አስደናቂና እጅግ አስገራሚ የሱርማዎች ፎቶግራፎች

(ሳተናው) በደቡብ ኢትዮጵያ ምዕራባዊ ክፍል የኦሞ ወንዝን በመታከክ በአረንጓዴ በተሞላ ጫካ ውስጥ ለምለሙ ምድራቸው ከሚያበቅለው እየበሉ አረንጓዴውን ሳር ለውበትና ለጸሐይ መከላከያት እየተጠቀሙ የሚኖሩ ዜጎች ይገኛሉ፡፡

የሱርማ ማህበረሰብ ከሱሪና ሙርሲ ጎሳዎች የተገኘ ነው፡፡ይህ ማህበረሰብ ለውበትና ለሴቶቹ ማንነት በሚጠቀመው የከንፈር ላይ ጌጥ ተለይቶ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የአገሪቱ መንግስት በሚኖሩበት አካባቢ ግድብ መገንባት በመጀመሩ፣ብሄራዊው ፓርክ እንዲስፋፋ በመደረጉና መሬቶቻቸውን ለኢንቨስተሮች መስጠት በመጀመሩ ከተከሰተው ድርቅ ጋር ተያይዞ ማህበረሰቡ እየተበታተነና እየጠፋ ይገኛል፡፡

ማህበረሰቡ ከመጥፋቱና በዚህ ቦታ እንዲህ አይነት ህዝብ ይኖር ነበር ተብሎ ከመነገሩ በፊትም የዴይሊ ሜይል የፎቶግራፍ ጋዜጠኛዋ ሉዊሳ ሴቶን ይህንን አስደናቂ ማህበረሰብ በምስልና በተንቀሳቃሽ ምስል ለማስቀረት ወደ ስፍራው በማቅናት የምንመለከታቸውን ፎቶግራፎች አንስታለች፡፡

በናይሮቢ ኬንያ መወለዷ የሚነገርላት ጋዜጠኛዋ በአሁኑ ወቅት የምትኖረው በአውስትራሊያ ሲዲኒ ከተማ ነው፡፡ባለፈው ዓመት ከሱርማ ማህበረሰብ አባላት ጋር ወደ ኢትዮጵያ በማቅናትም ረዘም ላሉ ወራቶች በሱርማ ቆይታ በማድረግ ሐመሮችን ጭምር በካሜራዋ ቀርጻ አስቀርታለች፡፡

የኢትዮጵያ ቆይታዋንና ፎቶግራፎቿን በማስመልከት ለሲኤንኤን በሰጠችው አስተያየት ‹‹ወደ አፍሪካ የሚመጡ የፎቶግራፍ ባለሞያዎች በአብዛኛው የሚያተኩሩት በአህጉሪቱ ባለው ርሃብ፣ጦርነትና ትግል ላይ ነው፡፡እኔ ግን የእነዚህን አስገራሚ፣ጠንካራና በጣም የተከበረ ህዝብን ውበት ማሳየትን ምርጫዬ አድርጌያለሁ››ብላለች፡፡

ምንጭ ዴይሊ ሜይል

surmaሱ1ሱ2ሱ3ሱ4ሱ8ሱ7ሱ10ሱ11ሱ12

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: