Yeharerwerk Gashaw
እህታችን የትመወርቅ ጃጋማን እግዚአብሄር ቶሎ ይማርለን።
የጀግናው የነጻነታችን አባት ከሆኑት አንዱ የአንበሳ ቁንጮ ከጀነራል ጃጋማ መወለድዋ አንዱ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደም እና ልጁም ስትሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ እራስዋ ክብርዋ መላልሳ የምትለብሰው እንክዋን አባትዋ እና ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጀግኖች ወድቃ ያነስዋትን የኢትዮጵያን እና የመላው ሕዝብዋን አረንጉዳውዴ ፡ ቢጫ ቀይ ያሸበረቃትን ሰንደቅ አላማችንን ነው። ሶስተኛው በጣሊያን አገር የምትኖረው ልጅዋ የትመወርቅን የምታስታምመውም ልክ እንደ አያትዋ እና እናትዋ ክብራ ኢትዮጵያን የሚያንጸባርቀውን የኢትዮጵያአ ሰንደቅ አላማ ማሸብረቂያዋ አድርጋ በዚህ በመታወቅዋ ነው። ይሄ የጀነራል ጃጋማ ቤተሰብ ከእህታችን የትመወርቅ ባለቤት ጭምር ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም እና ክብር ያገለገሉ ናቸው። በመሆኑም እንክዋን የትመወርቅ ጃጋማን አይደለም ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ እንደምንችለው አቅማችን እንደሚፈቅደው ጉዳያችን ብለን መርዳት ግዴታችን ነው ብዬ አምናለሁ በበኩሌ። የትመወርቅ በጣም ጥሩ ሰው ሰው አክባሪ እና በጎ ለሁልም ሰው የምትመኝ እህት ነች።
የታመመውን ሁሉ እሱ ክርስቶስ በትንፋሹ ያድንልን፡ ይዳብስልን በየቤቱ። በምድር ላይ ባስተማረብት ጊዜ መድሃኒአለም እየሱስ ክርስቶስ እንዳዳናቸው ከደዌያችው ሁሉንም አሁንደግሞ እህታችንን የትመወርቅንም ዳብሶ ያድንልን። ጀነራል ጃጋማም ባለቤትዋም አቶ ንጉሴ ልጆችዋም መላው ቤተሰቡ የትመወርቅ ድና የአገርዋን ምድር የምትኖርባት አድርጎ ያሳያቸው። በክርስቶስ ሁሉም ይሆናል. አሜን።
