ፈርዖናዊው የወያኔ አገዛዝ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ሲደገም ምን ይመስላል?

ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር፤ ጎንደር  ኢትዮጵያ

በ24 አመታት ውስጥ በተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢ ጥቂት የሚባሉ መልካም ለውጦች ቢኖሩም እንኳ ጀግናው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አይደለም የመልካሙን ለውጥ ሊያጣጥም እንዲያውም በተቀነባበረ ሁኔታ የዛሬ 24 አመት ከነበረበት የህልውናና  ኑሮ ብዙ እጥፍ አሽቆልቁሎ ተምዘግዝጎ ወርዶበታል፤ ወያኔ አሰቃይቶታል፤ ህይወቱና አኗኗሩ አመሰቃቅሎበታል፤ ለብዙ መከራና ስቃይ ሞትና እንግልት መታሰርና ደብዛ መጥፋት መሰደድና መሸማቀቅ ዳርጎታል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከ1972 ጀምሮ የወያኔ መርዝ የተርከፈከፈበት ህዝብ ነው። አሳዛኙ ነገር ወያኔ የፈጠረው ችግር በሁሉም የኢትዮጵያ መርዙን ከመትፋቱ ጋር ተያይዞ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወገኑ የየራሱን ህመም ሲያዳምጥ ስለኖረ ከህመም ሁሉ ህመም፣ ከእልቂት ሁሉ እልቂት ሲፈጸምበት፣ በእስራኤላውያን ላይ በኦሽዊትስ ካምፕ በናዚዎች የተቀነባበረው የዘር ማጥፋት በ21ኛው መ.ክ.ዘ በወያኔዎቹ በግልጽና በድብቅ ሲደገም የሚዲያ ሽፋን ስለማይደርሰው ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹ ሊያውቁለትና ሃይ ሊሉት አልቻሉም መከራዉን ከ1972 አ/ም ጀምሮ ወገኖቹ ሳይደርሱለት ብቻውን ሲጎነጭ ኖሯል።

እዚህ ላይ ለማሳሰብ እምፈልገው ዋና ነጥብ  በአማራነታችን እየደረሰብን ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ህወሃት በመልካም አስተዳደር ስም ለማስተባበል መሞከር በፍጹም አይቻልም፤   የመልካም አስተዳደር ችግርማ አሜሪካም ውስጥ ቢሆን ይኖር ይሆናል። እኛ አንደላቃችሁ አኑሩን አይደለም እያልን ያለነው። ዋናው ጥያቄያችን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብና መሬት አማራ ስለሆነ ወደ እናት አገራችን ወደ ጎንደር ወደ አማራነታችን መልሱን የሚል ነው። ሰላምን ፈልገው ከመለሱን እጅግ ደስ ይለናል ካልሆነ ደግሞ የእነርሱ ፈቃድና ምስክርነት ሳያስፈልገን በራሳችን ራሳችንን አማራነታችንን አስረግጠን እንመልሳለን።በቃ ይሔው ነው!!! ይህ በትግራይ ተስፋፊና ነጻ አውጭ ቡድን፣ በትግራይ ፖሊስ፣ በትግራይ ልዩ ሃይል፣ በአጋዚ ወታደር፣ በትግራይ አስተዳደር አመራሮችና ካድሬዎች ማዳፈን የማይቻል የሚፋጅ ረመጥ ጥያቄ ነው።

የኢትዮጵያ ወገኖቻችን ሆይ ታሪክ የሚመሰክረስው እውነት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብና መሬት የአማራ እንጂ የትግሬ ሆኖ እንደማያውቅ እንድታውቁሉን ነው። የታሪክ  መዛግብት ከሚመሰክሩት እውነት በተቃራኒ ታሪኩን በማዛባት እንደማጣቀሻ ከሚያቀርቡ የትግራይን ህዝብ ከማይወክሉ የወያኔ ባንዳ የሆኑ የታሪክ ሙሁር ነን ባዮች ለምሳሌ እንደ ዶክተር  ገላውዲዮስ ያሉ የውሸት ታሪክ አጣቃሾች ታሪክ ይፋረዳቸዋል። በነገራችን ላይ ገላውዲዮስ በትግሬኛ የአሜሪካን ድምጽ ሬድዮ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ያጣቀሱት መጽሓፍ መጽሓፉ ከሚለው በተቃራኒ ስለሆነ ክስ ለመመስረት  ዲግሪያቸውን ለማስነጠቅና ሌላም ህጋዊ ቅጣት እንዲወሰድባቸው ሙሁራኖች እየሰሩ ነው። በዉሸት የህዝብን ጥያቄ አዳፍኖ ዘሩን መጨረስ እንደማይቻል ሊማሩ ይገባቸዋል እነዚህ ከንቱና ጠፊ ዘራፊዎች።  ሌላው የተማረ ኢትዮጵያዊ  ያለ የማይመስላቸው ጠባቦቹና ዘረኞቹ የትግራይን ምስኪን ህዝብ የማይወክሉ ወረበሎች የኢትዮጵያ ህዝብ በቃችሁ ሊላቸው ይገባል። በዚህ አጋጣሚ የታሪክ እውነተኛ ሙሁር አቻምየለህ ታምሩን ስለሚያደርጉት የውሸተኞች ካድሬ ሙሁሮችን ሴራ ማጋለጥ በእጅጉ የወልቃይት ጠገዴ  ህዝብ ልባዊ ምስጋና እንዳስተላልፍላቸው ይፈቀድልኝ። እንዲሁም ክቡር ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም፣ክቡር አቶ ገብረመድህን አር አያ፣ ክቡር አቶ ያሬድ ጥበቡንና ሌሎች ውድ  የኢትዮጵያ አንድነት የሚገዳቸውና አጥብቀው የሚሰሩ እውነተኛ  ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ  አብዛኛው ሙሁር በወልቃይት ጠገዴ ዝምታውን መርጦ  የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ እንደበግ ለመታረድ ወያኔ የውሸት ታሪክን እንደቅመም እየተጠቀመበት ባለበት ስአት እውነተኛ ቃላቸውን ስለሰጡ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ልዩ ምስጋናየን አቀርባለሁ። ሌሎች ሙሁራን ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሁንም ህዝቡ የግረሱልኝ ጥሪውን በማስተጋባት ላይ ነውና እባካችሁ ድረሱልን።ተሳትፎ ያደርጋችሁ ሙሁራንም  ሳይለየን የአገራችን ህግ በወያኔ ምክንያት ካልዳኘን ወደ አለማቀፍ ህግ ጉዳያችን ወስዳችሁ ከሞት እንድትታደጉን እርዳታችሁ እንዳይለየን በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።

ወያኔ ይህ ሁሉ ስቃይ የሚፈጸምበት ምክንያት ህዝቡ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት የሚታይበት ከዘረግኝነት የጸዳ ኢትዮጵያዊ  ህዝብ ስለሆነ ነው። ይህም  ማለትም እስከቅርቡ ድረስ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያየ ብሔር  ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በአሁኑ ግዜም ቢሆን ለአፍሪካዉያንም  ጭምር ማለትም  ሰሜንም ደቡብም ሱዳናዉያን የመሳሰሉ የአፍሪካ ዜጎችም ሰርተው ህይወታቸውን ቀይረውበት በሰላምና  በፍቅር ደስ ብሏቸው የሚኖሩበት  ከኢትዮጵያዊነቱ  በዘለለ በአፍሪካዊነቱም የማይታማ ህዝብና በጣም ለምና በተፈጥሮ ሃብት በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የሆነ አካባቢ በመሆኑ ዘረኞቹ ወያኔዎችና ትግሬዎቹ የተፈጥሮ ሃብቱን ቋመጡት፤ ኢትዮጵያዊ ስሜቱንም አልወደዱትም። የሚገርመው ነገር ህዝቡን አጥፍተው ‘ታላቂቷን ትግራይ’ በመመስረት ከሱዳንና ኤርትራ ጋር እንዋሰናለን አማራም እናጠፋለን ብለው ተነሱ።  የሚገርመው ነገር ላለፉት 36 አመታት እነርሱ የሚፈጸሙት ስቃይ አላረካ  አልበቃ ብሏቸው በሱዳን ልዩ ሃይሎች ከፍተኛ የአፈናና ግድያ አስፈጸሙበት።  የስንቱ የሃገር ጀግናና የአገር አልኝታ ህይወት ቀጠፉት አስቀጠፉት መሰላችሁ። ጀግናው ህዝብም የሚቻለውን ያህል ታገለ ቢሆንም ግን ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ብሗላ ወታደራዊ ሃይሉን አጠናክሮ በመምጣት ቦታውን ተቆጣጠረ ህዝቡንም በተለይም ወንዶችን ልክ እንደፈርዖን እያደነ ማሰር፣ ማሳደድ፣ ማሰቃየትና መዝረፍ ጀመረ በተለይ ከ1983 አ/ም ጀምሮ።

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ይህ ሁሉ ግፍ፣ መከራና እልቂት ሲጎነጭ፤ ህዝብ እንደህዝብ በመስቀል ሲሰቀል ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹም አላወቁለትም። ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በተነሳው ገንጣይ የወያኔ ቡድንና ግብረ አበሮቹ ህጻን አዋቂ፣ ወንድ ሴት፣ ገበሬ ነጋዴ፣ቀይ ጥቁር፣ አጭር ርዥም፣ ገጠር ከተማ፣ ሃብታም ድሃ ፣ያገባ ያላገባ፣ ቆላ ደጋ  ሳይለይ ሌት ተቀን ለ24 አመታት በተቀነባበረና ሳይንሳዊ አካሄድ በተሞላበት መንገድ ሞት፣ ስቃይና እንግለት ተፈጽሞበታል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን አሁንም ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ አላወቁለትም፤ ከህመም ሁሉ ህመም ይሉሃል እንዲህ ነው። እ ንዲያውም ከዚህ በተቃረነ መልኩ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ትግሬ አይደለም እንዴ ወያኔበኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርሰው ስቃይ በሌሎች ብሔር ብቻ አይደለም በእኛ በትግረዎቹ ላይም ይፈጸመዋልለማለት ፈልጋቹህ ነው?” የሚሉ አንዳንድ ሁኔታውና መሰረታዊ ችግሩ ያልገባቸው ወገኖችም አልጠፉም። በወያኔ የፖለቲካ ሴራ ተጠልፎ መውደቅ ማለት ይሔ ነው። እውነታው ግን ፍጹም እንደዛ አይደለም፤ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጠለምትም ጨምሮ ትግሬ ሳይሆኑ አማራ ናቸው። ይህ ሁሉ ግፍና የዘር እልቂት የሚፈጸምበት ስለ ሁለት አበይት ምክንያት ነው። እነርሱም፦

1ኛ. የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የብጌምድር የጎንደር አማራ ህዝብ እንጂ ወያኔና ካድሬዎቹ እንደሚሉት ትግሬ ባለመሆኑ ነው፤ ለዚህም ስለእውነት ይመስከር ቢባል ወያኔና ካድሬዎቹ ጥሩ ምስክር ይሆኑ ነበር። ትግሬም እንዳልሆነ ስለሚያውቁም ነው ይህ ሁሉ የእልቂት ግፍ ለ36 አመት የፈጸሙበታና አሁንም እየፈጸሙበት ያሉት። ሌላኛው ነጥብ ደግሞ ህዝቡ ትግሬ ቢሆን ኖሮ ትግሬነት በራሱ ጥቅም በሚያሰጥበት ወቅት ለምን ታድያ እውነትኛ የትግሬ ማንነቱን ጥሎ አማራነትን ይመርጣል? ለዛውም አማራነት ማለት “ወንጀል” አማራነት ማለት “ሞት፣ ስደትና መፈናቀል” ማለት በሆነበት ስአት፤ በአንጻሩ ደግሞ ትግሬነት ማለት “ቁጥር አንድ ምርጥ ዘር” ሆኖ በስርአቱ በተቆጠረበት ግዜ በዚህም ምክንያት ትግሬነት ማለት “ሃብታምነት፣ምርጥ ዘር፣ የበላይ ገዥ፣ ባለስልጣን” ማለት ሆኖ የተለያየ ጥቅም በሚያስገኝበት ስ አት እንዴት አንድ ህዝብ አማራ ነኝ ትግሬ አይደለሁም ብሎ ይነሳል። ይሔን ጥያቄ አንድ ደረጃ ከፍ እናድርገውና በኢትዮጵያ እውነታው እንዲህ በሆነበት ግዜ ጭራሽ እነርሱ እንደሚሉት እንዴት ትግሬ ሆኖ ሳለ አማራ ነኝ ይላል። አያችሁ ወያኔ በጣም ወንበዴና ህሊና-ቢስ ነው። ህዝቡ  ንጹህ አማራ እንጂ ትግሬ ባለመሆኑ ምክንያት ነው እኔ ትግሬ ሳልሆን አማራ ነኝ ያለው። ይህን ህጋዊ የህዝቡ ጥያቄ በማዳፈን ማለፍ አይቻልም አሁን ማለት ትላንት ማለት ስላልሆነ። የሚደንቀው ባለፈው መጋቢት ሁለተኛው ሳምንት 14ና 15 ላይ በሁመራ አባይ ወልዱና አባዲ ዘሞካድሬዎች ሰበሰበው ይህ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ለማዳፈን 80 ሚሊዮን ብር ወጭ እንዳደረጉና ይህም እስካሁን ድረስ ማስቆም ስላልተቻለ እርምጃ እንደሚወስዱ በድጋሚ በድፍረት ተናገሩ። ተወላጆቹ ካድሬዎቹ ግን ይህን አንመክርም የለንበትም በማለት በድፍረት እዛው ስብሰባው ላይ እቅጩን ነገሯቸው። ህዝብ ለማጫረስ የሚደረግ የድንቁርና ውሳኔ ካልሆነ በቀር የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ በፍጹም ማስቆም እንደማይችሉ ይሔው አረደሗቸው። በአሁኑ ስአት ለሞት ምንም የሚፈራበት ምንም ምክን ያት የለውም መፍራት ካለባቸው በድሎት ያሉት እነርሱ ናቸው፤ እኛማ ለየትኛው ህይወትና ኑሮ ብለን ሞትን እንፍራ?

2ኛ. አንድ ካድሬ በ1984 አ/ም እንዳለው ለታላቂቷ ትግራይ እጅ መንሻ “የወልቃይት ጠገዴ መሬቱና ሴቱ ስለሚፈለግ” ብቻ ነው። ይህም በድብቅ ሳይሆን በየስብሰባ መድረኮች ተናግረው በተግባር ሲፈጸም አይተናል።

በዚህ ጽሑፍ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከደረሱት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ግፎች መካከል ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ለግንዛቤ ያህል ጥቂቶቹን እጠቅስላቸሗለሁ። ይህም  ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ያለንበት አጣብቂኝ ሁኔታ ተረድተው ጨርሰው ሳያጠፉን እንዲደርሱልን ለማሳሰብ ነው እንጂ በሌላ ግዜ ለአለማቀፍ ማህበረሰብ የሚሆን ጽሑፍ በሰፊው አዘጋጅቼ እመለስበታለሁ። አሁን ሳይንሳዊ  በሆነ መንገድ ወያኔ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ሙሉ የዘር ማጥፋት እቅዳቸውን እንዴት ሲያከናውኑ እንደቆዩና አሁንም አይከናወኑ እንዳሉ  ከዚህ ጽሑፍ ተነስታችሁ መተንበይ አያቅታችሁም። አሁን ግዜ ሳልወስድባቸሁ ወደ ነጥቦቹ ላሸጋግራችሁ።

1ኛ. የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እንደለሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ በጣም ሃይማኖተኛ የሚባል ህዝብ ነው፤ ቢሆንም ግን ከልቡ ያለውን እምነት እምኳን መፋቅ ባይችሉም እምነቱ እንዲጠፋ ተደርጓል። ታዋቂ ታሪክ አዋቂ  ሙስሊም  አባቶች ታስረዋል ንብረታቸው ተዘርፏል። ክርስቲያኖች ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚቻልበት ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኖቹ  ቅርሶች እጅግ በጣም በተቀነባበረ ሁኔታ በወያኔ ካድሬዎች ተዘርፎ ለውጭ አገሮች ተሽጧል ተበርብሯል እንዲሁም ታዋቂ ታሪክ አዋቂ ቀሳውስቶች ተገድለዋል። የዋልድባ ገዳምም ሳይቀር ተደፍሯል ተበርብሯል።

ለልማት እየተባለ ህዝቡ የእርሻ መሬቱ ከነፍሬው፣ ከብቶቹ የሚያሰማራበት ቦታውንና ቤቱን ሳይቀር ያለካሳ ተነጥቆ ምንም የጤና አገልግሎት ሰጪ ድርጅት በሌለበት በሃይል በወታደር እየተጠበቀ እንዲሰፍር ተደርጎ በወባና በካላዛር በሚአሳዝን ሁኔታ እንዲያልቅ ተደርጓል።

2ኛ. በወልቃይት ጠገዴ ሶስት አይነት የትግራይ ሰፋሪዎች አሉ። በጠቅላላ ወደ 800,000 የሚሆኑ የትግራይ ሰፋሪዎች ነው ህዝቡን ሳያማክር መሬቱን እየነጠቀ በህዝቡ ላይ አምጥቶ ያፈሰሳቸው:: አንደኞቹ በ1983 አ/ም የሰፈሩ የወያኔ የቀድሞ ወታደሮቹ ሲሆኑ ወደ 30,000 የሚጠጉ በዳንሻ አካባቢ እንደገና እስካፍንጫቸው አስታጥቆ ያሰፈራቸው ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ በ1985 አ/ም እና  1989አ/ም ከሱዳን የተመለሱ ላጅን የሚባሉ ሲሆኑ በሁመራ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ በረከት፣ ራዉያን፣ አዲጎሹ ያሰፈራቸው ወደ 70, 000 የሚጠጉቱ ናቸው:: ሶስቶኞቹ ደግሞ አዲሶቹ ሰፋሪዎች ሲሆኑ ከ1996 አ/ም ጀምሮ የመጡ የታጠቁ ሰፋሪዎች ናቸው። አዲሶቹ ሰፋሪዎች ከ630,000 በላይ ቁጥር ያላቸው ናቸው::ነገሩን የእብደት የሚያደርገውና በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ የሚያስብለው ደግሞ  ተጨማሪ ሌላ 70 ሺ ለማስፈር እቅዱን አቅደው ለተግባርዊነቱ መዘጋጀታቸው ነው። ይምጡ ችግር የለም ለመተራረድ ይምጡ!

እዚህ ላይ ለወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በጣም አስደንጋጭ የሆነው ነገር የሶስትዮሽ ጎን የአሰላለፍ ዘመቻ (Triangular Campaign) የሚባል ሚስጥራዊ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የማጥፋትና የታላቂቷ ትግራይ የተስፋፊነት ህልም እውን የሚያድርግ እቅድ ይዘው ነው የተነሱት። አሰላለፉ እንዴት ነው ቢሉ አንደኛው መስመር ትግራይን ተሻግረው ከተከዜ እስከ ሁመራ በ15 የሰፈራ ማእከሎች የሰፈሩ ሲሆኑ ከጥርጊያ በታች የወልቃይት ሰው እንዳይወድ በማድረግ ወደ ደጋው እየገፉ የሚወጡ ተስፋፊ ነጻ አውጭ ቡድን ናቸው። ሁለተኛው መስመር በሁመራ አከባቢ ያሉ አዳዲስ ከተማዎች ማቋቋምን ጨምሮ ከሁመራ ዳንሻና ሹመሪን ጨምሮ እስከ የጎንደር ድንበር ሶሮቃ ድረስ ጥርጊያውን ተከትለውና ከጥርጊያው በታች በሙሉ የሰፈሩ ሲሆኑ እነዚህም ከድሮ ሰፋሪዎች ጋር አንድላይ በመሆን የእርሻና ከብት ማርቢያው ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር ወደ የወላቃይት ጠገዴ ደግማው አከባቢ በሂደት እየገፉ የሚዘልቁ አደገኛ ቡድኖች ናቸው። ሶስተኛው መስመር ደግሞ በአጭር ግዜ ውስጥ ወልቃይት ጠገዴን ህዝቡን አጥፍቶ ለመቆጣጠር የመጨረሻው የድል መስመር ብለው የሚጠሩት ከሽሬ ጀምሮ ወልቃይት ጠገዴን ለሁለት ከፍሎ ሱዳን ድረስ የሚወስደው በፍጥነት ያለቀው እጅግ በጣም ዘመናዊው የአስፋልት መስመር  ተከትለው ማንም ሳያውቅ የሰፈሩ በጣም ጥጋበኛና ግፍ ፈጻሚ ተስፋፊዎች የሰፈሩበት ነው። ይህኛው መስመር አንድም ወልቃይት ጠገዴን ለሁለት ከፍሎ እንዳይገናኙ ለማድረግ ይልቁኑ በአዳዲስ የሰፈራ ከተሞች ምክን ያት በማድረግ ወደ ወልቃይትና ጠገዴ ከላይኛው የደጋ በኩል ወደ ቆላዎቹ ቦታዎች በመግፋት በቆላዎቹ ከሚመጡ ተስፋፊ ቡድኖች ጋር በቀላሉ ለመገናኘት የታሰበ እ ጅግ በጣም ቀጥተኛውና አድገኛው የሞት መስመር ነው። ይህን የጥርጊያ መስመር እንዲሰራ አንፈልግም ያሉ ከ129 ሰዎች በላይ ታፍነው ተወስደው የት እንዳሉ አይታወቅም። እጅግ በጣም አዉዳሚ መስመር ነው። ከዚህ በተረፈ ወልቃይት በሚገኘው የስኳር ፋብሪክ ፕሮጀክት አማካይነት የሰፈሩ ከ30,000 በላይ አተራማሽ ተስፋፊ ቡድኖችም በህዝቡ ህልውናና ንብረት እንዲሁም ተፈጥሯዊ ሃብት ያደረሱትናእያደረሱት ያሉት ጭካኔና ግፍ ለመናገር ሌላ ጽሑፍ የሚጠይቅ ነው። እንግዲህ በዚህ መልኩ ነው ወያኔዎች የወልቃይት ጠገዴ ህዝብን እየገደሉ፣ እያሰሩ፣ እያሰደዱ፣ እያፈናቀሉ፣ ንብረቱን እየዘረፉ ለመስፋፋት እየሞከሩ ያሉት። ወገኖቻችን ሆይ ስቃያችንን ተመልከቱ፤ ይህ የአስተዳደር ችግር አይደለም የማንነትና የህልውና ጉዳይ ነው እንጂ። አማራነታችን እንዲከበርና ለዘር የሚተርፍ ትውልድ እንዲኖረን እርዱን ድረሱልን።

ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ሆይ ስለዚህ ጉዳይ በጥልቀት ለመረዳት በቅርቡ “የህወሓት ሴራ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ” የሚል ከእጃቸው በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን የተጋለጠው ሴራዊ ዶክመንት እንድታነቡ በትህትና እጋብዛለሁ። ይህ ጽሑፍ በድረ-ገጽ ታገኙታላችሁ።

ከአብዛኞቹ የሱዳን ተመላሾች በቀር ሰፋሪዎቹ ብዙ ግዜ ነገር ነገር የሚሸታቸውና ታጥቀው የሚጓዙ ናቸው። ከህዝቡ ጋር ይጣላሉ፣  አንዳንዴም ሴቶችን ይደፍራሉ፣  የህዝቡን ክብትና በግ ዘርፈው ወደ ሱዳን ይሸጣሉ። ለህዝቡ ፍጹም በጥላቻ መነጽር ብቻና ብቻ የሚያዩ ናቸው። ምን አይነት የጥላቻ የፖለቲካ ትምሀርት ለስንት ግዜ በምን አይነት ሁኔታ እንደተሰጣቸው እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው። ከጥርግያ በታች ወይንም ቆላው አካባቢ የነበሩ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ንብረቱ የሚያቆይባቸው ቦታዎች ሁሉ ለእነዚህ ሰፋሪዎች ስለተሰጠ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ንብረቱንም ስለሚዘረፍበት ህዝቡ ያለው አማራጭ ንብረቱን በዋነኝነት ከብቶቹ፣ በጎቹና ፍየሎቹ መሸጥ ስለሆነ ንብረቱን ሽጦ ከተማ ገብቶ አንዳንድ የኑሮ እንቅስቃሴ ሲጀምርና የተካነበት የእርሻ ሙያውን ባለችው መሬት ማረሱን ሲቀጥል በተለያይዩ ምክን ያቶች ተስፋ እንዲቆርጥ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ሁሉ ያለምንም ተቀናቃኝ በቆዩና በአዲስ ሰፏሪዎቹ እንዲሁም በአዲስ ከትግራይ በሚመጡ ሰፋሪ ያልሆኑ የትግራይ ልጆችና የባለስልጣን ዘመዳሞች ቁጥጥር ስር ወድቋል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብም ይህ ወልቃይት ጠገዴ እኮ እኛም ተወልደንበታል ኢትዮጵያውያን ነን ሲል “እንኳን ቆላው ደጋውና ሴቶቻችሁ ገና እንረካበአችሗለን” በማለት ህዝቡን እንደ ቄሳር መንግስት ያስጨንቃሉ። በዚህ መልኩ ህዝቡ ነፍጥኝነት ሲያነሳ ቤተሰቦቹን የነፍጠኛ ዘር እያሉ ሲጨርሱት ስለቆዩ በራስ ላይ ሞት ከማምጣትና ቤተሰብ ከማስጨረስ በቀር ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ከባለፉት ግዝያቶች በህይወቱ ስለተማረ ምንም እንኳን ውስጡ ባይሸነፍም የበይ ተመልካች ሆኖ እየኖረ ይገኛል።

ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ የሚሰራው ግፍ በዞህ ብቻ የሚያበቃ እንዳይመስላችሁ ከታች  ለመጠቃቀስ እንደሞከርኩት እንዲህ እየባሰ ክፋቱና መልኩ እየቀያየረ እየቀጠለ ነው እንጂ።

