጥ ቢራከስም፣ አሁንም ቢሆን አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ነገድና ኃይማኖት ሳይለይ የሚያስተባብር ጥልቅ ስሜት ነው።

ይልቅ ወያኔን ከኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ ለማውረድ ወቅቱ የሚጠይቀው ትግል እና አደረጃጀቱ የሚከተለውን ሊመስል ይችላል።

ወያኔ ከሌሎች መንግስቶች የተለየ አይደለም። ህዝብን የሚቆጣጠርበት የጠላቶቹንም እንቅስቃሴ የሚሰልልበት የኢኮኖሚና የወታደራዊ አውታሮቹን ከጥቃት የሚከላከልበት ዋና መሳሪያው የጸጥታ መዋቅሩ ነው። የስለላው መረብ በሰፊው ከዳር ወደ መካከል በረጅም ሰንሰለቶች የተገነባ ሲሆን የቀለበቶቹ ብዛት ለወያኔ ጥንካሬ የሆነውን ያክል ከሌላው ተፈጥሮው በበለጠ ለአደጋ የሚያጋልጠውም ችግሩ ይኽው ነው። ይህ ማለት ከብዙ ትናንሽ ነገሮች የተገነባ አካል ብዙ የሚሰናከሉ ክፍሎች ይኖሩታል።

በበለጠ ለማብራራት፣ ወያኔ ለአምስት ኢትዮጵያውያን አንድ ሰላይ አለው ይባላል። ከዛ ሌላ የየአካባቢውን ነዋሪ በዛው በአገሬው ሰው ነው የሚያሰልለው። ይህ ሁሉ ሁለት ስለት ያለው ቢላዋ እንደሆነ ግልጽ ነው። ወያኔ ሰላዮቹን እንደሌላው መንግስት ሁሉ በገንዘብ ቀጥሮ ነው የሚያሰራቸው። እነዚህ ሰላዮች በጣም ብዙዎቹ ደሞዛቸው ሃብታም አያደርጋቸውም። በጎረቤቶቻቸው ላይ እያሴሩ ለአለቆቻቸው የረባውንም ያልረባውንም ወሬ እያቀበሉ የሚኖሩ ቅጥረኞች ናቸው። ቅጥረኞች ደግሞ አይነተኛ ባህሪያቸው ከተከፈላቸው ምንም የማያደርጉት ነገር አለመኖሩ ነው።

በአጭሩ ወያኔ የገዛውን ቅጥረኛ የወያኔ ተቃዋሚ የሆነም ሊገዛው ይችላል። የገንዘቡ መጠን የግልጋሎቱንም መጠን እንዲሁም ጥራት ይወስናል። ዋናው ነጥብ ግን ቅጥረኛ ተአማኒነቱ ለገንዘብ መሆኑ ነው። በዚህ መልክ የወያኔን የፀጥታ መዋቅር ማደናገር፣ ከውስጥ መቦርቦርና ከጊዜ ብዛት መናድ ይቻላል።

ይህ ታላቅ ግኝት አይደለም፤ ስልቱ የኖረና የተፈተነ ነው። የምዕራቡ ኃያላን በየቦታው በሰፊው እየተገለገሉበት ይገኛሉ። በደርግ ዘመን በኢትዮጵያ ላይም ተጠቅመውበት ትንሽ ጊዜ ቢወስድባቸውም መንግስት አፍርሰውበታል። በንጉሱ ዘመንም ሆነ በሁዋላ የኤርትራ ወንበዴዎች እንዲሁም ሌሎች መሰል ቡድኖች በተንኮል በመንግስት ላይ ብዙ ጥፋት አድርሰዋል።

እና ሁሉም የሚያውቁት የነበረው ታላቁ የአደባባይ ምስጢር በየትም ይገኝ፣ መንግስት የሚባለው ሰው ሰራሽ ተቋም በእውነትም በተፈጥሮው የእምቧይ ካብ መሆኑን ነው። ይህ ማለት የመንግስት ሕልውና ከቀን ወደቀን የተጠበቀ የሚሆነውና እና ቀጣይነትም የሚያገኘው በርከት ያሉ መንግስታዊ ክንዋኔዎች ሁሉም በአንድ ጊዜ ያለመሰናክል ሲካሄዱ ነው።

ይህ ማለት ደግሞ ለምሳሌ ገቢ የሚያፈልቁ የንግድና የመሳሰሉ ተቋማት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጠላትን ክንድ እንዳያደነድኑ መንግስት የማያቋርጥ ክትትል ማድረግ ይኖርበታል። ይህ ብቻውን ቀላል ሃላፊነት አይደለም። በሌላ ጎን ደግሞ የየትኛውም መንግስት የጀርባ አጥንት የሚሆነው ወታደራዊ ተቀጥላው አለጥያቄ ትእዛዝ መቀበሉ ብቻ ሳይሆን ትእዛዙን ማስፈጸሙ በበኩሉ የምግብ፣ የማመላለሻ አገልግሎት፣ የነዳጅ፣ የመሳሪያ እና የመሳሰሉትን አቅርቦት ላይ የሚመረኮዝ እንደመሆኑ መንግስት ለመንጠላጠያ በጣም በርካታ ሲባጎዎችን መቀጣጠል ይኖርበታል።

ይሄ ሁሉ ሳያንስ በተለይ እንደወያኔ ላለ 80 ሚሊዮን ሕዝብ ጠላት አድርጎ ለሚኖር መንግስት ከሚሊዮኖች ሰላዮቹ የሚሰበስበው መረጃ አስተማማኝ መሆኑን ማረጋገጥ መቻል ደግሞ እጅግ አድካሚ፣ እፎይታ የማይሰጥ ሃላፊነት እንደሆነ መገመት አያዳግትም።

ከላይ እንደምሳሌ በጠቀስኩዋቸው ሶስት ተቋማት ውስጥ ብቻ ቁጥር ስፍር የሌላቸው የተጋለጡ ሊሰናከሉ፣ ሊደናቀፉ የሚችሉ አካላት ይገኛሉ። ከመደጋገም ብዛት የወያኔን መንግስት አሽመድምደው፣ ከሌሎች ነገሮች ጋር ተደምረውም የሚንዱት ናቸው። ሌላው ቀርቶ ጊዜና ቦታ እየተመረጠ በርከት ያሉ የወያኔ ተሽከርካሪዎች ጎማዎቻችው ሁሉ በየወሩ በየከተማው ቢተረተሩባቸው በዚያ ሳቢያ በእነዚያ ቀናት ሊፈጠር ከሚችለው የስራ መጓተት ሌላ፣ በተለይም ለወያኔዎቹ ለራሳችው ወያኔ ድንጉጥና ደካማ እንደሆነ የሚመሰክር፣ ለኢትዮጵያውያንም ታላቅ የስነልቦና ድል፣ ገፋ ላለ ነገርም የልብ ልብ የሚስጥ አጀማመር ይሆናል።

ይህንን ለማድረግ ድርጅት ያስፈልጋል። አዋጅ አያስፈልግም። ወደ ጎረቤት ሀገር ሄዶ መሸፈትንም አይጠይቅም። ጥቂት ሰዎች በታላቅ ጥንቃቄና ጥበብ በትንሹ ጀምረውት እያደረ ሊጎለብት የሚችል የወያኔን አከርካሪ የሚሰብር ትግል ነው።

“እንዳለፈው ጊዜ ይሄ መንግስት ይፍረስ እንጂ የባሰ አይመጣም ብለን ከወያኔዎች የከፋ ነገር የሚያስከትልብንን ስህተት እንዳንሰራ” የሚለው መሸበር በመሰረቱ በመረጃ የተደገፈ ፍርሃት አይደለም። ከዚህ አስተያየት ጀርባ ደርግን ያፈረሰው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የሚል የተሳሳተ ግምትም ያስተጋባል።

ደርግን የኢትዮጵያ ሕዝብ አፈረሰው ማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጦርነቱ ጊዜ በወያኔዎች እና በሻእቢያ ሲመራ ነበር፣ እንዲሁም በሽግግሩ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔ ተወክሎ ነበር እንደማለት ይቆጠራል። ያ ደግሞ ትክክል አይደለም። በኢሰፓ ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት ሲፈርስ ኢትዮጵያውያን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ቢተባበሩም፣ ደርግን ያፈረሱት በመሰረቱ ምዕራባውያን ኃያላን ናቸው። እነርሱ ደግሞ በየትኛውም ጊዜ የኢትዮጵያን መንግስት አፍርሰው በምን እንደሚተኩት ግራ ተጋብተው እንዳልነበረ በሎንዶኑ ስብሰባ ግልጽ ነበር። እና ከላይ የተጠቀሰው ሽብር የአሸናፊዎች ጭንቀት አይደለም።

ግን፣ እንዳለፈው ጊዜ ሁሉ፣ የኢትዮጵያውያን ጸረ ወያኔ አመጽ ወያኔዎችን ከማፍረሱ በፊት ፈረንጆቹ እጃቸውን ማስግባታቸው አይቀርም። የኢትዮጵያውያን ጭንቀት መሆን ያለበት በድርድሩ ጠረቤዛ ዙሪያ የሚወክላቸው ኃይል ወንበር ማግኘቱና፣ ምኞታቸውና ፍላጎታቸውን የሚያቋጥር ወያኔዎችን የሚተካ መንግስት መቋቋሙ መሆን አለበት። በሌላ አነጋገር፣ ፈረንጆቹ “እንደወያኔ ያለ ጸረ ኢትዮጵያ መንግስት እንደገና የምትሾሙብን ቢሆን ወዲያውኑ እናፈርሰዋለን” የሚል መልዕክት ከኢትዮጵያውያን ጸረ ወያኔ አመጽ እንዲደርሳቸው መሆን ይኖርበታል።

ድል ለኢትዮጵያውያን!
ዝናዬ ታደሰ

ማስተር ፕላኑ ይቁም ከተባለ፤የታሰሩት ይፈቱ፣ገዳዮችም ለፍርድ ይቅረቡ! (ይድነቃቸው ከበደ)

ማስተር ፕላኑ ይቁም ከተባለ፤የታሰሩት ይፈቱ፣ገዳዮችም ለፍርድ ይቅረቡ! (ይድነቃቸው ከበደ)

“….የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ንጹሃና ዜጎች በመንግሥት ታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን አስመልክቶ፣ መጽናናትን ለቤተሰቦቻቸው ከመመኘት ባለፈ ምንም አይነት ውሳኔ አለማሳለፉ ፣በእርግጥም ውሳኔው የኦህዴድ እንዳልነበረ የሚያሳብቅ ነው፡፡”

“የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን” የሚል ስያሜ የተሰጠው መንግሥታዊ ውንብድና ፣በአገራችን አለመረጋጋትን ፈጥሯል፤መተኪያ የሌለው የሰው ልጅ ሕይወት እንዲጠፋ፣ የንብረት ውድመትና ኪሳራ እንዲደርስ ምክንያት ሆኗል፡፡ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ማስተር ፕላኑን እንዲቆም እና ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ያላትን ጥቅሞች ተግባራዊ ለማድረግ ወስኛለው ማለቱ እየተሰማ ነው፡፡
የሕዝብ ጥቅም እና ፍላጎትን ያልጠበቀ ውሳኔ ማሳለፍ ከአንባገነን መንግሥት ሁሌም የሚጠበቅ ድርጊት ነው፡፡የፌደራል መንግሥትም ሆነ የኦሮሚያ ክልል አስተዳዳር “የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን”ን አስመልክቶ፤ የጉዳዮ ቀጥተኛ ባለቤት የሆነው የአካባቢ አርሶ አደሮች፣ የክልሉ ነዋሪዎችና የሚመለከታቸው ሁሉ በጋር በግልፅ ድርጊቱን ሲቃወሙ ነበር፡፡
ለሕዝብ አቤቱታና ተቋውሞ፣ ተገቢውን ክብርና ምላሽ የማይሰጠው የህውሓት/የኢህአዴግ አንባገነን መንግሥት፣ ይህ ነገር ለእኛ አይጠቅምም ያሉ፣ቅሬታቸውን በሠላማዊ መንግድ የገለጹ ፣በታጣቂ አይሎች በአደባባይ እንዲገደሉ ተደርጓል፣የአካል ጉዳትም የደረሰባቸው አሉ፣በመንግሥት የማሰቃያ እስር ቤቶች እየተሰቃዩ የሚገኙ ሰላማዊ ዜጎች እና የፖለቲካ አመራሮች እንዲሁም አባላት ይገኛሉ፡፡
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ፣በህውሓት የሞግዚት አስተዳደር የሚመራው ፣የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ እንደ-ቀልድ ማስተር ፕላኑ ይቁም ማላቱ ፣ከውሳኔው ጆርባ ያለው ፓለቲካዊ አንድምታ ብዙ ርቀት ሄዶ ምርምርን የሚጠይቅ አይደለም፡፡የአፍንጫ ሥር ፖለቲካ ቁማር ነው ! ኦህዴድ ቀድሞ ነገር “የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን”ን አስመልክቶ የእቅዱ ባለቤት አልነበረም ፣ልሁንም ቢል የማይቻለው ነገር ነው፡፡ለዚህ እንደ-ማሳያ ብዙ ነገሮችን ማንሳት የሚቻል ቢሆንም ፣ከማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ፣ለሁለት ዓመት ያኸል ሕዝብ በይፋ ማስተር ፕላኑን ሲቃወም ነበር፤ኦህዴድ በሕዝብ የሚመራ ከሕዝብ የተመረጠ፣በራሱ ድርጅታዊ አቋም የሚጸና ቢሆን ኖሮ፣አሁን ላይ ሳይሆን ከሁለት ዓመት በፊት፣ የመሬት ወረራና ንጥቂያ በቆመ ነበር፡፡ግን አልሆነም፣መሆን ስለማይቻል!
በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የሥልጣን ተዋረድ እንዲሁም የኃይል አሰላለፍ፣ በቁጠር ብዛት እንጂ በውሳኔ ሰጪነት ቦታ የማይኖራቸው እህት ድርጅቶች ፣ሁሌም ቢሆን ከሚወክሉት ሕዝብና አካባቢ ይልቅ፣ለበላይ ተጠሪያቸው ለህውሓት ማገልገል እና ታማኝ መሆን መገለጫ ባህሪያቸው ነው፡፡የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በተመለከተ የቀረበውን መሪ እቅድ በዋነኝነት ይደግፉ የነበሩት እንዲሁም ለተግባራዊነቱ ዘብ የቆሙት፣አቶ ሙክታር ከድርና አስቴር ማሞ በግንባር ቀደመ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
እነዚህ ሁለት የኦህዴድ ባለስልጣናት በመከተል ቁጥራቸው የበዛ የኦዴድ ካድሬዎች ፣ የወከላቸውን የኦሮም ሕዝብ ከማገልገል ይልቅ ፣የግል ጥቅማቸውን በማሰብ ለአሳድሪያቸው ገብረዋል፣አሁንም እየገበሩ ይገኛሉ!ጫና የበዛበት ፣የአስተዳደር በደል መሸከም ያቃተው የኦሮሞ ሕዝብ ፣ዓይን ባወጣ መልኩ ከቦታው በሃይል እንዲፈናቀል መደረጉን አምርሮ በመቃወሙ፣ይህም ተቃውሞ ዓይነቱና መጠኑ እየበዛ መምጣቱን ተከትሎ ፣ለአገዛዙ ሥርዓት አስጊ መሆኑን የተረዳው የህውሓት/ኢህአዴግ ገዢ መንግሥት “የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን”ን እቅድ እንዲቆም ወስኗአል፡፡
እቅዱ እንዲቆም መወሰንና እቅዱን መሠረዝ፣ የየራሳቸው ትርጉም እና እሱን ተከትሎ የሚመጣ ፖለቲካዊ መዘዙ ብዙ ነው፡፡የታሰበው የማስተር ፕላን እቅድ እንዲቆም መደረጉ ሳይሆን፣ መሠረዝ ወይም ማስቀረት ብቻ ነው፣ ለኦሮሞ ሕዝብ ለጥያቄው ትክክለኛ ምላሽ የሚያስገኝለት!!! ይህን በቅጡ ያልተረዱ ወይም ለመረዳት ያልፈለጉ የኦህዴድ ባለሥልጣናት “ሾላ በድፍኑ” አይነት ውሳኔ እንዲያሳልፉ በተሰጣቸው ትዝዛዝ መሠረት ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡
የተወሰነ ውሳኔ እንደሚያመለክተው “የውዝግቡ መንስኤ ሆኖ የቆየው የአዲስ አበባና በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሙሉ በሙሉ እንዲቆም” በማለት ወስኗል፡፡ውሳኔው የመሬት ነጠቃና ወረራ ላወገዙ፣ተቃውማቸውን በአደባባይ ለገለጹ ኢትዮጵያዊን ሁሉ ትልቅ ድል ነው፡፡ ትንንሽ ድሎችን በመሰብሰብ ለተሻለ ደል መብቃት በእርግጥም ተጨማሪ ሥራ ይጠይቃል፡፡ነገር ግን የኢህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ንጹህና ዜጎች በመንግሥት ታጣቂ ሐይሎች መገደላቸውን አስመልክቶ፣ መጽናናትን ለቤተሰቦቻቸው ከመመኘት ባለፈ ምንም አይነት ውሳኔ አለማሳለፉ ፣በእርግጥም ውሳኔው የኦህዴድ እንዳልነበረ የሚያሳብቅ ነው፡፡
“በየትኛውም የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ሕዝብ የልማትና የግልፅነት ጥያቄዎችን ማቅረቡ ድርጅቱ ከሌሎች ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር በመሆን እየገነበ የሚገኘው ስርዓት ውጤት በመሆኑ በአድናቆት እንደሚመለከተውና ከፍተኛ ክብር እንዳለው” የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ ውስጥ ተካቶ ይገኛል ፡፡በሕዝብ ላይ ከዚህ በላይ መቀለድ ምን አለ ?! እነሱ እንደሚሉት ሕዝብ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄውን በማቅረቡ እና በመቃወሙ ብቻ ሕይወቱን እንዲያጣ ተደርጓል፡፡ኦህዴድ እወክለዋለው የሚለው ሕዝብ በጠራራ ፀሐይ ሙሉ ትጥቅ በታጠቁ ወታደሮች ሲገደል፣ይህን ድርጊት የፈጸሙ ግዳጁን እንደጣለ ጀግና በአደባባይ ሲዘባበቱ፤የሟች እና የገደይ ድርጊት ኦህዴድ “…..ከሌሎች ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር በመሆን እየገነበ የሚገኘው ስርዓት ውጤት በመሆኑ በአድናቆት እንደሚመለከተውና ከፍተኛ ክብር እንዳለው” ብቻ አይቶ ማለፉ፣ ድርጅቱ እውነትም የሕዝብ ውክልና አለው ወይ ብሎ የሚያስጠይቅ ነው፡፡
የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን በመቃወማቸው ብቻ፣የተገደሉ ዜጎቻችችን ደም ደመከልብ ሆኖ መቅረት የለበትም! የመግደል ትእዛዝ የሰጡ ፣ግድያውንም የፈጸሙ እና ያስተባበሩ ፣በእውነተኛ ፍርድ ቀርበው መዳኘት አለባቸው፡፡ይህ ሲሆን ብቻ ነው የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ የሚያገኘው፡፡ከዚህ ባነሰ “ሕይወታቸውን ላጡ እናዝናልን” ማለት ብቻ በቂ አይደለም፣ንጹሃንን የገደሉ እና ያስገደሉ ለፍርድ ይቅረቡ !!!
ይህም ብቻ አይደለም፣አሁን ላይ የፌደራል መንግሥትም እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል አስተዳዳር የሚመራው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ ስሕተት መሆኑ አውቆ ይቁም ስላለው ማስተር ፕላን ፤አስቀድመው ማስተረት ፕላኑን እንደማይጠቅም የተረዱ፣ መረዳታቸውንም በአደባባይ በመግለፃቸው ብቻ፣በተለያየ የአገዛዙ ሥርዓት የማሰቃያ እስር ቤቶች የሚገኙ፤ የኦሮሞ ተወላጆች፣ የፓለቲካ መሪዎችና አባላቶች እንዲሁም ማንኛውም ዜጋ ፣ከማጎሪያ እስር ቤት ሊፈቱ ይገባል፡፡እናም ማስተር ፕላኑ ይቁም ከተባለ፤ የታሰሩት ይፈቱ፣ ገዳዮችም ለፍርድ ይቅረቡ!

 

ማለቴ ለማኝነት ( ሄኖክ የሺጥላ )

ማለቴ ለማኝነት ( ሄኖክ የሺጥላ )

ቋር ላይ የተነጣጠረ ምስማር ቢጣመም ጥፋቱ የምስማሩ ፣ ወይም የቋሩ ወይም የመዶሻው አይደለም ። ጥፋቱ ያናጢው ነው ።
በግብርና መር ኢኮኖሚ የሚመራ ስርዓት፣ ህዝቡ በድርቅ ምክንያት ለረሃብ ወይም ረሃቡ ገፍቶ ለቸነፈር ‘ና ለጠኔ ቢዳረግ ፣ ችግሩ የገበሬው ፣ ወይም የመሬቱ ወይም የአየሩ አይደለም ፣ ችግሩ የስርዓቱ ነው ። ድርቅ ተፈጥሯዊ ክስተት ነው ። ረሃብን ግን ተፈጥሯዊ የሚያደርገው የአስተዳደር ችግር ነው ። እንድንናገር ከተፈቀደልን የሃገረችን ነገር “ለማ” ብለን ሳንጨርስ “ገለማ” የሆነውም በዚሁ በአስተዳደር ዙሪያ ባለው ችግር ነው( ይመስለናል ይላሉ ሙሁሮቹ!) ። አስተዳደር ስል ፣ እያስተዳደርን ነው ለሚሉት ቦታ መስጠቴ አይደለም ፥ ግን አለ አይደል ፎርማል ለመሆን እንጂ ። ፎርማል ስል <ፎርማሊን> ትዝ አለኝ ። አዎ ፎርማሊን በአስተሳስቡ ለሞተ ሰው የሚወጋ የ ድንቁርና ማድረቂያ መድሃኒት ቢሆን ኖሮ ፣ ወያኔን ምን ትጠብቃለህ ” ተጠቀም እንጂ !” ብዬ የማይነጥፍ ምክሬን በለገስኩ !
እሱንም በልመና ኣስገብተው በልማታችን ባይሉን ምን ኣለ በሉ !

