የዘንድሮዋ ግንቦት 20 – እስክንድር ነጋ ፤ የሕሊና እስረኛ (ከቃሊቲ)

Eskinder-Nega

ይኸው የወርሃ ሚያዝያ 2008ን የመጀምሪያ ሳምንት አገባደድን:: ግንቦት ተንደርድሮ እየመጣ ነው:: ኢሕአዴግ ሥልጣን የያዘበትን 25ኛ ዓመት ለማክበር ደፋ ቀና ማለት ጀምሯል:: ሩብ ምዕተ ዓመታትን በታላቁ ቤተመንግስት ማሳለፍ ቀላል አይደለም:: የአንድ ትውልድ ዕድሜ ነው:: እንኳን በተማሪዎች አብራክ ውስጥ ለተወለደ ድርጅት ይቅርና፣ በነባሮቹ የኢትዮጵያ ነገሥታት ሚዛንም ረዥም የሥልጣን ዕድሜ ነው:: ሥልጣን ላይ ለረዥም ጊዜ መቆይታቸውን እንደጀብድ ለሚቆጥሩት የኢሕአዴግ ነባር መሪዎች፣ የዘንድሮዋ ግንቦት 20 በተለየ ሁኔታ ጮቤ የሚረገጥባት ናት::

ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ትሩፋት ነው:: ንቅናቄው ከውልደት እስከ ህልፈቱ ከ1953 – 1966 – 13 ዓመታትን አስቆጥሯል:: ከ1966ቱ አብዮት በኋላ፣ የአባላቱ ብርቱ ሕልም ፍሬ አፍርቶ ወደ ተደራጀ የፖለቲካ ትግል ቢያድግም፣ በአንድ ጥላ ሥር ሊያስገባቸው የሚችል መሪ ድርጅት Vanguard Party የሚሉትን መፍጠር ባለመቻሉ ተማሪዎቹ ወደ ተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደጨው ተበትነዋል:: በትህምርት ቤት የነበራቸው መፈቃቀር፣ መተሳሰብ፣ በቅንነትና ተስፋ የውሃ ሽታ ሆኖ፣ ወደ መወነጃጀሉ ፣ ወደ መከፋፈሉ፣ ወደ መካካዱ፣ ወደ መቀኛነቱ፣ ወደ ክፋቱና ወደ መጠፋፋቱ ዓለም ጭው ብለው ገብተዋል::

1

2 001

2

4

5

6 (1)ይህ ሂደት ብልጭ ድርግም እያሉ የኖሩ በርካታ የፖለቲካ ቃላትን አፍርቷል::: አብዮት፣ ኢምፔሪሊያዝም፣ ፊውዳሊዝም፣ ተራማጅ፣ አድሃሪ፣ በዝባዥ፣ ጨቋኝ ፣ ፋሺስት፣ አናርኪስት፣ ጠባብ፣ ትምክህት፣ አምባገነን፣ ዴሞክራሲ፣ ገንጣይ፣ አስገንጣይ፣ አክራሪ፣ ለዘብተኛ፣ ጽኑ፣ ወላዋይ፣ ሐቀኛ፣ አስመሳይ፣ ጀግና፣ ባንዳ፣ ታማኝ፣ ከሃዲ፣ ሃገር ወዳድ፣ ቅጥረኛ፣ ታጋይ፣ ነፍጠኛ፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ ሊብራል ዲሞክራሲ፣ ቦናፖርቲስት፣ ተንበርካኪ፣ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝቦች፣ ወዘተ::

እነዚህ ቃላት የሚጋሩን የአፍሪቃ ሃገራት ማግኘት በእጅጉ ይከብዳል:: ኢትዮጵያ እንደሃይማኖቶቿ፣ እንደ ምግቦቿ፣ እንደ አላብስቶቿ፣ እንደዜማዎቿ፣ እንደነሥነጽሁፏ፣ እንደ ስዕሎቿ፣ እንደ ታሪኳ፣ እንደ መሬት አቀማመጧ ሁሉ በፖለቲካውም ልዩ ናት::

እንዲህ ዓይነቱን የተለየ ማንነት አሜሪካውያን ኤክሴፕሽናሊዝም (exceptional-ism) ይሉታል:: በብዙ መመዘኛዎች አሜሪካ ኤክሴፕሽናል ናት ብለው ያምናሉ:: በዚህ እሳቤ እስከ ሁለተኛው ዓለም ጦርነት ድረስ ራሳቸውን ከዓለም ፖለቲካ አግልለው ኖረዋል:: በአውሮፓ እንግሊዞች፣ በኤሺያ ጃፓኖች፣ በመካከለኛው ምስራቅ ኢራኖች፣ ይህን ስሜት ይጋሩታል:: በላቲን አሜሪካ “ኤክሴፕሽናል ነኝ” የሚል ሃገር ስለመኖሩ አላውቅም:: ዓለም ላይ ካሉት 200 ሃገራት መካከል በዚህ ምድብ ሊካተቱ የሚሉት ከአስር ቢያንሱ እንጂ አይበልጡም:: ለጥሩም ሆነ ለመጥፎ፣ ስብሰቡ የጥቂቶች ነው::

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄም ከሃገሪቱ ታሪክ ባልተለየ መልኩ ልዩ የሚያደርጉት ገጽታዎች አሉት:: “ሙሉ ለሙሉ የተለየ ነበር” ማለት ግን አይቻልም:: ይህን መንታ ባህሪ “በ66ቱ አብዮት ላይ ጥሩ መጽሐፍ ነው” የሚባለው የጆን ማርካኪስ (John Markakis) – አናቶሚ ኦፍ ኤ ትራዴሽናል ፖሊቲ ( Anatomy of a Traditional Polity) ውስጥ ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል::

ንቅናቄዎን ልዩ ከማያደርጉት ባህሪያቱ መካከል፣ በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በብዙ ሃገራትም የተማሪዎች እንቅስቃሴ የነበረ መሆኑ አንዱ ነው:: በሌላ አነጋገር፣ የተማሪዎች ንቅናቄ የዘመኑ ፋሽን ነበር:: ጆን ማርካኪስ እንዲህ ያስቀምጡታል::
“Radical student agitation was a hallmark of the 1960s in all non-communist Countries Ethiopia Students, eager to imitate western models, naturally became engaged”
“በ1960ዎቹ ( እ.ኤ.አ) ኮሚኒስት ባልነበሩት ሃገራት የተጋጋለ የተማሪዎች ንቅናቄ የዘመኑ መለያ ነበር:: ይህ የምዕራባዊያንን ፈለግ ለመከከተል ጉጉት የነበራቸው የኢትዮጵያ ተማሪዎች የራሳቸውን ንቅናቄ አቀጣጥለዋል” (በcontext የተተረጎመ ነው::)

ልዩ ከሚያደርጉት መካከል ደግሞ ሦስት ባህሪያቱን ማንሳት ይቻላል:: በቀዳሚነት ተማሪዎቹ ለሥልጣንና ለሹመት የነበራቸው ከፍተኛ ጉጉት ይገኛል:: ይህ ጥማት በምዕራዊያኑ ተማሪዎች ዘንድ አልነበረም:: ማርካኪስ እንዲህ ያስቀመጡታል:-

“The First Ethiopians who came back with degrees from abroad had become ministers and ambassadors. Students felt entitled to advance as rapidly. Law and Humanities courses were overflowing. Engineering and since were less appealing. Many students disdained and avoided teaching or other forms of social service in the province.”
“ከውጭ ሃገራት ድግሪ ይዘው ወደ ሃገራቸው የተመለሱት የመጀመሪዎቹ ኢትዮጵያውያን ሚኒስተሮችና አምባሳደሮች ሆነዋል:: (እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ የነበሩት) ተማሪዎችም “በዚያው ፍጥነት የማደግ መብት አለን” የሚል ስሜት ነበራቸው:: (በተማሪዎቹ ዘንድ) ምህንድስናና ሳይንስ ብዙም ተፈላጊ አልነበሩም:: ወደ ክፍለሃገር ሄዶ ማስተማርም ሆነ ማህበራዊ አገልግሎት መስጠትን ይጠሉና ይሸሹ ነበር::”

በዚያ ዘመን የነበረው ቢሮክራሲ ግን፣ እንኳን ሚኒስትርና አምባሳደር ሊያደርጋቸው ቀርቶ ፣ የተመረቁትን ሁሉ ተቀብሎ ሥራ ለመስጠት እየተንገዳገደ ነበር:: የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ፣ “ከምረቃ በኋላ ሥራ እናጣለን” ብለው የሰጉ ተማሪዎች ንቁ ተሳትፎ ያደረጉበት ነበር:: ተማሪው ለሃገርና ለሕዝብ ብቻ ብሎ አልተነሳም::: ከኢትዮጵያ ሌላ ለየትኛውም ሃገር ንቅናቄ ይህን ማለት አይቻልም::

ማርካኪስ፣ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የነበረውን ነፃነት ለንቅናቄው መወለድና ማበብ እንደ አበይት ምክንያት ያስቀምጡታል:: ይህም የኢትዮጵያን ተማሪዎች ንቅናቄ ልዩ ከሚያደርጉት – በሦስተኛ ዓለም ከነበሩት – ገጽታዎቹ አንዱ ነበር::

ማርካኪስ እንዲህ ብለዋል:-

“With the university, the students succeeded in joining almost complete freedom of expression, and their publications launched quite uninhibited attacks on the regime although they refrain from attacking the person of the emperor”

“ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ሃሳብን በነጽሳነት የመግለጽን መብት ከሞላ ጎደል ሙሉ ለሙሉ ለማስከበር ችለዋል:: ሕትመቶቻቸውን የአጼውን ስብዕና ከማጥቃት ቢቆጠቡም መንግስትን ግን ያለምንም ፍርሃት ይተቹ ነበር” ((በcontext የተተረጎመ)

የተማሪዎቹን ቀልብ በዋናነት የሳበው ግን፣ ወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አልሆነም:: ወሳኝ የሆኑትን የሃገራቸውን ታሪክ፣ ፖለቲካና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አልሆነም:: ወሳኝ የሆኑትን የሃገራቸውን ታሪክ፣ ፖለቲካና ኢኮኖሚ በሁለተኛ ደረጃ አስቀምተው ማርክሲም ላይ አተኩረዋል:: ይህ ሲሆን መንግስት ጣልጋ አልገባባቸውም:: በዚህ ሳቢያ ማርክሲዝም በአደባባይ ከተሰበከባቸው ጥቂት የአፍሪካ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ለመሆን በቅታለች:: ይህ እውነታ የተማሪውን ንቅናቄ የአጼው መንግስት የአካዳሚ ነፃነት ውጤት ያደርገዋል:

በሦስተኝነት፣ የኢትዮጵያን ተማሪዎች ንቅናቄ ልዩ ከሚያደርጉት ባህሪያቱ መካከል የአባላቱ ድህነት ጉልህ ስፍራ ይሰጠዋል:: ይህ ክፍተት ንቅናቄው የግድ የውጭ ኃይሎች፣ ጥገኛ አድርጎታል:: የንቅናቄው አድማስ ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ውጥቶ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲዛመት፣ ከተማሪዎች በሚሰብሰብ መዋጮ የተደራረበውን ወጪ የሚሸፈንበት ሁኔታ አልነበረም:: በዚህ ክፍተት፣ በዘመኑ ከነበሩት ሁለት ልዕለ ኃያላን መካከል አንዷ የነበረችው ማርክሲሥቷ ሶቭየት ኅብረት ተማሪዎቹን ስኳር ታልሳቸው እንደነበር ማርካኪስ ጽፈዋል::

“After Haile Selassie expelled several soviet and East European embassy officers in 1968 and 1969 for subversive contacts with students, Moscow refined its techniques. It was less risky to work with Ethiopian students abroad. Hence forth, money, propaganda and advice for student’s agitation in Ethiopia came in large part through Marxist- dominated Ethiopia student organizations in Europe and America. Under the guise of supporting literacy campaigns and welfare projects, these organizations sent far larger sums of money than they would conceivably have collected on their won to their counter parts in Addis Ababa’

“እ.ኤ.አ በ1968 እና በ1964 የሶቭየትና የምሥራቅ አውሮፓ ዲፕሎማቶች ‘ከተማሪዎች ጋር ሕገ-ወጥ ግንኙነት አድርጋችኋል’ ተብለው ከተባረሩ በኋላ፣ ሞስኮ ስልቷን ቀየረች:: ውጭ ካሉት ተማሪዎች ጋር መሥራቱ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ተገኘ:: ከዚህ በኋላ ሃገር ውስጥ ለነበረው የተማሪዎች ንቅናቄኤ የሚሰጠው የገንዘብ፣ የፕሮፓጋንዳና የምክር ድጋፍ፣ ማርክሲስቶች በሚመሯቸውና በአውሮፓና በአሜሪካ በነበሩ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበራት በኩል እንዲላክ ተደረገ:: እነዚህ ማህበራት ለመሰረተ ትምህርትና ለማህበራዊ ዋስትና ድጋፍ እንሰጣለን’ በሚል ሽፋን ከአባላቶቻቸው ሊያሰባስቡት ከሚችሉት በላይ ገንዘብ ወደ አዲስ አበባ ልከዋል::”

ይህ ሁሉ በጥቂት ተማሪዎች ፈቃድ የተፈጸመ ሲሆን በእኔ ግምት በክሮኮዳይሎች crocodiles ብዙሃኑ ተማሪዎች እስከአሁን ድረስ ምን እንደተደረገ አያውቁም:: ይህ መረጃ ጨለማ፣ በብዙሃኑ ተማሪ በጭፍን ይከተላቸው የነበሩትን የንቅናቄው መሪዎች፣ ማርክሲዝምን የተቀበሉት ለገንዘብ ብለው ነበር ወይ? የሚል ጥያቄ እንዳስነሳ ያስገድደኛል:: የተማሪው ንቅናቄ ከከሰመ በኋላ እንደታየው፣ በመሪዎቹም ሆነ በብዙሃኑ ተማሪ ዘንድ፣ ማርክሲዝም ቅብ ነበር እንጂ ውስጣቸው ሰርጾ የገባ እምነት አልነበረም::

ፈረንጆች “…with the benefit of hindsight…” የሚሉት ነገር አላቸው:: “ግዜው ካለፈ በኋላ በአንክሮ ሲታይ” እንደማለት ነው:: የተማሪው ንቅናቄ በዚህ ዓይነቱ መነጽር ሲቃኝ የውጭ ኃይሎች መሣሪያ መሆኑ ብዙም አያስደንቅም:: የገንዘብ ብቻ ሳይሆን የታሪክም ደሃ ነበርና:: ጥራዝ ነጠቅ ማርክሲዝምን በተላበሰው ንቅናቄ ዘንድ፣ ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ኃይማኖት የመሳሰሉ ነገሮች በመደብ የተከፋፈለ ማህበረሰብ ኋላቀር ቅሪቶች ናቸው ተብለው በመፈረጃቸው በንቀት የሚታዩ ነበሩ:: ለኢትዮጵያ የተለየ ታሪክና ማንነት ቦታ አልነበረውም::

በዚህ ሳቢያ፣ ስለ1984ቱ “ፓሪስ ኮሚውን” (የፓሪስ አመጽ) መወያየትና መከራከር ይወዱ የነበሩት የተማሪው ንቅናቄ አባላት – ልክ የዛሬ ዘመን ወጣቶች ስለ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በአንክሮ እንደሚከራከሩት – እንኳን የጥንቱን የኢትዮጵያ ታሪክ ይቅርና፣ በፓሪስ ኮሚውን የቅርብ ርቀት (እ.ኤ.አ በ1860ዎቹ) የእንግሊዝ ጦር በኢትዮጵያ ላይ ስለፈጸመው ወረራና ስላስከተለው እንደምታ ምንም እውቀት ሳይቀራምቱና ሳይመጋገቡ ቀርተዋል::

ተማሪዎች በዚህ መልክ እስከ 1966 ድረስ ከቀጠሉ በኋላ፣ በአብዮቱ ፍንዳታ ማግስት ያቋቋሟቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ወስደዋቸዋል:: ህብረብሄራዊ ድርጅቶች ያቋቋሙትም ማክርሲዝም ላይ ተቸክለው በመቅረታቸው መንግስታዊ ጭቆናን እስከመጨረሻው ድረስ መቋቋም የሚችሉ አባላትን ማፍራት ሳይችሉ ቀርተዋል:: እነ ኢሕ አፓና መኢሶን በደርግ ጭፍጨፋና አፈና ብቻ አልጠፉም:: በማርክሲዝም ብቻ የታነጹት አባሎቻቸው፣ በድንጋያማ መሬት ላይ እንደወደቀ ዛፍ፣ ጸሃይ ሲበረታባቸው – በመከራ ጊዜ – በቀላሉ ደርቀዋል:: በአንጻሩ፣ የብሄር ድርጅቶች ያቋቋሙት ተማሪዎች – የኤርትራ፣ የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የሲዳማ፣ ወዘተ – ሃገራዊውን ታሪክ ከማርክሲዝም ያልተናነሰ ቦታ በመስጠታቸው፣ ብርቱ መከራን መቋቋም የሚችሉ አባላትን አፍርተው – በተለይ የኤርትራና የትግራዮቹ – ደርግን ለመጣል በቅተዋል:: የሕብረብሄራዊ ድርጅቶች ማርክሲስቶች እንደተመኙት፣ ታሪክን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ነቅሎ ማውጣት አልተቻለም::

ተማሪዎቹ እንቅስቃሴያቸውን ከጀመሩ 55 ዓመታት በኋላም ከ1953 – 2003 የዮሐንስና የምኒልክ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ፖለቲካ የፈጠረው ሽኩቻ፣ የኢሕአዴግ ቅኝት ጸረ-ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ምክንያት ከሆኑት ግብአቶች መካከል አንዱ ሆኖ ይገኛል:: የታሪክ ጣጣ የኦሮሞና የተማሪ ብሄረተኞችን ነፍስ እረፍት እንደነሳ ነው:: የታሪክን ህጸጾች የማይቀበሉ ቀላል የማይባል የፖለቲካ ኃይልም አለ:: ይህ ሁሉ ተደማምሮ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተጋረጠ አደጋ ነው:: መፍትሄው ከአዲሱ ዘመን ዴሞክራቶች ይጠበቃል::

እስክንድር ነጋ፣
የሕሊና እስረኛ፣
ቃሊቲ::

(የጋዜጠኛ እስክንድርን የእጅ ጽሁፍ በኮምፒተር የለቀመው ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ ነው)

አንድነት፤ አንድነት ስንል ከአራባ ዓመታት በላይ አሳልፈናል —–ፈቃደኛነት ካለ ለመተባበር ይቻላል (አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

እኛ ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ ቆመናል የምንለው ሁሉ አንድነት፤ አንድነት፤ ህብረት፤ ህብረት ስንል ከአርባ ዓመታት በላይ አሳልፈናል። አንድም ውጤት አላስገኘነም። የፖለቲካ ባህላችን ድርጅትን ፈጥሮ መከፋፈል፤ ማጥፋት፤ መተካትና መጠላለፍ እየሆነ አንዱ ሌላውን በመተቸት ሁለት ትውልዶች አልፈው ሶስተኛውን ጀምረናል። ይህ በአንድ በኩል ተስፋ ሰጭ፤ በሌላ በኩል አድካሚ የፖለቲካ፤ የማህበረሰብና የመነፈስ ባህርይ የጀመረው በንጉሱ ዘመነ መንግሥት በተማሪዎች እንቅስቃሴ ነው። በዚያ ወቅት የነበረው ትውልድ ከራሱ በላይ ለአገሩና ለወገኖቹ የሚያስብ ነበር ለማለት እደፍራለሁ። የአሁኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይተቸው። የብሄረሰብ ፖለቲካም መሰረት የያዘው በዚያ በእኔ ትውልድ አካባቢ ነው። በተከታታይነቱ ሲታይ፤ የኢትዮጵያ ምሁራንና ልሂቃን ባህል ሁለት ወሳኝ የሆኑ ገጽታዎች አሉት። –— [ሙሉውንለማንበብ እዚህ ይጫኑ}

መንድሜ፣ እስክንድር (አይበገሬው) ነጋ፡ ብቻህን አይደለህም እናም እንወድሀለን!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ወንድማችንን እስክንድር ነጋን እናስታውስ፣

Eskinder Nega 1ዘ-ህወሀት (የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ) ታላቁ እስክንድር ነጋ ከሕዝብ ትውስታ እና ህሊና ተፍቆ እና ጠፍቶ ከማየት በላይ የሚወደው ነገር የለም፡፡ ዘ-ህወሀት ዓለም እስክንድር ነጋን እንዲረሳው ይፈልጋል፡፡ የእርሱ ትዝታ እየደበዘዘ ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ ይፈልጋሉ፡፡ እርሱ መታወስ ያለበት ከሆነ ደግሞ የዓለም ሕዝብ እርሱን በአሸባሪነት ማስታወስ እንደሚኖርበት ይፈልጋሉ፡፡

የእስክንድር ጉዳይ እ.ኤ.አ በ1964 በደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች ዘረኛ የበላይ አገዛዝ አፓርታይድ ኔልሰን ማንዴላን አሸባሪ በማለት በሀሰት በመወንጀል የእድሜ ልክ እስራት በመበየን ወደ ሮቢን ደሴት የማጎሪያ እስር ቤት ወስደው ዘብጥያ ካወረዷቸው ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ ማንዴላ ከ27 ዓመታት የአፓርታይድ የእስራት ጊዜ በኋላ ከማጎሪያው እስር ቤት በመውጣት ደቡብ አፍሪካን ከመጥፎ አደጋ አድነዋታል፡፡

አናሳው የደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች የበላይነት አገዛዝ አፓርታይድ ማንዴላን ከሕዝብ ትውስታ ሰውሮ በማቆየት ጥረቱ ላይ ስኬታማ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ዘ-ህወሀትም በተመሳሳይ መልኩ እስክንድር ነጋን ከሕዝብ ትውስታ ለማጥፋት ከቶውንም አይችልም፡፡ እስክንድር ነጋ ከማጎሪያው እስር ቤት ይወጣል፣ ወዲያውኑም የእርሱን ቦታ አሳሪዎቹ ተክተው ይወስዳሉ፡፡

የእስክንድር ነጋ ምስል፣ ጽሑፎች እና ሌሎች የትችት ስራዎቹ እና በረከቶቹ ሁሉ በማህበራዊ ሜዲያዎች እና በበርካታ ድረ ገጾች ታላቅ ክብር ባላቸው ዓለም አቀፍ የፕሬስ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጭምር ይወጣል፡፡ ከሳምንት በፊት አንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት የእስክንድር እስራት በሕገወጥ መልኩ እና በዘ-ህወሀት አጭበርባሪነት መሆኑን ገልጾ  በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የእስክንድር ነጋ ምስል በማህበራዊ ድረ ገጼ አናት ላይ ይገኛል፡፡ በእኔ ማህበራዊ ድረ ገጽ (https://www.facebook.com/al.mariam) እኔን የማይመስል ምስል እንዳለ ሰው ሳይጠይቀኝ የዋለበት ጊዜ የለም፡፡ አትጨነቁ እያልኩ እንደህ በማለት እነግራቸዋለሁ፡፡ “ያ የወንድሜ የእስክንድር ነጋ ምስል ነው!”

አንባቢዎቼ ጥቂት ውለታዎችን እንድታደርጉልኝ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡

ይህንን ትችት ከማንበባችሁ በፊት የእስክንድርን የእጅ ጽሑፍ እና የዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር እየተባለ ከሚጠራው እስር ቤት ቤት የተጻፈውን ደብዳቤ እንድታነቡት እጠይቃለሁ፡፡ (ይህንን ደብዳቤ ለማንበብ በእንግሊዘኛ  እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡)

(**የእስክንድርን የእጅ ጽሑፍ ደብዳቤ በማያቋርጥ መልኩ በዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር ቤት ዘበኞች እና ሰላዮች ክትትል ስር ሆኖ ይህንን የመሰለውን ጠንካራ ሀሳቡን ለመግለጽ ባደረገው ልዩ የሆነ ጥረት ምክንያት የኮምፒውተር የፊደላት መክተቢያ ቆልፎችን ሳንጠቀም ለክብሩ ስንል እንዳለ አቅርበነዋል፡፡)

ከዚህም በተጨማሪ በዋሺንግተን ፖስት ጋዜጠኛ በካርል በርነስተይን (እ.ኤ.አ ነሐሴ1974 የዋተርጌትን ቅሌት ያጋለጠው እና ፕሬዚዳንት ሪቻርድ ኒክሰንን ከስልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ያደረጋቸው እና በዓለም ላይ ታላቅ እውቅና ያለው ጋዜጠኛ) እና ሌቭ ሽሬበር (እ.ኤ.አ የ2016 የኦስካር ምርጥ ስዕሎች አሸናፊ የሆነው እና የተከበረ ዳይሬክተር፣ ያዘጋጁትን ተንቀሳቃሽ ፊልም አንባቢዎቼ እንዲመለከቱት እጠይቃለሁ፡፡

(የቪዲዮ ምስሉን ለመመልከት እዚህ ጋ ይጫኑ ፡፡ ካርል በርንስተይን እና ሌቭ ሽሬበር አሸባሪን ለመከላከል ብለው እንደዚህ ያለ በፍቅር የተሞላ መሳጭ ንግግር ያደርጋሉን?) 

ከሁሉም በላይ ደግሞ በእስክንድር ነጋ ላይ በባለቤቱ በሰርካለም ፋሲል (እርሷም የተከበረ የጋዜጠኝነት ሽልማት አሸናፊ ኢትዮጵያዊት ጋዜጠኛ እና ለመብቷ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ለፕሬስ ነጻነት መከላከል ከባለቤቷ ጋር ታስራ የነበረችው) አማካይነት (በእንግሊዝኛ ንኡስ ርዕሶች) የተዘጋጀውን እና ልብ የሚሰብረውን የ3 ደቂቃ የቪዲዮ ፊልም አንባቢዎቼ እንዲመለከቱት እጠይቃለሁ፡፡ (የቪዲዮኑን ፊልም  እዚህ ጋ በመጫን  መመልከት ይችላሉ፡፡)

ሰርካለም ልጇን ናፍቆትን በዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር ቤት እ.ኤ.አ በ2007 ተገላግላለች፡፡

Amnesty 4እስክንድርን ወንድሜ ብዬ ስጠራ እና ሰርካለምን እህቴ ብዬ ስጠራ ኩራት ይሰማኛል፡፡ በእነርሱ መስዋዕትነት፣ በእነርሱ ድፍረት፣ ጽናት እና አይበገሬ ታማኝነት እና በእነርሱ ግላዊ አርአያነት እራሴን ዝቅ አድርጌ እመለከታለሁ፡፡

እስክንድር ነጋ እና ሰርካለም ለኢትዮጵያ ምርጦች እና ባለብሩህ አእምሮ ጋዜጠኞች፣ ለሰላማዊ አማጺዎች፣ በዘ-ህወሀት ግልጽ እና ድብቅ የማጎሪያ እስር ቤቶች ውስጥ በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት የፖለቲካ እና የሲቪክ ማህበረሰብ መሪዎች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አርአያ እና ቀንዲል ናቸው፡፡ እስክንድር ነጋን በማስብበት ጊዜ በቀለ ገርባን፣ አህመዲን ጀቤልን፣ ውብሸት ታዬን፣ ተመስገን ደሳለኝን፣ አንዷለም አራጌን፣ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ እማዋይሽ ዓለሙን፣ ዴልዴሳ ዋቆ ጃርሶን፣ አኬሎ አቆይ ኡቹላን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማርያንን እና በሺዎች የሚቆጠሩትን የሌሎችን የፖለቲካ እስረኞችንም በተጨማሪ አስባለሁ፡፡

እስክንድር ነጋን በምናስብበት ጊዜ ሁሉንም በሙሉ እናስታውሳለን!

የእስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ሂደት እና ስቃይ፣

እስክንድር ነጋ ልዩ የሆነ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ እና በኢትዮጵያ ጽኑ የፕሬስ ነጻነት ተሟጋች  ነው፡፡ እ.ኤ.አ ከ1993 ጀምሮ የዘ-ህወሀት ፍርሀት የለሽ ተቺ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ እስክንድር እና ባለቤቱ ሰርካለም በዘ-ህወሀት የተዘጉ ጋዜጦችን ማለትም ኢትዮጲስ፣ አስኳል፣ ሳተናው እና ምኒልክን ጨምሮ የተለያዩ ጋዜጦችን እያቋቋሙ መስራት ጀምረው ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 በዘ-ህወሀት በቁጥጥር ስር ውሎ ወደማጎሪያው እስር ቤት እስከገባበት ጊዜ  ድረስ እስክንድር እረፍትየለሽ በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ዘንድ ሰፊ አንባቢ ያለው ጦማሪ ነበር፡፡ ዘ-ህወሀትን በተለይም አሁን በህይወት የሌለውን መሪውን አምባገነኑን መለስ ዜናዊን ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ መጠቀምን፣ ሙስና እና የመልካም አስተዳደር እጦት ጉዳዮች ላይ ግንባሩን ሳያጥፍ ፊት ለፊት ይታገል ነበር፡፡ ዘ-ህወሀት እስክንድር ነጋን ለመቁጠር በሚያዳግት ለበርካታ ጊዚያት በሸፍጥ ውንጀላ ክስ እየመሰረተ በማጎሪያው እስር ቤት ሲያስረው ቆይቷል፡፡

ዘ-ህወሀት እስክንድርን እ.ኤ.አ በ2011 አሸባሪነት የሚል የሸፍጥ ክስ በመመስረት ወደ ማጎሪያው እስር ቤት ዘብጥያ ወረወረው፡፡ የእርሱ ወንጀል ሆኖ የተቆጠረው፣

1ኛ) በፕሬስ ነጻነት ላይ ጭቆና እያራመደ ያለውን ዘ-ህወሀትን መተቸቱ፣

2ኛ) ዜጠኞች በጅምላ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እየተደረጉ ወደ ዘብጥያ መጣልን በመቃወሙ፣

3ኛ) የዓረብ የጸደይ አብዮት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረውን እንደምታ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማወያየቱ ነበር፡፡

ዘ-ህወሀት እስክንድር የአሸባሪ ቡድን አባል ነው፣ ለውጭ ኃይሎች ሰላይ ነው፣ እናም በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የአሸባሪዎች ጥቃት ለማሳለጥ የተዘጋጀ አሸባሪ ነው በማለት በእስክንድር ላይ ስም የማጥፋት እና የማጠልሸት ያልተሳካ የፕሮፓጋንዳ ሙከራ ዘመቻውን ለማሳየት ሞከረ፡፡

አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በግል በእስክንድር ላይ ከፍተኛ የሆነ ጥላቻ እንደነበረው ታማዕኒነት ያላቸው መረጃዎች አሉኝ፡፡ መለስ እስክንድር እንደሚያደርገው በተስፋ የተሞላ ንግግር ዓይነት ማድረጉን አይደግፍም፡፡

እስክንድር ለአምባገነኑ ለመለስ ቅንጣት የምታህል ፍርሀት አያሳይም፡፡ እስክንድር ስለመለስ የፈለገውን ያህል የሚመጣ ነገር ቢኖርም ባይኖርም በእራስ መተማመን ስሜት ይናገራል፡፡

አምባገነኑ መለስ እስክንድርን ይጠላዋል ምክንያቱም ይፈራዋል፡፡ አምባገነኑ መለስ የእስክንድርን ብዕር ይፈራዋል ምክንያቱም የእስክንድር ብዕር በመለስ ላይ ያለውን ያልተቀባባውን ደረቅ እውነታ መዞ ያወጣልና፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በርካታ ነገሮችን መከላከል ይችላል፡፡ ሆኖም ግን እውነትን መከላከል ፈጥሞ አይችልም፡፡

እ.ኤ.አ በመስከረም 2010 እስክንድር እና ሰርካለም የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለሆኑት ለሊ ቦሊንገር ደብዳቤ በመጻፍ ስለአምባገነኑ መለስ ያለውን እውነታ ተናግረዋል፡፡ በዚያ ደብዳቤ እስክንድር እና ሰርካለም አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በእነርሱ ላይ በግል እና በፕሬስ ነጻነት ላይ የሰራቸውን ወንጀሎች በሙሉ ዘርዝረው አቅርበዋል፡፡ ለአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ጥሪ እንዳይደረግለት እንዲህ የሚል ተመጽዕኖ አቅርበዋል፣ “በሀገሩ የመናገር ነጻነትን በትጋት የሚደፈጥጥ መሪ የእራሱን ሀሳብ በክብር ለመግለጽ በነሐሴ ወር በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሚደረገውን ጉባኤ በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡“

እ.ኤ.አ መጋቢት 2011 “ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ” በሚል ርዕስ እስክንድር ለአምባገነኑ መለስ እውነታውን እስከ ጥርሱ ድረስ ነግሮታል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አምባገነኑ መለስ ምናልባትም ስሙን መለስ ከሀዲው በሚል በመቀየር ባታላይነቱ እና በከሀዲነቱ ለበርካታዎቹ ለዘ-ህወሀት ለታገሉ እና ለሞቱ ጓደኞቹ እንዲህ የሚል የነብይነት ከሀዲ ዕጣ ፈንታውን በትክክል ይገልጻል፡

“ማናቸውም መሪዎች [ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ ወታደራዊው ጠንካራው መንግስቱ ኃይለማርያም እናም ሌሎችም የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች] ኢትዮጵያዊ ወይም ደግሞ አሜሪካዊም ቢሆኑ መለስ ዜናዊ እንዳደረገው ሁሉ በንዴት የሚጦፉ እና ስሜታዊነት የሚያጠቃቸው እና የጓደኝነት ምግባራቸውን ሊመለስ በማይችል መልኩ ሊያቋርጡ ይችላሉ፡፡ በመለስ ዜናዊ እና በስዬ አብረሃእንዲሁም በሌሎች መካከል የጠፋው ጓደኝነት በጣም አስቸጋሪ በሆነው ጊዜ ለሶስት አስርት ዓመታት ዘልቋል፡፡ አዲስ ጓደኞች በጠፉት በሌሎች የሚሸፈነውን ክፍተት ሊሞሉ አይችሉም፡፡ ሆኖም ግን አውሪያዊ ስሜታዊነት እና ከብቸኝነት ሊመጣ የሚችለው ባህሪ ግን ትንሹ የመለስ መገለጫ ነው፡፡“

በዚያ አንቀጽ ላይ የሰፈረው እውነታ የመለስን ውስጣዊ ባህሪ እንዴት እንደሚነጣጥለው ማሰብ እችላለሁ፡፡ አምባገነኑ መለስ በቅርብ ጓደኞቹ እና በወታደራዊ ጓደኞቹ ላይ ያደረገውን ነገር የሚያውቅ እና ጸጸትም የሚሰማው ነው ይባላል፡፡ (መለስ ለተፈጸመ ስቃይ እና መከራ ምንም ዓይነት ጸጸት እና ርህራሄ አለው ብዬ አላምንም፡፡) ሆኖም ግን ጸጸት እና ርህራሄ የሚኖረው ቢሆን እንኳን እንዲህ የሚለውን የሸክስፒርን ጥልቅ የግጥም ስሜት የሚያስብ ከሆነ በጣም የሚገርመኝ ይሆናል፡ “…እራሴን አከበርኩ እናም ለዕጣ ፈንታዬ ቃል ገባሁ፣/በተስፋ አንዱ ዋና ከበርቴ ለመሆን፣/ እንደ እርሱ ለመሆን፣ እርሱ እንዳሉት ጓደኞች ለመሆን…“ አምባገነኑ መለስ ጠላት እንጅ ጓደኞች አልነበሩትም፡፡

በዚያው ደብዳቤ ላይ እስክንድር ለአምባገነኑ መለስ ወደፊት ማለቱን ትቶ ስልጣኑን እንዲለቅ እንዲህ በማለት ነግሮታል፡

“አቶ መለስ ዜናዊ፡ አንተ ከስልጣንህ እንድትወርድ እና ቢሮህን እንድትለቅ ሕዝቡ ይፈልጋል፣ ሕዝቡ አንተን አይፈልግም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህንን ደብዳቤ እየጻፍኩ ባለበት ጊዜ ህዝቡ በሰሜን አፍሪካ እየተፈጸመ ያለውን ክስተት በቅርበት በመመልከት ላይ ነው፡፡ ሕዝቡ በአፍሪካ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሚኖሩት እንደምታዎች ላይ በመከራከር ላይ ይገኛል፡፡ እናም በተራዎቹ ሊቢያውን ጀግንነት ላይ በመደመም ላይ ይገኛሉ፡፡ ጊዜው ከመምሸቱ በፊት ሕዝቡን አዳምጥ፡፡“

እ.ኤ.አ ሐምሌ 2011 የጭቆና አገዛዝ ወደ ታሪክ ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ይጣላል፣ እናም ዴሞክራሲ በዘ-ህወሀት አመድ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያብባል በማለት እስክንድር ለመለስ እንዲህ ሲል በአጽንኦ ነግሮታል፡

“ዴሞክራሲ የሰው ልጆች ሁሉ የጋራ ዕጣፈንታ ነው፡፡ ኤስኪሞ ወይም ደግሞ ዙሉ፣ ክርሰቲያን ወይም ሙስሊም፣ ነጭ ወይም ጥቁር፣ የሰለጠነ ወይም በማደግ ላይ ያለ ብትሆንም እንኳ ልታስወግደው አትችልም፡፡ በእርግጠኝነት ይኸ ጉዳይ ዓለም አቀፋዊ ክስተት ነው፡፡ እናም ከረዥም ጉዞ በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ትግል እውን ለመሆን በማዕዘኑ አካባቢ በመዞር ላይ ይገኛል፡፡ ሁላችንም በዚያ አካባቢ ነን፡፡ ነጻ እንሆናለን!“

እ.ኤ.አ ነሐሴ 2011 ነገሮች ሁሉ አሁን ባሉበት ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነ መለስ የጋዳፊን ዓይነት አስፈሪ ዕጣ ፈንታ እንደሚገጥመው እንዲህ በማለት አስጠንቅቆት ነበር፡

“የአፍሪካን ግዙፍ አምባገነናዊ አገዛዝ የሚመራው የኢትዮጵያው መለስ ዜናዊ በርካታዎቹ እንደሚጠረጥሩት በመጀመሪያ ጋዳፊ እንዳደረገው ስሌት በመስራት ጽኑ ማስታወሻ ይይዛል…እናም የዓረቡ ዓለም ታላቋ አምባገነን ግብጽ በሙባረክ የአገዛዝ ዘመን እንደሆነችው የጸደይ አብዮት ወርቃማ ሽልማት እንደሆነችው ሁሉ የሰብ ሰሀራ ታላቋ አምባገነን ኢትዮጵያም በተመሳሳይ መልኩ የአፍሪካ የጸደይ አብዮት ሽልማት ትሆናለች፡፡ ካለግብጽ የዓረቡ ዓለም የጸደይ አብዮት ሊኖር አይችልም ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ከኢትዮጵያ ውጭ የአፍሪካ የጸደይ አብዮት ሊኖር አይችልም፡፡“

እስክንድር እ.ኤ.አ መስከረም 2/2011 አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ለሰላማዊ የለውጥ ሽግግር እንቅፋት እንዳይሆን እንዲህ በማለት መክሮት ነበር፡

“ለበርካታ ዘመናት ሰላማዊ ሽግግር ባለመኖሩ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ውድቀት፣ ምናልባትም አደገኛ የሆነ የኃይል እርምጃ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ማለት የተፈለገው የነበረው ሁኔታ በነበረበት መልኩ ሊቀጥል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በኢትዮጵያ ሰላማዊ እና ሕጋዊ የለውጥ እርምጃ ለማድረግ ጥሪ የሚደረግበት ጊዜ ደርሷል፡፡ ታሪክ ላልተወሰነ ጊዜ ሊተላለፍ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም፡፡“

እ.ኤ.አ መስከረም 14/2011 እስክንድር በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

እ.ኤ.አ ሐምሌ 13/2012 እስክንድር በዘ-ህወሀት የይስሙላ የዝንጀሮው ፍርድ ቤት የ18 ዓመታት እስራት ተበየነበት፡፡

ዘ-ህወሀት በእስክንድር ላይ የአሸባሪነት ወንጀል ማስረጃ ይሆነኛል ብሎ ያቀረበው በጥራት ያልተቀዳ በአንድ በከተማ አዳራሽ ለተሰበሰበሰ ሕዝብ የዓረቡ የጸደይ አብዮት በኢትዮጵያ ላይ ስለሚኖረው እንደምታ በሚል ርዕስ እስክንድር ያቀረበውን ንግግር ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ነሐሴ 20/2012 አምባገነኑ መለስ መሞቱ ይፋ ሆነ፡፡

የኢትዮጵያ ሳቴላይት ቴሌቪዥን እ.ኤ.አ ሐምሌ 20/2012 (እ.ኢ.አ ደግሞ ሐምሌ 13 ቀን 2004) አምባገነኑ መለስ መሞቱን ይፋ አደረገ፡፡

ቅዱሳን ጽሑፎች አምላክ “ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ” ስራውን ይሰራል ይላሉ፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እስክንድርን የሚጠላው በሚያሳየው ድፍረት፣ ፍርሀትየለሽነት እና ባለው ጽናት ምክንያት ብቻ ኤደለም፡፡ ሆኖም ግን መለስ በእስክንድር ምሁራዊ ክህሎት ላይ ቅናት ያድርበት እንደነበር ጭምር ያሉኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ባለፉት አስር ዓመታት በተደጋጋሚ ስናገረው እንደቆየሁት መለስ የእራሱን ልዩ ክህሎት ተጠቅሞ እና የነገሮችን ውልመሰረት አጢኖ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶችን ማሳመን የሚችል ጎበዝ አፈ ምላጭ የውሸት ምሁር ነው፡፡ መለስ ፍሬከርስኪ ስለሆኑ እና ምንም ዓይነት እርባና ስለሌላቸው ነገሮች ብዙ የማውራት ተሰጥኦ የነበረው አጭበርበሪ ከመሆን የዘለለ ሰው አልነበረም፡፡ የቀድሞው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩትን ዶናልድ ያማማቶን እንዲህ በማለት በዊኪሊክስ በተለቀቀው መልዕክት የተታለሉ መሆናቸው ግልጽ ሆኗል፣ “በበርካታ አጋጣሚዎች መለስ ዝርዝር የሆኑ ምላሾችን በመስጠት ስለአንድ ጉዳይ አሳሳቢ ሁኔታ ያለባቸውን ቡድኖች በአንድ መስመር ላይ የማሰለፍ ችሎታ እንዳለው ተመልክተናል፡፡“ ቡድኖችን በአንድ መስመር ማሰለፍ እና በቀላሉ የሚሞኙ የምዕራብ ሀገሮች ዲፕሎማቶችን ማቅረብ የመለስ ዋናው ድብቅ ሚስጥር ነው፡፡ መለስን በሚገባ ለሚያውቁ የለየለት አታላይ መሆኑን በውል ይገነዘባሉ፡፡ እስክንድርም ይህንን ነገር አሳምሮ ያውቃል፡፡ መለስ እንደሚበሳጭ የውኃ ተርብ ዓይነት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ይቆጣል፣ ወዲያው ወዲያው በፍጥነት ይተነፍሳል እናም በላይ ያሉት የአካል ክፍሎቹ ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፡፡ ሆኖም ግን ከተቃዋሚዎቹ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ በመከራከር እና በመወያየት ተግባራት ላይ አይሰማራም፡፡

ለመሆኑ እስክንድር ነጋ ማን ነው?

እስክንድር ነጋን ለመግለጽ ቀላል እና እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ እስክንድር የኢትዮጵያ ታዋቂ ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ እስረኛ ነው፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2013 አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እስክንድር ነጋ “የህሊና እስረኛ” ነው የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ በተመሳሳይ መልኩ እስክንድር የህሊና እስረኛ ለመሆኑ እውቅና ሰጥቷል፡፡ ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የፕሬስ ድርጅቶች ተመሳሳይ የሆኑ መግለጫዎችን አውጥተዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ እስክንድር በጽናት፣ በምክንያታዊነት እና የፕሬስ ነጻነትን በመከላክል ረገድ በርካታ የሆኑ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ሽልማቶችን አሸናፊ ነው፡፡

እስክንድር ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ሁሉ እና ሌላም ተጨማሪ ነገር ነው፡፡

እስክንድር ነጋ ለእኔ ልዩ ጀግናዬ የሆነው በርካታ ጽሑፎች መጻፍ በመጀመሩ፣ የፕሬስ ነጻነትን ለማስከበር ፍርሀት የለሽ በመሆኑ፣ ወይም ደግሞ ለእርሱ የሚገባውን ዓለም አቀፍ ክብር እና ዝናን በመጎናጸፉ ምክንያት አይደለም፡፡

እስክንድር ለእኔ ልዩ ጀግናዬ ነው ምክንይቱም የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘ የነጻነት ታጋይ ነው፡፡ ለመታገል ግን ጠብመንጃ፣ ቢላዋዎችን ወይም ሽብርን አይዝም፡፡

የእርሱ ምርጡ መሳሪያዎቹ ቁራጭ እርሳስ ወይም ደግሞ ብዕር ናቸው፡፡ የእርሱ ብዕር  እውነትን ዘክዝኮ በመትፋት ዘ-ህወሀትን ሽባ የሚያደርግ እና ግራ የሚያጋባ ክስተትን መፍጠር ነው፡፡ የእርሱ ሀሳቦች ተፈጥሯዊ ኃይል አላቸው፡፡

እስክንድር ውሸትን፣ ሙስናን፣ ከሕግ አግባብ ውጭ ስልጣንን መጠቀምን እና ሕገወጥነትን በእውነት ጎራዴ በመጠቀም የሚመትር ጀግና ነው፡፡

ብዕርን ብቻ በመታጠቅ እስክንድር ጨለምተኝነትን በተስፋ፣ ፍርሀትን በድፍረት፣ ቁጣን በምክንያታዊነት፣ እብሪትን በትህትና፣ ድንቁርናን በእውቀት፣ አለመቻቻልን በትዕግስት፣ ጭቆናን በጽናት፣ ጥርጣሬን በእምነት እና ጥላቻን በፍቅር ይዋጋል፡፡

ሆኖም ግን እስክንድር በብዕር ከመዋጋትም በላይ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ እስክንድር የደፋርነት ንጉስ ነው፡፡ እስክንድር በቀልተኛ የሆኑትን የዘ-ህወሀት አውሬ ዓይኖች ከተመለከተ በኋላ እንዲህ አለ፡

“ለስምንተኛ ጊዜ በቁጥጥር ስር ልታውሉኝ እና ልታስሩኝ ትችላላችሁ፡፡ ልትደበድቡኝ፣ ልታሰቃዩኝ እና ከሌላው እስረኛ ለብቻ ነጥላችሁ ልታስሩኝ ትችላላችሁ፡፡ መከራ ልታደርሱብኝ እና የሸፍጥ ክስ በመመስረት በተንዛዛ ቀጠሮ እያመላለሳችሁ ፍዳ ልታሳዩኝ ትችላላችሁ፡፡ በሚከረፋው የማጎሪያ እስር ቤታችሁ በረሀብ እንድቀጣ እና የሕክምና አገልግሎት እንዳጣ ልታደርጉ ትችላላችሁ፡፡ ስሜን ልታጠፉ እና ባሕሪዬን ጠላሸት ለመቀባት ትችላላችሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ባለቤቴን ልታዋርዷት እና የእናንተ ወሮበሎች በእኔ ላይ የሚያደርሱትን በደል እየተመለከተ ልጄ እንባ አውጥቶ ሲያለቅስ እናንተ ልትስቁ ትችላላችሁ፡፡ እኔን እና ቤተሰቤን ልታስፈራሩ፣ ልታሸማቅቁ እና ለእኛ ህይወት በመሬት ላይ ገሀነም እንድትሆን ልታደርጉ ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም ግን ለእናንተ የጭቆና አገዛዝ፣ ለእናንተ የበከተ ሙስና፣ ለእናንተ የጭካኔ ፌሽታ፣ ለእናንተ አረመኒያዊ ድርጊት እና እንስሳዊ ኋላቀርነት ባህሪ በፍጹም በፍጹም በፍጹም አላጎበድድም፡፡ እስክንድር ነጋ እንደመሆኔ መጠን የእራሴ ዕጣ ፈንታ አዛዥ እና የህይወቴ መርከብ ነጂ/ካፒቴን ሌላ ማንም ሳይሆን እኔው እራሴ ነኝ!“

ከእስክንድር ነጋ እና ከእርሱ ባለቤት ከሰርካለም ፋሲል የበለጠ የማከብራቸው፣ የማደንቃቸው እና የማወድሳቸው በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ እነርሱን ለማክበር የምስጋና ደብዳቤ ጽፊያለሁ፡፡ እስክንድር፣ ሰርካለም እና ልጃቸው ናፍቆት (ቀኑ ሳይደርስ በእስር ቤት የተወለደ እና በአረመኔው በቀልተኛ በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የህይወት ማዳኛ ኢንኩቤተር የተከለከለው) ናቸው፡፡

እኔ ማድረግ የምችለው ቢሆን ኖሮ እነዚህን የተከበሩ እንቁዎች የሌላ የማንም ሀገር ወይም ደግሞ ተቋም የእኔ ናቸው ብሎ እንዳይጠይቅ ለማድረግ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ እሴቶች ናቸው በማለት አውጅ ነበር፡፡ በዚያ ጉዳይ ላይ ሌላ ምርጫ አይሰጣቸውም!

እስክንድርን የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ተሟጋች አድርጌ ለመናገር አልፈልግም፡፡ ከእኔ ይልቅ ስለዚህ ሁኔታ የበለጠ ግልጽ በሆነ መልኩ ሊናገሩ የሚችሉ በርካታዎቹ አሉ፡፡

እስክንድር በዓለም ሁሉ ካሉ የፕሬስ ነጻነት ጀግናዎች ሁሉ ጀግና ነው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ሰላማዊ አመጸኛ ጋዜጠኞች ሁሉ ስለእርሱ ተናግረዋል፣ በአስቸኳይ ከእስር ቤት እንዲለቀቅም ጠይቀዋል፡፡ ከበርካታዎቹ ጥቂቶቹ የሚከተሉትን ያካትታል፣ ኬኔት ቤስት ከላይቤሪያ፣ ሊዲያ ካቾ ከሜክሲኮ፣ ጁአን ፓብሎ ካርዲናስ ከችሌ፣ ሜይ ችዲያክ ከሊባኖስ፣ ሰር ሀሮልድ ኢቫንስ ከዩናይትድ ኪንግደም፣ አክባር ጋንጂ ከኢራን፣ አሚራ ሀስ ከእስራኤል፣ ዳውድ ክታብ ከዮርዳኖስ፣ ግዌን ሊስተር ከናሚቢያ፣ ሬይሞንድ ሎው ከደቡብ አፍሪካ፣ ቬራን ማቲክ ከሰርቢያ፣ አዳም ሚችንክ ከፖላንድ፣ ፍሬድ ሜምቤ ከዛምቢያ፣ ኒዛር ኔዩፍ ከሶርያ፣ ፓፕ ሳይኔ ከጋምቢያ፣ ፋራጅ ሳርኮሂ ከኢራን፣ ኔዲም ሴነር ከቱርክ፣ አሩን ሻውሬ ከሕንድ፣ ሪካርዶ ኡሴዳ ከፔሩ፣ ጆሴ ሩቤን ዛሞራ ከጓቲማላ ናቸው፡፡ ሌሎች የሰብአዊ መብቶች እና የፕሬስ ድርጅት መሪዎች ደግሞ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡ ማርክ ሀምሪክ የናሽናል ፕሬስ ክለብ ፕሬዚዳንት ከዋሺንግተን ዲ.ሲ፣ አርየህ ኔይር የኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽንስ ፕሬዚዳንት፣ ኬኔዝ ሮት የሂዩማን ራይተስ ዎች ዋና ዳይሬክተር፣ ጆኤል ሲሞን የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ ዋና ዳይሬክተር፣ ዊሊያም ኢስተርሊ በኒዮርክ ዩኒቨርሲሰቲ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡

እስክንድር ነጋ፡ አይዞህ ብቻህን አይደለህም!

እስክንድር ነጋ ያልተረሳ መሆኑን እንዲያውቅ እፈልጋለሁ፡፡ ሰርካለም እና ናፍቆት እስክንድር በፍጹም የማይረሳ መሆኑን እንዲያውቁት እፈልጋለሁ፡፡ ለክብራችን እና ለነጻነታችን ሲል ከዘ-ህወሀት ግንባር ለግንባር ገጥሞ እየተፋለመልን ያለውን እንቁ ጀግና እንደምን ልንረሳው እንችላለን?

በአሁኑ ጊዜ የዓለም ሕዝብ በኢትዮጵያ በማጎሪያው እስር ቤት ውስጥ እየማቀቁ ያሉትን እስክንድር ነጋን እና ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች እንዲያስታውስ እፈልጋለሁ፡፡

እስከንድር ነጋን እናስታውሳለን፣ ሁልጊዜ፡፡ እስክንድር ነጋን እናደንቃለን፣ እናከብራለን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ አስደናቂ እና አፍቃሪ ባል እና አባት በመሆኑ እስክንድር ነጋን እንወደዋለን፡፡

ከሁሉም በላይ እስክንድር ነጋ የኩሩዋ ኢትዮጵያ ልጅ በመሆኑ እናከብረዋለን፣ እናስታውሰዋለን፡፡

የሚካኤል ጃክሰንን የግጥም ስንኞች ትንሽ ለወጥ በማድረግ እኛ የእስክንድር ነጋ ወንድሞች እና አህቶች ስለእርሱ ምን እንደሚሰማን ያለንን ስሜት እንዲህ በማለት ለመግለጽ እንወዳለን፡

ብቸኛ አይደለህም አለን ከጎንህ፣

ሌት ከቀን በማሰብ የምንሳሳልህ፣

ስለውሎ አዳርህ ጤናና ምግብህ፣

ስለጥልቅ ሀሳብህ የሕዝብ ፍቅርህ፡፡

አንተ ለኛ ብለህ፣

ባፋኞች ተወግረህ፣

ስቃይ ተሸክመህ፣

ከደስታ ርቀህ፣

ባጥር ተከልለህ፣

በሸፍጥ ተይዘህ፡፡

ብትኖር በስቃይ፣

ሁሉን ነገር ሳታይ፣

ቢደረመስ ሰማይ፣

ወይ ንቅንቅ ካላማህ ነጻነትን ሳታይ፡፡

በአካል ሩቅ ሆነን ካንተ ጋር ባንሆንም፣

የስቃይ ተጋሪህ ጓደኞች ባንሆንም፣

እኔ ልተካልህ የማንል ብንሆንም፣

በመንፈስ አንድ ነን ልዩነት የለንም፣

ብቸኛ ነኝ ብለህ ፍጹም እንዳትቆዝም፣

በጀግናው ጽናትህ ከቶ አንረሳህም፡፡

ፍቅርህ ቤቱን ሰርቶ በልባችን ውስጥ፣

ሌት ቀን እንድንተጋ ለወሳኙ ለውጥ፣

ለሕዝቦች አርነት ለእድገት መሳለጥ፡፡

አንደበተ ርትኡ የጠላት መጋኛ፣

የሕገወጥነት ታጋይ አመጸኛ፣

የዘር ናፋቂነት የአድልኦ ቀበኛ፣

ሙስናን ተዋጊ ተፋላሚ ዳኛ፣

የፍትህ መሀንዲስ የጠራ እውነተኛ

ፍትህ ሳያሰፍን ከቶ የማይተኛ፣

ብቸኛ አይደለህም ከጎንህ ነን እኛ::

አረመኔ ስርዓት በሸፍጥ ተነስቶ፣

በዘር በኃይማኖት ልዩነት መስርቶ፣

ጥላቻና በቀል በሀገር አስፋፍቶ፣

ነጻነትን ገፎ ፍቅርን አጥፍቶ፣

የሀገሪቱን ሕዝብ ረግጦ አደህይቶ፣

ጉልብትና ኃይሉን ሸፍጡን ተመክቶ፣

ለመጥፎው ድርጊቱ ህይወቱን ሰውቶ፣

በኢትዮጵያ ላይ አይቀር እንዲህ ተንሰራፍቶ፡፡

እኔ እስክንድር ነጋ ነኝ! 

አይበገሬው እስክንድር ነጋ! 

እስክንድር ነጋ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሁሉም የፖለቲካ አስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ!!!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ሚያዝያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም 

ኒምኦ እና ሂንዲያ በማህሌት ፋንታሁን ZONE9·

በመጀመሪያ ጣውላ ቤት
ከታሰርኩበት ሚያዚያ 17/2006 አመሻሽ ጀምሮ ለቀጣዮቹ ሰማኒያ አራት ቀናት “የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ” (ማዕከላዊ) እኖርበት የነበረው ክፍል በተለምዶ ጣውላ ቤት ይባል ነበር። አምስት ክፍሎች አሉት። በፊት እነዚህ ክፍሎች የወንዶች እስረኞች ነበሩ። እኔ ከመግባቴ ከአራት ወር በፊት እዛው አካባቢ የምትገኝ አንዲት ክፍል ውስጥ ነበር ሴት እስረኞች የሚኖሩት። ወይም ብቻቸውን እንዲሆኑ የሚፈለጉ ሴት እስረኞች ከአምስቱ በአንዱ ክፍል ለብቻቸው እንዲኖሩ ይደረጋሉ። ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ማዕከላዊ የቆየችባቸውን ጌዜ በሙሉ ከአምስቱ ክፍሎች በአንዱ ብቻዋን ነበር የምትኖረው። ሴቶቹ የሚኖሩባት ክፍል ለእስረኞቹ እየጠበበቻቸው ስትመጣ እዛ መኖራቸው ቀርቶ አምስቱ ክፍሎች ያሉበትን (ጣውላ ቤት) ሁለቱ (1 እና 2 ቁጥር) ተለይቶ በረንዳው ላይ በቆርቆሮ ተጋርዶ ፤ እንደታሳሪው ብዛት ሶስቱ ክፍል ላይ ሴቶች፤ ሁለቱ ላይ ወንዶች ወይም ሁለቱ ላይ ሴቶች ሶስቱ ላይ ወንዶች ይኖሩበታል። ጣውላ ቤት የሚኖሩ ወንድ እስረኞች በብዛት የመርማሪዎች ድብደባን መቋቋም ሲያቅታቸው በሌሎች እስረኞች ላይ (በተመሳሳይ የሽብርተንነት ወንጀል ተጠርጥረው ለታሰሩ) ለመመስከር በግዳጅ የፈረሙ ናቸው። አልፎ አልፎ አስም እና ተዛማጅ ህመሞች የሚጠቁ በሽብርተንነት የተጠረጠሩ እስረኞች ጣውላ ቤት እንዲኖሩ ይደረጋል። በአማካኝ 3 ሜትር በ4 ሜቴር ስፋት ያለው ሲሆን በመደበኛ ጊዜ ከ4 እስከ 20 እስረኞች ይኖሩበታል።
ጣውላ ቤት ብዙ ነገር ለማየት እና ለማስተዋል አማካኝ ቦታ ነው። ከጣውላ ቤት ላይ ያለው ፎቅ ‘መመርመሪያ’ (መደብደቢያ) ክፍሎች ናቸው። ከእያንዳንዱ ጣውላ ቤት አናት የየትኛው ‘መርማሪ’ ክፍል መሆኑን ለማወቅ ከሳምንት በላይ አይጠይቅም። መርማሪዎች ለመመርመር እያሉ በማታ እና በለሊት ጠርተውን ሊያሰቃዩን ከክፍላችን ከመወሰዳችን በፊት ክፍላችን ሆነን በኮቴያቸው እናውቃለን። አብዛኛውን ቀናት (በብዛት ከእሁድ በስተቀር) ጣሪያችን በኮቴያቸው እንደተሸበረች ነው። የጣሪያችን መሸበር እኛንም ጭንቀት ለቆብን እንቅልፍ ይነሳናል። መርማሪዎች ከፎቁ (ወለሉ እና ደረጃው ጣውላ ነው) ሲወርዱ እና ሲወጡ ይሰማል ። በመርማሪዎች እስረኛ እንዲያመጡ የሚላኩ ፓሊሶች ኮቴ እና ከእጃቸው የማይለየው ካቴና ድምፅም ሌላው የስቃያችን ምንጭ ነው።
ጨለማ ቤትና እና የሳይቤሪያ ክፍሎች እስረኞች ከጣውላ ቤት ፊት ለፊት ባለች መንገድ ነው ወደ ‘ምርመራ’ ክፍል የሚሔዱት እና የሚመለሱት፡፡ በቀን የምትፈቀድላቸውን የ10ቸደቂቃ ፀሃይ የሚሞቁትም መተላለፊያ መንገዱን ሸገር ብሎ ያለች በጣም አነስተኛ ሜዳ ላይ ነው። ይህች ሜዳም ጣውላ ቤት ለሚኖር እስረኛ ፊት ለፊት ናት። የጣውላ ቤት ነዋሪዎችም ተራችን ሲደርስ ፀሃይ የምንሞቀው እዛችው ሜዳ ላይ ነው። ከሜዳዋ አለፍ ብሎ ደግሞ ብቸኛዋ ክሊኒክ እና የጣውላ ቤት ነዋሪዎች ሽንት ቤት ይገኛል። ከክሊኒኩ ጎን ደግሞ በየሶስት ሰዓቱ እየተቀያየሩ ለ24 ሰዓት እኛን (የጣውላ ቤት እስረኞችን) የሚቆጣጠሩ ‘ዋርድያዎች’ ማማ አለ።
ስለሆነም በጨለማ እና በሳይቤሪያ የሚኖሩ እስረኞች ለምርመራ፣ ፀሃይ ለመሞቅ እና ለህክምና ሲወጡ እና ሲመለሱ እናያለን። በእያንዳንዱ የሳይቤሪያ እና ጨለማ ቤት የሚኖሩትን እስረኞች መለየት ጊዜ አይፈጅም። ምክንያቱም ፀሃይ ሲወጡ በየክፍላቸው እና በየተራ ስለሆነ ከጊዜ ብዛት እንለምዳቸዋለን። ከክፍሉ ልጆች ጋር ፀሃይ ለመሞቅ ያልወጣን እስረኛ እንለይና እንጨነቃለን። ወይ በድብደባ ብዛት መውጣት ሳይችል ቀርቶ ነው ወይ ‘ምርመራ’ ሄዶ ነው። አንድ እስረኛ ብቻውን ከሚጠብቀው ፓሊስ ጋር ፀሃይ ለመሞቅ ወጣ ማለት ጨለማ ቤት ነው የታሰረው ማለት ነው ወይም ሌሎች በክፍሉ የሚኖሩት ሁሉ ታመው ከክፍላቸው መውጣት አልቻሉም ወይም ደግሞ ‘ምርመራ’ ሄደዋል ማለት ነው።
ከ11 እስከ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ክፍሎቻችን ከተቆለፉ በኋላ በበራችን ቀዳዳ ወደ ምርመራ ክፍል የሚያልፉትን እና የሚመለሱትን እናያለን። አንዳንድ ጊዜ በቀንም በራችን የሚዘጋበት አጋጣሚ አለ። ይህ የሚሆነው ‘ዋርድያው’ ክፉ ሲሆን እና አጋጣሚ በር ላይ ቆመን ከታየን እንዲሁም ከክሊኒክ/’ምርመራ’ ቦታ ከውጪ አዲስ እስረኛ ወደ ሳይቤሪያ ወይም ጨለማ ክፍል ለማስገባት ሲፈለግ እና የእስረኛውን ማንነት/የደረሰበትን አደጋ እንዳናይ ለማድረግ ሲታሰብ ነው። ሆኖም ግን እኛ በቀዳዳ ማየታችን አይቀርም። በወቅቱ በር ተዘግቶብን ሳለ በቃሬዛ ተይዘው ወደ ሳይቤሪያ እና ጨለማ ቤት ሲወሰዱ ያየናቸው እስረኞች ነበሩ፡፡ በተረፈ ግን ምርመራ ሲሄዱ ጤነኛ ሆነው ሄደው ሲመለሱ እያነከሱ፣ እየተንፏቀቁ፣ ቆስለው እና በድጋፍ ወደ ክፍላቸው ሲሄዱ ማየት የለት ተለት የሚያም ትዕይንት ነው።
እኔ በገባሁበት ወቅት ከሴት እስረኞች ‘ምርመራ’ የሚበዛብን እኔና ጋዜጠኛ ኤዶም ብቻ ነበርን። ሌሎቹ ከአንድ ቀን በላይ የሚጠሩበት አጋጣሚ ጥቂት ነው። በተለይ በር ከተቆለፈ በኋላ በማታ እና ሌሊት የምንጠራው እኛ ብቻ ነበርን። በሌሊት እና በማታ በምንወጣበት ጊዜ ካጠገብ ያሉ ክፍሎች ያሉ እስረኞች በበር ቀዳዳ ያዩን ነበር። ስንወጣና ስንመለስም የሚያዋስነንን ግድግዳ ሲያንኳኩ ስለኛ መጨነቃቸውን እና ማሰባቸው ይገባን ነበር። ነግቶ ሲያዩንም “አይዟችሁ!” “በርቱ!” “ዱላው እና ማሰቃየታቸው ቢበዛም ቻሉት። ያላደረጋችሁትን ነገር አረግን ብላችሁ አንዳታምኑ!” እና የመሳሰሉ ማበረታቻ ቃሎችን በምልክት እና በአፍ እንቅስቃሴ ያስተላልፉልን ነበር። በተለይ ጣውላ ቤት ያሉ ወንዶች ይህን አይነት ምክር መምከራቸው የገረመኝ፤ እነሱ ምስክር መሆናቸውን ያወቅኩ ጊዜ ነው። በውሳኔያቸው ተፀፅተው ይሆን? እያልኩም አስባለሁ።
ኒምኦ እና ሂንዲያ
ኒሞን እና ሂንዲያን ያወቅኳቸው ማዕከላዊ መጀመሪያ የገባሁ ቀን ነው። ሚያዚያ 17/2006 ከምሽቱ 1 ሰዓት። ኒሞ እና ሂንዲያ ሶማሌዎች ናቸው። እኔ የገባሁበት ክፍል ከኒሞ እና ከሂንዲያ ውጪ ሰው ወደ ውጪ ሃገር በመላክ ተጠርጥራ ታስራ የነበረች አንዲት ሴት (እኔ ከገባሁ ከሶስት ቀናት በኋላ ተፈታለች) ናት የነበረችው። ባጠቃላይ አራት እስረኞች ነበርን። ከገለፃቸው ኤዶም እዚህ ክፍል ገብታ እንደነበረ እና ከመምጣቴ ከደቂቃዎች በፊት ወደ ሌላኛው የጣውላ ቤት ክፍል መግባቷን ተረዳሁ። የተረበሸ ሁኔታ ውስጥ ብሆንም የተረጋጋሁ ለመምሰል በጣም እጥር ነበር። በፍተሻ ወቅት እቤት ባለመኖራቸው ሳላገኛቸው የመጣሁት እህት እና ወንድሜ መታሰሬን እንዴት እንደሚሰሙ? ሲሰሙስ እንዴት እንደሚሆኑ? መታሰሬ ዜና ዱብ እዳ ለሚሆንባቸው ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ ይህችን ምሽት እንዴት እንደምትነጋላቸው? ሌሎቹ የዞን 9 ጓደኞቼስ ታስረው ይሆን? አዳሬስ እንዴት ይሆን ይሆን? ይህን እና የመሳሰሉትን ሃሳቦች በጭንቅላቴ መመላለስ አላቆሙም። ይህን እያሰብኩ አንድ የሰፈሬ ልጅ ጣቢያ ታስሮ የመጀመሪያ ቀን ያጋጠመው ነገር ያጋጥመኝ ይሆን እያልኩ አስባለሁ። የሻማ ብር እንዲያዋጣ ብር ከሌለው ደግሞ የታዘዘውን ያክል ጊዜ ዘፈን እየዘፈኑ በክፍሉ ያሉ እስረኞችን እንዲያዝናና አማራጭ ተሰጥቶት በወቅቱ ብር ስላልነበረው ለመዝፈን እንደተገደደ አጫውቶኝ ነበር። የሻማ ያለኝም፣ ዝፈኝ ያለኝም አልነበረም። ምክንያቱም ይህ የማሰቃያ ማዕከል የሆነው ማዕከላዊ ነው። ቀልድና ጨዋታ የሚታወስበት ጊዜ የለም። በገባኁበት ቀን የክፍሌ ልጆች እራት በልተው ጨርሰው ነበር። ሶማሌዎቹ ጥቂት እንደቆየሁ ምግብ እንድበላ እነሱ ካስቀሩት ሩዝ በስጋ አቀረቡልኝ እና ጥቂት ቀማመስኩ። ከሁለቱ ውጪ ያለችው ሴትዮ ተኝታለች። ከሁለቱ ሶማሌዎች ጋር ሳንተኛ ካርታ እየተጫወትን ቆየን። በመሃል ከላያችን ያለው ‘ምርመራ’ ክፍል እና ኮሪደሩ በኮቴ ሲናወጥ ሃሳባችንን ሰረቀው ። እነሱ በጣም የሃዘን እና የጭንቀት ፊት ይታይባቸው ነበር። እኔ አልገባኝም። ጠየኳቸው። “አይ ምንም አይደል” አይነት ምላሽ ሰጡኝ። እኔ እንዳልጨናነቅ መሆኑ ገብቶኛል። የኔው ጓደኞች ወደ ‘መርማሪዎች’ ቢሮ ሲገቡ ነው ብዬ አሰብኩ። እኔም ጊዜዬን እንደምጠብቅ ጠርጥሬ ልጠራ እችል እንደሆነ ስጠይቃቸው “አይ ዛሬ አትጠሪም” አሉኝ። ይህም እኔን ለማረጋጋት ነው እንጂ የእውነት የሚሆን አልመሰለኝም ነበር። የምቀይረው የሌሊት ልብስ ሲሰጡኝ ‘መርማሪዎች’ ሲጠሩኝ በፒጃማ ከምወጣ ብዬ በዋልኩበት ልብስ ማደሩን መረጥኩ ። ከዛ በኋላ ባሉት ቀናትም በተመሳሳይ ምክንያት የሌሊት ልብስ አልብስም ነበር። ዱላውን፣ ቁጣውን እና ዛቻውን ለመቻል የቀን ልብስ ይሻላል። ይህን ምክንያቴን ስነግራቸው “ፓሊስ መጣ ነው። ነይ ነው። ቆይ ልብስ ቀይር ነው። ውጪ በር ቁም ነው። ቀይር ነው። ውጣ ነው።” ትለኛለች ሂንዲያ በሚቸግራት አማርኛ። ‘’ትወጫለሽ ፓሊስ ቢመጣም ልብስ ልቀይር ብለሽ ውጪ በር ላይ ይቆም እና ቀይረሽ መውጣት ትችያለሽ’’ ማለቷ ነው። እኔ ግን ‘ፓሊሶቹ ልብስ የመቀየሪያ ጊዜ ባይሰጡኝስ?’ ብዬ ‘ሪስኩን’ ላለመውሰድ ምክሯን ተግባራዊ አላደረኩትም ነበር። በተጨማሪም በጃኬት እና ወፍራም ሻርፕ ተጀቧቡኜ ነበር የምወጣው ለምርመራ ስጠራ ።
እነ ሂንዲያ ከታሰሩ 7ወር ሊሆናቸው እንደሆነ ያረዱኝ የዛኑ እለት ምሽት ነበር። በ2006 ጥቅምት ወር ላይ ኢትዮጵያና ናይጄሪያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚጫወቱበት ወቅት እና በሌሎች ህዝብ በሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ከሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች ጋር ቦንብ ሊያፈነዱ ነበር ተብለው ተጠርጥረው በግብረ አበርነት ከተያዙት ውስጥ ናቸው ኒሞ እና ሂንዲያ። ሂንዲያ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ “አጥፍቶ ጠፊዎቹ” ቦንቡ በድንገት ከፈነዳባቸው መኖሪያ ቤታቸው በፊት ተከራይተው ይኖሩበት የነበረው ቤት ጎረቤት ነበረች። ኒሞ ደግሞ ቦምቡ ከፈነዳበት ግቢ ተከራይታ ትኖር ነበር። ኒሞ ማእከላዊ ስትመጣ እራሷን እንደማታውቅ እና በፍንዳታውም የግድግዳ ፍርስራሽ ወድቆባት ቆሳስላ እንደነበር አጫውታኛለች። ሁለቱም ከፈነዳው ቦንብ ጋር በተያያዘ የሚያቁት ነገር እንዳለ ተብለው ብዙ ድብደባ ደርሶባቸዋል። በሂንዲያ የደረሰው በጣም የከፋ ነው። ለብዙ ጊዜ ጀርባዋን በኤሌክትሪክ ገመድ ስለምትገረፍ ቁስሏን ይጠራርጉላት እንደነበር እና ለሽንት ቤትም ሆነ መንቀሳቀስ ስትፈልግ በሰው እርዳታ እንደነበረ ከሌሎች ሴት እስረኞች ሰምቻለሁ። እኔ ስገባ 7ኛ ወራቸውን ቢያስቆጥሩም የሂንዲያ ጀርባ ገመዱ ያረፈባቸው ቦታዎች ጠባሳ በጉልህ ይታያል። ይህን ሁላ ጉድ ችለው አዲስ መጪውን ሲቀበሉ ክስ ተመስርቶበት ቃሊቲ የሚገባውን እና የሚፈታውን ሲሸኙ አንጀት ይበላሉ። ‘ግብረ አበር’ እና ‘ተሳታፊ ናችሁ’ ተብለው ለተወነጀሉበት ክስ ምስክር እንዲሆኑ ተብሎ ነው በእስር ክስ ሳይመሰረትባቸው ብዙ ጊዜ የቆዩት።
ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ለሽብር ተግባር ሊያውሉት አቅደው እዛው ቤታቸው ውስጥ ቦንቡ ፈንድቶ ህይወታቸው ካለፈ አጥፍቶ አጥፊዎች ጋር ግብረ አበር በመሆን ክስ ለተመሰረተባቸው እነ ሙሐመድ አብዱራህማን ሙሐመድ (8 በዜግነት ኢትዮጵያዊ እና ሶማሊያዊ የሆኑ ግለሰቦችና ሁለት ኢትዮጵያውያን ቤት አከራዮች) ለአቃቤ ህግ እንዲመሰክሩ ተብለው ነው ኒምኦ እና ሂንዲያ ያላአግባብ በእስር የተቀመጡት።
(በነገራችን ላይ እነ ሙሐመድ አብዱራህማን ሙሐመድ ከታሰሩ ሁለት አመት ከስድስት ወር ቢያልፋቸውም አሁን ድረስ አቃቤ ህግ ‘የጠፉ ምስክሮችን ልፈልግ’ በሚል ምክንያት ምስክሮቹን አሰምቶ አልጨረሰም።)
ማዕከላዊ በገባሁ ከሳምንት በኋላ ሂንዲያ ከጎናችን የነበረ ሌላ የሴቶች ክፍል ተቀይራ ሄደች። ከኒምኦ ጋር ደግሞ ኤዶም እኔ ያለሁበት ክፍል መጥታ እሷን ኤዶም የነበረችበት ክፍል እስኪወስዷት ለ20 ቀናት ያክል አብረን ነበርንን። ከዛ በኋላ ግንኙነታችን ለሽንት እና ለፀሃይ ስንወጣ ስንተያይ (እኛ ክፍላችን እነሱ ለሽንት እና ለፀሃይ ሲወጡ ወይም በተቃራኒው) በርቀት በምንለዋወጠው ሰላምታ ተገደበ። ኒምኦ ሌላ ክፍል ስትሄድ ምንጣፏን ሰጥታኝ ነው የወጣችው። ከኔ የበለጠ ምንጣፉ ለሷ እንደሚጠቅም ስለማውቅ (‘ሶላት’ ለማድረግ) እንድትወስደው ብጠይቃትም፤ ልትሰማኝ ፈቃደኛ ባለመሆን እያለቀሰች ወደ አዲሱ ክፍሏ ሄደች። ‘’ቀድመሽኝ ከወጣች ትሰጪኛለሽ’’ አለችኝ ። ከሶስት ወራት በኋላም ተከሰን ወደ ቃሊቲ ስንወርድ ምንጣፉን ይዘነው እንድንሄድ ሰጠችን።
እኛ ከማዕከላዊ ቆይታ በኋላ ተመስርቶብን ቃሊቲ ስንወርድ ኒሞና ሂንዲያ እዛው ነበሩ። አስር ወር ሞላቸው ማለት ነው። ቃሊቲ ከወረድን ከሁለት ወር በኋላ ይሆናል መለቀቃቸውን የሰማነው። ያለምክንያት ለአንድ ዓመት ያህል በማዕከላዊ ስቃይ በተሞላው እስር ቆይተው እንደዋዛ ተለቀቁ ማለት ነው። በታሰሩበት ወቅት ኒምኦ አዲስ አበባ በሚገኝ የጤና ኮሌጅ በነርሲንግ የትምህርት ዘርፍ ተማሪ የነበረች ሲሆን፤ ሂንዲያ ደግሞ ትዳር መስርታ የምትኖር የአንድ ልጅ እናት ናት። የኢትዮጵያ መንግስት ባደረሰባቸው በደል በጣም ተማረው፤ በኢትዮጵያ የመኖር ጉዳይ ተስፋ አስቆርጧቸዋል። ሶማሌ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ (ሶማሊ ኢትዮጵያውያን) በማንኛውም አጋጣሚ ለእስር ሊዳረጉ እንደሚችሉ እርግጠኞች ናቸው። አብረን በነበርንበት ወቅት ኒምኦ ከዚህ በኋላ አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር በኢትዮጵያ አቋርጣ (በትራንዚት) ወደ ሌላ ሃገር ለማለፍ ደህንነት ሊሰማት እንደማይችል ነግራኛለች።
ኒምኦ የሰጠችንን ምንጣፍ በተፈታንበት ወቅት ቃሊቲ ለተተኪ አስረክበን ወጣን። ኒምኦ እና ሂንዲያ ማዕከላዊ በነበሩበት አንድ ዓመት ለገቡ እስረኞች መፅናኛ እና መካሪ ነበሩ። አድራሻቸውን ሳልይዝ በመውጣቴ እና አሁን ላገኛቸው አለመቻሌ ያሳዝነኛል።

13. አማራነትና ኢትዮጵያዊነት – አሰፋ እንደሻው

74f3da87aa592b07926638fefa1936ecካሁን በፊት የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪከ ስናጠና ዛሬ አገሪቱን የሞሏትን ህዝቦች አመጣጥ ለመመልከት ሞክረን ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ ስለአማራውና ኦሮሞው ህዝብ ምንጭ ዘርዘር ያለ ውይይት አካሂደናል፡፡ ለጥናታችን መነሻ የሆኑን ባገር ውስጥና ባለም ዙሪያ ስለኢትዮጵያ ምርምር ያደረጉት አዋቂዎች ስራዎች ናቸው፡፡ የጥናታችን ውጤት አክሱም  ኢትዮጵያ–የህዝቦች ስብጥርና የአገዛዞች አወቃቀር አጭር ታሪክ በሚል በ2004 መልሶም በ2007 ለሁለተኛ ጊዜ ታትሟል፡፡ ዛሬ ያነሳነው ጉዳይ ያንን ጥናት እዚህ መልሶ ለማስፈር ሳይሆን በጉዳዩ ዙሪያ በተደጋጋሚ በክርክርም በመዘላለፍም በተለያዩ ወገኖች መካከል የሚቀርበውን ለመዳሰስና መረጃዎችን መሰረት ያደረጉ ትንታኔዎችን ለመሰንዘር ነው፡፡

ከሁሉ አስቀድሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ እየተሰራጨ ስላለው “ሀበሻ” ስለሚለው ስያሜ ብንነጋገር; የ1894 አም የብሪታንያ ስንክሳር “ሃበሻ አገር” በሚል ስር እንዳሰፈረው “ሃበሻ አገር ወይም ባግባቡ ሃበሻ የሚለው ስያሜ አመጣጡ ሃበሽ ከሚል ያረብኛ ቃል ነው፤ ይህም ሲተረጎም ድብልቅ ወይም የሚያምታታ ማለት ሲሆን በህዝቡ የተደበላለቀ ባህርይ የተነሳ በአረቦች ላገሩ የተሰጠ ነው፡፡ ፖርቱጋሎች ሲመጡ ይኸንኑ ስም በላቲን “ሃበሻ” ወይም “ሃበሺኖስ” ወደሚል ለውጠውት የዛሬውን ስያሜ ይዟል፡፡ ሃበሾች ራሳቸውን ኢትዮጵያዊ ብለው ሲጠሩ አገራቸውን ደግም ኢትዮጵያ ወይም የኢትዮጵያ መንግስት ይላሉ፡፡” የህዝቡን ዘር በተመለከተ ይኸው ስንክሳር ይህንን ይላል፡- “የሃበሻ አገር ነዋሪዎች በርካታ የተለያዩ ነገዶችን ባካተቱ ቁርጥ ያሉ ዘሮች ይመደባሉ፡፡ አብዛኞች የነጭ ዘር ናቸው፣ ባጠቃላይም ሰውነታቸው በደንብ የዳበረና መልከመልካም፣ ቀጥተኛና በመጠኑ የተጠማዘዘ [ጠጉር]፣ ወደጥቁርነት የሚጠጋ ግን ደማቅ የወይራ ፍሬ ቀለም ያላቸው ናቸው…ትገሬ፣ አማራ፣ አገውና ወዘተ ውስጥ የሚኖሩት ከዚህ ዘር ናቸው፡፡”

ትረካው ሁለት የተምታቱ ነገሮችን ይዟል፡፡ ባንድ በኩል ሃበሻ የሚለው ስያሜ አረቦች ከቀይ ባህር ወዲህ ላለው ህዝብ ያወጡት መሆኑን በትክክል ጠቁሞ “ድብልቅ ወይም የሚያምታታ” ብለው የሚመለከቱትን ህዝብ እንዴት በአረብ ባህረሰላጤ ከሚገኙት ሴማዊ ህዝቦች ማለትም ራሳቸውን ከነጮች ጋር ከሚመድቡት ጋር እኩል “አብዛኞች የነጭ ዘር ናቸው” ብሎ ያርፋል; “ድብልቅ”ነት መቀየጥን አያመለክትም; መቀየጥ ደግሞ የዱሮውን ወይም የመጀመሪያውን ማንነት አይለውጠውም; ስለሆነም “ሃበሻ” የሚለው አጠራር ወይ ምንም ነጭነት ለሌላቸው ወይም ለተደባለቁት ብቻ ማለትም ነጭነታቸው ለቀረባቸው እንጅ ለነጮች የሚሰጥ ሊሆን የታቀደ አይመስልም፡፡ በዚህ አይነትማ በዛሬው የአረብ ባህረሰላጤ የሚኖሩትም ህዝቦች “ሃበሻ” ቢባሉ ምንም ችግር ባልፈጠረ! ነገር ግን ዱባና ቅል…አይነት ነው፡፡
ሁለተኛ፣ አብዛኞች የኢትዮጵያን ጥንታዊ የህዝብ ስብጥር በተመለከተ የታተሙ ትረካዎች በኢትዮጵያ ሰሜን ያለውን ህዝብ ከፍተኛ ክፍል ከአረብ ባህረሰላጤ የፈለሰ ነበር ስለሚሉ ሴማዊ (በተሸፋፈነ ቋንቋ “ነጭ”) አድርገው በመሳል ያገሪቱን ህዝብ ለሁለት ከፍለውታል፡፡ ሴማዊው ክፍል የስልጣኔው ምንጭ፣ የአገዛዙ ባለቤትና የነጭነት ባህርይ የተላበሰ ተደርጎ ኩሻዊው ወገን ደግሞ በተደራቢነትና በተከታይነት እንደኖረ ሲለፈፍ ኖሯል፡፡ ይህ ግን በማስረጃ የተደገፈ ሳይሆን በመላምትና በፈጠራ የተገጣጠመ አንዱ የውጭ ተመራማሪ ነኝ ባይ ለሌላው እየተቀባበሉ ሲያናፍሱት የቆየ እንደነበር እላይ በጠቀስነው ጥናታችን ተገልጾአል፡፡ በጣም ስመ ጥር ሆኖ ለብዙዎች ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ትምህርት መምህርና በምርምራቸው ስራ ላይ በፈታኝነት የሰራው ኤድዋርድ ኡሉንዶርፍ ሳይቀር ኩሻዊ ተብሎ የሚመደበውን

የኦሮሞ ህዝብ በድፍረት “ለኢትዮጵያ ስልጣኔ ምንም ያበረከቱት የለም” ብሎ ኢትዮጵያውያን በሚለው መጽሃፉ ላይ አትቷል፡፡
ከአረብ ባህረሰላጤ ቀይ ባህርን ወደኢትዮጵያ ተሻግሮ አዲስ ግዛት ያቋቋመ አንዳችም የውጭ (ወራሪ; አሸናፊ;) ሃይል እንዳልነበረ የተረጋገጠ ሆኖ ሳለ ከየት ብሎ የሴማዊ (ነጭ) ሰራዊት የበላይነት ቀርቶ የተስፋፋ ስፍራ እንደያዘ የሚተረከው ሁሉ ባዶ ስብከት ሆኖ ቀርቷል፡፡ በሌሎች አካባቢዎች እንደተደረገው ሁሉ ጥቂት የደቡብ አረቢያ ስደተኞች ወደኢትዮጵያ ሸሽተው እንደኖሩ፣ ከሌላው ህዝብ ጋር ተደባልቀው ሰምጠው እንደቀሩ ግን ምልክቶች ተገኝተዋል፡፡ ይልቁንም አክሱማውያን ቀይ ባህርን ተሻግረው ደቡብ አረቢያን በተለይም ሳባውያንን አሸንፈው እንደገዙ የታሪክ ማስረጃዎች ሞልተዋል፡፡ ከዚያ በተጨማሪ ምናልባት የህዝብ ፍልሰት ከነበረ ከኢትዮጵያ ወደመካከለኛው ምስራቅ ብሎም ወደሌላው አለም እንደተካሄደ ዛሬ በመላው አለም ሊቃውንት እየታመነበት መጥቷል፡፡ በደራሲው ምርምርና እስካሁን በታተሙት የዘር ምንጭ ጥናቶች ላይ ተመስርቶ በሚሰጠው ግምት ከኢትዮጵያ ወደመካከለኛው ምስራቅ የነጎደው ህዝብ በአብዛኛው የአባይን ወንዝ የተከተለ ይመስላል፡፡ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ገናና ሆኖ የወጣው የኢንካ ስልጣኔ ሳይቀር የሰፈረው ህዝብ ምንጭ ይኸው ከኢትዮጵያ ተነስቶ በመካከለኛው እስያ ብሎ በአላስካ ላይ ወደታች የተምዘገዘገው ፍልሰት ነበር፡፡ ይህ ትረካ ገና ያልተጠናቀቀ ቢሆንም የዘር ጥናት ተመራማሪዎች ጭምር በየቀኑ እያረጋገጡት ነው፡፡

የኢትዮጵያን ህዝብ ምንጮች በነጭና በጥቁር ዘሮች ከፍሎ ከሚወተወተው ወሬ ተጠቃሚ የነበረው የአገው ነገስታትን ይዞታ ለማናጋትና ስልጣኑን መልሶ በአክሱማውያን እጅ ለማስገባት በተካሄደው ዱለታ ውስጥ “የሶሎሞናዊው ሃረግ” ተመዞ ወጥቶ ያንን ተመርኩዞ በትረ መንግስቱን የጨበጠው ወገን ነው፡፡ ይህም ባንድ በኩል በክርስትና ሃይማኖት መምጣት ያገሪቱ ቀደምት ነዋሪዎች (አገዎች) በክርስትናና በጥንታዊ (ኦሪት) እምነት ከመከፈላቸው ጋር ተሸናፊዎቹ ኦሪታውያን ለቀው (ፈልሰው) ወደደቡብ ምእራብ (ዳሞት)ና ወደስሜን እንዲሸሹ ከተደረጉ ወዲህ ስልጣኑን መልሰው ለመረከብ ሁሌም መታገላቸው ስላልበረደላቸው በጭራሽ ተስፋ ቆርጠው እንዲተው ለማድረግ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስትናን ከመቀበላቸው በላይ በያቅጣጫው እምነቱንና ያገሪቱን ግዛት በማስፋፋት ስራ የተጠመዱትን የአገው ነገስታትም የስልጣን ባለቤትነታቸውን መሰረት ለማናጋት በጠቅላላውም በስልጣኑ ላይ ለሚነሳው ማናቸውም ፉክክር በሃረጉ ዙሪያ ለተደራጁ የርእዮታለም ድጋፍ ለማብጀት የተቀየሰ ነበር፡፡ ለንግስና ማእረግ ሴማውያን መሆን ብቻ ሳይሆን በመንበረ ዳዊት (ሰለሞን) ላይ የመቀመጥ ችሎታና ውልደት እንደሚያሻ መናፈሱ በቤተ ክህነት ጭምር ጸድቆ በኢትዮጵያው ቤተክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ በአናት ላይ የሚቀመጡትን የሚመርጡት የኮፕት ቀሳውስት ርእዮታለማዊ ድጋፉን ማስጨበጫ ስነጽሁፍም (ክብረ ነገስትን) በፈጠራ ደርሰው እስኪሰዱ የተቀነባበረ መመሳጠር ነበረበት፡፡ መጀመሪያ በጥንቱ ቋንቋ በግብጽኛ እስክንድርያ ላይ ወደ7ኛው መቶ አመት አካባቢ ተዘጋጅቶ በምስጢር ወደአክሱም ተልኮ ቆይቶ ቆይቶ አገዎች ስልጣኑን ሲተው ወደእግዝ ተተርጉሟል፡፡ ስልጣኑ ከአገው ነገስታት ተወስዶ ወደ አክሱማውያን (ወይም በራሳቸው ምርጫ ወደ ”ሰሎሞናዊያን”) ከተዛወረ በኋላ የሴምና የካም ዘሮች የገዥና ተገዢነት ድርሻ ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ እንደመጣ መተረኩ ቀጥሎ እስከ አጼ ሃይለ ስላሴ ዘመን ቆይቷል፡፡

በክብረ ነገስት አማካይነት ርዮታለማዊ ልባስ የተጎናጸፈውና በተጭበረበረ ታሪክ የተሸፋፈነው የሁለት ዝርያዎች (ሴማዊና ኩሽ) ጎን በጎን በኢትዮጵያ መኖር ጉዳይ የሚናድበት አዲስ አቅጣጫ በቅርብ ተከፍቷል፡፡ ተመራማሪዎች ስለኢትዮጵያውያን ትውልድ ሃረግ ባደረጉት ቀዳሚ ጥናት ከግማሽ በላይ የሆኑት ከየመንና አረብ አገሮች ይልቅ ከእስራኤልና ከሶርያ ጋር የበለጠ መመሳሰል እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡ ከ60 ሺህ አመታት በፊት ከአፍሪካ ወደውጭ የመሰደድ እንቅስቃሴም “ከኢትዮጵያ ወይም ከግብጽ” እንደተጀመረ፣ ምናልባትም ከደቡብ አረቢያ ተሰደው ከመምጣታቸው ይልቅ በምስራቃዊው የሳሃራ ጫፍ አካባቢ (ግብጽ፣ ሱዳን) ሰፍረው እንደኖሩ፣ በደቡብ አረብና በኢትዮጵያ አካባቢ የቋንቋ መመሳሰልም በይበልጥ ከባህል (ለምሳሌ የንግድ) ግንኙነት የመነጨ እንደሆነ፣ በሳባዊና በኢትዮ-ሴማዊ ቋንቋዎች መካከል መያያዝ መፈጠሩ ዱሮም ባካባቢው (ኢትዮጵያ) ነባር ህዝቦች ውስጥ ሴማዊነት ስለነበር ያንን ሁኔታ መዘንጋት እንደማይገባ የሚያመለክቱ በርካታ ስራዎች አሉ፡፡ ሄዶ ሄዶ ግብጻውያን ከየመናውያን ይልቅ ለኢትዮጵያውያን (ሴማዊም ኩሻዊም) በዘራቸው እንደሚቀርቡ፣ አልፎም ሞሮኳውያን፣ ቤድዊኖችና ዱሩዞች ሳይቀሩ እንደዚሁ ከየመኖች ይልቅ እንደሚጠጉ ጥናቶች እያመለከቱ ነው፡፡

የሰው ልጅ እንዴት ብሎ ከኢትዮጵያ ፈልቆ ወደሌላው አለም እንደተሰራጨ ለመተለም የሚደረገው የዘር ህዋስ የማጥናት ስራ ገና አልተጠናቀቀም፡፡ እስካሁን በተገኙት አመልካች ውጤቶች ግን ከደቡብ አረብ የፈለሰ ህዝብ መኖሩ ቢያንስ ቢያንስ እጅግ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ ከዚያ አልፎ የደቡብ አረባውያን ያካበቱትን ስልጣኔ ተውሶ ባገሪቱ ሰሜን ክፍል የተቆናጠጠ የአገዛዝ አይነት አልተገኘም፡፡ እስካሁን በተደረጉ ቁፋሮዎች የሃ ላይ ገናና የነበረው የዳማት (ምናልባትም ዳሞት) አገዛዝ ወይም ስልጣኔ በቀል እንደነበረ አመልክተዋል፡፡ የዳማት መፈራረስ ከሱ ቀጥሎ የነበረው የአክሱም አገዛዝ እንደደረሰበት አይነት ከበስተሰሜን በኩል ለረዥም ጊዜ የቆዩት ተቀናቃኞች ስራ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡

ወጣም ወረደ የዳማት መፍረስ ያስከተለው የአክሱም አገዛዝ ባህርይና በስሩ የነበረው የህዝብ ስብጥር በድንገት ከሰማይ ዱብ ያላለ መሆኑን መከራከር አይቻልም፡፡ አክሱምን ያቋቋመ አንድ የህዝብ አይነት ወይም ገናና ንጉስ ባላመሆኑ ከዳማት ፍርስራሽ የተሰባሰበው ተቋም የቀደሙትን ትውፊቶች መልሶ ሳይጨብጣቸው አልቀረም፡፡ በዚህ ላይ የሃና አክሱም በጣም ተቀራራቢ ቦታና የአየር ንብረት የነበራቸው ናቸው፡፡ ስለሆነም ሁለቱም አገዛዞች አንድ ቋሚ ወይም ተወራራሽ የሆነ ባህርይ እንደተቀባበሉ መናገር ይቻላል፡፡ ከዳማት (ወይም ዳሞት) በፊት ስለነበረው ሁኔታ ብዙ የምናውቀው ባይኖርም ምናልባት የፑንት ስልጣኔና ሌሎች ያካባቢው ስብስቦችም ለትውፊቱ ምንጭነት ወይም መንደርደሪያነት ሳያገለግሉ እንዳልቀሩ መገመት ያስኬዳል፡፡

ሄዶ ሄዶ የዳማትና የአክሱም አገዛዞች መሰረቶች የተለያዩ ግን በህብረት እየተደጋገፉ የሚኖሩ ህዝቦች (ነገዶች፣ ጎሳዎች ወዘተ) ይመስላሉ፡፡ ለህብረታቸውና ለመረዳዳታቸው የተጠቀሰው የሰሜን ወራሪ ወይም ተቀናቃኝ ህዝቦች (ቤጃዎች ምናልባትም ሌሎች ጋር ተዳምረው;) ተደጋጋሚ እንዲያውም የማያቋርጥ ጥቃት እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ ቤጃዎች በጦርነት ችሎታቸው የላቁ ስለነበሩ ለግብጾች የጎን ውጋት ሆነው መኖራቸው ሲታወቅ ከነሱ በስተደደቡብ ለነበረው የዳማትና የአክሱም አገዛዞች የተለየ ዝንባሌ የሚያሳዩ አይሆኑም፡፡ ስለዚህ የማያቋርጠውን ወረራቸውን ለመመከት የሚያስችል ማህበራዊና ወታደራዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ስርአት ማብጀታቸው የማይቀር ነበር፡፡ ከዚህም በላይ የዳማትና የአክሱም አገዛዞች የሚፈሩትን የወረራ ጥቃት ለመቋቋም ሁልጊዜ መዘጋጀቱ ብቻውን ስለማይበቃቸው እነሱም አጻፋውን ለመመለስ የጦርነትና የወረራ ባህል እየተላበሱ መሄዳቸው አስገዳጅ ውጤት የሆነ ይመስላል፡፡

በአክሱም አገዛዝና ስልጣኔ ውስጥ ሰፊ ድርሻ ካበረከቱት ህዝቦች ውስጥ አገዎች ዋና እንደነበሩ ሁሉም ያውቀዋል፡፡ ነገር ግን ሌሎችም በተደራቢነትና በአጋርነት ይወሳሉ፤ ከነዚህ ውስጥ አጋመ የሚባል ህዝብ በስተምስራቅ እንዲሁም ወለቃ የሚባል በስተምእራብ እንደነበሩ ይተረካል፡፡ ሌሎች ህዝቦች እንደነበሩ ማረጋገጫ ቢኖርም ስማቸውና የነበሩበት ቦታ ስለተለዋወጠ በርግጠኝነት ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ያገዛዙ አባሪነት ወይም የባለቤትነት ድርሻ ሳይኖራቸው በተቃራኒነት ግጭት እየፈጠሩ ከአክሱም ጋር ይተናነቁ ከነበሩት መሃል ስሜኖች በስተምእራብ፣ አግአዝያን በስተሰሜን የሚባሉት ይጠቀሳሉ፡፡

የአክሱም አገዛዝ ካካባቢው ህዝቦች ጋር የነበረውን ግንኙነት በስምምነት ብቻ ሳይሆን በጦርነትና በማስገበር ስላዋቀረው የተደራጀ ጦር ሃይል አሰማርቶ ሁሌም ግዛቱን ለመጠበቅና ለማስፋት ይራወጥ ነበር፡፡ በስሩ ሆነው ግን እያመጹ የሚያስቸግሩትን ለመቆጣጠር ዋናውን ጦር በየስፍራው ማስፈር ብቻ ሳይሆን ተቀማጭ ያካባቢ ምልምሎችን ያበጅ ነበር፡፡ የዋናው ጦርና ያካባቢ ምልምሎች ቅንጅት የአክሱም ህልውናና መስፋፋት ቋሚ መሳሪያ፣ ያገዛዙ ባህርይ ቀራጭ ሆነ፡፡ ጦሩ በያቃጣጫው ዘምቶ፣ አስገብሮ፣ ያካባቢውን አስተዳደር በአካባቢው ሰዎች እጅ አስገብቶ መስራቱ ለህዝቦች መንቀሰቃስ፣ መፍለስና መደበላለቅ በር ከፍቶ ነበር፡፡ የጦር ሰራዊቱና የስምሪት ተግባሮቹ በተለይ ከህብረተሰቡ የተውጣጡ ነገር ግን አገልግሎታቸው ከያሉበት ተሰብስበው በጋራ እንዲኖሩና እንዲሰሩ ያስገደዳቸው በመሆናቸው ወደአንድ አካልነት እየተለወጡ እንዲሄዱ አደረጋቸው፡፡ ካንድ የተለየ ህዝብ የተመለመሉና አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ባለመሆናቸው የየራሳቸውን ባህልና ቋንቋ እየተው ነገር ግን የጋራ መግባቢያ ቀስበቀስ እየፈጠሩ እንዲገኙ ተገደዱ፡፡ ገዥዎቻቸው ግእዝ (በጥቂቱም የጽርእ ቋንቋ) ማወቃቸው ርግጠኛ ቢሆንም ሰራዊቱ መጀመሪያ ጉራማይሌ የመሰለ መግባቢያ (የመገበያያ ቋንቋ) ፈጥሮ ያንን በያለበት መጠቀምና ሌላውን ማስለመድ ተያያዘ፡፡

ከዚህ በፊት ይህንን ሂደት አክሱም  ኢትዮጵያ–የህዝቦች ስብጥርና የአገዛዞች አወቃቀር አጭር ታሪክ በሚለው ላይ ስለተረክነው እንደገና ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ የአማርኛ ቋንቋ አወላለድ በዚህ አኳሃን ነበር፡፡ በዚያን ወቅት አማራ የሚባል ህዝብ የትም ቦታ ስለመኖሩ ማስረጃም ፍንጭም አለመኖሩ በዚህ ምክንያት ነው፡፡ በዚያ ስም የሚጠራ ህዝብ በአክሱም ሆነ ከዚያ በፊት ባለፈው ዘመን አለመኖሩ በዘር ደረጃ አማራ ሆኖ የተፈጠረ አልነበረም ማለት ነው፡፡ ይህ በመላ ምትና በጋለ ስሜት በመወናጨፍ የሚደረስበት እውነት አይደለም፡፡ ፍቅሬ ቶለሳ በሚያስገርም አኳኋን እንደሚለው “የአማርኛ ቋንቋን በተመለከተ ከ3000 አመታት በፊት መወለድ ጀምረ፡፡ እንዲያውም ከተፈጠረ ከግእዝ በፊት አስቀድሞ ረዥም ጊዜ አድርጓል፡፡” ጨምሮም “ ቀዳማዊ ምኒልክ ሲለወለድ አማሮች ንጉስ ሰሎሞን ስለልጁ ምን እንደሚል ይጠይቁ ነበር፣ እናም ‘ምን ይልክ፣ አባትህ’ አሉት፡፡ የአማርኛ ቋንቋ ከ3000 አመታት በላይ ባይኖር ኖሮ እንዴት ብለው ከ3000 አመታት በፊት ምኒልክን ‘ምንይልክ’ ይሉት ነበር;” ይላል፡፡ በግልጽ አነጋገር የቋንቋው አመጣጥ ከታሪክም ከማህበራዊ ሳይንስም ሳይሆን አይንን ጨፍኖ ከመተንበይ የሚገኝ ቢሆን ምን ያህል ጭቅጭቅና ውጣ ውረድ ይቀርልን ነበር፡፡ እንዲህ ካንድ ስም አሰጣጥ ላይ የሚገኝ ከሆነማ ምኑን ምርምር አስፈለገው፡፡ ለነገሩ ያህል ይህ ትረካ ስለዳግማዊ ምኒልክ እንጅ ስለዚያኛው አይደለም፡፡

ይሁንና አማራ የሚባለው ህዝብ ከቋንቋው መፈጠርና መበልጸግ ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ ብርሃኑ አበጋዝ “የኢትዮጵያ አገዛዝ ስልትና እንቆቅልሽ የተሞላበት አማራ” በሚል ጽሁፍ በዘልማድ ምንም ማስረጃ ሳይቀርብ “አማራ” እየተባሉ የሚጠሩትን አካባቢዎች ከዘረዘረ በኋላ ዛሬ “አማራ” የተሰኘው ቃል በሶስት አይነት አጠቃቀም እንደሚውል ይናገራል፡፡ አንዱ የሃይማኖት መለያ ሲሆን፣ ሁለተኛው ብሄራዊ ማለትም የኢትዮጵያዊነት አመልካች፣ የፖለቲካዊ ማንነትን መግለጫ፤ ሶስተኛው የቋንቋውን ተናጋሪዎች የሚጠቁም ነው፡፡ ሁለተኛውን ገንጥሎ የተዳቀሉ ክፍሎች፣ በይበልጥ በከተሞች የሚኖሩት የሚጠሩበት አድርጎ ያወጣዋል፡፡ ነገር ግን ለዚህ ሃሳቡ ማስረጃ የለውም፡፡ የግምት አነጋገር ሰነዘረ እንጅ፡፡ ገና ከመነሻው የአማራ ህዝብን ማንነትና አመጣጥ ሳይመረምረው በይበልጥም የዛሬውን ትቶ የዱሮውን ሁኔታ ሳያጤነው መጨበጫና መቋጠሪያ የሌለው ትረካ ያቀርባል፡፡

በርግጥ “አማራ ነህ እስላም;” የሚለው የቆየ የዘልማድ አጠያየቅ እንደሚያመለክተው “አማራ” ማለት ለዘር (በውልደት ዝምድናው ለሚታወቅ) የተሰጠ ስያሜ ከመሆኑ በፊት የእምነት መለያ ሆኖ ጥቅም ላይ ይውል ነበር፡፡ አሁን አሁን ያ አጠቃቀም እየቀረ “ክርስቲያን ነህ እስላም” ወደሚለው ተለውጧል፡፡ አማርኛ የሚናገር ሰው እስላምም መሆን ስለሚችል የቀድሞው አጠያየቅ ምናልባት በገጠሩ አንዳንድ አካባቢዎች ብቻ እስካሁንም ይነገር እንደሆን እንጅ በከሞች እጅጉን አይሰማም፡፡ በግልባጩ ደግሞ አማርኛ ስለተናገሩ “አማራ” ነው የሚያሰኝ ግምት እየጠፋ ሄዷል፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሊ ሃብተ ወልድ ጄኔራል ታደሰ ብሩን በአማራነት መድቦ ስለኦሮሞዎች መማር ያለውን ስጋት ሲያካፍለው በዚያ የተሳሳተ ግምት ውስጥ እንደነበር ልንገምት እንችላለን፡፡
የብርሃኑ አበጋዝ ሁለተኛው የአማራነት ፍቺ እንዳልነው ማስረጃ ካለማቅረቡ ሌላ በውስጡ ብዙ ችግር አለበት፡፡ ዛሬ አማራ ተብሎ “ክልል” ተበጅቶለት በአንድ አስተዳደር ስር የገባው ህዝብ በሙሉ የዘር መሰረቱ የተደበላለቀ ነው፡፡ በታሪክ፣ ከመጀመሪያው (ካክሱም ዘመን) አንስቶ እስከዛሬ ድረስ፡፡ ስለሆነም ከያቅጣጫው በዘመቻ፣ በፍልሰት፣ በአስተዳደራዊ ምስቅልቅልና በሌሎችም ምክንያቶች አማርኛ ተናጋሪ ሆኖ የወጣው ህዝብ በአንድነት ተመድቦ “አማራ ነህ” መባሉ የጽንሰ ሃሳብና የፖለቲካ ችግሮች አሉበት፡፡ አንድ ህዝብ ለማንነቱ መግለጫው ከሁሉም በላይ ቋንቋ ይሁን እንጅ በብሄርነት ለመቆም እንዲችል የስነ ልቦና ውሁድነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ (ይህን ጉዳይ በተመለከተ በዚሁ መጽሃፍ ቁጥር 12ን ያንብቡ፡፡) ታዲያ በከተሞች ባብዛኛው የአማርኛ ተናጋሪነት እጅግ አስፈላጊና ለመኖርና ለመስራት አስገዳጅ እንደመሆኑ ባገሪቱ በሙሉ ያሉ ከተሞች የአማራ ከተሞች ናቸው ማለት አያስኬድም፡፡ ህዝቡም ቢሆን ሁኔታው እያስገደደው ካልሆነ በስተቀር ማንነቱን በቋንቋው ብቻ የሚለካና አማራነትን የሚቀበል ወይም የሚጠቅስ አይሆንም፡፡

