ሕወሓቶች የወልቃይት ጸገዴን ሕዝብ መስለው ሰልፍ ወጡ

 

(ዘ-ሐበሻ) “በመላዋ ኢትዮጵያ ሰልፍ መውጣት ወንጀል በሆነበት በዚህ ወቅት በትግራይ ክልል ግን ይፈቀዳል:: የሕዝብ እኩልነት ይህ አይደል?! ከሁለት ሳምንት በፊት የወልቃይት ጸገዴን ማንነት ለማስረዳት ወደ አዲስ አበባ የመጡት ተወካዮች መታሰራችው ይታወሳል::” ያሉን አንድ አስተያየት ሰጪ የሕወሓት መንግስት ዛሬ በጸገዴ ወረዳ አስደረጉት ስላለው ሰላማዊ ሰልፍ ሲያስረዱ “የጸገዴ ሕዝብ የአማራ ህዝብ መሆኑን ያውቃል; አውቆም ተቀብሎታል.. ዛሬ የራሱን የሕወሓት አባላትን ከየቦታው ሰብሰቦ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የብሄርን ግጭት ከማባባስ የባሰ ምንም ፋይዳ የለውም” ይላሉ::

መንግስታዊው ራድዮ ፋና “በትግራይ ክልል የፀገዴ ወረዳ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄያችን ተመልሷል አሁን ላይ ይህን የሚያነሱ እኛን አይወክሉም በማለት ሰልፍ ወጡ” ሲል ያስነበበው ዜና መነጋገሪያ ሆኗል:: የወልቃይት ጸገዴ ማንነት ጥያቄን የሚያነሱትን እና እኛ አማራ ነን በግድ ወደ ትግራይ ክልል እንድንጠቃለል ተደርገናል በሚል ተቃውሞ ሲያነሱ የነበሩትንም እንደተለመደው ሰልፈኞቹ “የጸረሰላም ሃይሎች ናቸው” ብለዋቸዋል ይለናል::

በጸገዴ ሕዝብ ስም ዛሬ ሰልፍ የወጡት የሕወሓት አባላት ይህን ሰልፍ የጠሩት አንድም የገቡበትን ውጥረት ለማብረድ በሌላ በኩልም ሕዝብን ለማናከስ እንደሆነ ማንም ያውቃል:: እንደፋና ዘገባ እነዚህ ሰልፈኞች “የፀረ ሰላም ሃይሎች የጀመሩት ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ዓላማ በጥብቅ እንደሚቃወሙ ሰልፈኞቹ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ ከዓመታት በፊት የተመለሰውን የህዝብ የማንነት ጥያቄ እና አብሮና ተስማምቶ የሚኖርን ህዝብ ለማጋጨት በአሁኑ ወቅት እንደ አዲስ እያነሱ የሚገኙትን የፀረ ሰላም ሃይሎች እንቅስቃሴን በጥብቅ እንደሚቃወሙም ነው ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ የገለፁት።”

የሕወሓት መንግስት ለሌላው ኢትዮጵያዊ የከለከለውን ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣትና ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በጸገዴ ሕዝብ ስም ለወጡት አባላት መፍቀዱ የሚያስደንቅ ባይሆንም ይህ ሰልፍ እንዲህ ባለው ሁኔታ መደረጉ ይበልጥ የወልቃይት ጸገዴን ሕዝብ እንደሚያነሳሳው አስተያየት ሰጪዎች በማህበራዊ ድረገጾች ሃሳባቸውን እየገለጹ ነው

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s