ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

Muluken Tesfaw's photo.

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

ዳኛ ራራ ደሴ ተከሳሽ በሌሉበት ጉዳያቸው መታየት አይችልም በማለታቸው ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ነገ ሀምሌ 25 ቀን 2008 ዓም በሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ የጎንደር ዐማሮች በጠዋት ፍርድ ቤት በመገኘት ለኮሎኔል ደመቀ አጋርነታቸውን ያሳያሉ።
ኮሎኔል ደመቀ የሰሩት ምንም ዓይነት ወንጀል ባለመኖሩ በነጻ ወይም በዋስ ነገ ሊለቀቁ ይችላሉ የሚል ግምት አለ። በሺዎች የሚቆጠሩ ጫና ካልተለቀቁ ግን ተከታታይ ተቃውሞዎች እንደሚኖር ይጠበቃል።
የዐማራ ተጋድሎ ይቀጥላል!!

ድሮም ሆነ ዘንድሮ ሄኖክ የሺጥላ

ድሮም ሆነ ዘንድሮ የ አማራ ጥፋቱ ኢትዮጵያዊነቱ ነው። ስለ አማራ ሳስብ ሁል ጊዜም በዕዝነ ህሊናዬ የሚመላለሰው የሄነሪ ፥ ፋን ፥ ዳይኬ የተጣፈው « አራተኛው ሰብዓ ሰገል » የሚለው አጭር ታሪክ ነው ። በዚህ ታሪኩ ሄነሪ ከሶስቱ ሰባ ሰገሎች በተጨማሪ አንድ በታሪክ ያልተገለፀ ፥ በራዕይ ያልተሰበዘ ፥ ኅሣሢ አራተኛ ሰባሰገል ታሪክ ነው። ይህ አራተኛ ሰባሰገል የፍቅሩን ለህፃኑ እየሱስ ለማበርከት እንዴት እንዳልተሳካለት ባለመሳካቱም እንዴት እንደተሳካለት ይተርክልናል።

ጠሃፊው ሲገልጠው « የሀሳቡን ለማድረግ አሰበ ፥ ያሰበውም አልተሳካለትም ፥ ባለመሳካቱ ግን ሃሳቡ ተሳካ » ይለናል ።

ፀሃፊው « ይኽ ሰው አውግስጦስ ቄሳር ንጉሰ ነገስት በነበረበት ፥ ሄሮድስ በእየሩሳሌም በነገሰባቸው ዘመናት ፥ በፋርስ ተራሮች በምትገኘው ኤቅባጣና ይኖር የነበረ ሰው ነበር ። ስሙም አርጣባን ይባላል ይላል ። »

ጠሃፊው ስለ አርጣባን ሃብት እና ክብር ሲናገር እንዲህ ነበር የገለጠው

« ቤቱ የመንግስት ግምዣ ቤት በከበበው በባለ ሰባቱ ቅጥር አውድ በውጭኛው አድሞ አጠገብ ነበር። ከቤቱ ባጥ ላይ ሆኖ ማዶውን አሻግሮ የጥቁርና የነጭ ፥ የሐምራዊ እና የሰማያዊ የቀይ የብርና የወርቅ የቅኝ ማዘዣዎችን ይዞ ዘውድ ላይ እንደተጎብጎበ ፈርጥ የሚንቆጠቆተው የጳርጢያን ነገስታት የበጋ ቤተ መንግስት እስካለበት ድረስ ማማተር ይቻለው ነበር » ይላል ።

አርጣባን እንደ ሶስቱ ሰባሰገሎች ( ቃስጳር ፥ ሚልሾር እና ባልጣፃር ( ወይም ብልጣሶር ወይም ባልተዛር) ጋር በመሆን ለህፃኑ እየሱስ እሱን እንደ ባልዠሮቹ ስጦታ ሊቸር በኮከብ ብርሃን ተመርቶ ወደ እየሩሳሌም ተጓዘ። ቤት ንብረቱንም ሽጦ ለህፃኑ እየሱስ የሚያበረክተውን ስጦታዎች ገዛ ( ሶስት እንቁዎች ፥ ሰንፔር ፥ ከርከንድ እና ሉል ) ። ጓደኞቹ ( ሰባሰገሎቹ አይደሉም ) ባንድም ሆነ በሌላ ምክንያት ከሱ ጋር አብረው ላለመሄድ ወሰኑ ። አርጣባን ጉዞውን ብቻውን ተያያዘው ። በጉዞው ላይ ግን ለእመቤታችን ልጅ ሊሰጥ ያዘጋጃቸውን ስጦታዎች ሁሉ በችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች ሰጥቶ ጨረሰ ። ልቡ በሃዘን እየተመታ ከቆመለት አላማ ውጭ መልካም ነገርን ለማድረግ ሲል ስጦታውን ለሌሎች ሰጠ ፥ ስለ ፍቅር እና ሰዋዊ ምክንያት ሲል ችሮታው ለህፃኑ ክርስቶስ ሳይሆን በመንገዱ ላይ ላገኛቸው ነዳያን አዋለው ። ያሰበውን ባያደርግም እና ባይሳካለትም ፥ ባለሰው ጉዳይ ያሰበው ተሳካ ። መልካምም ሆኖ ተቆጠረለት ።

ይህ የአርጣባን ታሪክ ያለ ነገር አልመጣም! ተጎንደር ህዝብ ሰልፍ የ አርጣባንን ታሪክ አስታወሰኝ ። የወልቃይትን አማራነት እንደ መሪ መፈክር አድርጎ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው የጎንደር ህዝብ ፥ መሃል ላይ በኦሮሞ ወንድሞቹ ሞቱ ልቡ ተነካ ፥ ስለዚህም ሰንፔሩን ለኦሮሞ ህዝብ አውጥቶ ሰጠ ፥ ቶፓዙን ለጋንቤላ ህዝብ አበረከተ ፥ ስለ ፍቅር የራሱን ህመም ችሎ ፥ ከአድማስ ማዶ ባለው ሰዋዊ ልቦና ተረታ።
ከርከንዱ የወልቃይት አማራነት ቢሆንም ቅሉ ፥ ውሉ ግን የሰው ልጆች ሰብአዊ መብት መከበር መሆኑን ተናገረ ። ልጆቹን የገበረበት ፥ የታረደበት እና የተገደለበት ዋነኛ ምክንያቱ አማራ መሆኑ ቢሆንም ፥ ደሙን ፥ ሞቱን ፥ ስቃዩን እና ህልፈቱን ከራሱ ባለፈ የሌሎእን ስቃይ ለማስታገስ ተጠቀመበት ።

አርጣባን መጉዞ ላይ ያገኘው እና በህይወት እና በሞት መሃከል የነበረው ሰው « ማነኽ አንተ እስቲ ሒወቴን እንደገና ለመመለስ ‘ኔን እዚህ ድረስ ለምን አሻኸኝ» ሲለው

አርጣባን « የኤቅባጣና ከተማው ሰባሰገሉ አርጣባን ነኝ የይሁድን ንጉስ ፥ ታላቁን ልዑል ፥ የሰው ልጅ ሁሉ ታዳጊውን ለመፈለግ ወደየሩሳሌም ነው የምሄደው » በማለት መለሰለት ።

አዎ የሰው ልጅን አዳኝ የሆነውን ክርስቶስን በመፈለግ ላይ ያለው አርጣባን ፥ ታሞ ፥ ደክሞ ፥ ዝሎ ፥ ደቆ ፥ ወድቆ ያገኘውን ሰው አንዳላየ ሆኖ ሊያልፈው አልቻለም ። ከጉዞ ራሱን ገትቶ ፥ የወደቀውን አንስቶ ፥ ከሸከፈው ፈቶ አብልቶ ፥ ከንፈሩን በውሃ አርሶ ፥ ህይወቱ ላይ ዳግም ነፍስ ዘርቶ ነው ጉዞውን የቀጠለው ።

ክርስቶስን መፈለግ ማለት በመንገድህ ላይ የምታየውን መከራ መታደግ ነው ። የጎንደር ህዝብ ለኔ አርጣባን ነው ። ለወልቃይት የማንነት ጥያቄ ሊታገል ወጥቶ መንገድ ላይ በወያኔ ጥይት ተመትቶ የወደቀውን የሃገሩን ልጅ ፥ ወንድሙን ፥ ደሙን የኦሮሞ ልጅ ትቶ ማለፍ ስላልቻለ ፥ « ሞታችሁ ሞቴ ነው !» ብሎ ያለው ።
ስቃያችሁ ስቃዬ ነው ብሎ የተናገረው ! ይህ ሰውነት ነው ! ይህ አርጣባንነት ነው! ይህ ክርስቶስን የሚፈልግ ሰው ሁነኛ መገለጫ ነው ። አው ክርስቶስን በአዳኝነቱ ስናመልከው ፥ እኛ ራሳችን ደራሽ ፥ ቋሚ ፥ ጠበቃ እና አዳኝ መሆናችንን እንዴት ዘነጋነው ?

አርጣባን በየደረሰበት የወደቀ ሲያነሳ ፥ የደከመ ሲደግፍ ፥ ቤተልሄም ሊደርስ አደልቦ ፥ እና አጠንክሮ ያደረሰው ፈረሱ ደከመበት ስለዚህም ለክርስቶስ ሊሰጥ ካሰበው ስጦታ ውስጥ አንዱን ( ሰንጴሩን ) ሽጦ የግመል ጠያሮች እና ስንቅ ለመግዛት ወሰነ ።

በደግነቱ ከጉዞው ቢስተጓገልም ፥ የሚጓዝበት እና ማየት የሚፈልገውን የፍቅር አምላክ እሱ ራሱ በተግባር ኖሮት ስለነበር ፥ ባያደርግም እንዳደረገ ሆኖ ተቆጠረለት ። የጎንደር ህዝን ሰላማዊ ሰልፍም ይህንን የሆነ እንደነበረ ይሰማኛል ።

እናመሰግናለን ! እናከብራችኋለን! እናፈቅራችኋለን ። አማራ ከጥንትም ለጉራጌ ለመሞት ፥ ለጉራጌ ለማገዝ እና ለመቆም ጉራጌ መሆን የሚያስፈልገው ህዝብ አልነበረም ፥ ወደፊትም አይሆንም ! ስለ አማራ ለመናገር ግን አማራ መሆን ግዴታ የሆነ ይመስላል ። መማር ከቻላችሁ ፥ ይህ ህዝብ ትልቅ ትምህርት ቤት ነው ! ተማሩት!

ሄኖክ የሺጥላ

Henoke Yeshetlla's photo.
Henoke Yeshetlla's photo.

ህዝብ ወደ ሰልፍ እየተመመ ነው- እነ ደብረ ጽዩን ግን ኢንተርኔት በጎንደር ዘጉ – ግርማ ካሳ  

 

121
ዛሬ እሁድ ሐመሌ 24 ቀን በጎንደር ሊደረግ የታቀደው ሰላማዊ ሰልፍ በአስደናቂ ሁኔታ ተጀምሯል። ሕዝቡ ግልብጥ ብሎ ወደ መስቀል አደባባይ እየተመመ ነው። በማስፈራራትና በዛቻ ሕዝቡ ፈርቶ እንዳይወጣ፣ አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር በሕወሃቶች እና የህወሃት አሽከር በሆኑ ብአዴኖች ሲደረግ የነበረው ጸረ-ሕዝብ፣ ጸረ-ሕገ መንግስታዊና ጸረ-ሰላም እንቅስቃሴዎች ሙሉ ለሙሉ ከሽፈዋል።

የጎንደር ሕዝብ በአገሩ፣ በምድሩ ድምጹን ለማሰማት በተነሳበት ጊዜ ሕዝቡን የወከሉ ሽማግሌዎች በሕጉ መሰረት ለባለስልጣናቱ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ማሳወቃቸው ይታወቃል። ባለስልጣናቱ ለአሥር ቀናት ይራዘም ብለው ስለጠየቁና ለሰልፉ ዝግጅት እንዲደረግ በሚል ሐምሌ 17 ሊደረግ የታሰበው ሰልፍ ወደ ሐምሌ 24 እንደሚዞረም ተገልጾ ነበር። ሆኖም ግን የሕወሃቱ ፋና ሰልፉ እውቅና አላገኘም በሚል ርካሽ ፕሮፖጋንድ እንዲረጭ ከማድረጉ በተጨማሪ ህወሃቶችና አፍቃሪ ሕወሃቶች በየቤቱ እየሄዱ የህዝቡን ስሜት ለማዳከም ሞክረዋል።

ሆኖም ግን ሕዝቡ በነቂስ ወደ አደባባይ መዉጣቱ የህወሃት ፖለቲካ መክሰሩን የሚያመለክት ነው።

በሕወሃቱ ደብረ ጽዮን የሚመራውም ቴሌ ፣ ሕዝቡ ሕግ መንግስታዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱን በማስከበር እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ከጎንደር ዉጭ ያለው ሕዝብ እንዳይሰማው፣ ፍጹም አሳፋሪና ነገሮች ከሕወሃት ቁጥጥር ዉጭ እንደሆኑ፣ ህወሃቶች ተስፋ እንደቆረጡ የሚያመላክት ተግባራት እየፈጸሙ ነው። በጎንደር ከተማ የኢንተርኔት አገግሎት በአሁኑ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል። በጎንደር እየታየ ያለው ኢንተርኔት እንደተከፈተ መለቀቁ አይቀሬ ነው። ሰዎቹ ራሳቸውን አስገመቱ እንጂ። ተሞኙ እንጅ።
እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው የአማራው ክልል መንግስት የሚቆጣጠረው ራዲዮና ቴሌቭዥን ሰልፉ እንዳልተፈቀደና እውቅና እንዳላገኝ የተናገረው ነገር እንደሌል ነው። ሕወሃት የሚቆጣጠረው ራዲዮ ፋና ነው ሰልፉ እውቅና የለውም እያለ ሲለፍፍ የነበረው። ኢንተርኔቱንም የዘጋው ብአዴን ሳይሆን እነ ደብረ ጽዩን ናቸው። በአጭሩ ህወሃት ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል የጎንደር ህዝብን ጥቅም ሆን ብሎ በበቀል ለመጉዳት ቆርጦ እየሰራ እንደሆነ ነው።

አሁንም ለሕወሃቶች ከጎንደር ህዝብ ጋር ከሚታገሉ የሕዝቡን ጥያቄ እንዳያከበሩ እመክራቸዋለሁ።ከእሳት ጋር ባይጫወቱ ጥሩ ነው። የብአዴን አባላት ከሕዝቡ ጎን የተሰለፉበት ሁኔታ ነው ያለው።

ሰበር ዜና፤ የጎንደር ህዝብ ቃሉን ጠብቆ አደባባይ ወጥቷል

  • የጎንደር ህዝብ ቃሉን ጠብቆ አደባባይ ወጥቷል
  • ተቃውሞው ህዝቡ በራሱ አነሳሽነት የሚያካሄደው እንጅ በማንም ውጭ በሚገኝ ቡድን የሚመራ አንዳልሆነ ታውቋል
  • አንዳንድ በስም እንጅ በተግባር የሌሉ ተስፈኛ ቡድኖች ከዚህ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለመቀላወጥና እነሱም እንዳሉበት አድርገው ለማወናበድ ሙከራ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል

የጎንደር ከተማ በሰላማዊ ሰልፈኞች ተጥለቅልቃለች ሕዝቡ ወደ መስቀል ኣደባባይ መጓዙን ይዟል ። የሕወሓት ወታደሮችና ፖሊሶች በግርምት ኣፍጥጠው እያዩ መንገድ እየዘጉ ሰልፈኛውን ለመቁረጥ ጥረት እያደረጉ ነው። ፤በፍርሃት እንዳይወጣ እያደረጉት ያለው ሕዝብ በልበሙሉነት ኣደባባዩ በሚሊዮኖች እየሞላ ነው፤የኢንተርኔት ኣገልግሎት ኣይሰራም።

የወልቃይት ጉዳይ የኣማራና የኣማራነት ማረጋገጫ እንደሆነ በተግባር እየታየ ነው። አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ ይሄ ባንዲራ ያንተ አይደለም ወይ በሚለው ከፍተኛ ጩሀት ያሰማል የክልሉ ፓሊስ ከህዝብ ጋር ሙሉ ለሙሉ ተቀላቀለ አንድነት ሀይል ነው ህዝብ ሀይል ነው።ሁለም አቅጣጫ በተለይም በፒያሣ አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሠልፋ ታዳሚ በመፈክሮችና በቀሥቃሽ ሙዚቃዎች ታጅቦ ወደ መሥቀል አደባባይ እየተመመ እንደሚገኝ የሠልፋ ተሣታፊ ከሥፍራው ነግሮኛል። ከኦሮሞ ሕዝብ ጎን መቆሙን አማራው በተግባር በሚሊዮኖች ድምጹ ኣረጋግጧል። በሕዝብ ዘንድ ጥላቻና ዘረኝነት እንዳሌለ የጎንደሩ ሰልፍ ለገዢዎች ኣሳይቷል። በጎንደሩ ሰልፍ የህዝብ ችግር ወያኔዎች እንደሆኑ እንጂ በሕዝብ መካከል ችግር እንደሌለና ኢትዮጵያዊነት እንዳስተሳሰረ በተግባር ከመመስከሩም በላይ የወያኔን ባንድራ ተቀባይነት እንዳሌለው ታይቷል።

የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ከሥፍራው እንደሌሉ እና አጋዚ ግን ከትናንት ጀምሮ ቢኖርም ህዝቡ ፍጹም ጨዋነት በተሞላበት ሰላማዊ መንገድ የሰልፉን ግብ ለማሳካት እርብርብ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁ። http://mereja.com/album/1092

ሰልፋን እየመሩት የሚገኙት የኃይማኖት አባቶች የክርስትያኑና የሙስሊሙ ሲሆኑ ምንም ያልተለጠፈበትን ንጹሁን የኢትዬጽያ ሰንደቅ ዓላማ እየተውለበለበ ይገኛል፡፡ በዚህ ሰዓት አንድም ፌደራል አይታይም፡፡ አሁን የሚሰማኝ ስሜት ልክ አባቶቻችን ጣልያንን ሲያሸንፉ፤ ልክ እንደ አድዋ ድል በማለት ደስታውን ገልፆልኛል፡፡ በቦታው ኮረኔል ደመቀ የላከው መልክት ሊነበብ እንደሆነም ገልፆልኛል፡፡ በአደራ የሰጠናችሁን ልጃችን ኮለኔል ደመቀ ዘውዱን መልሱልን! በግፍ የታሰሩ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በአስቸኳይ ይፈቱ! የሚሉና ሌሎችም የሕዝቡን ብሶትና ምሬት የሚገልጹ መፈክሮች ከፍ ባለ ድምጽና እጅግ በሞቀ ስሜት በመሰማት ላይ ናቸው።

የወያኔ የጎሳ ፖለቲካና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የተዋረደበት ህዝቡ አገዛዙን መጥላቱን ሕዝብ ያስመሰከረበት ሰልፍ ተካሄደ Minilik Salsawi

እናቶች በሰልፋ ለደከሙ ወጣቶች ውኃ እያቀረቡ ነው፤ የሃይማኖት አባቶች ተጋድሏችንን እየባረኩ ነው! አማራነት እኮ እንዲህ ነው! እቴጌ ባአድዋ ያደረጉትን አስታውሱ!

የወያኔ የጎሳ ፖለቲካና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የተዋረደበት ኣገዛዙን መጥላቱን ሕዝብ የመሰከረበት ሰልፍ
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Gonder‬ ‪#‎Amharaprotests‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi  ፖለቲከኞችን ያሳፈረው ሕዝብን ያነገሰው ዛሬ በጎንደር የተካሄደው ሰልፍ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ሂደት ውስጥ ራሱን የቻለ ጫና እንዳለው ያረጋግጣል።ሕዝብ በራሱ ያሰናዳውና የተሳካ ታላቅ ሰልፍ በጎንደር ደሞቆ ውሏል።ሕዝባዊ ኣንድነት ጎልቶ የታየበት የወያኔ የጎሳ ፖለቲካና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የተዋረደበት ኣገዛዙን መጥላቱን ሕዝብ የመሰከረበት ሰልፍ ነበር፤የሕወሓት ኣገዛዝ በቃኽን የተባለበትም ሰልፍ ነው፥ ሚሊዮኖች ኣደባባይ ወጥተው ወያኔን ልክ እንደሚያስገቡት ነግረውታል።

Minilik Salsawi's photo.

ሕዝብን በሃይማኖት ለመከፋፈል ሞከሩ ኣልተሳካም። ሕዝቡ ሃይማኖታችንን እንደያዘን የሌላውን ኣክብረን ቤታችን በታቸው ሆኖ የኣንዱ ደስታና ሃዘን የኣንዳችን ሆኖ በተሳሰረ የኢትዮጵያዊነት ሰንሰለት ላይፈታ ታስሯል ብሎ በተደጋጋሚ እያረጋገጠ ነው። የብሄረሰብ መብት ሽፋን በሚል ኣንዱን ጨቋኝ ሌላውን ተጨቋኝ ኣድርጎ ለማቅረብ ቢሞክርም ሰሚ ጆሮ ኣላገኘም ወያኔከኦሮሞ ሕዝብ ጎን መቆሙን ኣማራው በተግባር በሚሊዮኖች ድምጹ ኣረጋግጧል፤ በሕዝብ ዘንድ ጥላቻና ዘረኝነት እንዳሌለ የጎንደሩ ሰልፍ ለገዢዎች ኣሳይቷል። ችግሩ ወያኔና ፖለቲከኞቹ እንደሆኑ እንጂ በሕዝቦች መካከል ችግር እንደሌለ ኢትዮጵያዊነት እንዳስተሳሰረ በተግባር ከመመስከሩም በላይ የወያኔን ባንድራ ተቀባይነት እንዳሌለው ታይቷል በጎንደሩ ሰልፍ።

የጎንደር ሁኔታ — ዜና ጎንደር (Update)

Muluken Tesfaw

በዋናው የሰልፉ ዓላማ በሌላ ‹‹የተቀደሰ ዓላማ›› እንዳይዳፈን ስጋት አለ

ጎንደር በፌደራልና በልዩ ኃይል ፖሊሶች ተጨናንቃለች

ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቁ ዐማሮች ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣሉ፡፡ ይህን ተከትሎ ከባሕር ዳር፣ ደብረ ታቦር፣ ደባርቅ፣ ቆላ ድባ፣ ሳንጃና ጭልጋ መተማ የሚመጡ መኪኖች ላይ ታላቅ ፍተሸ እየተካሔደ ነው፡፡ ከጭልጋ ሰራባ አካባቢ እንዲሁም ከባሕር ዳር ብዛት ያላቸው የመከላከያ ኃይል አባላት ወደ ጎንደር መጥተዋል፡፡ በጎንደር የሚታየው ፖሊስ ዛሬ በጽጥታ አካላት ብቻ ሰልፍ የተካሔደ አስመስሎታል፡፡

ዐማሮች ከሁሉም ቦታ ወደ ጎንደር እየጎረፉ ነው፡፡ የሰልፉ ዓላማም አንድ እና አንድ ነው፤ ይኸውም የወልቃይት ዐማሮች የማንነት ጥያቄን ለማዳፈን የሚደረገውን ጥረት መቃወም ነው፡፡ ኮሚቴዎች በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ መጠየቅ፤ ወልቃይት ዐማራነትን መመስከር ነው፡፡

ይህ ሰልፍ ከዚህ የዘለለ ሌላ ዓላማ የለውም፡፡ ሆኖም ይህን ሰልፍ ዓላማ በሌላ ‹‹የተቀደሰ ዓላማ›› ለመሸፍ የሚደረግ ጥረት አለ፡፡ የኦሮሞ ወንድሞቻችን ግድያና አፈና፣ የሀብታሙ ሕመም ሁላችንም የምናወግዘው ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያን መበታተን ማንም አይሻም፡፡

እነዚህ ‹‹ቅዱስ ዓላማ›› ያላቸው መፈክሮች ጎልተው የሰፊውን ዐማራ ሕዝብ ጥያቄ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለማዳፈን የሚደረገው ጥረት ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ስለዚህ የዐማራውን ሕዝብ ትግል እንቅስቃሴ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል በማጋለጥ ላይ ብቻ ያተኮረ ነው፡፡ ሁሉም የሰልፉ ተሳታፊ የዐማራ ሕዝብ ከወልቃይት ጠገዴ የዐማራ የማንነት ጥያቄን በደንብ አጉልቶ ማውጣት አለበት፡፡

———————-

ማምሻውን ከተለያዮ ቦታዎች ወደ ጎንደር ህዝቡ በተለያዮ ተሽከርካሪዎች እና መጎጎዣዎች ወደ ጎንደር በመትመም ላይ ይገኛል።

ይህን የምትመለከቱት ህዝብ የጫነ ኤፍኤስአር መኪና ለፍተሻ ቁም ተብሎ የቆመ ሲሆን ህዝቡ አንፈተሽም በሚል በአቁማቸው ፀንተው ከሚፈትሹ ፓሊሶች ጋር እየተነታረኩ ይገኛሉ።

ከዚህ ከምታዮት የህዝብ መሀል በአብዛኛው መሳሪያ የያዘ ነው ፓሊሶችም በእነዚህ ታፍነው በመርበትበት ላይ ይገኛሉ ።

ሌሎች መኪኖችም ከወደ ሳንጃ ሙሉ መሳሪያ የታጠቁ የአካባቢው ህዝብ በመምጣት ላይ ይገኛሉ።

News, update from Gondar, Ethiopia

————————-

ጎንደር ዙሪያ ከተሞች ያሉ ጀግኖች በእብሪተኛው ወያኔ አስፓልት መንገዱ የተዘጋበትና ፍተሻው ቢያስመርረው በየጥሻው እያቆራረጠ ጎንደር እየገባ ነው። ከጎጃም ዳሞት ተሰባስበው የጎንደር ወገኑት ሊደግፍ የተጓዙት የበላይ ልጆች ጎንደር መግናታቸው ታውቋል።

Gondar to stage protest

 

