ሀብታሙ አያሌው በጠና በመታመሙ የዋሽግተን ሆስፒታል ሐኪሞች አልችልም በማለታቸው ወደ ቤቴል ሆስፒታል ተዘዋወረ

 

በሀብታሙ አያሌው ጤና መታወክ፣ እየተረባበሻችሁ ላላችሁ ሁሉ በያላችሁበት ሆናችሁ ፀሎታችሁን ቀጥሉበት። አሁንም በኮማ ውስጥ ነው ያለው። ለውጥ አልታየም። ከትንፋሽ ውጭ ሌላ እንቅስቃሴ የለም። ቤተሰብ በሙሉ ተረባብሿል። ነገር ሁሉ ግራ ገብቶኛል። ወገን ሆይ በክፉዎች እጅ ወድቀናል!!! ከሌሊቱ 8ሰዓት።(ዳንኤል ሺበሺ)

ከአገር ወጥቶ እንዳይታከም ተከልክሎ ነበር

የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የቀድሞ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ሀብታሙ አያሌው በጠና ታሞ ሆስፒታል ገብቷል። ሀብታሙ ከእስር ከተፈታ በሁዋላ ከሀገር ወጥቶ እንዲታከም በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዘሐበሳ አዘጋጆች አማካይነት ገንዘብ ቢአሰባስቡም አገዛዙ ከአገር እንዳይወጣ በጠቅላኢ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ሕግን ይግባኝ መሰረት አድርጎ ከልክላል። ሀብታሙ ከሁለት ሳምንት በፊት ፍርድ ቤት ሲቀርብ ቢአንስ ጉዳያቸው እልባት አግኝቶ ከአገር ወጥቶ ለመታከም ይችል እንደሁ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤት ተብዬው ለተጨማሪ አንድ ወር ቀጠሮውን አራዝሟል። ጤናው እንዲመለስ እየተመኘን ቃለ መጠይቁን አያይዘነዋል።የትግል አጋሩ ዳንኤል ሺበሺ ሌሊት ከሆስፒታል እንደጻፈው የሀብታሙ ሁኔታ አሳሳቢ ነው በክፎዎች እጅ ወድቀናል ነበር ያለው።ዳንኤል በዚህ አጭር ማስታወሻው በሀብታሙ አያሌው ጤና መታወክ፣ እየተረባበሻችሁ ላላችሁ ሁሉ

ሀብታሙ አያሌው በጠና ታሞ በሆስፒታል
ሀብታሙ አያሌው በጠና ታሞ በሆስፒታል

<<በያላችሁበት ሆናችሁ ፀሎታችሁን ቀጥሉበት። አሁንም በኮማ ውስጥ ነው ያለው። ለውጥ አልታየም። ከትንፋሽ ውጭ ሌላ እንቅስቃሴ የለም። ቤተሰብ በሙሉ ተረባብሿል። ነገር ሁሉ ግራ ገብቶኛል። ወገን ሆይ በክፉዎች እጅ ወድቀናል!!! ከሌሊቱ 8ሰዓት>> እግዚአብሄር ምህረቱን ይስጠው

ሀብታሙ አያሌው ዛሬ ለደረሰበት የጤና መታወክ ምክንያቱ በእስር ቤት የደረሰበት ስቃይ ነው። ሀብታሙ አያሌው ከህብር ሬዲዮ ጋር ስለ ጤናውና ስለ እስር ቤቱም ስቃይ ከህብር ሬዲዮ ጋር ተወያይቶ ነበር። ቃለ መጠይቁን ላላደመጣችሁ አያይዘነዋል

 8 1

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: