ፍሪደም ሃውስ ኢትዮጵያና ኤርትራን የጋዜጠኞች ወህኒ ቤት ብሏቸዋል

 

(ሳተናው) ዋና ጽ/ቤቱን በአሜሪካ ያደረገው ፍሪደም ሃውስ ባወጣው ሪፖርት ሁለቱን የምስራቅ አፍሪካ አገራት ኢትዮጵያና ኤርትራን ከሰብ ሰሃራን አገራት መካከል ዋነኞቹ የጋዜጠኞች እስር ቤት በማለት ሰይሟቸዋል፡፡

Eskinder-Nega-ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ የተወሰኑ ጋዜጠኞችንና ጦማሪያንን ከእስር ብትፈታም ሪፖርቱ ከኤርትራ በመቀጠል ዋነኛዋ ጋዜጠኞችን አሳሪ አገር በማለት ፈርጇታል፡፡

ሪፖርቱ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ አካባቢዎች የሚገኙ ጋዜጠኞች ባለፈው ዓመት የፖለቲካ ጫናዎች ተደርጎባቸዋል ብሏል፡፡

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር የብሩንዲው ፕሬዘዳንት ህገ መንግስቱን በማሻሻል ለሶስተኛ ጊዜ ለምርጫ እንደሚቀርቡ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነጻ የነበሩ የህትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ተዘግተዋል ወይም እንዲጠፉ ተደርገዋል በማለት ጠቅሷል፡፡

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በምስራቅ አፍሪካ በ2016 መጀመሪያ በኡጋንዳ በተካሄደው ምርጫ ጋዜጠኞች ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ሽፋን በመስጠታቸው ከፍተኛ አድልኦ ተደርጎባቸዋል፡፡በኬንያ ገዳቢ ህጎችን በሚዲያው ላይ ከማውጣት አንስቶ ስልታዊ የሆኑ ጫናዎች በጋዜጠኞች ላይ መደረጉን አጋልጧል፡፡

በፍሪደም ሃውስ ማውጫ መሰረትም ኢትዮጵያ፣ኤርትሪያ፣ሱዳን፣ደቡብ ሱዳን፣ሶማሊያና ጂቡቲ ከሌሎች 20 የአፍሪካ አገራት ጋር ነጻ ሚዲያ የሌለባቸው ተብለው ተቀምጠዋል፡፡

እንደ ሪፖርቱ ከሆነም ያለፈው ዓመት ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት በ12 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እጅግ ዝቅተኛ ነጥብ የተመዘገበበት በመሆን ተጠናቅቋል፡፡

በ2007 ሱዳንና ግብጽ ከፍተኛ የሆነ ማሽቆልቆል የተመዘገበባቸው አገሮች በመሆን ተመዝግበዋል፡፡

ሪፖርቱ ከአለማችን ህዝብ 41% በአንጻራዊነት ነጻ ሚዲያን የሚያገኝ ሲሆን 46% የሚሆነው ደግሞ ነጻ ሚዲያ በሌለበት ከባቢ ውስጥ ይኖራል ብሏል፡፡

ምንጭ ፍሪደም ሃውስ

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: