ጀግና ስንፈልግ ባጀን

 

ይህን ርእስ ከሀያ አምስት ዓመት በፊት በጦቢያ መጽሔት ላይ የተጠቀመበት በቅርቡ በሞት የተለየን  ታዋቂው ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታይ ሙሉጌታ ሉሌ በብእር ስም ፀጋየ ገብረመድን ነበር። ነብሱን አምላክ በፆድቃን ቦታ ያስቀምጥልንና። ሙሉጌታ እልፍ አእላፍ ጉዳይ ስለ ሀገራችን ፖለቲካ ፅፎል ለእኔ ግን ሁሌ የማልረሳው ጀግና ስንፈልግ ባጀን ብሎ የፃፈው ነው በተለይም እኔ ከማነሳው ሀሳብና ትችት አንፃር በጣም ተዛመደበኝና በሀያ አምስት አመቱ ይህን ርእስ ዳግም ልጠቀምበት ተገደድኩ።

ሙሉጌታ ሉሌ በዚህ ርእስ አንድ አግራሞቱን  የፃፈበት ምክንያት  ህዋት ወያኔና ሻቢያ በሰሜን የነበራቸውን የጦር ቀጠና አያሰፋፍ ጎንደርን ጎጃምን ወሎ ተቋጣጥረው ወደ ርእስ መዲናዋ አዲስ አበባ እየገሰገሱ፣  በደቡብ፣ በምስራቅና ምዕራብ ኢትዮጵያ የነበረው የኢትዮጵያ ሠራዊት የጦር ቀጠናውን እየለቀቀ ወደ ጎረቤት ሀገርና መሀል ሀገር እየሸሸ ሲሄድ ጊዜው የነዚህ አገር አጥፊዎች እንደነበር ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነበር ። የተፈራው አልቀረም አዲስ አበባን ተቆጣጠሩ ።የሺ ዓመት ታሪክ ያላት በጀግኖች አባቶቻችን የተከበረች በነፃነት ፋና ወጊነቷና ተምሳሌነቷ ዓለም ያወቃት ሀገራችን ኢትዮጵያ በእናት ጡት ነካሾችና በባንዳ ልጆች መዳፍ ስር እንደወደቀች ሁላችን አመነን። እና በዚህ ጊዜ ብዙ ብዙ ይባል ነበር።

ብዙ ተስፈኞች የተለያየ አሉባልታ መሰል ፕሮፖጋዳ ይናፈስ ነበር እነዲህ ይባል ነበር ብርጋዴል ጀረናል ዘለቀ በየነ ከባድ ጦር ይዘው ጎጃም ላይ የወያኔን ጦር ገጥመውታል ፣ብርጋዴል ጀረናል ኃይሌ ጎንደር ላይ እየተንቀሳቀሱ ነው ጆርናል ረጋሳ ጅማና ጀረናል አሰፋ ሞሲሳ በወለጋ  ኮረኔል መንግስቱ ኃይለማርያም  አምስት ከፍተኛ የጦር አበጋዞችን ፣ካሳ ከበደንና ኮርኔል ጎሹ ወልዴን እንዲሁም ከጅቡቴ እነ ሻለቃ መላኩ ተፈራና ሻለቃ ለገሰ አስፋው በመያዝ ተበትኖ ኬንያና ጁቡቲ የገባውን ጦር እያሰባሰቡ ነው። ወዘተ የሚል ወሪ ሁሉም አዋቂውም ፣ትንሹም ትልቁም ፖለቲከኛውም ካህኑም ቀን ከለሌት ማውራት ሆነ እና ይህ ያስገረመው ሙሉጌታ ሉሊ  “ጀግና መሆን ሲቅተን ጀግና ስንፈልግ ባጀን” ይልና እኛ ጀግና ሁነን ሀገራችንን ከአደጋና ከብተና ማደን ሲቅተን ነፃነታችን ማስጠበቅ ሳንችል ስንቀር ትናንት በአደባባይ ሲገሉን መብትና ነፃነታችንን አፍነው ሲገዙን የነበረ ሀገርና ትውልድን ያጠፍ አምባገነን መሪዎቻችን ነፃነት እንዲሰጡን የእርሱን ጀግንነት የምንመኝበት ጊዜ መጣ ።ትናንት አንድ ሐሙስ የቀረው መንግሥት የበሰበሰና የከረፋ መንግሥት እንዳላልነው ለዚህ ወታደራዊ መንግስት መውደቅ ተግተን እንዳልሰራን ዛሪ የበለጠ ሀገር  አፍራሽ ቡድን ሲመጣብን ሀገርን ለማዳን ባለመስራታችንና ባለመዘጋጀታችን ቢጨንቀን የትናንት አምባገነን ገዥዎቻችን ዛሪ ነፃ እንዲወጡን የእርሱን ጀግንነት ተመኘን ።

ጀግና መሆን ሲቅተን ጀግና ስንፈልግ ባጀን ነበር ያለው ሙሉጌታ ሉሌ።ዛሪስ? ዛሪ ደግሞ አሁንም ጀግና መሆን ብቻ ሳይሆን ያቃተን ጀግናን ማወቅ ፣ መምረጥና መለየት ጭምር ነው ያቃተን። ሙሉጌታ ሉሊ እኛ ጀግና መሆን ሲቅተን አምባገነን መሪዎቻች ነፃ እንዲወጡን እንመኛለን ነው ያለው ያ ማለት እነዚያ የደርግ መኳንኖችና ባለስልጣኖች ወታደራዊ ሙያቸውንና ችሎታቸውን አልካደም። ቢሆንም በዘመናቸውና  በጊዜቸው ለሀገርና ለሕዝብ ያልሰሩ አሁን ጊዜ ሲከዳቸው ቀን ሲጨልምባቸው በእነርሱ ጀግንነት ኢትዮጵያ ትጠበቃለች  ነፃነታችን እናገኛለን ብሎ ማሰብ የስንፍናችንና የደካማ ባህሪችን መግለጫ  ነው ለማለት ነው።

ታሪክ እንደሚረጋግጥልን ይህችን ሀገር በመውረር ህዝቡን በባርነት ቀንበር ለመግዛት የተፈጥሮ ሐብትና ንብረቷን ለመዝረፍ የእምነት ክህለቷንና ታሪኳን ለማጥፋት ባእዳን ወራሪዎች በተለያየ ዘመን ያላደረጉት ወረራና ጦርነት የለም።ነገር ግን ጀግኖች አባቶቻችን ባደረጉት መስዋዕትነት ይህችን ሀገር ከነ ሙሉ ታሪኳና ክብሮ አስረክበውን ነበር። ነገር ግን በኛ ትውድና በየ ዘመን ለሀገርና ለታሪክ መቋም አቅቶን ጀግና  መሆን አቅቶን ፣ ጀግና መውለድ፣ጀግና ማክበርና ማወቅ ተስኖን ሀገራችን በብተናና በጣረሞት እያለች ቁመን እናያለን ከሁሉ በላይ በለለ ጀግንነት ጀግናው እያልን እንኳፈሳለን።