ባደጉ ሀገሮች ድርቅ ከአንድ ተፍጥሯዊ ክስተትነቱ ባሻገር ፣ የምርምር እና የጥናት አጋጣሚን የሚፈጥር አንድ ትልቅ ቤተ ሙከራም ነው ። መሬት መንቀጥቀጥም ይሁን ፣ የመሬት መንሸራተት ፣ ከክስተትነት ባለፈ ለተሻለ መረዳት እና የወደፊት ጥንቃቄ ትተውት የሚሄዱት ለጥናት እና ምርምር ናሙና የሚሆን ሳይንሳዊ አሻራ አላቸው ። በኛ ሀገር ግን ሰውነቱን ጉበት ቀብቶ እንደሚንዘፈዘፍ አጭበርባሪ ለማኝ ፣ መንግስት ድርቁን እንደጉበት ሰውነቱን ተቀብቶ ፣ ሀገሪቷን እያንዘፈዘፈ ስንዴ መለመኛ ከማድረግ ባሻገር ፥ ከዛሬ ተምሮ ነገን ምን ማድረግ እንዳለበት ወደሚወስድ ሰዋዊ ባህሪ ለመመለስ ሲሞክር ኣላየነውም ። ይህ የመንግስት ባህሪ አንገት የሚያስቀረቅር ከሆነ ደሞ ሰንበት በት ብሏል ።
እንደውም ሳስበው ፣ የሀገራችን ኢኮኖሚ መሰረቱ ወረቀት ላይ ” ግብርና መር ” በተግባር ግን ” ልመና መር ” መሆኑ ነው ። ይህ ደሞ ስልጣንን ያለ እውቀት መቆናጠጥ ከሚያጎናጽፈው ንቀት እና ትቢት ባሻገር ፣የስልጣን ባለቤት ነኝ ለሚለው አካል፥ አብሮ በተጨማሪነት የሚደጉመው ውል አልባነት ፣ ሃሳብ አልባነት ፣ ጥበብ አልባነት ከፖለቲካ ኪሳራነት በተጨማሪ የክሽፈቱ ምንዳና ማሳያም በመሆኑ ነው ! ማለቴ ለማኝነቱ እና እግር ስር እንደ ህጣን ኣለሁ የሚለው ፈጣጣ (ፈንጣጣ) ልማቱም የግራ መጋባት እና የእውቀት ማነስ ውጤት ነው። ወጠጤ ጎልማሶች ኣልረዳ ኣሉን እንጂ!
በክላሽ እና በ ትራሽ ፖለቲካቸው ኣደከሙን እንጂ ! ስለ ሰ’ብኣዊ መብት ስትጠይቅ ስለ ኮብል ስቶን እያወሩ የመረዳት እና የማስረዳት ኣቅማችንን ለነሱ ስንል ” እታች” ኣወረዱት እንጂ ። ሀገር ስንል ጎሳ እያሉ ፥ መሬት ስንል ኣፈር እያሉ ፥ ህዝብ ስንል ፥ ዝንብ እያሉ ፥ ቆሻሻ ሌጋሲያቸውን ታሪክ ብለው ኣሰፈሩት ! “ያስፈራሉም ” ያሳፍራሉም !

