ኢትዮጵያዊነት ከቋንቋ በላይ ነው (ከይገርማል)

imagesየቃላት ጨዋታ እንዲህ እንዳሁኑ የደራበትጊዜ ያለ አይመስልም:: ብሄር: ብሄረሰብ:ጎሳ እያሉ ቃሉ ስለሚወክለው ትርጉምበየራሳቸው መንገድ የሚጠበቡ ሰዎች ዛሬላይ በጣም በርክተዋል:: አንዳንዶችየነርሱን ትርጓሜና አስተሳሰብ እንድንጋራየምናውቀውን ሳይቀር ሊያስጠፉንማወናበድ ቀጥለዋል:: በተለያዩ ሰዎችየተለያየ ትርጉም እየተሰጣቸው የጉንጭማልፊያ የሆኑን ሌሎች ቃላቶችም ብዙናቸው:: ይህ የቃላት ጨዋታለብዙወቻችን ምንም ላይመስለንይችላል:: ለአንዳንዶቹ ግን ለልዩነት እንደአንድ ምክንያት ሆኖ ይታይና ጦር የሚያማዝዝ እስከመሆን ያደርሳል:: 

በውስጣቸው ብዙ ትናንሽ ጎሳወችን ያቀፉ ትልቅ ነን የሚሉ ወገኖች የሌሎችን ህልውና ይውጡና ራሳቸውን ብሄር ነን ሲሉ ከምናውቀው የብሄር ትርጉምጋር ጨርሶ ይጣረሳል:: ከሶሻሊዝም ርእዮትአለም ጋር የገነነው የብሄር ጥያቄ የስርአቱን መፍረስ ተከትሎ ሊከስም ባለመቻሉ ዛሬም ላይ ከነትርጉሙሳይቀር ተምታቶብን ግራ እያጋባን ነው:: በውስጡ ብዙ ቋንቋወች: ባህሎች: ወጎች: ልማዶች: የአኗኗር ዘይቤወች: እምነቶች: ስነልቦናዊ አመለካከቶችናማህበራዊ ማንነቶችን የያዘና በሌሎችም አካባቢወች ተበትኖ የሚኖር ህብረተሰብ እንዴት ብሎ የብሄር ስያሜን ለማግኘት እንደሚችል ማሰብያስቸግራል: ብሄር ብሄር የሚሆነው በቋንቋ ተናጋሪው ብዛት ብቻ ሊሆን በፍጹም ስለማይችል::

ብሄር ነን ብለው የብሄር ጥያቄን ከሀገር ጥያቄ ለይተው ለብቻው ነፍስ ዘርተውበት የሚያራግቡት: ብሄራችን ነው ለሚሉት ህዝብ ነጻነት ለመታገልእየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የሚናገሩት የብሄር ካባ የለበሱ የጎሳ ድርጅቶች ናቸው::  የጎሳ ድርጅቶቹ ኢትዮጵያውያንን በሚያቀራርቧቸው ላይ ሳይሆንበሚያለያዩዋቸው ጉዳዮች ላይ አተኩረው ደከመን ሰለቸን ሳይሉ በመስራታቸው ህዝባችን ሆድና ጀርባ እንዲሆን አድርገው ለጋራ ነጻነት: ዴሞክራሲ:ፍትህ: እኩልነትና በሰላም አብሮ መኖር ለሚደረገው ትግል መሰናክል ሆነዋል::

የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ወገኖች እንቆቅልሽ እንደሆነ ቀጥሏል:: በጎሳ (ማንም የፈለገውን ማለት ከቻለ እኔምሁላችንንም የሚያስማማ አንድ ወጥ ትርጉም እስኪገኝላቸው ድረስ ቃላቶቹን እንደመሰለኝ እያቀያየርሁ ብጠቀምባቸው ችግር የለውም ብየ በማመኔድርጊቴ እንደ ድፍረት አይቆጠርብኝ) የተደራጁት ሀይሎች አሁን ላይ የብሄረሰቦችየራስን እድል በራስ የመወሰን እስከመገንጠልመብት ህዝባዊእውቅና እንዲሰጠውና ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ በዘመናዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የሚያምኑ በርካታ ናቸው:: እንደተባለውም ቀደም ሲልየመገንጠልን አላማ በግላጭ ሲያራምዱ የነበሩት እኒህ ድርጅቶች አካሄዳቸው አልይዝላቸው ሲል ሌላ ስልት ቀይረው ቀርበዋል የሚለውን ምልከታደፍሮ ውሸት ነው ብሎ ለማስተባበል የሚከብድ ይመስላል::   

አዲሱ ስልታቸው የሚባለው ስለኢትዮጵያ አንድነት የሚጨነቁትና የሚያስቡት አማሮች ብቻ ሳይሆኑ እነርሱም እንደሆኑ አድርገው ማቅረብ ነው::ይህንን ለማስረገጥ ሲፈልጉራሱን ብቸኛ የአንድነት ጠበቃ ያደረገበማለት አማራውን ይጎንጡና: የሀገር አንድነት ጉዳይ ከማንም ባላነሰ እነርሱንምእንደሚያሳስባቸው ይናገራሉ:: እንዲህ እያሉ ትንሽ ሲያዘግሙ ይቆዩና ወዲያው ግራ ኋላ ዞረው: የምንታገለው የራስን እድል በራስ የመወሰን  መብትለማረጋገጥ ነው ይላሉ:: ይህ አባባል ዝም ብለው ሲያዩት ጤነኛ ሊመስል ይችላል:: ቀጥለው የሚያመጡት ሀሳብ ግን ልብ ላለው ሰው ፍላጎታቸውንቁልጭ አድርጎ ያሳያል::  

ለምሳሌ ያህል አንዳንድ የኦሮሞ ድርጅቶች  “በአፍሪካ ውስጥ በብዛቱ ወደር የሌለው ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶቹ ተነፍገውት በጭቆና ስርእንዲኖር ተደርጓል:: ይህ ታላቅ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን እድሉ ሊሰጠው ይገባል:: ኦሮሞው እንደህዝብ መብት ከተሰጠው ከሌሎች ብሄርብሄረሰቦች ጋር አብሮ ለመኖር የሚገደው አይሆንም:: ትግላችን ህዝቡ የመብቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ነው:: ከዚያ በኋላ ከሌሎች ብሄርብሄረሰቦች ጋር እንዴት አብሮ ሊኖር እንደሚችል እራሱ ይወስናልይላሉ::

ይህ አካሄድ በአንድነት ሀይሉ ላይ እያሳደረ ያለው ተጽእኖ ቀላል የሚባል አይሆንም:: ሲያዩት አግባብ የሚመስል በመርዝ የተበከለ ቅስቀሳ የየዋሀንን ልብከአንድነቱ ጎራ ሊያስሸፍት እንደቻለ አንዳንድ መረጃወች አሉ::

አንቀጽ 39 በተመለከተ ጠቃሚነቱን ሲያስረዱብሄር ብሄረሰቦች መብታቸው ያለገደብ (እስከመገንጠልሊከበርላቸው ይገባል:: ሰው የተፈጠረውበነጻነት ነው:: ይህንን ነጻነቱን ማንም ሊያሳጣው አይገባም:: የመገንጠል መብት መኖር ለብሄረሰቦች አብሮ መኖር ዋስትና ነው:: አንዱ ብሄረሰብአድልኦ ተፈጽሞብኛል ወይም ተጨቁኛለሁ ብሎ ካመነ መገንጠል እፈልጋለሁ የሚል ጥያቄ ሊያቀርብ ስለሚችል ይህን መበታተን ለማስቀረት ሲባልየብሄረሰቦችን መብት የሚጋፋ አይኖርም

በማለትየራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከመገንጠልየሚለው ጽንሰ ሀሳብ ለብሄር ብሄረሰቦች አብሮ መኖር ዋስትና እንደሆነ ለማሳመንይደክማሉ::

በሌላ በኩል አንድነት አንድነት እያለ የግዳጅ አንድነት ለመፍጠር እየሰራ ያለው አማራው ነው በማለት የአንድነት ተሟጋቾችን ከአማራ ጋርሲያተሳስሯቸው ይታያል:: እንደተባለውም ስለአንድነት እየተከራከሩ ያሉት በአብዛኛው አማሮችና ደቡቦች ናቸው ቢባል ልክ ይመስላል:: በህብረብሄራዊአደረጃጀት ውስጥ የተሰባሰቡት አንዳንድ የሌሎች ክልሎች ሰዎች በተራዘመ የጎሰኞች ሰበካ እየተሸነፉ በመንፈስ ከጎሳቸው የወገኑ ወይም ለጎሳቸውየሚሰልሉ ሆነዋል የሚሉት ወገኖች በርካታ ናቸው::

የመገንጠል መብት ማንን ይጠቅማል?

ብዙ ሰዎችን ጠይቄ እንደተረዳሁት ከመገነጣጠል የሚገኝ ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊም: ማህበራዊም ሆነ ፖለቲካዊ ጥቅም የለም የሚል ነው:: ትግራይንለአብነት ብንወስድ ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ጋር ያለው ሁለንተናዊ ቁርኝት እንዲህ በቀላሉ የሚበጠስ አይደለም እንጅ ተነጥለው ራሳቸውን ችለው ይኑሩ ቢባል በታሪክ የሚታወቀው ክልሏ ዝናብ አጠር የሆነ: ተራራ የበዛበት: መሬቱ የተበላና ለእርሻ ብዙም የማይመች በመሆኑ የገንጣይ ቡድኑ አመራሮች ካልሆኑ በቀር ሌላው ህዝብ የአመት ቀለቡን እንኳ ለመሸፈን የሚያስችል የኢኮኖሚ አቅም አያገኝም:: የክልሉን ህዝብ አመት ከአመት ከመቀለብ አልፎየውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ ምርት ለማምረት የሚያስችል ለግብርና የተመቸ መሬት: ነዳጅ ወይም ሌላ የተፈጥሮ ማዕድን ሳይኖር ራሴን ችየ እኖራለሁማለትና የመገንጠል መብት አራማጅ ሆኖ መቅረብ ከእብደት ተለይቶ የሚታይ አይሆንም:: ጓድ መንግስቱ ሀይለማሪያም በአንድ ወቅትከትግራይየሚገኘው ገቢ ለቾክ መግዣ እንኳ የሚበቃ አይደለም” ያሉት ይህን የክልሉን የኢኮኖሚ ድህነት ለመግለጽ ነበር:: በጣም ብዙው የትግራይ ህዝብየሚኖረው በንግድና በተለያየ የአገልግሎት ዘርፎች በአብዛኛው በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ተሰማርቶ በሚያገኘው ገቢ ነው:: የመገንጠል መብት ተግባራዊየሚሆን ከሆነ የትግራይ ክልል ከሌሎች ክልሎች በሀይል የያዛቸውን አካባቢወች ለቆ በታሪክ በሚታወቀው ክልሉ ታጥሮ የሚቀመጥ ይሆናል ማለትነው::

ሌላው የመገንጠል መብትን ከሚያራግቡት ቡድኖች ውስጥ የኦሮሞ ድርርጅቶች ይገኙበታል:: እኒህ ድርጅቶች ለኦሮሞ ህዝብ ሳይሆን ለራሳቸውየበላይነት የሚሰሩ ናቸው:: አብዛኞቹን የኦሮሞ ድርጅቶች የሚያስማማቸውየራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከመገንጠልየሚለው በታኝ አላማነው:: የሚያለያያቸው ዋናው ጉዳይ ደግሞ አካባቢያዊነትና የስልጣን ጥም ነው:: ኦነጎችና ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች መለያየትን እንደመፍትሄ የሚወስዱሲሆን ሌሎች ወገኖች ግን የመገንጠል መብት እውን የሚሆን ከሆነ በዋናነት ተጎጅ የሚሆነው ኦሮሞው ነው የሚል እምነት አላቸው::

ለዚህ አባባላቸው የሚያቀርቡት ምክንያት የተለያየ ይሁን እንጅ ሲጠቃለል የኦሮሞ ህዝብ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ተበትኖ የሚኖር በመሆኑእንደአማራው ሁሉ ለጥቃት የተጋለጠ ነው:: በዚያ ላይ ወያኔ ከፈጠረለት ሀያአምስት አመት ያልሞላው ክልል ውጪ የእኔ ነው የሚለው ታሪካዊ መኖሪያየለውም:: ከታሪክ እንደምንረዳው ኦሮሞው ከደቡብ አካባቢ ፈልሶ ኗሪውን ህዝብ እያፈናቀለ በጉልበት እንደሰፈረ ነው:: ይህንን ታሪክ ወያኔም ሆነየኦሮሞ ድርጅቶች በምንም አይነት ታምር ከታሪክ ማህደርና ከህዝብ ዐዕምሮ በሆታና በውንብድና ሊፍቁት የማይችሉት እውነታ ነው የሚል ነው::

የኦሮሞ ድርጅቶች ከስሜታዊነት ወጥተው ወደዘላቂ ብጥብጥ የሚወስደውን መንገድ በመዝጋት ወደዘላቂ ሰላም የሚወስደውን መንገድ መያዝይገባቸዋል:: እንዲያውም ለኢትዮጵያ አንድነት ከማንም በላይ ሊታገሉ የሚገባቸው ኦሮሞወች ናቸው::” የሚሉት ወገኖችየመገንጠል መብት ተግባራዊይሁን ቢባል የኦሮሞው መኖሪያ የት ሊሆን ይችላል? አሁን እየኖርንበት ያለውን መሬት ለመገንጠል የሞራልም ሆነ የታሪክ መነሻ ይኖራል ወይ ብሎማሰቡ አዋቂነት ነው::  አንዳንዴ የራስን ንግግር ደጋግሞ ከማድመጥ ወጥቶ ሌላው የሚለውንም መስማት ለግንዛቤም ሆነ ለውሳኔ ይረዳልሲሉይመክራሉ::

በእርግጥም አልፎ አልፎ ብልጭ ድርግም እያለ ያለ ስሜት ይሁን እንጅ አሁንም ቢሆን የመሬት ይገባኛል ጥያቄ መነሳቱ አልቀረም:: ክልሎች የየራሳቸውንትናንሽ መንግስት እንመስርት ቢሉ ግን እንደተባለውም ችግሩ እንዲህ በቀላሉ የሚፈታ አይመስልም::

በበርሊን ጉባኤ ላይ አፍሪካን በማስመሪያና በርሳስ ከካርታ ላይ እንደተከፋፈሉት ቅኝ ገዥወች ሁሉ ወያኔም ኦነግን ይዞ እንደፈለገው የከለለው ክልልከሁለቱ ቡድኖች በስተቀር በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው አይደለም:: እያንዳንዱ ክልል ታሪካዊ ይዞታየ ነው የሚለው አካባቢና ወሰኑ በየግለሰቦችዐዕምሮ ሳይቀር ተሰልቶ ቁጭ ብሎ አመች ጊዜ እየጠበቀ ነው::አፋር: ሶማሌ ቤንሻንጉል: ደቡብ: አማራ: ጋምቤላና ሀረሪ  ካለአግባብ በኦሮሚያተይዞብናል የሚሏቸው ሰፋፊ አካባቢወች አሏቸው:: እኒህ ብሄረሰቦች ደግሞ ከኦሮሞ ፍልሰት በፊት አሁን ኦሮሞው በሚኖርባቸው ስፍራወች ይኖሩየነበሩ ቀደምት ህዝቦች (indigenous people) ናቸው:: ኦሮሞው አሁን የያዘውን ክልል አስጠብቆ ሊኖር የሚችለው ወይ በአንዲት ኢትዮጵያ ጥላስር እስከቀጠለ ድረስ አለበለዚያም ከሌሎች ኦሮሞ ካልሆኑ ህዝቦች ጋር እየተዋጋ በጉልበት አምበርክኮ የበላይነቱን ለማስጠበቅ እስከቻለ ድረስ ብቻነው::

ሌሎች ብሄረሰቦችም ቢሆኑ የየራሳቸው ያልተፈታ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ያላቸው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ቀውስ ውስጥ መግባታቸው የማይቀር ይሆናል::በሆነ የታሪክ አጋጣሚ በራሳቸው ወይም በሌላ አካል ስር ተነጥለው ኖረው የማያውቁ ጎሳወች ይህ ነው የሚሉት የተከለለ የግዛት ክልል ስለማይኖራቸውበየአንዳንዷ ስንዝር መሬት ላይ ጭቅጭቅና ከዚያም የከፋ ነገር ሊገጥማቸው ይችላል:: ይህ ደግሞ ጎሳወች ሊወጡ የማይችሉበት የጦርነት አዙሪት ውስጥእንዲገቡ ያደርጋቸውና ከልማትና ከሰላም ይርቃሉ::

በመሰረቱ በአንድ ባንዲራና በአንድ ሀገር ስር ሲኖሩ ከነበሩ ብሄረሰቦች መሀከል አንዱ እራሴን ችየ ተገንጥየ መንግስት እመሰርታለሁ ቢል ሌሎችየሚቃወሙበት አግባብ መኖሩ የማይካድ ነው:: ለምሳሌ ያህል የሰሜኑን የሀገራችንን ክልል እንውሰድ:: እንደሚታወቀው የሰሜኑ የሀገራችን ክልልከደርቡሾች: ከጣሊያኖች: ከቱርኮችና ከግብጾች ጋር ተደጋጋሚና እልህ አስጨራሽ ጦርነቶች የተደረጉበት ክልል ነው:: በእነዚያ ጦርነቶች የተሳተፉትየአካባቢው ኗሪወች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው:: በተከፈለው ደምና አጥንት ዜጎቻችን ሳይፈናቀሉ በምድራቸው ላይ ባለቤት ሆነውእየኖሩ ነው:: የሁሉም ደምና አጥንት የፈሰሰበት መሬት የሰሜነኞች ብቻ ሳይሆን የሌሎችም  ነው::  እኒያ ከሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ተውጣጥተውሰሜን ድረስ ዘልቀው የተዋጉት ሀገር ወዳዶች ሰሜን ድረስ ዘምተው መስዋእትነት የከፈሉት ሀገራችን ነው በሚል እምነት ነው:: ታዲያ ያን ሀገሬ ነውብለው ለዘመናት ደምና አጥንት የገበሩበትን ሀገር ከጊዜ በኋላ ሰሜነኞች ገንጥለን እንወስዳለን ቢሉ ሌላው ህዝብ እንዴት እሽ ብሎ ይቀበላቸዋል? እዚያአካባቢ የሚገኝ በረከት ቢገኝስ ከበረከቱ አትቋደስም ሊለው የሚችለው ማን ነው? ችግርን እንጅ ጥቅምን አትጋራም ማለትስ እንዴት ይቻላል?

ብዙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የጎሰኞችን አፍራሽ ጉዞ እያወገዙ ጉዳቱንም እየገለጡ ለማስረዳት ጥረት ማድረጋቸውን አላቋረጡም:: ጎሰኞችምስለአንድነት ጥቅም የሚከራከረውን ሰው አማራ ከሆነ ነፍጠኛ አማራ ካልሆነ ደግሞ የዱሮ ስርአት ናፋቂ በማለት የያዙትን የጥፋት ጉዞ ሙጥኝ ብለዋል::አንድም የኢትዮጵያን ጠላቶች አላማ ለማስፈጸም ለሚፈጽሙት አፍራሽ ተልእኮ የሚፈስላቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ሌላም  ከመበታተን ሊከሰትየሚችለውን ማህበራዊ: ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ባለመረዳት ለሁላችንም ሊጠቅም የሚችለውን ስርአት ለመገንባት የሚደረገውን ትግል እጅግእየጎዱት ይገኛሉ:: እኒህ ከአካባቢያቸው አርቀው ማየት የተሳናቸው (short sighted) ጎጠኞች የህዝብን ትግል በመበተን የወያኔ እድሜ እንዲረዝምገንቢ ሚና ተጫውተዋል: እየተጫወቱም ነው::

የአንድነት ሀይሎችም ቢሆኑ የጎሳ ድርጅቶችን በማሳበጥ በኩል ቀላል የማይባል ድርሻ አበርክተዋል ማለት ይቻላል:: እንደሚታወቀው 1997 .በተደረገው ምርጫ የኦሮሚያን ክልል ጨምሮ በሁሉም ክልሎች  ያሸነፈው ቅንጅት ነበር:: ቅንጅት ደግሞ የጎሳ ድርጅት አልነበረም:: በሁሉም አካባቢቅንጅት ተመረጠ ማለት መላው ህዝባችን ከጎሳው በላይ ሀገሩን መረጠ ማለት ነበር:: ነገር ግን ይህን መገንዘብ የተሳናቸው የአንድነት ሀይሎች የጎሳድርጅቶችን ወደማባበል በማዘንበላቸው ህዝቡ ለጎሳው ቅድሚያ መስጠት ጀመረ:: ኦሮሞው የኦሮሞ ድርጅቶችን ትቶ ቅንጅትን ሲመርጥ ሌላውምእንዲሁ በስሙ የተደራጁትን ድርጅቶች ትቶ ቅንጅትን ሲመርጥ መልእክቱ ምን ማለት እንደነበረ ግልጽ ነው:: ጎሳውን እወክላለሁ ብለው ከተደራጁትበላይ ድምጽ ያገኙት የአንድነት ሀይሎች አብረን እንስራ በማለት ዝቅ ብለው የጎሳ ድርጅቶችን ማባበልና መለማመጥ ሲጀምሩ ያየ ሁሉ ያመነበትንአንድነት ትቶ ያላመነበትን ጎሰኝነት እንዲያሰላስል መንገዱን ከፈቱለት::  

ኦሮሚያ ላይ ለማሸነፍ የኦሮሞን ድርጅቶች መያዝ ያስፈልጋልየሚለው ቀና የመሰለ አባባል (ይህ አባባል የመነጨው ምናልባት ከራሳቸው ከጎሰኞችሊሆን ይችላል) ኢትዮጵያዊነት ካባ የተላበሰውን ህዝብለካስ ወኪሌ የጎሳየ ድርጅቴ ነውብሎ እንዲቀበል ግፊት አድርጎበታል:: ሕዝቡ ካለማወላወልየሰጠው ድምጽ ጎሰኝነትን አውግዞ ኢትዮጵያዊነትን ያነገሰበት ውሳኔ ነበር:: በዚህ ውሳኔ ወኪሌ ቅንጅት እንጅ የጎሳ ድርጅቶች አይደሉም የሚል  ቁርጥያለ መልስ የሰጠ ሲሆን ይህን እድል እያሰፉ መሄድ የሚቻልበትን አግባብ መከተል ሲገባ ህዝቡን ትተው ከጎሳ ድርጅቶች እግር ስር መንከባለልበመጀመራቸው አባሎቻቸውን ገፍትረው እነርሱም ክብራቸውን አረከሱ:: የሚገርመው ነገር አሁንም ቢሆን ሊማሩ አለመቻላቸው ነው:: የጎሳ ድርጅትአመራሮች የሚተዳደሩት  በርዳታና በመዋጮ ገንዘብ የሚዘወሩት ደግሞ በጸረ አንድነት (ጸረ ኢትዮጵያ) ሀይሎች መሆኑ እየታወቀ ዛሬም ቢሆን ከነዚህአፍራሽ ሀይሎች ጋር ለመተባበር ደፋ ቀና የሚሉ ህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች መኖራቸው እጅግ የሚያሳፍርም የሚያሳዝንም ነው::

የጎሳ ድርጅቶች ተቀባይነት አለን ብለው ሊሉ የሚችሉት በዚያው እንወክለዋለን በሚሉት ህዝብ ዘንድ ብቻ ነው:: ህብረብሄራዊ ድርጅቶች ግን በሁሉምአካባቢ ተከታይ አያጡም:: 1997 . ምርጫ በኦሮሚያ ክልል ቅንጅት ስንት ወንበር አሸነፈ የሚለውን ለአብነት ያህል መጥቀስ ያስፈልጋል::በወቅቱ ኦህኮን ያካተተው የተቃዋሚ ሀይሎች ህብረት 17% ሲያሸንፍ ቅንጅት ደግሞ 10% ሊያሸንፍ ችሏል:: የደቡብ ህዝቦችን ያካተተው የተቃዋሚሀይሎች ህብረት በደቡብ ክልል 13% ድምጽ ሲያገኝ ቅንጅት ግን ያገኘው 22% ነበር:: ቅንጅት በሁሉም ክልሎች ማሸነፍ ሲችል ከኢህአዴግ ተለጣፊድርጅቶች ውጪ ያሉት የጎሳ ድርጅቶች ግን ድምጽ ያገኙት በተወሰኑ ክልሎች ብቻ ነበር:: ቅንጅት ሌላው ቀርቶ የወያኔ ነጻ ቀጠና ተብሎ በሚታወቀውየትግራይ ክልል እንኳ 1.7% ድምጽ አግኝቷል (ለማስረጃ ይህን ይጫኑ):: ኢህአዴግ ቅንጅትን በተለያየ መንገድ ወንጅሎ በድጋሚ ምርጫው የነጠቀውንመቀመጫ እንኳ ብንቀንስ  በጠቅላላ ያገኘው መቀመጫ 109 ሲሆን (ይህ ውጤት ኢህአዴግ በጉልበት የቀማውን የመቀመጫ ቁጥር አይጨምርም)ተቃዋሚ የብሄር ድርጅቶችን ያሰባሰበው የተቃዋሚ ሀይሎች ህብረት ያገኘው 52 መቀመጫ ነበር::

ይህ መረጃ የሚያሳየን ለኢትዮጵያዊነት ቅድሚያ የሚሰጡ ኢትዮጵያውያን በሁሉም ክልሎች እንዳሉ ነው:: በኢትዮጵያ ትልቁን ጎሳ ይወክላሉ የተባሉትድርጅቶች ያውም ከሌሎች ጋር ተጣምረው ያገኙት የፓርላማ ወንበር ከቅንጅት ጋር ሲነጻጸር ከግማሽም ያነሰ ነበር::

ኢትዮጵያዊነት ከቋንቋ በላይ ነው:: ኢትዮጵያዊነት በደምና በአጥንት የተገነባ ማንነት ነው:: ኢትዮጵያዊነት የሰፈር ደላሎች ሊያጠፉት ወይም ሊቀይሩትየማይቻላቸው የነፍስ ውሁድ ነው::

የአንድነት ሀይሎች መጀመሪያ ራሳችሁ ይህን እውነታ አምናችሁ መቀበል ይኖርባችኋል:: ከዚያም ለጎሳ ድርጅቶች እውቅና ሰጥታችሁ የገፋችሁትንኢትዮጵያዊ ለማስመለስ መስራት ይገባችኋል:: የጎሳ ድርጅቶች ከወያኔ ጋር ያላቸው ልዩነት የስልጣንና የጥቅም እንጅ የአላማና የግብ አይደለም::በመሀላችሁ ያለው ልዩነት በጊዜ ሂደት በህዝብ እንዲዳኝ በይደር ትታችሁ አሁን ሀገርን በማዳን ተግባር ላይ በጋራ ጸንታችሁ ልትቆሙ ግድ ይላል::እናንተ በአንድነት በጽናት ከቆማችሁ መላው ኢትዮጵያዊ ከጎናችሁ ይሰለፋል:: ጎሰኝነትን የምትፈረካክሱት እናንተ ጠንክራችሁ መውጣት ስትችሉ ብቻነው:: የአንድነት ሀይሉ አቅም መጠንከር የሰፈርተኞችን ጉልበት ያደክማል::

ኢትዮጵያዊነት ያብባል!

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

ህወሓት ለምን ኢትዮጵያን ወደብ-አልባ ማድረግ መረጠ? | ከታምሩ ለታ

የኢትዮጵያን ያህል ሕዝብ ብዛት ይዞና የኢትዮጵያን ያህል ለባህር ቀርቦ ወደብ-አልባ ሀገር በአለማችን የለም::ብዙ ወደብ-አልባ ሀገሮች ለወደብ-አልባነት የበቁት ከባህር አጅግ ርቀው በመኘታቸው ነዉ:: እንደምሳሌ ያህል ቻድ፣ ድቡብ ሱዳን እና ዩጋንዳ ከአፍሪካ; ፓራጉዋይ ከላቲን አሜሪካ; ሞንጎሊያ ከእስያ መጥቅሰ ይቻላል:: እኚህ ሀገሮች ከባህር በጣሙኑ ርቀዉ ነዉ የሚገኙት::  ስለዚህ ለኚህ ሀገሮች ወደብ-አልባነት ተፈጥሮ የጫነችባቸዉ መልክአምድራው አጣፈንታ ነዉ። በአንጻሩ ኢትዮጵያን የተመለከትን እንደሆነ ለቀይ ባህር በጅጉ የቀረበች ሀገር ናት። የአሰብ ውደብ ከኢትዮጵያ ድንበር ያለዉ ርቀት አዲስ አበባ ክብሾፍቱ (ደብረዘይት) ካላት ርቀት ጋር ተመጣጣኝ ነዉ። ይህን ያህል ለባህር ቀርቦ  ወደብ-አልባ የሆነ ሀገር በአለማችን የለም። ይልቁንም እንደ ኮንጎ ያሉ ከባህር የራቁ ሀገሮች ድንበር ስንመለከት ወደባህር የሚያሳልፍ ኮሪደር  ባለቤት ሆነዉ አናገኛቸዋለን። የህወሓት ዉሳኔ ኢትዮጵያን ለባህር በጅጉ ቀርባ ወደብ አልባ የሆነች ብቸኛዋ ሀገር አርጉዋታል።:

Asab Port
ወደብ-አልባ ሀገር መሆን ያመጣበንን ጣጣ በበዙዉ አይተናል። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ብዙ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ንብረታችዉን ወደብ ላይ ተወርሰዋል። ጅቡቲ ደርሳ ባታስጥለን ኖሮ የዓለም-ንግድ አንገታችን ተቆርጦ ነበር። ከዓለም ንግድ መቆረጥ እንደምታዉ ቀላል አይደለም። በድርቅ ሳቢያ የተራቡ ወአኖቻችንን ሕይወት ለማዳን እንኩዋን ስንዴዉ ከዉጪ መምጣት አለበት። ለዘወትር ፍጆታችን የምንጠቀምባቸዉ መሰረታዊ ነገሮችም (መድሃኒትና ነዳጅን ጨምሮ ) ዙዎቹ ከዉጭ መምጣት አለባቸው። ከጅቡትም የደረሰልን የነብስ-አድን አስተዋጽኦ በነጻ የተገኘ አይደለም — ሕዝብ እጅግ ደክሞ ያፈራዉን ሃበቱንና ሉዓላዊነቱን ገብሮበታል። ለወደብ ኪራይ የሚከፈለው ገንዘብ ማንንም ወገን የሚያስደነግጥ ነዉ። በየአመቱ ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ የምትፈጽመዉ ክፍያ ከመንግስት ኦፊሲዬላዊ ምንጮች ለማወቅ ባይቻልም  (ሆን ተብሎ በድብቅ የተያዝ ይመስላል) ቢያንስ አንድ ቢሊየን ዶላር እንደሚሆን ይገመታል። ይህ የገንዘብ መጠን ቁጥር አንድ የሆነዉ የኤክስፖርት ምርታችን ቡና ከሚያስገኘው ገቢ ይበልጣል። መላዉ የኢትዮጵያ ቡና አምራች ገበሬ ለፍቶ አምርቶ፤ ነጋዴዉ ደክሞ ሰብስቦ ለሃገሩ ያስግኘዉ ሃብት ሙሉ በሙሉ ለወደብ ክፍያ ይዉላል!! ያም ስለማይበቃ ተጨማሪ ገንዘብ ያስፈልጋል። ከዚያም አልፎ-ተርፎ ኢትዮጵያን ብሄራዊ ክብራችንን እና ሞራላችንን በሚነካ ደረጃ የጅቡቲ አጎብዳጅ እንድትሆን አስገድዷታል።

የህወሃት ሰዎች የሰጡን መልስ “ለኢትዮጵያ ብልጽግና ወደብ ያለዉ ፋይዳ እምብዛም አይደለም” የሚል ነው። ኤርትራ ስትገነጠል ኢትዮጵያ የወደብ-ይገባኛል ጥያቄ ብታስነሳ በሁለቱ ሃገሮች መሃል ግጭት ሊቀሰቅስና አላስፈላጊ ጦርነት ሊያስነሳ ይችላል። ወደብ ብዙም ፋይዳ ከሌለዉ ደግሞ ከኤርትራ ጋር የድንበር እሰጣገባ ዉስጥ መግባት ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል የሚል ነው።

“ለኢትዮጵያ ብልጽግና ወደብ ያለዉ ፋይዳ እምብዛም አይደለም” የሚለዉ መከራከሪያ የህወሃት/ኢህአዴግ ሰዎች ሽንጣቸዉን ገትረዉ የተክራከሩበት ነዉ። ይህ መከራከሪያ ዉሃ የማያነሳ መሆኑን ለማሳያ ከላይ የጠቅስኩዋቸዉ የወደብ-አልባነታችን መዘዞች ብቻ በቂ ናቸዉ። ወደብ-አልባነት አንድን ሃገር ክፉኛ እንደሚጎዳ እንኩዋንስ ሃገር መራለሁ ብሎ የተደራጀ ቡድን ይቅርና ማንም ተራ ዜጋ የሚገነዘበው ጉዳይ ነዉ። ኢኮኖሚስቶችም ለበርካታ አመታት ባደረጉዋቸዉ ጥናቶች ወደብ-አልባነት የሃገሮችን የብልጽግና እድል እንደሚያቀጭጭ በማያሻማ ሁኔታ የተደመደመበት ጉዳይ ነዉ። ኢትዮጵያ ወደብ-አልባ እንዳትሆን በግዜዉ በርካቶ ምሁራን ጩሀታቸዉን ለህወሃት/ኢሃዴግ አሰምተዋል። የተሰጣቸዉ ምላሽም ከስራ መባረርና ከሃገር መሰደድ ነበር (ከስራ የተባረሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችን ያስታዉሷል)።

ስለዚህም ህወሃት/ኢሃዴግ ኢትዮጵያን ወደብ-አልባ ያደረገዉ የወደብን ጥቅም ሳይገነዘብ ቀርቶ ነዉ ለማለት ያስቸግራል።ነገሩ በቀጥታ የማይመለከታቸዉ የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር እንኩዋን መለስ ዜናዊን ኢትዮጵያን ወደብ-አልባ ከማድረግ እንዲታቀብ አደራ-መሰል ማሳሰቢያ ሰጥትዉት ነብር። ኢትዮጵያን ወደብ-አልባ ማድረግ የሩቁን ጂሚ ካርተርን የቆረቆራቸዉን ያህል መለስን አልቆረቆረዉም።  ስለወደብ አስፈላጊነት የተናገሩ ምሁራንን ማሰሩንና ማሳደዱን ለተመለከተ፤ ህወሃት/ኢሃዴግ በርገጥም ኢትዮጵያን ወደብ-አልባ አድርጎ የማስቀርት ጽኑ ፍላጎት እንደነበርዉ ያሳያል። ህወሃት የረጅም ግዜ ግቡን በጥንቃቄ የሚተልም ድርጅት ነዉ። በክፋቱ፤ በጭካኔዉ፤ በአምባ-ገነንነቱ ሊኮነን ይችላል። የሚፈልገዉን ባለማወቅ ግን አይታማም። ግቡን ለመምታትም ምንም ከማድረግ ወደ-ሁዋላ አይልም። መታሰር ያለበት ይታሰራል፤ መደብደብ ያለበት ይደበደባል፤ መገደል ያለበትም ይገደላል።

ህወሃት ለዚህ ዉሳኔ እንዲበቃ (ማለትም ኢትዮጵያን ወደብ-አልባ ለማድረግ) ያነሳሳዉ ምክንያት ምንድነዉ? በዚህ ጽሁፌ ለማሳየት የምሞክረዉ የህወሃት (ኢትዮጵያን ወደብ-አልባ ያደረገበት) ዉሳኔ ከሚከተሉት ሁለት መሰረታዊ የህወሃት ግቦች የሚመነጭ እንደሆን ነው።

1ኛ፡ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደ አንድ ጠንካራ ሀገር ለረጅም ግዜ የመግዛት ራእይ የለዉም። እስከተቻለዉ ድረስ የኢትዮጵያን ህዝብ ከፋፍሎና አንድነቱን አዳክሞ ይገዛል።
2ኛ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሃትን በቃኝ ባለ ግዜ የህወሃት ገዢዎች ትግራይን ተቆጣጥረዉና ከኢትዮጵያ በሃይል ገንጥለዉ ገዢነታቸዉን በትግራይ ክልል ይቀጥላሉ።

ህወሃት ከላይ የጠቅስኩዋቸዉን ሁለት የረጅም ግዜ ግቦች ይዞ እንደሚንቀሳቀስ ብዙም የሚያከራክር አይመስለኝም። ህወሃት ከጅምሩም ቢሆን ጫካ ሲገባ የትግራይን መንግስት መመስረት አላማዉ እንደነበር በመመስረቻ ሰነዳቸዉ ሳይቀር ያስቀመጡት ጉዳይ ነዉ። የማታ ማታ የደርግን መዉደቅ ተከትሎ አቅም አገኙና ኢትዮጵያን ለግዜዉም ቢሆን መቦጥቦጥ እንደሚችሉ ሲረዱ ተለጣፊ ፓርቲዎችን አቋቁመዉ መላዉ ኢትዮጵያን በከፋፍለህ-ግዛ ስትራቴጂ ተቆጣጠሩ። ስለዚህም ኢትዮጵያን መግዛት ከጅምሩ የወጡነት አላማ ሳይሆን ይኋላ-ኋላ አጋጣሚ የፈጠረላቸዉ ችሮታ ነዉ። በዘላቂነት እንደማያስኬዳቸዉም ክማንም በላይ ያውቁታል።

የኢትዮጵያ ህዝብ የህወሃትን አገዛዝ በቃኝ የሚልበት ግዜ እንደሚመጣ ህወሃት ጠንቅቆ ይገነዘባል። ለዚያ ግዜ ያስቀመጠው ካርዱ ደግሞ ኢትዮጵያን መበታተን እና ትግራይን ገንጥሎ መግዛት ነው። ይህን አካሄዳቸዉን በምርጫ 97 ማግስት የህወሃት ስልጣን ሲንገዳገድ አቶ መለስ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል። ስብሃት ነጋም ቪኦኤ ላይ ቀርቦ ህገ-መንግስቱ ከተናድ (ማለትም ህወሃት ኢትዮጵያን ካልገዛ) እንደምንገነጣጠል ደግሞ ደጋግሞ አስጠንቅቆናል።

እናም ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት መሆኑዋ ከላይ ከጠቅስኩዋቸዉ ሁለቱ የህወሃት ግቦች ጋር በጅጉ ይጻረራል። ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ከሆነች የህዝቦችዋ የአንድነት ፍላጎት ይጠናከራል። ምክንያቱም ከኢትዮጵያ እገነጠላለሁ የሚል ክልል (አፋር ሲቀር)  ወደብ-አልባ ሆኖ ነዉ የሚቀረዉ። ወደብ ለመጠቀምም “አልፈልግሽም” ብሎ በተገነጠላት ኢትዮጵያ ላይ ጥገኛ ይሆናል። የትኛዉም ክልል  ይህን እያወቀ የመገንጠል ፍላጎት ይኖረዋል ለማለት ይከብዳል። በመሆኑም ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ብትሆን ኖሮ የህዝቦችዋ የአንድነት ፍላጎት ይበልጡኑ ይጠናከራል። ይህ ደግሞ ከላይ ከጠቀስኩዋቸዉ ሁለቱ የህወሃት ግቦች ጋር በጅጉ የሚጻረር ነው። አንደኛ ህወሃት የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት አዳክሞና ከፋፍሎ ለመግዛት ይበልጥ ያስቸግረዋል። ሁለተኛ፤ ወደቡ በኢትዮጵያ እጅ መሆኑ ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠል የረጅም ግዜ ግቡን አስቸጋሪ ያደርግበታል። የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ ዳግመኛ ለወደብ አገልግሎት ኢትዮጵያ ላይ ጥገኛ እንደሚሆን ሲገነዘብ በህወሃት የመገንጠል አጀንዳ ላይ ያለዉ ተቃዉሞ ይበረታል። አንድነቱ የተጠናክረዉ ሌላዉ የኢትዮጵያ ህዝብም የህወሃትን አጀንዳ ለማደናቀፍ (ሃይል መጠቅምን ጨምሮ) የተሻለ አቅም ይኖረዋል። ህወሃት ይህን ተቃዉሞ አልፎ እንኩዋን ትግራይን ቢገነጥል፤ ከኢትዮጵያ ጋር በጠላትነት የሚለያይ ሆኖ ሳለ ለወደብ አገልግሎት ግን ኢትዮጵያ ላይ ጥገኛ ይሆናል። ስለዚህም ወደቡ ወደፊት በሚገነጠላትና የለየላት ባላንጣዉ በምትሆነዉ፤ እንዲሁም አንድነቱዋ በጠነከረዉ ኢትዮጵያ እጅ መሆኑ ለህወሃት ማራኪ አማራጭ አልነበርም።  ይልቁንም ወደቡ ያኔ ወዳጁ በነበረዉና (ወደፊትም ጸበኛዬ ይሆናል ብሎ ባልጠበቀው) ሻቢያ እጅ እንዲቀመጥ መረጠ። ያ የክፉ ቀን መጥቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢነሳ፤ አንድነቱዋ የተዳከመዉና ወደብ-አልባዋ ኢትዮጵያ ትተራመሳልች፤ ትበታተናለች። ህወሃት አጋዚ ጦሩን ይዞ ትግራይን ይቆጣጠራል። የትግራይ ህዝብም የኢትዮጵያን ትርምስ ከመቀላቀል የህወሃት ጭሰኛ ሆኖና ቢያንስ የተረጋጋ የመንግስት ባለቤት ሆኖ ይቀጥላል። ህወሃትም የረጅም ግዜ  ወዳጄ ነዉ ብሎ ባሰበዉ ሻቢያ እጅ ያለን ወደብ ቢያንስ ተክራይቶ መጠቀም ይችላል። ወደቡ በጠላትነት በተለያት ኢትዮጵያ እጅ ቢሆን የመከራየትም እድል አይኖረዉም።

እናም በዚህ ክፉ የህወሃት ሴራ 100 ሚሊዮን ህዝብ ለፍቶ ጥሮ ያፈራዉን ሀብት ለጅቡቲ ይገብራል። ለመላው አፍሪካና ጥቁር ህዝብ የነጻነት አርማ የሆነች ሃገር ወድብ ፍለጋ ምናልባትም ከአንድ ወረዳ ለማይበልጡ እንደ ጅቡቲና ሱማሌ-ላንድን ለመሳሰሉ ትንንሽ ሀገሮች ታጎበድዳልች። እንዲህ የሀገራችንን ጥቅም ባደባባይ የሚሸጥ ቡድን ቀጥቀጦ ሲገዛን ማየት ማንንም ኢትዮጵያዊ በቁጭት ማንገብገቡ አይቀርም። ያለዉም አማራጭ ሁለት በቻ ነዉ — ህወሃት በቀደደልን ቦይ ቁልቁል መንገዋለል ወይም የስልጣን ኮርቻዉን በሀይል ነጥቆ ፈረሱን በምንፈልገዉ አቅጣጫ መጋለብ።

ትውልድ የሚሻገር መፍትሔ: እንዴት? – ሰቦቃ ዋቅቶላ

የዚህ ፅሁፍ ፀሐፊ የየትኛውም የ ፖለቲካ ድርጅት አባል አይደለም:: ሃሳቡም የግሉ ነው::

imagesየ ዛሬዋ ኢትዮጵያ የህዝቦችዋን የፖለቲካ ጥያቄን ፈትቻለሁ ብላ ብትፎክርም: ያው የተለመደ መፈክር ብቻ ከመሆን የዘለለ አይደለም:: ተደጋግሞ አንደሚባለው አሁን ያለው ህገ መንግስት አናሳ በሆነው ነገር ግን በታሪክ አጋጣሚ የመሳሪያ የበላይነት ያገኘው ወገን የፖለቲካ ፍላጎቴን ያስጠብቅልኛል በሚል ያረቀቀው: የመሳሪያ የበላይነቱን ተጠቅሞ ያስፀደቀው ነው:: ህገ መንግስቱ የፈታው የፖለቲካ ጥያቄ ቢኖር: የመሳሪያ የበላይነት ያገኘውን የትግራይ ብሔር ጥያቄ ብቻ ነው:: የ አንድ ብሄር  የፖለቲካ ቡድን: ከሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች ጋር ትርጉም ያለው ወይይት አና ድርድር ሳያደርግ: እንዲያውም ተቃዋሚዎቹን አጥፍቶ ለመጨረስ በዘመቻ ላይ ሆኖ:  ያቀረበው ‘እኔ አውቅልህ’ መፍትሄ: የኢትዮጵያን የብሔር ጥያቄ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት የነበረውን ዕድል ገደል የከተተ: ለአንድ ወይም ለብዙ መቶ አመታት ሊቆይ የሚችል ህገ መንግስት የመቅረጽ ዕድል ያጨናገፈ ነው::

ትውልዶችን ሊሻገር የሚችል መፍትሄ ማቅረብ : የህዝቦችን የፖለቲካ ፍላጎቶች  ማወቅ ይጠይቃል:: የህዝቦች የፖለቲካ ፍላጎት ለማወቅ ደግሞ ዲሞክራሲ ቅድመ ሁኔታ ነው:: ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ዕድል አግኝተው  የፖለቲካ ፍላጎታቸውን በቀጥታም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲ በመምረጥ ወይም በሌላ መንገድ ሊወስኑ ይችላሉ: በዚህን ጊዜ የአንድ ህዝብ የፖለቲካ ፍላጎት ታውቆል ማለት ይቻላል:: ‘እኔ አውቅልህ’ የፖለቲካ አራማጆች ቅድመ ሁኔታ የሆነውን የህዝብን በ ነጻ የመደራጀት: የመሰብሰብ: ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ የመሳሰሉትን ዲሞክራሲያዊ መብቶች አፍነው የህዝቦችን የፖለቲካ ፍላጎቶች ራሳቸው ይወስናሉ::

ትውልዶችን ሊሻገር የሚችል መፍትሄ ማቅረብ : ለሕዝቦች የፖለቲካ ፍላጎቶች ምላሽ መስጠት ይጠይቃል:: ለሕዝብ የ ፖለቲካ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት መሰረቱ የህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ እንጂ የመሳሪያ የበላይነት የያዘው ቡድን ፈቃድ አይደለም:: በመሳሪያ የበላይነት ስልጣን የያዙ የፖለቲካ ቡድኖች በእኔ አውቅልህ የህዝቦችን የፖለቲካ ፍላጎቶች እንደሚወስኑ ሁሉ ለሕዝቦች የፖለቲካ ፍላጎቶች ምላሽ የሚሰጡት ራሳቸው  በፈቀዱት ልክ ብቻ ነው::

ህወሀት/ ኢህአዲግ ያቀረበው መፍትሄ የህወሐትን የበላይነት ለዘለቄታው የሚያስጠብቅ ነው:: የዚህ ፅሁፍ አላማ መፍትሄዎቹን በዝርዝር የመቃኘት አይደለም:: ብዙዎችም ብዙ አንደፃፉ አገምታለሁ: ነገር ግን በጥቂቱ ላንሳው::  የ ህወሐት ታጋዮች የ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አሾሾም ና ስልጣን እንዲሁም : የፕሬዚደንቱን አሾሾምና ስልጣን ሲወስኑ: የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ከ ህወሐት ቁጥጥር አንዳይወጣ አድርገው ነው:: ኢህአድግ ያለ ህወሀት ስውር ሆነ ግልፅ መሪነት ህልውና አይኖረውም:: የኢሕአድግ መሪ  ደግሞ ሁልጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆናል:; ታጋዮቹ የክልልና የፌደራል ግኑኝነቶችንና የሀብት ክፍፍል ሲወስኑ የክልሎች ጠቃሚ ሀብቶች በሙሉ በ ፌዴራልና በሕህወሐት ስር አንዲሆኑ በማድረግ ነው:: ከዚህም በተጨማሪ ታዋቂውን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት በሕገ  መንግስቱ ሲያካትቱ “እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው” እንዲሉ ነው:: የፍንፍኔ/ አዲስ አበባ የፖለቲካ ስልጣን መነፈግ የህወሀት ታጋዮችን የፖለቲካ ፍላጎት የማሳካት አላማ ያለው እንጂ አንዳዶች እንደሚያስቡት የ ኦሮሞ ን ህዝብ ፍላጎት ለመጠበቅ አይመስለኝም::

ከዚህ ብዙ ልንማር ይገባናል:: ከአንድ ትውልድ የማይሻገር ህገ መንግስት ከእንግዲህ ሊኖረን አይገባም:: ከ እኔ አውቅልህ ፖለቲካ መላቀቅ ይኖርብናል:: የፖለቲካ ድርጅቶች ሊታገሉለት የሚገባ ነገር ቢኖር  የህዝቦች መሰረታዊ  መብቶች እንዲከበሩ ነው:: ህዝቦች የሚፈልጉትን እንደሚያውቁ ከልብ መቀበል ያስፈልጋል::

አንዳንድ ጊዜ በመንግስት ሚዲያ ላይ ተቃዋሚዎች ሲከራከሩ እሰማለሁ:: ዋናው ጉዳይ ሁልጊዜ ይድበሰበሳል:: እንደኔ አመለካከት ዋናው የ ፖለቲካ ጉዳይ አሁንም የብሔር ጥያቄ ነው:: የክልሎች አና የ ፌደራል ግኑኝነት ጥያቄ ነው:: ይህ ጥያቄ ሰፊ ነው:: የ ኦሮሞ ህዝብ አና የ ፖለቲካ ድርጅቶች ለረጅም ጊዜ ሲያነሱትና ሲታገሉለት የቆዩትን ጥያቄ የያዘ ነው:: ይህ ጥያቄ በኦሮምያ ክልል ውስጥ ያሉትን ከኦሮሞ ዉጭ ያሉ ህዝቦችን ይመለከታል:: ይህ ጥያቄ በፍንፍኔ/አዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩትን የተለያዩ ህዝቦችን ይመለከታል:: የ ኦሮሞ ህዝብ በፌደራል መንግስት ላይ የሚያነሳው የ ይገባኛል ጥያቄ የአማራና የሶማሌ የትግራይ እንዲሁም የሁሉንም ሌሎች ህዝቦችን ይመለከታል:: ይህ ጥያቄ ከ ኦሮሞ ዉጭ ያሉ ሌሎች ህዝቦች ከፌዴራል መንግስት ጋር ባላቸው ግንኙነት የሚያነሱትንና  የሚታገሉለትን  የስልጣን ክፍፍል ጥያቄዎች የያዘ ነው::

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ አይዶሎጅን መሰረት አድርገው የሚደራጁ መኖራቸው ይታወቃል:: ዋነኞቹ ሊበራል ዲሞክራሲን እንከተላለን ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ ሶሻል ዲሞክራሲን እንከተላለን ይላሉ:: ህወሀት/ ኢህአድግ ደግሞ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ነኝ ይላል/ አንዳንዴም ነጭ ካፒታሊስት/ ነኝ ይላል::  እነዚህ የፖለቲካ ቡድኖች በላይኛው ፓራግራፍ በተመለከተው ጥያቄ ግልፅ ልዩነት አላቸው:: ከ አድዮሎጂ ልዩነት ይልቅ ዋናው ልዩነታቸው አሱ ይመሰለኛል:: በክልልና በፌደራል ግኑኝነት ላይ ያላቸውን ፕሮግራም በቅጡ ሳይፈተሽ ወደ ፖለቲካ ሰልጣን ቢመጡ የራሳቸውን ዲዛይን በህዝቦች ፍላጎቶች ላይ አንደማይጭኑ ምንም ዋስትና የለም::

የፖለቲካ ድርጅቶች በክልልና የፌደራል ግኑኝነት ላይ ግልፅ የሆነ ፕሮግራም ሊኖራቸው ይገባል:: እንደ አኔ አመለካከት  የክልሎችና የፌደራል ግኑኝነት በዲሞክራሲያዊ መንገድ በሕዝብ ይወሰናል የሚሉትም ወገኖች ሆኑ: ግልፅ አቆም የያዙት ወገኖች የሕዝብን መደናገር በመቀነስ በኩል ምስጋና የሚገባቸው ናቸው:: በ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ይወሰናል የሚሉት በዲሞክራሲያዊ ባህል አመኔታን  መገንባት አለባቸው::

የፌደራልና የክልል ግኑኝነት ጥያቄ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ቁልፍ ጥያቄ ነው:: የፌደራል አና የክልል ግኑኝነት ምንም ማሻሻያ አያስፈልገውም  በሚለው በ ህወሀት ኢህአድግ ዘንድ: ጥያቄውን ማንሳት የሕገ መንግስቱን የበላይነት አለመቀበል ነው:: የፌደራል አና የክልል ግኑኝነት ጥያቄ በሌሎች  ወገኖች ደግሞ የ ኢትዮጵያን አንድነት አንደማዳከም ይወሰዳል:: የፌደራልና የክልል ጥያቄ የብሔር ጥያቄን በሚያነሱ ህዝቦች የህልውናቸው መሰረት: ጭቆናን የሚከላከሉበት: እኩልነታቸውን የሚያረጋግጡበት: ከሌሎች ህዝቦች ጋር የማይጋሩትን የራሳቸው የሆነውን ታሪካቸውን የሚያስተምሩበት:ባሕላቸውን የሚያሳድጉበት ዋስትና ሆኖ ይቀርባል::

የህወሀት ኢህአድግ የብሔር ጥያቄን በዋነኛነት ሲያቀንቅን አንዳልነበረ ሁሉ በአሁኑ ጊዜ የብሔር ጥያቄን የሚያነሱ ወገኖችን ሁሉ በዘረኝነትና በሽብርተኛነት በመክሰስ ላይ ነው:: ይኽም የሕገ መንግስቱ አላማ የ ኤርትራ ከ ኢትዮጵያ መገንጠል ሽፋን ለመስጠትና የትግራይን ህዝብ የብሔር ጥያቄ የመመለስ ውስን አላማ ብቻ አንዳለው ያረግግጣል:: የብሔር ጥያቄ የኢትዮጵያን አንድነት ያዳክማል የሚሉ ወገኖች “ኢትዮጵያ” ሲሉ ሚዛናውነት ሲለቁ ይታያል:: የራሳቸው ብሔር ታሪክና ባህል: ከኢትዮጵያ ታሪክና ባህል ለይተው ማየት ይሳናቸዋል :: የነሱ ብሔር ታሪክና ባህል  ከሌሎች ብሔሮች  ባህልና ታሪክ እኩል ሲሆን ሊደሰቱ እንጂ ሊከፉ አይገባም ነበር:: የኢትዮጵያ ብሔሮች ጥሩም ሆነ መጥፎ: የጋራ ታሪክ አላቸው:: የጋራና የግል ታሪካቸው ላይ መግባባት ይኖርባቸዋል:: የጋራ ታሪኩም ብቻ የኢትዮጵያ ታርክ ተብሎ ሊገለፅ ይገባል::

ሁሉም የፖለቲካ ሀይሎች: የሀወሀት/ ኢህአዴግ የፖለቲካ ሀይል: የአማራ ብሔር: የኦሮሞና የሌሎች የብሔሮች የፖለቲካ ሀይሎች ለሰላማዊውም ሆነ ውጤታማ የሆነ የፖለቲካ ሰልጣን ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ እዱሉ አላቸው::

የህወሀት ኢህአድግ የፖለቲካ ሀይሎች ፀሐይ አየጠለቀች መሆኑን መቀበል አለባቸው:: የህወሀት ኢህአዲግ የፖለቲካ ስልጣን ለጅትማሲ የነበረው የብሔር በሄረሰቦች መብት መከበር ጥያቄ የኦሮሞ ተቃውሞን: የጋምቤላን: የወልቃይትን: በደቡብ ኢትዮጵያ የተነሱ ተገቢ ጥያቄዎችን: በሀይል ለመመለስ ሀወሀት/ ኢህአድግ በወሰደው እርምጃ እርቃኑን ቀርቶል:: የህወሀት ኢህአዲግ ለራሱ ልማታዊ መንግስት የሚል ለጅትማሲ ለመፍጠር ቢሞክርም: ይኽ ምክንያት የውጭ መንግስታትን ከሚያማልል በስተቀር በሀገር ውስጥ ከጅምሩም ተቀባይነት ያገኘ አይደለም::

የህወሀት ኢህአዴግ የፖለቲካ ሀይሎች በሰላማዊ መንገድ የሰልጣን ሽግግር አንዲያደርጉ የታሪክ ሀላፊነት አለባቸው:: ይኽንን በሁለት አይነት መንገድ ማድረግ ይችላሉ:: የመጀመሪያው መንገድ በሀገሪቱ በጠቅላላ ነፃ አና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲደረግ ማድረግ ነው::  ይኽም በአንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ በሀገር ውስጥ አንዳይንቀሳቀሱ የወጡ አዋጆችን መሰረዝና: ለነዚህ የፖለቲካ ሀይሎች በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ዋስትና መስጠትን ይጠይቃል:: የምርጫውን ውድድር የሚመራው አካል በተወዳዳሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነትን ያገኘና ዋስትና ያለው መሆን ይኖርበታል:: ምርጫው በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የሚመራ ሆኖ ቢቻል የተባበሩት መንግሥታት በዋነኛት የታዛቢዎችን ቡድን አንዲመራ መደረግ አለበት:: ሀወሐት ኢህአድግ በፓርላማ አብላጫ ድምፅ ላገኘው የ ፖለቲካ ድርጅት ስልጣኑን በማሸጋገር ታሪክ መሰራት ይችላል:: በምርጫው ሂደት በአሁኑ ወቅት ያለው የፖሊስ ሰራዊትና የመከላከያ ሰራዊት ሚና የህገር ውስጥ ሰላምና የውጭ ጥቃትን በመከላከል መወሰን አለበት::

የህወሀት ኢህአድግ የፖለቲካ ኃይሎች ሌላ ሊያደርጉት የሚችሉት አሁንም  በአንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ በሀገር ውስጥ የመንቀሳቀስ ገደብ የሚጥሉትን አዋጆችና ዉሳኔዎች በመሻር: ከሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በመወያየትና በመደራደር ትውልድ የሚሻገር መፍተሄ መፈለግ ነው::

የህወሀት ኢህአድግ የፖለቲካ ቡድን የአንድን ብሔር ጥያቄ ከመመለስ ውጭ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ትርጉም ያለው የፖለቲካ መፍትሄ ያለመጣ ቢሆንም: ከሌሎች ብሔሮች ቀላል የማይባል የፖለቲካ ሀይል አሰልፎል:: ይኽ አሰላለፍ ግን ዘላቂነት የሌለውና  በሌላ አማራጭ ማጣት የተፈጠረ አሰላለፍ በመሆኑ  በማናቸውም ጊዜ ሊፈርስ አንደሚችል ሁለት ታላላቅ የፖለቲካ ክስተቶች አመላክተዋል:: የመጀመሪያው የ ፩፱፱፯ ምርጫ ሲሆን ሌላው ደግሞ በአሁኑ ወቅት በመካሄድ ላይ ያለው የኦሮሞ  ተቃውሞ ነው::

ሀወሀት ኢህአድግ በእድሉ ሳይጠቀም ከቀረ ሌሎቹ የፖለቲካ ሀይሎች ትውልድን የሚሻገር መፍትሄ  ለማምጣት መተባበር አለባቸው:: ህወሀት ኢህአድግ ማዕቀብ የጣለባቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች ማዕቀብ ያንሳ ስንል በተመሳሳይ ለሌሎቹም የፖለቲካ ድርጅቶች መስራት አለበት:: የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ከትብብር ውጭ መሆን የለበትም:: በመካከላቸው አስፈላጊ ያልሆነ  ግጭት ሊያመጡ ከሚችሉ ድርጊቶች መቆጠብ አለባቸው:: የትኛውንም የ ፖለቲካ ፕሮግራም ቢያራምዱ: በትብብሩ ሂደት ገና የህዝብ አዎንታ የሚፈልግ ፕሮግራም አንደያዙ አንጂ: በሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ዉሳኔ አዎንታ ያገኘ የፖለቲካ ፕሮግራም አንደያዙ መቁጠር የለባቸውም::  በአሁኑ ውቅት ባገኙት ድጋፍ አና አቅም ተኩራርተው ከትብብር ዉጭ መሆንም  የለባቸውም::

የአማራ የፖለቲካ ሀይሎች መሰረቱ የቀድሞ የፖለቲካ ስልጣን ነው:: ይኽ የፖለቲካ ሀይል በአብዛኛው ቀደም ስል በነበሩ ስርዓቶች ከ አማራው ተራማጅ አስተሳሰቦችን ሲያራምድ የነበረው ክፍል የፖለቲካ አስተሳሰብን የወረሰ ነው:: የዚህ የፖለቲካ ሀይል ደጋፊዎች ከብሄር ጭቆና ዉጭ ስለነበሩ ከሌሎች የፖለቲካ ሀይሎች በተሻለ ያለፉ ስርዓቶች የፈጠሩት የኢኮኖሚና የባህል የታሪክ የበላይነት የነሱ ነበሩ: ህወሀት ኢህአድግ የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ ሆነ የኢኮኖሚ የባህልና የታሪክ የበላይነት ለመያዝ በሚሰነዝረው ጥቃት ሁሉ የመጀመሪያ ኢላማው ናቸው:: ይኽ የፖለቲካ ሀይል በአሁኑ ወቅት  የፖለቲካ ስልጣን የሚያስገኘውን ጥቅም ቢያጣም  የቀዱሙት ስርዓቶች በፈጠሩለት መልካም አጋጣሚ በሌሎች ዘርፎች  የያዘውን የበላይነት አሁንም ሙሉ በሙሉ  አላጣም::  የፖለቲካ ስልጣንም ትግል በማድረግ ላይ ነው:: ፍትህ ዲሞክራሲና አንድነት ማምጣት የፖለቲካ ትግሉ ግብ አድርጎ ይገልፃል:: በህወሓት ኢህአድግ  የፖለቲካ ሀይሎች የፖለቲካ ህይሉ የሚታገለው አማራን ወደ ፖለቲካ ስልጣን ለመመለስ አና የአማራ የፖለቲካ የኢኮኖሚ የባህል የታሪክ የበላይነትን ለማስመለስ የሚታገል የፖለቲካ ሀይል ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን  ነገር ግን አንድ ስንዝር አንዳይራመድ ጥበቃ የሚደረግበት ነው:: ይኽ የፖለቲካ ሀይል በብሄር ጥያቄ ላይ ከሚያራምደው አቆም አንፃር በኦሮሞ ና በሌሎች የብሔር ጥያቄ በሚያነሱ የፖለቲካ ሀይሎች በጥርጣሬ የሚታይ ነው:: የአማራ የፖለቲካ ኃይሎች በሚመሩት አሰላለፍ ከሁሉም ብሔሮች የተሳተፉ ግለሰቦች ባይጠፉም በዋነኛነት በተለይ ከ አናሳ ብሄሮች በርከት ያሉ ደጋፊዎችን ማሰለፍ ችለዋል::  ይኽ አሰላለፍ አናሳ ብሄሮችም የብሔር ጥያቄ ያላቸው በመሆኑ: ዘለቄታው አስተማማኝ  አይመስለኝም::

የኦሮሞ የፖለቲካ ሀይሎች የብሔር ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል:: ይኽ የፖለቲካ ሀይል ከዚህ ቀደም በነበሩ ስርዓቶች በሀይል የተነጠቃቸውን: ያልተመለሱ የፖለቲካ ጥያቀዎችን ለማስመለስ አንደሚታገል ይገልፃል: ይኽ  የፖለቲካ ሀይል የኦሮሞ ህዝብ ከዚህ ቀደም በነበሩ የፖለቲካ ስርዓቶች በሀይል የተነጠቀው: ተመልሶለታል/ይበቃዋል በሚለው ሀወሀት ኢህአድግ የመረረ ጠላት ተደርጎ ተወስዶል:; ይኽ የፖለቲካ ሀይል በራሱ የፖለቲካ ሀይሎች ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ተመሳሳይ የብሔር ጥያቄ ያላቸው አጋሮች አሉት:: ይኽ የፖለቲካ ሀይል  በአማራ የፖለቲካ ኃይሎችና በሰልፉ ውስጥ በተካተቱት ሁሉ ወዳጅነትን ሲነፈግ ይታያል::

ትውልድ የሚሻገር መፍትሄ ለማምጣት በነዚህ የፖለቲካ ሀይሎች መካከል ወይይት: መተባበር; ድርድር ያሰፈልጋል:: ከትንሽ ወደ ትልቅ የሚያድግ ትብብር ቢሆን ይመረጣል:: ትብብር ማድረግ አስቸጋሪና ፈታኝ መሆኑን በቅድሚያ መቀበል ያስፈልጋል::  በ መሳሪያ ሀይል አንዱ የፖለቲካ ሀይል ሌላውን ለማንበርከክ የሚያደርጉት ጥረት ዉሀ ቢወቅጡት አንቦጭ እንዲሉ ከሚሆን ዉጭ ትውልድ የሚሻገር መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም:: ለብዙ መቶ አመታት የቆዩ የሌሎች ሀገሮችን ሕገ መንግስቶች እያየን አድናቂ ብቻ ሆነን: ሌሎች ግን አንደተደነቁብን አንቀራለን::

ቸር እንሰንበት::

የፓርቲ ፖለቲካ የትግል እርሻ – (ከዘላለም ክብረት እና በፍቃዱ ኃይሉ)

weyeyet

ከጠዋቱ ጤዛ እስከ ምሽቱ ቁር

አንጋው ተገኝ በሠላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለ ወጣት ነው። ፀጉሩን ያጎፍራል። ሲናገር በብዙ ነገሮች እየተደነቀ ነው። አንጋው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አብረሃ ጅራ ወረዳ ኃላፊ በመሆን እጅግ ፈታኝ ጊዜያትን አሳልፏል። የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የሀገሪቱ ክፍሎች መንቀሳቀስ የሚያስከፍለው ዋጋ ከባድ መሆኑን ደጋግሞ ይናገራል። የፓርቲው አመራር ሁኖ በሠራበት ወቅት ፓርቲ ስብሰባ እንኳን ማድረግ እጅግ ከባድ መሆኑን ያስታውሳል። ፖሊስና የደኅንነት ኃይሎች አመራሮቹን እየተከታተሉ ሲያስጨንቋቸው ‹የፓርቲው ሥራ ከሚቆም በሚል አንገረብ ወንዝ ወርደን እየዋኘን እንሰበሰብ ነበር› ይላል። እየዋኘን ሰው ወደኛ በመጣ ቁጥር እየተበታተንን፤ ሰው ራቅ ሲልልን ደግሞ እዛው ውኃው ውስጥ ሰብሰብ ብለን እየተንሳፈፍን ነበር ስብሰባ የምናደርገው የሚለው አንጋው በፓርቲ እንቅስቃሴ ምክንያት ስድስት ጊዜ ከሥራ ተባሮ ስድስት ጊዜ መመለሱን ሲገልጽ አንዳንዴ በሕይወት መቆየቴም ለኔ ግርም ይለኛል እያለ ነው። ይባስ ብሎ በሠላማዊ ትግል ቆርቦ በዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ የነበረው አንጋው ተገኝ የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ ሳይቀርብበት አሁን ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለህ በሚል ምክንያት በመጨረሻ ለእስር የተዳረገ ሲሆን፤ እስር ቤት ሁኖም የታገለለትና የደከመለት አንድነት ፓርቲ ሲፈርስና በእሱ አባባል ‹መፈንቅለ አመራር› ሲካሄድበት ተመልክቶ ያዝናል። ለዚህ ሁሉ መሆን አንጋው ተጠያቂ የሚያደርገው ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ነው። ‹ሕግ የማይገዛው መንግሥት› እያለ ሁሌም ይገረማል። ይህ የኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ችግር የገዥው ፓርቲ ቅጥ ማጣት ነው ከሚሉት ወገን የሚቀርበው ሐሳብ ትክክለኛ ተምሳሌት ነው።

ከዚህ አሳዛኝ ኹነት መለስ ብለን አርብ ሚያዚያ 28፣ 2008 ከጠዋቱ 4፡30 እስከ 5፡30 ድረስ በአንድ ሰዓት ውስጥ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጆች ለጽሑፉ ግብዓት የሚሆን መረጃ ለማግኘት በማሰብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ መሠረት እንዲሁ አለፍ አለፍ እያልን በአሁኑ ወቅት በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ከሚገኙ ሰባ አምስት ፓርቲዎች መካከል የሃያ አምስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የስልክ አድራሻ ላይ ስልክ የደወልን ሲሆን፤ ከሃያ አምስቱ ሙከራዎች መካከል ሁለቱን ስልኮች ያነሱልን ሕፃናት ሲሆኑ፣ የሰባቱ ስልክ ቢጠራም አይነሳም፤ የዐሥራ አምስቱ ስልክ ደግሞ ከነአካቴው የማይሠራ ሲሆን፤ የአንዱ ብቻ ማለትም ‘የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት’ ስልክ ላይ የፓርቲውን አመራር ልናገኝ ችለናል። በተመሳሳይ ጊዜ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያደረግነው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪም ስልኩ ሊነሳ ባለመቻሉ ማብራሪያ ማግኝት አልቻልንም። እንግዲህ ‹የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ ሰሞን ግርግር ከመፍጠር ያለፈ ምንም አይፈይዱም የሚለው ሐሳብ እንዲሁ ያለውን ሁኔታ ቀረብ ብሎ ካለማየት የሚመጣ ነው› የሚሉ ተችዎችም ሁሌም የሚፈተኑበት ጉዳይም ይሄው ተቃዋሚ ፓርቲ ተብለው የተመዘገቡት ፓርቲዎች በሚገባቸው ቦታ አለመዋላቸው ነው። ፓርቲዎቹ የስልክ እንኳን አድራሻ የሌላቸው/ቢኖራቸው እንኳን የማይሠሩ ስልኮችን ይዘው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የለውጥ መሠረት ይሆናሉ ብሎ ማሰቡንም ያከብደዋል። ይህ ደግሞ ተቃዋሚዎች የራሳቸው ሥራ ሳይሠሩ ገዥውን ፓርቲ ማውገዛቸው ተገቢ አይደለም የሚለው ሐሳብ ተምሳሌት ነው።

 

የጠዋቱ ጤዛ

‹የፓርቲ ፖለቲካ ማለት በሕግ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን አደራጅተው ለምርጫ የሚያደርጉት ትግል ነው› የሚለው ጠቅለል ያለ ትርጉም በኢትዮጵያ ፖለቲካ አኳያ ይሠራል ማለት ከባድ ነው። ከተመዘገቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች በማይተናነስ መልኩ የራሳቸው ፍላጎት እና ዓላማ ያላቸው ብዙ ቡድኖች ራሳቸውን የፖለቲካ ፓርቲ ብለው ሰይመው የሚንቀሳቀሱ ከመሆናቸው አንፃር የፓርቲ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ ዐውድ አንፃር ለምርጫ የሚደረግ ሠላማዊ ትግል ነው ከሚለው ትርጉም ፈቅ ያለ መሆኑንም ነው እነዚህ ፓርቲዎች የሚያስረዱን።

 

በቡድን ተደራጅቶ የፖለቲካ ፓርቲ የሚባል ድርጅት ፈጥሮ መንቀሳቀስ የተጀመረው ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲ ሞዴል (Party Political Model) የፖለቲካ ሒደት ከመጀመሯ ብዙ ቀደም ብሎ እንደሆነ የተለያዩ ጸሐፊዎች ያመላክታሉ። ከጣሊያን የአምስት ዓመታት ቆይታ በኋላ በተለይም ውጭ አገር ቆይተው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን በአውሮፓና በአሜሪካ ካዩት አሠራር በመነሳት የፓርቲ አደረጃጀት ኑሮ ፖለቲካው በዛው መሥመር እንዲቃኝ መፈለጋቸው አልቀረም። ዘውዴ ረታ ‹የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት› ባሉት መጽሐፋቸው በመጋቢት 1939 ንጉሠ ነገሥቱ ራሳቸው ስለ አገራችን ጠቅላላ ሁኔታና ስለ እኛ አመራር ሐሳባችሁን አቅርቡልኝ ባሉት መሠረት በወቅቱ የጽሕፈትና የሀገር ግዛት ሚኒስትርነትን ደርበው ይዘው የነበሩት ጸሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ ከሦስቱ የማሻሻያ ሐሳብ አቅራቢዎች መካከል አንዱ ነበሩ። በወቅቱ ወልደጊዮርጊስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት እየተንቀሳቀሱ ነው የሚል ሐሜት ይሰማባቸው ስለነበር ይሄን ሐሜት “እኔና አቶ መኰንን [ሀብተወልድ] እየተግባባንና እየተረዳዳን በመሥራታችን የፖለቲካ ፓርቲዎች በመሆናቸው ነው እየተባለ የሚነገርብን ደህና አድርገን እናውቀዋለን። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚያውቁት፤ የፖለቲካ ፓርቲ በአገራችን የለም።” በማለት ካስተባበሉ በኋላ ስለፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀት ሲያስረዱ “እኔ በዚያ በመከራው የስደት ዘመን እንዳየሁት፤ ዛሬ በአለንበት ሰዓት ለኢትዮጵያ አስተዳደር እንደ እንግሊዝ አገር፤ ንጉሥ የታሪክና የባሕል የበላይ ጠበቂ ሆኖ ይነግሳል፤ መንግሥት ደግሞ በፓርላማ ሕዝብ ቀጥታ ከመረጠባቸው እንደራሴዎች መካከል በፖለቲካ ፓርቲ አሸናፊ የሆነው ይመረጣል፤ የሚለውን ሐሳብ ወስዶ መጠቀም ይቻላል ብዬ አላምንም። እንደ እንግሊዝ አገር መሆን እንችላለን ብሎ ማሰብ፤ አቅምን ካለማወቅ የተነሳ በሸንበቆ ላይ እንደሚገነባ ምኞት የሚቆጠር ይሆናል” በማለት ነበር። ይህ ሐሳብ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ለቀጣዮቹ ሃያ ሰባት ዓመታት ንጉሠ ነገሥቱ የፖለቲካ ፓርቲ የሚባለውን አደረጃጀት በጥርጣሬ እንደተመለከቱት ከመንበራቸው ሳይወዱ በግድ ተወገዱ። በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የፖለቲካ ፓርቲ የማቋቋምም ሆነ የፓርቲ ፖለቲካን ለማካሄድ የሚያስችል ምንም ዓይነት የሕግ ማዕቀፍም ሆነ ቀናነት ያልነበረ ቢሆንም የፓርቲ ቅርፅ ያላቸው አደረጃጀቶች በተለይም በመጨረሻዎቹ የንጉሡ አምስት የሥልጣን ዘመናት አቆጥቆጠዋል። አንትሮፖሎጅስቱ ዶ/ር ወንድወሰን ተሸመ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የፖለቲካ ፓርቲ የዛሬ ሃምሳ ዓመት በ1958 የተመሰረተው ‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ካውንስል› ነው የሚሉ ሲሆን፤ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እዚህም እዚያም ማቆጥቆጥ የጀመሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሲወጡና ሲወርዱ ቆይተዋል።

 

ከንጉሠ ነገሥቱ ስርዓት ማብቃት ጋር ተያይዘው ብቅ ብቅ ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች በግራ የፖለቲካ አስተሳሰብ የተቃኙና በፍጥነት ወደመጠፋፋት በመዝለቃቸው ተስፋ የተደረገበትን የፓርቲ ፖለቲካ አካሔድ እዛው ካለበት ላይንቀሳቀስ ተተክሎ ቆይቶ ከኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ወደ ሥልጣን መምጣት ጋር ተያይዞ አዲስ ተስፋ በብዙዎች ዘንድ ማደሩ አልቀረም። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ከሚወደስባቸው ጉዳዮች አንዱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን (multi-party system) በሕግ ተቀብሎ በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጋዊ ዕውቅና የሚሰጥ ስርዓት መዘርጋቱ ነው።

የሃምሳ ዓመታት የሙከራ ታሪክ፤ የሃያ አምስት ዓመታት ሕጋዊ ዕውቅና ያለው የፓርቲ ፖለቲካ ከዕድሜው አንጻር ምን ትርፍ አመጣ? ለምንስ ፈተናና እክል በየቀኑ እያጋጠመው ይወድቃል የሚሉት ጥያቄዎች መሠረታዊና የወደፊቱን ለመረዳት የሚረዱ ናቸው። በኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ እንዳያብብ እና እንዲቀጭጭ ምን እክል አጋጠመው? ለሚለው ጥያቄ አንድ ዓይነት ምላሽ መስጠት አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም እንደ መላሾቹ የተለያ መልሶችን እናገኛለን።

 

ዴሞክራሲ የማያበቅል መሬት?

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሒደት በቅርበት የሚከታተሉ ምሁራን ለፓርቲ ፖለቲካ ስኬት ማጣትና ብሎም ዴሞክራሲ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይደረጅ መሠረታዊውን አስተዋፅኦ ያደረገው የመጠላለፍና አምባገነኖችን የሚያበቅል የፖለቲካ ባሕል መኖሩ ነው ይላሉ። በኢትዮጵያ ላይ ብዙ ጥናት ያደረጉት ጆን ያንግ በዐሥር ዓመታት ልዩነት በኢትዮጵያ የፓርቲ የፖለቲካ ሒደት ላይ በጻፏቸው ሁለት ጽሑፎቻቸው ላይ ለኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካና ዴሞክራሲ ዋነኛ እክል አድርገው የሚያቀርቡት በኢትዮጵያ ያለውን ከመንግሥታዊ መዋቅሩ ውጭ ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ ተቋም እንዲፈጠር ያለመፍቀድ አባዜንና በእርሳቸው ቋንቋ በሃገሪቱ ውስጥ ከ11ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን የቀጠለው ፈላጭ ቆራጭ የፖለቲካ ባሕልን (Authoritarian Political Tradition) ነው። እንደ ጆን ያንግ ሁሉ ዶ/ር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዩች ላይ አብዝተው የተመራመሩት ጆን አቢኒክና ማሪና ኦታዌ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የትናንት የባሕል ሸክም እንዳጎበጠው እየገለጹ መፍትሔውን ይሄን ባሕል መቀየር ላይ ያደርጋሉ። እንዲሁም ሳራ ቮጋን እና ኬቲል ትሮንቮል የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አወቃቀር፣ ከልጅነት እስከ ዕውቀት ድረስ በተዋረድ (hierarchy) የተሞላ መሆኑ ለዚህ የፖለቲካ ባሕል አለመዳበር እንደመንስኤ ይወስዱታል። “አብዛኞቹ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎች ተከራክረው፣ ሕይወታቸውን በተሻለ መንገድ ለመዘወር የሚያስችላቸውን አማራጭ ስለመለየት አያስቡም። ሌሎችም ይህንን ያደርጋሉ ብለው አይጠብቁም፤ የበላይ ወይም የበታች ከሚሏቸው ጋር ይህንን ማድረግ ደግሞ ጨርሶ የማይታሰብ ነው” ይላሉ።

ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግን ጨምሮ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በሙሉ በጋራ የሚስማሙበት የሚመስለው ጉዳይ ‹የኢትዮጵ የፖለቲካ ባሕል አለማደግን› ነው። የፖለቲካ ባሕል ሊገለጽ የሚችልባቸው ብዙ መንገዶች ቢኖሩም፣ ‹ጠርዘኝነት› ግን ዋነኛውና ብዙዎቹ የፖለቲካ አመራሮች እንደፈታኝ የሚወስዱት ችግር ነው። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት “የፖለቲካ ባሕላችን ቀኖናዊ ነው” ወይም በሌላ አነጋገር “perfectionist (ፍፁማዊ)… ወይ አርዮስ ወይ ቅዱስ ብሎ የመፈረጅ አባዜ አለበት” የሚሉ ሲሆን፤ አያይዘውም “በእኛ ባሕል የፖለቲካ ሐሳብ ልዩነት ሲኖርህ መጠፋፋት ነው” ይላሉ። ይህ የኢንጅነር ይልቃል ምልከታ ከላይ የጠቀስናቸው ሳራ ቮጋን እና ኬቲል ትሮንቮል ‹The Culture of Power in Contemporary Ethiopian Political Life› በሚል ጥናታቸውን ከደረሱበት ድምዳሜ ጋር የሚስማማ ነው። ምሁራኑ በጥናታቸው ‹መንግሥት እና ተቃዋሚዎች በነገሮች እና ርዕዮተ-ዓለም ጉዳዮች ላይ አይወያዩም። የራሳቸውን ብቻ የፖለቲካ አመለካከት ይዘው እርስ በርስ በመነጋገር ፈንታ፣ አንዱ ሌላውን ይወቅሳል።› አጥኚዎቹ አክለውም፣ ሌላው ቀርቶ በፌዴራል መንግሥቱ ቋንቋ አማርኛ ውስጥ እንደሁለት የተነጣጠሉ አካላት የሚታዩት ‘state’ እና ‘government’ ተነጣጥለው የማይታዩ እና ‹መንግሥት› በሚለው ቃል ብቻ የሚተረጎሙ መሆኑ አንዱ የፖለቲካ ባሕሉ አለማደግ ምልክት አድርገው ይወስዱታል።

የኢ.ዴ.ፓ. የቀድሞው ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው ከፖለቲካ ባሕል አለማደግ ጋር አያይዘው ‹የእኛ የፖለቲካ ባሕል በጦርነትና በመገዳደል ሥልጣን መያዝ ነው፤ የእኛ ፖለቲካ ሲታይ አንዱ ባለኃይል ሌላኛውን ባለኃይል ሥልጣን የሚቀማበት ነው› የሚሉ ሲሆን አያይዘውም “ሕዝብ እንደሚሳሳት ማወቅና እና ሲሳትም ተሳስተሃል ሊባል እንደሚገባው መስማማት ይኖርብናል።” በማለት ባሕሉን እየተቸን ካላሳደግነው የፖለቲካ ሒደቱ የትም አይደርስም የሚል መደምደሚያ ይሰጣሉ።

ነገር ግን ይህ የፖለቲካ ባሕል አለማደግ ነው፣ የፖለቲካችን መሠረታዊ ችግር በሚለው ሐሳብ ሁሉም ምሁራን አይስማሙም። በዚህ ከማይስማሙት ምሁራን አንዱ ቶቢያስ ሐግማን ናቸው። “የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከባሕል አንፃር ብቻ መተርጎም ስህተት ነው” ይላሉ ሐግማን ጆን አቢኒክ ከምርጫ 97 በኋላ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ለጻፉት ጽሑፍ ምላሽ በሰጡበት ጽሑፋቸው። “ከዚህ እይታ ባለፈ ገዥው ፓርቲ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ከውስጡ ምን ያህል የተማከለ እና ፈላጭ ቆራጭ እንደሆነ መረዳቱ ነው ወሳኙ የፖለቲካው ውድቀት መነሻ” የሚሉት ሐግማን “ከዚህ ባለፈ ግን ችግሩን ወደ ባሕል መውሰዱ ገዥውን ቡድን ነጻ ማውጣት ነው የሚሆነው” ብለው የችግሩ መነሻና መድረሻ ገዥው ቡድን እንደሆነ አጽንኦት ይሰጣሉ። ነገር ግን ምሁራኑም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ ባሕልን እንደ አንድ የችግሩ ምንጭ እንጅ የችግሩ ብቸኛው መነሻ አድርገው ላለመውሰዳቸው ጽሑፎቻቸውና አስተያየቶቻቸው ይገልጻሉ።

 

የታጠረው ምኅዳር

የፖለቲካ እሳቤዎች መዝገበ ቃላት እንደሚያስነብቡት የመድብለ ፓርቲ ስርዓት (multi-party system) ማለት በቁጥር የበዙ እና አሸንፈው መንግሥት በተናጥል ወይም በጥምረት የመመሥረት ዕድል ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ለብሔራዊ ምርጫ የሚሳተፉበት ስርዓት ነው። ሌላው ቀርቶ በእነዚህ ብያኔዎች መሠረት የዴሞክራሲያውያኑ ምዕራብ አገሮች፣ ለምሳሌ የአሜሪካ የፖለቲካ ስርዓት የሁለት-ፓርቲ ስርዓት ነው። በአሜሪካ ከስልሳ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢኖሩም ከሪፐብሊካን እና ዴሞክራቶች በቀር አሸንፈው መንግሥት ለመመሥረት የሚችሉበት ዕድል ስለሌላቸው (ወይም ዕድላቸው እጅግ ጠባብ ስለሆነ) የአሜሪካ ስርዓት የሁለት-ፓርቲ ስርዓት እንጂ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ሊባል አይችልም።