ስለሆነም የብርሃኑ አበጋዝ የአማራነት መለያ ቁጥር 2 ከፊል ገጽታውን ወደሙሉነት የማሸገገር ያስተሳሰብ ዝላይ ነው፡፡ ማለትም ከአማራው ውጭ አንዳንድ አካባቢዎች “ኢትዮጵያዊነት”ን መቀበላቸው በሁሉም ዘንድ የተስፋፋና ስር የሰደደ ክስተት አይደለም፡፡ ባንድ በኩል፣ ብዙ ድግግሞሽ ውስጥ ሳንገባ፣ እንኳን አማራነትን ከኢትዮጵያዊነት ጋር ማዋደድ (ማጣመር፣ ማቀላቀል) ይቅርና በተለያዩ ህዝቦች መደበላለቅ ብቻ ወደአማራነት መሸጋገር ተችሏል ብሎ መናገር መሳሳት ነው፡፡ የአማራ ህዝብ እየተባለ የሚጠራው ራሱን ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ያላንዳንች ችግር ቢቀበልም ሁሉም “አማራ ነን” ማለታቸው አጠያያቂ ነው፡፡ በዚህ ላይ በአገዛዙ ላይ የበላይነት ኖሮት ለዘመናት የቆየው ገዥ ክፍል ራሱን በአማራነት እየቀረጸ መምጣቱና የጥቅም ክፍፍሉ በዚያው መልክ መወሰኑ እየገፋፋቸው “አማራ ነን” ማለትን የሚመርጡት አማርኛ ተናጋሪ ግን ሌላ ቋንቋ የናት ቋንቋቸው የሆኑ ዜጎች እውነተኛ ማንነት ጉዳይ ግልጽ አይሆንም፡፡ እንዲያውም ያገሪቱ ትልቁ ችግር ከዚህ የመነጨ ነው፡፡ ከ1983 ወዲህ ህዝቡ በያለበት የራሱን ማንነት እንዲያበጃጅ በተፈጠረለት እድል ተጠቅሞ በሚያደርገው መነቃነቅ ስንቱ ነው በትክክል ይህን ሊረዳውና ወደሚመኘው ሊሸጋገር

የቻለው; የሚችለውስ; (የስልጤዎችንና መሰል ህዝቦች መተራመስ በአብነት ማንሳት ይበቃል፡፡)
በቅርቡ በካናዳ በተደረገ የሬዲዮ ቃለ ምልልስ አቶ አሰፋ ጫቦ በጋሞ ጎፋ ውስጥ ስላጋጠሙት “ነፍጠኞች” ያወራው አስደናቂ ነገር እዚህ ላይ ትዝ አለን፡፡ በሱ አመለካከት በምኒልክ ስር በአዛዥነት እንጅ በተራ ወታደርነት (በ“ነፍጠኛነት”) በጋሞ ጎፋ ሆነ በደቡብ ባጠቃላይ የዘመቱ ባብዛኛው ኦሮሞዎች ነበሩ! በጋሞ ጎፋ የነበሩትን አዛዦቹን ከነስማቸው እየዘረዘረ አማራ መሆናቸወን ሲያወሳ ሌሎች ግን ኦሮሞ እንደነበሩ እንደደረሰበት ተርኳል፡፡ ለካስ በደርግ ዘመን “በነፍጠኞች” ውስጥና መካከል እርስ በርስ መጋጨት ተፈጥሮ አቶ አሰፋ ጫቦ በአገር አስተዳዳሪነቱ ለማስታረቅ ባደረገው ጥረት ሁለቱም ተቀናቃኞች ስማቸው እስከአያታቸው ሲዘረዘር ኦሮሞ ነበሩ! ተከሳሾች (ጠብ ፈጣሪዎች) ኦሮሞነታቸውን ሸሽገው በአማራነት ራሳቸውን እንደመደቡ ሲተርክ የጥቅም ጉዳይ አይሎባቸው ከገዥዎች ጋር መወገናቸው ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ገልጾዋል፡፡

በተገላቢጦች መልክ ብርሃኑ አበጋዝ አማሮች ከሁሉም ህዝቦች በላይ የዘር ጉዳይ እንደማያስጨንቃቸው፣ ገዥዎቻቸውም (የሌቪንን ትንታኔ ተውሶ) ትልቅነታቸው ብዙ-ዘርን የሚያቅፍ (በዘር ሳይሆን በማህበረሰብነት) የአመራር ስልት እየተጠቀሙ የውጭ ወራሪን መቋቋማቸውንና የባህሎችን መጠጋጋት አከናውነው የታላቋን ኢትዮጵያ እቅድ ማራመዳቸውን ይጠቃቅሳል፡፡ ነገር ግን የአማራ ህዝብ ማንነት ገና በመዋቀር ላይ እንዳለ፣ ከተለያዩ ህዝቦች መቀያየጥ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ሂደቱ እንዳልተጠናቀቀ እንጅ ከሌሎች ህዝቦች የተሻለ ወይም የተለየ ሰብእና (አገር የመገንባት ተልእኮ ወዘተ) ስላለው እንዳልሆነ አልታየውም፡፡ ዋለልኝ መኮንን በጉልበት ወደአማራነትና ኢትዮጵያዊነት የሚያመራውን የአገዛዙን አሰራር ከተቃውሞ ጋር የዘረዘረውን ብርሃኑ አበጋዝ በምጸት መልክ አንስቶ ጭራሽ የረሳው መልካም ነገር እንደነበርና (የምግብ አይነቶች፣ አንዱ ዘር ከሌላው ጋር መጋባት፣ “ይሉኝታ”) ያ የሚያወግዘው የእድገት ጎዳና የተለያዩ ባህሎችን ወደ “ኢትዮጵያዊነት” እንደሚሸጋግር ያትታል!

ለማጠቃለል፣ ለብዙ የብሄር/ብሄረሰብ ማንነትና ነጻነት ጉዳይ ተሟጋቾች አስቸጋሪ የሚሆንባቸው ዛሬ ላይ ቆመው ወደኋላ ተመልክተው የዱሮውን እንደገና በፈለጉት አኳኋን ለመቅረጽ መፈለጋቸው ነው፡፡ የዛሬውን ምን ለማድረግ ከመወሰናቸውና የወደፊቱን ለመተለም ከማሰላሰላቸው በፊት የነበረውንና በታሪክና በፖለቲካ የተከናወነውን ከነምክንያቶቹ ፈልፍለው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የአማራው ህዝብ አነሳስ፣ ምንነትና የወደፊት እድልም እንደዚሁ አስቀድመው በጭንቅላታቸው ውስጥ ባስገቡት ስሜትና በደም ፍላት የሚፈረድ አይደለም፡፡ ታሪኩን ያጥኑ፣ እስካሁንም ኢትዮጵያን የሚወሰውሷትን የእድገት ጎዳናዎችና የእንቅፋት ጉድጓዶች ይለዩ፡፡ ለምሳሌ ከላይ የተጠቀሰው የሌቪን አስተያየት ከአክሱም አገዛዝ ብሎም ከዛጉዌ ነገስታት የተወረሰ አመራር እንጅ ከአማራው ክፍል የተቀመመ እንዳልነበረ ያገኙታል፡፡

አሰፋ እንደሻው

አሁን ከምንጊዜውም በበለጠ የጨበጣ ውጊያ ላይ ነን!

ምሕረቱ ዘገዬ

The end times are here and Bible prophecy is fast being fulfilled. “The hour of temptation, which shall come upon all the world, to try them that dwell upon the earth.” (Rev 3:10) will soon be upon us, and all who are not firmly established upon God’s Word and the righteousness of Jesus Christ will be deceived and overcome. Satan “works with all power and signs and lying wonders .. with all deceivableness of unrighteousness” (2 Thess. 2:9-10) to gain control of mankind, and his deceptions will increase right up to the very end.( http://www.end-times-prophecy.org/)

በተለይ ኢ-አማኒያንና ሴቴኒስቶች (atheists and satanists) ይህን ጽሑፍ እንዲያነቡ አልመክርም፡፡ ሁለቱም ልዩነታቸው አንድነታቸው ነው – ስልቻ ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎ ስልቻ፡፡ ዋጮ እንተገልበጥካዮ ዋጮ ኢዩ ከምዝብል ወዲ ትግራይ፡፡ ተጠራጣሪዎችና ከክርስትና ውጪ ያሉ የሌሎች ሃይማኖቶች ተከታዮችም ይህን ጽሑፍ ባያነቡት ይሻላቸዋል – እምብዝም አይጠቅማቸውም፡፡ … በዚህ ከቀጠልኩ ካለአንባቢ ልቀር ነውና “ማዕቀብ መጣሉ” ይቅርብኝ፡፡ መተቸት ይቻላል፤ ትችቱ ግን በዕውቀትና ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ይሁን – ከስሜት ሣይሆን፡፡

2053fountain_pen

ውድ አንባቢ ሆይ ዘመንህን መርምር፡፡ በቅድሚያ ግን በዚህች የደም መሬት በሆነች ወያኔን የመሰሉ አጋንንት መፈንጫ ሀገራችን ውስጥ ሰሞኑን በተከሰተው ወያኔያዊ ድራማ ሳቢያ ጋምቤላ ውስጥ ለተጨፈጨፉ ንጹሓን ሰማዕታት ወገኖቻችን የተሰማኝን ሀዘን መግለጽ እፈልጋለሁ – በአሁኑ ሰዓት ነፍሳቸው በነአብርሃምና ያዕቆብ አጠገብ መሆኑን ብረዳም ደንብ ነውና “ጌታ ነፍሳቸውን ይማር” እላለሁ – እንጂ በሰይጣናት ከሚቀላ አንገት የሚወጣ ነፍስ በምን አበሳው ሲዖል ይጣላል ብዬ ልመን? ጭፍጨፋንና ግፍ-በደልን ልብሳችን አደረግነውና ሀዘናችን የታመቀ መሰለ እንጂ ይህ የደረሰብን አሰቃቂ ውርጅብኝ ሀገር ምድሩን ማቅ የሚያለብስና – የኛ የሁላችን የምንለው መንግሥት ቢኖረን ደግሞ – ቢያንስ ለሰባት ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን የሚያሳውጅ  ነበር፡፡ ግና ዕድሜ ለወያኔ ዱሮ ገና ጫካ እያሉ ጀምሮ የሽሬን የገበያ ላይ ዕልቂት ጨምሮ ዐርባጉጉንና በደኖን ይዞ እስካሁኒቷ ሰዓት ድረስ ይኼውና በደም እየዋኙና እያስዋኙን ይገኛሉ፡፡ ይህ ሰሞነኛ ዕልቂት ወያኔ በእጅ አዙር ያደረገው ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ የጃቸውን ይስጣቸው፤ ፍርዳቸውንም በቅርቡ ከፈጣሪ ዘንድ እንደሚያገኙ በበኩሌ አልጠራጠርም፡፡

በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ሀገራችን ቢያንስ እንደደርግ ያለ ዐረመኔ የሚባል መንግሥት እንኳን ቢኖራት ኖሮ 200 እና 300 ሰው ተገድሎና ቆስሎ ይቅርና አንዲት ድመት ወይ አንድ ውሻ እንኳን በሌላ ሀገር ቢደፈሩ ብሔራዊ ጦርነት የሚያሳውጅ ትልቅ ክስተት ነው፤ እንደሀገርና ሕዝብ ቅስምን እስከወዲያው የሚሰብር ትልቅ ውርደት ነው የገጠመን፡፡ ሀገሩንና ሕዝቡን ሳያውቅ ብቻ ሳይሆን በማወቅ ሆን ብሎ እንደጠላና እንዳዋረደ፣ አዋርዶና ጠልቶም ለባዕድ ጠዪና አዋራጅ የዳረገ እንዲዘህ ያለ “መንግሥት” በዓለም ታሪክ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አያውቅም፡፡ ሂትለር እንኳን ከስድስት የማያንሱ የአውሮፓ ሀገራትን በወረራ ይዞ ሲገዛ ሕዝቦችን እንደራሱ ሕዝብ አድርጎ እንጂ እንደጠላት አልቆጠረም፡፡ የነዚህ የተለዬ ነው፤ አመጣጣቸውንና ሥነ ተፈጥሯቸውን ለሚረዳ ግን ከእንደነሱ ዓይነት ፍጡር መልካም ነገር እንደማይጠበቅ ያውቃል – የነሱ ዕኩይ ተግባር ከሰይጣን ከራሱም የከፋ እንደሆነ ሰይጣን ራሱ ሊመሰክረው የሚችለው የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ ሀገራችን ምን ዓይነት ውርጅብኝ እንደተጣለባት ምናልባት ጨለማው ሲገፈፍ ይበልጥ የሚታይ ይሆናል፡፡ ወደድንም ጠላንም መገፈፉ ደግሞ አይቀርም፡፡ ሲገፈፍ ግን እንዲህ በቀላሉ እንዳልሆነ ልብ ይሏል፡፡ በቅድሚያ ሀርሽ ቀልጦ ነው በኋላ ደጉ ዘመን የሚብተው፡፡ እንደሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢት ከሆነማ “አያድርስ!” ብለን ሱባኤ ገብተን  መጸለይ ይርብናል፡፡ በግምባር ብዙ ጉድ አለብን!

ይህን ልብ እንበል፡- እነዚህ የጥልቁ አባላት ጀመሩ እንጂ አልጨረሱም! ገና ብዙ ውድመት ያደርሳሉ፡፡

ዘመንህን መርምር፡፡ በአሁኑ ወቅት በአጋንንት ሠራዊት ቁጥጥር ውስጥ ያልገባ አንድም የምድራችን ክፍል የለም – ከአይሲስ እስከ አልሻባብ፣ ከቦኮሃራም እስከ ቱዋሬግ፣ ከሀሽሽ ካርቴል እስከ ታሊባን፣ ከኢሉሚናቲ እስከ ሕወሓት … ሁሉን አጢናቸው፤ ዓለምን ወደ መጨረሻ የውድመት ደረጃ እያቃረቡ ያሉ የጥልቁ አባላት ናቸው፡፡ ዜናዎችን ተከታተል፡- (ሱፕሪም ማስተር ቺንግሃይ ከምትባለዋ “የተገለጠልኝ ነኝ(Himalayan Enlightenment)” ባይ ቴሌቪዥን በስተቀር) ቢቢሲና አልጀዚራን በመሳሰሉ ሌሎች ዋና ዋና የዓለም መገናኛ ብዙኃን ምን የሚያዝናናና መንፈስን የሚያድስ ዜና ሰምተህ ታውቃለህ? ከሞላ ጎደል ሁሉም የዓለማችን ዜና ሽብርና ፍርሀት የሚለቅ ነው – “አይሲስ ኢራቅ ውስጥ የያዛቸው 475 ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን ወደእስልምና ለመቀየር ባለመፈለጋቸው አንገታቸውን በሠይፍ ቀላቸው፤ ወ/ሪት ጽንሰ-ሰንበትና ወ/ሪት ምንይሉሽ ባለፈው ዓርብ በኮንቲኔንታል ሆቴል ብዙ ዕድምተኛ በተገኘበት የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸውን ፈጸሙ፤ ሚስተር አንትሩማንና ሚስተር ዎልፍጋንግ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጌይ ሶዶማይት ዳግማዊ ባከናወኑላቸው የጸሎት ሥነ ሥርዓት ጋብቻቸውን ድል ባለ ፈንጠዝያ አከናወኑ….” የሚሉ ዜናዎች በሞሉባት ምድር ከአሁን በኋላ ምን ትጠብቃለህ?

ይህ ዓለምን በሰይጣናዊ ኃይል የመበወዝና አዲስ የዓለም መንግሥት የመመሥረት ክስተት (New World Order) በስፋትና በጥልቀት የተጀመረው እንደ አንዳንድ መረጃዎች ከሆነ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ነው፡፡ እርግጥ ነው  – ከዚያም በፊትና በቅድመ ልደተ ክርስቶስ ዘመንም አሁን የሚታየው ዓይነቱ  የሰው ልጅ ፍጅትና የእርኩሳን መናፍስት ጥቃት እንዲሁም የተፈጥሮ አደጋዎች በሰው ልጆች ላይ ይደርሱ ነበር፡፡ ከ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ ያለው ግን የብዙዎችን ትኩረት በሚስብ መልኩ ለየት ያለ ነው፡፡ ኋላ እንዳይቆጭህ መርምር ዘመንህን ታዲያ፡፡ ከትንቢቶች አንድስ እንኳን አልቀረም፤ ሁሉም ተሟልቷል፡፡ ይህን ግልጽ እውነት እንዳታውቅ ለማደደብ ሲባል ግን ዓለምን የተቆጣጠሩ የመሰላቸው የጥልቁ አባላት በ Mind Control (MC) ፕሮግራሞቻቸው አእምሮህን ሰንገው ይዘውታል – በፈጣሪህ ተስፋ ቆርጠህ እንድታምጽና ኤቲይስት እንድትሆን የምትገፋፋውም ለዚህ ዓላማ ነው፡፡ ምክንያቱም “ፈጣሪ የለም” የሚል ሰው ለኅሊናው ካላደረ በቀር ለምንም ዓይነት ወንጀል ቅርብ ነውና፡፡…

(እንደ መልካም ዕድል ሆኖልኝ ልበል ይሆን?) አንዳንዴ ሰይጣንን በመገሰጽ ሲሳካልኝም በማስወጣት የ“አማተር” ሥራ ላይ እሳተፋለሁ – (Believe me, I had and still have an experience of driving out evil spirits, you may say ‹exercising exorcising›. And I am not boasting of it but I want to make known the fight I seldom face with Mr. Satan.)፡፡ በዚያም ምክንያት ከብዙ የዓለም ዜጎች ሻል በሚል ሁኔታ ከክፉ መናፍስት ጋር የመወያየት፣ የመከራከርና ዕድል ከተባለ የመጨቃጨቅ ዕድል አለኝ፡፡ እነዚህ መናፍስት ከተራ የመንደር አውደልዳይ ልክስክስ መንፈስ አንስቶ ከፍ ያለ ዕውቀትና የኃላፊነት ደረጃ እስካላቸው “ቱባ ባለሥልጣናት” ይደርሳሉ፡፡ ብቻ በሰዎች ላይ ሲከሰቱና እንዲቀበጠጣጥሩ በእግዚአብሔር ኃይል ሲታዘዙ የሚሉት ብዙ ነው፤ ሁሉንም የሚናገሩትን (እንዳለ) ማመኑ ቢከብድም ከሚቀበጣጥሩት ውስጥ እውነት የለበትም ብሎ መደምደም ግን አይቻልም፡፡ አጠያየቁንና የ“ውይይቱ”ን አካሄድ ላወቀበት ሰው ብዙ ነገር ሊገበይ ይችላል፡፡ አጋንንት ሳቢ ደብተራዎችም እኮ ምሱን እያሟሉ (ከ“እክህደከ ክርስቶስ” ጀምሮ) በመቅረብ ነው በርካታ ዲያብሎሣዊ ሥራዎችን የሚ(ያ)ሠሩት፡፡ እናም እኔ በበኩሌ “እንዲህም ነኝ”ና ከላይ ከመግቢያየ ጀምሮ እስከታች በምላችሁ ነገር ብዙም አትጠራጠሩኝ – የሰውነት ዕዳ ከሚያስከትልብኝ የዐቅም ውሱንነት ውጪ ሆን ብዬ ላምታታና ሃይማኖትን ልሰብክ የምናገረው ነገር የለኝም፡፡ ለምን ብዬ? ለዚህች አንድ ሐሙስ ለቀራት ዓለም ምኑ ሲቀርብኝ ብዬ ሆን ብዬ እዋሻለሁ?

ሀገርህን ተመልከት፡፡ ይህ ከጥልቆቹ አባላት የተላከ የአጋንንት መንፈስ ያልተቆጣጠረው ቦታ ፈልግና እስኪ ንገረኝ? በሁሉም አቅጣጫ ተወጥረናል፡፡ አጓጉል ቀን ሲገጥም ቅል ድንጋይን ይሰብራል፤ ባሪያ የጌታዋን ሚስት ስትቀማና ቀጥ ያለ ጠፍቶ ጎባጣ ሲመለመልም አንድ ነው – ዘመኑ ይንጋደዳል፤ ቀኑ ይጨልማል፤ ያኔ ታዲያ ውሻ ወደሣር አህያ ወደሊጥ ቢሄዱ አይግረምህ – ማሙሽ በዱላ ቢነርትህ፤ ሚጡዬ በጅራፍ ብትገርፍህ ምን ታደርጋለህ? አስቀድመህ ከነቃህ ብዙ ልታደርገው የምትችለው ነገር አለ፤ እንዳትነቃና ይባስ ብሎም በሆነ ግልጽ ወይ ሥውር ኃይል እንዲደብትህ ከተደረግህ ግን ብቸኛ ምርጫህ “እስኪያልፍ ያለፋል!” እያልክ መጽናናት ነው – ተኝተህ፡፡ በቅድሚያ የመንፈሱን መገለጫዎች መጠቆሙ ተገቢ መሰለኝ፡፡ እስኪ በመጠኑ እንመልከት፡-

የመንፈሱ ዋና ተልእኮ የሰውን ልጅ ከክብሩ ማውረድ ነው፤ ፍቅርን ከምድር ማጥፋት ነው፡፡ እኛ ሰዎች ስንፈጠር በክብርና ለክብርም ነበር፡፡ በእግዚአብሔር አምሳል እንደመፈጠር ያለ ክብር የለም፡፡ የአሁኑን አያድርገውና መላእክት እንኳን፣ የኛን ያህል ክብርና ሞገስ እንዳልነበራቸው መጻሕፍተ ቅዱሣት ይመሰክራሉ፡፡ እናም አማፂው መንፈስ ቀድሞ ክብሩን ከተገፈፈ በኋላ የኋለኛውን ፍጡር አዳምን ከሞቀ ቤቱ ሊያስወጣ ሞከረ፤ ለተወሰነ ጊዜና በተወሰነ ደረጃም ተሣካለት፡፡ ይሄውና አሁን ዓለማችን ፍዳዋን የምትበላው በዚህ የዝኆኖች ፍልሚያ ነው – ክፋትንና ደግነትን እንደሁለት ተፎካካሪ ጎራዎች ወስደን ካወዳደርን ማለቴ ነው እንጂ ሣጥናኤል ከፈጣሪ ጋር የሚተካከል ሆኖ አይደለም፡፡ አሁን ግን አይካድም ዓለምን አንቀጥቅጦ እየገዛ ነው – በወኪሎቹ አማካይነት፡፡

እግዚአብሔር ሁሉን ነገር አሟልቶ ፈጠረን፤ ክብራችን በአመፀኛው ሽፍታ እስኪጓደልብን ድረስ እኛ ገነታውያን አንድም ነገር የሚቸግረን አልነበርንም፡፡ በኋላ ግን የሆነው ሁሉ ሆኖ ወደምድር ስንጣል በላባችንና በድካማችን ፍሬ እንድንተዳደር ተፈረደብን፡፡ ከዚያ በኋላ በመጡ ነገሮች ተጠያቂዎቹ በአብዛኛው እኛው ነን ወይም ልንሆን ይገባናል፡፡ ክፍተቶቻችንን ለማሟላትም ብዙ ጣርን፡፡ አዲሱን የምድር የመከራና የፃማ ኑሮ ለመጋፈጥ ዕውቀት መጨመር ነበረብን – በያይነቱ ጨመርን፡፡ ቴሌፓቲ በስልክ ተተካ፣ ቴሌፖርቴሽን በአውሮፕላን ካርጎ፣ በዚታ መኪኖችና በመርከብ ተተካ፣ ክሌቮራንስ በራጅ፣ በአልትራሳውንድና በስካነር ተተኩ፣ አስትራል ትራቭል በስፔስ ሻትሎች (በመንኮራኩሮች) ተተኩ … በርግጥም ፈተናውን ተጋፈጥነውና የላይኛው “አሃ! እነዚህ ፍጡሮቼ ለካንስን ምንም አይሉምና!” ብሎ “እስኪደነቅ” ድረስ በሥልጣኔ ተራመድን – ለጉድ መጠቅን እንጂ፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው? “የማያድግ ልጅ በአባቱ መሽኛ ይጫወታል” እንዲሉ ሆኖብን ያ የቀድሞ ጠላታችን ሣጥናኤል ተከትሎን መሬት ወረደና ሁሉንም መልካም ነገር በዳግማዊ ዐመፃ በከለው – ሥልጣኔያችን በቅጽበት ወደስይጣኔ ተቀየረና ብዙም ሳናጣጥመው ሁሉ ነገራችን ለመጥፊያችን ዋና መራጃ ሆኖ በተለይ ቀጣይ ትውልዶቻችን ባጭር ይቀጩብን ጀመር – (በአንድ ዐይናው ፒራሚድ ቁጥጥር ሥር በሚገኙ የ“መዝናኛ” ኢንዱስትሪዎች ተመርተው ወደገበያው የሚረጩትን ፊልምና ሙዚቃዎችን አስታውስ)፤ መንገድ መሥሪያ ዲማሚቱን ወደ ቦምብ፣ የተፈጥሮና ማኅበራዊ ሣይንሱን ወደ ሰው ልጅ ማውደሚያ፣ ምርምሩን ወደ ክህደት አምባ መውሰጃ … አደረገውና ከራሳችንም ከፈጣሪም ሣንሆን አውላላ ሜዳ ላይ አስቀረን – ከሁለት ያጣ ጎመን፡፡ በወያኔነት የምፈርጀው ሰይጣን ቂም አይረሳም፤ ጥላቻን ወደፍቅር የመለወጥ ባሕርይም በጭራሽ የለውም፤ እንቅልፍን የማያውቅ እጅግ ክፉ የክፉ ክፉ ጠላት ነው፡፡ ሊያጠፋው የዛተበትንና ቀን የቆረጠለትን አካል ልክ እንደወያኔ እግር በግር እየተከታተለ ሳያጠፋው አይለቀውም፡፡ ሰይጣን + ወያኔ = ሲዖል + ገሃነም፡፡

እናም እንዲህ ሆነ፡፡ “ሰይጣን ሰውን የማጠፋውና ከክብሩ የምለየው ምን ባደርግ ነው?” ብሎ “ በምሁራኑ ጥናት አደረገ”፡፡ የጥናት ውጤቱም “ሰውን ማጥፋት የሚቀለው፣ ሰውን ከፈጣሪ ክብር ገፍፎ ራቁቱን ማስቀረትና የኛ ባርያ ማድረግ የሚቻለው በሚወደውና በተከለከለበት ሲመጡበት ብቻ ነው፤ አዳም በተከለከለበት ጠፋ፡፡ በሚወደው ለመምጣትና የተከለከለውን እንዲያገኝ ለማድረግ ደግሞ በቅድሚያ መሪዎቹንና የሚወዳቸውን አባላቱን አ(ሳ)ስተን የኛ አባል ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ተራው ጀሌ እንደሆነ ከፊት ለፊቱ ያለው መሪና ታዋቂ የሚባል ሰው ከእምነቱ ወጥቶ በኛ ምሪት ሲነጉድ ካየው እርሱን ይከተላል፤ በዚያ ላይ ፍላጎቱን እየተከተሉ ማሟላት ነው፡፡ ልምዱ እንዳይጓደልበት መጠጡንም፣ ሙዚቃውንም፣ የዕርቃን ዳንስና ጭፈራውንም፣ የወሲብ ፊልሙንም፣ ሀሽሹንም፣ ጫቱንም፣ … ሁሉንም መሣሪያዎቻችንን ወልውለን እንደየአቅሙ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባናል፡፡ ከዚህ ወጥመድ የሚያመልጥና ከኛ ፍላጎት አንጻር የሚራመድ ቢኖር የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ይኖርብናል፤ የምድር መንግሥታችንን የምንመሠርተው በዚህ መልክ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ያለው ብልኃትና ዘዴ ብዙም አያዋጣም፡፡ ተግባር እንጂ ስብከት ብዙም ፋይዳ የለውም፡፡” የሚል ነው፡፡ የዓለም የአሁኑ ቅርጽ የተንጠለጠለበት መስቀያም የዚሁ ጥናት ውጤት የሆነው ሰይጣናዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡ (እ.አ.አ. 1972)

