ባበረውአያጣም

መገንባት  እንደሚችል ያሳየ ለማፍረስ የሚተባበረው አያጣም
አዎን”” “” ለፍትሕ፣ዲሞክራሲ፣እኩልነት፣ወዘተ… በሚሉየተስፋቃላትየሕዝቡንብሶትተጠቅሞናአታሎበመመረሽየአገሪቷንርዕሰመስተዳድር/ቤተ-መንግሥት/ ከተቆጣጠረበኋላእነዚያንየሚጣፍጡመፈክሮችሁሉየውሀሽታአድርጎውንብድናውን በሥልትበሥልቱእያስፋፋታይቶበማይታወቅየአገርክህደትአገራችንንናሕዝቦቻችንንለውርደትየዳረገውንሥርዓት ማፍረስአስፈላጊ ነው፤ነገርግንአብሮመታየትእናአብሮመታቀድያለበት ኅብረቱየሚያስፈልገውለ መገንባትምነው።ብዙዎችየፖሊቲካ ድርጅቶችከተቃወሚዎቻቸው ጋርበጠረጴዛዙሪያተነገጋርረው በጋራመስኮች አብረው መሥራታቸውንለሕዝብአላሳዩም። አንዳንዶቹእንዲየውምስለአገርጉዳይከተቃዋሚዎቻቸውጋርበጋራመታገልንየሚፈሩትይመስላል።ሌሎችደግሞበጋራ “ ” ለመሥራትመጀመራቸውንአብሥረውናል።እሰየውቢያሰኝምዓይንአይቶናጆሮሰምቶልብይፈርዳልይባላል።ሆኖም የተቃዋሚነትስምብቻበመያዝበተስፈኛነትመናከሰማይእስኪወርድበምኞትየሚጠባበቁሥልጣንናፋቂቡድኖችምአሉ፤ ያለተገቢሥራበተስፋየሚገኝምንምነገርስለሌለተጨባጭሥራመሥራትየግድነው፤የሎተሪዕድልእንኳለመመኛትትኬት መግዛትያስፈልጋል።
የወያኔሥርዓትይፍረስ፤ወያኔይወገድ፤የሚሉአስተሳሰቦችብቻቸውንየአውራጎዳናመፈክሮችሆነውይቀራሉ፤እነዚህንከአፍ የማያልፉመፈክሮችንምእራባውያንአገሮችየተወሰነሰላማዊሕዝብስልፍአድርጎየአገርመሪዎችንምስልናሌሎችአርማዎችን ቢያቃጠልእንኳወደአመጽእስካላደገድረስሆድየባሳቸውንየሕዝብክፍሎችእንደየስሜትማስተንፈሻመንገድይጠቀሙባቸዋል። ለስምተቃዋሚወይምለውጥይመጣልበሚልምኞትተስፋዘመናትንሲቆጥርየሚኖርምሆነበአገርተጨባጭሁኔታናበሕዝቦች ፍላጎትመመራትየማይችልድርጅትሕዝባዊግብላይሳይደርስየወረቀት ላይ ነብር ሆኖይኖራል።ምክንያቱምከሕዝቦችመሠረታዊ ፍላጎትስለሚርቅነው።እንደዚህለስሙተቃዋሚሆኖሕዝቡንየተስፋዳቦከመመገብምንጭበመቆፈር፣ክሊኒክበመሥራት፣ በኩበትጭስዓይናቸውንየሚጎዱእናቶችንመፍትሔእንዲያገኙበመርዳት፣ወዘተ… የተጎዳውንወገናቸውንቢታደጉትይሻልነበር።
በተረጋጋመንፈስናሚዛናዊኅሊናሲታይተራውናአብዛኛውሕዝብየመንግሥትንመፍረስበጥንቃቄነውየሚመለከተው፤ሙያዬ የሕዝብአስተዳደር/Public Administration/ ስለነበር፤ለመመረቂያጽሑፌከ36 ዓመታትበፊትከተጠቀምኩባቸው “ ቃለመጠቆችአንዱመንግሥትባይኖርምንችግርአለው?” የሚልነበር፤ከ180 የሁለተኛደረጃተማሪተጠያቂዎችመካከል9 መልስአልሰጡም፣40 መንግሥትየመጭቆኛመሣሪያስለሆነባይኖርምንምጉዳትየለውም፤48 ለሕዝብየቆመከሆነይኑርሲሉ፤ 83 ደግሞማንኛውምሕዝብአካባቢውንያስተዳድርለጋራመከላከያ፣ለጋራገንዘብ፣ለጋራመገናኛእናየጋራሀብቶችንአስተባብሮ ለማልማትናበጋራበእኩልለመጠቀምከሁሉምአካባቢሕዝብየተውጣጣአስተባባሪ( ፊደራልመንግሥት) እንዲኖርሐሳብሰጡ። ያውጥያቄለፋብሪካሠራተኞችታድሎየሚከተለውምላሽተገኝቷል፦
19 መልስአልሰጡም፤21 መንግሥትየመጨቆኛመሣሪያስለሆነአያስፈልግም፤136 ለሕዝብየቆመከሆነመንግሥትቢኖርጥሩ ነው፤4 ሕዝብአካባቢውንእያስተዳደረፌደራላዊአመራርይኑርአሉ።
ከምላሾቹእንደሚታየውአብዛኞቹየመንግሥትንመኖርየሚደግፉሲሆንበይዘቱናዓይነቱላይግንይለያያሉ።ይህአገርንየሚወክል በቂጥናትባይሆንም፣የሕዝብአስተሳሰብበሚዛናዊምክንያቶችእንደሚለያይየሚጠቁምነበር።
ሕዝብየሚያደርገውንነገርሁሉእያስተዋለናእያመዛዘነስለሆነየሚፈጽመውባህርእንደሚገባዓሣዘሎዘውአይልም።ዘውብሎ እንዲገባየሚያደርገውአሳማኝእናተጨባጭሁኔታመኖርአለበትማለትነው፤ምክንያቱምበማናቸውምችግርበግምባርቀደምትነት የሚጎዳውሰፊውወይምደሀውሕዝብነውና።ሠርቶመኖር፤የዘራውንአምርቶመሰብሰብ፤በሰላምወጥቶበሰላምመግባት፣ባለው ጥሪትልጆቹንበማሳደግቤተሰቡንማስተዳደርየሚፈልግቤተሰብሰላምየሚነሣውሳይሆንበሰላምተከባብሮየሚኖርጎረቤት እንዲኖረውለማድረግየሚችልበትነባራዊሁኔታዎችእንዲኖሩለትይፈልጋል።ማንኛውምቤተሰብጨቋኝመንግሥትባይፈልግም፣ የልጆቹናየቤተሰቡደህንነትምትልቅጉዳዩነው፤ጎረቤቱሲረበሽ፣ሲያዝንሲጨነቅበደስታየሚኖርየለም።ሌላውቀርቶ በሚያምንበትየአገርአድንዘመቻየሚዘምትሰውወደጦርሜዳሄዶበጤናስለመመለሱእንኳእርግጠኛበልሆነበትሁኔታየልጆቹና ቤተሰቡደህንነትጥያቄውስጥእንዳይገባይፈልጋል።ነፃነትያለትግልበቀናመንፈስወይምበችሮታእንደማይገኝበተደጋጋሚታሪክ ያሳየንሲሆን፤በአንፃሩትግልበባዶፉከራናግብታዊአሠራርሳይሆንበዕቅድናበስትራተጂመሆንይኖርበታልለማለትነው።ትግልም ድልምየሕዝብስለሆነሕዝብበሚገባያልተሳተፈበትትግልለሕዝባዊድልመብቃቱአጠራጣሪነው።ሕዝብስንልማንኛውንም – ሕጋዊሰውነትያለውንሰውበዋናከተሞችውስጥየሚገኘውንሕዝብብቻሳይሆንለከብቱየግጦሽሣርበማጣት፣በዘርናማዳበሪያ አቅርቦት፣በዝናብእጥረትምክንያትቡቃያውሜዳላይየሚደርቅበትን፣ኑሮውንለማሸነፍቆላደጋእየናወጠቸርችሮአዳረውን፤ በኑሮውድነትናበተለያዩበሽታዎችየሚሰቃየውን፣ከኑሮውተፈናቅሎበገዛአገሩስደተኛየሆነውንናየወገንያለህየሚለውን፣ሥራ አጡንጭምርነው።ሕዝብየሚባለውወንድ፣ሴት፣ሕፃን፣ሽማግሌ፣ብሎበዘር፣ቀለም፣እምነት፣ቋንቋ፣ባላገር፣ከተሜ፣ወዘተ… ሳይለይመሆኑቢታወቅም፣ብዙየፖሊቲካድርጅቶችሕዝብየሚለውንቃልበተግባርለምሳሌሕዝቡይደግፈናልብለው የሚገልጹትእነሱንየሚያቃቸውንናየሚደግፋቸውንየሕዝብክፍልብቻነው።የቀረውንሕዝብእነሱምስላልተቀላቀሉትበውስጡ
ተንቀሳቅሰውወይምለችግሩመፍትሔጠቋሚተግባራትንእስካላሳዩድረስበሕዝብናበሕዝብስምበሚንቀሳቀሱድርጅቶችመካከል የላላግንኙነትሊኖርይችላል።በአንድሕዝብስምምእርስበርሳቸውየሚቃረኑናእንዲየውምየጨቋኙሥርዓትወኪልሆነው የሚያገለግሉድርጅቶችበአማራ፣ኦሮሞ፣ጋምቤላ፣ወዘተ… የሕዝቡንአንድነትናትግልአሰናክለዋል፡፡
የወረቀትላይነብርበመሆንየአውራጎዳናመፈክሮችንእያነበነብን25 ዓመታትንአሳልፈናል።ሆኖምእውነቱንእየተነጋገርን ከድክመቶቻችንበመማርአስተሳሰባችንንብናርምየተሻለውጤትልናገኝእንችልነበር።እውነቱከወያኔናየጥቅምተካፋዮቻቸው ግለሰቦችበስተቀርየሥርዓቱንመለወጥየማይፈልግአለመኖሩነው።ቢሆንምጉዳትሊያደርስበሚችልአውሬላይመሰንዘርሳይሆን በእርግጠኛነትመትቶመጣልካልተቻለተመልሶበተጎነተለአውሬመጠቃትንእንደሚያስከትልሁሉ፣ስለወያኔመወገድሲነሣማንም ኃላፊነትየሚሰማውሰውእንደየቆሰለአውሬሆኖእንዲቀርሳይሆን፤ሊያስወግደውየሚችለውንሕዝባዊመሠረትማየት
ይፈልጋል፤ሊተካውየሚችልብቃትያለውንአካልበኅሊናውመዳሰሱሐቅነው።የተሻለእንጂየባሰበትምእንዳይመጣየፈልጋል። የፖሊቲካድርጅትዓይነተኛሕዝባዊሚናመንግሥትገልብጦሥልጣንእንዴትእንደሚገኝማቀድናመታገልብቻሳይሆን፤ሕዝቡ የሥልጣንባለቤትመሆኑንአምኖሕዝቡለዚያእንዲበቃለሕዝቡፍላጎትበመገዛት፤ምጣኔሀብትአድጎሕዝቦችበልጽገውማኅበራዊ እድገትፍትሐዊበሆነመንገድሰፍኖሕዝቦችከሌሎችሕዝቦችጋርበእኩልነት፣በፍቅር፣በሰላምእናበደስታመኖርንስለሚፈልጉ፤ የዚህንራዕይየሚያመለክታቸውንድርጅትማየትይፈልጋሉ።ጥላቻንናልዩነትንየሚሰብኩድርጅቶችግንአገርመምራት እንደማይችሉይርዳል።አብርሃደስታእንደገለጸውየፖሊቲካትምክህትየተጠናወታቸውጥቂትብሔርተኛድርጅቶችየየራሳቸውን ቡድንከማየትበስተቀርየቀረውብሔር- ብሔረሰብአይታያቸውም፤የሚያደርጉትምትግልየተናጥልነው፣እነሱምከምኞትያለፈ አንዲትስንዝርመራመድምአልቻሉም።ስለሆነምሕዝቦችየወደፊቱንአገርእጣፈንታለማየትየሚያስችላቸውራዕይከሌለምን አይተውበሕዝብስምየሚንቀሳቀሱድርጅቶችንአቅፈውነውየራሳቸውአካልየሚያደርጉት? ልዩነቶቻቸውንይዘውሰላማዊ ውይይትለምሳሌበዲያስፖራእንኳሲያደርጉአይታዩም፤ገለልተኛየሆኑአካላትመድረክአመቻችተውላቸውእንኳሊጠቀሙበት “ ” አልቻሉም፤የማያጠግብእንጀራከምጣዱያስታውቃልእንዲሉስለዲሞክራሲናፌዴራሊዝምእያነበነቡ፤ ዛሬከተቃዋሚዎቻቸው ጋርበጋራየአገርጉዳዮችላይበጋራመስክአንድነትፈጥረውለጋራእርምጃያልተሰለፉድርጅቶችእንዴትአገርንየሚያኽልትልቅ ነገርየመምራትብቃትይኖራቸዋልብሎሕዝብሊተማመንባቸውይችላል?
የድሮዎችንናየቅርብፖሊቲካፖርቲዎችንአነሳስ፣አወዳደቅወይምስኬታማነትየማይጠቃቅስየፖሊቲካድርጅትየለም፤ለምሳሌ በፈረንሳይሮቤስፓየርየመራቸውጃኮቢኖችቅጥያጣሥልጣንአብዮቱንቀልብሶኋላያስከተለውንየናፖሊየንቦናፓርትአምባገነናዊ አገዛዝ፣በኮንጎፍትሐዊበሆነምርጫየተመረጠውፓትሪስሉሙምባንለመጣልየተፈጸመውንየኢምፔሪያሊስቶችሴራእናየነሙሴ ሾምቤበውጭድጋፍየመገንጠልዓላማይዞመነሣትናከነዚህጋርተያይዞከፍተኛምጣኔሀብትያላትኮንጎተከፋፍላወደኃላ መቅረት፣በናይጂሪያየነያኩቡጎዋንንአነሣስ፣ውድቀትናየነኮሎኒልኦዱሚኩኦጁኩየመገንጠልዓላማቢከሽፍምከዚያበኋላ ተያይዘውየተከሰቱትተከታታይአምባገነናዊመፈንቅለ- መንግሥቶችአገሪቷንማዳከም፣ጋናንከአፍሪቃነፃነት/pan-African Movement/ ጋርለማራመድራዕይየነበረውንየቅዋሚንክሩማንበኢምፔሪያሊስቶችሴራመገልበጥእናሕዝባዊሕልሙን ማጨለም፤በቺሊ በሕዝብየተመረጠውንሳልቫዶርአየንዴንመንግሥትበመገልበጥበአውግስቶፔኖሼአምባገነናዊሥርዓት እንዴትናለማንጥቅምእንደተተካ፣በደቡብአፍሪካየነፒተርቦታንየአፓርታይድአገዛዝበመቃወምእሥርቤትእያለአፍሪካን ናሽናልኮንግሬስየተባለውንየፖሊቲካድርጅትመሪመሆኑየሚታወቀውጥቁሩኔልሰንማንዴላበድምፅተመርጦፍትሐዊነትን በማምጣትለነጮቹምትምህርትሰጥቶሰላምመፍጠር፤እንዲሁምየየመንን፣የሶማሌን፣የዩጎዝላቪያንተከፋፍሎበድህነትመቅረት፣ የርስበርስመለያየትበኢራቅ፣ሲሪያያስከተለውጥፋት፣ወዘተ… በተመሣሣይሁኔታበአገራችንየሕዝቡንአብዮትወደወታደራዊ አምባገነናዊአመራርየለወጠውደርግበተለይምበኃይለሥላሴአገዛዝየተፈጠረውንየኤርትራንጉዳይደርግምሆነወያኔፍትሐዊ መፍትሔሊያስመጡአለመቻላቸውናእንዲየውምከጎጥየተነሣችውወያኔይህንተጠቅማሕዝቡንበጎሣናበሃይማኖትከፋፍላበዚህ ክፍፍልላይተንሠራፍታበአምባገነንነትመቆየት፤ወያኔንለሥልጣንያበቃውናአሁንምማንእናለምንእንደሚደግፋትየማያውቅ ወይምማወቅያልነበረበትየፖሊቲካድርጅትይኖራልተብሎአይታመንም።ስለአገርጉዳይየተደራጀአካልየአገራችንንታሪክ ቢችልከሞላጎደልየጥንቱንከቅርቡጋርአገናዝቦለምሳሌከ17 ኛውመቶክ/ ዘመንጀምሮእስከአሁንያሉትንታሪኮችእንኳ ጠንቅቆናተረድቶከዓለምዕድገቶችጋርአገናዝቦቢያመዛዝንለሕዝቦቻችንየሚጠቅመውንመረዳትአይሳነውም።
ታሪክንወደኋላየምናየውካለፈውመልካምመልካሙንለመውሰድናአሻሽሎለማዳበርነው፣በማወቅወይምባለማወቅየቀድሞ መረዎችባጠፉትጥፋትያሁኑንትውልድለመበቀልሳይሆንካለፈውስህተትወይምጥፋትለመማርናወደፊትእንዳይደገምለማድረግ መሆንይኖርበታል፤እነቅዋሚንክሩማ፣ኔልሰንማንዴላምሆኑየነገሥታትእናትተብለውየሚታወቁትየሐዲያተወላጅ ንግሥትእለኔ፣እነፍታውራሪ አባዶዮ ዋሚ፣ ጀ . ጃጋማ ኪሎ ፣ደጃዝማችባልቻአባነፍሶ፣ራስእምሩኃይለሥላሴ፣ነጋድራስ ገብረሕይወትባይከዳኝ፣መኮንንሀብተወልድ፣ወዘተ… በቁጥርሊወሰኑየማይችሉአያሌአያቶቻችንአገርለመገንባትአርቀው ወደፊትያስተዋሉትንበመገንዘብአገራችንንለማሳደግናሕዝቦቻችንንለማበልፀግምንማድረግአለብንብሎማሰብንይጠይቃል።ነፃ አገርመሆንእንደብርቅበሚታይበትዘመንሕዝቦቻችንባደረጉትትግልየኢትዮጵያንነፃነትአስጠብቀውስላቆዩዋትየአፍሪካ
አንድነትድርጅትመሥራችአገርመሆንዋናየተባበሩትመንግሥታትቻርተርንካረቀቁትአገሮችአንድዋመሆንዋበዓለምኅብረተሰብ ዘንድከፍተኛቦታየነበራትአገርመሆኗማንኛውንምኢትዮጵያዊሊያኮራውይገባል።ዛሬግንበወያኔአመራርሕዝቦቻችንበጎጥና በጋጥደረጃእንዲያስቡእየተደረገሲሆንየፖሊቲካድርጅቶችበወያኔወጥመድውስጥመዳኸርሳይሆንይህንበወያኔየከፋፍሎ መግዣመረብለመበጣጠስአስፈላጊውንሚናእንዲጫወቱይጠብቅባቸዋል።የኢትዮጵያንሕዝቦችእንደቤተሰቡየሚያይአካል በአገራችንታሪክኮርቶ፤ተፈጽመውየነበሩስህቶትችእንዳይደገሙወይምእንዲታረሙለተሻሻለአስተዋፅዖበሚደረግጥረትቀዳሚ ሚናዎችንለመጫወትይሞክራል፤ሕዝቡለጋራጥቅሞቹእንዲተባበርያደርጋልእንጂጥቋቁርየታሪክጠባሳዎችንእየፈለገእንዲጋጭ አያደርግም።በአገራችንመከፋፍልአያምንም፤የከፋፋይወኪልምአይሆንም።መከፋፈልኃይልንማዳከምመሆኑንለማረጋገጥ የባለሙያትንተናአያስፈልገገውም፤ የሕዝቦችኅብረትወይምአንድነትደግሞየአገርሉዐላዊነትንለማስከበርያስችላል ፤ይኸውም ዳርድንበርንጠብቆብሔራዊባንዲራንበማውለብለብከማቆየትአልፎ፣መሬትን፣ወንዞችን፣የባህርበሮቹንበሚያካትተውየአገሪቱ ምጣኔሀብትላይውሳኔየመስጠትናየመጠቀምየሕዝብኃይልማምጣትዋናውነገርሆኖ፤በምጣኔሀብቱናበፖሊቲካውየተጠናከረ የሕዝብኃይልመፍጠርበቀጥታምሆነበእጅአዙርሊመጣየሚችልንየውጭተፅዕኖማስቀረትሲሆን፤አገርወዳድፖሊቲከኛ የሚቆመውምለዚህዓይነትሕዝባዊዓላማነውመሆንያለበት፡፡
የአገራችንትልቁታሪካዊችግርኋላቀርነትሲሆንለዚህአስተዋጽኦያደረጉት፣በሥልጣንሽኩቻየአካባቢየበላይለመሆንየተደረጉ የዘመናትየርስበርስጦርነቶች፣ብሎምአምባገነንመሪዎችሲሆኑ፣በኋላቀርነታችንየሚጠቀሙቅኝገዥዎችናኢምፒሪያሊስቶችም መሆናቸውመዘንጋትየለበትም።በአንድነታችንሕዝቦቻችንሁሉየጥቅምተካፋይሊሆኑሲችሉ፤በልዩነታችንየሚጠቀሙትሦስተኛ ወገኖችናቸው፤ለምሳሌኤርትራከኢትዮጵያጋርብትቆይኖሮሌሎችነገሮችንትተንየባህርበሮቹለሁለቱምይጠቅሙየነበረሲሆን፤ ዛሬግንተጠቃሚዎቹኢምሬቶችናሳኡዲዎችሆነዋል።እንዲህጥቅማቸውንለማስጠበቅእንዲያምቻቸውነውዛሬኢምፒሪያሊስቶች ያልበለፀጉአገሮችተከፋፍለውእንዲዳከሙየሚያደርጉት፦ለምሳሌኮንጎ፣ኮሪያ፣የመን፣ዩጎዝላቪያ፣ቺኮዝሎቫኪያ፤ኢትዮጵያ ይገኙበታል።በአንፃሩአንድነታቸውንበመጠበቃቸውከተጠናከሩትውስጥጀርመን፣ቪየትናም፣ካናዳ፣ብራዚል፣ወዘተ… ን ይመለከቷል።
አገርንየመበታተንድርጊቶችየሚፈጸሙትበነፃነትስምሲሆን፤እንኳንሕዝቡንበቋንቋውእየተናገሩበነፃነትስምየሚከፋፍሉት “ ከሕዝቡውስጥየወጡለሕዝቡቆመንለታልባዮችመሆኑቀርቶየውጭወራሪዎችእንኳሲወሩሕዝቡንብርሃንናብልፅግናይዘንመጣንላችሁ…” ማለታቸውይታወቃል።ሕዝብግንለተከታታይትውልድጭምርየሚጠቅመውንናየሚጎዳውንለይቶያውቃል። የቅኝገዥዎችቅኝግዛትንየጀመሩትከአካባቢየጎሣመሪዎችጋርውለታበሚፈጸሙወኪሎቻቸውአማካይነትእንደነበረሁሉ፤ በብሔርተኝነትየሚፈጠሩአገሮችመሪዎችምባለማወቅወይምአውቀውለሥልጣንበመጓጓትለጥቅምናፋቂየውጭአገሮች በወኪልነትየሚያገለግሉሲሆን፣የሚፈጠሩትትናንሽአገሮችራሳቸውንስለማይችሉእርዳታበመሻትየኃያላንአገሮችንጥቅም ለማስጠበቅየተመቹሆነዋል።ኢትዮጵያሉዐላዊነቷንጠብቃልትቆይየቻለችውየተለያዩየጥንትወራሪዎችንበተለይም ፎይኒሺያውያንየሚባሉትንአይሁዶች፣ሒምያሮችን፣አረቦችን፣አውሮፓውያንን፣ወዘተ፣በአንድነትየመከላከልባህልናመልካም እሴቶችስለአሉን።ከወረራበመከላከልአገራቸውንበነፃነትለማቆየትበተደረገውጥረትውስጥሕዝቦቻችንየተፈጥሮ መልከአምድሮችንማለትምተራሮችን፣ባህሮችንእናወንዞችንእንዲሁምበረሃዎችንጭምርእንደመከላከያበመጠቀምበተነፃፃሪነት ሲታይከሌላውዓለምጋርግንኙነታቸውውሱንቢሆንምአገራችንንበነፃነትሊያቆዩችለዋል፤በእርስበርስግጭቶች፣በወረራ፣ በወረርሽኝበሽታናየተፈጥሮመዛባትየተነሣብዙዎችተሰደዋል፤መቼናእንዴትእንደሆነለጊዜውባይታወቅምበእንዲህያለነውጥ ከኢትዮጵያፈልሰውወደአፍሪካመኸልየተበተኑየቱትሲ፣የማሳይሕዝቦችን፣ወደመካከለኛውምሥራቅየፈለሱትንየቤጃ/ በደዊን ጎሣዎችንበምሳሌነትማየትይቻላል።ኢትዮጵያውያንጥቃቅንየውስጥልዩነቶችይኖራቸውእንጂበውስጥባሳለፉትያንድነትና የግጭትአያሌዘመናትየእርስበርስመስተጋብሮቻቸውስለሚአይሉከሌላውዓለምሕዝቦችየተለዩእንዲሆኑአድርጎቸዋል፦ዛሬ አማራ፣ኦሮሞ፣ከምባታ፣ጉራጌ፣ወዘተ… በማለትበብሔር-ብሔረሰቦች ለይተንየምናያቸውሕዝቦቻችንበውስጣቸውእስከብዙ መቶዎችከሚቆጠሩቀዳሚኅብረተሰቦችየተዋለዱናበዘርየተቀላቀሉ መሆኑንየባለሙያዎች ጥናት ያመለክታል።በተለያዩሰው- ሠራሽናተፈጥሯዊክስተቶችየተነሣየሕዝቦችከአንዱአካባቢወደሌላውመዘዋወርወይምመሰደድሲፈጸምኖሯል ።በኢትዮጵያያሉ ብሔር- ብሔረሰቦችየስደት፣የዝውውርናየመዋለድውጤቶችናቸው፤ለምሳሌአማርኛከአረብኛ፣ከአገውኛ፣ከግዕዝ፣እንዲሁም ሌሎችቋንቋዎችተከላልሶበራሱነባራዊሁኔታተፈጥሮስላደገናየብዙሕዝቦችመግባቢያስለሆነነውብሔራዊቋንቋሊሆን የቻለው፤አማርኛበ10 ኛውመቶክፍለ- ዘመንበተነሣውየዛጉዌ(ኩሻዊ) ሥርወ- መንግሥትየዳበረቋንቋእንደሆነይታወቃል። እንዲሁምከ16 ኛውእስከ19 ኛውክ/ ዘመንአጋማሽድረስበተከናወነውየኦሮምሕዝብፍልሰትየተነሣአብዛኛዎቹሌሎች ኅብረተሰቦች ቋንቋቸውናባህላቸውበኦሮሞተውጧል፡፡ ዛሬአማርኛንባእድያደረጉየኦሮሞፖሊቲከኞችለምሳሌኦሮሞዋንግሥተ – ነገሥታት ዘኢትዮጵያ ሕንደኬ ከክርስቶስልደትበፊትከኦሮሞወገንመሆንዋንእናኦሮሞኢትዮጵያዊናየግዕዝቋንቋ ባለቤትመሆኑን፤የኦሮሞነገሥታትግዕዝእየተናገሩከሰሜኑክፍለሀገራችንኢትዮጵያንየገዙመሆናቸውንቢገነዘቡ፤በቅርቡእንኳ የኦሮሞሠራዊትበአድዋላይከሌሎችኢትዮጵያኖችጋርደሙንአፍስሶበፈጸመውጀብዱይህችንአገርካቆዩትሕዝቦችመካከል በከፍተኛደረጃየተሰለፈመሆኑን፣በማይጨው፣በጨለንቆእናሶማሌያወረራየጋራአገራችንንለመከላከልየፈጸመውንተጋድሎ፤
