ኢትዮጵያ ከወያኔ በፊት ነበረች ያለ ወያኔም ትኖራለች -ሰቦቃ ዋቅቶላ

Woyaneየወያኔ አላማ አንድ ብቻ ነው። በስልጣን ላይ መቆየት። አምባገኖኖች ሁሉ እንዲሁ ናቸው። ወደ ስልጣን ለመውጣት የነበረውን ሁሉ እንዳልነበረ ያደርጋሉ፡፡ በሰልጣን ላይ ለመቆየት ያፍናሉ:: ይገላሉ። ወደ ስልጣን ለመውጣትና በስልጣን ለመቆየት የሚጠቀሙበትን መንሰላል የበደልን ሸክም ያለርህራሄ ስለሚያሳርፉበት: የወጡበትን መንሰላል ለመውረጃ ሲፈልጉት አያገገኙትም:: ከወጡበት ለመውረድ ሲያስቡ የሚታያቸው ቁልቁል የመፈጥፈጥ አደጋ ነው::

ሰለዚህም የውስጥና የውጭ ግኑኝነታቸውን ሁሉ  በስልጣን ላይ ከመቆየት አንጻር ይመራሉ። የውጭውም የውስጡም አንድ ነገር እንዲቀበል ይፈልጋሉ። እነሱ ከሌሉ አይን ሁሉ ማየት እንደሚያቆም ጆሮ ሁሉ መስማት  እንደሚሳነው። ጻሀይ ብርሀን መስጠት እንደምታቆም። ሰማይም ዝናብ መስጠት እንደሚያቆም። ቢቻላቸው ሁሉ እንዲያምናቸው ይፈልጋሉ። በዙሪቸው ይኽንን የሚነግሮአቸውን ያከማቻሉ። አነዚያም የሚፈሉጉትን መልሰው  ይነግሮቸአዋል። በዙሪያቸው የሚሰበሰቡት ሞኞችም ብልጦችም ናቸው። ሞኞቹም  ተታለው ብልጦዎቹም ጥቅማቸውን አስበው። ፕሬዚደንት አባማ ከብልጦቹ ይቆጠራሉ። ልባቸው እያወቀ ምርጫው ዺሞክራሲያዊ ነው ብለው ተሳልቀዋልና። ሞኞቹን ቤት ይቁጠራቸው። ጉድ የሚፈላው የብልጦቹ ጥቅም የቀረ እለት። ሞኞቹም የነቁ እለት ነው። ሞኝነትንም ብልጠትንም የቀየጡም አይጠፉም።

እንደ መሰሎቹ አምባገኖኖች ሁሉ ወያኔ አመለካከት የሚል አባዜ አለበት። በወያኔ ፍልስፍና ሁል ጊዜ ሁለት አይነት አመለካከቶች አሉ። ልማታዊ እና ተቃራኒው። ኪራይ ሰብሳቢና ተቃራኒው። ቀደም ያሉትን እንተዋቸው። ወያኔ ራሱ ስለ አረጁበት ትቶአቸዋልና። ልማታዊው እንግዲህ ወያኔ ከሌለ ጸሀይም ዝናብም የለም የሚለውን የተቀበለ ነው።አለበለዚያ ኪራይ ሰብሳቢ ነው። የሚገርመው ነገር አቀባበሉ ከልብ ይሁን አይሁን ወያኔ ግድ የለውም። ወያኔ የሚፈልገው በየ አፋኝ መድረኮቹ ወያኔ ከሌለ ጻሐይም የለ ዝናብም የለ ተብሎ እንዲነገርለት ነው። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲክ ኤጀንሲ አና ፋና ስራቸው እንዲህ አይነት ዜናዎችን ማነፍነፍ ነው።ዜናዎች ሁሉ በዚህ መስፈርት ይመረጣሉ:: ይሰራጫሉ::

ወያኔ ፕሮፓጋንዳውን የዩኒቨርቲው መምህር ባያዳምጥ እሱ ምን ገዶት። ጭቁኑ ተማሪ ይሰማኛል ይላል።ጭቁኑ ተማሪ ፊቱን ወደ ነጻ ሚዲያ ሲያዞር፡ ወያኔ ጭቁኑ የከተማ ነዋሪ ይሰማኛል ይላል። ጭቁኑ የከተማ ነዋሪ ዲሽ በመትክል ከተማውን የሳተላይት ጣቢያ ሲያሰመሰለው ወያኔ ምን ገዶት የገጠሩ ገበሬ ይሰማኛል ይላል። ወያኔ በገጠሩ ገበሬ ላይ አንጀቱ አይቆርጥም። ጠቅላይ ሚኒሰትር ሃይለ ማርያም ነገሩ ገብቶአቸዋል። የ መለስ ተማሪ አይደሉ። ድሮም ጎበዝ ተማሪ እንደነበሩ አይዘንጉ። የመጨረሻ የፕሮፓጋንዳ ማፈግፈጊያቸው ገበሬው መሆኑ ገብቶአቸዋል::