ሰይጣናዊ መገለጫዎች ምንድናቸው? ቀላል ጥያቄ ከቀላል መልስ ጋር፡፡ ክፉ ነገር የምትለው ሁሉ የሰይጣን ነው፡፡ ደግ ነገር የምትለው ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን ችግር አለ – የአንጻራዊነት ችግር፡፡ የትኛው ደግ ነገር ለ(ነ)ማን ነው ደግ የሚሆነው? የትኛው ክፉ ነገር ለ(ነ)ማን ነው ክፉ የሚሆነው? ትልቅ ችግር ይመስለኛል – በተለይ ባለንበት ዘመን፡፡ ለምን ቢሉ ብዙዎቻችን በክፉና በደግ መካከል የነበረው ልዩነት ጠፍቶን ሁሉ ነገር ተወነባብዶብናል፡፡ የክፉ ዘመን ክፋቱ ይሄ ነው – የክፋትንና የደግነትን ድንበር ለይቶ አለማወቅ፡፡

ሰይጣን ከባድ ተፎካካሪ ነው፡፡ ግን ግን በአንዲት “በስማም” ዐርባ ክንድ የሚሸሽና ገደል የሚገባ ቦቅቧቃ ነው፡፡ ልብን ይጠይቃል፡፡ እርሱ እንደሚፈልገው እየሆንክለት ብታወግዘው ጓደኛው ነህና አንድ ቀርቶ አንድ ሺህ ውዳሤ ማርያምና መግረሬ ፀር ብትደግም ያሾፍብሃል እንጂ ስንዝር አይርቅልህም፡፡ ለዚህ ነው በየቤተክርስቲያናቱ አናት ቂብ ብሎ ቅዳሤውን በሥነ ሥርዓት እየኮመኮመ የሚያድረው፡፡ እኛም ልባችን ሌላ አንደበታችን ሌላ፣ እግራችን እዚህ ልባችን እዚያኛው … እየሆንለት መላ ሰውነታችንን እንደልቡ ይቆጣጠራል፡፡

ለማንኛውም የሰይጣን መገለጫዎች ብዙ ቢሆኑም ጥቂቶቹን አፌ እንዳመጣልኝ መናገር እችላለሁ – ዘረኝነት፣ አመንዝራነት፣ ሥልጣንን (ለራስ ዓላማና ፍላጎት) ከልክ ባለፈ መውደድ፣ ከተፈጥሮ ውጪ በሆነ ወሲብና ወሲባዊ ስሜት መጠመድ፣ ሀሰት መናገር፣ ገንዘብን ማምለክ(ከመጠን በላይ መውደድና ማፍቀር)፣ ሰውን ሁሉ እንደራስ አለመውደድ፣ ማጭበርበር … ማለቂያ የላቸውም እህቴ፡፡

የዓለምን ወቅታዊ ሁኔታ መርምር፡፡ ግብረሶዶማዊነትንና ሌዝቢያዊነትን  በግድ ሊጭኑብህ ከጥልቁ የተላኩ ባለዘንዶ ቀለበት የዓለም ባለሥልጣናት በሀገርህ በቅድስቲቷ ኢትዮጵያ ሣይቀር  አልመጡብህም? ወንድና ወንድን ካላጋባችሁ ዕርዳታና ብድር አንሰጣችሁም አልተባልክም? ብዙ ሽቁጥቁጥ ሀገሮች የተመሳሳይ ፆታን ጋብቻ ካልፈቀዳችሁና ህገ መንግሥታዊ የህግ ሽፋን ካልሰጣችሁ “ወዮላችሁ! ማዕቀብ እንጥልባችኋለን” እየተባሉ አይደለም? የኃያላንን ፖለቲካዊና ምጣኔ ሀብታዊ ተቋማት ዓርማዎችንና ባንዲራዎችን እስኪ ለአፍታ ቃኘት አድርግ፡፡ እስኪ ፍየሊቷንና የሦስት ማዕዘኗን ሉሲፈራዊ ተምሣሌት ፈልጋቸው – ከነማን ጋር ነው ያሉት?  “ማርታ ለ(ማን?)ምን ለምን ሞተች” … የሚባል መዝሙር ትዝ አለኝ፡፡ ሁጎ ሻፌዝ ለማን ለምን ሞተ? ደንቆሮው መንግሥቱ ኃይለ ማርያም በዘዴ ከሀገር እንዲወጣና ቅንቅኖቹ የጥልቁ ታዛዦች አራት ኪሎን እንዲቆጣጠሩ የተደረገው ለምንድን ነው? ሀገርህ በጥልቁ ቁጥጥር ሥር ነች ወንድሜ፡፡ ምን ኢትዮጵያ ብቻ – ሁሉም እንጂ፡፡

ለሰይጣን የሚቀርበው ዋናው ግብር ደም ሲሆን ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ዋናው መስዋዕት ደግሞ ፍቅር ከ“ተመስገን” ጋር ነው – በቃ፤ “ተመስገን አምላኬ” ካልክ ትልቁ የፈጣሪ “ጉቦ” ነው፡፡ ደም አይፈልግም፤ የዘመድ አዝማድ ምልጃ አይፈልግም፤ ሰንደልና ጪሳጪስ አይፈልግም … ፡፡ እውነተኛ ፍቅር ካለህ ሁሉም ነገር አለህ፡፡

የደም ግብር እየታደሰ የሚሄድ ሰይጣናዊ ግዴታ ነው፡፡ በሰይጣን የሚገዙ ሰዎች ተመቸን ብለው ግብሩን ቢያቋርጡ ወይም ሥልጣኑን ቢገዳደሩ ወዮላቸው፤ መጨረሻቸው የዶጋ ዐመድ መሆን ነው፡፡ ኃይለ ሥላሤን ያዬ በሰይጣን ሥልጣን አይቀልድም፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ቱባ ቱባ የዓለም ባለሥልጣኖችና ሀብታሞች የጥልቁ አባላት ናቸው፡፡ ይህን መናገር ስህተት አይደለም፤ “እኔ ግን አይደለሁም” ብሎ ማስረጃ ማቅረብና የሀብቱንና የሥልጣኑን ምንጭ መግለጽ የባለቤቱ ድርሻ ነው፡፡ እንደአጠቃላይ አካሄድ ግን አሁን ባለው ሁኔታ ሰይጣን ከቫቲካን እስከ ግብጽ እስክንድርያና እስከአፍሪካ ቀንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ሁሉንም ቤተ እምነቶች በቁጥጥር ሥር አድርጓቸዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ ድረገፆችን መጎርጎር ነው፡፡ በተረፈ ዐይን ዐይቶ ልብ ይፈርዳልና በቅርብም በሩቅም በማየት ምን ዓይነት አሳሳቢ ዘመን ላይ እንደምንገኝ መረዳት ይገባል፡፡

ሰይጣን ቤተ ክርስቲያናችንን እንደተቆጣጠረ ለማወቅ በቀሲስ አንቷን ሌቪ በተቋቋመችው ቤተ ሰይጣን የዲያብሎስ ማምለኪያ ቤት ውስጥ እንደሚደረገው ዓይነት የሰይጣን ቅዳሤ (Black Mass) በየቤተ ክርስቲያናችን እስኪቀደስ መጠበቅ አይኖርብንም፡፡ እንደዚያ ዓይነቱ የለየለት ድፍረት በቶሎ ስለሚያስነቃ አያደርጉትም፡፡ በተረፈ ግን ከፓትርያርክና ከጳጳስ ጀምሮ እስከቄስና ዲያቆን ግብረሶዶማዊ ማድረግ ወይም በአምልኮተ ንዋይ ተጠምዶ ዓለማችን ዐይታ የማታውቀውን ወንጀል እንዲሠራ ማብቃት … የዘመናችን ሰይጣናዊ የክተት ዘመቻ በጣም ቀላሉ ተግባር ነው፡፡ የአገርህን ቀሳውስትና ዲያቆናት ለምን አታይም? በአባውራ ሚስት የሚጣሉ ቄሶች አሉ አይደለም እንዴ? ባልና ሚስት አፋትተው ሚስትን ቅምጥ የሚያደርጉ በሀብትም በሃይማኖታዊ ሥልጣንና ማዕረግም አንቱ የተባሉ ወራዳ የአጋንንት ውላጆች አሉ አይደለም እንዴ? ሰይጣን ከዚህ በላይ እንዴት ይቆጣጠረን?

የሃይማኖት ተቋማት በተራው ሕዝብ ዘንድ በጣም እንደሚከበሩ፣ ባይከበሩ እንኳን እንደሚፈሩ ሰይጣን ያውቃል፡፡ ይህንን ታዲያ ለዓላማው በደምብ ይጠቀምበታል፡፡ በየመንደሩ የምናያቸው በምናምን እየሰከሩ ይገቡና “ፓንታራራም ሸንታራርሞራም፣ ባንጋዲሮጋሪጎጊሮም…” እያሉ የሚያጭበረብሩን ተራ ቁጭ በሉዎች እንኳን ሕዝቡን እንዴት ነው የሚያታልሉትና ሚስቱንም ገንዘቡንም የሚዘርፉት? ዐይንን ትንሽ ከፈት የማድረግ ጉዳይ እኮ ነው፡፡ ለይቶልን ታውረናል እኮ ምዕመናን!! እንጂ ስንትና ስንት ፊንታ ይሠራ የለም እንዴ በየአካባቢያችን? ችግሩ የልብ ልብ እየሰጠነው የሚያደድበን እርሱው ራሱ ሰይጣኑ፣ የሚያስዘርፈን እርሱው ራሱ ሰይጣኑ፣… ሆነና አሁን አሁን ሳስበው ያ የመጨረሻ ዘመን የምንለው መጽሐፍ ቅዱሣዊ ትንቢት ተንኳቶ ተንኳቶ በዚህ በኛ ዘመን እደጃችን እንደቆመ ያህል ይሰማኛል፡፡ በርግጥም የፊሽካው መነፋት እንጂ የቀረው ሰባራ ደቂቃም ያለ አይመስለኝም፡፡ ሁሉ ነገር በትንቢቱ መሠረት ተጠናቋልና፡፡

ልዩነቱ ደግሞ ግልጽ ነው፡፡ በኔ የልጅነት ዕድሜ እንዲህ ያለ ነገር እምብዛም አልነበረም፤ ቢኖር እንኳን የነውር ያህል ነበር፡፡ አሁን ግን የዱሮው ነውር እንደባህልና እንደሃይማኖት እየተቆጠረ፣ የዱሮው ባህልና ወግ አሁን እንደነውርና እንደጠያፍ እየታዬ ነው – ብትዋሽ እውነተኛ ነህ፤ ብትቀጥፍ ዘመናዊ ነህ፤ ብትገድል ነፃ ሰው ነህ፡፡ እውነትን ብትናገር ሞኝና ፋርጤ ባላገር ነህ፤ ባትሞስን ሌባኛ ነህ፡፡ በአንድ ትውልድ መካከል እንዲህ ያለ የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ከተፈጠረ በርግጥም ያለንበት ዘመን ሩጫ ከቀድሞው አንጻር ሲመዘን ፍጥነቱ በብርሃን ዓመት የሚለካ ነው፡፡ በጣም እየሮጥን ነው ጎበዝ፡፡ እኔም ሰዓቴ ስለደረሰ ወደ ሥራየ ልሩጥ፡፡ በሥራና በዐይን ቀልድ የለም፡፡ ደኅና ዋሉ፡፡

Ethiopia: Violence in Gambella kills at least 14

(AP) Clashes between different ethnic groups in west Ethiopia have left 14 dead, while UN and MSF offices were targeted by angry protesters, local security service sources said.Violence in Gambella

The violence was sparked after an NGO car with an Ethiopian driver ran over and killed two children from the Nuer ethnic group in a camp for South Sudanese refugees on Friday, the sources told AFP.

In response, a group of refugees attacked Ethiopians living around the camp, killing 10 men and women.

Ethopians from the Anuak ethnic group — traditional rivals of the Nuer — then marched on the city of Gambela, killing four Nuer Ethiopians in separate incidents on Saturday and Sunday.

“People are angry, we want revenge. If the police hadn’t got involved, plenty of Nuer would have been killed,” Addis Alemayu of the Anuak group said.

“With all these refugees coming from South Sudan, things are only getting worse… this is our land, we were here before them.”

Protesters also attacked buildings and vehicles belonging to the United Nations, which they accuse of aiding Nuer refugees.

“Protesters broke open the entry gate to one of our residences and destroyed a vehicle,” said Stephanie Savariaud, spokeswoman for the UN’s world food programme in Ethiopia.

Groups also targeted the offices of Doctors Without Borders (MSF), damaging some of the aid organisation’s vehicles and forcing staff to stay in a city hotel.

Gambela has a population of 300,000 but has taken in 270,000 mainly Nuer refugees fleeing the conflict in neighboring South Sudan. Several different ethnic groups live in the town and violence between them is frequent.

(AP) Clashes between different ethnic groups in west Ethiopia have left 14 dead, while UN and MSF offices were targeted by angry protesters, local security service sources said.Violence in Gambella

The violence was sparked after an NGO car with an Ethiopian driver ran over and killed two children from the Nuer ethnic group in a camp for South Sudanese refugees on Friday, the sources told AFP.

In response, a group of refugees attacked Ethiopians living around the camp, killing 10 men and women.

Ethopians from the Anuak ethnic group — traditional rivals of the Nuer — then marched on the city of Gambela, killing four Nuer Ethiopians in separate incidents on Saturday and Sunday.

“People are angry, we want revenge. If the police hadn’t got involved, plenty of Nuer would have been killed,” Addis Alemayu of the Anuak group said.

“With all these refugees coming from South Sudan, things are only getting worse… this is our land, we were here before them.”

Protesters also attacked buildings and vehicles belonging to the United Nations, which they accuse of aiding Nuer refugees.

“Protesters broke open the entry gate to one of our residences and destroyed a vehicle,” said Stephanie Savariaud, spokeswoman for the UN’s world food programme in Ethiopia.

Groups also targeted the offices of Doctors Without Borders (MSF), damaging some of the aid organisation’s vehicles and forcing staff to stay in a city hotel.

Gambela has a population of 300,000 but has taken in 270,000 mainly Nuer refugees fleeing the conflict in neighboring South Sudan. Several different ethnic groups live in the town and violence between them is frequent.

Floods cause deaths and block food aid in drought-hit Ethiopia

Flash floods in drought-stricken parts of Ethiopia have killed people and livestock and are blocking food aid deliveries to hungry communities, a charity said.

(Reuters) Ethiopians have been waiting for the spring rains to replenish water sources and to plant crops after the most severe drought in decades pushed more than 10 million people into hunger.Flash floods in drought-stricken parts of Ethiopia

But many livestock, weakened by the drought, have died following heavy rains in Ethiopia’s remote Somali and Afar regions, the Norwegian Refugee Council (NRC) said on Sunday.

“Not only are families losing their remaining livestock, but the heavy rain is making the roads inaccessible,” said Mohamed Hassan, who heads NRC’s work in the Somali region.

“Roads are turning into raging rivers and trucks carrying food assistance are unable to reach many communities.

“If people don’t get aid I am afraid that human lives might be lost,” he said in a statement.

Some 28 people were killed by flash floods in early April, the majority when a river passing through Jijiga, the capital of Somali region, burst its banks, the government said.

The two eastern regions, among the worst hit by the drought, are mainly home to herding communities. Cattle, sheep and goats often die after floods because infectious diseases increase and vegetation becomes toxic.

The government and aid agencies are revising upwards a joint appeal in December for $1.4 billion as the number of districts suffering a humanitarian emergency has widened.

The crisis is expected to deepen until August when people hope to harvest crops they will plant in June to catch the summer rains.

Floods can also contaminate water sources, causing diseases like cholera.

Ethiopia regularly suffers hunger crises as eight out of ten people are farmers who depend upon the rains.

“We will see this situation again and again,” said Hassan. “We must not only hand out food, but also help people find alternative livelihoods.”

የአሜሪካ የሕግ ምክር ቤት አባላት (ሴናተሮች) በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ መቆም አለበት እያሉ ይጮሃሉ!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ 

Cardin 6ባለፈው ሐምሌ ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ጎበኘ እና የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስበ (ህወሀት) አገዛዝ “ዴሞክራሲያዊ መንግስት” ነው በማለት አወጀ፡፡

ዘ-ህወሀት ዓይኑን በጨው ታጥቦ ተካሂዶ የነበረውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ መቶ በመቶ ወይም ደግሞ ሁሉንም 547 የፓርላማ መቀመጫዎች ያሸነፈ መሆኑን አይን ባወጣ ዉሸት ባለፈው ግንቦት ገለጸ፡፡

የኒዮርክ ታይምስ መጽሔት ይህንን ጉዳይ በማስመልከት “አሳፋሪ” ሲል ጠራው፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የኦባማን መግለጫ “አስደንጋጭ” (በሬ ወለደ አንደማለት) በማለት ጠርቶታል፡፡

እኔ ደግሞ የወረደ እና አሳፋሪ ቅሌት በማለት ጠርቸዋለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 20/2016 ሴናተር ቤን ካርዲን (የሜሪላንድ ዴሞክራት)፣ ማሪያ ካንትዌል (የዋሺንግተን ዴሞክራት)፣ ፓቲ ሙሪ (የዋሺንግተን ዴሞክራት)፣ ኤድ ማርከይ (የማሳቹሴትስ ዴሞክራት)፣ ክሪስ ኩንስ (የዴላዋሬ ዴሞክራት)፣ ቦብ ሜንዴዝ (የኒው ጀርሲ ዴሞክራት)፣ ፓትሪክ ሊዚ (የቬርሞንት ዴሞክራት)፣ አል ፍራንከን (የሜኖሰታ ዴሞክራት)፣ ዱክ ደርቢን (የኢሊኖስ ዴሞክራት)፣ አሚ ክሎቡቻር (የሚኔሶታ ዴሞክራት) እና ማርኮ ሮቢዮ (የፍሎሪዳ ሬፐብሊካን) በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በዘ-ህወሀት እየተደረገ የሚገኘውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በማውገዝ ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡

እርግጥ፣ “በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ ወንጀል” የሚለውን ሀረግ በትክክል ደፍረው ለመናገር አልተጠቀሙበትም፡፡ ሆኖም ግን ባሳለፉት ውሰኔ ላይ ማለት የፈለጉት በእርግጠኝነት ሌላ ሳይሆን ይህንኑ ጉዳይ ነበር፡፡

ሴናተር ካርዲን “በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥበቃን መርዳት እና ሁል አቀፍ አስተዳደር እንዲሰፍን ማበረታታት“ በሚል ረቂቅ ሕግ ርዕስ ባቀረቡት ጽሁፍ በመግቢያው ላይ እንዲህ ብለዋል፡

“በኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች በተፈጸመው አረመኒያዊ ድርጊት እና ግድያው ለተፈጸመባቸው ቤተሰቦች በተሰጠው የሀዘን መግለጫ እጅግ በጣም ደንግጫለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ዜጎቹ በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ መብታቸውን ያጎናጽፋል እናም በኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ኃይሎች የተወሰዱት እንደዚህ ያሉ እርምጃዎች በምንም ዓይነት መልኩ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በጋዜጠኞች ላይ እየተወሰዱ ያሉት ስልታዊ የመንግስት የኃይል እና የጭቆና እርምጃዎች እንዲሁም ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብትን ለመሸበብ እና በሕጋዊ የፖለቲካ መንገድ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ዜጎችን ለመከልከል እ.ኤ.አ በ2009 የወጣውን የጸረ ሽብር እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅን በተሳሳተ መንገድ በመጠቀም የዴሞክራሲያዊ ነጻነቶችን እና የሰብአዊ መብቶችን በመደፍጠጥ ላይ የሚገኝ ለመሆኑ ዋና ማሳያዎች ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሀገሪቱ ከምትገኝበት አውዳሚ ድርቅ እና የወሰን የጸጥታ ደህንነት እጦት ጉዳይ አንጻር መንግስት ከምንጊዜውም በላይ የእራሱን ሕዝቦች ከመነጣጠል ይልቅ አንድነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰድ በጣም ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋም እንዲችል ከተፈለገ መሰረታዊ የሆኑትን የሰብአዊ መብቶችን መጠበቅ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡“

ሴናተር ሩቢዮ አንድ ዓይነት አስተሳሰብን በማራመድ እንዲህ በማለት ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ ተናግረዋል፡

“በኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች መሰረታዊ መብቶቻቸውን በመጠቀማቸው ብቻ ሰላማዊ አማጺዎች እና የሲቪል ማህበረሰብ ወትዋቾች በቁጥጥር ስር ውለዋል፣ ስቃይ እና ግድያም ተፈጽሞባቸዋል፡፡ በመንግስት እየተፈጸሙ ያሉትን እንደዚህ ያሉትን ዓይን ያወጡ የተንሰራፉ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እና የኢትዮጵያን ሕዝቦች መሰረታዊ መብቶች መከልከልን አወግዛለሁ፡፡ የዩኤስ አሜሪካ እና የኢትዮጵያን ግንኙነት በተመለከተ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ቅድሚያ ትኩረት እንዲሰጠው እና የፖለቲካ የማሻሻያ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ የኦባማን አስተዳደር እማጸናለሁ፡፡“

ኦባማ የሴናተር ሩቢዮን ተማጽኖ ጆሮዳባ ልበስ ብሎ አልፎታል፡፡ በቁስል ላይ እንጨት መስደድ እንዲሉ ኦባማ አዲስ አበባ በመሄድ ቀጥ ብሎ በመቆም እና አሳፋሪ በሆነ መልኩ ዘ-ህወሀት “ዴሞክራሲያዊ መንግስት” ነው በማለት አወጀ፡፡

ኦባማ እ.ኤ.አ ሐምሌ 2016 ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ከመሄዱ ከጥቂት ቀናት በፊት የኢትዮጵያ መንግስት በእራሱ ሕዝቦች ላይ እያካሄደ ስላለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ያሳሰባቸው መሆኑን  በመግለጽ ለኦባማ ደብዳቤ ጽፈው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሴናተር ሩቢዮ እንዲህ የሚል  ደብዳቤ በመጻፍ አስጠንቅቀው ነበር፡

“ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢትዮጵያ አሸባሪነትን ለመዋጋት እና በቀጣናው ውስጥ የተረጋጋ ጸጥታን ለማስፈን የጋራ የሆነ ፍላጎት ያላቸው ቢሆንም ቅሉ ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተንሰራፋ ስላለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ጆሮዳባ ልበስ የሚል ምላሽ መስጠት የሌለበት ዋና ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ አማጺዎች ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ሀሳባቸውን እንዳይገልጹ የፖለቲካ ሂደቱ፣ የሲቪል ማህበረሰቡ ወይም የመገናኛ ብዙሀን እንዳይንቀሳቀሱ መንገዶችን ሁሉ በመዝጋት በሀገሪቱ ውስጥ እየተፈጠረ ባለው ችግር ላይ ነዳጅ በማርከፍከፍ ላይ ይገኛል፡፡“

በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች የሚወሰድ የኃይል እርምጃ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም ኢሰብአዊ ወንጀል ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ባንኪሙን እንዲህ ብለዋል፣ “በሶርያ መንግስት እየተፈጸሙ እና እየቀረቡ ያሉት የጭካኔ እርምጃ ዘገባዎች ሁሉ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ኢሰብአዊ ወንጀሎች ወይም ደግሞ የጦር ወንጀሎች በመባል ይካተታሉ፡፡ እንደዚህ ያሉ ኃይልን መሰረት ያደረጉ እርምጃዎች መመርመር አለባቸው እናም የወንጀል ድርጊቱ ፈጻሚዎች ተጠያቂ መሆን አለባቸው፡፡“

የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተሮች እየተናገሩ ያሉት እና በውሳኒያቸውም ጥሪ እያቀረቡ ያሉት ይህንኑ አንድ ዓይነት የሆነ ነገር ነው፡፡

የሴኔቱ ውሳኔዎች ግልጽ በሆነ ቋንቋ የሚያመላክቱት በኢትዮጵያ ውስጥ በዘ-ህወሀት አገዛዝ በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ አማጺዎች አካሂደውት በነበረው ተቃውሞ የጸጥታ ኃይሎች ከመጠን ያለፈ ኃይልን በመጠቀም በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሰብአዊ መብት ረገጣዎችን የፈጸሙ ስለሆነ እነዚህ የጸጥታ ኃይሎች ላጠፉት ጥፋት በሕግ ለፍትህ አካል ቀርበው ተጠያቂ መሆን አለባቸው የሚል ነው፡፡

ሆኖም ግን ውሳኔው ቀላል መግለጫ ከመስጠት እና ትችትን ከማቅረብ በዘለለ መልኩ ተጫባጭነት ወዳለው የድርጊት እርምጃ መሄድ አለበት፡፡

ውሳኔው በአራት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የሴናተሮችን አስተሳሰቦች፣ አመላካከቶች እና አቋሞች የሚወክል እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ውሳኔው፣

1ኛ) ዘ-ህወሀት የፈጸማቸውን ኢሰብአዊ ወንጀሎች ሙሉ በሙሉ አውግዟል፣

2ኛ) በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የሰብአዊ መብት ጥበቃ ጋር በተያያዘ መልኩ ኦባማ እስከ አሁን ድረስ ምንም ዓይነት ተጨባጭነት ያለው ነገር ያላደረገ በመሆኑ ትዕግስታቸው እየተሟጠጠ እና እየተሰላቹ የመጡ መሆናቸውን በግልጽ ያመላክታል፣

3ኛ) በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ ወይም ደግሞ ዩኤስ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው የእርዳታ አጠቃቀም እንደገና መመርመር እና መጤን ያለበት ጉዳይ እንደሆነ አጽንኦ በመስጠት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀጥተኛ የሆነ የፖሊሲ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ይጠይቃል፣

4ኛ) ዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች እና ተግባራት የሰብአዊ መብትን ከማክበር እና የዴሞክራሲያዊ ሂደቱን ከማጠናከር አኳያ ተቃኝተው መቅረብ እንዳለባቸው ግልጽ የሆነ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡

በውሳኔው ላይ የተዘረዘሩት የዘህወሀት ኢሰብአዊ ወንጀሎች፣

በመጀመሪያው የውሳኔ ክፍል ዘ-ህወሀት በሰው ልጆች ላይ ስለፈጸማቸው ወንጀሎች ክስ ተመስርቶበት ለሕግ አካል መቅረብ እንዲችል አንድ ዓይነት ዓላማ እና ፍላጎት እንዳለ አምናለሁ፡፡

የሴኔቱ ውሳኔ በዘ-ህወሀት ላይ እንዲህ በማለት ያውጃል፡

“የጸጥታ ኃይሎች ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብትን እና የመደራጀት ነጻነትን በመከልከል፣ ፖለቲካዊ ዓላማ ባላቸው ክሶች በመገፋፋት፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባላትን እና ጋዜጠኞችን በማስፈራራት እና በማሸማቀቅ አስከፊ በሆኑ የሰብአዊ መብቶች ድፍጠጣ ላይ ማለትም ዜጎችን በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር በማዋል፣ በመግደል እና ስቃዮችን በመፈጸም ተግባራት ላይ ተሰማርተዋል፡፡

በኦሮሚያ እና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች መብቶቻቸውን በመጠቀም በሰላማዊ መንገድ በመሰብሰብ ቅሬታዎቻቸውን በማሰማታቸው ብቻ መንግስት መር ለሆነ የኃይል እርምጃ በመዳረግ የጋዜጠኞችን ነጻነት በማፈን የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ከሚያጎናጽው መብት ባፈነገጠ መልኩ በመሄድ ከዴሞክራሲዊ የአሰራር መርሆዎች በተጻራሪ ቆሞ ይገኛል፡፡

እ.ኤ.አ በ2005 ከተደረገው አጠቃላይ ምርጫ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ የዴሞክራሲ ምህዳሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበበ መጥቷል፡፡

ምርጫን መቶ በመቶ አሸነፍኩ የሚል የሸፍጥ ምርጫ ተካሂዷል፡፡

የፕሬስ ነጻነትን ለመገደብ፣ ነጻ ጋዜጠኞችን ጸጥ ለማድረግ እና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ለማሰቃየት የጸረ ሽብር አዋጅ እየተባለ የሚጠራ ሕግ በሸፍጥ ተዘጋጅቷል፡፡

የሲቪል ማህበረሰቡን እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በተለይም ደግሞ በመንግስት ባለስልጣኖች የሚካሄዱ የሰብአዊ መብት ረገጣዎችን እየመረመሩ በማውጣት ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰቡ የሚያሳውቁ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ መገደብ እና ሙሉ በሙሉም እንዲዘጉ አድርገዋል፡፡

ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን በማሰቃየት እና በፍርድ ቤት ቀጠሮ እያመላለሱ በማንገላታት በፕሬሱ ላይ የፍርሀት እና የጭቆና ድባብ ከባቢ አየር እንዲያጠላ እና እንዲንሰራፋ አድርገዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ቢያንስ 200 እና ከዚያም ሊበልጥ የሚችል ቁጥር ያላቸው ሰላማዊ አማጺዎች በጸጥታ ኃይሎች ተገድለዋል፡፡“

በውሳኔው የዘህወሀትን አገዛዝ ማውገዝ፣

የሴኔቱ ውሳኔ ያለምንም ማወላወል፣

ሀ) በዘ-ህወሀት የጸጥታ ኃይሎች ከመጠን ያለፈ ኃይልን በመጠቀም ባመጹ ተቃዋሚዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ያወግዛል፣

ለ) ዘ-ህወሀት ሰላማዊ በሆነ መንገድ በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ሕገ መንግስታዊ የመሰብሰብ እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብቶቻቸውን በመጠቀማቸው ምክንያት በጋዜጠኞች፣ ተማሪዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ወትዋቾች እና የፖለቲካ መሪዎች ላይ እያደረገ ያለውን በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር የማዋል እና ዘብጥያ የማዋሉን ድርጊት ያወግዛል፣ እንደዚሁም

ሐ) ዘ-ህወሀት ሰላማዊ የፖለቲካ እና የሲቪል ማህበረሰብ አመጸኞችን እና የጋዜጠኞችን ነጻነቶች ለማፈን እና ለማጥቃት ሲል ከሕግ አግባብ ውጭ እየተገበረ ያለውን የጸረ ሽብር ሕግ ያወግዛል፡፡

በውሳኔው በዘህወሀት አረመኒያዊ ድርጊት ላይ የቀረበ ጥሪ፣

የሴኔቱ ውሳኔ እንዲህ የሚሉ ውሱን የሆኑ ጥሪ በዘ-ህወሀት ላይ አቅርቧል፡

o   በጸጥታ ኃይሎች የሚፈጸሙ ከመጠን ያለፉ የኃይል እርምጃዎች በአስቸኳይ ይቁሙ፣

o   በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በገለጹ ንጹሀን ዜጎች ላይ በኦሮሚያ ክልል ከመጠን ያለፈ ኃይልን በመጠቀም እልቂት በፈጸሙ የጸጥታ ኃይሎች ላይ የተሟላ፣ ታማዕኒነት ያለው እና ግልጽ የሆነ ምርመራ እንዲደረግ፣ እንዲሁም ጥፋቱን የፈጸሙ ወንጀለኞች ለፍትህ አካል ቀርበው ተጠያቂ እንዲሆኑ፣

o   ሰላማዊ አማጺዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ወትዋቾች እና 13 ጋዜጠኞች ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀም ስለአመጽ እንቅስቃሴው የዘገቡ 14 ዜጎችን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙት በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣

o   በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 18፣ 19፣ 30 እና 29 በግልጽ የተቀመጡት በነጻ የመሰብሰብ እና ነጻነትን የሚያጎናጽፉት መብቶች ይከበሩ፣

o   መንግስት ለልማት እያለ ከሚያወጣቸው ስትራቴጂዎች በተለይም ዜጎችን ከመሬት ይዞታቸው የሚያፈናቅሉ ስትራቴጂዎችን ከመተግበሩ በፊት በይፋና ግልጽ በሆነ መልኩ ከዜጎች ጋር ውይይቶችን እንዲያደርግ፣

o   አገዛዙ የፖለቲካ መሳሪያ በማድረግ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመመርመር እና በማውጣት በሰላማዊ የፖለቲካ አንቅስቃሴ ወይም ደግሞ ለበለጠ የፖለቲካ ነጻነት  ተግባራት ላይ ተሰማርተው በመወትወት ላይ የሚገኙትን የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን ማስፈራራት ወይም ደግሞ ለዓላማዎቻቸው ማስፈጸሚያ የሚሆነውን ገንዘብ ከለጋሽ እና በጎ አድርጎት ድርጅቶች ማግኘት እንዳይችሉ ለማድረግ ያዘጋጃቸውን አዋጆች እንዲሰርዝ፣

o   ዜጎችን ከመሬት ይዞታዎቻቸው የሚያፈናቅሉት አዋጆች ይሻሩ፣ ወይም ደግሞ አግባብነት ያላቸው መፍትሄዎች ወይም ትክክለኛ እና ተመጣጣኝነት ያለው ካሳ በመክፈል ወይም ተፈናቃዮች ፍትህ ለማግኘት ግልጽና ነጻ ዳኝነት ማግኘት እንዲችሉ እንዲደረግ፡፡

ወደፊት የኦባማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብት መሻሻልን በሚመከት ምንም ነገር ለማድረግየማያስችለውን ፖሊሲውን እርግፍ አድርጎ መተው አለበት፡፡

የሴኔቱ ውሳኔ የኦባማ አስረተዳደር በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብት መሻሻል ሁኔታ በጣም ትንሽ ወይም ደግሞ ምንም ነገር ያላደረገ መሆኑን ዴፕሎማሲያዊ በሆነ መልኩ ይፋ አድርጓል፡፡

ውሳኔው የኦባማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ስላለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ የተለያዩ ቃላትን በመጠቀም መናገር ብቻ እንጅ ምንም ነገር ያላደረገ እና እራቁቱን የቀረ መሆኑን እንዲሁም በየጊዜው ስለሰብአዊ መብት እየተናገረ የሰብአዊ መብት ጥበቃን እንደማይተገብር እና ምንም ነገር እንደማይሰራ ግልጽ አድርጓል፡፡

ውሳኔው ኦባማ እ.ኤ.አ ሐምሌ 2015 ወደ ኢትዮጵያ ሄዶ የዘ-ህወሀትን መሪዎች ሲገናኝ የዴሞክራሲያዊ ሂደቱን እንዲያጠናክሩት እና የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ እና እንዲሻሻሉ እንዲነግራቸው ያውጃል፡፡ ሆኖም ግን እስከ አሁን ድረስ ያለው ሁኔታ እልቂት እና የበለጠ ጭቆና ነው፡፡

ውሳኔው በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ሁኔታ አኳያ የሚሰጠው እርዳታ ከታለመለት ዓላማ አንጻር ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ጥቅም ስለመዋሉ አስተማማኝ እንዲሆን የደህንነት እርዳታው እንደገና እንዲጠና በማለት ለኦባማ አስተዳደር ጥሪ ያቀርባል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ውሳኔው ለኢትዮጵያ ስለሚሰጠው የዩናይትድ ስቴትስ እርዳታ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ዩኤስኤአይዲ/USAID ስለእርዳታው አጠቃቀም የበለጠ ትኩረት አድርገው እንዲከታተሉ እና ተጠያቂነትም እንዲኖር ጥሪ ያቀርባል፡፡

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት እንዲጠበቅ የሴኔቱ ጽኑ ድጋፍ፣

የዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት “ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመቆም የዴሞክራሲ ምህዳሩ እንዲሰፋ እና ዜጎች በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የተሰጣቸውን ሕገ መንግስታዊ መብት ያለምንም መሸራረፍ መጠቀም እንዲችሉ የሴኔቱ ውሳኔ ያረጋግጣል፡፡”

ውሳኔው በእርግጠኝነት ምን ማለት ነው?

የሴኔቱ ውሳኔ (ቀላል ውሳኔ) በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለውን እና ወደፊት ምን መደረግ እንዳለበት የሴኔቱን የሕግ ማዕቀፍ ፍላጎት ዓላማ መሰረት ያደረገ መሆኑን ማጤን ይገባል፡፡ (እ.ኤ.አ በ2/4/2015 የጸደቀውን የሴኔት ደንብ ቁጥር 30ን ይመልከቱ፡፡)

ሴኔቱ የእራሱን አመለካከት፣ ሀሳብ እና አቋም ለመግለጽ ሲፈልግ እና አጽንኦ ለመስጠት ወይም ደግሞ ስለአንድ ጉዳይ ጠቃሚነት ማስጠንቀቅያ ለማስተላለፍ እና መልዕክቱም በሁሉም ዘንድ እንዲደርስ ሲፈልግ ቀላል የሆነ ውሳኔ ያሳልፋል፡፡ በኢትዮጵያ የተላለፈው የሴኔቱ ውሳኔ የአብዛኞቹን ሴናተሮች ሀሳብ በመግለጽ ዓላማ ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡

እንደዚሁም ሁሉ እንደ መደበኛው ሕጎች እና ውሳኔዎች የሕግ ተፈጻሚነት አስገዳጅነት ወይም ደግሞ የፕሬዚዳንቱ ፊርማ ሳይኖርባቸው ሊተላለፉ የሚችሉትን ቀላል ውሳኔዎች መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡

ስለሆነም ምክንያታዊ ጥያቄ ሆኖ ሊቀርብ የሚችለው “ቀላል ውሳኔዎችን” ለማሳለፍ አሳሳቢ ሆኖ የሚቀርበው ለምንድን ነው? የሚለው ጉዳይ ነው፡፡

ቀላል ውሳኔዎች የተፈጻሚነት አስገዳጅ የሕግ ግዴታ የሚጣልባቸው ባይሆኑም ቅሉ ጥቂት ጠቃሚ ተግባራትን ለማከናወን ያገለግላሉ፡፡ በተወካዮች ምክር ቤት የሚከተሉትን ተግባራት ለማከናወን ያገለግላሉ፡

o   በአንድ በተወሰነ ጉዳይ ላይ ለመቀጠል እና የጋራ አቋም በመያዝ ድጋፍን ወይም ደግሞ ተቃውሞን ለመግለጽ በአንድ የተወሰነ ድርጊት፣ ፖሊሲ፣ የሕግ ረቂቅ፣ ሀሳብ፣ ዕቅድ፣ ፕሮግራም፣ ወዘተ ላይ በመመዝገብ ያገለግላሉ፣

o   በአባላት መካከል በአንድ በታሰበ ወይም በሚገመት ድርጊት ላይ ኃይልን ለማጠናከር አስቀድመው ድጋፍ ለማድረግ ወይም ደግሞ ለመቃወም ይረዳሉ፣

o   ሴኔቱ ወይም የተወካዮች ምክር ቤት በአንድ በተወሰነ ጉዳይ ላይ በጥልቀት እንዲያስቡ እና የበለጠ የተለመደውን የሕጋዊ አሰራር አስፈላጊነትን ሳይከተሉ እርምጃ ለመውሰድ እንደ ማሳሰቢያ ሆነው ያገለግላሉ፣

o   የዩኤስ ኮንግረስ አንድን የተወሰነ ጉዳይ ልዩ ትኩረት እና አጽንኦ በመስጠት መመልከት እንዲችል ለዩኤስ መምሪያዎች፣ ኤጄንሲዎች እና የውጭ መንግስታት እንዲያውቁት ያደርጋሉ፣

o   አንድ ጉዳይ በአንድ በተወሰነ ሀገር ወይም አካባቢ በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝቦች ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ከሆነ እና ሁኔታው በዚያው የሚቀጥል ከሆነ የሕግ እርምጃ ማዕቀፎችን ለመውሰድ እንዲቻል ለማድረግ በውጭ ጉዳዮች ላይ (ከውጭ መሪዎች) ጋር ለመግባባት ያገለግላሉ፣

o   በውጭ መንግስታት ላይ አስገዳጅ የፖሊሲ ለውጥ እንዲያደርጉ ተፈጻሚ ይሆናሉ፣

o   የፖሊሲ ለውጥ እንዲኖር ወይም ደግሞ ለቀጣይ የሕግ ማዕቀፍ አስፈላጊነትን ግልጽ ያደርጋሉ፣

o   የሕዝብ ተደማጭነት እንዲኖር ያደርጋሉ፡፡

ዋናው እና ተቀባይነት ያለው ነገር የሴኔቱ ውሳኔዎች በአብዛኞቹ የውጭ መንግስታት እና በዩኤስ መንግስት ኤጀንሲዎች እና መምሪያዎች ዘንድ በትኩረት እንዲታዩ ያደርጋሉ፡፡ የዘ-ህወሀት ደናቁርት በዚህ ጉዳይ ላይ እንደሚበሳጩ እና ነገሩን ከምንም እንደማይቆጥሩት መገመት ምክንያታዊ ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2007 ተመሳሳይ ከሆነ የሕግ ማዕቀፍ ሁኔታ ጋር በተጋፈጡበት ጊዜ አሁን በህይወት የሌለው የዘ-ህወሀት አምባገነኑ መሪ መለስ ዜናዊ እጅግ በጣም በመበሳጨት እና ምጸታዊ በሆነ አነጋገር በዩኤስ ኮንግረስ መካከል በመገኘት እንዲህ በማለት የቃላት ጥዝጠዛውን/ዘለፋውን አጉርፎት ነበር፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ያልተረጋጋ መንግስት ያላት ትንሽ ሀገር እና ወደ ውጭ በሚላክ በአንድ ምርት የውጭ ጥገኝነት ላይ የወደቀች ወይም ደግሞ በውጭ የገንዘብ እርዳታ የምትኖር ሀገር አይመኝም ወይም ደግሞ በዩኤስ ኮንግረስ ወይም በሌላ በማናቸውም ሀገር የምትሽከረከር ሀገር አይደለችም፡፡“ ድንቄም የምትሽከረከር አገር አይደለችም! ገበያ ባልወጣሽ ይሉሽን ባልሰማሽ ይላሉ ኢትዮጵያውያን ሲተርቱ፡፡

እ.ኤ.አ በ2009 የመለስ መንግስት በጂዳ ወይም በባህረ ሰላጤው እንደሚገኙ እንደማናቸውም ሀገሮች እንዲያዝ ይፈልጋል በማለት ገልጨ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ አምባገነኑ መለስ በሚሊዮኖች ሄክታር የሚቆጠረውን የኢትዮጵያን ለም መሬት ሳውዲ እና የባህረ ሰላጤው ሀገሮች ኢንቨስተሮች እየተባሉ ለሚጠሩት እያቀራመተ ይቸበችብ ነበር፡፡ አሁንማ ኢትዮጵያ በነ ሳውዲና ቻይና ትሽከረከራለች።

በኢትዮጵያ ስለተላለፈው የሴኔት ውሳኔ ጉዳይ ዘ-ህወሀት ትኩረት ይሰጠዋል አላለሁ። ዘ–ህወሀት ግዙፍ የሆነ ገንዘብ በመመደብ ህሊናቸውን ለገንዘብ ብቻ ለሸጡት ወትዋቾች በማስታቀፍ ውሳኔውን በእንጭጩ ለማኮላሸት ወደኋላ እንደማይል አልጠራጠርም፡፡ ዘ-ህወሀት ከቀድሞው (ኤች. አር/H.R 2003ን እናስታውስ) ተሞክሮው በመማር በገንዘብ ለሚቀጥራቸው ወትዋቾች በየወሩ 50,000 ዶላር የሚከፍል ከሆነ በዩኤስ ኮንግረስ የሚተላለፈውን የሕግ ውሳኔ የውኃ ሽታ አድርጎ ሊያስቀረው ይችላል፡፡

በሴኔቱ ውሳኔ የዩኤስኤአይዲ/USAID የተጠያቂነት ጥያቄ፣

አንባቢዎቼ ቀደም ሲል የዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ ለሆነችው ለጋይሌ ኢ ስሚዝ እ.ኤ.አ መጋቢት 16/2016 በጻፍኩት ደብዳቤ በኢትዮጵያ ውስጥ በዩኤስኤአይዲ/USAID የሚተዳደረው እርዳታ ላይ ተጠያቂነት እና ግልጽነት እንዲኖር ጥያቄ ማቅረቤን ታስታውሳላችሁ፡፡ ሚስስ ስሚዝን እንዲህ በማለት ጠይቂያት ነበር፡

“በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዥ አካል በእርዳታ ለሕዝብ የሚሄደውን 500 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ለፖለቲካ ዓላማው እንዳይጠቀምበት ለማረጋገጥ እንዲቻል ምን ያስቀመጥሻቸው የተቀመጡ የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች አሉ?

ከላይ የተጠቀሰውን ሰብአዊ እርዳታ በኢትዮጵያ ውስጥ ለማስተዳደር እና ከሙስና ለመከላከል ምን ዓይነት የተጠያቂነት ሂደቶች በስራ ላይ ውለዋል? በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ገዥ አካል ከተሰጠው 500 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ምን ያህሉን በእራሱ ስልጣን እንደሚጠቀምበት እና ምን ያህሉንስ በእራሱ ስልጣን ሊጠቀምበት እንደማይችል መጠኑ ይታወቃልን?“

ሴኔቱ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 20/2016 ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የፕሬዚዳንቱ የ2012 የሰብ ሰሀራ አፍሪካ ስትራቴጂን መሰረት ባደረገ መልኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ከየዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ ጋር በመጥራት ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ በምትሰጠው እርዳታ ላይ መሻሻል እንዲኖር እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንዲጠይቃቸው የማድረጉን ጉዳይ በጉጉት የምጠብቀው ነገር ነው፡፡

እሰከአሁን ያልተመለሱ ጥያቄዎች፣

ስለሴኔቱ ውሳኔዎች በርካታ የሆኑ ጥያቄዎችን የሚጠይቁ ዜጎች አሉ፡፡ ከእነዚህም ጥያቄዎች መካከል እስቲ የሚከተሉትን  እንመልከት፣

1ኛ) ይህ የሴኔቱ ውሳኔ በአሁኑ ጊዜ እንዲተላለፍ የተደረገው ለምንድን ነው?

2ኛ) ለእነዚህ ላለፉት በርካታ ዓመታት ሁሉ መወሰን የሚችሉት እነዚህ የሴኔቱ አባላት የት ገብተው ከርመው ነበር?

3ኛ) ይህ ውሳኔ በአሁኑ ጊዜ መወሰን ማለት ሴኔቱ ውሳኔውን በተግባር ለማሳየት እጅጌውን ከፍ ከፍ እያደረገ ነው ማለት ነውን?

4ኛ) ይህ በአሁኑ ጊዜ የተላለፈው ውሳኔ ዝም ብሎ ባዶ የአፍ ካራቴ እና የቃላት ጨዋታ እርባናቢስ የዥዋዥዌ ጨዋታ ንግግር ነውን?

5ኛ) በውሳኔው መተላለፍ ምክንያት በቀጣይነት ምን ሊከሰት ይችላል ተብሎ ይታሰባል?

6ኛ) ሴኔቱ በእርግጠኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብት ጥበቃ አያያዝ እንዲሻሻል የምሩን ጥረት እያደረገ እና ለተግባራዊነቱ በቆራጥነት እየሄደ ነውን?

7ኛ) ኢትዮጵያውያን ይህ የሴኔት ውሳኔ ቅጽበታዊ በሆነ መልኩ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት አጠባበቅ ሁኔታ ሊያሻሽል ይችላል ብለው ተስፋ ያደርጋሉን?

8ኛ) የሴኔቱ ውሳኔ ባዶ ንግግር ብቻ ሆኖ እና ምንም ዓይነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ የማይደረግበት ሆኖ ሊቀር ይችላልን? ወዘተ፣ ወዘተ

ለእነዚህ ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች ሁሉ ውሱን የሆኑ መልሶችን መስጠት ከባድ ነገር ነው፡፡

የዩኤስ የሕግ ሂደት ፕሬዚዳንቱ ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣንን በተጎናጸፈበት ሁኔታ እና በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሁለት የተለያዩ የሕግ አውጭ አካላት (ሴኔቱ እና የተወካዮች ምክር ቤት) ባለቡት ሁኔታ አንድን ሕግ በቀላሉ በማጽደቅ ወደተግባር የማሸጋገሩ ሁኔታ እጅግ በጣም ውስብስብ ነገር ነው፡፡ የአሜሪካ የሕግ ስርዓት መዋቅራዊ በሆነ መልኩ በጣም ዘገምተኛ እና ጥልቅ የማሰብ ሂደት የሚንጸባረቅበት እንዲሁም ለሕገ መንግስቱ እና ለውስጥ የሕግ ደንቦች ተገዥ ሆኖ የተቀየሰ ነው፡፡

ከልምድ ባለን ተጨባጭ መረጃ መሰረት የሰብአዊ መብት ጥበቃን እና ዴሞክራሲን ለማጠናከር በሚደረግ ጥረት ውስጥ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት እና ሕግ ሆኖ እንዲጸድቅ ለማድረግ መጠነሰፊ የሆኑ የውትወታ ጥረቶች ማድረግ እንደሚያስፈልግ ኤች.አር/HR. 2003ን (እ.ኤ.አ የ2003 የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ እና የተጠያቂነት ድንጋጌ) ስንሰራ በነበረበት ጊዜ በጥልቀት እና በስፋት የምናውቀው ጉዳይ ነው፡፡

ሆኖም ግን ያም ሆነ ለእኔ የሚያሳስበኝ ጉዳይ አይደለም፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መስራች አባቶች መካከል አንዱ ከሆኑት እና እ.ኤ.አ ታህሳስ 23/1776 እንዲህ በማለት ተናግረው ከነበሩት ከቶማስ ፔይኔ ጋር ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡

“የጭቆና አገዛዝ እንደ ገሀነም በቀላሉ ድል ሊደረግ የሚችል ጉዳይ አይደለም፣ ሆኖም ግን ይህ በስቃይ ላይ ያለ ምቾት በመካከላችን አለ፣ ይህም ማለት ግጭቱ እየመረረ እና እየከፋ በሄደ ቁጥር ድሉ ደግሞ የዚያኑ ያህል የጎመራ እና እንጸባራቂ ይሆናል፡፡ ርካሽ ሆኖ የምናገኘው ነገር እንዲህ የሚል ቀላል የሆነ ክብር እንሰጠዋለን፡ ማንኛውንም የእራሱን ዋጋ የሚሰጥ ሁሉ ውድ ነገር ነው…በችግር ወቅት ፈገግታ የሚታይበትን ሰው እወደዋለሁ፣ ምክንያቱም ከጭንቀት ጥንካሬን ተላብሷልና፣ እናም ጥንቃቄ የተሞላበት አስተሳሰብ እያደገ እና ጠንካራ እየሆነ ይሄዳል፡፡“

ስለዚህ ፈገግ እላለሁ!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ሚያዝያ 17 ቀን 2008 .

‘አቡሌ’ አብዱልከሪም | በዘላለም ክብረት

በዘላለም ክብረት

ረጅም ነው፡፡ ደረቱ ከልክ በላይ ሰፊ ነው፡፡ በደረቱ የጥይት እርሳስ አንጥሮ አንደሚመልስ በጉራ ሳቅ እያለ ይናገራል፡፡ ደረቱ ለምን እንደሰፋ ሲናገር ያለፈበትን ፈተና ያስተጋባል፡፡ ሸካራው እጁ እጅግ ጠንካራ ነው፡፡ ምን ቢሰራ ነው እንዲህ የጠነከረው? ያስብላል፡፡ እድሜውን በትክክል ባያውቀውም 29 ዓመቱ እንደሆነ ግን ይገምታል፡፡ አማርኛ መናገር ስለሚያስቸግረው ‘ተው ባክህ’ የሚል ሐረግ እዚህም እዚያም ጣል ያደርጋል፡፡ ሲናገር ፈገግታ ሁሌም ከፊቱ አይጠፋም፡፡ አፍንጫው በንግግሮቹ መሃል ይነፋል፡፡ የእጅ መሳሪያውና RPGው በአይኑ ላይ ውል ሲሉበት የመሳሪያ ድምፅ በአፉ እያወጣ፣ ጣቶቹን እንደ መሳሪያ ደቅኖ ትዝታውን ያስታምማል – አብዱልከሪም አብዱልሰመድ አብዱልቃድር፡፡
zelalem Kibret

አብዱልከሪም የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ወታደር ነው፡፡ ቤሕነን አብዱልከሪም ደም ውስጥ ይራወጣል፡፡ ለብዙዎች የግንባሩ ስም አዲስ ቢሆንም ቤሕነን ግን ረጅም ታሪክ ያለው ሲሆን፤ ቤሕነንን ከግምት ውስጥ ሳያስገቡም የቤኒሻንጉል/ጉሙዝ ክልልን የፖለቲካ ሁኔታ መረዳት አይቻልም፡፡
(ወታደራዊውን አምባገነን የደርግ መንግስት ለመጣል ወጣቶች ወደ ጫካ ገቡ፡፡ በኢሕአዴግ ቋንቋ ወታደራዊው መንግስት በወደቀበት ወቅት አስራ ሰባት የታጠቁ ሐይላት ራሳቸውን አስታጥቀው እየታገሉ ነበር፡፡ እንግዲህ ቤሕነን ከነዚህ አስራ ሰባት ድርጅቶች አንዱ ነበር፡፡ ኢሕአዴግ ስልጣን ይዞ በየክልሉ ስልጣን ለነዚህ አስራ ሰባት ድርጅቶች ማከፋፈል ጀመረ፡፡ ቤሕነንም የቀድሞው ክልል ስድስት፤ የአሁኑ ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ደረሰው፡፡)

በ2002 በአንድ ሰበበኛ ቀን አብዱልከሪም ከጓደኞቹ ጋር በተለምዶ ‹የደማዚን እርሻ› እየተባለ ወደሚታወቀው የሱዳን እርሻ በቆሎ ለመሰብሰብ ይሄዳሉ፡፡ አብዱልከሪምና ጓደኞቹ ለጥቂት ቀናት በቆሎ ሲሰበስቡ ከቆዩ በኋላ ግን ሕይወት እንዳሰቡት አላዋለቻቸውም፡፡ ባላሳቡበት ቅጽበት ከየት መጡ ያላሏቸው የታጠቁ ሩጣና ቋንቋ ተናጋሪዎች (ሩጣና የበርታዎች ቋንቋ ነው) እሱንና ጓደኞቹን በመሳሪያ አስገድደው ወደ ሩቅና ወደማያውቁት ሐገር ሊወስዷቸው መኪና ላይ ጫኗቸው፡፡

(የደማዚን እርሻ (Al-Damazin Farms) ከኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ የሚገኝ እርሻ ሲሆን በርታዎች የደማዚን መሬት በሙሉ የበርታ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ የደማዚን እርሻ በዓለማቀፍ ደረጃ ታዋቂነትትን ያተረፈ ቦታ ነው፡፡ ሟቹ የዓልቃዒዳ መሪ ኦሳማ ቢንላደን ከ1983 እስከ 1989 ድረስ ሱዳን በነበረበት ወቅት በባለቤትነት ያስተዳድረው የነበረ ሲሆን፤ በወቅቱ ቢንላደን የዓልቃኢዳ አባላትን በእርሻው ቦታ ያሰለጥንበት እንደነበረ ከታወቀ በኋላ የሱዳን መንግስት በደረሰበት ዓለማቀፍ ጫና ምክንያት ቢንላደንን ከሐገር ሲያባርር እርሻውን ደግሞ በመንግስት ቁጥጥር ስር አድርጎት ለረጅም ዓመታት ቆይቷል፡፡ በቅርቡ የግብፅ መንግስት ከዚሁ መሬት ላይ ‘ጥጥና ሱፍ አለማበታለሁ’ በማለት ሰፊ መሬት ወስዷል)

ከሶስት ቀናት አድካሚ ጉዞ በኋላ አብዱልከሪም እና ጓደኞቹ የማያውቁት በተራሮች የተከበበ በርሃማ ቦታ ላይ ወረዱ፡፡ በወቅቱ ግራ የተጋባው አብዱልከሪም ይህ ቦታ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት መኖሪያው እንደሚሆን በወቅቱ መገመት አልቻለም፡፡ ትንሽ እንዳረፉ ግን ስለ ቦታው ምንነትና እነሱ ለምን ወደቦታው እንዲመጡ እንደተደረጉ ገለጻ ተደረገላቸው፡፡ ያሉት በኤርትራ መሬት ላይ ሲሆን አሁን ያሉበት ቦታ ልዩ ስሙ ‘ሀሬና’ እንደሚባልና ከኢትዮጵያና ከሱዳን ድንበር እጅግ ቅርብ በሆነ አቀማመጥ ላይ የሚገኝ ቦታ እንደሆነም በተጨማሪ ተገለጻላቸው፡፡ ወደዚህ ቦታ እንዲመጡ የተደረጉትም የቤኒሻንጉል ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና በመቃወም ዳግም ወደ ጫካ የተመለሰውን የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ቤሕነን) እንዲቀላቀሉ ታስቦ መሆኑን ተነገራቸው፡፡ ነገር ግን ከሶስተኛ ክፍል ያልዘለለ መደበኛ ትምሀርት ላልተማረው አብዱልከሪም በወቅቱ የተሰጠው ምክንያት ብዙም የሚገባው አልነበረም፡፡

(ቤሕነን ቤኒሻጉልን ለአምስት ዓመታት ከ1984 – 1988 ካስተዳደረ በኋላ፤ በ1988 ‘የታምራት ላይኔ መፈንቅለ መንግስት’ ብለን ልንጠራው በምንችለው ሂደት ኢሕአዴግ ‘አልተመቸኝም’ ያለውን በበርታዎች የበላይነት ሲመራ የነበረውን የክልሉን መንግስት ‘የአሶሳ ልጆች’ ከ ‘መንጌ ልጆች’፣ ‘የደጃዝማች ሸህ ሆጀሌ ቤተሰቦች’ ከ ‘የደጃዝማች ሙስጠፋ ቤተሰቦች’ በሚል በርታዎችን ከሁለት ከፍሎ አቶ ታምራት ላይኔ በመሩት ስብሰባ የጉምዞች የበላይነት የሰፈነበት መንግስት አቋቋመ፡፡ ፍክክሩንም “በርታዎች ከጉምዞች” የሚል አዲስ መልክ አስያዘው፡፡ ቤሕነንም ከአምስት ዓመታት ረፍት በኋላ በድጋሚ መሳሪያውን አንስቶ ጫካ ገባ፡፡)

ከዛን ጊዜ ጀምሮ አብዱልከሪም ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ሀሬናን ጨምሮ በምዕራብ የኤርትራ በርሃዎች በየቀኑ የፕሮፓጋንዳ ትምህርትና ወታደራዊ ስልጠናዎችን እየወሰደ ከሌሎች ተዋጊ ቡድኖች ጋር ተቀራርበው እንደኖሩ ፈገግ እያለ ያስታውሳል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ አብዱልከሪም ለምን ታፍኖ ወደ ኤርትራ በርሃ እንደተወሰደ ይረዳል፡፡ አሁን የቤኒሻንጉል ሕዝብ ጥያቄም ለርሱ ግልፅ ነው፡፡ እንዲያውም ጥያቄውን በራሱ ቋንቋ በሩጣንኛና በአረብኛ በደንብ እንደሚተነትን ይናገራል፡፡

ከአምስት ዓመታት የበርሃ ስልጠና በኋላ አብዱልከሪምና ሌሎች ዘጠኝ ጓደኞቹ (ከዘጠኙ መካከል አብዱ ሐሚዝና ኢሳቅ ኢብራሒም የ16 እና የ17 ዓመት ልጆች ናቸው) ወደ ቤኒሻንጉል ተመልስው ገጠር በመግባት ሕዝቡን በፍትህና በዴሞክራሲ ጥያቄዎች ላይ ትምህርት እንዲሰጡ፤ ችግር ካጋጠማቸውም እንዲዋጉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው በመጋቢት 2007 ከአድካሚና ረጅም ጉዞ በኋላ የቤኒሻንጉል ምድር ደረሱ፡፡ ነገር ግን ነገሮች እንዳሰቧቸው ቀላል አልሆኑም፡፡ ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር በተደረገ አጭር የተኩስ ልውውጥ አንድ ጓደኛቸው ቢሞትባቸውም ከተኩስ ልውውጡ ይልቅ ፈተና የሆነችባቸው ግን ተፈጥሮ ነበረች፡፡ ውሃ ተጠሙ፡፡ ጫካ ውስጥ ያገኙትን ‘ውሃ ነገር’ ሁሉ ቢጠጡም የተፈጥሮ ጥያቄያቸውን መመለስ ግን አልቻሉም፡፡ ለዚህም መፍትሔ ሆኖ የታያቸው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ ትጥቃቸውን ሁሉ ጫካ ውስጥ ደብቀው ሱዳን ውስጥ የሚገኝ በአቅራቢያቸው ያለ አንድ መንደር ውስጥ ውሃ ለመጠጣት መሔድ፡፡ ሐሳባቸውን ተግባራዊ አድርገውም ኩርሙክ አጠገብ የምትገኝ ትንሽ መንደር ውስጥ ውሃ አግኝተው እየጠጡ-እየተጫወቱ እያለ በድንገት ከየት መጡ ያላሏቸው የሱዳን ወታደሮች ከበቧቸው፡፡ ተያዙ፡፡ ወዲያው ለኢትዮጵያ ወታደሮች ተላልፈው ተሰጡ፡፡
(በ1988 ኢትዮጵያና ኤርትራ እፍ ያለ ፍቅር ውስጥ ነበሩ፡፡ ኤርትራ ሎዓላዊነቷ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሱዳን ጋር ፀብ ውስጥ ገባች፡፡ በወቅቱ በፀቡ ላይ ገለልተኝነት እንዲያሳይ በሱዳን መንግስት በጥብቅ ሲጠየቅ የነበረው ኢሕአዴግ በግልፅ የኤርትራ ወገንተኛ መሆኑን በማወጁ የኢትዮጵያና የሱዳን ግንኙነት እጅጉን ሻክሮ ነበር፡፡ ከዚህ ጋርና በደቡብ ሱዳን ከነበረው ሁኔታ ጋር ተያይዞም በቤኒሻንጉል በኩል በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የድንበር እሰጣ-ገባ ተነሳ፡፡ በወቅቱ በኢሕአዴግ አቋም የተበሳጩት ፕሬዘደንት ኦማር አልበሽር “ሰራዊታችን በሁሉም መልኩ ዝግጅቱን አጠናቆ የትግሬ ወታደሮችን ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ እየጠበቀ ይገኛል” በማለት ሕወሃትን ብቻ ነጥለው መዛታቸውም ይታወሳል፡፡ በወቅቱ አልበሽር በሱዳኑ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው “በአላህ ፈቃድ ዝም አንልም፡፡ አስመራ፣ አዲስ አበባና ካምፓላ ላሉት ተንኳሽ መንግስታት መልስ አንሰጣለን፡፡ ለተቃዋሚዎቻቸውም መሳሪያ እናስታጥቃለን፡፡” ብለውም ነበር፡፡ አሁን አልበሽር ከኢሕአዴግ ጋር ፍቅር በፍቅር ሆነው ያማራቸውን የውጭ ጉዞ ጥማት አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ አሶሳ፣ መቐለ … እየተመላለሱ እየቆረጡ ነው፡፡ እንደ አብዱልከሪም ያሉትን የኢሕአዴግን ተቃዋሚዎችን ከሃያ ዓመታት በፊት አስታጥቃለው ካሉት ቃላቸው በተቃራኒው ይዘው ለኢሕአዴግ እያስረከቡ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ የኤርትራን ኤርትራ ደግሞ የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች እያሰለጠኑ ጸባቸውን አክርረው ቀጥለዋል፡፡)

አብዱልከሪምና ጓደኞቹ በተያዙበት ወቅት መጀመሪያ የተወሰዱት ወደ አሶሳ የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ነው፡፡ በማታ ወደ ካምፑ ታስረው የገቡት እነአብዱልከሪም በሰራዊቱ አባላት አሰቃቂ ድብደባ የተፈፀመባቸው ሲሆን፤ በፌሮ ብረት ውሃ ላይ ሲደበደብ እንደቆየ የሚናገረው አብዱልከሪም በተያዙበት እለት ሌሊቱን ሙሉ አብዱልከሪም ብቻ ‘አንተ ነህ መሪው’ በሚል መነሻ በተለምዶ ‘ሒሊኮፍተር’ እየተባለ የሚጠራውን የግርፋት አይነት እንደሚገፈፍ በግ ተሰቅሎ ሲገረፍ እንዳደረ ይናገራል፡፡ ዝናብ ሌሊቱን ሙሉ እየዘነበበት ዛፍ ላይ በሒሊኮፍተር ቅርፅ ተሰቅሎ ሲሽከረከር ያደረው አብዱልከሪም ከስምንት ሰዓታት ስቅላት በኋላ መሬት ሲወርድ እጆቹ ሁሉ መንቀሳቀስ አቅቷቸው እንደነበር ሲያስታውስ ፊቱ ላይ ሐዘን ይታያል፡፡

(‘ሒሊኮፍተር’ የተባለው የማሰቃያ ዘዴ (Torture Method) በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ የገነነ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኤርትራ ዜጎቿን በዚህ አይነት የማሰቃያ ዘዴ እንደምታሰቃይ በተደጋጋሚ ሪፖርት ተደርጓል፡፡ ኢትዮጵያም በተለይም ወታደራዊ ካምፖች ውስጥ በዚህ የስቃይ አይነት ዜጎችን እንደምታሰቃይ አብዱልከሪምና መሰሎቹ ምስክሮች ናቸው፡፡)

አብዱልከሪምና ጓደኞቹ በግንቦት አጋማሽ 2006 ነበር ወደ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) የመጡት፡፡ በዛን ወቅት አብዱልከሪም እኔ ያለሁበት ክፍል ውስጥ (በተለምዶ ሳይቤሪያ 5 ቁጥር የሚባል ክፍል) ተመድቦ የመጣ ጊዜ በባዶ እግሩ በጣም የተዳከመ ሆኖ ይታይ ነበር፡፡ የገባ ሰሞን በጣም እንቅልፍ ይተኛ ነበር፡፡ እጅግ በጣም አድካሚ መከራና ስቃይ አልፎ እንደመጣም ያስታውቃል፡፡ በዛ ላይ ደግሞ ማዕከላዊ ምንም እንኳን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያለውን ታሪኩን ደጋግሞ ቢነግራቸውም “የሕዳሴውን ግድብ ልናጠቃ ተልዕኮ ተሰጥቶን ነበር በማለት እመን፤ አመጣጣችሁን ዋሽተኸናል” እያሉ በየቀኑ ‘መርማሪ ፖሊሶቹ’ ይገርፉት ነበር፡፡ አብዱልከሪም ‘ለምርመራ’ ተጠርቶ ተደብድቦ ሲመጣ ድካሙ ስለሚብስበት ይተኛ ነበር፡፡ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነበር በጊዜው የነበረው፡፡ አንድ ቀን ማዕከላዊ ከጓደኞቹ ጋር ተጠርቶ ሲመለስ ‘ምን አሉህ?’ አልነው፤ እሱም ‘መሳሪያችን ከፊታችን አስቀምጠው ፎቶ አነሱን’ አለን፡፡ ለካ በቴሌቪዥን ካሜራ ቀርጸዋቸው በማታው የቴሌቪዥን ዜና ‘አስር አሸባሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ’ የሚል ዜና ተላልፎ ነበር፡፡ አብዱልከሪም ‘በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረሃል’ የሚለው ነገር ለረዥም ጊዜ ምን ማለት እንደሆነ አይገባውም ነበር፡፡ ‘ምንድን ነው ሽብርተኝነት?’ ይላል ሁሌ፡፡ ‘አሸባሪ እኔ እሆናለሁ እንዴ?’ እያለም ፈገግ ማለት የዕየለት ደንቡ ነበር፡፡ አያይዞም ‘እኔ ልማት የለም፣ ዴሞክራሲ የለም ብየ ለቤኒሻንጉል የታገልኩ ታጋይ ነኝ እንጅ አሸባሪ አይደለሁም’ ይላል በሚያስቸግረው አማርኛ፡፡ ፍርድ ቤት ቀርበው የሃያ ስምንት ቀን ቀጠሮ ሲሰጥ ምን ማለት እንደሆነ መረዳት እጅግ ይቸግረው ነበር፡፡ አንዳንዴ እንዲያውም ያለአስተርጓሚ ስለነበር የሚቀርቡት ዳኛዋ ምን ትዕዛዝ እንደሰጠች እንኳን ማወቅ ሳይችሉ ይመለሱ ነበር አብዱልከሪምና ጓደኞቹ፡፡

(የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ከሚታወቁት ሰላማዊ ግለሰቦችን ለማጥቂያ መሳሪያ ከመሆኑ ባሻገር፤ በዋናነት ሰለባ ያደረጋቸው የተለያዩ ብረት ያነሱ ኃይሎችን መሆኑ ክሶቹን ተመልክቶ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ብዙዎቹ የሕጉ ሰለባ ግለሰቦች አማርኛ ቋንቋ የማይናገሩ መሆናቸው ሕጉም ሆነ ክሳቸው ምን ማለት እንደሆነ ሳይገነዘቡ ለረጅም ዓመታት እስር መዳረጋቸው ደግሞ አሳዛኙ እውነታ ነው፡፡ ፍርድ ቤቶች በአስተርጓሚ እጦት የሚቸገሩ ከመሆናቸውም ባለፈ ባብዛኛው አስተርጓሚ የሚባሉት ራሳቸው ‘መርማሪ ፖሊሶቹ’ ስለሚሆኑ እንደአብዱልከሪም ላሉ ተከሳሾች ጥላቻና ንቀት ያላቸው ናቸው፡፡)

እኔ መደበኛ ክስ ተመስርቶብኝ ወደ አዲስ አበባ የቀጠሮ ማረፊያ ቤት (ቂሊንጦ) በሔድኩበት ወቅት አብዱልከሪም ምርመራ ጨርሶ የነበረ ቢሆንም ከቤኒሻጉል ተይዘው በመጡ አዲስ ተከሳሾች ምክንያት ዱላውና ድብደባው በአዲስ መልክ በርትቶበት ነበር፡፡ በጥቅምት 2007 ላይ አብዱልከሪም ከጓደኛው ፈተልሙላ አጣሂር ጋር እኔ ወዳለሁበት ቂሊንጦ ዞን አንድ ተመደበ እና በአጋጣሚ አንድ ቤት (ዞን አንድ፣ አንደኛ ቤት) አብረን ሆንን፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ማታ ማታ ሁሌ ብዙ ነገር እናወራ ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን አዝኖ ቤተሰብም ሆነ ጠያቂ ስለሌለው ራሱን በትንሽ ገንዘብ (በወር 60 ብር) ለመደጎም የጀመረውን ለእስረኞች ወጥ የማመላለስ ስራ ፖሊሶች እንደከለከሉት ነገረኝ፡፡ ‘ለምን?’ ብየ ስጠይቀው ‘እነዚህ ጥቋቁር ልጆች ምንም ስራ እንዳይሰሩ፤ አሸባሪዎች ናቸው’ ብሎ አንድ ፖሊስ ከለከለኝ አለኝ፡፡ ልብን ይሰብራል፡፡ ከመከልከሉ ይልቅ የተከለከለበት ምክንያት ደግሞ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ከዚህ የፖሊሶቹ ተግባር ባለፈ ረዘም ያሉና የቆዳ ቀለማቸው ጠቆር ያሉ ሰዎች ሁሉ የጋምቤላ ተወላጆች ለሚመስሉት አብዛኛው እስረኛ አብዱልከሪምን ‘ኡጁሉ’ እያለ የሚጠራው የነበረ ሲሆን፡፡ ገራገሩ አብዱልከሪም ግን ‘እኔ በርታ ነኝ፤ ምንድነው ኡጁሉ?’ እያለ ፈገግ ከማለት ውጭ አይከፋውም ነበር፡፡

(የቆዳ ቀለምን መሰረት አድርጎ የሚደረገው ፍረጃና ማግለል፤ በተለይም በጋምቤላ እና በቤኒሻጉል ክልሎች ላሉ የፖለቲካ ቡድኖች አንዱ የተቃውሟቸው መሰረት ነው፡፡ ቤሕነን በርታዎችን በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት ከምትገፋ ኢትዮጵያ የራሱን ሀገር መመስረት እንደሚመርጥ በፕሮግራሙ የገለጸ ሲሆን፤ ይሄም መጀመሪያ በርታዎች ከቤኒሻንጉል ክልል ተነጥለው በኢ.ፌ.ዴ.ሪ በሕገ መንግስት አንቀጽ 47 መሰረት የራሳቸውን ክልል ለማቋቋም ከጠየቁት ጥያቄ አንድ ርምጃ ወደፊት የሔደ ነው፡፡በአሁኑ ወቅት ጥፋተኛ ተብለው ፍርዳቸውን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዘደንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋዴን) የተባለ ተገንጣይ (secessionist) ፓርቲ ያቋቋሙበትን ምክንያት ሲያስረዱ “በአኝዋኮች ላይ ከሚደረገው የዘር ማጥፋት በላይ ‘ለማ’ እና ‘አዲስ ጎማ’ እተባልን በቆዳ ቀለማችን ምክንያት የምንገፋበት ሃገር ውስጥ መኖር አስፈላጊ አይደለም” በማለት ይገልጻሉ)

አንድ ቀን አብዱልከሪም አማርኛ ለማንበብ እየሞከረ ነበርና “‘ሕገ መንግስት’ የሚባለውን ‘ኪታብ’ ስጠኝ” ብሎኝ ሰጠሁት፡፡ እሱም ምንነቱን አይቶ ስለቤኒሻንጉል የሚያወራውን አንቀጽ እንዳሳየው ጠይቆኝ አንቀጽ 47/1/6 ላይ ከዘጠኙ ክልሎች አንዱ የቤኒሻንጉል/ጉሙዝ ክልል መሆኑን የሚጠቅሰውን ክፍል ሳሳየው ተገርሞ ‘እንዴት ጉሙዝ ይባላል? የቤኒሻንጉል ሕዝብ አንድ ነው እነሱ ለምን ጉሙዝን ለብቻ ሕገ መንግስት ላይ ይጽፋሉ?’ እያለ ተበሳጨ፡፡ እኔ ‘ሁለቱ ይለያያል ብለው ነው ይሄን ያደረጉት’ ብለውም ሊያምን አልቻለም፡፡ በርሃ እያለ የቤኒሻንጉል ሕዝብ ሁሉ አንድ መሆኑን በደንብ ተነግሮታል፡፡ የጉሙዝ ልጆች ከበርታ ልጆች ጋር አንድ ላይ ብረት አንስተውም ተመልክቷል፡፡ ‘ታዲያ ሕገ መንግስቱ ለምን ይለያየናል?’ ማለቱ እንግዲህ ከዚህ የራሱ እውነት የሚመነጭ ነው፡፡

(የቤኒሻንጉል ክልልን ፖለቲካ ያጠኑ ሊቃውንት ይሄ ‘ጉምዝ ከበርታ’ የሚለው ምንታዌ የፖለቲካ አሰላለፍ ኢሕአዴግ የለመደውን ሕዳጣንን በብዙኃን ላይ የማንገስ ዘይቤ ተቀጥላ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ለዚህም አሰላለፍ ያመች ዘንድ በክልሉ የሚኖሩ አምስቱም ነባር (indigenous) ሕዝቦች (በርታ፣ ጉሙዝ፣ ሽናሻ፣ ማኦና ኮሞ) የየራሳቸውን የፖለቲካ ፓርቲ እንዲመሰርቱ ያደረገው ኢሕአዴግ አንዱን የአንዱ አለቃ በማድረግ ክልሉን በሩቅ መቆጣጠር ችሏል፡፡)

አብዱልከሪም የምርጫ 2007 የፓርቲዎች የቴሌቪዥን ክርክርን እያየ ‘ወላሂ ሽማግሌው ጎበዝ’ ነው ይላል ዶ/ር መረራ ጉዲና ሲናገሩ ከት ብሎ እየሳቀ፡፡ መረራ የሕዝቡን ችግር ሕዝቡ በሚገባው ቋንቋ መንገራቸው ነው ለአብዱልከሪምና መሰሎቹ መረራን እንዲወዱ ያደረጋቸው፡፡ ቤኒሻንጉልን የተመለከተ ዜና ሲመለከት ልቡ የሚሰቀለው አብዱልከሪም፤ የሕዳሴው ግድብ ለቤኒሻንጉል ሕዝብ ምን ጥቅም እንደሚሰጠው ብዙም አይገባውም፡፡ ‘ልማት ማፍረስ የቤሕነን አላማ አይደለም’ የሚለው አብዱልከሪም ፍርድ ቤት ቀርቦ መከራከር የሚባለው ነገር አይገባውም፡፡ ‘እውነትን ብቻ መናገር ያስፈልጋል’ የሚለው አብዱልከሪም ‘መከራከር በመሳሪያ ነው’ ብሎ ያምን እንደነበር እየሳቀ ይናገራል፡፡ ‘አዎ እኔ የቤሕነን ወታደር ነኝ፤ ለልማትና ዴሞክራሲ ታግያለሁ፤ ልማት ላጠፋ ግን አልመጣሁም’ ብሎ ውሸት በማያውቀው አንደበቱ ንጽህናው ተናግሯል፡፡ ከሳሹ ግን ‘አይ ግድቡንም ሊያጠቁ ነበር’ ብሎ ከመካከላቸው ያስቀረውን ጓደኛቸውን ለምስክርነት አቅርቦባቸዋል፡፡ ነገር ግን ውሸትን ከሚጸየፉት የበርታ ልጆች አንዱ የሆነው የከሳሽ ምስክር ‘እኛ ግድብ ልናፈርስ አልመጣንም’ በማለት መስክሮ የነአብዱልከሪምን እውነት አረጋግጧል፡፡ ፍርድ ቤቱም ሁሉንም ተከሳሾች በጸረ ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀጽ 7/1 መሰረት ጥፋተኛ በማለት የአራት ዓመታት ጽኑ አስራት በሰኔ ወር 2007 መጀመሪያ ላይ ፈርዶባቸዋል፡፡

እነአብዱልከሪም ተፈርዶባቸው የተመለሱ እለት አራት ዓመት ማለት ምን እንደሆነ በቅጡ አልተረዳውም፡፡ ሁሌም የማይለየውን ፈገግታው ፊቱ ላይ ብትን አድርጎ ‘አቡሌ አይዞህ’ ይለኛል እኔኑ፡፡ ‘አቡሌ’ ማለት በበርታ ቋንቋ ‘ጓደኛዬ’ ማለት እንደሆነ ስንቴ ነግሮኛል? አብዱልከሪምን ሲፈታ ምን ማድረግ እንደሚፈልግ በጠየኩት ቁጥር ‘አሁን ረፍት ያስፈልጋል’ ይለኛል፡፡ ቤኒሻንጉል ውስጥ ወደ ትውልድ ቦታው ‘ቁቆ’ ተመልሶ በልጅነቱ ይወዳት የነበረችውን ‘ለይላ’ የምትባል ወዳጁን አግብቶ ማረስ እንደሚፈልግና ከዛ ትምህርት መማር እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ ይነግረኝ ነበር፡፡ ከእርሻ ቦታ ታፍኖ ወደ ጦር ካምፕ የተወሰደው አብዱልከሪም እናቱን ከተለያቸው ስምንት ዓመታት እንደሆኑ እየገለጸ በሕይወት መኖራቸውን እንኳን እንደማያውቅና ሲፈታ ግን እንደሚያገኛቸው ተስፋ አለው፡፡ ተወዳጁ ጓደኛዬ አብዱልከሪም ከታሰረ ሁለተኛ ዓመቱ ሲሆን፤ ወደ በርሃማው ‘የሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት’ ከሔደ ደግሞ አንደኛ ዓመቱ፡፡

ምንጭ – ዞን 9 ብሎግ