ትዉልድን ማክሰር ወይስ ብድር? -ፃዲቅ አህመድ

 
የሰብዓዊ መብት ረገጣና የለጋሾች ቸልታ።አበዳሪዎች በጅ አዙር የሰብዓዊ መብት ረገጣን ሲያበረታቱ።የምእራቡ አለም የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ደላሎች (lobbyist)አምባገነናዉያንን የስልጣን እስትንፋስ በመስጠት የየአገራቱን ዜጎች ሰብዓዊ መብት በማስረገጡ ረገድ የሚጫወቱት ሚና-ምንድን ነዉ?
አገርን ማልማት፣ አገርን መገንባት የዜጎች ሁሉ ግዴታ ነዉ። የአገር ልማትና እድገት ቅዋሜ የሚገጥመዉ ሳይሆን በዜጎች ሁለንተናዊ ጥረት ሎጎለብት የሚገባ የወል ተግባር ነዉ። ልማትና እድገት በአንባገነናዉያን እገር-ተወርች ተጠፍሮ ዜጎች እንዲሰቃዩ ሲደረግበት ከልማትና እድገት በስተጀርባ ያሉትን እዉነታዎች መፈተሹ ግድ ይላል።
በተራቡ፣በተቸገሩ እና እድገትን በሚሹ ዜጎች ስም ከለጋሾችና አበዳሪዎች የሚሰበሰብን መዋእለንዋይ ተጠቅሞ መንግስት ዜጎችን ለመግደል፣ ለማሰር፣የመናገርና የመጻፍን መብት ለመገደብ፣የፍትህ ስርዓትን ለማላሸቅ፣ የስቃይ አያያዝን (torture) ለማስፈጸም ሲጠቅም ለጋሾችና አበዳሪዎች በጅ አዙር ጭቆናንን ለማስፋፋት ተባባሪ አይሆኑም ለማለት አይቻልም።
ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች ለመረዳት እንደተቻለዉ ኢትዮጵያ ከመቸዉም ግዜ በላቀ መልኩ ከአለም ባንክ የ1.8 ቢሊየን ዶላር ብድር አግኝታለች። ብድሩ እንደታቀደዉም ለልማት ይዉላልን? እድገትን የሚሻዉ ድሃዉ ወገን ከብድሩ ተጠቃሚ ይሆናልን? ወይስ እንደ ማፍያ የሚንቀሳቀሰዉ ህወሃት መራሹ መንግስት የብድሩን ወፍራም ወፍራም ክፍል እየቆረሰ ወደ ትግራይ ይወስደዋል? ወይስ በህገወጥ የገንዘብ ዝዉዉር ብድሩን የህወሃት ዘራፊዎች ከአገር አስኮብልለዉና በባእዳን ባንክ አስቀምጠዉት ለህወሃት ልጆችና የልጅ ልጆች የተቀማጠለ ኑሮ መጪዉ ትዉልድ እዳ ከፋይ ይሆናል? በጉዳዩ ላይ ባለሙያ ጋብዘናል። በዳላስ ቴክሳሱ የካሊን ኮሌጅ የኢኮኖሚ ፕሮፌሰር የሆኑት ፕሮፌሰር ሙሐመድ አባ ጀበል ጣሒሮ ከኛ ጋር ቆይታ ያደርጋሉ።


ትዉልድን ማክሰር ወይስ ብድር?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s