ስደተኞች ወደ ምዕራብ አገሮች እንዳይፈልሱ ለመከላከል የአውሮፓ ህብረት ለወያኔ አገዛዝ የሰጠው የገንዘብ ስጦታ ውጤት አይኖረውም ተባለ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

 

ሐምሌ 22 ቀን 2008 ዓ.ም.
ርዕሰ ዜና
 ስደተኞች ወደ ምዕራብ አገሮች እንዳይፈልሱ ለመከላከል የአውሮፓ ህብረት ለወያኔ አገዛዝ የሰጠው የገንዘብ ስጦታ ውጤት አይኖረውም ተባለ
 ባለፈው ማክሰኞ በካይሮ ከተማ ከተመድ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሁለት ኢትዮጵያውያን በእሳት ተቃጠሉ
 በተለያዩ ቦታዎች የሚካሄዱት ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች እንደቀጠሉ ናቸው
 በሶማሊያ ሶስት የወያኔ ወታደሮች በአልሸባብ ተገደሉ
 ተመድ በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ የሚሰጠውን የሰብአዊ እርድታ ለጊዜው አቋረጠ
 10 የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ተመድ በደቡብ ሱዳን ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቁ
 የዚምባብየው ፓስተር ሰላማዊ የሆነ ሕዝባዊ ተቃውሞ ጠሩ
ዝርዝር ዜናዎች

Mediterranean-troubles
 ወደ ደቡብ አፍሪካም ሆነ ወደ ምዕራብ አገራት በብዛት ከሚሰደዱት መካከል ጎላ ያለ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች የሚመጡት ከኢትዮጵያ መሆኑ ሲታወቅ የስራ ዘርፎችን በመክፈት የስደተኛውን ቁጥር ለመቀነስ በወሰደው ፖሊሲ የአውሮፓው ህብረት 20 ሚሊዮን ዶላር ለወያኔ አገዛዝ የሰጠ መሆኑ ታውቋል። በኑሮ ችግር ምክንያት በ ስደተኞች አገር ለቀው መውጣታቸው የማይካድ ቢሆንም ከኢትዮጵያ የሚወጡት በርካታዎቹ አገዛዙ በሚያደርስባቸው በደልና ግፍ መሆኑ የሚታወቅ
በመሆኑ የተሰጠው ገንዝብ ስደተኞችን ለማስቀረት እምብዛም የማይረዳ መሆኑን ብዙዎቹ ይናገራሉ።

 ባለፈው ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2008 ዓም. በግብጽ የተመድ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በእሳት የተቃጠሉት ኢትዮጵያውን ቁጥር ሁለት መሆኑን የተላያዩ የግብጽ ጋዜጦች በአምዶቻቸው ላይ አስፍረው አውጥተዋል። በእሳቱ አደጋ የተጎዱት ጥገኝነት የሚጠይቁ ኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውንና የሁለት ልጆች እናት የሆነች ሴት ራሱን አቃጥሎ የነበረውን ሌላ ሰው ለማዳን ባደረገችው ሙከራ ተቃጥላ የሞተች መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ካይሮ የሚገኘው የተባበሩት መንግስት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ረቡዕ ሐምሌ 20 ቀን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በሴትዮዋ መሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለስደተኞች ብስጭትና ቁጣ የማመልከታችዎች ጊዜ መጓተና መሆኑንና ችግሩ ሊከሰት የቻለውም ቁጥራችው በጣም ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ለማብራራት ሞክሯል። በግብጽ ውስጥ በተመድ የስደተኞች ኮሚሽን በኩል የጥገኛነት ማመልከቻ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግና ሂደቱን ለማስጀመር በርካታ ወራት አንዳንዴም ዓመታትን እንደሚወስድ ይታወቃል።

 በተለያዩ ቦታዎች የሚካሄዱት ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች አሁንም እንደቀጠሉ እየተነገረ ነው። በምዕራብ ሀረርጌ በግራዋ የወያኔ አግአዚ ጦር አባላት በተኮሱት ጥይት የተመታ አንድ ወጣት የሞተ መሆኑ ተዘግቧል። በምዕራብ አርሲ በአዳባ በዛሬው ቀን ተመሳሳይ ህዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ መካሄዱ ተዘግቧል።