3ኛ. ሴት ተማሪዎች በአስተማሪዎቻቸው፣ በወታደሮቻቸው፣ በግብርናና በህክምና ባለሙያ ነን ባዮችና ጓደኞቻቸው ገና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያሉ ይደፈራሉ፣ ያረግዛሉ፣ ትምህርት ያቋርጣሉ፣ ይኮበለላሉ። አሳዛኙ ነገር ይሔን የሚያደርጉት የትግራይ ሰዎቻ አብዛኞቹ በትግራይ ባለትዳርና ባለልጅ መሆናቸው ነው። እንዲህ አይነት አጸያፊ ስራ በህዝባችን እንደነውር ስለሚቆጠር የተደፈሩ ህጻናት ልጆች ለቤተሰቦቻቸው ያጋጠማቸው የልብ ስብራት አይናገሩም አንድም ቢናገሩ በደፋሪዎቹ ቤተሰቦቻቸው አንድ ነገር ቢያደርጉ ቤተሰቡ እንደሚፈርስ በማሰብም ዝም የሚሉ አሉ፣ አንዳንዶቹ ራሳቸውን ያጠፋሉ ሌሎቹ ደግሞ ካራገዙ ብሗላ እውነቱን ይናገራሉ።

አብዛኞቹ ይህን መከራ የደረሰባቸው ለጋ ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር ተጣልተው ትምህርታቸውን አቋርጠው አባት የሌለውን ልጅ ታዳጊዎቹ አሳዳጊ ይሆናሉ። ምንም እንኳን በመጨረሻው ቤተሰቦቻቸው አዝነው በዝሙት ተዳድረው ከሚኖሩ ብለው ቢቀበሉዋቸውም በቤተሰብ ውስጥ ግን ሰላም የለም። ወንድ ተማሪዎችም የተለያዩ ምክንያት በመፍጠር መምህራኖቻቸው ትምህርት እንዲያቋርጡ ያደርጋሉ።

ይህን ሁሉ ግፍ ለሚያደርጉ በህግ ተጠያቂ እንደማድረግ የሚበቃውን ወንጀል የፈጸመን አካል ቦታ በመቀየር አበጀህ በሚል ስውር የሞራል አሰጣጥ የተሻለ ስልጣንና ደሞዝ ተደርጎላቸው በትግራይ የአስተዳደር ስራ ውስጥ ይቀመጣሉ አንዳንዴም በአከባቢው ይሾማሉ።

ለምሳሌ ይሆነን ዘንድ የዚህ ችግር ቀማሽ የሆነችው አታላ የተባለች የ13 አመት የ6ኛ ክፍል ተማሪ ከዳንሻ ከተማ መጥቀስ ይቻላል።  አስተማሪዋ ከደፈራት ብሗላ ደብድቦ የስነልቦና ጫና በማሳደር ፍርሃት እንዲሰማት ካደረገ ብሗላ ህጂና ከቤተሰብ ብር ሰርቀሽ ነይ ይላታል። ልጅቷም ሃብታም ቤተሰብ ስለ ነበሯት ሳጽን ሰብራ 60,000 ብር ወስዳ ከሰጠችው ብሗላ አፍኖ ወደ ትግራይ ወስዶ የሚፈልገውን ሁሉ ከፈጸመ ብሗላ ሆቴል ውስጥ ያስቀጥራታል። ለምን ስትለው ባለትዳር እንደሆነ ነግሮ ወደ አግርሽ ጥፊ ብሏታል። በቤተሰቡ ሊደርስ የሚችለው የልብ ስብራትና የሰላም መጥፋት ምን ሊሆን እንደሚችል ለእናንተ እተወዋለሁ። ህጻኗ እንዴት ወደ አገሯ መመለስ እንዳለባት እንኳን አታውቅም ነበር! የጭካኔው ብዛት ምክን ያቱ ምን እንደሆነ ባናውቅም ካስረከበችው 60 ሺ ብር እናኳን ለመሳፈሪያ የሚሆን ሰጥቶ ቢልካት ምን ነበረበት? ተመሳሳይ ችግር የደረሰባቸው ልጆች እግዚአብሔር ይቁጠራቸው። ታዳጊዎቹ አጋዥ የሌላቸውን ዲቃላ ህጻናትን እያስረከቡ ማህበረሰቡ ላይ ነገ አባቴን የሚል መርዝ ችግኝ እየተከሉ ይሔዳሉ፤ በጣም ያማል ወገኖቼ። የወልቃይት ጠገዴ ህዝባዊ ስብጥሩ በግድ ለመቀየር የሚአደርጉት ታሪክ ይቅር የማይለው ሴጣናዊ ድርጊታቸው ነው። የህዝቡን ህልውና የካዱ የሴጣን መንፈስ የሞላባቸው እርጉማን ሰዎች!!! በዚህ ጉዳይ በቅርቡ ዘግቤ አጋልጨ አስነብባችሗለሁ፤ ግፍን ማጋለጤን እቀጥልበታለሁ ከዛ ብሗላም ብሞትም እንኳን ሊቆጨኝ ደስ ብሎኝ ነው እምሞተው። ህዝቤንና አገሬን የሚታደግ ሰርቼ ስሞት ለእኔ የክብር ሞት ነውና!  ለመወሰን አንቸኩልም እንጂ ቆርጠን ከተነሳን ደግሞ ማን እንደሆንና ወደሗላ እንደማንል በደምብ ያውቁናል፤ ፈጣሪም ከእኛ  ከጭቁኖቹ ጋር እንዳለ በፍጹም መተማመን ላይ በሙሉ ልብ እንናገራለን። እኛ ግን ከህሊናችን ጋር ስላለን የማንነት ጥያቄው ይመልሳሉ ብለን አሁንም ቢሆን በትዕግስት እየጠበቅናቸው ነው፤ ካልሆነ ግን በኮሚቴው ላይና በህዝቡ ላይ እየፈጸሙ የሚያደርጉት  አፈናና ዛቻ ካላቆሙ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደምናመራ የተረጋገጠ እውነት ነው። ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሆይ የማንነት ጥያቄያችንን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመልሱልን እርዳታችሁ አይለየን።

4ኛ. ይሔን ሁሉ ፈተና አልፈው ዩኒቨርስቲ ወይንም ኮሌጅ ገብተው የተመረቁ አንዳንድ የወልቃይት ጠገዴ ልጆች በመንግስት ስራ አይመደቡም ቀደም ብለው የተመደቡትም መቶ በመቶ ማለት ይቻላል ከተመደቡበት ስራቸው ተባረዋል። የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሁሉ በአድዋ ልጆች አለፍ ካለም በአክሱም ልጆች ተተክተዋል። አንዳንድ በስራ የሚገኙ በዲፕሎማ ሙያ በአስተማሪነት ቢመደቡም እነዚህም ባሎቻቸው ፖሊስ ወይንም ስልጣን ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ከሆኑ ብቻ ነው።

አንዳንድ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ፖለቲካዊ ማግለሉና አስተዳደራዊ ጫናው ተቃቁመው ለመስራት ቢወስኑም ጫናውና ማስጠንቀቂያው ከባድ በመሆኑ ወይንም በራሳቸው ስራቸው ለቀው ያለስራ ይቀመጣሉ ወንም ደግሞ በአድዋና አክሱም አለቆቻቸው ይግባኝ በሌለው የስንብት ደብዳቤ ይሸኛሉ። አይ የመጣ ይምጣ ብለው ለመስራት ወስነው የነበሩ ጥቂት የመንግስት ሰራተኞችም ወንጀል ሰርተዋል ተበለው ማረሚያ ቤት የገቡም ነበሩ አሁንም ያሉ አሉ።

5ኛ. ከላይ በ ተራ ቁጥር 4 እንደነገርኳችሁ ማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤቶች መቶ በመቶ በአድዋና በአክሱም ተወላጆች የተያዙ ናቸው። እናም የተለያዩ አስተዳደራዊም ሆነ ግላዊ ችግር የደረሰባቸው የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች “የመንግስት ያለህ” ብለው ብሶታቸውን ለማሰማትና ፍትህ ለማግኘት ሲሔዱ ገና በንግ ግራቸውና በቋንቋቸው ለዛ ስለሚያውቋቸው እንኳን ብሶታቸው ሊሰሙላቸው ሌላ ችግርና ብስጨት መርቀው ይመልሷቸዋል። በጣም ተናዶ ለሄደ ወጣት ወይ ጎልማሳ ሰው በተካኑበትና ሴራ በተሞላበት መፍትሔ በሌለው “ችግሩን እናየየዋለን” ወይንም የኔ ቢጤ አቅም የሌለው ሰው ከሆነ ደግሞ በማፌዝ ፍትህ አጓድለው ህዝቡን እግዚአብሔር የሰጠውን ነጻነቱን ቀምተው በሓዘንና በቁጭት እንዲኖር አድርገዋል። የ80ና የ90 አመት አዛውንት በደረሰባቸው ችግር እንኳን ልጆቻቸውን ወክለው መክሰስና መሟገት አይችሉም፤ ነገሩ ከምነግራች ሁ በላይ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው።

ብዙ ግዜ “ለምን እንዲህ ይሆናል፤ ለምን እውነትን ትግደሏታላችሁ ተው ኧረ ተው ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ ይሔ ነገር አይጠቅማችሁም ለእኛም አይበጅ!!” ብለው የተናገሩ አባቶችና እናቶች ከዚህ መጣ በማይባል በፖሊስ ታፍነው ይጠፋሉ። ኧረ እንትና የት ገባ ሲባል ኧረ መቀሌ ማረሚያ ቤት እኮ ነው ያለው ይባላል ከሳምንታት ብሗላ። ማን ከሶት ታሰረ?  ለስንት ግዜ ነው የተፈረደበት? መልስ የለም። ኧረ ለመሆኑ ለምንስ እዚህ ቤተሰቦቹ ባሉበት አላሰሩትም? ኧረ እንዲያው ምንስ ብለው ነው ያሰሩት? አሁንም መልስ የለም። በነገራችን ላይ ቤተሰቦቻቸው እንዲጠይቋቸው የሚፈቀድላቸው አይሆንም።

6ኛ. አንዳንድ ባለቻቸው ንብረት በግላቸው በንግድ ስራ የሚንቀሳቀሱት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ገቢን መሰረት ያላደረገና በጣም ከፍተኛ የግብር ክፍያ አንዳንዴም ከጠቅላላ ካፒታላቸው በላይ የሆነ ክፍያ እንዲከፍሉ በማድረግ ከገብያ ውጭ ሆነው በብስጭት እንዲታመሙና ራሳቸውን እንዲያጠፉ ይደረጋሉ። ለገሚሶቹ ደግሞ መሰረትነት በሌለው የውንጀላ ስራዎችና ማስፈራሪያዎች ተደርጎባቸው የንግድ ስራቸው እንዲዘጉ ይደረጋሉ ይታሰራሉም። በዚህ መልኩ ከጨዋታ ውጭ ይደረጋሉ!! ከዛም ቤተሰቦቻቸው በሓዘንና በብስጭት እንዲሁም በእጦት ምክን ያት በአይነቱ ልዩ ልዩ ወደ ሆነ ስቃይ ገብተው እንዲኖሩ ይደረጋሉ።

እዚህ ላይ በወልቃይት ጠገዴ የሚሰሩት ከዚህ ጋር የተያያዘ ግፍ በጥቂቱም ቢሆን መንገር የግድ ይለኛል። በንግድ ሙያ የገቡ እነዚህ ሰፋሪ ትግሬዎቹ  በጣም ሃብታም ናቸው። ሃብታም የሚሆኑት ታድያ በወራት ውስጥ ነው፤ ግብር አይከፍሉም ልዩ ብድር ይመቻችላቸዋል። በአመት ውስጥ ከተማ ውስጥ ሶስት አራት ቦታ ላይ ቤት የሚሰሩና ባለመኪና ናቸው እነዚህ ሰፋሪዎች ናቸው። ወደ ጉዳይ እንመለስና እኒህ ሰፋሪ ነጋዴዎች ምን ያደርጋሉ ብትሉኝ ከላይ በጠቀስኩት አይነት ከፍተኛ የግብር ክፍያ የሚሰቃዩትን የወልቃይት ጠገዴ ነጋዴዎችን ጭንቀታቸውን ያዩና ቀረብ ብለው “አንተ ሞኝ ነህ እንዴ፤ለእኔ እኮ እንዳንተ ከፍተኛ ግብር ክፈል ብለውኝ ይሄን ያህል ለሻይ ይሁንህ ብየ ስሰጣቸው አንድ ሶስተኛውን ብቻ ነው ያስከፈሉኝ” በማለት ሹክ ብሎ ተወላጆቹ ሙስና እንዲከፍሉ ያበረታታቸዋል። ሌላ መንገድ እንደሌለ እቅጩን በዚህ መልኩ ይነገራሉ ፤ በህግ እሔዳለሁ የሚል ተወላጅ ካለ በተራ ቁጥር 5 የገልጽኩት ሂደት እንዳለ ስለሚያውቁ ለተደገሰላቸው የሙስና ጥያቄ ለዛውም ተሸማቀው እንዳይያዙ በመፍራት በጭንቅ ደጅ ጠንተው ህሊናቸው ሳያምነበት ከራሳቸው ጋር እየተጣሉ ይከፍላሉ። አብልግ ወይ በሰርግ የተዛመዳቸው ካለ ከእንደዚህ አይነት ስቃይ ነጻ ነው ግን እንዲህ ያደረጉ ትንሽ ተወላጆች ናቸው። ይህ ለምን ይደረጋል ብትሉ  ፈቅዶ ስለማይዛመዳቸው በግድ እንዲዛመዱት ለማድረግም ጭምር ነው። ዋናው አላማ ይህ ቢሆንም ከርሳቸውም ለመሙላትም ጭምር ነው እንጂ።

እንዲህ ከሚሉት የተወሰኑቱ  የሙስና በይዎቹ ቀንዳኛ ወዳጆች፣ ደላሎችና ተጠቃሚም ናቸው። ሌላው ከግብር ጋር በተያያዘ የሚሰሩት ድራማ ደግሞ ለሰፋሪዎቹ የትግራይ ተወላጆች “ይህን ያህል ብር በዚህ ግዜ ወደ ቢሮ ገቢ ካላደረክ ከዛሬ ጀምሮ የንግድ ስራህ ታሽጓል” ብለው ይዘጉቧቸዋል፤ ተመሳሳይ የንግድ ዘርፍና ካፒታል መጠን ያላቸው የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆቹንም እንዲሁ ካደረጉ ብሗላ የትግራይ ሰፋሪ ተወላጆቹን የግብር መጠን ግን ከፍ ያደርጉባቸዋል። እንዲህ የሚያደርጉት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ነጋዴዎች ግብር የመክፈል ችግር ኖሮባቸው ሳይሆን ያለምንም ድርድር ከፍተኛው የግብር ተመኑ እንዲከፈሉ ለማድረግ ነው፤ ከዛ የትግራይ ተወላጆች እየተጣሉ እየተጨቃጨቁ ከተወላጁ በላይ እንዲከፍሉ ካደረጓቸው ብሗላ ለትግራይ ተወላጆች ብሩ ይመለስላቸዋል።

እንዴ በጣም እኮ የሚአስደንቅ እኮ መአት ነው የተጣለብን፤ በሁለትና ሶስት ትራክተር ሲያርሱ የነበሩ ኢንቨስተር ተወላጆች በዚህ መልኩ ደህይተው ግብር የተተመነላቸው ከፍተኛ  ግብር መክፈል ብ አለመቻላቸው ወደ ሱዳን ሲሰደዱ በየወሩ በየቤቱ እየዞሩ የዉሃ ሒሳብ የሚያስከፍሉ የትግራይ ተወላጆች ደግሞ በአንጻሩ ባለሁለት ፎቅ ቤት አሰርተው አከራይተው ሲኖሩ ታያላችሁ በጣም አይን ያወጣ ኢኮኖሚያዊ ዘመቻ (economic ‘genocide’) እኮ ነው።

ተመልከቱ ወገኖቼ ከሞት ከእስራት የተረፉት የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ በምን አይነት ስቃይ ህይወታቸው እየመሩ እንዳለ። ከእነዚህ ሰዎች ጋር ነው 25 አመታቶችን ሙሉ የኖርነው፤ እነዚህ ሰዎች እኛን ትግሬ ናቹህ የሚሉን ማርና ወተት የምናፈልቅላቸው የሰውም የምድርም ከንዓን ስለሆንላቸው ነው እንጂ አማራነታችን እኮ ከኛ በላይ ሲመሰክሩልን ነው የኖረነው።

ታድያ እኛ ከእነርሱ ጋር ስንኖር ከሞቱት በላይ በዚች አለም ካሉት ሰዎች ሁሉ በታች ሆነን ነው!!!

7ኛ. የትኛውም አይነት ክፍት ስራ በመንግስት መስሪያ ቤት ካለ ብዙ ግዜ የስራ ማስታወቂያ ሳይለጠፍ ወገናቸውን ያስገቡበታል። የስራ ማስታወቂያ የሚለጠፍ ከሆነ ደግሞ ስራው ካለበት ከወልቃይት ጠገዴ ውጭ በትግራይ ከተሞች ነው የሚለጠፈው። አንዳንዴ ቀለል ላሉ ግዜያዊ ስራዎች ለምሳሌ ለጉልበት ስራ ኩንትራት እዛው አካባቢው ላይ ቢለጥፉም የሚላስ የሚቀመስ የሌለው በጣም ድሃ የተባለ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ሄዶ እንኳን አያመለክትም። የሆነ ግዜ ላይ ለእንደዚህ አይነት ስራ ሊያመለክት የሔደን የአካባቢው ተወላጅ ምን ልታደርግ ነው የመጣኸው ተብሎ በመዝጋቢዋ ተሹፎበታል። የቅጥር ዉሳኔው ከውድ ድሩ በፊት ማለትም ከምዝገባው በፊት በድፍረት እንዲህ ይናገራሉ!!! የትግሬዎቹ ጥጋብ እጅግ በጣም ልኩ ያለፈ ነው:: ይህን የሚያደርጉት እኛ ተማረን አገራችን ጥለንላቸው እንድንሔድ ነው። በነገራችን ላይ እጅግ በጣም አሳዛኝ ስግብግብ አንበጣዎች ናቸው።

8ኛ.  በወልቃይት ጠገዴ ተወላጅና ነገር ነገር በሚሸታቸው እንዳበደ ውሻ በሚክነፈነፉት የትግራይ ተወላጆች መካከል ተወላጁ ትዕግስቱ ተሟጦበት ችግር ከተፈጠረ ያለምንም ማጣራትና ያለምንም  ምንም ጥርጥር ለትግራይ ተወላጁ ስለሚፈረድለት ብዙ ግዜ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከእነርሱ ጋር በሰቀቀን ነው የሚኖረው፤ አመላቸው ራሱ የምትይዘው የምትጨብጠው አይነት ስላልሆነ ተወላጁ የቤተሰቦቹን ሰላም ለመጠበቅ ሲል ትንኮሳቸውን በመፍራት በጣም ርቋቸው ነው የሚኖረው። ለንግድና ለኑሮ የመጡ ትግሬዎች እንኳን ሲቪል ቢምስሉም አላማቸው ግልጽ ያልሆነ የፈርዖን አብጋዞች ናቸው። የሚደንቀኝ እርስ በርሳቸውም እንዲሁ ነው የሚበላሉት! አዎ ፍቅር የሚባል ነገር በመሃላቸው የለም፤ አንድ የሚሆኑት በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ብቻና ብቻ ናቸው። እናም የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በሃገሩ ወንጀል እንደሰራ አይነት ህዝብ ሆኖ እንደሁለተኛ ዜጋ በቁም እስር ነው የሚኖረው። ይህ በራሱ የሚያሳየው እነርሱ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እንደጠላታቸው ማሰባቸው ለወረራ መምጣታቸውና በግድ እኛን ትግሬ ለማድረግ ስላልቻሉ አላማቸው ባለመሳካቱ ምክን ያት የመጣ ንዴታቸው ነው፤  አማራነታችን ብንፈተንበታም ገና አንገታችን ቀና ብሎ ኮርተንበት በደስታ እኖራለን። አዎ አማራነት ወንጅል አይደለም አማራነታችን ይከበረልን!!!

9ኛ.  የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በአያቶቹና ቅድመ አያቶቹ የመሰረቷትን የሁመራ ከተማ ውስጥ ወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ማግኘት እንደትልቅ የምስራች የተቆጠረበት የግዜ ደፊ ላይ ነው የምንገኘው፤በቃ ያለነው ጥቂት ተወላጆችን ስንገናኝ በሓዘን ድባብ ሆነን ቆይ ግን ይህ ሁሉ ህዝብ በምን መልኩ ነው የጨረሱን ተባብለን እንላቀሳለን። ከዚህም የተነሳ ሰፋሪ ትግሬዎቹ የልብ ልብ ተሰምቷቸው ሁመራ የኛ ናት በማለት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅን ጸጉረልውጥ ይሉታል። ምናለ ሁመራን የሁላችን ነች ቢሉ እንኳ። በተለያየ ግዜ በተለያየ የኢትዮጵያ ቦታ በዋነኝነት ከአዲስ አበባና ጎንደር ቆይተው የሚመለሱ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆችን ሲያዩን “ፀጉረ-ልውጥ” አይተናል ብለው ለፖሊሶቻቸው በነፋስ ፍጥነት ሄደው ሪፖርት ያደርጋሉ። ፖሊስ ነን ባዮችም እኛን ተወላጆችን ይዘው “አንተ ማን ነህ”፤ “ከየት መጣህ”፤ “ለምን መጣህ” እያሉ ካዋከቡና የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች መሆናችንን ካረጋገጡ ብሗላ “አንተ የመስፍን ዘር” ፤ “አንተ የነፍጠኛ ዘር”  ብለው ያንገራግራሉ፣ ይሳደባሉ፣ ያስፈራራሉ፣ ይደበድባሉ እንዲሁም ያስራሉ። እንዲህ ስለሚያደርጉን ብዙ ግዜ ወደ ቤተስቦቻቸው የማይመለሱ ብዙ ናቸው። “ምን ሆንክ? ይህ እኮ ትግራይ ነው!” ይልሃል ፖሊሱ። በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው በአገራችን መኖሪያ እንጣ። በነገራችን ላይ በዚህ መሃል ያለ ውጣ ውረድና ወከባ ተዉት። ይህ እውነታ በሁሉም የወልቃይት ጠገዴ አካባቢ የነበረና አሁን ደግሞ በባሰ ሁኔታ ያለበት ችግር ነው። እኛ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ማንነታችን የሚያረጋግጡበት መንገድ በመታወቂያችን ሳይሆን ወላጆቻችና የሚታወቁ ቤተሰቦቻችንን ፖሊስ ጣብያ ጠርተን ካመጣን ብሗላ ነው። ይህ ጉዳይ ለእኛ ከፍተኛ የሆነ ስነልቦናዊ ስብራት ነው አብሶ ደግሞ ለወላጆቻችን!!! ይህ ችግር በቋንቋ ከምገልጸው በላይ በጣም በተቀነባበረ ሁኔታ ነው የሚፈጸመው። በልዩ ልዩ ስራና በትምህርት ምክን ያት ከአካባቢው ርቀው የቆዩ ሰዎች መታወቂያችንን ለማደስ የማንችልበት ሁኔታ ነው ያለው። ይህን የሚያደርጉት ህጋዊ ኗሪ አይደለህም ለማለትና ከአካባቢው እንድንለቅ ለማድረግ ታስቦ የሚፈጸም ዘግናኝ ድርጊት ነው።

በጣም አሳዛኙ ነገር ፖሊሶቹ በራሳቸው ለአካባቢው አዲስና በእነርሱ ቋንቋ ከዚህ በተያያዘ ታድያ በየቀኑ አዳዲስ የትግራይ ተወላጆች ማየት አዲስ ነገር አይደለም:: ተመልከቱ በእነርሱ የወረደ ኢትዮጵያዊ  ባልሆነ የዘረኝነትና ተስፋፊነት ቋንቋ እንድናገር አንዴ ፍቀዱልኝና “ፀጉረ-ልውጥ” እነርሱ ሆነው ሳለ እኛን ተወላጆቹን “ፀጉረ-ልውጥ” ብለው ያንገራግራሉ!!! የአካባቢው ተወላጆች ሌላው ቀርቶ 25 አመት ሙሉ የመኖሪያ ጎጇቸውን የሚሰሩበት ቦታ እንዲሰጣቸው እድሜ ልካቸው ጠይቀው ያልተሰጡ እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ሰፋሪዎች የትግራይ ተወላጆች ግን ተወላጆቹ ገና ስማቸው  እንኳን ሳያውቅ ከመኖሪያ ቤት ባለቤትነት በዘለለ በተለያዩ የልማት አደረጃጀት በሌላ አገላለጽ የፖለቲካ አደረጃጀት ተደራጅተው በወራት ውስጥ ሃብታም ሆነው የህዝቡ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው ማየቱና ከዚህ በላይ ደግሞ የፍትህ ማጓደላቸው ስራቸው ስትታዘቡ እንዴት ያማል መሰላችሁ።  በነገራችን ላይ የአካባቢው ተወላጅ የሆነ ማንም ሰው ወደ እንደዚህ አይነት አደረጃጀት እንዲገባ አይፈቀድለትም ህዝቡም ደግሞ በፍጹም መግባትም አይፈልግም።  ህዝቡን ተገልብጠው “አንተ ማነህ” የሚሉት እነዚህ የቀን ሃብታሞች  የሆኑ ዘራፊና ወራሪ “ኢትዮጵያውያን” ነን የሚሉ “የትግራይ ሰዎች” ናቸው። ግዜ አንገት ደፊ ያደርጋል፤ በእርግጥ የእኛ አንገታችን ብቻ ሳይሆን ስብእናችንንም ሕይወታችንም ለማስደፋትና ለመድፋት ጥረዋልም ይጥራሉም ግን ግን ከአሁን በፊትም አልቻሉም ከአሁን ብሗላም አይችሉም እንጂ። በዚህ ታላቅ፣ሀቀኛና ጀግና ኢትዮፕያዊ የጎንደር ህዝብ የሞራል ድቀት ለማምጣት ግን እንዲህ በብስጭቱ፣ ቁጭቱና ሃዘኑ ይስቁበታል ይሳለቁብታል።

10ኛ.  የህክምና አገልግሎት በአብዛኛው የኢትዮጵያ አካባቢ ከዛሬ 24 አመት ሲነጻጸር በተሻለ ደረጃ እንደሚገኝ ማንም ኢትዮጵያዊ የሚያስበው እውነት ይመስለኛል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ግን የህክምና አገልግሎት መዝጋት የህዝቡ ማለቂያ መሳሪያ ሆኖ ነው ያገለገለው፤ይህን መሰረታዊ ሰብ አዊ መብቱ ላለፉት 24 አመታት በትግራይ አስተዳደር እርምህ ይሁን ተብሏል።

ዛሬ የወልቃይት ጠገዴ  ህዝብ በአለም ተረት በሆኑ በሽታዎች እንደኩፍኝና ኮሌራ በየግዜው ህይወቱን ሲቀጥፉት ማየት የተለመደ ነው። በእነዚህና ሌላ ዉሃ ወለድ ሽታዎች በህዝቡ ውስጥ በወረርሺኝ መልኩ እየተነሱ የብዙ ህጻናትና አዋቂዎች ህይወት የሚቀጠፍበት አሳፋሪ ሁናቴ ነው ያለው።

የወልቃይት ጠገዴ እናቶች እጅግ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ በወሊድ ምክን ያት ከንህጻናቸው ጋር ይሞታሉ። ለ10,000 የትግራይ ሰፋሪዎች ሆስፒታል ተሰርቶላቸው አንቡላንስ ሲመደብላቸው ተወላጅ እናቶች ግን ህክምና ባለማኖሩ እንዲሁም መንገድ ባለ መኖሩ ምክን ያት በመንገድ በቃሬዛ ሳሉ ህይወታቸው ያልፋል። ይህ በትግራይ አስተዳደር በደምብ የሚታውቅ ግን ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። እንዲሁም የኛን ቤቶች ንብረቶች በሙሉ እየወረሱ ካስወጡን ብሗላ በአሁኑ ስአት 99.9% እነርሱ በተቆጣጠሯት ሁመራ ከተማ የቆየ ሆስፒታል ቢገኝም ህዝቡ በቀላሉ ሄዶ የሚታከምበት ሁኔታ አይደለም ያለው። ከዛ ገብተህ ለመታከም ብዙ ውጣ ውረድ አለበት እናም ለሰፊው ወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ግን ሆስፒታል ይቅርና አገልግሎቱን የሚወጣ የተሻለ ጤና ጣብያና ኬላ እንኳን የለውም። በእነዚህ የማይረቡ የሬሳ መጋዘን የሆኑ የጤና ድርጅቶች የሚገኙ የህክምና ባለሙያ ነን ተብዬ ሰራትትኖች እጃቸው የሚፈቱት በህዝቡ ስለሆነ የጠናበት ሰው ሲመጣባቸው ታዲያ ምን እናድርግህ አክሱም ወይ መቀሌ ሄደህ ታከም ይሉታል። እሺ በቃ እድሌን ልሞክር የሪፈር ወረቀት ወደ ጎንደር ጻፉልኝ ስንላቸው ‘አይ የሪፈር ወረቀት የምንጽፈው በትግራይ ወደሚገኙ ሆስፒታሎች የምትሄዱ ከሆነ ነው እንጂ ወደ ጎንደር የሪፈር ወረቀት አንጽፍም’ ይላሉ የራሳቸው ሰው በጠና ሲታመም ግን በአንቡላንስ ወደ ጎንደር ሪፈር አሲዘው ይወስዱታል። እኔ እንኳን በግሌ ቤተሰብ ታማብኝ  ህመሟ ሲጠናባት ‘ለምን ወደ ጎንደር ሪፈር አይጻላትም’ ብዬ የጠየኳት ባለሙያ ‘ህጉ አይፈቅደልንም’ ነበር ያለችኝ። ‘እንዴት ማለት’ ስላት ‘በቃአሰራሩ እንደዛ ስለሆነ’ አለችኝና በስጨት ብላ ‘ከፈልክ ለመንግስት መጠየቅ ትችላለህ’ ነበር ያለችኝ።ሰውኮ በጭንቀት ውስጥ ሆኖ ወደ ጎንደር ሪፈር ጻፉልኝ ብሎ ደጅ የሚጠናቸው ጎንደር ሆስፒታል ቅርብ ስለሆነ ነው እንጂ ሆስፒታሉ ህዝቡን በነጻ ስለሚያክም አይደለም።

በነገራችን ላይ እንዲህ የሚያናግሩት የጤና ‘ብሩካኖቹ’ ናቸው፤ አለዚያማ ሰው ኪሱ እስቲያልቅ ድረስ ወይንም ተስፋ ቆርጦ ሞቱን እስቲጠባበቅ ወይንም ደግሞ እስቲሞት ድረስ ‘ይሻልሃል’ እየተባሉ ስንቶቹ ወደ መቃብር እንደወረዱ የፈጠራቸው አምላክ ያወቃል ህዝቡም አይረሳቸውም እስከመቼውም ድረስ። እየሳቁ መግደል ይሉሃል ይሔን አይነቱን ነው።

ብር ያለው ተሎ ጎንደር ሄዶ ይታከማል፤ የሌለው ደግሞ ሞቱን ይጠባበቃል። የትግራይ ሰፋሪዎቹስ ብትሉኝ የወልቃይት ጠገዴ  በሚከፍለው ግብር ሁሉም ልጆቻቸውን ጨምሮ በነጻ ነው የሚታከሙት። እናማ የወልቃይት ጠገዴ በሽተኛ ግን ወገን ያለው ከሆነ ይህን ችግር ስለሚያውቅ ብር አዋጥቶ ወደ ጎንደር ወስዶ ሲያሳክም በብዛት ተዳክመው ስለሚደርሱ ወገኖቹ ሬሳ ወይንም ወደ ሬሳነት የቀረበ በሽተኛን ይዘው ይመለሳሉ። እና ህዝቡ ጎንደር  ሄዶ መታከም ማለት ሬሳ ሆኖ ከመመለስ ጋር ስላገናኘው በሽተኛው ስቃይ በዝቶበት ወደ ጎንደር ሊሄድ ነው ከተባለ የብሽተኛው ዘመዳሞችና ጎረቤታሞች በእንባ ተራጭተው ነው የሚሸኙት።  የሚገርመው ጉዳይ ታድያ እነኝህ የጤና ባለሙያ ነን ባዮች የትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን አባሎች ታድያ ልታምኑት ከምትችሉት በላይ ሃብታም ናቸው። ለምን ብትሉ ስራ ቦታቸው ሳይገኙ በአቋቋሙት የግል ክሊኒካቸው ድሃውና የጨነቀው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ወደ የመቃብር መጋዝን ክሊኒካቸው ስለሚጎርፍላቸው የጎንደር ሃኪሞች ከሚያስከፍሉት በላይ እያስከፈሉ አዎ በጣም ሃብታም ናቸው።

እነዚህ የጤና ባለሙያ ነን ባዮች እጅግ ስርዓተ ቢስ ናቸው። ለምሳሌ እንኳን ለመጥቀስ ያህል በወልቃይት ውስጥ በአዲረመጥ የሆነውን አሳዛኝ ክስተት ልንገራችሁ። ወላጅ አባት ዲያቆን ልጃቸውን ሊያገባ ስለነበር የዲያይቆኑ አባት ከዲያይቆኑ ልጃቸው የልጅቱ አባትም እንዲሁ ለጃቸውን ይዘው ለሁለቱ ኤች አይ ቪ ምርመራ እንዲደርግላቸው ለልጅቱ ደግሞ ድንግልናዋ እንዲረጋገጥ ወደ ጤና ጣብያው ይመጣሉ። የደም ምርመራ እንዲደረግላቸው ደም ከተወሰደ ብሗላ የልጅቱ ድንግልና ምርመራ የሚያደርገው የጤና ባለሙያ ልጅቱን ደፍሮ በመስኮት ዘሎ አምልጦ ሁመራ በማደር ከዛ ወደ ትግራይ ሄዷል። የልጅቱ ቤተሰብ ሃኪሙ በመዘግየቱ ተጨንቀው ለሌላ ሴት ሃኪም ነግረው ሃኪሟ ስታንኳኳ የሚከፍትላት ስላጣች በመስኮት በኩል ስት ሄድ ሃኪሙ የለም ልጅቱ ግን አለች። ከዛ ሁለት ሃኪሞች ገብቶ ህ በመስኮት ገብተው  ልጅቱን ሲያናግሯት ሃኪሙ እንደደፈራትና ወጥቶ ሲያመልጥ ግን ራሷን ስታ እንደነበር ተናገረች። ቀስም የሚሰብር ታሪክ በልጅቱና በሁለቱ ቤተሰብ እንዲህም በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ተደረገ። ሌላም በጣም ብዙ ተመሳሳይ ግር አለ። እንዲህ ያደረገው ሃኪም በትግራይ ውስጥ የፖለቲካ አመራር ውስጥ እስከቅርብ ግዜ በደቡብ ዞን እንደነበር እናውቃለን ይገኛል።

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በዚህ የጤና አገልግሎት ሰጭ ድርጅት እጦት ምክንያት የጎንደር ሃኪሞችን እንደነ ዶክተር ፍስሃ ያሉትን የተካኑ የበረሃ በሽታ ሃኪሞች እንዳደርጓቸው እነዚህ ሃኪሞች የሚያውቁ ይመስለኛል። ምንም እንኳን የህዝቡን ችግር ተረድተው ካላቸው በሽተኛ ብዛት የተነሳ በደምብ ባያክሙትም።

11ኛ. ታሪክ ነጋሪ ታላላቅ አዛውንት አባቶችንና እናቶችን በህይወት እንዳይኖሩ ገና ከጧቱ ብዙ አዛውንት አባዎራዎችና እማዎራዎች  ታፍነው ተወስደው ይሔው እስከዛሬ ድረስ መቃብራቸው እንኳን የት እንዳለ አልታወቀም። በአንድ ቀን እንኳን 43 አዛውንት ነበር ወስደው ያጠፏቸው።  ከ43 አዛውንት መጥፋት ብሗላም በፊትም ታሪክ የሚያውቁ የሱዳንን ታሪክ እንኳን ሳይቀር የሚተርኩ ሙስሊምና ክርስቲያን አዛውንቶች እየለቀሙ ደብዛቸውን ነው ያጠፏቸው። በህይወት እስከቅርብ ድረስ የነብሩትን ታሪክ አዋቂዎችንም “መስፍን ነበርክ”፤”ነፍጠኛ ነበርክ”፤ “የነፍጠኛ ሚስት ነሽ” ፤ “የነፍጠኛ አባት ነህ” እያሉ በዚህች ምድር በሰቀቀን እንዲኖሩ በማድረግ ፈጠሪያቸውን አሟሟታቸውን እንዲአይሳምርላቸውና የህዝቡን ስቃይ እንዲያይና በቃ እንዲል በጸሎት በማሳሰብ ነው ያለፉት። ወያኔዎች እንዲህ የሚያደርጉት ታድያ እሊህ አዛውንት በደል ኖሯቸው ሳይሆን አካባቢውን ትግሬያዊ ለማድረግ የሚያቀልላቸው ስለመሰላቸው ነው። በነገራችን ላይ እንዚህ የትግራይ ተወላጆች ሃይማኖት አላቸው፤ በፈጣሪ ያምናሉ ለማለት ለወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በጣም ይክብደዋል።

12ኛ. የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ለ25 አመት ባህሉን፣ዘፈኑን፣ ቋንቋውንና የአነጋጋአር ዘዬውን በግድ እንዲተው ተደርጎ በትግራይ ባህልና ቋንቋ እንዲተካው በክፈተኛ ዛቻና ስልታዊ አሰራር ተዘምቶበት ቆይቷል። ህዝቡ በትግራይ ትግሬኛ እንዲጽፍና እንዲናገር ካልሆነ ግን ምንም አይነት የመንግስት አገልግሎት እንዳያገኝ፣ ልጆቹንም እንዳያስተምርና ብሎም ከተወለደባት ወልቃይት ጠገዴ ለቆ እንዲጠፋ ተገዷል፤ እንዲወጣም መመሪያ ሲሰጠው ኖሯል። የወልቃይት ጠገዴ ልጆችም በትምህርት ቤት በግድ በትግሬኛ እንዲማሩ ተደርጓል። ስንቶቹ የአካባቢው ተወላጅ ተማሪዎች የትግሬኛ ትምህርት እንደወደቁ ትምህርት ቤት ይቁጠራቸው። አዎ አስተማሪዎቻቸው ይቁተሩዋቸው እንዳልል አስተማሪዎቹም ያው ነጻ አውጪ ታጋዮች ናቸው። በነገራችን ላይ በ25 አመት ውስጥ በወልቃይት ጠገዴ ከተመደቡት አስተማሪዎች አንድ ሴትና 3 ወንዶች አስተማሪዎች ጥሩ ሰዎች ነበሩ፤ ሃይማኖተኛም ነበሩ። ለእነዚህ ጥሩ አስተማሪዎች ጓደኞቻቸውና አመራሩ በጣም ያገሉዋቸው ነበር ምንም እንኳን በመጨረሻ የጽዋ ተራቸው ከወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጋር ብ አመሆናቸው ብቻ ለተለያየ አይነት ስቃይ ሰላባ ቢሆኑም እግዚአብሔር ውለታቸውን እንደሚካፍላቸው ግን እኔ በግሌ አምናለው። ከእነዚህ 4 አስተማሪዎች በተቀራኑ ደግሞ ስራን የሚሰሩ በዱላቸውም ተማሪዎችም የገደሉ አሉ፤ ይሔው ሁሉን ነገር ለእግዚአብሔር ሰጥተን ልጆቻችንን በዱላ መተው ከገደሉ፣ ከደፈሩ፣ አላግባብም ከትምህርት እንዲያቋርጡ ካደረጉ አስተማሪዎች ጋር እየኖርን ነው። ከዚህ ከወልቃይት ባህልና ዘፈን በተያያዘ ምልኩ ምንም አይነት የአማርኛ ዘፈን እንዲሰማና አዝማሪ እንዲታይ አይፈቀድለትም። ይልቁንስ አሸንዳን ሴቶቹ በጥቅማ ጥቅም አንታለልም አሸንዳ አንልም ቢሏቸው በግድ እንዲወጡ በማይክሮፎን እየለፈፉ በማስፈራራት ቅጣት እንዳለ ጀሯችን ያደነቁራሉ። ለአሸንዳና ጥጋቡ የእነርሱ ልጆች ይበቁ ነበር፤ እኛም ተሸማቀን  በየቤታችን ሆነን ቀን እስቲወጣልን ድረስ “እህህህ…እህህ”  እያልን መከታተሉን ባላቆምን ነበር። ተመልከቱ ወገኖቼ እንዴት በቁም እስር እንዳለን። የኛን ውቡ አማርኛ ባህላችን እየቀበሩ የእነርሱን በግድ ህይወት እንዲኖረው ይጥራሉ። በነገራችን ላይ በዚህ ፩ አመት የጀመሩት ሌላው አሳዛኙ ድራማ ደግሞ በሰርጋችና በማንኛውም ይደስታችንም የሃዘናችንም ግዜ የምናሳየው ባህላዊው የአማርኛ ዘፈንና ለቅሶ ተዘዋዋሪ በሆነ መንገድ በትግርኛ አድርጉት እያሉን ይገኛሉ።  “ሰርጉን በአማርኛ የደገሰ ማን ነው” በማለት ይሔን ባደረጉ አንዳንድ ተወላጆች የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ ልዩ ልዩ ግፍና ስቃይ መስራት ጀምረዋል። ተስፋፊዎቹ የዘራችን ማጥፋት (Genocide and Ethnic Cleansing) ብቻ ሳይሆን  የማንነታችን መገለጫ በሆነው ባህላችን ላይ የባህል ዘመቻ (Cultural ‘Genocide’ and Extinction) እየፈጸሙብን እንገኛለን። በዚህ አልበቃ ብሏቸው የድፍረታቸው ድፍረት ኑ በግ ውጡ ለውቢቷ ታላቂቱ  ትግራይ መወድስ አቅርቡ ይሉናል። አይ ግዜ እንድግዜ ያለ ድል አድራጊ ጀግና በአለም ውስጥ ማን ይኖር ይሆን። አማራነት ወንጀል ሆኖ እንዴት እንደሚያሰቃዩን ተመልከቱ።

13ኛ. ሌላው አሳዛኙ ድርጊት ደግሞ የወልቃይት ጠገዴ የአካባቢ ስሞች በትግራይ ከተሞች ስም፣ በትግራይ የአካባቢ ስሞችና ጀግኖቻችን ብለው የሚጠሩዋቸው ሰዎች ስም እንዲጠሩ የተደረገበት የክልሉ የአዋጅ ድራማ ነው። አንድ ምሳሌ ለመስጠት ያህል እንኳን ድሮ “እንዳይቀዳሽ” እየተባለ የሚጠራው  አሁን “ፍረወይኒ” ብለው አጋሜ በሚገኘው ከተማቸው ስም ጠርተውታል።   በወልቃይት ጠገዴ የሚገኙት የወንዞቹ፣ የተራሮቹ ፣የበርኻዎቹ፣ የትምህርት ቤቶቹ፣ የሽንተረሮቹና የከተማቹ ስሞች አጋዚ ፍሬ ስዋት ስብሓት አዲአህፈሮም ምናምን እየተባለ አዲስ ስም ተሰጥቷቸዋል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ በሌላ ጽሑፍ እመለስበታለሁ።

የአካባቢው ተወላጅ ከዚህ ከአዲስ ከተሰጣቸው ስም ውጭ አካባቢውን በድሮ ስማቸው ሲጠራ ቢሰማ “ትዕቢተኛ አምሓራይ” እና “ወዲ አድጊ” በማለት የሚጠብቀው የመልስ ምት ቅጣት አንድም ማታን ጨለማን ተገን አድርገው ይገድሉታል አለዚያ ደግሞ በፖሊስ የስድብና ማስጠንቀቂያ ወርጅብኝ ተሰጥቶት ከዚያ ብሗላ ምንም አይነት የመንግስት መስሪያ ቤት አገልግሎት እንዳያገኝ ተደርጎ ጥፋት ፈጽሟል ተብሎ ዘብጥያ እስኪወርድ ድረስ በአይነ-ቁራኛ ክትትል ይደረግለታል። የዚህ ሴራዊ አሰራር ድርጊት በጣም ያማል በቃ እበድ እበድ ይልሃል፤ በጣም ያሳዝናል። ፈጣሪ የያዘላቸው ጥፋት ስላለ ነው እንጂ እንዲህ በማድረግ የሚያጠፉን ከመሰላቸው በፍጹም የሚታሰብ አይደለም ይልቁንስ አብረን እንተላለቃታለን እንጂ። በዚህ በወልቃይት ጠገዴ ስም ሲኖሩ የትግራዩ የስምና የባህል ድባብም እያጣጣሙ አለማቸውን ያያሉ፤ ቆይ ግን አለማሰብ ነው እንጂ እስከመቼ ድረስ እንዲህ ሆኖ ይቀጥላል ብለው አስበው ነው።

14ኛ. የእያንዳንዱ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ የትውልድ ሃረጉና የአያቶቹ ታሪክ ይጽፋሉ፤ ታድያ ይሄን የሚደርጉት የህዝቡን ታሪኩና ቅርሱን ለትውልድ እንዲያሰተላልፉለት እንዳይመስላች ሁ። የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች የሚያስሩበትና የሚያሰቃዩበት ምክን ያት ሲያጡ በአባቱ፣ አባቱ ንጹህ ቢሆን በአያቱ፣ አያቱ ንጹህ ቢሆን በልጆቹ፣ በልጆቹ ንጹህ ቢሆኑ ባሉና በነበሩ አዝማዶቹ ሽፍታ ነበረ፤ መስፍን ነበር፤ ነፍጠኛ ነበር፤ ለትግራይ ህዝብ የነበረው አመልካከት እንዲህ እንዲያ እንደዛ እንደዚህ ወዘተርፈ ነበረ ለማለት ነው እንጂ። የአካባቢው ተወላጅም እንደዛ አልንበረም ወይንም እነርሱ እንደዛ ቢሆኑ እና እኔ ምን አደረኩ ሲል ድሮም አንተ የእነርሱ ዘር ሆነህ ለትግራይ ምን መልካም ነገር ይገኝብሃል፤ እንዴትስ ትግሬ ነኝ ብለህ እንድታምንና ልጆችህን ትግሬኛ እንድታስተምር እንጠብቃለን ይሉና አንዳንዱን በማስፈራራት ይለቁታል፤ ሌላውን ደግሞ ደስ ላላቸው ቀን ዘብጥያ ያወርዱታል። የታሰሩትን ለመጠየቅ የሚሄድ ዘመድ አዝማድና ወዳጅም ሁኔታቸው እየታየ ብዙ ስነልቦናዊ ሰለባ ይደርሰባቸዋል።

ሌላው ታሪኩንና ዝምድናውን የሚያጠኑበት አሳዛኝ ምክን ያት ስነግራች ሁ በጣም በከፍተኛ የልብ ስብራት ሆኜ ነው። ወልቃይት ጠገዴ አንድ ጎጂ ባህል አለ ደምነት የሚባል። ታድያ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ይህን ጎጂ ባህል የሚገራበት ሃይማኖታዊና ባህላዊ መንገድ በተሎ ዕርቅ መፈጸም ነው። ደምነት ውስጥ የገቡ ሰዎች ካሉ ዕርቅ ይፈጸማሉ፤ ከዕርቅ ብሗላ የገዳይ ቤተሰብ ከሟች ቤተሰብ ጋር በትዳር ይተሳሰራሉ ከዛም ደምነቱ ቀርቶ በፍቅር ይተካል ደሙም በቀሉም በዚህ መልኩ እንዲደርቅ ይደረጋል። ይህን ዕርቅ ያፈረሰ ወይንም በልቡ ለማፍረስ ያሰበ ወገን ካህናቱ ውጉዝ ከመአርዮስ ብለው በፍጹም ያወግዙታል። ከዛም ያን የገዳይ ቤተሰብ ሄዶ መግደል ራስን እንደመግደል ስለሚቆጠርና ቤተሰባዊ ፍቅርም ስለሚያሸንፈው ጊጂ ባህሉ ዘላቂ መፍትሔ ያገኛል ማለት ነው።

እናም አረመኔዎቹ ደም የጠማቸው የትግራይ ተወላጆቹ ግን ማን ከማን ቤተሰብ ጋር ያልተከፈለ/ያለተመለሰ ደምነት አለው የሚለውን ለማወቅ የእያንዳንዱ የወልቃይት ጠገዴ አዋቂ ተወላጅ ታሪክ ያጠናሉ። ይህን ካጠኑ ብሗላ በዕርቅ የቆመን ደምነት በተለይ ደግሞ ዕርቅ ያልተፈጸመለትን የደምነት እዳ ወያኔዎቹ አንዳቸውን ቤተሰብ ማጥቃት ሲፈልጉ ግዜ የትግራይ ተወላጆቹ በተለይም ፖሊሶቹ ሄደው የገዳይ ቤተሰብን የሟች ቤተሰብ እንደገደለው በማስመሰል ይግደላሉ። ይሔን ለማስመሰል በጥይት ከመቱት ብሗላ ተጠቂው ሰው ለመሞት እያጣጣረ ከሆነ ገዳይህ እኔ ደመኛህ እንትና ነኝ ብለው ድሮ እሱ ወይንም የእሱ ቤተሰብ የገደሉትን ሰው ስም ይነግሩታል ወይንም ደግሞ ቢሞትም ባይሞትም ማን ለምን እንደገደለው ወረቀት ጽፈው መልእክት ጥለው ይሄዳሉ። ከዚህ ይበልጥ ነገሩን በጣም አሳዛኝ የሚያደርገው ደግሞ በግልጽ የህግ አካል ሆነው ምስክር አቁመው የገዳይ የተባለው ቤተሰብን ደግሞ መጥተው ያስራሉ። የተገደለበት ቤተሰብ ደግሞ ውሎ አድሮ መግደሉ አይቀርምና ደግሞ ተመልሰው እነርሱንም እድሜ ይፍታህ ብለው ያስራሉ። በእንደዚህ አይነት አረመኔያዊ ስውር የሴጣን አሰራራቸው የወልቃይት ጠገዴ ጎጂ ባህሉን እያጠኑ ስንቱን ጀግና ጨረሱት መሰላችሁ። አሁን ግን ህዝቡ በከፊልም ቢሆን ስላወቀባቸው ቢአይንስ ለመግደል አይሯሯጥም ለዕርቁ እንጂ። ተመልከቱ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን እየደረሰብን ያለው ግፍን እልቂት። ይህ ሁሉ ሲሆን ታድያ እኛ ለእነርሱ ክፉ ሆነን ሳይሆን እንዲያውም ሲራቡ የምናበላቸው፣ሲጠሙ የምናጠጣቸው፣ ሲሰደዱ የምናስጠጋቸው፣ ስራ ቢፈልጉ ሰርተው የሚቀየሩብን፣ ሲያጡ የሚጠጉብን እውነተኛ እትዮጵያውያን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ነበርን። ለምን እንዲህ ይህ ሁሉ ግፍ እንዳደረሱብና እያደረሱብን እንዳለ በጥቂቱ ቢገባንም ለእኛ ግን እንደታላቅ መቅሰፍት ከመቁጠር ውጭ ለታላቂቱ ትግራይ ምስረታ ብለው ይሔን ሁሉ ግፍ በኢትዮጵያውያን ሰው ልጆች ማድረስ ምንም አሳማኝ አልሆነልንም።

