መወለድ ቋንቋ ነው !!

 

ለኛ በነፃነት ለመኖራችን ዋነኛ ሚና የተጫወቱ አያሌ ጀግኖች አያቶቻችን አባቶቻችን እንዳሉን የታወቀ ነው ….ከነዚህም ጀግኖች ውስጥ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ናቸው…ፋሽስት ጣልያን ሳይበግራቸው ሳያስራቸው እድሜ አልጋ ላይ ቢያውላቸውም አለንሎት ማለት ይገባናል…አልታደልንም እንጂ ለቬትራንስ የእድሜ ልክ ጡረታ የተሻለ ህክምና ሹፌር በተደረገላቸውና ቀሪውን ህይወታቸውን ተንከባክበን በክብር በሸኘናቸው ነበር….ሆኖም ከአፍ በዘለለ ምንም አድርገንላቸው ባናውቅም አሁን እሳቸው ስለከፈሉልን ውለታ ስንል የአቅማችንን በማድረግ ልጃቸውን የትምወርቅ ጃጋማ ኬሎን ካለችበት የኩላሊት ህመም መታደግ ይኖርብናል

የትምወርቅ ጃጋማ ኬሎ ኑሮዋ በጣልያን አገር ሲሆን ሁለቱም ኩላሊቶቿ ከጥቅም ውጪ ሆነው መስራት አቁመዋል ….ትራንስፕላንት ወይም የኩላሊት ዶነር ለማግኘት አቅሙ ስለሌላት በዳያለስስ እየተሰቃየች ትገኛለች…ገንዘቡም ቦታውም የማያመች በመሆኑ አሁን ወደኛ ወደ ልጆቿ ፊቷን አዙራለች አለንልሽ እንበላት ስልኳን ወስዳችሁ አዋሯት አነጋግሯት በህይወት እያለች ስለታሪኳ አወድሷት የምንችለውን እናድርግላት ላልሰሙት እናሰማላት….ካለፈች በኃላ የጀግና ልጅ ነበረች ማለት ምንም አይሰራምና

የትምዬ እመቤቴ አምላከ እስራኤል በመሃሪ እጁ ይዳብስሽ ተአምራቱን በአንቺ ይገለፅብሽ ዘንድ እመኛለሁ

የተወደዳችሁ ጓደኞቼ የምለምናችሁ የምትችሉት በፅሁፍ በግጥም በሌላም መንገድ የማሰባሰብ ወይም የማሳወቅ ዘዴ ተጠቅማችሁ ላልሰሙት ሼር በማድረግ በግድግዳችሁም በመፃፍ እንድትተባበሩ ነው …በየእምነታችሁ ምህረቱን እዲያድላት በፀሎታችሁ አስቧት የኢትዮጵያ አምላክ ያያልና!!

ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን!!

Pupitika Val's photo.
Pupitika Val's photo.
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s