 በሱማሊያ የባኮል ግዛት ዋና ከተማ ከሆነው ከሁዱር 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሞራጋቤ በተባለው ቦታ ላይ የአልሸባ ኃይሎች በሶማሌ መንግስት ወታደሮችና በአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ላይ ባካሄዱት ጥቃት አምስት ወታደሮች መገደላቸውና ከአምስቱ ሶስቱ የወያኔ ወታደሮች መሆናችው ሸበሌ ኒውስ የተባለው የዜና ምንጭ የአይን እማኞችን መረጃ ዋቢ በማደረግ ገልጿል። በውጊያው ምክንያት ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው የወጡ ሲሆን ለበርካታ ሰዓቶች
ከተደረጉ በቀላልና በከባድ መሳሪዎች የተኩስ ልውውጦች በኋላ የአልሸባብ ኃይሎች ቦታውን ለቀው የሄዱ መሆናችው ተገልጿል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሶማሊያ ውስጥ የሚሞቱና አካለ ስንኩላን የሚሆኑ የወያኔ ወታደሮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን ምንጮች እየገለጹ ነው፡:

 በናይጄሪያ ሰሜን ምስራቅ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ኮንቬይ ላይ ጥቃት ፈጽመው ጉዳት ያደረሱ መሆናቸው ታውቋል። በጥቃቱ የተመድ የእርዳታ ሰጭ ድርጅት አባል የሚገኝበት ሶስት ሰላማዊ ሰዎች ሁለት ወታደሮች የቆሰሉ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን ተመድ ወደ ቦርኖ ግዛት የሚያደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ለጊዜው ያቋረጠ መሆኑ ታውቋል። በቦኮ ሃራም ጥቃት ምክንያት ከቤት ንብረታችው ተፈናቅለው በስደተኛ ጣቢያዎች የሚኖሩት ዜጎች ቁጥር
ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሲሆን አብዛኞች ህጻናት በምግብ እጥረት እንደሚሰቃዩ ተነግሯል። ላለፉት ሰባት ዓመታ የሽብር ተግባሮችን ሲያካሂድ የቆየው ቦኮሃራም ባካሄዳቸው ተከታታይ ጥቃቶች ከ20 ሺ ሰዎች በላይ ህይወታቸውን ያጡ መሆናቸውንና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ መስደዳቸው ይታወቃል።

 በደቡብ ሱዳን እርዳታ በመስጠት ላይ የሚገኙ አስር የሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ኃይል በደቡብ ሱዳን ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ በመጠየቅ የጋራ መግለጫ አወጡ። ኦክስፋም፤ ኬር፤ ኢንተርናሽናል ሬስኩ ኮሚቴ የተባሉት የሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የሚገኙበት ይኸው ስብስብ ባወጣው የጋራ መግለጫ የመንግስት ኃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚወስዱት የግፍና የጭካኔ እርምጃ በተለይም ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ መሆኑንና
ለችግሮችም እርዳታ ለማድረስ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን በመጥቀስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ኃይል ኃይሉን አጠናክሮ እርምጃ መውሰድ አለበት ብለዋል። በደቡብ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ 12 ሺ የተመድ ወታደሮች ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ የኃይል እርምጃ እንዲወስዱ የተፈቀደላችው ቢሆንም ኃይላቸውን ተጠቅመው ሰላማዊ ሰዎችን ሲጠብቁ አልታዩም ብለዋል። በደቡብ ሱዳን 4.8 ሚሊዮን ሕዝብ በምግብ እጥረትና ረሃብ የሚሰቃይ ሲሆን ይህም ከሕዝቡ ቁጥር ግማሹ ነው ተብሏል። ሁኔታው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ እርዳታ ለመስጠት የሚቻልበት ሁኔታ እንደሌለ መግለጫው ገልጾ ከፍተኛ እልቂት ሊከተል እንደሚችል አስጠንቋል።

 ህይወታቸውን ከአደጋ ለመጠበቅ ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዙት ፓስተር ኢቫን ማዋሪሬ ሐሙስ ሐምሌ 21 ቀን 2008 ዓም በአንድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለተሰበሰቡ በርካታ የዚምባብዌ ዜጎች ባደረጉት ንግግር ዚምባዊ ውስጥ ያለው ሁኔታ በጣም አሳዛኝ መሆኑን ጠቅሰው ሕዝቡ በትግሉ ነጻነቱን መጎናጸፍ አለበት ብለዋል። ከአገራቸው የወጡት በህይወታችው ላይ አደጋ በመምጣቱ መሆኑን ገልጸው ሰላማዊ የሆነው ተቃውሞ መቀጠል አለበት የሚል መልክት አስተላልፈዋል። በዚምባዌ
የታወቀው የአርበኞች ማህበር ቃል አቀባይ በመንግስት ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው መዘገባችን ይታወሳል።