የሰላምን በር ጠርቅሞ የዘጋው ወያኔ ነው!!! አርበኞች ግንቦት 7

aseeየወያኔ አረመኔያዊ ያገዛዝ ስርዓት በህዝባችን ላይ የሚፈጽመው አፈና ግድያና ዝርፊያ በመጠኑም በዘግናኝነቱም ይበልጥ እያገጠጠ ስለመጣ ለወትሮው እንዳላየ አይተው የሚያልፉትን ምዕራባውያን ለጋሾቹንና ወዳጆቹን ሳይቀር በጅጉ ማሳስብ ጀምሯል። ወያኔ ለምዕራባውያን ደህና ሎሌ በመሆን ወንጀሌን እንዳላዩ እንዲያዩልኝ ማድረግ እችላለሁ የሚለው አካሔዱ በውንብድና ተግባሩ ለከት የለሽነትና ዘግናኝነት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ እየተሸረሸረበት ነው። ብዙዎቹ ምዕራባውያን ላለፉት ሁለት ወራት በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ የሚካሄደውን ጭፍጨፋና አፈና ለማውገዝ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
አሜሪካንን ጨምሮ የወያኔ ለጋሽ ሀገራት የሆኑት ምዕራባውያን ሰሞኑን በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ ወያኔ የከፈተውን የዕብሪት ጭፍጨፋ እስራትና አፈና አስመልክቶ ችግሩን በውይይትና በስልጡን መንገድ የፈታ ዘንድ የሚያሳስቡ ግልጽና ባንጻራዊ ደረጃ ሲታዩ ጠንከር ያሉ መግለጫዎችን አውጥተዋል።
የደረሰውም ጥፋት ተመርምሮ ጥፋተኛ ወገን እንዲጠየቅ የሚጠይቁና ችግሩም በሰላምና በውይይት እንዲፈታ እየጎተጎቱ ይገኛሉ። ባለፉት በርካታ ዐመታት ምዕብራባውያኑ የወያኔ ጉጅሌ ይህንን አቅጣጫ እንዲከተል ተጽዕኖ የመፍጠር አቅማቸውን ተጠቅመው ያደረጉት በቂ ግፊት እንደሌለ ይታወቃል። የአሜሪካ መንግስትና ያውሮፓ ሕብረት አባል ሀገሮች ዘግይተውም ቢሆን ሀገራችን ውስጥ የተካሄደውንና እየተካሔደ ያለውን ጭፍጨፋ ማውገዛቸውና ወደፊትም በዝርዝር ተመርምሮ ተጠያቂው እንዲታወቅ ያቀረቡትን ሀሳብ እንደ በጎ ጅምር እንመለከተዋለን።
ለሀገራችንና ለህዝባችን እጣ ፋንታ የምንጨነቅና የህዝቡ ጥቃት ያንገፈገፈን የሀገሪቱ ልጆች የችግሩ የመፍትሔ መጀመሪያ ይህ በጉልበቱ ህዝባችን ላይ የተጫነ መንግስት ነኝ ባይ የግፈኞች ጥርቅም በሃይል በሚደረግ ትግል ጭምር መወገድ አለበት ወደሚለው ውሳኔ የደረስነው የሰላም በርና ጭላንጭል ሁሉ በመዘጋቱ እንደሆነ ስንገልጽ ቆይተናል ። ላለፉት ሁለት ወራት በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውና ከመቶ ሀምሳ በላይ ወገኖቻችን ያለቁበት ጭፍጨፋ እንዲሁም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ተመሳሳይ ግዲያ እስራትና የተቀናቃኝን አድራሻ ደብዛ ማጥፋት እርምጃ የሚያሳየው ይህ ስርዓት የበለጠ ጥፋት ከማድረሱ በፊት በፍጥነት መወገድ ያለበት መሆኑ ላይ ያለን አቋም ለሁሉም ይበልጥ ግልጽ እየሆነ መምጣቱን ነው። እንደወያኔ ያለ ከህዝብ የተጣላ የፖለቲካ ሀይል የፖለቲካ ጥቅምን የሚያየው ከራሱ ህልውናና ደህንነት አንጻር እንጂ ከህዝቡ ሰላም ብልጽግናና ነጻነት ወይም ከሀገሪቱ የረጅም ጊዜ እጣ ፋንታ አንጻር አይደለም። የወያኔን ገዥዎች የሚያስጨንቃቸው የህዝቡ ኑሮ ሳይሆን የራሳቸው የዝርፊያ ስርዓት ባግባቡ መጠበቅ አለመጠበቁ ነው። ለዚህ ነው ስርዓታቸውን ለመጠበቅ የነጻነት ጥያቄ ኮሽታ በሰሙ ቁጥር የሚባንኑት። ለዚህ ነው በሰላም መብቱን የጠየቃቸውን ሁሉ መደዳውንና በጭካኔ በጥይት የሚረፈርፉትና የተረፋቸውን እንደ እንስሳ ወህኒ በረት ውስጥ የሚያጉሩት።
አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔ ጸረ ህዛብና ጸረ አገር እርምጃ ሊቆም የሚችለው ላለፉት 25 አመታት ወያኔ በመካከላችን የገነባው የመከፋፈልና የልዩነት ግድግዳ ለመናድ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንዳችን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በሁላችንም ላይ እንደ ተፈጸመ ቆጥረን በጋራ ስንንቀሳቀስ ብቻ ነው ብሎ ያምናል:: ዛሬ በኦሮሚያ ወገኖቻ ላይ እየተፈጸመ ያለው ሰቆቃና ግዲያ ትናንት በጋምቤላ ፤ በኦጋዴን ፤ በአፋር፤ በቤኔሻንጉል ፤ በደቡብና በአማራ ወገኖቻችን ላይ በፈረቃ ሲፈጸም የቆየና እየተፈጸመ ያለ መከራ መሆኑን የማይገነዘብ የለም:: በፈረቃ መገደል ፤ በፈረቃ ወህኒ መወርወር ፤ በፈረቃ መፈናቀል፤ በፈረቃ ለስደት መዳረግ የሁላችንም ዕድል ፈንታ ሆኖአል :: ይህንን ስቃይና መከራ ማስቆም ለፍትህና ለነጻነት የቆመ ዜጋ ሁሉ ግዴታ ነው::
ወያኔ የሰላም በሮችን በሙሉ ጠርቅሞ ሲዘጋ ለአገራቸው ጥቅም ሲሉ ዝምታን የመረጡ ምዕራባዊያን የህዝብ ብሶት ገንፍሎ አደባባይ ከወጣና ብዙዎች በአጋዚ ጦር ጨካኝ ግዲያ ህይወታቸውን ከገበሩ ቦኋላ ዘግይተውም ቢሆን መናገር መጀመራቸው መልካም ጅምር ነው:: ነገር ግን በእብሪት የተወጠሩ የወያኔ መሪዎች በባዕዳን አለቆቻቸው ቁጣ ከአቋማቸው ፍንክች ይላሉ ብሎ መጠበቅ መዘናጋት እንዳያስከትል መጠንቀቅ ተገቢ ነው:: : ችግሮችን ተነጋግሮ መፍታት ትልቅ አቅምና ችሎታን የሚጠይቅ የዘመናችን ሥልጣኔ ውጤት ነው:: በጠመንጃ ተጸንሶ በጠመንጃ የተወለደው ወያኔ ለእንዲህ አይነት ዕድገትና ሥልጣኔ አልታደለም::
አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔ ስርዓት ሊወገድ እንጂ ሊጠገን የማይችል የተበላሸ ስርዐት መሆኑን ይገነዘባል::በመሆኑም በህዝባችንና በአገራችን ላይ የሚፈጸመውን ወንጀል ለማስቆም የጀመረውን ሁለገብ ትግል የወያኔ አገዛዝ እስኪወገድና ሠላምና ዲሞክራሲ በአገራችን እስኪሰፍን ድረስ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ለወዳጅም ለጠላትም ያረጋግጣል ::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Brutal crackdown in Ethiopia

By Nick Robins-Early, World Post

Human rights groups say at least 140 people have been killed in protests over a land expansion plan.

