የህወሀት ኢህአዴግ ፖሊሲ ወጣቱን ወዴት እየወሰደው ነው?

 

UNiversity students

tplf

| ኤድመን ተስፋዬ

ከአፍሪካ አጠቃላይ ህዝብ ከ60 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው ከ ሰላሳ አምስት አመት በታች በሆነ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ እንደ መሆኑ አንባገነናዊ ስርአትን ከአፍሪካ  ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ወጣቶች ላይ ትኩረት ማድረግ የውዴታ ግዴታ ነው፡፡ ይህን የተናገሩት የዘር ሀረጋቸው ከጎረቤት ኬኒያ የሚመዘዘው የመጀመሪያው ጥቁር የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ባራክ ኦባማ ናቸው፡፡ ፕሬዝዳንት ኦባማ  ከላይ የጠቀስኩትን ቁጭት አዘል የሆነ ንግግራቸውን ከንግግር ባለፈ ተግባራዊ ለማድረግ መንግስታቸው በነደፈው ፖሊሲ መነሻነት  እ.ኤ.አ በ2012 ከመላው አፍሪካ ለተውጣጡ ስልሳ ለሚሆኑ ወጣቶች ከአመራር ጋር የተገኛኘ ስልጠና  በአሜሪካ እንዲከታተሉ አድርገዋል፣እያደረጉም ነው፡፡ እንደ አሜሪካ የስለላ ተቋም ሲአይኤ የመረጃ ቋት ከሀገራችን አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ውስጥ 64.3 ፐርሰንት የሚሆነው ከዜሮ አመት እስከ ሀያ አራት አመት በሆነ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ የእድሜ ክልሉን ከ 0 እስከ ሰላሳ አምስት ክልል ውስጥ ከፍ ስናደርገው ደግሞ አሃዙ ወደ 74 ፐርሰንት ይደርሳል፡፡ ይህም የሚያሳየን  ሀገራችን በወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህዝቦች በብዛት የሚኖሩባት ሀገር እንደሆነች ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ከአጠቃላይ የሀገራችን ህዝብ አብዛኛው በወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ እንደመሆኑ ሀገራችንን በየአምስት አመቱ በሚታደስ የምርጫ ውል እያስተዳደረ ያለውን ኢህአዴግን ፖሊሲዎቹን መነሻ በማድረግ   የወጣቱን ተጠቃሚነት እንዲሁም ወጣቱ ትውልድ የሀገሪቷ ሀብት ክፍፍል ላይ ተገቢውን ድርሻ ስለማግኘቱ ወጣቱ ትውልድ በኢኮኖሚ ስርአቱ ላይ ያለውን ተሳታፊነት መነሻ በማድረግ ማየት ተገቢ ይመስለኛል፡፡

ገዢው ፖርቲ ኢህአዴግ ወጣቶችን ማእከል ባደረገ መልኩ ያደረገውን እንቅስቃሴ በተመለከተ በዋኛነት የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋፋቱ እና የስራ እድል መፈጠሩ ላይ ትኩረት ባደረገ ምልኩ የሚገልፅ ሲሆን፣ በዋነኛነትም አስፋፋዉት የሚለው የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር እንዳለ ሆኖ የዩኒቨርስቲዎችን ማስፋፋቱን፣የሞያ እና ቴክኒክ ት/ም ቤቶችን ማስፋፋቱን እና በጥቃቅን እና አነስተኛ ወጣቶችን በማደረጀት ወጣቱን  የንብረት ባለቤት ማድረጉን ለማሳያነት ያቀርባል፡፡ እንደ እኔ እምነት ትልቁ ጥያቄ ገዢው ፖርቲ የሚለፍፈለትን  ወጣቱን ተጠቃሚ የሚያደርግ እና ያደረገውን ፖሊሲው  ነባራዊ የሆነ የሚታይ ለውጥ በብዙሀኑ ወጣት ላይ አምጥቷል ወይ የሚለው ሲሆን፣ ይህንንም  ለመፈተሸ ኢህአዴግ አስፋፋውት የሚለውን ዩኒቨርስቲዎችን፣ የጥቃቅን እና አነስተኛ ፖሊሲውን ወጤት እና ምንን መሰረት አድርጎ እንደተዋቀረ ግልፅ ያልሆነውን የፌደራሊዝም ስርአትን  ማእከል በማድረግ ማየት ተገቢ ይመስለኛል፡፡

ወጣቱን ተምሮ ስራ ፈት ያደረገው ኢህአዴግአዊ ፖሊሲ ለስራ ፈጣሪነትስ ምቹ ነው?    

ገዢው ፖርቲ በሀገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለብዙሀኑ ወጣቶች ተደራሽ እንዲሆን አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎችን በመክፈትም ሆነ ነባሮቹን በማስፋፋት  አስፋፋውት የሚለውን የዩኒቨርስቲ ትምህርት በነባራዊነት በትውልድ ተጋሪዬ ወጣት ላይ ያመጣውን ለውጥ ለማየት የስራ እድልን፣  የወጣትነት ባህሪን እና የማሰብ ነፃነትን ማእከል በማድረግ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ወጣትነት የእድሜ ክልል ራስን ከመቻል፣ቤተሰብን ከመርዳት ጋር ተገናኝ የሆኑ ፍላጎቶች የሚንሩበት እንደመሆኑ የከፍተኛ ተቋም ትምህርትን ለወጣቶች ተደራሽከማድረግ እኩል ታሳቢ መሆን ያለበት የስራ እድል የመሆኑን ሁነት እንደ ማርክ ዴን ያሉ የባህሪያዊ ኢኮኖሚደስቶች (Behavioural Economist) ይገልፃሉ፡፡ ሊዊንስተን በበኩሉ ከስራ እድል እና ራስን ከመቻል እና ቤተሰብን ከመርዳት ጋር የተገናኙ ፍላጎቶቹን ለማሳካት በገበያው ላይ ስራ ፈላጊ የሆነ ወጣት  ስራ ከማጣት ጋር በተያያዘ ለአይምሮ መታወክ እና ለድብርት ተጋላጭ የሚሆንበት እድል ከፍተኛ ስለመሆኑ ይተነትናል፡፡

እንደ ወጣት በዩኒቨርስቲ በሚኖረው ቀይታው በመጀመሪያ በነፃነት የሚማርበትን ስርአት መዘርጋት እና  ማመቻቸት የመንግስት ግዴታ ሲሆን ሲቀጥል ደግሞ በተማረው ሞያ ተቀጥሮ እንዲሰራ የስራ እድል ፈጣሪ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን በግብርናው፣በኢንደስትሪው እና በአገልግሎት ዘርፉ ከግል ባለሀብቱ ጋር በመተባበር መከወን ሌላው ግዴታው ነው፡፡ በእኔ እምነት ዋናው ቁምነገር ዩኒቨርስቲዎችን ከማስፋፋት ጎን ለጎን ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ለሚወጣው የስራ እድል መፍጠር እና ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ስርአት ማመቻቸት እንደመሆኑ ኢህአዴግ አስፋፋዋቸው እና አዲስ ከፈትኩአቸው ከሚለው ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው የሚወጡ የትውልድ ተጋሪዬ ወጣቶች በተማሩት ሞያ እንኳን የሀገራቸውን ችግር ሊፈቱ የራሳቸውን ችግር ሊፈቱ እንዳይችሉ ኢህአዴግአዊ ፖሊሲዎች ጋሬጣ ስለመሆናቸው መሞገት የሚቻል ይመስለኛል፡፡

 

ከየትኛውም የእድሜ ክልል በተለየ ወጣትነት ነፃነትን የሚፈልግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወጣት ትውልድ እምቅ ችሎታውን ተጠቅሞ የሀገሩንም ሆነ የራሱን የኑሮ ችግር ለመፍታት የሞያ ነፃነት ይፈልጋል፡፡ ኢህአዴግ አመጣውት የሚለውን የኢኮኖሚ እድገት ነባራዊነቱን፣ የዲሞራሲያዊ ስርአት በሀገራችን ለመተግበር ኢህአዴግ እስኬት ድረስ ይሄዳል፣ መንግስታዊ ሌብነት እና ሀገራዊ መመዙ ወዘተ  የሚሉ ጉዳዮችን ወጣቱ በዩኒቨርስቲ ቆይታው ሀገራዊ በሆነ ጥናት ከመፈተሸ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ፍላጎቱ ኢህአዴግ እንደ መንግስት  ድጋፍ  ያደርጋል ወይ የሚለውን መነሻ አድርገን ስናይ አንድ ለ አምስት  የሚለው የፖርቲው የጥርነፋ ስርአት በዩኒቨርስቲዎች ስርመስደዱ እና ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ስራ ለማግኘት ከዲግሪ ይልቅ የፖርቲ አባልነት መታወቂያ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑ በራሱ ከላይ የጠቀስኩትን ለመከወን መንግስታዊ እንቅፋት ስለመኖሩ አሳይ ከመሆኑም በላይ   የትውልድ ተጋሪዬ የሆነው ወጣቱ ትውልድ በዩኒቨርስቲ ቆይታው በነፃነት  የሀገሩን ችግር ከሞያው አኩአያ ለማየት ኢህአዴግአዊ የፖለቲካ ተግዳሮቶች እንቅፋት ስለመሆኑ አሳይ ይመስለኛል፡፡

በሀገራችን ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ የወጣ ወጣት ዲንጋይ ጠራቢ እና አስጠራቢ በሆነበት፣ ከዩኒቨርስቲ ተመርቃ የወጣች ወጣት ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል አልጋ አንጣፊ በሆነችበት ሁናቴ እንዲሁም በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ  ብርን ማእከል በማድረግ ማህበረሰባዊ እና ሀገራዊ ዋጋ በማያውቅ ነፈዝ ብራም የወሲብ ማስተንፈሻነት ገላዋን እስከ መስጠት የሚደርስ ተስፋ አስቆራጭ ሁነት ውስጥ እንድትገባ መንስኤው ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ከመውጣት በሁአላ በሰራተኛ ገበያው ያለው ተስፋ አስቆራጭ ሁናቴ መሆኑን በመጥቀስ ኢህአዴግ አስፋፋውት የሚለው ዩኒቨርስቲ   ለወጣቱ ያተረፈው ድብርትን እና ለአይምሮ መታወክ ተጋላጭነትን ስለመሆኑ  አሳይ ይመስለኛል፡፡

ገዢው ፖርቲ ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ስራ አጥ የሆኑ ወጣቶችን በተመለከተ በሚመስል መልኩ ብዙን ጊዜ ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ የሚወጡ ወጣቶች ከመንግስት ስራ ከሚፈልጉ ስራ ፈጣሪ መሆን እንዳለባቸው ይናገራል፡፡ በእኔ እምነት ገዢው ፖርቲ ስለ ስራ ፈጠራ ሲያወራ የዘነጋው ነገር ወጣቱ ስራ ፈጣሪ እንዲሆን  ዋናው ቅድመ ሁኔታ ነፃነት  መሆኑን ነው፡፡ ከዩኒቨርስቲ ተምሮ ባገኘው እውቀት ሀገሩን ለመርዳት በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ለመስራት በውስጠ ታዋቂነት ከትምህርቱ ይልቅ የኢህአዴግ አባልነት መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠለት ወጣት ስራ ፈጣሪ ሆኖ በኢኮኖሚ ስርአቱ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን  እዛም ቤት እሳት አለ እንዲሉ ፖለቲካዊ ወገንተኝነትን ማእከል ያደረገው ኢህአዴግ የሚመራው የሀገራችን የኢኮኖሚ ስርአት ላይ ወጣቱን ትውልድ ውድ የሆነውን ነፃነቱን ካልገበረ በቀር በመንግስታዊ ድጋፍ (ብድር፣የስራ ቦታ ማመቻቸት ወዘተ) መነሻነት ተሳታፊ የመሆኑን ነገር አስቸጋሪ ማድረጉ በእኔ እምነት የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ አመላካች ከመሆኑም በላይ ወጣቱ እንደ ትውልድ በተጋረጠበት መንግስታዊ ዳራ የተነሳ ዳራውን የጋረጠበት መንግስት ላይ እንዲዞር መንስኤ የሚሆን ይመስለኛል፡፡

ህወሃት ራሱን በራሱ ሸንጎ አስገምግሞ የእጁን ደም ሊያጸዳ ነው

 

337በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

የኮሚሽኑ ሪፖርት በኢህአዴግ ጽ/ቤት መሰራቱ ተጠቆመ

ህወሃት በኦሮሚያና በአማራ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸመውን ወንጀልና ርህራሄ አልባ ግፍ ራሱ አጣርቶ፣ ራሱ አጠናክሮ፣ ራሱ በፈጠረው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አማካይነት አቅርቦ፣ በራሱ ሸንጎ በማጸደቅ እጁን ከደም ሊያጸዳ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ለሪፖርቱ ማዳመቂያ የምስል ቪዲዮዎች መዘጋጀታቸው ታወቀ።

በኦሮሞና በአማራ ህዝብ ላይ የተወሰደውንና እየተወሰደ ያለውን የኃይል ርምጃ አስመልከቶ ድራማ እየተሰራ ነው ሲል የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪ ሪፖርተር የኢህአዴግ ጽ/ቤት ምንጮቹን ጠቅሶ ነው ስለ ሁኔታው የዘገበው። ህወሃት በአዋጅ ያቋቋመው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መሪ ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር ቀደም ሲል በጉዳዩ ዙሪያ ሪፖርት ያቀረቡትን የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እንደማይታመኑ ተናግረዋል።

በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መመሪያ ሰጪነት ህወሃት በኦሮሚያና በአማራ ክልል ሰላማዊ ጥያቄ ባነሱ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ላይ ሲያከናውን የቆየውንና አሁንም እየተካሄደ ያለውን ገደብ የለሽ ግፍ፣ የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ግድያ፣ እስር፣ አካላዊ ስቃይ፣ ማሳደድና አፈና  አስመልክቶ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነውን ሂውማን ራይትስ ዎችን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማትና መንግሥታትአውግዘውታል። አሁንም እያወገዙት ነው።

ህወሃት ለአገዛዙ ይጠቅመው ዘንድ በየደረጃው ካቋቋማቸው ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መሪ አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ባለፈው ሰኞ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በመግለጫቸው “ስለሰብዓዊ መብት ጥሰት ስናውራ ጥሰቱን ማን ፈጠረው” ተብሎ መሬት ተወርዶ ምርመራ መካሄድ እንደሚገባው አስገንዝበዋል። አያይዘውም በስም ባይጠሩትም ሂውማን ራይትስ ዎችን “የት ሆነው ሪፖርቱን እንደሚሰሩት ባናውቅም…” ሲሉ ህወሃትን ጥፋተኛ በማድረግ ድርጅቱ ያወጣውን ሪፖርት ሊታመን የማይችል ሲሉ ከወዲሁ ተችተዋል።

የቀድሞው የምርጫ ቦርድ ምክትል ኃላፊ የሚመሩትና “ሃቀኛ ሪፖርት ያቀረባል” የተባለው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፋ የሚያደርገው ሪፖርት ኢህአዴግ ጽ/ቤት እንደተጠናቀረየጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ አመልክቷል። እንደ ዘጋቢው፣ ሪፖርቱ ከክልል የደኅንነትና ጸጥታ መዋቀሮች የተሰበሰቡትን መረጃዎች በኮሚሽኑ ስም የሚያዘጋጀው የኢህአዴግ ጽ/ቤት፣ በኦሮሚያ የኦህዴድ ሃላፊዎች ላይ የተወሰደውን ርምጃ ያጎላል። ከህዝብ ጋር በተደረጉ “ውይይቶች” በሚል የተወሰደው የኃይል ርምጃ ከተቀሰቀሰው ረብሻ ጋር ሲነጻጸር እንደማይጋነን ህዝብ ምስክርነት እንደሰጠበትና ፈጣን ምላሽ የተወሰደበትን ጉዳይ ከጀርባ የውጪ ኃይሎች ወደ ረብሻ እንደቀየሩት አድርጎ ያሳያል።

ከዚህም በላይ የእስልምና አክራሪዎች እጅ ከጀርባ እንዳለበት በማጉላት ህወሃት የወሰደው ርምጃ “እጅግ ትዕግስት የተሞላበትና የተመጣጠነ” እንደሆነ በሪፖርቱ ይንጸባረቃል። በተጨማሪም ለማረጋጋት ተሰማራ በተባለው ሰራዊት ላይ፣ ባካባቢ ሚሊሺያዎች፣ ፖሊሶችና የሌላ ብሄር አባላት ላይ የግድያ ሙከራ መደረጉንና ቤተክርስቲያን መቃጠሉን ሪፖርቱ ህወሃት ለተጨማለቀበት ደም ማጽጃ በረኪና አድርጎ እንደሚያቀርብ ተመልክቷል።

ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም “ጥፋተኞች ነን፤ ህዝብን ይቅርታ እንጠይቃለን” ማለታቸውን ተከትሎ ይፋ የሚሆነው ሪፖርት፣ ህወሃት በውክልና አገሪቱን እንዲያስተዳድሩለት የመደባቸውን ካድሬዎች ማገዱ፣ ማባረሩ፣ በህግ ለመጠየቅ መዘጋጀቱ ከወንጀሉ በስተጀርባ ሆነው ትዕዛዝ ሲሰጡ የነበሩትን የህወሃት ሹማምንቶች ነጻ እንደሚያወጣ ኦህዴድን አጋፍጦ እንደሚሰጠው ለማወቅ ተችሏል። በዚህም የፌደራል አስተዳደሩ ጣልቃ ገብቶ የማስተካከሎ ስራ መስራቱ በበጎ ጎኑ የሚቀርብ እንደሆነ ከወዲሁ ታውቋል።

አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ መንግሥታት ኢህአዴግን ለወጉም ቢሆን ማብራሪያ እየጠየቁ መሆኑ፣ እንደ ሂውማን ራይትስ ዎች አይነት የሰብዓዊ መብት ተቋማት ያቀረቧቸውን ሪፖርቶች ለማጣጣል፣ ሪፖርቱ ከታሰበው ጊዜ በፊት ተጠናቅሮ እንዲወጣ ታምኖበታል። ከዚያም “በኢህአዴግ ሸንጎ ክርክር ተደርጎበት፣ ዳብሮና ተሻሽሎ ጸደቀ” ይባላል። የፖለቲካ ጨዋታ መሆኑ ቢታወቅም ለውጪው ዓለም ሚዛን ማሳቻ ይውል ዘንድ ህጋዊ ሽፋን ይሰጠዋል። ከዚያም ለፕሮፖጋንዳው ክፍሎች ተበተኖ ሥራ ላይ እንደሚውል ዘጋቢያችን አመልክቷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት (ሒውማን ራይትስ ዎች) ዘገባውን ካወጣ በኋላ ለአሜሪካ መንግሥት ኃላፊዎች በዝግ ተጨማሪ ማብራሪ የተሰጣቸው መሆኑን ጎልጉል የደረሰው መረጃ ይጠቁማል። በዘገባው ላይ ያልተጠቀሱ ተጨማሪ መረጃዎችና ማብራሪያዎች ለኃላፊዎቹ የተሰጣቸው በመሆኑ ባለፉት ቀናት የሕዝብ እንደራሴዎች በተለይ የውጭ ጉዳይ መ/ቤቱን (ስቴት ዲፓርትመትን) ለኮንግረስ ዘገባ እንዲያቀርብ መጠየቃቸው ተዛማጅነት እንዳለው ይነገራል።

አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ሪፖርቱ በሚወጣበት ቀንም ሆነ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በሁለቱም ክልሎችና በኮንሶ፣ እንዲሁም በጋምቤላ የደረሰውን ግፍና ወንጀል በማጠናከር ለዓለም አቀፍ ተቋማትና ሚዲያዎች፣ ለኤምባሲዎች፣ ለተለያዩ አገራትና በተለይም ለህዝብ በሚቻለው መንገድ ሁሉ ይፋ ማድረግ አግባብ ነው። በተለይም አስቀድሞ ለውጭ ሚዲያዎች መግለጫ በመስጠት ሪፖርቱን ራሱ ህወሃት ያዘጋጀው እንደሆነ ማስታወቅ አግባብ እንደሆነ ተገልጾዋል። ቢቻል ሪፖርቱ እየቀረበ ባለበት ወቅት የህወሃት አንጋቾችና ታማኞች እስካሀን ድረስ ያለማቋረጥ የፈጸሙትን አሰቃቂ ግፍ በማህበራዊ ገጾች ላይ አጉልቶ ማሳየት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ባገር ቤት ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሪፖርቱን አስመልክተው ይፋ ከመሆኑ በፊት ከወዲሁ ስራ መስራት እንደሚገባቸው ይመክራሉ።

 

ኢትዮጵያ – ከአምባገነን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዴት? በዲሲ የነገይቱ ኢትዮጵያ ኮንፈረንስ የቀረበ (የሽንጎው እይታና ራዕይ)

 

የኢትዮጵያ እውነታዎች

2016-03-27_18-48-39አሁን በስልጣን ላይ ያለው በህወሓት የበላይነት የሚመራው ቡድን በተለያዩ የውጭ ሃይሎች ድጋፍና በመሳርያ ሃይል ሀገሪቱን ከመቆጣጠሩ በፊት፣ ለሀገሪቱ ሁለንትናዊ ችግር ምንጭ የብሄር ጭቆና መሆኑንና ብቸኛውና ዋናው መፍትሄ ደግሞ በዋናነት በዚህ ችግር ላይያተኮረ መሆን እንዳለበት ሲያቀነቅን፣ በርዕዮተ-ዓለም ደረጃም የአልባንያን ሶሽያሊዝም  እንደመርህ ይዞ  ሁለገብ ዴሞራሲያዊ መፍትሄዎችን እንደማይቀበል ሲገልጥ እንደነበር ይታወቃል።

ይህን አስተሳሰቡን ይዞ ሀገሪቱን የተቆጣጠረው ኃይል፣ የመጀመሪያው እርምጃው የነበረው ይህን አስተሳሰቡን የማይቀበሉትን የፖለቲካ ኃይሎች (በተለይም ሀገር አቀፍ ድርጅቶች)ማጥቃትና ከፖለቲካው ሂደት እንዲገለሉ ማድረግ ነበር። የማግለል ፖለቲካውን በነዚህ ሀገራዊ የፖለቲካ ኃይሎች ላይ የጀመረው ህወሀት/ኢህአዴግ የሽግግሩ መንግስት ሊፈጠር አጥቢያ ተቋቁመውም  ይሁን ቀደም ብለው ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ብሄር ተኮር ድርጅቶች በሽግግር ሂደቱ እንዲሳተፉ ቢፈቅድም፣  (የነዚህን ድርጅቶች ማሳተፍ መቀበሉ ለጊዜአዊ ጠቀሜታ የተቀየሰ እንጂ ነጻ ሆኑ ድርጅቶችን ለማሳተፍ ከመነጨ እምነት አልነበረምና) ብዙም ሳይቆዩ ከሂደቱ እንዲገለሉና የተወሰኑትም በህገወጥነትና በጠላትነት ተፈርጀው ”ሰላማዊ“ ከሚባለው ፖለቲካዊ ሂደት በፍጹም እንዲወጡ አድርጓል።

የስርዓቱንአራማጆች ይህንኑ አመላካከት በመቀጠል እስካሁን ድረስ የተለያዩ አስተሳሰብና ራዕይ ያላቸውን ዜጎች በሰላምና ህግንበተከተለ መልክ በፖለቲካው ምህዳሩ እንዳይሳተፉ  የሚከለክልፖለቲካዊ አካሄድ እንዲከተሉ  ያደረጋቸውም ይኽው በአግላይነት ላይ የተመሰረተ ፍራቻን፣ጥላቻንና ለራሳቸው የሚሰጡት የተጋነነ አመለካከትን አካቶ የሚገለጸው ቅኝታቸው ነው።

በመሆኑም፣ ሐገራችን ኢትዮጵያና ህዝቧ ላለፉት 25አመታት እጅግ ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ  ወድቀዋል።ስርአቱ ምንም እንኳን ዴሞክራሲያዊና ባለ ብዙ ፓርቲ ስርአትን ያመላከቱ በመሠረታዊ የሕግ ሠነዶች (“ሕገመንግሥት፣ ሕጎችና ደንቦች”) ያሠፈረ ቢሆንም፣በተግባር የሚታየው ግን   የህወሀት/ኢህአዴግን በተለይም ደግሞ  የህወሀትን የበላይነት በሚያረጋገጥ መልኩ ተቀይሶና ተዋቅሮ የሚንቀሳቀስ ብሄርን/ዘውግን መሰረት ያደረገ የአንድ ድርጅት ፣ ከዚያም አልፎ የጥቂት ግለሰቦች አምባገነንንት የሰፈነበት መሆኑን ነው። ይህ ስርአት በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚውበኩል የሚያሳየው አግላይነት፣ የመብት መጣስ፤ ጭካኔና መጠነ ሰፊ ግፍ ህዝቡን ወደ ታላቅ ቁጣና ህዝባዊ እምቢተኛነትእየገፋው ነው።

ይህ የህዝብ ቁጣ  በተለያየ መልክ፣በተለያየ ጊዜ፣የተገለጠ ቢሆንም፣ በአንድ በኩል በስርአቱ ዘግናኝ አፈናበሌላ በኩል ደግሞ በተቃዋሚ ድርጅቶች መከፋፈል፤ ብቃት ማነስና ተባብረው መቆም አለመቻል፣ተፈላጊውን ግብ ሳይመታ ቆይቷል።

አሁን ደግሞ ይኸው የህዝብ የለውጥ ፍላጎትና አልገዛም ባይነት በተለያዩ ሀገሪቱ ክፍሎች ተቀጣጥሎ ቀጥሏል። በሽንጎው እይታ ይህ የህዝብ በቃኝ ባይነት፣የሀገርን አንድነትና የህዝብን መልካም ትስስር ሳያበላሽ የስርአት ለውጥን እውን እንዲያደርግ፣ ከዚያም አልፎ የግጭቶች  እና መጠፋፋት አዙሪትን ለመስበር በተቃዋሚዎች በኩል ምን መደረግ አለበት ብሎ መቀራረብ፤ መመካከር፣ እና ከቃላት በላይ ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ የወቅቱ ዋነኛ ጥያቄ ነው።

ሕወሀት ኢህአዴግ ለ25 አመታት ተግባራዊ ያደረገው ስርአት በራእዩም በተግባሩም በቅራኔና በግጭት የተወጠረ እንዲሁም የህዝብን መሰረታዊ ፍላጎት ሊያረካ የማይችል በመሆኑ ነው ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ጋር እየተጋጨ የራሱን መጨረሻ በፍጥነት እያቃረበ የሚገኘው። ስርአቱ የሚያራምደው በብሄር ማንነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካና ተግባረዊ ያደረገው ያስተዳደር ክልል በበቂ ጥናትና ህዝብን ባሳተፈ መልክ የታለመና የተተገበረ ስላልሆነ እነሆ ራሱ ህወሀት/ኢህአዴግን ሳይቀር ራሱ ባጠመደው ወጥመድ እርስበርስ ወደመባላት ያደረሰው ሲሆን  ሀገሪቱንም ወደ መፈራረስና ህዝቡንም ወደ እርስ በርስ ግጭት አደጋ ጠርዝ አድርሷታል።

በህዝብ እና በስርአቱ መካከል ያለው ቅራኔ የስርአቱ ባለስልጣናት እንደሚሉት በጥቂት “ኪራይ ሰብሳቢዎች” ምክንያት ወይም በየተዋረዱ የሚገኙ ባለስልጣናት ስራቸውን በደንብ ስላልሰሩ ወይም “ካፈጻጸም” ጋር በተያያዘ ምክንያት ብቻ የተከሰተ ሳይሆን ስርአቱ የህዝብን መሰረታዊ መብት ሊያከብር ባለመቻሉ፣ የህግ የበላይነትን ሊያከብር ባለመቻሉ የመንግስት ስልጣን ከህዝብ አመኔታ ብቻ መምጣት እንዳለበት ሊቀበል ባለመቻሉ፣ የሀገሪቱን ዳር ድንበርና ብሄራዊ ጥቅም ሊያሰጠበቅ ባለመቻሉ ህገመንግስት ተብሎ የቀረበው የፖለቲካ ፕሮግራምም የህዝብን አመኔታም ከበሬታም ያገኝ ባለመሆኑ፣ ህዝብ መንግስቱንም፤ ስርአቱንም የኔ ብሎ ስላልተቀበለው ነው። ቅራኔው በህዝብ የነጻነት ፍላጎትና በስርአቱ በአምባገነንነት እድሜልክ ለመግዛት ባለው ቅዥት መካከል ነው። ስርአቱ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል፣ እርስ በርስ ለማጋጨትና ተደላድሎ ለመግዛት ያጠመደው ፈንጂ ባሁኑ ሰአት በእጁ ላይ ፈንድቶ የሚያደርገውን አሳጥቶታል።

የስርአቱንና የህዝቡን ቅራኔ ባጭሩ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡

በፖለቲካና ሰብአዊ መብት ገጽታው፤

ያለፉትን 25 አመታት የሀገራችንን ሁኔታ ስንመረምር መረዳት እንደሚቻለው፤ የፖለቲካ ድርጅቶች በነጻ የሚንቀሳቀሱበት ምህዳር ጭራሽ ጠቧል፣ የብዙሀን መገናኛወች ፣ ከተራ ወከባ እስከ ግድያ በደረሰ መንግስታዊ ተጽእኖ ድምጥማጣቸውን ለማጥፋት ጥረቱ ቀጥሏል። የብዙሀን ድርጅቶች እንዳይመሰረቱ ከማገድ አልፎ ከተመሰረቱም አቅም የሌላቸው ሆነው እንዲቀሩ እየተደረገ ነው። ስርአቱ የዕምነት ነፃነትን በተደጋጋሚ ገፏል። የዕምነት ተቋማትንም አፍርሷል፣ በጣልቃገብነት አተራምሷል። የዜጎችን የመጻፍ የመናገር፣ በነጻ የመደራጀት፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማካሄድ ተቃውሞን የመግለጥ መብት ወዘተ አፍኗል። ህዝብ የሚያስተዳድሩትን መሪዎቹን በራሱ ድምጽ የመሾምም የመሻርም መብቱ ተገፎ፣ እነሆ ህወሀት ኢህአዴግ በ2005 አይን ያወጣ ያደባባይ የድምጽ ዝርፊያ አካሂዶ አሽንፌአለሁ አለ  በመቀጠልም በ 2010 በተካሄደውን ምርጫ በ99.6 % በ2015 ቱ ደግሞ በ100% አሽንፌአለሁ የሚል አስገራሚም አሳዛኝም ፖለቲካዊ ፊዝ ተከስቷል። ይኼ ተደጋጋሚ የምርጫ ማጭበርበር ኢትዮጵያዊያን በምርጫ ተስፋ እንዳይኖራቸው አድርጓል።

የኢኮኖሚያዊሁኔታዎችን ስንመለከት

 

ገዥው ህወሀት/ኢህአዴግ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከአመት አመት ከ 10% እና 12% እድገት አሳይቷል ሲል ቆይቷል። ሆኖም፤ የድሀው ፣ የበረንዳ አዳሪው፣ በቀን አንድ ጊዜ መብላት የማይችለው ህዝብ ቁጥር፣ የስራ አጡ ቁጥር ወዘተ እጅግ ከፍተኛ ነው።  የኑሮ ውድነት ህዝብ ሊቋቋመው ከማይችለው ደረጃ ላይ ደርሷል። ባለፉት 25 አመታት እጅግ ሰፊ ቁጥር ያለው ህዝብ በረሀብ አለንጋ ተገርፏል። ብዙወችም በየቦታው ሞተዋል። ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው ከምታውቀው ሁሉ የበለጠ ቁጥር ያለው ህዝብ ( በፊበርዋሩ 2016 የዩኤስ አይ ዲ ዘገባ መሰረት ከ10-15 ሚሊዮን ያክል ህዝብ) ዛሬ ተርቦ ይገኛል። የሚወራው የሁለት አሰርት አመታት የኢኮኖሚ እድገት ውጤት ለብዙሀኑ በተጨባጭ በህዝብ ህይወት መሻሻል ላይ አይታይም። በተጻራሪው የፓርቲና የመንግሥት ባለሥልጣናት ቤተሰቦችና ተቋማት በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ገቢና ኃብት ሰብስበዋል። የድሎትና የቅንጦት ኑሮ ይኖራሉ።

በሀገሪቱ የተለያየ ክፍሎች በከተማ መስፋፋትና በልማት፣ ባለሀብቶችን በማግባባትና በመሳብ ስም ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ከኖሩበት መሬት ያለፍላጎታቸው በጉልበት እንዲፈናቀሉ እየተደረገ ነው። የመሬት ነጠቃ በጋምቤላ፤ በቤነሻንጉል፤ በደቡብ፤ በኦሮሚያ፤ በአማራና በአፋር ወዘተ ክልሎች በሰፊው ተካሂዷል፤ እየተካሄደም ነው።  ሁኔታው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በከተሞችም በሚያሳዝን ሁኔታ ህዝብን ማፈናቀሉ በሰፊው መካሄድ ከጀመረ አመታት አስቆጥሯል።  ለምሳሌ በአዲስ አበባ ነዋሪ ግለሰቦች ሶስት እና አራት ትውልድ ከኖሩበት ቤታቸው በልማት ስም፣ መኖሪያ ቤታችሁ ለሰፋፊ ህንጻ ስራ ይፈለጋል ተብለው  ያለፍላጎታቸው እና ያለበቂ ካሳ እያለቀሱ እንዲፋናቀሉ እየተደረገ ነው።

በአዲስ አበባ በፍልውሀ አካባቢ፣ በዶሮ መነቂያ አካባቢ በአራት ኪሎ፣ በሜክሲኮ አደባባይ ወዘተ ብዚ ሽህ ኢትዮጵያውያን የተፈናቀሉት በዚህ መልክ ነው። ተመሳሳይ ማፈናቀል እና የመሬት ነጠቃ  በባህርዳርና በመቀሌ ወዘተ ተካሂዷል።

በቅርቡ በኦሮምያም  የተቀሰቀሰው የህዝብ መነሳሳት አንዱ ምክንያት ይኸው ቅጥ ያጣ፣ የመሬት ነጠቃና የህዝብን መሰረታዊ መብት እና የመኖር መብት ቅንጣት ያክል የማያገናዝበው የስርአቱ ስግብግብ ፖሊሲና የባለስልጣናቱም አልጠግብ ባይነት ነው።

የማህበራዊ ሁኔታ

በማህበራዊ ጉዳዮች  እንጻርም የኢትዮጵያ ህዝብ እጅግ አሰቃቂ ሁኔታ ላይ ይገኛል። ወጣቱ ተስፋ አጥቷል። ኑሮን ለማሽነፍ ሲባል ሴተኛ አዳሪነት እጅግ በርክቷል። አሁን ደግሞ ወጣት ወንዶችም በዚሁ ተግባር ተሰማርተዋል። ኢትዮጵያ ወጣቶች በገፍ ከሚሰደዱባቸው አገሮች መካክል አንዷ ናት። ወላጆች እጅግ ተስፋ ከማጣታቸው የተነሳ የወለዷቸውን ልጆቻቸውን፣ አባት እናት የሌላቸው በማስመሰል ለማደጎ መስጠት የተለመደ ሆኗል። ህጸናትን በማደጎ ለባእዳን እንደሽቀጥ በመላክ ኢትዮጳያ ካፍሪካ ግንባር ቀደም ሆናለች።

የጋራ በሆነው የሀገርና የታሪክ እሴት መኩራት እየተቡረቦረ ነው።  የህዝባችን አንድነት ተናግቷል፣ በመርዘኛ ከፋፋይ የሆነ ፖለቲካ የተነሳ በህብረተሰቡ ውስጥ መፈራራት፣ በጥርጣሬ መተያየት እጅግ አስፈሪ በሆነ ፍጥነት ተስፋፍቷል። ኢትዮጵያውያንን ካንዱ ክልል የዚህ ቋንቋ ተናጋሪ ስለሆንክ ልቀቅ ብሎ ማባረር የዚህ ቋንቋ ተናጋሪወች እንዳይመጡብን ማለት ዛሬ የተለመደ ሆኗል።

የዚህ ሁሉ መሰረት ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ህወሀት ኢህአዴግ ያለህዝብ ተሳትፎ፣ ያለበቂ ምክክርና ጥናት “ህገመንግስት“ ብሎ ተግባራዊ ያደረገው የፓርቲው ፕሮግራም እንዲሁም በቀጣይነት እየተተገበረ ያለው በጥላቻ ላይ የተማከለ የመንግስት ፖሊሲ ነው። ኢትዮጵያ ከዓለም አገሮች በተለየ ሁኔታ በብሄር/በዘውግ እንድትለያይ ተደርጓል። አንቀጽ 39 የመገንጠል መብትን ህጋዊ አድርጓል።  ይህን የብዙ ችግሮቻችን መሰረት የሆነውን ህገመንግስት አንቀበልም የሚሉትን አንዳንዶች ጸረ ፊደራሊዝም፤ የብሄርን የብሄረሰብን መብት ለመንጠቅ የተዘጋጁ ወዘተ አድርጎ ለማቅረብ ይጥራል። ይህ ሁኔታውን አለመረዳት ወይም ተራ ፕሮፓጋንዳ ነው። ፊደራሊዝምን የማይቀበሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ቢኖሩም እጅግ ጥቂት ናቸው፡ ፡ እኛም ሆን ብዙ ኢትዮ/ጵያውያን  የማንቀበለው በፊደራሊዝም ስም ተግባረዊ እየተደረገ ያለውን፣ አድልኦ የተሞላበት፣ ተገንጣይነትን የሚቀበል፤ ግጭቶችንና ቅራኔዎችን ቀፍቃፊ የሆነ ከፋፋይ ሥርኣትና አሰራርን ነው። የጋራ ማንነት የጋራ እሴት ከማዳበር ይልቅ ማዳከምን የሚያበረታታውን “እኛና እነሱ” የሚለውን አጥር የሚያጠናክረውን ህግ ነው። በተፈጥሮ ኃብት ላይ፤ በተለይ በመሬት ላይ የሚካሄደው ግጭት የህገመንግሥቱ ውጤት ነው። የኛ ራእይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቋንቋው ባህሉ፤ ማንነቱ የሚከበርነት አንድነታችንን የሚያጠናክር የሁሉም ዜጎች መብት ሙሉ በሙሉ የሚከበርበት፣ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በማንነታቸው ኮርተው ንብረታቸውን ሳይነጠቁ፣ ከቀያቸው ሰይፈናቀሉ፣ በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያለፍራቻ የሚኖሩበትን ህገመንግስታዊ  ዴሞክራሲአዊ ስርአትን እውን ማድረግ ነው።

በሀራዊ ሉአላዊነት ሰላምና መረጋጋት

ኢህአዴግ የመጀመሪያ አመታት መረጋጋት የነበረ ቢመስልም ይህ ግን ብዙም አልቀጠለም። በ2010 የክራይስስ ግሩፕ ዘገባ እንደተረጋገጠውም ከዘጠኙ ክልሎች ውስጥበኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በሶማሊያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኔሻንጉል፣ በትግራይ ይነስም ይብዛም እስከ መሣሪያ መጠቀም የደረሱ ግጭቶች ይታያሉ። ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ መረጋጋት እየጠፋባት፣ የውጭ ጠላት አገሮች ጣልቃ እየገቡባትና እየከበቧት፤ በፍጥነት ከባድ ወደሆነ ቀውስና ውድቀት እየገባች ነው። ለዚህ አመቻች የሆነው ሁኔታ የአገር ውስጥ መከፋፈል መሆኑ የሚያከራክር አይመስለንም።

ስርአቱ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት እና ሉአላዊነት ግድ የሌለው መሆኑን በተደጋጋሚ አሳይቷል። የኢትዮጵያን ህጋዊም ታሪካዊ ሁኔታን እንዲሆም ጥቅም ችላ ባለና ሀላፊነት በጎደለው አካሄድ ህወሀት ኢህእዴግ የኤርትራን መገንጠል አመቻችቶ ሀገራችንን የባህር በርም አሳጥቷታል፡፡ ይህ ሀላፊነት ጎደለው ውሳኔ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱ ለታላቅ አደጋ እንድትጋለጥ አድርጓል።

አሁን በቅርቡ ደግሞ በምእራቡ የሀገራችን ክፍል በኩል ለም ወሀ-ገብና ደን-ለበስ ሠፊ መሬት ለሱዳን እያስረከበ ነው ። ይህ አርቆ አሳቢነት የጎደለው ተግባር ዛሬ በራሱ በህወሀት ኢህአዴግ አባላት ሳይቀር ግንዛቤን እያገኝ ነው።

የግፍ ሞልቶ መፍሰስ እና የህዝብ በቃኝ ማለት

የስርአቱ የግፍ በትርና ያላቋረጠ አፈና የህዝብን የነጻነት ፍላጎትና ትግል ሊያከስመው ከቶውንም አልቻለም። በአሁኑ ሳአት ወገኖቻችን በኦሮሚያ በአማራ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ፣ በአዲስ አበባ ታክሲ ሾፌሮች ወዘተ እነሆ በታላቅ ቁጣ በቃኝ ብለው ተነስቷል።

አሁን የሚታየው ትግል አበረታች ገጽታወቹ ውስጥ የሚከተሉትን ጉልህ ሁኔታወች ማንሳት እንችላለን፡

የሰላማዊ ትግሉ ተስፋ ሰጭነት መታደስ

የህወሀት/ኢሕአዴግ አገዛዝ የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ደረጃ በደረጃ ሊያልፈሰፍሰው እና ደብዛውን ሊያጠፋ ሲጥር እነሆ አመታት ተቆጥረዋል። ይህ በህዝብ ሰላማዊ ትግል እና በገዝው ቡድን ረገጣ መካከል የሚካሄደው ትግል አንድ ጊዜ ሲጎለብት ሌላጊዜ ደግሞ ሲዳከም ቆይቶ  ባለፈው አመት (2007) ምርጫ ዋዜማ እጅግ የተቀነባበረ የጥቃት እርምጃ በመንግስት ደርሶበታል። ከዚህም የተነሳ ብዙወችሰላማዊ ታጋዮች ተገድለዋል ታሰረዋል፣ ሌሎች ለስደት ተዳርገዋል፣ ድረጅቶችምበጉልበት ህጋዊነታቸውን ተነጥቀው ተበትነዋል::  አንዳንዶች ደግሞ የሰላማዊ ትግሉ ተስፋ የለውም በኢትዮጵያ ውስጥ አይሰራም፤ በፍጹም ሊያንሰራራ ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል ብለው ተስፋ እሰከመቁረጥ እንዲደርሱ አድርጓል።

ይህ አይነቱ ተስፋ መቁረጥ በተለይም በሊህቃኑ በኩል አየተከሰተ ባለበት ሁኔታ ነው ሰላማዊ ትግሉ እጅግ ባልታሰበ ሁኔታ ፈንድቶ በሰፊ የሀገሪቱ ክፍል እየተቀጣጠለ የሚገኘው። ይህ ሰላማዊ የህዝብ ትግል ህዝባዊ እምቢተኛነት በኦሮሚያ ክልል በአማራ ክልል በተለይም በጎንደር የተለያዩ አካባቢወችና በወልቃይት በጠገዴ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ወዘተ በሰፊው እየተቀጣጠለ ይገኛል።

ህዝባችን የጭቆናውን ስርአት ለማስወገድ በህይወቱ ሳይቀር ዋጋ እየከፈለ ቆርጦ መነሳቱን እያሰመሰከረ ነው። ይህ እውነታ ባኦሮሚያ፣ በጎንደር በደቡብ ኢትዮጵጵያ፣ ባዲስ አባባ፣ በባህርዳር ወዘተ ተመስክሯል

የስርአቱ ድጋፍ እየተሟጠጠ መምጣት

በአሁኑ ሳአት በየቦታው በመቀጣጠል ላይ የሚገኘው የህዝብ መነሳሳት ገዥው ቡድን የድጋፍ መሰረቱ እጅግ እየጠበበ እንደሆነ ይደግፈኛል በሚለው በከተማው ብቻ ሳይሆን በገጠርም በሞስሊሙም በክርስትና ሀይማኖት ተከታዮችም፣ በኦሮሞ፣ በአማራ፣ በቤነሻንጉልም በአፋር፣ በኦጋዴን፣ በትግራይም በደቡብም ክልል የሚኖረው ህብረተሰብ ውስጥ  ቦታ ማጣቱን ያሳያል። ስርአቱን ያዋቀሩት ህወሀትና ሶስቱ ድርጅቶች እርስበርስ መተማመን፣ እየመነመነ ነው፣ አንዱ ሌላውን ይከሳል፤ እርስበርስ ባይነ ቁራኛ ነው የሚተያዩት። ይህ ሁሉየስርአቱ እድሜ ወደመጨረሻው እየደረሰ እንደሆነ አመላካች ነው።

በተጨማሪም በህዝብ ትግል ግፊት የአዲስ አበባና የአጎራባች ከተሞች የተቀናጀ የልማት ዕቅድ የተባለውን ኦህዴድና ህወሓት በዘገምታም ቢሆን መሠረዛቸውአንዳንድ ችግሮቹን አባብሰዋል፣ መልካም አስተዳደር የሚባለውንም በጎላ መልኩ አበላሽቷል፣ በሙስናም ተጋልጠዋል  የሚላቸውን ዝቅተኛና መለስተኛ ሹማምንት ገዥው ቡድን ከስልጣናቸው ማንሳት መጀመሩ የህዝብ ትግል እያስገኘ ያለውን ድል አመላካች ነው። ይህ ድል ዘላቂነት እንዲኖረው እንመኛለን፤ እንፈልጋለን።

ከድርጅቶች ባሻገር ህዝብን መሰረት ያደረገ ትግል መጠናከር

ሌላው በኦሮሚያም፣ ይሁን በአማራው ክልሎች አሁን የተነሳውን የህዝብ እንቅስቃሴ ካለፉት ሁሉ ለየት የሚያደርገው በቀጥታ ከላይ ወደታች  የሚመራ ሳይሆን በህብረተሰቡ መሀል በተፈጠረ አመራር ከህዝቡ መሰረታዊ ኑሮ ጋር በተዛመደ አጀንዳ በህብረተሰቡ ታቅፎ የሚንቀሳቀስ ዳይንሚክ ሀይል መሆኑ ነው።የዚህ አይነቱ መሰረት ያለው የህዝብ እንቅስቃሴ ሰፋ ያለ ውጤትን ለማስመዝገብ ያለው ችሎታ ከፍተኛና አበረታች ነው

ተጓዳኝ አደጋወች

ተስፋ ሰጭ ሁኔታወች እንደሚታዩት ሁሉ አሳሳቢ የሆኑና የሁሉንም ኢትዮጵየዊ ልዩ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ጉዳዩች ውስጥ  የሚከተለውን እንመለከታለን።

የሀገር አንድነት መናጋት አደጋ

የሀዝቡ ትግል እየተጠናከረ ሲመጣ “የትግሉ ባለቤት እኔ ነኝ አመራር ሰጭውም እኔ ነኝ “ የሚሉ የተለያዩ ክፍሎች ብቅ ብቅ እያሉ ይገኛል። ይህ አካሄድ አልፎ አልፎ አግላይ የሆነ አዝማሚያን የሚከተል ሲሆን አንዳንድ ጊዜም  እኛና አነሱ የሚለውን አጥር እጅግ በማጠናከር የተወሰነውን ህዝብ ትግል  ለተወሰነ አግላይ የፖለቲካ አጀንዳ መጠቀሚያ የማድረግ አዝማሚያ ይታያል። ለምሳሌም በኦሮሞ ክልል የተከሰተውን እንቅስቃሴ ከሌላው ጋር የማይያያዝ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪው የብቻ ወይም የተናጠል ጉዳይ እንደሆነና የሌላው ኢትዮጵያዊ ተግባር በተራ አጋርነት ደረጃ ማገዝ እንጂ ከዚያ ያለፈ፤ ሊሆን እንደማይገባው፤  በተወሰኑ ክፍሎች/ቡድኖች ተደጋጋሚ ቅስቀሳ ሲደረግ ተደምጣል። ይህ ህዝብን በጎራ ለይቶ በተለያየ ጠርዝ አስቀምጦ የሚያይ አካሄድ የሚያጠናክረው መቻቻልንና አንድነትን ሳይሆን ሩቅ ለሩቅ መተያትንና መከፋፈልን ነው

ቀረብ ብሎ ሲመረመርም ደግሞ አልፎ አልፎ ባንዳንድ ክፍሎች የሚገፋው የተቃውሞ  አካሄድ፣ “አኛና እነሱ” የሚለውን አመለካከት ጽንፍ አድርሶ ኢትዮጵያዊነትንና የሀገሪቱን የግዛት አንድነት በጥያቄ ውስጥ  የሚያሰገባ ቅኝት ይታይበታል።ለምሳሌ ባለፉት ጥቂት ወራቶች አንድን ያሀገሪቱን ክፍል ከጎረቤት ሐገር ጋር የማመሳሰል ሙከራ በተደጋጋሚ ተደምጣል።

ምንም እንኳ ከህዝብ አኳያና ከኢትዮጵያ ረዢም ታሪክ አንጻር ሲታይ፤ የኢትዮጵያዊነት መሰረት ጥልቅ ቢሆንም እንዲሁም ሀገሪቱ በታሪኳ እጅግ ብዙ ከፋፋይ አደጋወችን ያለፈች እንደሆነ ቢታወቅም በብሄር ላይ ያተኮረና ኢትዮጵያዊነትን  በጥያቄ ውስጥ ያሰገባ አካሄድ በጊዜ ካልተገታ በኤርትራ እንዳየነው ሁሉ ማእከላዊው መንግስት እየተዳከመ ሲመጣ  የሀገሪቱ ህልውናም ሆነ የህብረተሰቡ ደህንነት በአደጋ ላይ ሊወድቁ የሚችሉበት ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል በግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡ በእኛ እይታ ይህን አደጋ ለመቋቋም ከፍተኛ ጥረት ያሰፈልጋል።

ኢትዮጵያዊነትን አልቀበልም ያለ የብሄረተኛ ድርጅቶች መጠናከር አደጋ

ይህን አሁን የተጀመረውን የህዝቡ እንቅስቃሴ ለማፈን ህወሀት/ኢህአዴግ የሚወስደው የግፍ እርምጃ ብዙወችን በማንነት ላይ ያተኮረ አመለካከት እንዲያጠናክሩ ያበረታታል። በአንድ በኩል መብት ረጋጩ መሪ ፓርቲ በብሄር ላይ የተመሰረተ አገዛዝ በመሆኑ በሌላ በኩልም የሀገሪቱ ስርአት ማንነት ላይ አተኩሮ የተዋቀረ በመሆኑ ሁኔታውን በቀላሉ የብሄረተኛነት ሰለባ እንዲሆን ያደርገዋል። በዚህ የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ የሚደረግ እያንዳንዱ የጅምላ ጥቃት ብሄረተኞችን እያጠናከረ እንደሚሄድ የሻብያእንዲሁም የህወሀትእንቅስቃሴና የእድገት ታሪክ ብዙ ያሰተምረናል።

በአንዳንዶች በኩል ዛሬ የሚታየውን የህዝብ እምቢተኛነት  የአማራ ትግል፣ የኦሮሞ ትግል፣ የጋምቤላ ትግል የእነገሌ ትግል በሚል  ጥቅል የተጠቃሹ ቋንቋ ተናጋሪ ሁሉ አንድ ወጥ አስተሳሰብና አመለካከት ያለው አስመስለው ሲያቀርቡ ይስተዋላል። የትግሉ አቅጣጫም በሰፋፊ የቋንቋ ተናጋሪወች ተመድቦ  እንዲቃኝ የማድረግ አዝማሚያ ይታያል። በኛ አመለካከት አሁን ሀገራችን ባለችበት ውስብስብና የተካረረ ሁኔታ አደጋን ለመከላከል የሚያግዘው በቋንቋ ከፋፍሎ በያለበት ጎራ እንዲጸና የሚገፋፋ አመለካከት ሳይሆን ክፍፍሉን የሚያጠብ አንድነቱን የሚያጎላ ቅኝትና አሰራር ነው።

በሁሉም የሀገራችን  ማህበረሰብ ውስጥ የተለያየ ፖለቲካ አመለካከትና የፖለቲካ አጀንዳ አለ። የትናውም ማህበረሰባ አንድ ወጥ አይደለም። የማህበራዊ ፍትህን ( ሶሻል ጀስቲስ )  መሰረት በማድረግ፣ የማንነት ጥያቄ አግባብ ያለው ምላሽ እንዲኖረው የሚታገሉ፣ኢትዮጵያዊነትን መሰረት አድርገው  ዘረፋን፣ ምዝበራን ታሪካዊም ይሁን አሁን የሚታይን አግላይነት፣ ኢፍትሀዊነትን ወዘተ የሚታገሉ አንዳሉ መደገፍም እንዳለባቸው ምንም ጥርጥሬ የለንም። በኛ በኩል ከነዚህ ክፍሎች ጋር እጅ ለጅ ተያይዘን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሙሉ መብት የተከበረበት ዴሞክርሲያዊ ህገመንግስታዊ ስርአት እንዲመሰረት የምናደርገው ትብብር ተጠናክሮ ይቀጥላል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር መቀጠል የለባትም፣ እንዲያውም ኢትዮጵያ የችግራችን መሰረት ስለሆነች መፈራረስ አለባት ብለው የሚታገሉ መኖራቸውን በትክክል መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ይህን ሁኔታ እንደሌለ ማስመሰል ፤ተዛማጅ አደጋውን ደግሞ ዝቅ አድርጎ ወይም ከሚገባው በላይ አጋኖ ለማሳየት መሞከር ተገቢ አይሆንም። ይህ ለሀገርም ለህዝብም አይጠቅምም። ይህ ሁኔታ ሁላችንም ባጽንኦት ልንመለከተው እና ለመፍትሄ ፍለጋውም በጥንቃቄ ልንመክርበት የሚገባን ጉዳይ ነው።

የእርስ በርስ ግጭት አደጋ

የህዝባችን ለዘመናት አብሮ መኖር፣መዋለድና በአያሌ ማኅበራዊ ሀይማኖታዊና ባኅላዊ ግንኙነቶች መተሳሰር፣ ወዘተእሴት እንዳለ ሆኖ፣  ከፍ ብሎ የተገለጸው ከፋፋይ ሁኔታ እየጦዘ ሊመጣ እንደሚችል በጊዜው በመገንዘብ  አደጋውን መቀነስ ካልተቻለ እጅግ አሳሳቢ የሆነ የእርስ በርስ ግጭትን ሊጋብዝ የሚችል ሁኔታ በሀገራችን ውስጥ መኖሩን እንመለከታለን።  ይህ የህዝብ እርስ በርስ ግጭት በሕወሀት/ኢህአዴግ ወይም በተቃዋሚ ውስጥ በማንነት ላይ የተመሰረተ ግጭትመካረር ይጠቅመናል ብለው በሚያሰቡ ክፍሎች ተንኳሽነት ሊቀሰቀስ ይችላል። በተጨማሪም ሀገሪቱ በማያባራ የእርስ በርስ ግጭት እንድትዘፈቅ የሚሹ የውጭ መንግስታትም (ለምሳሌ ከ2 አመት በፊት ሾልኮ የወጣው የግብጽ መንግስት ባለስልጣኖች ውይይት እንደሰማነው) የዚህ አይነቱን እኩይ ተግባር፣ በቀጥታም ሆነ በእጅ-አዙር፣  ለመጠቀም ወደ ኋላ እንደማይሉ መገንዘብ ተገቢ ነው::

የሀገር አንድነት መናጋት አደጋና የእርስበርስ የግጭት ፍራቻ አሉታዊ ተጽእኖ

እጅግ ብዙው ኢትዮጵያዊ የሕወሀት/ኢህአዴግን መወገድ እና የሰርአት ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልግ ቢሆንም ለሀገሩ አንድነት የሚጨነቀው፤ የእርስ በርስ ግጭት የሚያሰጋውና ሌላ ያግላይ ድርጅት ስልጣን መያዝ የሚያሰሳስበው የህብረተሰብ ክፍል ስጋቱ ለህዝባዊ ትግሉ ድጋፉን እንዳይሰጥ ፣ ከዚህ የተነሳም የትግሉ አካልም ከመሆን እንዲቆጠብ ያደርገዋል። ይህ ደግሞ ትግሉንየሚያስፈልገውን በቂ ሀይልያሳጣዋል ያዳክመዋል፡፡ ተበታትኖለመጠቃት በር ይከፍታልም:: ምናልባትም ለገዥው ቡድን እንደገና መጠናከር ያልተጠበቀ ሁኔታ ሊፈጥርለት ይችላል፡፡ ይህ አደጋ የአለም አቀፍ ህብረተሰቡንም ላይ ተመሳሳይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል።

ስለሆነም ህዝብን ለምን አልተነሳም ብሎ ከማማረር በፊት በተቃዋሚው በኩል ህዝብን ከመነሳት ወደ ኋላ እንዲል የሚያደርገው እምነት እንዲያጣ የሚያደርግ ወይም እንቅስቃሴውን በጥርጣሬ እንዲያየው የሚያደርገው ምን ጉዳይ አለ ብሎ ወደውስጥ ተመልሶ መመልከት አስፈላጊውንም ማስተካከያ ማድረግ ተገቢ ይሆናል።

ስርአቱ እንዳለ መቀጠል በሀገር አንድነት መናጋታና እና በእርስበርስ ግጭት አኳያ ያለውን አደጋ እጅግ በማወሳሰብ ታላቁን ሚና ይጫወታል። በመሆኑም የችግሮቻችንን መፍትሄ ስናስብ የስርአት ለውጥ አስፈላጊነትን ለደቂቃም መዘንጋት የለብንም። የምሆኖ ግን በተቃዋሚው በኩል ያለውንም ሁኔታ ደግሞ በተጨባጭ መገንዘብ ተገቢ ነው።፤

ተስፋን ለማጠናከርናአደጋን ለመቀነስ  ምን ይደረግ?

በሀገራችን ውስጥ የሚታየውን የለውጥ መነሳሳት አጠናክሮ አደጋውን ቀንሶ የህዝቡን ተስፋ በማደስ ወደሚፈለገው ቦታ ለማድረስ እንዲሁም በሀገራችን ውስጥ የግጭት አዙሪትን ሰብሮ፣ ዘላቂ ሰላምን ተግባራዊ ለማድረግና ለልማት መሰረት ለማጣል የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሲቪክ ማህበራትና ምሁራን ታላቅ ሀላፊነት አለባቸው። ለዚህ የሚበጀው ከሁሉም በላይ ከቡድን በላይ የሃገርንና የሕዝብን ጥቅም ማስቀደም ነው።

ከላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎችንም በግምት ውስት በማስገባት ትግሉን በተቀነባበረ መልክ የመላ ሀገሪቱን ህዝብ ያሳተፈና የአለም አቀፉንም ህብረተሰብ ድጋፍ ሊያገኝ በሚያሰችለው መልክ ወደፊት ለመግፋት የሚከተሉትን አራት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ተግበራዊ እንቅስቃሴን ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለን እናምናለን።

የተቃዋሚው መሰባሰብና መተባበር

ተደጋግሞ እንደተነገረው የህወሀት ኢህአዴግ መንግስትና ስርአት እድሜ የረዘመው በስርአቱ ጥናካሬ ሳይሆን በተቃዋሚው መከፋፈል፤ አለመሳባሰብ እና አለመጠናከር ነው። በሌሎች ከአምባገነን ስርአት ወደ ዴሞክራሲ የተሸጋገሩ ሀገሮች ልምድ (ለምሳሌ ፖላንድ፣ ቱኒስያ፣ ፊሊፒንስ፤ በርማ) የምንረዳው በግልጽ አላማ ዙሪያ የተሰባሰበ ተቃዋሚ ለስርአት ለውጥ ብቻ ሳይሆን ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታም ወሳኝ እንደሆነ ነው። በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥም አሁን ያለውን የህዝብ መነሳሳት ወደሚፈለገው የስርአት ለውጥ እንዲያመራ ለማድረግ አንዱና ዋነኛው አጣዳፊ ተግባር በተወሰኑ ሀገራዊ ዓላማዎች (መርሆወች) ላይ የተሰባሰበ ሰፋ ያለ የተቃዋሚወች የጋራ ትብብር ባስቸኳይ መመስረት ነው።

ይህ ስብስብ ህብረተሰቡን በተቀናጀ መልክ እንዲታገልና፣ የእርስ በርስ ግጭትን ለማስወገድ ትልቅ መሳሪያ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በተለያየ ቦታ የሚታየውን አለመተማመንን ለመቅረፍ በመላ ሀገሪቱም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ሆነ ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ ገዥውን ቡድን ለመተካት የሚችል፣ የተባበረ፣ ሀገር ለመመምራት ብቃት ያለውና ሀላፊነት የሚሰማው ስብስብ (ድርጅት)፤ አመራርና ሀይል መኖሩን የሚያበስር ይሆናል።

በሽንጎው እይታ ፣ ከምስረታችን ጊዜ ጀምሮ እንደምንለው ይህ ስብስብ የሀገራችንን ግዛታዊ ሉአላዊነት እና የህዝቧንም መብትና አንድንት  ሙሉ በሙሉ ማረጋገጥ ይኖርበታል። ኢትዮጵያውያን ህወሀት /አህአዴግን ሲያሰወግዱ የሀገራቸው አንድነትና፣ የወደፊት ህልውናቸው ደግሞ ለሌላ አደጋ የማይዳረግ መሆኑን ማረጋገጥ ይፈልጋሉ። ህወሀት/ኢህአዴግን ለመተካት የሚጥረው ሌላ አግላይ ቡድን፣ ከህወሀት ኢህአዴግ ያውራ ፓርቲ ፍልስፍና ያልተላቀቀ ሀገራችን አሁን የምትገኝበት አደጋ ውስጥ የጣላትን ፖሊሲ ባዲስ መልክ ለመቀጠል የሚፈልግ ስብስብ እንዳልሆነ ማወቅ ይፈልጋሉ። ይህ ሳይሆን የህዝብን አመኔታና  ቆራጥ ተሳትፎ ማግኝት አስቸጋሪ ነው።

በሽንጎው እይታ ይህን ሰፋ ያለ የተቃዋሚወችን ስብሰብ ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉን አቀፍ የሆነ የተቃዋሚወች ጉባኤ መጥራትና ባአሰቸኳይም እንዲካሄድ ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው።

በዚህ አንጻር ሽንጎ የጉዳዩን አንገብጋቢነትና የሁኔታውን አጣዳፊነት በመረዳት ይህ የተቃዋሚወች ሰፊ ትብብር ባጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን  ሁሉም ባለድርሻወች ገና ከጅምሩ  የሂደቱም የውጤቱም ባለቤት እንዲሆኑ ሰፊ ተግባራዊ እንቅስቃሴን እያካሄደ ነው። ይህ እንቅስቃሴ ባጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ እንደሚሆን ታላቅ ተስፋ አለን።

የተቃዋሚውን  አቅም ግንባታ ማጠናከር

በሀገራችን የስርአት ለውጥን ለማስገኘትም ሆነ በግብታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉትን አንዳንድ አደጋወች ለመቀነስ  ተቃዋሚው አቅሙን በተለያየ መልክ  ለምሳሌም በድርጅት ጥንካሬ ፣ በተለያዩ ቦታወች መዋቅር በመዘርጋት፣ በቅራኔ አፈታት ክህሎት፤ በገንዘብ አቅም፣ በመገናኛ አቅም፣ በአመራር ብቃት በዲፕሎማኪክ ስራ ብቃት ወዘተ ሊያጠናክር  ይገባዋል። አንድ ድርጅት ብቃትና ጥንካሬ ከሌለው ከሰርአቱ ጥቃት በደረሰ ቁጥር መፍረክረክ እና ቀጣይነት ማጣት ይከተላል። ይህም ትግሉን በተደጋጋሚ በገዥዎች እንዲኮላሽ አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት እርምጃ ወደ ኋላ እንዲሄድ ያደርገዋል፡፡

ምንም እንኳ እያንዳንዱ የትግል እንቅስቃሴ ለቀጣዩ ትግል ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ቢሆነም ተደጋጋሚ ጥቃት ደግሞ ሊያሰከትል የሚችለውን ስነልቦናዊ ጉዳት በግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያሰፈልጋል።

ሰላማዊ ህዝባዊ ትግልን ማጠናከር

በሽንጎው እይታ ይህ አስከፊ ስርአት በህዝባዊ ሰላማዊ ትግልና የሕዝብ እምቢተኛነትዝብ አ ሊወገድ ይችላል። ይህ እንደሚቻልም በ1997 የታየው የህዝብ መነሳሳት፣ ረዘም ላለ ጊዜ በመቀጠሉ አርአያነት ያለው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሠላማዊ ትግል፣ በተለያየ ወቅት ህዝቡ በተለያዩ ከተሞች በሽወች በመውጣት ለተቃዋሚ ድርጅቶች ያሳየው ድጋፍ አሁን ደግሞ በኦሮሚያ እንዲሁም በአማራ ክልል የሚታየው የህዝብ አመጽ ያዲስ አባባ ታክሲ ሾፌሮች የስራ ማቆም አድማ አመላካች ናቸው። የተለያዩ አለም አቀፍ ጥናቶች እንደምንገነዘበው ሰላማዊ ትግልና ሕዝባዊ ዐመጽ ዴሚክራሲያዊ ስርአትን ለማዋለድ፣ ጦርነት የሚያሰከትለውን ጥፋት ለመቀነስና  ያልተጠበቀ ምስቅልቅልን ለማስወገድ ታላቅ አማራጭ ነው። ሀገራችን ውስጥ የሚታየው በተወሰኑ ሃይሎች የሚቀነቀነው እጅግ ግልጥ የሆነ ኢትዮጵያን የመገነጣጠል አደጋ ደግሞ ሰላማዊ ትግልና የተሳሰረ ሕዝባዊ ዐመጽን ይበልጥ ተመራጭ ያደግረዋል። ሌላው የሰላማዊ ትግልና ሕዝባዊ ዐመጽ ጠቀሜታ ደግሞ ትግላችን ከውጭ ጥገኝነት እንዲላቀቅ የሚያግዝ መሆኑ ነው። ሰላማዊ ትግልና ሕዝባዊ ዐመጽዝብአሕሕ የሚመካው በራሱ በተጨቋኙ ህዝቡ ላይ ነው።

ሁሉም እንደሚገነዘበው፤ ዛሬ የህዝባችን ትግል ከስር ፈንቅሎ በመነሳት ከፍተኛ አልበገሬነትን እያሳየ በመጓዝ ላይ ነው። የህዝብ ትግል ከአምባገነን  ስርአትም መወገድም በኋላ ወደ ተደላደለ ዴሞክራሲ ለማምራት የተሻለ እድል የሚኖረው  በሰላማዊና በሕዝባዊ ዐመጽ መንገድ የተካሄደ ለውጥ ሲሆን እንደሆነ ብዙ ጥናቶች አሳይተዋል። ከነዚህ ጥናቶችም  ወስጥ ከ1990 እስከ 2006 የተካሄዱ 320 ያክል ሳላማዊና የሕዝብ ዐመጽን ያካተቱ  ትግሎችን የገመገመ (Why Civil Resistance Works ) በሚል ርእስ በማርያ ስቲፋን እና ኤሪክ ቸንወርዝ (Maria J. Stephan and Erica Chenoweth፤ The Strategic Logic of Nonviolence) የቀረበው  ጥናት እንዲሁም በ2005 ለንባብ የበቃው  የ35 አመታት የስልጣን ሽግግር ታሪካን የፈተሽው “ነጳነትን እንዴት መጎናጸፍ ተቻለ”፤ ከህዝባዊ እምቢተኛነት ወደ ተረጋጋ ዴሞክራሲ” (How freedom is won ; from civic  resistance to Durable Democracy ) የሚለው የፍሪደም ሀውስ ጥናት በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው።

ብሄራዊ መግባበት እና አርቅ ተግባራዊ የሚሆንበትን መንገድ መሻት

ለብሄራዊ መግባባት እና እርቅ በዋናነት እንቅፋት የሆነው ህወሀት/ኢህአዴግ ቢሆንም  በሽንጎው እይታ ሀገራችን ከምትገኝበት እጅግ ውስብስብ ሁኔታ ወደ ሀገመንግስታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የሚደረገው ሽግግር ሁሉን አሳታፊ በሆነ ሄራዊ መግባበት እና አርቅ መሆኑ አማራጭ የሌለው ነው። ይህ ምርጫችን የፖለቲካ አግላይነትን ለማስወገድ፣ ቂም በቀል የተሞላበት ፖለቲካ እንዲወገድ ያጥፊኛ ጠፊ አዙሪትን ለማክተም ሁሉም ባለ ድርሻወች በሀገራችን ችግሮችም መፍትሄወችም ላይ ባለቤትነት እንዲኖራቸው ለማስቻልና ለረዥም ጊዜ ያልተፈቱ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ታሪካዊ ብሶቶችንና፣ ቅሬታወችን በመነጋገር፣ በመግባባትና፣ አንዱ የአንዱን መከፋት፣ ብሶትና ምኞት ወዘተ በማዳመጥ ለመፍታት የተሻለ አማራጭ ሆኖ ሰላገኘነው ነው፡፡

ሽንጎው ፖለቲካኞች ከስልጣን በተወገዱ ቁጥር መጨረሻቸው እስርቤት የሚሆንበት፣ አንድ መንግስት ከስልጣን ሲወርድ የመንግስቱ ደጋፊወች ንብረታቸው ተወርሶ ወደ ድህነት የሚገፉበትን ፣ የፖለቲከኞች ቤተሰቦች መጨረሻቸው ስደት የሚሆንበት የፖለቲካ አዙሪት እንዲቆም ይፈልጋል ይታገላልም።

 

ማጠቃለያ።

ከ24 አመታት የህወሀት ኢእአዴግ ከፋፋይና አግላይ ስርአት በኋላ እነሆ የስርአቱ መጨረሻ እየተዳረሰ ነው። ይህን የለውጥ ሂደት ለመቀልበስና የሚታየውን ተስፋ ለመዳፈን ገዥው ቡድን አሁንም የመጨረሻ ሙከራ እያደረገ ይገኛል፤፡የስርአቱ እንዳለ መቀጠል ለሀገር አንድነትም ሆነ ለህዝባችን ሰላም እጅግ ሰፊ አደጋን ይጋብዛል። በመሆኑም የስርአቱ መቀየር ለነገ የማይባል ተግባር ነው። አሁን መለወጥ አለበት።

የህዝባችን የለውጥ እንቅስቃሴ በዝቅተኛ የሰው ህይወት መጥፋትና የየንብረት መውደም የሚፈለገውን የስርአት ለውጥ እውን እንዲያደርግ መጭውንም ጊዜ የሰላም የመረጋጋት እና የዴሞክራሲአዊ ስርአት ግንባታ እውና ለመድረግ የሚያሰፈልገው ስራ መሰራት መጀመር ያለበት ካአሁኑ ነው።

ይህን እውን ለመድረግ በኢትዮጰያ ብሄራዊ አንድነት እና የህዝቧም የሉአላዊነት ሙሉ በሙሉ መረጋገጥ አለበት። በሀገራችን ውስጥ የተለያዩ ወገኖቻችን የተለያየ ብሶት አንዳላቸው፣ ግልጽ ነው፤ በወደፊቱ ስርአት ውስጥ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገራችን ችግሮች በሀገራችን አንድነት ስር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ መነጋገር፤ መወያየት፤ መደራደር፤ መሰማማትና ለዚህም መስራት ይኖርብናል።

ከዚህ ውጭ በሰበብ ባስባቡ ሀገራችንን ለመበታተን የሚደረግ እንቅስቃሴ ሁሉ ያለምንም ማወላወል ልንቃወመው ይገባናል። አሁን በህዝባችን ላይ የተጫነው ስርአት ተወግዶ  የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተከበረባት፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቋንቋው የተከበረበት፣ ማንነቱ የተከበረበት የህግ የበላይነት የሰፈነበት ህገመንግስታዊ ዴሞክራሲአዊ ስርአት መመስረት አጣዳፊ ተግባራችን ነው።

ይህንንም ለማድረግ አግላይ ያልሆነ የተቃዋሚ ሰፊ ግንባር/ትበብብር መመስረት አስፈላጊ ነው።በተበታተነ መልክ የሚካሄደው ትግል ለየብቻ በሚደረግበት ጥቃት ሰለባ ከመሆን አልፎ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገውን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ብሎ መገመት ያዳግታል። እንዲያውም ባለቤትና አስተባባሪ የለለው በመሆን አንድም እንደ ስልሳ ስድስቱ የሀገራችን አብዮት ህዝብ ፍሬውን ይነጠቃል፣ አለያም ድህረ አረብ ጸደይ በሊቢያየመንና በሌሎቹ  እንደሆነው ሁሉ ትርምስ ሀገሪቱን ይወርሳል። ስለዚህም በርግጥም ለሀገራችን ብሩህ ተስፋ ሰንቀው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ይህንን ተገንዝበው መላን የተላበሰ የተባበረ ትግል ማድረግ እጅግ አስፈላጊነው። ለዚህም ተግባራዊነት ሽንጎ ዝግጁ ነው። የተቃዋሚው ክፍል መተባበር፤ ቢያንስ ህወሓት/ኢህአዴግን ለማስገደድ አስፈላጊ መሆኑን እናሳስባለን።

የሀገራችን ችግር እጅግ ውስብስብ ነው፣ መፍትሄውም እንዲሁ ቀላል አይደለም። በሆይ ሆይታና ባሳካሪ ፖለቲካ (intoxiicating politics) አጥጋቢ መፍትሄ ማግኝት እንደማይቻል ያለፈው 25 አመት ታሪክ አሳይቷል። ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደደሴት ለብቻዋ ተነጥላ የምትገኝ አይደለችም፣ በጎረቤቶቻችንም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው ሁኔታ እኛንም ይመለከተናል በበጎም በክፉም እኛንም ይነካናል።

ተቃዋሚው ከአግላይ ፖለቲካና ከየአውራ ፓርቲ አባዜ ራሱን ማላቀቅ እጅግ አስፈላጊ ነው እንላለን ። እነዚህ ሁለት አባዜወች ሀገራችንን ላለፉት 25 አመታት እና ከዚያም በፊት ወደጥፋት አረንቓ የወሰዱ አሁን ለምንገኝበት ምስቅልቅልና ችግር መሰረት የሆኑ መሆኑን ተገንዝበን ይህን ስህተት ላለመድገም መጣር የግድ ነው እንላለን።

በህገራችን ውስጥ የነጻነት ትግሉ በስፉት ቀጥሏል። ወገኖቻችን በተለይም ወጣቶች ለሰብአዊና ዴሞካራሲያዊ መብታቸው መከበር እንደሁለተኛ ዜጋ እየተቆጠሩ መኖር እንዲያበቃ ለማድረግ ቆርጠው እየታገሉ፣ ውድ ህይወታቸውንም እየገበሩ ነው። ይህን መሰዋእትነት ለውጤት ለማብቃት በጋራ እንነሳ። የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን  ታላቅነት፣ የዚች ታሪካዊ ሀገርና ህዝቧ  ታላቅነት፣ እንዲሁም ብሩህ ቀን ከፊት ለፊታችን ነው።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

የነፃነት ትግላችን ዋነኛ ምሰሶ ለነፃነታችን በፈቃደኝነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችን ነው።>> በናትናሄል ፈለቀ (Zone9)

የነፃነት ትግላችን ዋነኛ ምሰሶ ለነፃነታችን በፈቃደኝነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችን ነው።>>

በናትናሄል ፈለቀ (Zone9)

ማዲባ “Long walk to Freedom”
አንዳንዴ <> ጠላታችን ይሆናል። ነገሮች እንደሚሻሻሉ ወይንም ከዚህ የባሰ እንዳይከፉ እያልን በተስፋ እየተታለልን ማድረግ የሚገባንን ሳናደርግ ወደን ሳይሆን ተገደን እንከፍላለን። ነፃነታችንን የሚያጎናፅፈን መክፈል ብቻ ሳይሆን የምንከፍለው ለነፃነት የሚገባውን መሆኑን አምነን በፈቃደኝነት ወደን ስንከፍል ነው።
አምባገነኖች በሚያስተዳድሯት ሀገር ተራ በተራ እያንዳንዳችን ላይ የጭቆና በትር ማረፉ አይቀርም። ጥያቄው እየሸሸንም ቢሆን ተራችንን ጠብቀን ዋጋ ከፍለን ጭቆናን እናራዝማለን ወይንስ በፈቃደኝነት ዋጋ ከፍለን ነፃነታችንን እንጎናፀፋለን? ነው።

image

ከዕስር ከመውጣታችን በፊት ለነፃነቴ መከፈል ከሚገባው ዋጋ ላይ እየቀነስኩኝ ነበር። እያንዳንዷ በዕስር የማሳልፋት ቀን ለነፃነቴ እያቀረበችኝ እንደሆነ ነበር የሚሰማኝ።
ከዕስር ከወጣሁ በኋላ ለነፃነቴ ለመክፈል ያለኝ ፈቃደኝነት በብዙ <> አብሮኝ የለም።
ወዳጄ የሺዋስ አሰፋ <> ይለኝ ነበር። ምናልባት ማረሚያ ቤት ካገኘሁት ዓይኑን እንዴት እንደማይ አላውቅም።
ይህች ጽሑፍ ምናልባት በራሴ የፌስቡክ ግርግዳ ላይ የማሰፍራት የመጨረሻ ልትሆን ትችላለች። የፊታችን ማክሰኞ መጋቢት 20 ቀን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ላይ የሚሰጠውን ውሳኔ ለመስማት ዳኞች ፊት ከጓደኞቼ ጋር እቆማለሁ። ተራዬ ደርሶ (ሁለተኛ?) የጭቆና በትር ይሰነዘርብኝ ይሆናል። ወይንም እንደገና <> ለማድረግ እቀጠር ይሆናል።
ለክፉም ለደጉም እስር ቤት ያስተዋወቀኝን አንድ ምርጥ ጸሐፊ ልጥቀስ እና የኔ ጉዳይ ለሚያሳስባችሁ ሰዎች ማልቀሻ ልተውላችሁ:–
“…And if it is a despot you would dethrone, see first that his throne erected within you is destroyed.
“For how can a tyrant rule the free and the proud, but for a tyranny in their own freedom and a shame in their own pride?
“And if it is a care you would cast off, that care has been chosen by you rather than imposed upon you.
“And if it is a fear you would dispel, the seat of that fear is in your heart and n

ነፃነት፣ ዲሞክራሲ ፣ የብሄረሰብ ጥያቄና የኢኮኖሚ ዕድገት ! -እንዴትና ለማን እንዲሁም ምን ዐይነት የኢኮኖሚ ዕድገት፟ ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

መግቢያ

እንደምንከታተለው የአብዛኛዎቹ የሶስተኛው ዓለም አገሮች፣ በተለይም ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮች እጣ፣ እንደህብረተሰብና እንደ አገር የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። አብዛኛዎች አገዛዞችና መሪዎቻቸው የአገርና የህዝቦቻቸው ጉዳይ የሚያሳስባቸው አይመስልም። የፖለቲካ አርቆ-አስተዋይነት የጎደላቸውና፣ ህብረተሰብአዊ ኃላፊነት የማይሰማቸው መሪዎች ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከማደለብ አልፈው የአገርን ሀብት ወደ ውጭ በማሸሽ እዚያ የውጭ ባንኮችና ኢንዱስትሪ አገሮች መጠቀሚያ በማድረግና የሀብት ክምችት አመቻች በመሆን፣ በአንፃሩ ደግሞ ህዝቦቻቸውን እያደኸዩ ነው። በተጨማሪም የአገሮቻቸውን የጥሬ-ሀብትና የእርሻ መሬት ለውጭ ኢንቬስተሮች፣ በመሰረቱ ዘራፊዎች አሳልፈው በመስጠት ከሀብት ዝርፊያ ባሻገር ህብረተሰብአዊ፣ ባህላዊ፣ የህሊናና የአካባቢ ቀውስ እንዲፈጠር እያደረጉ ነው። በዚያው መጠንም የአብዛኛዎቹ አፍሪካ አገዛዞች የመንግስት መኪናዎች በከፍተኛ ደረጃ በጭቆና መሳሪያ በመደለብና በመጠናከር የህዝቦቻቸው አለኝታ መሆናቸው ቀርቶ የዓለም አቀፍ ካፒታሊዝም ታዛዦች መሆናቸውን እያረገጋጡ ነው። በመሆኑም አገዛዞች ከህዝብ የሚነሳን ተቃዎሞን፣ የመብትና የነፃነት ጥያቄን ለማብረድ የሚፈልጉት በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ሳይሆን በጠብመንጃ በመታገዝ ሰላማዊ ህዝብ ላይ በመተኮስና በመግደል ነው። ከአምስት ወራት ጀምሮ በአገራችን ምድር፣ በተለይም በአሮሞ ክልል የሚካሄዳው ተቃውሞና የወያኔ አገዛዝ ያደረገውና የሚያደርገው ጭፍጨፋ ከዓለም አቀፍ ካፒታሊዝም የሀብት ምዝበራ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ብዙ ማስረጃዎችም እንደሚያረጋግጡት አግአዚ በመባል የሚታወቀው አስፈሪና ፋሺሽታዊ ጦር የሰለጠነውና የታጠቀው በአሜሪካኖች የስለላ ድርጅት በሲአይኤ(CIA) እንደሆነ ነው። ይህም ማለት የወያኔ አገዛዝ በኦሮሞ እህቶቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ ልጆቻችን፣ አባቶቻችንና እናቶቻችን ላይ የሚያካሂደው የነፍስ ማጥፋት ዘመቻ ከአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ስትራቴጂያዊ ስሌት ውጭ በፍጹም ሊታይ አይችልም። የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ኮሙኒዝምን እዋጋለሁ በማለት በብራዚል፣ በቺሌና በአርጀንቲና በስድሳኛውና በሰባኛው ዐመተ ምህረት አምባገነናዊና ፋሺሽታዊ አገዛዞችን አስታጥቆ ለስልጣን እንዳበቃና የዲሞክራሲንና የነፃነት ጥያቄን እንዳኮላሸ ሁሉ፣ በአገራችን ምድር ደግሞ ከሃያ አምስት ዓመታት ጀምሮ የወያኔን አገዛዝ በማስታጠቅ አገዛዙ በህዝባችን ላይ ጦሩን እንዲመዝ የሚያሰደርገው የላይኛው አንድ አካል ነው። በሌላ ወገን በስድሳኛውና በሰባኛው ዓመተ ምህረታት በብራዚል፣ በቺሌና በአርጀንቲና በህዝብ የተመረጡ አገዛዞች በአሜሪካ ታግዘው የመንግስት ግልበጣ ሲካሄድባቸውና ፋሺሽታዊ አገዛዞች ስልጣኑን ሲወስዱ፣ በአገራችን ምድር ግን „ህጋዊ በሆነ„ መንገድ የተካሄደ ቀስ በቀስ ወደ ፋሺሽታዊ አገዛዝነት የተለወጠ የስልጣን ሽግግር ነው። ለዚህ ደግሞ የጸጥታውን መስክ ከማጠናከር በሻገር፣ በነፃ ገበያ ስም የተካሄደው ፖሊሲ አገዛዙን ሀብት አካባችና፣ በዚያው መጠንም በውጭ ኃይሎች ጉያ ስር እንዲወድቅ አድርጎታል። ስለሆነም አገዛዙ የሚያካሂዳቸው እንደ ስኳር የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችና የመሬት መቀራመት ጉዳይ፣ እንዲሁም እንደሰሊጥ የመሳሰሉትን የቅባት እህሎች በመቆጣጠርና ወደ ውጭ በማጋዝ ደካማ አገሮችን ለዝንተ-ዓለም አደኽይቶ ለማቆየት ከታቀደው ከዓለም አቀፋዊ ካፒታሊዝም ስትራቴጂ ውጭ በፍጹም ተነጥሎ ሊታይ አይችልም። በሌላ አነጋገር፣ የዛሬው አገዛዝ የኢትዮጵያ ህዝብ ቀስ በቀስ አገሩን በጸና መሰረት ላይ ገንብቶ የነፃነትና የዕውነተኛ ስልጣኔ ባለቤት እንዳይሆን በምዕራቡ ካፒታሊዝም የሚደገፍና ድህነትም የባሰውን ስር እንዲሰድና አገራችንም እየተሽመደመደች እንድትኖር የሚያደርግ አገዛዝ ነው። ስለሆነም አገዛዙ የፈለገውን ያህል ህዝብ ይግደል፣ በህዝብ ነው የተመረጠ በማለት አሁምን ቢሆን ከካፒታሊስት አገሮች እርዳታውን ያገኛል።

የወያኔ አገዛዝ በህዝባችን ላይ የሚያካሂደውን የጭቆና አገዛዝና ጭፍጨፋ፣ እንዲሁም የሀብት ዘረፋ በተለይም ተቃዋሚ ነኝ ከሚለውና፣ እዚህና እዚያ በተናጠልም ሆነ በቡድን ውር ውር ከሚለው በሃሳብ ደረጃ ለውይይት ቀርቦ ጥናት ሲካሄድ አይታይም። በአብዛኛዎችም ዕምነት የዲሞክራሲ፣ የነፃነትና የኢኮኖሚ ዕድገት ጉዳይ ከውጭው ሁኔታ ጋር የሚያያዙ ሳይሆኑ የውስጥ ጉዳይ ብቻ ነው የሚል አመለካከትና ግንዛቤ ሰፍኗል። ችግሩ ከአገራችን የተበላሸ አገዛዝ የመነጨ እንጂ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት አገዛዙ በሚያካሄደው ጭፍጨፋና ድህነት መስፋፋት ላይ ምንም ዐይነት ተጽዕኖ የለውም፤ የኛን ችግር በውጭው ላይ ማሳበቡ አላዋቂነት ብቻ ሳይሆን፣ አክራሪነትም ነው ይሉናል። ስለሆነም ይላሉ፣ እነዚህ በአንድ በኩል አገዛዙን የሚጠሉና የሚታገሉ ኃይሎች፣ በሌላ ወገን ደግሞ የምዕራቡ ጣልቃ-ገብነት ሲነሳባቸው የሚያንገሸግሻቸው ለዲሞክራሲና ለነፃነት እንታገላለን ባዮች የምዕራቡን ጥቅም የማይቀናቀን አገዛዝ ስልጣን ላይ ከወጣ ዕርዳታውም ይጎርፍልናል፤ በደስታም እንድንኖር ያደርጉናል በማለት የእቅጩን ይነግሩናል። በመሆኑም ይሉናል፣ የኛ ትግል የነሱን ጥቅም የሚቀናቀን መሆን የለበትም። ጥቅማቸውን እስካልነካን ድረስ ሊረዱን ይችላሉ በማለት ከህብረተሰብ ዕድገትና ከሳይንስ ውጭ የሆነ ክርክር ያቀርባሉ። በሌላ ወገን ግን የምዕራቡ ዓለም ጥቅም ምን እንደሆን እይነግሩንም። ዕቃቸውን እንዲያራግፉና ጦርነትም እንድናካሂድላቸው፣ በዚያውም መጠንም የህዝባችንን የድህነት ዘመን እንድናራዝምላቸው ይፈልጉ አይፈልጉ እንደሆን እነዚህ ለዲሞክራሲ እንታገላለን የሚሉ እህቶቻችንና ወንድሞቻቸን በግልጽ ሊነግሩን አይችሉም። በተጨማሪም የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት በማድረግ ጠንካራና የተከበረች አገር ለመገንባት ያግዙን እንደሆነ ውድ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን አያብራሩም። እንዲያውም ይሉናል እሱማ አያስፈልገንም፤ የኛ ተግባር የዛሬውን አገዛዝ ማስወገድ ብቻ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ የሚመጣውን እግዚአብሄር ያውቃል በማለት ከሳይንስና ከፍልስፍና እንዲሁም ከቲዎሪ ውጭ የሆነ ክርክር ይገጥማሉ። ያም ሆነ ይህ በታሪክ እንደታየውና እንደተረጋገጠው፣ ከቀድሞው ሶቭየት ህብረት፣ ቻይናና ከጃፓን የምንማረው ሀቅ የውጭ ኃይሎች በርቀት እስካልታዩና ማንነታቸው ተገልጾ ውይይት እስካልተደረገና፣ ወደ ውስጥ ያተኮረ ሁለ-ገብ የህብረተሰብ ግንባታ እስካልተካሄደ ድረስ አንድ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ እንደማይችል ነው። በተጨማሪም ከነዚህና በመጠኑም ነፃነትን ከተቀዳጁ አገሮች የምንማረው ሀቅ አንድ ህዝብ በራሱ ኃይልና ዕውቀት ተማምኖ አገሩን ለመገንባት እስካልተነሳሳ ድረስ የዕውነተኛ ነፃነት ባለቤት ሊሆን እንደማይችል ነው። በመሆኑም የኢምፔሪያሊስት ኃይሎች በማንኛውም ረገድ የህዝባችን ተቆርቋሪና የነፃነት አጋዥ ሊሆኑ በፍጹም አይችሉም። ከዚህ ስነነሳ የነፃነትንና የኢኮኖሚ ዕድገትን ጉዳይ ጠለቅ ብለን መወያየት ያለብን ይመስለኛል።
እንደሚታወቀው ክርክርና ሰፋ ያለ የጭንቅላት ስራ በአውሮፓ የህብረተሰብ ታሪክ ወስጥ የተለመደውን ያህል እንደኛ ባሉ በኢኮኖሚና በህብረተሰብ አወቃቀር ወደ ኋላ በቀሩ አገሮች ውስጥ የህብረተሰብን ችግርና የወደፊት ዕድል አስመልክቶ መከራከር የተለመደ አይደለም። በተለይም ከ50ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የሶስተኛውን ዓለም አገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት አስመልክቶ በጣም ጥቂት ምሁራን ካልሆኑ በስተቀር አብዛኛው ክርክር ይካሄድ የነበረው ይህንን ወይም ያንን ርዕዮተ-ዓለም እናካሄዳለን በሚሉ በአውሮፓና በአሜሪካን ምሁራን ዘንድ ነበር። ለሶስተኛው ዓለም ተቆርቋሪ ሆነው የሚታገሉ ኃይሎች አብዛኛውን ጊዜ ከካፒታሊስት አገሮች የወጡና የተገለጸላቸው ኃይሎች እንጂ፣ የዕድገትና የፀረ-ዕድገት ጉዳይ በኛ ምሁራን ዘንድ ተንስቶ ክርክርና ጥናት የተደረገበት ጊዜ አልነበረም። በመሆኑም የኢኮኖሚ ፖሊሲ በውጭ ኃይሎች ተረቆ ሲቀርብ እሱን እንደቡራኬ ከመቀበልና ተግባራዊ ከማድረግ በስተቀር ፖሊሲው ዕውነተኛ የኢኮኖሚ ዕድገትን ያምጣ አያምጣ ለውይይት አይቀርብም። በሁለትና በሶስት ወራት ወይም ሳምንታት ቆይታና ከዚያ በኋላ ደግሞ ይህንን ወይም ያንን መጽሀፍም ሆነ መጽሄት እያገላበጡ ከዚያ በመነሳት ፖሊሲ አውጥቶ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ እንደምናየው የኛንም ሆነ የሌሎችን አፍሪካ አገሮችን ሁኔታ የባሰውኑ አባባሰው እንጂ ስርዓት ያለውና ተከታታይ ማህብረሰብ እንዲመሰርቱ አልረዳቸውም። የብዙ አፍሪካ አገሮችን ሁኔታ ስንመለከት ከ1950ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ በአወቅሁኝ ባይነት በራሳቸው ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች በሙሉ የበሳውኑ መቀመቅ ውስጥ ነው የከተቷቸው። የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት በመሆን ህብረተሰቦቻቸውን በስርዓት እንዲገነቡና እንዲያደራጁ አይደለም የረዷቸው።

ከዚህ ስንነሳ በኛ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከእንካስላንቲሃ በስተቀር የህብረተሰብአችንን የባህል፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ እንዲሁም ሌሎች ችግሮችን እያነሱ መከራከር የተለመደ አይደለም። እንዲያውም የህብረተሰብአችን ዕጣና የወደፊት ዕድል ለዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው እየተባለ ለሚጠራው የተጣለ ይመስላል። ሁሉም አድፍጦ ተቀምጧል ። ስልጣን ለመያዝ ጊዜን የሚጠባበቅ እንጂ ብሄራዊ ፕሮጀክት እንዳለው ሰፊ ጥናት በማቅረብ እንድንወያይ የሚያደርገን ኃይል ያለ አይመስልም። የአገርን ህልውናና በትክክለኛ ፖሊሲ መሰረተ-ሃሳብ የመገንባቱ ጉዳይ በመሰረቱ ተራማጅ አስተሳሰብ ካለው ኃይል የሚጠበቅ ጉዳይ ነበር። እንደምከታተለው ከሆነ የተራማጅ ወይንም የተገለጸለት አስተሳሰብ ያለው ምሁራዊ እንቅስቃሴ ስለሌለና፣ አንድ ሰሞን ተራማጅ ነኝ የሚለው ኃይል ተሟጦ ከአለቀ በኋላ በአሁኑ ወቅት የሊበራል ነፃ ገበያ እናካሂዳለን የሚሉት ዋናው ተዋናይና ግንባር ቀደም በመሆን ሜዳውን አጣቦታል። ድሮ ተራማጅ ነኝ ይል ከነበረው ኃይል ትንሽ ተሟጦ የቀረው ደግሞ ሹክክ ከማለት በስተቀር የሚፈልገውን ነገር ወደ ውጭ ወጥቶ ለመናገር የሚደፍር አይደለም። በዚህም በዚያም ብሎ ሌሎችን ተገን አድርጎ ወደ ስልጣን ሊመጣ የሚፈልግ ነው የሚመስለው እንጂ ለአገር የሚበጅ በፍልስፍና፣ በሳይንስና በቲዎሪ የተመሰረተና የተረጋገጠ ብሄራዊ ፕሮጀክት አለኝ ብሎ ወደ ውጭ ወጥቶ ሲያሰተምርና ሲከራከር አይታይም። ይህ ዐይነቱ የተድበሰበሰ አካሄድ እስካለ ድረስ፣ የፈለገውን ያህል ዲሞክራሲ እየተባለ ቢጮህም ህዝባችን ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ በፍጹም አይችልም። ከዚህ አስቸጋሪና አደናጋሪ ሁኔታ በመነሳት ስለ ነፃነት ሊኖረን የሚገባንን ግንዛቤና መደረግ ያለበትንም ትግል እኔ በምረዳው መልክ ከታች ለመተንተን እሞክራለህ። የነፃነትና የዲሞክራሲ ትርጉሞች ግልጽ ሲሆኑ ብቻ የኢኮኖሚ ዕድገትና የህብረተሰብ ግንባታም መልክ ሊይዙ ይችላሉ የሚል ዕምነት አለኝ።

የነፃነት ትርጉምና ለነፃነት የተደረገው ትግል!

ለመሆኑ ነፃነት ማለት ምን ማለት ነው ? ኢማኑኤል ካንት የሚባለው የጀርመኑ ታላቅ ፈላስፋ „ከሩሶ ስራ ጋር ከመተዋወቄ ወይም ጽሁፎቹን ከማንበቤ በፊት አምን የነበረው በሰው ልጅ አርቆ አሳቢነትና ዕውቀት(Reason and Knowledge)ነበር። ስለዚህም ስለሰው ልጅም የነበረኝ አስተሳሰብ ለየት ያለ ነበር። ያልተማረውን ወይም ደንቆሮውን የምንቅና የተማረውን ብቻ የማከብር ነበር። ሩሶን ካነበብኩ በኋላ ግን ሁሉንም ነገር በነፃ ፍላጎት (Free Will) ስር መሆናቸውን ተገነዘብኩኝ። ስለዚህም በሩሶና በአይሳቅ ኒውተን መሀከል ያለውን ልዩነት በመገንዘብ፣ የነፃነት ዓለም(The World of Freedom) ከተፈጥሮአዊ ዓለም (The World of Nature) የበለጠና ወርቃማ እንደሆነ ተማርኩኝ“ ይላል። በመቀጠልም ፣ “ሩሶ የነፃነትን የተደበቀ ምስጢር ለሰው ልጅ ሲያሰተምር፣ ኒውተን ግን የተፈጥሮን ህግ እንድንረዳ መንገዱን ከፈተልን። ሩሶ ኒውተናዊ የሰው ልጅ ሞራላዊ አባት ሲሆን፣ ውዥንብር በሰፈነበት ዘመን ስርዓት እንዲሰፍን ያደረገ ነው።“ በማለት የሰው ልጅ የግዴታ በነፃነት ዓለም ውስጥ መኖር እንዳለበት ያሳስበናል። በሌላ አነጋገር የሰው ልጅ ነፃ ሆኖ የተፈጠረና በራሱ ነፃ አስተሳሰብ መገዛት አለበት። ይህን ሲገነዘብ ብቻ የራሱን ነፃነት ከማስከበር አልፎ ለሌላው ላልተገነዘበውም ጠበቃ ሆኖ ይታገላል። ነፃነት በአንድ አገዛዝ ወይም ኃይል የሚሰጥ ሳይሆን አንድ ህዝብ በራሱ ተነሳሽነት ማንነቱን ተገንዝቦ የሚቀዳጀው፣ ለፈጠራ ስራና ለሁለ-ገብ የአገር ግንባታ የሚያስፈልግ ቅድመ-ሁኔታ ነው። በአውሮፓ የህብረተሰብ ታሪክ ውስጥም የተረጋገጠው፣ በተወሳሰበ መልክ የተካሄደውና በብዙ መልክ የሚገለጸው ነፃነት ተግባራዊ ሲሆን ብቻ ነው ቀስ በቀስ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊታይ የቻለው።

ይህ ብቻ ሳይሆን፣ በካንት ዕምነት ሩሶ እንደሚለው የሰው ልጅ ህይወት ዕውነተኛ ትርጉም በነፃነት ዓለም ሲኖር ብቻ ነው። ምክንያቱም ክብርና ነፃነት ለሰው ልጅ እጅግ አስፈላጊ ስለሆኑ ማንኛውም የሰው ልጅ የሌላ ሰው ፍላጎት ተገዥና በሱ እየታዘዘ መኖር የለበትም። በሌላው ፍላጎት መኖርና ማጎብደድ የራስን የኑሮ ትርጉም አለመረዳት ብቻ ሳይሆን፣ ራስን እንዳልነበሩ አድርጎ መሰረዝና ማዋራድ ነው። ስለዚህም ይላል ካንት፣ “በዚህ ዓለም ላይ እጅግ የሚያስከፋው ነገር በራስ ፍላጎት አለመመራት ወይም የሌላው ተገዢ መሆን ነው“፣ በማለት ነፃ ፍላጎት የቱን ያህል የሰውን ልጅ የመኖርና ያለመኖር፣ አንድ ህብረተሰብ በስነ-ስርዓት መገንባት መቻሉንና አለመቻሉን የሚረዳን ነው ይላል። ካንት ፍሪ ዊል ወይም ነፃ ፍላጎት ሲል አናርኪ ይፈጠር ማለቱ አይደለም። ወይም አንዱ ሌላውን አያክብር ማለቱም አይደለም። ካንት ስለ ሰው ልጅ ነፃነትና ዕውነተኛ ፍላጎት ሲያስተምር የሰው ልጅ ዕውነተኛ ነፃነት ሲሰማው የመፍጠር ኃይሉም ይዳብራል። ራሱንና የሌላውን ሰው ማንነት በመረዳት የበለጠ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ግኑኝነት ይገነዘባል። በካንት ዕምነት፣ ኒውተን እንደሚለው ተፈጥሮ በድን አይደለችም ወይም ህይወት የሌላት ነገር አይደለችም። የሰው ልጅም የተፈጥሮምና የማይታየው ወይም የረቀቀው መንፈስ አካል ነው። ድርጊቱ ሁሉ የተፈጥሮን ህግ በመረዳት የሚካሄድ ነው። በካንት ዕምነት የነፃነት አስተሳሰብ በብዙ ቅራኔዎች የተወጠረ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት የሰው ልጅ ጭንቅላት ውስጥ ገብተው የሚብላሉ ብዙ ነገሮች ስላሉ አስተሳሰቡ በመወሰንና ባለመወሰን፣ እንዲሁም በነፃነት መሀከል ይዋልላል። ከዚህ የአዕምሮ ጭንቀትና የአስተሳሰብ ቅራኔ ለመውጣት፣ ተግባራዊ በሚሆን የአርቆ አስትዋይነት ወይም አሳቢነት ነው የመዋለሉ ጉዳይ መስመር ሊይዝ የሚችለው። ይህም ማለት እያንዳንዱ ግለሰብ ለራሱ የሚሆን የአርቆ አስተሳሰብ መመዘኛ ያወጣል። ይህ መመዘኛው ራሱን የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳው መሆን አለበት። ስለሆነም ይህ ለራሱ ብሎ የደነገገው ሞራላዊ መለኪያ ለሌላውም የሚያገለግል መሆን አለበት። በሌላ አነጋገር መጽሀፍ ቅዱሱ እንደሚለን፣ „በራስህ ላይ ሊደረግ የማትፈለገውን መጥፎ ድርጊት ለሌላው ሰው አትመኝ፣ ወይም አትፈፅምበት“ የሚለውንም አስተሳስበ ካንት በመቀበል የሰው ልጅ የግዴታ በአርቆ-አሳቢነት መመራት እንዳለበት ያስተምረናል። ካንት ካቴጎሪካል ኢምፔራቲቭ(Categorical Imperative) በሚለው ስለሌላው ሰው ማሰብና መሰማት በሚያስተምረው አዌርነስ(Awarness) በሚለው ብዙ መሰረተ-ሃሳቦችን በያዘው ፍልስፍናው ውስጥ ነው የሚያስተምረን። የካንት አቀራረብ የእንግሊዞቹን የሆበስ፣ ሎክንና ሁምን አመለካከት የሚጻረር ነው። በእንግሊዞች የኢምፔርሲስት ፈላስፋዎች ዕምነት የሰው ልጅ የፍላጎቱ ተገዢ ነው። አርቆ-አሳቢነቱም ከፍላጎቱ በታች የሚገኝ ነው። ስለዚህም ድርጊቱ ሁሉ አንድን ጥቅም ከማግኘት ጋር የተያያዘ ነው። በተለይም በሁም ዕምነት አርቆ-አሳቢነት የፍቅር ስሜት(Passion) ባሪያ ነች። ከዚህም በመነሳት እያንዳንዱ ግለሰብ በዚህ ሎጂክ የሚመራ ነው። በሰው ልጅ አስተሳሰብ ውስጥ ግብረ-ገብነትና(Morality) ስነ-ምግባር(Ethiccs) ቦታ የላቸውም። ግብረ-ገብነት ከአርቆ-አሳቢነት ውጭ የሚገኝና፣ በራሱ ህግ የሚተዳደር ነው። በመሆኑም በኢምፔሪሲስታዊ የሳይንስ አመለካከት ውስጥ ግብረ-ገብነትና ስነ-ምግባር ቦታ የላቸውም።

ካንት ከሩሶ የተማረው የነፃነት ዓለም በግሪኩ ስልጣኔ ዘመን ሌላ ትርጉም ነበረው። እንደሚታወቀው በግሪኩ ስልጣኔ ዘመን በእነ ሶክራተስና በፕላቶን ዕምነት የሰው ልጅ ችግር ሁሉ አርቆ አለማሰብ ወይም የዕውቀት ችግር ነው። በእነሱ ዕምነት በጊዜው ይታይ የነበረው ችግር፣ ረሃብ፣ ድህነት፣ ጦርነትና በውዥንብር ዓለም ውስጥ መኖር የዚህ ሁሉ ዋናው ምንጭ ዕውነተኛ ዕውቀት አለመኖርና አለመዳበር ሲሆን፣ የሰው ልጅም የራሱን ምንነት ለመረዳት አለመቻል ነው። ስለዚህም አርቆ አሳቢነትን ከትክክለኛ ዕውቀት ጋር በማዋሃድ የሰው ልጅ ነፃነቱን እንዲቀዳጅ ማድረግ ይቻላል ይሉናል። በጥንት የግሪክ ፈላስፋዎች በአንድ በኩልና፣ በሌላ ወገን ደግሞ በሩሶና በካንት መሀከል ተቃራኒ አስተሳሰብ ያለ ቢመስልም ሁለቱም አስተሳሰቦች የሚደጋገፉ ናቸው። ይሁንና ግን በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያሉ የገዢ መደቦች፣ ወይም ደግሞ የተሻለ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ሁኔታ ያላቸው የህበረተሰብ ክፍሎች የተቀረው የህብረተሰብ ክፍል ለዘለዓለም ተገዢ ሆኖ እንዲቀርላቸው ዕውቀት የሚባለውን ነገር እነሱ በፈለጉት መልክ እየቀረጹ በማውጣትና በማስተማር ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርጋሉ። በመሆኑም እነሶክራተስና ፕላቶ ሶፊስቶችን ሲዋጉ ያመለክቱ የነበረው የተሳሳተ ዕውቀት የሰው ልጅ ሚናውን እንዳይረዳ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን፣ በዕውነትና በውሸት መሀከል ያለውን ልዩነት እንዳይገነዘብ ያግደዋል። በመሆኑም የገዢ መደቦችና አፈቀላጤዎቻቸው የአንድን ህብረተሰብ ሂደትና አኗኗር ራሳቸው በፈለጉት መልክ በመተርጎምና በማጣመም ሰፊው ህዝብ ነፃ አስተሳሰብንና ዕውነተኛ ዕውቀትን እንዳይጎናፀፍ ያደርጉታል። ስልጣናቸውንም ለማራዘም ሲሉ በህብረተሰብ ውስጥ የሀብት ሽግሽግ በማድረግና ለጦርነት በመዘጋጀት አንድ ህዝብ ተስማምቶ እንዳይኖርና ታሪካዊ ስራዎችን እንዳይሰራ እንቅፋት ይሆኑታል። በዚያውም መልክ እኩልነትና(justice) ጥበባዊ ስምምነት ትርጉም አጥተው ጥቂቱ የህብረተሰብ ክፍል ብቻ የሚጎናፀፋቸውና የሚደሰትባቸው ይሆናሉ። ይህ በራሱ ደግሞ የግዴታ ካንት የሚለውን ነፃ ፍላጎት(Free Will) እንዳይዳብር ያግዳል። በእኔ ዕምነትም ሆነ የካንትን ተከታታይ ስራዎች ላነበበ በትክክለኛ ዕውቀትና በነፃ ፍላጎት መሀከል ተቃራኒ አስተሳሰብ የለም። ሁለቱም የሚደጋገፉ ናቸው።

ካንት መገለጽ ማለት ምን ማለት ነው ? (What is Enlightenment ?) በሚባለው ግሩም ጽሁፉ በጊዜው የነበረውን በዲስፖቲያዊ ወይም በፊይዳላዊ አገዛዝ ይሰቃይ የነበረውን ህዝብ ችግር በማሳየት፣ አንድ ህዝብ ከተተበተበበት፣ ነፃ አስተሳሰብን ከሚያፍን ስርዓት የግዴታ መላቀቅ እንዳለበት ያመልከታል። በሱም አባባል መገለጽ ማለት እያንዳንዱ ግለሰብ በራሱ ድክመት የተነሳ ከተተበተበት ሃሳብን ከሚያፍን ስርዓት ለመላቀቅ የሚያደርገው የመጀመሪያው እንቅስቃሴ ነው። የሰው ልጅ በመሰረቱ ሰነፍ ስለሆነ የማሰብ ኃይሉን አይጠቀምም። አንድ ስርዓት ሲያሰቃየው እሱን እንደ ተፈጥሮ ህግ አድርጎ በመውሰድ የድንቁርናው ወይም የማሰብ ኃይል ድክመቱ ተገዢ በመሆን እሱን በሚመስለው በሌላ ሰው መብቱ ይረገጣል። ካንት እንደሚለን ማንኛውም ሰው በተፈጥሮ የተሰጠው የማሰብ ኃይል ሲኖረው ይህንን ውስጣዊ ኃይሉን በራሱ ጥረት ከፍ ማድረግና ጥያቄዎችን በመጠየቅ ከተተበተበት የጭቆና ስንሰለት መላቀቅ አለበት። በጊዜው ዲስፖቲያዊ አገዛዝ ከሃይማኖት ጋር በመጣመር በተለይም ሰፊውን የጀርመን ህዝብ ማንነቱን እንዳያውቅና የህይወቱ ባለቤት እንዳይሆን አፍኖ ስለያዘው ካንት ብቻ ሳይሆን፣ ከካንት በፊትም የነበሩ ሌሎች ምሁራንና፣ በኋላ ደግሞ ሌሎች አዳዲስ የተገለጸላቸው ምሁራን እንደ አሸን በመፍለቅና የመገለጽን ምንነት በማስፋፋት በጊዜው ከነበረው ሃሳብን አፋኝ ስርዓት ጋር መጋፈጥ ጀመሩ። በዚህ መልክ የተቀጣጠለው እሳት በመስፋፋትና አፋኙን ስርዓት መፈናፈኛ በማሳጣት ጀርመንን የገጣሚዎችና የአሳቢዎች ወይም የፈጣሪዎች አገር ማድረግ ተቻለ።

ከዚህ ስንነሳ የነፃነትን ትርጉም ለማያውቁ ወይም ደግሞ ስልጣን ላይ ቁጥጥ ብለው ሌላውን አምሳያቸውን እንደፈለጋቸው ልናሽከረክረው እንችላለን ለሚሉ፣ ነፃነት የሚለው አስተሳሰብ በመጽሀፍ ቅዱስም በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ ሰፍሯል። የብሉ ኪዳይ ሞሰስ ምዕራፍ ዘጠኝ ላይ፣ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ በአምሳሌ ፈጠርኩት ይላል። ይህም ማለት ማንኛውም የሰው ልጅ በእግዚአብሄር ፊት እኩል ነው ማለት ነው። በሌላ አነጋገር መጽሀፍ ቅዱሱ የሚለን አንደኛው ሌላውን የመግዛትና እንደፈለገው የማድረግ መብት የለውም። የሰው ልጅ የነፃነት ደረጃ ይለያይ እንጂ የመጨረሻ መጨረሻ ነፃነት የህይወት ትርጉም ነው። የነፃነት ደረጃ ስል አንድ ከእናቱ ማህፀን ያልወጣ ወይም ገና ያልተወለደ እዚያው ውስጥ ለማደግ ሙሉ በሙሉ ጥገኝነቱ በእናቱ ነው። ሲወለድና የመጀመሪያውን ብርሃን ሲያገኝ የተወሰነ ነፃነት አገኘ ማለት ነው። በመቀጠልም መዳህ ሲጀምር የተሻለ ነፃነት ያገኛል። እንደዚያ እያልን ስንሄድ አንድ ልጅ ለአቅመ-አዳም ሲደርስ ሙሉ ነፃነቱን ተቀዳጀ ማለት እንችላለን። ይህ ግን ከአካል አንጻር ስናየውና ከዚህ ቀደም ራሱ ማድረግ የማይችላቸውን መፈፀም ሲችል ነው። ይህ ዐይነቱ የአካል ነፃነት ግን ከጭንቅላት ነፃነት ጋር የማይጣጣምበት ሁኔታ አለ። የአንድ ልጅ የአእምሮ ነፃነት በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ በዳበረና ስር በሰደደ ኋላ-ቀር የአኗናር ስልትና ለፈጠራ ወይንም ራስን በደንብ ለመግለጽ በማቻልበት መልክ ሊወሰን ይችላል። በሌላ አነጋገር፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የሚገኝ የማቴሪያልና የአስተሳሰብ ሁኔታ የአንድን ልጅ በአዕምሮ መዳበርና አለመዳበር ይወስናል። ለምሳሌ በዘልማድና በባህል በተጠመደ ህብረተሰብና በሌላ በሰለጠነ ህብረተሰብ ውስጥ ተወልዶ ባደገ ልጅ ወይም ሰው መሀከል ነፃ አስተሳሰብና ፍላጎት የዕድገት ደረጃቸው አንድ አይደሉም። በኢኮኖሚም ሆነ በባህል ወደ ኋላ በቀረ ህብረተሰብ፣ ወይም ነፃ አስተሳሰብ እንደልብ በማይሽከረከርበት ህብረተሰብ ውስጥ ተወልዶ የሚያድግ ልጅ ሳያውቀው የግዴታ በህብረተሰብ ውስጥ የተነጠፉ አስተሳሰቦችን፣ የራስን ፍላጎት ወደ ውጭ አውጥቶ አለመናገር፣ ጥያቄ አለመጠየቅ፣ ለመከራከር አለመድፈር፣ አጎድብድዶ ወይም አጎንብሶ መጥፎም ነገር ቢሆን እሺ ብሎ ተቀብሎ መሄድ እንደተፈጥሮአዊ ህግ ተደርጎ የሚወሰድበት ሁኔታ አለ። በተለይም በአገራችን አሁንም ቢሆን ከላይ የተዘረዘሩ የኢትዮጵያውያን ጨዋ ባህል እየተባሉ የሚወራላቸው የሰውን አስተሳሰብ እንደወጠሩት ነው። ስለዚህም እንደዚህ ዐይነት ህብረተሰብ ውስጥ ጥቂት እናውቃለን የሚሉና ስልጣን የጨበጡ ወይም ተማርን የሚሉ ህብረተሰቡን አፉን እንደሚያሲዙትና አጎብድዶም የነሱን አሰተሳሰብ ብቻ እንዲቀበል የማድረጉ ኃይል ከፍ ያለ ነው። ከዚህም በላይ እነዚህ ኃይሎች ከውጭው ኃይል ጋር በመቆላለፍና የርዕዮተ-ዓለምና የጥቅም ሰለባ በመሆን አንድ ህዝብና ታዳጊ ወጣት አጎብዳጅ ሆነው እንዲቀሩ ያደርጋሉ። በዚያው መጠንም የድህነቱ ዘመን እየተራዘመ በመሄድ፣ አንድ ህዝብ በማቴሪያል ዕጦት ብቻ ሳይሆን ራቁቱን የሚቀረው የአስተሳሰብ ድህነትም ቁራኛ በመሆን ራሱን እንዳይችል ይደረጋል።

በመሆኑም ከጥንቱ የግሪክ ስልጣኔ ታሪክ ጀምሮ እስከ አውሮፓው የህብረተሰብ ግንባታ ድረስ ለዕውነተኛ ዕውቀትና ነፃነት የተደረገውን ትግል ስንመለከት ልማዳዊና ባህላዊ የሚባሉ አኗኗሮች የቱን ያህል የሰውን ልጅ የተፈጥሮ ተገዢ ብቻ ሳይሆኑ፣ በስልጣን ላይ የተቀመጠው ኃይል ተገዢም በመሆን እግዚአብሄር የሰጣቸውን ዕውነተኛ ነፃነት እንዳይጠቀሙና ችግራቸውን ፈቺ እንዳይሆኑ በመረዳት ነው አዕምሮን ነፃ ለማውጣት ትግል የተደረገው። የግሪኩ ስልጣኔም አነሳስ የሰውን ልጅ መሰረታዊ ቦታ በመረዳት የተደረገ እንቅስቃሴ ነው። የመጀመሪያው ታለስ የተባለው የግሪኩ ፈላስፋ 1ኛ) እግዚአብሔርን የማመሰግነው እንስሳ አድርጎኝ አለመፍጠሩ፣ 2ኛ) አረመኔ ሳልሆን የሰለጠንኩ በመሆኔ ነው ይላል። በዚያን ዘመን ግሪኮች ራሳቸውን ከሌሎች ህዝቦች ጋር በማወዳደር እነሱ ብቻ የሰለጠኑ መሆናቸውን ያምኑ ነበር። አንዳንድ የፍልስፍና አስተሳሰቦችን በተለይም ከግብፅም ሆነ ከህንድ ቢወስዱም፣ ለፍልስፍና መልክ የሰጡትና የዕውቀት ሁሉ አባቶች እንዲሆን ያደረጉት የግሪክ ፈላስፎች ናቸው። በተለይም ፍልስፍናን ወደ ውጭ አውጥቶ በገበያ ላይ መከራከሪያ ማድረግና ሌላውን ቻሌንጅ ማድረግ በግሪክ ፈላስፋዎች የተስፋፋና ለዕውነተኛ ዕድገትና ነፃ አስተሳሰብ መዳበር አስፈላጊ መሆኑን ግንዛቤ የተደረሰበት ነው። በተለያዩ የግሪክ ፈላስፎች የዳበሩትን ዕውቀቶች ስናገላብጥ፣ የሰው ልጅ ዕድል ቀደም ብሎ እንደሚታመንበት በአምላኮች የሚደነገግ አልነበረም። የጥፋቱም ሆነ የጥሩ ዕድሉ ወሳኝ ራሱ የሰው ልጅ ብቻ ነው። ይህም ማለት የሰው ልጅ የማሰብ ኃይሉን መጠቀም ከቻለ ኑሮውን ለማሻሻል ሲል የግዴታ መሳሪያም የሚፈጥርና እስከተወሰነ ደረጃም ድረስ ተፈጥሮ የምታደርስበትን አደጋ በመቋቋም ወደፊት መራመድ ይችላል። ከዚያም በመቀጠልም ስርዓትና የተረጋጋ ህብረተሰብ በመፍጠር ለተከታዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይችላል። የሰውን ልጅ የስልጣኔ ታሪክ ካለብዙ ጭንቀት ስንመረምር የበለጠ ነፃ በሆነ ቁጥር የማሰብ ኃይሉ ይዳብራል። የመፍጠር ኃይሉ ይጨምራል። ስርዓትና ስምምነትን ከጭንቅላቱ ጋር በማዋሃድ የተሻለ ኑሮ ይመሰርታል። ነፃነት በሌለበት ቦታ ደግሞ የሰው ልጅ የተፈጥሮ አደጋ ሰለባ ይሆናል። ለበሽታና ለረሃብ ይጋለጣል። ተፈጥሮን የመቆጣጠርና ልዩ ልዩ ነገሮችን እያመረተ ለመጠቀም ያለው ኃይል ይዳከማል። ይህ ሁኔታ በተለይም በአውሮፓ ምድር ውስጥ የካቶሊክ ሃይማኖት ባየለበት ከክርስቶ ልደት በኋላ ከሰድሰተኛው ክፍለ-ዘመን እስከ አስራአምስተኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የአውሮፓ ህዝብ በጨለማ ዓለም ውስጥ እንዲኖር አድርጎታል። ይህ የጨለማ ዘመን ሊደመሰስ የቻለው በሪናሳንስ እንቅስቃሴ፣ ቀጥሎ ደግሞ በሪፎርሚሽን፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ግኝት አማካይነት ነው። ያረጀውና ህብረተሰቡን ተብትቦ የያዘው ስርዓት በአዲስ ዕውቀት ሲፈተንና ግፊት ሲገጥመው ለአዲሱ ቦታውን በመልቀቅ የአውሮፓ ህዝብ፣ ዕደ-ጥበብን፣ ንግድን ማስፋፋት፣ ከተማዎችን መገንባትና ሌሎች ተዓምር የሆኑ ስራዎችን መስራት ቻለ። ይህ ሁሉ የተገኘው ከላይ በተወረወረ ወይም በገዢዎች ቡራኬ ሳይሆን የዕውነተኛ ነፃነትን ትርጉም በተረዱና ራሳቸውን ለመሰዋት በተዘጋጁ ኃይሎች አማካይነት ነው። የነፃነት ትግል አልፎ እልፎ ካልሆነ በስተቀር የተጀመረውና መስመርም መያዝ የቻለው በግለሰብ ታታሪዎች አማካይነት ነው። ይህ ዐይነቱ ትግል በተገለጸላቸው ቄሶች፣ ፈላስፎችና ሳይንቲስቶች፣ እንዲሁም የልዩ ልዩ ጥበብ አዋቂዎች የተቀነባበረ የጭንቅላት ትግልና ተግባራዊም የሆነ ነው። ስለዚህም ከጥንት ዘመን ጀምሮ ለነፃነት የተደረገው ትግል ቁንጽል ሳይሆን ሁለንታዊና የሰውን ልጅ ብቁ(Perfect)እንዲሆን ከማድረግ ጋር የተያያዘ ነው። ካንት እንደሚለው የሰው ልጅ ማቴሪያላዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም ነው። የመንፈስ ደስታውን የሚጎናፀፈው የግዴታ በሚያገኘው ገቢ ብቻ ሳይሆን መንፈሱ የሚያድስልትን ነገርም የተጎናፀፈ እንደሆን ብቻ ነው። መንፈሳዊ ደስታዎች በልዩ ልዩ ነገሮች ነገር ግን ደግሞ በረቁቁም ሆነ በቀጥታ በሚታዩና ርካታን በሚሰጡ የሚገለጹ ናቸው። የተለያዩ ሰዎች አንድ ዐይነት ስሜት ስለማይኖራቸው የሚረኩበት የመንፈስ ደስታም ይለያያል። እንዲሁም የንቃተ-ህሊናቸው ደራጃ የመንፈስ ርካታቸውን ሁኔታ ሊወስነው ይችላል።

አብዛኛውን ጊዜ ስለነፃነት የሚጽፉ ኢትዮጵያውያንም ሆነ አንዳንድ በኒዎ-ክላሲካል የኢኮኖሚክስ ትምህርት የተካኑ የአውሮፓ ምሁራን የነፃነትን ትርጉም ከገበያ ኢኮኖሚ ጋር ነው ለማያያዝ የሚሞክሩት። ይህ ዐይነቱ አቀራረብ የታሪክን ሂደት የሚያጣምም ብቻ ሳይሆን፣ ነፃነት የሚለውን ትርጉም እጅግ በጠባቡ እንድንረዳና የንግድ ሰዎች ብቻ እንድንሆን የሚያደርገን ነው። ስለዚህም ነው ከአስራሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ በጀርመንና በእንግሊዝ ፈላስፋዎች መሀከል የጦፈ ትግል የተካሄደው። የጀርመን ፈላስፋዎችና ሳይንቲስቶች መንገድ የበለጠ ነገሮችን ወደ ውስጥ ጠለቅ ብሎ እንድንመረምር የሚያስችለን ሲሆን፣ የእንግሊዞቹ ደግሞ በቀጥታ በምናየው ላይ ብቻ ያተኮረና የአንድን ነገር ርስ በርሱ መያያዝና ውስጣዊ ኃይል እንዳለው እንድንገነዘብ የሚያደርገን አይደለም። ለምሳሌ የአዳም ስሚዝን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ስንወስድ በኒውተን አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ነው። በኒውተን ዕምነት ተፈጥሮና ህዋ ርስ በራሳቸው የተያያዙ አይደሉም። ማንኛውም ነገር ወደ ጥቃቅን ነገር፣ ለምሳሌ እንደ አቶም ተበጣጥሶ የሚቀነሰና የሚታይ ነው። እነዚህ ተበጣጥሰውና ተሰበጣጥረው የሚገኙ ነገሮች በተፈጥሮ ውስጥ በሚገኝ ህግ የሚተዳደሩ ስለሆነ፣ እግዚአብሔር ከውጭ ሆኖ ድርጊታቸውንና እንቅስቃሴያቸውን የሚመለከት ነው። ጣልቃ አይገባም። ተፈጥሮም ስርዓት ያላትና በተወሰነ የአርቆ አስተሳሰብ ሎጂክ ስለምትዳደር፣ የሰው ልጅ ይህንን የተፈጥሮን ህግ የመረዳት ኃይል ይኖረዋል። የስው ልጅ እየረቀቀና እያሰበ ሲሂድ በማቲማቲክስ ፎርሙላ አማካይነት አንድን ነገር መረዳት ይቻላል። ልምምድና ነገሮችን ጠጋ ብሎ መመልከትና መመርመር ቦታ የላቸውም። ይህ አሰተሳሰብ ወደ ኢኮኖሚክስ ሲተረጎም በአንድ ህበረተሰብ ውስጥ የሚኖር እያንዳንዱ ግለሰብ በራሱ ዓለም ብቻ የሚሽከረከር ነው። ለራሱ ጥቅም በሚያደርገው እሽቅድምድምና በማይታየው ወይም በረቀቀው እጁ(Invisible Hand) አማካይነት በህብረተሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ መዛባቶችን ወደ ሚዛናዊነት እንዲመጡ ያደርጋቸዋል። ከፍ ብለን ስንሄድ ደግሞ በዛሬው የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚክስ ቲዎሪ መሰረት፣ እግዚአብሄር በፈጠረው ተፈጥሮ ላይ ጣልቃ የማይገባውን ያህል፣ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በሚከሰትበትና ብዙ ህዝብን በሚያሰቃይበት ጊዜ መንግስታት ጣልቃ መግባት የለባቸውም፤ በገበያው ውስጥ ያሉ ኃይሎች በራሳቸው ኃይል ቀውሱን ስለሚያርሙ መንግስታት ዝም ብለው ነው መመልከት ያለባቸው። ኢኮኖሚውን ከገባበት ቀውስ ለማውጣት ጥረት ማድረግ የለባቸውም። ወደ አዳም ስሚዙ ስንመጣ ደግሞ የሰው ልጅ ወደ ምርትና ወደ ፍጆታ(Homo Economicus) ተቀንሶ የሚታይ ነው እንጂ ሌሎች መንፈሱን የሚያድሱ ፍላጎቶች የሉትም።

ከዚህ ጋር በተያያዘና እንዲሁም ደግሞ የነፃ ንግድንም ሆነ ነፃ ገበያን በህብረተሰብ ግንባታ ውስጥ ያለውን ቦታ በሚመለከት እንደዚሁ የጦፈ ትግል ተካሂዷል። በሌላ አነጋገር፣ የጀርመን ክላሲኮች የገበያን ኢኮኖሚ ባይቃወሙም ከህብረተሰብና ከአገር ግንባታ ውጭ ተነጥሎ መታየት እንደሌለበት ያስተምራሉ፤ ያሳስባሉ። ምክንያቱም በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ዜጋ በስራ-ክፍፍል ቢለያይምና በገበያ አማካይነት የሚገናኝና የሚተሳሰር ቢሆንም፣ ይህ ዐይነቱ ግኑኝትና የስራ-ክፍፍል ጠንካራ አገርንና ህብረተሰብን ከመመስረት ተነጥሎ መታየት የለበትም። ማንኛውም ግለሰብም በመነጣጠል ሳይሆን ዕውነተኛ ነፃነቱን የሚቀዳጀውና ኢኮኖሚውንም በጠንካራ መሰረት ላይ ገንብቶ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችለው፣ በአንድ ባንዲራ ስርና ለአንድ ዓላማ የቆመ እንደሆነ ብቻ ነው። በተለይም ህብረ-ብሄሮች እየተመሰረቱና አንዳንድ አገሮች ጠንካራ ኢኮኖሚ እየገነቡ ሲመጡ፣ በብዙ መሳፍንቶች ተከፋፍላ የምትገዛውና የውጭ ወራሪዎች ሰለባ የሆነችው ጀርመን በኢኮኖሚ ዕድገት ወደ ፊት መግፋት አልቻለችም። በፈላስፋዎችና በሌሎች ምሁራን ዕምነት ትናንሽ አገሮች እዚያው በዚያው ተከፋፍለው የሚኖሩ ከሆነ ህዝቦቻቸው በፍጹም ዕውነተኛ ነፃነትንና ዕድገትን እንደማጎናጸፉ፣ ስለሆነም ይህ ዐይነቱ ክልላዊ አስተዳደር ቆሞ ጀርመን በአንድ አገዛዝ ስር መተዳደር እንዳለባትና፣ የጉምሩክ ኬላዎችም መጥፋት እንዳለባቸው ስምምነት ላይ ደረሱ። በዚህም አማካይነት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ብቻ ሳይሆን ግለሰብአዊ ነፃነትም ቀስ በቀስ ተግባራዊ እንደሚሆን ግልጽ ነበር። ምክንያቱም ማቴሪያላዊ ዕድገት በሌለበትና፣ አንድ አገር በተለያዩ የመገናኛ መስመሮች እስካለተያያዘና፣ ህዝቡም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መንቀሳቀስ እስካልቻለ ድረስ ዕውነተኛ ነፃነትን በፍጹም ሊቀዳጅ አይችልምና። በመሆኑም ግለሰብአዊና ህብረተሰብአዊ ፍላጎቶች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉትና አንድም ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊጎናጸፍ የሚችለው ከክልሉ ወጣ ብሎ ማሰብ ሲችልና፣ ከሌላው ጋር በተለያዩ መልኮች ግኑኝነቱን ሲያጠናክር ብቻ ነው። በተጨማሪም ግለሰብአዊ ፍላጎቶች ሊሟሉና እያደጉ ሊሄዱ የሚችሉት አንድ አገር በቴክኖሎጂ እየመነጠቀች ስትሄድ ብቻ ነው። ይህ ዐይነቱ ሂደት ግለሰብአዊ ነፃነትን የሚፃረር ቢመስልም፣ ማንኛውም ግለሰብ ዕውነተኛ ፍላጎቱን ሊያረካ የሚችለው እንደ ሮቢንሰን ክሩሶ በደሴት ላይ ብቻ በመኖርና በመታገል ሳይሆን፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ በተቀናጀ፣ ይሁንና ደግሞ ነፃነትን በማያፍን ህብረተሰብ ውስጥ ነው። ከዚህ አንፃር ነው እነ ላይብኒዝ ሲያስጠነቅቁ የነበረው። በኢምፔሪሲዝምና በነፃ ገበያ ስም ተሳቦ የሚሰበከው ነፃነት የመጨረሻ መጨረሻ ግለሰቦችን ወደ ርስ በርስ ጦርነት እንዲያመሩ የሚያደርግ፣ ወይም ደግሞ ዛሬ እንድምናየው ዓለም ጥቂት ኃይሎች የራሴ ጥቅም ተደፈረብን በማለት አገር የሚያተራምሱበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለው በመስጋት ነው የእንግሊዝ ፈላስፎችን አስተሳሰብ አጥብቀው ይዋጉ የነበረው። የእነ አዳም ስሚዙ የነፃ ገበያ አሰተሳሰብና የነፃነት ትርጉም በጥቂት ኃይሎችና ፍላጎት በፎርማል ደረጃ የሚታይና የሚገለጽ ሲሆን፣ በመሰረቱ የሩሶንና የካንትን የነፃነት ትርጉም ወይም አስተሳሰብ የሚቃወም ነው። ምክንያቱም በግል ሀብት አማካይነት የናጠጡ ኃይሎች ከመንግስት መኪና ጋር በመቆላለፍ በነፃነት ስም ሌላውን የነሱ ተገዢና በነሱ ፈቃድ ብቻ እንዲተዳደሩ ስለሚያደርጉ ነው። እዚህ ላይ የግል ሀብትን ለመቃውም ሳይሆን፣ ቁጥጥር የማይደረግበት የሀብት ማጋፈፍ የግዴታ ስላምን ያሳጣል። በሀብት የናጠጡ ለሌላው ደንታ ስለማይኖራቸው ጦርነትን ይናፍቃሉ። መንፈሳቸው ባካበቱት ኃይል ስለሚሸፈን ጦርነት ቢቀሰቀስ እነሱ ከጦርነት የሚድኑ ይመስላቸዋል። ስለዚህም ነው የጀርመኑ ሰብአዊነት ከተደመሰሰ በኋላ በአስራስምንተኛውና በአስራዘጠናኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ ላይ ብቅ ያሉት አዳዲስ የጀርመን ምሁራን የእንግሊዙን ልቅ የነፃ ገበያ ስልት በመቃወም ህብረተሰብአዊና ማህበረሰብአዊ ኃላፊነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተግባራዊ መሆን እንዳለበት አጥብቀው ይታገሉና ያሳስቡ የነበረው።

የነፃ ገበያና የነፃ ንግድ አስተሳሰብ በአሸናፊነት ከወጣ ከ18ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ በዚያው መጠንም የኃይል አሰላለፍ ይለወጣል። የሀብት ቁጥጥርና ክፍፍልም ልዩ መልክ እየያዘ ይመጣል። በካፒታሊስት ህብረተሰብ ውስጥ ሁሉም በዕኩልነት ደረጃ ሀብት መቆጣጠር የማይችሉበት ሁኔታ ይፈጠራል። ስለዚህም ህግና የህግ የበላይነት ከዚህ አዲስ የህብረተሰብ ግኑኝነት አንፃር የሚነደፉ ሆኑ። ቀስ በቀስ የተገነባውን የኃይል አሰላለፍ የሚያረጋግጡ ናቸው ማለት ነው። የገበያ ኢኮኖሚና የነፃ ንግድ ደግሞ የርዕዮተ-ዓለም ተቀባይነት እንዲኖራቸው የሚሰበክባቸው መሳሪያዎች ወደ መሆን አመሩ። ማንኛውም ግለሰብ በነፃ ገበያ አማካይነት ብቻ ዕውነተኛው ነፃነቱን የሚቀዳጅ ነው በሚል በከፍተኛ ደረጃ መሰበክ ተጀመረ። ይሁንና ይህ ዐይነቱ የነፃ ገበያ በጥቂት ካፒታሊስቶች ቁጥጥር ስር ያለና፣ ማንኛውም ግለሰብ የራሱንም ቢሆን ጥቂት መጦሪያ እንኳ እንዳያዳብር የሚያግድ ነው። በተለይም የፊናንስ ካፒታሊዝም እያደገ ሲመጣ፣ ጥቂቱ ብቻ የብድር ዕድል በማግኘት አብዛኛውን የህዝብ ሀብት የሚቆጣጠርበት ሁኔታ መፈጠር ቻለ። እንደመሬት የመሳሰሉትም የተፈጥሮ ሀብቶች ወደ ሸቀጣ ሸቀጥነት በመለወጥ ጥቂት ግለሰቦች፣ ባንኮችና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚቆጣጠሩበት ሁኔታ ተመቻቸ። እንደዚህ ዐይነቱን የግል-ሀብት ዘረፋና ድህነትን የሚያስፋፋ ፖሊሲን የሚቃወም በክፉ ዐይን የሚታይና ለክፉ አደጋ የሚጋለጥ ሆነ። በዚህ መልክ የነፃነት ትርጉም በካፒታሊዝም የቴክኖሎጂና የሳይንስ ዕድገት፣ እንዲሁም የሀብት ክምችት ዘዴ በመጣመም፣ ሰፊው ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ የማይችልበት ሁኔታ ተፈጠረ።

ካፒታሊዝም ለመጨረሻ ጊዜ የበላይነትን ከተቀዳጀ ከ19ኛው ክፍለዝ-ዘመን ጀምሮ በነፃ ገበያ ስም የተሰበከው ነፃነትን መቀዳጀት ተግባራዊ እንዳልሆነ በዘመኑ የተደረገውን ካፒታሊዝምን የሚጻረር ትግል መመልከቱ ይበቃል። በኢንዱስትሪ አብዮት አማካይነት ከእርሻ መሬት እየተፈናቀለ ስራ ለመፈለግ ሲል ወደ ዋና ከተማዎች እንዲፈልስ የተደረገው ጉልበቱን ከመሽጥ በስተቀር ሌላ ነፃነት እንዳልነበረው በዚህ አካባቢ የተጻፉ አያሌ መጽሀፎች ያረጋግጣሉ። ሰፊው ስራ ፈላጊ ህዝብ እንደ ቆሻሻ የሚታይና በየመንገዱ ላይ የሚያድርና፣ ከመንገድ ላይ ምግብን እየፈለገ የሚመገብ ነበር። በየፋብሪካው ተቀጥሮ የሚሰራው ሰራተኛ ደግሞ ለአሰሪው ታዛዥ ከመሆን በስተቀር በሙያ ማሀበር የመደራጀት መብት እለነበረውም። እጅግ በሚያሰለች መልክ ከማሽን ጋር እየታገለ ከማምረት በስተቀር ብሶቱንና ፍላጎቱን የመግለጽ መብት አልነበረውም። እንደዚህ ዐይነቱ ሁኔታ ሰፍኖ ይገኝ የነበረው ከሶስት መቶ ዐመት በፊት የሰውን ጭንቅላት የሚያድስ የባህል አብዮት ከተካሄደና፣ በተከታዩ ደግሞ ኤላይንተሜንት የተባለው በሞናርኪዎች ፍጽም አገዛዝ ላይ የተነሳው ምሁራዊ እንቅስቃሴ ብዙ የአውሮፓ አገሮችን ካዳረሰ በኋላ ነው።

በ20ኛው ክፍለ-ዘመን ካፒታሊዝም በማያወላውል መልክ የበላይነትነትን ሲቀዳጅ የሰው ልጅ ነፃነት በፍጆታ ግዢና ጥቅምን ከማሳደግ አንፃር ብቻ የሚታይ ሆነ። ማንኛውም ግለሰብ በገበያ ፊት ቢያንስ በፎርማል ደረጃ ነፃ ሆኖ የሚታይ ሆነ። ይህም ማለት ነፃንቱ ሊወሰን የሚችለው ባለው የመግዛት ኃይል(Effective demand) ብቻ ነው። በሌላ አነጋገር የነፃ ገበያ እዚያው በዚያው የማግለል ባህርይም አለው ማለት ነው። በዚህ መልክ ካፒታሊዝም በአገር ደረጃ መወሰኑን ሲያቆምና ዓለም አቀፋዊ ባህርይ ሲወስድ በትምህርት ደረጃ የኢኮኖሚክስ ትምህርት የሰውን ልጅ የነፃነት ትርጉም በዚህ የአስተሳሰብ ክልል ብቻ እንዲወድቅ አደረገ። በንግድ አማካይነት ሁሉም አገሮች የሚተሳሰሩበት ሁኔታ ተፈጠረ። በማምረት አማካይነት ሳይሆን አንድ ህብረተሰብ የሚሻሻለው በንግድ አማካይነት ከሌላው ዓለም ጋር የተሳሰረ እንደሆነ ነው የሚለው በሰፊው መሰበክ ተጀመረ።

በአስራሰባተኛውና በአስራምንተኛው ክፍለ-ዘመን ብቅ ያሉት የእንግሊዝ ፈላስፎችና የነፃ ገበያ አራማጆች እዚያ በዚያው የቅኝ ግዛት አራማጆች የነበሩ ያዋቀሩት እንደ ኢስት- ኢንዲያን ካምፓኒ(East Indian Company) የመሳሰሉት አዲስ በተፈጠረው ዓለም አቀፋዊ ግኑኝነት ልዩ አወቃቀር በመያዝ ዛሬ የሶስተኛው ዓለም ተብለው የሚጠሩ አገሮችን ወደ ተራ ጥሬ-ሀብት አምራችነት መለወጥ ቻሉ። የነፃነት ትርጉምም በዚህ የንግድ እንቅስቃሴ ክልል ውስጥ የሚታይ ሆነ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ቀደም ብለው የተዋቀሩ የስራ-ክፍፍሎችና የህብረተሰብ አወቃቀሮች እንዲጨናገፉ በመደረግ ቀስ በቀስ እያለ በማደግ ላይ ባለው ግሎባል ካፒታሊዝም መዳፍ ስር እንዲወድቁ የተደረገው። ልክ ሩሶና ካንት እንዳስተማሩን አንድ ሰው የሌላው ጥገኛና ታዛዥ ከሆነ ነፃነቱን ተገፈፈ ማለት ነው ብለው እንዳስተማሩን፣ በግሎባል ካፒታሊዝም ስር የተዋቀረው ዓለም አቀፋዊ ንግድ በብዙ ሚሊዮን የሚጠጉ የሶስተኛውን ዓለም አገር ህዝቦች ወደ ባርነት ለወጣቸው። ይህም ማለት አንድ ሰው ወደ ተራ አምራችነት ከተለወጠ እግዚአብሔር የሰጠውን የመፍጠር ኃይል ተነጠቀ ማለት ነው። ባርያ ሆነ ማለት ነው። በማሰብ ኃይሉ ልዩ ልዩ ነገሮችን በመፍጠርና በማምረት ፍላጎቱን አሟልቶ ወደ ህብረተሰብ ኃይል ሊሸጋገር አይቸልም። ነፃ አገር ሊመሰርት አይችልም። ከዚህ በመነሳት ነው በኛና በተቀሩት የሶስተኛው ዓለም አገሮች ሊኖር የሚገባውን የነፃነት ትርጉም ምንነት መረዳት የምንችለው። በሌላ አነጋገር አገዛዞች ቢለዋወጡም አንኳ፣ ይህ ዐይነቱ ዕውነተኛ ነፃነትን የሚያፍን የስራ-ክፍፍልና የነፃ ንግድ የሚለው አስተሳሰብ እስካለተናጋና መሰረታዊ የአስተሳሰብና የአመራረት ለውጥ እስካልተካሄደና ተግባራዊ እስካልሆነ ድረስ፣ ነፃነት ያስፈልጋል የሚለው አባባል ለአብዛኛው ህዝብ ትርጉም አይኖረውም ማለት ነው።

ያም ሆነ ይህ ለግለሰብአዊም ሆነ ለህብረተሰብአዊ ነፃነት የተደረገው ትግል በተወሰኑ ነገሮች ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን ከአጠቃላዩ የህብረተሰብ አወቃቀር ጋር የተያያዘ ነው። ይህም ማለት በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የተዋቀረው መንግስታዊ መኪና፣ የምርት ግኑኝነት፣ ባህላዊና ርዕዮተ-ዓለማዊ ጉዳዮች፣ የጠቅላላው የህዝቡ አኗኗር ጉዳይ፣ መንግስትና አገዛዙ ዕድገትንና ስልጣኔን በሚመለከት ያላቸውን አሉታዊ ተፅዕኖ፣ … ወዘተ.፣ እነዚህና ሌሎችንም፣ ለአንድ ግለሰብም ሆነ ለጠቅላላው ህብረተሰብ ዕድገት እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን የመመርመሩና እነዚህን የመታገሉ ጉዳይ የነፃነት ትግል መሰረታዊ ሃሳቦች ናቸው። በሌላ ወገን ደግሞ ለነፃነትና ለነፃ ሃሳብ እንታገላለን የሚሉ ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ከአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የሚፈልቁ ሲሆን፣ ከነበረው ለዕድገትና ለስልጣኔ ከማያመች ሁኔታ ቀድመው የሄዱና፣ የአንድም ህብረተሰብ ዕድል በእንደዚህ ባለ የጨለማና የተዝረከረከ ኑሮ መወሰን እንደሌለበት የተረዱ ናቸው። ይህም ማለት ጭንቅላታቸውን ሙሉ በሙሉ ከፊዩዳላዊ ወይም ከኋላ-ቀር አስተሳሰብ ያጸዱ ሲሆን፣ የነፃነትን መሰረታዊ ሃሳብ በፍልስፍናና በቲዎሪ መሳሪያ በሰፊው እያብራሩ ማስተማር የሚችሉ ናቸው። በአውሮፓ የህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ ለግለሰብአዊና ለህብረተሰብአዊ ነፃነት የተደረገውን ትግል ስንመለከት በመጀመሪያ ደረጃ በጠብመንጃና በመጋፈጥ የተደረገ ትግል ሳይሆን በከፍተኛ የጭንቅላት ምርምር፣ አርቆ-አስተዋይነትን(Rationality)፣ ህብረተሰብአዊ ኃላፊነትን(Awareness)፣ የሌላውን ሰው የኑሮ ሁኔታ መሰማትንና(Feeling) ሌሎችንም ነገሮችን ያካተተ የትግል ዘዴ ነው። እንደዚህ ዐይነቱ የትግል ዘዴ በየኤፖኩ መልኩን ይለዋውጥ እንጂ፣ የመጨረሻ መጨረሻ ዋናው ዓላማው አንድን ህብረተሰብ ወይም ህዝብ የማንም ተገዢ እንዳልሆነና፣ ማንኛውም ግለሰብ የራሱን ዕድል በራሱ መወሰን እንዳለበት ለማስጨበት ሲሆን፣ በዚህም አማካይነት ታሪክን ሰርቶ በስምምነትና በሰላም እንዲኖር ለማድረግ ነው። እንደዛሬው በጊዜው የነበረው ግንዛቤ የሰላምና የነፃነት ጠንቅ የሚሆኑ ስልጣንን የጨበጡና በሀብታቸው የሚመኩ ናቸው። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ኃይሎች የማሰብ ኃይላቸውን መጠቀም ስለማይችሉና ሀብት ካላቸው ጋር በጥቅም ስለሚተሳሰሩ አንድ ህዝብ ነፃነቱን እንዳያገኝ የተለያየ ዘዴ በመፍጠር ፍዳውን ያሳዩታል። በዚህም ምክንያት የተነሳ የዕድገት እንቅፋት በመሆን አንድ ህዝብ በዘለዓለማዊ ድህነት ውስጥ እንዲኖር ያደርጋሉ። በአንድ አገር ውስጥ የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብት ቢኖርም እንኳ ሰፊው ህዝብ እነሱን በስነስርዓት አውጥቶ ቅርጽ በመሰጠትና በመለወጥ አዲስ ህይወት እንዳይገነባ ያግዱታል። ኑሮው ሁሉ እንዲጨልም ያደርጋሉ። ስለሆነም ነው በአውሮፓ ምድር ውስጥ በፍልስፋናና በሳይንስ አማካይነት ህብረተሰቡን ነፃ ለማውጣት እልክ ያስጨረሰ ትግል የተካሄደው። ትግሉን የጀመሩት ደግሞ ተራ ሰዎች ወይም ቃልን በመወርወር በሚዝናኑ ሰዎች ሳይሆን፣ ልክ ከእግዚአብሄር የተላኩ ይመስል የራሳቸውን ህይወት በመሰዋት አንድን ህዝብ ከጨለማ ኑሮ ማውጣት አለብን ብለው ቆርጠው በተነሱ ሰዎች ነው። ሶክራትስን እግዚአብሄር ከሰማይ ዱብ አድርጎ የላከው ፍጡር ነው ማለት ይቻላል። ሌሎችም እንደ ፕላቶንና አርስቴቶለስ፣ እንዲሁም አያሌ የግሪክ ፈላስፋዎች፣ የሳይንስና የድራማ ስዎች እንደዚሁ ልዩ ፍጡሮች ናቸው። የኋላ ኋላም ብቅ ያሉት፣ እንደ ቄስ ኩዛኑስ፣ ዳንቴ፣ ዳቪንቺ፣ ጋሊልዮ፣ ኬፕለር፣ ላይብኒዚ፣ ሺለርና ካንት፣ እንዲሁም ሌሎችም እነሱን የመሳሰሉት የጀርመን አይዲያሊስቶች ዕንቁ ጭንቅላት የነበራቸውና ከተንኮል አስተሳሰብም የጸዱ ሲሆን፣ ዕውቀታቸውም ዓለም አቀፋዊ ባህርይ ያለው ነው። ስለሆነም ነው የአውሮፓ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የዓለም ህዝብ በጠቅላላው ከጨለማ በመላቀቅ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር እርስ በርሱ መገናኘት የቻለው።

ከዚህ ዐይነቱ የተወሳሰበና ከፍተኛ የጭንቅላት ምርምርን ከሚጠይቅ ትግል የምንገነዘበው ሀቅ፣ አንድ ሰው ነፃነት የሚለውን ጽንሰ-ሃሳብ ከመወርወሩ በፊት ራሱ የቱን ያህል ነፃ እንደወጣ ማሳየት መቻል አለበት። በሌላ አነጋገር ጭንቅላቱ ከማንኛውም እቡይ አስተሳሰቦች የጸዳና፣ የአንድን ህብረተሰብ አስቸጋሪ ሂደት የተረዳና፣ ይህንንም በጥሩ የቲዎሪና የፍልስፍና መነጽር መመርመር የሚችል መሆን አለበት። በበሁለተኛ ደረጃ፣ ዕውነተኛ ነፃነት በጉልበት ወይም በጠብመንጃ የማይገኝ መሆኑን የተገነዘበ መሆን አለበት። ይሁንና ግን አንድ አገዛዝ ወደ ቲራንነት ከተለወጠና ከፍተኛ በደል የሚፈጽም ከሆነ ለዚህ ጸሀፊ አመጻዊ ትግል አስፈላጊ እንደሆነ ይገነዘባል። አንድ አገዛዝ በማንኛውም ጊዜ ቢሆን በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ስዎችን ቀርቶ አንድን ሰው እንኳ የመግደል መብት የለውም። ከዚህም በላይ አንድ አገዛዝ ቆርጦ በመነሳት ዕድገትን የሚቀናቀን ከሆነ የግዴታ አመጻዊ ትግል ከፍልስፍናና ከቴዎሪ ጋር እየተጋዘ ተግባራዊ መሆን አለበት። በሶስተኛ ደረጃ፣ ለነፃነት የሚደረገው ትግል የመጨረሻ መጨረሻ አንድን ህዝብ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት የሚያደርገው መሆን አለበት። በዚህም አማካይነት አንድ ህዝብ ጥበባዊ አገር ለመመስረት ወይም ለመገንባት መቻል አለበት። በሌላ አነጋገር፣ የአንድ አገር ህዝብ ኑሮ በቆንጆ ከተማዎችና፣ በቆንጆ መንደሮች የሚገለጽ መሆን አለበት። በባህላዊ ዕድገት የሚታይ መሆን አለበት። አንድ ህዝብ ከልማዳዊ ኑሮ ተላቆ ህይወቱን በአዲስ መልክ ማደራጀት መቻል አለበት። በአራተኛ ደረጃ፣ ዕውነተኛ ነፃነት አንድን ህዝብ የስልጣን ባለቤት(Empower) የሚያደርገው መሆን አለበት። ይህ ሲሆን ብቻና፣ በየጊዜው እየነቃ ሲሄድ አንድ ህዝብ በእርግጥም ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ ይችላል።

ወደ አገራችን ስንመጣ እስካሁን ድረስ ለነፃነት የተደረገው ትግል ግቡን መምታት ያልቻለው ከላይ የተዘረዘሩትን መሰረተ-ሃሳቦች ማሟላት ባለመቻሉ ነው። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በአጠቃላይና፣ ብሄረሰቦች በተናጠል በሳይንስ፣ በፍልስፍና፣ በስዕል፣ በድራማ፣ በአርክቴከቸርና በከተማ ግንባታ፣ በዕደ-ጥበብ ሙያና በንግድ እንቅስቃሴ የሚገለጽ ምሁራዊ እንቅስቃሴ አልነበራቸውም። ህብረተሰባችንም የተገለጻለቸው ምሁሮችን የማፍራት ዕድል አልነበረውም። በዚህም ምክንያት የተነሳ አገዛዞችንና ልማዳዊ የአኗኗር ስልትን የሚጋፈጥና ሌላ የዕድገት አቅጣጫን ሊያሳይ የሚችል ወይንም አዲስ የህይወት ብርሃንን ሊያፈናጥቅ የሚችል ኃይል ሊፈጠር አልቻለም። ስለሆነም ህዝባችን የተፈጥሮን ምንነት ተገንዝቦ ወደ ተወሳሰበ የህብረተሰብ ግንባታ ለመጓዝ የሚያስችል መንፈሳዊ ኃይልን ሊቀዳጅና ኑሮውን በአዲስ መልክ ሊያደራጅ አልቻለም። የጠቅላላው ህዝብ ኑሮ ተደጋጋሚና የዘልማዳዊ ኑሮ በመሆኑ ለፈጠራ አያመችም ነበር። በዚህም ምክንያትና በሌሎች አያሌ ምክንያቶች የተነሳ የነፃነትን ትርጉም ተረድቶ በከፍተኛ እምርታ ሊታገል የሚችል ኃይል ብቅ ሊል አልቻለም። አብዛኛውን ጊዜ ባለማወቅ የተነሳ የተዋቀረው ጠቅላላው ስርዓትና ከዚህ የፈለቀው አስተሳሰብ በራሳቸው የነፃነት ተቀናቃኝ በመሆናቸው በቴክኖሎጂና በልዩ ልዩ ነገሮች ሊገለጽ የሚችል ዕድገት ሊታይ አልቻለም።

በአለፉት ሃምሳ ዐመታት ለዲሞክራሲና ለነፃነት የተደረገውን ትግል ስንመለከት፣ ይደረግ የነበረው ትግል ጠቅላላውን ህብረተሰብአዊ አወቃቀርና የህዝቡን የአስተሳሰብ መነሻ አድርጎ ከመመርመር ይልቅ በተወሰኑ ነገሮች ላይ ብቻ በማትኮር ነበር። በአገራችን የተለመደ አንድ አነጋገር አለ። ለዕድገት ጠንቅ የሆኑት አገዛዙና ስርዓቱ ናቸው የሚል ተራ አባባል አለ። በሌላ በኩል ግን ለምን አገዛዙና ስርዓቱ ለዕድገት ጠንቅ ሆኑ? ተብሎ ጥያቄ አይቀርብም። በማወቅ ወይስ ባለማወቅ ? የዕድገት እንቅፋት ሊሆኑ ቻሉ ብሎ ነገሩን ዘርዘር አድርጎ ለመጠየቅ ሙከራ አይደረገም። እንደሚታወቀው አብዛኛውን ጊዜ እንደዚህ ያሉ ለዕድገት ጠንቅ የሆኑ ፊዩዳላዊ ስርዓትን የመሳሰሉት የሚዋቀሩት በማወቅ አይደለም። ህብረተሰቦች በጨቅላ ዘመን በሚገኙበት ወቅት እንደዚህ ዐይነት ዕድገትንና ስልጣኔን የሚቀናቀኑ በተለያየ መልክ የሚገለጹ የአሰራርና የአመራረት ስልቶች መፈጠራቸው እንደተፈጥሮአዊ ሆነው የሚታዩ ናቸው። ጭቆናዎች ሲበዙና የህዝቡም ኑሮ ባለበት የረጋ ከሆነ ይህ ዐይነቱ ሂደት ትክክል ሆኖ የማይታያቸው ምሁራን ከመቅጽበት ፍልቅ የሚሉበት ጊዜና ቀስ በቀስም አስተሳሰባቸውን በማዳበርና በማስፋፋት ስርዓቱን የሚጋፈጡበት ጊዜ አለ። ይህ ዐይነቱ የመመራመርና የመጋፈጥ ባህል ወይም ልምድ ወይም ደግሞ ደቀ-መዝሙሮችን የማፍራት ባህል ባልተለመደበት አገር ህብረተሰቦች ባሉበት ረግጠው እንዲቀሩ ይገደዳሉ። በዚህም ምክንያት ነው የኢትዮጵያው ፊዩዳላዊ ስርዓት በተለይም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ግዛት ለስምንት መቶ ዐመታት ያህል ተንሰራፍቶ መቆየት የቻለው።

የተማሪው እንቅስቃሴ የፊዩዳሉ ስርዓት፣ የኋላ ኋላ ደግሞ ከቢሮክራሲ ካፒታሊዝምና ከኢምፔሪያሊዝም ጋር በመቆላለፍ ለዕድገት ተቀናቃኝ ነው ብሎ ውሳኔ ላይ ሲደርስ፣ በእኔ ዕምነት በተለይም ስርዓቱ ለምን እንደ አውሮፓው ፊዩዳሊዝም ውስጣዊ ኃይል አግኝቶ ሊዋጋው የሚችል ውስጣዊ ኃይል ሊያፈልቅ አልቻለም? ብሎ ጠለቅ አድርጎ በመመራመር በሰፊ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ሊጋፈጠው አልቻለም። ስርዓቱን ሊቀናቀን የሚችል ውስጣዊ-ኃይል ሊፈልቅና ሊዳብር የሚችለው እንደሚታወቀው እያደገ ሊሄድ የሚችል የስራ-ክፍፍልና የንግድ እንቅስቃሴ ሲኖር ብቻ ነው። በተጨማሪም ከተማዎችና መንደሮች ሲቆረቆሩና ህብረተሰብአዊ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ(Social Mobility) ስርዓቱን የሚቀናቁኑ የተገለጸላቸው አዳዲስ ኃይሎች ብቅ ይላሉ። እንደሚታወቀውና ማርክስም እንደሚተነትነው ካፒታሊዝም ከማደጉና የበላይነትን ከመቀዳጀቱ በፊት ቅድመ-ሁኔታዎች የተጣሉት በፊዩዳላዊ ስርዓት ውስጥ ነው። በእኔ ዕምነት የተማሪው እንቅስቃሴ ይህንን ያልተገነዘበ ብቻ ሳይሆን፣ በአውሮፓ ምድር ውስጥ በሬናሳንስ፣ በሪፍርሜሽን፣ በኢንላይተንሜንትና፣ የኋላ ኋላ ደግሞ በትራንፎርሜሽን ዙሪያና በዘመናዊነት አካባቢ የተደረገውን ሰፋ ያለ ክርክር ጋር በበቂው የተለማመደ ባለመሆኑ የኢትዮጵያን ህዝብ ሰፋ ያለውን የዕድገትና የስልጣኔ ጥያቄ ቀነስ አድርጎ እንዲመለከተው ተገደደ። በመሆኑም ሶስት መፈክሮች ይዞ ሲነሳ በዚህ አማካይነት ብቻ ህብረተሰብአዊ ለውጥን እንደሚያመጣ ነበር የተገነዘበው። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ የተማሪው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ውጤት በመሆኑኗ፣ በተለያየ መልክ በሚገለጽ ሰፋ ያለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ጋር የተለማመደ ስላልነበር የግዴታ አመለካከቱ ውስን እንዲሆን አስገደደው። እየተከማቸ የመጣውን ችግር አገዛዙ መፍታት ሳይችልና፣ እንደመሬትና የብሄረሰብ የመሳሰሉት ጥያቄዎች እንደ መሰረታዊ አጀንዳዎች ሆነው ሲታዩ፣ በተለይም በአመራር ደረጃ ያለው የበለጠ ራዲካል እየሆነ መጣ። ይህ ኃይል የደመደመው አገዛዙን በመሳሪያ ታግዞ ከመጣል በስተቀር ሌላ አማራጭ እንደሌለ ነበር ታየው። በሌላ ወገን ደግሞ የአገራችንም ሆነ በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ የቅኝ አገዛዝንም ሆነ ቀጥተኛ ወረራን ለመዋጋት የጦፈ ትግል ይካሄድ ስለነበር ሁኔታዎቹ ሰፋ ካለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ይልቅ ለመሳሪያ ትግል የሚጋብዙ ነበሩ። መስረታዊ ችግር ይህ ቢሆንም፣ አብዮቱ ከፈነዳ በኋላ የተፈጠረው የዚህ ዐይነቱ ግልጽ ያልሆነና ተወዳዳሪ ያጣው የተማሪው እንቅስቃሴ ያስከተለው እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ኃይልን አስተባብሮ በጋራ ለመታገል አንዳይቻል ሁኔታውን አበላሸው። በመሆኑም ሰፋ ባለ የጭንቅላት ተሃድሶ ጉዞ ውስጥ ማለፍ ያልቻለው ወይም ዕድል ያላገኘው የተማሪው እንቅስቃሴ እንደሶቭየት ህብረትና ቻይና፣ በኋላ ደግሞ እንደ ቬትናም ቢያንስ ኃይሉን በማስተባበርና የአስተሳሰብ ጥራት በማዳበር አዲስ አገርና ህብረተሰብ መገንባት አልቻለም። ከብሄራዊና ከስልጣኔ አጀንዳ ይልቅ ስልጣንን ለመጨበጥ በመሽቀዳደሙ አገሪቱን በቀላሉ ሊፈታ የማይችል ችግር ውስጥ ከትቶ አለፈ። የኋላ ኋላም ቶሎ ብሎ የርማት እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ እልክ ውስጥ በመግባት የፖለቲካውን ሁኔታ ብቻ ሳይሆን፣ ጠቅላላው የአገሪቱ ሁኔታ እንዲበላሽ የበኩሉን አስተዋፅዖ አደረገ።

ነገሩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ፣ በ1917 ዓ.ም እ.አ ሶቭየትህብረት ውስጥ በቦልሺቪኮች የሚመራ ማርክሲስታዊ ሌኒናው ኃይል ስልጣንን ከመቀዳጀቱ በፊት፣ ቀደም ብሎ በታልቁ ፔተርና በታላቋ ካታሪኒ ራሺያ ውስጥ ሰፋ ያለ የዘመናዊነት ፖሊሲ ተካሂዷል። ከተማዎች ተገንብተዋል። በራሽያ ውስጥ ካፒታሊዝም ቀስ በቀስ እያለ ሊዳብር ችሏል። ይህ ዐይነቱ መጠነኛ የሆነ የኢንላይንትሜንት ክንዋኔ በራሺያ ምድር የበሰሉ፣ በተለያየ መልክ ሊገለጹ የሚችሉ ምሁራን ብቅ ሊሉ ችለዋል። እነ ቶልስቶይና ማክሲም ጎርኪ የዚህ ዐይነቱ ሰፋ ያለ የጥገና ለውጥ ውጤቶች ናቸው። በዚያን ወቅት ነው በራሺያ ውስጥ የክላሲካል ሙዚቃ መዳበር የቻለው። እነ ሌኒንና ስታሊን እንዲሁም አያሌ ጠለቅ ያለ የማርክሲስት ኢኮኖሚክስ ዕውቀት ያላቸው እንደ ቡሃሪንና ትሮትስኪ የመሳሰሉት ምሁራን የዚህ ዐይነቱ ከበርቴያዊ የጥገና ለውጥ ውጤቶች ናቸው። ስለሆነም እነ ሌኒን በ1917 ዓ.ም ስልጣን ሲጨብጡ የጀርመን ወረራ ካደረሰባቸው ኢኮኖሚያዊ መንኮታኮትና የህዝብ ዕልቂት በመላቀቅ ቀስ በቀስ ወደ ኢንዱስትሪ ፖለቲካ ለመራመድ የቻሉት የተወሰነ መሰረት ስለነበራቸው ነው። ስታሊን የሰራውን ትልቅ ወንጀል ወደ ኋላ ትተን፣ ከፍተኛ የሆነ የእንዱስትሪ ተከላና እንቅስቅቃሴ መታየት የጀመረው በ1930ዎች ገደማ ነው። ስለሆነም ሂትለር ሶቭየትህብረትን ከወረረና ብዙ ጉዳት ካደረሰ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ታንኮች በማምረትና በማሰማራት የሂትለርን ወራሪ ጦር መደመሰስ ተቻለ። ይህም የሚያሳየው፣ 1ኛ፟) የዕውቀትን ሁኔታ ነው፣ 2ኛ) የአደረጃጀትን ጉዳይ ነው። 3ኛ) የዲሲፕሊን ጉዳይ ነው። 4ኛ) የመተባበርንና ለአንድ ዓላማ ቆርጦ መነሳትን ነው። እነስታሊን ከጦርነቱ በድል ከወጡ በኋላ ትላልቅ ከተሞችን መልሰው መገንባት የቻሉት ባላቸው ዕውቀትና ዲሲፕሊን የተነሳ ነው። ከዚያም በኋላ ሶቭየትህብረት የአቶም ኃይል መሆን የቻለችውና ከአሜሪካ ቀድማ ሰውን ወደ ህዋ መላክ የቻለቸው ባላት ምሁራዊ ኃይልና ቆራጥነት ነው። ወደኛ ስንመጣ ግን ነገሩ ሁሉ የተገላቢጦሽ በመሆን በአንድ አገር ውስጥ ከአስር በላይ የሚሆኑ የጦር እንቅስቃሴዎችና የከተማ የደፈጣ ተዋጊዮች በመፈጠር ህብረተሰቡን ማዋከብ ጀመሩ። ብዙ ሺህ ወጣቶችና ምሁራኖችን እንዲገደሉ አደረጉ። ይህም የሚያመለክተው በጊዜው የነበረውን የተማሪውን እንቅስቃሴ ከፍተኛ የማሰብ ኃይል ድክመት ነው። ሁኔታዎችን አለማጤን፣ የሃሳብ ጥራት አለማዳበር፣ በዲሲፒሊን አለመገዛት፣ ለመተባበር አለመዘጋጀት፣ ሁሉም በየፊናው በመሆን ለስልጣን መታገልና፣ የሚቀናቀነውን መግደል፣ ሰፋ ባለ ዕውቀት ላይ በመመርኮዝ ጠንካራ ድርጅትን አለመመስረት፣ ለግልጽ ዓላማ ከመታገል ይልቅ በህቡዕ በመታገል አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ ዲሞክራሲያዊ ቶለራንስን ከማስቀደም ይልቅ፣ ከሚቀድመኝ በፊት ልቅደማቸው በማለት ሁኔታዎችን የባሰውኑ ማዘበራረቅ፣ … ወዘተ. እነዚህና አያሌ ምክንያቶች ተደራርበው በታሪክ ውስጥ ያልታየ የደም መፋሰስና እስከዛሬ ድረስ አልላቀቅ ያለ የቂም በቀል ቁስል በጭንቅላት ውስጥ በመተከል ህዝባችንን ፍዳውን እንዲያይ የተደረገው የህብረተሰብን ህግና በጊዜው የነበረውን አስተሳሰብ ካለመገንዘብ የተነሳ ነው። በአርቆ-አሳቢነትና በምርምር ከመመራት ይልቅ በስሜት ብቻ በመመራቱ በቀላሉ ሊፋቅ የማይችል ቁስል ተጥሎ ታለፈ። ይህንን የማትተው የተማሪውን እንቅስቃሴ ለመወንጀል ሳይሆን ምሁራዊ እንቅስቃሴን ባልለመደና የመንፈስ ተሃድሶን ባለተጎናጸፈ ህብረተሰብ ውስጥ የተፈጠረን ችግር ለማሳየት ብቻ ነው። ይሁንና ግን አሁንም ቢሆን አስቸጋሪው ጉዳያችን ይህንን ድክመታችንና የተሰራውን ከፈተኛ ስህተት አለመገንዘቡ ወደፊት እንዳንጓዝ አድርጎናል ማለት ይቻላል።

ወደ ቻይናም ስንመጣ ልክ እንደሶቭየትህብረት እንኳ ባይሆንም የኦፕየም ጦርነትና በኋላ ደግሞ በጃፓኖች በመወረር ፍዳዋን የምታይ አገር ነበርች። የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አድሃሪ ከሚላቸው ኃይሎች ጋር በመተባበር የጃፓንን ኢምፔሪያሊዝም ካባረረ በኋላ በጊዜው አምስት መቶ ሚሊዮንን የሚጠጋ ህዝብ በማደራጀት ነው ወደ አገር ግንባታ ማምራት የቻሉት። ቻይና እንደ ሶቭየትህብረት መለስተኛ የከበርቴው አብዮት የተካሄደበት አገር ባትሆንም፣ ለብዙ ሺህ ዐመታት የዳበረው ድርጅታዊና ቢሮክራሲያዊ አገዛዝ፣ እንዲሁም ደግሞ የቻይና በቴኮኖሎጂ መዳበርና ለመንፈስ መዳበር የሚያግዝ የራሷ ፍልስፍና ስለነበራት ስልጣን ከተያዘ በኋላ ህዝቡን አደራጅቶ አገር መገንባቱ ከባድ አልነበረም”። ይህም የሚያመለክተው አንድ የሚሰማና በዲሲፕሊን የታነፀና እንዲሁም ለመተባበርና ለመቻቻል ዝግጁ የሚሆን ኃይል ካለ አገር መገንባቱ ከባድ አይሆንም። ከዚህ ስንነሳ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በዚህ የታደለ አይደለም። ህብረተሰቡ ተንኮለኞችንና አመጸኞችን እንዲሁም አገር አፍራሾችን የማያመርት ነው የሚመስለው። እዚያው በዚያው ደግሞ ኩራትና አጉል ጉራ የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል መለዮች እንደሆኑ መገንዘብ ይቻላል።

ሰለሆነም፣ ስለነፃነት በሚወራበት ጊዜ ብዙ የምናነሳቸው ነገሮች አሉ። ራሳችንንም መጥየቁ አጅግ አስፈላጊ ነው። አንዱ በሌላው ላይ ለማላከክ የሚፈልግ ከሆነና፣ በግልጽ ለመወያየት ዝግጁ እስካልተሆነ ድረስና፣ ትችትንም መሰንዘር እንደ ስድብ ተቆጠሮ የሚታይ ከሆነ በፍጹም አንድ እርምጃ እንኳ መራመድ አይቻልም። ትችት እንደ ነጹህ አየር ወይም ምግብ መታየት ያለበት ጉዳይ ነው። ትችት ወደ ስድብ የሚቆጥር ሳይሆን፣ ትችት ተፈጥሮአዊ ግዴታና ለአንድ ህብረተሰብ ዕድገት አስፈላጊ ሆኖ መወሰድ ያለበት ጉዳይ ነው። ስለሆነም ትችት የቲዎሪ፣ የፍልስፍናና የሳይንስ አካል ነው። በዚህም ምክንያት ነው በአውሮፓ ምድር ውስጥ ዕውቀት ሊስፋፋ የቻለው። አያሌ ሊትሬቸሮችን ላገላበጠ የሚረዳው አንደኛው ምሁር ተፈጥሮንና የተፈጥሮን ምንነት በአንድ ዐይነት ሊገልጽ ሲሞክር፣ ሌላው ደግሞ በዚህ መልክ ሊገለጽ አይችልም በማለት የሱን አሰተያየት ያዳብራል። በዚህ ዐይነት ትችታዊ አመለካከትና ነገሮችን መረዳት ህብረተሰብአዊ ዕድገት ሊመጣ ይችላል። ህብረተሰብአዊ ትችት እንደ ጦር በሚፈራበት አገርና፣ አንድ ምሁር እንደ እግዚአብሄር በሚታይበት አገር ዕድገትና ስልጣኔ በምንም ዐይነት ሊመጡ አይችሉም።
አብዮት ተካሂዱል በሚባልበት አገር አሁንም ቢሆን እንዲያውም ከፊዩዳሉ ኢትዮጵያ በባሰ ሁኔታ ዛሬ ሃሳብ እንዳይዳብር ሁሉ ነገ ተቆልፎ ተይዟል። ትችታዊ ሃሳብን ማዳበር አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። አገዛዙ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚ ነን የሚሉ ግለሰቦችም አምባገነናዊ ባህርይን ያሳያሉ። ለነሱ የመደንገግ መብት የተሰጣቸውው ይመስል አንድ አዲስ ሃሳብ ሲሰነዘር ቶሎ ብሎ ለማፈን ይሞክራል። ሌላው ደግሞ ለመማታት ይቃጣል። አንዳንዱ ደግሞ ወደ መናቅ ያመራል። እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው ማለት ነው። ከዚህ ዐይነቱ በሽታ ለመላቀቅ የግዴታ የጭንቅላት ጅምናስቲክ መስራትና ቴራፒ ማድረግ የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ልክ ሰውነታችንን ሲያመን ለመመርመርና ለመታከም ወደ ሃኪም ቤት እንደምንሄድ ሁሉ ጭንቅላታችንም ምርምር ያስፈልገዋል። የጭንቅላታችን በሽታ ግን ሰውነታችን ላይ እንደሚታየው ወይንም ቁርጠት ሲይዘን እንደሚያጎራብጠንና አላስቀምጠን እንደሚለው ዐይነት የሚገለጽ ሳይሆን፣ የጭንቅላት በሽታ የማይታይ፣ የማይዳሰሰና የማይጨበጥ ነው። ሊታወቅ የሚችለው ግን አንድ ህዝብም ሆነ የህብረተሰብ ክፍል ያለበትን ሁኔታ ማየት ሳይችል ሲቀርና ዝም ብሎ አልፎ ሲሄድ የሚገለጽ በሽታ ነው። ይህንን ውድ ወንድማችን ዶ/ር ምህረት ደበበ „የተቆለፈበት ቁልፍና ሌላ ሰው“ በሚለው ግሩም መጽሀፎቹ ውስጥ አብራርቷል። ከዚህም በላይ የጭንቅላት በሽታ በችኮነት፣ በቂም በቀልነት፣ ተንኮል በመስራት፣ የሰውን ስም በማጥፋት፣ ለትችት ዝግጁ ባለመሆን፣ ለመደባደብ በመነሳት፣ ኃላፊነትን ባለመሰማት፣ በዲሲፕሊን እጦት፣ ለሆነው ላልሆነው በመገዛት አገር ለማጥፋት መዘጋጀት፣ ለስልጣንና ለሀብት መስገብገብ፣ ወንጀል ሰርቶ አልሰራሁም ብሎ መዋሸት፣ የራስን ጥፋት በሌላ ሰው ላይ ማላከክ… ወዘተ. የሚገለጽ የረቀቀ በሽታ ነው። ይህ ሁኔታ ነው ለጦርነት መፈጠር፣ ለሰላም እጦትና ለዕድገት ጠንቅ የሚሆንና፣ ስልጣኔዎችና ታሪክ እንዲፈራርስ የሚያደርገው። ስለዚህም ነው እያንዳንዱ ሰው ራሱን ነፃ ካላወጣ ወይም የጭንቅላት ተሃድሶ(Self Emancipation) እስካላደረገ ድረስ አንድ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነትን ሊጎናጸፍና ራሱን በራሱ ማግኘት አይቻልም የሚባለው።

የብሄረሰብና የነፃነት ጥያቄ !!

በአውሮፓው የሶስት ሺህ ዓመታት ታሪክ ውስጥ የሰውን ልጅ ከጨለማ አውጥቶ እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን ዕድል ራሱ ወሳኝ ለማድረግ ትግል ሲጀመር ፍልስፍና፣ የኋላ ኋላ ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስ ነበሩ ነፃነትን አጎናጻፊ መሳሪያዎች ሆነው የታመነባቸውና፣ እንዲዳብሩና እንዲስፋፉም ርብርቦሽ የተደረገባቸው። በፍልስፍና መሰረተ-ሃሳብ መሰረት፣ ማንኛውም ግለሰብ ከሃይማኖት ወይም ከብሄረሰብ ዕምነት ጋር በመያያዝ የሚወለድ ሳይሆን፣ እንደግለሰብና በእግዚአብሄር አምሳል የሚፈጠር ነው። በተወለደበት አካባቢ ሲያድግ በዚያ ያለውን ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉ ኖርሞችንና ባህሎችን በመወሰድ ሳያውቀው ይኖርበታል፣ ይለማመደዋል። ይሁንና ማንኛውም ግለሰብ በአስተሳሰቡ ሊያድግና በተወሳሰበ መልክ በማሰብ ፈጣሪ በመሆን ነፃነት የሚሰማው ከተተበተበበት የባህል ሰንሰለት ሲላቀቅ ብቻ ነው። እንደየሁኔታው ባህል ጎታችም ነው፤ ለዕድገትም የሚያመች ነው። አዳዲስ ዕውቀቶች በማይስፋፉበት፣ የስራ-ክፍፍል በማይዳብርበትና፣ አንደኛው የማህበረሰብ ክፍል ከሌላው ጋር በማይገናኝበት ቦታ ከትውልድ ወደትውልድ የሚተላለፉ ባህል-ነክ ነገሮች ውስጣዊ-ኃይላቸው በጣም ደካማ ነው። የሰውን የማሰብ ኃይል በማፈን እያንዳንዱ ግለሰብ የማሰብ ኃይሉን በመጠቀም የራሱን ዕድልና ህይወት ወሳኝ እንዳይሆን ያደርጉታል። በአጠቃላይ ሲታይ ግን ባህል ራሱ ውስጠ-ኃይላዊ ክንዋኔ(Dynamic Process) ነው። እስከተወሰነ ደረጃ እስካልሆነ ድረሰ ማንኛውም ማህበረሰብ የራሴን ባህል መጠበቅ አለብኝ ብሎ የሙጥኝ ብሎ እሱን ጠብቆ ሊኖር አይችልም። እንዲዚህ የሚያደረግ ግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ የስልጣኔን ብርሃን ሳይጎናፀፍ ያልፋል። በሌላ ወገን ግን በአሁኑ በግሎባል ካፒታሊዝም ዘመን ቀርቶ የሰው ልጅ በስራ-ክፍፍልና በንግድ ልውውጥ አማካይነት መገናኘት ከጀመረ ጀምሮ እየተሳሰረና እየተዳቀለ መጥቷል። በተለይም በአሁኑ በግሎባል ካፒታሊዝም ዘመን ሁላችንም በቴክኖሎጂ አማካይነት በመደገፍ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመንቀሳቀስ ኑሮአችንን ሌላ አገር በመመስረት፣ የአኗኗርና የአስተሳሰብ ለውጥ አምጥተናል። አስተሳሰባችን ክልላዊና አገራዊ መሆኑ ቀርቶ ኮስሞፖሊታን ወይም ዓለም አቀፋዊ ሆኗል። በጋብቻም ከተለያዩ የውጭ አገር ሴቶችም ሆነ ወንዶች ጋር በመጋባት ተቀላቅለናል። ከዚህ ስንነሳ ህይወታችን በክንፈት ዓለም ውስጥ የሚኖር ነው። በአንድ በኩል በአንድ ቦታ ረግተን የምንኖር ብንመስልም ገና ያልተጠናቀቁ ወይም ተግባራዊ ያልሆኑ ህልሞች ስላሉን በሃሳብ ምናልባትም አገራችን ውስጥ ወይም ከመጣንበት ብሄረሰብ ውስጥ ገብተን በሃሳብ እንዋኛለን። ህይወታችን በቅራኔ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ነው ማለት ነው። ስለሆነም፣ በአንድ በኩል በሰለጠነ ዓለም ውስጥ እየኖርን፣ በሌላው ወገን ደግም ወደ ኋላ ስንትና ስንት ሺህ ዘመን ተመልሰን የድሮውን ባህል ለመመለስ የምንፈልግ አለን። በአሁኑ ዓለም አቀፋዊ ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ የኋሊት ጉዞ የማያዋጣ ብቻ ሳይሆን፣ አደገኛም ነው።

ይህ አንደኛው ሲሆን፣ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በግለሰብ ደረጃም ሆነ በግሩፕ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንቅስቃሴ ሲኖር በዚህ አማካይነትም ሆነ፣ በየብሄረሰብ ውስጥ በሚኖረው ውሰጠ-ኃይል ብሄረሰቦች በመጀመሪያው ወቅት የነበራቸውን „የጋርዮሽ መለያ“(Collective Identity) በማጣት እየተሰበጣጠሩና እየተለያዩ(Social Differentiation) ይመጣሉ። በተለይም በአንድ ብሄረሰብ ውስጥ በሚፈጠረው የስራ-ክፍፍል አማካይነትና፣ በዚህም የተነሳ ከሌላው የብሄረሰብ ክፍል ጋር በሚደረገው ግኑኝነት የግሩፕ መለያ እየጠፋ የበለጠ የራስን ጥቅም ማሳደድ በሚለው ላይ አትኩሮ ይደረጋል። በዚህም ምክንያት የተነሳ በአንድ አካባቢ ብቻ ሳይሆን፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ በሚፈጠረው የስራ-ክፍፍልና ህብረተሰብአዊ እንቅስቃሴ አንዳንድ ግለሰቦች ህይወታቸውን ለማሸነፍ ሲሉ የተወለዱበትንና ያደጉበትን አካባቢ በመተው ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ እዚያ ስራ ካገኙ ተቀጥረው በመስራት አዲስ ህይወት መገንባት ይጀምራሉ። በዚህ መልክ ባህሪያቸውና የአኗኗር ስልታቸው ይቀየራል። አንዳንዱ በፋብሪካ ወስጥ ተቀጥሮ ሲስራ፣ እዚያ ውስጥ ከመሰሉ ጋር በሚያደርገው የቀን ተቀን ግኑኝነት ቀስ በቀስ እያለ ባህርይው ይለወጣል። በዚያው መጠንም አዳዲስ የአነጋገር፣ የአረማመድ፣ የፍጆታ አጠቃቀም ባህርይ በማዳበር ገጠር ውስጥ ካለው ከተመሳሳዩ ብሄረሰብ በተለያዩ ነገሮች እየተለያየ ይመጣል። ስለሆነም ከአንድ ብሄረሰብ የተውጣጡ፣ ከፊሉ አራሽ ሆኖ ሲቀር፣ የተቀረው ደግሞ አንጠረኛ፣ የፋብሪካ ሰራተኛ፣ ነጋዴና ሀብታም፣ እንዲሁም የመንግስት ሰራተኛ በመሆን በጥንት ዘመን የነበራቸውን „ኮሌክቲቭ አይደንቲቲ“ ያጣሉ። በተለይም በህሊና አወቃቀራቸው የተለያዩ ስለሚሆኑ የማይግባቡብት ሁኔታ ይፈጠራል። እንደዚሁም አውሮፓና አሜሪካ ተሰዶ የሚኖረው ከዚህና ከዚያኛው ብሄረሰብ የተውጣጣ ግለሰብ በአስተሳሰቡ እየተለየ ይመጣል። በመሆኑም ይህንን ተፈጥሮአዊ የሰው ልጅ ሂደተና መሰበጣጠር፣ እንዲሁም የአኗኗር ስልት ቀልብሶ አዲስ መለያ(Identity) ለመፍጥር መሞከር ብሄረሰቡን ወደ ኋላ ተጓዝ እንደማለት ይቆጠራል። አንተ ከሌላው የተለየህ ስለሆንክ እዚያው ያለህበት ቦታ በመቅረት መብትህን አስጠብቅ፣ ሀብትህንም ተቆጣጠር ማለት እድገትና መሸሻል አያስፈልግህም እንደማለት ይቆጠራል።

ይህንን ትተን ወደ ሌላ ጉዳይ ስንመጣ አንድን ብሄረሰብ በጥቅሉ ወስደን መለያይ ይህ ነው፣ በአንድነት ተነስተህ ለመብትህ ታገል ማለት አይቻልም። ለምሳሌ የኦሮሞ ብሄረሰብን ብንወሰድ በአገራችን በየቦታው ተሰብጣጥረው የሚኖሩና የህሊና አወቃቀራቸውም እንደተሰማሩበት የሙያ ሁኔታና በንግድና በተለያዩ የማህበረሰብ ነክ ጉዳዮች ላይ ባላቸው ግኑኝነት የሚለያይ ነው። የባሌው ኦሮሞ ምናልባት በቋንቋ ካልሆነ በስተቀር ከወለጋው ኦሮሞ በብዙ መንገዶች የሚለያዩበት ሁኔታ አለ። ለምሳሌ በወለጋ ውስጥ ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል ኦሮሞዎች የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች ሲሆኑ፣ የባሌው ኦሮሞ እስላምም የኦርቶዶክስ ክርስቲያንም ተከታይ አለ። ወደ ሸዋ ስንመጣ ደግሞ በዚያ የሚኖረው ኦሮሞ አብዛኛው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ዕምነት ተከታይ ነው። ወደ ጅማና አካባቢው ስንመጣ አብዛኛው እስላም ሲሆን፣ በህሊና አወቃቀሩ ከወለጋውም ሆነ ከኢሉባቦሩ ኦሮሞ በብዙ ነገሮች ይለያል። እንደዚሁም ከባላባቱ መደብ የወጡ ኦሮሞዎች፣ በተለይም ከአባጅፋር ጋር የዘመድ ግንድ አለን የሚሉ ኦሮሞዎችና ዘመናዊ ትምህርት የቀመሱ በአኗኗራቸው ከገበሬው ወይም ከነጋዴው ኦሮሞ በብዙ መልኩ የሚለዩ ናቸው። ይህ ዐይነቱ የባህርይና የአመለካከት፣ እንዲሁም የአኗኗር ስልት ልዩነት አማራ ተብሎ በሚጠራው ብሄረሰብም ውስጥ ያለ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ ጎንደርና ጎጃም አዋሳኝ ሆነው፣ ኑዋሪዎቹ በአነጋገርም ሆነ በአኗኗር ስልት ይለያያሉ። የዘፈናቸውም ቅኝታ ወይም አዘፋፈን ይለያያል። ከዚህ ስንነሳ በተላለየ አካባቢ የሚኖሩና፣ በተለያየ ሙያ እየሰሩ የሚተዳደሩ ግለሰቦችን በአንድ መለያ ለማጠቃለል መሞከር ከሶስዮሎጂ ወይም ከማህበራዊ ሳይንስ አንፃር ትክክል አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ አርቲፊሻል መለያ በመፍጠር አንደኛው ብሄረሰብ በሌላው ላይ እንዲነሳ በማድረግ የስልጣኔውን በር መዝጋት ብቻ ሳይሆን፣ ዘለዓለማችንን እርስ በራሳችን እየተበጣበጥን እንድንኖር ለሚፈልጉና የኛን በዘለዓለማዊ ድህነት እንድንኖር ለሚመኙት ቀዳዳ መስጠት ነው። ስለሆነም አርቲፊሻል መለያ መፍጠርና መረጋጋት እንዳይኖር ማድረግ ራሳችንን አዳክመን የውጭ ኃይሎች መጥተው በቀላሉ እንዲወሩን መንገዱን ሁሉ አዘጋጅቶ እንደመስጠት ይቆጠራል።

በእኛ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለው ትልቁ ችግር፣ ይህንን አስቸጋሪ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ነገሮች ከሳይንስ አኳያ እያነሳን ማጥናትና መከራከር የተለመደ ሳለልሆነ ሌሎችን ላለማስቆጣት ሲባል ብቻ አንዳንድ አስፈላጊ ነገሮች ክርክር ሳይደረግባቸው ተቀብረው እንዲቀሩ ይደረጋሉ። በዚህም የተነሳ በየጊዜው አዳዲስ ሁኔታ ሲፈጠር ሁሉም በየፊናው የፖለቲካ ተዋናይ በመሆን የራሱን አጀንዳ ይዞ በመቅረብና እንደ አዋቂ በመሆን ሌላውን የዋሁን በማሳሳት የስልጣኔና የዕድገት መንገዱን ያጨልምበታል። ትግሉ ለዕውነተኛ ነፃነት መሆኑ ቀርቶ የፖለቲካ መነገጃና እሮሮ ማሰሚያ ይሆናል። ችግራችንን ውስጥ ለውስጥ በሳይንሳዊ መንገድ እየተወያየን ከመፍታት ይልቅ ፈረንጆች ጋ እየሄድን እሮሮ በማሰማትና ባለን መጠነኛ ቅራኔ ውስጥ ሰርገው እንዲገቡብን በማድረግ ተከፋፍለን እንድንቀር እናደርጋለን። ስለዚህም ከእንደዚህ ዐይነቱ አካሄድ ተላቀን ከዚህም ሆነ ወይም ከዚያኛው ብሄረሰብ እንደመጣን ሳይሆን እንደግለሰብ በአመለካከትና በርዕይ ደረጃ ብንቀራረብና ብንወያይ ችግሩን የበለጠ መረዳት ብቻ ሳይሆን መፍትሄም ለመፈልግ ያስችለናል። ከዚህ በመነሳት ነው የጥያቄውን አነሳስ መመርመርና፣ የተፈጠረውን ውዥንብር በመጠኑም ቢሆን መረዳት የሚቻለው።

በእኔ ዕምነት የተማሪው እንቅስቃሴ የብሄረሰብን ጥያቄ እንደ አንገብጋቢ ጥያቄ አድርጎ ሲያነሳ በጊዜው ያላያቸውና ያልተገለጹለት ነገሮች ነበሩ። በመጀመሪያ ደረጃ፣ አንዳንድ ግዛቶች ወይም አብዛኛዎቹ ማለት ይቻላል በአንድ ማዕከላዊ ግዛት ውስጥ እንዲጠቃለሉ ሙከራ ሲደረግ ኃይል ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ነው። የታሪክን ማህደር ላገላበጠ በህብረተሰብ ታሪክ ግንባታ ውስጥ ኃይል ወሳኝ ሚናን ተጫውቷል። አንዱ አገር ሌላውን ገባር ለማድረግ ሲል ባህርና ውቅያኖስን በማለፍ አንዳንድ አገሮችን በቁጥጥሩ ስር በማድረግ ሲያስገብራቸውና ዕድገታቸውን ሲወስን ኖሯል። የሮማውያንና የፐርሽያኖች ወረራና ግዛትን ማስፋፋት የተመዘገበና የብዙ አገሮችን ህይወትና ሂደታቸውን የወሰነ ነው። ሮማውያን ያልረገጡብት አንድም የአውሮፓ አገር የለም። በገዙበት ቦታ ሁሉ መሰረት ጥለው አልፈዋል። በባሪያ አገዛዝና በቅኝ ግዛት ዘመንም የተካሄደው አገሮችን ለማስገበርና የነሱ ቅኝ ግዛት አድርጎ ለማስቀረት ነው። ዛሬ ታላቅ የሚባለው አሜሪካንም የጥንት ኗሪ ሰዎችን በመጨረስና፣ ጥቁሩን ባሪያ አድርጎ በመዝበርና በማሰቃየት፣ እንዲሁም ደግሞ በከፍተኛ የዘርኝነት ስሜት በመወጠርና ዝቅ አድርጎ በማየት በመብዝበዝ የተገነባ አገር ነው። ዛሬም ቢሆን ኢንስቲቱሽናላይዝድ የሆነ ዘረኝነት በመስፈን ጥቁር አሜሪካኑ እንደሁለተኛ ዜጋ የሚታይበት አገር ነው። ያውም ወርቅ የመሰለ ህገ-መንግስት እያለና፣ በየአራት ዐመቱም የፕሬዚደንትና የኮንግረስ ምርጫ በሚካሄድበት አገር ዘረኝነት ሰፍኖ ሰፊው ጥቁር ህዝብ ፍዳውን ያያል። ወደ ኮሌጅና ወደ ዩኒቭርሲቲም ለመግባት የሚችለው በጣም ጥቂቱ ጥቁር ብቻ ነው። ይህ ዐይነቱ አካሄድ የማይደገፍ ቢሆንም በታሪክ ውስጥ የታየና አንዳንድ አገሮችም ያለፉበት ሁኔታ ነው።

ወደ አገራችን ተጨባጩ ሁኔታ ስንመጣ በኢትዮጵያዉያን ምሁራን ዘንድ ተነስቶ ያልተብላላ የጭቆና ጉዳይ አለ። ቀደም ብሎም ሆነ በኋላ በአፄ ኃለስላሴ ዘመን አጠቃላይ ጭቆናን በሚመለከት በህብረተሰቡ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ ውስጥም የነበረ ነው። ጭቆናው ተጨቆኑ የሚባሉ ብሄረሰቦችን የሚመለከት ብቻ ስይሆን፣ ፊዩዳላዊ ስርዓት በሰፈነበት ህብረተሰብ ውስጥ ራሳቸው የፊዩዳል ልጆችም ይጨቆኑ እንደነበር ግልጽ ነው። የፊዩዳል ልጅ ሆኖ ካለዕድሜው ብዙ ከባድ ከባድ ስራዎችን የሚሰራና፣ ቤት ውስጥም ጭቆና የሚደርስበት ልጅ እንደነበር ይታወቃል። እነዚህ ጭቆናዎች በተለያዩ መልኮች የሚገለጹና የአንድን ልጅ ጤናማና ጤናማ ባለሆነ መልክ እንዲያድግ የሚወስኑ ሲሆኑ፣ አብዛኛውን ጊዜም በማወቅ የሚደረጉ አልነበሩም። ወደ አማራው ክልል ስንመጣም እስካሁንም ድረስ ለአቅመአዳም ከመድረሳቸው በፊት ልጃገረዶች እንዲያገቡ ይገደዳሉ። ከዚህ ስንነሳ በብሄረሰቦች ላይ ሰፍኗል ይባል የነበረውን ጭቆና ከአጠቃላዩ የፊዩዳላዊ አኗኗር ስልትና ከዕውቀት ማነስ ጋር ቢያይዝ ነገሩን ይበልጥ መረዳት እንችላለን። በሌላ አነጋገር፣ አንድ ህብረተሰብ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉ የአኗኗር ስልቶችን ይዞ የሚኖር ከሆነና፣ በሌላ በተገለጸለት አስተሳሰብ እስካለተጋፈጠ ድረስ ጠቅላላው ህብረተሰብ የዚህ ዐይነቱ የዕድገት ጠንቅ አኗኗር ሰላባ በመሆን አስተሳሰቡ ውስን መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ አኗኗሩም እንደ ተፈጥሮአዊ ተደርጎ በመወሰድ ድህነት ዘለዓለማዊ መልዮው ይሆናል። በእንደዚህ ሁኔታ ውስጥ የምሁራን ተግባርና ተልዕኮ ችግሩን ከሁለንታዊ አንፃር በመመርመር ሳይንሳዊ መፍትሄ መስጠት መሞከር እንጂ የማይሆኑ መፈክሮችን በማንሳት አንድ ህዝብ በቀላሉ ሊወጣው የማይችል ችግር ውስጥ መክተቱ ከፍተኛ ስህተት ነው። ይህንን አልፈን ወደ ህብረ-ብሄረ መንግስት ምስረታ ጉዳይ እንምጣ።

በአንንድ አካባቢ የሚገኙ የተሰበጣጠሩ በመሳፍንት ይተዳደሩ የነበሩ ግዛቶችን ሁኔታ ስንመለከት፣ የታሪክ ግዴታ ሆኖ ትናንሽ ግዛቶች በዚያው ሁኔታቸው ለመኖር አይችሉም ነበር። በተለይም በአስራሰባተኛውና በአስራስምንተኛው ክፍለ-ዘመን የጠነከሩ መንግስታት ደከም ብለው ይገኙ የነበሩ እንደ ጀርመን የመሳሰሉ፣ ገና በአንድ ማዕከላዊ አገዛዝ ጥላ ስር የማይተዳደሩ አገሮችን እየወረሩና እያጠቁ ስላስቸገሩ የግዴታ ጀርመን እንደ አንድ ማዕከላዊ አገዛዝ መዋቀር ነበረባት። በጊዜው ጠንከር ብሎና በባህል ዕድገት ተሽሎ የሚገኘው የፕረሺያው አገዛዝ አልገበርም ያሉትን በሙሉ በጦርነት በመውረርና በማጠቃለል ጀርመን አንድ ለመሆን ስትቃረብ፣ ኃይል በማግኘት ከፈራንሳይና ከአውስትሪያ የተሰነዘረባትን ጦርነት መክታ በመመለስ በ1871 ዓ.ም እ.አ የመጀመሪያው በአንድ ባንዲራ ስር የተጠቃለለ አገዛዝ ተመሰረተ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጀርመን ለዕድገት እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በማስወገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ የኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ ባለቤት በመሆን እንግሊዝንና ፈረንሳይን ቀድማ መሄድ ቻለች። በፕረሽያ አገዛዝ ጊዜ ተግባራዊ የሆነው አጠቃላይ የትምህርት የጥገና ለውጥ የኋላ ኋላ በጀርመን ምድር ሳይንቲስቶች እንደ አሸን እንዲፈልቁ አደረገ። ለመጀመሪያ ጊዜ በሃያኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ ላይ ሁለት ሶስተኛው የሚሆነው የኖቭል ሽልማት አሸናፊ የሆኑ ሳይንቲስቶች ከጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ነበሩ። ይህ ሁሉ የማዕከላዊ አገዛዝና ልዩ ዐይነት የዕውቀት ውጤት ነው። በሌላ አነጋገር ጀርመኖች ተሰበጣጥረው ቢኖሩ ኖሮ እድሜያቸውን በሙሉ በውጭ ኃይሎች በመጠቃት የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባላቤት መሆን ባልቻሉ ነበር።

ወደ አገራችን ስንመጣ በተለይም አፄ ምኒልክ ወደ ደቡቡ የአገራችን ክፍል ያደረጉትን መስፋፋት አስመልክቶ ድርጊቱ ሲኮነንና፣ ጨለማን እንዳመጡ ተደርጎ ይታያል። አንዳንዶቹ እንደሚሉን ከሆነ፣ አፄ ምኒልክ ወደ ደቡብ ግዛታቸውን ከማስፋፋተቸው በፊት ህዝቡ የሰለጠነና፣ የራሱ ቴክኖሎጂና ሳይንስ የነበረው፣ እንዲሁም ደግሞ ከተማዎችን ገንብቶ በስራ-ክፍፍልና በንግድ አማካይነት በመገናኘት ተዝናንቶ ይኖር የነበረ ነው ብለው ሊያሳምኑን ይሞክራሉ። ሀቁ ግን አነሰም በዛም ሁሉም ግዛቶች ተመሳሳይ ሁኔታ ነበራቸው። የአማራውም ሆነ ሌላው በኋላ በአንድ ማዕከላዊ አገዛዝ ስር የተጠቃለለው ክፍል በስራ-ክፍፍልም ሆነ በንግድ አማካይነት የዳበሩ አልነበሩም። በመሆኑም በቴክኖሎጂ የሚገለጽ ዕድገት አልነበራቸውም። ይህ በራሱና ማዕከላዊ አገዛዙ በነበረው ውስጣዊ ድክመት የተነሳ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ እንደ አንድ ማህበረሰብ፣ ህብረተሰብና ህብረ-ብሄር በማዋቀር በሳይንስና በቴክኖሎጂ የተመሰረተ ስርዓት አጠናቆ መገንባት አልተቻለም። በሌላ አነጋገርር፣ ኢትዮጵያ በአፄ ምኒልክ ዘመን፣ የኋላ ኋላ ደግሞ በፄ ኃይለስላሴ ዘመን ወደ ማዕከላዊ መንግስትነት ብትቀየርም፣ ለአንድ አገር እንደ አገር መኖር የሚያስፈልጓት መሰረተ-ሃሳቦች ይጎድሏት ነበር፤ ዛሬም ይጎድሏታል። እነዚህም፣ 1ኛ) የዳበረና የተስፋፋ የስራ-ክፍፍል፣ 2ኛ) ሰፋ ያለ የውስጥ ገበያ፣ 3ኛ) በስነስርዓትና በዕቅድ የተገነቡ ከተማዎችና መንደሮች፣ 4ኛ) ብቃት ያላቸው ኢንስቲቱሽኖች፣ 5ኛ) መንገድና ድልድዮች፣ እንዲሁም የባቡር ሃዲድ፣ 6ኛ) ለአንድ አገር ዕድገትና መሻሻል የሚያስፈልጉ ሳይንስና ቴክኖሎጂዎች፣ 6ኛ) ሰፋ ያለ የዕውቀት መገብያ ኮሌጆች፣ የዕደ-ጠበባ ማሰልጠኛ ተቋሞች… ወዘተ. 7ኛ) የሳይንስ አካዳሚ፣ 8ኛ፟) የቲያትርና የሴኒማ ቤቶች፣ 9ኛ) የስፖርት ተቋሞች፣ 10ኛ) ለሲቪል ሶሳይቲ ማበብ የሚረዱ የሙያ ማህበሮች፣ እነዚህ ሁሉ በጊዜው ደረጃ በደረጃ ታስቦባቸው ለመቋቋም ስላልቻሉ በውስጣዊ ድክመት የተነሳ፣ በአንድ በኩል አገራችን እንደ አንድ ህብረተሰብና ህብረ-ብሄር ልትዋቀር አልቻለችም፤ በሌላ ወገን ደግም እንደዚህ ዐይነቱ ክፍተት የተሳሳተ አጀንዳ ላላቸውና አንድ ህዝብ ተስማምቶ ለጋራ ዓላማ እንዳይነሳ ለሚታገሉ ኃይሎች ቀዳዳ በመስጠት እስከዛሬ ድረስ ራስ ምታት ሰጥቶን ሲያሰቃየን ይኖራል። ይሁንና ግን በኢትዮጵያ ምድር ዕድገት አለመታየቱ ሁሉንም ክፍለ-ሀገሮችና ብሄረሰቦች የሚመለከት እንጂ አንዱን ብሄረሰብ ጠቅሞ ሌላውን ለመጉዳት ሲባል አፄ ምኒልክም ሆነ አፄ ኃይለስላሴ በዕውቅ የወሰዱት ጎጂ ፖሊሲ አልነበረም። እኔ እስከማውቀው ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ የፀረ-ዕድገት ዘመቻ ተካሂዷል ከተባለ ይበልጥ የተጎዳው የአማራው ግዛት ነው። ቡና ወደሚመረትባቸው ክፍለ-አገሮች ወይም በዛሬው አጠራር ክልሎች የሚሰደደውና ቡና ለቃሚ የሆነው፣ የጎንደሬው፣ የጎጃሜው፣ የወለዬውና የትግሬው ሰው ነው። ስለዚህም ስለበደልና ስለብሄረሰብ ጭቆና ሲወራ ነገሩን ካለማውቅና ሰፋ ያለ የዕድገትን አስፈላጊነት ካለመገንዘብ ጋር ማያያዝ ያስፈልጋል እንጂ፣ ኢትዮጵያ የጨለመችና አስቀያሚ ታሪክ የነበራት አገር ናት እያሉ ማውራትና ማስፋፋት ኢ-ሳይንሳዊ፣ ኢ-ምሁራዊ፣ ኢ-ፍልስፍናዊና ኢ-ጥበባዊ ነው። የህብረተሰብን ዕድገት ታሪክ የሚፃረር አባባል ነው። አንድ ግለሰብም ሆን ህብዝ ሶሻላይዝድ በመሆን ራሱን በራሱ እሲኪያገኝ ድረስና ታሪክን ይሰራ ዘንድ ብዙ ውጣ ውረድ ያለባቸውን መንገዶች መጓዝ ያለበትን ሁኔታ ካለመረዳት የተነሳ ቀደም ብለው የነበሩ አገዛዞችን አረመኔዎች አድርጎ ለመሳልና አገራችንም ጨለማ እንደነበረችና፣ በተለይም ጭቁን የሚባሉት ብሄረሰቦች ከፍተኛ በደል ይደረስባቸው እንደነበር ኢ-ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ይቀርባል። አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ነገሩን ለማሳመር ወይም የሰውን ልብ ለመንካት ሲሉ የሚሆን የማይሆን፣ የህብረተሰብን ህግና ሳይንስን የሚጥስ ነገር ሲናገሩ ይታያል። በተለይም በአሁኑ ዘመን ፕሮፌሽናል ፖለቲከኞች በጠፉበት ዘመንና፣ በተለይም የፖለቲካ ሳይንስ ትርጉም ተጣሞ በሚቀርብበት ዘመን፣ ፍልስፍና፣ ሶስዮሎጂ፣ አንትሮፖሊጂና ሳይኮሎጂ እንደመመሪያ መመርመሪያ ተደረገው በማይወሰዱበት አገር ፖለቲካ መተንተኛና ሳይንሳዊ መሳሪያ መሆኑ ቀርቶ ወደ መደንፊያነት በመለወጥ የአንድ ህዝብ ታሪክ እንዲጣመም ይደረጋል። በተለይም፣ ፖለቲካን ወደ መነገጂያና መኖሪያ የለወጡ ግለሶቦች አስቸጋሪ ሁኔታንና የታሪክ አጋጣሚን በመገጠም፣ እንዲሁም ከአንዳንድ ሚዲያዎች አላስፈላጊ ቦታ እንዲያገኙ በማድረግ በሚቀጣጠለው እሳት ላይ ቤንዚን እያርከፈከፉ የባሳውኑ እንዲጋይ ያደርጋሉ። እነዚህ ግለሰቦችም ሆነ ለእነዚህ ግለሰቦች ሁኔታውን የሚያመቻቹላቸው ሚዲያዎች ማወቅ ያለባቸው ነገር ድርጊታቸው ፀረ-ህዝብ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው ጥቁር ህዝብ ላይ እንድተሰዘነረ መረዳት አለባቸው። ወሬን ከማራገብና ሁኔታውን አመቻችቶ ከመስጠት ይልቅ ድርጊታቸውን ከሁሉም አንፃር መመርመሩ እጅግ ጠቃሚ ነው። ለዚህ ደግሞ የሚዲያና የፖለቲካ አማካሪዎችን ድጋፍ ቢጠይቁ ስራቸውን ሊያቃልልላቸው ይችላል። ከስህተትም ሊቆጠቡ ይችላሉ። ስለሆነም የሚላክላቸውን ጽሁፎች በደንብ መመርመር አለባቸው። ቃለ-መጠይቅ የሚጠይቁ ሚዲያዎችም ኮታን ለማሟላት ሲሉ መጠየቅ የሌላበቸውን ሁሉ በመጠየቅ ችግራችንን የባሰውኑ ውስብስብ ማድረግ የለባቸውም። ይሁንና ግን ማንኛውም ሚዲያ የራሱ መብት ስላለው እንደፈለገው ጽሁፎችን ማስተናገድ ይችላል። ለማለት የሞከርኩት ሁላችንም ሰላምንና ብልጽግናን የምንሻ ከሆነ የባሰውኑ ውዝግብ ውስጥ የሚከተን ሁኔታ ውስጥ እንዳንገባ መጠንቀቅ አለብን ለማለት ብቻ ነው።
እንደዚህ ስል ግን በአንዳንድ ብሄረሰቦች ላይ በደል አልነበረም፤ ውይም የለምም ለማለት አይደለም። በኮሎኮንታው፣ በወላይታውና እንዲሁም በከፍቾው ብሄረሰቦች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ መባል የማይገባቸው ነገሮች ይባሉ ነበር። እነደዚህ ዐይነቱ አባባልና የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል ማግለልና ለመጥፎ ነገሮች ተጠያቂ ማድረግ በተለይም በአውሮፓ ምድር ውስጥ በማዕከለኛው ዘመንና እስከ ኋለኛው ማዕከለኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የተስፋፋ ነበር። በተለይም ካለምንም ምክንያት ይሁዲዎች የሚናቁና የሚጠሉ፣ እንደውሻም የሚታዩ ነበሩ። ስለሆነም ይሁዲዎች የተስቦና የኮሌራ እንዲሁም የልዩ ልዩ በሽታዎች ምንጮት ተደርገው በመቆጠር ከሌላ የህብረተሰብ ክፍል ጋር መጋባት አይፈቀድላቸውም ነበር። ይሁንና ግን ይሁዲዎች ይህንን ሁሉ ከመጤፍ ሳይቆጥሩ፣ ቀስ በቀስ በመማርና በንግድ በመሰማራት የአገሬውን ሰው እየበለጡ ይሄዳሉ። ፈላስፋዎች፣ የሙዚቃና የሊትሬቸር ሊቆች፣ በኋላ ደግሞ ሳይንቲስቶችና የቴክኖሎጂ አፍላቂዎች በመሆን በተለይም ለጀርመን ዕድገት ልዩ ዕምርታን መስጠት ቻሉ። ተሰደብን፣ ተናቅን፣ ተዋረድን ብለው ወደ ጫካ በመግባትና ጠብመንጃ በማንሳት ጦርነት አላወጁም። የሚንቃቸውን በዕውቀት አማካይነት ማሸነፍ እንደሚችሉ ማረጋገጥ ቻሉ። ይሁንና ግን የተሻልን ነን ብለው በመዝናናት ቂም በቀል መወጣት አልጀመሩም። ቀስ በቀስ በመጋባትና በመዋለድ እንዲሁም ዕውቀታቸውን በማስፋፋት ነው ለህብረተሰቡ ልዩ ዕምርታን መስጠት የቻሉት።

