ከሞኝ ገበሬ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል! – አገሬ አዲስ

 

ያገራችን ብዙሃኑ ደሃ ገበሬ ባለችው ጠባብም ትሁን ሰፊ መሬት በሬ እያጣመደ ለሚያርሰው እርሻ ከበሬ ቀጥሎ ከሚያስፈልጉት መሣሪያዎች መካከል ቀንበርና ሞፈር ዋናዎቹ ናቸው።እነዚህን አስፈላጊ የሆኑ መሳሪያዎች በወፍ ዘራሽ ከበቀለ ጫካ ወይም በቅድሚያ ከመሬቱ ላይ ከተከለው ዛፍ ያገኛቸዋል።እነዚህ መሳሪያዎቹ ካልተሟሉለት እርሻ የሚባል ነገር አይታሰብም።ብዙሃኑ ያገራችን ገበሬ ቀናና ደግ፣ተንኮል የማያስብ ሲሆን ከመካከሉ አንዳንድ ብልጦች(አታላዮች) አሉበት።ብልጦቹ ከውጣ ውረድ ይልቅ በዘዴ የሚሹትን ለማግኘት የሚያስችል ተንኮልን ይጠቀማሉ።የደጉንና የየዋሁን  ገበሬ ማሳ ለመንጠቅ፣ድንበሩን ለመግፋት፣የማይሸርቡት ተንኮልና ዘዴ የለም።ገበሬ በመሆናቸው ለደሃ ገበሬው ጥቅም የሰጡ መስለው በአጥፊ ምክርና ድለላ ንብረቱን ይነጥቁታል።የሚያርስበትን መሬት፣በሬ፣ሞፈርና ቀንበር ወይም እነዚህን የሚያገኝበትን መንገድ ሁሉ ይዘጉበታል።ከርዕሱ ብንነሳ አንዱ መንገዳቸው ለወደፊት ይጠቅመኛል ብሎ ተክሎ ፣ተንከባክቦ ያሳደገውን ለሞፈርና ቀንበር ሊሆን የሚችል ዛፍ በዘዴ አታለውና አባብለው ቆርጠው ለራሳቸው እንደሚጠቀሙበት የሚያሳየውን ተግባራቸውን ነው።በዚህ መልክ የተነጠቀው ገበሬ ሞፈርና ቀንበሩ ቢሰበር ወይም ከጥቅም ውጭ ቢሆን በቀላሉ ከደጃፉ ቆርጦ የሚተካው አይሆንም፤የግድ ጫካ ገብቶ መፈለግና መቁረጥ ተሸክሞም ማምጣት ግዴታው ይሆናል።ለዚህም ነው ከሞኝ(ከየዋህ)ገበሬ ደጃፍ ሞፈርና ቀንበር ይቆረጣል የተባለው።

በተመሳሳይ ደረጃ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ አገሩን ይወዳል፤ አገሩ  ላይ ሰላም ወርዶ፣ቀና መንግሥትና ስርዓት ሰፍኖ፣ለማየት ትልቅ ፍላጎትና ጉጉት አለው።ሌሎች አገሮች ከደረሱበት ደረጃ ለመድረስ ወይም ለመብለጥ የማይመኝ ዜጋ የለም።አገሩን ከመውደዱ የተነሳ በስደትም አገር ቢሆን የሠራውን ሠርቶ ፣አንጀቱን አስሮ በአገሩ ላይ ንብረትና ሃብት ይዞ ተመልሶ በአገሩ ላይ የመቀመጥ ፍላጎትና ምኞት አለው።በአንጻሩም እንደ አጭበርባሪው ገበሬ በአገር ፍቅር ስሜቱ እየገቡ ፣ለበጎ ነገር ያጠራቀማትን የሚነጥቁ ጮሌዎች በየጊዜው እንደሚነሱ በተግባር ታይቷል፣አሁንም እየታዬ ነው።የኢትዮጵያዊውን አገር ወዳድነት ፣አገር ወዳድ መስለው በመግባት እየቦረቦሩት፣ንቃቱን አጨልመው፣በተሳሳተ መንገድ እየነጎደ ፣በመከራ የያዛትን ገንዘብ እያራቆቱት ሲሄዱ በመመልከት አድራጎታቸውን የሚቃወመውን ዜጋ በጥላቻ መንፈስ ፣የአገር ጠላት፣የልማትና የዕድገት ጸር እንደሆነ እያወገዙና እያስፈራሩ ጸጥ ለማድረግ ይሞክራሉ።  የሚበዘብዙት ዜጋ እንዳይሰማና እምቢ እንዳይል በማይደርሰው ጥቅም ዓይኑንና አፉን፣ጆሮውንም በመድፈን ያራቁቱታል።አገር ወዳድና ለአገር ጥቅም የቆሙ መስለው ሌላው በነሱ ስር እንዲሰለፍ ማራኪ  የልማት ዕቅድ በመንደፍ  በሆነ ባልሆነው መንገድ ይዘርፉታል፣ያታልሉታል።የዋሁ አገር ወዳድ በቃላት ከመታለሉም በላይ ከአንዱ ወገኑ ተነጥቆ ለሚሰጠው ቁራሽ መሬት እራሱን ሲሸጥ ማየቱ ይዘገንናል።

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ ከድህነት ወጥታ ከሌሎች አገሮች በልጣ ለማየት ይሻል።ያ ደግሞ ሊሆን የሚችለው ኢትዮጵያዊ አገር ወዳድ፣ዴሞክራትና በሕግ ስር የሚያድር ፣በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት ሲኖር ብቻ ነው።ማንኛውም ቀና አሳቢ ኢትዮጵያዊ የልማት እቅዶች በተግባር እንዲገለጹ የማይሻ የለም።የዓባይም ወንዝ ተገድቦ ለአገር ጥቅም እንዳይውል የሚቃወም የለም።ካለ የኢትዮጵያ ጠላት ብቻ ነው።ግን ዓባይ እንዴትና በምን መልክ ለጥቅም ይዋል የሚለው ጥያቄ ተገቢ ሲሆን ያንን የሚጠይቅ እንደጠላት የሚያስቆጥር ጥፋት አይደለም።ተገቢ ጥያቄን ጥፋት አድርገው የሚቆጥሩ ከዓባይ ግድባ በስተጀርባ ለመጠቀምና የዓባይን ግድብ ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል የሚሽቀዳደሙ አጭበርባሪዎች ብቻ ናቸው።

የሕወሃት/ኢሕአዴግ ቡድን በዓባይ ግድብ ሳቢያ በውጭ አገርና በአገር ውስጥ በማስገደድና በማታለል ከኢትዮጵያውያን ብዙ ገንዘብ ሰብስቧል፤ቦንድ እየሸጠ፣በእርዳታ፣በብድር፣መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ ሰብስቧል፣አሁንም እየሰበሰበ ነው።ለባለገንዘቡ ግን ምን ያህል እንደሰበሰበ፣ምን ያህል እንደወጣና እንደቀረ የሚገልጽ ወቅታዊ ሪፖርት አይሰጥም።በቦንድ ግዢ የተሳተፈውም ኢትዮጵያዊ ደፍሮ አይጠይቅም።በሚሰጡት የማታለይ ጥቅማ ጥቅም አፉን ሸብቦ፣አውጣ ሲሉት እያወጣ፣ደግፍ ሲሉት እየደገፈ፣የጥፋት ተባባሪ ሆኗል።አሁንም እየሆነ ነው።

በየጊዜውና በየቦታው እንደሚያደርጉት አሁንም በመጭው ቅዳሜ (june 25/2016) በኔዘርላንድ፣ ሮተርዳም ከተማ የሃያአምስተኛ ዓመት የሥልጣን ዘመናቸውን ለማክበርና የፈረደበትን የዓባይ ግድብ ቦንድ ለመሸጥ ስብሰባ ጠርተዋል።በዚህ የሚሳተፉትን ወገኖቼን ፍላጎታቸውን ባከብርም፣የሚያዋጡት ገንዘብ የት እንደሚውል፣እስከዛሬስ የተዋጣው፣የተሰበሰበው የሕዝብ ገንዘብ ከምን እንደደረሰ ሪፖርት እንዲቀርብላቸው እንዲጠይቁ ሲሆን በተጨማሪም የሚሰጡት ገንዘብ በውጭ አገር ባንክ ለባለሥልጣኖቹ ተከፋፍሎ እንደሚቀመጥ፣የነሱ በየቀኑ እያተመ በሚረጨው ዋጋ ቢስ የኢትዮጵያ ብር(ያግኙት አያግኙት ዋስትና የለም)የሚቀየር መሆኑን እንዲገነዘቡት ነው።በተጨማሪም በሥልጣን ላይ ያለው ቡድን በቀውስና ውጥረት ላይ በመሆኑ  በአገሪቱ ላይ ለደረሰው ስብራትና ለተፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ የሆኑት ባለሥልጣኖቹን በሹመት ስም በያገሩ እያሶጣ ነው።በዓባይም ሆነ በቤት ግንባታና  በሌላ የልማት ዕቅድ ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ በነዚሁ ባለሥልጣኖች ካዝና ገብቶ  እንደሚቀር ሊያውቁት ይገባል።እንደ የዋሁ ገበሬ ከምትኖሩበት አገር ድረስ እየመጡ የሚበዘብዟችሁን ዘራፊዎች አትመኗቸው።ነቄ! በሏቸው።

ለማወናበድና ለማጭበርበር የሚጠቀሙበት ጥሪ ይህን ይመስላል

ተባብረን ዘራፊዎችን እናሶግድ!!!

አገሬ አዲስ

1E

 

Breaking: ታላቋ ብሪታንያ ከአውሮፓ ሕብረት ለመውጣት በሪፈረንደም ወሰነች

 

england

(ዘሐበሻ) ዛሬ ዓለምን ሲያነጋግር የነበረው ትልቁ ዜና የታላቋ ብሪታንያ ሕዝብ ከ43 ዓመታት በኋላ የሄደበት ሪፈረንደም ነበር:: በአውሮፓ ሕብረት እንቆይ ወይስ አንቆይ:: ዛሬ ሙሉ ቀን በእንግሊዝ; ዌልስ; ስኮትላንድ እና ሰሜን አየርላንድ ድምጽ ሲሰጥ የዋለ ሲሆን በለንደን እና በዌልስ የሚኖሩ እንግሊዛውያን በአውሮፓ ሕብረት ስር ለመቆየት ብዙ ድምጽ ቢሰጡም በሰሜን አየርላንድ; በሌሎች የኢንግላንድ ግዛቶች እና በዌልስ አብላጫው ሕዝብ በአውሮፓ ሕብረት መቆየት የለብንም ብሏል::

52% የሚሆኑ ብሪታንያውያን በአውሮፓ ሕብረት መቀጠል የለብንም ያሉ ሲሆን 48% የሚሆኑት ግን እንቀጥል ብለው እንደነበር ከሪፈረንደሙ ውጤት ዘ-ሐበሻ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል::

በስኮትላንድ እና በሰሜን አየርላንድ ከ67% በመቶ ሰዎች ከአውሮፓ ሕብረት እንውጣ ብለው ድምጽ ሰጥተዋል::

 

የ ታላቋ ብሪታንያ  ከአውሮፓ ሕብረት ለመውጣት መወሰን በአውሮፓ ኢኮኖሚ እና በሴክዩሪቲ ጉዳዮች ላይ ትልቁን ጫና ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል::

《 የሰላም ደጆች ሲዘጉ የአመጽ በሮች ይከፈታለሁ! 》ወጣት ሜሮን አለማየሁ

 

Meronሰማያዊ ፓርቲን በመቀላቀል ለዓመታት የገዥውን ፓርቲ በሰላማዊ መንገድ ስትታገል የቆየችው ወጣት ሜሮን አለማየሁ ፤ መንግስት በየጊዜው ሰላማዊ ታጋዮችን ወደ እስር ቤት እየወረወረና እየገደለ በሰላማዊ ትግል ሊቀየር እንደማይችል በተደጋጋሚ አሳይቶናል በሚል መንፈስ የትግል ስልቷን መቀየሯን እና ነፍጥ አንስታ ስርዓቱን ለመፋለም እንደተዘጋጀች ለአርበኞች ግንቦት 7 ራዲዮ ከሰጠችው ቃለ መጠይቅ ላይ ለመረዳት ተችሏል።

ወጣት ሜሮን ያለ አንዳች ጥፋት በተደጋጋሚ በበሬ ወለድ ክሶች ለእስር እንደተዳረገች እና በእስር በነበረችበት ዘጠኝ ወራቶች ውስጥ የህወሃት መርማሪዎች በሷና በሌሎች የህሊና ታሳሪዎች ላይ የፈፀሙትን አሰቃዊ ግፎች በቃለ መጠይቋ አስታውሳለች።

ወጣት ሜሮን በአሁኑ ሰዓት ኤርትራ የሚገኙትን የነጻነት ኃይሎች ተቀላቅላ ትገኛለች። አርበኛ ታጋይ ሜሮን በአገሬ ላይ የተጫነውን አምባገነናዊ ስርዓት ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ነፍሴን ልሰጥ በረሃ ገብቻለሁ ስትል ተደምጣለች።

በመጨረሻም ወጣቷ ባስተላለፈችው መልእክት “ሁላችንም እራሳችንን ነፃ ማውጣት አለብን። በብዛት ሲታይ የተወሰነ ሰው መስእዋት ከፍሎ ሌላው ተደስቶ መኖር ነው የሚፈልገው ፤ ነገር ግን ሁላችንም መታገል ብንችል ከዚህ አንባገነን ስርአት ነፃ መውጣት እንደምንችል እንዲረዱልኝ እፈልጋለሁ።” ብላለች።

13509063_153062655111815_4952311655502711181_n13501555_153063618445052_8878627178979514138_n

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ

 

ጠቡ የሻእቢያ እና የሕወሃት እንጂ የሕዝብ አይደለም | ግርማ ካሳ

solders ethiopian
(በአዲስ ገጽ መጽሄት እትም 13 የተወሰደ)

ሰሞኑን በሰሜኑ የአገራችን ግዛት ጦርነት ተቀስቅሷል። አስመራም፣ አዲስ አበባም ያሉ ገዢዎች ጦርነት መደረጉን ማመን ብቻ ሳይሆን “ይሄን ደመሰስን፣ ይሄን ያህል ገደልን” እያሉ በመማጸደቅ ላይ ናቸው። አለም የትናየት ደርሳለች፣ ትላንናት እኛ እየረዳናቸው ነጻ የወጡ የአፍሪካ አገራት እንኳን የትናየት ደርሰዋል፣ እኛ አሁንም መግደልን እንደ ጀብዱ አድርገን እናወራለን።

አንዳንድ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ከሻእቢያ ጋር የሚደረግን ጦርነት ከአንድ የዉጭ አገር ወራሪ ጋር እንደሚደረግ ጦርነት አድርገው ነው የሚያዩት። በኔ እይታ ይህ የተሳሳተ አመለካከት ነው። በሻእቢያ እና በኢሕአዴግ መካከል የሚደረገው ጦርነት ከኢትዮጵያ ህዝብ እና ከኤርትራ ህዝብ ጥቅም ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። ጦርነቱ ፣ በዜጎች ደም የሰከሩ፣ የሁለት አምባገነን ቡድኖች ጦርነት ነው። የነርሱ ጣጣ ነው። ለጥቅማቸው፣ ለስልጣናቸው ሲሉ የሚያደርጉት።

ምንም እንኳን ላለፉት 25 አመታት ኤርትራ በፖለቲካ አስተዳደር፣ በሻእቢያ እና በሕወሃት ሴራ፣ ከኢትዮጵያ ብትለይም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የኤርትራ ህዝብ ግን በመንፈስ የተለየ ህዝብ አይደለም። በታሪክ፣ በባህል፣ በስጋ፣ በሃይማኖት እርስ በርሱ የተሳሰረና የተዋለደ ወንድማማች ህዝብ ነው። እግዚአብሄር ፈቅዶና ህዝቡ በትግሉ በርትቶ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታት በአስመራና በአዲስ አበባ ቢመጡ እንደገና ተስማምቶ ሊዋሃድ የሚችል ህዝብ ነው።

ብዙዎቻችን ላለፉት 25 አመታት ከነበረው ፖለቲካ የተነሳ፣ ሻእቢያን ከህዝቡ መነጠል አቅቶን፣ ሻእቢያ ላይ ችግር ስላለብን፣ ኤርትራዉያን ላይ በጅምላ እንፈርዳለን። ይህ ሌላ ትልቅ ስህተት ነው። እስቲ ስለ ኤርትራ ህዝብ ትንሽ ላካፍላችሁ። የሰማሁትንና ያነበብኩትን ሳይሆን ያየሁትንና እና ያለፍኩበትን። የአስመራ ዮኒቨርሲቲ ተማሪ የነበሩኩኝ ጊዜ የማስታወሰዉን። (ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ሆና የመጨረሻዎቹ የአስመራ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ነበርን)

ኤርትራ፣ አስመራ ሲባል ብዙ ጊዜ ወደ አይምሯችን ከሚመጡት ነገሮች ጥቂቶቹ፣ ግፈኛው ሻእቢያ ሲሆን ሌላው ደግሞ ብዙ ጊዜ በፖስት ካርድ ላይ የምናየዉ፣ ዘንባባዎች በዳርና በዳር ያሉበት መንገድ በመሃከሉ የሚያልፈው፣ ፒያሳ ወይንም ኮምፖሽታቶ የሚባለዉን ሰፈር ነዉ። በዚያ መንገድ ብዙ ኬክ ቤቶችና ቡና ቤቶች ነበሩ። ትዝ ይለኛል በአምሳ ሳንቲም አንድ ኬክና ምን የመሰለ ካፑቺኖ እናዝ ነበር። በተለይም ሲመሽ ከመብራቶቿ ጋር ከተማዋ በጣም ታምር ነበር። (በነገራችን ላይ አሁን አስመራ ያኔ የነበራት ዉበት የላትም። የተንኮታኮተችና ያረጀች ከተማ ሆናለች። የቀድሞው የክፍለ ሃገር አወቃቀር ብንመለከት የትግራይ ክፍለ ሃገር ቢያንስ አራት ፣ ጎንደር ሁለት፣ ጎጃም ሁለት፣ ወሎ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች እያንዳንዳችው ሲኖራቸው፣ ኤርትራ የነበራት፣ እኛ የተማርንባት አንዱ ዩኒቨርሲቲ ተዘግቷል። ከከተማዉ ዉበት ባሻገር የማልረሳዉና በዉስጤ የተተከለ አንድ ሌላ ነገር ቢኖር የሕዝቡ ፈሪሃ እግዚአብሄርነትና ደግነት ነበር። እስቲ አንዳንድ ያጋጠሙኝን ላጫዉታቹህ።

አንድ ቀን በዮኒቨርሲቲ ዉስጥ ወዳለዉ ካፍቴሪያ እራቴን ለመብላት እየሄድክ ሳለ ጓደኞቼ አገኙኝና «አትሄድም እንዴ ? » አሉኝ። «የት ?» አልኳቸው። «ንግደት» አሉኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ያንን ቃል የሰማሁት። ጓደኞቼ ነገሩን ያውቁ ነበርና ምን እንደሆነ በኋላ አስረዱኝ። ያን ቀን በአስመራ በሰሜን ምዕራብ በኩል ቪላጆ የሚባል ሰፈር፣ የሚካኤል ይሁን የገብርዔል ቤተ ክርስቲያን አለ። (የቱ እንደሆነ አሁን አላስታወስም)። የዚያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት የሚወጣበት ቀን ነበር። ታዲያ ቤተ ክርስቲያኗ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ታቦቱ በነገሰበት ቀን ግብዣ አድርገዉ በአካባባዉ ያሉትን ሁሉ ይጋብዙ ነበር። ይሄ ስርዓት ነዉ እንግዲህ ንግደት የሚባለዉ።

ያኔ መኪና የለንም። በእግራችን ከአንድ ሰላሳ ደቂቃ በኋላ በቪላጆ ደረሰን። አራት ተማሪዎች ነበርን። በሰፈሩ ስንሽከረከር «ኑ ግቡ» ብሎ የሚጠራን ሰዉ አጣን። ለካ ኑሮ በጣም ስለተወደደ እንደድሮ በየመንገዱ እየቆሙ «ብሉልን ጠጡልን» ማለት ቆሟል። «መቼም የዩኒቨርሲቲ ካፍቴሪያ ምግባችንን ትተን ባዶ ሆዳችንን አንመለስም» ብለን ወደ አንዱ ቤት አመራንና አንኳኳን። «እንኳን አደረሳቹህ ? » ስንል ፣ አንዲት ያኔ ወደ አርባ አመት የሚጠጋት እናት፣ በእጇ አንድ ሕጻን ልጅ ታቅፋ ወጣችና «ግቡ፣ ግቡ » አለችን በፈገግታ። የቤቱ በር ጠባብ ነበር። ጎንበስ ብለን ገባን። የነበረችዋን ጠረቤዛ ከበብናት። በትልቅ ትሪ እንጀራ ቀረበልን። ሴትየዋ ድስቱን አመጣችና ወጡን እንዳለ እንጀራዉ ላይ ደፋችዉ። ብዙ ጊዜም አልፈጀብንም ትሪዉን ጠረግነዉ። ከዚያም በትላልቅ ጣሳዎች ጠላ አመጣች። ለኔ ዉሃ ተሰጠኝ። ምን ልበላቹህ ምን የመሰለ መስተንግዶ ተደረገልን።

አሰመራን ሳስብ፣ የአስመራ ነዋሪዎችን ሳስብ፣ ያቺን ሴት አስባለሁ። ለእግዚአብሄር ፍቅር ስትል፣ እንግዳን በደስታ የምትቀበል ! ችግረኛ ናት፣ ነገር ግን ከፊቷ ውስጣዊ ሰላም ያላትና ሰዉን የምትወድ ትልቅ ሴት ነበረች!! ያኔ በትግሪኛ አልነበረም ያናገርናት። «የኔ ዘር ናቸዉ» ብላ አልነበረም ያስተናገደችን። ነገር ግን ትልቅ ሴት በመሆኗ እንጂ።

የማያልፍ ነገር የለምና የዪኒቨርሲቲ ትምህርታችንን አጠናቀን የምረቃችን ቀን ደረሰ። ባጽእ (ምጽዋ) በሕዝባዊ ሀርነት ኤርትራ ግንባር ሥር ከወደቀ በኋላ በምጽዋና በአስመራ መሃከል ከሚገኝ አንድ የከፍታ ቦታ፣ «ግራፒ» እንለዉ የነበረ ከሩቅ የሚተኮስ መድፍ በየጊዜው አስመራ ከተማ ላይ ያርፍ ነበር። በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ መብረሩን አቁሞ ነበር። የጦር አይሮፕላን ግን ማረፉን አላቆመም። በወቅቱ ደግሞ ሕወሃት በትግራይ ጥቃቶች ያደረግ ስለነበረ ከአስመራ አዲስ አበባ ያለው መንገድ ሙሉ ለሙሉ ተዘግቶ ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለማይበርም ቤተሰቦቻችን ለምረቃችን ከአዲስ አበባ ሊመጡ አልቻሉም። ስለዚህ የምረቃ ስነ ሥርዓታችን ብዙ አልጓጓንለትም ነበር። የምረቃችን ስነስርዓት ቀን በወንዶች ሽንት ቤት ዉስጥ ትልቅ ፈንጂ ፈነዳ። ያን ሰዓት ትልቅ ድንጋጤ በዩኒቨርሲቲ ጊቢ ዉስጥ ለጥቂት ደቂቃዎች ተፈጠረ። ወዲያዉ ሻቢያ የደስታ መግለጫ መልዕክት ማስተላለፉ ነዉ ብለን ቀልደን አለፍን። ከሩቅ በሚተኮስ መድፍ በግራፒ ተምሮ በፈንጂ መመረቅ ይሉታል ይሄ ነዉ።

ያ ቀን ከፈንጂ ፍንዳታዉ ሌላ የማልረሳዉ፣ በጣም ልቤን የነካና ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ዘላቂ ፍቅር እንዲኖረኝ ያደረገ አስደናቂ ነገር ሆነ። ቤተሰቦቼ ከአዲስ አበባ ስላልመጡ የምረቃ ልብሴን አዉልቄ ወደ ዶርሚተሪ ለማምራት እየተዘጋጀሁ ሳለ ድንገት፣ አንዲት ሴትዮ አበባ ይዘዉ ብቅ አሉ። ትዬ ዘይዳ ነበሩ። ትንሽ እንደቆየዉ ደግሞ አንዲት አሮጊት ሴትዩ ሌላ እቅፍ አበባ ይዘዉ መጡ። አደይ ጸሃይቱ ነበሩ። ሁለቱም አይተዋወቁም። በአራት አመት የአስመራ ቆይታዬ የተወዳጀኋቸዉ እናቶች ናችዉ። ያኔ ብቻዬን የሆንኩኝ መስሎኝ ነበር። ግን ከአንድም ሁለት እናቶች እንደ እናቴ ሆነዉ አበባ ይዘዉ በምረቃዬ ተገኙ። እነዚህ ሁለት እናቶች ዶሮ አርደዉ ቤታቸዉ ድግስ አዘጋጅተዉ ነበር። ሁለቱም ወደ ቤታቸዉ እንድመጣ ፈለጉ። ግራ ገባኝ። በኋላ አንዳቸዉ ጋር ምሳ ሰዓት ፤ ሌላኛዋ ጋር ደግሞ ሲመሽ ለእራት ሂጄ ከጓደኞቼ ጋር የተዘጋጀልኝን ድግስ ተካፈልኩ።

አስመራን ሳስብ፣ የአስመራን ሕዝብ ሳስብ ትዬ ዘይዳና አደይ ጸሃይቱን አስባለሁ። እነዚህ እናቶች በስጋ እናቶቼ አይደሉም። እንደነርሱ ትግሬ አይደለሁም። እንደነርሱ የኤርትራ ተወላጅ አይደለሁም። ነገር ግን የእነዚህን እናቶች የዋህነት፣ ፍቅርና ያላቸዉን ፈሪሃ እግዚአብሄር የሞላባቸው ትልቅ ሴቶች ናቸው። ደጎችና ለዘር ቦታ የማይሰጡ። እግዚአብሄር ባሉበት ቦታ ይባርካቸው።

የመጨረሻ አመት ተማሪ እያለን በአንድ ሃይ ስኩል፣ ለሶስት ወር ማስተማር ነበረብን። ባርካ ተብሎ በሚታወቅ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመደብኩኝ። የተመደብኩበት ክፍል አስተማሪ ክፍሉ በጣም ረባሽ ክፍል እንደሆነ አስጠነቀቀኝ። በጣም ፈራሁ። ነገር ግን ማስተማሩን ስጀምር አስተማሪው ከነገረኝ የተቃረነ ሁኔታ ነዉ ያየሁት። ተማሪዎቹ በጣም የሚያዳምጡ፣ በአክብሮት ከታያዙ ብዙ ሊሰሩ የሚችሉ ሆነዉ ነበር ያገኘኋቸዉ። አስተማሪያቸዉም ብሆን ጓደኞቼም ሆነዉ ነበር የተለያየነዉ። ያኔ ከተማዋ ችግር ላይ ነበረች። እንደዚያም ሆኖ ግን ከፊታቸዉ፣ ከሁኔታቸዉ ያየሁት ፍቅርንና ደስታን ነበር።

አሰመራን ሳስበ፣ የአስመራን ሕዝብ ሳስብ፣ ያኔ ወርቃማ ዩኒፎርም ለብሰዉ የማስተምራቸዉን፣ ያዳምጡኝና ሳስረዳቸዉ ፊቴን ያዩ የነበሩትን የባርካ ተማሪዎችን አስታወሳለሁ። እርግጥ ነዉ ብዙ የሚያሳዝኑ ነገሮች በአስመራ አይቻለሁ። እርግጥ ነዉ ከተማዋ ያኔ መለስተኛ ጦር ግንባር ነበረች። እርግጥ ነዉ በየጊዜዉ ሳይታሰብ በሻቢያ የሚተኮስ መድፍ ባልተጠበቀ ቦታ ያርፍ ስለነበረ ብዙ ሰዎች አልቀዋል። እርግጥ ነዉ በደርግ ወታደሮች የተሰሩ ብዙ ግፎች ነበሩ። ነገር ግን እንደዚያም ሆኖ፣ የሕዝቡ ፍቅር አሸንፎኝ ነዉ የጦር መሳሪያ በተሸከመ የጦር አይሮፕላን፣ መሳሪያ ላይ ተቀምጬ ከተማዋን የለቀኩት።

አሁንም ለአስመራ ትልቅ ፍቅር አለኝ። አሁንም አሰመራን ከአዲስ አበባ ቀጥሎ እንደከተማዬ ነዉ የማያት። አሁንም ያንን ሕዝብ እንደ ሕዝቤ ነዉ የማየዉ። አሁንም ኤርትራዉያንን ከተቀረዉ ኢትዮጵያዊ እንደተለዩ ተደርጎ ሲታይ አያስደስተኝም። በዚህም ምክንያት ነዉ የኤርትራን መገንጠል አጥብቄ የተቃወምኩት። አሁንም የምቃወመዉ። ለዚህም ነዉ ከመረብ ደቡብ ይኖሩ የነበሩ ወደ ኤርትራ ፣ ከመረብ ሰሜን ይኖሩ የነበሩ ደግሞ ከኤርትራ በግፍ እንዲባረሩ መደረጉ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነዉ የምለዉ። ለዚህ ነዉ የባድመ ጦርነት የወንድማማቾች የርስ በርስ ጦርነት እንጂ ከዉጭ ኃይላት ጋር የሚደረግ ጦርነት አይደለም የምለዉ።

የኢትዮጵያ ህዝብ መንቃት አለበት። የኢሕአዴግ መንግስት በባድመ ጦርነት እንዳደረገው አሁንም ኢትዮጵያዉያንን ለመገበር እየተዘጋጀ ያለ ይመስላል። በኦሮሚያ፣ በጎንደር በመሳሰሉት ቦታዎች እንዳየነው፣ ህዝባችን በኢሕአዴግ ታጣቂዎች የሚታረደዉና የሚገደለው አንሶ፣ እንደገና ከሻእቢያ ጋር በሚደረግ ጦርነት የሚማገድበት ምንም ምክንያት የለም። በመሆኑም ለኢሕአዴግ የጦርነት ጡሩምባ ጆሮዉን ይደፍን ዘንድ እመክራለሁ። ሕወሃት/ኢሕአዴግ ለአገርና ለሕዝብ አስባለሁ፣ ለአገርና ለሕዝብ ደህንነት እቆማለሁ የሚል ከሆነ፣ አገር ማለት መሬቱ ሳይሆን ህዝቡ ነውና ህዝብን መጀመሪያ ያክብር።

በሌላ በኩል ለዴሞክራሲ ቆመናል እያሉ፣ አለም በወንጀለኛነት የሚፈለገው የአረመኔው የኢሳያስ አፈወርቂን አገዛዝ መደገፍና እድሜዉንም ለማራዘም ደፋ ቀና ለሚሉ ተቃዋሚ ነን ባይዮችም ፣ መልእክት አለኝ። የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን የሚቃወም፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሚነቀፍና በሻእቢያ የተዘጋጀ ፔቲሽኖችን ኢትዮጵያዉያን እንዲፈርሙ እንዳንድ እንደ ግንቦት ሰባት ያሉ ደርጅቶች የቅስቀሳ ዘመቻ መጀመራቸው በጣም የሚያሳፍር ነው። የሻእቢያ መንፈስ በአሁኑ ወቅት የኤርትራ ህዝብ ጠላት ነው። የሻእቢያ መንፈስ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ነው። የሰብዓዊነት ጠላት ነው። ከሻእቢያ ጎን በቆምን ቁጥር በሻእቢያ እጅ ለሚፈሱ ደሞች ሁሉ ተጠያቂ ነው የምንሆነው። በመሆኑም ከሻእቢያ ጋር የምናደረገውን ዳንኪራ በአስቸኳይ ማቆም አለብን።

እኛና ጦርነት – ጊሼይ ጊሻ

ethiopia-eritrea-war-375x251

ጦርነት አስከፊ አውዳሚና ለሰው ልጆች በአጠቃላይ ሰቆቃ ውጤት ያለው ድርጊት መሆኑን በተግባር ያዩት ቀርቶ በፊልም የተመለከቱትም ቢሆኑ ሳይገነዘቡ የሚቀር አይመስለኝም። በአለም ላይ የተካሄዱ አስከፊ ጦርነቶችን ዛሬ የሆሊዉድ ሰዎች እነደመዝናኛ አድርገው በፊልም ሲያቀርቡት ትውልዱ ጦርነትን በመዝናኛ መልኩም ጭምር ቢመለከተው አስደናቂ አይሆንም። ዛሬ አሜሪካንና አውሮፓን በመሳሰሉ ሃገሮች እጂግ ዘመናዊ የሆኑ በአንድ ጊዜ በርካታ ሰዎችን ህይወት ለማጥፋት በሚያስችሉ መሳሪያዎች በየቀኑ የሽብር ተግባር ሲካሄድ የምናየው የጦርነት ፊልሞችና ያም የፈጠረው ለሰው ልጅ ክቡር ህይወት ደንታ ቢስነት ውጤት ነው። በጦርነት ሰበብ ያደጉ ማለትም (በቴክኒዎሎጂ)እንዳሉ ሁሉ ጦርነት ደግሞ ያቀጨጫቸው ሃገሮች በርካቶች ናቸው። ከነዚህ ሃገሮች አንድዋ ሃገራችን ኢትዮጵያ ናት ቢባል ማጋነን አይሆንም ። ታሪክ መመዝገብ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እንኳን ከሽህ በላይ ጦርነቶችን አስተናግዳላች። አሁን እየደከመ ባለው ትውልድ ዘመን እንኳን ከንጉሱ ስርአት ጀምሮ ቢያንስ ከሃያ በላይ የሚሆኑ ጦርነቶችን አስተናግደናል፥፥

አሁን ባለው ትውልደ እንኳን

በሻቢያና  በኢትዮጵያ መንግስት ( በንጉሱ በ ደርግ ዘመን የተካሄደው  ጦርነት )

በዋቆ ጉቱ የሚመራው የኦሮሞ ንቅናቄና በንጉሱ መንግስት የተካሄደው ጦርነት

ህዋሀት ኢሃዴግና በኢትዮጵያ መንግስት (ደርግ የተካሄደው ጦርነት

በኦሮሞ ነጻ አውጭ ድርጂትና  በደርግ መንግስት  የተካሄደው ጦርነት

በአፋር በሲዳማ ነጻአውጭዎችና በደርግ መንግስት  የተካሄደው ጦርነት

የታላቁዋ ሶማሊያ መስፋፋት አላማ በንጉሱ በደርግ ዘመን የተካሄደው ጦርነት

ኢህአፓና ኢዲዩ ከደርግ መንግስት ጋር ያደረጉት ጦርነትና እርስ በርሳቸውም ኢሃፓ ወያኔ እዲዩ ያካሄዱት ጦርነት

በወያኔ ኢሃዴግ የስልጣን ዘመን ደግሞ

በህዋሃት ኢሃዴግ መንግስትና  በ ኦ ኤል ኤፍ  መካከል የተደረገው ጦርነት ዛሬም የቀጠለው ጦርነት

በህዋሃት ኢሃዴግ መንግስትና በኦ ኤን ኤል ኤፍ  መካከል የተደረገው ጦርነት ዛሬም ያለው ጦርነት

በህዋሃት ኢሃዴግ መንግስትና በአልሻባብ እየተደረገ ያለው ጦርነት ዛሬም ያለው ጦርነት

በህወሃት ኢሃዴግ መንግስትና በሻቢያ በሚመራው የኢርትራ መንግስት መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት

አርበኞች ግንቦት ፯ ( በኤርትራ መንግስት ድጋፍ  የጀመረውና ትኩሱ የርስ በርስ ጦርነት

እነዚህ ጎልተው የታዩና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን  የሃገራችንን ዜጎች የበሉ ይህ ትውልድ የሚያውቃቸው ጦርነቶች ናቸው

ከሁሉም በላይ በየስራቱ መሳሪያ አንግበው ጦርነት ውስጥ ሳይገቡ በአምባገነናቱ መንግስታት በተለይም  በደርግና ህወሃት ኢሃዴግ   በሰላማዊ ዜጎች ላይ  በየጊዜው የሚፈጸመው እልቂት ኢትዮጵያና ጦርነትን ደም ማፍሰስን  ለይቶ ማየት እንደማይቻል ይህ ትውልድ በሚገባ የሚገነዘበው የመስለኛል። የኢቲዮጵያውያን የሃገር ምንነት  ስነልቦና የጦርነት ስነልቦና ቢሆን አያስገርምም ። እድሚያችሁ በ ፷ አመት ወይም ከዚአም በላይ ወይም በታች የሆናችሁ ጦርነት የሌለባት ኢትዮጵያን ስለማናውቃትና የኢትዮጵያን እንደሃገር መኖር በደም መፍሰስ ብቻ ስለምናስባት የችግሮች መፍቻ ሌሎች አማራጮችን ማየት ባንችል አያስደንቅም። በኛ ዘመንና በቀደምት አባቶቻችን መካከል ያለው ልዩነት እነርሱ ከጣሊያን ከቱርክ ከእንግሊዝ በአጠቃላይም ከቅኝ ገዝዎች ሃገራችንን ለመጠበቅ የከፈሉት መስዋእትነት ሲሆን በዘመናችን ይህ መሰሉ ጦርነት በጅ አዙርም ይሁን በቀጥታ  ከውጭ ሃይሎች   ጋር ተመሳሳይ ጦርነት ያካሄድነው የመስፋፋት አላማ ዪዛ ከተነሳችው ሶምሊያ ጋር ብቻ ነው። የተቀረው ግን እኛው በእኛው የተጨራረስንበት ጦርነት ነው። ምናልባት ዛሬ ኤሪትራ ሌላ ሃገር እንድትሆን እኛው ወስነን እኛው ፈቅደን የሌሎች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጻረሩ ሃይሎች መሳሪያ  እንድትሆን አድርገን የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች እርስ በርስ እንዲጨራረሱ ያመቻቸነውም እኛው ነን ። ስለዚህ ጦርነቱ የእርስ በርስ ነው። በእርስ በርስ ጦርነት ደግሞ ሃገር ቂምበቀል የቋጠረ ዚጎችን ይዛ ወደፊት መራመድ እንደማትችል እሙን ነው። ስሞኑን በወጣው የአለም አስሩ ደሃ አገሮች ተርታና ረሃብተኛ ከሚባሉት ውስጥም  መገኘታችን ባያስገርምም ያለን ሃብትና ክምችት ለኛ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢያችንም የተትርፈረፈ እንደሆነ ብዙ ጥናቶች ያሳያሉ።

 

እነሆ ዛሬም የርስበርሱ ጦርነት አታሞ ከየአቅጣጫው እየተጎሰመ ነው። ለጦርነቶች ሁሉ ደግሞ መንስኤ አላቸው። በተለይ የርስ በርስ ጦርነት ትልቁ ምክንያት በአንድ ሃገር ውስጥ ያለው ስራት ኢፍትሃዊነት ኢዲሞክራሲያዊነት መሆኑ አያጠያይቅም ። በህዝቦች መካከል መተማመን በመንግስታትና በህዝብ መካከል ጤናማ ግንኙነት እስካለ ድረስ የርስ በርሱ ጦርነት አይታሰብም ። ምክንያቱም በተፈጥሮ የሰው ልጅ በሰላም ኖሮ በሰላም መሞትን ዪመርጣል። ከሰው ልጆች ውስጥ ጥቂቶች ከግል ስግብግበነት ወይም በስልጣን ጥቅም ታውረው ዜጎችን እርስበርስ በማባላት የስልጣን ዘመናቸውን ለማርዘም በሚያድርጉት ኢፍትሃዊ ጉዞ ለኢፍትሃዊነታቸው የተለያዩ ካባዎችን በሚደርቱ የፕሮፓጋንዳ ሰዎቻቸው እየታጀበ የሚከናውን ድርጊት ነው። የርስ በርስ ጦርነት እንዲካሄድ የሚያስችለው ደግሞ ሁሉም የርስ በርስ ጦርነቶች በህዝብ ጥቅም ስም ወይም በሃገር ሉዓላዊነት ስም መደረጉ ነው።

እኔ ለአንተ ከሱ የተሻልኩ ነኝ ወይም እኔ ከሱ የበለጠ ለሃገር ተቆርቁዋሪ ነኝ በሚሉ ወገኖች አነሳሽነት የሚፈጠር ቀውስ ነው። አንተ የሚሉትን ህዝብ ግን ማዳመጥ የማይችሉ ግብዞች ስራ ውጤት ነው። ካልሆነማ ሁላችንም ለህዝብና ለሃገር ካሰብንማ የህዝብን ደም ከሚያፈስ የመፍትሄ ሃሳብ ወጣ ባልን ነበር ። የፖለቲካ መፍቻችን የሰውን ልጆች ክቡር ህይወት ሊሰጥ የማይገባ እስከሆነ ድረስና በጋራ ሃገራዊ ጥቅምና ትርፍ እስካላስገኘ ድረስ ለሃገር ብዬ ነው ለህዝብ ብዬ ነው የሚሉት የፕሮፓጋንዳ ሃረጎች ትርጉም የላቸውም።

ስለዚህም ሃገራችንን የምንወድ ኢትዮጵያውያን ስለኢትዮጵያ ህዝብ ወይም ስለሃገራችን ህዝብ አንድነት የምንጨነቅ ሁሉ ዛሬ ከሁሉም አቅጣጫ  እየተመታ ያለውን የጦርነት ከበሮ ማስቆም ታሪካዊ ግዴታ አለብን ። የሚካሄደው ጦርነት ባህርይን ጠንቅቆ መገንዘብና በውንድማማቾች መካከል የሚደረገው ጦርነት ማንም በአሸናፊነት ቢወጣ ኢትዮጵያዊነት በቂምና በቁርሾ ላይ ሊያብብ እንደማይችል መረዳት ተገቢ ይሆናል። ጦርነት አምባገነኖችን ብቻ ከስልጣን አውርዶ የሚቆም ክስተት አይደለም ማህበራዊ እሴትን የማናጋት ባህርዩ ከፍተኛ ነው። በተለይ ምንም እንኳን በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነኖች በሚፈጥሩት ደባና የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም በምክንያትም የተደገፈ ይሁን ያለምክንያት ጦርነቶችን መጫር ወይም መተናኮስ ባህሪያቸው ቢሆንም መንግስታቱ አምባገነኖች በመሆናቸው ብቻ በዘለቄታ ብሄራዊ ጥቅማችን ላይም ጭምር ከለየላቸው የሃገራችን ጠላቶች ጋር አለመቆማችንን    ማረጋገጡ አስፈላጊ ይሆናል፡

ስራቱ ከጊዜ ወደጊዜ ከመሻሻል ይልቅ እየዘቀጠና  በተለይም በተወሰኑ እኛ ብቻ አዋቂዎች ብለው በሚመጻደቁ ጥቂት ቡድኖች የማእከላዊነት አመራር  ወይም ሃላፊነት የጎደለው አክሂድ እየሄደ መሆኑ ግልጽ ነው። ሃላፊነት የጎደለው ስንል ደግሞ ለሰው ልጅ ህይውት ከሚሰጠው ክብርና ግምት አንስቶ ስለራሱም የወደፊት ህልውና ማሰብን ጭምር የሚያመለክት ቢሆንም በ እብሪትና በማን አለብኝነት የሚፈጥራቸውን ቀውሶች በሙሴ ህግ እጅን የቆረጠ እጅ አይንን ያጠፋ አይን ለሃገር ፖለቲካ መፍቻ ምላሽ ለመስጠት ከመሞከር ይልቅ ሃላፊነት የተሞላበትና የሚከፈለውም መስዋእትነት ዘለቂታና አስተማማኝ ውጤት ሊያመጣ እንዲችል ከጦርነት ባሽገር ያሉ ህዝባዊ ትግሎች እንደገና ሊፈተሹ ይገባል። ሊሎች የትግል ስልቶች የህይወት መስዋእትነት አያስከፍሉም ማለት እንዳልሆነ ባለፉት አመታት በተግባር አይተነዋል።  መስዋእትነቱ በጋራ መቆምን አስተምሮአል በጋራ በአንድ እስርቤት መከራን በመካፈል ለጋራ ትግል አነሳስቶአል። በህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት በሰከነ መንገድ ለማየት አስችሎአል። የስራቱ ደጋፊዎችን ጭምር ልባቸውን አሸፍቶአል። በተቃዋሚነት የተሰለፈው ጎራ ከድክመቱ አንሰራርቶ በጠንካራ አመራር  በስልት የተደገፈና  ህዝባዊ እምቢተኝነትን ትግል እያዳበረ ከሄደ የሃግራችን ትንሳኤ እሩቅ አይሆንም።

ስለዚህም በምንም መልኩ ቢሆን ለሃገራችን የምንጨነቅ ሁሉ ዳግም በሃገራችን የርስ በርስ ጦርነትም ሆነ በውጭ ሃይሎች በሚቃጣብን ወረራ  የኢትዮጵያዊ ወገን አስከሬን መሳለቂያችን ወይም ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ በማዋል ሃገራችን የምንወድ ለህዝባችን የቆምን አድርገን እራሳችንን ከቆጠርነው አሁንም እራሳችንን መመርመር የሚያስፈልግ ይመስለኛል።

የአምባገነኑን ስርዓት ለመታገል በተለያየ አቅጣጫ የተሰለፉ ወገኖች  ወይም በዚያች ሃገር ውስጥ  ማንኛውም አይነት ህዝብን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ክፍሎች ከሌሎች ተመሳሳይ ችግር ካላቸው ወገኖች ጋር ቢያንስ በጠረጰዛ ዙሪያ ተቀምጠው የጋራ ሃገራችንን እጣ ፈንታ ላይ ለመወያየት የሚያስችል ወኔና ድፍረት ከሌላቸው ከጦርነት የሚያገኙት ፍርፋሪ የወገኖቻቸውን ሰቆቃ ብቻ ነው።

እውነታው ዛሬ ህዝብ በስራቱ ተንገሽግሾአል። ስራቱም ብቻ ሳዪሆን ደጋፊው ጭምር ይህ ስራት መበስበሱንና መለውጥ ያለበት መሆኑን ዪፈልጋል።  ህዝብ ያጣው አንድ ነገር ነው፡ ስራቱን ተክቶ ሃገርን ለመምራት የሚችል የብዙዎችን ኢትዮጵያውያንን ጥያቀዎች ማእከል ያደረገና ሊዩነቶችን በበሰለ የፖለቲካ ጥበብ መፍታት የሚችል፡ የሃገሪቱን ሏላዊነት ለማስጠበቅና የኔ ብቻ መንገድ ከሚል እብሪት የጸዳ የፖለቲካ ሃይል ነው። ዛሬ ሁሉም እብሪተና በሆነበትና በኔ መንገድ ብቻ በሚል ፻ ድርጂት ወይም ስብስብ  ባለበት የሃገሩን ደህንነት በግርግር ለማንም አሳልፎ ላለመስጠት ሲል ብቻ በአምባገነኖች መዳፍ እየተደቆሰና መስዋእትነት እየከፈለ ይገኛል። በባህር ማዶ  ወይም በሃገር ውስጥ ተቀምጦ ተጨቁነሃል ተበድለሃል እያለ ብሶቱን የሚነግረውን አይደለም የሚፈልገው። ብሶቱን በህይወት ተሞክሮ ያውቀዋል፡ በዚህም ሆነ በዚያ ገፈቱን በቀጥታ እየተጎነጨው ነው። ያውቀዋል። ያጣው እምነት ነው። ብዙ ሲታለል የኖረ ህዝብ ነው። በስሙ ስንት ነገር እንደተሰራ ያውቃል። ዛረ ትውልዱም እየተቀየረ ሲመጣ የሃገር ፍቅር፡ የመስዋእትነት ልኩን እየተገነዘበም ይመጣል ። የኢንፎርሜሽን ዘመን በመሆኑም ብዙ ዪነጋገራል። በአጠቃላይም ትውልዱ የተሻለ ስራአት መምጣት እንዳለበት ቢፈልግም ስራቱን ለማምጣት በሚታገሉ ሃይሎች ላይ ኮንፊደንስ ገና አላደበረም ። እነሱም ቀልቡን በሚገባ አልሳቡትም። ለአንድ አላማ ቆመናል እያሉ በየቀኑ እየትማማሉ ተመልሰው እሳትና ጭድ ሆነው ሲታዩ እምነቱ ከየት ይመጣል፧ ለዚህም ነው መፍትሄው አንድብቻ የሚሆነው። በሃገራችን ለውጥ እንዲመጣ አምባገነኑም ስራት እንዲወገድ ያገባኛል የሚሉ ሁሉ በየፊናቸው የሚያደርጉትን ሩጫ አቁመው በጠረጰዛ ዙሪያ ተገናኝተው የልባቸውን መነጋገርና መተማመን ሲፈጥሩ ብቻ ነው። መሪ ነን ባዮች በማይተማመኑበት መንደር ህዝብ እንዲያምናቸው መጠበቅ ሞኝነት ነው። ለዚህም ነው ይህ ባልለየበት ሁኔታ በየትኛውም በኩል የሚጎሰመውን የጦርነት አታሞ አጥብቀን ልናወግዘው የሚገባን።

ጦርነት ምንጊዜም የህዝብ ምርጫ አይደለም። ጦርነት ምንጊዜም በህዝብ ስም ተለውሶ የሚቀርብ መርዝና በጥቂቶች ለጥቂቶች ሲባል የሚደረግ እኩይ ተግባር ነው።

 

ጊሼይ ጊሻ

በሕዝብ ደም የሥልጣን ዕድሜ ማርዘም! – የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ መግለጫ

shengoበዓለም ላይ ከሚታዩት መንግሥታት ውስጥ ሁለት ዓይነት መንግሥታት ጎልተው የሚታዩ ሲሆን፤ ሁለቱም ወደ ሥልጣን እርካብ የሚወጡበት መንገድ የተለያየ ነው። አንደኛው በሕዝብ ምርጫና ፍላጎት፣ በዴሞክራሲ መንገድ ሥልጣኑን ለተወሰነ ዓመት የሚረከብ ሲሆን ሌላው ደግሞ በራሱ ፍላጎትና ውሳኔ፣ የሕዝብን ድምፅና ፍላጎት ሳይሰማና ሳይጠይቅ በመሣሪያ ኃይል አስፈራርቶና ደምስሶ የሥልጣኑ ባለቤት የሚሆን ነው። የመጀመሪያውን የስልጣን ባለቤትነትን የሚከተል የግድ የዲሞክራሲን ሕግና ባህል የተቀበለና በዛም የሚያምን መሆንን፣ ችሎታንና ሕዝባዊነትን፣አገር ወዳድነትን ይጠይቃል።በሁለተኛው የስልጣን አወጣጥ ግን ሃይልን፣  –– [ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]— 

ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች ሆይ፤ እባካችሁ ከናዚ ሐኪሞች የደም ታሪክ ከመዘፈቅ ታቀቡ!

 

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ehtህሊናው ባሸነፈው ሐኪም አማካኝነት የሁለት መቶ አምሳ ልማታዊ ሐኪሞች ያየር ባየር ንግድ እንደገና አደባባይ ወጥቷል፡፡ ያያር ባየሩን ንግድ ከምድር ለማውረድ ከዚህ ህሊናው ካሸነፈው ጎበዝ በቀር ሁሉም ልማታዊ ሐኪሞች ኢትዮጵያውያኖች በወንጀል የሚከሱትን ቴድሮስ አድሃኖምን እሽኮኮ ተሸክመው ከወንበር ለመስቀል በውድም ሆነ በግድ ተስማምተዋል፡፡[1] ይህ ያየር ባየር ንግድና ወንጀለኛን በክትፎ ባበጠ ጫንቃ እሽኮኮ መሸከም የናዚ ሐኪሞችን ታሪክ አስታውሶኛል፡፡ በዘረኝነት በተገነባው የናዚ አገዛዝ ዘመን ከግማሽ በላይ የጀርመን ሐኪሞች ከሂትለር ጎን ተሰልፈው ነበር፡፡ [Nazi doctors list 2-4]. እንዲያውም ዶክተር ኢርነስት የተባሉ አይሁዳዊ ያልሆኑ ተመራማሪ “ያለ ሐኪሞች ተሳትፎ ሆሊኮስት እሚባለው የአይሁዶች እልቂት አይሳካም ነበር” ሲሉ በታወቀው የአለም አቀፍ የበሽታዎች ስርጪት መጽሔት (International Journal of Epidemiology) እ.ኤ.አ. በ2001 ዓ.ም ጽፈዋል፡፡ [5]

እንዳገራቸው ባህልና ሥርዓተ- አምልኮት ሐኪሞች የሚገቡት “ሂፖክራቲስ ኦዝ”[6] እሚባለው ቃል ኪዳን “ሥራዬን በንጹሕነትና በቅድስና ሳከናውን እኖራለሁ፤ ከአጭበርባሪነትና ሙስናዊ ተግባራት እቆጠባለሁ …” የሚሉ ፅንሰ-ሐሳቦች ይገኙበታል፡፡ እነዚህንና ሌሎችንም የቃል ኪዳን ፅንሰ-ሐሳቦች ብቻ ሳይሆን የሰውነትን ባህሪም ቡጭቅጭቅ አድርገው የበሉ ሐኪሞች ሂትለር እንደ መለስ ዜናዊ “ያይኑ ቀለም አላማረኝም” ያለውን ሁሉ አስፈጅተዋል፡፡ ሐኪሞቹ ሕዝብን ያስፈጁት ለናዚ አገዛዝ የሐሳብ፣ የመንፈስና የቁሳቁስ ድጋፍ ከመስጠት በተጨማሪ ሂትለር እሚጠላቸውን ዘሮች በማምከን፣ በጀርም በመበከል፣ በጋስ በማፈን፣ ጣጣቴ በመተኮስና በሌሎችም መንገዶች ሕዝብን በማሰቃየት ነበር፡፡ [7,8]

ከናዚው እልቂት ከአምሳ ዓመታት በኋላ በዘርኝነት ቦንብ የተገነባ አገዛዝ በኢትዮጵያ ተዘርግቷል፡፡ ይህ በዘርኝነት ቦንብ የተገነባ አገዛዝም በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በኦጋዴን፣ በጋምቤላ፣ በአሶሳ፣ በመተከል፣ በአምቦ፣ በወልቃይት፣ በሁመራ፣ በጉራ ፈርዳ፣ በአፋር፣ በሰቆጣ፣ በኮንሶ፣ በወለጋ፣ በሲዳሞና ሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች በዘራቸው ወይም በቋንቋቸው ምክንያት ዜጎች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡ የዚህ እልቂት መረጃም በመላው የኢትዮጵያ ምድር ተቀብሮ ይገኛል፡፡ ከተቀበረው መረጃ ኢምንቱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ ጪሮ አውጥቷል፡፡ [8] እንደ ሂዩማን ራይትስ ዋች[9]፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል[10]፣ ፍሪደም ዋች[11] የመሳሰሉት ድርጅቶችም ኢምንቱን መዝግበዋል፡፡ የዘር ማጥፋትን ወንጀል የሚከታተለው ጀኖሳድ ዋችም ነፍሰ-ገድዮች ላለም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጠይቋል፡፡[12] የጀርመኑ ዘረኛ አገዛዝ አይሁዶችን እንዳመከነው የኢትዮጵያው ዘረኛ አገዛዝም አማሮችን በማምከን ወንጀል ተከሷል፡፡ [14-16] አብዛኛው የዘረኝነት እልቂት መረጃ ግን ቆፍሮ እሚያወጣ ጋዜጠኛ፣ የቅሬት አካል ባለሙያ፣ የታሪክ ተመራማሪ፣ የሕግ  ባለሙያና ህሊናውን ያልገፈፈ ዜጋ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ዘርን ወይም ቋንቋን መሰረት አድርጎ በተለያዩ ዘዴዎች ያለቀው ሕዝብ ወደ ፊት በትክክል ሲቆጠር በሆሊኮስት ካለቀው ሕዝብ እንደሚበልጥ ይገመታል፡፡

ልማታዊ ሐኪሞች ሆይ! በጀርመን ሕዝብ  ከበረት ተከማችቶ እንደተጨፈጨፈው በኢትዮጵያም ሕዝብ በክልል ታጉሮ እየተጨፈጨፈ መሆኑን የምትገነዘቡ ይመስለኛል፡፡ ካልተገነዘባችሁም ጭፍጨፋውን ላለመረዳት አውቃችሁ ተኝታችኋል፡፡ ተገንዝባችሁ ጪጭ ካላችሁም ሳትሞቱ በሽንፍላ ከፈን ተከፍናችኋል፡፡ ጭፍጨፋ እንደሌለ የምትሰብኩትም እንደ መለስ ዜናዊና ቴድሮስ አድሃኖም ዓይናችሁን በጨው ታጥባችኋል፡፡ ዓይናችሁን በጨው የታጠባችሁት ሳይቀር በጮሌነት “አገዛዙ በድሎናል” በሚል ማመልከቻ የእንጀራ መጉረሻ መኖሪያ ፈቃዳችሁን በሰሜን አሜሪካ አግኝታችኋል፡፡ የማመልከቻችሁ ቀለም ሳይደርቅ በደሉን ካላችኋቸው ዘረኛ ነፍሰ-ገዳዮች ጀርባ በልማታዊ ሐኪምነት ቆማችሁ የሂፖክሪትስን መሐላ እንደ ናዚ ሐኪሞች ዘንችራችኋል፡፡

የሂፖክሪትስን መሐላ ከዘነቸራችሁት ሐኪሞች አንዳንዶቻችሁን ለምን ድሃ ከፍሎ ሊታከምበት የማይችል ዘመናዊ ሆስፒታል ከነፍሰ-ገዳዮች እግር እየወደቃችሁ እንደምትገነቡ ስንጠይቃችሁ “ውጪ አገር እየሄዱ የሚታከመውን ከበርቴዎች እዚያው ለማስቀረት” እሚል መልስ ሰጥታችኋል፡፡ ውጪ አገር እሚታከሙት ከበርቴዎች ደግሞ ነፍሰ-ገዳይዎች ወይም ከነፍሰ-ገዳይዎች ጋር የተሻረኩ ቱጃሮች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ነፍሰ-ገዳይዎችና ከነፍሰ-ገዳይ የተሻረኩ ቱጃሮች በድሃ ሥም የተረጠቡትንና ከድሃ ደም ሥር የመጠጡትን የደም ገንዘብ ለመካፍል ኪሳችሁን እንደ ካናዳ ኬሻ ከፍታችኋል፡፡ ከነፍሰ-ገዳዮች እየተዳራችሁ በጥይትና በግርፋት የሚያልቁትን ድሆች ረስታችኋል፡፡ ከአፋቸው እየሞለቀቁ በእንቁላልና በፍርፍር ያስተማሯችሁን እንጀራ ጋጋሪዋን ወይዘሮ ስለእናትን፣ እርፍ ጨባጩን አቶ አድማሱን፣ አምባሻ ጋጋሪዋን ወይዘሮ ሀዳስን፣ እንጨት ለቃሚዋን ወይዘሮ ዘይነባን፣ ቡና ለቃሚውን አቶ ረጋሳን፣ ቆሎ ሻጯን ወይዘሮ ሀሊማን፣ ጨጨብሳ አንጓቿን ወይዘሮ ጫልቱን፣ እንሰት ላጊውን አቶ ዘበርጋን፣ ጪቃ አቡኪውን አቶ ደሌቦን፣ ሸማ ሰሪውን አቶ ጫቦን ከድታችኋል፡፡

የናዚ ሐኪሞች የዘረኛውን የሂትለርን ጀኔራሎች እርካብ ሆነው ከፈረስ እንደሰቀሉ እናንተም በዘር  ከተለከፈው “መለስ ዜናዊ ጋር መስራት መባርክ ነው” ያለውን ቴድሮስ አድሐኖምን ባርጩማ ሆናችሁ ከወንበር ለመስቀል ትከሻችሁን ዝቅ አድርጋችሁ አጎብድዳችኋል፡፡ በነቴድሮስ አድሃኖም ጠባቂዎች ጭካኔ እየፈሰሰ ያለውን የአምቦዋን፣ የወልቃይቷን፣ የሁመራዋን፣ የጋንቤላንዋን፣ የወለጋዋን፣ የኮንሶንዋን፣ የኦጋዴኗንና የመተከሏን እናት እንባ ወደ ደም ቀይራችሁታል፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሕክምና ጥበባቸውን የወረሳችሁትን ዳሩ ግን በቂ ሕክምና ተነፍጓቸው ያለፉትን ፕሮፌሰር አስራትን መቃብር ውስጥ በጦር ወግታችኋል፡፡ በነቴድሮስ ወታደሮች በመላ አገሪቱ በተረሸኑት ዜጎች ቀልዳችኋል፡፡

ሂትለርና አብረውት ዘግናኙን ወንጀል የፈጠሙት ሐኪሞች በስብሰው ፈራርሰዋል፡፡ በአድርባይነትና በሆዳምነት ድምጣቸውን አጥፍተው የነበሩት ሐኪሞችም ትቢያ ሆነዋል፡፡ እርግጥ ነው ስስታሙ አንጎላቸው፣ ጨካኙ እጃቸው፣ ሰፊው ከርሳቸውና አጎብዳጁ ወገባቸው ከገደል እንደ ወደቀ ሸክላ  ብትንትን ብሏል፡፡ አይሁዶችን በማምከን ሥራ ተጠምደው የነበሩት እንደነ ዶክተር ራይተር ያሉ ሐኪሞችም ከሞቱ በኋላ ክብራቸው ተገፏል፡፡ [17] ዘግናኝ ታሪካቸው ግን ዘመን በገፋ ቁጥር የበለጠ እየጎላና እየተንቀለቀለ ይሄዳል፡፡ እንደ ናዚ ሐኪሞች ሁሉ የእኔና የእናንተም ስስታም አንጎል፣ ሞጭላፊ እጅ፣ ቀላዋጭ ዓይን፣ ሰፊ ከርስ፣ አዙሮ እማያይ አንገትና አጎብዳጅ ወገብ ነገ ተበጣጥሶ ትቢያ ይሆናል፡፡ የማይበጣጠሰውና ትቢያ እማይሆነው እንዲያውም ዘመን በገፋ ቁጥር እየጎላ እሚሄደው ታሪካችን ይሆናል፡፡ እኛ እየተሽሎኮሎክን ያመለጥን ብንመስልም ታሪክ ድምጡን አጥፍቶ በመመዝገብና በመጠረዝ ላይ ይገኛል፡፡ በታሪክ መዝጋቢነትም  እንዳለመታደል እኛም እንደ ጀርመኖች የወንጀለኞችና ያልተባረኩ ሐኪሞች ዝርዝር ይኖረናል፡፡

ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች ሆይ! ሕዝብን ደም ካስለቀሱ ወንጀለኞች ጋር መሽኮርመሙ ይቅርባችሁ፡፡ ስስትና አድርባይነት የሚያብከነክነውን ሥጋችሁን ለማርካት ስትሉ እባካችሁ ዓይናችሁን ጨፍናችሁ ከናዚ ሐኪሞች የደም ታሪክ ከመዘፈቅ ታቀቡ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ዋቢ

 1. ቃለ መጠይቅ ከዶክተር ግርማ መኮንን ጋር http://ethsat.com/esat-radio-wed-15-june-2016/ (Last accessed on June 18, 2016)
 2. List of Nazi MDS, https://en.wikipedia.org/wiki/List_of_Nazi_doctors (Last acessed on June 18, 2016)
 3. The Nazi Docotrs: http://www.auschwitz.dk/doctors.htm (Last accessed on June 18, 2016)
 4. Nazi doctors: http://faculty.webster.edu/woolflm/nazidocsandothers.html ((Last accessed on June 18, 2016)
 5. Earnest: The Third Reich—German physicians between resistance and participation, Int. J. Epidemiol.(2001)30 (1):37-42.doi: 10.1093/ije/30.1.37  http://ije.oxfordjournals.org/content/30/1/37.full
 6. Hippocratic Oath (400 BC) as translated by by Francis Adams (1849)http://www.britannica.com/topic/Hippocratic-oath ((Last accessed on June 18, 2016)
 7. The Nazi Doctors and the Nuremberg Code: Human Rights in Human Experimentation” Oxford University Press. May 7, 1992. Page 19 ((Last accessed on June 18, 2016)
 8. 13. Exhibition Examines Scientists’ Complicity In Nazi-Era Atrocities” The New York Times. Author, Warren E. Leary. November 10, 1992 ((Last accessed on June 18, 2016) (Last accessed on June 18, 2016)
 9. ሰብአዊ መብት ጉባኤ ሪፖርት 2008 ዓ.ም. http://ehrco.org/wp-content/uploads/2016/06/HRCO-141st-Special-Report-Amharic-Sene-01-2008.pdf (Last accessed on June 18, 2016)
 10. Protest Crack Down killed hundreds, Ethiopia, Human Rights Watch https://www.hrw.org/news/2016/06/15/ethiopia-protest-crackdown-killed-hundreds (Last accessed on June 18, 2016)
 11. Extrajudicial executions, Arbitray arests and detntions Amnesty International

 https://www.amnesty.org/en/countries/africa/ethiopia/report-ethiopia/ (Last accessed on June 18, 2016)

 1. Ethiopia, Police Open fire on Protesters https://freedomhouse.org/article/ethiopia-police-open-fire-protesters (Last accessed on June 18, 2016)

13 . Genocide watch documents on Ethiopia     http://www.genocidewatch.org/ethiopia.html (Last accessed on June 18, 2016)

 1. Three million Amhars Missing, Berhanu Abegaz https://www.youtube.com/watch?v=3-g-YWYBdbM ((Last accessed on June 18, 2016)
 2. Three Million Amara are Missing: An Analysis based on the 1994 and the 2007 Ethiopian Population Censuses, Berhanu Abegaz, http://ethiomedia.com/101facts/4513 9 ((Last accessed on June 18, 2016)
 3. Human right violation of Amharas Muluken Tesfaw http://video.ethsat.com/?p=24983 ((Last accessed on June 19, 2016)
 4. Experts Re-Examine Dr. Reiter, His Syndrome and His Nazi Past

https://partners.nytimes.com/library/national/science/health/030700hth-doctors.html ((Last accessed on June 18, 2016)

 

ሰኔ ሁለት ሺ ስምንት ዓ. ም.

ግንቦት ሰባት ከኤርትራ ሊለቅ ይችላል- ኖአሚን በጋሻው

 

ኖአሚን በጋሻው   (ሎንግ ቢች – ካሊፎርኒያ)

naominbegashaw@gmail.com

Ginbot-arbegnoch.gif

ሁለት ራዲዮ ጣቢያዎች አሉ። ከዲሲ የሚተላለፉ። የግንቦት ሰባት አመራር የሆኑትን አቶ ንአመን ዘለቀን አቅርበው አወያይተው ነበር። የነጻነት ራዲዮና የአቶ አበበ በለው አዲስ ድምጽ ራዲዮ። በሁለቱራዲዮዎች መካከል ትልቅ ልዩነቶች ይታያሉ። አንደኛው፣ የነፃነት ራዲዮ፣ የወያኔው ፋና ራዲዮ ነው የሚመስለው። የፕሮፖጋንዳ ራዲዮ። ገና አዳምጬ ሳልጨርስ ነው የዘጋሁት። ሁለተኛው የአዲስ ድምጽራዲዮ ግን፣ ለሁለት ሰዓት የተላለፈ ቢሆንም ሙሉዉን አደመጥኩት። የተለያዩ አመለካከቶች የተስተናገዱበት ዘመናዊ ራዲዮ ጣቢያ ነው።
በፕሮፖጋንዲስቱ የነጻነት ራዲዮ በተላለፈው ላይ ብዙ ጊዜ አላጠፋም። የአዲስ ድምጽ ራዲዮ ላይ ግን በተላለፈው ላይ አንዳንድ ሐሳብ መጨመር እፈልጋለሁ።
አቶ ንአመን፣ አቶ አበበ ጥያቄዎችን እንኳን እስኪጨርሱ ለመታገስ ትግስት ጎድሏቸው በመሃል ጣልቃ እየገቡ ፣ እየደጋገሙ ያቋርጡ ነበር። ዶናልድ ትራምፕን ነው የመሰሉኝ።
“በምን ምክንያት ነው ግንቦት ሰባት ሻእቢያን በመደገፍ ፔቲሽን ለማስፈረም የሚንቀሳቀሰው ?” የሚል ጥያቄ ነው መጀመሪያ አቶ ንአመን የቀርበላቸው። ሲመልሱም ሶስት ምክንያቶች አስቀምጡ። አንደኛውምክንያታቸው “በኤርትራ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ካለው አይበለጥም። Double standard ፣ hypocrisy አለ ” የሚል ነበር። “ኮሚሽኑ ፣ ኢትዮጵያ የሰዎች መብት የሚከበርባት አገር ናት ብሎቢናገርና እናንተ ያንን ብትቃወሙ እሺ። ግን ስለኢትዮጵያ የተናገረው ነገር የለም። ከኢትዮጵያ ጋር ምን ግንኙነት አለው ?” ብለው ሲጠየቁ አቶ ንአመን መልስ አልነበራቸው። በሻእቢያ ላይ የደረሰውማበረታቻ ሆኖን፣ “ወያኔዎችም ለፍርድ የሚቀርቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የበለጠ መስራት አለብን፤ ከኤርትራዉያኖች መማር አለብን” ማለት ሲገባ “ወያኔዎች የሚሰሩት ግፍ ስላልተካተተ የሻእቢያግፍ ለምን ይነሳል” ብሎ መንጨርጨር አስፈላጊ አልነበረም።

 

ሁለተኛው አቶ ንአመን ያቀረቡት ምክንያት በጣም የሚያስቅና የሚያስተዛዝብ ነበር፡፡ “እንዴ …ምን ነካቸው አቶ ንአምን ? “ ብዬ እጆቼን ራሴ ላይ እስካደረግ ድረስ ነበር የደነገጥኩት። “ኮሚሽኑበኤርትራ ያሉ ጥሩ ነገሮችን ያላገናዘበ ነው። በኤርትራ ማህበረሰባዊ ፍትህ (social justice) አለ። እንደዉም እዚያ ሄጄ ያነጋገርኳቸው ኤርትራዉያን፣ ነጻ ምርጫ ቢደረግ ኢሳያስን ነው የምንመርጠውነው ያሉኝ” ሲሉ ነበር፣ ሰው በላውን ኢሳያስ አፈወርቂን፣ ሳያፍሩና አይናቸውን በጨው አጥበው እንደ መልአክ ሊያቀርቡልን የሞከሩት።

 

እነዚህ ሁለት ምክንያቶች ፈር የለቀቁና ዉሃ የማይቋጥሩ፣ ደካማ ምክንያቶች ናቸው። ግንቦት ሰባቶች በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኤርትራዊያን ብቻ ሳይሆን ለስብእና ትልቅ ንቀት እንዳላቸው ነው ያሳዩት።

 

አቶ ንአመን ያቀረቡት ሶስተኛ ምክንያት፣ በኔ አስተሳሰብ ትልቁና ዋና ምክንያታቸው ነው። “ኤርትራ ብቸኛ ደጋፊያችን ናት። ሻእቢያ ተዳከመ ማለት እኛ ተዳከምን ማለት ነው” ሲሉ በትክክልጭንቀታቸውን ነው ለሕዝብ ይፋ ያደረጉት። በርግጥም ሻእቢያ ከተመታ ፣ ሻእቢያ ከሞተ፣ የግንቦት ሰባት መጨረሻ ነው የሚሆነው። ግንቦት ሰባት እድል ፈንታዉ ሙሉ ለሙሉ ከሻእቢያ ጋር ስላደረገባለው አቅሙና ጉልበቱ ሻእቢያ ከመጠበቅ ዉጭ ሌላ አማራጭ አይኖረዉም። ለነርሱ ሻእቢያን መደገፍ የሕልዉና ጉዳይ ነው። ለዚህም ዶር ብርሃኑ ነጋ፣ በዲሲ ባደረጉት ስብስባ፣ ለሻእቢያ ድጋፍእንዲሰጥ፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን የሚቃወም ፊርማ እንዲፈረም፣ ተማጽኖ ያቀረቡት። ለዚህም ነው ግንቦት ሰባት እንደ ድርጅት፣ የወልቃይት ጠገዴ ፣ ለሱዳን የሚሰጠው መሬት የመሳሰሉትንበርካታ ኢትዮጵያዊና አገራዊ ጉዳዮችን ያካተቱ ፔትሽኖችን የማሰባሰብ ሥራ በተሰራበት ወቅት፣ አንዳቸውም ጊዜ “ይሄን ፔቲሽን ፈርሙ “ ብሎ ፣ መግለጫ አውጥቶ የቀሰቀሰበት ሁኔታ ሳይኖር፣ ሻእቢያንለመደገፍ በአዝማችነት ፔቲሽኖችን እያስፈረመ ያለው። ለዚህም ነው፣ እንደ አቶ ንአምን ያሉ አመራሮች በተለያዩ ሜዲያዎች በመቅረብ (media blitz) ከፍተኛ “ሻእቢያዊ” ቅስቀሳ ማድረግ የተያያዙት።

 

በነገራችን ላይ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን የኤርትራ መሪዎችን በሰው ዘር ማጥፋት ቢከስም ዉሳኔው የመጨረሻ ዉሳኔ አይደለም። ዉሳኔው 47 አገራት ( ኢትዮጵያን ጨመሮ12 ከአፍሪካ፣ 8 ከአሜሪካ፣ 13 ከእሲያና 14 ከአዉሮፓ) ባሉበት በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባዬ ይታያል። ጉባዬዉም የአጣሪ ኮሚሽኑን ሪፖርት ተመልክቶ ዉሳኔ የሚሰጠው ከአንድሁለት ሳምንት በኋላ ሲሆን፣ በአለም ዙሪያ ሁሉ ያሉ ኤርትራዉያን ጉብዬው፣ የኮሚሽኑን ዉሳኔ እንዲያፀድቅ ግፊት ለማድረግ፣ በጄኔቫ በሂን 23 ቀን 2016 ዓ.ም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል።

 

ጉባዬው ዉሳኔውን ካጸደቀ፣ ወደ ተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ያመራል። የጸጥታው ምክር ቤትም የጉባዬዉን ዉሳኔ በማጽደቅ የአለም ፍርድ ቤት አቶ ኢሳያስን እና ጓዶቻቸዉን ለፍርድእንዲቀርቡ መመሪያ ይሰጣል። ክሱ በጸጥታው ምክር ቤት የሚወሰን በመሆኑም እነ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂን ከነሚሎሶቬች ምድብ ይቀመጣሉ።
በመጨረሻ አንድ ነጥብ ላስቀምጥ። ሻእቢያ ከተባበሩት መንግስታት ጋር በሰብአዊ መብት፣ በፍትህና በሕግ የበላይነት …ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ፍቃደኛ ከሆነ፣ ግንቦት ሰባቶችና ሻእቢያእንደተመኙት፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉብኤ፣ የአጣሪ ኮሚሽኑን ዉሳኔ ሊቀለብሰው ይችላል።

ሻእቢያዎች የሰብአዊ መብት አጣሪ ኮሚሽኑን ለማነጋገርም ሆነ ወደ ኤርትራ ገብቶ ማጣራት እንዲያደርግ ፍቃድ ለመስጠት ከጅምሩ ፍቃደኛ አልነበሩም። ሪፖርቱ ከወጣ በኋላም፣ ኮሚሽኑን መሳደብናማውገዝ ነበር የመጀመሪያው ስራቸው። ሆኖም ጥቂት ቀናት እንዳለፉ፣ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ንግግራቸውን እያስተካከሉ የመጡ ይመስላል። በዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ኦስማን ሣሌ በኩልለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባዬ በላኩት ደብዳቤ፣ አገራቸው በሰብዓዊ መብት መከበር ዙሪያ ለመወያየት ዝግጁ እንደሆነች ነው የገለጹት። “ I wish to assure the Council that Eritrea shall remain open and committed to constructive engagement to promote and protect human rights and fundamental freedoms and Eritrea will lend its hands to make this body more credible and relevant to all stakeholders.” ነበር ባለስልጣኑ ያሉት። ይሄ በሻእቢያ ታሪክ ተሰምቶ የማያወቅ፣ ሻእቢያአፍንጫው ተይዞ ፣ ተገዶ የደረሰበት አቋም ነው።

 

ይሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ሻእቢያ ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉብዬ ጋር አብሮ ለመስራት ከወሰነ፣ እንደፈለገ ሊሆን አይችልም ማለት ነው። በተለይም በተባበሩት መንግስታት፣ በአፍሪካሕብረት በመሳሰሉት የማይወደዱና የሚያስነቅፉ ተግባራቱን ማቆም ይኖርበታል።

የጸጥታው ምክር ቤት እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ2009 ያወጣው ፣ ” ሕግ 1907″ የተባለው፣ በኤርትራና በሶማሊያ ዙሪያ ያስቀመጣቸው ነጥቦች አሉ። አንዱ ኤርትራ በአካባቢዋ ያሉ አገራትመንግስታትን የሚቃወሙ የትጠቅ ትግል የሚያደርጉ ድርጅቶችን መደገፍና መርዳት እንድታቆም የሚጠይቅ ነው። ከዚህም የተነሳ ሻእቢያ፣ ፈልጎ ሳይሆን ተገዶ በኤርትራ ያሉ የትጥቅ ትግል የሚያደረጉተቃዋሚዎችን ሊያግድ ይችላል።

 

በመሆኑም በነ አቶ ኢሳያስ ላይ የተወሰነው ዉሳኔ፣ ተቀለበሰም፣ አልተቀለበሰም፣ ግንቦት ሰባትና ሌሎች አስመራ ያሉ ደርጅቶች፣ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነው የወደቁት። በኤርትራ በኩል እናደርገዋለንየሚሉት ትግል መጨረሻም ሊሆን ይችላል። ወይም አቶ ኢሳያስ ለፍርድ ቀርቦ ፣ ግንቦት ሰባቶች ወዳጃችን ያሉትን በማጣት ዜሮ ይገባሉ፤ አሊያም ኢሳያስ ለራሱ ሲል፣ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋርመስማማት ስላለበት ይሽጣቸዋል። በዚህም በዚያ ኤርትራ ያሉ ተቃዋሚዎች ቀለጡ ማለት ነው።

 

ለዚህም ነው በኢትዮጵያ ለዉጥ ለማምጣት የሚደረገው ትግል፣ በምን አይነት ሁኔታ ከሻእቢያ ጋር መያያዝ የለበትም አይሉ ብዙ ሲከራከሩ የነበሩት። ሻእቢያ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደንታ የለውም።በማናቸዉም ጊዜ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ከገደል ላይ ለጥቁሙ ሲል የሚፈጠፍጥ ነው። ታማኝነት ብሎ ነገር በታሪኩ አያውቅም።የኢሕዓፓ ወዳጅ ነበር፤ ወዲያው ተገልብጦ ወደ ወያኔ ሄደ። ብዙምሳይቆይ ደግሞ ከወያኔ ጋር ደመኛ ሆነ። ነገርም ግንቦት ሰባቶች እንደ ቁሻሻ ይወረወራቸዋል።

 

በተለይም በዳያስፖራ ብዙ ወገኖች ለግንቦት ሰባት ድጋፍ እንዳላቸው ይታወቃል። አብዛኛው የግንቦት ሰባት ደጋፊ ድጋፍ የሚሰጠው በኤርትራ በኩል ያለው ሁኔታ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ተደረጎስለተነገረው ነው። አገሩን ከመዉደዱ፣ ለወያኔ ካለው ጥላቻ የተነሳ ነው።

 

ሆኖም ለሕዝቡ እየተነገረ ያለው ነገር ዉሸት ነው።ህዝቡ  በሂደት እዉነቱን ይረዳና አይኖቹን ከሻእቢያ አንስቶ ወደ ራሱ ይመልሳል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ”

ብዙዎች እንደሚሉት ኢትዮጵያ ዉስጥ ለዉጥ የሚመጣው በኢትዮጵያዉያን ነው። መመካት እና ማደራጀት የሚያስፈለገው የኢትዮጵያን ህዝብ ነው። እኛዉ ኢትዮጵያዉያን በቂ ነን።

 

( አቶ አበበ ከአቶ ንአምን ጋር ያደረጉትን ለመስማት 36 ደቂቃ ወደ ፊት ይሂዱ)

 

http://www.addisdimts.com/radio-show-for-june-122016-2/

የኢትዮጵያ-ኤርትራ የጦርነት ጨዋታዎች፣

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ይህን አስቂ ኝ (አስለቃሽ) ትአይንት  (ትያትር)  ፊልም ከዚህ ቀደም አላየነውምን?

Wargames Amharic

 

 

 

 

 

 

 

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 ዘ-ህወሀት የሕዝብን ስሜት ለማስቀየስ (ለማወናበድ ) ስለሚያካሂደው የጦርነት ጨዋታ  ትችት በጽሁፍ አቅርቤ ነበር፡፡

ዘ-ህወሀት ማለት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ስም ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተመዝግቦ የሚገኝ አሸባሪ ድርጅት ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 አሁን በህይወት የሌለው የዘ-ህወሀት መሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመለኮስ እና ከግብጽ ጋር ደግሞ የውኃ ጦርነት ለማካሄድ የጦርነት ነጋሪት በመጎሰም ስለጦርነት አይቀሬነት ድምጹን ከፍ አድርጎ በማጉላት የወሬ ክኩን ይሰልቅ ነበር፡፡

በዚህም መሰረት ይኸው በአሁኑ ጊዜ እ.ኤ.አ ሰኔ 2016 ወደለመድነው የጦርነት አረንቋ ተመልሰን ለመዘፈቅ አሀዱ/አንድ በማለት ጀምረናል፡፡

ባለፉት ጥቂት ቀናት እንደገና በድጋሜ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ስለ”ጦርነት” ሰበካ፣ ስለጦርነት ሟርት እና ስለጦርነት ከበሮ ድለቃ ሌት ከቀን እየተለፈፈልን ሳንወድ በግድ እንድናዳምጥ በመደረግ ላይ እንገኛለን፡፡

እናም ይህንን የሕዝብ ስሜት/ቀልብ ማስቀየሻ ጦርነት እንደገና መመልከት ይኖርብናልን?

የዘ-ህወሀት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ጌታቸው “አፈ ጮሌው” ረዳ እንዲህ በሏል፣ “በሁለቱም ወገኖች በኩል ከፍተኛ የሆነ እልቂት ተፈጽሟል፣ በይበልጥ ደግሞ በኤርትራ በኩል ያለው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን ስንወስድ ቆይተናል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ እስከ አሁን ድረስ ስንወስዳቸው ከቆዩት እርምጃዎች በዓይነቱ እና በመጠኑ ከፍ ያለ እርምጃ መውሰድ በጣም ጠቃሚ ነገር ስለሆነ አስተማሪ የሆነ እርምጃ ወስደናል፡፡“

ኤርትራ በበኩሏ 200 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በመግደል ከ300 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ቁስለኛ አድርጊያለሁ የሚል መግለጫ ይፋ አድርጋለች፡፡

የካሊፎርኒያ ግዛት የዩኤስ አሜሪካ ታዋቂ የምክር ቤት አባል/ሴናተር የሆኑት ሂራም ጆሀንሰን ከብዙ ጊዜ በፊት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ጦርነት በሚመጣበት ጊዜ የመጀመሪያው የጥቃት ሰለባ የሚሆነው “እውነት” ነው፡፡“

ሁለት የጦርነት ተፋላሚ ቡድኖች በአንድ ዓይነት “እውነት” ላይ የጋራ ስምምነት ሲያደርጉ የምመለከት ከሆነ “እውነት” የመጀመሪያ እና ብቸኛ የጥቃት ሰለባ ሆኖ ስለመቆየቱ መገረም የምጀምር ይሆናል፡፡

እንደዚሁም ሁሉ የጠነባን ዓይጥ ማሽተት እጀምራለሁ፡፡ የጠነባን ዓይጥ ገና ከ10 ሺ ሜትሮች ርቀት ላይ ማሽተት እችላለሁ፡፡ ያ ሽታም  በኢትዮጵያ-ኤርትራን ጦርነት በሚባለው ላይ ተንሳፎ ይገኛል! (እፍ እፍ እፍ!!!)

በእርግጥ የጆሀንሰን ቁም ነገር የጦርነት ሰለባ መርህ አነጋገር  በጦርነት ተጫዋቾች ላይ አይሰራም፡፡

ለበርካታ ዓመታት ሳስተውለው እንደቆየሁት የዘ-ህወሀት አመራሮች ከሕዝብ ጋር መጥፎ የሆነ የግንኙነት አባዜ ላይ እንደወደቁ አድርገው እራሳቸውን በሚቆጥሩበት ጊዜ ለዚያ ማስቀየሻ ዘዴ ጦርነትን ያውጃሉ፡፡

ዘ-ህወሀት በህዝብ ላይ የሚፈጽመውን ሰብአዊ ወንጀል፣ ሙስና፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀም እና ሰላማዊ ዜጎችን መጨቆንን ለመደበቅ ሲያስብ የአገር ውስጥ እና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ስሜት ለማስቀየስ የሚያጋልጡትን መጥፎ ዜናዎችን ማፈን እና የሕዝብን ስሜት የማስቀየስ መንገድ እንደሚጠቀም እገምታለሁ፡፡

ያለፉት ጥቂት ሳምንታት ለዘ-ህወሀት መጥፎ ዜናዎች እንደነበሩ ምንም ዓይነት ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም፡፡

ባለፈው ሳምንት የዩኤስ አሜሪካ የቦንድ እና የአክሲዮን ልውውጥ ኮሚሽን ዘ-ህወሀት ህገወጥ ወንጀለኛ በሆነ መልኩ ከደጋፊዎቹ እና ጥቅም አገኛለሁ ብለው ለቦንድ ግዥ ክፍያ ሲፈጽሙ ከቆዩት ኢትዮ-አሜሪካውያን 6.5 ሚሊዮን ዶላር በህገወጥ መልክ ዘርፎ በመገኘቱ ያወናበደዉን ገንዘብ ከነወለዱ እንዲመልስ ቅጣት ጥሎበታል፡፡ ዘ-ህወሀቶች ኮሚሽኑ ለሚያቋቁመው አስተዳዳሪ እ.ኤ.አ ሀምሌ 8/2016 ከማለፉ በፊት መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡

ይህ ድርጊት ለዘ-ህወሀት ትልቅ ውርደት እና የኢትዮጵያውያንን እና የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ኪስ በማራቆት በአፍሪካ ታላቅ ግድብ እሰራለሁ በማለት መቋጫ የሌለው ዲስኩሩን ሲያሰማ በነበረው እና አሁን በህይወት በሌለው በወሮበላ ዘራፊው መሪ በአምባገነኑ መላስ ትውስታ ላይ ታላቅ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ ነገር ነው፡፡

ባልተመዘገበ እና ህገወጥ በሆነ የቦንድ ሽያጭ በማጭበርበር ግዙፍ የሆነ ግድብ በአፍሪካ እገነባለሁ ማለትን እስቲ አስቡት ጎበዝ! ቦንድ የማጭበርበር እኩይ ምግባሩን መከላከያ ዘዴ መሆኗ ነውን?

በዩኤስ አሜሪካ ሕግ መሰረት ያልተመዘገበ ቦንድ መሸጥ ሕገ ወጥ ነው በማለት ከሶስት ዓመታት ገደማ በፊት የተናገርኩ ሲሆን ከተናገርኩ ከሶስት ዓመታት በኋላ የዘ-ህወሀት መሪዎች የማጭበርበር አባዜ የተጠናወታቸው በመሆኑ ከማሰሮው ውስጥ እጃቸውን እንዳስገቡ እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ ማሰብ እችላለሁ፡፡

የሚሰማ ጆሮ እና የሚያስተውል አእምሮ የላቸውም እንጅ እ.ኤ.አ ግንቦት 8/2013 ፊት ለፊት እና በቀጥታ ነግሪያቸው ነበር፡፡ ይህንን ነገር አታድርጉ! ያልተመዘገበ ቦንድ አትሽጡ! በዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራል እና የአካባቢ መንግስታት ሕግ መሰረት ወንጀል ነው ብዬ ነግሪያቸው ነበር፡፡ ወንጀልን አትስሩ፣ ከጊዜ በኋላ አደጋው የሚያንዣብብ እና የሚያስጠይቃችሁ ይሆናል በማለት በግልጽ ተናግሬ ነበር፡፡

እንደተናገርኩት ከሶስት ዓመታት በኋላ ያልተመዘገበ ቦንድ ሽያጭ (ወንጀል ነው፣ የ1933 የቦንድ ድንጋጌ ክፍል 20 (b)ን ይመልከቱ) ወንጀል ስለሆነ ማጅራታችዉን ተያዙ፡፡

ሆኖም ግን የዘ-ህወሀት ያልተመዘገበ ቦንድ ዋና ሻጮች የወንጀል ቅጣቱን በማጭበርበር አንደተለመደው ሊያልፉት አልቻሉም፡፡

በእርግጥ አላለፉትምን?

የዘ-ህወሀት መሪዎች ለበርካታ ዓመታት ያህል ሰብአዊ መብቶችን እየደፈጠጡ ምንም ዓይነት ተጠያቂ ሳይሆኑ ደረታቸውን ነፍተው ተቀምጠው እንደሚገኙት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በአሜሪካ ሕጎች ላይም አፍንጫቸውን በመንፋት ከወንጀል ተጠያቂነት የሚያመልጡ መስሎ ታይቷቸዋል፡፡

በምንም ዓይነት መልኩ ሊሆንላቸው አልቻለም፡፡

ጉዳዩ በኮሚሽኑ (SEC) ግልጽ እና ይፋ ከሆነ በኋላ የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው ሂዩማን ራይትስ ዎች (ሂራዎ)/Human Rights Watch (HRW) “ጭካኔ የተመላበት እርምጃ፡ ለኢትዮጵያ ኦሮሞዎች ተቃውሞ የተሰጠ የግድያ እና እስራት ምላሽ“ በሚል ርዕስ ትልቅ ዘገባ አቅርቧል፡፡

ያ ዘገባ “ከመጠን ያለፈ እና አላስፈላጊ የሆነ የጥላቻ ኃይል መጠቀም እና ዜጎችን በጅምላ በቁጥጥር ስር የማዋል፣ መጥፎ የእስር ቤት አያያዝ፣ የሰላማዊ አመጽ እንቅስቃሴውን ለማኮላሸት የመረጃ ምንጮችን መቆጣጠር“ በማለት ዝርዝሩን አቅርቧል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በማስመልከት የሂራዎ/HRW የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክር የሆኑት ሌዝሊ ሌፍኮው እንዲህ ብለው ነበር፣ “የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች የሰው ልጆችን ህይወት ከቁብ ሳይቆጥሩ የጭካኔ ተኩስ በመክፈት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን፣ አርሶ አደሮችን እና ሌሎችን ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል፡፡“

ለሰው ልጆች ህይወት ምንም ዓይነት ቁብ ሳይሰጡ በሰላማዊ ተቃዋሚ ስብስብ ላይ የጭካኔ ተኩስ መክፈት በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ ሰብአዊ ወንጀል ነው፡፡ ይህንን የምለው ለታሪክ ምዝገባ ብዬ ነው፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 የዘ-ህወሀት ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በአመጹ ላይ የተገደሉት ሕዝቦች “ሁከት እና ብጥብጥን ዓላማ ያደረገ የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል በመፍጠር ሞዴል አርሰ አደሮችን፣ የህዝብ መሪዎችን እና ሌሎች በክልሉ የሚኖሩትን የጎሳ ቡድኖች መግደል በመጀመራቸው ነበር” ብሏል፡፡

የሚገርም ነገር እኮ ነው ጎበዝ! በመንገድ ላይ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ የሁለተኛ ደረጃ እምቦቃቅላ ተማሪዎች እና የኮሌጅ ተማሪዎች በምን መስፈርት እና መለኪያ ነው “የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል” ሊባሉ የሚችሉት? ወያኔ በእራሱ የፍርሀት ምዕናብ እየፈጠረ በህዝብ ላይ የሚነዛው ሽብር ካልሆነ ሌላ ምን ሊባል ይችላል?

ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት ምድር ፑፍ የተባለው ድራጎን (ዘንዶ)፣ ሳንዲ እየተባለች የምትጠራውን ተንቀሳቃሽ ሲኒማ ልጃገረድ ውሸት እና ቅጥፈት ወደሚነገርባት ምድር የወሰደበትን ታሪክ  አስታወሰኝ፡፡ ሳንዲ እዚያ ከደረሰች በኋላ በሬ ወለደ እያለ የሚናገረውን ፕናክዮንን አገኘችው፡፡

ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት ምድር ፑፍ እና ሳንዲ ማንም አይቷቸው የማያውቅ ቀይ እና ሰማያዊ ላም እንዲሁም ቀይ እና ነጭ ዝሆንም አዩ፡፡

13 ወራት ሙሉ ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት በዘ-ህወሀት ቁጥጥር ስር ባለችው ኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ልጆች እና የኮሌጅ ተማሪዎች ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር እንደተዘጋጀ ቡድን ተቆጥረው “የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል” ሆነው ይታያሉ፡፡

ኢትዮጵያ 13 ወራት ሙሉ የፀሐይ ብርሀን የሚፈነጥቅባት ሀገር መሆኗን ነበር እኔ የማስታውሰው፡፡

በነገራችን ላይ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ሌሎች እ.ኤ.አ በ2007 በኬንያ ተደርጎ በነበረው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት ተከስቶ በነበረው ውዝግብ ወደ 2000 ገደማ በሚሆኑ ሰላማዊ ኬንያውያን ዜጎች እልቂት ላይ እጃቸው አለበት በሚል የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እ.ኤአ. በ2012 ክስ መስርቶባቸው ነበር፡፡

ሂራዎ/HRW በኦሮሞ ሰላማዊ አመጸኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው እልቂት እንዲጣራ ነጻ የሆነ አጣሪ አካል እንዲቋቋም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት እንደተለመደው የዝሆን ጆሮ (የጅብ ሆድስ አለኝ) ይስጠኝ በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል፡፡

ዘ-ህወሀት ወደ 20 ሚሊዮን ገደማ የሚሆነውን ህዝብ እያሰቃየ ያለውን የረሀብ ሁኔታ አያያዝ በሚመለከት እያደረገ ስላለው ፍጹም የሆነ ብቃትየለሽነት እና ይኸ አውዳሚ የሆነ ረሀብ በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ሰቆቃ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እይታ ደብቆ ለማቆየት እያደረገ ባለው አሳፋሪ ጥረት የህዝብ ግንኙነት ስራው በመጥፎ ሁኔታ ተበላሽቶበታል፡፡

ከዩኤስኤአይዲ/USAID እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ የድህነት ወትዋች አቃጣሪዎች መጥፎ ሸፍጥ ጋር በመተባበር ዘ-ህወሀት ድርቁ ካጠቃቸው አካባቢዎች ምንም ዓይነት መረጃ እንዳይወጣ በማድረጉ እና ጋዜጠኞች ወደ አካባቢው በመንቀሳቀስ እውነታውን ለእራሳቸው እና ለህዝቡ ፈልፍለው እንዳያወጡ በመከልከሉ ደባ ተሳክቶላቸዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ ዘ-ህወሀት ስለረሀቡ ሁኔታ ስለጠቅላላ ተጠያቂነቱ እና ግዴለሽነቱ፣ ለብቃትየለሽነቱ እና ወንጀለኛነቱ ምንም ነገር ባለመሆኑ ስኬታማ ሆኗል፡፡ (ለዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ ለጋይሌ ኢ. ስሚዝ የጻፍኩትን ደብዳቤ ይመልከቱ፡፡)

ዘ-ህወሀት ሁሉንም መጥፎ ዜናዎች ሁሉ ፍጹም በሆነ መልኩ ለምን እንደሚያፍን ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡

ዘ-ህወሀት የህዝብን ስሜት ለማስቀየስ መጥፎ ዜናዎችን በማፈን የጦርነት ወሬዎችን ከማምረት እና የጦርነት ነጋሪት ከመጎሰም የተሻለ ምን የተሻለ ስልት ሊኖረው ይችላል?

በዘ-ህወሀት እና በስተሰሜን በኩል ባሉት ጠላቶቹ መካከል የሚካሄደው ጦርነት በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ይደረግ እንደነበረው የጽጌረዳ ጦርነት ዓይነት ነው፡፡ የተለያዩ አባላት በሆኑት በአንድ ቤተሰብ መካከል የሚደረግ ጦርነት የውስጥ ጦርነት ነው፡፡

ዘ-ህወሀት እና ጠላቶቼ ናቸው እያለ የሚወነጅላቸው ኃይሎች በወንድማማችነት በአንድ ላይ ሆነው ለበርካታ ዓመታት በመዋጋት ወታደራዊውን አገዛዝ በማስወገድ ስልጣንን ተቆጣጠሩ፡፡ በወታደራዊ ኦፕሬሽን እና በህዝብ ግንኙት ስራ በአንድ ላይ ሆነው በመረዳዳት በወታደራዊ ጓደኝነት ሲታገሉ ቆይተው ነበር፡፡

በርካታ የዘ-ህወሀት አመራሮች ከጠላቶቻቸው ጋር የቤተሰብ እና የስጋ ዝምድና ትስስር እንዳላቸው ከበቂ በላይ ማስረጃ ሊቀርብበት የሚችል ጉዳይ ነው፡፡

ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ1991 ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ አሁን እየከሰሷቸው ካሉት ጋር አስቂኝ በሆነ የመድረክ ላይ ተውኔት በደስታ ስልጣንን ተካፍለው እንደ አበደ ውሻ ጭራቸውን በመቆለፍ ቆዩ፡፡ ያ ሁኑታ ግን እ.ኤ.አ በ1993-94 ላይ ተቋረጠ፡፡

እ.ኤ.አ ከ1998-2000 ባለው ጊዜ ውስጥ ሁለቱ የጦር ጓደኛሞች በድንበር ጦርነት ተጠመዱ፡፡ ኤርትራውያን የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት በመጣስ የኢትዮጵያን ግዛት ተቆጣጠሩ፡፡ ሆኖም ግን በግጭቱ ከ70 እስከ 120 ሺ የሚገመት የወታደሮች እና የሲቪል ዜጎች ህይወት ከተገበረ በኋላ ተቆጣጥረውት ከነበረው ግዛት በኃይል ተባረሩ፡፡

አሁን በህይወት የሌለው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስቡ አለቃ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ወዲያውኑ የድል ዜናን አወጀ፣ እናም በዓለም አቀፍ የሽምግልና እርቅ ሰበብ በተሰላ የፖለቲካ የሸፍጥ ስሌት እና በሀገር ክዳት ወረውት የነበረውን የሀገሪቱን አንጡራ ግዛት ተመልሶ ኤርትራውያኖች እንዲወስዱት በመፍቀድ የተንበርካኪነቱን የመድረክ ላይ ተውኔት አከናወነ፡፡

አምባገነኑ መለስ ጠንካራ የሕግ መከላከል ጥረትን ማድረግ ሲችል የሽምግልና የዕርቅ ስምምነቱ የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ አያወጣም በማለት የሀገርን ጉዳይ እንደተራ ነገር በመቁጠር ጉዳዩን አጣጣለው፡፡

በአሁኑ ጊዜ የቀድሞ የጦር ጓደኛሞች በጦርነት ላይ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ የሌባ ጣቶቻቸውን አንዳቸው በአንዳቸው ላይ በመቀሰር የተለመደ ተራ ቅጥፈታቸውን በማራመድ ላይ ናቸው፡፡

ሆኖም ግን እነዚህ ውሸት እንጅ እውነት በአፋቸው የማይገባ ኃይሎች በእርግጠኝነት ጦርነት ያካሂዳሉ ወይስ ደግሞ የጦርነት ጨዋታ በመጫወት ላይ ነው የሚገኙት?

ሆኖም ግን ለምን እርስ በእርሳቸው እንደሚዋጉ ትክክለኛውን ነገር አይናገሩም፡፡

አንድ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳቀረበው ውንጀላ ከሆነ የኤርትራ መሪዎች በሰው ልጆች ላይ የመብት ረገጣ ማለትም ማሰቃየትን፣ ግድያ እና በባርነት መያዝን ጨምሮ የሰብአዊ መብትን ይደፈጥጣሉ የሚል ዘገባ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የምታቀርበው ኢትዮጵያ ናት የሚለው የመድረክ ላይ ትወና የተተወነው በኢትዮጵያ ነው በማለት በኢትዮጵያ ከምስክሮች የሚሰበሰበው መረጃ እንዳትረጋጋ ለማደረግ ጥረት ለምታደርገው ሀገር ለኤርትራ ጥሩ የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ እንድታገኝ አስችሏታል፡፡

የተመድ ዘገባ ለጦርነቱ መንስኤ መሆን ችሏልን?

“ሀገሮች ለምን እንደሚዋጉ“ በሚል ርዕስ ሪቻርድ ኔድ ሌቦው በ2010 በጻፉት መጽሐፋቸው ላይ አራት ታሪካዊ ዓላማዎች፡ ፍርሀት፣ ፍላጎት፣ ዝና እና በቀል በሚል መንግስታት ጦርነትን እንዲቀሰቅሱ ይመሯቸዋል በማለት የክርክር ጭብጣቸውን አቅርበዋል፡፡ አብዛኞቹ ጦርነቶች ለዝና እና ቀደም ሲል አንዱ መንግስት በጠላቱ ላይ ድልን በመቀዳጀት ግዛቱን ያስለቀቀው ከሆነ ያንን ለመበቀል ሲባል የሚደረጉ ናቸው በማለት ይሞግታሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ዝና፣ በቀል እና ግዛትን ለመያዝ ሲባል በሁለቱ መንግስታት መካከል ለጦርነት መንስኤ ሊሆን ይችላልን?

እኔ የማደርጋቸው የአምባገነንነት እና ጦርነት ጥናቶች በእነዚህ ነገሮች የሚቀሰቀስ ሌላ የተለዋጭ ገለጸ ሀሳብ ያቀርባሉ፡፡

“የጦርነትን ካርድ” ማውጣት በአምባገነኖች የእጅ መጽሐፍ ውስጥ ያለ አሮጌው የማጭበርበር ዘዴ ነው፡፡

የእጅ መጽሐፉ እንዲህ ይላል፣ “የህዝብ ጥላቻ ሲመጣ ጦርነትን አውጅ፡፡ እውነተኛ ወይም ደግሞ የውሸት የማስመሰያ ጦርነት አውጅ፡፡ ምንም ዓይነት ችግር የለውም፡፡ ስለጦርነት አውራ፡፡ የጦርነት ቅስቀሳን ሆን ብለህ አሰራጭ፡፡ የጦርነት ከበሮ ምታ፡፡ የጦርነት ጨዋታዎችን ተጫወት፡፡“

ግን ለምን ጦርነት?

ምክንያቱም ጦርነት የተረጋገጠ እና በተግባር የተፈተነ የህዝብ ስሜት ማስቀዬሻ ፍቱን ዘዴ ነው!

ከሮማ ነገስታት ጀምሮ እስከ አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ የጦርነት ጌቶች እና ትናንሽ አምላኮች የጦርነት ካርድን ተጫውተዋል፣ እናም በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመቆየት የግዛት ዘመናቸውን ለማስቀጠል ሲሉ በህዝቡ ልብ ውስጥ የአርበኝነት ትኩሳትን ይቀሰቅሳሉ፡፡

በምዕተ ዓመታት የጦርነት ቴክኖሎጂው ሊቀየር ይችላል ሆኖም ግን የማታለል ማሽኑ፣ ማጭበርበሩ፣ ሸፍጡ እና የጦርነት ናፋቂዎች የከበሮ ድለቃ ዜማ እና አፈጻጸም እስከ አሁንም ድረስ ያው ነው፡፡

አምባገነኖች ሁልጊዜ በጦርነት ቃላት ይጀምራሉ፣ እናም ህዝቦቻቸውን በጦርነት ውሸት ፕሮፓጋንዳዎች፣ ፍብረካዎች እና ስለጦርነት ዝርዝር መረጃዎች የሌለው እና አሳሳች መረጃዎችን በማቅረብ በፕሮፓጋንዳ ጎርፍ እንዲጥለቀለቅ ድርጋሉ፡፡

አምባገነኖች በጦርነት መጀመሪያ አካባቢ ሊተነበይ የሚችል የአካሄድ ስርዓትን ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ ስለጦርነቱ አስፈላጊነት ግዙፍ የሆነ መግለጫ ለህዝብ ያቀርባሉ፣ እንደዚሁም ሁሉ በሀገር ውስጥ ታላቅ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ተስፋን በመሰነቅ በጠላታቸው ላይ ግዙፍ የሆነ ጥላሸት የመቀባት ዕኩይ ምግባርን ያራምዳሉ፡፡

ታምራዊ በሆነ መልኩ የእናት ሀገር ፍቅርን ከመቅጽበት ይለብሳሉ፣ በሰንደቅ ዓላማዎቻቸው ውስጥ ይጠቀለላሉ እናም ኃያል አርበኞች ይሆናሉ፡፡ አርበኝነትን ለማነሳሳት በመሞከር የተወሰዱ ግዛቶችንም እናስመልሳለን በማለት ቃል ይገባሉ፡፡

አምባገነኖች የህዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ዓይን ባወጣ መልኩ በሀገር ወዳድ ብሄራዊነት እና የትምክህት እንቅስቃሴዎችን ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ ስለማይቀረው የጦርነት ጥቃት፣ ስለማይታዩ ጠላቶች፣ ሳይታሰብ ስለሚመጡ አሸባሪዎች፣ ስለሀገር ሉዓላዊነት መደፈር እና ስለሌሎች ነገሮችም ሁሉ ገደብ የሌለው ፕሮፓጋንዳ እና ቅስቀሳ በማካሄድ በህዝቡ ዘንድ ፍርሀት እንዲነግስ ያደርጋሉ፡፡

በሚያገኙት በማንኛውም አጋጣሚ ሁሉ ህዝቡ ስሜታዊ ሆኖ በጠላቶቻቸው ላይ በቁጣ እንዲነሳ በመቀስቀስ የህዝብን ድጋፍ ለማግኘት አሳፋሪ እና የሌለ ታሪክ በመፍጠር እነርሱ አገር ወዳድ አርበኛ የእነርሱ ተቃዋሚዎች እና ጠላቶች ደግሞ ምንም ዓይነት የሀገር ወዳድነት አርበኛነት የሌላቸው አድርገው ይፈርጃሉ፡፡

ሁሉም ነገር ሲከሽፍ እና ሲወድቅ አምባገነኖች በህዝቡ ላይ ፍርሀት እና ስሜታዊነት እንዲነግሱ በማድረግ የህዝብን ስሜት በማስቀየስ እነርሱ ከተዘፈቁበት ሰብአዊ ወንጀል እና አምባገነናዊ አገዛዝ ለማምለጥ ጥረት ያደርጋሉ፡፡

አብዛኛውን ጊዜ የጦርነት ቃላት ስለአርበኝነት እና ስሜታዊነት በመቀስቀስ ከመክሰስ እና ጥላሸት ከመቀባት የበለጠ ኃይል የላቸውም፡፡ ወደ ሌላ ወደየትም ፈቀቅ ሳይሉ ስም በማጥፋት እና ጥላሸት በመቀባት ላይ ብቻ ተወስነው ይቀራሉ፡፡

ሆኖም ግን አምባገነኖች አብዛኛውን ጊዜ በጦር ሜዳ አውድ ውስጥ የጥይት ጭሆት ካቆመም በህዋላ ስለጦርነት ማውራት እና የጦርነት ነጋሪት መጎሰምን አጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡

ሆኖም ግን ጦርነት ለአምባገነኖች የማታለያ ሀሳብ ነው፡፡

የአምባገነኖች የመኖር ህልውና በጀመሩት ጦርነት የማሸነፍ ዝንባሌ የሚወሰን ይሆናል፡፡

በጦርነት የአምባገነኖች መሸነፍ ማለት የህልውናቸው ፍጻሜ ማለት ነው፡፡

የተሸነፉ አምባገነኖች አብዛኛውን ጊዜ በመፈንቅለ መንግስት ወይም ደግሞ በሌሎች ህዝባዊ አመጾች ሊወገዱ ይችላሉ፡፡ አምባገነኖች በሚሸነፉበት በእያንዳንዱ ጦርነት የመሰደድ፣ የመታሰር እና የመሞት ዕድላቸው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡

ጥቂት የአፍሪካ አምባገነኖች ዓይን ባወጣ መልኩ ያለምንም ተጨባጭነት ሁኔታ በለኮሱት ጦርነት ቢሸነፉም ቅሉ ለበርካታ ጊዚያት በስልጣን ላይ ተጣብቀው ቆይተዋል፡፡ በእርግጥ ሽንፈታቸውን ለምክንያት እና ለይቅርታ በመጠቀም ህዝቦቻቸውን ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ለመግዛት ይጠቀሙበታል፡፡ ጠላቶቻቸውን እንደ ጭራቅ በመቁጠር በእራሳቸው ህዝቦች ላይ እንደማስፈራሪያ በመጠቀም ህዝቡ ለጥ ገጥ ብሎ እንዲገዛላቸው ይጠቀሙበታል ፡፡

አምባገነኖች ስለሚጭሩት የጦርነት እሳት እውነታነት የሂትለር ቀኝ እጅ ከነበረው ከኸርማን ጎሪንግ የበለጠ እውነታውን ያረጋገጠ በዚህ ዓለም ላይ የለም፡፡ ኸርማን እ.ኤ.አ በ1945 ኑረምበርግ በተሰየመው የዓለም አቀፍ ችሎት ላይ ቆሞ ሲጠየቅ እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡

“በተፈጥሮ ተራው ህዝብ ጦርነትን አይፈልግም፡፡ ይኸ ነገር ግንዛቤ የተወሰደበት ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከሁሉም በላይ የሀገሪቱ መሪዎች ናቸው ፖሊሲውን የሚወስኑት እናም በዚያ አቅጣጫ ህዝቡን የሚስቡት… ድምጽ ወይስ ድምጽ አልባ [ዴሞክራሲያዊ ወይስ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ያልሆነ መንግስት] ህዝቡ ምንጊዜም ቢሆን መሪዎች በሚያስቡት ነገር ላይ ሊመጣ ይችላል፡፡ ያ ቀላል ነገር ነው፡፡ ሁላችሁም ልትሰሩት የምትችሉት ነገር ቢኖር ጥቃት እየደረሰባቸው መሆናቸውን ንገሯቸው፣ እናም የአርበኝነት ጉዳይን ቸል በማለት ሀገሪቱን ለከፍተኛ አደጋ በሚጥሉት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ውግዘት አካሂዱ፡፡ ይህ ጉዳይ በእያንዳንዱ ሀገር ሙሉ በሙሉ ይሰራል፡፡“

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 አሁን በህይወት የሌለው የወሮበላ ዘራፊው ሀዋሃት መሪ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የጎሪንግን አባባል እንዳለ በመውሰድ እንዲህ በማለት የገደል ማሚቶውን አሰምቶ ነበር፡

“አሁን በቅርቡ ኤርትራ አልሸባብን እና በሀገር ውስጥ የበቀሉትን አውዳሚ ኃይሎች በማሰልጠን በሀገራችን ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ ትገኛለች፡፡ ሆኖም ግን ግብጽ ለዚህ የሽብር ድርጊት በዋናነት ከጀርባ ቆማለች፡፡ እስከ አሁን ድረስ የነበረን ስልት ልማታችንን በማፋጠን የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስከበር ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ዝም ብለን በቸልታ ቆመን ምንም ዓይነት መከላከል ሳናደርግ የምናይበት ሁኔታ የለም፡፡ ዝም ብሎ መከላከል የሌለው ድርጊትን እያራመድን መቆየትን እንደ ብቸኛ አማራጭ አድርገን ለመቀጠል አንችልም፡፡ ስለዚህ የኤርትራ ህዝብ አምባገነኑን አገዛዝ ለማስወገድ የሚያደርገው ትግል እንዲፋጠን መንገድ መቀየስ አለብን፡፡ ይህንን ስንል እንዲሁ ዘው ብለን በሀገራቸው ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ እንገባለን ማለት አይደለም፣ ሆኖም ግን ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነውን እጃችንን ረዘም አድርገን ወደዚያ መላክ ይኖርብናል፡፡ የኤርትራ መንግስት በእኛ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚሞክር ከሆነ እኛም ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ እንሰጣለን“ ነበር ያለው አፈር ይቅለለውና፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2006 የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረትን ከሶማሊያ ለማስወጣት እና አልሻባብን ለማጥፋት 843 ቀናት ያህል ጦሩን እዚያ ካቆየ በኋላ ስኬታማ ሳይሆን ሀፍረቱን ተከናንቦ ሰራዊቱን ከሶማሊያ በሚያስወጣበት ወቅት በተመሳሳይ መልኩ እንዲህ በማለት ነበር የጦርነት አመክንዮውን የገለጸው፡

“አካላዊ ጉዳትን በሚመለከት ወይም ደግሞ የወረራው አካላዊ ሁኔታን በሚመለከት ካለፈው የክረምት ወቅት ጀምሮ ምን እንደተደረገ ለመግለጽ የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የታጠቁ ኃይሎችን በማሰልጠን፣ በማስታጠቅ እና ሰርገው እንዲገቡ በማድረግ ላይ ቆይቷል፡፡ እነዚህ ኃይሎች በኢትዮጵያ ውስጥ መረጋጋት እንዳይኖር ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩት እነዚህ ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው በመግባት ከደህንነት ኃይሎች ጋር ግብግብ በመግጠም ላይ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህልም የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት እነዚህን ሰርጎ ገብ ኃይሎች  አሰልጥኗል፣ አስታጥቋል፣ እስከ ድንበሩ ድረስ ለሰርጎ ገቦቹ የመጠለያ እና የትራንስፖርት አገልግሎትም አቅርቧል፡፡ በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ ላይ የጥቃት እርምጃ ለመውሰድ ቀጥተኛ በሆነ መንገድ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ድርጊት ካለፈው የክረምት ወቅት ጀምሮ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ እስከ አሁንም ድረስ ቀጥሏል፡፡“ 

እ.ኤ.አ በ2009 ጭራውን በእግሮቹ መካከል በመወተፍ ከሶማሊያ ሲወጣ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የፈላስፋ ሸፍጡን በመያዝ እንዲህ በማለት ጉራውን ቸረቸረ፣ “ለኢትዮጵያ አዎንታዊ አመላካከት የሌለው የሶማሊያ ህዝብ መንግስት ቢኖርም እንኳ በአሁኑ ጊዜ ያለው ሁኔታ የተሻለ ነው፡፡ በሶማሊያ ውስጥ የተረጋጋ መንግስት እንዲኖር ማድረግ ብሄራዊ ፍላጎታችን ነው፡፡“        

ይኸው አምባገነን ሰው እ.ኤ.አ ታህሳስ 2006 አሸባሪዎችን ከሶማሊያ ውስጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድል በማድረግ አባርረን እንመለሳለን ብሎ ነበር፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የሰራው ነገር ቢኖር በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሲቪል ሶማሊያውያን ሞትና እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ የጅምላ ተፈናቃይ የመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡

በሶማሊያ ውስጥ ሄደው የሞቱ የመለስ ዜናዊ የጦር ወታደሮች ብዛት ስንት ነው?

እ.ኤ.አ በ2009 አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከይስሙላው ፓርላማ ፊት በመቅረብ እንዲህ በማለት ተናገረ፣ “በሶማሊያ ውስጥ ስንት ወታደሮች እንደሞቱ ፓርላማው ማወቅ አስፈላጊው አይደለም፡፡“

አምባገነኖች ህዝቦቻቸውን የጦርነት እራት እንዲሆኑ በማድረግ በጦርነቱ ምን ያህል ወታደሮች እንደሞቱ ማወቅ የእናንተ ስራ አይደለም በማለት መናገር ይችላሉ፡፡

እንደዚሁም ሁሉ በአሁኑ ጊዜ ዘ-ሀወሀት እና ኤርትራ የጦርነት ከበሮ በመደለቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በጦርነት ከበሮው የድምጽ ቅላጼ በመደነስ ላይ ይገኛሉ፡፡

በእርግጥ አስገዳጁ የጦርነት ማስጠንቀቂያ ሁልጊዜ ከሚጠበቁት ሲመጣ የቆየ ነው፡፡

የዩኤስ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “ጥላቻው በአስቸኳይ እንዲቆም” እና “ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሁለቱም መረጋጋትን ለማስፈን እንዲተባበሩ እና በቀጣናው ዘላቂ የሆነ ሰላም እንዲመጣ” በማለት የተለመደ የተዕማጽኖ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ባንኪሙን ኢትዮጵያ እና ኤርትራ “ከሰባት ዓመታት በፊት የድንበር ውዝግባቸውን በሰላም እንዲፈቱ የቋጨውን ሕግ በማክበር ከማንኛውም ጠብ አጫሪነትን ከሚቀሰቅሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል“ የሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዋና ጥያቄ ሆኖ መነሳት ያለበት ጉዳይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ጦርነት ነው ወይስ ደግሞ የጦርነት ጨዋታዎች ናቸው የሚለው ነው፡፡

እኔ የማውቀው ነገር የለኝም!

ለእኔ የጦርነት ጨዋታዎችን እያካሄዱ ይመስለኛል፡፡

ሁለቱም ወገኖች በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ገደልን አቆሰልን እያሉ በመለፍለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ለእኔ ሁሉም ነገር አጠራጣሪ ነው፡፡

እኔ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር ቢኖር ይህንን የሰርከስ ተውኔት ቀደም ሲል የተመለከትኩት መሆኑን ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 ዘ-ህወሀት ሲፈጽም የነበረውን የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ፣ ሙስና፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀምን እና ሌሎችንም ዕኩይ ድርጊቶች መፈጸሙን በማስመልከት ለመደበቅ እና የኢትዮጵያን ህዝብ እና የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ስሜት በማስቀየስ ላይ ዒላማ ያደረገ ባለሶስት ዙር የፖለቲካ ጦርነቶችን የፕሮፓጋንዳ ሰርከስ ተመልክቻለሁ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉም ስለጦርነቱ እየተደረገ ያለው ንግግር እና የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ ዘ-ህወሀትን ጥልቅ በሆነ መንገድ ሊያስወግድ የሚችል ድብቅ የህልውና ጦርነት ነውን?

በእኔ አስተያየት ግብታዊ በሆነ ህዝባዊ አመጽ ምክንያት ዘ-ህወሀት አእምሮው በማይቀረው ስልጣኑን እና ቁጥጥሩን የማጣት አባዜ ውስጥ ተዘፍቆ ስለሚገኝ የማስመሰያ የፍርሀት ጋጋታ ጨዋታ ነው፡፡ ሁሉም የጦርነት ዲስኩሮች በድብቅ አእምሮ ውስጥ ተሸብቦ ለሚገኘው አገዛዝ ጥልቅ ፍርሀት እና መሰረታዊ የሆነ የፖለቲካ ብስጭትን የሚገልጹ ናቸው፡፡

ፕሬዚዳንት ኬኔዲ በአንድ ወቅት እንዲህ የሚል ምልከታ አድርገው ነበር፣ “ቀደም ሲል  በቂልነት በነብር ጀርባ ላይ ሆነው መጋለብን ይፈልጉ የነበሩ ሰዎች መጨረሻቸው በነብሩ ሆድ ውስጥ ሆነው መገኘት ነው፡፡“

ወደፊት በተቆጣ እና በተራበ የነብር ሆድ ውስጥ ሆኖ የመገኘት ዕድል የዘ-ህወሀትን አመራሮች እና ደጋፊዎች ሌት ቀን እንቅልፍ ነስቶ ሁሉንም ቀናት የጦርነት ነጋሪትን በመጎሰም እንዲቆዩ አስገድዷቸዋል፡፡

ዘ-ህወሀት ስለጦርነት በጥልቅ በማሰብ ላይ ይገኛል፣ ሆኖም ግን ከኤርትራ ጋር ስለሚያካሂደው ጦርነት አይደለም፡፡

እያሳሰበው እና ሌት ቀን ረፍት ነስቶ እያሰጨነቀው ያለው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ስለሚያደርገው ጦርነት ነው፡፡

እኔ ስለዘ-ህወሀት እውነቱን በመናገር ላይ ነው ያለሁት ምክንያቱም የዘ-ህወሀት አባላት እያንዳንዳቸው ሁልጊዜ እየተነጋገሩ ያሉበት ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲህ ቢያድርግ ምን…? በማለት ብርክ ይዟቸዋል፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2016 የጦርነት ማቆሚያ ስለመሆኑ ወይም ደግሞ ቀደም ሲል ጀምሮ የሚተዋወቁት ወንድማማች ቡድኖች የህዝብን ስሜት ለማስቀየስ ሲሉ የጦርነት ጨዋታዎችን ሲያካሂዱ ለማየት ስለመቻሌ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የለም፡፡

በአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ላይ ያሉ ባሉ ቡድኖች መካከል ጦርነት ሊካሄድ ይችላልን? በማህጸን ውስጥ ያሉ አንድ ዓይነት መንትዮች በህይወት ለመቆየት የአንዱ መኖር ለሌላው ህልውና አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን በተመሳሳይ መልኩ ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች በስልጣናቸው ላይ ለመቆየት እያንዳንዳቸው እርስ በእርስ ይፈላለጋሉ፡፡ ያላንዱ ህልውና የሌላው ህልውና ሊቆይ እንደማይችል ያውቃሉና፡፡

በአሁኑ ጊዜ ጦርነት ማናቸውም ቢሆኑ የማይፈልጉት ነገር ነው፣ እናም ይህንን በሚገባ ያውቁታል፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2015 የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ተግባራዊ እንዲሆን አጽድቋል፡፡ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ የተጣለበት ሀገር ጦርነትን አካሂዶ ስለማሸነፉ ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ነው፡፡

ጨካኝ እና አረመኔ የነበረው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔቪል ቻምበርላይን በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፣“በጦርነት ጊዜ የትኛውም ወገን እራሱን አሸናፊ ነኝ በማለት ሊጠራ ይችላል፡፡ ማንም ቢሆን አሸናፊ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ሁለቱም ወገኖች ተሸናፊዎች ናቸው፡፡“

በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ማን ነው ተሸናፊ ሊሆን የሚችለው?

ስለጦርነት ሁለት ዝሆኖች በሚገጥሙ ጊዜ የሚጎዳው ሳሩ ነው የሚል የተለመደ አባባል አለ፡፡

በዝሆኖች መካከል በሚደረገው ጦርነት ሳሩ አሸናፊ ሆኖ ሊወጣ የማይችለው ለምንድን ነው?

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 እንዲህ በማለት ጽፌ ነበር፣ “ከኤርትራ ጋር ጦርነት ወይም ደግሞ ጣልቃገብነት ለማድረግ ስለመሞከሩ እና ከግብጽ ጋር የውኃ ጦርነት ስለመደረጉ ወደፊት ጊዜ የሚያሳየን ይሆናል… ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ በዚያ ዕጣ ፈንታ ላይ ማንም ቢሆን ዓይኑን ለአንድ አፍታም ቢሆን አይነቅልም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሊደረግ የሚችለው ብቸኛው የዜናዊ ጦርነት የህዝብን ስሜት የማስቀየስ ጦርነት ብቻ ነው“ ብዬ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝ 2011 “የኤርትራ ህዝብ አምባገነኑን አገዛዝ ለማስወገድ ፈጣን መንገድ መከተል አለበት“ በማለት ዜናዊ አስፈራርቶ ነበር፡፡

ያለፉት አምስት ዓመታት እውነታ ለእራሳቸው ይናገራሉ፡፡

ምንም የማታውቅ ሞኝ ነህ ብላችሁ ጥሩኝ፡፡ ከዚህም በላይ ስለጅኦ ፖለቲካ ምንም ዓይነት ግንዛቤ የሌለኝ ትላንት እንደተወለድኩ አድርጎ መናገር ይቻላል፡፡

ምንም የማላውቅ እና ትላንት እንደተወለድኩ አድርጎ ማየቱ እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ትላንት ማታ አልተወለድኩም!

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 የተናገርኩትን እንደገና እ.ኤ.አ ሰኔ 2016ም እደግመዋለሁ፡፡ “የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የህዝብን ስሜት ለማስቀየስ የተደረገ የጦርነት ጨዋታ ነው፡፡”

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ሰኔ 13 ቀን 2008 ዓ.ም

ራስህን ጠይቅ ( ሄኖክ የሺጥላ )

 

politicsፖለቲከኛ ማለት ከአብዛንኛው ህዝብ በተለየ የመዋሸት ስጦታ የተሰጠው ሰው ማለት ነው ። ፖለቲከኞች መጀመሪያ ታጋይ በመሆን ይጀምሩና ፥ የሚታገላቸውን በማፍራት ይጨርሳሉ!

ፖለቲከኞችን ሁሉ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ፥ ሁሉም የሚያወሩት ስለ አንድ ጭቁን ገበሬ ሲሆን ፥ በሚገርም ሁኔታ ሁሉም ገበሬውን አያውቁትም !

ፖለቲከኞች ሁሉም ስለተጨቆነ ህዝብ በተሰናሰነ መንገድ ማውራት ይችላሉ ። በዚህም ዲስኩራቸው ከጎናቸው እልፎችን ያሰልፋሉ ። በተከታይ ሲፋፉ ፥ መናጢ ሳሉ ያምኑበት የነበረውን ውይይት እና ሃሳብ ማንሸራሸር አንቅረው ይተፉታል ፥ የመናገር ነፃነት ይከበር ብለው ትግል የጀመሩት ፥ « እነዚህማ በመናገር ነፃነት ያምናሉ » ብለህ ስትናገራቸው ፥ ስትወቅሳቸው ወይም ስታርማቸው ፥ እንደ ጎረምሳ ድመት ያብጣሉ ።
በ ተቆርቋሪነት ስም የኮለኮሏቸውን የነሲብ ተከታዮች ፥ የገበሬውን ጭቆና ለማቅለል ከመጠቀም ይልቅ ፥ የሃሳብ ነፃነትን ለማድቀቅ ያሴሩበታል ።

ይህ ይህ ነው በማይባሉ አድር ባይ ጋዜጠኞች ፥ ውሸታም አክቲቪስቶች ፥ ሌባ ታጋዮች ፥ እና ከምንም በላይ ዱርዬ የሃገር መሪዎች ላይ የሚታይ ተመሳሳይ በሃሪ ነው ።
ሁሉም በአንድነት ስለ ፍትህ እና ነፃነት ያወራሉ ፥ ሁሉም ግን ከትዕቢት እና ተንኮለኝነት ነፃ አይደሉም ። ሁሉም !

ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅምን ከዘለቄታዊ ሃገራዊ ጥቅም አንፃር ለክተው እና መዝነው ሳይሆን የገቡበት ውስጥ የሚገቡት ፥ በነሲብ እና የሚፈልጉትን ነገር ለማስፈጠም ቀዳዳ በመፈልግ በመጠመድም ነው ። ይህ ደሞ ለውጥ ሳይሆንን ልውውጥ ነው የሚያመጣው ።
ለምሳሌ ህዝቡ ሰልችቶታል ። ውሸት ሰልችቶታል ፥ ድህነትም ሰልችቶታል ! ለምሳሌ እውነት መስማት እንፈልጋለን ። ትግል ውስጥ ነን የሚሉትም ሆኑ ትግሉን የሚደግፉት መሰረታዊ ምክነታቸው ምክንያታቸው ነፃነትን መሻት አለመሆኑ ነው ።

የጥገኝነት ወረቀት ለማግኘት ሲሉ የተቃዋሚ የትግል ጎራን የተቀላቀሉ ብዙዎች ነበሩ ፥ አሉም ። የጥገኝነት ወረቀታቸውን ሲያገኙ የትም የትም ሲታዩ አይስተዋሉም ። ከነሱ ወረቀት ባሻገር ያለው ገበሬ ህይወት የሚኖረው የነሱ ወረቀት እስኪሳካ ብቻ ነው ። መሪዎች ነን ባዮች ይህንን በደንብ ያውቃሉ ፥ በማወቃቸው የአመለካከት ለውጥ ብሎም መሰረታዊ የነፃነት ጥያቄ ምን መሆን እንዳለበት ፈር ከማስያዝ ፥ ከማስረዳት እና በዚያ ጎን ከማደራጀት ይልቅ ልቦናቸው እያወቀው ፥ የሚሰበስቡትን ሰብስበው ፥ አንድ ሁለት ጥቅስ ተናግረው ስብሰባውን ይበትናሉ ። ይህንን ድክመታቸውን ደፍሮ የሚናገረውን ፥ ቆምንለት የሚሉትን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ሃሳብ ገፍትረው ጥለው እውነቱን ከመሞገት ይልቅ በስድብ እና በ character assasination ይጠመዳሉ ።

እስቲ ለምን ይመስላችኋል ትናንት ሲቃወም የነበረው ዛሬ ኢትዮጵያ ስላፈራው ሃብቱ በመፍራት ዝምታን መርጦ ቁጭ ያለው ? ወያኔ ጠንካራ ስለሆነ ነው ? አይደለም!የተቃዋሚ መሪዎች ፥ ደጋፊዎቻቸው መሰረታዊ የፖለቲካ ንቃት ፥ መረዳት ብሎም እውነቱን በአግባቡ የማወቅ ስራን ስለማይሰሩ ነው ። ሰራን የሚሉት ከሰሩት አንፃር ይህ ነው የሚባል ስላልሆነም ነው ። በየቦታው የሚነሱን ህዝባዊ አመፆች « የኔ ነው » ብሎ ከማለት ውጪ የነሱ ስለመሆኑ አንዳችም ማሳያ በሌለበት ሁኔታ ፥ ለወረቀቱ ሲል ደጋፊ የሆናቸውን ጥቅማም ተከታይ እንዴት የሃገር መፍረስ እንዲገባው ልናደርግ እንችላለን ?

በግርግር የሚመጣ ለውጥ የለም ። ቢመጣም የግርግር ስርዓትን ነው ፈጥሮ የሚያልፈው ። ከጭብጨባው ጀርባ ያለውን እና ያልተሰራውን ትልቅ ስራ ለመስራት በመጀመሪያ ድክመቶቻችንን አምነን እንቀበል ። ሲነግሩን እንስማ ። ሲመክሩን ቢያንስ « ቢሆንስ » ብለን እንበል ። ስለ ነፃነት እየሰበክን ፥ ነፃ ስብዕናዎችን እይገደልን መኖር እንዴት ይቻለናል ። ለምን ይህን ያህል ለፍተን አልተሳካም የሚለውን መመለስ የምንችለው ህዝቡን ሳይሆን ራሳችንን በመመርመር ብቻ ነው ! ( በመጀምሪያ !)