15ኛ. የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አብሮ መኖርና አብሮ ተካፍሎ መብላት ለቸገረው ሰው መርዳትና የዋህነት ማህበረሰባዊ ባህሉ ነውና በወልቃይት ጠገዴ መጥተው ያለፈላቸው የትግራይ ተወላጆች ግን እውነትነትና መሰረት በሌለው በጥቅማጥቅም ተደልለው ህዝቡን በውሸት መረጃነትና ስለላ እያሰቃዩት ይገኛሉ። የእነዚህ ህዝቦች ባህሪ ምን አይነት በጣም እጅግ በጣም ለመረዳት ከባድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለእኛ አስገራሚ የህይወት እንቆቁልሽ ናቸው። ለህዝቡ ወዳጅ መስለው በውሸት መረጃ ስንቱን ንጹህ ተወላጅ እንዳስጨረሱት እነርሱ መቁጠር የሚከብዳቸው ይመስለኛል፤ በእርግጥ ለእነርሱ ቢከብድም ቤተሰቦቻቸው አንረሳቸውም ከዚህም አለፍ ሲል ፈጣሪያቸው ያውቃቸዋልና ደማቸው በፊቱ እየጮኸ ነው ግፋቸውን ትተው ለህዝቡ መበደሉን ካላቆሙ እርሱም መፍረዱ አይቀርም። ለምሳሌ ያክልም፦ በዳንሻ ከተማ የሚገኝ የታጋዮች የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ የዛሬው ኢንቨስተርና ደህንነት አቶ ተላ፤ የትላንትናው የስአትና ሬድዮ ጠጋኝ የዛሬው ኢንቨስተርና ደህንነት ወዲ ሃጎስ፣ የትላንትናው ባለፉል ቤት የዛሬው ኢንቨስተርና ዋና ደህንነት ወዲ ሃበሽ እንዲሁም በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እሟሃይ እናቱና ወንድሙን እየተረዱ በዚህ መልኩ አድጎ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ   የሂሳብ ባለሙያው ህዝቡ ያስተማረው የዛሬው ዋና ደህንነትና ነጋዴ ገብረግዚአብሔር ነጋሽ የሚጠቀሱ ናቸው። በዚህ ጉዳይ በንጹሃን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ግፍ የፈጸሙትን የጡት ነካሾችን አሳዛኝ ታሪክ የሚያጋልጥ ለእናንተው ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በቀጣይ በስፊው ይዘን እንመለሳለን።

16ኛ. የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ገጽታን አጥቁረው በወልቃይት ጠገዴ የማይኖሩና የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ሁሉ ያለ አንዳች ምህረት እንዲያሰቃዩ በማሰብ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጠላታቸው እንደሆነና ትግል ውስጥ እንዳሉ ለህዝባቸው ይስብካሉ። እኔ እንኳን ሽፍታ ብለው የገደሏቸውን የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆችን በአንድ መኪና ሁለት ሶስት መኪና አስረው ሲጎትቱ አይቼያለሁ፤ በመሃል ከተማ አምጥተው ከጣሏቸው ብሗላ ጭንቅላታቸውን በጥይት ሲያፈራሩሱት በአይኔ አይቻለሁ። እስከቅርብ ግዜ ድረስም ሳስታውሰው እጨናነቅ ነበር፤ አሁንም ይሔን ስጽፍ እንባዬን እየረጨሁ ነው። ማለት አይሲስ የሚባለውስ ከዚህ ውጭ ምን አደረገና። ብዙ ታሳሪዎች ናቸው ያሏቸውን የወልቃይት ጠገዴ ሰዎች በሩቅ ጫካ ወስደው ካሰሩዋቸው ብሗላ ጅብ እንዲበላቸው የተደረጉም ነበሩ በ1985/6። እዚህ ላይ ሳልጠቅስ ማለፍ የማላልፈው የአንድ ዘመዴ አሟሟት ልንገራቹህ። ሰውየው የ63 አመት ሃብታም አባወራ ነው። እና ጫካ ወስደው አሰሩት እኛም ጠፍቶ ስንፈልግ ስንፈልግ ካንድ የደረቀ እንጨት የሗሊት ታስሮ ትክሻው ላይ ሆኖ አንድ ትልቅ አሞራ ያንገቱን ስጋ እየዘነጠለው ነው ያገኘነው። ሌላም አንድ በጣም ሃብታም የነበር ዘመዳችንም ጎረቤታችንም ከብቶቹ ለማየት ወደበረሃ ሄዶ አራት እረኞቹ ጋር ምሳ ስአት ቁጭ ብለው ሳለ መጥተው ወሰዱት።   ብሗላ አመሻሽ ላይ ግን ሶስቱን እረኞች ከገደሉ ብሗላ አንዱ ያመልጣቸዋል። ለሰዉየውም ካንገቱ በታች ጉድጓድ ቆፍረው ከቀበሩት ብሗላ ከ700 በላይ የሆኑት የግዛ ራሱ ከብቶች በራሱ ላይ መልሰው መላልሰው ነዱበት። ከብቶች እየተጨነቁ ‘እምቧእምቧ እምቧ’ እያሉ ሲጨነቁና  እንስ ሳዊ ለቆሷቸውን እያሰሙ ሲበረግጉ ሊያመልጡ ያሉትን ከብቶችም ጭምር በጥይት ይጥሏቸው ነበር። የጌታቸው ጭንቅላት እንደሊጥ እየፈረጠ እንደማስቲካ ሽሆናቸው ላይ ተለጠፈ:: የተቀሩትንም ገሚሶቹ ወደ ሱዳን ገሚዞቹ ደግሞ ወደ ትግራይ ነዷቸው። የሁለቱም ሰዎች ስም ያልጠቀስኩበት ዋናው ምክኛት ለቤተሰቡ ደህንነት ብዬ ነው። እንግዲህ እሊህ የትግራይ ሰዎች ከእንሰሳ በታች የሆነ ልቦና ነው ያላቸው አረመኔ ናቸው እምለው ለዚህ ነው። እንግዲህ እኒህ ሰዎች ናቸው እኛን ትግሬ ናቸውና ከእኛ ጋር ይሁኑ የሚሉን፤ እጅግ በጣም የሚገርም ነገር እኮ ነው። የፌደረሽን ምክር ቤት እንግዲህ አሳልፎ ዘራችን እንዲጠፋ እነደማይተወን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ለነገሩ ተስፋስ ያለው በአንዱ በአዳኙ በኩል ነውና እርሱ ይርዳን። ኦ አምላቼ ምነው ምን በደልነህ ብለን እኛስ አናማርም ግን እባክህን ከንዚህ አላቀን ወደ ወገኖቻችንም ጨምረን::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና እንደዚህ ሁሉ እያደረጉ ለህዝባቸው ጥላቻን ቢያስተምሩዋቸውም በተለያየ ስራ ወይንም ዘመዶቻቸውን ጥየቃ በለው የመጡና ብሗላም ኗሪ የሆኑ አንዳንድ ደግ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ተወላጆች ከህዝቡ ኖረው ህዝቡን የተረዱ ሰዎች አይደለም ደሞዝ ተጨምሮልን በነጻ ለዚህ ህዝብ ብናገለግልስ፤ ምርጥ ህዝብ አይደል እንዴ፤ አገርቤት የሚወራውኮ እንደዛ አይደለም ተቃራኒው ነው የሚደመጡ አሉ። ታድያ ከእነዚህ ደግ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ተወላጆች እንዲህ ሆነው ቃላቸውን በዚሁ ንግግራቸው የሚያጸኑ በጣም ላጭር ግዜ ብቻ ነው፤ ለምን ቢሉ ጽዋቸው ከወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጋር እንዳይሆን ፖለቲካዊ ዛቻ ስለሚደርስባቸው ሳይወዱ በግዳቸው ሰልፋቸው ከማይመስሏቸው ከአረመኔዎቹ ጋር ይሆንና ህዝቡን እያዘኑ ሲበድሉ ይታያሉ። እነዚህ እንኳን በከፊል ያሳዝኑናል ቢያንስ የህሊናቸው እስርኞች ናቸውና። ሰልፋቸው ከእነርሱ ጋር ሆነው በተለያየ መልኩ ቢበድሉንም እንኳን የተሴረውን የሴጣን ምክር ለተጠቂው ህዝብ አንዳንዴ ሹክ ብለው የሚያስመልጡ ደግነታቸው ያልተለያቸው ጥሩ ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ ፈጣሪ ዋጋቸው እንደሚከፍላቸው አንጠራጠርም። በወልቃይት ጠገዴ ምድር ቸር የሆነ የትግራይ ተወላጅ ማግኘት ለእኛ በጣም ብርቅ የሆነን ሰዎች ነን።

17ኛ. ሌላው የወያኔዎቹና ሰፋሪ ትግሬዎቹ አሳዛኝም አብሳጭም ባህሪ ደግሞ ማንነታቸውንና በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ብሎም በኢትዮጵያው ያላቸውን አመለካከት የሚያሳየውን ነው። እነዚህ አረመኔዎች የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጠላት ብቻ ሳይሆኑ የተፈጥሮም ጠላት ናቸው።

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ለዘመናት እንደ አካሉ፣ እንደአይን ብሌኑና ውርሱ አድርጎ ጠብቆት የኖረውን ተፈጥሯዊ ሃብቶቹ ለምሳሌ እንደወርቅ፣ እጣን፣ ጥንታዊ ደኖችና እደሜ ጠገብ እጽዋቶች ከህዝቡ እጅ ተነጥቆ የተሰጡት ለሰፋሪዎቹ ናቸው። በእርግጥ እጣን ለተወላጁ ቢሰጥም አሁን ደግሞ ለሰፋሪዎቹ ለመስጠት እቅድ አውጥ ተው እየተንቀሳቀሱ ነው። ለምለሚቷ ጎጆ እያሉ የሚቋምጣትን ወልቃይት ጠገዴ ከአረንጓዸው ልማት ልፈፋና የዝርፊያው የመለስ ፓርክ መላ በተቃረነ ሁኔታ የረዥም እድሜ ባለጠጋ የነበሩትን ግ ርማ ሞገስ የተላበሱትን እጅግ በጣም ጥንታዊና አግርኛ እጽዋቶቿ በመቁረጥና በመጨፍጨፍ የግብርናው ባለሙያ እንኳን ሳይቀር ከሙያቸው በተቃረነ ሁኔታ በትግራይ ልዩ ልዩ ከተሞችና በአዲስ አበባ የሃብታም  የትግራይ ሰዎች ልዩ ልዩ ቤቶች መስሪያ ሆነዋል። ቀሪውም በየግዜው በመቶዎች በሚቆጠሩ  መኪኖች እያጓጓዙ በአዲግራት፣ በአድዋ፣ በአክሱም፣ በመቀሌና ሽሬ ይሸነሽኑታል ይቸበችቡታል። በዚህ ሃብታም ሆነው ወደ ከፍተኛ ኢንቨስተርነት የተሸጋገሩ የትግራይ ተወላጆች በጣም ብዙ ናቸው ቢሆንም ዝርዝራቸው ያለን የ193 ዘራፊዎች ግን ወንጀላቸው ከነሙሉ ስማቸውና አድራሻቸው ታሪክ እንደከተበው ሊያውቁት ይገባል።

ከእነዚህ ሰዎች በላይ ሰፋሪዎቹ በየቀኑ ከስራቸው ሳይቀር መዘው እያወጡ ስራቸው የሚቆፍሩ የአካባቢው ግርማ ሞገስ የነበሩ ደኖች ምስክር ይሁኑባቸው፤ በእውነት እንዚህ ሰዎች አገር አጥፊ ናቸው።ይህን ያልኩበት አስተሳሰብ ትግራይ ውስጥ ችግኝ ሁሌ ከመትከል ተቆጥበው አያቁም ቢሆንም አንድም ተራራ እንኳን በተከሉት እጽ መሸፈን አልቻሉም፤ እንዲህ ሲሆንባቸው በቃ ዝም ብለን እንተወውና የሚሆነውን እኝ ብለው ይሔው ይጠብቁታል አንድም እጽ ግን ሲወጣ አላየንም በቴሌቭዥናቸው ትግራይ ለመለመች ብለው እንደሚያሳዩን ከሆነ። እንዲህ በሆነበት ሁኔታ ታድያ ለምንድን ነው በወልቃይት ጠገዴ የሚገኘውን አዝማናትን ያሻገረን ደን የሚጨፈጭፉት። በእውነት ከንቱ ምቀኞ ናቸው፤ የህዝቡን ትግሬ ያለመሆን ሁኔታ ስለተረዱ ትግራይ እንዳልሆነ ስለሚያውቁ ነገ ጥለነው ለምንሄድ ብለው አማራውን ህዝብ የተበቀሉ መስሏቸው በተፈጥሮ ላይ ግፍ የሚፈጽሙ ዲንጋይነታቸውን የሚያሳይ የአረመኔ ግብራቸውን ነው የሚነግረን።

ለነገሩማ እንደነርሱ ነፍስና ስጋ ያለውን የሰው ህይወት ያላሳዘናቸው ስለተፈጥሮ እንዴት ሊያስቡና ሊያዝኑ ይችላሉ። ፈጣሪ አይፈቅደላቸውም እንጂ እንደየበርኻው እቅዳቸው እኮ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ጨርሰው አጥፍተው ወልቃይት ጠገዴ የትግራይ ቢአይደርጉ እንኳን ደኑ አሁንም ይጠቅማቸው ነበር ባይ ነኝ። ግን እነርሱ አይምሯቸው አርቆ የሚያስበው ለጥፋት እንጂ ለልማት አይደለምና ይሔንን እቅዳቸው የዋልደባ አምላክ እንደማይፈቅድላቸው ስለሚያውቁ የወልቃይት ጠገዴ ተፈጥሮ ይሔው እንዲሁ በቀላሉ ሲያጠፉት ነበር አሁንም ያጠፋሉ። ከታች እስከላይ ያው እነርሱ ስለሆኑ ህዝቡን እንኳን የተፈጥሮ ጸጋ ስጦታውን ህይወቱን እንኳን መታደግ ስላላቻለ ወልቃይት ጠገዴ ክዳኗን አውልቀው በባዶ ገላዋ ራቁቷን አቅሟዋታል። ለነገሩ ምን ይገርማል ኢትዮጵያን የምታህል ቅድስት ሃገርንስ ለአለም ልጆቿን ቸብቸበው እራቁቷን አቁመው ለዝሙት አየቸበቸቧት አይደል እንዴ። ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን ሆይ የነዚህ ግፋቸው ከሰው ልጅ ከቋንቋ በላይ ነው።

18ኛ. እያንዳንዷ የሚፈጽሟት ግፍ፣ የሰብ አዊ መብት ጥሰት፣ አፈናና ግድያ አንሰላስለው አቅደው  ስለሆነ ህዝቡ እንደጠቀየማቸው ስለሚያውቁ ከፍርሃታቸው የተነሳ ዝም ብለው ብድግ ብለው “ምንም አታመጡም፤ ገና ስታስቡት ልክ ትገባላችሁ፤ አሁንኮ ትላንት አይደለም ዛሬ ነው  መሸፈቻ ቦታ የለም፤ ኢትዮጵያ እንደሆነች በእጃችን ነች የትም አትገቡም ብትገቡም አታመልጡንም፤ አንድ ነገር ብትሉ እስከነ ልጆቻቹህ እንጨርሳቹሗለን” ብለው በድፍረት በአደባባይ በየስብሰባው ህዝቡን በስሜት ሆነው ይወርፋሉ ይናገራሉ። ኧረ እናንተየ  ሆይ ፈጣሪ ከሰው ልጅ ሲለይ የሰው ልጅ እንዲህ ከንቱ ይሆናልን? እናማ እንዲህ እያሉ ህዝቡን ስሜት ውስጥ እንዲገባና እርምጃ እንዲወስድ ይገፋፋሉ፤ እያንዳንዷን ቀን ያለመረጋጋት ህይወት እንዲኖረው ጠክንረው ሲሰሩ ይታያሉ። ህዝቡ ደግሞ ተንኮላቸውን ስላወቀ የአየር ሁነታው እስቲስተካከል ድረስ በተቻለው መጠን በትዕግስት በአርምሞ ለማሳለፍ ይሞክራል። ግን ዝምታው ደግሞ ብርድ ብርድ እስከሚላቸው ድረስ ሲያንቀጠቅጣቸው ታያላችሁ፤ የፈጣሪ ስራውና  ግብሩ እንዴት እጅግ ግሩም ነው። ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ሆይ በእርግጠኝነት የምነግራቹህ በወልቃይት ጠገዴ መጥታቹህ ለአንድ ቀን ብትውሉና ብታድሩ በጣም የሚያሰጠላና የሚያምምም ስሜት ይሰማችሗል። ኑና እዩት ብየ እናንተን ዉድ ወገኖችቸን አልረግማችሁም። በነገራችን ላይ የሌላ ብሔር ኢትዮጵያዊ በወልቃይት ጠገዴ ውስጥ እንዲኖር ቀርቶ ለቀናት እንዲገኝ አይፈቀድለትም። ለምን እንደሆነ ለእኛ እ ስካሁን ድረስ ግልጽ የሆነ ነገር የለንም።

19ኛ. በአካባቢው ማለት በወልቃይት ጠገዴ ምንም አይነት ሌላ አካል ለምሳሌ እንደ ግብረሰናይ ድርጅቶች፣ ጋዘጠኞች፣ በህዝቡ ሊቋቋሙ የሚችሉ ማህበራት፣ የሌላ ብሔር ያለው ኢትዮጵያዊ እንዲገኝ አይፈቀድም። እነዚህ የጠቀስኳቸው ነገሮች እጅግ በጣም በጥብቅ የተከለከሉ ናቸው። ሌላው ይቅር በተለያየ ስራ የወጡ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች እንኳን እንዲመለሱ አይፈቀድላቸውም።

እኛ ጋር ብትመጡና ብታስተዉሉት የተወላጁ ድባቡና መንፈሱ ሶሪያ ውስጥ በጦርነት መሃል ያላችሁ ያህል ነው የሚሰማችሁ። በአንጻሩ ደግሞ ትግሬዎቹ አንድን ከተማ መሉ በሙሉ ደምስሶ ድል አድርጎ የተቆጣጠረን ሰራዊት በሚመስል መንፈስ እዚህና እዚያ በደስታ ሲወራጩ ታዩዋቸዋላች ሁ። በጣም የሚያስገርም ነው፤ ወሬያቸው ሁሉና ደስታቸው የሚመነጨው ከአማራው ህዝብ የህዘን ድባብ ነው እንዴ የሚል ጥያቄ መልሱን አዎ ብላችሁ እንድትሄዱ የሚያደርግ ገራሚና አስጥሊታ ድባብ።

20ኛ. በአጠቃላይ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በፈርዖን አገዛዝ ስር ነው ያለው። ወያኔና ካድሬዎቹ የፈርዖንን አገዛዝ ከዛም በላይ ካለ እነዚህ አረመኔዎችን በሚገባ ይገልጻቸዋል  ምንም እንኳን ቢያንሳቸውም። እነዚህ የዘመኑ አዶልፍ ሂትለርና ስታሊን ናቸው። በእርግጥ ከፈርዖን የሚለያቸው አንድ ነገር አለ። አዎ ፈርዖን እስራኤላውያንን ያስጨነቀው በሀገሩ ነው፤ ግብጽ ድረስ ሄደውበት ነው የዘመኑ ፈርዖኖች ወያኔዎች ግን የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ በአጠቃላይ ደግሞ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደፈርዖን የሚያስጨንቁት በሀገሩ ነው።

21ኛ. ቢሆንም አዎ ቢሆንም ጀግናውና ቆራጡ የወልቃይት ጠገዴ የጎንደር ህዝብ ግን የተደገሴትን የሞት ጽዋ ለ36 አመታት እንደኢየሱስ ክርስቶስ ሞቱን እየተጎነጨ ቃሌ አንድ ነው፤ እውነት አይቀየርም ይላል። አሁንም እንዲህ ሆኜ ህያው ሆኜ ኢትዮጵያን እታደጋለኡ ይላል። ምንም እንኳን በሞት ቀይ ባሕር መካከል ለማለፍ ለ36 አመታት ወደ ቀይ ባሕር ፊት ለፊት ለመቆም ሲጓዝ ቢቆይም አሁን ከቀይ የሞት ባሕር ተፋጦ ቆሟል።  ሙሴን ወክሎ ይሔን የሞት ባሕር የሚባርክ የኢትዮጵያ ወገኖቹን ትእዛዝ እንዲሰጥ ይሔው በተጠንቀቅ ቆሞ ይጠብቃል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጠላቴ ሆይ ደስ አይበልህ ይሔው ህያው ነኝ ህያው ሆኜ እየተሻገርኩኝ ነው አለ። ሰልፉ የሁላችን ነውና ኑ ተቀላቀሉኝ ይላችሗል፤ “አዋጅ!”“አዋጅ!!”“አዋጅ!!!” ኑ ህያው ሆነን እንሻገር ይላችሗል። አዎ “አዋጅ!”“አዋጅ!!”“አዋጅ!!!”…….ጀሮ ያለው ይስማ፤ ልብ ያለው ልብ ይበል!!!…..የሞት ሰማያዊ ያይደለ  ቀይ ባሕሩን ተሻግረን ወደ ነጻነትና ፍትህ የሞላባት አገር  በደስታና በአንድነት ተሰባስበን ኑ በሓሴት እንዘምር ይላችሗል። ፈርዖን ታሪክ እንደሆነ አረመኔው ወያኔና ህዝባዊ ያልሆኑት ካድሬዎቹም ታሪክ ይሆናሉ። ኢትዮጵያ ለዘላለም ከልጆቿ ጋር በሰላም በክብር ትኑር፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፤ አሜን።

ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ አንዳንድ ነገር በጥልቀት ለመረዳት “የማያልቀው ወያኔያዊ_የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ስቃይ” የሚለውው ንጽሑፍ ከwelkait.com ወይንም ecad forum.com ድረ ገጽ እስቲ አንብብሉኝ።

በዚህ ጉዳይ በባለፈው መጣጥፌ ላይ ካሰፈርኩት የለቅሶ ጽሑፍ እስቲ ቀንጨብ አድርጌ እስቲ ላስነብባችሁ። አንድ የወልቃይት አባት የተናገሩት ነው።

እነዚህ ሰፋሪ ነን ወራሪዎች ለወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እጅግ በጣም የመረረና የከረረ ያላቸው ናቸው። ወያኔ ለስንት ግዜ በምን አይነት ዘዴ ለምን አላማ ኮትኩቶ እዚህ ደረጃ ለደረሰ አመለካከት እንዳደረሳቸው እግዜር ብቻ ነው የሚያውቀው።

በገዛ ሃገራችን ሁሉን ነገር አሳጡን የቀራችው ያችው ማንነታችን ለመዝረፍም ይሔው አሁንም ያሰቃዩናል፣ያስሩናል፣ ይገድሉናል፣ ያሳድዱናል፣ ይደበደቡናል ፤ ሴቶቻችንን ይደፍራሉ።  እንኳንስ አማራ ሆነን ወደ ፈለግነው መሆን ምርጫው የኛው አይደል እንዴ? ለምንድን ነው የሚያሰቃዩን። ይህ ሁሉ ግፍ የሚደርስብን አማራ በመሆናችን ብቻ ነው፤ ዘር ወንጀል የሆነበት አገር በዚህ መንግስት በኢትዮጵያ ብቻ:: አሁን ደግሞ ትግሬ ነን ካላላችሁ ይሔን አገር ለቃችሁ ጥፉ ይሉናል፤ አይ የእግዜሩ ትዕግስት። በትዕግስት እንደቆየነው አንልም እንጂ በጄ እሺ ትግሬ ነን ብንል እንኳ በሕይወት እንደማያስኖሩን በደምብ እንረዳለን፤ ወገን ምነው ኢትዮጵያ እንዲህ ስቃይ ሞላባት?

እሊህ አባት ይህ “አልበቃ ብሏቸው ደግሞ ” ይላሉ “የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በግድ ትግሬ ነን በሉ እያሉ በየቤታችን እየዞሩ ያስፈራሩናል” ይላሉ….“ከእንግዲህስ እንተላለቅ እንደሆን እንጂ በቀረችን አንዷ ሃብታችን በማንነታችን እንኳ ከንግዲህ ብሗላ አንደራርደርም” ብለው ማስጠንቀቂያ ያዘለ ሃሳባቸውን ይገልጻሉ።

በመጨረሻም እሊህ አባት  “እግዚአብሔር ስቃዩና ስቅላቱ በቃቹህ ብሎን ከወገኖቻችን ጋር በሰላም የምንኖርበት ግዜ ያምጣልን” በማለት የጥልቅ ሃዘናቸውን መርሻ የሆነውን ተስፋቸውን በቃላቸው ገልጠዋል።

እባክዎ ይህቺን ጠቃሚ ጽሑፍ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን እንድትዳረስ በማድረግ የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ ዘር መጥፋት እንዲቆም የማንነት ጥያቄው እንዲመለስለት ይረዱን ዘንድ በዋልደባው አምላክ በትህትና እንጠይቃለን። ፈጣሪ ውለታዎትን ይክፈል!!!

ሰላም ሁኑ፤ የዋልድባ አምላክ ቸር ወሬ ያሰማን!!!

አንበሳው የመይሳው የቴዎድሮስ ዘር  ወልቃይት ጠገድቼው ነኝ

ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር ፤ጎንደር  ኢትዮጵያ

19 መጋቢት 2008 አ/ም

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s