ከገዢው ፓርቲ ውጪ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል እና አንድ በግል የተመረጡ አባላት ብቻ ከተወከሉበት ምርጫ 2002 ወዲህ ገዢው ፓርቲ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ራሱን ‹አውራ ፓርቲ› በማለት መጥራት ጀምሯል። ይህንኑም ልማታዊ ዴሞክራሲ እያለ ከሚጠራው ከኢኮኖሚ ዕቅዱ ጋር አዋድዶ ለመቀጠል ትልሙ እንዳለው በተለያዩ መድረኮቹ አስታውቋል። ይሁን እንጂ  ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ‘የአውራ ፓርቲ’ (dominant party) ስርዓት እያራመደ ሳይሆን በኢፍትሐዊ መንገድ ያገኘውን የሕዝብ ተወካዮች ወንበር በሕዝባዊ ይሁንታ ያገኘው ለማስመሰል ከመጣሩም ባሻገር ምጣኔሀብታዊ ጠቀሜታ ያለው በማስመሰል ሕዝባዊ ቅቡልነት ለመግዣ እየተጠቀመበት ነው ከሚል ትችት አልዳነም። የአውራ ፓርቲ አካዳሚያዊ ብያኔ ‹አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ተከታታይ ምርጫዎችን በበላይነት ሲያሸንፍ፣ ወደፊትም የመሸነፍ ዕድሉ አነስተኛ ሆኖ ለመገመት የሚያስቸግርበት ስርዓት› እንደሆነ ይደነግጋል። ይህ ዓይነቱ ስርዓት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የታየው በተለይ በጃፓኑ ዴሞክራቲክ ሊበራል ፓርቲ እና ሌሎች ጥቂት አገራት ብቻ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ የአውራ ፓርቲ ስርዓት የተከሰተባቸው አገራት ታሪክ የሚያሳየው አውራ ፓርቲው ‹አውቶክራት› (ለዴሞክራሲ ያልበቃ፣ በሌላ በኩል የወጣለት አምባገነንም ያልሆነ) ስርዓት ነው።

ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ራሱን አውራ ፓርቲ በማለት መጥራት የጀመረው ፓርቲው ‹ልማታዊ ዴሞክራሲያዊነት በተግባር ተፈትሾ ነጥሮ ወጥቷል› እንዲሁም ምርጫው ‹በኪራይ ሰብሳቢዎች ካምፕ ድንጋጤና ውዥንብር ፈጥሯል› ብሎ በገመገመው ምርጫ 2002 ማግስት ነበር። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ይሄን ‹አውራ ፓርቲ› የሚል ማዕረግ ለራሱ ሲሰጥ የአውራ ፓርቲ ስርዓት የዘረጉ ዴሞክራሲያዊ አገሮችን ሲዊዲንና ደቡብ ኮሪያ እያለ እያጣቀሰ የአንድ ፓርቲ ስርዓት ሳይሆን ወደ አውራ ፓርቲ ስርዓት እያመራን ነው፤ ይሄም ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ታላቅ እመርታ ነው በማለት ግምገማውን በወቅቱ አስቀምጧል። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ራሱን አውራ ፓርቲ ብሎ ከመሰየሙ ሦስት ዓመታት ቀደም ብሎ በ1999 የፓርቲዎች የሥነ ምግባር ደንብ ሙሉ ለሙሉ ተገልብጦ መጥቶበታል የተባለው ‹International Institute for Democracy and Electoral Assistance (IDEA)› የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ባቀረበው ሪፖርት ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ከምርጫ 97 ማግስት ወዲህ አውራ ፓርቲ እንደሆነ የሚያትት ነው። ‹IDEA› የአውራ ፓርቲ ስርዓት የሚባለው ስርዓት በአራት መልኩ የዴሞክራሲ ፀር እንደሆነ በሰነዱ ላይ የገለጸ ሲሆን እነዚህም አንደኛ፣ የፉክክር ፖለቲካን ያቀጭጫል፤ ሁለተኛ፣ የሕግ አውጭውን ሥልጣን ጠቅልለው በመያዝ በአንድ አገር ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ፍላጎቶች ይቆጣጠራል፤ በሶስተኝነት፣ ጠያቂ ስለማይኖርበት ተጠያቂነት የሌለበት ስርዓት ይፈጥራል እንዲሁም በመጨረሻም፣ የሥልጣን ትዕቢት በመፍጠር ለዜጎች ጥያቄ ደንታ ቢስ መንግሥት እንዲፈጠር ያደርጋል የሚሉ ናቸው። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የምርጫ ሥነ ምግባር ሕጉንና የአውራ ፓርቲ ፅንሰ ሐሳብን ከ‹IDEA› ወስዶ ይሄን የድርጅቱን የአውራ ፓርቲ የሰላ ትችት እንዳላየ ሁኖ በማለፍ በተለያዩ የፓርቲው ሰነዶች አሁንም አውራ ፓርቲ መሆኑን እየገለጸ ይገኛል።

የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ታላቁ ሊቅ ሳሙኤል ሀንቲንግተን ‹ዴሞክራሲ ሊጠናከር የሚችለው መንግሥት በምርጫ ሥልጣን ሊያጣ ሲችልና ሥልጣን ላይ የወጣው አዲስ ፓርቲም እንዲሁ ሥልጣኑን በምርጫ ሊያጣ ሲችል ብቻ ነው› በማለት የሥልጣን ሽግግር የዴሞክራሲ ምሰሶ መሆኑን ያስረዳሉ። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የወዳጆቹንም የጠላቶቹንም ምክር ወደ ጎን ብሎ የት እንደሚያደርሰው ባይታወቅም አሁንም የፖለቲካ ሥልጣኑን ሙሉ ለሙሉ ጠቅልሎ ይዞ ይገኛል።

አሁን አሁን ደግሞ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ራሱን የሚጠራበት ‹አውራ ፓርቲ› የሚለው ስያሜ የሚያንሰው እንደሆነ ተቺዎች መናገር ጀምረዋል። አንዳንዶች አሁን ፓርቲው ከመሠረቱ ሲያራምደው ከነበረው ሶሻሊስታዊ የብዝኃ አደረጃጀት (Mass Party) ቅርፅ ላይ የመንግሥታዊ ፓርቲነት (Cartel Party) ካባ ደርቦ ወፍሯል የሚለው ትችት ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው። መንግሥታዊ ፓርቲዎች የመንግሥትን ሀብት እንደፈለጉ የሚጠቀሙ ፓርቲዎች ሲሆኑ፤ አንዳንዴ የፓርቲና የመንግሥት መዋቅሮችን መለየት እስኪያስቸግር ድረስ አንድ ላይ የሚያዋህድ ቅርፅ ነው። ከዚህ መንግሥትና ፓርቲን ካልለየ አካሄድ ጋር ተያይዞ “ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ” የጣሊያናዊውን ማውሮ ሴሊዜን (Mauro Calise) ቋንቋ በመዋስ “ወደ ፓርቲክራሲ (Particracy) ቀይሮታል” ወደሚል መደምደሚያ ላይ እየደረሱ የሚገኙ ብዙዎች ናቸው።

በዚህ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የመጠቅለል አካሄድ ላይ ስጋት የገባቸው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢ.ዴ.ፓ.) የቀድሞ ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው “ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. በይዘት ከቻይና አስተሳሰብ ብዙም አይለይም” ይላሉ። የቻይና አስተሳሰብ የሚሉት፣ ‹አሁን ባለንበት ሁኔታ ዴሞክራሲ አያስፈልገንም፣ የሚያስፈልገን የኢኮኖሚ ሪፎርም ነው› የሚለውን ነው። የቻይና መንግሥት ይህንን የሚያደርገው በይፋ የአንድ ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲን ደንግጎ ነው። በቻይና ሕጋዊ ዕውቅና ያለው አንድ ‹የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ› ብቻ ነው። የቻይና የፖለቲካ ስርዓት አሀዳዊ እንጂ አውራ ፓርቲ ስርዓት አይባልም። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ግን ይህንን ማድረግ ያልቻለው፣ ደርግን ጥሎ አዲስ አበባ እግሩ በረገጠበት ሰዓት የቀዝቃዛው ጦርነት እየከሰመ ዓለም በሁለት ‹ብሎክ› የሚጠራበት ስርዓት እያበቃ በአንድ ዓለምዐቀፍ አስተሳሰብ እየተጠራ ስለነበር “የቻይና አካሔድ የሚበጅ ሆኖ ባለማግኘቱ” እንደሆነ አቶ ልደቱ ይናገራሉ። ስለሆነም “በወረቀት የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን ደንግጎ፣ በተግባር ግን የቻይናን መንገድ ይከተላል”።

እንደ አቶ ልደቱ ገለጻ “ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ያስፈልገዋል ብሎ አያምንም። ለዚህ ሕዝብ አሁን ዴሞክራሲ አያስፈልገውም… የዳቦ ጥያቄው ከተመለሰ በኋላ ይደርስበታል ብሎ ነው የሚያምነው።”

የኦሮሞ ፌዴራል ኮንግረስ (ኦ.ፌ.ኮ.) ሊቀመንበር እና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዶ/ር መረራ ጉዲናም ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የመድብለ ፓርቲን የሚያስተናግድ አስተሳሰብ እንደሌለው ይናገራሉ። “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ይላሉ ዶ/ር መረራ “የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን ለማስተናገድ የተፈጠረ አይደለም”። በኢትዮጵያ መድብለ ስርዓትን የሚፈቅድ “የይስሙላ ጨዋታ” የተፈቀደው ዕርዳታ ለጋሽ አገራትን ለማስደሰት ብቻ ነው” በሚል ነው ዶ/ር መረራ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት አለ ሊባል የሚችለው ብለው የሚያስቡት።

የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን የመጀምሪያ የሥልጣን ዘመናት በገመገሙበት ጽሑፋቸው ይሄን አካሄድ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የአግላይነት ፖለቲካ (politics of exclusion) ያሉት ሲሆን፤ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ያልተመቸውን ሰውም ሆነ ድርጅት ወደ ጎን እየገፋ ዙሪያውን በራሱ ሰዎች መክበብን እንደ ዋነኛ የሥልጣን ላይ መቆያ ዘዴ እንዳደረገው አያይዘውም ይገልጻሉ። ዶ/ር ካሳሁን ይህን ካሉ ከ15 ዓመታት በኋላ ይህ አካሄድ መባስ እንጅ መሻሻልን እያወቀ አይደለም።

 

የተበላሸ ዘርና ተጣሞ ‘ያደገ’ ተክል

የፓርቲ ፖለቲካ ላይ የሚቀርበው ሌላው መሠረታዊ ትችት የፖለቲካው ተዋንያንንና ከተዋንያኑ አደረጃጀት ጋር ተያይዞ የሚቀርብ ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቋቁሟቸው ግለሰቦች በራሳቸው ብዙ የራሳቸው የግል ፍላጎት ያሏቸውና ተደራጅተው ከሌሎች ጋር መሥራት የሚቸግራቸው ናቸው ከሚለው ሐሳብ ነው ትችቱ የሚጀምረው። ዶ/ር ወንድወሰን ተሾመ በአሁኑ ወቅት ያሉ የኢትዮጵያ ፓርቲ ፖለቲካ ተዋንያንን በሰባት መደቦች ያስቀምጧቸዋል። በዐፄ ኃይለሥላሴ ስርዓት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ (ex-minsters of the ancien régime)፣ የግራ ፖለቲከኞች (leftists)፣ የቀድሞ የግራ ፖለቲከኞች (ex-leftists)፣ ፋኖ ያሉ ፓርቲዎች (rebels)፣ ታማኝ ተቃዋሚዎች (loyal oppositions)፣ አስመሳይ ተቃዋሚዎች (phony oppositions) እና በፊት ኢሕአዴግ ውስጥ የነበሩ (ex-EPRDF members) በማለት። እንግዲህ እነዚህ በተለያዩ የዕድሜ ክልሎች ላይ ያሉ ተዋናዮች (አንዳንድ ከሁለት በላይ ባሉ መደቦች ውስጥ እየገቡ) የራሳቸውን ፍላጎት ለማራመድ ሲሉ ሌሎችን እየጠለፉ ሁሉም የፖለቲካው ከፍታ ላይ መድረስ እንዳይችሉ ሁኗል።

 

የኢትዮጵያ የፖለቲካ የውስጥ ፓርቲ የዴሞክራሲያዊነት (intra-party democracy) ችግር እንዲሁም ተቋማዊ ቁመና (Institutionalization ) የመያዝ ችግር አለባቸው የሚለው ትችትም ሁሌም የሚሰማ ነው። ሮበርት ሚሸልስ የተባሉ ምሁር የውስጥ ፓርቲ ዴሞክራሲን ይዞ የተደራጀ መዋቅር ያለውና ተቋማዊ ቁመና ያለው ፓርቲ ማቋቋም አብረው ሊሄዱ የማይችሉ (inconsistent) ጉዳዩች ናቸው ይላሉ። ፓርቲን ተቋማዊ ቅርፅ አስይዞ በተመሰሳይ ወቅት ዴሞክራሲያዊ ላድርግ ማለት የኋላ ኋላ ሁለቱንም ያሳጣል የሚል ነው የሐሳቡ አንኳር። ኢንጅነር ይልቃል በዚህ ሐሳብ የሚስማሙ ይመስላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ‹የፓርቲ አባላትን ዲስፕሊንድ አድርጌ የውስጥ ፓርቲን ዴሞክራሲ አሰፍናለሁ ማለት በዚህ ዘመን ከባድ ነው› ይላሉ። አያይዘውም የውስጥ ዴሞክራሲን በፓርቲ ውስጥ አስፍኖ የፓርቲ ዲሲፕሊን የሚባለውን ጉዳይ ወደ ጎን  ብሎ የንቅናቄ ቅርፅ ያለው ፓርቲ ይዞ መቀጠልን እንደሚመርጡ ይገልጻሉ።

የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ አሉባቸው ከተባሉት የአባላት ችግር እና የውስጠ ፓርቲ ቁመና ችግር ባለፈ ያለምንም ዓላማ አዳዲስ ፓርቲዎች እየተቋቋሙ እርስ በርሳቸው ይጠላለፋሉ የሚል ትችት ይቀርብባቸዋል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ድረ-ገጽ ላይ (ሚያዝያ 28/2008 እንዳየነው) የተዘረዘሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች 75 ናቸው። ከ2007 ምርጫ በፊት ‹ለቀጣዩ ምርጫ በንቃት የሚሳተፉ ፓርቲዎች ዝርዝር› በሚለው ስር የተዘረዘሩት ፓርቲዎች ቁጥር ግን ጠቅላላ ከተባለው የፓርቲዎች ዝርዝር ይበልጣል። እሱም በእንግሊዝኛው እና በአማርኛው ላይ የተለያየ ሁኖ እናገኘዋለን። በእንግሊዝኛው 79 ሲሆኑ፣ በአማርኛው 76 ናቸው። ከዚህ የቁጥር ዝብርቅርቅ በተቃራኒው፣ ብዙዎች የሚተቹት ብዛታቸው እና የርዕዮተ-ዓለም ልዩነታቸው የማይጣጣም መሆኑን ነው። ምንም እንኳን ብዙዎቹ ፓርቲዎች በዘውግ ከመደራጀታቸው በቀር ልዩነት ባይኖራቸውም መንግሥት ለመመሥረት በሚያስችላቸው ቁመና ለመቆም ጥምረት ወይም ግንባር ሲፈጥሩ አይታዩም። ኅብረ-ብሔራዊ መሠረት ይዘው የተደራጁትም፣ ግልጽ የሆነ የርዕዮተ-ዓለም ልዩነት ባይኖራቸውም ተደራጅተው ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ለመገዳደር በሚያስችላቸው መዋቅር ለመቅረብ አልሞከሩም፣ ቢሞክሩም አልተሳካለቸውም።

ዶ/ር መረራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር መብዛት ችግር ነው ብለው አያምኑም። “እስራኤል 5 ሚሊዮን ሕዝብ ብቻ ነው ያላት፤ ነገር ግን ከ30 በላይ በአገሪቱ ሕልውና የማይደራደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ስለዚህ ለ100 ሚሊዮን ሕዝብ ብዙ ፓርቲዎቹ ቢኖርም ያን ያክል ችግር አይደለም። ችግሩ፣ እነዚህ ፓርቲዎች ለሕዝብ ጥቅም የቆሙ ናቸው ወይስ አይደሉም፤ ለራሳቸውም ሥልጣን ለማግኘት ቢሆን ችግር የለውም፤ እንዲሁ የገዢው ፓርቲ ቀለብ የሚሰፍርላቸው ናቸው የሚለው ነው የሚያሳስበው” ይላሉ። የሌሎች አገራትን ተሞክሮ ስንመለከትም ዶ/ር መረራ ከሚሉት እውነታ ብዙም የራቀ ድምዳሜ ላይ አንደርስም። ኬኒያ በአንድ ወቅት እስከ 160 የሚደርሱ የተመዘገቡ ፓርቲዎች ነበሯት፤ ናይጄሪያም 60 የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ደቡብ አፍሪካንም የወሰድን እንደሆን ከ80 በላይ ፓርቲዎች ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱባት ሀገር ነች። ከዚህም አንፃር ኢትዮጵያ ውስጥ የፓርቲዎች መብዛት መሠረታዊ ችግር ነው የሚለው ሐሳብ ትክክል ነው ማለት አይቻልም። መሠረታዊው ችግር ያለው ‹እነዚህ ፓርቲዎች እንቅስቃሴያቸው ምን ይመስላል? የፓርላማ ውክልናቸውስ?› የሚለው ነው የሚሆነው። ኬኒያ ካሏት ፓርቲዎች መካከል 23 የሚሆኑት የፓርላማ ውክልና አላቸው፤ በናይጀሪያም 6 ፓርቲዎች በፓርላማ መቀመጫ ያለቸው ሲሆን፤ ደቡብ አፍሪካ ደግሞ 13 በፓርላማ ወንበር ያላቸው የፓርላማ ፓርቲዎች (Parliamentary Parties) አሏት። እንግዲህ የኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ አሳዛኝና አሳሳቢ የሚሆነውም ከዚህ አንጻር ስንመለከተው ነው። በአሁኑ ወቅት ገዥው ፓርቲ ብቻ በፓርላማ ተወክሎ የፈለገውን የሚወስንበት ጊዜ ሲሆን፤ ይሄም የፓርቲ ፖለቲካ የሚባለውን ሐሳብ ሙሉ ለሙሉ እንዳይቀብረው የብዙዎች ስጋት ነው።

ዶ/ር መረራ በኢትዮጵያ ‹የፈሉትን› የፖለቲካ ፓርቲዎች “አንዳንዶቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከራሳቸው [ከሊቀመንበሮቹ] የግል ዝና ያለፈ ቁመና ያላቸው አይመስለኝም…” ሲሉ አቶ ግርማ ሰይፉ ደግሞ “በአንድ ሰው የሚዘወሩ ሱቆች ወይም ከሱቅ በላይ ማዕረግ የሌላቸው ናቸው” ይሏቸዋል። አቶ ግርማ የሚያስገርማቸው “አንደኛ፣ እንደዚህ ዓይነት ፓርቲዎች እንዲቋቋሙ የሚፈቅድ መንግሥት መኖሩ እና ፓርቲዎቹ ውስጥ ለመሰባሰብ የሚፈቅዱ አባላት መኖራቸው” ነው። አቶ ግርማ፣ ሲቪክ ማኅበራት ሲዋቀሩ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያስቀምጥ መንግሥት፣ አገር እንመራለን ብለው የሚደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ‹በነጻ የመደራጀት መብትን ለማክበር› በሚል ሰበብ ብቻ እንዲሁ መተው ተገቢ እንዳልሆኑ ይናገራሉ። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕ/ር መርጋ በቃና በሕዳር ወር 2007 በሰጡት ይፋ ቃለ ምልልስ “75 [የፖለቲካ ፓርቲዎች] አሉ። ነገር ግን የሕግ ጉዳይ ያላሟሉና ሥልጣንን ሞኖፖላይዝ ያደረጉ እንዲሁም ራሳቸው ባወጡት ደንብ መሠረት ለ18 ዓመታት ጠቅላላ ጉባኤ ያልጠሩ አንዳንድ ፓርቲዎች ይገኙበታል። ለዴሞክራሲው ስንል በሆደ ሰፊነት ነው የምንይዛቸው” ብለው ነበር። አመራር የነበሩበት አንድነት ፓርቲ በእርሳቸው አገላለጽ ‹ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ› በምርጫ ቦርድ ጣልቃ ገብነት የተሰነጠቀባቸው እና ለሌሎች ተላልፎ የተሰጠባቸው አቶ ግርማ ሰይፉ ግን ይህ አባባል አይዋጥላቸውም። “ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. እንዲህ ዓይነቶቹን ‹ሱቅ› የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝም የሚላቸው ለሥልጣኑ ስለማያሰጉት እና ስለሚፈልጋቸው ነው።” በማለት ነው ሐሳባቸው የሚገልጹት።

አቶ ልደቱ አያሌው “ኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ የተመዘገበ፣ ሰርቲፊኬት ያለው ተቃዋሚ ፓርቲ እንጂ በተግባር ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የትግል እንቅስቃሴ የሚመጥን ተቃዋሚ ፓርቲ እስካሁን አልተፈጠረም። በምርጫ ቦርድ መስፈርቱን አዘጋጅተን ተመዝግበናል። ሕጋዊ ፈቃድ አለን፣ ቢሮ አለን፣ እንንቀሳቀሳለን። ምርጫ እንወዳደራለን። አሁን ካለው የኢትዮጵያ ሁኔታ አንፃር ግን፣ በተለይ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ዓይነት ግዙፍ ድርጅት ተቋቁሞ ለሥልጣን መብቃት የሚችል የፖለቲካ ፓርቲ እስካሁንም አልተፈጠረም፤ አሁንም የለም።” በማለት አቶ ግርማ ‹ሱቅ› እያሉ የሚጠሯቸው ብቻ ሳይሆኑ ሌሎቹም ፓርቲዎች ሕዝቡን በሚመጥን ቁመና ላይ እንደሌሉ ይሟገታሉ። አቶ ልደቱ ለዚህ ችግር መንስኤ ናቸው የሚሏቸውን አምስት ነጥቦች ዘርዝረዋል። “አንደኛ፣ ፖለቲካችን የሐሳብ ፖለቲካ አልሆነም፤ ሁለተኛ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና መጫወት የሚችለው የኅብረተሰብ ክፍል በተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ ተሳትፎ አያደርግም፤ ሦስተኛ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጣዊ ዴሞክራሲ የላቸውም፤ አራተኛ፣ አካባቢያዊ ስሜት በፓርቲዎች ውስጥ ነግሷል፤ አምስተኛ፣ ፓርቲዎቹ የውጪ ፖለቲከኞች ላይ ጥገኛ ናቸው” በማለት ያስቀምጧቸዋል።

የኢትዮጵያ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥራቸው ቢበዛም በአሁኑ ወቅት አንድም የፓርላማ ወንበር መያዝ አልቻሉም። ከላይ ካነሳናቸው የውጭና የውስጥ ችግሮች በተጨማሪ ከውሕደትና ጥምረት ጋር ተያይዘው የሚቀርቡባቸው ትችቶችም አሉ። ትችቱ ተዋሃዱ የሚል ብቻ ሳይሆን ለመዋሃድ ሲባል ፓርቲዎች መሠረታቸውን እየናዱ ይፈርሳሉ፤ መዋሃድን እንደ ግብ መውሰዳቸው ስህተት ነው የሚልም ነው። በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ከሁሉም ፈታኝ የሆነ ችግር እንደሆነ ብዙዎች የሚስማሙበት መተባበር አለመቻልን ነው። መተባበሩ ቀርቶ አንድ ፓርቲ ሳይሰነጠቅ እየጎለበተ መሄድ የሚችልበት ሁኔታም በተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሚናፈቅ ነገር ሆኗል የሚሉም አልታጡም። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ አቶ አስናቀ ከፋሌ ‹The (un)making of opposition coalitions and the challenge of democratization in Ethiopia, 1991–2011› በሚል ርዕስ ባሳተሙት ጥናታቸው ላይ ምርጫ 97 ላይ የመተባበር (coalition) ፖለቲካ እመርታ ታይቶ እንደነበር ይገልጻሉ። በዚህም ተቃዋሚዎች ‹ለምርጫ ሕጎች መሻሻል እና በአካባቢያዊ እና ብሔራዊ ደረጃ ጉልህ ውክልናን ለማሸነፍ በሚያስችል ሁኔታ መደራደር ቢችሉም፣ ያንን ማስቀጠል አልቻሉም። ያኔ እና ከዚያ በኋላ ትብብሮች ውጤታማ ሊሆኑ አልቻሉም› ብለዋል።

አቶ አስናቀ በዚሁ ጥናታቸው፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ትብብር አለመሳካት መንስኤ ሆነዋል የሚሏቸውን ሰባት ምክንያቶች በጽሑፋቸው ላይ ዘርዝረዋል። 1ኛ፣ ከልካዩ የፖለቲካ ምኅዳር እና የመንግሥት ተፅዕኖ፤ 2ኛ፣ በርዕዮተ-ዓለማዊ መግባባት ሳይሆን በሥመ-ተቃዋሚነት ብቻ ለመተባባር መስማማት፤ 3ኛ፣ የዳያስፖራ ፖለቲከኞች በተለያዩ ቡድኖች የመቧደን ተፅዕኖ፤ 4ኛ፣ የጋራ መግባቢያ የመፍጠር ልምድ ማነስ እና የዴሞክራሲ ባሕል እጦት፤ 5ኛ፣ የድርጅት ነጻነት (independence) ከግምት ውስጥ ያላስገባ ‹ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ› በሚለው ግፊት ብቻ የማይዘልቅ ጥምረት መመሥረት፤ 6ኛ፣ በተጣማሪዎቹ ድርጅቶች መካከል ያለ የኃይል/ሥልጣን ሽሚያ፤ እና 7ኛ፣ በተጣማሪ ቡድኖች መካከል መተማመን አለመኖር ለብዙዎቹ ጥምረቶች ስኬት ማጣት እና መልሶ መፍረስ ሰበቦች መሆናቸውን አመላክተዋል።

ከዚህ ከአቶ አስናቀ ትችት በተመሳሳይ አቶ ልደቱ አያሌው ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች ‹አንዱ መተባበርን እንደግዴታ የሚወስድ ባሕል መኖሩ እንደሆነ ይናገራሉ። የተለያየ የፖለቲካ ግብ ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ለመገዳደር ብቻ ሲባል እንዲተባበሩ ግፊት ይደረግባቸዋል። የሚተባበሩት በርዕዮተ-ዓለም አንድ ሆነው ስላይደለ ኅብረታቸው አይሰምርም› ይላሉ። ማኅበር (ወይም የፖለቲካ ድርጅት) መመሥረት በራሱ መተባበር እንደሚጠይቅ የሚናገሩት ኢ/ር ይልቃል ደግሞ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል “የመተባበር አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነገር አይደለም” ባይ ናቸው። ይልቁንም፣ ኢንጅነር ይልቃል እንደችግር የሚወስዱት ያላደገው የፖለቲካ ባሕላችን ችኩልነትን እና ፍፁማዊነትን መሻቱን ነው። ማኅበሮች በችኮላ እንዲመሠረቱ እና ፍፁማዊ ስኬት እንዲያስመዘግቡ ይጠበቃል። ይህ ደግሞ አይሳካም ይላሉ። “አለመተባበርም፣ ለውጤት የመጓጓትም ችግሮቹ አንድ ናቸው፤ ምንጩን ስናየው ውጤቱን በአንድ ሌሊት ለማየት መጓጓት ነው። ቅንጅትንም ያፈረሰው ይሄው ነው” ብለዋል።

በመጨረሻም ፓርቲዎች ውጤት ለማምጣት ላለመቻላቸው የሚጠቀሰው ምክንያት የአደረጃጀታቸው ጉዳይ ነው። ይሄም ሕብረ-ብሔራዊና የዘውግ (ethnicity) አደረጃጀት የሚለው ክፍፍል ኅብረ-ብሔራዊ የሚባሉት ፓርቲዎች ጎልተው እንዳይወጡ አድርጓቸዋል፤ የብሔር መሠረት ያላቸው ፓርቲዎች ደግሞ ከራሳቸው ማዕቀፍ ወጥተው ጠንካራ ተገዳዳሪ መሆን እንዳይችሉ አደረጃጀታቸው በራሱ ያግዳቸዋል የሚለው ነው።

በ1960ዎቹ በጋናዊው ኩዋሚ ኑኩሩማህ ጀማሪነት የተጀመረው የአፍሪካ ፓርቲዎችን በንዑስ መሠረት (particularistic) ላይ እንዳይመሠረቱ መከልከል እየተለመደ መጥቶ ከ1990ዎቹ ወዲህ እጅግ ሰፍቶ በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ውጭ ፓርቲዎች ዘውግንም ሆነ ሃይማኖትን መሠረት አድርገው የተደራጁበት የሰሃራ በታች የሚገኝ የአፍሪካ ሀገር አለ ማለት አይቻልም። አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ፓርቲዎች ዘውግን መሠረት አድርገው የሚደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕግ የተከለከሉ ናቸው። ለዚህም የሚሰጠው ዋነኛ ምክንያት እንደዚህ ያሉ አደረጃጀቶች ከፋፋይና (divisive) የሲቪል የፖለቲካ ሂደት እክል ናቸው የሚል ነው። ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ከላይ ባየነው የአፍሪካ እውነታ በተቃራኒው በአሁኑ ወቅት ገዥውን ግንባር ጨምሮ አብዛኞቹ ሕጋዊ ዕውቅና ያላቸው ፓርቲዎች የአደረጃጀት መሠረታቸው ዘውግ ነው።

ከዚህ መሬት ላይ ያለ እውነታም በመነሳት ‹በአሁኑ ወቅት በተሻለ የጥንካሬ ቁመና ላይ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች በብሔር ወይም በዘውግ የተደራጁት ናቸው፤ ኅብረ-ብሔራውያኑ ተዳክመዋል። ኅብረ-ብሔራውያኑ ፓርቲዎች የመሰነጣጠቅ አደጋ የሚያንዣብብባቸው በውስጣቸው በዘውግ የመቧደን አባዜ ስለሚከሰት ነው› በማለት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሚከሰቱ ውስጣዊ መዳከሞች እና መከፋፈሎች ላይ መንስኤው በዘውግ መደራጀት መፈቀዱ ነው የሚሉ ፖለቲከኞች ጥቂት አይደሉም። በአፍሪካ ውስጥ (ኬንያ እና ጋናን ጨምሮ) በዴሞክራሲ እያበቡ ያሉ አገራት በዘውግ መደራጀትን በይፋ በማገዳቸው የመድብለ ፓርቲ ስርዓታቸው ፈተና ውስጥ እንዳልወደቀ የሚከራከሩ አሉ።

አቶ ልደቱ አያሌውም ፖለቲካችን በከፍተኛ ሁኔታ የብሔር ፖለቲካ ያጠላበት መሆኑን አምነው፤ እንደሌሎች የአፍሪካ አገራት በዘውግ መደራጀትን ማገድ ያስፈልግ ይሆን ወይ ለሚለው ጥያቄ “የብሔር ፖለቲካን በሕግ ማገድ ያስፈልጋል ባልልም፣ እንደማይጠቅም ግን አምናለሁ” ይላሉ።

በሌላ በኩል በዘውግ የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ‹ኅብረ-ብሔራዊ የሚባል ፓርቲ የለም። ኅብረ-ብሔራዊ ነን ብለው የሚደራጁት የአንድ ብሔር ሰዎች እና የከተማ ሰዎች ብቻ ናቸው› ብለው በተቃራኒው ይከራከራሉ። ባለፈው የፓርላማ ዘመን በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ እና የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አባል የነበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ ይህንን አስመልክቶ “አንድነት ፓርቲ የሁሉም ቤት ይሁን ብለን ስንሠራ ትልቁ ተግዳሮት የሆነብን ብሔር ተኮር የሆነው አመለካከት የሚጎትታቸው ብዙ ሰዎች መኖራቸው ነው። ለምሳሌ አንዳንድ አባላት የብሔር ፖለቲካ ታማኝነታችን መድረክ [አሁን የብሔር ድርጅቶች ብቻ ስብስብ] ውስጥ በመቆየት የሚገለጽ የሚመስላቸው አሉ። አንድነት ፓርቲ ውስጥ አባል ሆነው የሚቆዩት ፓርቲው የመድረክ አባል ሆኖ እስከ ቆየ ድረስ እንደሆነ ቅድመ ሁኔታ አድርገው የሚያስቀምጡ አሉ። ኅብረ-ብሔር ነኝ ብሎ ተደራጅቶ ውስጣዊ ፍልስፍናው ዘውጋዊ የሚሆንበትም ጊዜ አለ” ብለዋል።

አቶ ልደቱ የአንድ ብሔር ሰዎች አንድ ድርጅት ውስጥ በዝተው ስለታዩ ፓርቲው ኅብረ-ብሔራዊ አይደለም አያሰኘውም። ይልቁንም “ፓርቲው የተደራጀበት አስተሳሰብ ነው ድርጅቱ ኅብረ-ብሔራዊ ነው አይደለም የሚለውን የሚወስነው” ይላሉ። ለምሳሌ ‹ኢዴፓ 46 በመቶ የሚሆኑት አባላቱ የደቡብ አካባቢ ሰዎች ናቸው› በማለት፣ ከአስተሳሰባቸው በተጨማሪ ኅብረ-ብሔራውያን ነን የሚሉት የአንድ አካባቢ ሰዎች ናቸው የሚባለው ሁሉ እውነት እንዳልሆነ ይከራከራሉ። አቶ ልደቱ “በተጨማሪም፣ አንዳንድ ጊዜ የመረጃ እጥረት ያለ ይመስለኛል” ይላሉ። “ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ ጠንካራዎቹ እነማን ናቸው የሚለው ላይ እስካሁን ድረስ በተካሄዱት ምርጫዎች ላይ የተገኙትን ድምፆች መለስ ብለን ብናየው፣ ብዙ ድምፅ ያገኙት የብሔር ድርጅቶች ሳይሆኑ ኅብረ-ብሔር ድርጅቶች ናቸው” ይላሉ።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ከዚህ የተለየ አመለካከት ነው ያላቸው። ኢ/ር ይልቃል “ኅብረ-ብሔራዊ” በሚለው አላምንም ይላሉ። እንደእርሳቸው ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን “ኅብረ-ብሔራዊ” ብሎ አይጠራም። “ምናልባት አንዳርጋቸው ጽጌ በሚጠቀምበት አማርኛ ‹ዘውግ-ዘለል› ብንለው ይሻል እንደሆን አላውቅም፤ ፓርቲዎች ወይ የዘውግ ፓርቲዎች ናቸው አለበለዚያ ደግሞ የርዕዮት-ዓለም ፓርቲዎች ናቸው ማለት ነው። በሐሳብ ደረጃ በዜግነት ላይ የተመሠረቱ ፓርቲዎች አሉ፤ አለበለዚያ ‹ኅብረ-ብሔር› የሚለው ቃል ራሱ የመጣው የአንድ ብሔር አደለንም ለማለት ነው እንጂ ዘውግን መሠረት አላደረጉም ማለት አይደለም” ይላሉ። ይሁን እንጂ ኢ/ር ይልቃል የዘውግ አደረጃጀት በቅርብ የሚያስተሳስሩ የወል ሥነ-ልቦና ስለሚኖሩት በፍጥነት የተወሰነ ጊዜ መዝለቅ የሚችል ድርጅት ለመፍጠር እንደሚጠቅምም አበክረው ይናገራሉ። ‹ዘውግ-ዘለል› የሆነ ተቋም ለመመሥረት ግን ጊዜ ስለሚወስድ በመሐል ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ም በቀላሉ መስበር የሚችልበት ዕድል ይኖረዋል፤ ሌሎችም ሁኔታዎች ይፈታተኑታል በማለት በርዕዮት-ዓለም የሚደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘውግ ከሚደራጁት ይልቅ ከፍተኛ ተግዳሮት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

አቶ ግርማ ሰይፉ በዘውግ መደራጀት “ግብ የለውም” ብለው ነው የሚያምኑት። “ሌላው ቀርቶ ብዙ ሕዝብ ያለው የኦሮሚያ ክልል ነው። ኦሮሚያ ክልልን መሠረት አድርገው የተደራጁት እንኳን አገር የማስተዳደር ግብ የላቸውም። ክልል ማስተዳደርን ግብ ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ይህ ግን ሰንካላ ግብ ነው። አገር የማስተዳደር ግብ ሊኖራቸው አይችልም። አገር ለመምራት ከፈለጉ ሌላ አንድ ድርጅት መፈለግ አለባቸው። አንድ ፓርቲ ሲቋቋም በራሱ መንግሥት ለመመሥረት እንዲችል ሆኖ መሆን አለበት።” በማለት መንግሥት ለመመሥረት ከሚያስችል ባነሰ አደረጃጀት የሚቋቋሙ ድርጅቶች ግብ የላቸውም በማለት አምርረው ይተቻሉ። “በደቡብ ክልል አንዳንዶች አንድ የፌዴራል ምክር ቤት መቀመጫ የሚያስገኝ የዘውግ አደረጃጀት ይዋቀራሉ፤” የሚሉት አቶ ግርማ “እነዚህኞቹ ድርጅቶች በክልል ምክር ቤትም ይሁን በፌዴራል ደረጃ ምንም ፋይዳ የላቸውም። ግብ የላቸውም” ብለዋል።

ዶ/ር መረራ ጉዲና በዚህ ዘውጋዊ አደረጃጀትን የማይቀበል አካሄድ አይስማሙም። “[በዘውግ መደራጀት በሌሎቹ አገራት] በሕግ ባይፈቀድም በተግባር ግን አለ፤ ኬንያን ለምሳሌ ብትወስድ ኪኩዩ ካልሆንክ ለፕሬዚዳንትነት ተወዳድረህ ማሸነፍ ያስቸግርሃል።… ለምሳሌ ኦዲንጋ እና ኡሁሩ ኬንያታ በምንም አይገናኙም። ኦዲንጋ በልምድም በዕውቀትም ይበልጠዋል። ኡሁሩ ያሸነፈው ኪኩዩ ስለሆነ ነው። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ዙማ ፕሬዚዳንት የሆነው ዙሉ ስለሆነ ነው እንጂ በመደበኛ ትምህርት እንኳን አልዘለቀም። እኔ የአፍሪካ ፖለቲካን እስካነበብኩ ድረስ ታንዛንያውያን ብቻ ነው ይሄ ነገር የሌለባቸው። እነሱም [የዘውግ] ቡድኖቻቸው ትንንሽ በመሆናቸው ነው። ይሄ ነገር የሚቀንሰው ካፒታሊስቶቹ ጋር ነው። እነሱ የሚደራጁት በጥቅም ፍልስፍና ነው። ነገር ግን በዘር መቧደን እዛም ይቀራል ማለት አይደለም። ለምሳሌ ጥቁር አሜሪካውያን 80 በመቶ ኦባማን ሲመርጡ እንደነበር ይታወቃል” ይላሉ። አያይዘውም አንድ ፓርቲ ኅብረ-ብሔራዊ ነኝ ስላለ ብቻ የብሔር መሠረት የለውም ማለት አይደለም በማለት መከልከሉ ምንም ዓይነት ውጤት ያመጣል ብለው እንደማያስቡ ይገልጻሉ።

ነገሩ መነሳቱ በአደረጃጀት ደረጃ ያለውን ግንዛቤ ያጠራዋል በሚል ሐሳብ እንጅ ገዥው ፓርቲ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ራሱ በዘውግ የተደራጀ ፓርቲ ሆኖና ሕግ የማውጣቱን ሒደትና መሣሪያ ሙሉ ለሙሉ ተቆጣትሮት ባለበት ሁኔታ የራሱን አደረጃጃች ሕገ ወጥ የሚያደርግ መመሪያ ያወጣል ብለን ማሰብ ቅዥት ነው የሚሆነው።

 

ቻው ቻው የፓርቲ ፖለቲካ?

አሁን አሁን በኢትዮጵያ የሠላማዊ የፖለቲካ መድረክ ላይ ለብዙ ዓመታት ተዋናይ የነበሩ ግለሰቦችን ጨምሮ በብዙዎች ዘንድ የፓርቲ ፖለቲካን በአሁኗ ኢትዮጵያ ማካሄድ አይቻልም የሚል ድምዳሜ ላይ ሲደርሱ ይታያል። ከእነዚህ የፓርቲ ፖለቲካ ተስፋ ከቆረጡ ግለሰቦች መካከል አቶ ግርማ ሰይፉ አንዱ ናቸው። አቶ ግርማ ‹ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን የሚያክል የሠላማዊ ትግል እክል ባለበት አገር ተቃዋሚዎችን ለመውቀስ የሞራል ብቃቱ የለኝም› ይላሉ። ለአቶ ግርማ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. በኢትዮጵያ ተወልዶ የነበረውን የፖለቲካ ፓርቲ ትግል ወደ መቃብር ሸኝቶታል የሚል እምነት አላቸው። ከዚህ በኋላ በፓርቲ ቁመና ተደራጅቶ ልታገል ማለት ተደራጅቶ ለኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. መመቸትና ለመጥፋት መንደርደርም ነው ብለው ያምናሉ። ከዚህም ተነስተው ከዚህ በኋላ አራማጅነትን (Activism) መሠረት ያደረጉ እንቅስቃሴዎች እንጅ የፓርቲ ፖለቲካ ለውጥ ያመጣል ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ። “አሁን ያለው የፓርቲ ፖለቲካና የእስካሁኑ ትግል እርሾ ሁኖ ይቀጥል በሚለው ሐሳብ አልስማም” የሚሉት አቶ ግርማ ነገሮችን በአዲስ አተያይና አዲስ አካሄድ ማስጀመር መልካም መሆኑን ይገልጻሉ።

 

“ተስፋ ብንቆርጥማ እዚህ ምን እንሠራለን?”

በታኅሣሥ 2001 የብዙ ግለሰቦችን ጥያቄ ይፈታል የተባለለት በኦሮሞ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እና የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ ፓርቲዎች ሁለት መሆናቸውን ትተው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦ.ፌ.ኮ.) በሚል አዲስ ስያሜ ተዋህደው አንድ ወደ እንቅስቃሴ መግባታቸው ለብዙዎች ተስፋ የሰጠ እርምጃ ነበር። ኦ.ፌ.ኮ. ከዛን ጊዜ ወዲህ ከሌሎች አራት ፓርቲዎች ጋር በመሆን ‹መድረክ› የተባለ ግንባር በመፍጠር እየተንቀሳቀሰም ይገኛል።

ኦ.ፌ.ኮ. በሐገሪቱ ውስጥ ካሉት ዘጠኝ የፌደራል ክልሎች መካከል በሕዝብ ብዛትና በቆዳ ስፋት ደረጃ ትልቁ በሆነው የኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው ብቸኛው ፓርቲ ነው ለማለት በሚያስችል መልኩ የሚገኝ ሲሆን፤ ፓርቲው የብዙዎችን ትኩረት የሚስበውም ከዚህ አቅሙ አንፃር ነው። ነገር ግን ባለፉት አምስት ወራት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከተካሔዱት ሕዝባዊ ተቃውሞች ጋር በተያያዘ የድርጅቱ ዋነኛ አመራሮች የታሰሩበት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በክልሉ ውስጥ በቡሌ ሆራ ከተማ የቀረች አንድ የፓርቲ ቢሮ ብቻ እንዳለችው የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በጥርጣሬ ይገልጻሉ። የድርጅቱ ሠላማዊ ታጋዮች ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. በክልሉ እየወሰደው ባለው ርምጃ ተጠቂዎች እንደሆኑ የገለጹት ዶ/ር መረራ የፓርቲያቸው ድል አድርገው የሚቆጥሩት “ሕዝቡን በተለያዩ መንገዶች አንቅተነው አሁን እኛ ባንኖርም መብቱን የሚያውቅና ለማስከበርም ቆርጦ የተነሳ ሕዝብ መፈጠሩ ነው” ይላሉ። ከዚህም ተነስተው “በፓርቲ ፖለቲካማ ተስፋ እንዴት እንቆርጣለን? ተስፋ የምንቆርጥ ከሆነማ እዚህ ምን እንሠራለን?” በማለት ተስፋ አስቆራጭ ነው ስለሚባለው የፖለቲካ ምኅዳር ላቀረብንላቸው ጥያቄ ምላሻቸውን ይሰጣሉ። “ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ከመቼውም ጊዜ በላይ የተዳከመው አሁን ነው” የሚሉት ዶ/ር መረራ “ኢሕአዴግ በ101 ችግሮች ተብትቦ ቢይዘንም አሁንም የሚሻለው ያሉብንን የመተባበር ችግሮች ተሻግረን ወደፊት መሄድ ነው” ይላሉ። መሪ የሚሆን ፓርቲ በሌለበት ሁኔታ ለውጥ እንኳን ቢመጣ በለውጥ ማግስት የሚፈጠረው ክፍተት የመረራ ስጋት ነው።

 

ፍሬውን ለማየት

በኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ እና የፖለቲካ ባሕል ውስጥ ተዘርዝረው የማያልቁ ችግሮች አሉ። ለችግሮቹ ተጠያቂ የሆኑ ዐብይ አካላት ቢኖሩም፣ ችግሮቹን ሁሉ ለአንድ ወገን ብቻ ጠቅልሎ መስጠት የትም እንደማያደርስ ከአጥኚዎች እስከ ፖለቲከኞች ድረስ ይስማማሉ።

አቶ ልደቱ አያሌው “ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዋነኛው ችግር ቢሆንም ብቸኛው አይደለም፤” ይላሉ። “ኢሕአዴግን የችግሩ አካል ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ የመፍትሔ አካል አድርጎ ማየት ያስፈልጋል። እስከዛሬ ድረስ የሚጠቆሙት መፍትሔዎች በሙሉ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. መቃብር ላይ ለማድረግ የሚታሰቡ መሆናቸው ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. በተፃራሪው እንዲሠራ አድርጎታል” ይላሉ። ስለዚህ ወደ መድብለ ፓርቲ የሚደረገው ጉዞ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን የችግሩ ብቻ ሳይሆን የመፍትሔው አካል ማድረግ አለበት። በሁለተኝነት፣ አቶ ልደቱ በተመሳሳይ መንገድ “ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመፍትሔው አካል ነን፤ ነገር ግን የችግሮቹም አካል እንደሆንን ማመን አለብን። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ውስጥ ያሉ ችግሮች በሙሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ውስጥም አሉ። ይህንን አምነን የተሻለ ሁነን ለመገኘት ራሳችንን የመገምገም እና ውስጣዊ ዴሞክራሲን ለመለማመድ መሥራት አለብን” ይላሉ።

ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው፣ “ችግር ስላለ ነው እዚህ ያለነው” በማለት ነው ነገሩን የሚያብራሩት። “ፓርቲ መመሥረት አንችልም፤ ማኅበረሰባችን ለድርጅት ግንባታ ገና ነው፤ አምባገነንም ድርጅቶች አማራጭ ሆነው እንዲያድጉ አይፈልግም፤ ይሄ ወደትግል የመጣንበት ምክንያት ነው። ስለዚህ… ወደትግል የመጣንበት ምክንያት ውጤት ሆኖ ከትግል ሊያስወጣን አያስፈልግም።… ሁሉ ነገር የተደላደለ ከሆነማ ቀድሞውን መምጣት አያስፈልገንም ነበር።” በማለት ችግሩ ስላለ ነው የገባንበት፣ ከውድቀቶቻችን እየተማርን እንቀጥላለን እንጂ ልንቀርፈው በገባነው ችግር ተገፍተን አንወጣም በማለት የፖለቲካ ትግሉ እስኪያፈራ ድረስ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ እንዲቀጥል ይመክራሉ።

አንጋው ተገኝ በሠላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለ ወጣት ነው። ፀጉሩን ያጎፍራል። ሲናገር በብዙ ነገሮች እየተደነቀ ነው። አንጋው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አብረሃ ጅራ ወረዳ ኃላፊ በመሆን እጅግ ፈታኝ ጊዜያትን አሳልፏል። የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የሀገሪቱ ክፍሎች መንቀሳቀስ የሚያስከፍለው ዋጋ ከባድ መሆኑን ደጋግሞ ይናገራል። የፓርቲው አመራር ሁኖ በሠራበት ወቅት ፓርቲ ስብሰባ እንኳን ማድረግ እጅግ ከባድ መሆኑን ያስታውሳል። ፖሊስና የደኅንነት ኃይሎች አመራሮቹን እየተከታተሉ ሲያስጨንቋቸው ‹የፓርቲው ሥራ ከሚቆም በሚል አንገረብ ወንዝ ወርደን እየዋኘን እንሰበሰብ ነበር› ይላል። እየዋኘን ሰው ወደኛ በመጣ ቁጥር እየተበታተንን፤ ሰው ራቅ ሲልልን ደግሞ እዛው ውኃው ውስጥ ሰብሰብ ብለን እየተንሳፈፍን ነበር ስብሰባ የምናደርገው የሚለው አንጋው በፓርቲ እንቅስቃሴ ምክንያት ስድስት ጊዜ ከሥራ ተባሮ ስድስት ጊዜ መመለሱን ሲገልጽ አንዳንዴ በሕይወት መቆየቴም ለኔ ግርም ይለኛል እያለ ነው። ይባስ ብሎ በሠላማዊ ትግል ቆርቦ በዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ የነበረው አንጋው ተገኝ የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ ሳይቀርብበት አሁን ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለህ በሚል ምክንያት በመጨረሻ ለእስር የተዳረገ ሲሆን፤ እስር ቤት ሁኖም የታገለለትና የደከመለት አንድነት ፓርቲ ሲፈርስና በእሱ አባባል ‹መፈንቅለ አመራር› ሲካሄድበት ተመልክቶ ያዝናል። ለዚህ ሁሉ መሆን አንጋው ተጠያቂ የሚያደርገው ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ነው። ‹ሕግ የማይገዛው መንግሥት› እያለ ሁሌም ይገረማል። ይህ የኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ችግር የገዥው ፓርቲ ቅጥ ማጣት ነው ከሚሉት ወገን የሚቀርበው ሐሳብ ትክክለኛ ተምሳሌት ነው።

ከዚህ አሳዛኝ ኹነት መለስ ብለን አርብ ሚያዚያ 28፣ 2008 ከጠዋቱ 4፡30 እስከ 5፡30 ድረስ በአንድ ሰዓት ውስጥ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጆች ለጽሑፉ ግብዓት የሚሆን መረጃ ለማግኘት በማሰብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ መሠረት እንዲሁ አለፍ አለፍ እያልን በአሁኑ ወቅት በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ከሚገኙ ሰባ አምስት ፓርቲዎች መካከል የሃያ አምስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የስልክ አድራሻ ላይ ስልክ የደወልን ሲሆን፤ ከሃያ አምስቱ ሙከራዎች መካከል ሁለቱን ስልኮች ያነሱልን ሕፃናት ሲሆኑ፣ የሰባቱ ስልክ ቢጠራም አይነሳም፤ የዐሥራ አምስቱ ስልክ ደግሞ ከነአካቴው የማይሠራ ሲሆን፤ የአንዱ ብቻ ማለትም ‘የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት’ ስልክ ላይ የፓርቲውን አመራር ልናገኝ ችለናል። በተመሳሳይ ጊዜ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያደረግነው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪም ስልኩ ሊነሳ ባለመቻሉ ማብራሪያ ማግኝት አልቻልንም። እንግዲህ ‹የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ ሰሞን ግርግር ከመፍጠር ያለፈ ምንም አይፈይዱም የሚለው ሐሳብ እንዲሁ ያለውን ሁኔታ ቀረብ ብሎ ካለማየት የሚመጣ ነው› የሚሉ ተችዎችም ሁሌም የሚፈተኑበት ጉዳይም ይሄው ተቃዋሚ ፓርቲ ተብለው የተመዘገቡት ፓርቲዎች በሚገባቸው ቦታ አለመዋላቸው ነው። ፓርቲዎቹ የስልክ እንኳን አድራሻ የሌላቸው/ቢኖራቸው እንኳን የማይሠሩ ስልኮችን ይዘው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የለውጥ መሠረት ይሆናሉ ብሎ ማሰቡንም ያከብደዋል። ይህ ደግሞ ተቃዋሚዎች የራሳቸው ሥራ ሳይሠሩ ገዥውን ፓርቲ ማውገዛቸው ተገቢ አይደለም የሚለው ሐሳብ ተምሳሌት ነው።

 

ይህ ጽሑፍ በሃገር ቤት ታትሞ በወጣው ውይይት መጽሄት ላይ የወጣ ነው:: በሃገር ቤት ያላችሁ መጽሄቱን ገዝታችሁ በማንበብ ጋዜጠኞቹን አበረታቷቸው::

መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብሎ ሞተ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

መስፍን ወልደ ማርያም
Pro-Mesfin1.jpg
መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፣ ይቅናችሁ ማለት ነው፤ ለልማት ለሚሰማሩ ሰዎች ምርቃት ይሆናል፤ ለጥፋት ለሚሰማሩ ሰዎች እርግማን ነው፤ እርግማን ብቻም አይደለም፤ የጥፋት ምኞትም ነው፤ ሰዎች ለጦርነት ሲዘጋጁ፣ ሰዎች ሌሎች ሰዎችን ለመግደል ሲሰናዱ፣ ሰዎች እርስበርሳቸው ለመገዳደል ጦራቸውን ሲስሉ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ማለት ከጀግና አንደበት የሚወጣ አይደለም፤ ብዙ ሰዎች ለእንጀራ ብለው ሕይወታቸውን ወደአጥርነት ለውጠው ሕይወቱን የሚጠብቁለት ሰው ጦር ቢወረወር አይደርስብኝም ብሎ ሌሎችን ለሞት ቢዳርግ አይደንቅም ይሆናል፤ አጥሩን ጥሶ ወደሱ የሚገሰግስ ሞት ሲያይ ቢፈረጥጥም አያስደንቅም፤ ሆኖም የሞት መንገድ ከጎን ብቻ ሳይሆን ከላይም ሊሆን እንደሚችል አለማወቁ ቀላል አለማወቅ አይባልም፡፡

ባህላችን ገዳይን የምናከብር፣ ለገዳይ የምንዘፍን ሕዝብ ቢያደርገንም፣ በድንቁርና ዘመን የነበረውን ይዘን ዛሬ ትንፋሽ የማትችለዋ ቢምቢ ሰውን መግደል እንደምትችል እያወቅን ለገዳይ ብንዘፍን ለሰውነታችን ውርደት ይሆናል፤ ይህንን ብለን ጉዳዩን እንዳንዘጋው በመግደል ልቡ የደነደነ፣ በድን ያልሆነለትን ሁሉ መግደል ልማዱ የሆነ፣ ከመግደል በቀር እምነቱን የሚገልጽበት መንገድ የሌለው፣ ከመግደል ሌላ እንጀራ የሚበላበት ሙያ የሌለው … እንዲህ ያሉ ሰዎች ሁሉ ተሰባስበው መገዳደልን የኑሮአቸው ዓላማና ዘዴ ሲያደርጉ በዝምታ መቀበል፣ ማለት አባቱ ሲገደል ልጁ ዝም ሲል፣ ባልዋ ሲገደል ሚስት ዝም ስትል፣ … ማንም ሰው አለፍርድ ሲጠቃ እያዩ ዝም ማለት ገዳዮችን ያራባል እንጂ ግድያን አያቆምም፤ እንዲህ ያለው በመንፈስ የሞቱ የበድኖች ዓለም ነው፤ በአውሬዎች ዓለም ጉልበት ያለው ደካማውን እየበላ ይኖራል፤ የተፈጥሮ ሕግ ነው፤ የሰው ልጅ በዚህ በአውሬዎች የተፈጥሮ ሕግ አይመራም፡፡

የሰው ልጅ በተፈጥሮ ሕግ የማይመራበት ምክንያት ምንድን ነው? አውሬዎች አያስቡም፤ የሰው ልጅ ግን ያስባል፤ የሰው ልጅ አእምሮ አለው፤ አእምሮ ስላለው ያስባል፤ ያስባል ማለት ከተግባር በፊት ትክክለኛውንና ስሕተት ያለበትን ለይቶ ያውቃል፤ ይህ የተፈጥሮ ሕግ አይደለም፤ የሰው ልጅ ሕግ ነው፤ ያሰበውንም ይናገራል፤ የሚወደውንና የሚጠላውን ስሜቱን ለይቶ ይናገራል፤ የሰው ልጅ ኅሊናም አለው፤ ‹‹ሌሎች ለአንተ እንዲያደርጉልህ የምትፈልገውን አንተም ለሌሎች አድርግ!›› ይላል፤ ይህ የተፈጥሮ ሕግ አይደለም፤ የሰው ሕግ ነው፤ ስለዚህም መግደል፣ በተለይም የመግደል ሱስ፣ የአራዊት እንጂ የሰው ልጅ የችግር መፍቻ ዘዴ አይደለም፤ አራዊት የሚገድሉት ሊበሉ ነው፤ ሰውም ወደአራዊትነት ሲለወጥ የሚገድለው ሊበላ ነው፤ እዚህ ላይ ሰውና አራዊት ይመሳሰላሉ፡፡

በመሠረቱ የመግደል ዓላማ ዝም ለማሰኘት ነው፤ ድንቁርና ነው እንጂ ካፍ ከወጣ አፋፍ ነውና የሚጠሉት ሀሳብ በሌላ ሰው አንደበት ይደገማል፤ መግደል የመጨረሻውን ዝምታ የሚያስከትል ቢሆን ክርስትናም እስልምናም 2007 ዓ.ም. አይደርሱም ነበር፤ ገዳዮች ሰዎችን ሁሉ ጨርሰው ብቻቸውን በመቅረት የሚያገኙት ጥቅም እንደሌለ ስለሚያውቁ የመግደል አማራጮች በሆኑ ሌሎች ዘዴዎች ይጠቀማሉ፤ አንዱ ማሰቃየት ነው፤ ሌላው ማሰር ነው፡፡

ሰዎችን በሀሳብና በእምነት ገባር ለማድረግ ጉልበተኞች የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች መግደል፣ መግደል አላዋጣ ሲል ማሰቃየት፣ ማሰቃየት አላዋጣ ሲል ማሰር፣ ማሰር አላዋጣ ሲል አስሮ ማሰቃየት ነው፡፡

አውሬነትን የተላበሱ ሰዎች የማይገባቸው አንድ ነገር አለ፤ የሚጠሉትና ሰዎችን እስከመግደል፣ እስከማሰርና ማሰቃየት የሚያደርሳቸው ነገር በውስጣቸው ተቀብሮ አለ፤ ነፍሳቸው ከዚያ ነገር ጋር ተቆራኝታለች፤ በመጨረሻም የሚሸነፉት በዚያው ነፍሳቸው ውስጥ በተቀበረው ነገር ነው፤ በውስጣቸው የተቀበረው ነገር አስገድሎ አስገድሎ በመጨረሻ ይገድላቸዋል፤ ጥላቻም አስገድሎ አስገድሎ ይገድላል! በጥላቻና በመጋደል ሰላም አይገኝም፤ ‹‹ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል እግዚአብሔር!›› (ኢሳይያስ 48/22)

መንገዱን ጨርቅ ያድርግልን! ለሰላም!
መንገዱን ጨርቅ ያድርግልን! ንስሐ ለመግባት!
መንገዱን ጨርቅ ያድርግልን! ይቅር ለእግዚአብሔር ለመባባል!

የዛሬ ዕብሪተኞች የሙሶሊኒን (ተዘቅዝቆ የተሰቀለውን)ና የጋዳፊን ቦይ ውስጥ ተወትፎ የተገኘውን አስበው ልባቸውን ለምሕረትና ለእርቅ እንዲከፍቱና ለልጆቻቸው የፍቅርና የመተማመን ዘመን እንዲያውጁ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ወኔ ይስጣቸው፡፡

ተጠራጣሪነት ለኛ ለኢትዮጵያዊያኖች አዲስ ነገር ነው እንዴ?

nega

(ሄኖክ የሺጥላ)

አርበኛ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ሰሞኑን በሲያትል ተገኝተው ያሰሙትን ቅንጭብ ( ወይም ጭላጭ) መልዕክት አደመጥኩ። የንግግራቸው አንኳር ሃሳብ ይሁን አይሁን ወደፊት የምገነዘበው ጉዳይ ቢሆንም ፥ ስለ ተጠራጣሪነት በጣም በግርድፉ እና በጨረፍታ « ከአንድ ኢኮኖሚስት የሚጠበቅ ነው » አንስተው ያልፋሉ ። በዚህ ንግግራቸው ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠራጣሪነት የገረማቸው ይመስላል ። በእውነት ተገርመው ከሆነ ፥ እኔ ደሞ መገረማቸው የምር ሊገርመኝ ይችላል ። ምክንያቴን እንደሚከተለው አቀርባለሁ ።

ተጠራጣሪነት ለኛ ለኢትዮጵያዊያን አዲስ ግኝት አይደለም ። ቀደም ባሉት ዘመናት ለምሳሌ የዘመነ መሳፍንት ግብዓተ መሬት ከተፈጠመ ብኋላ ፥ በአፄ ቴዎድሮስ አማካኝነት ፥ ሃጋሪቱን ወደ ተማከለ እና ጠንካራ አስተዳደር ለማምጣት ሲባል ዘመናዊ ስልጣኔን ከ ኣውሮጳ ለማስገባት ንጉሱ ያደረጉትን ጥረት ፥ በንጉሱ አካባቢ ያሉ የቅርብ ረዳቶቻቸው እና ባለ ሟሎቻቸው ይኽን ጉዳይ ሃገርን ለባዕዳን የመክፈት ጉዳይ እንደሆነ አድርገው ወስደውት ነበር ። የንጉስን አስተሳሰብ « ታሪክን እና በህልን የሚመርዝ ፥ ሃይማኖትን የሚቀይጥ ፥ እና የሚለውጥ ፥ ሃገሪቱን ለውጭ ሃይሎች ( ባዕዳን ) ክፍት የሚያደርግ አካሄድ ስለሆነ ፥ ይህን ከውጭ ሃገራት ጋ ሊደረግ የታሰበውን የዕውቀት ልውውጥ እንዳይፈጠም ለማድረግ የሞከሩ ጥቂቶች አልነበሩም ። ምንም የማያውቁትን እና ለአንድ ቀን እንኳን ያልሰሙትን አካል አጥፊ ብሎ መፈረጅ ከልክ ያለፈ የተጠራጣሪነት መንፈስ ውጭ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል ?

በአጤ ሚኒሊክ ዘመንም ጊዜ ይሄው የጥርጣሬ ማዕበል ነገስታቱን እና መነኩሳቱን ያሰመጠ እና የዋጠ ታሪክ ስለመሆኑ ተጥፎ እናያለን ። በይበልጥ አጤ ምኒሊክ ከአድዋ ድል ማግስት ፥ ከውጭ መንግስታት ጋ በመገናኘት ሃገራቸውን በእድገት ጎዳና ለመምራት ማቀዳቸውን ለካህናቱ እና «መሳፍንቱ» ሲያስረዱ ፥ ካህናቱ « እንደነሱ የጠራ መሳሪያ ባይኖረንም ፥ ጠላቶቻችንን የኢትዮጵያ አምላክ ድል ስለሚያደርግልን ፥ ከነሱ ጋ ይየምናደርገው ትውውቅ እና ትስስር ቢቆም ይሻላል » እያሉ ይመክሯቸው ነበር ። ይህ የተጠራጣሪነታችን አንዱ ማሳያ ነው ።

«በመሳፍንቱ እና መኳንንቱ» ፥ ብሎም በካህናቱ ቁጥጥር ስር የነበረው ማህበረሰብ የሚያሳየው ወግን የማጥበቅ ስርዓት እና ነገሮቹን ሁሉ በጥርጣሬ አይን የማየት እውነታ ፥ ስልጣኔን ለመቀበል ፥ ወደፊት ለመራመድ እና ካደጉት ከተፈሩት እና ከተከበሩት ሃገሮች ተርታ ለመቆም የሚደረገውን ጉዞ እጅግ አዳጋች ብቻ ሳይሆን የማይቻል አድርጎት ነበር ። ዛሬም ከዚያ የተለየ ነገር ያለ አይመስለኝም። የስልክ መምጣት ፥ የባቡር መንገድ መዘርጋት እና መሰል ነገሮች በህዝቡ ዘንድ የፈጠረው ከፍተኛ ጥርጣሬ ወደር የሌለው እንደነበረ አሁንም የታሪክ መዘክሮች ይዘግባሉ ። ወመዘክሩ በኪሉ ባይሸጥ ኖሮ መጥሃፍ በጠቆምኳችሁ ።

ንጉስን የሾመው እግዚያብሄር ነው ብሎ የሚያምን ማህበረሰብ ፥ እንደ አፈ ወርቅ ገብረየሱስ አይነት ተራማጅ አስተሳሰብ ፥ እንደ ነጋድራስ ገብርህይወት ባይከዳኝ አይነት ባለ ሰላ ብዕር ፥ እንደ አለቃ ታዬ ያሉትን ባለ ተራራ መስተሃልይ ግለሰቦች ያቀርቡት የነበረው የህብረተሰቡን ስር የሰደደ የተጠራጣሪነት መንፈስ ፥ የካህናቱን በአንድ አይነት አስተሳሰብ ላይ ተተክሎ መቆም እና አደጋውን መተቸት ራሱ በህብረተሰቡ ዘንድ መማሪያ ከመሆን ይልቅ እነዚህ ምሁራኖችንም ፈርጆ በተመሳሳይ የጥርጣሬ ኮሮጆ ውስጥ ከቶ የነጮች ( የባዕዳን ቅጥረኞች ) ፥ ሃገራቸውን ለማጥፋት የሚያሴሩ የውጭ ሃገራት ተላላኪዎች ተደርገው ይታዩ ነበር ። ምክንያቱ ደም ምንም አይደለም፥ ያው ጥርጣሬ እንጂ !

ጥርጣሬ እና ተጠራጣሪነት ለኛ ለኢትዮጵያዊያኖች በእርግጥ አዲስ ነገር አይደለም ። ድክመታችንን በተራ አሉባልታ ፥ ውድቀታችንን በማጥላላት ፥ ሽንፈታችንን በጥርጣሬ ፥ አለመቻላችንን በእምነታችን እያሳበብን የኖርን ህዝቦች ስለመሆናችን ከበቂ በላይ ማስረጃም መረጃም አለን ። በታሪካችን መስራት መቻል የሚያስቀቅስ ፥ አፈድፋጅነት የሚያስሞግስ እንደነበር የታወቀን ነው ። ብረት ሰሪውን ጠይብ ፥ጠሃፊውን ጠንቋይ ፥ ሸማ ሰርቶ እራቁት ከመሄድ ቢታደግ ሸማኔ እና ቡዳ ፥ ቤተክርስቲያን ቢያገለግል ደብተራ ፥ ብረት ቢያቀልጥ ባለ እጅ ፥ ሸክላ ቢጠፈጥፍ ሟርተኛ ፥ ሬሳ ገልባጭ እና ወዘተ እያልን እያንዳንዱን መልካም ነገር ስንጠራጠር የኖርን ስለመሆናችን ከማንም የተደበቀ አይደለም ።

ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል ( ብላቴን ጌታ ) ፥ ዝክረ ነገር በተባለው ሁለተኛ መጥሃፋቸው ፥ አጤ ሚኒሊክ ራሳቸው በዚህ ህብረተሰብ ከልክ ያለፈ የመጠራጠር አባዜ ተቆጥተው በ ጥር 17 ቀን 1900 ዓ.ም የሚከተለውን አዋጅ አውጀው እንደነበር ከትበውልናል

” ሰራተኛውን በስራው የምትሰድብብኝ ተወኝ ። ከዚህ ቀደም ብረት ቢሰራ ጠይብ ፥ ሸማ ቢሰራ ሸማኔ ፥ ቢፅፍ ጠንቋይ ፥ ቤተስኪያን ቢያገለግል ደብተራ ፥ እያላችሁ አርሶ ነጩን ከጥቁር አምርቶ የሚያገባውን አራሽ ፥ ከዘውድ ይበልጣል የሚባለውን ገበሬ እያላችሁ ፥ ነጋዴ ነግዶ ወርቁን ግምጃውን ይዞ ሲገባ አንተ ነጋዴ ገጣባ ( ያህያ ፥ የበቅሎ የፈረስ አጣቢ )፥ እያላችሁ በየስራው ሁሉ ትሳደባላችሁ ። እጁ ምናምን ስራ የማያውቀው ሰነፉ ብልኹን እየሰደበ አስቸገረ ። ” እያሉ ይገልጡና ይህንን ሁሉ ለማስቆም ” ዳግመኛ ሲሳደብ የተገኘ መቀጫው አንድ አመት ይሆናል !” ። ይላሉ ።

ጥርጣሬ የማንነታችን አካል ነው ። እስከ አሁን ማሸነፍ ያቃተን ከነፃነት በላይ ለትግላችን ማነቆ ፥ ለመንገዳችን እሾህ የሆነ ።

ሌላ ምሳሌ ልጥቀስ
ተፈሪ መኮንን ( ግርማዊ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ በወቅቱ ራስ ተፈሪ ) የሲኒማ ቤትን ሲያስተዋውቁ ፥ ህብረተሰቡ በጥርጣሬ ነበር የተቀበለው ። ለዚህም የሰይጣን ቤት የሚል ስም ሰጥቶታል ። የድሃ ልጆችን ሰብስበው ሲያስተምሩ ፥ ትምህርቱን በጥርጣሪ ያዩት መሳፍንቱ እና መኳንንቱ ንጉሱ ለድሃ ልጆች ደብተር እና እስክርቢቶ ገዝቶ ማስተማር በመወሰናቸው ተቃውመው ለንግስት ዘውዲቱ አቤቱታ አቅርበው ነበር ። ምክንያታቸው ደሞ የባዕዳን ትምህርትን ልጆቻችን ሊማሩብን ነው የሚል መሰረት የሌለው ጥርጣሬ ነበር ። የ ዘውዴ ረታን ( የቀዳማዊ ሃይለስላሴ መንግስት) መጥሃፍ ማንበብ የተሻለ ነገሩን ለመረዳት ይጠቅማችኋል።

ሌላ ምሳሌ ልጥቀስ ( እየሰማሁ ሳይሆን እያየሁ ካደግሁት )

እናቶቻችን ጠላ ከቀዱ በኋላ ካናቱ የሚቀምሱት ነገር ምንጩ ባህል ሳይሆን የተጠራጣሪ ካቲካለኛ መንፈስ ለማረጋጋት የሚደረግ ጥረት እንደሆነ በጥናትም ፥ በንባብም ፥ በመኖርም ያገኘኋቸው መረጃዎች ያስረዳሉ ። በቀደመው ዘመን ደብተራዎች ፥ አፈ ሹሞች ፥ ከፍ ሲልም የንጉሱ ባለ ሟሎች እና ካህናቶቹ የሚጠፋፉበት አንዱ መንገድ የተመረዘ መጠጥ እንደሆነ መዛግብት ይናገራሉ ። ይኽም ታሪክ የጥርጣሬ መንፈስን በተዋረድ የመንደር ካቲካላ መሸጫ ድረስ ይዞት ተመመ ። ዛሬም ድረስ ታዲያ ፥ አንድ ሰባራ ስልጣንም ይሁን ድንቡሉ ሳንቲም የሌለው ሰካራም ጠላ ቤት ገብቶ የሚያዘውን አንድ ጣሳ ጠላ አስቀምሶ ( ወይም እመነኝ መርዝ የለውም ) ተብሎ እንደሚጠጣ እናውቃለን ።

አክሱምን እና ፋሲልን የመገንባት ባህላችን ሳይሆን ጠላ አስቀምሶ የመጠጣት ባህላችን ዘመን የተሻገረበትም ዋናው ምክንያት ከእድገት እና ለውጥ ይልቅ ለተጠራጣሪነት የቀረብን ህዝቦች ስለሆነንን ይመስለኛል ። አዎ ተጠራጣሪነት ለኛ ለኢትዮጵያዊያኖች አዲስ ነገር አይደለም !

የሚዲያና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በኢሕአዴግ ላይ የሰላ ትችት አቀረቡ

‹‹ሙስና የሥርዓቱ ባህል እየሆነ መጥቷል›› በማለት ኢሕአዴግ ላይ የሰላ ትችት ያቀረቡት የሚዲያና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ባለፉት 25 ዓመታት ሙሉ የሚወራው ስለሙስና መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Bribeባለፈው ዓርብ ግንቦት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. 25ኛውን ዓመት የግንቦት 20 የብር ኢዮቤልዮ በዓል አስመልክቶ ከጋዜጠኞችና ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር በብሔራዊ ቴአትር በተደረገው ውይይት፣ ተሳታፊዎቹ ኢሕአዴግንና እሱን የሚመራው መንግሥትን ገምግመዋል፡፡ ድርጅቱ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ስለሙስና፣ ስለኪራይ ሰብሳቢነትና በሥልጣን ስለመባለግ ቢወራም ተመጣጣኝ ዕርምጃ ሲወሰድ አልታየም በማለት ክፉኛ ተችተዋል፡፡

ለውይይቱ መነሻ የሚሆን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬሕይወት አያሌው የግምገማ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት ይደበቃል፡፡ ሕዝቡ ግልጽ ሆኖለት ከተታገለው ግን እታች ተወርዶ ማቃጠል ይቻላል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ይህች አገር ፈርሳ ነው እየተሠራች ያለችው፡፡ እስካሁን ያስመዘገብናቸው ድሎችም ሊፈርሱ ይችላሉ፤›› በማለት ነበር የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋን አስመልክተው በሰጡት ሐሳብ ጽሑፋቸውን የደመደሙት፡፡ ‹‹ኢሕአዴግ ፈተናው ትልቅ ነው ይላል፡፡ አይደለም ድልን ልናስመዘግብ ያረጋገጥነውም ሊበላብን ይችላል፣ ወደኋላ ሊወረውረንም ይችላል፤›› በማለት፡፡

ውይይቱን የመሩት የብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ኃላፊ አቶ ዘርአይ አስገዶም መድረኩን ለተሳታፊዎች ክፍት ሲያደርጉ አንዳንድ አድናቆቶች የቀረቡ ቢሆንም፣ በአብዛኛው የትችት ሐሳቦች ተንፀባርቀዋል፡፡

አቶ እንድርያስ ተረፈ አስተያየት ከሰጡት መካከል የመጀመርያው ናቸው፡፡ ‹‹ኢሕአዴግ ወደ አዲስ አበባ ሲገባ ‘ሌባ አይወድም’ ይባል ነበር፡፡ ዛሬ ግን ራሱ ኢሕአዴግ ሌብነት መገለጫው እየሆነ መጥቷል፡፡ 25 ዓመት ሙሉ የምናወራው ስለሙስና ነው፡፡ ሌብነት የሥርዓቱ ባህል እስከመሆን ደርሷል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹መኖር ከአቅም በላይ በሆነበት ዘመን ዛሬም የምናወራው ስለሙስና ነው፡፡ ከ25 ዓመት በኋላ ዛሬ ምን ተለወጠ? ምን አገኘንና በምን እንለካው?›› በማለት አክለዋል፡፡

‹‹ቤት አገኛለሁ ብዬ ኮንዶሚኒየም የተመዘገብኩት 97 ላይ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ቤቶቹ ጠፉ እየተባሉ ነው፡፡ አንድ ሕንፃ ሲጠፋ ማን ተጠየቀ? ሕንፃዎቹ እስኪጠፉ መንግሥት የት ነበር?›› ብለዋል፡፡

የኪነጥበብ ባለሙያው አቶ ኃይላይ ታደሰ በበኩላቸው የቀረበው ሪፖርት ወደ ጥንካሬው ያመዘነ መሆኑን ገልጸው ነበር ትችታቸውን ያቀረቡት፡፡ ‹‹እንደ ባለሙያዎች እምብዛም ተጠቃሚ አይደለንም፡፡ አንቀጽ 29 ላይ የተቀመጡ መብቶችን እንዳንጠቀም የሚያግዱ አፋኝ ደንቦች እየተረቀቁ ይገኛሉ፡፡ ይኼ ከሴንሰርሺፕ (ሳንሱር) ተለይቶ የሚታይ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

አቶ ኃይላይ ትችታቸውን በመቀጠል፣ ‹‹ኢሕአዴግ ከአፄ ኃይለ ሥላሴና ከደርግ ጋር ራሱን እያወዳደረ ዕድገት አስመዘገብኩ ሲለኝ ያንስብኛል፣ ይወርድብኛል፤›› በማለት ድርጅቱ እንደ መንግሥት በራሱ ከያዘው ዕቅድ አንፃር፣ ከሰፊው ሕዝብ ተጠቃሚነት አንፃር መመዘን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

‹‹ስብሰባና በዓል ታበዛላችሁ፡፡ ይኼ ሁሉ የተከፈለው መስዋዕትነት በተግባር ቢለካ አንድ ሰው ሌባ ከሆነ ሌብነቱን በሕዝብ ፊት አጋልጡት፡፡ አለበለዚያ ቁርጠኝነቱ ያላችሁ አይመስለንም፡፡ ከአንድ ቦታ አንስታችሁ ሌላ ቦታ ትሾሙታላችሁ፡፡ ለእኔ ቀልድ ነው የሚመስለኝ፡፡ ተግባብቶ ለውጥ የሚያመጣ ተግባር እያካሄዳችሁ አይመስለኝም፤›› በማለት ቀጥለዋል፡፡

‹‹አንድ ለልማት ተነሽ የሆነ አካባቢ ስታፈርሱትና ስታነሱት በጣም ነው የምትጣደፉት፡፡ አጥራችሁ ስታስቀምጡ ግን ረዥም ጊዜ ነው፡፡ አራት ከንቲባዎች ሲቀያየሩ ታጥሮ የተቀመጠ ቦታ የለም ወይ?›› በማለት የፍትሕ ማጣትና ሌሎች ማሳያዎችንም አቅርበዋል፡፡

ሕዝቡ የዕድገቱ ተጠቃሚ አለመሆኑንና ከአቅሙ በላይ በኑሮ እየተሰቃየ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ ‹‹ዕድገቱ ጤነኛ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ጥቂት ከጉምሩክና ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር የሚመሳጠሩ ዜጎች ያገኙትና የተሠሩ ነገሮች እንደ ዕድገት ከተለኩ እኔ ትክክል አይመስለኝም፡፡ የሕዝቡ ቁጥር መጨመርና ዘመኑ የደረሰበት ቴክኖሎጂ መለኪያው ያ ከሆነ አይገባኝም፤›› በማለት መንግሥት ባልተሠሩ ነገሮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲንቀሳቀስ አሳስበዋል፡፡ ‹‹ችግሮቹ ያመዝናሉ፤›› በማለት፡፡

‹‹ሥርዓቱ ውስጥ በተደራጀ በቡድን አንዱ ሌላውን የሚጠልፍበት ሁኔታ የለም? ከሕዝብ የተደበቀ ነው? አይመስለኝም፡፡ ራሳችሁን ፈትሹ፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነትን የፈጠራችሁት እናንተ ናችሁ፡፡ ከሕዝብ የተደበቀ ነገር የለም፡፡ የክፍለ ከተማ ሹማምንቶች ቪ-8 አይደለም የሚያሽከረክሩት? ቪ-8 የሚነዳባት አገር ናት እንዴ ይህች አገር? ታክስ አልከፈልክም ተብሎ ግን ዘብጥያ ይወርዳል፤›› በማለት አስተያየታቸውን የቀጠሉት አቶ ኃይላይ፣ ‹‹ትግሉን ረስታችሁታል፡፡ ከተከፈለው መስዋዕትነት አንፃር ያማል፡፡ ስለዚህ የዚች 25 ዓመታት ስኬት እንደ ትምክህት እንድትወስዷት አልፈቅድም፡፡ መውደቂያችሁ እሱ ነው የሚመስለኝ፡፡ በ1993 ዓ.ም. ታደስን ትላላችሁ፡፡ እሱ ህዳሴ አልነበረም፡፡ መታደስ ያለባችሁ ዛሬ ነው፤›› በማለት ሐሳባቸውን ቀጠሉ፡፡

የመድረክ መሪዎችም ተሳታፊዎችም በፅሞና እያዳመጡ ነው፡፡ አቶ ኃይላይ ግን ትችታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ‹‹ለምሳሌ ያ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለበት አካባቢ ምን ይመስላል? ዛሬ ከማንም የተደበቀ አይደለም፤›› በማለት አንዳንድ የትግራይ ክልል አካባቢዎችን በመጥቀስ በትግል ጊዜ የተጠቀሙበት መንገድ ባለበትና አህያም ተጭና የማትሄድበት ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሌላው አስተያየት ሰጪ የዓባይ ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ሲሆን፣ ውይይቱ እንደተለመደው የፕሮግራም ማሟያ እንዳይሆን ሥጋቱን ገልጾ አስተያየቱን ጀመረ፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት የተሠሩ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ገልጾ፣ ‹‹የተሠሩ ትልልቅ ነገሮችን የሚሸፍኑ የማይረቡ ትንንሽ ስህተቶች ትሠራላችሁ፤›› ሲል በሕዝቡና በመንግሥት በኩል አሉ ያላቸውን ችግሮች ተናግረዋል፡፡ ‹‹በአሁኑ ጊዜ ወረዳዎችና ቀበሌዎች እኮ ትልልቅ መንግሥታት ናቸው፤›› በማለት የተዘረጋው ሥርዓት ለሌብነትና ለስርቆት የተመቸ መሆኑን ተናግሯል፡፡

በጋዜጠኛው ሌባ ለማስያዝ የሚደረግ ጥረት እንደማይሳካና ፍርድ ቤት ተሂዶም ፍትሕ እንደማይገኝ ገልጾ፣ ‹‹እንዲያው ሳስበው ዛሬ ፍትሕ ያለው በኢቢሲ የሚተላለፈው ‹‹ችሎት›› ፕሮግራም ላይ ብቻ ነው፤›› በማለት ተሰብሳቢዎችን ፈገግ አሰኝቷል፡፡ ‹‹ትልቅ ስህተት የምለው፣ የኢሕአዴግ ትልቅ ስህተት የምለው የቀበሌና የወረዳ አስተዳደሮች የፓርቲው አባል በመሆናቸው ነው፡፡ ከአንድ ቦታ በሌብነት የተባረረ ሌላ ቦታ ተቀይሮ ተሹሞ እናገኘዋለን፡፡ ደንበኛ የአሠራረቅ ልምድ ይዞ ሄዷል፡፡ እዚህ ቀበሌ ሌባ የነበረ ሰው እዚያ ሲሄድ ወንበዴ ይሆናል፡፡ ማንም የማይመልሰው ወንበዴ፡፡ ከዚህ በኋላ ያፈጠጡ ሌቦች እንዲሆኑ እያደረጋችኋቸው ነው፡፡ የፓርቲ አባል ስለሆኑ፡፡ በእኔ እምነት ይኼ ሁሉ የፓርቲ አባል አያስፈልጋችሁም፡፡ የፓርቲ ቁጥር አይደለም ሥራ የሚሠራው፡፡ አስተሳሰቡ ያልተለወጠ ሰው ለውጥ አያመጣም፤›› በማለት አንድ ምሳሌ አነሳ፡፡

‹‹በሌላ እንዳይያዝብኝ ስለፓርቲ አይደለም እያወራሁ ያለሁት፤›› በማለት ቀጥሎ ያቀረበው ምሳሌ በ1997 ዓ.ም. ምርጫ ቀንደኛ የቅንጅት ደጋፊ የነበረ ሰው፣ የኢሕአዴግ ደጋፊ ናቸው ብሎ ያሰባቸው ብዙ ሰዎችን ጉዳት እንዳደረሰባቸው ተናግሯል፡፡ ‹‹አሁን ብትሄዱ ወረዳውን አልነግራችሁም ራሳችሁ ድረሱበት፤›› ካለ በኋላ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ የአንድ ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ እንደሆነ በመግለጽ፣ ‹‹ያን ጊዜ ያላዳረሳቸውን አሁን ለማዳረስ እንዲመቸው ይሁን እኔ አልገባኝም፡፡ ይኼ ሰው በሌላ ማልያ እንዲጫወት ተፈቅዶለታል፡፡ በትክክል ሥራቸውን ሲሠሩ የነበሩ ሰዎች ደግሞ ችግር ደርሶባቸው ሌላ ችግር ላይ የወደቁ አሉ፤›› በማለት እንዲህ ዓይነት ችግሮች እንዲስተካከሉ አሳስቧል፡፡

እንደ ጋዜጠኛ በ2004 ዓ.ም. ተንዳሆ መሄዱን አስታውሶ ቦታው ላይ የነበረው ሥራ የሚያስደስት እንደነበር ይናገራል፡፡ ‹‹25 ሺሕ ቶን ስኳር ማምረት ይችል ነበር፡፡ በአፍሪካ ሁለተኛ መሆን ይችል ነበር፡፡ ያኔ መጠናቀቅ ነበረበት፡፡ ዛሬም ድረስ ግን አልተጠናቀቀም፡፡ ስኳር ፋብሪካው ሲወድቅ በሒደት ነው፡፡ በአንድ ጊዜ ግንድስ አላለም፡፡ በአንድ ጊዜ ግንድስ ቢል ይሰማ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ነው ዛሬ የተገነደሰው፡፡ የት ነበራችሁ? 88 ሕንፃዎች ጠፉ ሲባል የት ነበራችሁ? የተረከበውና ያስረከበውን የት ገቡ? ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው ፈርመው ያስረከቡት? ስለዚህ ችግሮቹ በአንድ ጊዜ የመጡ አይደሉም፡፡ ፀረ ሙስና ጠንካራ ነው ስትሉን ሳቄ ነው የሚመጣው፡፡ የሚከሰው የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ ነው፡፡ ፀረ ሙስና ይዞ የሚለቃቸው ሰዎች አሉ እሱም ተከፋይ ነው፤›› በማለት ጋዜጠኛው ምሳሌዎችን በመደርደር ወቀሳውን ደርድሯል፡፡

ወ/ሮ ፍሬሕይወት በሰጡት ምላሽ ያቀረቡት ሪፖርት ሚዛኑ የጠበቀ መሆኑን ተናግረው፣ የቀረቡትን ቅሬታዎች ማጣራት ያስፈልግ ይሆናል በማለት አልፈዋቸዋል፡፡

የኪራይ ሰብሳቢነት ምሽግ የተባሉ ዘርፎች ተለይተው በዚያ መሠረት ዕርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ፣ እያንዳንዱ ተቋም በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ የሚገመገምበት ቋሚ አሠራር መዘርጋቱን ተናግረዋል፡፡ ከቀበሌ ጀምሮ ላይ ያሉት ዥንጉርጉር አሠራሮች መስተካከል እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነትን በተመለከተ ግን፣ ‹‹መንግሥት ሊፈጥረው አይችልም፡፡ ሕዝብን አገለግላለሁ የሚል መንግሥት ሙስናን ሊፈጥር አይችልም፤›› በማለት ተመጣጣኝ ዕርምጃ አይወሰድም የሚለውን አልተቀበሉትም፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ግን መንግሥትን ጨምሮ የማይረባ ሥራ እንደሚሠራ ተቀብለዋል፡፡

‹‹ዋናውን ጉዳይ ግን መንግሥት ሕዝባዊ ነው፣ ያነሳችኋቸው ችግሮች የሉም ማለት አይቻልም፣ ጨለማ ግን አይታየኝም፤›› ብለዋል፡፡

አቶ ዘርአይ በሰጡት የማጠቃለያ ሐሳብ፣ ‹‹ሥርዓቱ 100 ሺሕ፣ 200 መቶ ሺሕ መስዋዕትነት ተከፍሎበት የመጣ ነው፡፡ ሥርዓቱ በቃኝ ይኼን ሠርቼያለሁ ብሎ ከቆመ የሞተ ነው ማለት ነው፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡

‹‹ኢሕአዴግ የራሱን ሌቦችም እየቆረጠ የሚጥል ነው፡፡ ታጋይ የነበሩ በኃላፊነት ላይ ሆነው ሲባልጉ ቆርጦ የሚጥል ቆራጥ ነው፡፡ ኢሕአዴግ እንደ ኢሕአዴግ ሌባ አይደለም፡፡ አሁንም ቦታው ላይ ነው ያለው፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ በጋምቤላ በተፈጸመው ጥቃትና በኤርትራ በተፈጸሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ላይ ዕርምጃ ለምን አይወሰድም ተብሎ ጥያቄ ቀርቧል፡፡ አቶ ዘርዓይ፣ ‹‹የኤርትራ መንግሥት በ1993 ዓ.ም. አይደለም የገደልነው፡፡ አሁን ነው የገደልነው ጦርነት ባለመግጠም፤›› በማለት ሐሳባቸውን ደምድመዋል፡፡ ከዚህ ውጪ የመንግሥት ሚዲያን በተመለከተ በርከት ያሉ ትችቶች ቀርበዋል፡፡ ሚዲያው ራሱ ነፃና ሳይሆን የሕዝብ ሳይሆን፣ ሚዲያ ሳይያዝ ሙስናን እንዴት መታገል ይቻላል የሚሉ ጥያቄዎችም ቀርበዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ሕወሓት 40ኛ ዓመቱን ሲያከብር አርቲስቶችና ጋዜጠኞች ወደ ድርጅቱ ታሪካዊ ቦታዎች እንዲሄዱ ባደረገበት ወቅት፣ ለድርጅቱ ሹማምንት ተመሳሳይ ጥያቄዎች ቀርበው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

Sponsored by Revcontent

TRENDING ARTICLES

መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ያላት የሰው ድሀ ሀገር ኢትዮጵያ (ይገረም ዓለሙ)

ይገረም ዓለሙ

በ1982 ዓም  ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆነ አይደለም የት ላይ አንዳለች አንኳን መናገር የማይቻልበት ወቅት .ከአንድ ባልንጀራየ ጋር እየሄድን እኔ ከማላውቀው የእርሱ ጓደኛ ጋር መንገድ አገናኘን፡፡ እናም ሰላምታ ተለዋውጠው  ታዲያስ አንዲት ነህ እንዴት ናችሁ ሲለው  ምን እባክህ ሰውም አለን ሰውም የለንም  ሲል መለሰለት፡፡

ሁለቱ ተለያይተው እኛ መንገድ እንደጀመርን ምንድን ነው ያለው ስል ባልንጀራየን ጠየኩት፡፡ እባክህ እሱ አመሉ ነው፡ ከርሱ ጋር ስናወራ ጓደኞቹ ሁሉ አንደተቸገርን ነው፤ በቀጥታ መናገር አይሆንለትም አለኝ፡፡ ምንድን ነው ስራው ስል ጥያቄ አከልኩ ስራው ወታደራዊ ካድሬ ፣ትውልዱ ጎንደሬ፣ፖለቲካውን በጎንደር አማርኛ እየመሰጠረ ነው የሚያስቸግረን  በማለት ባላንጀራየም እንደመራቀቅ እያደረገው መለሰልኝ፡፡ ሰው አለን ሰው የለንም  የሚለውን አባባል ምንነት ለመረዳት ከባልንጀራየ ጋር ብዙ አውርተንበታል፤ብቻየንም ብዙ ግዜ አውጥቼ አውርጄዋለሁ፡፡

ይህ በሆነ  አስር ዓመት ግድም ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም በጦቢያ መጽሄት ላይ ኢትዮጵያ የሰው ድሀ ካልሆነች ታዲያ የምን ድሀ ልትሆን ነው የሚል ጽሁፍ አስነበቡን፡፡ ይህም ከሆነ አስር ዓመት ግድም (አጋጣሚው ሊገርም ይችላል)   ፕ/ር መስፍንን አግኝቻቸው  ከላይ የጠቀስኩትን ጽሁፋቸውን አስታውሼ ከ90 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ያላት፣ በተለያዩ የዓለም ሀገራት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተሰማርተው የሚሰሩ አንቱ የተባሉ ልጆች ያሏት በማለት ብዙ ነገር ዘረዘርኩና እንዴት የሰው ድሀ ትባላለች ስል ጠየኳቸው ፡፡ በጥሞና አዳምጠው በርጋታ የሰጡኝ ማብራሪያ ረዥምና አጥጋቢ ነበር፡፡ ከግዜው ርዝመት አንጻር ማስታወስ ቢገደኝም አንኳር ነጥቡ እነዚህ የምትላቸው ሰዎች ለራሳቸው ኖረው ሊሆን ይችላል፤ ላስተማራቸው ሀገርና ሕዝብ ምን ሰርተዋል? ከአገዛዝ አላቀውታል? ከድህነት አውጥተውታል? ሰው በሚፈለግበት ግዜና ቦታ ካልተገኘ መኖሩ ብቻ ለሀገር ምን ይጠቅማል የሚል ነበር፡፡

የርሳቸውን ማብራሪያ እያዳመጥኩ አስር ዓመት ያህል ወደ ኋላ ተመልሼ ሰው አለን ሰው የለንም ያለውን የወዳጄን ወዳጅ አስታወስኩት፡፡ የአባባሉ ምንነትና እንደዛ ለማለት ያበቃውም ምክንያት በፕ/ር ንግግር ውስጥ ግልጽ ብሎ ታየኝ፡፡ በቁጥር ብዙ ሰው አለ፤ በቁም ነገር መድረክ በተግባሩ መስክ ግን  ..ማለቱ ነበር የሰው ድሀ ማለት ይህ አይደል ታዲያ፡፡

ብቸኛው ፓርቲ ኢሰፓ ከሲቭልም ሆነ ወታደራዊ ማዕረጋቸው የሚቀድመውን ጓድ መጠሪያቸው ያደረጉ ብዙ እጅግ ብዙ አባላት ነበሩት፡፡ነገር ግን አባሉ በቁጥር በዝቶ  ቁም ነገር ያለው ግን አንሶ  አይደለም ሀገሪቱን ሲያንቆለጳጵሱዋቸው የነበሩትን መሪ ከስደት፤ ፓርቲውን ከሞት፤ ራሳቸውን ከውርደት መታደግ ሳይችሉ ቀሩ፡፡

ኢሰፓ ያልነበሩ እንደውም ኢሰፓን ተቃውመው መንግስቱን አውግዘው ሲታገሉ የነበሩ ባይታገሉም ሥርዓቱን ይቃወሙ ዴሞክራሲን ይመኙ የነበሩ በቁጥር ብዙ  ነበሩ፡፡ ግና ቁም ነገራቸው ሚዛን የሚደፋ የተግባር ሰውነታቸው እስከመስዋዕትነት የደረሰ ጥቂቶች ሆኑና ኢትዮፕያ ሰው እያላት የሰው ድሀ ሆነችና  ከወታደራዊ አገዛዝ ወደ ተጋዳላዮች አገዛዝ ለመሸጋገር በቃች፡፡

ዘመነ ወያኔንም ስናይ ከመነሻው ጀምሮ ወያኔን የሚቃወመው፣ ስለ ለውጥ  የሚደሰኩረው፣  ስለ ዴሞክራሲ  የሚሰብከው፣ ወዘተ ቁጥሩ የትየለሌ ነው፡፡ ግና ከቁም ነገሩ መድረክ ከተግባሩ ስፍራ የሚገኙት ጥቂት በጣም ጥቂት ሆኑና ወያኔ ማን አለኝ ከልካይ እያለ የሻውን እየፈጸመ ሀያ አራት ዓመታት ለመግዛት ቻለ፡፡ ሌላው ቀርቶ በቅርቡ ኢሳትና ቪዥን ኢትዮጵያ በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡትን  በተለያየ የሙያና የእውቀት ዘርፍ ከጫፍ የደረሱ ምሁራንን የተመለከተ  የእነርሱ መሰሎች ሀገር ኢትዮጵያ እንዲህ በአገዛዝ ስትማቅቅ፤፣ከዴሞክራሲ ጋር ሆድና ጀርባ ሆና ስትኖር፣ ሕዝቡ በየግዜው በረሀብ አለንጋ ሲገረፍ ሰው እያላት ሰው ያጣች ሀገር አያሰኝም ትላላችሁ!

የኢትዮጵያ የሰው ድሀነት በወያኔም ውስጥ በገሀድ ይታያል፡፡ በተለያየ መንገድ የድርጅቱ አባልም ደጋፊም የሆኑ አባልና ደጋፊም ባይሆኑ ደግሞ የማይቃወሙ በተለያየ የእውቀትና የሙያ መስክ ላይ የሚገኙ በውጪም በውስጥ ብዙ ዜጎች አሉ፡፡ነገር ግን እነርሱም ቁጥራቸው እንጂ ቁም ነገራቸው የሚታይ ባለመሆኑ ድርጅታቸው በሀገርና  በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ጥፋት ማሰቆም ቀርቶ አንድ መለስ ያለእኔ ማን አለ ብለው ፓርቲም መንግሥትም ግለሰብም ሆነው ናውዘው ለሞት ሲበቁ ሊታደጉዋቸው አልቻሉም፡፡

ይህም ብቻ አይደለም ከአስር ዓመት በፊት ከአምስት ሚሊዮን በላይ አባላት አሉኝ ያለ ድርጅት በቁጥር እንጂ በቁም ነገር (ከሱ ፍላጎት አንጻር) ሚዛን የሚደፋ ሰው አጥቶ ከቦታ ቦታ የሚያገላብጣቸው የተወሰኑ ሰዎችን ነው፡፡ ሴቶችማ ለቁጥርም የሉ፡፡የአሁኑ አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ አንዴ ጀነራል አንዴ አቶ እየተባሉ ስንት ቦታ አንደተገለባበጡ ማስታወሱ ብቻ ለዚህ በቂ ይመስለኛል፡፡

የትውልድ ድርሻውንና የዜግነት ግዴታውን ቅንጣት ሳይከውን በሥልጣኔ ስም ሰይጥኖ ወደ ላይ አንጋጦ ትናትን የማውገዝ ድፍረት በተላበሰው ትውልድ የሚነቀፉ የሚዘለፉት አባቶቻችን በቁጥር ጥቂት ሆነው ከነዛው መካከል ግን የቁም ነገር ሰዎች ብዙም ብርቱም የነበሩ በመሆናቸው ነበር በዙሪያችን ያሉ ሀገሮች በቅኝ ግዛት ሲማቅቁ ኢትዮጵያ በነጻነት የዘለቀችው፤ ዳር ድንበሯን አስከብራ የባህር በሯን አስጠብቃ ለመኖር የቻለችው፡፡ለዓለም ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተምሳሌት ሆና የኖረችው፡፡

ዛሬ ግን አንደ ቁጥራችን ብዛት ከቁም ነገር ያፋቱን፣ ከተግባር ያራቁን ችግሮቻችን በዝተው እኛ የሚናቁት የሚወገዙና የሚኮነኑት አባት እናቶቻችን የቆዩንን ሀገር፣  ዳር ድንበር፣ የባህር በር፣ወዘተ ማስከበርና መጠበቅ ሳንችል ቀረን፡፡  ከወያኔ አገዛዝ ተላቀን የምናወራለትን ዴሞክራሲ እውን ለማድረግ  መስኩ ላይ መገኘት አቃተን፡፡ በእውቀት የበለጸጉ በሙያ የተካኑ በልምድ የዳበሩ አያሌ ልጆቿ  በመላው ዓለም በተለይም በምእራቡ የዓለም ክፍል ተሰማርተው እውቀት ጉልበታቸውን ለሌላ ሀገር እየሸጡ የተደላደለ ኑሮ መኖር ቢቻላቸውም  እውቀታቸውም ሆነ ሙያቸው፣ ልምዳቸውም ሆነ ጉልበታቸው፣ ለሀገራቸው የሚፈይድ አልሆነም፡፡ አንዲህም ሆነና እናት ሀገር ኢትዮጵያ መቶ ሚሊዮን የሚሆን ሰው እያላት  የሰው ድሀ ሆና  አገዛዝ እንደተፈራረቀባት፣ ዴሞክራሲ አንደናፈቃት፣ ረሀብ ልጇን እንዳሰቃየባት ትኖራለች፡፡ ዛሬ እየሆነ ካለው በላይ  የነገው ተስፋ የለሽነት  ይብስ ይከፋል፡፡

መቼ ይሆን! ኢትዮጵያ ልጆቿ  ቁጥራችን ብቻ ሳይሆን ቁም ነገራችንም በዝቶ ሰው እያላት የሌላት የሰው ድሀ ከመሆን የምትወጣው? መቼ ይሆን! በዘር፣ በሀይማኖት፣ በአመለካከት ልዩነት ተለያይተው የመቶ ሚሊዮኖች እናት ግን የሰው ድሀ ያደረጉዋት ልጇቿ ከምንም ነገር በፊት እናታችን ብለው እውቀታቸውን አቀናጅተው ሀይላቸውን አስተባብረው  ነጻነት የሚያቀዳጇት? መቼ ይሆን! ልጆቿ ከራስ በላይ ነፋስ አስተሳሰብ ተላቀው፣ ከመጠላለፍ አዙሪት ወጥተው፣ ከቁልቁለት ጉዞ የሚያቃኑዋትና  የነበረ ዝናና ክብሯን መልሰው የሚያቀዳጁዋት? አረ መቼ ይሆን! ልጆቿ  ዴሞክራሲ እየተረገዘ የሚጨነገፍበትን ሲወለድም   በአጭር የሚቀርበትን በሽታ ተርደተው መድሀኒትም አግኝተውለት ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማድረግ የሚበቁት ? አረ መቼ ይሆን! ልጆቿ የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ሀገር የሰው ድሀ የሆነችው እነርሱ ተለያይተው በመቆማቸው፤ በስልጣን ጥም በመታወራቸው፤ ከእኔ በላይ በሚል አስተሳሰብ በመታጠራቸው፣ለራስ እንጂ ለመጪው ትውልድ የማይጨነቁ በመሆናቸው ወዘተ መሆኑን ተረድተው ከየራሳቸው ታርቀው፣ ርስ በርሳቸው ፍቅር መስርተው፣ አንደ ብዛታቸው ቁም ነገራቸውም ለሀገርና ለወገን ሲበጅ የሚታየው መ? መቼ አረ መቼ !

ተዋቂው የብእር ሰው ሎሬት ጸጋየ ገብረ መድህን  ይድረስ ከእኛ ለእኛ በሚለው ተከታታይ ግጥም ውስጥ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡

ይድረስ ወገን ከእኛ ለኛ “እሳት አንሆን ወይ አበባ”

የነገን ራዕይ አንዳናይ ፣በሐቅ እንቅ ስንባባ

መክሊታችንም ባከነች፣ዕድሜአችንን ስናነባ፡፡

ፍቅር ፈርተን፣ሰላም ፈርተን

አንድታችንን ጠልተን ፣ተስፋችንን አጨልመን

የነፍስን አንደበት ዘጋን፣

የልጆቻንን ተስፋ ፣እምቡጥ ሕልማቸውን በላን፡፡

ሳይነጋ እየጨለመ ነው፣ተው ወንድሜ እንተማመን፣

ዓለም ባበደበት ዘመን፣የብረት ምሽግ ነው ወገን፡፡

ኢትዮጵያ ዘለዓለሚቷ፣አንድነት ነው መድኃኒቷ

ሕብረት ነው መፍትሔው ስልቷ፡፡

የግንቦት 20 ትርፍና ኪሳራ – ባለፉት 25 ዓመታት

የግንቦት 20 ትርፍና ኪሳራ - ባለፉት 25 ዓመታት

 Addis Admass

ፖለቲከኞች ምን ይላሉ?

የግንቦት 20 በዓል 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር መንግስት አስታውቋል፡፡ ግማሽ ክፍለ ዘመን
ባስቆጠረው የኢህአዴግ መራሹ መንግስት የተመዘገቡት ስኬቶችና ውድቀቶች እንዴት ይገመገማሉ? የግንቦት 20 ትርፍና ኪሳራ
እንዴት ይገለጻል? የተለያዩ የፓርቲ አመራሮችና ፖለቲከኞች አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ
አንበሴ የሁሉንም ሃሳብና አተያይ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል፡፡

“ለኔ ግንቦት 20፣ እንደ ማንኛውም ሰኞና ማክሰኞ ነው”    አቶ ግርማ ሠይፉ – የቀድሞ የፓርላማ አባል)

ግንቦት 1983 ላይ ምናልባት የ23 አመት ወጣት ነበርኩ፡፡ እውነቱን ለመናገር የመንግስት ለውጡ ሲመጣ ምንም የተለየ ነገር አልጠበኩም ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ሲመጡ አገር መምራት ይችላሉ ወይም ይመራሉ የሚል ግምት አልነበረኝም፡፡ ከራሳቸው አስተሳሰብ እንኳ ስንነሣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በወቅቱ እየተጠላ የመጣውን ሶሻሊዝም ያውም የአልባኒያ ሶሻሊዝም ተከታይና ይሄንኑ ይሰብኩ የነበሩ ሰው ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ለዚህች ሃገር ይጠቅማሉ ወይም ይህቺን ሃገር ይመራሉ የሚል እምነት አልነበረኝም፡፡ ሆኖም በራሳቸው ባይችሉም እንኳን ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ አገሪቷን ወደተሻለ አቅጣጫ ሊመሯት ይችላሉ የሚል ተስፋ ነበረኝ፡፡ አቅምም ስለሌላቸው ሌላውን ያሳትፋሉ የሚል ግምት ነበረኝ፡፡
በሽግግር ቻርተሩ ጊዜ ነፃ ሚዲያ፣ ሳንሱር ቀርቷል የሚሉ ቃላት የተጨመሩበት ስለነበር ጥሩ ነገር ሊመጣ ይችላል የሚል ተስፋ ነበረኝ፡፡
መጨረሻ ላይ ግን ሁሉንም ያሳተፈ ነው በሚል የራሳቸውን ኮንፈረንስ ሲያካሂዱ በዚያኑ ወቅት አንዱ ከሣሽ አንዱ ተከሳሽ ሆኖ የሚቀርብ ሣይሆን ሀገራዊ እርቅ የሚወርድበት ሁኔታን ስለአሸናፊነት ስነልቦና ወርደው ቢያመቻቹ ኖሮ ወደምንፈልገው ምዕራፍ የምንሸጋገርበት እድል ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡
ከዚያ በኋላም ይሻሻላሉ ተብለው ሲጠበቁ ብሶባቸው በ1993 ዓ.ም የኢትዮጵያ ህዝብ እስኪንገሸገሽባቸው ድረስ ደርሰዋል፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ ያኔ ያዳናቸው በወቅቱ የተከሰተው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ነው፡፡ ጦርነቱ ለእድሜያቸው መራዘም መልካም እድል የፈጠረላቸው ይመስለኛል፡፡ ጦርነቱ ተከስቶ ኢትዮጵያውያን አንድ የሚያደርግ ነገር ባይፈጠር ኖሮ  ይገጥማቸው የነበረውን ችግር መቋቋም አይችሉም ነበር፡፡ ያ ለእነሱ አንድ እድል ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በአለማቀፍ ደረጃም ለመጀመርና ዘልቆ ለመግባባት ጦርነቱ እድል የከፈተላቸውም ይመስለኛል፡፡
ሌላኛው በኢህአዴግ የ25 አመት ጉዞ ውስጥ በጉልህ የሚጠቀሰው የ1997 ምርጫ ነው፡፡
በወቅቱ ከህዝቡ የቀረበባቸውን ተቃውሞ ሊቋቋሙ አልቻሉም ነበር፡፡ አጋጣሚውን ለበጎ መጠቀም ሲችሉ አልተጠቀሙበትም፡፡
ከዚያ በኋላም “ስልጣናችን የሚያበቃው በመቃብራችን ላይ ነው” ብለው ቆርጠው ተነስተው ይኸው እስከዛሬ አሉ፡፡
የግንቦት 20 ፍሬዎች
ስኬታቸው ይሄ በመሠረተ ልማት አገኘን የሚሉንን ከሆነ እኔ አልስማማም፡፡ ስኬት በቁስ ብቻ ሳይሆን በሰው ልጅ ሰብዕና እና ነፃነት ላይ የሚመሰረት ነው የሚል ዕምነት አለኝ፡፡ ከተማ ውስጥ ከምናያቸው አስፓልቶች በላይ ከ25 አመት በኋላም 20 ሚሊዮን ህዝብ በእለት ደራሽ እርዳታና በሴፍቲኔት የሚረዳ ህዝብ መኖሩን ነው የማስበው፡፡ ይሄን ሁሉ ጉድ ይዘን ተሣክቶልናል የምንል ከሆነ፣ እንደ ባህላችን ያው “ተመስገን” ብለን መኖር አለብን ማለት ነው፡፡
ከዚህ መለስ ብለን ማየት አለብን ብዬ የማስበው ጦርነት ባይኖር ኖሮ ደርግስ መሠረተ ልማት የሚባለውን መስራት አይችልም ወይ? የሚለውን ነው፡፡ በሚገባ ይሠራ ነበር፡፡ ከዚህች ድሃ ሀገር በየአመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ባይሸሽ ደግሞ ምን ሊሠራ እንደሚችል ማሠብ ያስፈልጋል፡፡ አንዳንዴ በሚኒልክ ጊዜ ስልክ አልነበረም፤ዛሬ ሞባይል አምጥተናል ሲሉ ይገርመኛል፤ ሞባይልን እነሱ ባያመጡትም ማንም ሊያመጣው የሚችል ነው፡፡ ዘመኑ የፈቀደው የቴክኖሎጂ ውጤት ነው፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ባይኖርም ሞባይል ይኖር ነበር፡፡ መንገድ ሠርተናል የሚለውም ቢሆን ጣሊያንም በሚገባ መንገድ ሠርቷል፡፡ በ5 አመቱ ብዙ መንገድ ሠርቷል፡፡ ስለዚህ ጣሊያን ይሻለን ነበር ልንል ነው?
መንግሥት ሲቀየር የነበርዎት ተስፋ ምን ነበር? ተስፋዎት ከ25 ዓመት በኋላ ተሟልቶ አግንተውታል?
እኔ እዚህ ሀገር የምኖረው በየዓመቱ ተስፋ ስላለኝ ነው፡፡ እኔ ተስፋ አልቆርጥም፤ በአገሪቱ ውስጥ ነገሮች እንዲሻሻሉ የራሴን አስተዋጽኦ ማበርከት አለብኝ ብዬም አምናለሁ፤ በግሌም ከመሰሎቼ ጋር ሆኜም፡፡ የኔ ልጆች፤ “ይህቺን ሃገር እንዲህ አድርገው ያስረከቡን አባቶቻችን ናቸው” ብለው እንዲወቅሱኝ አልፈልግም፡፡ እንዲለወጥና እንዲሻሻል ጥረት አደርጋለሁ፡፡ መለወጥና ማሻሻል ባልችል እንኳ ልጆቼ፣ “አባቴ ዝም ብሎ ቁጭ ብሎ ነው እንደዚህ አይነት ሀገር ያስረከበኝ” እንዳይሉኝ በግሌ ሙከራ አደርጋለሁ፡፡ እኔ እያንዳንዱ ሰው የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለለውጥ የራሱ ድርሻ አለው የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ፡፡ ግን ብንተባበር ለውጡን እናፋጥናለን፡፡
ለኔ ግንቦት 20 እንደ ማንኛውም ሠኞና ማክሰኞ ነው፡፡ በትግል ለውጥ ለማምጣት ግንቦት 20ን መጠበቅ አያስፈልገኝም፡፡ አንድ ሴትዮ ምን አሉኝ መሰለህ? “ኢህአዴግ ያመጣልን ለውጥ ሴት ልጆቻችን በቪዛ ውጭ ሀገር እንዲሄዱ ማድረግ ብቻ ነው፡፡” እኔም እሱ ባይመጣ ኖሮ ይቀርብን ነበር የምለው ዛሬ ላይ ያለ አንድም ነገር የለም፡፡ አሁን ያሉት ነገሮች ሁሉ እሱ ባይመጣም ምናልባትም በተሻለ መጠን የሚመጡና የሚፈጠሩ ነገሮች ናቸው፡፡ እንደውም የተሻሉ ብዙ ነገሮች ይኖሩ ነበር፡፡ ሞባይልም፣ ቴሌቭዥንም ሌላውም እነሱ ቢኖሩም ባይኖሩም ይመጣሉ፡፡ እኔ የሚቆጨኝ ያልመጡ ብዙ ነገሮችን ሳስብና የተበላሸውን ነገር ሳስተውል ነው፡፡
ዛሬ አንድ ሚኒስትር ሲሾም ስሙን ለመስማትና በዘር ለመፈረጅ እንድንጣደፍ ያደረጉን እነሱ ናቸው፡፡ መታወቂያችን ላይ ብሄር የፃፉልን እነሱ ናቸው፡፡ በየእለቱ ስለ ብሄር እንድናስብ አድርገውናል፤ እነዚህ ሁሉ ጥሩ አይደሉም፡፡

========================================

“አገሪቱ የባህር በር ያጣችው ከግንቦት 20 በኋላ ነው”     አቶ ልደቱ አያሌው፤ ፖለቲከኛ)

የመንግስት ለውጡ ሲመጣ የተለያዩ ጭንቀቶች ነበሩ፡፡ ይህቺ ሀገር ወደ ሁከት ሜዳ ትሸጋገራለች የሚል ፍርሃት ነበር፡፡ ኢህአዴግ ከሚያራምዳቸው አንዳንድ አቋሞች በመነሳት ደግሞ ሀገሪቱ ትበታተናለች የሚል ስጋትም ነበር፡፡ እኔም እንደ ማንኛውም የወቅቱ ወጣት በነዚህ ሀሳቦች መሃል ነበርኩ፡፡
በመጀመሪያ ግንቦት 20 ደርግ ወድቆ ኢህአዴግ የተተካበት ነው፡፡ በአንፃራዊነት በሃገሪቱ ውስጥ ለረዥም አመታት በርካታ ወጣቶችን የጨረሰው ጦርነት የቆመበት ጊዜ ነው፡፡ እሱ በራሱ ስኬት ነው፡፡ ሁለተኛው ውጤት በሀገሪቱ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለማቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኙ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ተቀባይነት ያገኙበት ጊዜ ነበር፡፡ የነፃ ፕሬስ፣ የብዙሃን ፓርቲ አሰራር ቢያንስ በህግ ደረጃ እውቅና አግኝተዋል፡፡ ቆይቶ ቢሆንም የኢኮኖሚ እድገትም የታየው ከግንቦት 20 በኋላ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ያሳጣን ብዬ የማነሳው አንዱና ዋነኛው የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ የተነጣጠለው በግንቦት 20 አማካኝነት መሆኑ ነው፡፡ በታሪኳ የባህር በር ያጣችውም ከግንቦት 20 በኋላ ነው፡፡ የአንድነት ስሜት ጥያቄ ውስጥ ገብቶ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የአካባቢያዊ ስሜት የበለጠ ቦታ ያገኘበት ጊዜ የመጣው በግንቦት 20 ነው፡፡ የሀገሪቱ አንድነት ጥያቄ ውስጥ ገብቶ እስካሁን ዘልቋል፡፡ በየጊዜው አዳዲስ ቅራኔዎችና ግጭቶች እየተፈጠሩ ነው፡፡ በሂደትም ደግሞ ስልጣን በአንድ ፓርቲ የበላይነትና ሁለንተናዊ ቁጥጥር ውስጥ የወደቀበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው፡፡ ከዚያ በኋላ ያሉት ነገሮች ሁሉ የህብረተሰቡ አመለካከቶች ነፀብራቅ ሳይሆን የአንድ ፓርቲ ነፀብራቅ ነው በአጠቃላይ የህዝቡን ህይወት እየወሰነ ያለው፡፡ በህገ መንግስቱ የሰፈሩና በጎ ናቸው ያልናቸው ነገሮች በተግባር ላይ የውሃ ሽታ የሆኑበት አጋጣሚም በሂደት ተፈጥሯል፡፡
አንፃራዊ ሠላም መገኘቱ በሌላ ጎኑ በበጎ የሚታይ ነው፡፡ ይሄን ስል ጦርነት የለም ማለቴ አይደለም፡፡ ግንቦት 20 ማክበር ከጀመርን 25 ዓመት ሆኖናል፡፡
በዚህ መሃል በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካው፣ በማህበረሰብ እድገት፣ በፍትህ … ዘርፍ ያሉ ጉዳዮች በሰፊው መገምገም አለባቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ግን የሚያሳስበው የሀገሪቱ አንድነት አደጋ ላይ መሆኑ ነው፡፡

==================================

“ድርጅታችን ለስርአቱ አደጋ የሆኑትን በተሃድሶ አጥርቷል”     (አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው፤ የቀድሞ ታጋይ)
በእነኚህ 25 ዓመታት ውስጥ በርካታ ፖለቲካዊ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ድሎች ተመዝግበዋል፡፡ እንደሚታወቀው የስርአት ለውጥ ነው የተደረገው፡፡ ያለፉት መንግስታት ህዝቦችን በተለያየ መልኩ የሚጨቁኑ ነበሩ፡፡ ያንን የጭቆና ስርአት የገረሰሰ ድል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለመጀመሪያ ጊዜ የሰብአዊና ዲሞክራሲዊ እድሎቻቸውን እንዲጠቀሙ፣ የራሳቸውን እድል በራሳቸው መወሰን የሚችሉበት፣ የግልም ሆነ የቡድን መብቶቻቸው እንዲከበር ያደረገ ነው፡፡
በዚያው መጠን ሀገራችን ከድህነት አረንቋ እንድትወጣ እያደረገ ያለ ድል ነው፡፡ በድህነትና በኋላ ቀርነት የምትታወቀውን ሀገራችንን በልማት እንድትታወቅ አድርጓል፡፡ የልማት አቅጣጫን በመቀየስ በሀገሪቱ ልማት የሚፋጠንበትና ህዝቡ በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል መሰረት የተጣለበት ቀን ነው፡፡ በማህበራዊ መስኩም እንደዚሁ ዜጎች የሀገሪቱ አቅም በፈጠረው መጠን ከትምህርት፣ ከጤና፣ ተጠቃሚ የሚሆኑበት፣ ሰራተኞች የላባቸው ተጠቃሚ የሚሆኑበት፣ ጥቅማቸው እንዲከበር መሰረት የተጣለበት ቀን ነው፡ በጨቋኝ ስርአት ስር የነበረን ህዝብ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ያሻገረ ቀን ነው፡፡
የሽግግር መንግስቱ ቻርተር የሀገሪቱን ብሄር ብሄረሰቦች ያሳተፈ ነበር፡፡ አለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የፕሬስ ነፃነት የታወጀበት እለት ነው፡፡ ኢኮኖሚውም ቢሆን ግብርና መር የሆነ ፖሊሲ ወጥቶ ሀገሪቱን ከውድቀት ታድጓል፡፡ ወደ እድገት ሊያመራ፣ የሠለጠነ የሰው ሃብት ሊያፈራ የሚችል ህገ መንግስት መሰረት የተጣለበት ቀን ነበር፡፡ በነዚህ አመታት አብዛኛውን ህዝብ ከድህነት ያወጣ፣ መሰረተ ሰፊ የሆነ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገቡን ማንም የሚክደው አይደለም፡፡ በጋራ የፌደራል ስርአት ተፈጥሮ፣ ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ የቡድን መብት ተከብሯል፡፡
በዚያው ልክ ባለፉት 25 ዓመታት ያጋጠሙ ፈተናዎችም አሉ፡፡ የህዝቡ ተጠቃሚነት እየሰፋ በሄደ ቁጥር በጣም ብዙ ፍላጎቶች ይፈጠራሉ፡፡ ጠያቂና ሞጋች የሆነ ህብረተሰብ እየተፈጠረ ነው ያለው፡፡
የመንግስት መዋቅርን አለ አግባብ ለመጠቀም የተደረጉ ሙከራዎች ታይተዋል፡፡ ድርጅታችንም ለስርአቱ አደጋ የሆኑትን በተሃድሶ አጥርቷል፡፡ አሁንም በመልካም አስተዳደርና በኪራይ ሰብሳቢነት የሚታዩ ችግሮች የስርአቱ ፈተናዎች ናቸው፡፡ ኢኮኖሚው ባደገ ቁጥር በዚያው ልክ ፈተናዎቹ ውስብስብ እየሆኑ ነው የሄዱት፡፡ 25 ዓመቱን ሙሉ እንዲህ በቀላሉ አልዘለቅንም፡፡ እየታገልን ነው፡፡ ከዚህ በኋላም ትግላችን ቀጥሎ እቺን ሀገገር ወደ ተሻለ ምዕራፍ የማሸጋገር ስራ ይሰራል፡፡ ሀገራችን ከኋላቀርነት ወጥታ የእድገት ማማ ላይ የምትደርስበትን አቅጣጫ ስለያዘች ደስተኞች ነን፡፡ በቀጣይ ጉዟችን ፈተናዎችን እያለፍን የታፈረች፣ የተከበረችና ህዝቦቿ በነፃነት የሚኖሩባት ሀገር እንገነባለን፡፡ በዚህ መንፈስ ነው የምናከብረው፡፡

=================================

“ኢህአዴግ በ25 ዓመት ወደ ቅቡልነት አልተሸጋገረም”      (ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፤የፍልስፍና ምሁር

የግንቦት 20 በአል 25ኛ ዓመት ሲታሰብ፣ ያለፉትን 25 ዓመታት በሶስት ዘርፎች መገምገም ያስፈልጋል፡፡ አንደኛ ከዲሞክራሲ አንጻር፣ በነዚህ 25 ዓመታት ውስጥ ስርአቱ የዲሞክራሲ ጅማሮ ላይ ነው ቢባልም ከጉልበት ወደ ቅቡልነት ሲሸጋገር አላየንም፡፡ አልተሸጋገርንም፡፡
ይልቁንም ወደ ፈላጭ ቆራጭነት (አውቶሪቶሪያን) የበለጠ ተሸጋግሯል፡፡ ሁለተኛ በፌደራሊዝም ዙሪያ ጅማሮው በጎ የሚባል ነበር፤ኋላ ላይ ግን ፌደራሊዝሙ ቀርቶ ወደ ብሄረሰብ ተኮር አሃዳዊነት (ethnic totalitarianism) ተሸጋግሯል፡፡
የተወሰኑ ክልሎች አሉ፤በአሃዳዊ ስርአት የሚተዳደሩ፡፡ ሶስተኛ ኢኮኖሚውን በተመለከተ ጅምሩ ጥሩ ነበር፤ኋላ ላይ የሙሰኛው ሲሳይ ሆነ እንጂ፡፡ ሙሰኛው እየበላው ነው ያለው፡፡ ሙሰኛው የደረሰበት ደረጃ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ዝም ቢባልም  ጠንክረው እናሻሽል ቢሉም ስርአቱን የሚያፈርስ ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ የፖለቲካ አዙሪት ውስጥ ገብቷል ብለን ልንደመድም እንችላለን፡፡ያሉትን ማህበረ-ፖለቲካዊ  ቅራኔዎች ከባድ የሚያደርጋቸው ከኋላ የወረሳቸው ሳይሆን ራሱ የፈጠራቸው ችግሮች ፈጠው ሲመጡ አደጋው የከፋ መሆኑ ነው፡፡ ኢህአዴግ እንደሚያወራው ቢሰራ ኖሮ ከየአቅጣጫው ጥያቄ ባልተነሳ ነበር፡፡

How TPLF conned born suckers of the world and who muddied President Obama’s Africa legacy

Ethiopians continue to wonder; how a small time world recognized terrorist group known as Tigray People Liberation Front (TPLF) pulled the greatest scum in history of Ethiopia.

It is unspoken rule without saying; TPLF is a mercenary group unleashed on the people of Ethiopia. But, the question remains whether its supporters and apologists are part of the scum or on only in it for the money.Obama and Susan Rice

Nevertheless, how it is a hardline Marxist-Leninist ethnic liberation pushing TPLF clowns turned 360 degree to become Ethiopia’s # 1 snake oil salesmen of the century in a matter of two decades to put the nation in the auction block to foreigners?

More bewildering g is; how did the same internationally recognized ‘terrorist ’ turned ‘mercenary’ accused of elaborate assassinations, kidnapping and   racketeering ended up to be endorsed by non-other than the leader of the Free World and the first ‘African-American’ President of the United States of America as a ‘democratically elected government of Ethiopia’ and its assassination squad as mercenaries for hire – reducing President Obama’s Africa legacy into the ashes of history with no one noticing it?

Wait, it gets worst. How it is the same TPLF clowns outwitted US authorities to circumvent the laws of the land to receive US taxpayers’ money and charities in the form of foreign aid and import and export what they extorted from the people of Ethiopia in and out of the US and got away at will for these long without being noticed, charged and jailed.

Don’t go yet, there is more. How it is TPLF outsmarted the World Bank, IMF as well as the Donor Group and Foundations to pour in 100s of millions of dollars all these years without knowing TPLF’s scum of laundering it to its own coffer? And, who is responsible for the entire debacle?

As I said before; the devil is all in the details.

But, before I go on to say who could possibly be responsible to the crises brought on our people and nation; it is appropriate to say why it was possible (the cause) to begin with. I firmly believe; the slash-and-burn politics of our contemporary elites opened the door wide for TPLF clowns and associated con artists, criminals, drifters, invaders, pseudo intellectuals, lookalike journalist and preachers to believe the people of Ethiopia are disposable for their personal adventure or interest and the nation is their playground at their disposal. That said, I also believe, there is foreign interest behind the elites behavior at the expenses of the rights and liberties of our people.

This uncomfortable yet row truth continues to be the biggest hindrance for the democratic movement to free the people from a smalltime mercenary-led ethnic Apartheid regime.

Let me explain briefly why what I say is true before I become another causality of the slash-and-burn politics of the usual suspects including the mercenary TPLF clowns.

There is unspoken rule among the Ethiopian elites. That is, they knowingly and unknowingly believe; the freedom and liberty of the people of Ethiopia are under their mercy. Therefore, depending their mood or political and economic ‘adventure’; they reduced the right and liberty of the people into a zero-sum game to their liking and worse yet; a trial and error experiment of their prevailing imagination of what the people’s rights and liberty ought to be.

For instance, in the last four decades since the traditional monarchy rule ended, the ruling political elites implemented Marxism, ethnic liberation and crony capitalism on the people to produce the two most criminal regimes in the modern history of Africa with millions of death, displacement, famine and corruption to show for it and it continues to be so at the present. But yet, not one elite involved in both regimes took any responsibility or made accountable by anyone for crimes of the century, not one.

Now, unlike the Derg regime’s elites; Ethiopians are under ethnic elites that mastered the worst of Marxism, ethnic politics and crony capitalism combined all-in-one never seen in modern experience since the South African Apartheid regime rule ended.

But yet, have you noticed how many self-appointed political elites play slash-and-burn politics –reducing the rights and liberty of the people of Ethiopiaconditional to their ever changing political adventure or interest from ridding the ruling elites?  This reality alone should be sufficient to illustrate the ever changing self-serving conditions the elites forward on the democratic rights of the people of Ethiopia as a principle cause for the people not to own their freedom and liberty all these years. In other words, the people’s freedom and democratic rights are conditional to the self-appointed political elites’ imagination of what democracy means to our people.  If that is not the case; why are the elites not coming together for democratic rule to end Apartheid tyranny besides inserting democracy in their slogan in the last hour?

That said, coming back to the subject matter; the ruling TPLF elites’ slash-and-burn politics and the ever changing political and economic adventure (Marxism, ethnic liberation, revolutionary democracy, crony capitalism and more to come) came out of the same belief—Ethiopians are disposable for the elites’ political adventure or economic interest in general.  What makes TPLF elites different and more dangerous than others is; their willingness to be mercenaries for hire to foreign interest against the interest of the people of Ethiopia never seen in history. Credit (‘legacy’) is due to the leadership of the late TPLF con artist extraordinary Melse Zenawi.

Now, the screaming crying TPLF clowns/apologist must swallow the bitter truth; they are conned to commit heinous crimes of atrocities and corruption instead of blaming anyone or skirting the issue and live with it.

But, If there are two ‘important’ ‘foreigners’ among many around the world that consistently duped the world on behalf of TPLF clowns to get away with ‘murder’ and at the mean time to make a mockery of President Obama’s African legacy, Susan Rise, the former Secretory of African Affairs and UN Ambassador and the present Senior National [in] Security Adviser and honorary Ambassador/lobbyist of TPLF followed by Gale Smith, the present Director of USAID should take the credit.

The dual recruited early on brought TPLF in the world stage and did more damage on the Africa people rights and liberties on behalf of one dictator or another, particularly the late dictator/conman of Tigray/Ethiopia Melse Zenawi than any other foreign official ever did. The Rwanda genocide under Susan Rise watch and how she got away to become the lead expert and adviser to President Obama should tell you there is more than the hype we hear.

Susan and Gale that pride themselves as close friend of the late dictator of Ethiopia since his gorilla days up to his death in mysterious circumstances essentially wrote the African policy of the Clinton as well as the Obama Administration in what appears the copy of Melse’s policy. The con artist that groomed the dual since they were junior State Department officials assigned in Africa owes him for what they know about Africa and the position of power they hold in the US government.

Journalist and historians will do Ethiopians and Africans in general and the American people in particular a great favor if they obtain and dig in on the dual’s official correspondence with the then guerilla leaders under the Freedom of Information Act to find out how he conned and coached the two clueless junior American officials not only to become lobbyist on behalf of TPLF on expenses US taxpayers and against the people of Ethiopia but, to write the US policy on Africa.

Likewise; informing the American people how the dual on behalf of TPLF duped President Obama that despised African dictators at the beginning of his administration to end up embracing them at the end of his term to the point of calling TPLF led Ethiopian rogue regime ‘democratically elected government’. At the meantime, it would be appropriate to find out who TPLF agents the two US government officials rely on at present to utter the hogwash we have been hearing from the Administration officials.

Regardless, the first ‘African American’ President’s legacy on Africa turned out to be nothing more than historical embracement– a hype to dupe Africans in believing things will change for the better under his Administration when in reality it got worst, thanks to Susan Rise and Gale Smith lobbying on behalf of African dictators against the interest of United States as well as Africans.

Ethiopians is the Diaspora should also take responsibility for failing to make the two officials accountable in the court of law or concerned congressional oversight committees as Professor Al Mariam continue to hound them.

When conning Westerners weren’t enough, how TPLF clowns managed to out maneuver the Chinese Communist Party, Indian and Arab government officials and investors with a pyramid scheme without being discovered for far too long is another saga in the arsenal of the mercenary TPLF.

Think about it. The late Melse Zenawi, the mastermind of slash-and-burn politics at home and pyramid scum abroad wasn’t an ordnary con artist. He knew all along every bodies ‘expectation of African small men and the right incentive for greed to blind and entice the greedy to come and throw their repetition for diplomatic cover and their money in to TPLF coffer. After all; he and his comrade in arms were expert selling sand as wheat out of the mouth of starving Ethiopians to dupe Westerners out of their cash. Therefore, for scum artists that use human disaster as opportunity to pickpockets; the greedy are easy prey to entice.

A good example of a born sucker of TPLF scum in recent memory was the arrogant and greedy owner of Karuturi Global that salivated to get free land the size of Belgium not knowing TPLF’s scum. The stupid man deserve what he got for believing  a few pages contract signed by TPLF cadre posed as government official  is good enough to grab land a size of a country.  But, again many Ethiopians in diaspora are tripping over each other to grab a little plot of land they don’t even know who it belongs just because an illiterate TPLF cadre in Diaspora told them to do so. Many end up crying behind closed doors scammed of their money as TPLF clowns planned it.  Greed not only blind people not to see what is coming; they put more money in hope of getting what they know was a scam.

Quite frankly, if people closely followed what TPLF scum artist Melse professed for different audience at different times  like ‘over my dead body—land will be privatize’ while he was dispensing it for his cronies like candy they wouldn’t be crying foul. What he actually saying was; Ethiopians have no dollars but land to give TPLF but, no one listened.  Only his loyal cronies and foreign nationals with dollars will get land practically for free to keep them silent and milk them for more later on.  That is not all, they will even get subsidized loan in birr to entice them to come in. When you think about it; why would he gives his self-proclaimed enemies (Ethiopians) their own land when he can sell/lease it for a dollar to fatten his coffer? If you look at who was first in line to grab prime urban and rural land (good luck finding the complete list) you would understand what TPLF scum/policy is all about.

Moreover, the most preferred foreign land grabbers beside TPLF’s cronies are Arabs, Indians and Chinese in that order.  They weren’t picked for being good stewards of the land nor because they are legitimate investors but for their contribution to enhance TPLF occupation and robbery without raising questions or making noises.

Obviously, the Arabs have special place in TPLF’s heart. It wouldn’t be an exaggeration to say Arab governments invented TPLF and without them there wouldn’t be TPLF period. In fact, TPLF con artist Melse Zenawi was heard saying he is Arab before he was born-again Ethiopian.-When he found out there is easy money to be made being Ethiopian the entire TPLF con artists became more Ethiopian than the Ethiopians they despised. And, the ring leader ended up buried; not in Tigray he supposedly liberated from his ‘Ethiopian enemy’ but in the heart of the ‘enemy’ nation —reducing the bogus ‘Tigray liberation’ in to the ashes of history with the ‘golden people’ he profess to belong disposable at will.

The irony is; even his TPLF cronies couldn’t see being conned in daylight– scrambling to build a Foundation for the conman; not in Adwa where he declare to belong but, Addis Ababa. After all, they are too busy selling and stealing like urban drag kingpin to see anything else.

Looking at the top real-estate con artist/Ambassadors assigned in each country to sell Ethiopian’s land will tell you the other side of the story. The successive handpicked TPLF agents/ Ambassadors in the petro rich Arab countries’ embassies tell you why they were assigned there. But, noting come close to the unofficial TPLF Ambassador and biggest land- grabber/broker/investor than the Saudi national Sheikh Mohammed Al-Amoudi. A close confidant of TPLF conmen Melse Zenawi and Birket Simon (an Eritrean national masquerading as Amhara official) he became the de facto TPLF regime official.

Al-Amoudi became a nuisance among Ethiopians since he started playing his Ethiopian nationality to do TPLF’s political bidding and his Saudi nationality to do TPLF’s economic bidding and showed his true color. The irony is; why would a man of enormous wealth and business interest around the world reduce himself to associate with the most dangerous mercenary masquerading as the government of Ethiopia raises more questions than answers.

When that wasn’t enough; Al-Amoudi went out of his way to disfranchise and harass Ethiopians in the diaspora   and to lobby US government officials on behalf of TPLF– spending millions of dollars. His 20 million dollar contribution for the Clinton Foundation on behalf of the ‘government of Ethiopia’ is the tip of the iceberg of how far he would go to defend TPLF clowns his questionable investment depends on. There got to be more than financial gain that motivate him to put everything he got online on  a small time corrupt regime led by TPLF. Ethiopians can only guess why he isn’t coming out to explain his reason to cover up for TPLF crimes against the people of Ethiopia.

His denial;  his  contribution on his official website stating “The Sheikh made a donation of only $6m to the Clinton Foundation but donated separately $16m to AIDS awareness in Africa wholly unconnected to the Clinton Foundation” by skirting the issue sounds fear of being implicated by US laws and contradicts his public statement of  unwavering political and financial support for TPLF regime and how far he goes to undermine the oppositions in Diaspora. His recent unsuccessful attempt to break up the Ethiopian Football Federation in North America by spending millions of dollars bribing players and officials is a testimony to his commitment to sustain the corrupt TPLF regime.

Here again, the elites conspiracy to believe the people of Ethiopia are disposable to their will is at work.  If Al-Amoudi with an enormous wealth and influence that could afford to take a stand for the people’s freedom and right is not a testimony to that facts who could be? In fact, he is a prime example of what is wrong with contemporary elites that reduced our people as their indenture servants.

Moreover, the legality of an investor of a Saudi national to influence Western governments on behalf of a third party corrupt foreign regime in the name of ‘Aid awareness’ is a million dollar question that requires investigation by legal experts and mainstream Media alike.

In Asia, one of the TPLF mob boss/real-estate agent/Ambassador assigned to deal with the Communist Party of China that trained him to be a Marxist assassin then and “Developmental State’ crony capitalist at present is the Dishonorable TPLF conman Seyom Mesfin. The main reason the Former Foreign Minister sent to China as Ambassador was to use the Chinese Communist party to expand TPLF political as well as economic hegemony on Ethiopia behind closed doors and to counter Western governments’ pressure for reform. In that capacity; he managed to make TPLF owned EFFORT companies the number one exporters of stolen commodities’ destination in Asia countries he oversee from his base in China and China the number one contractor of infrastructure projects. It appears; the officials of China have no clue how TPLF duped them; partly because no one inform them they are dealing with TPLF con artistes posed as Ethiopian government officials.

But, the real-estate agent/Ambassador Gent Zewde in India stand out as the only none TPLF con women that appears to work for commission to sell her country’s land to Indians for a bargain. Her unconventional tactics never heard of in history speaks for itself.

In an interview she conducted with Indian ITMI TV (video deleted for unknown reason) , she confessed the true nature of TPLF. She said referring to listening Indian audience; ‘

“You don’t have to buy the land in Ethiopia because the government gives you the land for an almost negligible lease price for 25 to 50 years, which is then, of course, renewable. There are other government incentives as well.”

She was also allegedly responsible for multiple advertisements on local newspapers for Indians to come and grab cheap land in Ethiopia. Indians were rushing to grab in the greatest land- rash since the Westward Expansion of European Americans from East Coast to West Coast of US to grab land in the late 19th century. Unfortunately, at the meantime; TPLF was chasing Ethiopians out of their land at the other end in a cover of Villagazation Program–cashing in more money from the World Bank and the Donor Group while agents like Gent were selling the land to Indians.

(See also Haliamriam Desalegn mumbled on an interview with Vickram Bahl of ITMI TV regarding land give away claiming lands given are empty land with no settlement.

One Indian farmer that took the offer early on was heard saying “my land in Ethiopia is bigger than my village in India” while Ethiopians were pushed out of their land into exile by TPLF cadres.

The February 2013 Guardian article; ‘India-investors-forcing-Ethiopians-off-land’ partially showed Gent Zewde’s accomplishments during her tenor.  Again, the irony is no one including the Indian government that poured in 100s of millions of dollars into TPLF coffer in the name of building sugar factory makes her or TPLF conmen accountable.

Tell me; what else can you call TPLF scavengers but mercenaries for hire?

The crime of TPLF clowns & associates are many to list here. In fact, as a policy; TPLF elaborately sealed off any information that exposes its and associates crimes from coming out of the country.  Therefore, not a fraction of the crimes committed against the people of Ethiopia are known to the public and the world at large made possible by fake propaganda Medias in the English language masquerading as Free Press. If you look at the propaganda machines posed as private press at home you understand mercenaries are on the loss in your beloved Ethiopia.

By now; there is absolutely no doubt in every Ethiopian mind the ‘Adwa’ gorillas & associates allover Ethiopia and in diaspora proven to be the enemies of Ethiopians. Therefore, the ball is in Ethiopians’ court to rid the enemies within. The only things holding back Ethiopians at the moment are those that ask what ‘if-and-but’ for one reason or another in denial to accept the reality – TPLF clowns institutionalized criminality against their own people in the name of ethnic Fedralsim. Therefore, the democratic struggle is not about ideology but criminality.

There’s a saying “Do it right or don’t do it at all”. Ethiopians must and will be free from tyranny once and for all to be ruled under democratic regime of their choice, it is a matter of time. The question is what do the political elites want? If opportunist elites keep asking what if-and-but, or continue to play slash-and-burn politics; they aren’t any better than the conning TPLF clowns in insulting the intelligence Ethiopians.  Ethiopians should and must make them accountable for extending the rule of TPLF.

The fate of Ethiopians can only be drawn by the people themselves no one else. No more Ethiopians can be duped by opportunist elites that kept the rogue regime alive and extending the misery of the people for far too long.

They say ‘talk is cheap’. Let every elite swallow the bitter truth and submit for the will of the people to be free and governed under democratic rule. Anything else is opportunism at its worst.

The conning and conniving TPLF clowns must and will surrender for the people will by choice or by force. The question is; can the rest of the elites love their people more than themselves to surrender in kind for the people will to shorten the live of TPLF Apartheid rule? If-and-but is the answer or crying foul is sufficient; there must be accountability by the people that are paying the ultimate price of TPLF tyranny. A little humility to tell the truth and accept personal responsibility to do the right thing goes a long way to end the nuisance of tyranny for good and to tell the world; Ethiopians means business this time around.

Warning for TPLF clowns: Committing crimes against the people of Ethiopia from your hiding is not going to help you. Only confessing your crimes in public may help. Your fate is on your hand to do right by surrendering for the will of the people than TPLF. But, expecting to con your way out of your predicament as usual or looking for someone as scapegoat will not help you avoid the unavoidable.  The sooner you accept you are nothing more than a henchman for TPLF Apartheid regime the sooner you realize you are ‘dead fish’ in the ocean.

End of the story

This article is dedicated to our people jailed, displaced and exiled by TPLF land-grab policy. Until the struggle for democracy achieves its goal to rid the regime do not give up hope.