A protest outside the United Nations in New York City. Human Rights Watch claims the Ethiopian government has killed over 140 protesters in demonstrations over the Addis Abba expansion plan. PACIFIC PRESS/GETTY IMAGES

In Ethiopia, 2016 is off to a violent start. Authorities in the East African nation have killed at least 140 people in a brutal crackdown on protests over the last two-and-a-half months, according to human rights groups, amounting to the worst ethnic violence in years.

The violence has brought renewed attention to the struggle over land rights and political tensions in the country and it has highlighted rights abuses in a nation deemed an important U.S. ally in the fight against terror.

Anger Mounts In Oromia In The Fall Of 2015
In November 2015, discontent intensified in Ethiopia’s Oromia region over a government plan to expand the borders of the country’s capital, Addis Ababa, into the surrounding rural areas.

Protesters marched to voice their opposition, fearing that the state’s Addis Ababa Integrated Development Master Plan, as the proposal is called, would seize land from the Oromia region’s marginalized Oromo ethnic group, which makes up around 35 percent of Ethiopia’s population. The area of Oromia that the city seeks to incorporate is already home to two million people, according to Human Rights Watch.

The protesters’ fears were informed by years of deep discontent with the ruling Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front. Though the nation’s capital of Addis Ababa is surrounded by the ethnic Oromia region, the city was established by the Amhara people, The Washington Post notes. As the city expanded, there have been clashes over forcible evictions, as well as ethnic and linguistic identity. Furthermore, the authoritarian government has a history of attempting to stamp out dissent, especially among ethnic groups it views as being in opposition to its ruling coalition.

Over 5,000 Oromos have been arrested on charges relating to protests and dissent in the past five years, according to an Amnesty International report. Oromos who were detained were sometimes subject to horrific abuse, including rape, torture and beatings.

A map of Ethiopia, which shows the capital of Addis Ababa. The Oromia region makes up two-thirds of the country, and surrounds the capital. LONELY PLANET/GETTY IMAGES

Demonstrations spread throughout the Oromia region over the course of November, as groups including farmers and students rallied against the government.

Ethiopian authorities responded to the largely peaceful protests with force, seeking to quash the growing dissent. Police used live ammunition to disperse protesters at rallies, activists and rights groups say, killing dozens of people in separate incidents in the areas around Addis Ababa.

As the unrest continued through December, rights groups also reported widespread arrests, beatings and torture at the hands of security services. Even senior members of opposition parties, including Bekele Gerba, a prominent member of the Oromo Federalist Congress — the largest Oromo political party — did not escape the crackdown.

And The Protests Escalate
The security forces’ crackdown on demonstrators failed to prevent the protest movement from intensifying — it actually expanded its demands to also call for an end to police brutality. As of the end of December, over 140 people had been killed in the protests, according to Human Rights Watch — and the rising death toll began to attract international criticism.

The United States, which has collaborated with Ethiopia on anti-terror efforts and until last September operated a drone base out of the country, issued a statement of concern and called for the government to allow peaceful protests.

Instead of moving toward reconciliation, however, the government doubled down on its position. Authorities denied protesters’ requests to hold rallies in Addis Ababa and accused the Oromo protesters of committing terrorism in a bid to destabilize the government.

As demonstrations continued, the Ethiopian government finally caved to the months of pressure on Jan. 13, and scrapped its expansion plan.

What’s Next?
While the protests met their initial goal of stopping the urban expansion, demonstrators have been invigorated by the crackdown and have continued to rally against the government.

“The complaints of the protesters have now expanded to include the killing of peaceful protesters and decades of marginalization,” Human Rights Watch Horn of Africa researcher Felix Horne told The WorldPost over email.

What began as a protest over land rights is now representative of a number of grievances with the government and ruling EPRDF. Ethiopia has seen a period of rapid economic growth in the past 10 years, but its urban and industrial expansion has also resulted in land disputes, corruption and authoritarian crackdowns on opposition groups.

As demonstrators increasingly demand solutions for Ethiopia’s many social and political problems, rights groups worry that the unrest and violence will continue.

“Human Rights Watch continues to receive reports daily about excessive force being used by security forces in Oromia,” Horne said. “The death toll continues to rise and the arrests continue.”

Source: Axis of Logic