ከጣልያንመሸነፍናከኢትዮጵያመውጣትበኋላእንግሊዝየግኝግዛትምኞቷንለመቀጠልያደረገችውንጥረትለማምከንእነክቡር “” አቶይልማዴሬሳያደረጉትንዲፕሎማሲያዊትግልናድል፤ወዘተቢያውቁኖሮኦሮሞንወያኔበከለለውኦሮሚያከመወሰንይልቅ መላውኢትዮጵያአገራቸውመሆኑንተረደተውአያቶቻቸውየገነቡትአገርእንዳይፈርስከሚቆሙትውስጥየመጀመሪያዎቹይሆኑ ነበር።ኢትዮዮጵያንኢትዮጵያያደረገውመሬቱብቻሳይሆንየሕዝቦቹየዘመናትመዋሓድውጤትነው፤ኢትዮጵያውያንተመሣሣይ የቆዳቀለም፣ተመሣሣይአመጋገብ፣ተመሣሣይአለባበስ፣ተመሣሣይየፀጉርአበጣጠር፣ተመሣሣይየሙዚቃ/ ዘፈንቅኝት፣ተመሣሣይ እምነት፣በአጠቃላይተመሣሣይባህልሊኖራቸውችሏል፤አንድንኢትዮጵያዊበቆዳውቀለምብቻሳይሆንበአረማመዱ፣በጥላውና በስሜቱእንኳመለየትይቻላል። አማራ፣ኦሮሞ፣ትግሬ፣ጉራጌ፣ሲዳማ፣ወላይታ፣ወዘተየሚሉትመለያዎችበተወሰነየታሪክዘመን የተከሠቱነገሮችሲሆኑ፣ኢትዮጵያውያንከዚያየበለጠትሥሥርእናአንድነትየነበራቸውሕዝቦችናቸው።ሦስቱታላላቅ – ሃይማኖቶችየአይሁድእምነት፣ክርስትናእናእስልምናበብዙየአውሮፓ፣አፍሪቃ፣አሚሪካናእስያክፍለዓለሞችሁሉበፊት ለመጀመሪያጊዜየገቡትወደኢትዮጵያነው። ኢትዮጵያ የስዎችንሰብአዊመብትበማክበርእናበልዩነትተከባብሮበመኖር በምሳሌነትዋበቀዳማዊነትየምትታወቅአገር እንደነበረች የንጉሥአርማህ/ ሙስሊሞችነጃሽብለውመስጊድበስሙየሠሩለትን/ በ 7 ኛው መቶ ክ / ዘመን የነበረን የኢትዮጵያ መሪ በመረጃነት ማየት ይቻላል።
የአገራችንናየብዙሌሎችአገሮችንታሪኮችብናስተያይበተለይበ18ኛውና19 ኛውእስከ20 ኛውመቶክፍለዘመናትበአንድ በኩልትናንሽየአካባቢመንግሥታትንበውዴታምሆነበግዴታአንድአገርእንዲሆኑበየክፍለዓለማቱአገርየማቅናት/unification/ ድርጊትሲከሠት፣ይህንተከትሎበተለይአውሮጳውያንአገሮችየምጣኔሀብትምንጭ/resource/ ለማግኛትባደረጉትሽምያደካማ አገሮችንበቅኝየመያዝሂደትውስጥሲያልፉየያዙዋቸውንአገሮችድንበርበመወሰንናበሕዝቦቹማንነትላይከፍተኛተጽዕኖ አድርገውባቸዋል።የብዙአፍሪካአገሮችካርታበዚህመሠረትየተፈጠረሲሆንበአፄምኒሊክዘመንበአንድበኩልየውጭ ተስፋፊዎችንበመቋቋምበሌላብኩልአገርንከውስጥየማቅናትተግባርባይፈጸምኖሮየኢትዮጵያካርታየተለየሊሆንከመቻሉም በላይዛሬ የምናውቃቸውየአንዳንድብሔር- ብሔረሰቦችማንነት/identity/ ሊጠፋወይምሊለወጥይችልነበር።
አገርበሚባለውነገርውስጥብዙየተለያዩየአመለካከት/ የፍልስፍና፣የጥቅም፣ወዘተግጭቶችይኖራሉ፤እንኳንበአገርውስጥበአንድ ቤተሰብውስጥእንኳንልዩነቶችናግጭቶችምመኖራቸውየታወቀሲሆን፣አገርንመምራትእነዚህንልዩነቶችንአቻችሎአገራዊ መፍትሔበመስጠትማስተናገድነው።ዛሬ በልፅገውየምናያቸውአገሮችተመሣሣይችግሮችሳይኖራቸውቀርቶሳይሆን፤ በአገሮቻቸውውስጥየተለያዩሕዝቦችተከባብረውበዲሞክራሲታቅፈውበመኖራቸውነውሊበለጽጉየቻሉት።ሕዝብበቀናነት የሚጠብቀውአገርወዳድፖሊቲከኞችልዩነቶችንተከትለውእንዲከፋፍሉት፣እንዲበታትኑትሳይሆንበልዩነቶቻችንላይዲሞክራሲ እንዲሰፍንናጠንካራየጋራአገርማድረግንነው።ሆኖምአንዳንድጠባብፖሊተከኞችእንደመንጋሕዝብንወደሚፈልጉትአቅጣጫ ለመንዳትመሞከራቸውለአገርእድገትሳይሆንለሁሉምድክመትነውአስተዋፅዖያደረገውናየሚያደርገው።ስለሆነምማንኛውም ሕዝብደጉንናክፉዉን፤ልማትናሰላምየሚያመጣውንእናበአንፃሩየተስፋዳቦብቻየሚመግበውንለይቶየሚሰማበትናየሚያይበት ብዙጆሮዎችናብዙዓይኖችስለአሉትበሕዝባዊመሠረታዊፍላጎቶችናጥቅሞችላይያልተማከለየፖሊቲካድርጅትየሕዝቦችንድጋፍ አግኝቶለአስተማማኝሕዝባዊድልመብቃትአይችልም።በአጠቃላይማንኛውምሕዝብለማፍረስከመሰለፉበፊትበሚፈርሰው ፋንታግንባታስለመኖሩአሳማኝምልክቶችንበመሬ ትላይማየትይፈልጋል። ሕዝቦችንማዕከልያደረገናአገርንየሚያማክልየጋራ ራእይያለውየፖሊቲካተቋማትጥምረትወይምኅብረትከሌለሕዝባዊየጋራትግልሊኖርአይችልም፤ ስለዚህእስከአሁንሕዝቡ ለጋራዓላማተሰልፎወደድልያልተመራመሆኑሊያስደንቀንአይገባም፤ያልዘሩትንመሰብሰብስለማይቻል።
ማፍረስንማወያኔዎችተክነውበታል፤በመተማ፣በአድዋ፣በማይጨው፣በጨለንቆ፣ወዘተጦርነቶችበጋራተሰልፎየጋራአገር ያቆየውንሕዝብየታሪክንደካማጎኖች/ጠባሳዎችን/ አጉልቶበማቅረብናሕዝቦችንበዘርአከፋፍለውበማካለል፤በሃይማኖትናቋንቋ በማናቆርእርስበርሱየማያቃርጥግጭትውስጥእንዲገባእናበአንፃሩለጋራየአገርጉዳይእንዳያስብአድርገውታል፤የነፃነትንና የፍትሕንመርህአዛብተውበበረቶችእንደሚለያዩከብቶችሊነዱትሞክረዋል፤አሞሌእየላሱእረኛቸውንእንደሚከተሉሙክቶች የራሳቸውንሕዝብበጭቆናለማስገዛትወኪልየሆኑላቸውመሪዎችንናቅጥረኞችንም/mercenaries/ ተጠቅመውባቸዋል፤ለዘመናት አብሮየኖሩትንሕዝቦችታሪክበመቶዓመትውስጥገድበውየጋራአገርእንዳልነበራቸውአድርገውታሪካቸውንአዛብተዋል።በይህ መሠሪሴራቸውእስካሁንበሥልጣንራሳቸውንለማቆየትተሳክቶላቸዋል።ሞኝእስካለድረስሌባየሚሠርቀውአያጣምና፤በወቅቱ ስህተትንማረምአዋቂነትናጥንካሬሲሆንከስህተትየማይማርከመጃጃልስለማያልፍእንኳንመገንባትማፍረስምአይሆንለትም። በእርግጥለሕዝብየቆመከሆነመገንባትእንደሚችልያሳየድርጅትለማፍረስየሚተባበረውአያጣም።
ተፈራድንበሩ
teferadinberu@yahoo.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s