ጀግንነት የሚወለደው ከጦር ሜዳ ብቻና ብቻ ነው። ኢትዮጵያ የወላድ መካን አልነበረችም እልፍ አዕላፍ ጀግኖች ነበሯት ሁሉም ከመቃብር በላይ የሆነው ታሪካቸው የሚነግረንና የሚመሰክርልን ማንነታቸው ያገኙት በጦር ሜዳ በፈፀሙት ተጋድሎና ውሎ ለሀገራቸው በከፈሉት መስዋዕትነት በጦር አመራር ችሎታቸውና ብቃታቸው ነው። አፄ ዮሐንስ መተማ ግንባር ጦራቸውን በመምራት ድንበሪን አላስደፍረም ብለው በመውደቃቸው ታሪካቸው ዝንተ ዓለም ይነገራል የጦር አበጋዛቸው ራስ አሉላ ባህሪን አላስደፍርም ብለው ከጣሊያን ከግብጾች ከፕሮችጋሎችና ከመሃዲስቶች ጋር  ባደረጉት ወጊያና ባስመዘገቡት ድል ይታወቃሉ። መቅደላ አፋፍ ላይ የወደቀው ባለ ራዕይ ንጉስ አፄ ቴዎድሮስ የጦር አበጋዛቸው ገብርዬ ንግስቲቱ ተወበች የጀገንነት ታሪካቸው ያገኙት በሰሩት ተጋድሎ ነው። የዓድዋው ጦርነት የፊት መሪ ንጉሥ ሚኒሊክ ንግስቲቱ እቴጌ ጣይቱ እነ ራስ መኳን፣ራስ ሚካኤል ፣ራስ መንገሻ ዮሐንስ ፣ራስ ወሌ፣ደጃዝማች ተሰማ ናደው፣ራስ ዳርጌ፣ ደጃዝማች አያሌው ብሩ፣ደጃዝማች መኳነን፣ፊታውራሪ ሀበተ ጊዮርጊስ፣ ደጃዝማች አዳነ መኳነን፣ በላይ ዘለቀ፣አበበ ረታ ወዘተ እነዚህና ሌሎች ጀግና የተባሉት በጦር ሜዳ ባሳዬት ተጋድሎ ነው። ያ ትውልድ የሚነገርለት ላመነበት አላማ እየዘመረና እየፎከረ ሲሞት አይተናል በሱማሌና በሰሜን ጦርነት ለሀገራቸው ክብር ለዳን ድንበሮና ለአድነቷ ሲሉ እልፍ አእላፍ ጀግኖች ባንዲራዋን ለብሰው  እንደተሰዉላት እናውቃለን ።

ድሮ ሕዝባችን ጀግና ያከብራል ጀግና ይወዳል። አሁን ግን የጀግንነት መለያውን እየሳትን ነው ። ለዚህ ፅሁፍ መነሻየ የሆነው የግንቦት ሰባትና የአርበኞች ሊቀመንበር   ዶ/  ር ብርሀኑ ነጋ፣ የድርጅቱን ፀሐፊ ነአምን ዘለቀና ኤፍሬም ማዴቦ ን ጀግናና አርበኛ የሚለው ስያሜ ስላሳፈረኝ ነው። በተለይ በዋሽንግተን ዲሲና በአውሮፖ ግንቦት ሰባት ባደረገው ስብሰባ ላይ በዘፈንና በፍከራ በታጀበ ዝማሪ በደጋፊዎቻቸው ታጅበው ዶክተር ብርሀኑ ወደ መድረክ ሲገቡ በጀግንነት በሚመስል መልኩ እጃቸውን እያራገቡ  የእጃቸውን ጡንቻ በሌላው እየነካኩ ጀግናው ፕሮፊሰር ብርሀኑ፣አርበኛው፣የቁርጥ ቀን ልጅ ፣ መጣ አንበሳው እያገሳ ወዘተ የሚለው ቀረርቶና ዝማሪ አሳፋሪ የወረደ፣ ይህን ሽለላና ሙገሳ ይገባኛል ለሚለው የዶክተር ብርሀኑ መወጣጠርና መኳፈስ ይበልጥ የሚስቅ የሕፃናት ቲያትር የሚመስል ነው።እንዴት ወርደናል እንዴት አንሰናል። እንዴት እራሳችንን ንቀናል።

የፅሁፊ መነሻ ጀግና መሆን ሲቅተን ጀግና ስንፈልግ ባጀን የሚልነ ነው። ሙሉጌታ ሉሊ ከደርግ ወድቀት ማግስት ሻቢያና ወያኔ አዲስ አበባንና አሥመራን እንደተቆጣጠሩ  ለአስራ ሰባት በስልጣን ላይ የነበሩትን የሀገሪቱና የህዝቡ እጣ ፈንታ በእጃቸው ሁኖ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ሲገድሉ የነበር የደርግ የጦር አበጋዞችን እንደ ገና  ሠራዊቱንና ህዝቡን አሰባስበው አደራጅተውና አስታጥቀው ነፃ ሊውጡን ነው ያሉትን የቅዥት ተስፈኞች ፕሮፖጋዳ  ሙሉጌታ ሉሊ እንዲት እንደተጠየፋቸው ና እነደናቃቸው አይተናል። ዛሪ ደግሞ ከሀያ አምስት አመት በሆላ ጭራሽ ሀገራችን ላለችበት መከራና አደጋ ዋና አቅጣጫ ቀያሽ በሆነው በሻቢያ መንግሥትና በኢሳያስ ድጋፍ ነፃ እናወጣለን የሚሉ ተስፈኟች በመምጣታቸውና እነደ አሜሪካ ጎረምሳ ሱሪቸውን ዝግ አድርገው የሚሄድ ግንባታዎች እነ ዶክተር ብርሀኑና ነአምን ዘለቀን አርበኞች፣ጀግኖች፣የቁርጥ ቀን ልጆች፣  በስድስ ዲጅት የሚቆጠረውን የአሜሪካ ዶላርና የዘነጠ ኖሯቸው ትተው በርሀ በመውረድ ሀገራችንና ህዝባችን ከህዋት ወያኔ አምባገነን ለመታገድ  ያሉ ጀግኖች ሲባል የሙሉጌታ ሉሊ የሀያ አመት ትችት ትዝ አለኝ ጀግና መሆን ሲቅተን ጀግና ስንፈልግ  ባጀን ነው ያለው እኔ ግን ጀግና መሆን ሲቅተን ጀግናም ማወቅ አቃተን ብለው እወዳለሁ ።

የጀግንነትን ታሪክ እየተማረ በጀግንነት ለዓላማቸው መስዋዕትነትን ሲከፍሉ ያየ ትውልድ የግንቦት ሰባትን ሰዎች እነ ኤፍሪም ማዴቦ፣ነአምን ዘለቀ፣ብርሀኑ ነጋን ጀግና ሲላቸው አፍራለሁ ። እነዚህ ሰዎች ከምቾት ኖሯቸው ለአንድም ቀን ዝቅ ያለ ሕይወት  መኖር  አይቻላቸውም ። ኤፍሪም ማዲቦ ሁለት ወር አስመራ ኮንቲኔታል ሆቴል ከርሞ ለመምጣት ነው እንዴ የአስራ ሰባት ዓመት ልጄን ስለየው እንባዬ መጣ ከዚህ በኃላ እግዜአብሔር ካለ ከነፃነትና ከድል በኃላ እንገናኝ ብዬው በእንባ ተለያየን ያልከው ለዚህ ነበር? እዚያ ከሄድክ በኃላ አንዴ ከአርበኞች ሰፈር ሌላ ጊዜ ከጀግኖች መንደር እያልክ ስትዘባርቅ የነበር ለዚህ ነው? ነአምን ዘለቀ ሌላው ለገሰ አስፋው የኤርትራውና የበርሀ ግዳጀን ፈፅሜ ተመለስኩ ስትል በቃ አንድ ጥይት ሳይተኮስ አንድ ወረዳ ሳያዝ ግዳጀን ጨርሸ ተመለስኩ ስትል የአንተ ግዳጅ አለቀ? አንተ ሙያህ ጋንግ ስተር አሰማርተህ ሰውን ማሰደብ እንጅ የወንድነት የጀግንነት ልብ እንደለለህ ተክለ ሰውነትህ ያስታውቃል። ሊቀመንበር ብርሀኑ ነጋ  የአርበኞች ግንቦት ሰባት ጠቅላይአዛዥ መሆነዎትን እናውቃለን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ብለው ተሰናብተውን ነበር ኤርትራ የገቡት አሁን አሜሪካና አውሮፖ በየወሩ የሚመላልሰወ ምንድ ነው? ሳይናገሩ የሚሉት ይገባኛል የአውሮፖ ሕብረትና የአሜሪካ ምክር ቤት ለስብሰባና ለምክር ፈልጎኝ ነው የሚሉት ።ለመሆኑ ድርጅተዎ የዲፕሎማሲውን ሥራ የሚሰራ እርዳታና የገንዘብ ማሰባሰብ የሚደርግ እርሰዎንና ድርጅተዎን ወክሎ የሚሰራ ስብስብ የለዎትም።  ስለ ረሀብና ድርቁ ገለፃ ለማድርግ እርሰዎ የጦር መሪና አዛዥን ከኤርትራ በርሀ በወ/ ሮ አና ጎመዝ ከሚጠሩ በሀገሪቱ በቦታውና በምድሩ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሙሁራን የሉም? በአጠቃላይ የያዛችሁት ማጭበርበር ና ማታለል ነው። ስለሆነም  እነዚህን ግለሰቦች እንደ አርበኛና ጀግና ናቸው ብሎ የሚመልክባቸው ሰዎች  ተስፋ ቢሶች ለጀግና ሳይሆን በፖለቲካ ዱርዬዎች ሰላባ የሆነ ለሀገሩ ነፃነት ሳይሆን ለነዚህ ግለሰቦች ቡድናዊ ስራ የሚሰራ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል።

በዚህ ዘመን ከጦር ሜዳ ባልተናነሰ የሰላማዊ ትግል ያፈራቸው ብዙ ጀግና ኢትዮጵያውያን አሉ። ነገር ግን ግንቦት ሰባት በዚህ በህዋት ወያኔ በግፍ በተገደሉና በታሰሩ ኢትዮጵያውያን ሰማእታትና ጀግኖች ስም ይነግዳል እንጅ ከበሪታ የለውም ። እነ አንዶለም አንዳርጌ ፣ሀብታሙ አያሌው፣እስክድር ነጋ፣ውብሸት ወዘተ በሺ የሚቆጠሩ የሥርዓቱ ሰለባዎች በስማቸው የሚነግደው ግንቦት ሰባት እንደ ድርጅትትና እንደ ሰብአዊ ፍጡር ለቤተሰቦቻቸው አንድም ድጋፍ አድርጎ አያውቅም ። በቅርቡ በእስር የተፈታውና በሥርዓቱ በደረሰበት ስቃይና ሰቆቃ የእንኩላሊት በሽተኛ የሆነው በጀግንነቱ በቁርጠኝነቱ የህዋት ወያኔን ሥርዓት ያንቀጠቀጠ የዘመናችን አርበኛ ሀብታሙ አያሌው ለማሳከም በሚደረገው ጥረት በስሙ የነገድ የግንቦት ሰባት ድርጅት አንድም ተሳትፎ አላደረጉም።  እውነት ለሀብታሙ አያሌው ለመሰለ ጀግና አደባባይ ላይ ልመና መደረግ ነበረበት ወይ? ጀግና መሆን ብቻ ያቃተን ጀግና ማወቅና ማክበር አቅቶናል ።  ለዘመናት ታሪካችን እየተንከበላለ በየዘመኑ እልፍ አዕላፍ ጀግኖችን ታሪካቸውን ሰምተናል አይተናል።

ያን ያየ ትውልድ እነዚህን ከሀገሪቱ መሰረታዊ ጠላቶች ጋር የሚሞዳሞድና የሚላላኩ ቡድኖችን እንደ አርበኛ ሲመልክ  ይገርማል።ለኢትዮጵያ ታሪክና ሀገራችን እንደ ሀገር እንድትቀጥል ላደረጉ መሪዎች ና ጀግኖች ከበሪታ ለለላቸው በታሪካችን ለሚፍሩ ለሻቢያ ባንዳዎች ለተንበረከኩ አርበኛ ሳይሆን ባንዳ ወይም ሙሽ ሙሽ ነው የሚባሉት ። ደማችንና ማንነታችን ከጥነትት ጀምሮ ከኢዛና እስከ አሉላ፣ከአሉላ  እሰከ አሞራው ውብነህ፣አበበ ረታ ፣ደስታ ዳምጠው ከዚያ አሰፋ አየና፣ ታሪኩ ለአይኔ፣ፀጋየ ገብረመድን (ደብተራው)፣ተስፋየ ደበሳይ ፣አስራት ወለደየስ ፣ አሰፋ ማሩ የነዚህ ጀግኖች የትውልድ  ቅብብሎሽ የሆነን  ለሀገራችን ቀናኢ የሆነን ትውልዶች እንዴት ጀግና ማውጣትና ጀግና ማወቅ አቃተን ።

በመጨረሻ በአንድ ለቅሶ ያጋጠመኝን ገጠመኝ ላውራችሁና ፅሁፊን ልዝጋ። ሴትየዋ የስድስት ልጆች አባት ሞቱባቸው ። ባል በለጋ እድሜቸው የታወቁና የተመሰከረላቸው ጀግና ነበሩ ጀግንነታቸው ጠላትም ወዳጅም ያውቃል። እና በሀገሪ በቡልጋ ጀግና ሲሞት ይፎክራል እነጅ አይለቀስም ። ዘመድ አዝማድ በየ ቦታው መጥቶ በተጠለለ ሜዳ እየተተኮሰ የሞቹን የጦር ገድልና ጀግንነት እየተጠቀሰ ይፎከራል። ሚስት የባሎን ኮት ደርባ በጀብድ የተሸለመውን ኒሻንና ሜዳሊያ አድርጋ እንዲያ በል! እያለች ትከተላለች በዚህ የሟች ሚስት አይኖ ሲወረወር  አንዷ እንደ ማሾፍ ብላ በነጠላዋ አፍን ይዛ ስትስቅ አየቻትና ተናደደች።የሳቀችው ሴት ባልዋ ከሞተ ስድስት ወር ሁኖታል። ባሎ በጠላት ጊዜ ጋለሞታ ሴቶችን ከጣሊያኖች ጋር ያገናኛል፣የቤት ሰርሳሪ ሊባም ነበር ይባል ነበር። ከስርቆት ብዛት ዋጋ ያለው እቃ ሲጣ የቡሆ እቃ ሁሉ ሰርቆል ስለሚባል በጊዚው የተናቀ ነበር። ንጉሱ ከስደት ሲመጡ ሁሉንም እኩል አግድም ወንበር ላይ እኩል አስቀምጧቸው ያ ሳይሆን ባንዳዎች ይበልጥ ለመሳፍንቱ ቀርበው በሀገሪቱ ተጠቃሚ ሆኑ ጀገኖች ብዙዎች በድህነት ይኖሩ ነበር እና የዚች ባል ሊባው ቀን ከወጣላቸው አንድ ሁኖ ዘመኑን በደስታ ሲኖር ቆይቶ ሲሞት ለእሱም ተፎክሮለት ነበር አይ ጀግና አይ አርበኛ እየተባለ እና የጀግናው ሚስት የዛ የሊባ ሚስት ሳቅ  አናደዳትና ለፎካሪው እነዲ በል! በል ባክህ! ያ ጀግና ያንሰዋል  እንዲ በል አለችና እኳን ለዚህ ጀግና ለማንም የቡሆ እቃ ሊባ እነኳ ተፈኩሮል አለች ። ስለዚህ ጀግናና ሌባን እንለይ። ማስተዋል ይስጠን።

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ  ዳግም ትነሳለች!!!
ኢትዮጵያ  ለዘላለም ትኑር።

ከእለኔ አለሙ                                                                                                                                                                     6/

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s