ወደ አገራችን ስንመጣ ያለው ችግር የህብረተሰብን ዕድገት ታሪክ ብቻ ሳይሆን፣ የራሳቸውን ብሄረሰብ የመንፈስና የማቴሪያል ዕድገት ሁኔታ በደንብ ያላጠኑ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች ነገሩን ሁሉ በመጠምዘዝ የአማራው ብሄረሰብ እንደዚህ አደረገ፣ እንደዚያ ፈጠረ በማለት በየዋሁ ህዝብ ላይ ጦርነት በመክፈት ስንትና ስንት ህዝብ ፈጅተዋል። ራሳቸው ማርክሲስት ነን ይሉ የነበሩ ግለሰቦች ሁሉ ሳይቀሩ አማራውን በነፍጠኝነት በመክሰስ አሳቃይተውታል፤ ገድለውታልም። ይህ ሁሉ ከታሪክ ጋር ሳይገናዘብ በተለይም ፊደል ቆጥረናል፣ ዩኒቨርሲቲም ገብተን ተምረናል በማለት በሚዝናኑ አንዳንድ ግለሰቦችና በድርጅት ደረጃ የተወሰዱ አላስፈላጊ እርምጃዎች ናቸው።
ያም ተባለ ይህ ፣ ሬኔ ዴካ የሚባለው የፈረንሳዩ ፈላስፋ በአንድ ወቅት የተደረገን ድርጊት ሙሉ በሙሉ ማረጋጋጥ ስለማይቻል እንደሳይንስ ሊወሰድ አይቻልም። ሳይንስ የተፈጥሮ መነጋገሪያና መመርመሪያ፣ እንዲሁም የህብረተሰብ ማደራጃ መሳሪያ ነው። ስለዚህም የዛሬውን ችግር በታሪክ መነጽር ወይም መሳሪያ መፍታት አይቻልም። ያለፈ ነገር ያለቀለትና የደቀቀለት ነው። ስላለፈው ነገር እየደጋገሙ ማውራት፣ „ውሃ ቢውቅጡት እምቦጭ“ እንደሚሉት አባባል ነው። ስለዚህም ላይብኒዝ እንደሚለን፣ የአዲሱ ትውልድ ተግባር ዛሬ አፍጠው አገጠው የሚታዩ ችግሮችን በሳይንስና በፍልስፍና መሳሪያ መፍታትና ለመጭው ትውልድ ታሪክን ሰርቶ ማለፍ ብቻ ነው።
ከዚህ ስንነሳ የብሄረሰቦች ችግር መብታቸውን በማወቅ ብቻ ሊፈታ ይችላል ወይ ? መብትስ ሲባል ምንድ ነው ? በራስ ቋንቋ መነጋገር፣ ወይም ደግሞ የራሴ ባህል የሚሉትን መጠበቅ ? ሌላው ደግሞ ሀብትን ወይም ሬሶርስን የመቆጣጠር ጉዳይ፣ ሌሎችን አባሮ ሁሉንም የራሴ ብሎ መቆጣጠርና መዝናናት ? ለመሆኑ እነዚህ በመታወቃቸው እያንዳንዱ ብሄረሰብ ያለበትን መሰረታዊ ችግር፣ ለምሳሌ እንደ ንጹህ ውሃ ማግኘት፣ ተመጣጣኝ የሆነ ምግብ በጥራትም ሆነ በብዛት ማግኘት፣ መብራትና የምግብ መቀቀያ ጉዳይ፣ ቤትና የትምህርት ቤት ጉዳይ፣ እንዲሁም ህክምና… ወዘተ. እነዚህ መሰረታዊ የማንኛውም ሰው ፍላጎቶች የላይኛዎቹ መብቶች በመታወቅ ብቻ ሊፈቱ ይችላሉ ወይ ፟? ወይስ ዋናው ነገር የመብት ማዋቅን ጉዳይ መፍታትት ነው? ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉንም ለማለት ነው የሚፈለገው? ከዚህም ባሻገር አንድ ብሄረሰብም ሆነ ማህበረሰብ ወይም ህብረተሰብ ተከታታይነት ያለውን ጤናማ ኑሮ ለመኖር ከፈለገ የግዴታ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ማዳበር ያስፈልገዋል። የቴክኖሎጂንና የሳይንስን ዕድገት የተመለከትን እንደሆን በክልል ወይም በብሄረሰብ ደረጃ ሊያድጉ ወይም ሊዳብሩ፣ ወይም ሊፈጠሩ የሚችሉ አይደሉም። በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር የተለያየ ጎሳ በጋብቻ ሲቀላቀልና፣ በስራ-ክፍፍልና በንግድ አማካይነት ግኑኝነቱን ሲያጠናክር የመፍጠር ኃይሉም ያድጋል። የቴክኖሎጂና የሳይንስ ባለቤትም ይሆናል። ይሁንና ግን በአጠቃላይ ሲታይ የቴክኖሎጂ ዕድገት ዓለም አቀፋዊ ጉኑኝነትንና፣ በዘዴ ቴክኖሎጂዎችንም መስረቀንና ማዳበርን ይሻል። በዚህ አማካይነት ብቻ ነው አንድ ህዝብም ሆነ ግለሰብ ኑሮውን ማሻሻል የሚችለው። ራሱን አገልሎ የሚኖር ማህበረሰብም ሆነ ብሄረሰብ በሃሳብ ይቀጭጫል። ዕድገትን ማየት አይችልም። ያለውንም ሬሶርሱን ወይም ሀብቱን በስነስርዓት መጠቀም አይችልም። በእኔ ዕምነት እንደዚህ ዐይነቱን ችግር ለመፍታት በመጀመሪያ ደረጃ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ማቋቋም ያስፈልጋል። አዲሲቱን ኢትዮጵያ ለማስተዳደር የሚችሉ ከሁሉም ብሄረሰብ በችሎታ ተመርጠው ሊስለጥኑ የሚችሉበት ሁሉኑም ዕውቀት ያካተተ ልዩ ዐይነት የኤሊቶች ዩኑቨርሲቲ ማቋቋም ያስፈልጋል። ይህ ዐይነቱ ልዩ የኤሊቶች ኢንስቲቱት በየክፍለ-ሀገሩ ወይም በየክልሉ የሚቋቋም ሲሆን፣ ፍልስፍናን፣ ታሪክን፣ ሊትሬቸርን፣ የተፈጥሮ ሳይንስን፣ ሜካኒካልና ኤልክትሮቴክኒክ ኢንጂነሪንግን፣ ጥበብና ሙዚቃን፣ የፖለቲካ ሳይንስና የሶስይሎጂ ዕውቀቶችን፣ አርክቴክቸርን… ወዘተ.፣ የሚያጠቃላል መሆን አለበት። በተጨማሪም በየክፍለ-አገሩ በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ሁሉንም ዐይነት መጽሀፎች ያጠቃለሉ ቤተ-መጻህፍቶች መቋቋም አለባቸው። አገሪቱ እያደገች ስትመጣ ደግሞ በየቀበሌው የህዝብ መማሪያ ትምህርትቤቶች ቢቋቋሙ ህዝቡ የመማር ዕድልና ከዕደ-ጥበብ ሙያ ጋር የመተዋወቅ ባህልን ያዳብራል። ይህ በራሱ በአጭር ጊዜ ውስጥ እምርታን በማሳየት በህዝቡ ዘንደ ያለውን በማያስፈልግ መልክ የተሰራጨውን አሉባልታ በማስወገድ ህዝባችን በመከባበርና በሰላም እንዲኖር ይረዳዋል። ስለሆነም ስለነፃነትና ስለመብት በምንናገርበት ወይም በምንጽፍበት ጊዜ ነገሩን ሰፋ ባለመልክ መመልከቱ የሚጠቅም ይመስለኛል። ከዚህ ውጭ የሚደረግ ዘመቻና የመብት ጥያቄ እንዲያውም የተገላቢጦሹን ነው የሚያመጣው። ድህነትን ፈላፋይ ነው የሚሆነው። የሳይንስና የቴክኖሎጂን ዕድገት አፋኝ ነው የሚሆነው። ጥበብ እንዳይስፋፋ፣ የሰዎች የመፍጠር ችሎታ እንዳይዳብር አፍኖ ይይዛል። በተጨማሪም መብት ወይም ነፃነት የሚከፈል ወይም እየተከፋፈለ የሚሰጥ ጉዳይ ሳይሆን፣ የሁሉም ሰው ጥያቄ ነው። አብዛኛውን ጊዜ መብትና ነፃነት ግለሰብአዊ ባህርይ ሲኖራቸው፣ በሌላ ወገን ደግሞ ከስራና ከሙያ ጋር በተያያዘ አንድ ፈብሪካ ውስጥ ተቀጥረው ወይም በሌላ የሙያ ማሀበር ተደራጅተው የጋርዮሽ ጥቅማቸው እንዲጠበቅላቸው የሚነሳ ጉዳይ እንጂ በብሄረሰብ ደረጃ የሚታይ ነገር አይደለም። ሳይንሳዊም ሊሆን አይችልም።

ዓለም አቀፋዊ ካፒታሊዝምና የነፃነት ትግል አስቸጋሪ ሁኔታ!

ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የተዋቀረው ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ፣ የሚሊታሪና የኢኮኖሚ ስርዓት የአብዛኛዎችን የሶስተኛውን ዓለም አገሮች፣ በተለይም የአፍሪካን አገሮች፣ የኛንም ጨምሮ የዕድገታችንን አቅጣጫ ለመወሰን ችሏል። በተለይም ከ1950ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ ዘመናዊነት(Modernization) በመባል የሚታወቀው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በኛና፣ የኋላ ኋላ ደግሞ ከቅኝ ግዛትነት ከተላቀቁ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ በኛም ሆነ በነዚህ አገሮች ውስጥ አዲስ ህብረተሰብአዊ ግኑኝነት፣ የፍጆታ አጠቃቀምና፣ ለየት ያለ የህሊና አወቃቀር ሊፈጠር ችሏል። ከዚህም ባሻገር የየመንግስታቱ መኪና በአዲስ መልክ በመዋቀርና በመጠናከር አዲስ የተፈጠረውን ህብረተሰአብዊ ግኑኝንት ሊያጠናክረው ችሏል።

የምትክ ኢንዱስትሪ ተከላ፣ (Import Substitution Industrialization) ወይም ደግሞ በአጠቃላይ ዘመናዊነት በመባል የሚታወቀው የኢኮኖሚ ፖሊስ በውጭ አማካሪዎች ግፊት ተግባራዊ ሲሆን፣ ዓላማው በዚህ ዐይነቱ ፖሊሲ አማካይነት ዕድገቱ ቀስ በቀስ ወደ ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎችም በመዳረስ(Trickle–down) ኋላ-ቀርነት ተወግዶ ሁሉም አገሮች አነሰም በዛም የምዕራቡ የዕድገት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ የሚል ግምት ነበር። ይሁንና ግን የኢኮኖሚ ፖሊሲው ባለው ውስጣዊ ድክመት የተነሳ እንደታሰበው የእኛና የተቀሩት የአፍሪካ አገሮች ዕድገት ወደፊት ሊራመድ አልቻለም። በተለይም የየመንግስታቱ መኪና በመጠናከርና፣ የነበረውን ስርዓት እዚያው አፍኖ በመያዝ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሊታይና የህብረተሰቡም ፈጠራ ከፍ ሊል አልቻለም። በዚህም ምክንያት የተነሳ አዲስ ውስጠ-ኃይሉ ከፍ ያለና ህብረተሰብአዊ ኃላፊነትን ሊሸከም የሚችል የከበርቴው መደብ ብቅ ሊል አልቻለም። በሌላ ወገን ደግሞ ከታች ወደ ላይ ከኢኮኖሚው ዕድገትና ከህብረተሰቡ የማሰብ ኃይል ጋር እየተቀናጀ ያልተገነባው የመንግስት መኪና የባሰውኑ ጨቋኝ በመሆንና ከህብረተሰቡ በመራቅ ተጠሪነቱ ይበልጥ የውጭ ኃይሎች በመሆን፣ ወደ ውስጥ ደግሞ ሁለ-ገብ የሆነ የኢኮኖሚና የህብረተሰብ ዕድገት እንዳይመጣ እንቅፋት ሆነ።

በ1950ዎቹ መጀመሪያ ላይ ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ የተጠበቀውን ውጤት ሳያመጣ ሲቀር፣ እንደዚሁ በውጭ አማካሪዎች በስም የሚለያዩ፣ ይዘታቸው ግን ተመሳሳይ የሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ተግባራዊ በመሆን ሁለ-ገብ የኢኮኖሚ ዕድገትን ከማምጣት ይልቅ ሁኔታውን የባስውኑ አዘበራረቀው። በመሆኑም እርስ በርሳቸው ያልተያያዙ የኢኮኖሚ ክንዋኔዎች በመፈጠር፣ ዘመናዊ በሚባለው የኢኮኖሚ መስክና በእነዚህ ለካፒታሊዝም ዕድገት በማያመቹ የተሰበጣጠሩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች መሀከል ከፍተኛ ቅራኔ መታየት ቻለ። በአንድ በኩል የዘመናዊ የኢኮኖሚ መስክ ተጠቃሚ የሆነው ክፍልና፣ በሌላ ወገን ደግሞ በተለያዩ ግን ደግሞ ጥሩ ገቢን በማያስገኙ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በተሰማራው የህብረተሰብ ክፍል መሀከል „የባህል ልዩነት“ መታየት ጀመረ። በጊዜው የነበረው የአፄው አገዛዝ ይህንን ህብረተሰብአዊ ቅራኔ ለመፍታት የሚያስችል ፖሊሲ ስላልነበረው፣ እየተከማቸ በመጣው ቀውስ የተነሳ ቀስ በቀስ እያለ ከስልጣን የሚወገድበተን መንገድ አዘጋጀ። ይህ ሁኔታና፣ በጊዜው የነበረው ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ቀውስ ተደራርበው ለየካቲቱ አብዮት ምክንያት ሆኑ። አብዮቱ ከፈነዳ በኋላ የተወሰዱት እርምጃዎች ከሞላ ጎደል ትክክል ቢሆኑም፣ በነበረው ትርምስ የተነሳ ግልጽ የሆነ ለካፒታል ክምችት የሚያመችና ለሰፊው ህዝብ የስራ መስክ ሊከፍት የሚያስችል የኢኮኖሚ ፖሊስ መንደፍ አልተቻለም። የወታደሩ አገዛዝ ከስልጣን ከተባረረ በኋላ በውጭ ኃይሎች ግፊት ተግባራዊ የሆነው የነፃ የገበያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመሰረቱ የአገራችንን የተወሳሰበ ችግር ለመፍታት ሳይሆን አዲስ የህብረተሰብ ኃይል በመፍጠርና በማጠናከር፣ በዚያውም መጠንም ድህነትን አስፋፍቶ ሰፊውን ህዝብ አቅመ ቢስ የሚያድርገው ሆነ።

በተለይም የግሎባል ካፒታሊዝም ባለፉት ሰለሳ ዓመታት የብዙ አፍሪካ አገሮችን ዕድል ወሳኝ በመሆኑ፣ በዚያው መጠንም የየመንግስታቱን መኪና በማጠናከርና ከሰፊው ህዝብ በመገለል፣ የየአገሮቹ መንግስታትና ህዝቦች ሆድና ጀርባ ለመሆን በቅተዋል። በዚህ መልክ የዓለም አቀፍ ካፒታሊዝም በየአገሮች መንግስታት መኪና ውስጥ ሰርጎ በመግባት፣ መንግስታቶች የህዝብ አለኝታ እንዳይሆኑ ቆልፎ በመያዝ፣ በአንድ በኩል ህዝባዊ ጭቆና፣ በሌላ ወገን ደግሞ ሸበርተኝነትን መዋጋት ያስፈልጋል በማለት የጎሳና የሃይማኖት ግጭት እንዲስፋፋ ተደረገ። ስለሆነም በዚህም መልክ የየመንግስታቱ ተግባር በመጨናገፍና ሀብት ያልአግባብ ምርታማ ባልሆነ ቦታ በመፍሰስ የአፍሪካ መንግስታት፣ የአገራችንም ጭምር ከውጭው ኃይል ጋር እጂና ጓንቲ በመሆን ህዝቦችን መፈናፈኛ እንዳያገኙ ለማድረግ ችለዋል። በዚህም ምክንያት የተነሳ በተለያዩ ዘርፎች መልክ የሚደርሱና የሚክሰቱ መዛባቶችና በደሎችን ሊዋጋ የሚችል ብቃትነት ያለው የሲቪል ህብረተሰብ ሊቋቋም አልቻለም። ይህ ሁኔታ ደግሞ በራሱ የዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ለሚባሉት መስፋፋትና የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል በማበላሸት፣ የኛም ሆነ የብዙ አፍሪካ አገር ህዝቦች በራሳቸው ላይ ዕምነት እንዳይኖራቸው ሊደረጉ በቃ። በዕርዳታ ስምና ከላይ በተዘረዘረው መልክ ሰርጎ የገባው ኢምፔሪያሊዝም የህዝቦችን ነፃ ፍላጎት አኮላሸባቸው። የማሰብ ኃይላቸውን ተጠቅመው አዳዲስ መሳሪያዎችን በመፍጠር የዕድላቸው ወሳኝ እንዳይሆኑ ተደረጉ። በዚህም ምክንያት የተነሳ የኛና የተቀረው የአፍሪካ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን እንዳይጎናፀፉና የዲሞክራሲ ስርዓት እንዳይገነባ ከሁሉም አቅጣጫ ከፍተኛ እንቅፋት ተደቀነበት። የአፍሪካ መንግስታትም ኢክስፐርት ነን ከሚሉት በሚሰጣቸው የተሳሰተ ኢንፎርሜሽንና የኢኮኖሚ ፖሊሲ የተነሳ ወደ ውስጥ ያተኮረ የኢኮኖሚ ግንባታ ማካሄድ አልተቻለም። ይበልጥ ለኤክስፖርት መስኩ አትኩሮ በመስጠትና ዕዳን ከፋይ በመሆን ለገንዘብ እንቅስቃሴና ለምርት ክንውን ይህ በራሱ እንቅፋት ሆነ። በግሎባል ካፒታሊዝም ግፊት የተነሳ የብዙ አፍሪካ አገሮች የማምረት ኃይል ሲዳከም፣ በዚያው መጠንም የቆሻሻ መጠያ ሆኑ። ሰከንድ ሃንድ ምርቶች የሚራገፉባቸው በመሆን፣ ይህ ዐይነቱ እንቅስቃሴ በተለይም የዋና ከተሞች ገጽታ ሊሆን በቃ። ይህ አጠቃላይ ሁኔታ በሰፊው ህዝብ የማሰብ ኃይል ላይ ከፈተኛ የሆነ አሉታዊ የህሊና ተፅዕኖ በማድረግ ለዲሞክራሲና ለነፃነት የሚደረገውን ትግል ይበልጥ አዘበራረቀው።

ይህንን የተወሳሰበ ዓለም አቀፋዊ ካፒታሊዝም በአገራችንም ሆነ በሌሎችም አፍሪካ አገሮች ሰርጎ መግባትን አስመልክቶ በተለይም ባለፉታ 25 ዓመታት በኛ ዘንድ ምንም ጥናት አልተካሄደም። በአገራችን ምድር ስልጣን የጨበጠውን ኃይል ከውጭው ዓለም ጋር ምንም ግኑኝነት የሌለው ይመሰል እስካሁን ድረስ የሚደረገው ትግል የተሟላ ሳይሆን እጅግ የሚያሳስትና ለዕውነተኛ ነፃነት የሚደረገውን ትግል በማጨናገፍ ላይ። በተለይም ወጣቱ ትውልድ አስተሳሰቡ የሾለና የበሰለ እንዳይሆን እስከዛሬ ድረስ በአገራችን የደረሰው በደልና ኋላ-ቀርነት የውጭው ኃይል ተጠያቂ ሊሆን አይችልም፣ እነሱንም ማስቆጣቱ ተገቢ አይደለም እየተባለ የትግሉን አቅጣጫ ለማዛነፍ ጥረት ይደረጋል። ሳይንሳዊ ጥናት እንዳይካሄድ መንገዱን በመዝጋት ለዕውነተኛ ነፃነትና በሳይንስና በቴክኖሎጂ ለተመሰረተ የኢኮኖሚ ግንባታ የሚደረገው ሁለ-ገብ ነፃነት መልክ እንዳይዝ የሚሆን የማይሆን ፊዩዳላዊ አሉባልታ በማውራት የድህነቱ ዘመን እንዲራዘም እየተደረገ ነው።

በእኛ በኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ በተለይም ደግሞ ለስልጣን በሚታገሉ ኃይሎች ዘንድ ያለው የተሳሳተ ግንዛቤ በብዙ የሶስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮችና፣ የኛንም ጨምሮ በግሎባል ካፒታሊዝም ወይም ይህንን በሚወክሉ መንግስታትና በኛዎች ፖለቲከኛ ነን ባዮች ዘንድ ምንም ዐይነት ግኑኝነትና የጥቅም መተሳሰር የለም። ለምሳሌ ባለፉት 25 ዐመታት በአገራችን ምድር ሲካሄድ የነበረው ፖለቲካና ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በወያኔ አገዛዝ ዕውቀትና ኃይል ብቻ የተካሄዱና የሚካሄዱ ናቸው። የውጭ ኃይሎች፣ በተለይም እንደ ቅዱስ የሚታየው ታላቁ አሜሪካን እንደ እግዚአብሔር ከውጭ ሆኖ የወያኔን አግዛዝ የሚሰራውን የሚያይ እንጂ ምንም ዐይነት ተፅዕኖ እንደማያደርግ ነው። በተጨማሪም እነ ዓለም የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ብድር ሲጠየቁ ከማበደር በሰተቀር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ውስጥ ምንም ዐይነት ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ተፅዕኖ የላቸውም። ከዚህ በመነሳት የሚካሄደውም ትግል ለስልጣን የሚደረግና የወያኔን አገዛዝ የማስወገድ ትግል ብቻ ነው። የነፃነቱም ትግልና ዕውነተኛ ኢኮኖሚያው ዕድገትን የመቀዳጀቱ ጉዳይ ወያኔን ከማስወገድ ውጭ ሊታሰብ አይችልም። ወያኔ ከተወገደ በኋላ ከውጭ ኃይሎች ጋር በሚፈጠረው መልካም መቀራረብ ህዝባችን ዕውነተኛውን ነፃነት ሊቀዳጅ ይችላል የሚል አስተሳሰብ ተስፋፍቷል፤ ተቀባይነትም አግኝቷል። ይህም ማለት እስከአሁን ድረስ የወያኔ አገዛዝ ቢያንስ በኢኮኖሚ ፖሊሲና በርዕዮተ-ዓለም ደረጃ ከእነ ዓለም የገንዘብ ድርጅት ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ህብረተሰብ ያወላገዱበትንና ያዘበራረቁትን ሁኔታ በትክክለኛው የቲዎሪ መነፅር እየተመለከትን መዋጋት የለብንም ማለት ነው። በሌላ አነጋገር፣ የዓለም ኮሙኒቲ የሚባለው በብዙ ሚሊዮን ህጎች የተበተባቸው ስምምነቶችና አገሮችን በሱ ቁጥጥር ስር የማድረጉን ልዩ ልዩ ሴራዎች ሁሉ አምነን መቀበል አለብን። ይህም ማለት ለነፃነት የሚደረገው ትግል የተወሰኑ ኤሊቶች በተረጎሙትና የዓለም አቀፈ ኮሙኒቲው በሚደነግገው መልክ ብቻ የሚካሄድ ነው። በዚህም መልክ የሚተረጎም የነፃነት ትርጉም እንደገና ለውዝግብና ለሌላ የማያቋርጥ ትግል የሚጋብዘን ይሆናል። ልክ የደቡቡ አፍሪቃ ሁኔታ በኛው አገርም ይደገማል። ናኦሚ ክላይን ዘ ሾክ ዶክትሪን(The Shock Doctrine) በሚለው መጽሃፏ ውስጥ የሌሎችን አገሮች ሁኔታ ስታስረዳ እንደገለጸችውና፣ በተከበሩት ኔልሰን ማንዴላ የሚመራው አዲሱ የደቡብ አፍሪቃ መንግስትም ተገዶ ተግባራዊ እንዳደረገው የኢኮኖሚ ፖሊሲና ህብረተሰቡን ለድህነት የዳረገው ዐይነትም መመሪያ፣ በኛው አገርም በአዲሱ ሁኔታና በአዲሱ መንግስት ተግባራዊ ይሆናል ማለት ነው። ከዚህ ስንነሳ በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን እንደ መጽሀፍ ቅዱስ የሚደገመውን የአማርታያ ሴንን የነፃነትንና የመንግስት አተረጓጎም ሁኔታ ጠጋ ብለን እንመልከት።

በትክክል አማርታያ ሴንን ካነበብኩትና ከተረዳሁት አንደኛውና ዋናው የነፃነት እንቅፋት የሚመነጨው ከመንግስታት የጭቆና አወቃቀር ጋር የተያያዘ ነው። የአለፉት ስድሳ ዐመታት የሶስተኛው ዓለም አገሮችን የየመንግስታቱን ኢኮኖሚ ፖሊሲና፣ እንዲሁም ደግሞ የኢንዱስትሪ አገሮችን መንግስታት ፖሊሲ ስንመለከት ሴን የሚለው ትክክል ነው። ይሁንና ግን እንደዚህ ዐይነቱ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮችና፣ በአገራችንም የተገነቡት የመጨቆኛ መሳሪያዎች የቱን ያህል ከውጭው ኃይል ጋር በጥቅም እንደተሳሰሩና እንደተዋቀሩ ከሴን መጽሀፍ ውስጥ ፈልጌ ላገኝ አልቻልኩም። ሴን ለማሳየት እንደሚሞክረው የሶስተኛው ዓለም መንግስታት በራሳቸው የቆሙና በራሳቸው ፍላጎት ብቻ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን እንደሚያወጡ አድርጎ ነው። በተለይም የአፍሪካ መንግስታት እንደዚህ ዐይነቱ ሁኔታ ውስጥ እንደወደቁና፣ ኃላፊነት ያለው አገዛዝ ለመመስረት እንዳልቻሉ የአፍሪካን መንግስታት አወቃቀር ችግርና የአገዛዞችን ፖሊሲ የመረመረ አይደለም። ከዚህም ባሻገር በአብዛኛዎች የአፍሪካ አገሮች የኢኮኖሚ ፖሊሲንና የማህበራዊ ሁኔታን ጉዳይ አስመልክቶ የመከራከር ልምድ አለመኖርና፣ መንግስታትም ከውጭ የሚመጣባቸውን ግፊት ለመቋቋም የሚችሉበት ምሁራዊ መሳሪያና ኃይል ይኑራቸው አይኑራቸው ሴን የመረመረ አይመስለኝም። በመሆኑ አገራችንም ሆነች ሌሎች የአፍሪካ አገሮች በዓለም አቀፍ የግሎባል ካፒታሊዝም ሎጂክና በጭቆና ሰንሰለት ስር የተዋቀሩ መሆናቸውንና፣ ድህነትን እንደሚያስፋፉና ነፃነትንም እንዲሚገፉ ለማሳየት አልሞከረም። ከመንግስቱ ቢሮክራሲ፣ ከወታደር፣ ከጸጥታና እስከፖሊስ ኃይል ድረስ ያሉት አወቃቀሮች ቀድሞውኑ በታሰቡትና በተዋቀሩት የጎሎባል ካፒታሊዝም ሎጂክ አወቃቀር ስልት የተዋቀሩ እንጂ ከየአገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር የተያያዙ በመሆን የየአገሮችን ደህንነት ለመጠበቅ ተብለው አይደለም የተመሰረቱትና እንዲደልቡ የተደረገው። ይህም ማለት አብዛኛዎቹ የሶስተኛው ዓለም የመንግስታት መኪናዎች ከታች ወደ ላይ ከማቴሪያላዊ ፍላጎትና ከረጂም ጊዜ የህብረተሰብ ዕድገት ጋር እየተሻሻሉ የተዋቀሩ ሳይሆን፣ በየአገሩ የሰፈኑትን ገዢዎች ጥቅም ለማሰጠብቅና ወደ ውጭ ደግሞ ታዛዥ በመሆን አገርን ማመሰቃቀል ነው። በዚያው መጠንም አገዛዞችና የመንግስት መኪናዎች በካፒታሊዝም ሎጂክ ውስጥ በመውደቅ ወደ ውስጥ አጠቃላይ የሀብት ክምችት እንዲዳብርና እንዲስፋፋ የሚያደርጉ ሳይሆን፣ እንዲያውም ዕድገትን የሚቀናቀኑና፣ እንዲሁም ድህነትን የሚያስፋፉና የሚያጠናክሩ ናቸው። ምንም ዐይነት ጭንቅላትን የሚያድስ ምሁራዊ እንቅስቃሴ በሌለበትና፣ የኃይል አሰላለፉም ውስን በሆነባቸው አገሮች ስልጣን ላይ ቁጥጥ የሚሉ ኃይሎች የራሳቸውን ጥቅም ከማስጠበቅና የውጭ ኃይሎችን ፍላጎት ተግባራዊ ከማድረግ በስተቀር አልፈው ሊሄዱ የሚችሉ አይደሉም። ስለሆነም አንድ አዲስ አገዛዝ ከፍተኛ ንቃተ-ህሊና እስከሌለው ድረስና፣ በዲስፕሊንና በስርዓት የታነፀ እስካልሆነ ድረስ፣ በተለይም ደግሞ የስልጣኔና የዕድገትን ትርጉም የተረዳ እስካልሆነ ድረስ፣ በዲሞክራሲና በነፃነት ስም ምሎ ተገዝቶ ስልጣን ላይ የሚወጣ ኃይል ቀድሞውን የተገነባውን የመንግስት መኪና እንደገና በማዋቀርና የመጨቆኛ መሳሪያ በማድረግና ከውጭ ኃይሎች ጋር በመመሰጣጠር የድህነቱን ዘመን እንደሚያራዝም በብዙ የሶስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮች የታየ ጉዳይ ነው። በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች፣ አገራችንንም ጨምሮ አብዮት የተካሄደበትን፣ ወይም የአስተዳደር ለውጥ የተደረገበትን ሁኔታ ስንመለከት አብዮቶች ወይም የአገዛዝ ለውጦች ተጨናግፈው የሚቀሩት ይህንን የሚቀናቀን ወይም የሚገታ ኃይል ከመጀመሪያውኑ ስለሌለ ነው። ለምሳሌ በኢትዮጵያ አብዮት ወቅት ህዝባዊ ድርጅቶች በየቦታው ተቋቋመው ነበር። ይህ ዐይነቱ ዱዋል ፓወር በጣም ጥሩ ጅምርና፣ ቢሮክራሲውን የሚተካና የሚቆጣጠር ኃይል ሆኖ የታቀደ ቢሆንም፣ የራሳቸን ጥቅም ተነካብን የሚሉ ኃይሎች ከውጭው ዓለም ጋር በመቆላለፋ፣ በተጨማሪም ውስጥ በተፈጠረው ጨቅላ አስተሳሰብና አላስፈላጊ ትግል ይህ ዐይነቱ የመጀመሪያው የዲሞክራሲ ፅንስስ በእንጭጩ እንዲቀጭ ተደረገ።። ወደ ሌሎች አገሮች ስንመጣ ደግሞ በተጨባጭ ሲታይ እንደ አውሮፓው የምሁር እንቅስቃሴ ህብረተሰብን በሚመለከቱ ማንኛውም ጥያቄዎች ላይ ውይይትና ክርክር ስለማይደረግ በአንዳች አጋጣሚ ስልጣን ላይ የሚወጡ ኃይሎች ስልጣናቸው የህዝብን ፍላጎት ማሟያና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንቢያ ከማድረግ ይልቅ የራሳቸው ጥቅም መሳሪያ በማድረግ ወደ ጨቋኝነት ይለውጧቸዋል። የአንጎላንና የዚምባብዌን እንዲሁም የደቡብ አፍሪካን ሁኔታ መመልከቱ ይበቃል። አንዳንድ አገዛዞች ደግሞ አሻፈረኝ ሲሉና የራሳቸውን መንገድ መከተል ሲጀምሩ እንዲገደሉ ይደረጋል። የቶማስ ሳንካራን ሙከራና አከሻሸፍ መመልከቱ ብቻ በቂ ነው። የቶማስ ሳንካራ ጓደኛ ከፈረንሳዩ የሶሻሊስት መንግስት ነኝ ባዩ የስለላ ኃይል ጋር በመመሰጣጠርና ድጋፍ በማግኘት ቶማስ ሳንካራ እንዲገደል ተደረገ። በተለይም የፈርንሳይ ፓርቲዎች፣ ሶሻሊስቶች ሆኑ ወግ-አጥባቂዎች ምንም ዐይነት ለውጥና የኑሮ መሻሻል እንዳይመጣ በድሮ ቅኝ ግዛቶቻቸው ላይ የሚፈጽሙት ወንጀል በሰፊው ተመዝግቧል። ስለሆነም የካፒታሊስት አገሮች የአፍሪካ አገሮች እንዳያድጉ፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ እንዳይበለጽጉ አንድ አገዛዝ ለየት ያለ መስመር የሚከተል ከሆነ የተለያየ ምክንያት በመፈልግ ብጥብጥ እንዲነሳ ወይም የመንግስት ግልበጣ እንዲካሄድ ያደርጋሉ። ምክንያቱም አገሮች ሁልጊዜ እየተዋከቡ መኖር አለባቸው። እርስ በራሳቸው ሲፋጠጡና ወደ ጦርነት ሲያመሩ ህብረተሰብአዊ መዛባት በመፈጠር የህዝቦች ዋናው ተግባር ጦርነት ይሆናል። ዕድገትና ስልጣኔ የአፍሪካ አገሮች ዋናው የትግል መመሪያ መሆናቸው ቀርቶ የሰው ትግል ወደ ውንብድናነት ይቀየራል። በዚህ መልክ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት በአፍሪካ ምድር ከስድሳ የማያንሱ የመንግስት ግልበጣ ሙከራዎች ተካሄደው ተሳክተዋል። እነዚህ ሁሉ የመንግስት ግልበጣዎች የተካሄዱት ልዩ የክርስትናንና የሊበራሊዝም እሴት አለኝ በሚለው የምዕራቡ ካፒታሊዝም፣ በተለይም በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይና በአሜሪካን መንግስታት አማካይነት ነው። ለሶት መቶ ሺህ ምሁራን ዕልቂት ተጠያቂው የሆነው ኢዲ አሚን በእንግሊዝና በእስራኤል የስለላ ድርጅት ነው ፕሬዚደንት ሚልተን ኦቦቴን አስዎግዶ የግድያ ዘመቻውን የከፈተው።

እንደገና ወደ አገራችን ስንመጣ በደርግ ዘመን የተዋቀረው የጭቆና ስርዓት ቢፈራርስም የወያኔ አገዛዝ የአሰራር ስልቱን በመውሰድ የጭቆና ሰንሰለቱን በእዲስ መልክ መዘርጋት ችሏል። ይሁንና ደግሞ ይህንን የጭቆናና የከፋፍለህ ግዛ አጋዛዙን ለማጠናከር የምዕራቡ ዓለም፣ በተለይም እንግሊዝና አሜሪካ እንደተባበሩት ግልጽ ነው። ሸበረተኝነትን መዋጋት ያስፈልጋል የሚለው ፈሊጥ ሌላው የትግል መፈክር በሆነበት ዘመን በመሀከላቸው ያለው መተሳሰርና ወደ ውስጥ ደግሞ ጭቆናን አስፍኖ ነፃነትን መግፈፍና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዳይመጣ ማድረግ ዋናው የትግል ስትራቴጂ መሆኑን የኔ ትንተና ብቻ ሳይሆን፣ ብዙ ጥናቶችም ያረጋግጣሉ። በተለይም እንደኛ ባለው ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ ድክመት በሰፈነበትና፣ ተማርኩኝ የሚለው አንዳንዱ ዝም ብሎ ሁኔታውን በሚያይበት አገርና፣ ለስልጣን የሚሯሯጠው ደግሞ የሚታየውን ነገር ለማየትና ለመተንተን በማይፈለግበት አገር ለነፃነትና ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ የሚደረገው ትግል እጅግ አድካሚ ይሆናል። ስለሆነም የየካቲቱ አብዮትና በኋላ ደግሞ የምርጫ 97 ውጤት ሊከስሽፉ የቻሉት በመዘናጋት፣ የውጭ ኃይሎችን በመተማመንና ለስልጣን በመስገብገብ የተነሳ ነው። ብሄራዊ አጀንዳን ከማስቀደም ይልቅ የራስን የአጭር ጊዜ ህልም ተግባራዊ ለማድረግ ሲባል ነው እጅ ውስጥ ሊገባ የነበረው ስልጣን እንዲነጠቅ የተደረገውና ህዝባችንም እስከዛሬ ድረስ ፍዳውን እንዲያይ የተፈረደበት። ስለሆነም ከምርጫ 97 በኋላ በውጭ ኃይሎችና በወያኔ አገዛዝ መሀከል ያለው የእከክልኝ ልከክልህ ግኑኝነት የባሰውኑ እየተጠናከረ እንደመጣ እንመለከታለን። ለዚህ ደግሞ የአግአዚ ጦር በቂ ማረጋገጫ ነው። ይሁንና ግን አሁንም ቢሆን ይህንን ሀቅ ለመቀበል የማይፈልጉ ተቃውሚ ነን የሚሉ ኃይሎች አሉ። ታዲያ በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ምን ዐይነት የነፃነት ትግል ነው ሊካሄድ የሚችለው ? ምንስ ዐይነት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት ነው ትግል የሚካሄደው ?

ታጋይ ነን የሚሉ ኃይሎች በሙሉ በርግጥም ለነፃነት እንታገላለን የሚሉ ከሆነ፣ 1ኛ) የመንግስትን መኪና አወቃቀር ከቲዎሪ አንፃር በሰፊው በማጥናትና በመገምገም ውይይት እንዲደረግበርት ማድረግ አለባቸው። የመንግስትን ምንነትና ተግባርን አስመልክቶ ከፕላቶን ጀምሮ እስከነ ሺለሩ ጥበባዊ መንግስት ድረስ ሰፊ ውይይትና ክርክር ተካሂዷል። የማርክሲስት ምሁራንም፣ በተለይም እነ ፖላንትሳስ የካፒታሊዝምን መንግስት ምንነትና የሀብት ክምችት አጋዥነት በሰፊው አጥንተው በመጽሀፍ መልክ ለንባብ አቅርበዋል። በተጨማሪም ሌሎች የሶስተኛው ዓለም አገሮችና አንዳንድ የአውሮፓ ምሁራን እንደዚሁ በሶስተኛው ዓለምና በካፒታሊስት አገሮች መሀከል ስላለው መተሳሰርና የዕድገት ማነቆነት በበቂው አትተዋል። ጆን ጋልቱን የሚባለው የስዊድሹ የሶስዮሎጂና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር፣ እንደዚሁ „ኢምፔሪያሊዝምና የኃይል አወቃቀር“(Imperialism and Structural Power) በሚለው ግሩም መጽሀፉ፣ በኢምፔሪያሊዝም አማካይነት በሶስተኛው ዓለም አገር ህዝቦች ላይ የሚደርሰውን ጭቆናና በመንግስታቱ መሀክል ያለውን የጥቅ ም መተሳሰረና የዕድገት ማነቆነት ሳይንሳዊ በሆነ መልክ አትቷል። ከዚህ በሻገር በተለይም የፋይናንስ ካፒታሊዝም አይሎ በመወጣበት ባሁኑ ወቅት የብዙ ካፒታሊስት አገሮች የመንግስት መኪና በፊናንስ ካፒታሊዝም ቁጥጥር ስር እየዋለና የስለላ መዋቅሩንም እያጠናከረ በመምጣት ነፃነትን አፋኝ እየሆነ መጥቷል። በመሆኑም ይህ ጉዳይ በሶስተኛው ዓለም አገሮች በመስፋፋት መንግስታቱን ተቀጣይና ትዕዛዝ ተቀባይ አድርጓቸዋል። በተለይም ይህ ዐይነቱ ነፃነትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማፈኑና ህዝብን መቆጣጠሩ በአሜሪካን ምድር የተስፋፋ ነው። ሳልማድ ሩድሺን ስድሳ አስምስተኛ ዕድሜውን ሲያከብር ባደረገው ንግግር የነፃነት ትርጉም በተለይም በአሜሪካ ምድር እየታፈነ እንደመጣና፣ ማን ምን ዐይነት መጽሀፍን እንደሚያነብ እንደሚመዘገብ በንግግሩ ላይ ጠቅሷል። 2ኛ) የአገራችንን የመንግስት አወቃቀር ከታሪክ አንፃር ማጥናትና፣ ለምንስና እንዴት ለኢኮኖሚ ዕድገት ጠንቅ እንደሆነ ማማልከቱ የምሁራን ተግባር ነው። ከዚህ ስንነሳ ከ40ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ በአገራችን ምድር የተዋቀረው መንግስታዊ መኪና ከውጭው ኃይል ጋር የተሳሰረ እንደነበረ ማጥናትና ለውይይት ማቅረብ የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ይህ ጥያቄ በሰፊው ሳይጠናና ለክርክር ሳይቀርብ ወደ ስልጣን የሚደረግ ጉዞ የመጨረሻ መጨረሻ የነፃነቱንና የዕድገቱን ዘመን ያጨልመዋል። 3ኛ) ኢትዮጵያ ከውጭው ዓለም ጋር ግኑኝነቷን ካጠናከረች በኋላ በርዕዮተ-ዓለምና በአመለካከት ደረጃ፣ እንዲሁም ደግሞ በፍጆታ አጠቃቀም ያገኘችውንም ጥቅም ሆነ የደረሰባትን ጉዳት አንስቶ መወያየቱ ለነፃነት የሚደረገውን ትግል ግልጽ ያደርገዋል። በተለይም በባህል ላይ የሚደርሰው ወረራና ወጣቱን ማዘናጋቱ የቱን ያህል ራሳችንን እንዳናውቅና የነፃነቱንም ትግል አስቸጋሪ እንዳደረገው መወያየቱ ጠቃሚ ይመስለኛል። ከዚህም በመነሳት የዓለም ኮሙኒቲ የሚባለው የሚለፈፈውን የህግ-የበላይነትና የገበያ ወይም ነፃ ንግድ ኢኮኖሚ ውስንነት መመርመርና እኛ ከምናልመውና ከምንታገልለት ነፃነትና ዕድገት ጋር ይጣጣም ወይም አይጣጣም እንደሆን መወያዩቱ እጅግ አስፈላጊ ነው። የህግ የበላይነት ዛሬ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያገኘ ኖርም ነው ብሎ ማተቱ ብቻ የሚበቃ አይመስለኝም። የህግ የበላይነት ከጥቂት ግለሰቦች በሀብት መደለብ ጋር የተያያዘና፣ ይሁንና ግን ሁሉም በህግ ፊት እኩል ነው የሚለውን የተዛባ አመለካከት የሚያንፀባርቅ መሆኑን ማሳየት ያስፈልጋል። በተጨማሪም በዛሬው ዓለም ብዙ አገዛዞችና ኢንስቲቱሽኖች በሎቢይስቶች በሚደገፉበትና በተሰገሰጉበት ዘመን የህግ የበላይነትና ተራ ምርጫ የሚባሉት ቦታ እንደሌላቸው መረዳት ያስፈልጋል። የፈለገውን ያህል ህዝባዊ ተቃውሞ ቢደርስም በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ፊርማዎች ለአገዛዞችና ለህዝብ ተጠሪዎች ቢቀርቡም፣ መንግስታት በሎቢስቶች ግፊት የተነሳ የህዝብን እርሮና ጩኸት እንደማይሰሙ እንከታተላለን። በአሜሪካንና በአውሮፓ አንድነት የሚካሄደውን የነፃ ንግድ ስምምነት(TTIP) ለተከታተለው የምንገነዘበው ድርድሩ በተዘጋ መልክ የሚካሄድና ህዝብም እንዲያውቀው የሚደረግ አይደለም። ራሳቸው የህዝብ ተጠሪዎች ነን የሚሉ ፓርሊሜንቴሪያን እንኳ የስምምነቱን ውልና አካሄድ ምስጢር ማንበብ አይፈቀድላቸውም። እስከዚህ ድረስ ነው የዘመኑ ካፒታሊዝም የህዝቦችን ነፃነት መግፈፍ የቻለው። በምንመገበው ምግብ ውስጥ ያሉትን ንጥረ-ነገሮች እንኳ የማወቅ መብት የለንም። መታወቅ ወይም በፓኬቱ ላይ በዝርዝር መቀመጥ የለባቸውም። ምክንያቱም ይህ ዐይነቱ ግልጽነት የነፃ ገበያን መሰረተ-ሃሳብ ይፃረራል የሚል ነው። ከዚህ ስንነሳ እኛ ኢትዮጵያውያን በነፃነትና በኢኮኖሚ ዕድገት መሀከል ያለውን ዲያሌክቲካዊ ግኑኝነት በአንድ በኩል፣ በሌላ ወገን ደግሞ በዓለም አቀፋዊው ካፒታሊዝምና በመንግስታችን መሀከል ያለውን መተሳሰርና መደጋገፍ፣ ከዚህም በመነሳት ይህ ዐይነቱ የእከክልኝ ልከክልህ መደጋገፍና መተሳሰር የቱን ያህል ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለነፃነት፣ እንዲሁም ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንቅፋት እንደሚሆን መወያየቱ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ዲሞክራሲና የዲሞክራሲ ትርጉም!

በጥንታዊቱ ግሪክ ዘመን ዲሞክራሲ የሚለው ጽንሰ-ሃሳብ ከህዝብ አገዛዝ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ተግባራዊነቱ በሶስት ኢንስቲቱሽኖች የሚወሰን ነበር። በ507 ዓ.ም ከክርስቶስ ልደት በፊት ሲሌይስቴነስ የሚባለው መሪ ፖለቲካዊ የጥገና ለውጥ ያደርጋል። በጥገና ለውጡ መሰረት የውስጡን ፖለቲካና የውጭውን ፖሊሲ የሚያስተዳድር አካል ይመርጣል። ይህ አካል ህግን የሚያወጣና ተግባራዊ የሚያደርግ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ፣ ከተለያዩ የአቴን ጎሳዎች የተውጣጡ ተወካዮች የሚሳተፉበት መድረክ ይቋቋማል። በሶስተኛ ደረጃ፣ ህዝቡ ብሶቱን ወይም ቅሬታውን የሚያቀርብበት ፍርድቤት ይቋቋማል። ይህ ዐይነቱ ዲሞክራሲ ከዚህ ቀደም ብሎ በአሪስቶክራሲውና በተራው ህዝብ መሀከል የነበረውን ልዩነት ከሞላ ጎደል የሰበረ በመሆኑ፣ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ህዝቡ ከህግ ፊት እኩል ነበር። በሌላ ወገን እንደዚህ ዐይነቱ ዲሞክራሲ የተወሰነውን የአቴንን ዜጋ የሚመለከትና ሴቶችንም ያገለለ ነበር። ይሁንና ከጊዜው የህብረተሰብ ዕድገት አንፃርና በጎሳዎች መሀከል ከሚደረገው ሽኩቻ ሁኔታ ስንነሳ ይህ በአቴኑ መሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ የሆነው የዲሞክራሲ ጽንሰ-ሃሳብ አንድ እርምጃና ከዚያ በኋላ ለተነሳው የአውሮፓ የዲሞክራሲ ትግልና አስተሳሰብ መሰረት የጣለ ነው ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። በመሆኑም በአቴኑ ዘመን ተግባራዊ የሆነው የዲሞክራሲ አስተሳሰብ ከጎሳ ፖለቲካ ጋር የተያያዘ ሳይሆን ቀስ በቀስ ለሲቪል ሊበሪትና ለግለሰብአዊ ነፃነት በሩን የከፈተ ነው ማለት ይቻላል። እንደዚህ ከክርስቶስ ልድት በፊት በ594 ዓ.ም ስልጣንን የተረከበው ሶሎን የሚባለው መሪ አዲስና የተሻሻለ የጥገና ለውጥና ህገ-መንግስት እንዲወጣ ያደርጋል። በጥገና ለውጡም መሰረት ህዝቡ ተጠሪዎችን በመምረጥ በፖለቲካ አወቃቀሩ ላይ ተሳትፎ እንዲኖረው ይደረጋል። በዚህም መሰረት አዲስ የተመረጠው የህዝብ ተጠሪ ሶስት ተግባሮች እንዲኖሩት ይደረጋል። ኦርጋኑም ህግን የሚያወጣ፣ የመንስት ሰራተኞችን የሚመርጥና ጦርነት መካሄዱንና አለመካሄዱን የሚወስን ይሆናል። ይሁንና ግን በዚህ ዐይነቱ ፖለቲካዊ የጥገና ለውጥ ሴቶች፣ አገልጋዮችና የውጭ ሰዎች የመምረጥ መብት አልነበራቸውም። በህገ-መንግስቱ መሰረት፣ በእርጋኑ ውስጥ ተሳትፎ የነበራቸው የመሬት ከበርቴዎች፣ ሀብታም ነጋዴዎች፣ የተለያየ ደረጃ ያላቸው አንጥረኞችና ገበሪዎች ነበሩ። በዚህ መልክ በሶሎን አማካይነት የተዋቀረው አዲሱ ዲሞክራሲያዊና ሚዛናዊ አገዛዝ በዕዳ የተተበተበውንና በባላባቱ ስር ጥገኛ የሆነውን ገበሬ ነፃ በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰፋ ያለ የስልጣኔ መሰረት ለመጣል ረዳ። በእርግጥ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው ፍልስፍናም ሆነ ማቲማቲክስ፣ እንዲሁም ጥበብና አርክቴክቸር ቀጥሎም ድራማ የበለጠ በሰው የመፍጠር ኃይል ተግባራዊ ሊሆኑ የቻሉት። ሶሎን ራሱ ፈላስፋና፣ በከፍተኛ ደረጃም የተገለጸለት መሪ ስለነበር የዲሞክራሲን ሰፊ ትርጉም በመረዳት በልዩ ልዩ መልኮች ሊገለጹ የሚችሉበትን ሁኔታ ማዘጋጀት ቻለ። ይህ ሁኔታ በግሪክ ምድር ውስጥ በተለይም በአቴንና በአካባቢው ለስራ ክፍፍል መዳበርና ለንግድ ልውውጥ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል። በዚህ መልክ ቀደም ብሎ በልዩ ልዩ ጎሳዎች ይደረግ የነበረው ውጊያና ፍጥጫ ቆሞ ጠቅላላው ህዝብ ለስራና ለንግድ ታጥቆ ይነሳል። ይሁንና ግን ሶሎን ስልጣኑን ከለቀቀ በኋላ ይህ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ፈተና ይደርስበታል። ሶፊስቶች የመንግስቱን መኪና ወይም አገዛዙን በመክበብና ለራሳቸው መጠቀሚያ በማድረግ የጦርነት ምንጭ ያደርጉታል። የኋላ ኋላም የግሪኩ ስልጣኔ በሮማውያን ወራሪዎች ቀስ በቀስ ድምጥማጡ ይጠፋል። ታላቁ አሊክሳንደር አልገበርም ያሉትን ሁሉ ካሸነፈ በኋላ ከግብጽ፣ በሱ ስም ከተጠራው አሊክሳንደሪያ ከተማ በመነሳት በአካባቢው ስልጣኔን ለማስፋፋት ያደረገው ሙከራ በሮማውያን ወራሪዎች ይከሽፋል። ወደ ሰባት መቶ ሺህ የሚጠጉ መጽሀፎችን ሁለት ጊዜ ካቃጠሉና፣ ከግብጽም ሀብት ከዘረፉ በኋላ የግሪክ ስልጣኔ ሲደመሰስ በሱ ምትክ ወደ ሰባት መቶ ዓመታት የሚጠጋ የጨለማ ስርዓት ይዘረጋል። የሮማውያን ወረራና ሌሎችን ገባር አድርጎ መግዛት ቀስ በቀስ እየተዳከመ ይመጣል። በየቦታው የተስፋፋው የሮማውያን ኃይሉ እየተሟጠጠ ይመጣል። የመጨረሻ መጨረሻም በጀርመን ወራሪዎች በመደምሰስ ለፊዩዳሉ ስርዓት በሩን ይከፍታል። በካቶሊክ ቄሶችና በአሪስቶክራሲው የአውሮፓ ህዝብ መሰቃየት ይጀምራል። ይህ ሁኔታ ግን የኋላ ኋላ በተገለጸላቸው ኃይሎች፣ በተለይም በተፈጥሮ ሳይንስ አማካይነት መጋፈጥ ሲጀምር፣ አዳዲስ ኃይሎች በመፈጠር የድሮው አገዛዝ በአረጀው መልኩ ሊቀጥል እንደማይችል ግልጽ ይሆናል ።

ከኢንላይተሜንት ጀምሮ የተደረገውን በፍጹም ሞናርኪዎችን አገዛዝ ላይ ይካሄድ የነበረውን የተቃውሞ ትግል ስንመለከት ሪፑብሊክን መመስረትና ገበሬውን ከአርስቶክራቲውና ከፊዩዳሉ መደብ ለማላቀቅ የተደረገ ትግል ዲሞክራሲያዊ ትግል ነው ማለት ይቻላል። በተለይም በካቶሊክ ሃይማኖት ተከታዮችና በፕሮቴስታንት የሃይማኖት መሪዎች መሀከል የነበረው ትግል በአልተገለጸላቸውና በተገለጸላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መሀከል የተደረገ የመረረ ትግል ነበር። ሁለቱ የሃይማኖት ተከታይ መሪዎች በከፈቱት ጦርነት በአንዳንድ ቦታዎች ሁለት ሶስተኛው የሚሆነው ህዝብ እንዳለቀ የታሪክ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ። ከዚህ ውጣ ውረድና የርስ በርስ መተላለቅ በኋላ ነው ጥቂት የተገለጸላቸው ምሁራን ጣልቃ በመግባት መረጋጋት ሊፈጥሩና፣ በፊዩዳሉ አገዛዝ የተሰቃዩ አገዛዞች በፍጹም ሞናርኪያዊ አገዛዝ በመጠቃለል ብዙ የአውሮፓ አገሮች ወደ ህብረ-ብሄር ግንባታ መሸጋገር የቻሉት። ከዚህ የምንረዳው ለዲሞክራሲና ለነጻነት የሚደረገው ትግል በጣም አስቸጋሪና፣ የግዴታም የተገጸላቸው፣ ሰፋና የጠለቀ ዕውቀት ያላቸው ሳይንቲስቶችና ፈላስፋዎች ጣልቃ ገብነት የቱን ያህል ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወት ነው። ምክንያቱም በጊዜው የነበሩት አገዛዞች በጣም አክራሪዎች ስለነበሩና፣ ህዝቡም በበሽታና በድህነት ይሰቃይ ስለነበር ከዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለመውጣት እንዴት አድርጎ አገዛዞችን የጥቅማቸው ሳይሆን የመንፈሳቸው ተገዢዎች ማድረግ ይቻላል? የሚለው አስተሳሰብ ነበር ምሁራንን ያስጨንቃቸው የነበረው። ምክንያቱም ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ፣ የባሰ ችግር ውስጥ ላለመግባት ሲባል የተደረሰበት ውሳኔ ከፍተኛ የጭንቅላት ሰራ መስራትና የምሁራኑን መሰረት ማስፋት ነበር። ይህ ዐይነቱ አካሄድ በአውሮፓ ምድር ውስጥ በልዩ ልዩ መልክ ሊገለጽ የሚችል ምሁራዊ እንቅስቃሴ እንዲስፋፋና እንዲዳብር በማድረግ የዲሞክራሲን ጥያቄና አፈታት የበለጠ እምርታና መልክ ሰጠው።

በሌላ ወገን ካፒታሊዝም እያደገ ሲመጣ የወዝ አደሩ መደብም አዳዲስ ጥያቄዎች ማንሳት ጀመረ። በሙያ ማህበር መደራጀት፣ የስራ ሰዓት መቀነስና ከምርት ዕድገት ጋር ሊሄድ የሚችል ጥያቄዎች በመነሳት የከበርቴውን መደብ ማፋጠጥ ቻለ። ቀስ በቀስም የማርክስ ስራዎች ሲስፋፉ የተወሰነው የሰራተኛው መደብ ራሱን በኮሙኒስት ወይም በሶሻሊስታዊ አመለካከት ማደራጀት ቻለ። በየጊዜው ለሚነሳው የኢኮኖሚ ቀውስና ጥልቀት ያለው ብዝበዛ የካርል ማርክስና የፍሪድሪሽ ኤንግልስ ስራዎች እንደመመሪያ በመሆን አማራጭ የህብረተሰብ ማደራጃ ዘዴ ሆነ። ከካፒታሊዝም የኢኮኖሚና የህብረተሰብ አደረጃጀት ባሻገርም ሌላም ስርዓት መፍጠር እንደሚቻል ቲዎሪው እንደ አማራጭ ሆኖ ቀረበ። የማርክስ ስራዎች በጊዜው የነበረውን የካፒታሊዝም ዕድገት ነፀብራቆች ወይንም ውጤቶች ናቸው ማለት ይቻላል። የጊዜው መንፈስ(Zeitgeist) የወለደው ሲሆን፣ ዝም ብሎ ከሰማይ ዱብ ያለ ሳይሆን፣ ማርክስ ከሃያና ከሰላሳ ዐመታት ጥናትና ምርምር በኋላ ቀስ በቀስ ያዳበረው ነው። የማርክስ ስራዎችም የሚያረጋግጡት አንድን ህብረተሰብ፣ በተለይም የካፒታሊዝምን ስርዓት እነ አዳም ስሚዝና ሌሎቹ የጥንት ኢኮኖሚስቶቸ(Classical Economists) በመባል በሚታወቁት በተረጎሙት መልክ ሳይሆን በሌላ መልክም መተርጎም እንደሚቻልና፣ በማርክስ አባባል ይኸኛው ሳይንሳዊ የህብረተሰብ መተንተኛ ዘዴ መሆኑን ነው ለማሳየት የተሞከረው። በዚህ መልክ አዳዲስ ቲዎሪዎች ሲፈልቁና ሲስፋፉ የምሁሩም አስተሳሰብ በተወሰነ አመለካከት ብቻ የሚሽከረከር ሳይሆን፣ የነገሮችን ሂደት ከሌላም አኳያ መመርመር እንደሚቻል ግንዛቤ ተደረሰበት። ስለሆነም እየተስፋፋ የመጣው ቲዎሪና የሰራተኛው መደብ በሙያ ማህበሩ መደራጀት በኢንዱስትሪ ውስጥና ከዚያ ውጭ ከከበርቴው መደብ ጋር በተጠሪዎቹ አማካይነት ቁጭ ብሎ ለመደራደር የሚቻልበት ሁኔታ ተፈጠረ። ይህ የሚያሳየው ምንድነው ? አንድ ህብረተሰብ መስመሩን እንዳይስት፣ ወይም ደግሞ የጥቂቶች መጨፈሪያ እንዳይሆን ከተፈለገ የግዴታ ሁሉንም አስተሳሰቦች ሊያስተናግድ የሚችል ምሁራዊና ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ነው።

በዘመናችን የዲሞክራሲን ትርጉምንና ተግባራዊነት ስንመለከት፣ ተግባራዊነቱ ተወካይን በመምረጥና በመመረጥ የሚገለጽ ቢሆንም፣ ይህ ዐይነቱ ሂደት ሊገለጽ የሚችለው በሶስት ኦርጋኖች መሀከል ባለው የስራ-ክፍፍል ነው። ይህም ማለት ኤክስኪዩቲቭ፣ የህግ አውጭና ህግ አስፈጻሚ። ሌሎች ዲሞክራሲያዊ ኢንስቲቱሽኖች በሙሉ በዚህ ስር ሲጠቃለሉ፣ በተለይም ከ1980ዎች ጀምሮ እያየለ የመጣው መንግስትንና ፓርላሜንትን የሚቆጣጠር ሰፋ ያለ የሲቪክ ማህበራት አለ። ስለሆነም በነፃ መደራጀት፣ ሃሳብን መግለጽ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግና ህዝብንና አካባቢን የሚጎዱ ነገሮች እንዲቆሙ ማድረግ በትግል የተገኙ ብቻ ሳይሆኑ፣ የጠቅላላው የህብረተሰብ ጉዞና ዕድገት አጋዥ እንደሆኑ ማየት የተቻለው ከብዙ ውጣ ውረድና በከፍተኛ ምሁራዊ ተሳትፎ አማካይነት ነው። እዚህ ላይ አስቸጋሪ የሚሆነው የዲሞክራሲ አነሳሰና ትግል፣ የጥያቄው አቀራረብ በጣም ስፊና ውስብስብ ስለሆነ በማቲማቲካል ሞዴሎች ማቅረብ አይቻልም። ይህ ዐይነቱ አቀራረብ እጅግ አሳሳች ከመሆኑም የተነሳ ወደ ማይሆን አቅጣጫ እንድናመራ በማድረግ ለዕውነተኛ ነፃነት የሚደረግውን ትግል እንድንዘነጋ ያደርገናል። በሌላ አነጋገር፣ ዲሞክራሲ የሚጨበጥና የሚዳሰስ አይደለም፤ የምንለማመድበት፤ የምንኖርበት፣ ስሜታችንንና ቅሬታችንን የምንገልጽበት፣ የሚያሳስበንና የሚያስጨንቀንን ወደ ውጭ አውጥተን ለመወያየት የሚያስችለን መሳሪያ ነው። ስለዚህ ነው ዲሞክራሲን አታየውም፣ ትኖርበታለህ፣ ትለማመድበታለህ፣ የህይወትህ አንደኛው አካል እንዲሆን ታደርገዋለህ የሚባለው። ስለሆነም የዲሞክራሲ ምንነት በቁጥር የሚለካ ወይም በማቲማቴካል ሞዴል የሚረጋገጥ አይደለም። ከዚህ ስንነሳ የዲሞክራሲ ጥያቄ፣ ሶሻል ጀስቲስንና የኢኮኖሚ ጀስቲስን፣ እንዲሁም የፖለቲካ ጀስቲስኝ የሚያካትት ሲሆን፣ እነዚህ ነገሮች ደግሞ የግዴታ ዲሞክራሲያዊ ሆነው ከተዋቀሩ ኢንስቲቱሽኖች ጋር መያያዝ አለባቸው። ይሁንና ግን የካፒታሊዝም ዕድገትና መስፋፋት የሰው ጭንቅላት ከሚሸከመው በላይ በመሆኑ፣ አብዛኛው ህዝብ አቅመ-ቢስ እየሆነ እንደመጣ እንመለከታለን። በተለይም ጊዜ ወስዶ ምሁራዊ ጥናት የሚያደርገው በጣም ጥቂቱ ስለሆነ፣ ሰፊው ህዝብ በቴክኖከራቲክ ጽንሰ-ሃሳብና የአሰራር ዘዴ እየተደናበረና ግራ እየተጋባ ነው። ከዚህ በሻገር የመንግስት መኪናዎች ይበልጥ በኤክስክቲቩ የሚመሩ ስለሆነና፣ የሚሊታሪ ኢንደስትሪያል ትስስር(Military Industrail Complex) ስር እየሰደደና እየተጠናከረ በመምጣቱ፣ የፓርሊሜንታሪ ዲሞክራሲን እያዳከመው፣ ተጠሪዎች የህዝብ ተወካዮች መሆናቸው ቀርቶ የራሳቸውን ህይወት ማራዘሚያ መድረክ አድርገውታል ማለት ይቻላል። ስለሆነም ስልጣንን የጨበጡ ፓርቲዎችና ፕሬዜደንቱ ወይም ጠቅላይ ሚኒስተሮች የአንድ አገር ተጠሪ ቢመስሉም፣ በቀጥታ የሚያንፀባርቁት የኢንዱስትሪና የሚሊተሪ ትስስርን ጥቅምና፣ በፀጥታ ኃይሎች አማካይነት የተሳሳተ ኢንፎርሜሽን እየተሰጣቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጦርነትን የሚያስፋፉና መንግስታትን የሚያወድሙ ሆነዋል። የከበርቴው የሊበራል ዲሞክራሲ እሴትና የክርስቲያን ቫልዩ የሚባለው አብዛኛው የምዕራብ አውሮፖና የአሜሪካ የሚኩራሩበት፣ በመሰረቱ ባዶ አነጋገር ነው ዛሬ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት አለው እየተባለ የሚለፈፈው። በዚህ መልክ ለሁላችንም የማይታይ ቀስ በቀስ ስር የሰደደ የመንግስት ግልበጣ ተካሂዷል ማለት ይቻላል። ያም ሆኖ ግን ይህንን የሚያጋልጡና የሚዋጉ ኃይሎችና ድርጅቶች እንደ እንጉዳይ ፈልተዋል። ስለሆነም ለዕውነተኛ ዲሞክራሲና ነፃነት የሚደረገው ትግል ያለቀለት ሳይሆን፣ ገና በአዲስ መልክ የሚቀጥል መሆኑን እንገነዘባለን።

ወደ አገራችን ስንመጣ ለዲሞክራሲ ያለን ግንዛቤ አስቸጋሪ የሚሆነው፣ የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄን ስልጣን ላይ ያሉ ኃይሎች በቀላሉ ስልጣን ለመስጠት ወይም ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ለመገንዘብ ዝግጁ አለመሆናችን ነው። በዚህም ምክንያት የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ የረጅም ጊዜ ምሁራዊ ትግልን እንደሚጠይቁና፣ ለዚህ ደግሞ ከፍተኛ መስዋዕትነት መከፈል እንዳለበት አለመገንዘባችን በምን መልክ ትግሉን ማካሄድ አንዳለበን ለመወያየት ዝግጁ ባለመሆናችን ትግሉን ውስብስብ እያደረገው መጥቷል። ከዚህም በላይ የስልጣን ጥያቄ ከስልጣኔና ከዕውነተኛ የዲሞክራሲ ፕሮጀክት ጋር ሊያያዝ ባለመቻሉ ትግሉ ለስልጣን ብቻ የሚደረግ ትግል እንጂ ለመሰረታዊ ለውጥ እንዳይደለ ሁኔታዎችን ለተከታተለ ሊገነዘብ ይችላል። በሌላ ወገን ግን በአብዛኞቻቸን የተደረሰበት ድምዳሜ አንድን አገዛዝ በኃይል አስወግዶ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ማስፈን ይቻላል የሚለው አደገኛ ግንዛቤ ነው። ምክንያቱም እነዚህ በአጭር መንገድ፣ ይሁንና የዲሞክራሲን አፈታት የባሰውኑ የተወሳሰበና አድካሚ የሚያደርገውን ትግል የሚያካሂዱት እኛ የተሻለ የዲሞክራሲ ግንዛቤ አለን ከሚለው አስተሳሰብ የመነጨ አጉል ስሌት ነው። ይህ እንደማይሆን ደግሞ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮችና በአገራችንም ጭምር ተረጋግጧል። ምክንያቱም እነዚህ በአጭር መንገድ ስልጣን ለመያዝ የሚታገሉ ኃይሎች ራሳቸውም የዚያው ያልተገለጸለት ህብረተሰብ ውጤት በመሆናቸው አጭሩን መንገድ እንመርጣለን ብለው ሲነሱ የባሰውኑ ትግሉን ውስብስብ በማድረግ ሁላችንም በቀላሉ ልንወጣው የማንችለው ችግር ውስጥ ይከቱናሎ። በተጨማሪም እነዚህ የተሻለ የዲሞክራሲ ግንዛቤ አለን የሚሉ ኃይሎች ለግልጽ ውይይትና ክርክር የተዘጋጁ አይደሉም። የአገራችንን ያለፉትን አርባና ሃምሳ ዓመታት ትግል ስንመረምር፣ ለዲሞክራሲና ለመብታችን እንታገላለን ብለው የሚነሱ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ስልጣን ከጨበጡ በኋላ የባሰውኑ አፋኘና ገዳይ እንደሚሆኑ ነው። ህብረተሰብን ከማዘበራረቅና የድህነቱን ዘመን ከማራዘም በስተቀር ሌላ የሚታያቸው ነገር የለም። በዚህም የተነሳ ስንትና ስንት መቶ ዓመታት የተገነቡ እሴቶችንና ባህሎች እንዲበጣጠሱ በማድረግ ህዝቡ በውዥንብር ዓለም ውስጥ እንዲኖር ያደርጉታል። በኤርትራ ምድር የሰፈነው ፋሺሽታዊ አገዛዝና፣ ወደ ፋሽሺዝም የሚያመራው የአገራችን አመራር ከተሳሳተ የትግልና የዲሞክራሲ አስተሳሰብ የመነጨ አጉል አካሄድ ነው። ህዝቡን በዘለዓለማዊ ፍጥጫና መፈራራት ውስጥ በመክተት ሰብአዊ መብቱ ተገፎ ፍዳውን እንዲያይ የተደረገው መጀመሪያውኑ የዲሞክራሲ ጥያቄ ከዕውነተኛ የጭንቅላት ወይም የመንፈስ ተሃድሶ ጋር ሊያያዝ ባለመቻሉ ነው። የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ ከጭንቅላት ምርምርና ተሃድሶ ሳይሆን በጠብመንጃ ኃይል ይገኛል ተብሎ ውሳኔ ስለተደረሰበት፣ ይህ በራሱ ከረጅም ጊዜ አንፃር ሌላ የጭቆና አገዛዝ ምንጭ ሊሆን በቃ።

በአገራችን ምድር በስልጣን ላይ የሚወጡ ኃይሎች ስለዲሞክራሲ ሲነሳ የሚያስፈራቸው ነገር የዲሞክራሲን አስፈላጊነት አለመገንዘባቸው ብቻ ሳይሆን፣ ዲሞክራሲያዊ መብት ተፈጥሮአዊ መብትም መሆኑን ለመረዳት ባለመቻላቸው ነው። በዚህም የተነሳ የወታደሩ አገዛዝ ስልጣን ከጨበጠ በኋላ በዲሞራሴ ጥያቄ ላይ እንዴት እንዳንገራገረና፣ የኋላ ኋላ ደግሞ የባሰውኑ ወደ አፋኝና ወደ ጨፍጫፊነት እንዳመራ እንገነዘባለን። ህዝቡ እየነቃ ሲመጣና ህዝባዊ ድርጅቶች እንደ አሸን መፍለቅ ሲጀመሩ እሱ ብቻ ሳይሆን ቢሮክራሲውም ጭምር መርበድበድ ጀመሩ። ተራማጅ ነን በሚሉ ኃይሎች ዘንድ የተደረገውን መገዳደል ትተን፣ ወርቃማ ጎኑን ስንመለከት ለመጀመሪያ ጊዜ ህዝባዊ ድርጅቶች እንደ አሸን የፈለቁበትና፣ እንዲሁም የዕደ-ጥበብ ሙያዎችና የልዩ ልዩ ብሄረሰብ-ባህሎች የዳበሩበት ዘመን የዲሞክራሲ ጭላንጭል በሚታይበት በአጭር ጊዜ ውስጥ ነበር። ውስጥ ባለው የአገዛዝ ቅራኔና፣ በተለይም ደግሞ ተራማጅ ነኝ በሚለው ኃይል መሀከል ከወረቀት ትግል ይልቅ የጠብመንጃ ትግል ነው የሚያዋጣው በማለት የትግሉን አቃጣጫ ለመቀየር ሙከራ ባይደረግ ኖሮ፣ የዲሞክራሲው ጥያቄ ሌላ መስመርን ይዞ ይጓዝ ነበር። ብዙ ምክንያቶች ተደራርበው፣ በተለይም ደግሞ ተራማጅ ነኝ ይል የነበረው ኃይል ኃሉን አስተባብሮ በቀና መንፈሰ በዕውቀትና በሃሳብ ዙሪያ በመሰባሰብ ቢታገል ኖሮ የወታደሩን አገዛዝም መቆጣጠር ይቻል ነበር። ይህም ሊሆን ባለመቻሉ ቀስ በቀስ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ሲወጣ የዲሞክራሲ ጥያቄ የባሰውኑ መታፈን ጀመረ። በመጀመሪያ አገርን ማዳን በሚለው ስር በተለይም አድርባዩ ሁሉ በመሰባሰብና ቢሮክራሲው ጉያ ስር በመውደቅ ከቀይ ሽብርና ከነጭ ሽብር በተረፉት ላይ ዘመቻውን በማካሄድ አገሪቱን የምሁር አልባ ለማድረግ በቃ። እዚህ ላይ ያልገባኝ ነገር፣ መኢሶን በኢህአፓ ላይ፣ ወይም ኢህአፓ በመኢሶን ላይ ሲዘምቱና ሲገዳደሉ ሰውን ብቻ ሳይሆን ዕውቀት ያለውንም ምሁራዊ ኃይል እንደገደሉ አለመገንዘባቸው ነው። ደርግም ሆነ የተቀሩት ለደርግ ያደሩ የማርክሲስት ሌኒንስት ድርጅቶች ነን ባዮች አባሎች የተረፈውን ምሁር እየጠቆሙ ሲያስገድሉ በኋላ አገሪቱ በምን ኃይል ለመገንባት እንደሚችሉ አለመረዳታቸው ነው። እነ ኮለኔል መንግስቱም ቀሪውን የተማረ ኃይልና ጂኔራሎችን ሲገድሉ ምን ታይቷቸው ነው? ለመሆኑ አንድን አገር ባልተማረ ኃይል መገንባት ይቻላል ወይ? እሲከዚህ ድረስ ምርር አድርጎ ርስ በርስ የሚያጫርስ ነገር ምንድነው ? በየትስ አገር ነው የታየው? የሚገርመውና የሚያሳዝነው ነገር ሁሉም ኃይሎች በማርክሲዝም ሌኒኒዝም እየማሉ ነበር ግድያውን ያጧጥፊት የነበረው። ያም ሆነ ይህ፣ ይህ የመረረ ሁነታ ያለፈ ቢመስልም፣ ዛሬም ቢሆን ከቂም በቀላቸው ያልተላቀቁ ኃይሎች እንዳሉ መገንዘብ ይቻላል። እነዚህ ኃይሎ አብዮቱ ተቀለበሰ ከተባለ በኋላ ተቀምጠው ጊዜ ውስደው ለምን ያህ ሁሉ ጭፍጨፋ እንደተካሄደና ታሪክ እንደወደመ ጥያቄ ለመጠየቅና ግልጽ ውይይት ለማድረግ ስላልቻሉ የጭንቅላት ተሃድሶ ሊያገኙ አልቻሉም። አንዳንዶቹ አሁንም ቢሆን በድሮው ዓለም ውስጥ በመዋኘት ለቀና ውይይትና ለግልጽነት በሩን ሁሉ ዘግተዋል። በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ የፈለገውን ያህል ለአገሬ ነው የምታገለው ቢባልም እያንዳንዱ ለሰራው ስራ ተጠያቂ መሆኑን እስካላመነ ድረስና፣ የመጥፎም ሆነ የጥሩ ድርጊቱ ተካፋይ መሆኑን እስካለተገነዘበ ድረሰና ራሱን ለመጠየቅ ዝግጁ እስካልሆነ ድረስ ይህ ዐይነቱ ግትርነት ሊዲሞክራሲና ለነፃነት የሚደረገውን ትግል ያጨናግፋል። አገርም ባላፈበት የትግል ዘዴ፣ -ትግል ካልነው፟- ሊገነባ አይችልም። ስለዚህም ዛሬ አዲስና ሌላ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ የወደቅን መሆናችንን በመገንዘብና ከድሮው ህልም በመላቀቅ አስተሳሰባችንን በመለወጥ ለአዲስ ህልምና ለአዲስ ዓላማ መነሳት ያለብን ይመስለኛል። አይ ያልተወራረደ ሂሳብ ስላለብን እሱን ካላጠናቀቅን ወደፊት ማምራት አንችልም የምንል ከሆነ ትርጉም ለሌለው ለራሳችን ጥቅም ወይም ዓላማ ነው የምንታገለው ማለት ነው። ይህ ደግሞ በጠቅላላው ኢትዮጵያ ላይ እንደመዝመት ይቆጠራል። ቀናውን መንገድ እንከተላለን የምንል ከሆነ ደግሞ ቂም በቀልን ብቻ ሳይሆን፣ ከገባንበት የድርጅት አምልኮ መላቀቅ አለብን። ራሳችንን ከድርጅት አምልኮ ስናላቅቅ ብቻ ነው ዕውነተኛ ነፃነትንና፣ ካንት የሚለውን ፍሪ ዊል ማዳባር የምንችለው። ይህን ካልኩኝ በኋላ ትንሽም ቢሆን ወደዛሬው አገዛዝ ልምጣ።

የወያኔ አገዛዝ ስለ ዲሞክራሲና ስለ ኢኮኖሚ ዕድገት ያለው የተበላሸ ግንዛቤ ዛሬ የተከሰተ ሳይሆን ወይም አዲስ ነገር ሳይሆን፣ የድርጅቱ ባህርይ ሆኖ ተቆራኝቶት የኖረ ነው። ራሱ በብሄረሰብ ደረጃ መደራጀትና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ የጥገና ለውጦች ላይ መዝመቱ የሚያረጋግጠው ወያኔ የቱን ያህል ፀረ-ዲሞክራቲክና ፀረ-ዕድገት ኃይል መሆኑን ነው። በሌላ ወገን ደግሞ ከእንደዚህ ዐይነቱ በብሄረሰብ ደረጀ ከተደራጀ ቡድን ዲሞክራሲያዊ መብቶችን መለመኑ ወይም መጠበቁ እጅግ የዋህነት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ድርጅቱ በምሁራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በማለፍ የዲሞክራሲን ምንነት በመረዳት ወደ ውጭ ወጥቶ ለህዝብ ያስተማረና ለጋራ ትግል እጁን የዘረጋ እልነበረም። ከሌሎች ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር በመተባበር ወታደራዊው አገዛዝን ሲዋጋ፣ የትግል አጋሮቹን የስልጣን መወጣጫና መጠቀሚያ ለማድረግ እንጂ በመሰረቱ እነሱን እንደ ትግል አጋሮቹ በማየት አብሮ በእኩልነት ለመግዛት አልነበረም። በመሆኑም እንደ ብሄረሰብ የመሳሰሉት ጥያቄዎች ለስልጣን መወጣጫ ያገለገሉና የኋላ ኋላ ደግሞ ለከፋፍለህ ግዛ እንዲያመች እሱ በሚፈልገው መልክ ተግባራዊ የሆኑ ናቸው። በመሆኑም የክልል አስተዳዳሪዎች ቢያንስ የራሳቸውን ውስን መብት በማግኘት አካባቢያቸውን ለማስተዳደር እንዳይችሉ ተደርገዋል። በሌላው ወገን ደግሞ ራሳቸው የክልል ተወካዮች በምሁር ደረጃ የዳበሩና በራሳቸው የሚተማመኑ ስላይደሉ አገዛዙ ጋር በእኩል ደረጃ በመደራደር መብታቸውን በማስከበር የክልላቸውን ሀብት በማንቀሳቀስ ለየብሄረሰባቸው የኑሮ መሻሻልን ሊያመጡ አልቻሉም። የክልል አስተዳዳሪዎች በሀብት ሲደልቡና በቪላ ቤት ሲኖሩ፣ አሁንም ህዝቡ መሰረታዊ ነገሮችን ማግኘት አቅቶት ሲሰቃይ ይታያል። የየመንደሮችንና የከተማዎችን ሁኔታ ለተመለከተ በብሄረሰብ ነፃነት ስም አገራችን የቱን ያህል የኋሊት ጉዞ እንደምታደርግ መረዳቱ ቀላል አይደለም። ስለዚህም ከዛሬው አገዛዝ ጋር ተወዳድረን እሱን በምርጫ አሸንፈን፣ ወይንም የውጭው ኃይል ጣልቃ በመግባት አስታርቆን የስልጣን ተጋሪ በመሆን ዲሞክራሲን እናመጣለን የሚለው አካሄድ አደገኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ፣ የድህነቱን ዘመን ለብዙ መቶ ዐመታት እንዲያራዝመው እንደማድረግ ይቆጠራል። የነፃነትንና የዲሞክራሲን፣ እንዲሁም የዕውነተኛው የስልጣኔ ፕሮጀክት ህልማችንን ከወያኔ አገዛዝ ባሻገር ተግባራዊ እንደሚሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል። ከዚህ ስንነሳ ብሄራዊ ዕርቅ ያስፈልጋል እየተባለ የሚናፈሰው የትግል መፈክር እጅግ አሳሳችና፣ ለዕውነተኛ ነፃነት የሚደረገውን ትግል የሚየዘናጋና ውስብስብ የሚያደርገው ነው። ጸቡ በወያኔና ተቃዋሚ ነኝ በሚለው ኃይል መሀከል ያለ ሳይሆን፣ ያለው ችግር ስልጣኔን፣ ዕድገትን፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትንና ዕውነተኛ ነፃነትን በሚጠላው አገዛዝና፣ ዕውነተኛ ነፃነትንና ስልጣኔን በሚመኘው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ መሀከል ነው። ትግሉ አገርን ከሚያፈርስ፣ ታሪክን ከሚያበላሽና ከውጭ ኃይሎች ጋር እጅና ጓንቲ በመሆን ህዝባችን በዘለዓለማዊ ጨለማ ውስጥ እንዲኖር ከሚያደርገው ኃይል ጋር የሚደረግ የነፃነት ትግል ነው። ስለሆነም፣ የብሄራዊ ዕርቅ ያስፈልጋል የሚሉ ኃይሎች የማይገባቸው ሎጂክና ሳይንስ አለ። ይኸውም የብሄራዊ ዕርቅ ከተባለ፣ አገዛዙ እስካሁን ድረስ ያካሄደውን የተበላሸና አገርን የመቸብቸብና፣ ለውጭ ኃይሎች የጦር ካምፕ በመስጠት ሌላ ህዝብ እንዲጨፈጨፍ የሚያደርገውንና፣ ጠቅላላውን የኒዎ-ሊበራል ፖሊሲ ፕሮጀክት በሙሉ አምኖ እንደሚቀበሉ የተገነዘቡ አይመስለኝም። ይህ ዐይነቱ አካሄድ የስልጣን ድርሻ ሲኖረን እኛም አብረን አናቦካለን፣ አገርራችንን ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ እናጠፋለን እንደማለት ሊተረጎም ይችላል። አይ ይህንን ለማለት አይደለም የምንፈልገው ከተባለ ደግሞ በሰፊውና ሎጂካዊ በሆነ መልክ ተብራርቶ መቅረብ አለበት። ይህ እስካልሆነ ድረስ የፖለቲካ መድረኩ በሚሆኑ በማይሆኑ መፈክሮችና አርዕስቶች በመያዝ ሰፊውን ህዝብ ግራ የሚያጋባ ይሆናል።

የወደፊቱ የዲሞክራሲ ፕሮጀክት ላይም ስንመጣ እንዲያው የዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው የተቀበለው የህግ የበላይነት ብቻ ነው ሊሰራ የሚችለው ብለን ነገሩን አደፋፍነን መሄድ አንችልም። በመጀመሪያ ደረጃ ይህ የዓለም ኮሙኒቲ የሚባለው ማን ነው? ብለን መጠየቅ አለበን። ሰባት ቢሊዮን ህዝብ፣ ይህንን እወክላለሁ የሚለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ወይም ሰለጠንኩኝ የሚለው የምዕራቡ ዓለም? ይህ ጉዳይ በግልጽ መቀመጥ አለበት። በየአገሮች እንደታየው፣ በተለይም ደግሞ እንደ አገራችን ባለ በብዙ ሽህ ችግሮች በተተበተበ አገር ተራ ዲሞክራሲና ምርጫ እንዲሁም መደብለ ፓርቲ የሚባሉት ፈሊጦች አንድ እርምጃ እንኳ ፈቀቅ ሊያደርጉን አይችሉም። እነዚህ አባባሎች ወይም መፈክሮች በመሰረቱ የኢሊት መፈክሮች ወይም ህልሞች በመሆናቸው ሰፊውን ህዝብ ሙሉ በሙሉ የስልጣን ባለቤት ሊያደርጉት አይችሉም። ማንነቱን እንዲረዳና ፈጣሪ እንዲሆን አያግዙትም። ስለዚህም ህዝባችንን የስልጣን ባለቤት ወደሚያደርገው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሸጋገር መቻል አለበን። ይህ ማለት ግን ፓርሊሜንተሪ ዲሞክራሲ አይስፈልግም ለማለት ሳይሆን፣ በዛሬው ወቅት ፓርቲዎች በርዕይና በፖሊሲ ደረጃ በደንብ ተደራጅተው በማይታገሉበት አገርና፣ ከፍተኛ ምህራዊ ክፍተት በሚታይበት አገር ውስጥ የመደብለ ፓርቲን ስርዓት ለመፍጠር እጅግ አስቸጋሪ ነው። በሌላ አነጋገር የአገራችንን የተወሳሰበ ችግር ለመፍታት በመጀመሪያ ደረጃ የተሰበጣጠረውን ኃይል ሊያሰባስብ የሚችል መድረክ በመፍጠር ለሚቀጥሉት ሃምሳ ዓመታት አገሪቱን በጸና መሰረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል ሁለ-ገብ ፕሮግራም መንደፍ አማራጭ የሌለው ሂደት ነው ብዬ እገምታለሁ። የተወሳሰበው ችግራችን በመደብለ ፓርቲና በምርጫ ሊፈታ የሚችል አይደለም። ወይም አንዱን ድርጅት ወይም ግለሰብ ውክልና በመስጠት ሊቀርፍ የሚችል አይደለም። የአገራችንን የተወሳሰበ ችግርና የመጭውን ትውልድ ዕድል ከራሳችን ጥቅምና ዝና ባሻገር ማየት ያለብን ይመስለኛል። ስለሆነም ሁለ-ገብና የሰፊውን ህዝብ የማሰብ ኃይሉን አዳብሮ ነፃነት እንዲሰማው የሚያደርገውን የዲሞክራሲ ስርዓት መዘርጋት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ይህ ዐይነቱ የተቀደሰ ዓላማ ወይም ህልም ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ከዛሬው አገዛዝ ባሻገር ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ የሬናሳንስ እንቅስቃሴ ወይም በሁሉም መልክ የሚገለጽ ምህራዊ እንቅስቃሴ መፈጠር አለበት። በተለይም ይህ ዐይነቱ እንቅስቃሴና ለዲሞክራሲና ለነፃነት የሚደረገው ትግል ለፖለቲካ ስልጣን እንታገላለን በሚሉ ኃይሎች የሚካሄድ ሳይሆን ከፖለቲካ ውጭ ያሉ በተለያዩ ሙያ በሰለጠኑ አማካይነት ብቻ ነው። በህብረተሰብ ታሪክ ግንባታም የተረጋገጠው ይህ ነው። ለፖለቲካ ስልጣን እንታገላለን የሚሉ ሰፊውን ህዝብ በቀን ተቀን የአገር ግንባታ ውስጥ ማሳተፍ የቻሉና የሚያስችሉ ስላይደለ ይህ ዐይነቱ የነሻነት ትግል መስመር ሊይዝ የሚችለው በተገለጸላቸው ምሁራን አማካይነት ብቻ ነው። የብዙዎች አገሮች ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎች የኒዎ-ሊበራል አጀንዳዎች ስለሆኑ አንድን ህዝብ የስልጣንና የስልጣኔ ባለቤት አያደርጉትም ። በረቀቀ መንገድ ነፃነትን የሚያሰገፍፉና፣ ሀብት እንዲበዘበዝ የሚያደርጉ ናቸው። ስለሆነም ከኤሊት ዲሞክራሲ ወደ ህዝብ አሳታፊ ዲሞክራሲ የምናመራበት ዘዴ ለውይይትና ለጥናት መቅረብ አለበት።

ምን ዐይነት የኢኮኖሚ ዕድገትና ለማን!

ስለ ኢኮኖሚ ዕድገት የተጻፉ ሊትሬቸሮች ሺህ በሺህ የሚቆጠሩ ናቸው። ቁጥራቸውም ከመብዛቱ የተነሳ ትክክለኛውን ሃሳብ ለመጨበጥ በጣም ያስቸግራል። በሌላ ወገን ግን ሰለ ኢኮኖሚ ዕድገት በሚወራበት ወይም በሚጻፍበት ጊዜ ከተወሰነ ርዕዮተ-ዓለም ክልልና የኃይል አሰላለፍ ውጭ ነጥሎ ማየት አይቻልም። ምክንያቱም በአውሮፓ ህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ በየጊዜው አዳዲስ ኃይሎች ብቅ ሲሉ አዲስ ከተፈጠረው የኃይል አሰላለፍ ጋር ለማቀናጀት ሲባልና፣ አንዳንድ ምሁራን የዚህኛውን ወይም የዚያኛውን መደብ ወይም የህብረተሰብ ክፍል ጥቅም እናስጠብቃለን ብለው ስለሚታገሉ፣ ኢኮኖሚክስም በርዕዮተ-ዓለም ትግል ክልል ውስጥ በመካተቱ የአንድን ህብረተሰብ የኢኮኖሚ ሁኔታ በዚህኛው ወይም በዚያኛው የቲዎሪ መነጽር ማየት አስገደደ። ስለሆነም፣ በተለይም ኢኮኖሚክስ ከሌሎች የትምህርት ዐይነቶች እየተነጠለ ሲወጣ የባሰውኑ በርዕዮተ-ዓለም መነፅር መታየት ጀመረ። ኢኮኖሚክስም ሆነ ሌሎች የሶሻል ሳይንስ ትምህርቶች እሴተ-አልባ(Value-free) መሆናችው ቀርቶ ተጣመው በመቀርብ ለዕውነተኛ ነፃነት የሚደረገው ትግል አስቸጋር እየሆነ ሊመጣ ቻለ።

በህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ የህብረተሰብ ግንባታንም ሆነ የኢኮኖሚ ዕድገትን ታሪክ ለተመለከተ ዕድገት የሚባለው ነገር ስልጣን ላይ ባለው ኃይልና ከሱ ጋር በጥቅም ከተቆላለፉ ኃይሎች ጋር የተያያዘ ነው። ለዚህም ነው ከጥንታዊቱ የግሪክ ስልጣኔ ጀምሮ ዕኩልነትና(Justice) ሚዛናዊነት ለአንድ ህብረተሰብ መረጋጋትና በሰላም መኖር አስፈላጊ ናቸው እየተባለ ትግል የተጀመረው። ምክንያቱም ስልጣን ላይ የሚወጡ ኃይሎች አብዛኛውን ጊዜ በፍልስፍናና በሳይንሳዊ ህግ ስለማይመሩ የተወሰነ የኢኮኖሚ ፖሊሲን በመከተልና የራሳቸውን ጥቅም ስለሚያስቀድሙ የግዴታ ለድህነት መፈልፈል በአንድ በኩል፣ በሌላ ወገን ደግሞ ጥቂቱ ሀብት በመቆጣጠር የጠቅላላውን ህዝብ የመኖርና ያለመኖር ዕድል እንዲወስን መንገዱን ያመቻቻሉ። የኢኮኖሚ ታሪክን መጽሀፎች ላገላበጠ በዚህ ዙሪያ የተደረገውን ዕልክ አስጨራሽ ትግል መመልከት ይቻላል።

ወደ ቲዎሪ ጥያቄ ስንመጣ ደግሞ፣ አንድ አገር ሀብት መፍጠር የምትችለው እንዴት ነው? በሚለው ዙሪያ የተለያዩ አስተሳሰቦች ይስፋፉ ነበር። በፊዚዮክራቶች፣ የመጀመሪያው የነፃ ገበያ ፍልስፍና አፍላቂዎች ወይም ላሴዝ-ፌር (Laissez faire) አሳቢዎች አመለካከት የአንድ አገር ሀብት ምንጭ እርሻ ነው የሚል ነው። ከገበሬው በስተቀር ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ምርታማ(Unproductive) ያልሆኑና፣ ከእርሻ የሚመጣው ትርፋማ ምርት(Surplus product) ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተከፋፍሎ የተቀረው እንደገና ለመዋዕለ-ነዋይ በመዋል በዚህ አማካይነት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ይመጣል ይሉናል። በመርከንታሊስቶች ዕምነት ደግሞ የአንድ አገር ሀብት ዋናው ምንጭ ከውጭ ንግድ የሚመጣ ወርቅና የወርቅ ክምችት ሲሆን፣ ተፈጥሮና ምድርንም ጨምሮ የሰው ጉልበት የሀብት(Wealth) ማመንጫ ዘዴዎች ናቸው ይሉናል። የሰው ጉልበት ወይም ኃይል ወይም ስራ ከተፈጥሮ ውስጥ ቆፍሮ የሚያወጣውን ንጥረ-ነገር በኃይል አማካይነት ወደ ፍጆታ ጠቀሜታ ከለወጠውና፣ የተወሰነው ደግሞ ለመዋዕለ-ነዋይ ከዋለ በዚህ አማካይነት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ይመጣል ይላሉ። በኋላ ብቅ ያሉት የመርከንታሊስት ኢኮኖሚስቶች ነገሩን በማስፋፋት፣ አንድ ህብረተሰብ በኢኮኖሚ ዕድገት አማካይነት እንዲተሳሰር ከተፈለገ የማኑፋክቱር አብዮት ማካሄድ እንደሚያስፈልግ ያረጋግጣሉ። ምክንያቱም ከእርሻ ይልቅ የማኑፋክቱር መስክ የሚስፋፋና የሚያድግ እንዲሁም የማባዛት ኃይል ስላለው ዕውነተኛ የስራ-ክፍፍልና የኢኮኖሚ ዕድገት በዚህ አማካይነት ብቻ ነው ሊፈጠር የሚችለው ብለው ይነግሩናል። በተግባርም የታየው ይህ ነው። የከተማዎች ግንባታ፣ የንግድና የዕደ-ጥበብ መስፋፋት፣ እንዲሁም የከበርቴው መደብ ማደግና ቀስ በቀስም ብሄራዊ ባህርይ እንዲወሰድ መደረጉ፣ አንድ አገር በመገናኛ መንገድ በመተሳሰር ሰፋ ያለ ገበያ መዳበር የቻለው በመርከንታሊስት የኢኮኖሚ ፍልስፍና ወይም ፖሊሲ አማካይነት ነው። ከዚህም ጊዜ ጀምሮ ነው የኢኮኖሚ ዕድገት መልክ እያየዘ መምጣት የቻለውና፣ ቀስ በቀስም ህብረተሰብአዊ ሀብት(National or Social Wealth) ሊፈጠር የቻለው።

ከቲዎሪ አልፈን ተግባራዊ የሆኑ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችስ ስንመለከት፣ ከአስራሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እየሆነ የመጣው የመርከንታሊስቶች የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው ለካፒታሊዝም ዕድገትና መስፋፋት መንገድ የቀደደው። በጊዜው ቢያንስ ማደግ ለሚፈልጉ ኃይሎች መንገዱ ክፍት ነበር። እንደ አገራችን ሁኔታ በጎሳ የተገደበና አፋኝ አልነበረም። እንዲያውም ንቁ የሚባሉ ኃይሎችን(Active forces) በተለያየ መንገድ መርዳትና፣ የውስጥን ገበያ ደግሞ ከውጭ በሚመጣ ዕቃ እንዳይጥለቀለቅ አስፈላጊ የጉምሩክ ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ የፖሊሲውና የሀብት ክምችቱ አንድ ዘዴ ነበር። ይህ ዐይነቱ በብዙዎቹ የምዕራብ አውሮፓ አገሮች ተግባራዊ የሆነ ፖሊሲ ነው ለካፒታሊዝም ዕድገት ዕምርታ በመስጠት ህበረተሰቡን ማስተሳሰር የተቻለውና ክልላዊና ሌሎች ገደቦችን በማስወገድ ብሄራዊ አንድነት እንዲፈጠር የተደረገው። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ ነው ግለሰቦችም የመፍጠር ጭሎታቸውን ማዳበር የቻሉትና፣ አገሮችም እንደ አገር ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ህብረተሰብና ነፃነት እንዳላቸው ግንዛቤ የተገባበት። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ ነው ብሄራዊ ነፃነት(National Sovereignty) የሚባለው እንደ መሰረተ-ሃሳብ በመወሰድ ማንኛውም አገር በሌላኛው አገር ጣልቃ መግባት እንደማይችል የተደረሰበትና፣ አገዛዞችም የራሳቸውን ነፃነት መጠበቅና መከላከል እንዳለባቸው ስምምነት የተደረሰበት። የብሄራዊ ኢኮኖሚ ቀስ በቀስ እያለ ከተገነባና ህብረተሰብአዊ መተሳሰርና የፈጠራ ስራዎች እየተጠናከሩና እየዳበሩ ሲመጡ የእነ አዳም ስሚዙ የነፃ ገበያና ንግድ ፖሊሲ መስፋፋት ጀመሩ። የራስን ጥቅም ማሳደድ የሚለው ሃሳብ በመስፋፋት፣ ይህ ዋናኛው የሰው ልጅ ውስጣዊ ባህርይ ወይም አብሮት የተፈጠረ ነው በማለት ኢምፔሪሲስታዊ አመለካከት ያላቸው ፈላስፋዎች ይህንን ውስን አመለካከት በማስፋፋት ዋናው የኢኮኖሚ ዕድገት አንቀሳቃሽ ኃይል አድርገው መስበክ ጀመሩ። ስለሆነም የነፃ ገበያና የነፃ ንግድ በሃሳብና በርዕዮተ-ዓለም ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈለቁትና መዳበር የጀመሩት በእንግሊዝ አገር ነው። በአዲሱ የዩሊታሪያን አስተሳሰብ መሰረት ህብረተሰብአዊ ሀብትን ለመፍጠር ወይም አንድን ምርት ለማምረት ሶስት ነገሮች መጣመር አለባቸው። ይኸውም፣ የሰው ኃይል፣ ካፒታልና መሬት ናቸው። በተጨማሪም የረቀቀው የሰው እጅ (Invisible Hand) ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ እንደሆነ አዳም ስሚዝ ያትታል። ይህ እንዳለ በመወሰድ የትምህርትቤት ኢኮኖሚክስ በዚህ መልክ ረቀቀ። ሁላችንም በዚህ መልክ ሰለጠን።

ወደ ማርክስ ቲዎሪ ስንመጣ ደግሞ፣ የመርከንታሊሲቶችን ሃሳብ በመቀበልና፣ የአዳሚ ስሚዝንም የቫልዩ ቲዎሪ በማስፋፋት፣ የስራ ኃይል ወይም የሰው ጉልበት ዋናው የዋጋና፣ ተከታታይ የካፒታሊዝም ዕድገት መሰረት እንደሆነ ያብራራል። ከዚህ ጋር በማያያዝ፣ የካፒታሊዝምን አፀናነስና ዕድገት፣ ደረጃ በደረጃ ካተተ በኋላ ውድድር(Competition) የካፒታሊዝም ዋናው የዕድገት አንቀሳቃሽ ኃይል መሆኑን ያመለክታል። በዚህም አማካይነት የምርት ኃይሎች ወይም የማምረቻ መሳሪያዎች በየጊዜው እየተሻሻሉ በመምጣት ለካፒታሊዝም ዕድገት ምጥቀትና መስፋፋት ይሰጡታል። የደሞዝ ዕድገትና፣ የኑሮ መሻሻል፣ እንዲሁም የፍጆታ ማምረቻ ዋጋ መቀነስ ከማምረት ወይም ከማሺኖች ምርታማነት ጋር የተያያዙ እንደሆኑ መገንዘቡ ከባድ አይሆንም ። በተጨማሪም ፋይናንስ ካፒታል ወይም ብድር ለካፒታሊዝም ዕድገት አንቀሳቃሽ ኃይል በመሆን፣ ካፒታሊዝም ከዝቅተኛ የምርት ክንዋኔ ወደ ከፍተኛና ወደ ተወሳሰበ ደረጃ መድረስ እንደቻለ እንመለከታለን። የፊናንስ ካፒታል በምርት ክንዋኔና በአዳዲስ መዋዕለ-ነዋይ ላይ ብቻ ሳይወሰን፣ ተጠቃሚውንም በማካተት የካፒታሊዝምን ዕድገት ማፋጠን እንደቻለ ግልጽ ነው።

ለመሆኑ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ካለሳይንስና ካለቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ወይ? አብዛኛውን ጊዜ ስለሶስተኛው ዓለም የኢኮኖሚ ዕድገት ችግር የሚጽፉ ኤክስፐርቶች የሚዘነጉት ነገር ሳይንስና ቲኮኖሎጂ በኢኮኖሚ ዕድገት ውስ|ጥ ያላቸውን ሚና ከቁጥር ውስጥ ባለማስገባት ነው። በተለይም የኒዎ-ክላሲካል ኢኮኖሚስቶች ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ ቦታ አይሰጡትም። ለማንኛውም ብዙ ሳናወጣና ሳናወርድ፣ ወይም በትንሹ ስናሰብ የሰው ልጅ ዕድገት ከቲክኖሎጂ ጋር የተያያዘ ነው። የተሻሉ የምርት መሳሪያዎች መጠቀም ሲጀምር የበለጠና በብዛት ማምረት ይችላል። ስራውንም ያቃልላል። በዚህም ምክንያት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መሆን ከጀመሩ ከ18ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የምርት መሳሪያዎች መብዛት ብቻ ሳይሆን በጥራትም እየመጠቁም መምጣት ችለዋል። በዚያውም መጠንም የዛሬ ሁለት መቶ ዐመት መመረት የማይችሉ ምርቶች፣ የተለያዩ የሰብልና የፍራፍሬና እንዲሁም የቅጠላ ቅጠል ዐይነቶች ተስፋፋተው ይገኛሉ። ይህም የሚያረጋግጠው በቴክኖሎጂዎች መስፋፋት የሰው ልጅም የማሰብና የማምረት ኃይል ሊያድግ እንደቻለ ነው። ከዚህ ስንነሳ ኋላ-ቀርነትና የረሃብን ምክንያት መገንዘቡ ቀላይ አይደለም። 1ኛ) ዕውነትኛ ዕውቀተ ባልተስፋፋበት አገር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሊፈጠሩና ህብረተሰብአዊ ባህርይ ሊወስዱ አይችሉም። 2ኛ) ሰፊው ህዝብ ካልተማረ ራሱ ምርትን በተለያየ ዐይነት ማምረት ብቻ ሳይሆን አንድንም ምርት በብዛት ማምረት ያቅተዋል። ኢምፔሪካል ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት የሰው ልጅ ዕድገት በቁጥር መቀነስና ረሃብና ድህነት መወገድ፣ ከሰፊው ህዝብ የመማርና የማሰብ ኃይል ጋር የተያያዙ እንደሆነ ነው። ስለሆነም ሰፋ ያለና ዕውነተኛ ዕውቀት ዋናው የስልጣኔ ቁልፎች ናቸው። በሁሉም መልክ የሚገለጽ ዕውቀትና በአንድ ክልል ብቻ ያልተገደበ ዕውቀት ነው አንድን ህዝብ ሀብት ፈጣሪ የሚያደርገውና ከድህነትና ከረሃብም ሊያላቅቀው የሚችለው።

ወደ ሌሎች ቲዎሪዎች ስንመጣ፣ የአንድ አገር ሀብት(Wealth) የሚወሰነው ወይም የሚመነጨው በሶስት ነገሮች አማካይነት ነው። 1ኛ) ኃይል(Energy)፣ 2ኛ) ቴክኖሎጂና 3ኛ) ፈጠራ፣ እነዚህ አንድ ላይ ሲጋጠሙ ወይም ሲጣመሩ አንድ አገር ተከታታይነት ያለው ሀብት መፍጠር ይችላል። በተለይም የዚህ ቲዎሪ አራማጅ የስኮቲሹ ተወላጅና በኬሚስትሪ የኖቭል ዋጋ ተሸላሚ የነበሩት ፕሮፌሰር ፍሪድሪሽ ሶዲ ናቸው። ፕሮፌሰር ሶዲ ስለ ኃይል በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ያለውን ሚና በማስመር፣ ኃይልን መቆጠብና ኃይልን በመለወጥ መሀከል ያለውን ዲያሌክታዊ ግኑኝነት በማያያዝ፣ የአንድ አገር ዕድገት ሊወሰን የሚችለው በኃይል አማካይነት ብቻ እንደሆነ በግሩም መልክ ያብራራሉ። በመሆኑም ፀሀይ የኦርጋኒክና ኦርጋኒክ ያልሆኑ ነገሮች አንቀሳቃሽ ኃይልና ለዋጭ በመሆን የሰውን ልጅ ዕድገትና የተፈጥሮን ምንነት ወሳኝ ነች። በፀሀይ ኃይል ወይም ሙቀት አማካይነት ነው ፍሬ ሊሰጡ የሚችሉና ፍሬ ሊያበቅሉ የማይችሉ ዛፎች ሊያድጉና ሊያብቡ፣ እንዲሁም ፍሬ ሊሰጡ የሚችሉት። በምድር ውስጥ የተከማቹት እንደዲንጋይ ከሰልና ዘይት የመሳሰሉት የጥሬ ሀብቶችና ሊሎችም ንጥረ-ነገሮች የብዙ መቶ ዐመታት የፀሀይ ክምችት ውጤቶች ናቸው። ከዚህ በመነሳት የአንድ አገር ዋናው እንቅፋት ይህንን የተፈጠሮ ህግ አለመረዳት ሲሆን፣ የጭንቅላት ወይም የአዕምሮ ድህነት ያለባቸው አገሮች ፍዳቸውን የሚያዩት የተሳሳሰተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመከተላቸው እንደሆነ ያስተምሩናል። ምክንያቱም በተፈጥሮ ውስጥ ያሉትን ፀሀይንም ሆነ ውሃ፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ ንጥረ-ነገሮችን መጠቀም ያለመቻል አንድን አገር ወደ ዘለዓለማዊ ድህነት እንደሚያመራው ነው። ፕሮፊሰር እሪክ ራይነትም በሌላ መልክ ለአንድ አገር ዕድገት ጥሬ-ሀብት ተትረፍርፎ መገኘቱ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ የማሰብ ኃይልና፣ ለስራ ወይም ለስልጣኔ ያለው ፍላጎት ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወቱ ነው የሚያስተምሩን።

ከላይ አጠር ብሎ ከተዘረዘረው አስተሳሰብ ስንነሳ በመጀመሪያ ደረጃ ስለ ኢኮኖሚ ዕድገት በምናወራበት ጊዜ ግልጽ ማድረግ ያለብን ነገሮች አሉ ማለት ነው። በደፈናው የኢኮኖሚ ዕድገት ብሎ ነገር የለም። ከዚህ ጋር መያያዝ ያለበት ጉዳይ፣ ኢኮኖሚ ዕድገት ለምንና ለማን? ብለን መጠየቅ አለብን። ኢኮኖሚ ዕድገት ለዕድገት ሲባል፣ ወይስ ኢኮኖሚ ዕድገት የሰውን የማቴሪያል ፍላጎት አሟልቶ በአስተሳሰብም ደረጃ እንዲያጎለምሰውና ፈጣሪም እንዲያደርገው? ይህንን በሚመለከት የትምህርትቤት ኢኮኖሚክስ የሚለው ወይም የሚሰጠን መልስ የለም። እንዲያው በደፈናው ሁሉም ነገር በገበያ አማካይነት ብቻ ሊወሰን እንደሚችል ለማረጋገጥ ይሞክራል። ለምሳሌ በትምህርት ቤት ኢኮኖሚክስ ማንኛውም ህብረተሰብ በመጀመሪያ ደረጃ፣ ምግብ፣ ንፁህ ውሃና መጠለያ ማሟላት እንዳለበትና፣ ከዚያ በመነሳት አንድን አገር መገንባት እንዳለበት አያሰተምርም። በሁለተኛ ደረጃ፣ በትምህርት ቤት ኢኮኖሚክስ፣ ከተማ ምን እንደሆን አይታወቀም። የሚታወቀው ገበያ ብቻ ነው። ማለትም ገበያ ካለ ቦታና ሰዓት(Space and Time) የሚካሄድ ነው። በሶስተኛ ደረጃ፣ የትምህርት ቤት ኢኮኖሚክስ ህብረተሰብ ማለት ምን ማለት ነው? እንዴትስ ነው የሚተሳሰረው? እንዴትስ ነው የስራ-ክፍፍል የሚቀናጀውና የሚዳብረው? የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ አያቀርብም፤ አይመልስም። ከዚህ ስንነሳ የኢኮኖሚ ዕድገት በራሱ ብቻ እንደሚጓዝ አድርገን መመልከት ከፍተኛ ስህተት ነው። ፕላቶን እንደሚያስተምረን፣ አንዱ የወረውረውን ማስተጋባት ሳይሆን፣ መመርምርና መፈተን ያስፈልጋል። ከዚያ በመነሳት የራስን ውሳኔ መስጠት ሳይንሳዊው መንገድ ነው።

እስቲ ከቲዎሪ ተላቀን ወደ ተግባራዊ ነው ወደምንለው ነገር እንመጣ። ባለፉት 25 ዐመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገ የመጣ ነው ወይ? ይህንን ጥያቄ መመለስ የምንችለው፣ ከየትኛው ሁኔታ በመነሳት ነው? የምንገመግመው ወይም የምንለካው? የሚለውን ጥያቄ ካስቀመጥንና ለመመለስ የቻልን እንደሆን ብቻ ነው። ሌሎች እጅግ አብስትራክት የሆኑ የጂዲፕ አሰላልና የምርት ጭማሮና ከውጭ የመጣን ልዩ ልዩ ወደ ምርት ውስጥ የሚገቡ በግማሽ የተፈበረኩና የጥሬ-ሀብት ጉዳዮችን ትተን እንዲያው በደፈናው ስንመለከት ከተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል አንጻር፣ ምናልባት 1% ለሚጠጋው የህብረተሰብ ክፍል „የኢኮኖሚ ዕድገት“ መጥቶለታል ማለት ይቻላል። ይህ ዕድገት በትላልቅ ህንጻዎች፣ በሆቴል ቤቶች ስራና ጋጋታ፣ በመንገድ ስራ፣ የስኳርና የቢራ ፋብሪካ የሚገለጽ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ከመንግስት ጋር በሺህ ድሮች የተቆላለፉ አየር በአየር ንግድ ውስጥ በመሰማራት፣ የውስጥን ጥሬ-ሀብት በመሸጥ የገቢያቸው መጠን በፍጥነት የተተኮሰ የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ የነዚህ ህብረተሰብ ክፍሎች የፍጆታ አጠቃቀም በከፍተኛ ደረጃ አድጓል። ከውጭ የሚመጣው የቅንጦት ዕቃ የማህበራዊ ስታተሳቸውን ከፍ አድርጎለታል። ይህንና ከዚህ ጋር የተቆላለፈውን ሀብት ጨራሽ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ነው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተብሎ የሚወደስልን። ይህንን ዐይነቱን የኢኮኖሚ ዕድገት በመርከንታሊስቶችም ሆነ በፕሮፌሰር ፍሪድርሽ ሶዲና ፕሮፌሰር ኢሪክ ራይነርት የኢኮኖሚ ቲዎሪ መነፅር ስንመረመረው አዲስ ሀብት የፈጠረ አይደለም። ቲክኖሎጂያዊ ምጥቀትን ያመጣ አይደለም። የውስጥ ገበያ እንዲስፋፋና እንዲዳብር ያደረገና የሚያደርግ አይደለም። ለስራ ፈላጊው ሰፊ ህዝብ የስራ መስክ የከፈተና የሚከፍት አይደለም። የባሰ ጥገኝነትንና፣ ኢኮኖሚያዊ መዝረክረክን ያስከተለና የሚያስከትል ነው። ሀብትን የሚያባክን ነው። በተፈጥሮና በሰው ልጅ ላይ ዘመቻ የከፈተ „የኢኮኖሚ ዕድገት“ ነው። ይህንን ዐይነቱን ዕድገት ጥፋት እንለዋለን። የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል በማባለግ፣ ሰፊውን ህዝብ በማድኸየት አቅመ-ቢስ ያደረገ ነው። እንደሚታወቀው አንድ አገር እንደ አገር የምትከበረው ከሁሉም አንፃር ማደግ ስትችል ነው። ግርማ ሞገስ ያላቸው ከተማዎችና የመኖሪያ ቤቶች ሲሰሩና ለሰፊው ህዝብ ሲዳረሱ ነው። ህዝቡ የመፍጠር ችሎታው ሲዳብር ነው። እንደ አንድ ዜጋ ሲታይና ጠንካራ ህብረተሰብ ለመመስረት ሲችል በእርግጥም ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አለ ማለት ይቻላል። ልዩ ልዩ መናፈሻ ቦታዎችና ሲዘጋጁለትና የኬነትና ቤተ-መጻህፍቶች ሲቋቋሙለት ኢኮኖሚው ማደጉ ብቻ ሳይሆን፣ ህዝቡም አዲስ አስተሳሰብ ማዳበር ይችላል። የሰው ልጅ በዳቦ ብቻ አይኖርም፤ ፍቅርና ልዩ ልዩ መንፈሱን የሚያረኩ ነገሮችም ያስፈልጉታል። ከማያስፈልጉ ነገሮች እንዲቆጠብና ውድ ወንድሙን እንደሰው እንዲያይ ከተፈለገ በሳይንስ የተጠና ባህልም መዳበር ከኢኮኖሚው ዕድገት ጋር መያያዝ ያለበት ጉዳይ ነው። የዛሬው በወያኔ አገዛዝና እንዲሁም በኒዎ-ሊበራል ኤክስፐርቶችና አማካሪዎቹ ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመሰረቱ ማጅራት መቺዎችንና ማፊያ መሳዮችን የፈለፈለና ድህነትን ያስፋፋ ነው። በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚታተመው በሪፖርተር ላይ የወጣውን ዘገባ መመልከቱ ሁኔታው የቱን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ለመረዳት ያስችለናል።

ከዚህ በመነሳት እኛ ኢትዮጵያውያን ምሁር ሆን አልሆን ለምን ዐይነት ሀብረተሰብና ለምን ዐይነት አኮኖሚ ነው? የምንታገለው ብለን መከራከር አለብን። እኛን የሚያሳሰብን የዚህኛው ወይም የዚያኛው ብሄረ-ሰብ ነፃ መውጣትና አለመውጣት አይደለም። እኛን የሚያሳስበን ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው የአርሞው፣ የአማራው፣ የትግሬው፣ የወላይታው፣ የጉራጌው… ወዘተ የኑሮ ሁኔታ ነው። እኛን የሚያሳስበንና አንጀታችንን የሚያቃጥለን ሺህ በሺህ ለአረብ አገሮች በመንግስት የሚሸጡት ልጆቻችንና እህቶቻችን ህይወት ነው። የሚያሳስብን በመንገድ ላይ የሚያድረው፣ ከቆሻሻ እየለቀመ የሚበላው፣ የዕፅ ሱሰኛ እንዲሆን የተገደደው ልጃችን ህይወት ነው። እኛን የሚያስጨንቀን የህዝባችን ኑሮ መጨለሙ ነው። እኛን የሚያሳስበን የአገራችን ውድመትና መቸብቸብ ነው። ህዝቡ እንደ አንድ ዜጋ እንዳይተሳሰር መደረጉ ነው። እኛን የሚያሳስበን ህዝባችን ዕውነተኛ ነፃነቱን እንዳይጎናፀፍና ዕድሉን ወሳኝ እንዳይሆን መደረጉ ነው። በዚህ ዐይነቱ ውጥቅንጡ የወጣ ስርዓት ግለሰብአዊ መብቶች መጣሳቸው ነው የሚያስጨንቀን። ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ መሪ የሌለው መደረጉ ነው ሌት ከቀን እንቅልፍ የነሳን። የሚያሳስበን ያረጀ የብሄረ-ሰብ ጥያቄ ሳይሆን የዘጠና ሚሊዮኑ ህዝብ ዕድል ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ከ50ና ከ100 ዐመት በኋላ ኢትዮጵያችን ምን ትመስላለች የሚለው? ነው የሚያሳስበን። የዚኸኛው ወይም የዚያኛው ፓርቲ ለስልጣን መውጣትና መራወጥ አይደለም አንጀታችንን የሚያቃጥለን። ባጭሩ የአገርና የህዝብ ደህንነት፣ ከሁሉም አቅጣጫ ዕድገት አለመኖር፣ ዕድገት እንዳይኖር ከውጭ የተሸረበብን ሴራና በጣም የደከመው ምሁራዊ እንቅስቃሴ ነው እንቅልፍና ዕረፍት የነሳን።

የዛሬው ሁኔታ በዚህ መልክ አፍጦ አግጦ ባለበት ወቅት አንዳንድ ምሁራን ስለተከታታይነት(Sustainable Economic Growth) ስላለው የኢኮኖሚ ዕድገት ይጽፋሉ። በየጊዜው ይህንን በማስመር የሚጽፉት ምሁራን፣ 1ኛ) ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ምን እንደሆነ ለተራው ሰው ሲያስረዱ አይታዩም። 2ኛ) ባለፉት 25 ዐመታት በአገራችን ምድር ተግባራዊ የሆነውን የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ትችታዊ በሆነ መልክ በመመርመርና በመጻፍ አላስተማሩንም። 3ኛ) ዛሬ አገራችን ምድር አፍጦ አግጦ ለሚታየው ድህነትና ረሃብ ዋናው ምክንያት ምን እንደሆነ አልነገሩንም። እንዲያው በደፈናው ብቻ ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ያስፈልጋል እያሉ ነው የሚነግሩን። ይህንን ካላብራሩልን ደግሞ የውር ድንብራችን ነው የምንራመደው ማለት ነው። በሌላ ወገን ደግሞ ከዚህ ዐይነቱ አባባል የምንረዳው ኢኮኖሚው አድጓል፣ ይሁንና ግን ተከታታይነት የለውም የሚል ድምደማ ነው። በመሰረቱ የተለያየ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊኖር አይችልም። በተለያዩ አገሮች የተለያዩ የህብረተሰብ አወቃቀሮችና አገዛዞች ቢኖሩም፣ የኢኮኖሚ ዕድገት ዋናው አንቀሳቃሽ ሃይል ፈጠራ፣ ከዚህ የሚፈልቁት ሳይንስና ቴክኖሎጂዎች ናቸው። ከዚህም ባሻገር ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ጉዳይ የቁጥር ብቻ ሳይሆን የዐይነትም ጭምር ነው። እነዚህ ጉዳዮች ደግሞ የግዴታ ከሰው ልጅ የኑሮ መሻሻል ጋር በቀጥታ የተያያዙ ናቸው። ስለተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገት በምናወራበት ጊዜ፣ ስለሪሶርስ አጠቃቀም ጉዳይ፣ ስለ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መፈጠር ጉዳይ፣ ስለ አካባቢ ደህንነት ጉዳይ፣ ስለ ከተማዎችና መንደሮች በደንብ በፕላን መታቀድና መገንባት ጉዳይ፣ ስለ ፍሳሽና ስለቆሻሻ መጣያ ወይም ሪሳይክል ማድረጊያ ጉዳዮች… ወዘተ. ማተት ያስፈልጋል። በተለይም የተፈጥሮን ሀብትና ጫካንም በስነስርዓት መንከባከቡና መጠበቁ የተከታታይ ዕድገት ዋናው ዕምብርት ነው። ንጹህ አየር መተንፈስና ጤንነታችንም ሊጠበቅ የሚችለው የአካባቢያችን ሁኔታ ከሳይንስ አንፃር እየተጠና እንክብካቤ ሲደረግለት ብቻ ነው። በተጨማሪም የወንዞችንና የባህሮችን ህይወት መንከባከቡ እጅግ አስፈላጊ ነው። እንደሚባለው አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ወንዞች የተመረዙና እየደረቁ የሄዱና ህይወትም የሌላቸው ናቸው። ለዚህ ሁሉ በብዙ የስልጣኔ ተመራማሪዎችና የኳንተም ሳይንስ ምሁራን የተደረሰበት ድምዳሜ ለተከታታይ ዕድገት ዋናው ወሳኝ ኃይል ንቃተ-ህሊና( Quantum Consciousness) ነው። በሌላ አነጋገር ዝቅተኛ ንቃተ-ህሊና በሰፈነበት አገር ስለ ተራ ዕድገትም ሆነ ስለ ተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገት ማውራት አይቻልም።

ስለሆነም ተከታታይነት ስላለው የኢኮኖሚ ዕድገት በምናውራበት ጊዜ፣ 1ኛ) የመንግስትን መኪናና የሚከተለውን ፖለቲካና የኢኮኖሚ ፖሊሲ መመርመር ያስፈልጋል። ይህ እንቅፋት ሆኖ ከታየ ደግሞ የግዴታ ይህንን መለወጥ ያስፈልጋል። አንድ አገዛዝ እንደፈለገው በራሱ „ሎጂክ“ እየተመራ የአገርን ሀብት ሊመዘብርና ህዝብን ሊያደኸይ አይችልም። መብትም የለውም። 2ኛ) ተከታታይነት ስለሚኖረው የኢኮኖሚ ዕድገት ሲነሳ ወይም ሲጻፍ የግዴታ ስለነፃነትና ስለዲሞክራሲ አስፈላጊነት ማንሳትና መጻፍ ያስፈልጋል። 3ኛ) ተከታታይነት የሚኖረው የኢኮኖሚ ዕድገት የወጭ ኃይሎችን ግፊታዊ ጣልቃ-ገብነት ይቃወመል። በሌላ አነጋገር በዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው ግፊት ተግባራዊ የሚሆን ፖሊሲ አንድን አገር የግዴታ መቀመቅ ውስጥ እንደሚከታት ማስተማር ያስፈልጋል። ይህም ማለት በአገራችን ምድር ተከታታይነት የሚኖረው የኢኮኖሚ ዕድገት ተግባራዊ ሊሆን የሚችለውና ህዝባችንም የዕውነተኛ ስልጣኔ ባለቤት የሚሆነው ከዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው መዳፍ ስር ሲላቀቅና በከፍተኛ ምሁራዊ ኃይል በግሎባል ካፒታሊዝም አማካይነት በሁሉም አቅጣጫ የሚመጣብንን ግፊት መቋቋም የቻልን እንደሆን ብቻ ነው። መልካም ንባብ !!

ፈቃዱ በቀለ
fekadubekele@gmx.de

‹ሀገር ማለት ሰው ነው›፤ እስኪ ሙት በለኝ! (ዲ/ን ዳንኤል ክብረት )

‹ሀገር ማለት ሰው ነው›፤ እስኪ ሙት በለኝ!

 Addis Admass : ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገርሙኝ ዘፈኖች አንዱ ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው ነው፡፡ እሥራኤላዊና ጂፕሲ ይህንን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? እላለሁ፡፡ አይሁድ በመላው ዓለም ለ1900 ዓመታት ያህል ተበትነው ሲኖሩ በየአካባቢው ሰው ነበራቸው፤ ያውም እንደ ብረት የጠነከረ ማህረሰብ፤ ሀገር ግን አልነበራቸውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ አይሁድ ሀገር ፍለጋ ከሺ ዓመታት በላይ መኳተን አልነበረባቸውም፡፡ በአውሮፓ የሚኖሩት ጂፕሲዎች የታወቀ ማኅበረሰብ አላቸው፡፡ ነገር ግን ሀገር የላቸውም። ሀገር ማለት ሰው ቢሆን ኖሮ ጂፕሲ የሚባል ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ጂፕሲ የሚባል ሀገርም ይኖር ነበር፡፡ ግን የለም፡፡
በአሜሪካ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ‹በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን› የምትባል ሀገር ግን የለቺም፡፡ 1.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ግሪኮች በአሜሪካ ይኖራሉ፡፡ ‹የአሜሪካ ግሪኮች› የምትባል ሀገር ግን የለችም፡፡ ‹ግሪክ፤ ሲሠራ አሜሪካ ይኖራል፣ ሲያረጅ ግሪክን ይጦራል› የተባለው ሀገር ሰው ብቻ ስላልሆነ ነው።
ሰዎች ተሰብስበው ሀገር ሊመሠርቱ አይችሉም፡፡ በየሀገሩ የተሰበሰቡ ማኅበረሰቦች ‹ኮሙኒቲ› ይባላሉ እንጂ ሀገር አይባሉም፡፡ ሀገር  ሀገር ለመሆንና ለመባል ከሰው በተጨማሪ የምትፈልገው ብዙ ነገር አላትና፡፡ ሀገርን ሀገር ለማስባል መሬትም ያስፈልጋል፤ መሬት ሳይኖርህ ሰው ስለሰበሰብክ ብቻ ሀገር ልትሆን አትችልም፡፡ ያውም የእኔ የምትለው፣ የምትሞትለትና የምትለፋለት ታሪካዊ መሬት ያስፈልግሃል፡፡ አይሁድን በ1930 አካባቢ በኡጋንዳ ኡዋሲን ጊሹ (UasinGishu County) በተባለ ቦታ እንዲሠፍሩና ሀገር እንዲኖራቸው ታስቦ ነበር፡፡ እንደ ቴዎዶር ኸርዝል ያሉ ታላላቅ የጽዮናዊነት መሪዎችም ለጊዜውም ቢሆን  ተስማምተውበት ነበር፡፡ብዙኀኑ አይሁድ ግን ‹ሀገር ማለት የሆነ መሬት አይደለም፡፡ ታሪካዊ መሬት ነው› ብለው ተቃወሙት፡፡ ሀገር ማለት የሆነ መሬት ብቻ ቢሆን ለአይሁድ ከዛሬዋ እሥራኤል ይልቅ በአየር ንብረትና በተፈጥሮ ማዕድን፣ ብሎም በአቀማመጥ ኡጋንዳ ትሻላቸው ነበር፡፡፡፡
ባድሜ ለምትባል ከጦርነቱ በፊት ብዙው ሕዝብ ሰምቷት ለማያውቅ መሬት የተደረገውን ጦርነት የረሳ ሰው ነው ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚል፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለባድሜ የተደረገው ጦርነት ለማን የተደረገ ነው ሊባል ነው፡፡ በሄግ ፍርድ ቤት የነበረው ክርክርስ የመሬት ክርክር እንጂ የሰው ክርክር ነበር እንዴ?
ሰውስ ስለ ሀገሩ ሲያነሣ ወንዙን፣ ተራራውን፣ ሸለቆውን፣ ሜዳውን፣ ጫካውን እያነሣ ለምን ይዘፍን ነበር ሀገር ማለት ሰው ቢሆን ኖሮ፡፡
‹ያገሬ ተራራ ወንዛ ወንዙ ለምለም
እማማ ኢትዮጵያ ኑሪ ለዘላለም› ለምን ይል ነበረ፡፡
ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ይሄ የኔ ክልል፣ ጎጥና መንደር ነው የሚለው ክርክር ከየት ይመጣ ነበር? ሀገር ማለት ሰው ከሆነ የተለየና የታወቀ የሀገር ድንበርና ካርታ ለምን ያስፈልግ ነበረ? ሰውማ የትም ነው የሚኖረው፡፡ ካርታ አያሻውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለምን የአብዛኞቹ ሀገሮች ብሔራዊ መዝሙር ስለ መሬቱና ስለ ድንበሩ ያወራል? ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለሰው ፓስፖርትና ቪዛ ለምን ያስፈልገዋል? ሰው ያለበት ቦታ ሁሉ ሀገሬ ስለሆነ ለምን እንደፈለግኩ አልገባም፡፡ አንድ ሰው ወደ አንድ ሀገር ገባ የሚባለው ወደ መሬቱ ሲገባ እንጂ የሀገሩን ሰው ሲያገኝ ነው እንዴ? ምናልባትም ከአንታርክቲካ በቀር ቪዛ መጠየቅ ያለበት ሀገር አልነበረም፡፡ እርሱ ሰው የለበትምና ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው አይመለከተውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ በሰማይ የሚሄድ አውሮፕላን ‹የአየር ክልሌን ጣሰ› ብሎ መሟገት ምን የሚሉት ሞኝነት ነው? ሰውን አልጣሰ፣ የጣሰው አየር ነው፡፡
ደግሞም አገር ማለት መሬት ብቻ አይደለም፡፡ ያማ ቢሆን ኖሮ አንታርክቲካ ሀገር ይሆን ነበር፡፡ ያማ ቢሆን ኖሮ በዓለም ላይ የሚገኙ ወደ ሃምሳ የሚጠጉ ሰው አልባ ደሴቶች(nonecumene) ‹ሀገር› ተብለው በተባበሩት መንግሥታት ይመዘገቡ ነበር፡፡ ሀገር ማለት መሬት ቢሆን ኖሮ መሬት ያለው ሁሉ ሀገር ይኖረው ነበር፡፡ የአሜሪካ ሕንዶች፣ የአውስትራልያ አቦርጅኖች፣ ከጥንት ጀምሮ የሚኖሩበት መሬት አላቸው፡፡ የራሳቸው የሆነ ሀገር ግን የላቸውም፡፡ ደቡብ ሱዳናውያን የራሳቸው የሆነ የሚኖሩበት መሬት ነበራቸው፤ ሀገር ለመሆን ግን መዋጋት ነበረባቸው፡፡ ደቡብ ሱዳኖችን ያን ሁሉ ዘመን ያዋጋቸው የመሬት ጥያቄ ሳይሆን የሀገርነት ጥያቄ ነው። ያውም የራሳቸው ፖለቲካዊ መሬት አግኝተው እንኳን ሀገር ለመሆን ገና እየተሠሩ ነው፡፡ ፍልስጤማውያን ይብዛም ይነስ የሚኖሩበት መሬት አላቸው፡፡ አገር ግን የላቸውም፡፡
አገር ከዚህ ሁሉ በላይ ነው፡፡ ሰው፣ ሰው የኖረበትና ታሪክ የሠራበት መሬት፣ ማኅበረሰብ ከማኅበረሰብ፣ ሰው ከሰው፣ ሰው ከማኅበረሰብ፣ ሰው ከመሬት፣ ሰው ከአራዊት፣ ሰው ከተፈጥሮ፣ ሰው ከወራሪ ጋር የነበረው ትግል፣ ውጊያና ወዳጅነት፤ የተረተው ተረት፣ ያወጋው ወግ፣ የፈጠረው አፈ ታሪክ፣ ያከማቸው ትዝታ፣ ሰው ለመሬቱ፣ ለወገኑና ለእምነቱ የከፈለው መሥዋዕትነት፤ የዘፈነው ዘፈን፣ ያቅራራው ቀረርቶ፣ የፎከረው ፉከራ፤ ያገኘው ድልና የተሸከመው ሽንፈት፤ ያደረሰው በደልና የደረሰበት በደል ይሄ ሁሉ ነው ሀገር፡፡
መገለጫው ቅርስ፣ መዋሐጃው ባህል፣ መታያው ልብስና መዋቢያው ጌጣጌጥ፣ መገናኛው ቋንቋ፣ መዝናኛው ጭፈራ፤ ማስተማሪያው ተረት፣ መክበሪያው ዓመት ባል፣ መጠበቢያው ምግብ፣ መቆዘሚያው እንጉርጉሮ፣ መተከዣው ልቅሶ፣ መተኪያው ልደት፣ ማሳረጊያው ቀብር፤ መገምገሚያው ምግባር፣ ማነወሪያው ነውር፤ መኩሪያ ጀግንነቱ፣ ማፈሪያ ገመናው፤ መደበቂያ ቤቱ፣ መመረሪያ ጫካው፤ ይሄ ሁሉ ነው ሀገር፡፡ ታሽቶ ተገርኝቶ ያመጣው አንድነት፣ ተጣልቶ ተባልቶ ያመጣው ልዩነት፣ እንደ ዘሐ ዘጊ የተጠላለፈው፣ እንደ እግር ሠንሠለት የተቆላለፈው፣ ሲፈተል፣ ሲገመድ፤ ሲባዘት፣ ሲዳወር፤ ሲከካ፣ ሲሰለቅ፤ ሲጣላ፣ ሲታረቅ፤ ሲያውቅና ሲማይም፤ ሲሠለጥንና ሲደኸይ፤ ሲሰፋና ሲጠብ፤ የኖረውና የኖረበት፣ የኖረለትም ነው ሀገር፡፡
ሀገር ትዝታ ነው፡፡ የትም ቦታ ስትሄድ ጠምዶ የሚያመጣህ፡፡ ምንም ሥጋ ብትቆርጥ ከብቱ ትዝ ይልሃል፤ ምንም ቢች ዳር ብትዝናና ወንዙ ትዝ ይልሃል፤ ምን በሽቱ ብትታጠን አፈሩ ይሸትሃል፤ ምን በሥጋጃ ላይ ብትሄድ ጉዝጓዙ ይመጣብሃል፡፡ በኮምፒውተር እየሠራህ ያቦካኸው ጭቃ ይናፍቅሃል፤ በጄት እየበረርክ አህያና በቅሎው ያምርሃል፤ ማንሐተን ተቀምጠህ ሰባተኛ፣ ሎንደን ተቀምጠህ ቂርቆስ፣ ኖርዌይ ሆነህ ጅግጅጋ፣ ካናዳ ሆነህ ሐረር ይወዘውዝሃል፡፡ ሀገር ማለት ትዝታ ነው፡፡
ሀገር ማለት ከምትገልጠው ብታስበው፣ ከምትኖርበት ብትሞትበት፤ ከምትስቅለት ብታለቅስለት የምትመርጥለት ነገር ነው፤ ሀገር ማለት ትተኸው ብትሄድ ትቶህ የማይሄድ፣ በራቅከው ቁጥር ልብህ ውስጥ የሚቀር፣ ባወቅከው ቁጥር የምትንገበገብለት፤ በተረዳኸው ቁጥር የምትሳሳለት፣ አንተን እርሱ ውስጥ እንደምታገኘው ሁሉእርሱንም አንተ ውስጥ የምታገኘው፤ የተሠራህበት ውሑድ፤ የተቀረጽክበት ማንነት ነው ሀገር፡፡
ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ዘመድ የሌለው ሰው ወደ ሀገሩ ለመምጣት ባልናፈቀ ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ዘመዶቹ ሁሉ ከእርሱ ጋር ውጭ የሚኖሩለት ሰው ‹ሀገሬን ሀገሬን› እያለ መከራ ባላየ ነበር። ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ሰዎች በየዘመናቱ የበደሉት ሰው ሀገሬ በደለችኝ ባለ ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ሰው ስለ ሀገሩ ሲያስብ ተራራውና ወንዙ፣ አዕዋፉና አራዊቱ፣ ማሳውና ቀየው ለምን ትዝ ይለው ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ያሸነፈ አትሌት፣ ድል ያደረገ ኳስ ተጨዋች ባንዴራው ሲሰቀል ለምን ያለቅስ ነበር?
‹አዙረሀ አዙረህ ሀገሬ መልሰኝ
በሹም ታዘዘ አፈር አታልብሰኝ› ብሎ ለምን ያንጎራጉር ነበር፡፡ ዐጽሙ በአፈሩ እንዲያርፍ ለምን ይናዘዝ ነበር፡፡ ለምን ሙሾውን፣ የሠርግ ዘፈኑን፣ ወጉን ማዕረጉን ይፈልገው ነበር፡፡
ሀገር በአርምሞ እንጂ በንግግር፣ በተግባር እንጂ በዝርዝር ሊናገሩለት የማይቻል ነገር ነው፡፡ ውጥንቅጥ ሰበዞች የሰፉት ሞሰብ፣ ዓይነተ ብዙ  ድርና ማጎች የሸመኑት ጋቢ፣ ልዩ ልዩ ቅመሞች የሠሩት ወጥ፣ ብዙ ገባሮች የፈጠሩት ዓባይ፣ ብዙ ትውልዶች የከመሩት ተራራ፣ ከአራቱ አቅጣጫ ተሰብስቦ በአንድ ወፍጮ የተፈጨ እህል፣ ከየአበባው ተቀስሞ በአንድ ቀፎ የተሠራ ማር፣  ከየእህሉ ወጥቶ በአንድ ማድጋ የተጠመቀ ጠላ፣ ከየ እንጨቱ ተለቅሞ በአንድ ጽንሐ የታጠነ ዕጣን ነው ሀገር፡፡
ሀገር ማለት ሰው ነው? እስኪ ሙት በለኝ!

TPLF ethnic apartheid rebels went to the bush to liberate their ethnic group not Ethiopia

by Obang Metho

When the ethnic apartheid rebels of the TPLF went into the bush, they were motivated to do so in order to liberate their own ethnic group and region. The TPLF did not fight for the interest of Ethiopia, to liberate Ethiopia or for the well being of the Ethiopian people, but only for their own tribal interests.

Nazi TPLF

Their cousins, the Eritrean Peoples’ Liberation Front (EPLF), did the same. The EPLF went to fight for the interest of Eritreans who wanted to divide their region from Ethiopia. Many other groups were the same; for example, the Oromo Liberation Front fought for the interests of the Oromo. The same was duplicated by the people of Gambella, the Ogaden, Benishangul, Afar and elsewhere.

When the Dergue fell, had there been a body that represented the national interests of all Ethiopians, these self-appointed TPLF tribal leaders would have not had such an easy time to take over. The people of Ethiopia missed their opportunity and the tribal interests took over and remain in competition with everyone else.

Over the last 25 years, the TPLF have been promoting their tribal agenda and are not there for the national interests of the Ethiopian people. As a result of their narrow ethnic apartheid policy, they have not only put themselves at great risk of downfall, but in doing so, when they fall, if it is done in the wrong way, it could jeopardize all of the people of Ethiopia. This makes it imperative for the people of Ethiopia to come up with the body that cares for the well being of the entire people so we might make a way for a different kind of transition. No one ethnic group will be free until we all are free.

Right now, Ethiopians have been divided by tribe; people don’t talk to each other, but only about each other. As previously mentioned, Ethiopians from all over the world express their fear that Ethiopia could turn into a Rwanda. This is the fruit of the tribal policy—its inevitable conclusion.

May He help us to see the beauty of the God-given humanity in others for then we will not be limited by our differences.

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ ወደ የት? -ትብብር ወይንስ ውድድር?- አክሎግ ቢራራ (ዶር)

rp_aklog_birara1.jpg
የብዙ ሽህዎች አመታት ተከታታይ ታሪክ፤ መንግሥታትና ዝና ያላት ኢትዮጵያ የምትታወቀው ከሁሉም ብሄር፤ ብሄረሰብና ሕዝቦች ተወጣጥተው ግዛታዊ አንድነቷን፤ ነጻነቷን፤ ክብሯን፤ ዘላቂ ጥቅሟንና ሉዐላዊነቷን ባስጠበቁት ጀግኖቿ መስዋእት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም። አፍሪካ፤ የመካከለኛው ምስራቅ፤ የላቲን አሜሪካና ካሪቢያን እና የኤዥያ አገሮች በቅኝ ገዢዎች እጅ ወድቀው ሲማቅቁ፤ ድሃና ኋላቀርም ብትሆን፤ ኢትዮጵያ ነጻነቷንና ሉዐላዊነቷን በራሷ አቅም አስከብራ ለተከታታይ ትውልድ አስተላልፋለች። በጀግኖቿ ትግል ከፋሽስት ወረራ ነጻ ከሆነች በኋላ በዓለም ደረጃ እውቅና ያገኘችው ከሰማይ የወረደ አይደለም። አገር ወዳድ የሆኑ ልጆቿ ጠንክረውና ተባብረው ስለሰሩ ነው። ለምሳሌ፤ ኢትዮጵያ ሌሎች ታዳጊ አገሮች ገና ከቅኝ ገዢዎች መዳፍ ነጻ ሳይወጡ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ የተባለውን አቅም የሌለው ዓለም አቀፍ ድርጅት ተክቶ በአዲስ መልክ በ1945 ዓ.ም. የተቋቋመውን የተባበሩት መንግሥታትን ከመሰረቱት አገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ወጣቱ ትውልድ እንዲያስታውሰው የምፈልገው አንድ ነጥብ አፄ ኃይለ ሥላሴ በሊጉ ቀርበው ለአገራቸው ነጻነት ሲሟገቱ ታሪክ የሚያስታውሰውን ንግግራቸውን ከራሳቸው መሰረተ ሃሳብ ጨምቀው ንግግሩን ካዘጋጁት ኢትዮጵያዊያን መካከል ከፍተኛውን ቦታ የያዙት ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር አክሊሉ ኃብተወልድ ናቸው። የአጼ ኃይለ ሥላሴ አቤቱታ፤ የቀረበው ንግግርና የሰጡት ታሪካዊ ማስጠንቀቂያ ድጋፍ ባያገኝም፤ የተገኘው ትምህርት ከፍተኛ ነበር። ክቡር አቶ አክሊሉ ሊጉ ደካማ ስለሆነ ኢትዮጵያን ለፋሺስቶች ጥቃት እንዳጋለጠ ያውቁ ነበር። የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ከተካሄደ በኋላ፤ የዓለም ጦርነት ተደጋጋሚ እንዳይይሆን ከተፈለገ ወደፊት የሚቋቋመው ድርጅት የተለየ መሆን አለበት የሚል እምነት እንደነበራቸው ይጠቀሳል። በአዲስ መልክ የተቋቋመው የተባበሩት መንግሥታት ከሊጉ የተለየና ለጋራ ደህንነት (Collective Security) አስተማማኝ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ካደረጉት መንግሥታት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነበረች። በተለይ የተባበሩት መንግሥታት አካል የሆነው የደህንነቱ አካልይ (UN Security Council) እንዲመሰረት በተደረገው ጠረት ልይ። ይኼን ታሪክ የመዘገበውን የኢትዮጵያ አስተዋፆ ስኬታማ ያደረጉት ደርግ በጭካኔ የገደላቸው ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አክሊሉ ኃብተወልድ እንደነበሩ መረጃዎች ያሳያሉ። እኒህ ከራሳቸው ጥቅምና ዝና ባሻገር ለአገራቸው ነጻነት፤ ክብር፤ ግዛታዊ አንድነት፤ ሉዐላዊነትና ዘመናዊነት ቀን ከሌት ይሰሩ የነበሩ ትሁት፤ ብሩህና አስተዋይ ኢትዮጵያዊ ለአገራቸው ያበረከቱት አስተዋፆ በዚህ የተወሰነ አልነበረም። የአገራቸውን ታሪክ ሂደት መሰረት በማድረግ የወደፊቱ ደህንነቷና ዘመናዊነቷ አስተማማኝ የሚሆነው ጣሊያኖች በመሳሪያ ኃይል ቅኝ ያደረጓት የኢትዮጵያ አካል የነበረችው ኤርትራ ወደ እናት አገሯ ስትቀላቀል ብቻ መሆኑን የተገነዘቡ መሪ ነበሩ። ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የዲፕሎማሲ እውቀትና ጥበብ አስፈላጊ መሆኑን የተገነዘቡት እኒህ የታወቀው የፈረንሳይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሶቦርን ምሩቅ፤ ታሪካቸው እና ለአገራቸው ያበረከቱት ግዙፍ አስተዋፆ በሚገባ ያልተመዘገበና እኛ ኢትዮጵያዊያን እንደ ጥሩ ምሳሌ ልንጠቅሳቸው የሚገባ አገር ወዳድ ናቸው። በእኔ ግምት፤ ሌሎች አገሮች እንዳደረጉትና እሁንም እንደሚያደርጉት የኢትዮጵያ ተከታታይ ትውልድ የእኒህን አገር ወዳድ ታሪክና ልዩ አስተዋፆ ለማስታወስ ኃውልት ቢሰራላቸው አግባብ ይኖረዋል። ኢትዮጵያ እንድትጠፋ ሆነ ተብሎ የተደረገው፤ አሁንም የሚደረገው አገር ወዳዶችን በማጥፋት ነው። ስለሆነም፤ ይህ ወንጀል በተካሄደባት ኢትዮጵያ እንደሳቸው ያሉትን ማስታወስ አግባብ አለው። ከጀርባ ሆነው፤ ሌሎችን፤ በተለይ የታባበሩት መንግሥታት አባላት አገሮችን በማሳመን ያደረጉት የተቀደሰ ተግባር ውጤት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ተመልሳ እንድትቀላቀል ማድረጋቸው ነው። ይኼን ታሪክ የመዘገበው የብዙ መቶ ሺህ ኢትዮጵያዊያን ህይወታና ንብረት የወደመበት የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት እንዲፈርስና ኢትዮጵያ ለጥቃት እንድትጋለጥ ያደረጉት ህወሓትና ሻቢያ ናቸው። ይህ ክህደት አገሪቱን ለጥቃት አጋልጧታል። የባህር በሯ ከተዘጋ በኋላ የሌሎች ጥገኛ ሆናለች። በተጨማሪ፤ ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ያላት ግንኙነት ጠንካራ እንዲሆን ካደረጉት ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ ናቸው። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አዲስ አበባ ላይ እንዲቋቋም አገሪቱ ካላት የተወሰነ ኃብት ቀንሳ እንድታበረክት ማድረጓን ታሪክ ያስታውሳል። ምጣኔ ኃብቷን ተጠቅማ ለአፍሪካዊያን ነጻነት አስተዋፆ አድርጋለች።

ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ነጻነት፤ ግዛታዊ አንድነት፤ ዘላቂ ጥቅምና ሉዐላዊነት አስተማማኝ የሚሆነው ኢትዮጵያ ዘመናዊ ኢኮኖሚ ሲኖራት፤ ሕዝቧ ከድህነት፤ ከረሃብና ከጥግኝነት ራሱን ነጻ ሲያወጣ ብቻ መሆኑን የተገነዘቡ በራሳቸውና በሃገራቸው ሕዝብ እምነት የነበራቸውና የኋላውን ትምህርት አድርገው የወደፊቱን ለመቀየስ ያልተቆጠበ ጥረት ያደረጉ አስተዋይ ግለሰብ ነበሩ። የተባበሩት መንግሥታትን ለመመስረት ለተደረገው ጥረት ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ የሚጓጓዙበት የራሳቸው አየር መንገድ የላቸውም ነበር። የሚጓጓዙት በአሜሪካኖች ችሮታና አውሮፕላኖች ነበር። ይኼን ግልጽ የሆነ የእድገት ክፍተትና ተግዳሮት መቋቋም ብሄራዊ ግዴታችን ነው ብለው ያመኑት አክሊሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲቋቋም ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉበት ምክንያት ይኼው ነው። አየር መንገድ ዘላቂ ብሄራዊ ተቋም ነው፤ እንዲሁ በምኞት አይመሰረትም። የአቅም ግንባታ ያስፈልገዋል። ሜካኒኮች፤ አውሮፕላን አብራሪዎች፤ አስተናጋጆች፤ ጠጋኞች ወዘተ ያስፈልጋሉ። ለዚህ አመቻች የሆነው ከአሜሪካው ትራንስ ወርልድ አየር መንገድ ጋር የተደረገው ስምምነት ነበር። በተፈጥሯቸው አገር ወዳድና በፍጥነት ለመማር የሚችሉት ኢትዮጵያዊያን በአጭር ጊዜ አየር መንገዱ ራሱን እንዲችል አድርገዋል። ዛሬ ህወሓት በበላይነት የሚቆጣጠረውና የሚነግድበት አየር መንገድ የተቋቋመው የተባበሩት መንግሥታት ሲቋቋም ነው። ዛሬ ኢትዮጵያዊያንን ከአየር መንገዱ አገልግሎት እንዲባረሩ እያደረገ፤ የውጭ ዜጋዎችን ቀጥሮ ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፈልበት አየር መንገድ በሰው ኃይል ራሱን ከመቻል ታግቦ ጥገኛና የፖለቲካ መሳሪያ ሆኗል። አገር ተከል ተቋምና እድገት አስፈላጊ ነው የሚለውን መርህ ካስተማሩን ኢትዮጵያዊያን መካከል አክሊሉ ኃብተወልድ ከፍተኛ ቦታ ቢኖራችውም ዛሬ የሚካሄደው ጎሳዊ ፖለቲካና የተቋማት መዳከም ጥገኝነትን እያጠናከረ ነው። ጥገኝነት ኢትዮጵያዊያን የማይቀበሉት የሉዐላዊነት ጸር ነው።
እኒህን አስተዋይ፤ አገር ወዳድና ለኢትዮጵያ እውቅና ያበረከቱ ኢትዮጵያዊ በክፉ ጊዜ ያፈራቸው ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። የፖለቲካ ፓርቲ ወይንም አንድ ጎሳ አይደለም። አጋጣሚ ሆኖ ለጥቂት ደቂቃዎችም ቢሆን በ1972 በአካል አነጋግረውኝ ነበር። በአጭሩ የተማሪው እንቅስቃሴ በጦፈበት እና ተገንጣይ ኃይሎች ስር ሰደው ኢትዮጵያዊያንን እንዲከፋፈሉ ባደረጉብት ቀውጢ ቀን ከአሜሪካ ተመልሸ አገሬን ለመጎብኘትና ወላጆቸን ለመጠየቅ፤ ትዳር ለመያዝና ለዶክተሬቴ ምርምር ለማድረግ ስሄድ ቦሌ እንደደረስኩ ፖሊስ ወደ እስር ቤት ወሰደኝ። ነገሩ ሲጣራ የታሰርኩበት ምክንያት Challenge በተባለው የተማሪዎች መጽሄት በስሜ፤ ማለትም በውሸት “የኤርትራን መገንጠል” እደግፋለሁ የሚል ግዙፍ ድርሰት በራሴ ስም ተጽፎ ለመረጃ ስለደረሰ ነበር። ይኼን ድርሰት ያዘጋጁት እነማን እንደሆኑ አውቃለሁ። ተጠቃሚዎቹሻቢያናሌሎችተገንጣይኃይሎችነበሩ።“የውሸቱተግዳሮት(TheforgedChallenge)” በሚል አርእስት ማስተባበያ ጽፌ፤ ሰነዱን በእጀ ይዠ ነበር። የፖሊስ ጣቢው መሪዎች እኔን ስላላመኑኝ ጉዳዩ ለበላይ ባለሥልጣናት እንዲቀርብ ያደረጉልኝ ምንም የማላውቃቸው፤ አሁን “የነፍስ አባቴ” የሆኑት ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች መካከል ከፍተኛ ቦታ የያዙት “አባታችን” አቡነ መልከፀዲቅ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትሩና የደህንነት ሃላፊው ኮሎኔል ሶሎሞን ከዲር በየተራ በግል አነጋገሩኝ። ጽሁፉን እኔ እንዳልጻፍኩት፤ እንዲያውም በብሄረሰቦች የመገንጠል ጥያቄ ላይ የማያወላውል አቋም እንዳለኝ፤ ዲሞክራሳዊ ስርዓት እንዲመሰረት እንጅ መገንጠልን እንደማልደግፍ፤ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ገዢ ጥያቄ ሳይሆን የመደብ፤ የአስተዳደር፤ የሰብአዊ መብቶች አለመከበር፤ የዲሞክራሲ አለመኖር ወዘተ ጥያቄ መሆኑን አስረዳሁ። “ካሰራችሁኝ የመሳፍንቱን አገዛዝ ተቃውመሃል ብላችሁ እሰሩኝ… በኤርትራ መገንጠል ጥያቄ ግን ልታስሩኝ አትችሉም” ብየ ተከራከርኩ። ይህ ለፖለቲካ ጥቅም የሚደረግ የውሸት ፖለቲካ ባህል አሁንም ቀጥሏል።
ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ እውቅና አግኝታ አሁንም ፌውዳል፤ ኋላ ቀርና ከሌሎች ነጻ ከሆኑ የአፍሪካ አገሮች–ጋና፤ ኬንያ፤ ናይጀሪያ ወዘተ ጋር ተመጣጣኝ እድገት የማታሳይ መሆኑን ለማሳየት ሞክሬ ነበር። የንጉሰ ነገሥቱ ስርዓት ዘመናዊ ካልሆነ አደጋው እየተባባሰ እንደሚሄድ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች፤ በተለይ ግብጾች አገሪቱ እንዳትቀጥል ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። እኔም በበኩሌ የውጭ ጠላቶች የሚገቡባቸው ቀዳዳዎች ኢትዮጵያዊያንን በመለያየትና ረቂቅ በሆነ መንገድ በመጠቀም፤ በማሳደድ ኢንዲገደሉ በማድረግ መሆኑን ተጋርተናል።
ከሁሉም በላይ ትዝ የሚለኝ ጠቅላይ ሚንስትሩ የማዳመጥ ችሎታ ያላቸው፤ በፈገግታ፤ በትህትና፤ በአስተዋይነትና የወደፊቱን በማሰብ ምክር የሚሰጡ መሆናቸው ነው። ስለራሳቸው አንድም ጉዳይ አልነገሩኝም። ጭንቀታቸው ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ ሁኔታ ነበር። “አንተና ሌሎቻችሁ፤ እኛ እንዳደረግነው ወደ አገራችሁ ተመልሳችሁ ኢትዮጵያን ማገልገል፤ ዘመናዊ ማድረግ” ወዘተ ግዴታችሁ ነው የሚል ምክር ለግሰውኝ ተሰናበትኩ። ይኼን ምክራቸውን ስራ ላይ አውየዋለሁ። ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ፊት ቀርቤ “ይቅርታ” ጠይቄ እንደምለቀቅ ቃል ገቡልኝ። “ይቅርታ” ለምን እጠይቃለሁ አላልኩም፤ ሌላ መዘዝ ላለማምጣት። የተባልኩትን አድርጌ ከእስር ቤት ተፈታሁ። ቁም ነገሩ የእኔ መታሰር አይደለም። ስንት ኢትዮጵያዊያን ታስረዋል፤ ተገድለዋል፤ ተሰደዋል። ቁም ነገሩ ስለ እኔ አይደለም፤ እኒህ አስተዋይ መሪ

የሚመጣው አደጋ የታያቸው መሆኑን ለማስታወስ ነው። See DireTube TV: The Untold Story of Aklilu Habte-Wold – NEW! Documentary. http://www.diretube.com/diretube-tv-the-untold-story-of-aklilu- habte-wold-new-documentary_d3714ad21.html
የዚህ ሃተታ መሰረት እኛ ኢትዮጵያዊያን የምንከተለው ጎሳዊ የሆነ የፖለቲካ ባህል ለኢትዮጵያ አፍራሽ መሆኑን ለማቅረብና አስቸኳይ የሆነ ብሄራዊ ውይይት እንዲካሄድ ደጋግሜ ለማሳሰብ ነው። ባለፉት አርባ ሁለት ዓመታት ከላይ በአጭሩ ያቀረብኩትን የነጻነትና የሉዐላዊነት ታሪክ እንደ ተራ ነገር እያየን አባክነነዋል። ብንቀበልም ብንክድም የእኛ መነታረክ፤ መጨቃጨቅ፤ መጠላለፍ፤ መናናቅ፤ እርስ በርስ አለመተማመን፤ ልዩነቶችን በጨዋነት ለመፍታት አለመፈለግ፤ ራስንና ቡድንን፤ ራስንና ጎሳን፤ ራስንና ኃይማኖትን፤ ራስንና ንብረትን ወዘተ ከአገር በላይ ማስቀመጥ ወዘተ አገራችን እንድታመልጠን ግብአቶች እያደረጉ ነው። ይህ የፖለቲካ ባህል በፍጥነት ካልተለወጠ አገራችን ለማደን አንችልም። ደርግና ህወሓት ካደረጓቸው ጥፋቶች መካከል የኢትዮጵያን የሰው ኃይል፤ በተለይ አገር ወዳዱንና ዲሞክራቱን እየገደሉና እያሳደዱ ማባከናቸው ነው። እንዴት? ብለን ብንጠይቅ፤ ለሃገራችን ነጻነት፤ ደህንነት፤ ሉዐላዊነትና ዘላቂነት እና ለመላው ሕዝቧ ህብረት የቆሙትን ኢትዮጵያዊያን ግለሰቦችና ተቋሞች አውድመዋል፤ እንዲከፋፈል አድርገዋል። ለምሳሌ፤ ህወሓትና ሻቢያ የሚያኮራ ታሪክና ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከተውን፤ የኢትዮጵያን ስብጥር ሕዝብ የወከለውን የኢትዮጵያን መከላከያ ኃይል አፍርሰዋል። በምትኩ የህወሓትን መከላከያ እዝ ተቋማዊ አድርገዋል። ይኼን የምልበት ምክንያት፤ የደርግንና የአሁኑን አገዛዞች የፖለቲካ የበላይነት እና ለይቶ የማጥቃት ታሪክ ሁኔታ ቀረብ ብሎ መመርመር ለውይይቱና ችግሩን እንዳንደግመው ስለሚረዳ ነው።
ከዚህ ላይ ለማሳሰብ የምገደደው ማንም መንግሥት ለአገር ተቆርቋሪ የሆነውን ትውልድ አጥፍቶ በጎሰኛ ትውልድ ሲተካው የአገር አስተማማኝነትን ለማጠናከርና ዘላቂነትና ተደጋጋፊነት ያለውን ዘመናዊ ሕብረተሰብ ለመመስረት አይችልም። የኢትዮጵያን የወደፊት እድል የሚወስነው ሕዝብ መሆኑ አያከራክርም። ሆኖም፤ ሕዝብ በጎሳና በኃይማኖት ከተከፋፈለ አገርን የመደገፍና አምርቶ ራሱን የመቻል አቅሙ ደካማ ይሆናል። ከደርግ አገዛዝና ራሱ ባባባሰው ድክመትና ውድቀት በኋላ እንዳየነው ከሕዝብ ዐመጽ የሚመጣ እድል የፖለቲካ ፓርቲዎችና የስልጣን ፈላጊዎች ውሳኔ ብቻ ሊሆን አይችልም። ጥንካሬና ዘላቂነት የሚኖረው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዜግነቱን መብት ተጠቅሞ ውሳኔ ለማድረግ ሲችል ነው።
ካልረባ የስልጣን ውድድር ወደ ብሄራዊ ትብብር መሸጋገር ወሳኝ ነው
ኢትዮጵያ የምትባል አገር “አለች ወይንስ የለችም?” የሚለው ጥያቄ አነጋጋሪ መሆኑ እንዴት የፖለቲካ ልሂቃንና ምሁራን ሕዝቡን በጎሳ አደራጅተው፤ ባያደራጁም የገዢውን ፓርቲ የጎሳ ፖለቲካ አጀንዳ እየተከተሉ ኢትዮጵያን ለአደጋ እንዳጋለጧት ያሳያል። ከደርግና ከአሁኑ መንግሥታት በፊት በማይታሰብ ደረጃ የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች ጥይት ሳይተኩሱ ያገኙት እድልና ድል እንደተከሰተ መጠራጠር አይቻልም። ያለፉትን አገር ወዳዶች ከመቃብራቸው የሚቀሰቅስ ክስተት ነው። ለምን እዚህ ደረጃ ደረስን የሚለውን ጥያቄ ሳንሰላስል ባለፉት 25 ዓመታት በስርዓት ደረጃ የተካሄደውን የፖለቲካ፤ በተለይ የሕገመንግሥቱን ሂደት ማንሳት ተገቢ ሆኖ አገኘዋለሁ። ETHIOPIA’S CONSTITUTION: CAN IT STAND THE TEST OF TIME? MARCH 11, 2016 ADDISSTANDARD
በተባለው ጋዜጣ ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፤ የመጀመሪያው የኢህአዴግ ፕሬዝደንት አገር ወዳድ የሆኑ ግለሰቦችንና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን አግልሎ የተመሰረተውን ሕገመንግሥት እንዲህ ሲሉ አቅርበውታል። “ወደኋላ ዞር ብየ ስመለከተው ከፍተኛ ስህተት ያደረግነው ከዚህ ላይ ነው…ቢያንስ ቢያንስ ረቂቁን መልሰን ለሕዝቡ ማቅረብና ድምፅ እንዲሰጥበት ማድረግ ነበረብን። የሕዝቡን ተስፋና ምኞት የሚያንጸባርቅ ወይንም የማያንጸባርቅ መሆኑን መፈተሽ ነበረብን። Looking back at it today, I would say this was where the biggest mistake was committed…. we should have presented it back to the people of Ethiopia in a form of referendum where the people could have had the chance to decide on whether what we formulated was according to their wish or not. That we did not do and I believe it was a mistake.” አንድ የቀድሞም ሆነ የአሁን የአገር መሪና ታዋቂነት ያለው ግለሰብ እንደዚህ በግልጽና በድፍረት ስህተቱን ሲቀበል ዶር ነጋሶ የመጀመሪያው ሳይሆኑ አይቀሩም። በዚህ አጋጣሚ ለዶር ነጋሶ የግሌን አድናቆትና ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለኝን ተስፋ አስመርበታለሁ። ከላይ ጠቅላይ ሚንስትር አክሊሉ ኃብተወልድን የጠቀስኩበት ዋና ምክንያት በዘመነ ህወሓት/ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ መሪዎች የሌሉ መሆናቸውን ስላየሁ ነው።
ህገመንግሥቱ ጉድለት ያሳየበት ምክንያት ብዙ ቢሆንም ጥቂቶቹን ማቅረብ ተገቢ ነው። አገር ወዳድ ምሁራን፤ አባቶች፤ ባለሞያዎች፤ የቀድሞ ባለሥልጣናት፤ ሕብረ ብሄር ፓርቲዎች እንዳይሳተፉ ተደርጓል። ኢህአፓ፤ መኤሶን፤ ኢዲዩ፤

ኢሰፓ፤ የመምህራን ማህበር፤ የሰራተኞች ድርጅቶች…,The All Ethiopian Socialist Movement (AESM), the Ethiopian Workers Party (EWP), and the Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRP) should have participated but unfortunately they didn’t.” በወቅቱ ከፕሮፌሰር አስራት የአቤቱታ ድምጽ ውጭ ለኢትዮጵያ ሉዐላዊነትና ለመላው ሕዝቧ አንድነት የቆመ ኃይል የለም ነበር። የትግል ሜዳው የተሰጠው ለነጻነት ለቆሙት የጎሳ ቡድኖች ብቻ ሆነ። የዚህን አደጋ ቀደም ሲል ለማወቅ ይቻል ነበር። እነዚህና ሌሎች የህብረብሄር ድርጅቶች ቢሳተፉ ኖሮ ህገመንግሥቱ እንደ ጋናና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች “የኢትዮጵያ ሕዝብ” የሚል መግቢያ ይኖረው ነበር፤ አንቀጽ 39 አይታሰብም ነበር።
“የመገንጠል መብትና የመሬት ይዞታ አከራካሪ ነበሩ…በእነዚህ አበይት ጉዳዮች ላይ የተደረጉት ውሳኔዎች በሕዝብ ውይይት አይደለም፤ በሽግግሩ መንግሥትና በሚቆጣጠረው ፓርላማ ነው…The two questions that I remember vividly: the right to self-determination, which is now Article 39, and the question of land. These were very controversial even for the Commission. So what we did was put two alternative versions for each of these articles and brought the draft constitution to the Transitional Parliament. The Transitional Parliament discussed on that draft and brought it to the Constitutional Assembly for adoption.” እነዚህን አዲስ ተቋሞች ማን በጀርባ ሆኖ ይቆጣጠራቸው ነበር? ሻቢያ፤ ህወሓትና ኦነግ ናቸው። አገር ወዳዶች አገርን የሚያፈራርስ አንቀጽ ህጋዊ አድርገው “ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሄር፤ ብሄረሰብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ የተጠበቀ ነው” ብለው አገራቸውን ለማፈራረስ ቃል ኪዳን አይገቡም። ይኼን የሚያደርግ ቡድን ኢትዮጵያን የሚጠላ እንጅ ታሪኩን የሚቀበል አይደለም። አንቀጽ 39 (1). የመጀመሪያው ውጤት ኤርትራ ከእናት አገሯ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል አደረገ፤ እነ መለስ የፈለጉት ሆነ። በዚህ አላቆመም፤ መገንጠል መብት ነው የሚለው ወሳኝ መርህ ህጋዊ ሆነ። ያመቻቸው የኢትዮጵያን ፈራሽነት እንጅ አንድነት እና ሉዐላዊነት አይደለም።
ፈረንጆች እንደሚሉት “You reap what you sow.” አንድ ግለሰብ ወይንም ቡድን፤ ወይንም መንግሥት የዘራው ፍሬ ምን ውጤት እንደሚያስከትል አስቀድሞ ማወቅ ግዴታው ነው። የመከፋፈልን ፖለቲካና ባህል የዘራ መከፋፈልን ስኬታማ ያደርጋል። ጥላቻን የዘራ ጥላቻው ወደራሱ እንደሚመጣ አስቀድሞ ማወቅ ግዴታው ነው። የመገንጠል መብት አለ ከተባለ መገንጠል የሚፈልጉ ኃይሎችን በማባበል ሊገታቸው አይችልም። በተጻራሪው በሕዝብ መካከል የማይታረቅ ልዩነት የለም፤ መደጋገፍ የአንድ ህብረተሰብ ጥንካሬ ምልክት ነው ወዘተ የሚል መልእክትና ትምኅርት ማስተላለፍ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ያጠናክራል። ህወሓት የዘራው ፍሬ ጥላቻን፤ አለመተማመንን፤ መከፋፈልን፤ ስስታምነትን፤ ስግብግብነትን፤ ራስ ወዳድነትን፤ ቂም በቀለኛነትን፤ ዘረኛነትን ወዘተ ነው። የዘራውን ፍሬ እያመረተ ነው። ይኼን ተቋማዊ ያደረገው የአንድን ትውልድ ስነልቦናና አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ በመማረክና በመለወጥ ነው። አማራው ትግራዩን፤ ኦሮሞው አማራውንና ትግራዩን፤ አማርው ኦሮሞውንና ትግራዩን፤ ደቡቡ ኦሮሞውንና አማራውን፤ አኟኩ አማራውንና ትግራዩን ወዘተ ይጠራጠረዋል። በአገር ደረጃ ለመተባበር አስቸጋሪ የሆነው የጎሳው ባህል ጥልቀት ስለያዘ ነው። የኦሮሞው ወጣት በገፍ ሲገደል፤ ሲታሰርና እንዲሰወር ሲደረግ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነጻነትና ሰብአዊ መብት እድል ከፍቷል። ቀደም ሲልና አሁንም፤ አማራው በየቦታው እልቂትና ውርደት ሲካሄድበት ሌላው ዝም ብሎ አይቷል። የአሁኑ መሰረታዊ ጥያቄ አንድ ነው። ይኼን ከሕዝብ እምቢተኛነት እድል ወደ አገር አቀፍ ሕዝብዊ ዐመጽ ለመለወጥ ምን ጎደለን? የሚለው ነው።
የሕገመንግሥቱ ችግር የመገንጠሉ መብት አንቀጽ ብቻ አይደለም። በተመሳስይም ባይሆን በአፍራሽነቱ ማህበራዊ ግንኙነቶችን፤ ተቻችሎ መኖርን፤ ተደጋጋፊነትን፤ ሰጥቶ መቀበልን ወደጎን ትቶ “ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሄር፤ ብሄረሰብ ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለው” የሚለው አንቀጽ 39 (3)ን ያጠናከረው የተገንጣይነትንና ያለመቻቻል ፖለቲካን ነው። ራስን በራስ ማስተዳደር ዲሞክራሳዊ መሆኑን እቀበላለሁ። ሆኖም ሚዛናዊ ያልሆነ ራስን በራስ ማስተዳደር ማለት ከመሳፍንት ዘመን በምንም አይለይም። ይህ አንቀጽ በጎሳ መሪዎች ሲተረጎም ማንኛውም የተፈጥሮ ኃብት “የእኛ እንጅ” (ክልል) የሌለው ኢትዮጵያዊ ሊሆን አይችልም የሚል አስጊ የሆነ ውድድርን አስከትሏል። የብሄረሰብ ማጽዳት ቀላል የሆነበት መሰረት ህገመንግሥቱ ነው። ባይሆን ኖሮ አንቀጽ 32 “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሕጋዊ መንገድ በመረጠው የሃገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቤት የመስራት ነጻነት” አለው የሚለው ሕግ ያለምንም ገደብ ስራ ላይ ይውል ነበር፤ አልዋለም። ከማንነት ጋር እንዲያያዝ የተደረገው የመሬትና ሌላ የተፈጥሮ ኃብት ይገባኛልነት በሕገመንግሥቱም መግቢያ ላይ ተሰምሮበታል። “እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች፤ ሕዝቦች” ብሎ ጀምሮ “የራሳችንን እድል በራሳችን የመወሰን መብታችንን ተጠቅመን፤ በነጻ ፍላጎታችን፤ በሕግ የበላይነት እና በራሳችን ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ መስርተናል” ይላል። “ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ መስርተናል”

ሲባል የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ዘጋ፤ በዜግነቱ ብቻ ተቀብለናል ማለት ነው ወይንስ ሌላ? የሕግ የበላይነትን ስራ ላይ የሚውለው ማነውና ለማን?
“ አንድ ማህበረሰብ” ሲባል ማንን ያካትታል፤ ማንን ለማግለል ያስችላል፤ ይኼንን ማን ይወስናል? ብለን ብንጠይቅ የሚወስኑት ሕገመንግሥቱን የመሰረቱት የጎሳ ልሂቃንና ተተኪዎቻቸው ይሆናሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ አይደለም። ለምሳሌ፤ አኟክ ያልሆነው ኢትዮጵያዊ በጋምቤላ ለመኖር የሚችለው ህወሓቶችና የህወሓት ደጋፊ የጎሳ ልሂቃን ሲፈቅዱ ብቻ ነው። ቁጥራቸው በቅጡ ባይታወቅም ብዙ ሚሊየን ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን በኦሮምያ ይኖራሉ። እነዚህ ሰብአዊ መብት አላቸው። እንደ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው መብታቸው ምንድን ነው እና ምን ዋስትና አላቸው? በደቡብ ክልሎች የሚኖሩ የትግራይ፤ የጉራጌ የአፋር፤ የኦጋዴን ሶማሌ፤ የአማራ ወዘተ ብሄር አባላት ምን ህገመንግሥታዊ መብት አላቸው? በእነዚህ ክልሎች የሚኖሩ “የውጭ” ተወላጆች (ከጎሳው ውጭ) የመምረጥና የመመረጥ መብት አላቸው ወይንስ የላቸውም? ራስን በራስ ማስተዳደር ማለት ሌላውን ማግለል፤ ሌላውን ከቀዩ ማባረር፤ የሌላውን መብት ማፈን፤ ሌላውን መግደል ሊሆን አይችልም። ይህ ጸረ ሕዝብና ጸረ ዲሞክራሲ ነው። የጎሳ ልሂቃን ይኼን ለመቀበል ችግር ሆኖባቸዋል። “ወደቀድሞው ስርዓት አትውሰዱን” የሚሉም አሉ። በእኔ ግምት ወደ አፄውም ሆነ ወደ ደርግ ስርዓት እንመለስ የሚል ግለሰብ ወይንም ቡድን የለም። ይኼን በማስረጃ የልተደገፈ የፈጠራ ወሬ ሆነ ብለው የሚያስተጋቡት ህወሓቶችና አጋሮቻቸው ናቸው። ያነጋገርና የአቀራረብ ግድፈት ካልሆነ በስተቀር፤ እኔ እስከማውቀው ድረስ በህበረብሄር ፖለቲካ ውድድር የሚያምኑ ግለሰቦችና ስብስቦች ወደ ኋላዎቹ አገዛዞች እንመለስ የሚሉ ፈልጌ አላገኘሁ።
በአጭሩ ግን “የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች፤ ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉዐላዊ ስልጣን (Sovereign Power) ባለቤቶች ናቸው” የሚለው አንቀጽ 8 ያጠናከረው መገንጠልንና በጎሳ መለያየትን ነው። መገንጠልንም ባይሆን ልክ የደቡብ አፍሪካን የሚመስል አፓርታይድ ወይንም መለያየትን ነው። የጎሳ ክልሎች “የኢትዮጵያ ሉዐላዊ ስልጣን ባለቤቶች” ስለሆኑ የተለያዩ አገሮች ተፈጥረዋል ወይንም እንዲፈጠሩ ተደርጓል:: ልክ እንደ ደቡብ ሱዳንና ኬንያ ጎረቤት አገሮች እየተመሰረቱ ነው። ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መብቶች መከበር አንጻር ብናየው እነዚህ “ሉዐላዊነታቻው” በህገመንግሥቱ የጸደቀላቸው ክልሎች ሌላውን ለማገልል፤ ለማባረር ቢችሉ አያስገርምም። ራስን በራስ በማስተዳደር ብሂል የሞተው፤ ከኃብቱ የተፈናቀለውና የተሰደደው ሕዝብ ብዛት ግዙፍ ነው። የመሳሪያ አቅም ያላቸው የሌላውን መሬት ቢነጥቁ አያስደንቅም። ህወሓት የሚከተለው የከፋፍለህ ግዛው፤ በተለይ የማንነት ፖለቲካው ድንበርና ገደብ የሌለው ሆኗል። ሌላው ቀርቶ አማራውን ከአማራው ለመከፋፈልና ለማዳከም ልዩ ዞኖች ተፈጥረዋል። ኦሮሞውን ከኦሮሞው ለመለየያት ተመሳሳይ ሁኔታ ቢፈጠር ምን ያስደንቃል።
የዚህ ውጤት ምን ይሆናል?
ዶር ነጋሶ ያሉት አግባብ አለው። “እኔ የምፈራው ህገመንግሥቱ አሁን ( የእኔ ነጥብ) ካልተሻሻለ አገሪቱን በአንድነት የሚያቆያት ነገር፤ ተቋም ( የእኔ ነጥብ) የለም…ሁኔታዎች ከእጃችን ውጭ ይወጣሉ፤ አገሪቱ ለአደጋ ትጋለጣለች፤ አንድ ነገር መደረግ አለበት… I fear if something is not done this constitution will not hold the country together; people will eventually ask why we should have this constitution. If things are not improved, I fear the controversies will get out of hand and eventually put the country’s unity in danger. Something has to be done.” ከላይ እንዳልኩት፤ ከጅምሩ ኢትዮጵያ አስተማማኝ መከላከያ ኃይል እንዳይኖራት ሻቢና ህወሓት በትነውታል። የአንድ አናሳ ብሄር የበላይ እዝ አስተማማኝ የሆነ ውጤት ሊያስገኝ አይችልም።
ማንኛውም አገር ዘላቂነት የሚኖረው ተቆርቋሪ ትውልድ ለማፍራት ሲችል ነው። በደርግ አገዛዝ የተወለደው፤ ወጣት የነበረውና ህወሓት/ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ በኋላ የተወለድውና የተማረው ወጣት ትውልድ ኢትዮጵያን እንዳያውቅ ተደርጓል። የአሁኑ ገዢ ፓርቲ ያስተማረው የአገሪቱን ረጂም ታሪክ፤ የሕዝቧን ተቻችሎ መኖር አይደለም። የጎሳ ፖለቲካን፤ ማንነትንና ክልላዊነትን ነው። ማንነት ብዙ ትርጉም እንዳለው ከዚህ በፊት ባቀርብኳቸው ሃተታዎች አሳይቻለሁ። የአንድን ግለስብ ወይንም ጎሳ ማንነት መቀበል የሁላችንም ግዴታ ነው። የተለያዩ ዜጎች በሚኖሩበት አገር ማንነት ትርጉምና ዘላቂነት የሚኖረው አንዱ የሌላውን ሰብእነት ሲቀበልና ሲያከብር ነው። ይኼ ተቀባይነት እንዳይኖረው የምናደርገው ራሳችን ነን። የራሳችን አመለካከት ካልተለወጠ ችግሩ ይባባሳል።
የአሁኑን የጎሳ ህገመንግሥት አደጋ ብዙ ምሁራንና ባለሞያዎች ተችተውታል። ከእነዚህ መካከል ጆን አቢንክ ያቀረበውን ጥናት እጋራለሁ። እንዲህ ይላል “In contemporary Ethiopia thé discourse of ethnicity has become strongly politicized, more so than ever before, and has created “realities” which did not

previously exist. Few of the parties concerned (libération movements which emerged largely in the 1970s and largely “mono-ethnic” political parties dating from the early 1990s) fully realize the artificial aspect of the matter or the implications of their aspirations, especially when they are cast in the inevitable and ubiquitous idiom of “national self-détermination”. Neither do they recognize the fact that Ethiopian government discourse on ethnicity, and its political government —be established. በአሁኗ ኢትዮጵያ ስለ ብሄረሰብ የሚነገረው ሁሉ ፖለቲካዊ ሆኗል፤ ከመቸውም በበለጠ ደረጃ አዲስ ሃቆችን ፈጥሯል። በ70ዎቹ የተመሰረቱት የብሄር ነጻ አውጭ ግንባሮችና በ1990ዎቹ የተቋቋሙት የብሄር ፖለቲካ ፓርቲዎች የፈጠሩት ሰው ሰራሽ የፖለቲካ ባህልና የራስን እድል በራስ የመወሰን ሕጋዊ መብት የሚያስከትለውን አደጋ በሚገባ አላወቁትም። የኢትዮጵያ መንግሥትም የተከተለውና ስራ ላይ ያዋለው መርህና ተቋም የአገሪቱን የወደፊት እድል ወደየት እንደሚያመራ አላጤነውም” ይልና በዚህ ይደመድማል።
“The issue of recognizing ethnic diversity in a polyethnic polity like Ethiopia deserves much attention. The present government has made a serious effort, although its societal and institutional basis for constitution-making, and for decision-making in general has been slim. There is no going back to a unitary state structure in Ethiopia which denies ethnoregional différences and rights, or which Iets one group dominate the state. The formula of ethnicization (although in a different, more effective, fédéral form) should perhaps be encouraged if, first, it is generally interpreted and implemented as libération and democratization; secondly, it is sustained also in the domain of respecting individual human rights within the ethno-regions; thirdly, it works in the economie domain: and finally, it is a tendency and a frame of mind accepted by the “rural masses”, the majority. If, however, all this does not happen and if the ethnic emphasis combined with economie problems would instead lead to ethnocentrism, regional economie disparities and a reproduction of inequalities on the intermediate level of the new ethno-regional states, then one wonders what is new, and whether the Ethiopian people have won anything yet by the constitutional récognition of their being ethnically separate.” JON ABBINK, Journal of African Law, 41: 159-174 ETHNICITY AND CONSTITUTIONALISM IN CONTEMPORARY ETHIOPIA.
በአጭሩ “ኢትዮጵያ ወደኋላ መመለስ አትችልም….የብሄረሰብ ፖለቲካ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ እስከሆነ ድረስ አግባብ አለው። ይኼም መደገፍ ያለበት በሁሉም ክልሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ግለሰቦች ሰብአዊ መብት በሕግ ሲከበር ነው፤ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የኢኮኖሚ መብትና ተሳትፎ ሲከበር ነው፤ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ተስማምቶ ሲቀበለው ነው… ይኼ ካልሆነና የጎሳ ፖለቲካው ትኩረት ከኢኮኖሚው ችግሮች ጋር (ለምሳሌ ድህነት፤ ረሃብ፤ ስራ አጥነት)፤ በሕዝቦችና በክልሎች መካከል ከሚታየው የተዛባ እድገትና በዜጎች መካከል ከተከሰተው (የሚዘገንን) የገቢና የኑሮ ልዩነት ጋር ተደማምሮ ከቀጠለ እኔ የምደመድመው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ አገዛዝ ያገኘው አዲስ ጥቅም የለም” የሚል ነው። የህገመንግሥቱ ተጠቃሚዎች የህወሓት የበላዮች፤ ቤተሰቦችና አጋሮች መሆናችው በብዙ ማስረጃ ቀርቧል። ደራሲው እንደሚለው የጎሳው ፖለቲካ ፍትሃዊና ዲሞክራሳዊ አይደለም፤ ለሁሉም ዜጎች፤ ብሄሮች ጥቅም አላገለገለም።
ለማጠቃለል ዛሬ ያለው አደገኛ የፖለቲካ ቀውስ ከልዩ ልዩ አቅጣጫዎች በፉክክርና ውድድር ይንጸባረቃል፤
 የፖለቲካ ስልጣን ሽሚያና ውድድር
 የመገንጠል መብት ውድድር
 የተፈጥሮ ኃብት ባለቤትነትና ማንነት ውድድር
 የውጭ ኃይሎች የበላይነት ውድድር
 የኃይማኖት የበላይነት ውድድር (ሳውዲዎች፤ ካታሪዎች፤ ኢራኖች፤ ፓኪስታኖች፤ ግብጾች ወዘተ)
 የምሁራንና ልሂቃን ግለሰባዊነትና ቡድናዊነት ውድድር
 የሕብረብሄር ድርጅቶች ድክመት፤ መከፋፈል፤ መጠላለፍና አለመተማመን ወዘተ

ይህ በአገር ብሄራዊ ልእልናና በሕዝብ እኩልነትና የፖለቲካ የበላይነት ላይ ትኩረት ያልሰጠ ውድድር ለገዢው ፓርቲ ድጋፍ እየሰጠ ህልውናውን አራዝሞታል። ህወሓት፤ ኢህአዴግን ከማውገዝና ከመቃወም ባሻገር ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ አማራጭ አልተፈጠረም። ያም ሆነ ይህ ከፊታችን ላይ የተደቀነው ተግዳሮት አገሪቱን ተባብሮ ከመፈራረስ ማዳንና ሽግግሩን ማመመቻቸት ነው። አገርን ማዳን ስል በኢህአዴግ ውስጥ የተሰበሰቡትንም ኢትዮጵያዊያን ያካትታል።
ለማጠቃለል፤ የመንግሥትና ተቃዋሚ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ስብስቦችና ግለሰቦች በመግባባትና በአንድነት አገሪቱን ከጥፋት ማዳን የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። በመግቢያው እንዳሳሰብኩት፤ የጣሊያን ወረራ ሆነ ሌላ ብሄራዊ ተግዳሮት ያስተማረን አገር ከሌለ የእርስ በርስ ግጭት፤ ባርነት፤ ጥገኝነት፤ ኋላ ቀርነት፤ ረሃብና ድህነት የሚቀጥል መሆኑን ነው። ኢትዮጵያ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሚሆን መሬት አላት። የጠፋው አብሮና ተከባብሮ የመኖር የፖለቲካ ባህሪና ለአገር ተቆርቋሪ የሆነ ዲሚክራሳዊ መንግሥትና አመራር ነው። ኢትዮጵያ አለች ወይ? የሚለው ጥያቄ የሚያመራን ተቆርቋሪ መንግሥት፤ መሪዎችና ተቃዋሚ ክፍሎች የሉም ወደሚለው ድምዳሜ ነው። ስለሆነም፤ ለሕዝብ የስልጣን የበላይነት፤ ለፍትህ፤ ለእውነተኛ የሕዝብ እኩልነት፤ ለዲሞክራሲ ምስረታ አብሮና ተባብሮ መቆም ወሳኝ ነው።
ዞር ብለን ማየት ያለብን አንድ ክስተት አለ። ይኼውም ሁሉም እንተባበር፤ አብረን እንስራ ወዘተ ሲል አርባ ዓመታት አልፈዋል። ለመተባበር በሚል እምነት ተወያይተን መለያየት የፖለቲካ ልማዳችን ሆኗል። የጎደለው ክፍተት ዲስኩሩን ተግባራዊ ከማድረጉ ላይ ነው።
በመጨረሻ፤ ኢትዮጵያ ከሌለች የምናወራው ፌዝ ይመስላል። ከማፌዝ በላይ ለመሄድ ከተፈለገ መጀመሪያ አገሪቱን ተባብሮ ከጥፋት አድኖ እነዚህ መርሆዎችና እሴትቾ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆኑ የተለያዩ አመለካከቶችንና አማራጮችን ማስተናገድ ግዴታ ነው። እንደገና ከተለመደው የፍክክር ባህል መጥቀን ወጥተን የጋራ አገራችን ከመፈራረስ አድንነን ወደሚቀጥለው የማይቀርና ወሳኝ ወደሆነው አገር አቀፍና የተቀነባበረ ሕዝባዊ፤ ዲሞክራሳዊ ትግል እንሸጋገር እላለሁ።

ተመስገን ደሳለኝ የታሰረችውን ሀገሩን ለማስፈታት ታስሯል

 

ተመ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እስካሁን  መንግስት ሲያሻው ቤተሰብም ሆነ ወዳጅ እንዳይጠይቀው፣ ሲፈልግ ከቤተሰብ ውጪ ማንም እንዳያየው ፣ ሲያሰኝው ደግሞ ተመስገንን  አስሮ ብቻ ማስቀመጤ ስላላረካኝ በማለት አንዴ ጭለማ ቤት አንድ ግዜ ቅጣት ቤት አንድ ግዜ አደገኛ የእስር ክፍል የሚለው ውስጥ ሲያንገላታው ከርሟል፣ እየከረመም ነው።

እንዲሁም የጀርባ፣ የወገብና የጆሮ ህመሙ ምንም ያህል ቢያሰቃይህ እንድትታከም አላደርግህም በማለት ትእቢቱን አሳይቷል እያሳየውም ነው። ደግሞም ምንም አይነት መፅሀፍ አታነብም፣ ከማንም እስረኛ ጋርም አትነጋገርም በማለት የእሰር ቤት አለቃነቱን አሳይቷል እያሳየም ነው። ለተመስገን አልተኛም ያለው መንግስት ከየካቲት 9/2008ዓ.ም ጀምሮ ለ 40 እስረኛ ይበቃኛል ብሎ በሰራው የእስር ክፍል ውስጥ 167ተኛ አድርጎ ተመስገንን አጎሮታል። በዚህ ክፍል አልጋ የለም፣ የአእምሮ ህመምተኞች ይገኛሉ፣በተደጋጋሚ በመንግስት የሚመሩ ፀበኛ እስረኞች ይኖራሉ። በዚህ የእስር ክፍል ውስጥ በአሁን ሰዓት ተመስገን በቀን 1 ግዜ እንኳን የመፀዳጃ ቤትና የውሃ አገልግሎት አያገኝም። ተመስገን ከታሰረበት ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ ይህ ሁሉ ሲሆን ለአንድ ሰከንድም እንኳን‹‹ እንዲህ ሆኛለሁ ፣እንዲህ ተደርጌለሁ፣ ይህ እየተፈፀመብኝ ነው ››ብሎ ነገሮኝ አያውቅም። ይህ የእርሱ ባህሪ አይደለምና።

እኔ ግን ህመሙን አይቻለሁ፣ እንግልቱን ሰምቻለሁ ፣ በደሎቹን ታዝቤለሁ አረጋግጫለሁም። ተሜ እንዲዚህ እየሆንክ ነው እለዋለሁ ሳቅ ብሎ ዝም ይለኛል ድጋሜ እጠይቀዋለሁ ያኔ አገጩን እየዳበሰ ፈግግታው ከፊቱ ሳይጠፋ አሻግሮ ይመለከታል። ምን አንደሚያስብ አስባለሁ ምንድን ነው የምታስበው ግን ብዬው አላውቅም። ግን እርግጠኛ ነኝ “ለምን ይህ ሁሉ ሆነብኝ ብሎ እንደማያስብ” ህልሙ ሁሉ ሀገሩ ለሆነው ተሜ ለምን ብሎ በሆነው ሁሉ ይቆጫል? ስለ ምንስ ይከፋል? የሆነውም የሚሆነውም ለተሜ ከሀገሩ በታችና በታች ነው።

እንግዲህ የተመስገን ነገር ይህ ነው።

አንዳንዶች በመልዕክትና በአካል ተመስገን ይፈታ ፣ ተመስገን ተንገላታ ፣ተመስገን ታመመ፣ ተመስገንን መጠየቅ ተከለከልን፣ ተመስገን ጨለማ ቤት ገባ ተመስገን እንዲህ እንዲህ ሆነ አትበል ምክኒያቱም ተመስገን ለሀገሩ ሲል ነው የታሰረው ተመስገን አሁን ላላቸው ኢትዮጲያ በቻ ሳይሆን የወደፊቷን ኢትዮጵያ ለሁላችንም እንድትሆን ያሳየ ያሳሰበ ያመለከተ ነው፣ ተመስገን ያሰበውን የኖረ ነው፣ ኢትዮጲያዊነትን ዳግም የቀሰቀሰ ነው። ደግሞስ ለሀገሬ ስለ ጉዞዬ ቀራኒዮ ድረስ ነው ማለቱስ ቀደሞ ለሀገሩ ለመሰዋት የተዘጋጀ መሆኑን ያሳያል ስለዚህ ነው ስለ ተመስገን እንደዚህ አትበል የምንልህ ይሉኛል።

ልክ ናቸው። ትክክል መሆናቸውንም እመሰክራለሁ። በንግግሮቻቸው ሁሉ እስማማለው። በተመስገንም እኮራለሁ እላቸዋለሁ።

ግን ተመስገን ለደካማዋ እናታቸን ልጇ የዓይኗ መርፊያዋ ጧሪዋ ነው ለኔ አባቴም ወንድሜም ነው። ታዲያ ወንድሜ ታሟል ግን ህክምና ተከልክሏል፣ ወንድሜ ጨለማ ቤት ነው፣ ወንድምህን እንዳትጠይቅ ተባልኩኝ እንዲህ ሆነ እንዲህ ተደረገ የምለው ለኔ የወንድሜ ጉዳይ ሆኖብኝ ለናቴ ደግሞ የልጇ ነገር ሆኖባት ነው እንጂ የተመስገንን ጀግንነት በኛ እሮሮ ለመሸፈን አይደለም። የሆነውን ሁሉ ቢሆንም ግን ዛሬ “ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የታሰረችውን ሀገሩን ለማስፈታት ታስሯል በዚህም መላው ቤተሰቡና አገሬ ትኮራለች፡፡

በታሪኩ ደሳለኝ  (የጋዜጠኛ ተመስገን ታናሽ ወንድም

በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጣዊ መግለጫዎች – አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ

ማክሰኞ መጋቢት ፲፫ ቀን፣ ፳፻፰ ዓመተ ምህረት

eskemecheገዢው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በየዕለቱ በሚያደርገው ፀረ-ኢትዮጵያዊ ተግባር፤ የተለያዩ የፖለቲካ ሕዝባዊ ስብስቦች መግለጫ ያወጣሉ። አዳዲስና ነባር የፖለቲካ ድርጅቶች፤ አለን በማለት ስማቸውን በአንባቢዎች ያስመዘግባሉ። ለመሆኑ ጋዜጣዊ መገለጫዎች ለምንድን ጉዳይ ነው የሚወጡት? ማነው የሚያወጣቸው? መግለጫዎችን ተከትሎ የሚተገበሩት ምንድን ናቸው? አሉስ ወይ? መግለጫ አውጪዎቹና መግለጫ ያላወጡ የፖለቲካ ሕዝባዊ አካሎች መለያቸው ምንድን ነው? መግለጫዎችና አውጪዎቻቸው፤ ሕዝባዊ ናቸው ወይንስ ጠባብ ወገንተኛ? መልዕክት አላቸው ወይንስ አደረግሁ ለማለት የተወረወሩ? አስፈላጊነታቸውስ ምን ያህል ነው? በተደጋጋሚ ጋዜጣዊ መግለጫ በተንጎደጎዱ ወቅት የደረሱኝ እጦማሮች ነበሩ። ሁሉም ወቀሳዎች ናቸው። “ለምን መግለጫ አታወጣም?” “ካሁን በፊትም ዝም ብለሃል!” የሚሉና ሌሎችም ከጠላት ጋር ወግነሃል ያሉኝም ነበሩባቸው። ለምንድን ነው መግለጫ ማውጣት ያለብኝ? መግለጫ አላወጣም። ይሄን ግልጽ በሆነ መንገድ ማስቀመጥ አለብኝ።

መንግሥታትና ድርጅቶች መግለጫ ሲያወጡ፤ መሠረታዊ ዓላማው፤ ጉዳዩ ካተኮረባቸው አካላት ጋር ተባባሪ መሆናቸውን አንባቢ ወይንም አዳማጭ እንዲያውቅላቸው አይደለም። መግለጫውን የሚያወጡት፤ ነግ ለኔ ብለው፤ ካሁኑ ቀድሜ እርምጃ እወስዳለሁ ማለታቸው ነው። ከማንኛውም መግለጫ ጋር፤ አብሮ የሚሄድ መልዕክት አለ። “የሚያስፈልገውን ለማድረግ እንጥራለን!” “ከዛሬ ጀምሮ ይሄን ወይንም ያኛውን እናደርጋለን!” “በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ልንረዳችሁ ዝግጁ ነን!” “ሊረዷችሁ የሚችሉ ሰዎችን ልከንላችኋል!” “ለመቋቋሚያ እንዲያግዛችሁ ገንዘብ ልከንላችኋል!” እና የመሳሰሉት ናቸው። እንግዲህ ልብ ብለን ብናጤነው፤ ዋናው የመግለጫው ማሠሪያ፣ ይሄ ከወደኋላ የተከተለው ተግባር ነው። እስኪ ወደኛ፤ በተለይም የገዢውን ቡድን ተግባር የሚያወግዙትን ጋዜጣዊ መግለጫዎችና አውጪዎቻቸውን እንመለስ።

በጠላትን ፈርጀው የሚታጋሉትን ገዢ ቡድን፤ “ይሄን በማድረጉ አውግዘናል!” ማለት ምንድን ነው ትርጉሙ? ካወገዙስ በኋላ ምንድን አንው የተከተለው? “ድርጅታችን የበለጠ ትግሉን ይቀጥላል!” ማለትስ ምንድን ነው ትርጉሙ? “ያንን እስኪያደርግ ድረስ የበለጠ አልተጋልንም!” የሚል ኑዛዜ ነው? “የታሰሩትን እንዲፈታ እንጠይቃለን!” ማለት ለፌዝ ነው?“ከሌሎች ጋር እንተባበራለን!” የሚል ማስፈራሪያ አስቀምጦ ድምፅን ማጥፋትስ ለምን አስፈለገ? በተለይ የመተባበርን ጉዳይ አስመልክቶ፤ “እተባበራለሁ!” ያላለ ድርጅት የለም። ትግሉ “ያለአንድነት የትም አይደርስም!” ያላለ ድርጅት የለም። አስፈላጊነቱን ያላሰመረ፣ የሕዝቡ ጥያቄ መሆኑን ያላስገነዘበና ጥሪውን በተደጋጋሚ ያላወጀ ድርጅት የለም። ታዲያ አሁን የት ላይ ቆመናል? መግለጫዎቹ አደረግሁ ለማለት ነበር የወጡት? ለመተባበር ጥሪ ያደረገ ድርጅት፤ ከወዲሁ አብሮ የመሥራትን አስፈላጊነት ማመን ብቻ ሳይሆን፤ ለማስተባበርም ኃላፊነቱን መውሰዱ ነው። ታዲያ ያንን ኃላፊነት ለመውሰድ የወሰነ ድርጅት፤ ሌሎች ለሚጠሩት ትብብር ለምን መልስ መሥጠት ገደደው? ምን መልስ ሠጠ? እኔ ለጠራሁት ሌሎች መልስ ይሥጡ እንጂ፤ ሌሎች ለጠሩት እኔ መልስ አልሠጥም ማለት ይሆን? አስመሳይነት ማለት ምን ማለት ነው? ዋሾነት በምን ይከሰታል? በዚህ ጉንጉን የተተበተበ ሂደት ምን ያህል ካለበት ፎቀቅ ማለ ይቻላል?

እዚህ ላይ ነው የኔ መግለጫ አለማውጣት ትርጉም የሚሠጠው። የምደግፈው ተግባራዊ ጉልበት በማልሠጥበት ሂደት፤ መግለጫ አላወጣም። በርግጥ አንዳንድ ያደረግኋቸውን ለማመላከት፤ የእስላሞችን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በግፍ መሪዎቻቸው ሲታሰሩ እኛም ሰለምን፤ በማለት ከትቤያለሁ። አብረሃ ደስታ ሲታሰር አሻንጉሊቶች ናችሁ በማለት ከትቤያለሁ። ሌሎችንም በዚሁ ማስታወሻ መድረኬ ጠቃቅሻለሁ። ዋናው ቁም ነገር ግን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ብዬ ያሰቀመጥኩትን ቡድን፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ይሄን! ወይንም ያንን! ሠራ ብዬ መግለጫ በማውጣት ውግዘት አላሽጎደጉድም። ጠላት ከዚያ የተለዬ ምን ሊያደርግ ኖሯልና! ጠላቴ ብዬ ፈርጀዋለሁ እኮ! ይልቅስ ይሄንን ጠላት ብለን የፈረጅነውን አካል፤ በተግባር በመተባበር ለመጣል በአንድነት እንሰለፍ።