የፕሬዝደንት ኦባማ “ታሪካዊ ጉብኝት” — አምባገነን አወዳሽ ወይንስ ዲሞክራሲ አጎልማሽ?

አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

ፕሬዝደንት ኦባማ ኢትዮጵያን ለምን ጎበኙ?

ፕሬዝደንት ኦባማ በስልጣን ላይ ካሉ የአሜሪካ መሪዎች የመጀመሪያው ሆነው ወደ ኢትዮጵያ የሄዱበት ምክንያት “ዱብ እዳ” አይመስለኝም። የኢትዮጱያና የአሜሪካ ግንኙነት የተመሰረተው በብልሁና ዘመናዊው መሪ በአፄ ምኒልክና በአሜሪካው ፕሬዝደንት ቲዎዶር ሮዝቤልት አማካይነት ነው። ኢትዮጵያ በአድዋ የተጎናጸፈችው ድል በዓለም እውቅና እንደሰጣት ታሪክ መዝግቦታል። ይህ ሃቅ ማንም ግለሰብ ወይንም ቡድን ወይንም መንግሥት ሊለውጠው የሚያስችል የሚራል ብቃት የለውም። አሜሪካኖችና ሌሎች መንግሥታት “ምን አይነት የጥቁር መሪ ነው የአውሮፓን ኃያል ለማጥቃት የቻለው” ብለው እንደተነጋገሩ ይታወቃል። በዚያ ወቅት የአረብ ምሁራን ኢትዮጵያ “ልክ እንደ ጀርመኒ በፍጥነት ለማደግ ትችላልች” እንዳሉ አውቃለሁ። ሆኖም አገራችን በውስጥና በውጭ ጠላቶቿ ምክንያት ሰላም አላገኘችም ነበር። ቁም ነገሩ፤ ከዛሬ ሁለት መቶ አስራ ሁለት ዓመት በላይ የተመሰረተው የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት በፋሽስቱ ወረራና በደርግ ፀረ-አሜሪካንነት ፕሮፓጋንዳ ቢበከልም፤ ተከታታይነት አለው።Obama in Addis Ababa, Ethiopia

ተከታታይ የኢትዮጵያ መንግሥታት የራሳቸውን አገር ጥቅም ለማስከበር ሙከራ እንዳደረጉ ሁሉ፤ የአሜሪካም መንግሥት የራሱን ጥቅም ለማስከበር ሞክሯል፤ አሁንም ይኼን መርህ ተከትሏል። ፕሬዝደንት ኦባማ የታሪክ፤ የውጭ ግንኙነትና የፖለቲካ ምሁር እንደመሆናቸው መጠን በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል የቆየውን ግንኙነት በጽሞና ያውቃሉ። አንድ መንግሥት በሌላ ቢለወጥ ግንኙነቱ የሚቀጥል መሆኑን ይገነዘባሉ ብል ከሃቁ የራቅሁ አይመስለኝም።

ለመሆኑ በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መርሆዎች የቶቹ ናቸው? የትኛው ይቀድማልና ለምን? ሽብርተኞች በአሜሪካ ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ሲያደርሱ፤ የቡሽ መንግሥት በዓለም ዙሪያ ወዳጆች ፈልጎ በአሜሪካ ጥቅም የተመሰረተና ስትራተጂክ የሆነ የቅርብ ወዳጆች ፈጥሯል። ኢትዮጵያ ለዚህ አመችና አስተማማኝ የሆነ አገዛዝ አላት ከሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሶ በህወሓት ከሚመራው የኢህአዴግ መንግሥት ጋር ሽብርተኞችን ለማዳከም፤ ቢቻል ለማጥቃት “ቃል ኪዳን” ተገባ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መርሆዎች ከሆኑት፤

አንድ፤ ሽብርተኞችንና አመፀኞችን መታገልና ማጥቃት፤

ሁለት፤ ንግድንና ኢንቬስትሜንትን ማስፋፋት፤

ሶስት፤ ከቻይና ጋር አቻ ለአቻ በሆነ ደረጃ መወዳደር፤

አራት፤ ድህነትን ለመቅረፍና እርጋታን ለማጠናከር እርዳታ መስጠት፤

አምስት፤ በረዢም ጊዜ ስሌትም ቢሆን፤ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ስር እንዲሰድ ድምጽ ማሰማትና የተቻለውን ድጋፍ ማድረግ፤

ስድስት፤ የአሜሪካን ድጋፍ ለማግኘት የአፍሪካ አንድነት ድርጅትና የተባበሩት መንግሥታት በአፍሪካ ለሚያደርጉት የጸጥታ እንቅስቃሴ ድጋፍ የሚሰጥ ወዳጅ መንግሥትን መርዳት ናቸው።

ከእነዚህ መካከል አሜሪካ ቅድሚያ የምትሰጠው ለመጀመሪያው ነው… [ሙሉውን ለምንበብ እዚህ ይጫኑ ]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s