ይኸ የመጨረሻ ማፈግፈጊያ ከተለቀቀ ፕርፕፓጋንዳው እጅ ይሰጣል:: ወያኔም አብሮ::  ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ አሉ ገበሬው ጥያቄውን አቅርቦ ወደ ቤቱ ገብቶአል:: ጥያቄዬን ይኽ መንግስት ይፍታልኝ ነው ያለው ብለውን እርፍ:: ወያኔ የሚናገረው ገበሬው እውነትና ውሽት አይለይም ብሎ አይደለም። በትከሻው ላይ መንጠልጠል ከ እንግዲህ እንደማይቻል ገበሬው ለወያኔ ነግሮአል:: ወያኔም ሰምቶአል። ወያኔ ታዲያ ለምን አሁንም ውሸት ይናገራል።ውሽት ሲደጋገም እውነት ይመስላል የሚለው የዲያቢሎስ አባዜ ልማድ ሆኖበት ነው። ለዚህም የወያኔ ሰራዊቶች: ፋና እና የኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ያለመታከት ይደክማሉ:: ወያኔ ከሌለ ጸሀየም የለ ዝናብም የለ እያሉ ሌት ተቀን ይዘፍናሉ። አይነ ደረቆች:: ውሸት መሆኑን አያወቀ ውሸት መሆኑን ለሚያውቁ ሰዎች ውሸት የሚያወራ በአገራችን አይነ ደረቅ ይባላል::

ሰሞኑን  ደግሞ ወያኔ አንድ የዕድሜ ማራዘምያ መድሀኒት ይዞ ብቅ ብሎአል። ሃላፊነት መውሰድ ይባላል።

በኦሮሚያ በኦሞ በወልቃይት በጋምቤላ ለደረሰው እልቂት ወያኔ ሃላፊነቱን መውሰዱን ነገረን። ለሞቱት ለቆሰሉት ለተፈናቀሉት ለተሰደዱት ለንብረቱ ውደመት ሀላፊነቱ የወያኔ አስተዳደር የፈጠረው ብልሹ አሰራር እና የመልካም አስተዳደር አጦት መሆኑ ተብራርቶ ተገለጸልን።

ከፍተኛ ሀብት የፈሰሰበት የ ስኮር ፕሮጀክት በኮንትራት አመራር ብልሹ አሰራር ምክንያት ባክኖ መቅረቱና ወያኔ ሃላፊነቱን መውሰዱን በዚያው በፓርላማ መድረክ ሲነገር ሰማን::

የአትሌቲክስ ስፖርት አባላት በተከሰሱበት የማነቃቂያ መድሐሃኒት መውሰድ ችግር የወያኔ ብልሹ የስልጠና አሰጣጥና ምልመላ ብቸኛ ምክንያት መሆኑን ፍርጥርጥ አድርጎ ወያኔ ነገረን:: በፓርላማው ፊትም ወያኔ ሀላፊነት ወሰደ::

ቀደም ሲልም የወያኔ ጸረ ሙሰና ግብረ ሃይል ባደረገው ማጣራት የኢትዮጵያ የመንግስት ተቆማት በሙስና መዘፈቃቸውን

ማረጋገጡ ተነግሮናል:: በዚህ አላበቃም ለሙስናው መስፋፋት ዋናው ምክንያት የወያኔ አመራር በሙስና መዘፈቁ  በመሆኑ

ወያኔ በሌሎች ላይ ጣቱን መቀሰር እንደሌለበት አዉቆ ሃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን ወያኔ ራሱ ነግሮናል።መፍትሄውም የወያኔ ከፍተኛ አመራር ባለስልጣናት የዘረጉትን የሙስና ኔትዎርክ መበጣጠስ አንደሆነ ወያኔ ጨምሮ ነገረን::  አንዳዶቻችን አመንን:: አንዳንዶቻችን ተጠራጠርን:: ያልጠረጠረ ተመነጠረ ሆነ::

የሆነው አንዲህ ነው::

እያንዳንዱ የወያኔ ሰራ አሰፈጻሚ የዘረጋው ወዋቅር የአደባባይ ሚስጥር ሆነ። ወያኔ በሙስና መዘፈቁን ህዝቡ አንደሚያውቅ: ወያኔ አወቀ::  ወያኔ ህዝቡ ማወቁን ሲያውቅ ግድ አልሰጠውም። ሰው በተናጠል በየቤቱ ቢነጋገር ወያኔ ግድ አልነበረውም:: አይነ ደረቅ ሰለሆነ:: ህዝቡ በአደባባይ መወያየት ሲጀምር ወያኔ ልቡ ራደ::በሀይል ወደ አደባባይ ሳይወጡብኝ መቅደም አለብኝ አለ:: መላ ፈለገ:: አገኘ። ሀላፊነት በአደባባይ መውሰድ:: ወያኔ ማንን ፈርቶ::

የመንግስት ሥራ የተለያየ መሆኑ ለማንም አይነገርም:: ጥፋትም የተለያየ ነው:: የመንግስት ባለስልጣን ለሰራው ጥፋት ሀላፊነት ሲወስድ የሚያስመሰግነው ነው:: ቅጣት የሌለው ሀላፊነት ግን የለም:: የቅጣቱም መጠን የተለያየ ነው::አንዳንዱ ሀላፊነት በይቅርታ የሚታለፍ ሊሆን ይችላል:: ይኽም ይቅርታ ጠያቂው በግልጽ ይቅርታ ሲጠይቅና ይቅርታ አድራጊው በግልጽ ይቅርታ ሲያደርግ ነው::

በሌሎች ሀገሮች የመንግስት ባለስልጣናት ሀላፊነት ሲወስዱ በፈጸሙት ጥፋት አይነትና መጠን የሚያስከትለውን ቅጣት ይቀበላሉ:: የተፈጸው ጥፋት ከፍ ያለ ጉዳት ካደረሰ  ደግሞ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ይለቃሉ::

አሽባሪዎችም ለሰሩት ጥፋት ሀላፊነት ሲወስዱ በተደጋጋሚ ሰምተናል:: ሀላፊነት ሲወስዱ ከምር ነው:: በፈጸምነው ግድያ ሌላ ማንም አንዳይጠየቅ ማለታቸው ነው:: የፈጸምነው ጥፋት በስቅላት የሚያስቀጣ ከሆነ በስቅላት የምንቀጣው አኛ ነን ማለታቸው ነው::

ወያኔ በሀገሪቱ የተንሰራፋው የሙስና ወዋቅር የራሱ የባለሰልጣናቱ ወዋቅር ለመሆኑ ሀላፊነት ወሰዶ ሲያበቃ: ወዲያው ወያኔ ከሌለ ፀሀይም የለ ዝናብም የለ ወደሚለው ዘፈኑ ተመለሰ::

በዚህ መች አበቃ:: በኦሮሚያ አንደ ሰደድ አሳት የተቀጣጠለውን የህዝብ አምቢተኛነት ወያኔ ባልታጠቁ ተማሪዎች አናቶች አባቶች ላይ የጥይት  ዝናብ በማዝነብ ምድሪቱን የደም መሬት አድርጎ ሲያበቃ ወያኔ ይቅርታ ጠይቆ ለራሱ ይቅርታ አደረገ:: ይባስ ብሎ ተበዳዮችን አሰረ:: ከሰሰ::

ይኽንን የ አንበሳ ቀዳዳ ተከትለው የወያኔ ሚኒስትሮች የሀገር ሃበትና ንበረት ካወደሙ በሆላ በ ፓርላማ ፊት አየቀረቡ ኃላፊነት ወስጃለሁ አያሉ ለጀግኝነታቸው አየተጨበጨላቸው ነው:: በሹመት ላይ ሹመት አየተጨረላቸው ነው:: ከአንዱ የስልጣን ቦታ ወደ ሌላ የሰልጣን ቦታ አየተቀየረላቸው ነው:: አባይ ፀሀዬን የስኮር ፕሮጀክቱን መሪ ልብ በሉ: የፕሮጀክቱን ስራ እየበደለ የግድያና የአፈና ስትራተጂ ሲነድፍ የቆየውን: በሰልጣንም ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ የተሾመውን: ደብረፅዮን ገብረምካኤልን ተመልከቱ ሀገሪቱን የኢንተርኔት ጭራ አድርጎ ሲያበቃ: ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ የተሾመውን: አርከበ አቁባይን ተመልከቱ የአዲስ አበባን መሬት ለወያኔ ካድሬዎች ቅርጫ አድሮጎ ሲያበቃ: ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ የተሾመውን::

ታሪክ ፀሀፊውም እየፃፈ ነው::   ዛሬ ደግሞ ወያኔ ትልቁ አሳ የሚበላው ስለ አጣ  ትንንሾቹን አሳዎች ሊበላ አፉን ከፍቶአል:: መዝፈኑንም ቀጥሎል:: ህዝቦቿ ደግሞ ኢትዮጵያ ከወያኔ በፊት ነበረች ያለወያኔም ትኖራለች አያሉ ለወዳጅም ለጠላትም  አንቅጩን አየተናገሩ በአንባ ፈጣሪያቸውን አየተማፀኑ ነው:: ፍርዱም አይዘገይም::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s