SBS የአማርኛ አገልግሎትን እንደታዘብኩት

 
ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ
ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ

ከአዉስትራሊያ የሚተላለፈው የSBS የአማርኛ አገልግሎት በሀገራችን ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ህይወት ውስጥ ጉልህ ሚና ያላቸውን ኢትዮጲያዊያን አስሶ በመጋበዝ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ቁምነገሮችን ሲያቀርብልን ቆይቷል። በዚህ በኩል በኔ ግምት ከሌሎች የበለጠ በርካታና ግዙፍ ስራዎችን እንደሰራ ይሰማኛል። በዚህም የታዋቂውን ጋዜጠኛ የካሳሁን ሰቦቃን የሞያ ክህሎት እና ትጋት ለመገንዘብ ችለናል።

ለጋዜጠኛው ያለኝ አድናቆት እና ክብር እንደተጠበቀ ሆኖ አንዳንድ ያልተመቹኝን ሁኔታዎች ግን ባጭሩ ላስቀምጥ እወዳለሁ።
ስለ ጋዜጠኝነት ጠለቅ ያለ እውቀት ባይኖረኝም የበርካታ እውቅ ጋዜጠኞችን ስራዎች ሳነብ ስሰማና ስመለከት ኖሬአለሁ። በጋዜጠኝነት ሞያ ውስጥም ሚዛናዊነት የሚባል የሞያው መርህ እንዳለ አውቃለሁ። ይህ ማለት ግን እኩይና በጎ ድርጊቶችን ሀሰትን እና እውነትን እኩል እስኪሆኑ እና ተጣፍተው ዜሮ እንዲሆኑ ማድረግ አይደለም። ለምሳሌ በተጨባጭ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ያካሄደ አካል ተወካይ ጋዜጠኛ ጋ ተገናኝቶ እንዲህ በዋዛ መመለስ አይገባውም ። ማስረጃዎችን እያጣቀሰ ደግሞ ደጋግሞ ሊያፋጥጠው ይገባል። እስከዚህ ድረስ መኬድ እንዳለበት እዬታመነ ይባስ ብሎ ጥያቄው ጭራሽ ሳይነሳ ሲቀር ግን የሚያሳዝን ነው የሚሆነው። በተጠያቂው በኩል በአሉታዊ መልኩ የተጠቀሰ እያለ ተጠቃሹ የበኩሉን መልስ እንዲሰጥ አለመጋበዙም አስተዛዛቢ ጉዳይ ነው።

ሌላው የታዘብኩት ደግሞ ተጋባዣቹ ከሞያቸውና ተያያዥ የሆኑ ጥያቄዎች አስቀድመው በጋዜጠኛው በተዘጋጁ ወይም በውይይቱ ላይ ከሚነሱ ነጥቦች በመነሳት ሊቀርብላቸው ይገባል። የሚታወቁ ብቻ ሳይሆኑ የተደበቁ ጉዳዮችንም ጋዜጠኛው የመፈልፈል እና የማጋለጥ ሀላፊነት አለበት ። የጋዜጠኛው ግብ ሊሆን የሚገባው ህዝቡ ጋ እውነት እንዲደርስ የተቻለውን ማድረግ ነው።

ከላይ የጠቀስኲዋቸውን ጉዳዮች ለማንሳት የተገድድኩት ጋዜጠኛ ካሳሁን በአውስትራልያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሰልጣን አምባሳደር ከሆኑት ከወይዘሮ ትርፉ ኪዳነማርያም ጋ ባለፈዉ ወር መጨረሻ ያደረገው ቃለ መጠይቅ ነው።
ካሳሁን አምባሳደሯን “እስዎ በአውስትራልያ 3ኛዋ የትግሬ አምባሳደር ነዎት ” ይልና ዘሎ የመጀመሪያዋ የሴት አምባሳደር ነዎት” ወደሚለው ይሻገርና ጥያቄውን በፆታ አቅጣጫ ይገፋበታል። ብሄር ጠቅሶ ወደ ጀመረው የጥያቄ መንደርደሪያ ተመልሶ ይጠይቃል ተብሎ ሲጠበቅ በዛው የውሀ ሽታ ሆኖ ይቀራል።  የተጠቀሰው የብሄር ስም ሳይታሰብ ካፍ ያመለጠ ሳይሆን አይቀርም። በርግጥ አመለጠ ተብሎ በካፈርኩ አይመልሰኝ በዛው መቀጠሉ ስህተትን ለማረም ተብሎ የሚፈጠር የባሰ ስህተት ሊያስከትል ይችላል። ይህ ግን ሊያመልጥ ሳይሆን ሆን ተብሎ ሊጠቀስ የሚገባውና በርካታ ጥያቄዎች ሊያስነሳ የሚችል ነው።

ለምሳሌ
1- ለምን ሶስታችሁም ከአንድ አናሳ ብሄረሰብ ሆናችሁ
2- በአለም ዙሪያ ካሉት የኢትዮጲያ አምባሳዶሮች ውስጥ አብዛኛዎቹ ለምን የዚህ ብሄር አባላት ሆኑ
3- የሌሎች ብሄረስቦች አባላት አምባሳደር በሆኑባቸው አገሮች ውስጥስ ምክትሎቻቸው በሙሉ ለምን ትግሬዎች ሆኑ
4- የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ከ25 አመታት በላይ ለምን በዚሁ አናሳ ብሄር ስዎች ተያዘ
5- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቁልፍ ቀልፍ ቦታዎች ለምን በትግራይ ተወላጆች ብቻ በሞኖፖል ተያዙ
እና ሌሎችም ጥያቄዎች ማቅረብ ይቻል ነበር።

ሌላው በዚሁ ቃለመጠይቅ የታዘብከት አውስትራሊያ የሚገኙትን  ተቃዋሚዎች 0 ነጥብ ምናምን ናቸው።” አሸባሪዎች የኦብነግና የኦነግ አባላት ናቸው። አገር ቤት ወንጅል ሰርተው የመጡ ናቸው” በማለት ሴትዮዋ መልስ ሲሰጡ ጋዜጠኛው ለተጠቀሱት አካላት ተመጣጣኝ እድል ሰጥቶ መልስ እንዲሰጡ ማድረግ ነበረበት። ቁጥርንም አስመልክቶ ጋዜጠኛው ባይኑ በብረቱ ያዬውን ያለፈውን ወር ተቃውሞ በእማኝነት በመጥቀስ ተጋባዧን መሞገት ነበረበት። ባለፈው ወር በተደረገው ተቃውሞ እስከ 700 የሚገመቱ ኢትዮጺያዉያን የተሳተፉ ሲሆን የመንግስት ከፍተኛ የ ልኡካን ቡድን የአምባሳደሯን ባለቤት ጨምሮ የጠራው ስብሰባ በኒሁ ተቃዋሚዎች ተቃውሞ ምክንያት ሲሰረዝ ጋዜጠኛው በቦታው እንደነበረ በአይኔ አይቼዋለሁ ። የመንግስት ደጋፊዎች አንድ አውቶቡስ ያልሞሉና በቦታው ከነበሩበት የፖሊስ መኪናዎች እንኳን ያነሱ ነበሩ። ለስብሰባው ለምን የትግራይ ተወላጆች ብቻ እንደተጠሩም መጠየቅ ነበረባቸው አምባሳደሪቱ።
በዚህ አጋጣሚ ሳልጠቅሰው የማላልፈዉ ይሄው የልኡካን ቡድን ከታስሜኒያ በደረሰበት ተቃውሞ የተነሳ ከተማዋን ባስቸኩዋይ ለቆ እንዲወጣ የተደረገ መሆኑንና እንዲሁም ሜልበርን ውስጥ ሀያት ኢንተርናሽናል የተባለው ትልቅ ሆቴል ጣጣ ታመጡብናላችሁ በማለት ልኡካኑን እንዳይክራዩ እንደከለከላቸው ነው። በነዚህ ተቃውሞዎች ዙሪያ አንድም ጥያቄ አልተነሳም።

በዚሁ ቃለመጠይቅ የኦርሚያው ጭፍጨፋ የወልቃይት ጉዳይ የጋምቤላው ጉዳይ የድንበሩ ነገር ሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ሳይነሱ ቀርተዋል።

በመጨረሻም በሞያው የማከብረው ካሳሁን የሴትዮዋን ጨምሮ በብዙ ቃለመጠይቆቹ ላይ “አዳላህ እባል ይሆን” በሚል ይመስለኛል ፈራ ተባ እያለ ጥያቄዎችን እንደሚያቀርብ አስተውዬዋለሁ። የኢዲቶሪያል ፖሊሲ ጉዳይ ነው እንዳንል SBS ን በሌሎች አገልግሎቶቹ ስለምናውቀው አያስኬደንም። ከሞያ ስነምግባር አንፃር ከሄድንም ይልቅስ የማያስኬደው እውነቱን ለመፈለግ አስፈላጊው ጥረት አለመደረጉ ነው።

ጋዜጠኞች እውነትን ፍለጋ በእስር ቤት በመማቁባት ባሽባሪዎች ጥይት በሚቀሰፉባት አለም ውስጥ እየኖርን ፍፁም ነፃነት እና ስላም በሰፈነባት አውስትራሊያ ውስጥ ፍርሀት ይሉ ነገር መታሰብ አልነበረበትም። እንኳን የኢትዮጵያን የአውስትራሊያን መንግስት እስከ ጥግ የመሞገት መብት እንዳለው ጋዜጠኛው በሚገባ ያውቀዋል።

ይህን ሁሉ ብዬ ሳበቃ ግን ወደፊት እጅግ የተሻሉ ፕሮግራሞችን በዚሁ አገልግሎት እንደምንሰማ ተስፋ በማድረግ ነው።

ሊንኩን በመጫን የአምባሳዶሯን ቃለመጠይቅ የመጀመሪያ ክፍል ማዳመጥ ይችላሉ

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: